ትምህርት ሚኒስቴር @timihert_minister Channel on Telegram

ትምህርት ሚኒስቴር

@timihert_minister


ተጨማሪ መረጃዎችን
በዌብሳይት - www.moe.gov.et


በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia

በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/

በቴሌግራም-https://t.me/timihert_minister
ይከታተሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር (Amharic)

የስራውን ስነ-ምህረት አስቸጋሪ እና ከላይ እንዴት እንደሚፈልግ የሚወቅ ስልጣን፡፡ ከዚህ በታች ከትምህርት መንግሥት ጋር የሚያደርጉት ትውልድ፡፡ በዚህ ክፍል በትክክል የሚገልጹ መረጃዎች ለመጠቀም ምን እንደሚፈልጋቸው እና ለአስተያየታቸው ስልጣን ተመልከቱ፡፡ በአሁኑ በሰዓት ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን እና አገልግሎትን ከእኛ ለማግኘት በመጠቀም የሚያስችል መረጃዎችን ያሳያል፡፡ በትዊተር፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራሜም እና ሊንክዲን በቪዲዮ እንደሚቀንብላቸው እናም ተጨማሪ ምንድን ነው የሚሳተፉት በመጠቀም ብሎ መደበል ችሎት ይሆናል፡፡ በቴሌግራም ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም እርስዎ ምንቸቫን ለመጠቀም በመሆን የተዘጋጀ እና አገልግሎት ተብሎ ተጨማሪህን መረጃዎች እና አስተዳደሮችን ለመሸጥ እና ለመመረጥ መርምር ችላት ይሆናል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

05 Nov, 06:06


ማስታወቂያ
*

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች   የምዝገባ  ጊዜ ኀዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
• የማህበራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ:-

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ትምህርት ሚኒስቴር

04 Nov, 12:52


Website: https://placement.ethernet.edu.et
Telegram: https://t.me/moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር

01 Nov, 13:40


ትምህርት ሚኒስቴር ከሁዋዌና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር የሚያዘጋጀው የአይሲቲ ውድድር አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

ከሁዋዌ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ፍጻሜ ለተወዳደሩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

ሽልማቱ የተበረከተው የሁዋዌ የ2024/25 አይሲቲ የውድድር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ ባስተላለፉት መልእክት ውድድሩ ለተማሪዎች የስራ እድልን በማመቻቸት እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን ከማጎልበት አኳያ ሰፊ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ዘላለም አክለውም ሁዋዌ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎችን ክህሎት ለማዳበር እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን መሠል ጥረቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢትዬጵያ ሚስተር ሊሚንግየ በበኩላቸው ውድድሩ ለወጣቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

31 Oct, 16:51


____________________________
"በእሳቤና በንግግር ከፋፋይ የሆኑ ሀሳቦችን እያጠፉ ሰብሰብ ለማድረግ ይሰራል።
የሚያሰባስቡ የማይለያዩ እሳቤዎችን በታሪክ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማካተት ቀጣዩ ትውልድ እንዲገነባው ይደረጋል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በ6ኛ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የትምህርት ሴክተሩን በተመለከተ የተናገሩት።

ትምህርት ሚኒስቴር

24 Oct, 12:53


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም በመደበኛው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ መስፈርት መሠረት ቅበላ ያገኙና #ከአዲስ_አበባ_ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን ብቻ ከዛሬ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በየተመደቡበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ምዝገባ ያካሒዳል፡፡

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ በፊት መገለፁ ይታወቃል፡፡

ለሁሉም ተማሪዎች (በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆናችሁትን ጨምሮ) አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ትምህርት ቤት ሦስት ተማሪዎች ሽልማቶችን አበርክቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበውን 568 ያመጣው ተማሪ ራጂ ተስፋዬ ዘመናዊ ላፕቶፕ እና የ30,000 ብር ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

በተመሳሳይ 545 ያመጣው ተማሪ ሁንዴሳ ፈይሳ እና 535 ያስመዘገበው ተማሪ ቶልቻ ቦጃ ዘመናዊ ላፕቶፕ እና የ20,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


#ማስታወሻ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #በመደበኛ እና #በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እንድትሞሉ ትምህርት ሚኒስቴር ያራዘመው የመሙያ ጊዜ ነገ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በቀሩት ጊዚያት ይሙሉ!

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


#Update

ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ለተሳናቸው የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው ተሸፍኖ) የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት እንደሚከተለው ይሆናል፦

► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192
► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186
በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224
► በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ጥቅምት 3 እና 4/2017 ዓ.ም ይቀበላል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች መገናኛ እና ቃሊቲ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በዚህም እሑድ 5፡00 ሰዓት እንዲሁም ሰኞ 4፡00 ሰዓት በተጠቀሱት ቦታዎች በመገኘት፣ የዩኒቨርሲቲውን ሎጎና የእንኳን ደህና መጣችሁ ባነር የተለጠፈባቸው አውቶቡሶችን መጠቀም እንደምትች ተገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ እና ለ2016 ሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሱ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

22 Oct, 17:28


#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

10 Oct, 13:18


#update

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው  ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ይገልጻል።

ትምህርት ሚኒስቴር!
@timihert_minister

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Oct, 06:56


ማስታወቂያ
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በተጨማሪም
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር

19 Sep, 12:05


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬሽን ማዕከላት መጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ
--------------------------------------
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን በማጠናከር ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን ማጠናከር በተቋማቱ ያለውን የተዛባ ሚዛን ያስተካክላል ብለዋል። አሁን ባለው ግምገማ በተቋሞቻችን ያለው የኢንኩንቬንሽን ማዕከላት አሰራር ከዘመኑ ጋር ያልተራመደ በመሆኑ ስልጠና ማዘጋጀት ማሰፈለጉን ጠቁመው በቀጣይ በዚህ ዘርፍ ላይ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር   ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል በበኩላቸው ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዩንቨርሲት ኢንዱስትሪ ትስስር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና እንኩንቤሽን ማዕከላት ኃላፊዎች የሚሰጠው ስልጠና ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ጠቁመው ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይህንን የሪፎርም ተልዕኮ በብቃት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። አቶ ተሾመ አያይዘውም ስልጠናው በፈጠራ ስነምህዳር፣ በስራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ማዕከላት እና የምርምር ውጤቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ገበያ ለማስገባት በሚከናወኑ አስተዳደራዊ ስራዎች  ላይ የሚስተዋለውን የግንዛቤ እጥረት መፍታትን ትኩረት ያደርገ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ባለሙያች እውቀታቸውን ይጋሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ከየተቋማቱ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ማዕከላቱ በሚጠናከሩበት ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በስልጠናው ብዙ ልምድ እንዳገኙ ጠቁመዋል።