@cmmt grade 9-12 @cmmt_grade_9_12 Channel on Telegram

@cmmt grade 9-12

@cmmt_grade_9_12


@cmmt grade 9-12 (English)

Are you a high school student looking for a place to connect with peers, discuss school topics, and get help with your homework? Look no further than the @cmmt grade 9-12 Telegram channel! Here, students in grades 9-12 can join a supportive community where they can ask questions, share study tips, and engage in conversations about various subjects. Whether you need help with math, science, English, or any other subject, there is always someone willing to lend a hand. This channel is not only a place for academic support but also a place to make new friends and have fun while learning. Join @cmmt grade 9-12 today and start your journey to academic success and community building!

@cmmt grade 9-12

09 Feb, 07:10


የተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች የሁለተኛ ሴሜስተር ትምህርት ነገ የካቲት 3/2017 ዓም የሚጀምር ሲሆን የመማር ማስተማሩን ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ የሚከተሉትን የወላጅ ሀላፊነቶች  እንድትወጡልን እንጠይቃለን።        
1,ተማሪዎች ከጠዋቱ 2:30በፊት ት/ቤት የመገኘት ግዴታ አለባቸው። 
  2,ዪኒፎርም የት/ቤቱ ባጅ ያለበት መደረግ አለበት  
  3,የወንዶች ፀጉር በአጭሩ የተቆረጠ በደረጃ ያልተቆረጠ ወይም አንዱ ከአንዱ የማይበላለጥ መሆኑን።           
4     ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ የጆሮ የእጅ የጰጉር  የማይፈቀድ ሲሆን የከንፈር ቀለም ዊግ ያደገና ቀለም የተቀባ ጥፍር የተከለከለ መሆኑን               
   5,ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ስልክን ጨምሮ በምንም ሰበብና ምክንያት ይዞ መገኘት የተከለከለና ከተገኘም የማይመለስ መሆኑን።               
ከላይ በዝርዝር የተመለከቱትን ተግባራዊ ያላደረገ ተማሪ ወደ ት/ቤት ግቢ የማይገባ በመሆኑ ወላጆች ተማሪዎች ይህንን ተግባራዊ ማድረጋቸውን እንድታረጋግጡ እያሳሰብን የተጓደሉ ከሆነ ግን ት/ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን ደግመን በጥብቅ እናስታውቃለን።      

@cmmt grade 9-12

31 Jan, 08:07


ቀን 23/05/2017 ዓም
በገዳመሲታውያን ማርያም ጽዮን ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ
ሰኞ26/05/2017 ዓም የመጀመሪያ መንፈቅ አመት ውጤት ከየመምህራኖቻችሁ ፈተናችሁን መቀበያ ቀን በመሆኑ በተባለው ቀን እንድትቀበሉ እናሳስባለን ፡፡
ት/ቤቱ

@cmmt grade 9-12

05 Nov, 18:09


የ2016 ዓ,ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ስለመጣ እንድትወስዱ::

@cmmt grade 9-12

29 Oct, 11:51


https://t.me/+BeldL9jgJWphM2Jk

@cmmt grade 9-12

25 Oct, 07:03


ቀን 13/02/2017 ዓም
በገዳመሲታውያን ማርያም ጽዮን ካቶሊክ ትምህርት ቤት ከ40 ዓመት በላይ ሲያገለግሉ የቆዩ መ/ርት እፁብ ድንቅ ተገኘን አሁን ላይ በጡረታ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር መምህራን እና የአስተዳድር ሰራተኛ በተገኙበት ቀሪ ዘመናቸው መልካም ጊዜ እንዲገጥማቸው በመመኘት ከስራ ባልደርቦቻቸው እና ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ስጦታ ተበርክቶላቸው ተሸኝተዋል ፡፡

@cmmt grade 9-12

11 Oct, 03:51


Share 'የ2017 ዓ፣ም የትምህርት ቤታችን ህግና ደንብ ለተማሪዎች የቀረበ.pptx'

@cmmt grade 9-12

08 Oct, 16:17


1. ማስታወቂያ

የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

2. ማስታወቂያ

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

@cmmt grade 9-12

17 Sep, 10:29


ለተማሪ ወላጆች
የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
የገዳመሲታውያን ማርያም ጽዮን ካቶሊክ ትምህርት ቤት የ2017 ዓ,ም የትምህርት ዘመን ትምህርት መጀመራችን ይታወቃል :: በመሆኑም ስለ 2017 ዓ,ም የትምህርት ዘመን የጋራ የምናደርገው ጉዳይ በመኖሩ መገናኘት አስፈልጎናል ስለሆነም ቅዳሜ 11/1/2017ዓ,ም ከጠዋቱ 2:30 እንድትገኙ እያሳስብን የማይገኝ ወላጅ ተገኝተው በተግባባነው ሃሳብ ተገዥ ይሆናል::

@cmmt grade 9-12

15 Sep, 11:05


እንኳን ደስ አላችሁ
የ2016ዓ፣ም የትምህርት ዘመን የ12 ክፍል  ተማሪዎች ውጤት በትምህርት ብትና በተማሪዎች ዕቅድ አቅደን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል ::ይሁን እንጅ እንዳቀድነው ግባችንን ባይሳካም ከ236 ተማሪዎች ውስጥ 95 ተማሪዎችን ከ300 በላይ ማስመዝገብ  የቻልን ሲሆን ከዚህ  በታች በፎቶ የለጠፍነው ደግሞ ከ350 በላይ ያመጡት ተማሪዎች ወላጆችና ተማሪዎች  እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንፈልጋለን፡፡

@cmmt grade 9-12

05 Sep, 15:26


አስቸኳይ
በ2017 ዓም ወደ 11ኛ ክፍል ለተዛወራችሁ ተማሪዎች በሙሉ አዲስ የተጨመሩ የተግባር ትምህርት ስላሉ ሰኞ ከዚህ በታች ያሉትን የመምረጫ ፎርም ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመመካከር ለሰኞ 4/13/2016 ዓ.ም ራሳችሁ ተማሪዎች መርጣችሁ በአካል ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ይህን ሳታደርጉት ቀርታችሁ ሳትመርጡ ብትቀሩ ትምህርት ቤቱ ራሱ መድቦ የሚሄድ መሆኑን እናሳውቃለን ::
ተቋሙ ካሉት የትምህርት ዘርፎች ውስጥ የመረጣቸው
#ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች
1, communication And Social
A . journalism
2. Busines Science
A. Accounting And Finance
B. Marketing And Sale Mangement
# የተፈጥሮ ሳይንስ
1.ICT
A. Software development
B.mantinenace
c.multimedia design and development

@cmmt grade 9-12

02 Sep, 12:02


በድጋሜ ለመጨረሻ ጊዜ
የተማሪዎች ዩኒፎርም ለማሰፋት  መለካት እና ማሰፋት ካለበት ተማሪዎች ውስጥ የተወሰነ ተማሪዎች ብቻ ሳይለኩ በመቅረታቸው ወላጆች ትምህርት ቤቱን ፕሮግራም ይያዝልን በማለት የጠየቁ በመሆኑ ሀሙስ 30/12/16 ዓም  6:30 ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ እንድትለኩ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የማናስተናግድ እና አንዳንድ ክፍያ ያልከፈላችሁ ተማሪዎች ሀሙስ 30/12/16 ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን ::

@cmmt grade 9-12

30 Aug, 08:37


ለ2017 ዓ,ም ለ12 ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
ሰኞ 27/12/2016 ለ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ውይይት ማድረግ ስላስፈለገ ጠዋት 2:30 እንድትገኙ እናሳስባለን ::

@cmmt grade 9-12

16 Aug, 10:17


በድጋሜ
ለአዲስ ተማሪዎች
የተማሪዎች ዩኒፎርም ለማሰፋት መለካት እና ማሰፋት ካለበት ተማሪዎች ውስጥ የተወሰነ ተማሪዎች ብቻ ሳይለኩ የቀሩ በመሆኑ እስከ ሰኞ13/12/16 ዓም 6:30 ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ አንዳንድ ክፍያ ያልከፈላችሁ ተማሪዎች ሰኞ 13/12/16 ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን ::

@cmmt grade 9-12

13 Aug, 10:06


ለአዲስ ተማሪዎች
የተማሪዎች ዩኒፎርም ሰኞ ለማሰፋት መለካት ስለሚጀምር ሁሉም ተማሪ እንድትገኙ እናሳስባለን በማለት ማሳወቃችን ይታወቃል ይሁን እንጅ መለካት እና ማሰፋት ካለበት ተማሪዎች ውስጥ 70 ተማሪዎች ብቻ ሳይለኩ የቀሩ በመሆኑ እስከ ነገ 6:30 ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ አንዳንድ ክፍያ ያልከፈላችሁ ተማሪዎች ነገ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን ::

@cmmt grade 9-12

10 Aug, 11:43


ለአዲስ ተማሪዎች
የተማሪዎች ዩኒፎርም ሰኞ ለማሰፋት መለካት ስለሚጀምር ሁሉም ተማሪ እንድትገኙ እናሳስባለን