Hana Hailu

@hanahailu


መንቃት እና ማንቃት
መብቃት እና ማብቃት
የሰው ልጅ ልክ እንደውቅያኖስ ነው ስፋቱ እንጂ ጥልቀቱ አይታይም!
በየቀኑ እማራለሁ- የተማርኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩ!

በዚህ ቻናል የተማርኩትን የገባኝን ከሌሎች ከራሴ ለእናንተ አካፍላለሁ!
ራሴን እና ሌሎችን ለማንቃት እጠቀማለሁ


አስተያየት
@HanahailuEth

ዌብሳይቴን ይጎብኙ
Www.hanahailu.com

Hana Hailu

22 Oct, 03:16


ምስሌን ፍለጋ በአስቴር አበበ በድምፅ ሊመጣ ነው!

ብዙ ሰው እጅ ገብቶ ተነቧል በጣም የምወዳት የማደንቃት ሴት እጅ በድንገት ገብቶ ማየቴ ግን ከሁሉ በላይ አስደስቶኛል!
ማጋነን እንዳይሆንብኝ በሺ የሚቆጠር ሰው ያነበበው ያህል ነው የተሰማኝ.....!
እንዲሁ በሩቅ እንደማውቅሽ እና እንደማይሽ በሰራሽው እንደምጠቀመው ሳይሆን አንቺው ፈልገሽኝ ማበረታታሽ አልበቃ ብሎሽ በዚሁ የተባረከ በድምፅሽ በኦዲዪ ልትሰሪው ስለሆነ
በጣም ደስ ብሎኛል።
+ ምክርሽን እና ፀሎትሽ የሆነ ነገሬን እንደገና ወደ ፊት እንዲያስቀጥል አድርጓል ተባረኪ እወድሻለሁ!

ማን እጅ እንደሚደርስ አታቂም ብቻ አንቺ ውስጥሽ ያለውን ፃፊ ብያለሁ ለራሴ....!

#Book #AsterAbebe #Reader #ምስሌንፍለጋ

Hana Hailu

14 Oct, 09:17


በትላንትናው እለት #ልጅህን_ታደግ የሚለው የ ኢዮሲያስ ግርማ Eyosias Girma ስድስተኛ መጽሓፍ በደመቀ ስነስርአት ተመርቋል!!

እኔም "ሌላ ፍቅር" በሚል ርዕስ ንግግር አድርጌያለሁ!
ልጅነቴን በማስታወስ መጽሐፉንም አንብቤ የተረዳሁት ነውና ከተናገርኩት ጥቂቱን እነሆ
በልጅነቴ በጣም ጠያቂ ልጅ ነበርኩ ቤተሰብ ካልመለሰልኝ ከሌሎችም ቢሆን መልስ እስካገኝ ድረስ እጠይቃለሁ!
-ለልጆቻችን ወይ እኛ ጥያቄ ሲጠይቁ ትክክለኛውን እንመልስላቸዋለን ወይም ሌሎች የተሳሳተም ቢሆን ይመልሱላቸዋል! መልሱን ግን ማግኘታቸው አይቀርም
- ወይ እኛ በአግባቡ እናሳድጋቸዋለን ወይም ሶሻል ሚዲያ እና ሌላው አለም ያሳድጋቸዋል ማደጋቸው ግን አይቀርም!
ብቻ ልጆችን በልጅነታቸው በመታደግ ለተፈጡሩበት አላማ እንዲኖሩ ማድረግ የእኛ ግዴታ ነው!
ልጅ እንኳን ባንወልድ እኛ በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ልጆች አሳዳጊዎች ነን። ስለዚህ ይሄን መጽሐፍ ሁላችንም ልናነበው ይገባል!

መልካም ንባብ....
ልጅህን ታደግ እንዲሁም የኢዮሲያስ ሌሎች መጽሐፎች የእኔንም ምስሌን ፍለጋ መጽሐፍ ብታዙ እና ብትገዙ በነፃ ያላችሁበት ታደርስላችኋለች! በዚህ ስልክ ደውሉላት +251939309055 (ፍሬ)p

Hana Hailu

07 Oct, 16:20


🎉 Celebrating a Milestone! 🎉

After an impactful five years, the USAID/OTI Ethiopia Support Program (ESP) is coming to a close. I’m honored to be part of this incredible journey, as the youngest female leader partnered with ESP through Abriminds.

I was a guest speaker, sharing our achievements from Abriminds' four key projects working with ESP under the project which is called Small Light and Birtucan. These initiatives are transforming lives, reaching over 500 youth across more than six cities. 🌍

Thank you, USAID/OTI ESP, for the platform and partnership to make a lasting impact.

#ESP #Abriminds #Change #Ethiopia

Hana Hailu

04 Oct, 05:13


#Bookshower
Memory of the First Book Shower!

Now a Days We're celebrating both a bride-to-be and a mom-to-be in a unique way. I’ve taken this special moment and turned it into an inspiring opportunity by sharing my book. It’s a fresh approach to marketing and supporting one another.
This book is deeply personal to me, as I poured to much time, energy, and resources into making it a reality.

It has been an incredibly rewarding journey, filled with meaning and purpose.

Get Your Copy:

In Addis Ababa: Free delivery and discounts! Call: +251939309055

Available at various bookstores in Addis.

Internationally:

Get easly on
kulu Books https://lnkd.in/eAVxSiEA

on amazon https://lnkd.in/e5YXhhfs

#Book #መጽሐፍ #Bookshower #motivation #fypシviralシ2024 #ምስሌን #ምስሌንፍለጋ

Hana Hailu

02 Oct, 04:30


#ጨለማው_አዳራሽ
ዛሬ በሸራተን ለመጀመሪያ ጊዜ ስሞል ላይት የተሰኘ ለሁለት አመት ከ5 በላይ ከተሞች ላይ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር የሰራነው ፕሮጀክት በኢትዮጲያ የአሜሪካ አምባሳደር እና የUSAID ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለኤግዚቢሽን በቅቷል!
ትልቅ ጨለማ ውስጥ ትንሽ ብርሀን ያለውን ዋጋ ለማሳየት ይሄንን ቤት ገንብተናል በውስጡም ስራችን ተጎብኝቷል።

ሰው ቤቱ ገብቶ መብራት ሲጠፋበት ሻማ ይፈልጋል እንጂ ስለጨለማ ቁጭ ብሎ አያወራም....ውጤታማ ስራ ነበረን!

USAID Ethiopia U.S. Embassy Addis Ababa
#Abriminds

Hana Hailu

30 Sep, 06:40


🚨 አስፈላጊ መረጃ! የሐዋሳ ኢንፎ ሴሽን የቦታ ለውጥ 🚨

📍 አዲሱ አድራሻ፦ ሳውዝ ስታር ሆቴል (South Star Hotel)፣ ሐዋሳ
🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:30 ሰዓት

የመስራት ፕሮግራም ንግድዎን እንዴት ማጎልበት እንደሚችል፣ ስለ ሥራ ፈጠራ ፕሮግራማችን ቁልፍ ግንዛቤዎች እና ስለ ቴሌግራም ቦት ስልጠና ጥቅሞች ምንመለከትበት ዝግጅት ነው።

ከታች ባለው ሊንክ ተመዝገቡ!
https://forms.gle/RFt2RTUhznLSi7np9

#Mesirat #Entrepreneurship #Hawassa #BusinessGrowth

Hana Hailu

25 Sep, 04:49


ለሚመለከተው አካል የተፃፈ...

-የሆነ ቀን የሰዎች ከበባ ትንፋሽ ያሳጣችኋል!
-ወዳጃችሁ ይበዛል ያላችሁን ሁሉ መስጠት ትጀምራላችሁ ከምንም በላይ ጊዜያችሁን።
-ፈገግታቸው የልባቸው ፎቶ ይመስላችኋል
እናንተ ፊት ሲያለቅሱ ሲስቁ እናንተም የልባችሁን መዘርገፍ ትጀምራላችሁ።
-ሩቅ እያሉ የማያውቁትን ድክመታችሁ ያዩታል በዛው ጉዳይ መልሰው ያደክሟችኋል!
የሆነ ቀን የከበበ ይርቃችኋል ፣ ያጀባችሁ ይበተናል ያን ጊዜ ወደ ላይ ቀና በሉ ለሰዎች የሰጣችሁትን ያህል ልብ እንኳን ባትሰጡት
በድክመታችሁ ፣በጥፋታችሁ፣ በውድቀታችሁ ፣በከፍታችሁ የማይተዋችሁ ጌታ አለ!
Let Go and Let God

2016 ዓ.ም ሲጨመቅ Let Go and Let God

Hana Hailu

20 Sep, 11:30


⚠️ ሐዋሳ ውስጥ ከሆናችሁ! ⚠️

ቢዝነስዎን ስኬታማ ለማድረግ እንደግፍዎታለን!

በ https://forms.gle/RFt2RTUhznLSi7np9 ተመዝግበው ቦታዎን ያሲዙ።

🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:30
📍 በኬር አውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Ker-Awud International Hotel), ሐዋሳ

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም Info Session ጥቅሙ ምንድን ነው?
- መስራት ምን እንደሆነና ቢዝነስዎትን እንዴት እንደሚደግፍ ያውቃሉ፣
- ፕሮግራሙን እንዴት መቀላቀል እንደሚቻል ያውቃሉ፣
- ስለሚሰጡት ድጋፎች እና ለሚኖርዎት ጥያቄ መልስ ያገኙበታል።
- በቴሌግራም ቦት በኩል ለሚሰጥ ሥልጠና መመዝገብ ይችላሉ።

#መስራት #ስራፈጠራ #Mesirat #Hawassa #Entrepreneurship #Opportunity #GPM