እንኳን ለወርሃዊው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።"
መዝ. ፴፫፥፲፯ /33፥17/
❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በ፲፫/13/ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ቅዱስ አባት ናቸው
❤ ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በታህሣሥ ፳፱/29/ ቀን ሲሆን ስማቸውም "ገብረ መንፈስ ቅዱስ" ተባለ
❤ ጻድቁ አባት ከ፭፻ /500/ ዓመት በላይ በዚህ ምድር ላይ የኖሩ ታላላቅ የቅድስና ስራዎችን የሰሩ ገዳማዊ ናቸው
❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከገዳማዊነታቸውም በዘለለ ከትግራይ እስከ ሸዋ ባለው የሀገራችን ክፍል እየተዘዋወሩ ወንጌልን የሰበኩ አባት ናቸው
❤ ጻድቁ አባታችን ሁለት ታላላቅ ገዳማትን መትከላቸውን ታሪካቸው ያስረዳል
➻ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና ምድረ ከብድ ገዳም ናቸው
❤ ጻድቁ አባታችን በተወለዱበት ቤት አልኖሩም በበረሃ ብቻቸውን ኖሩ እንጂ
❤ በበዓታቸው እየጾሙ እየጸለዩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ የኖሩት ጻድቁ አባታችን በኖሩባት ምድር በኢትዮጵያ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥተዋል
❤ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ዘመናቸው ሲፈፀም ጌታችን የተለያዩ ቃል ኪዳኖችን ከገባላቸው በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ
የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምልጃና በረከት አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ድንግል
#ተዋህዶ
#OrthodoxChurch
#ኢትዮጵያ
@ortodox_27