በግጥም እናውጋ @begitimenawga Channel on Telegram

በግጥም እናውጋ

@begitimenawga


ሰላም ቤተሰቦች እንደምን አላቹ?
እንካን ወደ እኛጋ በሰላም መጣቹ።
በቻናላችን ላይ ግጥምን ተጠቅመን፣
ከቶ ሳንነካ ብሄር ሀይማኖትን፣
ሁሉን የሰው ልጅ በእኩል እያየን፣
እውነት እውነታውን እናወጋለን።


ሀሳብ አስተያየት ምክርም ካላቹ፣
በ @BegitimEnawgaBot ታገኙናላቹ።

በግጥም እናውጋ (Amharic)

የትናንቱ ቤተሰብ መሆኑን እንወጋለን! ስለሆነ እናቴን ፡፡ በረግማን ሳሔሽን ስላላነፌ አንልለዋለን። ይህም ግጥም እናውጋ ቤተሰብ ነው፣ ለእኛ ሰላምን እንዲያመልጥ መጣቹ። ከሌላ በሰላም መኝታ እንደምን አላቹ፣ በቻናላችን ላይ ግጥምን ተጠቅመን፣ ከቶ ሳንነካ ብሄር ሀይማኖትን፣ ሁሉን የሰው ልጅ በእኩል እያየን፣ እውነት እውነታውን እናወጋለን። ፅሁፎቻው ማድረግ ለሁሉን ተስፋ እና በመጠቀም ምክንያቱ እውነቱን ታውቂውበታለን። አዝናኝ ትናንትን ከ @BegitimEnawgaBot ታገኙናላቹ።

በግጥም እናውጋ

27 Sep, 03:51


በዓሉን ለምታከብሩ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ!!!

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

11 Sep, 05:54


🌻 2017 🌻

ሰዓታት አለፉ 🌻 ቀናት ወራት ወልደው 🌻
🌻አመት ተቆጠረ

አሮጌው ተተካ🌻 እነሆ ዛሬ ላይ 🌻
🌻 አዲስ ተጀመረ

እንኳን አደረሰን🌻 እንኳን ለዚህ አበቃን🌻
🌻መልካም አዲስ አመት

የሰላም የደስታ🌻 የተድላ የፍቅር
🌻 ያርገው የበረከት


    🌻🌻መስከረም -1-2017ዓ.ም🌻🌻

🌻🌻🌻
@BegitimEnawga🌻🌻🌻
🌻🌻🌻
@BegitimEnawga 🌻🌻🌻

በግጥም እናውጋ

10 Sep, 21:00


🌻 🌻መልካም አዲስ አመት!!!!🌻 🌻

🌻🌻አዲሱ አመት የደስታ፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ ያሰብነው የሚሳካበት አመት ይሁንልን!!!🌻🌻

🌻🌻2017ዓ.ም🌻🌻

🌻🌻🌻
@BegitimEnawga🌻🌻🌻
🌻🌻🌻
@BegitimEnawga 🌻🌻🌻

በግጥም እናውጋ

19 Aug, 07:30


ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

🥖መልካም በዓል!!🥖

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

18 Aug, 09:33


ፈጣሪ አምላኬ ~ ይቅር በለኝ ዛሬ
         ህግህን ሳፈርሰው

አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም
        ፈርዳለው በዚህ ሰው።

የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን
        ገደቦች ላለፈ

ያንዲት ምስኪን ህፃን ~ ክብሯን በግፍ ገፎ
         ነፍሷን ለቀጠፈ

የእጁን እንዲያገኝ ~ ስቃይ እና ሞቱን
          ለሱ መመኘቴ

የጨቅላዋን ህመም ~ ማሰብ ቢያቅተኝ ነው
       ባይችል ነው አንጀቴ



የቆሰለ ውስጧን ~ የእናቲቱን እምባ
ሚያብሰው ሲጠፋ

ፍትህ እየተዛባ ~ ተበዳይ ሲበደል
ውስጣችን ቢከፋ

አቤቱ ፈጣሪ ~ አነባን ወዳንተ
አነባን ወደላይ

ፍርድህን አሳየን ~ ክፉዎች ቀጥተህ
በምድርና በሰማይ



#ፍትህ_ያለእድሜዋ_በግፍ_ለተነጠቀች_ነፍስ
#ፍትህ_ለሔቨን

@BegitimEnawga

በግጥም እናውጋ

16 Jun, 02:41


🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

🌙በዓሉን የደስታ፣ የሰላም እና የፍቅር ያድርግላችሁ!!🙏

             መልካም በዓል!!

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

09 Jun, 16:06


ድንቄም ገጣሚ

       ሳያዘጋጅ ብእር

       ሃሳብ ሳይደረድር

ስላሰኘው ብቻ ለመግጠም ሲሞክር

        አልሳካ ቢለው

በሰከነ መንፈስ ደግሞ ሳያስበው

የማይመስል ስንኝ ፅፎ እያሰፈረ

ካለበቂ እውቀት ለመግጠም እየጣረ

ቤት መታለው በሚል ቤት ማፍረስ ጀመረ::
:
:
ከሰማ ንገሩት
ቤት አታፍርስ በሉት::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

⌲ Share       ⌲ ሼር       ⌲ Share

     የመወያያ ግሩፕ👉 click_here

            ለተጨማሪ ግጥሞች👇👇
     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

12 May, 11:53


👆👆👆 አሪፍ ግጥም በአሪፍ አቀራረብ ተጋበዙልኝ::    
        
               በቃሉ ሹምዬ
                🎙 ያኔት
Editor: @begitimenawga


🤰መልካም የእናቶች ቀን

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

⌲ Share    ⌲ ሼር    ⌲ Share

     የመወያያ ግሩፕ👉 click_here

          ለተጨማሪ ግጥሞች👇👇
    👉JOIN: @BegitimEnawga 
    👉JOIN:
@BegitimEnawga
    

በግጥም እናውጋ

12 May, 06:33


🤰መልካም የእናቶች ቀን!!!

❇️ ለእናታቹ ያላቹን ስሜት comment ላይ እየገለፃቹ እለፉ።

             🙌 መልካም ቀን

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

05 May, 00:26


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉን የደስታ፣ የሰላም እና የፍቅር ያድርግላችሁ!!🙏

             መልካም በዓል!!

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

01 May, 04:33


🙌 ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ??

❇️ግጥሞች ስለቅ ማሳወቂያ(notification) እንዲደርሳችሁ እና እናንተም የምታዩት እይታ እንዲቆጠር የሚከተለውን ማድረጋችሁን አረጋግጡ።

ከላይ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች  MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት።

❇️ከታች ያለው UNMUTE  የሚል ከሆነ ደግሞ አንድ  ጊዜ በመጫን  MUTE የሚል መምጣቱን ያረጋግጡ።

❇️ይህን በማድረጋቹ ግጥም ስለቅ ማሳወቂያ ስለሚደርሳቹ በየጊዜው መከታተል ያስችላችኋል።
❇️ በተጨማሪም የሚለቀቁ ፖስቶችን ስታዩ እይታቹ ስለሚቆጠር ለቻናሉ እድገት እያገዛችሁም ይሆናል ማለት ነው።

            🙌 መልካም ጊዜ

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

29 Apr, 16:00


💎💎የከበረው ድንጋይ💎💎

ካምሳሎቹ መሀል በመሆን የበላይ

በዋጋው ተልቆ የከበረው ድንጋይ

ማግኘት በመቻሉ ከሰው ልዩ ቦታ

ለመቀመጥ በቅቷል ከንግሱ ከፍታ::
:
:
ሆኖም
:
:
የታለቅነትን  ትርጉሙን እረስቶ

ወርዶ ከተገኘ አቅጣጫውን ስቶ

መንገዱን ካረገ ከስህተት ጎዳና

ያገኘውን እምነት ካደረገው መና

ካልቀየረ በቀር የሳተውን መንገድ
          ጥፋቶቹን አምኖ

  ክብሩን ያጣውና  ባዶውን ይቀራል
          ድንጋይ ብቻ ሆኖ::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

⌲ Share       ⌲ ሼር       ⌲ Share

     የመወያያ ግሩፕ👉 click_here

            ለተጨማሪ ግጥሞች👇👇
     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

29 Apr, 09:00


▬▬▬▬▬▬▬▬📝📝▬▬▬▬▬▬▬▬

ቅድመ ግጥም ዳሰሳ

🙌 ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ለሁላችሁም ሰላምታዬ እና አክብሮቴ ባላቹበት ይድረሳቹ።

❇️ የዛሬ የምለቀው ግጥም ብዙም ማብራሪያ ባያስፈልገውም የተወሰነ ነገር ለማለት ያክል፤

❇️ ሰዎች ከሰዎች እምነት እና ክብርን አግኝተው የተለየ ከፍ ያለ ቦታ ሲሰጣቸው እነሱም በምላሹ ከከፍታ ላስቀመጧቸው ሰዎች ተገቢውን ክብር እና የተሰጣቸውን ቦታ የሚመጥን ተገቢ እና ጠቃሚ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

❇️ አንዳንዴ ሰዎች ከከፍታ ሲወጡ ሊወርዱ እንደማይችሉ የሚያምኑ በሚያስመስልባቸው መልኩ ብዙ ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ያደርጋሉ።

❇️ ሀሳቤን ሳጠቃልል ነገሮች እንዳሉ ሚፀኑት የተገነቡበት ነገር ጠንክሮ ከቀጠለ ነው። እናም ከፍታን  በሰዎች ክብር እና እምነት ያገኘ ሰው በከፍታው እንዲቀጥል የሰዎች እምነት እና ክብር በጥንካሬው መቀጠል አለበት ካልሆነ ግን የጊዜ ጉዳይ እንጂ ከከፍታው መውረዱ አይቀርም።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

❇️ዛሬ የለቀኩት ቅድመ ግጥም ዳሰሳ ዛሬ የምለቀውን ግጥም በተገቢው መንገድ ለመረዳት እንዲረዳቹ ብዬ ያዘጋጀሁት ነበር።

❇️ግጥሙን ወደ አመሻሽ አካባቢ እለቀዋለው አስከዛው ድረስ

              🙌 መልካም ቆይታ

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

28 Apr, 16:00


▣►▸የተገዙት ወርቆች◂◄▣

የዝምታ ሀይል ገብቶት ያገሬ ሰው
        ዋጋውን ተረድቶ

ወርቅ ነው ይሉታል ጥቅሙን ከጉዳቱ
         በጥበብ አስልቶ።
:
:
የቃላቱ   ትርጉም   ስሌቱ ሲዛባ
        አሁን በኛ ዘመን

ወርቅ የሆንን መስሎን እንዲያው እንደዘበት
          ተለጉመን ቀረን።
:
:
ዋጋ እንዲኖረው ጥቅም እንዲሰጠን
           ሚኖረን ዝምታ

መተግበር ግድ ይላል ባስፈላጊው ጊዜ
           በተገቢው ቦታ
:
:
ካለበለዚያማ

የኛ ዝምተኞች  በመጠን ቁጥራችን
        በሀገር ከበዛ

ለምን ይገርመናል ገዢ ቢበረክት
        ወርቆችን ሚገዛ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

⌲ Share       ⌲ ሼር       ⌲ Share

የመወያያ ግሩፕ👉 click_here

            ለተጨማሪ ግጥሞች👇👇
     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

28 Apr, 10:00


▬▬▬▬▬▬▬▬📝📝▬▬▬▬▬▬▬▬

ቅድመ ግጥም ዳሰሳ►➊◄

        ''ዝምታ ወርቅ ነው''

❇️ ዛሬ የምለቀው ግጥም ከላይ በገለፅኩት ተረትና ምሳሌ ላይ የተመሰረተ ነው።

❇️ ብዙ ማብራሪያ ባያስፈልገውም ተረትና ምሳሌው የዝምታን ሀያልነት በውድ ዋጋ ከሚገዛ እና ከሚሸጠው ወርቅ ጋ በማነፃፀር ይገልፀዋል።

❇️ ነገር ግን ዝምታ ወርቅ ሊሆን የሚችለው በተገቢ ጊዜና ቦታ ላይ ብቻ እንጂ ዝም ማለት በሌለብን ሰዓት ዝም ማለቱ ዋጋቢስ እና ትልቅ ጉዳት ያለው መሆኑ መረሳት የለበትም።

❇️ ብዙ በዝርዝር ባልገባም በሀገራችን በተደጋጋሚ የአብዛኞቻችን ተገቢ ባልሆነ ጊዜና ቦታ ዝምተኛ መሆን ያስከፈለንን ዋጋ ታሪክና ነባራዊው ሁኔታ ምስክር ነው።

❇️  ሀሳቤን ሳጠቃልል ዝምታን ከመምረጣችን በፊት ጥቅም እና ጉዳቱን እንለይ።

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

28 Apr, 10:00


▬▬▬▬▬▬▬▬📝📝▬▬▬▬▬▬▬▬

ቅድመ ግጥም ዳሰሳ►❷◄

        ''ገዢ እና መሪ''

❇️ አብዛኛዎቻቹ የሁለቱን ቃላት ልዩነት ብታቁም ጥቂት የማይባል ሰው ሁለቱን ቃላት እየቀያየረ ይጠቀማል። ዛሬ የሁለቱን ቃላት ትርጉም ባጭሩ እንመልከት።

❇️ ገዢዎች➲ ያላቸውን ስልጣን በመጠቀም ሰዎች በነገሮች እንዲያምኑ ወይንም ስራዎችን እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

  ▪️ስራዎች እንዲሰሩ በቀጥታ ትዕዛዝ ሰጥተው ያስፈፅማሉ።

  ▪️ከብዙ ታሪኮች በመነሳት በብዛት ገዢዎች በመጥፎ ተግባር ይታወቃሉ ነገር ግን ሁሌም ባይሆንም በአንዳንድ አጋጣሚዎች ገዢዎች ያስፈልጋሉ

❇️ መሪዎች➲ ያላቸውን የመናገር፣ የማሳየት እና የማስረዳት ችሎታ ተጠቅመው ሰዎችን ያሳምናሉ ወይንም የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

   ▪️ስራዎችን እየሰሩ በማሳየት ሌሎች ሰዎችም ስራውን እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

❇️ ከላይ ያለውን ምስል የገለፅኳቸውን በቀላሉ ለማጠቃለል ተጠቅሜበታለው።

በዚሁ አጋጣሚ ለሀገራችን መልካም መሪ እንዲመጣልን ምኞቴን ገልጬ ማለፍ ፈልጋለው።

እናንተ ከምታቁት የመሪ አንድ እና የገዢ አንድ ምሳሌ comment ላይ እየሰጣቹ እለፉ።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

❇️ዛሬ የለቀኳቸው ሁለት ቅድመ ግጥም ዳሰሳዎች ዛሬ የምለቀውን ግጥም በተገቢው መንገድ ለመረዳት እንዲረዳቹ ብዬ ያዘጋጀሁት ነበር።

❇️ግጥሙን ወደ አመሻሽ አካባቢ እለቀዋለው አስከዛው ድረስ

              🙌 መልካም ቆይታ

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝

በግጥም እናውጋ

28 Apr, 05:00


▬▬▬▬▬▬▬▬📝📝▬▬▬▬▬▬▬▬


🙌 ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ለሁላችሁም ሰላምታዬ እና አክብሮቴ ባላቹበት ይድረሳቹ።

❇️ በተለያዩ ምክኒያቶች ለረጅም ጊዜ በቻናሌ ላይ የምፅፋቸውን ግጥሞች መልቀቅ አቋርቼ ነበር። ከዛሬ ጀምሮ አቋርቼ የነበረውን ስራዬን በድጋሚ እጀምራለው። በቻልኩት አቅም በየጊዜው በአዳዲስ ስራዎችን ወደናንተ ለማድረስ እሞክራለው።

❇️በፊት ከማቀርበው ትንሽ በተለየ አዲስ አቀራረብ ስራዎቼን ለማቅረብ ተዘጋጅቻለው።

❇️ እስካሁን በትግስት ቻናሌን leave ሳትሉ አብራችሁኝ ለቆያቹት ሁሉ ምስጋናዬን እያደረስኩ አብሮነታቹ አይለየኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ።

❇️ በቻናሉ ላይ ያላችሁን አስተያየት፣ ይሻሻል ወይም ይጨመር  የምትሉት ነገር ካለ ሀሳባችሁን አሳውቁኝ።

     ╔════════════════╗
      👉JOIN: @BegitimEnawga 
      👉JOIN:
@BegitimEnawga
     ╚════════════════╝