✍ በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
የመስጂድና መስጂድ የመስገድ ትሩፋቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ቤት በመስገድ ፣ በመቅራትና በሌሎችም ዒባዳዎች ፤ ቤታችንን የአምልኮ ስፍራ ማድረግ መዘንጋት የሌለብን ወሳኝ ነገር ነው ።
በተለይ ለሴት…
በአላህና በመጨረሻው ቀን አምና መልእክተኛዋን ለምትከተል ሙስሊም ሴት … በጥቅሉ የተሻለው መስገጃ ፤ ቤትዋ, ለዛውም ክፍሏ ነው ።
عَنْ عَمَّتِهِ أُمِّ حُمَيْدٍ - امْرَأَةِ أَبِي حُمَيْدٍ السَّاعِدِيِّ - أَنَّهَا جَاءَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَتْ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنِّي أُحِبُّ الصَّلَاةَ مَعَكَ. قَالَ : " قَدْ عَلِمْتُ أَنَّكِ تُحِبِّينَ الصَّلَاةَ مَعِي، وَصَلَاتُكِ فِي بَيْتِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي حُجْرَتِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي حُجْرَتِكِ خَيْرٌ مِنْ صَلَاتِكِ فِي دَارِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي دَارِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي مَسْجِدِ قَوْمِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي مَسْجِدِ قَوْمِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي مَسْجِدِي ". قَالَ : فَأَمَرَتْ، فَبُنِيَ لَهَا مَسْجِدٌ فِي أَقْصَى شَيْءٍ مِنْ بَيْتِهَا وَأَظْلَمِهِ، فَكَانَتْ تُصَلِّي فِيهِ، حَتَّى لَقِيَتِ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ.
ኢማም አሕመድ በሙስነዳቸው በዘገቡት ሐዲስ ላይ ኡሙ ሑመይድ የተባለች ሰሐቢያህ (ረዲየሏሁዐንሀ) ወደ ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጥታ "አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ከእርሶ ጋር (መስጂድ መጥቼ) መስገድ እወዳለሁ ።" አለቻቸው ። ረሱላችንም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲመልሱላት "በእርግጥ ከእኔ ጋር መስገድ እንደምትወጂ አውቃለሁ ። (ነገር ግን) በክልልሽ (የግል ክፍል ውስጥ ደበቅ ያለ ቦታ) የምትሰግጂው ሰላት ፤ በክፍልሽ ከምትሰግጂው የተሻለ ነው ፣ በክፍልሽ የምትሰግጂው ሰላት ፤ በቤትሽ ከምትሰግጂው የተሻለ ነው ፣ በቤትሽ የምትሰግጂው ደግሞ በሰፈርሽ መስጂድ ከምትሰግጂ ይሻልልሻል ፣ በሰፈርሽ መስጂድ የምትሰግጂው ደግሞ በእኔ መስጂድ ከምትሰግጂው ይበልጥልሻል ።" አሏት ። እርሷም… ከቤቷ ጥግ ፣ ድብቅና ጨለም ያለ ቦታ ላይ መስገጃ አሰርታ ፤ እስከለተሞትዋ ድረስ እዚያው ነበር የምትሰግደው ። (ረዲየሏሁ ዐንሀ)
ለወንድሳ? …
ወንድ ደግሞ ግዴታ ከሆኑና ከኢማም ጋር ከሚሰግዳቸው ሰላቶች ውጪ ያለውን ተጨማሪ ሱና ሰላቶች ፤ ቤቱ ቢሰግድ የተሻለ ነው ።
عَنْ زَيْدِ بْنِ ثَابِتٍ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ اتَّخَذَ حُجْرَةً ، قَالَ : حَسِبْتُ أَنَّهُ قَالَ : مِنْ حَصِيرٍ فِي رَمَضَانَ فَصَلَّى فِيهَا لَيَالِيَ، فَصَلَّى بِصَلَاتِهِ نَاسٌ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَلَمَّا عَلِمَ بِهِمْ جَعَلَ يَقْعُدُ، فَخَرَجَ إِلَيْهِمْ فَقَالَ : " قَدْ عَرَفْتُ الَّذِي رَأَيْتُ مِنْ صَنِيعِكُمْ، فَصَلُّوا أَيُّهَا النَّاسُ فِي بُيُوتِكُمْ ؛ فَإِنَّ أَفْضَلَ الصَّلَاةِ صَلَاةُ الْمَرْءِ فِي بَيْتِهِ إِلَّا الْمَكْتُوبَةَ
"የወንድ ልጅኮ በላጩ ሰላት ፤ እቤቱ የሚሰግደው ሰላት ነው ።" ቡኻሪ ዘግበውታል
እናም… ግዴታችንን መስጂድ ከሰገድን በኋላ ወደ ቤታችን የምንመለስ ከሆነ ፤ አዝካርና ዱዐ መስጂድ ጨርሰን ሱናዎቹን ቤት ብንሰግዳቸው የበለጠ ነው ። ነገር ግን ቤት መስገድ የማይቻልበትና ለኹሹዕ ምናምን የምንቸገርበት ሁኔታ ሲኖር ፤ መስጂድ መጨረሱ የተሻለ ነው ።
والله أعلم
ለማንኛውም ተቃረቡ ↴☘☘☘
https://t.me/yehussenmun