አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡
ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።
ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡
ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡
ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡
እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን
በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡