ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር @fictional27 Channel on Telegram

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

@fictional27


❤️ያልተነበቡ ድርሰቶችን..ግጥሞችን..የፍቅር ታሪኮችንና ሌሎች መጻጽፎችን ያገኙበታል። Page Join ብለው ይቋደሱ።
.
.
.
በfacebook ለመከታተል ከታች ያለውን Link ይንኩት
👇
👉www.facebook.com/fictional27
👇
👇
👉ለማነኛውም ሀሳብ አስተያይት!!!
👇
👇
👉https://t.me/Groups16

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር (Amharic)

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር ይከታተሉ! በተጨማሪ እና በአስተማሪም በጽሑፉን መሰለከት እና የመንጫውን ሐሳብ በሚያበረታቸው እቃዎችና መረጃዎች በፍቅር እንዲሁም ሌሎች እንደገና ያማሩበታል። fictional27 በፊትና በፊት ስለፍቅር ሁሉም መረጃዎችን በቀላሉ ይገኛል። የፍቅር ታሪኮችን ከማንኛውም በለስ እንመለስ፣ በfacebook ለመከታተል የምንስ እንችላለን። ከዚህ በፊት ያነሱን ምርጫዎችን ለመጫን በሚችል እርስዎ በፍቅር እንጠናቀቅ። እስኪመጣችሁም እንግዲህ በተጨማሪ እርስዎ አስተያይት። ለምሳሌ በስብስብ ተጨማሪ የቤተሰብ ትኩረት ከመከታተል በፊት ለመሸላጨት ግባት እንጠቀማለን።

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

19 Jan, 15:59


እ-ረ-ስ-ቼ-ዋ-ለ-ሁ!

#Ethiopia | አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....

"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!

ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡

እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።

ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።

አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡

ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።

ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።

አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።

አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤

"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...

"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...

"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡

እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

ሰው እንጂ እግዚአብሔር ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።

እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!

ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሄርን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!

በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳት እኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነው...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን ...

   "እግዚአብሔር ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!
በፌስቡክ ለመከታተል
http://www.facebook.com/fictional27
በቴሌግራም ለመከታተል
https://t.me/fictional27
ለበለጠ ሀሳብ እና አስተያየት
https://t.me/Groups16

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
        መልካም ጊዜ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
      ይጠብቅልን አሜን
❥❥__⚘_❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

01 Aug, 23:35


የአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን
ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል!!
ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው
በቅደም ተከተል አስቀመጠA b c d e f g h i j k l m n o p
q r s t u v w x y z። የነዚን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል
ኣስቀመጠ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23 24 25 26
በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ
ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን
ሰጠ።በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ።
1. ትጉ ስራ
(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%
2. እውቀት
(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%
3. ፍቅር
(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%
4. እድል
(L+u+c+k)=47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም ለውጥ
መቶ ፐርሰንት(100%)ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ። ታዲያ
(100%)ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ብር ይሁን
እንዴ??
5. ገንዘብ (M+o+n+e+y)
(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሁን?
6. አመራር
(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97%
አሁንም አይደለም!
ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ፣አካሄድ አኳኋናችንን
ስንቀይር ይቀየራል። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ።
7. አስተሳሰብ
(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
እናም ወዳጄ ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው
የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ።
© ከወደዱት Share,Like and comment ያድርጉ😍
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና
ህዝቦቿን ይጠብቅልን
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

28 Jun, 16:27


😘የከንቲባው ልጅ😘
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
#የመጨረሻው ክፍል
አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል ። አባቷም ከሚስቱና ከህፃን ልጁ ጋር ወደ አሜሪካ በረዋል ። ከሰኔ #13 እስከ #21 final ፈተና ተፈትነን ስንጨርስ ከመሄዳቸው በፊት አባቷን አግኝቼ አነጋግሬያቸው ነበር ። ስለ ሁሉም ነገር እንዲህ ብለው ነገሩኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን እንደመጣሁ አካባቢ በስራ ላይ አንዲት ሴትን ተዋወኩኝ ። በድሬዳዋ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ናት ። ሁለታችንን አንድ የሚያመሳስለን ነገር ነበር ። እሷ ባሏን እኔ ደግሞ ሚስቴን በሞት አጥተናል ። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ውስጤን ሰርስራ ገባች ። በስራና በኑሮዬ ጭምር ገብታ ታግዘኝና ትረዳኝ ጀመር ። በዚህ መሀል ግን አንድ ችግር ነበር ። እሱም በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በኛ ስራና ግኑኝነት አለመደሰት ነበር ። የሚገርምህ ሁሉም በአንድነት ይቺን ምስኪን ከተማ ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ሲስማሙ እሷ ብቻ ነበረች ከጎኔ የነበረችው ። ድሬዳዋ ከተማ በሁለት ክልል መሃል ያለች በመሆኗ በየ አራት ዓመቱ ባለስልጣናት አንዴ ከኦሮሚያ ከአራት ዓመት በዋላ ደግሞ ከሶማሌ ክልል እያለ ተራ በተራ #4 ዓመት እየጠበቀ ስለሚፈራረቅ ሁሉም ባለስልጣናት ሀሳባቸው ድሬን ማልማት ሳይሆን እራሳቸውን ማልማት ነበር ። እኔ ደግሞ ከንቲባ የሆንኩበት ዋነኛው ምክንያት ይህንኑን ስርዓት ለማጥፋት ነበር ። ከዛ በዋላ ያለው ታሪክ ህይወት እንደነገረችህ ነው ። የኛን መንገድ የማይከተሉ ሰዎች በበቀል ተነሳስተው ልጄን ለመግደል ብለው አቤልን ቀጠፉ ። እናም ወጣት ተስፋዬ ባለፈው ተከትለኸኝ ያየሀት ሴት በዛ አስቸጋሪ ጊዜ ከጎኔ የነበረች ጀግና ሴት ናት ። በዛው ወቅት በመሃላችን በተፈጠረው የፍቅር ግኑኝነት ልጅ ፀነሰችልኝና ተወለደ ። ይሄን ሁሉ ታሪክ ደግሞ ለልጄ በጊዜው እንዳልነግራት ለራሷ በጣም መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነበረች ። እንዴት ልጄ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎ በጣም የምትወደው ጓደኛዋ ሞቶ ስለራሴ ደስታና ሀሴት እነግራታለሁ ...? ምን አይነት ስቃይ ውስጥ እንደነበረች ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ። አሁን አንተን ስታገኝ ነው እንደዚህ ተቀይራ ያየሀት ። ለማንኛውም ሁሉንም ነገር ወደ ውጪ ስንሄድ ላሳውቃት ነበር የፈለኩት ። ባለቤቴንና ትንሹ ልጄን ከህይወት ጋር አንድላይ አሜሪካ ወስጄ ለሁሉም እውነታውን ልገልጽ ነበር እቅዴ ። እንደምታየው አሁን ሁሉም ነገር ተበላሽቷል ። ልጄም አኩርፋኝ ሸሽታኛለች" አሉኝ በሀዘን ። በስተመጨረሻ ልንለያይ ስንል ያሉኝን ግን እስካሁን ድረስ አምኜ አልተቀበልኩትም ። እንዲህ ነበር ያሉኝ "የህይወትን በህይወት መኖር ከኔና ካንተ ውጪ ማንም ሰው አያውቅም ። ለህይወት በህይወት መኖር ሲባል ይህ ምስጢር እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። እሷን ካንተ ለይቼ ወደ ውጪ ልወስዳት አልችልም ። ስለዚህ ልጄን ላንተ ሰጥቼሃለሁ ። ይዘሃት ወደ ሀገርህ ሂድ ። ከፈለጋችሁ እዛው ፤ ካልሆነም ደግሞ አዲስ አበባ ደስ የሚል ኑሮ መኖር ትችላላችሁ ። ዕድሜያችሁ ከ #20 ስላለፈ እራሳችሁን ችላችሁ መኖር አይከብዳችሁም ። ለብር ደግሞ ብዙም አትጨነቁ ። በባንኳ ውስጥ አንቀባሮ የሚያኖራችሁ በቂ ገንዘብ አለ" ። ታድያ የህይወት አባት እንዲህ ብለው መርቀው ልጃቸውን ሲሰጡኝ እንዴት ብዬ ልመን ...? በሌላ በኩል ደግሞ ማራኪዬ ስለኔ ምን እያሰበች እንደሆነ ለማወቅ በስልክ ሳዋራት "ሙሉ በሙሉ እንደረሳችኝና ሌላ ህንወት እንደጀመረች" ነገረቸኝ ። አሁን ከህይወት ጋር ነኝ ። ከቤተሰቦቼ ጋር አስተዋወኳት ። ለቤተሰቦቼም ሁሉን ነገር ነግሬያቸው ተስማምተን አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ከህይወት ጋር ለመጀመር ተዘጋጅተናል ። ልክ እንደባልና ሚስት ሳይሆን እንደ ፍቅር ለመኖር ጉዞ ጀምረናል ። ከህይወት ጋር ስትኖር ፤ በህይወት መኖርህን ትወደዋለህ ። ስለ ህይወት ለማውራት ፣ እኔ ቃል የለኝም ፤ እሷ ካለች አለሁ ፣ ያለዚያ ግን የለሁም ።

ህይወት መዝሙር ነች ፤ ዘምራት
ህይወት ሰቀቀን ነች ፤ ቻላት
ህይወት ተግባር ነች ፤ ተወጣት
ህይወት ሽፍንፍን ነች ፤ ግለጣት
ህይወት ሀዘን ነች ፤ ተቋቋማት
ህይወት ስጦታ ነች ፤ ተቀበላት
ህይወት ውርርድ ነች ፤ ተወራረዳት
ህይወት ትግል ነች ፤ ታገላት
ህይወት ምስጢር ነች ፤ ፍታት
ህይወት ውበት ነች ፤ አጊጣት
ህይወት ጉዞ ነች ፤ አጠናቃት
ህይወት ቃል ነች ፤ አሟላት
ህይወት አጋጣሚ ነች ፤ ተጠቀማት
ህይወት ጀብዱ ነች ፤ ድፈራት
ህይወት ፍቅር ነች ፤ ፈልጋት ።
.
.
.
.
✍🏽~~~ተፈፀመ~~~~✍🏽 ☞ የስው ልጅ መጨረሻው ሲያምር ነውና ፤ ፈጣሪ መጨረሻችንን ያሳምርልን! እኔ አሜን ብያለሁ፡፡

#ይሄ የባለታሪኩ የተስፋዬ በትሩ መገኛ አድራሻ ነው...ገንቢ አስተያየታችሁን እንደምታደርሱት...መልካም ምኞታችሁን እንደምትገልጹለት አምናለሁ።👇👇
#እኔም የተስፋዬና የህይወት ፍቅር አብቦ ወደሌላኛው የህይወት ምእራፍ እንደሚሸጋገሩ...ትዳራቸው ሰምሮም ፍሬ እንደሚያዩ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ...አመሰግናልሁ።።😘
ውድ Fictional27 ፔጅ ተከታታዮች ፦ ደበረን ሰለቸን ሳትሉ ወርቅ ግዜያቹን ሰውታቹ ጀምሬ እስከምጨርስ ድረስ ስለተከታተላችሁኝ ፣ እንዲሁም በውስጥ መሰመር እየገባቹ ላስተካክለው የሚገባኝን እንዳስተካክል ስለረዳቹኝ ከልብ አመሰግናለሁ እወዳችዋለሁ፣ አከብራችዋለሁ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ መልካሙን ተመኘሁላቹ፡፡
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

27 Jun, 16:50


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 40
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
#ሊጠናቀቅ 1 የመጨረሻ ክፍል ብቻ ይቀረዋል..
ህይወት ለጊዜው ሆቴል ይዤ መረጋጋት ይኖርብኛል ብላኝ ነበር ። እኔ ግን ለብቻዋ እንድትሆን ስላልፈለኩኝ ከሷ ጋር ተቀራራቢ መልክ ካላት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ልጅ ID card ለምኜ ወደ ጊቢ ይዣት ገባሁ ። በር ላይ መታወቂያውን ልብ ብለው ስለማያዩት ማንም በማንም ሰው ID መግባት ይችላል ። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ደንግጣ ነበር ። እንደ high school ጠባብ አይደለም ። በዛላይ ከ #15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአንድ ጊቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው ትንሽ ግር ይላል ። ሰዓቱም ወደ ምሽት እየተጠጋ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ለእራት ከጊቢ እየወጣ ነበር ። ለተባበረችን ልጅ Id መልሼ ፡ እኛ እንደነገሩ ጊቢ ውስጥ ካለው ላውንጅ እራት በልተን ከዚህ በፊት ብቻዬን አዘውትሬ የምቀመጥባት ፣ ከማራኪዬ ጋርም ስልክ የማወራባት የነበረው ቦታ ወሰድኳት ። ቦታው ጨረቃን ወለል አድርጎ ከማሳየቱም በተጨማሪ ጭር ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ፣ በዛላይ ደግሞ እራስን ለማዳመጥ በጣም አመቺ ነው ። "ሳልማር ዩኒቨርሲቲ ገባሁ አይደል...?" አለችኝ ህይወት በተከፋ ድምፅ ። እንዳይሰማት ብዬ 'እኛ ተምረን ይመስልሻል እዚህ የደረስነው ...? ዩኒቨርስቲ ከገባ ውስጥ #10% አይሆንም ተምሮና በራሱ ጥረት እዚህ የገባው ። አብዛኛው ኮርጆ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ነው እራሱን እዚህ ቦታ ላይ ያገኘው ። ዞረሽ ብትጠይቂያቸው "እኔ ለቤተሰቦቼ ብዬ ነው የምማረው ፡ እኔ ላይፉን ለማየት ነው የመጣሁት ፣ እኔ ከ famly ርቄ ነፃነቴን ለማግኘት ነው የመጣሁት ፣ ወዘተ ይሉሻል ። አላማ አለኝ ፣ ትምህርቴን ጠንክሬ ጨርሼ ለሀገሬና ለወገኔ እንደዚህ ላደርግ ነው የመጣሁት የሚልሽ በጣት የሚቆጠሩ ልጆች ብቻ ናቸው ። ታዲያ አንቺስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለመግባትሽ ማመስገን እንጂ ማማረር ነበረብሽ ...?' አልኳት ። ደግሞም የምሬን ነው ። የከሰረ ትውልድ ይዛ ፣ ትርፍ ለማግኘት የምትሯሯጥ ሀገር ላይ ነን ። ይሄንን ትውልድ ማስተማር ያለብን physics ፣ chemistry ፣ biology ሳይሆን ትምህርት ምን እንደሆነ ፣ ምን ምን ጥቅም እንዳለው ፣ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር ማሳየት አለብን ። ከሁሉ ነገር መቅደም ያለበት ለትምህርት ያለን ፍቅርና ፍላጎት ነው ። እሱ ላይ ከተሰራ ሌላው ሁሉ በራሱ ጊዜ ይመጣል ። ይሄ ትውልድ ትምህርት የሚለውን ቃል እራሱ መስማት አይፈልግም ። በቃ ከሰይጣን በላይ ጠልቶታል ። ስለዚህ የጠላውን ነገር በግድ ተማር ከምንለው ፡ ለምን እንደጠላ መርምረን ፣ ምን ብናደርግ ደግሞ መውደድ እንደሚችል አስበን ወደ ቀልቡ መመለስ የተሻለ ይሆናል ። እንዲሁ ስለ ዩኒቨርስቲ እያወራን እያለ #01:30 ላይ የህይወት አባት እቤት ገብተው አጧት መሠለኝ ስልኳ ላይ ደወሉ ። አንስታው እንድሰማቸው ነው መሠለኝ loud speaker ላይ አደረገች ። "የኔ ህይወት ፡ የት ሄደሽ ነው ፣ ከቤት አጣውሽ እኮ ...?" ሲሏት "አያይ ብዙም አልራኩም ፡ ባሌንና ልጄን አይቼ ለመመለስ ብዬ ነው" አለቻቸው ፈርጠም ብላ ። "ስለምን ባልና ልጅ ነው የምታወሪው ልጄ ...?" አሏት መልሰው ። ህይወትም ትንሽ የፌዝ ሳቅ እንደመሳቅ አለችና "ለካ አልነገርኩህም ፡ ባል አለኝ እኮ ፣ ለዛውም አንድ ቆንጂዬ ህፃን ልጅ ከሶስት ዓመት በፊት ወልደናል" አለቻቸው ። ምንም መልስ የለም ፣ ፀጥ ፡ ሴኮንዱ ይቆጥራል ፡ አሁንም ግን ምንም አይነት መልስ ከህይወት አባት አልመጣም ። ህይወት ዝምታው ሲበዛባት "አየህ ፡ ምንም መልስ የለህም ። ቆይ ግን እስከመች ነበር እኔን ለመደበቅ ያሰብከው ፣ እስከዘላለም ...? ንገረኛ ...? ለማንኛውም ከኔጋር ከምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ይልቅ ከነሱ ጋር የምታሳልፋቸው አምስት ቀናት የተሻሉ ስለሆኑ እነሱ ይሻሉሀል ። ቆይ ግን ልጅ አለኝ ፣ ሚስት አለኝ ብትል የምቃወምህ መስሎህ ነበር ...?" ስትላቸው "የኔ ልጅ እቤት ተመለሺና እናውራ" ብለው ይማፀኗት ጀመር ። "ሶስት ዓመት ሙሉ እኮ እቤት ነበርኩ ። ያኔ የት ነበርክ ። ለማንኛውም አትፈልገኝ ፣ የተሻለ ቦታ ላይ ነው ያለሁት ። መገናኘት ሲያስፈልገን እራሴው እቤት እመጣለሁ" ብላ ስልኩን ዘጋችው ።ምንድነው ሰው ሁሉ ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ መላክ የመሰለው ፣ እንዴት ነው ሰማዩ እንዲህ ተጠቅልሎ በእጄ የምይዘው መሀረብ ያከለው ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው ፡ መሬት መዞር ትታ በእፎይታ ያቆማት ፣ ምንድነው ጨረቃን ከሰማይ አውርዶ ምድር ያሳረፋት...? እያልኩ አስባለሁ ። ደግሞም አላቆምም መልሼ መላልሼ አሁንም አስባለሁ ። ማነው በመንገዴ ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ ፣ ማንስ ነው ግማሽ ልቤን ሸርፎ የወሰደው ፡ በትልቁ ቆርሶ ፣ መንገደኛው ሁሉ የተከፋ ፊቱን በማን ተነጠቀ ፣ ከጨፍጋጋ ፊት ላይ እንዲህ ያለ ብርሃን እንዴት ፈነጠቀ ፣ ሚሊዮን ህፃናት ከልብ በሚነሳ ስርቅርቅ ድምፃቸው ፡ የት ቢዘምሩ ነው ልቤ ሚሰማቸው ፣ እኮ በምን ምክንያት ይህ ሁሉ ተቀየረ ፣ ያልነበረ ወደነበረ እንዴት ተመለሰ ...? እያልኩ አስባለሁ ። አሁንም አስባለሁ ። ምንድነው እንደዚህ ፊቴን በብርሃን ፡ ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው ፣ እንዴትስ ነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም በጠዋት የሚፈልቀው ፣ የጠሉኝን ሁሉ ድንገት መውደዴ ፡ መሬቱን ለቅቄ አየር ላይ መንጎዴ ፡ ምንድነው ምስጢሩ ፣ ቆይ ውስጤን ምን ነካው ...? አለም እንዲህ ጠቦ በእርምጃ የሚለካው ፣ ውቅያኖስ በእፍኝ ተጨልፎ የሚደርቅ ፣ ተራራው በክንዴ ተጎሽሞ የሚደቅ ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው እያልኩ አስባለሁ ። እኔ ደግሞ ቤሳቤስቲን ሳንቲም ኪሴ ሳይጨመር ፣ ዓመት የለበስኩት ልብሴ ሳይቀየር ፣ የዘውትር ጉርሴ ጣዕሙ ሳይነካ ፣ እኔነት እኔ ውስጥ ተቀይሯል ለካ ። እኮ በምን ምክንያት እኔ ተቀየርኩኝ ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል ፡ እኔ ሌላ ሆንኩኝ እያልኩ አስባለሁ ። ለካስ ከህይወት ጋር ስለሆንኩኝ ነው ። ያውም ከአባቷ ተለይታ ከድሬዳዋ ለቃ ከዩኒቨርስቲ የዚህን ዓመት ትምህርት ጨርሼ ስመለስ አብራኝ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ ሙገር መጥታ ። አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል ።ይቀጥላል...
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

26 Jun, 17:24


ነገር ብቻ ልለምንህ ፡ ከዚህ ቦታ ይዘህኝ ሂድ" ብላ ተማፀነችኝ ።ይቀጥላል...
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

26 Jun, 17:24


😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 39

የነ ህይወት በር ላይ ደርሼ የእጅ ሰዓቴን ሳይ ከምሽቱ #12:00 ሰዓት አልፏል ። ሰማዩም እየጠቆረ ነው ። እዚህ ከቆየሁ ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ በወቅታዊው ችግር ምክንያት በጊዜ ስለሚዘጋ ማደሪያ አጣለሁ ። ሲጀምር እነ ህይወት ቤት ገብቼ ምን ልላቸው ነው ...? ለማንኛውም አሁን ቤታቸውን ስላወኩኝ የማደርገውን ሁሉ በደንብ አስቤበት ነገ ተመልሼ ብመጣ ነው የሚሻለው ብዬ ወደ ጊቢ ተመለስኩኝ ። ደስ የሚለው ዛሬ ጠዋት ነበር የዘንድሮውን በጀት ዓመት class ያጠናቀቅነው ። final exam ከአስር ቀን በዋላ እንጀምራለን ። መሽቶ ሲነጋ ቁጥር አንድ አላማ ያደረኩት ትናንት የህይወት አባት መጀመሪያ ላይ የሄደበት ቤት መሄድ ነበርና ወደዛው አመራሁ ። ደብተርና ብዕር ይዤ በሩን አንኳኳሁ ። ትናንት የህይወት አባት ስመዋት የነበረችው ሴት ናት ። ሰላምታ ተለዋውጠን "ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ" ። እኔም የመመረቅያ ፅሁፌን ድሬዳዋ ላይ እየሰራሁ እንደሆነ ነገርኳትና ምናልባት አሁን ስላለንበት ሰፈር አመሠራረትና ለየት ያለ ታሪክ ካወቀች እንድትነግረኝ ጠየኳት ። የድሬ ሰው ደግም አይደል ...? እሷም "የድሬ ፀሃይ እረፍት የላት መቼም ፡ በር ላይ ከማቆምህ ወደ ውስጥ ብትገባ የተሻለ ይሆናል" አለችኝና ወደ ቤታቸው ጋበዘችኝ ። እኔም ሳላቅማማ ገባሁ ። ሳሎናቸው ውስጥ ስዘልቅ የትናንቱ ህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ carton network እያየ ነበር ። ቁጭ በል አለችኝና "ስለ ለገሀሬ ብዙም አላውቅም ግን አባቶቻችን እንደነገሩን ከሆነ...!" ብላ የሆነ ታሪክ ነገረችን ። የኔ ፍላጎት እሱ ስላልሆነ ብዙም ትኩረት ሰጥቼ አላዳመጥኳትም ። አይኔ ቤት ውስጥ ያሉትን ነገሮች search እያደረገ እያለ አንድ ፎቶ ላይ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ ። ሴትዮዋ ፣ ህፃኑና የህይወት አባት በጣም የሚያምር የቤተሰብ ፎቶ ተነስተው ቁጭ ። ማፍጠጤ የታወቀኝ ሴትዮዋ "ምነው ፎቶው ላይ ፈዘዝክ" ስትለኝ ነበር ። 'አያይ ምንም' አልኳትና ቀጥዬ ወደ ጉዳዬ ለመግባት መንገድ ስለሆነኝ 'ትዳራችሁ በጣም ያስቀናል ፣ ስንት ጊዜያቹ ነው ...?' ስላት ፤ "መጀመሪያ ግን ፎቶው ላይ ያለው ሰው ማን እንደሆነ አውቀሃል...?" አለችኝ ። 'ካልተሳሳትኩኝ ከንቲባው ናቸው አይደል ...!' አልኳት እያወኩ እንዳላኩ እየሆንኩ ። "ልክ ነህ ፡ አሁን ግን የስልጣን ዘመኑ ስላበቃ ከቦታው ላይ በዚሁ ወር ለቋል ። እና ፎቶው ላይ አይተኸው ትዳራችሁ ያስቀናል ላልከው ፡ ባንተ እይታ ሊሆን ይችላል ። እንዳልከውም ግን የኛ ትዳር ያስቀናል ። ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎበታልና ። ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ብላ ትክዝ ስትል ሁኔታው ይበልጡኑ አጓግቶኝ 'ማለት ፡ ምን ተፈጠረ' አልኳት ሰፈፍ ብዬ ። ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ብንን አለችና "ምንድነው የምቀባጥረው ፡ ተወው እርሳው በቃ ዝም ብዬ ነው" አለችኝ መናገር የሌለባትን ነገር እንደ ተናገረች በሚያስታውቅባት አነጋገር ። ጫን ብዬ ከጠየኳት ማንነቴ ላይ ችግር ስለሚያስከትል ተውኩትና እንዳይነቃብኝ ስለ ድሬዳዋ ጥቂት ጥያቄዎችን ጠይቄ አመስግኜ ልወጣ ስል ሴትዮዋ ህፃኑን "አቤል ፡ ቻው አትላቸውም አንግዳውን" አለችው ። ህፃኑም የእናቱን ቃል ተቀብሎ በሚያሳሳ ድምፅ "ቻው" አለኝና ፈገግ ብዬ ወጣሁ ። አንድ ነገር ግን ጥያቄ ሆኖብኛል ። የልጁ ስም ። አቤል ። የህይወት ጓደኛ የነበረው ፣ በሷ ፋንታ የተሰዋው ፣ ያ ምስኪኑ ልጅም ስሙ አቤል ነበር ። ሴትዮዋ ካለችኝ ነገር ጋር ተደምሮ ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ አለብኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ። ምን ማለቷ ነው ...?ሳስበው ሴትዮዋ ልትለኝ የነበረው ስለ ህይወት ሞት ነውና ፤ የህይወት አባት ሚስት ሆና እንዴት በህይወት ፋንታ አቤል መሞቱን እንዳላወቀች ገርሞኛል ። የህይወት አባት ደግሞ ሆን ብሎ በህይወት ፋንታ የተገደለውን ልጅ ለማስታወስ አቤል የሚል ስም ለልጁ እንዳወጣም ይሰማኛል ። ስገምት ሴትዮዋ የህይወትን በህይወት መኖር የምታውቀው ነገር የለም ። ህይወትም እንደዛው ስለዚህ ቤተሰብ ምንም መረጃ የላትም ። ይሄን ያክል ምን ቢፈጠር ነው ግን ከንቲባው በእነዚህ ሰዎች መሀል ድንበር ሰርቶ እንዳይተዋወቁ ያደረገው ። መልሱንም ከራሱና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅ ። ለማንኛውም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው በሚለው ቃል በማመኔ እያተረፍኩኝ ነው ። ይህ አጋጣሚ ህይወት ትኩረት ሰጥታ እንድታዳምጠኝ ይረዳኛል ። ላወራህ አልፈልግም ብትል እንኳን የአባቷን ከሌላ ቤተሰብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ photo ሳሳያት ደንግጣ ከኔጋር መስማማቷ አይቀርም ። ከሴትዮዋ ቤት እንደወጣሁ ቅድምያ ወደ ፎቶ ቤት ነበር የሄድኩት ። ከዛ መልስ #08:00 ሰዓት አካባቢ ወደ አዲሱ የነ ህይወት ቤት ሄጄ ትንፋሼን ሰበሰብኩና በራቸውን አንኳኳሁ ። ብዙም ሳያስጠብቁኝ በሩ ተከፈተ ። ህይወት ናት ። ልክ እንዳየችኝ ነበር ደንግጣ በሩን በሀይል መልሳ የዘጋችው ። በሩን ክፈቺና እናውራ ስላት ፡ ልትሰማኝ እራሱ ፍቃደኛ ልትሆን አልቻለችም ። እንባ በተናነቀው ድምፅ "ፀባይህ መቼም አይገባኝም ፣ መተሀል ስል ትሄዳለህ ፤ ሄደሃል ስል ትመጣለህ ። ለምንድነው ግን የምታሰቃየኝ ...? እባክህ ላይህ አልፈልግም ፤ ሂድልኝ" አለችኝ ። በቃ ደጋግማ የምትለኝ ቃል ቢኖር "ሂድልኝ" የሚለው ብቻ ነው ። 'እሺ በቃ ይቅርታ' አልኳትና ፎቶ ቤት ሄጄ ከስልኬ ላይ ያሳጠብኩትን የአባቷንና የሌላኛው ቤተሰቡ ፎቶ በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ጊቢ ለመመለስ መንገዴን ጀመርኩኝ ። አስር እርምጃ ሳልራመድ ከዋላዬ "ጥለኸኝ አትሂድ" የሚል ከዚህ በፊት የማውቀው አሳዛኝ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። ዞር ስል ህይወት ናት ። ቀጥ ብላ ቆማ ወደኔ እያየች ነው ። በጣም ናፍቃኝ ስለነበር በሩጫ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ምን እየተሰማት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው ። ሁሉ ነገሯ የሆነው አባቷ እሷ ሳታውቅ ከአንዲት ሴትና ህፃን ልጅ ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ፎቶ ስታይ ልቧ እንደሚሰበር ግልጽ ነው ። ቀና ብላ አየችኝና "እነዚህ ሰዎች ማናቸው ፡ ፎቶውንስ ከየት አገኘህ ...?" አለችኝ ። 'ውስጥ ገብተን ብናወራ አባትሽ ይመጡብን ይሆን ወይስ እቤት ናቸው ...?' ስላት "በቅርብ ሰዓት ስለወጣ ቶሎ አይመጣም ፡ ስለዚህ ወደ ውስጥ ብንገባ ይሻላል ። ሲጀምር መምጣትም ይችላል ። ስለ ሁሉም ነገር ልጠይቀው እፈልጋለሁ" አለችኝና ወደ አዲሱ ቤታቸው አብረን ገባን ። የማውቀውንና ያየሁትን ሁሉ በቅደም ተከተል ስነግራት ፡ ስለ አባቷ የማታውቀው ነገር በመኖሩ በጣም ተገረመች ። "ቆይ እንዴት ይደብቀኛል ፣ ሚስት ቢያገባ እኔ ለሱ የማልደሰት መስሎት ነው ...?" ትላለች አንዴ ወደዚህ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዛ እየሄደች ፡ ያሳጠብኩትን ፎቶ ደግሞ ትኩር ብላ እያየች ። አንዴ ደግሞ ትቀመጥና "ቆይ እሺ ፡ በኛ ምክንያት የአንዲት ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን ማለትስ ምን ማለት ነው ...?" ትልና ድጋሜ ደግሞ ከተቀመጠችበት ተነስታ "በኛ ምክንያት ካለች ፡ በሷና በአባቴ ምክንያት ማለቷ ነው" አለችና ትንሽ እንደ ማሰብ ብላ "የኔ ህይወት እንደዚህ የመሆኑ ጉዳይ ላይ የአባቴም እጅ አለበት ለማለት ፈልጋ ብቻ እንዳይሆን ...?" አለች እኔ ላይ አፍጥጣ ። ለማረጋጋት ብዬ 'በቃ ተረጋጊ ፡ ለጊዜው ስለምንም ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ ምንም ማድረግ አንችልም' ስላት "የኔ ጌታ አንድ

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

25 Jun, 16:49


😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 38

ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
ደንግጬ ቀጥ ብዬ ቆምኩኝ ። ቁጭ ብዬ እንደነበር እራሱ አላወኩም ነበር የእጅ battery አበራና ፡ "push up ሲራ" አለኝ ። አንድ ሁለት መስሎኝ ዝቅ ብዬ ተፍ ተፍ ስል እሱ ይበቃል ሊል ነው ...? በግምት ከ #40 በላይ የሚሆን ሰርቼ እጄን ደክሞኝ ስንቀጠቀጥ አይቶኝ አዘነልኝ መሠለኝ "ቤቃ ቴኔስ" አለኝ ። ደስ ብሎኝ ስነሳ "አሁን ዴሞ sit up ጄምር" አለኝ ። እንደዛው ከሃያ ደቂቃ በላይ ሲያፈጋኝ ከቆየ በዋላ "ካውን ቤዋላ እንደቂዲሙ ቲሆኒና ፡ ዋ" አለኝና "ሂድ አውን" ሲለኝ ደስ ብሎኝ ወደ ቶኒ በር በፈገግታ ስሮጥ የቅድሙ ጥበቃ እየሳቀብኝ "መጀመሪያ ሱሬውን ቀይረህ ና" አለኝ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #07:44 ይላል ። ዶርም ደርሼ እስክመለስ #08 ሰዓት ይሆናል ። በ #1 ደቂቃ ውስጥ ደግሞ በ plane እራሱ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል መድረስ አልችልም ። ቢያንስ ከቶኒ እስከ ሆቴሉ ለመድረስ ከ #20 ደቂቃ በላይ ይወስድብኛል ። ጥበቃው እሺ ብሎ ቢለቀኝ ኖሮ #4 ደቂቃ ባረፍድ ነበር ። አሁን ግን ተስፋ በቆረጠ መንፈስ ወደ ዶርም በሩጫ ተመልሼ ሱሪ ቀይሬ ተመለስኩኝና ፡ በባጃጅ ከቶኒ እሸት ፣ ከእሸት ሼል ተሳፍሬ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ፊትለፊት ስወርድ #08:20 ሆነ ። በበሩ ወደ ሆቴሉ ልገባ ስል የሆቴሉ ጥበቃ ትኩር ብሎ ካየኝ በዋላ "ተስፋዬ ነህ...?" ሲለኝ 'አዎ ነኝ' አልኩት ። "እንካ ይሄ ላንተ ነው" ብሎኝ ሁለቴ የታጠፈ ወረቀት ሰጠኝ ። ገልጬ ለማንበብ ደቂቃ አላባከንኩም ። የህይወት እጅ ፅሁፍ ነው ። አንድ አረፍተ ነገር ብቻ ነው የተፃፈበት ። እሱም "እኔም በጣም እወድሃለሁ" የሚል ነው ። ጥበቃውን የት እንደሄደች ስጠይቀው "ከትንሽ ደቂቃ በፊት ነው በዚህ በኩል በባጃጅ የሄደችው" ብሎኝ ወደ ከዚራ የሚወስደውን መንገድ ጠቆመኝ ። ጥበቃውን አመስግኜ ባጃጅ ውስጥ ገባሁና ወደዚያው አመራሁ ። ከዚራ ስወርድ ግን የት መሄድ እንዳለብኝ ዞሮብኝ ባለሁበት ቦታ ቁጭ ብዬ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ሳወጣ ሳወርድ በስተመጨረሻ አሪፍ ሀሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ አለልኝ ። በደስታ ብድግ አልኩኝና ስልኬን ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ የነ ህይወት ቤት ላይ የተለጠፈውን የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ ፎቶ አውጥቼ ስልኩ ላይ ደወልኩኝ ። እድሜ ለ technology እያልኩ የኔን ድምፅ ወደ ትልቅ ሰው የሚቀይረው option ላይ አደረኩት ። የህይወት አባት ስልኩን አነሱትና ማውራት ጀመርን ። ቤታቸውን ለመግዛት እንደምፈልግና ከዛ በፊት ግን በአካል ቢቻል ዛሬውኑ ተገናኝተን እንድናወራ ጠየኳቸው ። የመሄጃቸው ቀን እየደረሰ ስለሆነ ነው መሠለኝ በደስታ ተስማሙ ። በአቅራቢያቸው ወዳለው ቦታ መምጣት እንደምችል ስነግራቸው ከዚራ እንደሆኑ ነገሩኝ ። ነገር ቀለለ ብዬ #10:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ይዘን ስልኩን ዘጋሁት ። የኔ አላማ እንዳልኩትም ቤታቸውን መግዛት አይደለም ። የህይወት አባት በቀጠሮው ቦታ ላይ ሲገኙ እኔ ሰበብ ፈጥሬ እንደቀረሁ እነግራችኋለሁ ። ከዛን እሳቸው ደግሞ ተናደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከዋላቸው ተከትያቸው ቤታቸው የት እንደሆነ ማወቅ ። ቤታቸውን ካወኩኝ ህይወትን በቀላሉ አገኘዋት ማለት አይደለም...? ከአንድ ሰዓት በዋላ የቀጠሮው ሰዓት ሲደርስ ከተባባልንበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ ተደብቄ ቁጭ አልኩኝ ። የህይወት አባት ልክ በሰዓቱ ወደ ቦታው ከዚህ በፊት በማውቃት የቤት መኪና መጡ....በእቅዴ መሠረት ስልኬን አውጥቼ ለህይወት አባት ደወልኩኝ ። አስቸኳይ ጉዳይ እንደገጠመኝና ለዛሬ እንደማይመቸኝ ስነግራቸው ፡ "ይሁን" የሚል መልስ ቢሰጡኝም ፣ በትንሹም ቢሆን ድምፃቸው ላይ የቅሬታ አይነት ሁኔታ ይሰማል ። ስልኩን ዘጋሁና ተነስተው ወደሚሄዱበት ቦታ ለመሄድ ከተቀመጥኩበት ቦታ ተነሳሁ ። በመኪና ስለሆነ የሚሄዱት እንዳያመልጡኝና ለመከታተል እንዲያመቸኝ ያለችኝን #100 ብር ለባጃጅ ኮንትራት ከፍዬ የግል ሹፌር ቀጥሬያለሁ ። እና አሁን የህይወት አባት በ rava #4 ፊትለፊቴ ፣ እኔ ደግሞ በባጃጅ ከዋላቸው ነኝ ። መኪናቸውን ለገሀር/chemin de fer ወደ ሚወስደው መንገድ እየነዱት ይገኛሉ ። ለገሀር ከጊቢ በጣም ስለሚርቅ ፡ ከኔ ለመሸሽ ከሆነ ሰፈራቸው እዛ ሊሆን ይችላል አልኩኝ በልቤ ። ብዙ ደቂቃ ከተጓዝን በዋላ የህይወት አባት የሆነ ቤት አጠገብ መኪናቸውን አቆሙና ክላክስ አደረጉ ። አኔ ደግሞ ከባጃጁ ወርጄ በሆነ ግንብ ተከልዬ የሚያደርጉትን እያየሁ ነው ። ብዙም ሳይቆይ የቤቱ የውጪኛው በር ተከፈተና የሆነ ህፃን ልጅ እየሮጠ የመኪናውን በር ከፈተና ገባ ። ከዛን መኪናዋ ወደ ውስጥ ገብታ ከፊትለፊቴ ተሰወረች ። የሆነች ሴትም ውጪውን በሁለቱም አቅጣጫ ቃኘችውና በሩን ዘጋችው ። ጠጋ ብዬ ቤቱን በደንብ አየሁት ። ደስ የሚል የቤተሰብ አይነት ቤት ነው ። ህይወት እንደነገረችኝ ከሆነ ምንም አይነት ዘመድና የሚያውቁት ሰው የለም ። ታድያ እነዚህ ሰዎች እነማናቸው ...? የህይወት አባትስ እዚህ ምን ሊሰሩ መጡ ...? ብዙ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ውስጥ ሲመላለሱ ከቆዩ በዋላ የህይወት ስልክ ደወልኩኝ ። እንደተለመደው አይሰራም ። ስለዚህ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ የህይወት አባት ከመምሸቱ በፊት ከቤቱ ወጥተው ሌላ ቦታ የሚሄዱ ከሆነ ጠብቆ መከታተል ። ካልወጡ ደግሞ ተስፋ ቆርጦ ወደ ጊቢ መመለስ ነው ። ከሰላሳ ደቂቃ በዋላ በሩ ሲከፈት ካለሁበት ደንግጬ ተነሳሁ ። የቅድሟ መኪና ተመልሳ ወጣች ። የህይወት አባት መኪናውን አቆሙትና ወርደው በሩ ፊትለፊት የቆሙትን አንዲት ሴትና ህፃን ለጥቂት ሴኮንድ ካወሩ በዋላ ግንባራቸውን ስመው ወደ መኪናው ተመለሱ ። ምናልባት ከጠቀመኝ ብዬ ትንሽ ራቅ ቢልም በስልኬ ፎቶ አንስቻለሁ ። ከዛን መኪናዋ እኛ ወዳለንበት መንገድ መምጣት ጀመረች ። በፍጥነት ባጃጁ ውስጥ ገባሁና ተደበኩኝ ። ሲያልፈን እኛም በሹፌሬ አማካኝነት መከታተሉን ተያያዝነው ። ጭንቅላቴ ግን ያለ እረፍት ያሰላስላል ። እነዚያ ሰዎች ማናቸው ...? ወደ ሰላሳ አምስት ዓመት የሚሆናት ሴት እና አንድ ወደ #4 ዓመት የሚጠጋ ህፃን ልጅ ። በውስጤ ሚስቱና ልጁ ይሆኑ እንዴ እላለሁ ። ግን ሳላረጋግጥ መፍረድም አልፈለኩም ። ብዙ ደቂቃዎችን ከሄደን በዋላ ወደ መጣንበት ወደ ከዚራ ተመልሰን የህይወት አባት አሁንም እንደ ቅድሙ የሆነ ቤት ፊትለፊት መኪናቸውን አቆሙና ከጥቂት ሴኮንድ በዋላ የውጪኛው በር ተከፍቶ መኪናዋ ወደ ውስጥ ገባች ። የድሬዳዋ ሰፈር አሰራር ደስ የሚለው መተጣጠፍ ስለሚበዛው ተደብቆ ለማየት በደንብ ያመቻል ። መኪናዋ ከገባች በዋላ በሩ ላይ አንዲት ቆንጅዬ ሴት ልጅ ቆማ እንደ ቅድሟ ሴትዮ ግራና ቀኙን ስትቃኝ የልብ ምቴ ከዚህ በፊት ታይቶብኝ በማያውቅ ሁኔታ እንደ ፈረስ ይጋልብ ጀመር ። በአካባቢው ከእኛ ውጪ ማንም ስላልነበረ በሩን ወዲያው ዘጋችው ። ልጅቷ ህይወት ናት ፡ አዎ ህይወት ። እኔም ባለ ባጃጁን ሸኘሁትና ወደነ ህይወት ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ.....ይቀጥላል...
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

24 Jun, 16:07


ይቀጥላል...
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

24 Jun, 16:07


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 37
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
ከቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ለመድረስ ስለፈለኩኝ #07 ሰዓት ላይ ከዶርም ወጥቼ በቶኒ በር ለመውጣት ጉዞ ጀመርኩኝ ። ቶኒ በር ላይ ስደርስ ግን ጥበቃው "ተመለስ" አለኝ በንቀት አይነት ድምፅ ። ደንግጬ ዞር ብዬ አየሁትና 'ምነው ያጠፋሁት ነገር አለ እንዴ ...?' አልኩት በትህትና ። "የለበስከው ልብስ ትክክል አይደለም" ሲለኝ ፡ በሆዴ 'ጌታ ሆይ ቀሚስ ነው የለበስከው እንዳትለኝ ብቻ' እያልኩኝ ዝቅ ብዬ የለበስኩትን ሾፍኩት ። በቅርቡ የገዛሁት አዲሱና የምወደው ጅንስ ሱሪ ነው ። ከላይም ቢሆን ካሉኝ ልብሶች ቆንጆ የምለውን ሸሚዝ ነው የለበስኩት ። ትንሽ እንደ መገረም ሆንኩኝና 'ልብሴ ምን ሆነ አልኩት ...?' በድጋሜ ትህትና በሞላው አነጋገር ። "አትሰማም እንዴ የምትባለውን ፡ ሱሪክ የተቀደደ ነው ። በእንደዚህ አይነት ልብስ ደግሞ መውጣትም ሆነ መግባት አይቻልም" አለኝ ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ ። የተቀደደ ሱሪ እንደሆነ ስለማላውቅ በድጋሜ ዝቅ ብዬ አየሁት ። ሱሪው የተቀደደ ሳይሆን ትንሽ ጭረት ነገር ጉልበት ላይ አለው ። ትንሽ ቦታ ብቻ ነው ክሮቹ የተፈቱት እንጂ ምንም የተጋነነ ነገር የለውም ። እንደውም ከቅርብ እንጂ ከሩቅ መተልተሉ እራሱ አይታወቅም ። በጥበቃው ሁኔታ በጣም ስለተገረምኩኝ 'ኧረ የኔ ወንድም ብዙም እኮ አይደለም የተቀደደው ፡ ደግሞም የምቸኩልበት ቦታ ስላለኝ እንጂ ተመልሼ እቀይረው ነበር' አልኩት በመማፀኛ ቋንቋ ። እሱ ግን ሊሰማኝ ነው ...? ጭራሽ ከተቀመጠበት ተነስቶ "ለምንድነው ስራዬ ውስጥ ገብተህ የምትረብሸኝ ፡ ተመለስ አልኩህ አይደል እንዴ ...?" አለኝ ሸሚዜን ጨምድዶ ይዞት ። ከዚህ በፊትም በተሰጣቸው ትንሹ ስልጣን ተማሪዎች ላይ የሚያደርሱት አንዳንድ ያልተገባ ስራቸው ከዛሬው ጋር ተደምሮ በጣም ስላናደደኝ 'እመለሳለሁ አ ፡ ልቀቀኝ ወደዛ' አልኩትና ወደ መጣሁበት ልመለስ ስል ጊቢውን ከሚጠብቁት የመከላከያ ሰራዊት አባል አንዱ "ና ዌዴዚህ ...!" አለኝ በሃይለኛ ድምፅ ። ቆሌዬ ብቻ ሳይሆን ቆዳዬ ጭምር ነበር የተገፈፈው ። በልቤ 'አቤት የኔ ጌታ ፡ ምን አልከኝ' እያልኩ ድምፁን ወደ ሰማሁበት አቅጣጫ ሄጄ ፊትለፊቱ ሹክክ ብዬ ቆምኩኝ ። Ak4 የሚባለው መሳሪያ ይዟል ። ፊቱ ጠቆር ብሎ የሚያስፈራ ሲሆን ቁመቱ ደግሞ ረዘም ያለ ነው ። ፈራ ተባ እያልኩ ወደላይ እያየሁት 'አቤት ፡ ምን ነበር ...?' አልኩት ። ትንሽ የፌዝ ሳቅ ሳቀብኝና "ጢቤቃውን ሜን ሲቲሌው ኔበር ...?" አለኝ በተወላገደ አማርኛ ። 'ምን አልኩት ፡ ያው ፡ እእእ ፡ ምን መሠለህ ፡ እእእ ፡ ቸኩዬ ስለነበር የምለውን ነገር አላውቅም ነበር ፡ እእእ ፡ እና ካጠፋው በጣም ይቅርታ' አልኩት በየመሃሉ ምራቅ እየዋጥኩኝ ። "ኢሱን ፡ በዴንብ ኢናዎራሌን ፡ ና ፡ ቴኬቴሌኝ አሁን" ብሎኝ ቶኒ አዲሱ በር ላይ ከተሰሩት ወደ አንደኛው ክፍል እየመራኝ ይዞኝ ገባ ። ሰዓቴን ሳየው #07:21 ይላል ። በዚህች ምድር ላይ ከሁሉ በላይ ድንቅ የሚለኝ ነገር የሰዓት ጉዳይ ነው ። መች ነው የሚነጋው እያለን ስንጨነቅ ከቆመበት ንቅንቅ አይልም ። ቀጠሮ ኖሮን ቦታው ላይ ለመድረስ ችግር ሲገጥመን ግን ሰዓቱ እንደ ሴኮንድ መሮጥ ይጀምራል ። የቶኒ በር ገና ያላለቀና በመሠራት ላይ ያለ ስለሆነ ክፍሉ ባዶና ቀለም እንኳን ገና ያልተቀባ ፣ በዛላይ ደግሞ መብራት ጭምር የሌለው ጨለማ ክፍል ነው ። በሩ ላይ የተሰሩት ክፍሎች ለጥበቆች ሻዎር ፣ ልብስ መቀየሪያ ፣ መፀዳጃ እና እቃ ማስቀመጫ ይሆናሉ ተብለው የተሰሩ ቢሆኑም ፡ ለኔ ግን በአሁኑ ሰዓት ከማዕከላዊ አሳንሼ የማላየው አስር ቤት ሆነው እየታዩኝ ነው ። መሳሪያ የያዘው ሰውዬ ...ሰሚራ ትባላለች ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት fashion design ተማሪ ናት ። ቤተሰቦቿ ሙስሊም እሷ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ። በዚሁ ጉዳይ ነበር በቴሌግራም የተዋወቅነው ። ከሳምንት በዋላ ጊቢ ውስጥ ICT WAP አካባቢ ከምሽቱ #03:00 ላይ ተቀጣጠርንና ተገናኘን ። እያወራን እያለ ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ሁለት ፌደራሎች አንደኛው መሣሪያ ሌላኛው ደግሞ የጎማ ገመድ ይዘው ወደኛ መጡ ። ያለንበት ቦታ እና ሰዓት በትምህርት ቤቱ ህግ መሠረት ወንጀል አይደለም ። ጊቢ ውስጥ እስከ #04:00 ሰዓት ድረስ እንደፈለግን መንቀሳቀስ ይቻላል ። ሲጀምር ያለንበት ቦታ ለመደበቅያነት የሚያመች ሳይሆን ለማንም ሰው የሚታይና ፊትለፊት የሆነ ቦታ ነው ። ፌደራሎቹ ኮስተር ብለው በጥያቄ ያፋጥጡን ጀመር ። "እዚህ ምን እየሰራችሁ ነው ...?" ሲለን አንዱ 'ምንም ፡ ዝምብለን እያወራን ነው' አልኩት ። "ID አምጡ" አለንና ሁለታችንም ሰጠነው ። ትኩር ብሎ አየና ብሔር የሚለውን ፈልጎ አጣ መሠለኝ "ከየት ነው የመጣችሁት ...?" ብሎ የማይመለከተውን ጥያቄ አቀረበልን ። እኔ 'ከአዲስ አበባ' ስለው ሰሚራ ደግሞ "ከመቱ" አለችው ። ሁለተኛው ፌደራል ወደኔ ተጠጋና በእርግጫ እናቴን መታኝ ። ምን እንዳጠፋው ባይገባኝም ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩኝ ። ሰሚራ ግን በድንጋጤ ልትጮህ ብላ አፏን አፍና ያዘች ። "አንቺ አፍሽን ዝጊ" አላትና አንደኛው በጥፊ መታኝ ። ጉልበታቸውን እና ስልጣናቸውን ሊያሳዩን ስለፈለጉ ሞኝነታቸውን በልቤ አምቄ ተሸነፍኩላቸው ። ባላጠፋነው ነገር ሁለታችንም "እሺ በቃ አጥፍተናል ፡ ይቅርታ" እያለን መለመን ጀመርን ። ጭራሽ ብሶባቸው በእርግጫ የመታኝ ፌደራል ፀጉሬን ይዞኝ መሬት ላይ ጎተተኝ ። አስቡት እንግዲህ ፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ፡ ያውም በ FB library እና ICT WAP መሀል በሚገኘው ቦታ ላይ ሆነን ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ተማሪዎች በቦታው ላይ የሉም ። ለነገሩ ቢኖሩም ከመሸሽ ውጪ ምንም የሚረዱን ነገር አይኖርም ። ሰሚራ እያለቀሰች ነው ። እኔ ደግሞ የፌደራሎቹ ጅልነት አናቴ ላይ ወጥቶ በብስጭት ልፈነዳ ነው ። እነሱ አቅማቸውን እያሳዩን ፡ እኛ ደግሞ ምንም አቅም እንደሌለን act እያደረግን ወደ #10 ደቂቃ ሆነን ። የመፍራት ስሜት አልተሰማኝም ። እነሱ በዚህ ሰዓት ከኛ የሚፈልጉት ከነሱ በታች መሆናችንን እንድናሳያቸው ስለሆነ ፡ እነሱ የሚሉንን ሁሉ አዎ ልክ ናችሁ ፡ እኛ ነን ጥፋተኞቹ እያልን ነው ። ህገ መንግሥት እንጂ ህግ የሌላት ሀገር ፣ ትንሹም ትልቁም ባለው ትንሽ ስልጣን ፈጣሪ ካልሆንኩ የሚልባት ምድር ። በስተመጨረሻ "በቃ ሂዱ ከዚህ" አሉን ID ሳይመልሱልን ። ለሱም ከደቂቃዎች በላይ የሚሆን ከስግደት ያልተናነሰ ልመና አቅርበን መለሱልን ። እንድንሄድ የፈቀዱልን በምን ምክንያት እንደሆነ ሳውቅ ግን በጣም አፈርኩኝ ። እነሱ የሚፈልጉትን ቋንቋ ስንናገር ነበር ደንግጠው የተውን ። እስካሁን በኛ ላይ ሲፈፅሙ የነበረው በሌላ ብሔር ላይ እያደረጉ ያሉ መስሎአቸው ነበር ። ግን በተቃራኒው የሁለታችንም እና የፌደራሎቹ መገኛ ፡ እነሱ በሚያስቡት መንገድ ከአንድ ብሔር ነው ። ደግነቱ እኔ እንደነሱ ብሔር አለመቁጠሬ ነበር ። ፈልገን ባላገኘነው ነገር መኩራትም ማፈርም ጅልነት ነው ። የዚህችን ቀን ትውስታ ቶኒ በር ጭለማ ክፍል ውስጥ ሆኜ ሳስብ ቆየሁና ፡ አሁን ደግሞ ፊትለፊቴ የቆመው መከላከያ ምን ያደርገኝ ይሆን እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ "ተነስ" የሚል የሚያስፈራ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ።

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

23 Jun, 16:08


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 36
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
ስልክ ቁጥሩ ከጠቀመኝ ብዬ ቤታቸው ላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ በስልኬ ፎቶ አነሳሁትና ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመለስኩኝ ። #10 ሰዓት ላይ class ነበረኝና በፍጥነት ቁና ቁና እየተነፈስኩ ክፍላችን ደረስኩኝ ። #20 ደቂቃ አርፍጃለው ። ሆኖም ግን አስተማሪው ተንበርከክ ሳይለኝ አስገባኝ ። የ machine element መምህራችን ህንዳዊ ዜጋ ነው ። ያው የሱ ትምህርት ትርጉም በስለሺ እስኪመጣልን ድረስ ምንም እየገባን አይደለም ። ድንጋዩ ማነው እንዳትሉኝ እንጂ ድንጋይ ላይ ውሃ እያፈሰሰ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ሰውዬው ከሚያወራቸው ነገሮች አንዲት እንኳን አትሰማም ። ከሱ እንግሊዝኛ ይልቅ የ shah rhuk khan ህንደኛ በስንት ጣዕሙ ። ደግሞ መቸክቸክ አይደክመውም ። አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ black board እያጠፋ እየፃፈ ፡ እኛንም ያለ ሞያችን ደራሲ አርጎናል ። እኔ ለሰባቱም ትምህርቶች ትበቃለች ብዬ የገዛዋትን አንዷን ባለ #50 ወረቀት ደብተር እሱ በአንደኛው ቀኑ ነበር ብቻውን መሃል ላይ ያደረሳት ። anyways ግን ከህንድ የሚመጡት አስተማሪዎች ይሄን ሁሉ km አቋርጠው የሚመጡበት ምክንያት አይገባኝም ። ሀገር ውስጥ አስተማሪ ጠፍቶ ነው እንዳንል ስንቱ ተመርቆ ስራ ጠፍቶ እቤት ውስጥ ተጎልቷል ። የማስተማር ብቃት ፈልገውም ከሆነ የኛዎቹን የሚበልጡበት አንድም የተለየ ብቃታቸው አይታየኝም ። እንግሊዝኛቸው ግራ የሆነ ። ከኛ ጋር መማር ማስተማሩ ላይ በቋንቋ ካልተግባባን ምኑን ተማርን ። በቋንቋም ብንግባባ ደግሞ የትምህርት አሰጣታቸው የህፃን ጨዋታ ነው ። ሰሌዳው ላይ የሀገር Note ይፅፉና እሱኑ መልሰው ያነቡልናል ። አለቀ ፡ ደቀቀ ። እኛ ማንበብ ከብዶን ነው እንዴ የመጣነው ...? እንዳልኩትም ራጅ ኩማር ሰሌዳው ላይ የቸከቸከውን አንብቦልን መጨረሻ ላይ quiz ፈተነን ። ከፈለጋችሁ ከደብተር ላይ ስሩ ሲለን እኔ ደግሞ የትልቅ ሰው ምክር አይናቅም ብዬ እሱ እንዳለን ከደብተር ላይ copy paste አደረኩት ። ድፍን ምስር ሳልበላ የደፈንኩት የመጀመሪያው ፈተና ሆኖም በ UNESCO ላይ ተመዝግቦልኛል ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ከ class መልስ ወደ ዶርም ገባሁ ። እንዲህ ደክሞኝ እያለም ግን የያዘኝ ሱስ ሊያስተኛኝ አልቻለም ። high school እያለሁ በጣም ሱሰኛ ነበርኩኝ ። ቤተሰብ እንኳን እስኪማረርብኝ ድረስ የጦፈ ሱስ ውስጥ ገብቼ ነበር ። የተያዝኩት #9ነኛ ክፍል እያለሁ ነው ። ያለሱ አይሆንልኝምና ቤተሰቦቼ በጣም ስለሚያዝኑብኝ ከነሱ ተደብቄ እጠቀም ነበር ። ለሱሴ የሚሆን ገንዘብ አላጣም ። ያለኝን ብር በሙሉ እሱላይ ነበር የማጠፋው ። እንደምንም እየቆጠብኩም ቢሆን ከወር ወር ያደርሰኛል ። campus ስገባ ደግሞ እሱኛውን ሱስ ትቼ ሌላ ሱስ ውስጥ ወደኩኝ ። ይሄ ደግሞ ጭራሽ ከድሮው ሱሴ የባሰ ሆነብኝ ። ስራዬ ሁሉ እሱ ብቻ ነው ። ማጥናት ፣ መማር ፣ ምናምን የለም ። ሙሉ ሰዓቴን እሱ ላይ ነው የማሳልፈው ። ዛሬ ግን ለመተው አስቤአለሁ ። ከቻልኩ እስከነጭራሹ ላለመጠቀም ፤ ካልሆነም በየቀኑ ላለመጠቀም ወስኛለሁ ። ብዙ መጎዳትን እንጂ ጥቅምን አላገኘሁበትም ። ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ገንዘቤን ለ tele መገበር ብቻ ነው ። #9ነኛ ክፍል እያለሁ የጀመረኝ የ facebook ሱሴ ካምፓስ ስገባ ወደ telegram ተቀይሮ ይሄው አይኔ እስኪጠፋ ድረስ ስበላ ፣ ስጠጣ ፣ ስማር ፣ ስሄድ ፣ ስቀመጥ ፣ ስተኛ ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ #24 ሰዓት ከስልኬ ጋር እንደተቃቀፍኩ ነው የምውለው ።የሰው ልጅ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ፈጥሯል ። ለኔ ግን እስካሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለት ፣ የትኛውም ፈጠራ የማይተካከለው ነገር ቢኖር #መተኛት ነው ። እዚጋ አንድ ጊዜ ተረጋጉና ሌላ አለም ውስጥ ሳትገቡ በፊት ነገሩን ላስረዳችሁ ። "መተኛት" የሚለው ቃል ተኛ ፣ ደቀሰ ፣ ወገቡን ፈተሸ ፣ አንሶላ ውስጥ ገባ ፣ አሸለበ እና ከመሳሰሉት የግሪክ ግሶች የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም ያው ግሪኮች ከላይ ያሉት ነው ። መተኛት በሶስት ይከፈላል ። አንደኛው ፦ የህዝብና ቤት ቁጠራን ለማባዛት የሚተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ባልና ሚስት ። ሁለተኛው ፦ ፈጣሪ የማይወደው ፡ እኛ ሰዎች ግን ደስ ብሎን የምንተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ከጋብቻ በፊት ወንድና ሴት የሚተኙት ። ሶስተኛው እና ወሳኙ መተኛት ደግሞ ብቻህን በር ዘግተህ ለጥ የምትለው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ተስፋዬ የሚተኛው ። እና ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስተኛ ነው የዋልኩት ። እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ አልጋ ሂዱ ፤ እሱም ያሳርፋችዋል የተባለ ይመስል ለምሳና ለእራት ብቻ ነበር ከአልጋዬ ላይ የወረድኩት ። አልጋም ላይ ብውልም ግን ምንም አልተኛሁም ። ማሰብ ፣ ማሰብ ፣ እንደገና ማሰብ ። ብዙ ካሰብኩኝ በዋላ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ በራሴ አፈርኩኝ ። ፍቅር እውር ያደርጋል የሚሉት ተረት በኔ ላይ ሲደርስ አየሁኝ ። ቆይ ከነ ህይወት ጋር ለመሄድ ሳስብ እንዴት ቤተሰቦቼን ዘነጋዋቸው ...? ዝም ብዬ እንደ በግ ለማንም ምኑንም ሳልተነፍስ እብስ ብዬ ልጥፋ ነበር እንዴ ...! አባቷ እንኳን ይሁን የኔን ስም process ውስጥ ለማስገባት ብለው ነው አስቀድመው ከመሄዳቸው በፊት የኔን ውሳኔ ለመስማት የፈለጉት ። እኔስ ምን አስቤ ነው ...? anyways አሁን ግን መሄድ እንኳን ብፈልግ መሄድ የማልችልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ። ይሄን ደግሞ ለህይወት እንዳልነግራት ስልኳንና በሯን ዘግታብኛለች ። የማገኝህ አብረኸኝ እንደምትሄድ ከወሰንክ ብቻ ነው ብላኛለች ። ለዚህ ብዬ ከቀጠሮው ቦታ ከቀረሁ ለዘለዓለም ከህይወት ጋር መቆራረጤ ነው ። በቦታው ላይ ተገኝቼ አልሄድም ካልኳት ደግሞ ቅስሟን መስበር ይሆንብኛል ። ልክ በቀጠሮው ቦታ እንደተገኘሁ ስታየኝ በቃ አብሮን ሊሄድ ወስኖ ነው የመጣው ብላ በደስታ ታብዳለች ። እኔ ደግሞ በተቃራኒው እንደቀረሁ ስነግራት ከመቅረቴ ይልቅ በቦታው ላይ መገኘቴ ይበልጡኑ ያሳብዳታል ። እንደማልሄድ ነግሬያት ለምን እንደቀረሁ ቁጭ ብላ ምክንያቴን የምትሰማኝ አይመስለኝም ። ብትሰማኝም ግን ለመቅረት ምክንያት የምደረድር ነው የሚመስላት ። ሁሌም ህይወት በኔ ላይ እንዲህ ነች ። መምረጥ የማልችላቸውን ሁለት ነገሮች ፈትፍታ ታቀርብልኛለች ። እኔ ደግሞ የትኛውን መጉረስ እንዳለብኝ አላውቅም ። ለአንድ በሽታ ሁለት መዳኒቶች ቀርበውልኝ የትኛውን እንደ ምውጥ ግራ ገብቶኛል ። ሁለቱም እኔን የማዳን ትልቅ ሀይል አላቸው ። ነገር ግን ሁለቱም በአንድ ላይ አይወሰዱም ። የግድ አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ። የቀጠሮው ቀን ደረሰ ። ህይወት #08 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ባለችኝ መሠረት ዛሬ በቦታው ላይ በተስፋ እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ ። አሁን የቀረው የኔ ወስኖ መሄድ ወይም የኔ ጨክኖ መቅረት ብቻ ነው ።
"ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፡
ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፣
ልቤ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ፡
ከቶ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ።
ስቋጥር ስፈታ ፡ ሳሰላስል ፡ አንዱን ይዤ ፡ አንዱን ስጥል ፣
ዞሬ ዞሬ ከሁለት ሰው ፡ መምረጥ አንዱን ተቸግሬአለሁ ።ይቀጥላል...
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

22 Jun, 17:36


ሰላም ሰላም ውድ ተከታታዮቼ እንዴት ናችሁልኝ? 10k ደርሰናል እንኳን ደስ አለን? የእናንተ ድጋፍና ገንቢ ሃሳባችሁ ነው እዚህ ያደረሰኝ እና ሁሌም ሀሳብ ድጋፋችሁ እንዳይለየኝ በማለት ለሌሎች ጓደኞቻችሁ በመጋበዝ (Invite) በማድረግ ፖለቲካን ለፖለቲከኞች ትተን ፍቅርን እንዝራ፣ፍቅርን እናቀንቅን? ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና ያላወቅነውን እንወቅ፣እናሳውቅ
ሰላማችሁ ይብዛልኝ
አመሰግናለሁ!!!

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fictional27
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

22 Jun, 16:08


😘የከንቲባው ልጅ 😘

🔥ክፍል 35

ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
ጠዋት እንደተለመደው ወደ ክፍል ሄጄ እስከ ምሳ ሰዓት ተምረን ፣ ቶኒ ምሳ በልተን ወደ ዶርም ገባሁ ። Telegram መጠቀም በጣም ስለምወድ ስልኬን አወጣሁና ገባሁ ። ትናንት በተላከልኝ ፣ መልሼ ስደውል እምቢ ባለኝ ስልክ ቁጥር አዲስ መልዕክት ተላከልኝ ። "እንዴት ነህ የኔ ጌታ ፡ በመጀመሪያ የሚያናድድህ ነገር አድርጌ ከሆነ በጣም ይቅርታ ። ትናንት ያንን መልዕክት እኔ ነኝ አዲስ ሲም ካርድ አውጥቼ የኩልህህ ። ሁለት ልብ ሆነህ ሳይክ በመሀል ተጨነኩና እንዲቆርጥልህ ብዬ እንደዛ አደረኩ ። ስለ ፍቅር ካንተ አንድ የተማርኩት ትልቅ ነገር ቢኖር 'እራስ ወዳድ መሆን የለብንም' የሚለው ነው ። እኔም እራስ ወዳድ መሆን አልፈለኩም ። ከኔ ይልቅ ለማራኪክ የበለጠ ስሜት እንዳለህ በትንሹም ቢሆን አውቅ ነበር ። ትናንት ግን ሙሉ በሙሉ አረጋገጥኩኝ ። መልዕክቱንም እኛው ቤት እያለህ ልልክልህ የፈለኩት ፊትህ ላይ ምን አይነት ስሜት እንደሚፈጠር ለማየት ነበር ፤ ደግሞም አየሁት ። አውቃለሁ ምናልባት አንተ ትናንት ስትመጣ ከናንተጋር እሄዳለሁ ልትለን ይሆናል ። እንደዛ የምታደርገው ደግሞ የማራኪክ ፍቅር ሳይወጣልህ ፣ ለኔ ስትል ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ። ይሄ ደግሞ የኔን ራስ ወዳድነት አጉልቶ ያሳያል ። አንተ በህይወቴ ከመጣህ ጀምሮ እንደ አዲስ መኖር ጀመርኩኝ ፣ ብዙ ነገር አደረክልኝ ። አንተ ያደረክልኝ ነገር ላንተ ምንም መስሎ ሊታይህ ይችላል ። ለኔ ግን ብዙ ነገር ነው ። ብቻዬን ነበርኩኝ ፤ ያውም እስር ቤት ውስጥ ። አንተ ግን መተህ ፈታኸኝ ። ፈተኸኝም ዝም አላልከኝም ፤ አለሜን አሳየኸኝ ። በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ዓመታት ተዘግቶብኝ በፊልም ፣ በመፅሐፍ እና በሙዚቃ የማውቀውን አለም እጄን ይዘህ አሳየኸኝ ። በልቦለድ ላይ የምመኘውን ገፀባህሪ አለበስከኝ ። እናቴ ሰጥታኝ ሰዎች የነጠቁኝን ህይወት መልሰህ ሰጠኸኝ ። ታውቃለህ ፡ ካንተ ጋር ያሳለፍኳት እያንዳንዷ ቅፅበት አሁንም ድረስ ፊቴ ላይ እየተመላለሱ እንደ አዲስ ነፍሴን ወደ ሰማይ ይልኳታል ። ልለይህ መቼም አልፈልግም ነበር ። ይህ ግን ሊሆን አይችልም ። ከዚህ በዋላ እንደ በፊቱ ልጫንህ አልፈልግም ። እኔ ያንተ ብሆንም ፤ አንተ ግን የኔ አይደለህም ። በግድ ደግሞ የኔ ላደርግህ አልሻም ። ምናልባት የፈጣሪ ስራ አይታወቅምና ወደፊት አንድ ቀን አንተን ለኔ ካለ ተመልሰን ልንገናኝ እንችላለን ። ይህ ደግሞ የኔ የወደፊቱ ብቸኛው ምኞቴ ነው ። አሁን ስለኔ ይቅርና ካንተ አንድ የምፈልገው ነገር አለ ። ማራኪህን በጣም ትወዳታለህ ። እሷን እንደ ቀድሞህ ለመመለስ ደግሞ የሚቻልህን ማድረግ አለብህ ። ለፍቅር የሚከፈለውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍለህ የራስህ እንድታደርጋት እፈልጋለሁ ። ይሄን ካደረክ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ። ከዚህ ውጪ ግን ከሶስት ዓመት በዋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ እመጣለሁ ። ያኔ ግን ብቻህን ሆነህ ካገኘሁክ የእናቴን ቀን ይስጠኝ አለቅህም ። ድል ባለ ሰርግ አግብቼህ የራሴ አደርግሃለሁ ። እስከዚያው ግን ፈጣሪ መላዕክቶቹን ልኮ ይጠብቅህ ። መልሼ እስካገኝህ በጣም ትናፍቀኛለህ የኔ ጌታ" ይላል መልዕክቱ ። ባለሁበት ደንዝዤ ቀረሁ ። እንደምንም ወደ ራሴ ተመለስኩና ፡ ከዶርም ወጥጬ ወደነ ህይወት ቤት በረርኩኝ ። ቤታቸው በር ላይ ስደርስ ግን ...ያጋጠመኝ ፡ ህይወትን ለማግኘት ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ነገር ነው ። ቤታቸው ላይ በትልቁ በፖስተር ተደርጎና በር ላይ ደግሞ ወረቀት ላይ ማስታወቂያ ተፅፎ ተለጥፏል ። "for sell ፡ የሚሸጥ ፣ kan gurguramu" የሚል በሶስት ቋንቋ የተፃፈ ነው ። ከስር ደግሞ ስልክ ቁጥር ተፅፎበታል ። ይሄ ማለት እነ ህይወት ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ማለት ነው ። ምናልባት ካሉ ብዬ በሩን በደንብ አንኳኳሁ ፤ ግን ሰሚ የለም ። የህይወት ስልክ ላይ ደወልኩ ፤ ጭራሽኑ አይሰራም ። ተስፋ በቆረጠ አንጀቴ ወደ መጣሁበት ልመለስ አንድ እርምጃ ሳነሳ ከበራቸው ስር የሆነ ፖስታ አየሁኝና ዝቅ ብዬ አነሳሁት ። ገና ስከፍተው የህይወት እንደሆነ በእጅ ፅሁፏ አወኩኝ ። "እዚህ እንደምትመጣ ስላወኩኝ ነው ይሄን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ። አየህ አንተ አሁንም ድረስ ሁለት ልብ እንደሆንክ ነው ያለኸው ። ትናንት እንደ ማራኪክ ሆኜ መልዕክት ስልክልህ ወዲያውኑ ፊትህ ተቀያይሮ አባቴ ጋር ጥለኸኝ ሄድክ ። አሁን ደግሞ መልዕክቱ የተላከልህ ከማራኪክ እንዳልሆነ ስትረዳ ወደኔ ሮጠህ መጣህ ። እየወቀስኩህ አይደለም ። እራስህን በደንብ እንድታዳምጥ ስለፈለኩኝ ነው ። አንተ በሁለት ሰዎች መካከል ቆመህ ልብህ እንደ pendulum ወደዛ ወደዚህ እያለብህ ነው ። ይሄ ደግሞ ላንተም ጥሩ አይደለም ። መወሰን አለብህ ፣ መቁረጥ አለብህ ፤ ለዛ ደግሞ ጊዜው አሁን ነው ። ማንንም ጣልቃ ሳታስገባ ከራስህ ጋር የራስህ የሆነ ንግግር አድርግ ። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አንድ መቶ አንድ ጊዜ አስብ ። ሁሉንም መርምር ፤ የሚበጀውን ደግሞ ምረጥ ። ያኔ ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰው ልብ ያርፋል ። በዚች ምድር ላይ ከአስከፊ በሽታዎች ሁሉ የላቀ ህመም ፤ ቁርጡን ሳያውቁ ዝም ብሎ በተስፋ መቀመጥ ነው ። አገኘው ይሁን ፡ አጣው ይሁን ...? ፣ የኔ ይሁን ወይስ የሌላ እያሉ ቀን ከለሊት ያለ እረፍት ማሰብና መጨነቅ የህመሞች ሁሉ አስከፊው ህመም ነው ። እኔ ደግሞ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆን አልፈልግም ። ወይ አንተን ብቻ ማሰብ ወይም ደግሞ አንተን እስከነ መፈጠርህ መርሳት ይኖርብኛል ። ይሄን ደግሞ ለማድረግ ያንተ እርዳታ ያስፈልገኛል ። አንተ በኔ ላይ ያለህ ተስፋና ለኔ ያለህ ፍቅር ለውሳኔዬ ይረዳኛል ። ለዚሁ መልስ ደግሞ ከመሄዴ በፊት አንድ ዕድል እሰጥህና ለመጨረሻ ጊዜ እንድንገናኝ አደርጋለሁ ። የማገኝህ ያንተን የመጨረሻ ውሳኔ ለማወቅ ብቻ ነው ። ያንቺ ነኝ ወይም ያንቺ አይደለሁም የሚለውን እንድታሳውቀኝ ብቻ ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ ግዴታ ቃል ማውጣት አይጠበቅብህም ። ሰኞ #08:00 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ። በቦታው ላይ በሰዓቱ ከተገኘህ ከኔጋር ለመሆን ፍቃደኛ እንደሆንክ እቆጥረዋለሁ ። ከኔጋር ለመሆን ካልፈለክ ግን ወደ ቦታው መምጣት እራሱ አይጠበቅብህም ። ለብዙ ደቂቃ የምጠብቅህ እንዳይመስልህ ። ባልኩህበት ቦታና ጊዜ በተስፋ እጠብቅሃለው ። እስከዚያው ግን በአካልም ሆነ በስልክ መገናኘት የለብንም ። ከሁሉም ነገር ተገልለህና ብቻህን ሆነህ በንፁህ ህሊናና ልብ በደንብ አስበህበት ላንተም የሚበጀውን ውሳኔ ትወስናለህ ብዬ አስባለሁ ። ስለሁኔታው አባዬ ምንም አያውቅም ። ይሄንን የማደርገው ከሱ ተደብቄ ነው ። ስላንተ ሁሉንም ነገር ነግሬው በጣም ተናዷል ። ፍቅረኛ እንዳለህ ሲሰማ ፊቱ እንዴት እንደተለዋወጠ ብታየው አታውቀውም ። ካሁን በዋላ እንዳገኝህ እንደማይፈልግም ነግሮኛል ። እንደ ምንገናኝ ካወቀ ምን እንደሚያደርግ አላውቅም ። ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ ። እስከዚያው ግን ... ። #ህይወት" ።ይቀጥላል....
.
.
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

20 Jun, 16:04


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 34
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ እስከ #5 ሰዓት ተማርኩኝና በግብዣዬ መሠረት ምሳ ሰዓት ላይ ወደነ ህይወት ቤት ሄድኩኝ ። አባትና ልጅ ደስ በሚል ፈገግታ እሷ ከውጪ ከአጥሩ በር ፣ አባቷ ደግሞ ከቤቱ መግቢያ በር ላይ ተቀበሉኝ ። አባቷ በኔና በእሳቸው መካከል ስለነበረው ግኑኝነት በሙሉ ስለነገሯት ከህይወት ጋር ምንም አይነት ድብብቆሽ መጫወት አይጠበቅብንም ። ምሳ እኔም ስላልበላሁ ፣ እነሱም እየጠበቁኝ ስለነበር የምግብ ጠረጴዛውን ከበን የቀረቡትን የምግብ አይነቶች መርጠን አነሳንና ለመብላት ተዘጋጀን ። አባትና ልጅ ምግቡን ባርከው ተጎራርሰው መብላቱን ቀጠሉ ። እኔ ደግሞ ስርዓቴን ጠብቄ ብቻዬን እየበላሁ ነው ። ማን ያውቃል ምናልባት የወደፊት አማቼም ሊሆኑ ስለሚችሉ በወግ ልማዳችን መሠረት ሰብሰብ ብዬአለሁ ። ምግቡም አለቀና ፣ ጨዋታ ጀመርን ። ስለ ትምህርት ፣ ቤተሰቦቼ ፣ ወቅታዊ ጉዳይ ፣ ምን ያላወራነው ነገር አለ...! በስተ መጨረሻ ህይወት "መጣሁ ተጫወቱ" ብላ ተነስታ ወደ ኩሽና አመራች ። አባቷም ከዚህ በፊት በደምብ አስብበት ብለው የጠየቁኝን ጥያቄ አስታውሰውኝ መልስ መጠበቅ ጀመሩ ። ማታ በዚሁ ጉዳይ እንቅልፍ አልተኛሁም ነበር ። ሳወጣ ሳወርድ ፣ በሀሳብ ስሄድ ስመለስ ነው ያነጋሁት ። በብዙ አቅጣጫ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ወደ ውስጥም አስቤ ልቤን በደንብ ለማዳመጥ ሞክሬ ነበር ። ጭንቅላቴ ውስጥ 'ሂድ ፡ ቅር ፣ ሂድ ፡ ቅር' የሚል ድምፅ ከጩኸት በላይ እየተሰማኝ እንዲሁ ፍዝዝ ብዬ ነው ያደርኩት ። ስለ ማራኪዬ በደምብ አሰብኩኝ ። ስልኬን ካላነሳች ፣ txt ካልመለሰች ፣ በጓደኞቿ በኩል ላገኛት ስሞክር ካልተሳካልኝ ፣ ታድያ በሷ ላይ የቀረኝ ተስፋ ምንድነው ...? ብዬ በጣም ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ከማንምና ከምንም በላይና በፊት አሰቀድማ እኔን ነው የምታምነው ያልኳት ልጅ ፤ እምነቱ ቀርቶብኝ ስልኬን እንኳን ለአንድ ደቂቃ የማንሳት አቅም አጣች ። ሁለታችንም ቃል ነበረን ። በማንምና በምንም አይፈርስም ብለን የተሳሰርንበት ቃል ። በመሃላችን ስለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ፣ ከሰዎች ምንም ይምጣ ምንም ፣ ከሁለታችን አፍ ሳንሰማ ላንከዳዳ ቃል ተግባብተን ነበር ። አሁን ግን ሁለታችንም ስለተፈጠረው ነገር ምንም ሳንባባል ፣ ለመባባልም ጊዜ አጥተን ተለያይተናል ። በሷ ተስፋ ለመቁረጥ ጫፍ ላይ ደረስኩኝ ፤ ግን አልቆረጥኩም ። "ልጅ ተስፋዬ" አሉኝ የህይወት አባት ። ከእንቅልፍ እንደሚባንን ሰው ከሀሳቤ ነቃሁ ። "ምነው ጥለኸኝ ጠፋህ እኮ" አሉኝ አስከትለው ። እኔም ፈራ ተባ እያልኩ 'አያይ እዚሁ ነኝ ፤ የትም አልሄድኩም' አልኳቸውና ለጥያቄያቸው መልስ ልሰጥ ስል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ ከፈትኩት ። የማላውቀው ቁጥር ነው ። "ማራኪዬ እንዴት ነህ ...? ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ ። እየውልህ ፡ በሰዓቱ ባንተ በጣም ተናድጄ ስለነበር ስልክህን ላለማንሳትና መልዕክትህን ላለመመለስ ለራሴ ቃል ገባሁ ። ጠልተህኛል ብዬ ጠላሁክ ። እንደውም ከጊዜ በዋላ ያንተን መልዕክት ላለማየት ብዬ ስልክ ቀየርኩኝ ። ለዛም ነው አሁን በአዲሱ ስልክ ቁጥሬ የማወራህ ። አንተ ምናልባት ረስታኛለች ብለህ ታስብ ይሆናል ። ማራኪዬ ፡ ስላንተ ላለማሰብና ላለማውራት ለራሴ ቃል ገብቼ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ስላንተ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም" ይላል መልዕክቱ ።በስንት መከራና ጭንቀት በስተመጨረሻ ፡ ለአባቷና ለህይወት ልክ እሺታዬን ላበስር ስል ረስታኛለችና ልርሳት ፣ ትታኛለችና ልተዋት ያልኳት ማራኪዬ "ልረሳህ አልቻልኩም" የሚል መልዕክት ልካልኝ ለእሺታ የተዘጋጀውን አፌን ቆለፈችው ። በድንገት 'መሄድ አለብኝ' ስላቸው ተደናግጠው "ምነው የተፈጠረ ችግር አለ እንዴ ...?" አሉኝ የህይወት አባት ። 'አያይ ምንም ችግር የለም' ብዬአቸው ተነሳሁ ። በሁኔታዬ ግራ ቢጋቡም በዝምታ ሸኝተውኝ ባሉበት ፍዝዝ ብለው እያዩኝ ከቤታቸው ከህይወት ጋር ወጣሁ ። "ምን ሆነሃል የኔ ጌታ...?" አለችኝ ህይወትም ። ስልኬን ሰጠዋትና መልዕክቱን አስነበብኳት ። አንብባ ስትጨርስ "እና ለዚህ ነው እንደዛ ባንዴ ተደናግጠህ የተነሳኸው ...?" ስትለኝ ፤ 'ታድያ በዚህ ሰዓት ከዚህ በላይ የሚያስደነግጥ ምን አለ ...?' አልኳት ። "ደስ ብሎሃል አይደል ...?" አለችኝ ቀጥላ ። እኔ ግን ያለሁበትን ሁኔታ እንዴት እንደ ምገልፀው ግራ ገብቶኛል ። መደሰት ይኑርብኝ መከፋት ፣ ማልቀስ ይኑርብኝ መሳቅ ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ። ግን አንድ ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ እየተመላለሰ ይገኛል ። 'መሄድ የለብህም ፡ ለማራኪክ የገባኸውን ቃል አስታውስ ፣ ከዚህ በፊት አንቺ የልጆቼ እናት ነሽ ያልካትን አስታውሰህ ወደሷ ተመለስ ፣ መጀመሪያም ዝምታዋ ነበር እንድትሄድ ያስወሰነህ ፡ ይኸው አሁን ከአንደበቷ ሰምተሃል ፡ ስለዚህ ከህይወት ጋር ወደ ውጪ መሄድ የለብህም' ይለኛል ። ይሄን ውሳኔ ተቀብዬ ለህይወት ማሳወቅ ደግሞ ለኔ ከሞት በላይ ያስፈራኛል ። ዝም ብላ ካየችኝ በዋላ "ከኔጋር መሄድ አትፈልግም አይደል ...?" አለችኝ ። አይኖቿን እያየሁ መመለስ ስለከበደኝ 'አላውቅም ህይወት ፣ አላውቅም' አልኳት አንገቴን ደፍቼ ። "ስሜትህ ይገባኛል ። ማራኪክ አንተጋ ምን ያክል ቦታ እንዳላት መገመት አይከብደኝም ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሯን የሳምካት ልጅ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ላይ የምታውቀውን የፍቅር ህይወት በእውን ያሳየችህ ሴት ፣ በፍቅርም ለሁለት ዓመታት ርቀት ሳይበግራችሁ በስልክ ብቻ እያወራችሁ ያልተለያያችሁ ጥንዶች ፣ በስልክም ከአምስት ሺህ በላይ መልዕክት የተፃፃፋችሁ ፣ በየ ሳምንቱም ተደዋውላችሁ የምታወሩ ፣ በመሃላችሁ በተፈጠረው አለመነጋገር ምክንያት ብቻ ለወራት ሳታወሩ ብትቀሩም በስተመጨረሻ ግን ረስታኛለች ብለክ የደመደምከው ነገር በተቃራኒው ከልብህ ከማንም በላይ የምትወዳት ፍቅርህ "ልረሳህ አልቻልኩም" ስትልክ ምን እንደ ሚሰማክ አውቃለሁ ። አንተ ለሷ ያለህ ስሜት ፡ እኔ ላንተ ያለኝ ስሜት ስለሆነ በደንብ ይገባኛል ። ሲጀምርም አባቴ ከኛ ጋር ሂድ ማለት አልነበረበትም ። እኔኮ በጣም ደህና ነኝ ። አንተን ባጣ እራሴን የማጠፋ መስሏችሁ ነው ...? በፍፁም እንደዛ አላደርግም" ። አለችኝና እስኪጨንቀኝ ድረስ ጥብቅ አርጋ አቅፋኝ ፣ ጉንጬንም ስማኝ በቆምኩበት ትታኝ ወደ በሩ ሄደች ። በሩ ጋር ስትደርስ ዞር ብላ አየችኝ ። ፊቷ በእንባ ተሸፍኗል ። ልቤን ስትበላኝ ወደሷ ሄጄ ላቅፋት ስል ወደ ውስጥ ገብታ በሩን ዘጋችው ። እኔም ሰፈራቸውን ለቅቄ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሁ ። መልዕክቱ በተላከልኝ ስልክ ላይ ደወልኩኝ ። ነገር ግን ቴሌ "አሁን ማግኘት አይችሉም" አለችኝ ። እስከ ምተኛበት ሰዓት ድረስ ደጋግሜ ብደውልም ሊሰራልኝ አልቻለም ። ምን እየተካሄደ ነው ...? መልዕክት ልኮ ስልክ ማጥፋት ምን የሚሉት ጉዳይ ነው ...?
ይቀጥላል....
.
.
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

19 Jun, 16:48


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 33
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
ተነሳሁ አፌም ተከፈተ ። 'ለዚህ ሁሉ ነገር ሶስት አካላትን መውቀስ እፈልጋለሁ ። (ጥቅም ባይኖረውም ...😢) ። #1ኛው :- ያው ሁላችንም በስም ብቻ የምናውቀው መንግስት ተብዬው ነው ። ወንጀል በማንኛውም ሁኔታ ፣ ቦታና ፣ ጊዜ ፡ በሆነ ሰው/ቡድን ሊፈፀም ይችላል ። የመንግሥት ዋነኛ ስራው ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ፤ ካልሆነም ወንጀለኞቹን ይዞ ህግ ፊት ማቅረብ ነው ። ይህን ካላደረገ መንግስት የለም ማለት ነው ። እባክህ መንግስት ሆይ ፡ ከሰማኸኝ በጣም ናፍቀህኛል ፡ ላገኝህ እፈልጋለሁ ። ብቻህን ቢሆን ይመረጣል ስል ሁሉም ባንድነት አሽካኩ ። #2ኛው :- ከሁሉ ደግሞ የገረመኝ ነገር ፡ የሚዲያዎቹ ነው ። "በኮርያ በተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት የሁለት ተማሪ ህይወት አልፏል" EBC ። ስንቱ ምስኪን ሀገሩ ላይ እየሞተ እያለ ስለማያገባን ፈረንጅ ይተርክልናል ። ምናለበት እስኪ ብያንስ እንኳን ነፍስ ይማር ቢል ...?😢 ። ነው ወይስ ግዴታ ባለስልጣን ወይንም አርቲስት መሆን አለብን ...? ። ለስሙ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው ። እኔ ግን የመንግስት ቴሌቪዥን ብዬዋለሁ ። እስቲ እውነት የኛ ሚዲያ ከሆኑ "ተማሪዎች ላይ ስቃይ እየደረሰ ነው ፡ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል" ይበሉ ። #3ኛው :- ህዝብ ነው ። ምነው ይህ ህዝብ ለስንቱ እንዳልተሰለፈ ፡ ዛሬ ለተማሪ ሲሆን ዝም አለ ። ለዘይት ፣ ስኳር ፣ አብይ ፣ ኦነግ ፣ ግንቦት #7 ፣ ጃዋር ፣ እንደዛ በየ አደባባዩ እንዳላሽቃበጠ ፡ ምነው ዛሬ የራሱ ልጅ ባደባባይ ሲገደል ፀጥ አለ ...?😥 ። ብያውቁ ሁላቸሁም ተማሪ ሆነው አልፈዋል ። ተማሪዎች ሲገደሉ ፣ ሲሰደዱ ፣ ሲደበደቡ ፣ ሲሰደቡ እያዩ ባልሰማ ዝም ፤ በተቃራኒው ግን ለአንድ ለማይረባ ነገር ብለው #5 ሚሊዮን ሆነው አደባባዩን ይሞሉታል ። እስቲ የተማሪዎች ህመም ከተሰማቸው ለምን "እኔም ተማሪ ነኝ" ብለው አደባባይ አይወጡም ። ለማንኛውም ፡ በዚህ ዘመን ሰው አለኝ ማለት ከንቱ ነው ። መንግስትም ህዝብም ያጣ generation ...😔 ። እንደኔ የዚህ ክፉ ዘመን የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆናችሁ ተስፋችሁን እግዚአብሔር ብቻ አድርጉ ። "አሁንስ ተስፋዬ ማነው ፡ እግዚአብሔር አይደለምን ...?" አይደል ቅዱሱ መፅሐፍም የሚለው ። ይህን ስናገር ታዛቢ እንጂ ሰሚ እንደሌለኝ እያወኩኝ ነው ። ግን ብያንስ ስለተነፈስኩኝ ቀሎኛል ። እውነቱን ሸሽገህ የህሊና እስር ቤት ከምትገባ ፡ እውነቱን ተናግረህ የመንግስት እስር ቤት ብትገባ ይሻልሀል' ብዬ ስቀመጥ ሁሉም ተማሪዎች በጭብጨባ ክፍሉን አናወጡት ። እኔም 'አመሰግናለሁ ፣ ኧረ አይገባም አመሰግናለሁ' እያልኩ አሽቃበጥኩ ። ወዲያው ግን ግንባሬን የሆነ ነገር ቋ ሲያደርገኝ ደንግጬ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ። ከዛን የ Fluid አስተማሪያችን "ምንድነው የምታመሰግነው ...?" አለኝ ኮስተር ብሎ ። ለካ ያን ሁሉ ስብሰባው ላይ ያወራሁት ክፍል ውስጥ ሆኜ ስቃዥና ሳንቀላፋ ነበር ። ውሃ በላኝ ።....

ከህይወት ጋር የልደቴ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ከተያየን እንደ ቀልድ አምስት ቀናት ተቆጠሩ ። በጣም እንደናፈቀችኝ ያወኩት ክፍል ውስጥ ሴት መምህራችን ስታስተምረን መልኳ ወደ ህይወት ፊት ተቀይሮ ፈገግ ብዬ በፍቅር አይን ስመለከታት ተገርማ "ተስፋዬ ምን ፈገግ የሚያስብል ነገር ተገኘ ...?" ስትለኝ ነበር ። ጥቁር ሰሌዳው ላይ ፣ ደብተሬ ላይ ፣ ጠረጴዛ ላይ ፣ ግድግዳ ላይ ፣ በሄድኩበት ሁሉ የምትታየኝ እሷ ብቻ ሆናለች ። ከሷ ጋር ያሳላፍኳቸውን እያንዳንዷን ቅፅበት ሳስታውስ ነፍሴ በደስታ ትፈነድቃለች ። ለሊት ብቻዬን በዶርማችን በር በኩል ሽቅብ ከማያቸው እልፍ አእላፍ ከዋክብት ይልቅ በልቤ ውስጥ የምታንፀባርቀው እሷ ሆናለች ። ከሷ ጋር ሳሳልፍ የተሻሉ ቃላትን ተጠቅሜ ደስ ላላሰኛት እችላለሁ ። ነገር ግን በክንዶቼ መሃል አስገብቻት ፣ ደረቴ ላይ ተለጥፋ ፣ ጆሮዎቼ የሷን ድምፅ ብቻ ሲሰሙ ፣ አይኖቼም እሷኑ ብቻ እያዩ ፣ ከልቤ ሃሳቧን ፣ ጭንቀቷን ፣ ሀዘኗን ፣ ደስታዋን ፣ ሳቅና ሰቀቀንዋን ሁሉ ስካፈላት ከምን ጊዜውም በላይ ስለምትደሰት ፤ ደስታዋ ደስታዬ ሆኖ ከዋለ ካደረ ቀናቶች ተቆጥረዋል ። ከረገጠችው መሬት በላይ በኔ ላይ ዕምነት ኖሯት ሳያት ታስደምመኛለች ። እኔም ልክ እጆቿን ይዤ አይኖቿ

​​ን ስመለከት ብርሃን ይታየኛል ፤ ጉልበት ይኖረኛል ። እራሷ ደካማ ጎኔ ሆኗ እራሷ ታበረታኛለች ። በስልክ በየ ሰዓቱ እናወራለን ። አባቷ ያንኑ ዕለት እሁድ ምሽት ወደ ቤት እንደ ተመለሱና የዛሬ ሳምንት ማለትም ልክ እኔና እሷ በተዋወቅን በወሩ ግንቦት #30 ወደ አሜሪካ እንደ ሚበሩ ነግራኛለች ። ልክ ይሄንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ብሎ ነበር ። ከአካላቶቼ መሃል አንዱ የተቆረጠ ያህል ህመም ተሰማኝ ። የመጨረሻ ውሳኔዬን ነገ እቤታቸው ሄጄ እንዳሳውቃቸው አባቷ ደውለው ነገሩኝ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ። ጉዞው ሁሉ ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። እኔን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የሷ አለመኖር ያማል ። የኔ አለም ለመሆን በተቃረበች ማግስት ከተለየችኝ ከአለም ጋር መጣላት ይሆንብኛል ። እሷን በፀሃይ ፋንታ እንደ ምትክ ሆና በተሰጠችኝ በመጨረሻዋ ሰዓት መሄጃዋ ሲደርስ ብርሃን ማጣት ይሆንብኛል ። ትታኝ መሄዷን ሳስብ ፀሃይ ፊቷን አዙራብኝ ፣ ጨለማ የዋጠኝ ያክል ተሰማኝ ። ጨለማ ውስጥ ወደኩኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ላይ ተጣልኩኝ ፣ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፣ በናፍቆት ውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑን እና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልምብኛል ። እኔ እሷን ካጣሁ እንኳን ቀኑን እራሴንም መርሳቴ አይቀርም ። የኔና የሷ ፍቅር ቀናት ስለተቆጠሩ አይደለም ። ፍቅር የጊዜ ማጠርና መርዘም አይደለም ። ፍቅር ማለት ፡ ያ በማንኛውም አጋጣሚ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ፣ በየትኛውም ቦታ ላይ ያሳለፍናት ያቺ ጊዜ ፣ ደቂቃም ትሁን ቅፅበት የማይረሳ ትዝታን ያሳለፍንባት ፣ በልቤ በልቧ የተነጋገርንባት ፣ በደስታ ሰክረን ያሳለፍናት ፣ አዎ እሷ ናት ። ልክ ፀሃይ አለምን ለማብራት እንደ ተፈጠረች ፣ ህይወትም ለመኖር ፣ ዝናቡም ሊዘንብ ፣ አበቦች ሊፈነዱ ፣ ሌሎችም ሌሎችም ለአላማቸው ልክ እንደተፈጠሩ ፣ የኔ መፈጠርም እሷን ለማፍቀር ቢሆንስ እያለ ልቤ ከራሴ ጋር ይሟገቱ ጀመር ።ይቀጥላል...

.
.
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ንባብ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

19 Jun, 06:18


ሳውዲ
አዲስ መረጃ
በትንሹ ከ 33ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን
* ህፃናት
* ሴቶች
* ወንዶች
በስሞኑን አፈሳ በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ገብተዋል::
ጉዳዩን የሰላም ሚኒስቴር እየተክታተልኩት ነው ቢልም
* ኢቢስ
* ፋና
ቢዘግቡም
ጉዳዮን ግን እጅግ አሳሳቢ ነው
በአስቸኳይ መፍትሄ ካልተወሰደ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን
በእስር ቤት
* በበሽታ
* በጭንቀት
እስከ ሞትም ሊያደርሳቸው የሚችል ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ::
አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሰጥልን?
* መረጃ ተለዋወጡ
* ሼር አድርጉ
ድምፅ ሁኑ
አሁንም ቢሆን ተሰፋችን ፈጣሪያችን ብቻ ነው
.
.
.
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
http://t.me/fictional27
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን
ይጠብቅልን አሜን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

18 Jun, 16:25


😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 32
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
"ግንቦት #17,1989 ዓ.ም ከለሊቱ #06 ሰዓት አካባቢ ። ሰማዩ ከሰይጣን በላይ ጠቁሯል ። (ቆይ ግን ሰይጣንን ማንም ሰው ካላየው ፡ መልኩ ጥቁር እንደሆነ በምን አወቅን ፣ ነው ወይስ የማይታይ ነገር ጥቁር ይመስለናል...?) ። ምድርም ያለ ፀሀይ ብርሃን የላትምና የሰማይ ተከታይ ሆናለች ። ከአንዲት እናት በስተቀር ሰፈሩ በሙሉ ፀጥ ረጭ ብሏል ። እናቲቱ ግን እያቃሰተችና እየጮኸች ትገኛለች ። እንዲህም ሆኖ ግን ማንም ሰው አልተረበሸም ። በተቃራኒው ሁሉም ሰው ተጨንቆ ወደላይ አንጋጦ ፀሎት እያደረገ ይገኛል ። በዚያች የጭንቅ ለሊት ሁሉንም ወደ ሳቅ ፣ ደስታና ዕልልታ የቀየረ አንድ ነገር ተፈጠረ ። በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ወንድ ልጅ ይቺን ምድር በሰላም ተቀላቀለ ። እናቲቱም የልጁን ስም ተስፋዬ ብላ ሰየመችው ። የወደፊት ተስፋዋን እሱ ላይ ጥላለችና" ። ይሄን ታሪክ የስልኬ Note ላይ ፅፌው ስለነበር ፣ ህይወት የልደቴን ቀን ከዛ ላይ አይታ እንዳወቀች ነግራኛለች ። በ #17 ለሊት ስለ ተወለድኩኝ ልደቴን በ #18 ነው የማከብረው ። እና ዛሬ ልደቴ ነው ፤ #22 ዓመት ሞልቶኛል ። (እና ምን ይጠበስ ...😬) ። ዛሬ እንኳን ጥብስ አይደለም የምፈልገው ። ልደትም አይደል ፣ ለፎቶው ድምቀት ድፎ ዳቦ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ፣ ለስላሳ ፣ ፊኛ ፣ ፈንዲሻ እና ግብዳው ሻማ ይሁንልኝ ። እንደውም #21 ዓመት ስላለፍኩኝ አንድ ሳጥን ቢራ ይዛችሁልኝ ኑ ። በነገራችን ላይ በዚህ ዓመት መምረጥ ብቻ አይደለም ፤ መመረጥም እችላለሁ ። እንደውም በቀጣዩ ምርጫ ላይ መሳተፍ እፈልጋለሁ ። በዚሁም እግረ መንገዴን የምርጫ ቅስቀሳ ባደርግ ውስጤ ነበር ። ግን በልደት ቀን ስለ ፖለቲካ አይወራም ። እዛው #MA ሆቴል ምሳ በልተን ፣ ህይወትን ቤቷ ድረስ ሸኘዋትና ጊቢ ውስጥ ስለ ወቅታዊው ችግር ስብሰባ እንዳለና መቅረት እንደሚያስቀጣ ተደውሎ ስለተነገረኝ ለዛው ብዬ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገብቻለሁ ። ስብሰባው #08 ሰዓት ተብሎ #10 ሰዓት ተጀመረ ። ስብሰባውን የተጠሩት ሁሉም የጊቢው ተማሪዎች ሲሆኑ ፤ የተገኙት ግን ስብሰባ የሚወዱ ተማሪዎች (አብዛኛው የ Law ተማሪዎች ናቸው...🙆) ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ባለስልጣናት ፣ የጊቢው አመራር አካላትና የሰሙትን ወሬ ላልሰሙት የሚያወሩ ጋዜጠኞች ናቸው ። የስብሰባው አጀንዳ ፡ ሰሞኑን ጊቢ ውስጥ በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል ነው ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ተጣሉ የተባሉትን ተማሪዎች ማስታረቅ ግድ ነው ። ስብሰባው ላይ ደግሞ የተጣሉት ተማሪዎች አልተገኙም ። ሆኖም ግን በስተመጨረሻ ያልተጣላነውን እኛኑን አስታርቀውን ለሁለት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት ነገ እንዲጀምር ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ ። ምሽት ላይ ጓደኞቼ #ማራኪ club ይዘውኝ ሄደው አንድ ሁለት እያለን ቆንጆ ምሽት አሳልፈን ወደ ዶርም ገባን ። እንኳን ተወለድክልን ያላችሁኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ፈጣሪ ውለታ መላሽ ያድርገኝ ። ለዚህች ቀን ያደረሰኝ ፈጣሪ ነውና ከሁሉ በላይና በፊት ምስጋናውን እርሱ ይውሰድ ። ጠዋት ነግቶ ቁርስ ሳንበላ ለ #16 ቀን ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ተጀመረ ። የልደቴ ቀን ግን ለጊቢው እንደዚህ በረከትን ይዞ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር ። በጊቢው ሰላም መሆን ደስ ቢለኝም ትምህርት በመጀመሩ ግን ከፍቶኛል ። አስቡት እስኪ ፡ #2 ሳምንት ሙሉ ስለ ትምህርት ሳናስብ አሳልፈን በአንዴ ወደ ትምህርት ግቡ ሲባል ትንሽ አይከብድም...? እኔ በበኩሌ ለትምህርት የምንዘጋጅበትን ሌላ ሁለት የዕረፍት ሳምንት ቢሰጠን ባይ ነኝ ።በበላይ አካላትና የሀይማኖት አባቶች በየክፍሉ አስቸኳይ ስብሰባ ተደረገና ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ወደ ፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ እንድንነጋገር ተደረገ ። እንደ ዕድል ሆኖ እኛ ክፍል የደረሰው የጊቢው president ናቸው ። ስሜን ማን እንደነገሯቸው አላውቅም ፤ "ተስፋዬ እስቲ ኢትዮጵያዊነት ላንተ ምንድነው...?" አሉኝ ከዛ ሁሉ ተማሪዎች እኔን መርጠውኝ ። መጀመሪያ ስሜን ሲጠሩ ደንግጬ ነበር ። ከተነሳሁ በዋላ ግን የኢትዮጵያ አምላክ እረድቶኝ ሰይጣን ይዞት ፀበል እንደ ገባ ሰው መለፍለፍ ጀመርኩኝ ። 'እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም' ብዬ ንግግሬን ስጀምር ሁሉም አፈጠጡብኝ ። 'አይገርማችሁም ፡ እናንተም ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ። በልባችሁ ፡ "አሜሪካዊ ናችሁ በለን" እንደ ምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሁልሽም ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተወለድሽ ብቻ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ተሳስተሻል ። ትንሽ እንኳን አናፍርም ...? ፡ ለዚች ክብርት ሀገር ብለው የሞቱ ስንቱ ደግና አንበሳ አባት ፡ ስንቷ ሩህሩና ጀግና እናት በተጠሩባት ፤ እኛ በዘር በሀይማኖት እየተባላን ፡ ከነሱ እኩል ኢትዮጵያዊ ተብለን ስንጠራ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጠንም ...? ፡ እኔ በበኩሌ ስማቸውን ጠርቼ ከማልጨርስና ከማልጠግብ የሀገራችን ባለውለታዎች እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ መጠራት አልፈልግም ። እስቲ ለዚች ሀገር ሲሉ የሞቱትን ጀግኖች እናስባቸው ። አፄ ቴዎድሮስና በላይ ዘለቀ የሞቱት ለአማራ ክልል ነው ...? ፡ ጀነራል ታደሳ ብሩና ገረሱ ዱኪ የሞቱት ለኦሮሚያ ክልል ይመስላችኋል ...? ፡ አቡነ ጴጥሮስስ የሞቱት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው ...? ፡ ነው ወይስ አሚር የሞተው ለእስልምና ይመስላችኋል ...? ። እንደዛ ካሰብባችሁ ተሳስታችኋል ። እነሱ በጊዜያቸው ክልል የሚል ድንበር አልነበራቸውም ። በሀይማኖት መከፋፈል ሀሳቡም አልፈጠረባቸውም ። እነሱና እነሱን የመሰሉ ስንቶቹ ለዚች ክብርት ሀገር ኢትዮጵያ ብለው እንጂ ለዘራቸው አልነበረም ጥብቅናቸው ። ምን ነካን ጎበዝ ...? ፡ ጠላት ከውጪ ሲመጣብን አንድላይ ሆነን እንዳልመከትን ፡ ዛሬ ላይ እርስ በእርስ መጫረስ ምን የሚሉት ጉድ ነው ...! አሁንም ሳስበው ጥላቻው የኛ አይመስለኝም ። እናም ወገኖቼ ፡ የኛን አንድነት የማይፈልጉትን አንድ ላይ ሆነን በፍቅር እንመክታቸው ። ጥፋታችንን የሚፈልጉትን ተቃቅፈን እናሳፍራቸው ። እንደ ክልልና ሀይማኖት ሳይሆን ፡ እንደ ሰው አስበን ኢትዮጵያን ከጥፋት እናድናት ። ያኔ እኔም እናንተም ልክ እንደ ቀደምቶቻችን ኢትዮጵያዊ ተብለን እንጠራለን ። ክልል ሳይሆን ሀገር ስላስረከብናቸው ልጆቻችንም ይኮሩብናል' ብዬ ቁጭ አልኩኝ ። እናንተ ፡ እህህህ የሚለኝ አጣሁ እንጂ እተነትነው የለ እንዴ ...? ። ሁሉም ተራ በተራ የሚሰማቸውን ከተናገሩ በዋላ ፕሬዚዳንቱ "እስቲ ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ምንድነው ትላለህ ወጣት ተስፋዬ" አሉኝ በድጋሜ ።ይቀጥላል......
.
©fictional27
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ጊዜ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

17 Jun, 20:57


😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 31

ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
"የኔ ሻህሩክ ፡ እኔኮ ስቀልድ እንጂ አትሆንም ብዬ አይደለም" አለችኝና ከወንበሩ ላይ ተነስታ በጀርባ በኩል ጥምጥም ብላብኝ ጉንጬን ግጥም አርጋ ሳመችኝና "ይቅርታ እሺ የኔ ጌታ ...!" ብላኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች ። እኔም 'አያሳስብም ፣ ደግሞም ምንም አለተቀየምኩሽም ። ቆይ ግን አንቺስ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ...? ያው ስታድጊ ያላልኩሽ already አርጅተሻል ብዬ ነው' አልኳት ። "ሙት እሺ ፡ እኔ እንኳን መሆን የምፈልገው እንዳንተ ቀላል ላይሆንልኝ ይችላል ። እንዳልከው ማንኛውንም ነገር ከተፋለምንለት ልናገኘው እንችላለን ። የኔ ህልም ግን ያን ያክል ቀላልና በዋዛ የሚኮን ነገር አይደለም ። በቃ ህልም ብቻ እንጂ እውን አይሆንም" ስትለኝ ፡ ይሄን ያክል ምን ለመሆን ብትመኝ ነው አልኩና ህልሟ ምን እንደሆነና በምችለው ሁሉ እውን እንዲሆንላት ከጎኗ እንደምሆን ነገርኳት ። እሷም "የወደፊቱን ህልሜን ብነግርህ እንዲሳካልኝ ከጎኔ እንደ ማትቆም አውቃለሁ ። ይሄን የምታደርገው ደግሞ እኔን ለመጉዳት እንዳልሆነም አውቃለሁ ። የኔ ህልም ያንተ ሚስት መሆን ነው ። እና እውን እንዲሆንልኝ ትረዳኛለህ ...?" አለችኝ ። 'እኔኮ እየቀለድኩ አይደለም የምሬን ነው' ስላት "በቃ እንደውም እሱን እርሳውና አንድ ነገር አምሮኛል" አለችኝ ። 'በአንድ ቀን አርግዘሽ እንዳይሆን ያማረሽ' ስላት "እኔም እየቀለድኩ አይደለም የኔ ጌታ ። ስወድህ ግን እምቢ እንዳትለኝ ። ዋና በጣም አምሮኛል ፤ በእናትህ የምታውቀው ቦታ ካለ እዛ ውሰደኝ" አለችኝ በነዚያ መንግስትን እንኳን ሀሳብ ለማስቀየር ሀይል ባላቸው አይኖቿ ጭምር እየተማፀነችኝ ። የለስላሳውን ሂሳብ ከፍለን በመኪናችን እዛው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው #MA ሆቴል በረርን ። ደርሰን ልብሳችንን አውልቀን የዋና ልብስ ከዛው ተከራይተን ለመዋኘት ተዘጋጀን ። ደግነቱ ከኛና ከሚያስዋኘው ልጅ ውጪ ማንም ሰው በቦታው የለም ። "ስማኝማ ፡ ለምን ደብረ ዘይት ያለማመድከኝን ዛሬ ከ #10 test አትፈትነኝም ። ከፈለክ እንደውም final አርገው" አለችኝ ህይወት እየሳቀች ። እኔም 'በዋላ ከከበደሽ ግን የለሁበትም' አልኳትና ወደ ዋና ገንዳው ገፈተርኳት ። አንዴ ጠጥታው ስትወጣ ፣ ሌላ ጊዜ ወደ ውስጥ ስትሰምጥ መጨረሻ ላይ እንደምንም ተረጋጋችና ውሃውን ተቆጣጠረች ። ቀና ብላ ወደላይ እያየችኝ "ጨካኝ መምህር ነህ እሺ" አለችኝ ። 'እሺ የኔ ጉረኛ ተማሪ' አልኳትና ወደ ውሃው ውስጥ ዘልዬ dive ገባሁ ። ብዙም perfect ስላልሆነች ትንሽ አለማመድኳት ። ለመልመድ ብዙም አልተቸገረችም ። እንደውም ከባለፈው ይልቅ በጣም ተሻሽላ ከኔም ጋር ፉክክር ጀምራለች ። ዕረፍት እየወሰድን እየዋኘን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። "ካሁን በዋላ እንደውም እኔ እራሴ እንዳላለማምድህ" አለችኝ እዛው ውሃ ውስጥ የገንዳውን ጫፍ ግድግዳ ተደግፈን እንደቆምን ። make up ስለማትጠቀም ውሃ ነክቷትም መልኳ እንደዛው ውብ እንደሆነ ነው ያለው ። እንደውም ውሃ ሲነካው ይብስበታል ። እጆቼን በእጆቿ ስትይዘኝ ውሃ ውስጥ ቆሜ ሙቀት ይገለኛል ። መላ ሰውነቴን የሆነ ነገር ውርር ያደርገዋል ። አይኖቿን አይኖቼ ላይ ከጣለች ደግሞ በቃ ልቤ ወጥቼ ከሷ ልብ አጠገብ ካልተቀመጥኩ ይላል ። "እኔን ውሃ ውስጥ አቁመህ ስለምን እያሰብክ ነው ...?" አለችኝና ከሃሳቤ ባነንኩኝ ። 'ስላንቺ ነዋ ፣ ሌላ ስለማን አስባለሁ' ስላት "ስለኔ ምን የኔ ጌታ" ብላኝ ይበልጡኑ ወደኔ ተጠግታ አይን አይኔን ማየቱን ቀጠለች ። የሆነ ነገር ልነግራት እፈልጋለሁ ። ግን ይተናነቀኛል ። አፌ ለመናገር ሲጨናነቅ አይኖቼ አውቀውበት ከንፈሯ ላይ ጣሉኝ ። ያ የማይፋታኝ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ፊቴ ላይ ድቅን ሲል ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አዋሀድኩት ። መቼም ልቀቁኝ የማይል ጣፋጭና ስስ ከንፈር ።

"ሳማት ሳማት አለኝና ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣
ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር...

ይቀጥላል...

.
.
©fictional27

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ጊዜ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

16 Jun, 16:54


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
መልካም ጊዜ
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን
❥❥________⚘_______❥❥

ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር

16 Jun, 16:54


😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 30

ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
.
.
.
ድሬዳዋ በሰላም ገብተ

​​ናል ። ህይወት "ከልደትህ ቀን ላይ አንድ ሰዓት ሰጥተኸኝ ለትንሽ ጊዜ እንኳን አብረኸኝ አትሆንም ...?" አለችኝ ወደ ጊቢ እንደምሄድ ስነግራት ። ያንን አሳዛኝ ፊቷን እያሳየችኝ ስትለምነኝ ጥያት የመሄድ ምንም አቅሙም አይኖረኝም ። የድሬ ከተማ መግቢያ ላይ ወደ ሚገኘው #CCECC ሆቴል አመራን ። የቻይናዊ ሰው ሆቴል ነው ። "ከዚህ በፊት እዚህ መጥተህ ታውቃለህ እንዴ ...?" አለችኝ አየመራዃት ወደ ውስጥ ስንገባ ። 'አዎ' ስላት "መቼም የቻይና ምግብ አምሮህ እንዳልመጣህ ተስፋ አለኝ" አለችኝ እያሾፈችብኝ ። 'አይደለም ፤ ፊልም ለመስራት ነው የመጣሁት' አልኳት ። "የድሬ ልጅ ነች የከዚራ ፤ ስለ ውበቷ ስንቱን ላውራ የሚል ፊልም መሆን አለበት" አለችኝ በድጋሜ እየቀለደችብኝ ። 'ርዕሱን ለጊዜው አላውቅም' ስላት "እንዴዬ ፡ አንተ የምርህን ነው እንዴ አለችኝ" ኮስተር ስላልኩባት ። 'አዎ የምሬን ነው ። እንደውም አምስት ወር ሊሆነው #4 ቀን ይቀረዋል ። ታህሳስ #22 ነበር ። እዚሁ ሆቴል ውስጥ በአክተሮች ፣ ካሜራ ማኖች እና ሜክ አፕ አርቲስት ተከብቤ ነበር ። ቃልኪዳን ጥበቡ (የባባ ሚስት) ፣ ከዘመን ድራማ ተዋናዮቹ እነ አዩ ግርማ ፣ ሄኖክ ድንቁ ፣ እና የመሳሰሉት ነበሩ የፊልሙ ተዋናዮች ። ለካ ፊልም እንደዚህ ተቀርፆ ነው እኛ ጋር የሚደርሰው ። ብታይ የአምስት ደቂቃ ትዕይንት ለመቅረጽ ከሃያ ጊዜ በላይ ነው Cut ፣ action የተባለው ። ከስምንት ሰዓት እስከ #11 ሰዓት ቁጭ ብዬ ሲቀረፅ ያየሁት የ #10 ደቂቃ ትዕይንት አትሆንም ። ፊልሙ ድሬ ብቻ ሳይሆን ሀረርም እንደሚቀረፅ ነግረውኛል' አልኳት ። "መቼም የፊልሙ አክተር አንተ መሆን አለብህ" እያለች ትስቃለች ። 'በመጀመሪያ ደረጃ በዘመድ ነው famous የሆንከው እንዳትይኝ እንጂ ፤ የፊልሙ producer የዶርሜ ልጅ ጓደኛ በመሆኑ ነው እዛ የመሄድ እድል ያገኘሁት ። በመቀጠል ደግሞ እኔን የፈለጉኝ ፊልሙ እዚህ ሆቴል ውስጥ ሲቀረፅ በአክተሮቹ ጀርባ ከሆነች ልጅ ጋር ቁጭ ብዬ ሻይ እንድጠጣ ነው' ስላት ሳቋን በሀይል ለቀቀችውና አስተናጋጁ ሳንጠራው ደንግጦ መጣ ። ምሳ ሰዓት እስኪደርስ እስከዚያው ለስላሳ አምጣልን አልኩትና ተመልሶ ሄደ ። ማፌዟን አላቆመችም ። "እና ይሄን ሁሉ part ሸፍነህላቸው ስንት ብር ከፈሉክ ...?" አለችኝ ። 'እኔ ከጥበብ ገንዘብ አልቀበልም' ስላት "owk የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ስም መሆኑ ነው ጥበብ" አለችኝ ። ህይወት በመሆኗ ነው ዕድለኛ የሆነችው እንጂ ሌላ ሰው ፤ በተለይ ደግሞ ወንድ ቢሆን እንደዚህ የሚመልስልኝ እዚሁ ነበር ሰይፌው የምሄደው ። (ወንድ ልጅ አይኑር ያለው ማነው ...?😳) ። በኔ ላይ የመቀለድ ፣ የማሾፍና የማፌዝ መብት ያላት ብቸኛዋ ሴት እሷ ሆናለች ። እሷን የመቀየም ፣ የማኩረፍና በሷ ላይ የመናደድ አቅም የለኝም ። እራሷ ናት ያሳጣችኝ ። ስትስቅ ፣ ስትደሰት ፣ ሁሉን ነገር ረስታ ቀልቧን ሁሉ ስትጥልብኝ በህይወት በመኖሬ እደሰታለሁ ። ፈገግ ባለች ቁጥር የሷን ብቻ ሳይሆን የኔንም ዕድሜ በዕጥፍ ትጨምራለች ። በተለይ ደግሞ "የኔ ጌታ" እያለች ስታቆለጳጵሰኝ ሰማይና ምድሩን እኔው እራሴ በእጄ ጠፍጥፌ የሰራሁላት ነው የሚመስለኝ ። ስታዝን ፣ ስትጨነቅ ፣ ስታለቅስ ፣ ስታኮርፍ ፣ ህይወት ግልብጥብጥ ስትልባት ፣ በቃ ያኔ ነው በህይወት መኖሬን የምጠላው ። ከእሷ አይን የምትፈስ እያንዳንዷ የዕምባ ዘለላ ከእሳተ ገሞራ በላይ ውስጤን የማቃጠል ሀይል አላቸው ።

'ፊልም መስራት የልጅነት ህልሜ ነው ። ትዝ ይለኛል የ #1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለሁ ነበር የወሰወሰኝ ። ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ እያለሁና በትምህርት ቤትም ብዙ የመድረክ ድራማዎችን ሰርቼ ነበር ። አሁንም ድረስ የኔ የወደፊቱ ህልሜ በመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተመርቄ ስራ መስራት ይቅርታ ስራ ማፈላለግ አይደለም ። የፊልም አክተር መሆንና መሆን ብቻ ነው እቅዴ ። ከፊልም ውጪ plan B እራሱ የለኝም ። ፍላጎቴ ብሩና ዝናው አይደለም ። ፊልም መስራቱን ብቻ ነው የምፈልገው ። መንገድ ላይ የፊልም director ባገኝ እግሩ ላይ ወድቄ ከፈለክ በነፃ #10 ፊልም እሰራልሀለው ማለቴ አይቀርም' ስላት "እሺ የኛ shah rhuk Khan" አለችኝ ህይወት ትኩር ብላ ካዳመጠችኝ በዋላ ። በነገራችን ላይ የፊልም አፍቃሪ እንድሆን ያደረገኝ የህንዱ አክተር ሻህሩካን ነው ። የሱን ታሪክ በጣም ስለምወደው አጠር አርጌ ልንገርሽ አልኳትና ለትረካው ተሰናዳሁ ። "በልጅነቱ ጎበዝ ተማሪ ነበር ። ስፖርት በተለይ ደግሞ ኳስ መጫወት በጣም ይወዳል ። በልጅነቱ ትምህርት ቤት እያለ አንድ ቀን አስተማሪያቸው ወደ ፊት አወጣውና ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ ብሎ ጠየቀው ። እሱም አፉን ሞልቶ በኩራት የቦሊውድ ምርጥ አክተር እሆናለሁ አለው ። ክፍል ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች ሳቁበት ። አስተማሪውም የማይሆን ህልም እንደሆነና ሀሳቡን ቀይሮ ትምህርቱ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ነገረው ። ለሻህሩክ ግን ይህ አልተዋጠለትም ። ህልሙን እውን ለማድረግ የ #2ኛ ዲግሪ ትምህርቱን አቋረጠና ወደ ፊልም ጉዞ ጀመረ ። ነገር ግን በዛ ሰዓት ሁለት ነገሮች ፈተና ሆኑበት ። የመጀመሪያው ወላጆቹን በሞት ማጣቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታላቅ እህቱ የአይምሮ ህመምተኛ መሆኗ ነበር ። በዛ ምክንያት ቤተሰቦቹን የማስተዳደር ሀላፊነት እሱ ላይ ወደቀ ። ከድህነት ጋር ትግል ገጠመ ። ስራ ለመፈለግ ወደ ሙምባይ ከተማ ሄደ ። የቤት ኪራይ የሚከፍለውን አጥቶ ከቤት ተባሮ ሁለት ቀን ጎዳና ያደረበት ቀን ነበር ። የሰዎች ሱቅ ስር ያደረበት ቀን ደግሞ ስፍር ቁጥር የላቸውም ። ሆኖም ግን በዚሁ ችግር ውስጥ ሆኖ ተዋናዮች የማይደፍሩትን ትወናዎች ይሞክር ነበር ። የሆነ ቀን ለመወዳደር ሄዶ የፊልሙ director "አንተ አርቲስት የምትሆን ሰው አይደለህም" አለው ። እሱ ግን ምንም ሳይመስለው ትቶት ሄደ ። ግን ተስፋ አልቆረጠም ፤ ወደዋላም አልተመለሰም ። ሁልጊዜ ወደ ህልሙ በሚወስደው መንገድ ላይ ይረማመድ ነበር ። ያለምንም ክፍያ ሲኒማ በር ላይ ቆሞ የመግቢያ ticket ይሸጥ ነበር ። በወረደ ሂሳብ እንደ ካሜራና መብራት ያሉ የፊልም መሳሪያዎችን ተሸክሞ ከአርቲስቶች ዋላ ይሄድ ነበር ። ነገር ግን አንድ ቀን መጣ ። የሱ ቀን ። የለውጥ ቀን ። ትንሽ ብር ተከፍሎት አንድ ፊልም (#Deewana) እንዲሰራ ተነገረው ። ከዛው ላይ ተነሳ ፣ ቀጠለበት ፣ ድህነትን ማሸነፍ ጀመረ ፣ እውቅና ትከተለው ጀመር ፣ ህልሙም እውን ይሆን ጀመር ። ለአርት አትሆንም የተባለው ሰው ምርጥ አክተር መሆን ጀመረ ። ዛሬ እንደ ህንድ ብቻ ሳይሆን እንደ አለም በጣም ታዋቂና ዝነኛ አክተር ነው ። በድህነት የሰዎች ቤት ስር ያድር የነበረው ዛሬ ላይ ከአለማችን ሀብታም አክተሮች መሀል አንዱ ነው ። ከብዙ ተቋማት ብዙ ሽልማት ያገኘ ፣ ከራሱም ተርፎ ለህዝቡ የደረሰ ጀግና ነው" ። እናም የኔ ህይወት ሰው ትሆኛለሽ ፣ አትሆኝም ስላለሽ አይደለም ። እሆናለሁ ካልሽ የማትሆኝው የለም ። ዋናው ለምንፈልገው ነገር እስከመጨረሻው ድረስ መስዋዕትነት መክፈል ነው ። ትግልሽን አሪፍ ካደረግሽ ብትወድቂ እራሱ አንድ ቀን ከላይ መሆንሽ አይቀርም ።

ይቀጥላል....
.
.
.
©fictional27