ሳቅ እና ቁም ነገር @saki_ena_chewata Channel on Telegram

ሳቅ እና ቁም ነገር

@saki_ena_chewata


ሙሌ አድስ ነገር

👉ችግር ለመፍጠር ሳይሆ ችግር ለመፍታት ኑር።

👉የራስህን መንገድ ጥረግ እንጂ የሌሎችን መንገድ አትዝጋ።

👉የራስህን ራዕይ በህሊናህ ተመልከት።

👉ግብህን ቅረፅ።

👉በራዕይህና በግብህ መካከል የሚገጥሙህን ፈተናዎች በትግስት እለፋቸው።

👉ከዚያም ውጤቱ ያማረ ይሆናል። 💚 💛

ሳቅ እና ቁም ነገር (Amharic)

ሳቅ እና ቁም ነገር በእሁድን በኢትዮጵያና በአማርኛው በቁም ነገር አሁን ተመሳሳይ ነው። 'saki_ena_chewata' በጣም ሳያብርት ሽግር ለመፍጠር በሚል ሥራ እና ሽግር ለመፍታት በሚል እንጂ ሌላ ሰውን ሽግር አትዝጋ። ስለራስሓይ በቅርብ ወንጌላው ማሰሪያ በማሳሰብ ስርዓት አትከትል። ራስህን መንስርት አንዶችን እናመልከት። ግብህን ቅረፅ። ለራስህና ለግብህ ጉልቻዎች ምታለን። በትክክለኛ ህይወት አምላክ ተበቀሉ። በዚህ ውጤቱ በመማር ብር ብር ቦር እና ሌሎች ዓይነትን ውጤታዎችን ይመለሳል።

ሳቅ እና ቁም ነገር

27 Sep, 11:52


በወንጌሉ ላመናችሁ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ

ሳቅ እና ቁም ነገር

10 Sep, 11:42


ዉድ ሳቅና ቁምነገር ቻናል ተከታታዮ እንደምን ሰነበታችሁ እንደምንስ ከረማችሁ እንኳን ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏💚💛
እንግዲህ 2012 ዓ.ም አሮጌዉን አመት ለማለት ሰዓታት ብቻ ቀርተዋል ዉድ የዚህ ቻናል ተከታዮች እንግዲህ አዲሱ ዓመት ስመጣ ሰዉ ብዙ ያቅዳል ስለዚህ ይህ አዲሱ አመት ያቀዳችሁ የሚሳካበት ስኬትንና ብልፅግናን ያጎናፅፋችሁ እያል በተለያዩ በጎ ተግባራትን የምንከዉንበት እንዲሆን እመኛለዉ ።ቸር ዋሉልኝ🙏🙏💚💛

ሳቅ እና ቁም ነገር

24 Aug, 18:16


ወድ ሳቅ እና ቁምነገር ቻናል ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችሁ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረዉ ቻናላችን በአዲስ መልክ መቷል ። እያዝናና ቁምነገን ይዞ ከች ብሏል😘😘😘😘

ሳቅ እና ቁም ነገር

24 Oct, 08:08


ሙሌ አድስ ነገር

👉ችግር ለመፍጠር ሳይሆ ችግር ለመፍታት ኑር።

👉የራስህን መንገድ ጥረግ እንጂ የሌሎችን መንገድ አትዝጋ።

👉የራስህን ራዕይ በህሊናህ ተመልከት።

👉ግብህን ቅረፅ።

👉በራዕይህና በግብህ መካከል የሚገጥሙህን ፈተናዎች በትግስት እለፋቸው።

👉ከዚያም ውጤቱ ያማረ ይሆናል። 💚 💛

@mulemule

ሳቅ እና ቁም ነገር

24 Oct, 08:06


# ግጥም ,,,,,,,,,,,,~=>

አንተ የማን ልጅ ነህ - ከየት ነህ አትበሉኝ ፡
ብሔሬን ተውና ችግሬን ጠይቁኝ ።
አማራ ይመስላል - ለምን ትላላችሁ ?
ኦሮሞ ይመስላል - ለምን ትላላችሁ ?
እርቃኔን ቁጭ ብዬ - በርዶኝ እያያችሁ
ከደቡብ ነህ እንዴ ? ለምን ትላላችሁ ?
ትግራዋይ ነው መሰል - ለምን ትላላችሁ ?
እህል ሆዴ ናፍቆ - ተርቤ እያያችሁ ።
ከጋምቤላ ነህ ወይ ፤ ለምን ትላላችሁ ?
አፋርም ይመስላል ፥ ለምን ትላላችሁ ?
መናገር አቅቶኝ - ታምሜ እያያችሁ ።
ሱማሌ ነህ መሰል - አፍህ ይጣፍጣል
ቆለኛ መሆንህ - በደንብ ያስታውቃል
ይህ የአደሬ ልጅ ነው ፤ ከጀጎል የወጣ ፥
ወይም የቤኒሻንጉል - ከአሶሳ የመጣ ፥
በማለት ጎሣዬን - ምን አሰቆጠራችሁ ?
ተስፋዬ ጨላልሞ - ተክዤ እያያችሁ ።
ሆድ ብሶኛል እና ፥ ይብስ አታስብሱኝ ፤
የሚዲያ አስቤዛ - ፍጆታ አታድርጉኝ ።
ስለዚህም ማን ነህ ? ከየት ነህ ? አትበሉኝ ፤
ብሔሬን ተውና ፥ ችግሬን ጠይቁኝ ። .....
በኢትዩጲያዊነቱ የሚያምን ብቻ #

ሳቅ እና ቁም ነገር

10 Sep, 03:40


#JIMMA ጅማ ከተማ ቤተክርስቲያን #ተቃጠለ፤ አገልአጨጋዮችም እየታረዱና እየተገደሉ ነው፤ በሚል በፌስቡክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። ይህን ስራ እየሰሩ ያሉት ምንም ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ናቸው ያለው የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን በከተማይቱ ውስጥ ንብረት አልወደመም ሰዎች ላይም ጉዳት አልደረሰም፤ እየተናፈሰ ያለውም በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ በመልቀቅ ህዝቡን ማደናበር ነው ብሏል። በመሆኑም ሁሉም አካላት የጉዳዩን ጥንስስ አላማን በመረዳት ዋስትና ለሆነዉ ሰላምና አንድነት ተግቶ በመስራት ጅማን #ወደቀድሞ ሰላሟ ለመመለስ እየተደረገ ላለዉ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ዞኑ ጥሪ አስተላልፏል።

የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን⬆️
___________________________________

ከጅማ ከተማ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተጣሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን፦

•ዛሬ በከተማይቱ አንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው ውጥረት ምክንያቱ ምንድነው?
•በእርግጥ በከተማው በአሁን ሰዓት በፌስቡክ ላይ እየተወራ እንዳለው የከፋ እና አስጊ ችግር አለ?

📑የከተማይቱን ነዋሪዎች፣ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንዲሁም የከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ስለተፈጠረው ሁኔታ ምን ይላሉ? የሚለውን እንዳዘጋጀንና እንደጨረስን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባል።
@muleadisneger

ሳቅ እና ቁም ነገር

22 Jun, 11:19


በአትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)የቀጥታ ሽፋን የሚያገኘው እና 40 ሺህ ሰው ተሳታፊ የሚሆንበት ታላቅ ሩጫ በአርባምንጭ ከተማ በቀን 16/10/2011 ዓ.ም ከጥዋቱ 12 :00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ሩጫው የሚጀመረው ከሲቀላ ጋሞ አደባባይ ሲሆን የሚጠናቀቀው ሼቻ ከለምለመ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ነዉ
አትሌት ሙክታር እድሪስ እና ሰለሞን ባረጋን ጨምሮ የአገራችን ስመ ጥር አትሌቶች በሩጫው ይሳተፋሉ፡፡

በዕለቱ አዝናኝ የፈረስ ጉግስ ይካሄዳል፡፡

የጋሞ አባቶች ለወጣቶች አደራ የሚያስተላልፉበት ስነ- ስርዓት ተዘጋጅቷ፡፡
Soccer Gamo Zone Administration public Relation office

@mulesport @mule_sport_2

ሳቅ እና ቁም ነገር

01 Jun, 03:40


#update በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ሳቢያ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በሽታው ከሚያዝያ 18/ 2011 ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ እንደተከሰተ የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የኅብርተሰብ ጤና ስጋት ቅብብል ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"እስካሁን በሦስት ወረዳዎች እነሱም በሰሜን ጎንደር ጠለምት እና በይዳ ወረዳዎች እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ደግሞ አበርገሌ በሚባል ወረዳ በሽታው ስለመከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል" ብለዋል።

በጤና ተቋምና ባለሙያዎች ቤት ለቤት እየሄዱ ባደረጉት ሪፖርት መሠረት፤ እስከትናንት ድረስ 190 ገደማ ሰዎች በአተት መያዛቸውን ባለሙያው ገልጸዋል። "በአተት ምክንያት በተቋም ደረጃ መሞታቸው የተረጋገጠው 5 ሰዎች ናቸው" ብለዋል።

አቶ አሞኘ እንደሚሉት፤ በሽታው የመቀነስ እዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም በቁጥጥር ሥር ማዋል ግን አልተቻለም። "አሁን ባለው ሁኔታ ሰሜን ጎንደር ላይ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል። እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ምንም አይነት ህመምተኛ ሪፖርት አልተደረገም" ይላሉ።
ሆኖም አበርገሌ ላይ አልፎ አልፎ ሪፖርት እንደሚደረግ ያስረዳሉ።

"ትናንት ሪፖርት አልነበረም። ቆሟል ማለት አይቻልም። አሁን ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ነገር ግን ቆሟል ከእንግዲህም አይነሳም የምንልበት ሁኔታ የለም። ምክንያቱም ሰፊ ሥራ ይጠይቃል" ሲሉ አቶ አሞኘ ይገልጻሉ።

የተከሰተው አተት ነው ወይስ ኮሌራ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ "አተት በተለያዩ ነገሮች ሊከሰት ይችላል። በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፕሮቶዞዋ ወይም በምግብና ውሃ መመረዝ ሊከሰት ይችላል።

አተት ከሚያመጡት ውስጥ አንዱ ባክቴሪያ ሲሆን፤ ከባክቴሪያዎቹ ውስጥ ደግሞ አንዱ ኮሌራ ነው፤ ልዩነታቸው ይሄ ነው። አተት ሰፊ ነው። በብዙ ነገሮች ሊከሰት የሚችል ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ማለት ሲሆን፤ ኮሌራ ማለት ግን አተትን ከሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች አንዱና በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት ነው" ብለዋል።

አተት በብዙ ነገሮች ሊከሰት ስለሚችል እያንዳንዱ ኮሌራ እየተባለ ሪፖርት በቢደረግ ስህተት ሊፈጠር እንደሚችልም ተናግረዋል።

አክለውም "ናሙና እየወሰዱ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፤ ማንኛውንም ምልክት የሚያሳይ ሰው አተት በሚል መረጃውን እየተቀባበልን የመከላከልና መቆጣጠር ሥራ እንሠራለን" ብለዋል።

ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ያለበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ እንዳለበት አቶ አሞኘ አሳስበዋል።

አሁን የተከሰተውን ችግር ለመከላከል ባለሙያዎችና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደቦታው በመላክ ከአጋር ተቋማት ጋር እየሠሩ መሆኑንም ባለሙያው ገልጸዋል።

Via #BBC
@muleadisneger

ሳቅ እና ቁም ነገር

01 Jun, 03:38


⬆️የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከነገ ጀምሮ መከበር ይጀምራል

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡

የዋዜማ በዓሉ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ስነ ስርዓች በጎዳና ላይ በሀዋሳ ከተማ ተከብሮ ውሏል፡፡

በሲዳማ ብሔር ባህላዊ ጭፈራ“ቄጣላ ” እና በሌሎች ስነ ሰርዓቶች ነው በሃዋሳ ከተማ ጎዳናዎች የፊቼ ጫምባላላ ሲከበር የዋለው፡፡

በርካታ ባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች እንዳሉት የሚነገረው ፊቼ የሲዳማ ብሔር አንኳር የሆኑ ባህላዊ ገጽታዎች የሚንጸባረቁበት እንደሆነ ይነገራል፡፡

የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ የሚታወቅ ነው፡፡

በዓሉ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡

ምንጭ:- FBC
@muleadisneger