ንባብ ለህይወት @nibabalehiwotdawitiv Channel on Telegram

ንባብ ለህይወት

@nibabalehiwotdawitiv


ከሁሉም ልብህን ይበልጥ ጠብቅ ህይወት ከሱ ትፈልቃለች እና!!!

ንባብ ለህይወት (Amharic)

ንባብ ለህይወት የትምህርት ቤት እና አዘጋጅ በመሆኑ እንዴት እንደሚቆይ አዲስ የተለያዩ ህይወት መረጃዎችን ስለሚወስድ ዳይስ እና ምርጥ መረጃዎችን እሳት እና ክፍል ይመልከቱ ያሉ ህይወት ከዝናሽ ወደ ችግር እንደምትገናኙ ከትግራይ ለሚወጣ በርካዶች ያቀረቡና ያደረጉ አጋማሽ ሬዲዮ መረጃዎችን በሞያ አቅርበን ማድረግ ከመሆኑ እንዴት እንደሚከበርሉ መረጃዎች ተዘንግብልን። የትምህርት ቤቱ ንባብ ለህይወት የዝናሽ ወደ ችግር ማወጃለል ይሆናል!

ንባብ ለህይወት

26 Aug, 05:56


"የኔ ችግር ተራራው ሳይሆን ጫማየ ውስጥ ያለችው ጠጠር ናት።"መሀመድ አሊ

ንባብ ለህይወት

23 Aug, 15:30


የkobe bryant አባባሎች
+
1. “ ከሰነፍ ሰው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም፡፡አንድ አይነት ቋንቋ አናወራም፡፡ሰነፍ ከሆንክ አልረዳህም፡፡ልረዳህም አልፈልግም፡፡ ”– kobe Bryant

+

2. “ጫናን ተግዳሮትንና አሉታዊ ነገሮችን ሁሉ የምወስዳቸው  ሊያነሱኝ  እንደ መጡ መልካም አጋጣሚ አድርጌ ነው፡፡
”– kobe Bryant

+

3. “ማረፍ መሃል  ሳይሆን መጨረሻ ላይ ነው፡፡”– kobe Bryant

+

4. “በራስህ ተማመን ሌላ ሰው ላንተ ባራሱ ሊተማመን አይችልም፡፡”– kobe Bryant

+

5. “ ምን ያህል በማሸነፍ ሱስ እንደተጠመድኩኝ ሰዎች አይረዱም፡፡ ”– kobe Bryant

+

6.  “ ቀጣዩ ማይክል ጆርዳን የመሆን እቅድ የለኝም፡፡እኔ መሆን የምፈልገው ኮቢ ብርያንትን ብቻ ነው፡፡ ”– kobe Bryant

+

7.  “ውድቀትን የምትፈራ ከሆነ አሁን የመውደቅ እድልህ ከፍ ያለ ነው፡፡”– kobe Bryant

+

8. “ እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር መሞከር እና ሰዎችን በማነቃቃት በመረጡት የስራ መስክ ታላቅ እንዲሆኑ መደገፍ ነው፡፡ ”– kobe Bryant

+

9. “ተስፋ ስትቆርጥ ሌላ ሰው እንዲያሸንፍ እየፈቀድክለት ነው፡፡ ”– kobe Bryant

+

10. “ዋናው የቡድንህ አባላት የምትጥረው ለእነሱ እንደሆነና እነሱ ስኬታማ እንዲሆኑ እንደምትፈልግ ማወቃቸው ነው፡፡”– kobe Bryant

+

11. “ የምችለውን ሁሉ ቆንጆ አድርጌ ከውኛለሁ፡፡ከዚህ በኋላ ያለውን መንገድ ደግሞ እግዚአብሔር ይመራኛል፡፡በዚህም ከልክ በላይ ደስተኛ ነኝ፡፡ ”– kobe Bryant

ንባብ ለህይወት

22 Aug, 13:36


እውነተኛውን ተከተል !

ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር ብቻ ይምራህ አለም ላይ ብዙ ነገር ሰምተሀል አይተሀል ከዚህም በኋላ ገና በጣም ብዙ ነገሮችን ታያለህ ነገር ግን ሁሉም አይጠቅሙህም ዛሬህን የሚገነባልህ ነገህንም የሚያራምድህ መልካምና ትክክለኛ የሆነውን የፈጣሪ መንገድ እየተከተሉ ማደግ ብቻ ነው !

ንባብ ለህይወት

16 Aug, 07:33


ተማር !

ለመማር መቼም ጊዜ አይረፍድም ነገሮች ያልተሳኩልን እድለቢስ ስለሆንን ሳይሆን ያላወቅነው እና ያልገባን የሆነ ነገር ስላለ ነው ቢገባን ያሰብነውን ነገር ማሳካት በጣም ቀላል ነገር ይሆንልን ነበር እናም በህይወትህ ዘመን በሙሉ ተማሪ ሁን !

ንባብ ለህይወት

14 Aug, 04:25


ብትዘገይም አድርገው !💪

አንዲት እናት ለረጅም ግዜ ያላየችው ልጇ እንደሚመጣ ቢነግራት እና በነገራት ሰዓት በጉጉት እየጠበቀችው አንድ አጋጣሚ ገጥሞት ለረጅም ሰዓት ቢቆይ በር በሯን እያየች በስስት ምን ነካብኝ ብላ ስትጠብቅ ትቆያለች ታድያ ይሄ ልጅ ረፍዷል እና ቀረው ቢላት የእናት ወገብ ቁርጥ አይልም 😔

የፈለገ ቢዘገይ ነገር ግን ከመጣ ሁሉን ረስታ የልጇን ፍቅር እስከጥግ ታጣጥማለች ፤ እድሜዬ ሄደ ፣ በሰዓቴ አልሰራውም ምናምን እያልን እጃችንን ለማጣጠፍ የተዘጋጀን ሁሉ ለለውጥ የረፈደ ቀን የለም ፈፅሞ ካለማድረግ መዘግየት ይሻላል !

ንባብ ለህይወት

08 Aug, 20:23


ሙከራ ጀምር !

"ደፋር ማለት የማይፈራ አይደለም ግን ፍርሀቱን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ ነው" ይለናል ኔልሰን ማንዴላ። ምንም ነገር የሚያስፈራህ መሞከር እስክትጀምር ነው መለወጥ ከፈለክ ግን አሁኑኑ ጀምር!

ንባብ ለህይወት

08 Aug, 20:21


ትኩረት ለማግኘት !

ትኩረት አጥቻለው ምን ላድርግ?  የምንል ከሆነ ስለዛሬ ብቻ እናስብ፣ የቀን ውሎአችንን ለማሳመር እንሞክር። ለነገ ክፋቱ ይበቃዋል አይደል የሚለው ታላቁ መፅሀፍ? ስለዚህ ነገ የት እንደምደርስ አውቃለው እንጂ ስለ ነገ በመጨነቅ ዛሬዬን አላባክንም! ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም✌️

ንባብ ለህይወት

07 Aug, 03:31


ተመስገን 🙏

መንቃት በጣም ደስ ይላል ዛሬን ማየት አዲስ ቀን መመልከት አዲስ እድል ማግኘት ዛሬን የሰጠንን አምላካችንን እስኪ ከልብ እናመስግነው ! በቀናችን እንጠቀምበት የሚገባውን እናድርግ !

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 19:22


ደውሉን እናዳምጠው !🔔

ሁሉን ነገር በቀላሉ ስናልፍ የነበርን ሰዎች የሆነ ጊዜ ላይ የያዝነው የሚከብደን ማለፍ ዳገት የሚሆንብን እየታገልን እንኳን ማሸነፍ የሚከብደን ቦታ ይገጥመናል እንዴ ምንድነው እየሆነ ያለው የሚያስብል ነገር ይገጥመናል

ያኔ ቆም ብለን እናስብ መለወጥ ያለብን የሆነ መንገድ አለ እና ራሳችን ላይ የመስሪያ ጊዜያችን ነው ይሄን ደውል አንዘናጋበት ካልሆነ ጥሎን ይበራል !

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 07:58


በጊዜው ሁሉ ይሆናል እንኳን ሁሉ ይቅር እና የተወለድነው ራሱ እኮ በተፈቀደልን ጊዜ ነው ታድያ አሁን እየፈለግነው ያለውም ነገር ጊዜው ሲደርስ ይገኛል !
+
   ስለዚህ አሁን ጊዜህ በሰጠህ ነገር በደንብ ተጠቀምበት 🤗

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 07:53


ሰውነትህ ላይ ለውጥ የሚያመጣልህ የምትችለው አስር ፑሽ አፕ ሳይሆን የማትችለው አስራ አንደኛ ፑሽ አፕ ነው ፣ ህይወት ላይም ለውጥ ማምጣት ከፈለግህ ሁሌም ከምትችለው እለፍ !

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 02:21


የእግዚአብሔር ጥበቃ !

ትላንትና ማታ ቤተክርስትያን ቁጭ ብለን አባትና ልጅ አጠገባችን መጥተዉ ገና ቁጭ እንዳሉ ልጅ አባቷ እቅፍ ዉስጥ ሆና “አባዬ ወክ እንዉጣ” እያለች ታስቸግራለች

አባት ማስቸገሯን መቀጠሏ ስለረበሸዉ እዛዉ አካባቢ እንድትንቀሳቀስ ይለቃታል ልጅ ገና ከመለቀቋ ፊት ለፊቷ ወዳገኘችው መንገድ ሩጫዋን ቀጠለች

ይሄንን ያየ አባት ልጁ ሳታየዉ ከኃላዋ ይከተላት ጀመረ  እንዳትወድቅበት ሊይዛት ፣ እንዳትጠፋ ሊጠብቃት ፣ ፍላጐቷን ሳይነፍጋት እንድትራመድ ፈቅዶ እያደረግኩልሽ ነዉ ሳይል በሚችለዉ ሁሉ አለላት

በጣም ርቃ ባይደርስባት እንኳን ፊት ለፊቷ ያሉትን ሰዎች ያዙልኝ ይላል እንጂ ተስፋ ቆርጦ አይተዋትም

ታድያ የፈጠረን ለእኛ ሲል ራሱን መስዋዕት ያደረገልን  የሰማዩ አባታችን እማ እንዴት እየጠበቀን ይሆን ?

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 02:01


እውነትን ይበልጥ ስትረዳው ስቃይ ሚባል ነገር ከነአካቴው አያውቅህም(ዮቶር)

ንባብ ለህይወት

06 Aug, 01:53


መሰላሉን መውጣት ከመጀመርህ በፊት የመሰላሉ ጫፍ የምትፈልገው ቦታ ላይ መሆኑን እርግጠኛ ሁን (ፐርሺያ)

ንባብ ለህይወት

02 Jun, 21:20


ሰዎች የሚያከብሩህ በምትሰጣቸው ማንነትህ ልክ ነው ! ቃላቶችህ ማንንም አይሸውዱም ዛሬ ላይ በእነርሱ ብትከበር ነገ ተግባርህ መልሶ ሊጥልህ ይችላል !
+
ለሰዎች ከምትነግራቸው በላይ ስጣቸው ከልብህ ሁንላቸው አስብላቸው ያኔ ስጡኝ ሳትላቸው የሚገባህን ክብር የሚሰጡህ እነርሱ ናቸው ከምንም ነገር በላይ ግን መልካም ሁን !

ንባብ ለህይወት

21 May, 19:20


#አሁን_እንጀምር!

የጠፈር መንኩራኩር ወደ ጠፍር በሚያደረገው ጉዞ, ሙሉ ጉዞውን ለማድረግ ከሚፈጀው ነዳጅ ይልቅ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ደቂቃዎች ውስጥ የሚፈጀው ነዳጅ ይበልጣል።

መንኩራኩሩ ለመነሳትና የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ጉዞዎች ለማድረግ ከፍተኛ ሀይል ይወስድበታል።

በእኛ ህይወት ውስጥም መጀመር ከባዱ ነገር ነው። ብዙ ጉልበት ይጠይቃል። አንዴ ከጀመርን በኋላ ግን ነገሮች እየቀለሉ ይመጣሉ፤ ከዚያም ማስቀጠሉ ብዙ አስቸጋሪ አይሆንም።

ንባብ ለህይወት

16 Apr, 11:51


" ከልባችን አጥብቀን የፈለግነውን ነገር እንድናገኝ በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ ይመሳጠራሉ" ይለናል ፖውሎ ኮሊዮ
+
ብቻ የእውነት ፈልግና ከልብህ ሞክር ፈጣሪ የሚያመቻቹልንን ሁሉ እየቀደመ ያዘጋጅልናል🙏

ንባብ ለህይወት

16 Apr, 11:49


እምቢ ማለት የለውን ዋጋ በመንፈሳዊ እና በአለማዊ እውቀት ያለውን ቦታ እናያለን እምቢ ማለት ለመንፈሳዊያንም ይሁን ለአለማዊያ የመውደቅም የመነሳትም ምክንያት ነው። በመንፈሳዊው ስናይ ሄዋን በእባብ ተመስሎ የመጣውን ሳይጣን "እንቢ"ብትለው ኖሮ የሰው ልጅ ሁሉ ወደ ምድረ ባልወረደ ነበር።ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ እያለ ሊፈተነውን የመጣን ሳይጣን የመለሰው እንቢ በማለት ነበር ድንጋዩን ዳቦ አላረግም.ላንተ አልሰግድም.ከመቅደስ ላይ አልዘልም በማለት ነበር የመለሰለት።በአለማዊም አንድ ነገር ድደረግ ስንጀምር ሌላ ነገር ድደረግ ያምረናል ያኔ ንነቢ ማለት ካልቻልን ከሁለት ያጣን ሁነን እንቀራለን ጓደኞቾቻን ወደአለለሆልታ ሲወሲወስዱን እንቢ ማለት ካልቻልን ህይወትቻን ይበላሻል።ለልጆቻችን ልናሰጣቸው የምንችለውም ውዱ ስጦታ እንቢ ማለትን ነው።አድርጉልን የሚሉትን አላስፈላጊ ነገሮች "እምቢ" በማለት ስንከለክላቸው ነው የዛሬ የወላጆች አስፈላጊ እምቢታ የነገ የልጆች የፈተና ጊዜ መልስ ይሆናል። ዛሬ ወላጅ ሁሉን እሽ እያለ ካሳደገ ነገ ልጆች ወንጀልና ክፋትን እንቢ የሚሉበት አቅም ያጣሉ።ለምን? ከልጅነት ስላልተማረ።

ንባብ ለህይወት

13 Jan, 04:42


#8ቱ_ወርቃማ_ምክሮች
ከ #የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ

🥇ችግሩ ችግር አለመሆኑን ተገንዘብ፤ ችግሩ ስለ ችግሩ ከመጠን በላይ ማሰብህ የፈጠረው ነው፡፡

🥇አስታውስ፤ ስለቻልክ ብቻ ማድረግ ይገባሃል ማለት አይደለም፡፡ ነገሩ ቀላል ነው ማለት ጠቃሚ ነው ወይም ጊዜህ ይገባዋል ማለትም አይደለም፡፡ በሕይወትህ ቀላል የሆነውን ሳይሆን፣ ትክክል የሆነውን አድርግ፡፡

🥇በባዶ ድካም እና ዋጋ በሚያወጣ ድካም መሀል ያለውን ትልቅ ልዩነት እወቅ፡፡ ሕይወት በጣም አጭር ናት፡፡ አብዝተህ በምትፈልገው ስራ ወይም እንቅስቃሴ ላይ ብቻ ጊዜህን፣ ገንዘብህንና ጉልበትህን አፍስስ፡፡

🥇ስትሳሳት ስህተትህን አምነህ በመቀበል ከዚህ ቀደሙ በበለጠ አሁን የመብሰልህን ሐቅ ተቀበል፡፡

🥇“እሺ ማለትህ” ብርቅ መሆን ይጀመር ዘንድ “እምቢ” እና “አይሆንም” ማለትን ልመድ፡፡

🥇ያለ ምንም በቂ ምክንያት ስለሚጠሉህ ጥቂት ሰዎች ለመጨነቅ ጊዜ እንዳይኖርህ የሚወዱህን ሰዎች በመውደድ ስራ ራስህን ጥመድ፡፡

🥇ፍላጎት አሳዳሪ ከመሆን ይልቅ ፍላጎት የሚያድርበት ሰው መሆን ላይ ይበልጥ አተኩር፡፡

🥇ምን ያህል ሀብታም እንደሆንክ፣ ቤተሰቦችህና ጓደኞችህ ውድ እንደሆኑ፣ ጊዜህ ወርቅ መሆኑን እና ጤናህም እውነተኛ ሀብትህ ስለመሆኑ አስብና አመስግን፡፡

#የስኬት_አቡጊዳ_መጽሐፍ

3,145

subscribers

72

photos

0

videos