ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official) @zehabeshaofficial Channel on Telegram

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

@zehabeshaofficial


#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
ጥያቄ፣ጥቆማ፣ማስታወቂያ ለማሰራት በዚ አድርሱን
👉 @Zehabesha_offical_Bot
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official) (Amharic)

በዚህ ታሪክ የተሰጠው የዕለቱ ዜና ማህበር ተብሏል። ዘ-ሀበሻ ዘርፍ ለኢትዮጲያና ለአዲስ መንግሥት ሀላፊና ታሪኩ ምስላት ነው። ወንድማማችንንና ሴቶችን እንዲያሳድዳል፣ በተጨማሪ ታሪኩን እና የአያት ሰፊ አገልግሎትን ለማቅረብ ጥያቄዎችና ጥቆማዎችን በፈለጋለት። የጎንደርንና የሕዝብን ውስጥ በመከላከል በብዛት ያደርጋል። በዚህ ታሪክ የሚድያ ተቋም ለማፍረስ የለመዳኖችን በአሰቃቂ መረጃዎች የወቅታዊ ውድ የሚሰጥ እንዲሆን መፍታት እና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎችን በሚፈልጉ ተመልከቱ። ለበጀራ የቱም ያለውን ዝግጅት እና ስለ ዘርፍ ተወዳድሩ።

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

25 Jun, 07:47


አቶ ይርጋ ሲሳይ አቶ ግርማ የሺጥላን በመተካት የአማራ ክልል ብልፅግና ጋርቲ ሀላፊ ሆነው ሊሾሙ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል። ለመሆኑ አቶ ሲሳይ ማን ናቸው? በዕለቱ የዘ-ሐበሻ ዜና ላይ አጠር ያለ ዝርዝር አለ።

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

24 Jun, 15:54


በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ እገታ ግድያ ግፍና ሰቆቃ ገደፉን አልፏል!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እለት ከእለት እየጨመረ የመጣው የንጹሐን ዜጎች መፈናቀል፣ እገታ፣ አፈና እና ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ያስጨንቀዋል፡፡ በተለይ እራሱን "የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት" እያለ የሚጠራው ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እና እንግልት ቀን በቀን እየተባባሰ መጥቷል፡፡

የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በሰላም በድርድር እና በውይይት ለመፍታት መሞከር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ላይ ግርታ ባይኖርም ለሰላም ነው እየተባለ ንጹሐን ዜጎች ላይ በጠራራ ጸሐይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ አፈና፣ ግድያ፣ ግፍና ሰቆቃ ሊታገሱት ይገባል ማለት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡

በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. የተፈረመውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ባወጣነው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች ላይም ለሰላም ውይይትና ድርድር በር አንዲከፈት አሳስበን የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልል የነበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ እንደፈቱ ተዘግቧል፡፡ መንግሥትም የሰላም በሩን ከፍቶ በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ኦነግ ሸኔ ከሚለው አሸባሪ ቡድን ጋር ታንዛኒያ ላይ ሰላማዊ ውይይት እንደጀመረ ሲያሳወቅ ተስፋ አድረገን የነበረ ቢሆንም ከድርድሩ በኃላ የሽብር ቡድኑ ጥፋት እየባሰበት ሲመጣ እንጂ ሲቀንስ ወይም ጨርሶ ሲጠፋ አላስተዋልንም፡፡ ይህም ንጹሐን ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ለአፈና እና ግድያ እየዳረጋቸው መደበኛ እለታዊ ሕይወታቸውን ተረጋግተው እንዳያከናውኑ እያደረጋቸው ነው፡፡

በመንግሥት በኩል የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ቡድኑን ጨርሶ ለማጥፋት እንዳልተቻለ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ፤ የሸኔ የሽብር ቡድንን አስቸጋሪ አወቃቀር በመጥቀስ እርምጃ ለመውሰድም ኾነ ለመደራደር የሚመሩት መንግሥት መቸገሩን ሲገልፁ ሰንብተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የሽብር ቡድኑ አባል ነን የሚሉ ታጣቂዎች በወለጋ ሁለት ዞኖች፣ በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ በሱሉልታ ወረዳ ቦቁ ጎልባ፤ ኤካ ጋጆና፤ ቦቁ ሁሩታ እና ሞዬ ጋጆ በሚባሉ ቀበሌዎች፤ በዝዋይ፣ መቂ፣ ሰዴን ሶዶ ወረዳ፣ የአዳ ባርጋ ወረዳ፣ ኩዩ ወረዳ፣ ገርበ ጉራቻ፣ ዋጫሌ ወረዳ፣ በአዳማ፣ በመተሀራ፣ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ በአርሲ ዞን፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ንጿሃን ዜጎችን እያገተ እና እየገደለ ፣ የትራንስፖርት እና እቃ ማጓጓዣ መኪና ሹፌሮችን እያፈነ እና በርካታ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ተግባራት እየፈጸመ እንዳሻው እየተንቀሳቀሰ የዜጎችን ህልውና እየተፈታተነ፣ ሀገራችንንም የምድር ሲኦል እያደረገ ነው፡፡ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ጭምር የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ፤ ኢሞራላዊ በኾነ መንገድ የሃይማኖት ሥፍራዎችን ሳይቀር እያዋረደ ነው።

ይህንን የሚያክል የሀገር ህልውና ችግር በየእለቱ እንደተራ ዜና እየሰሙ ማለፍ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የሚመለከታችሁ የመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች ልብ ልትሉት ይገባል፡፡ በምንም መልኩ የዜጎች በሕይወት የመኖር ዋስትና በመንደር ሽፍቶች ሲገፈፍ በቸልታ ሊታለፍ አይችልም፡፡

መንግሥት የሚጠየቀውን መስዋዕትነት ኹሉ ከፍሎ የዜጎችን ደኅንነት ካላስጠበቀ፤ አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም ሥፍራ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ተንቀሳቅሶ መሥራት፣ ያለሰቀቀን መኖር እና የደኅንነቱ መጠበቅ እንደ ዳገት ሊከብደው አይገባም፡፡

በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የመንግሥት በጣም ትንሽ የሚባለው ኃላፊነት የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህንን መሠረታዊ መንግሥታዊ ግዴታ አለመወጣት የአቅም ማጣት ወይም የግዴለሽነት ችግር ነው፡፡ መንግሥት ያለበትን ሁኔታ በግልጽ አሳውቆ፤ ሕዝብን በማስተባበር ዘመቻ በማካሄድ የሽብር ቡድኑን አደብ ማስገዛት ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን አለማድረግ ግን የቸልተኝነት ወይም የግድያው ተባባሪነትን ማሳያ ከመኾን ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ እዚህ ጋር መረሳት የሌለበት ዋና ጉዳይ ግን መሰል አይነት በደሎች የሚፈጥሩት ብሶት ዜጎች በራሳቸው ተደራጅተው ሰላምና እና ደህንነታቸውን ወደ ማስጠበቅ ይገቡና ወደ አላስፈላጊ ትርምስ ውስጥ ሊያስገባን እንደሚችል ነው፡፡ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ነገ ዛሬ ሳይሉ አፋጣኝና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚኖርበት መንግስትን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ምንም እኳን ላለፉት ጥቂት ዓመታት መንግሥት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሽብር ድርጅቶች እንዲሁም በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሴራ ተጨባጭ የሰላም እና ደኅንነት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ብንገነዘብም፤ ባለንበት ወቅት በራሱ አንደበትና በመገናኛ ብዙኀን እንደምንመለከተው መንግስት ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ማደራጀቱን እና የማያዳግም የሰላም ማስከበር ሥራ እያከናወነ መኾኑን እየገለጸ ስለኾነ፤ የሸኔ የሽብር ቡድን እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እንዳሻው መፈንጨት ምንም አይነት ምክንያት ሊቀርብበት የማይችል ሙሉ በሙሉ የመንግሥት የራሱ ድክመት መሆኑን ሊያምን ይገባል፡፡

በሕዝብ ይሁንታ የመንግስት መንበር ይዣለሁ ብሎ የሚያምን ኃይል ከመንግሥት ኃላፊነት ቀዳሚ የሆነውን መተላለፊያ ኮሪደሮች ማስከበር አለመቻል ሰበብ እንጂ ምክንያት ሊገኝለት አይችልም። እንዲህ አይነት አንገብጋቢ እና ቅድሚያ ሊሠጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ቢኖሩም አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ባልሆኑ ችግሮች ላይ ትኩረት መሥጠቱ ዜጎችን ለከፍተኛ ጥርጣሬ ዳርጓል። በመኾኑም፤ ይህንን ሀገራዊ የኅልውና አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን አስቸኳይ እና ዘላቂ እርምጃዎች እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

1ኛ/ የፌደራል መንግሥት በየጊዜው የጥፋት ተልዕኮውን እያሰፋና የራሱን ኃይል ለማግዘፍ የሚፍጨረጨረውን ኦነግ ሸኔን አደብ ለማስያዝና ዜጎችን ከሰቆቃ ለመታደግ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለህዝብ በይፋ እንዲያሳውቅ!

2ኛ/ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ እንደገለጽነው በራሱ ብልጽግና መንግሥት ውስጥ ተሰግስገው ለአሸባሪው ቡድን ሚስጥራዊ ድጋፍ በማድረግ የህዝብን ሰቆቃ የሚያባብሱና የቡድኑን እኩይ ተግባር በቸልታ የሚመለከቱ በተዋረድ ያሉ አካላትን ቁርጠኛ ሆኖ በመታገል ምንጩን እንዲያደርቅ!

3ኛ/ አሸባሪው ቡድን በዚህ ወቅት አፋፍሞ በየአቅጣጫው እየፈጸመ ያለውን መርህ አልባ እንቅስቃሴ ከወዲሁ እንዲሽመደመድ ካላደረገና ትጥቅ በፍጥነት ማስፈታት ካልቻለ የተጀመረውን ድርድር ማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንበት አጥብቀን መግለጽ እንሻለን።

በመጨረሻም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በአሸባሪው ሸኔ ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙትም ኾነ ከዚህ በኋላ ለሚፈጸም ግድያ፣ መፈናቀል፣ እገታ፣ ውድመት እና ሰቆቃ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በህሊና፣ በሕግ፣ በሕዝብ እና በታሪክ ተጠያቂ እንደሚኾኑ ሊያውቁት ይገባል፡፡

የኢትዮጵ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
ሰኔ 17/2015 ዓ.ም.

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

24 Jun, 13:34


በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ገደብ ከተጣለ ወራት ተቆጥሯል።

ይህን ሁሉ ጊዜ ማን ? ለምን ገደብ እንደተጣለ ? መቼ ገደቡ እንደሚነሳ ፤ የትኛውም የመንግሥት አካል ይፋዊ ማብራሪያ ለህዝብ አልሰጠም።

ይህን ገደብ ለማለፍ ሰዎች #VPN እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

ትላንት በህ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የኢትዮ ቴሌኮምን የ2015 ዓ/ም የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት በዚህ ገደብ ጉዳይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር።

ከምክር ቤት አባል የተጠየቀ ጥያቄ ፦

" ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን መሰረት ተደርጎ አንዳንዴ የአጠቃቀም ገደብ ይጣላል። በተለይ የዳታ አጠቃቀም ገደቦች ይጥላሉ።

ባለፈው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን መሰረት በማድረግ ገደብ ተጥሎ ነበር ከዛ አንፃር አሁን ያለው ሁኔታ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን የሚጠይቅ penetrate አድርገን እንዳንገባ የሚያደርግ ገደብ አለ።

ይሄ እስካሁን አልተለቀቀም፤ አንደኛ ይህ የግለሰቦችን የዳታ አጠቃቀም ላይ ገደብ እየጣለ ስለሆነ ፤ ሁለተኛ የሌሎች ሀራትን permission የሚጠይቅ ስለሆነ ይሄ ለምድነው እስካሁን ያልታረመው ?

ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አጠቃቀም ጀምሯል። ጥሩ ስራ ተጀምሯል፤ ቁጠባ፣ ከነዳጅ ጋር የተያያዘውም በጣም ውጤታማ ናቸው ፤ ግን እራሱ የተደረገው ገደብ ቴሌብር active እንዳይሆን እየከለከለው ነው። በተፈለገው direction እንዳይገባ እንዳይወጣ እያደረገው ነው ምክንያቱም ዳታ Permission ይጠይቅና ወደዛ ሲገበብ block እየተደረገ ያለበት ሁኔታ አለ እናተም ታውቃላችሁ ይሄን ችግር ለመቅረፍ ለምንድነው የማይሰራው ?

አሁንም ቢሆን ችግር አለ ወይ ? የምናውቀው ነገር ካለ በጋር መጋራት አለብን። "

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ምላሽ ፦

" ከVPN ጋር ተያይዞ የተነሳው ትክልል ነው።

በደንበኞቻችን ላይ እየፈጠረ ያለው ጥሩ ያልሆነ ተሞክሮ ነው።

ሁላችሁም እንደምትገነዘቡት ይሄ የኢትዮ ቴሌኮም Mandate አይደለም።

የሚመላከተው የመንግሥት አካል ከVPN ውጭ ኢንተርኔት access እንዲደረግ ፍቃድ ሲሰጠን ማስተካከያ እናደርጋለን።

የደንበኞቻችንን የኢንተርኔት አጠቃቀም ተሞክሮ ላይ ችግር እንደፈጠረ እኛም ተረድተናል።

በተለይ ጥሩ ማስፋፊያ እያደረግን የተሻለ ኔትዎርክ አጠቃቀም እንዲኖራቸው የ ' service experience ' የምንለው እንዲኖራቸው ነው የምንፈልገው።

በዚህ ምክንያት ቅሬታ እንዲኖራቸው አንፈልግም።

ከነዳጅ ግብይት እንዲሁም ሌሎችም ግብይቶች automate ከማድረግ አንፃር ቴሌ ብርን በሰፊው እየተጠቀምን ነው ለሱም እንቅፋት ይሆናል የተባለው ትክክል ነው።

ይሄን በሂደት የተዘጋበት / ይኽን እርምጃ የወሰደው የመንግሥት አካል ምክንያት አለው እንዲከፈት እና የተሻለ አገልግሎት ደንበኞቻችን እንዲያገኙ በእኛ በኩል አስፈላጊውን ስራ እንሰራለን። ግን ይህ mandate የኛ አይደለም። "

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

24 Jun, 08:27


የቅጥረኛው ቫግነር ቡድን መሥራችና መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን የሩሲያን መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች “ልክ አስገባለሁ” ሲል ዛተ።

የቡድኑ መሪ ይህን ለማድረግ ‘የትኛውንም ርቀት እንሄዳለን’ ብሏል።

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

24 Jun, 02:37


የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሌላ አገር ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ከሽብርተኝነት እስከ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ማስፈጸሚያ ሊውል የሚችለውን ድርጊት ማስቆም ያልተቻለበትን ምክንያት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ ተቋማትን ጠይቋል።
የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ችግሩ መኖሩን እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

በኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የጉዞ ሰነዶች አሰጣጥ ዳይሬክተር ቡድን መሪ ዓለምጸሀይ አንባቸው÷ ከአገር የሚወጡ የኢትዮጵያን ፓስፖርት በህገ ወጥ መንገድ የሚይዙ የውጭ ዜጎች በርካቶች ስለመሆናቸውም ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ለአገር ትልቅ አደጋ እንዳለው ነው የሚጠቅሱት። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የባህል፣ ቋንቋ እና ማንነት መጋራት ያላት በመሆኑ ለማጥራት ሂደቱ ትልቅ ፈተና እንደሆነበት አንሰተዋል። ከዚህ በላይ በተቋማት ውስጥ ያለው ብልሹ አሰራር ለችግሩ እድል ሰጪ ሆኖ መገኘቱን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ ዋና ዳሬክተር ዮናስ አለማሁ በበኩላቸው የሀሰተኛ መረጃ ፈተና እና የፈፃሚዎች ክፍተት ችግሩን እንዳባባሰው ይናገራሉ።
የሲቪል ምዝገባ የነዋሪዎች አገልግሎት እና የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጉዳዩን የፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አንድ መቶ ሃያ አምስት ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ደግሞ አንድ መቶ ሀምሳ ሶስት ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ማድረጉን ጠቁሟል።
ከዚህ ወስጥም ሀምሳ ዘጠኘ የሚሆኑት የተቋሙ ሰራተኞች መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

23 Jun, 17:37


Good News : ሀገራችን በአፍሪካ ትልቁን የትራክተር ፋብሪካ እንዲኖራትና በሂደትም ሙሉ ለሙሉ ትራክተርና ኮምባይን ሐርቨስተሮችን ለማምረት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበት ስምምነት በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና በ YTO-CAMACO መካከል ተፈረመ።

አዲሱ ፋብሪካ በከፍል አውቶሜትድ የሆነ በመሆኑ በዓመት 10,000 ትራክተሮችን የማምረት አቅም ይኖረዋል። በዚህም የሀገራችንን የግብርና ሜካናይዜሽን ፍላጎት ከማሟላት አልፎ የግብርና ማሽኔሪዎችን ለአፍሪካ ገበያ የማቅረብ የሚያስችል ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን::

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

23 Jun, 14:35


"የሚያደናቅፍ አመራር ቦታውን መልቀቅ እንጂ ምክንያት መደርደር አያስፈልግም። መጥራት አለበት። ሕዝባችን የሚፈልገው ሰላምና ልማት ነው"

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ጋሻው አወቀ(ዶር)

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

23 Jun, 14:35


በአዲስ አባባ የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው ነዋሪዎች ቅሬታ የሚያቀርቡበት አሰራር ይፋ ሆነ

በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት አሰራር ይፋ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ የቤት ኪራይ መጨመር እንደማይችል መወሰኑ ይታወሳል::

በዚህ መሰረትም የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ነዋሪዎች ቅሬታቸውን በሚኖሩበት ወረዳ የመልካም አስተዳደርና አቤቱታ ስራ ክፍል እንዲሁም የወረዳ ስራ አስፈፃሚ ቢሮዎች በመገኘት ማቅረብ እንደሚችሉ መገለጹንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

23 Jun, 14:35


ኢራን 2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ፋታህ በሚል ሰየመችውን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ይፋ አደረገች፡፡

የእስላማዊ አብዮት ጠባቂዎች(IRGC) ከፍተኛ አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል አሚር-አሊ ሀጂዛዴህ፣ፋታህ የተሰኘችው የሚሳኤል ስሪት አሁን ካለው 1 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ከሚወነጨፈው ሚሳኤል ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ 600 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዞ ኢላማውን መምታት የሚችል ነው ብለዋል፡፡

የሀገሪቱን የመከላከያ ሃይል በማጠናከር ረገድ ታሪካዊ ስኬት ነው ብርጋዴል ጄኔራሉ ፋታህ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለኢራን ጦር ሃይሎች ለእይታ ቀርባ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ኢራን በቅርብ ጊዜ ወዲህ የራሷ ስሪት የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን እያስተዋወቀችና አለፍ ሲልም ሙከራ እያደረገች እንደምትገኝ የፕሬስ ቲቪ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

23 Jun, 14:32


የአማራ ህዝብ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ ስኬት ለሌሎች አካባቢዎች ምሳሌ ነው - አደም ፋራህ

የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

"ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለተኛ ምዕራፍ የመጀመሪያው ዙር ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፣የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው በይፋ የተጀመረው።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ጎሃ ቀበሌ
በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት አቶ አደም የመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው ህብረተሰቡ ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአማራ ህዝብ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ ልማት ለሌሎች አካባቢዎች ምሳሌ ነው ያሉት አቶ አደም ተግዳሮቶችን በማለፍ ከብልጽግን ከፍታ መድረስ እንደሚቻል ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው ህብረተሰቡ ያሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በየዓመቱ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል ከዘርፉ የፍራፍሬና መሰል ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን ለማግኘት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ይህንን ደን የመጠበቅ መልካም ባህል እንዲያጎለብት ማበረታታትና መደገፍ ይገባል ያሉት አቶ አደም፣ ደንን ሳያጠፉ ከዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለመሆን ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)
አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ ብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ አካል ነው መሆኑን ገልጸው ባለፋት አራት ዓመታት በተተከሉ ችግኞች የፅድቀት ምጣኔያቸው ማደጉንና የአፈር ለምነት መጨመሩን አመልክተዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ 25 ቢሊዬን ችግኞች በመላ አገሪቱ መተከላቸውን ያወሱት ርዕሰ መስተዳደሩ በሁለተኛው ምዕራፍ እንደ አገር 50 ቢሊዬን ችግኞች በህብረተሰቡ ተሳትፎ ይተከላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ፈተና ውስጥ መሆኗን ገልጸው ከዚህ አኳያ ሁላችንም ህዝቡን በማሳተፍ ለአረንጓዴ ልማት ስኬታማነት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል ።

የክልሉን ብሎም ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዘርፉን ከፍ ለማድረግ የአካባቢውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብትን ከሰው ኃይል አቅም ጋር በማስተሳሰር አልምቶ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መስራት ይገባል ነው ያሉት።

መረጃው የጽ/ቤቱ ነው

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና Zehabesha (official)

22 Jun, 09:17


በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ሚኒ ባስ መኪኖችን መገጣጠም ጀመረ።

ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ መለስተኛ አውቶቡስ እና የከተማ አውቶቡስ ተሽከርካሪዎችን የማምረት  አቅም አለው ።

ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ሚኒ ባስ  መኪኖችን ከደብረ ብርሃን በተጨማሪ ገላን በሚገኘው መገጣጠሚያው  መገጣጠም ጀምሯል።

በደብረ ብርሃን ከተማ በተገነባው ፋብሪካ በአሁኑ ሠዓት ከ250 በላይ ለሚደርሱ ወገኖች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል።