Wolaita Times @wolaitatimes Channel on Telegram

Wolaita Times

@wolaitatimes


Proving Media and Advertising Service

Wolaita Times (English)

Are you looking for a reliable source of news and information related to Wolaita? Look no further than the "Wolaita Times" Telegram channel! With the username @wolaitatimes, this channel is dedicated to providing media and advertising services to the Wolaita community and beyond. Whether you are a resident of Wolaita looking to stay updated on local news, events, and developments, or simply interested in learning more about this vibrant region in Ethiopia, this channel is the perfect place for you. The team behind "Wolaita Times" is committed to delivering timely and accurate information to its followers, ensuring that you are always in the know. With a focus on quality journalism and engaging content, you can trust "Wolaita Times" to provide you with the latest news and updates from Wolaita and the surrounding areas. Join the "Wolaita Times" Telegram channel today and experience the best in media and advertising services!

Wolaita Times

15 Feb, 14:46


ምክር ቤቱ የብልፅግና ኃላፊውን አፈጉባኤ በማድረግ ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩን የመንግስት ዋና ተጠሪ አደረገ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ የነበረውን አቶ አለማየሁ ባውዲን የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ መድቧል።

በሌላ በኩል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን ተሹመዋል።

በተጨማሪም ዶክተር አበባየሁ ታደሰን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ተደርጎ ተሾመዋል።

ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ተፈሪ አባተ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቃለማላ ፈፅሟል።

አቶ ንጋቱ ዳንሳ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ እና የክልሉ የፖለቲካና ሪዮታለም ዘርፍ ኃላፊ፣ ኢንጅነር ፍሬዘር ኦርካይዶ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ እና የክልሉ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም

1ኛ- አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ ወ/ሮ ፀሀይ ወራሳ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

3ኛ አቶ ዳዊት ገበየሁ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ

4ኛ ወይዘሮ አፀደ አይዛ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

5ኛ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሆነው ተሹመዋል።

በትናንትናው ዕለት የጀመረውና በነገው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ሹመትን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን በማፅደቅ ውሳኔ እና አቅጣጫ እያስቀመጠ ይገኛል።

በጉዳዩ ዙሪያ ለዝርዝር ምልከታ እንመለስበታለን!

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5481

Wolaita Times

08 Feb, 14:53


"ልማትም በኦሮ_ማራ ቀመር ነው እንዴ የሚሠራዉ የሚል ጥያቄን ይፈጥራል"

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ

የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ አዳዲስ የፍጥነት መንገዶች፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ነቀምትና ጅማ ለመገንባት ጥናት እያካሄደ መሆኑን አሳዉቋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያሎት አስተያዬት ምንድነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በጣም ጥሩ ጅምር ነው። በተለይ ነቀምት ለዘመናት፣ አሁን ያለዉን መንግስት ጨምሮ ስትገፋ የኖረች የወለጋ ከተማ በመሆኗ፣ ለልማቱ በመታጨቷ በተለዬ ሁኔታ አስደስቶኛል። የፍጥነት መንገድ ወይንም express way ማለት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲደሩሱበት ታቅዶ የሚገነባ መግቢያና መዉጫዉም ዉስን የሆነ መሄጃ እና መመለሻውም በግልጽ ተለይቶ የሚሰራ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለዉ መንገድ ማለት ነው።

በኢትዮጵያ ቀድሞ የተሰራዉ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እንደነበረም ይታወሳል። መንገዶቹ የጉዞ ሰዓትን በመቀነስ ትልቅ ጥቅም ያስገኛሉ። ለኢኮኖሚ እድገትም ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ። ሰሞኑን የተገለጹ መንገዶችም ከዚህ አኳያ መሠራታቸዉ ጥሩ ሆኖ፤ መንገዶቹ በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ብቻ መሠራት አሁንም ልማት በኦሮ_ማራ ቀመር ነው እንዴ የሚሠራዉ የሚል ተጨማሪ ጥያቄን ይፈጥራል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በተለይም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስመር፦ ከአዲስ አበባ ቡታጅራ - ወራቤ - ሆሳዕና - ዎላይታ ሶዶ -አርባምንጭ - ኮንሶ - ሞያሌ መስመርም ቀጥተኛ 3 ክልሎችንና ኬንያና ትላልቅ ከተሞችን ስለሚያገናኝ ፈጣን መንገድ Express way ያስፈልገዋል በሚል በርካቶች ይሞግታሉ። ምን ሀሳብ አለዎት ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በእዉነቱ ስለ ፍትሐዊ ልማት ከሆነ የምናወራዉ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ሁለት ሁለት አግኝተዉ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ሶዶ፣ ከሱማሌ ጅግጅጋ፣ ከትግራይ መቐለን ጥናቱ አለማካተቱ ጥያቄ ያስነሳል። ልማት በፍትሐዊነት ካልተዳረሰ ሌላ ችግር እንደሚፈጥርም ይታወቃልና ሌሎች ክልሎችም ላይ ልማት መሠራት አለበት እንደ የአስፈላጊነቱ በተጨማሪም እነኝህ መንገዶች ይሠራሉ የተባሉባቸዉ ክልሎች ጦርነት አለባቸዉ ስለዚህ ሰላም በሌለበት የመንገድ ስራ አስቸጋሪ ነዉና ለሰላም ቅድሚያ መሰጠት አለበት።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በአጠቃላይ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ የሚሰሩ የፍጥነት መንገዶች ከግምት ማስገባት አለባቸዉ ብለዉ የሚያነሷቸዉ ነጥቦች ካለ ቢጠቁሙን ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንደኛው ድሮ መንገዶች ሁሉ ወደ ሮም ያመራሉ ይባል ነበረ። በኢትዮጵያም መንገዶች የሚሰሩበትን እሳቤ ስታይ መንገዶች ሁሉ ወደ አዲስ አበባ ያመራሉ በሚል ፍልስፍና የሚመራ ይመስላል። የጎንዮሽ ግንኙነት ብዙ ትኩረት ተሰጥቶት አያዉቅም፣ ብዙ ቦታ የሚኬደዉ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደዉ መንገድ እየሄዱ ዞሮ በመመለስ ነው።

ወደቦችን ከክልል ከተሞች፣ የክልል ከተሞችንም ከክልልና የዞን ከተሞች ጋር ለማስተሳሰር አቅም በፈቀደ መጠን በትኩረት መሠራት አለበት። በርግጥ ከሞጆ ወደ ባቱ እና ወደ አዋሳ እንዲሁም ከድሬዳዋ ደወሌ የተሰራዉም ጥሩ ነዉ፥ የተጀመሩትም ከብልጽግና በፊት ነው፣ ብልጽግና ደግሞ ሁሉንም ከአዲስ አበባ ጋር ብቻ ለማገናኘት ማቀዱ መታረም አለበት። የአዋጭነት ጥናት እንደተጠበቀ ሆኖ።

ሁለተኛዉ የፍጥነት መንገዶችን ከመደበኛው መንገድ ዲዛይን ከሚለያቸዉ ነገሮች አንዱ የግድ ከተሞች እንዲያቋርጡ አለመደረጋቸዉ እና በሚያጥረዉ በኩል (shortest route)ላይ የበለጠ ስለሚተኮር ነው። ስለዚህ ብዙ መገንጠያ እና መግቢያ በማስቀመጥ ከየ ትንንሽ ከተሞች ጋር ማገናኘት ባይቻልም፤ ትልልቅ ከተሞች ግን መገንጠያና መግቢያ እንዲኖራቸዉ ቢደረግ መልካም ነዉ። ከወዲሁ ዲዛይኑ ይህንን ከግምት ማስገባት አለበት። አለበለዚያ ብዙዎችን የበይ ተመልካች አድርጎ ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል ብቻ ዲዛይኑ ጥንቃቄ ይፈልጋል ለማለት ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ከዚህ ቀደም በኢትዮጲያ ከተሰሩ የፍጥነት መንገዶች በመነሳት ምን መሻሻል አለበት ይላሉ ? ሌላ ተጨማሪ የሚሰጡት አስተያዬትም ካለ ያክሉበትና የዛሬዉን ቆይታችንን እናጠናቅቅ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እና ወደ ባቱ የሚሄደዉን የፍጥነት መንገድ የወሰድን እንደሆነ በጣም አስደማሚ ሥራ ነው። ምናልባት መንገዱን ተከትሎ የተተከሉ ዉብ ዛፎች በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የትራፊክ ምልክቶችን የሸፈኑበት ሁኔታ አለ። ይህ አደገኛ ስለሆነ አሁኑኑ መታረም ያለበት እና ለወደፊትም ዛፎች የትራፊክ ምልክቶች ካሉበት ቀጥለዉ ወይንም ወጣ ተደርገዉ ቢተከሉ የተሻለ ነው። በምንም መልኩ የትራፊክ ምልክት ካለበት ፊትለፊት ዛፍ መተከል የለበትም፣ ሲያድግ ምልክቱን በመጋረድ አደጋም ሊያስከትል ይችላል።

ሁለተኛዉ ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እና ባቱ የሚወስደዉ መንገድ ሁለቱም በኦሮሚያ ክልል የሚገኝ ሆኖ እያለ የትራፊክ ምልክቶች ግን ጽሁፉ በኢንግሊዝኛና በአማርኛ ብቻ መጻፉ ተገቢ አይደለም። በተጨማሪነት በኦሮምኛም መጻፍ ነበረበት፣ ይህ አሁንም መታረም ያለበት ነው። በሶስት ቋንቋ መጻፉ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለዉም፣ ሕዝቡም ልማቱን የእኔ ነው እንዲል ያግዛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Amhara #oromo #Tigray

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5476

Wolaita Times

07 Feb, 18:55


በሀገር ቤት መስራት ኩራት ሲሆን ከስደት ሀገር መስራት ደግሞ ውርደት ነው!!

የሀገር ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ዜጎች ሀሳባቸውን ያለማንም ከልካይ በነፃነት መገለፅ ሲችሉ ነው። የዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ከምግብ በላይ ለሰው ልጅ የሚያስፈልግ ተፈጥሯዊ ስጦታ ነው።

ምክንያቱም ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ሁኔታ ውስጥ ተበዳይ አይኖርም፣ በዳይ ተደብቀው ከፍትህ አያመልጥም፣ መንግስት ሆነ ግለሰቦች ከህዝብ ተደብቀው በጓዳ የሚያደርጉት ምስጢር አይበዛም እንዲሁም ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ባለበት ህብረተሰቡ መብቱን ተጠቅሞ ለምን ብለው በአደባባይ ስለሚጠይቁ የፖለቲከኞች ህዝብን ከህዝብ ጋር አጋጭቶ በስልጣን የመቆየት ዕድል አይኖርም።

በአጭሩ የዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በአንድ ሀገር እንዲከበር ማድረግ ለዘላቂ ሰላም፣ ለልማት፣ ለዴሞክራሲና ተቀዳሚ ሰብዓዊ መብት መስፈን የመጀመሪያውና የመጨረሻው ምንጭ ነው። የትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ መሠረቱን በዜጎች ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ ላይ ሳያደርግ የሚያደርገው ጉዞ ለአጭር ጊዜ ቢሆን እንጂ አሸዋ ላይ እንደተሰራ ቤት የሚፈርስ ይሆናል።

መሠረትን በዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በማክበር እንዲሁም የሚዲያ ዘርፍን ከየትኛውም ተፅዕኖ በፀዳ መንገድ እንዲሰሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ በመስጠት ሰላም፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚና ፖለቲካ አካሄድ መመስረት ይቻላል።

ሀገሬ ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር እያላት የዜጎችን ሀሳብን የመግለፅ መብት ሆነ የሚዲያ ነፃነት በመንፈግ በየወቅቱ በሀሳብና በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት ብቻ በሰላማዊ ውይይት ከመፍታት ይልቅ ወደ ጦርነት ሜዳ እየገባች ለበርካታ ትውልድ የሚበቃ ልማት መስራት የሚያስችለውን ገንዘብ እያወደመችና የዜጎቹን ህይወት በከንቱ እንዲያልፍ እያደረገች የሀገሪቱ ዕድገት ከአለም ወደኃላ እንዲቀር እያደረገች ነውና ወደ ሰላማችንና ዕድገታችን መንገድ ለመጓዝ ሁላችንም እንረባረብ👐
#Pressfreedom

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መስራችና አዘጋጅ
ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ
ናይሮቢ፤ ኬኒያ

Wolaita Times

07 Feb, 06:15


ሰበር ዜና

"ዎላይታ ሶዶን ከታሪካዊና ህጋዊ ባለቤቱ ነጥሎ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ተጠሪነቱ በብዙህ-ብዝሃነቶች ለተገነባዉ ክልል ይሁን ማለት ከሕገመንግሥት ጋር የሚጣረስና የዎላይታን የሀገር ባለቤትነት መብት የሚገፍ አደገኛ የፖለቲካ ሴራ ነዉ"- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ

"መንገዱ አጭር መዳረሻው ገደል" በሚል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሪጅዮፖሊስ ከተሞች ለማደራጀት ያወጣውን አዋጅ በመቃወም የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ/ዎብን፣ የዎላይታ ሕዝብ ደሞክራሲዊ ግንባር/ዎህዴግ/ እና የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ/ዎሕነን/ የጋራ የአቋም መግለጫ አወጣ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ካቢኔ ጥር 16/2017 ዓ.ም የከተሞችን ፈርጅ ለውጥ ለማድረግ በተቀመጠበት የክልሉን የ54 ከተሞች ደረጃ ለውጥ እንዲደረግ የወሰነ ሲሆን ከነዚህ 54 ከተሞች መካከል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በቀድሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት በከተሞች የደረጃ ፍረጃ በፈርጅ አንድ ደረጃ ተመድበው የነበሩ ሶስት ከተሞችን ማለትም የዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና የዲላ ከተሞችን ወደ ሪጂዮፖሊስ ከተማ አስተዳደርነት የከተማነት የፈርጅ ለውጥ አድረጓል፡፡

አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተዋቀረ ከአንድ ዓመት በኋላ በከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተሞችን ፈርጅ ለመወሰን የወጣውን አዋጅ መነሻ በማድረግ አስጠንችያለሁ ባለው ምንም ሳይንሳዊ መስፈርት ያለሟላ ጥናት መሠረት በማድረግ እነዚህን ሶስት ከተሞች (ዎላይታ ሶዶ፣አርባምንጭ እና ዲላ) በሪጂዮፖሊስ ደረጃ እንዲፈረጁ እና በልዩ ሁኔታ እንዲያድጉ ለማድረግ ታስቦ የወጣ በተባለው “የደቡብ ኢትዮጵያ ክሌላዊ መንግሥት የሪጅዮፖሊስ ከተሞች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ” በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ለመስወሰንና ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ የፖለቲካ ውሳኔ ቢያንስ በከተሜነት፣ በከተማ ልማት ፖሊሲ እና ህጋዊ ማዕቀፍ/urbanization, urban development policy and legal framework/ በዘርፉ ዕውቀትና ልምድ ያለቸውን ምሁራንን ያገለለ የይስሙላ ውይይት ህዝቡን በማደናገር ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ/ዎብን፣ የዎላይታ ሕዝብ ደሞክራሲዊ ግንባር/ዎህዴግ/ እና የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ/ዎሕነን/ ፓርቲዎች ከሚመለከታቸው በዘርፉ ሰፊ ዕውቀትና የአለም አቀፍ ልምድ ካላቸው ምሁራን ጋር ሰፊ ምክክር እና ውይይት ግብዓት መሰረት በማድረግ ፓርቲዎች በጋራ በቀን 29/05/2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ ያወጣውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አድርሷል፡፡

1. ዎላይታ ሶዶ የዎላይታ ብሄር፤ ታሪክ፤ ባሕል፤ ኢኮኖሚና ፖለቲካ ማዕከል/እምበርት ናት፡፡ የብሄሩ ማንነት መገለጫ ብሄራዊ ቅርሱና ርስቱ ናት። የዎላይታን ሕዝብ ከዎላይታ ሶዶ እና ዎላይታ ሶዶን ከዎላይታ ሕዝብ ነጥሎ ለመግለጽ-ማሰብ ዘሬም ነገም አይቻልም፡፡

በርካታ የተለያዩ ማንነቶች፤አይዲጆሎጂዎች እና የተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች አካቶ የያዘ የክልሉ መንግስት እና መስተዳድር ምክር ቤት ስለ ዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ይዞታ የመወሰን ስልጣንና ሞራላዊ ብቃት የለዉም፡፡ ዎላይታ ሶዶን ከታሪካዊና ህጋዊ ባለቤቱ ነጥሎ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ተጠሪነቱ በብዙህ-ብዝሃነቶች ለተገነባዉ ክልል ይሁን ማለት ከኢፌዲሪ ሕገመንግሥት ጋር የሚጣረስና የዎላይታን የአገር ባለቤትነት መብት የሚገፍ አደገኛ የፖለቲካ ሴራ ነዉ።

አካሄዱ የአዳማን ከተማ ተጠሪነት ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የጎንደር ከተማ ተጠሪነት ለአማራ ብ/ክ/መ፤ የሃዋሳ ከተማ ተጠሪነት ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንደማድረግ አለመሆኑ ሊሰመር ይገባል፡፡

2. በረቂቂ አዋጁ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ም/ቤት እና ከተማዉን ወክለዉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ም/ቤት አባላት ከከተማዉ ነዋሪዎች መካከል የሚመረጡ ይሆናል የሚባለዉ /ዎላይታን እና ዎላይታ ሶዶን የዎላይታን ሕዝብ እና የዎላይታ ሶዶ ከተማን ህዝብ የመለያየት ብሎም የዎላይታን ህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን /self-rule/ መብት የሚገፍ አደገኛ የፖለቲካ ጠቅላይ እና አግላይ የኢምፔሪያል ፕሮጄክት ነዉ፡፡

በጣም አብዛኛዉ የብሄሩ ልህቃን (የፖለቲካ፤ የባህል፤ የኢኮኖሚ፤ የአካዳሚ፤ የሃይማኖት) እና ፐብሊክ ምሁራን መኖሪያቸዉ ዎላይታ ሶዶ ከተማ እንደመሆኑ እነኚህ ልህቃን እንደወትሮአቸዉ ሁሉ ህዝባቸዉን እንዳያገለግሉና እንዳይወክሉ እንደዚሁም ከከተማዉ ዉጭ ያለዉ የብሄሩ ልህቅ የአያቶቹን አጽመ ርስት (ቅርስ) የሆነችዉን ዎላይታ ሶዶ የማገልገልና የማልማት ታሪካዊ፤ ሰብአዊና ህገመንግስታዊ መብትና ነጻነቱን የሚገፍና የልዩነት ግድግዳ የሚፈጥር በጣም አደገኛ የፖለቲካ ፕሮጄክት መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ መንግስት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

3. እነዚህ ሶስቱም ከተሞች በጋራ ዕኩል ደረጃ (ፈርጅ አንድ) ደረጃ የሚገኙ የነበሩትን ብቻ አንድ ደረጃ በማሳደግ ሁሉንም ወደ ሪጂዮፖሊ የከተማ አስተዳደርነት ማሳደግ በከተሞቹ መካከል ለፈርጅ ለውጥ የተደረገውን ውድድር የይስሙላ መሆኑን እንረዳለን፣

4. ከዚህም በተጨማሪ የሪጂዮፖሊ ከተማ ላለበት አከባቢ ማዕከል ሆኖ በዙሪያው ያሉ ከተሞችን አስተሳስሮ የሚያሳድግ ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መስፈርት ስናይ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ውጪ ሌሎች ከተሞች በ20 ኪሎሜትር ራዲየስ እንኳ ሌላ የከተማ አስተዳደርም ሆነ የወረዳ ማዕከል እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ግን በ20 ኪሎሜትር ራዲየስ ብቻ እንኳን 3 የከተማ አስተዳደርና 7 የማዘጋጃ ቤት ከተሞችን አቅፋለች፡፡ ይህ እውነታ በከተማ ገቢ፣ በህዝብ ብዛት፣ በቆዳ ስፋት፣ በዕድገት ፍጥነት፣ በንግድና አገልግሎት ማዕከልነት፣ በቀጣይ የማደግ ዕድል ወዘተ ጉዳዮችም ጭምር በልዩነት የሚታይ ሆኖ ሳለ የዎላይታ ሶዶ ከተማን በዚህ ማዕቀፍ በልዩነት አለማየት እና ከላይ በተጠቀሱ መስፈርቶች በተመሳሳይ መዳኘት የፈርጅ አወጣጥ ስርዓቱን ወደ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመውሰድ የታለመ በመሆኑ አጥምቀን እንቃዎማለን።

5. በክልሉ በኩል ከዚህ ቀደም ለዎላይታ ሶዶ ከተማ የተሰጠው የከተማ ደረጃ ፍረጃ ምንም ያስገኘው ውጤት አልነበረውም፡፡ ክልሉም የፈርጅ አንድ ከተሞችን በልዩነት ለመደገፍና በሚያስመዘግቡት ውጤት ላይ ተንተርሶ የደረጃ ፍረጃ ለማከናወን የተጓዘበት ርቀት ባለመኖሩ ከተሞቹ ባሉበት ያለምንም ልዩነት የፈርጅ ለውጥ እንዲያደርጉ መደረጉ ከስድስቱ የክልሉ ማእከላት ከተሞች የዕኩልነት ውሳኔ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

6. በክልሉ ውስጥ ከዎላይታ ሶዶ የሚበልጥ ከተማ ባለመኖሩ የፈርጅ ለውጥ ይኑር ቢባል እንኳን ከዎላይታ ሶዶ የሚጀምር በመሆኑ በተለየ ሁኔታ ጠቃሚ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፣ የክልሉ መስተዳደር ሆነ የክልሉ ምክር ቤት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታም ሆነ አስተዳደር በራሳቸው የመወሰን ሉዓላዊና ህገ-መንግስታዊ ስልጣን በተጎናጸፉ የዎላይታ ብሔር እና ሌሎች የብሔረሰብ ዞኖች የውስጥ ጉዳይ በመግባት መዋቅር ቆርሶ ለሌላ መዋቅር ተጠሪ እንዲሆኑ የመወሰን ስልጣን የላቸውም፣ ኢ-ህገመንግስታዊም ነው፡፡

Wolaita Times

07 Feb, 06:15


7. ለዎላይታ ሶዶ ከተማ በርካታ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል ከሚል አዎንታዊ ዕይታና ተስፋ የተነሳ የዎላይታ ሶዶ ከተማ በሪጅዮፖሊስ ፈርጅ መካተቱን ማንም የዎላይታ አይቃወምም፡፡ ሲቃወም አይታይም፡፡ ይሁን እንጂ ዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ተጠርነቱ ለክልሉ መንግስት መሆኑና የከተማዉ ም/ቤት አባላት እና በሕዝብ ተወካዮች እና ክልል ም/ቤቶች ከተማዉን የሚወክሉ ሰዎች ከከተማዉ ነዋሪዎች መካከል የሚመረጡ ይሆናሉ ተብሎ መደንገጉ በምንም ዓይነት መስፈርት ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ብለን እናምናለን፡፡

ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ጎን እየሰፋ የነበረዉ ከተማ በሪጅዮፖሊስ ከመፈረጁ ጥቂት ወራት በፊት በዞኑ እርሻ ሰብል ምርት እና እንስሳት እርባታና ምግብ ዋስትና ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ የነበሩትን በርካታ የገጠር ቀበሌዎችን ከዳሞታ ጋሌ፤ ዳሞታ ዎይዴ፤ ሶዶ ዙሪያ፤ ቦሎሶ ሶሬ፤ ሁምቦ እና ዳሞታ ሶሬ ወረዳዎች ያቀፈዉ ዎላይታ ሶዶ በመንግስታት ትኩረት ያልተሰጠዉ ነገር ግን አራት የዎላይታ ትዉልዶች በቁጭት ተነሳስተዉ ሀብታቸዉን ገንዘባቸዉን፤ ዕዉቀታቸዉንና ክህሎታቸዉን አፍስሰዉ ያለሙትና በሚያስደንቅ ፍጥነት እየለማ የሚገኝ ከተማ ነዉ፡፡

8. የከተሞች የፈርጅ ለውጥ የከተሞች የዕድገት መለኪያ እንጂ ከከተማው ፖለቲካዊ ተጠሪነት ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ መሆኑ የዎላይታን ህዝብ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ የበላይ ባለቤትነት በማውጣት የከተማውን ተቋማት ከዞኑ አስተዳደር ይልቅ ለክልሉ የላይኛው ተቋማት በማድረግ በከተማው አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የዎላይታ ህዝብ በላቡ ባለማው ከተማ ሚና ሙሉ በሙሉ እንዳይኖረውና የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ በመሆኑ መነሻ ከከተማው የሚነሱ ይግባኞች እና ቅሬታዎች በዞኑ በኩል ስለማይታዩ ወደተበታተኑት የክልሉ የማዕከል ከተሞች ነዋሪዎችን እንዲጉላሉ የሚያደርግ፣

ለዎላይታ ዞን አጠቃላይ አመራር በዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ምንም ዕጣ ፈንታ እንዳይኖረው የሚያደርግ፣ የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች በዎላይታ ሶዶ ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ የሚገድብ የዎላይታ ህዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን በገሃድ ቀልብሶ ማዕከላዊ ጠቅላይ አሃዳዊ ስርዓት ስር እንድትሆን የሚያደርግ የየስልጣን ጥማት እና በአገሪተሀ ላለፉት 6 ዓመታት የዘለቀው አውዳሚ የእርስበርስ በጦርነት፣ ሙስና እና አላስፈላጊ ውጪ ምክንያት ክልሉ የገጠመውን የአገሪቱን እና የክልሉን በጀት እጥረት የከተሞችን መሬት ለመቸብቸብ እንዲያመች ስልጣንን ከዞኖች ነጥቆ በመውሰድ ነገ ጠያቂ የሌላችው ከተሞች የሙስና እና የጥገኛ ዋሻ የሚድረግ ነው፡፡

ስለሆነም በየትኛውም መልኩ የሚቀርብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማህበራዊ መደራደሪያ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ለክልል ተጠሪነት መፈቀድ የለበትም፡፡ የደቡብ ክልል መንግስት ከተሞችን ስልጣን እና የሪሶርስ ቀምቶ ስልጣንና ሀብት ባለቤትነት ጠቅልሎ ለክልል መንግስት በማድረግ በተለይ የዞኑ ህዝብ በከተሞች ምንም ሚና እንዳይኖር በማድረግ ከተሞችን እድገት ለማቀጨጭ እና የከተሞችን ሀብት ለመመዝበር እናም እድገታቸውን ለመቀልበስ የሚሰራው ማንኛም Power centralization and economic exploitation የእጅ አዙር ግዞትና ቅኝ አገዛዝ ስርዓት ላለፉት ሁለት /2/ ዓመታታ ተጠሪነታቸው ለክልል የሆኑትን /አስራ ሁለት/12 ዞኖችን እንኳን መምራት ያልቻለው እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከተሞችን በክልሉ ስር ለማድረግ ማሰብ ለእድገትና ለልማት ሳይሆን ለጠቅላይነት እና ለብዝበዛ ህጋዊ ማዕቀፍ ለማበጀት ነው።

ከሁሉም በላይ ከተሞችን ያለሙት የዞኖቹ ህዝቦች አርሶአደሮች፣ ተማሪዎች መንግስት ሰራተኞች እና የንግዱ ማህበረሰብ ጡረተኞች በመላው አለም የሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች ከመቀነታቸው እና ከእለት ጉርሳቸው ቀንሰው የገነቡትን ህዝብ ባለቤትነት ቀምቶ ወደ ቤት ግባ ማለት የፌደራሊዝም ትሩፋት የሆነውን በብሔር ብሔረሰቦች ደምና አጥንት ዋጋ ተከፍሎበት የመጣውን የዞን የከተሞች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ከዞን ቀምቶ ያልተማከለ ፌደራላዊ ስርዓት በመናድ በክልሉ የተማከለ ጠቅላይ አሃዳዊ አስተዳደር ስርዓት የመዘርጋት እንቅስቃሴ አስቸኳይ እንዲቆም አጥበቀን እናሳስባለን።"

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ/
#ዎብን፣ የዎላይታ ሕዝብ ደሞክራሲያዊ ግንባር/#ዎህዴግ/ እና የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ/#ዎሕነን/ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሪጅዮፖሊስ ከተሞች ለማደራጀት ያወጣውን አዋጅ በመቃወም የጋራ የአቋም መግለጫ

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Wolaita #southethiopia

Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5471

Wolaita Times

05 Feb, 15:40


"ፋኖ ከደቡብ ህዝብ እገዛ ከመጠየቁ በፊት ለብሄር ብሄረሰቦች ያለውን የንቀት አመለካከት ይቀይር" .. Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5467

Wolaita Times

05 Feb, 15:40


"አብዛኛው የደቡብ አከባቢ ህዝብ የፋኖ ዕዝ መቋቋም ይቅርና ፋኖ መኖሩንም አያውቅም"፤ "ከብሄር ብሄረሰቦች ከተወጣጡ መካላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት ከገጠሙት ታጣቂዎች ምን ህብረት አለን?!" - መልስምት

ሰሞኑን በአንዳንድ ሚዲያዎች "በደቡብ የፋኖ ዕዝ ተመስርቶ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል" በሚለው ወሬ መነሻ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በአከባቢው የተለያዩ አካላት ሀሳብ በማሰባሰብ ተከታዩን ዘገባ ሰርቷል።

"ጦርነት ችግሮችን እያባባሰ ይሄዳል ነው። መፍትሔም አያመጣም፥ በተለይም ደግሞ የእርስ በርስ ጦርነት ሲደረግ በስሜት ብዙዎች የሚገቡበት ሲጠናቀቅ የሚጸጸቱበት ነው። ሌላዉ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ አንስቶ ማስመለስ አይቻልም ለሚለዉ ያም ካልሆነ እኔ ሰላማዊ ትግል ይሻላል ባይ ነኝ።"

"የፋኖ አመራሮቹ ታዉቀዉ የሚያራምደው የትግል አላማ ታዉቆ ጥያቄዎቼ እነዚህ ናቸዉ ብሎ ዝርዝሩን ቢያስቀምጥ በጣም ጥሩ ነበር። አሁን ባለዉ ግን የተለያዩ የፋኖ አመራሮች የሚያወሩት የተለያዬ ነገር ነው። አንዱ ሕገመንግሥት የሚያከብር ነገር ይናገራል፣ አንዱ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ማፍረስ አለብን ይላል፣ አንዱ ብሔረሰቦችን ወዳጆቼ ናቸዉ ይላል፣ አንዱ ይዝታል፣ አንዱ ስለአማራ እና አማራ ብቻ ያወራል፣ አንዱ ስለኢትዮጵያ ያወራልና የራሱ ግልጽ አላማ የሌለው በደቡብ የፋኖ ዕዝ ተቋቁሟል ማለት ከቅዠት ያለፈ ፋይዳ የለውም" ብሏል።

"እኛ በተለይም ደቡብ አካባቢ ህዝብ ትምህርት ቤት ተዘግቶ፣ ጤና ተቋማት፣ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ንግድ ተቋማት ተዘግቶ እንዲሁም የህዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ቆመው በጦ'ር መሳሪያ የመገ'ዳደል ፖለቲካ በፍጹም አማራጭ መፍትሔ አድርገው የሚቀበል አይደለም። እኛ ግን የምናበረታታዉ ጦርነትን ሳይሆን ሰላማዊ ድርድርን ነው። የአማራዉ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ወንድማማች ነው። የወንድማማች መገዳደል ሊቆም ይገባል እንላለን" በሚል ምክር ለግሷል።

"በአሁኑ ሰአት በአማራ ክልል እጅግ በተካረረ ሁኔታ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ በእዉነቱ በጣም አሳዛኝ ነው። ከእርስ በርስ ጦርነት መዉጣት አለመቻላችን በጣም ያሳዝናል። ከዛ በተረፈ ይህ ጦርነት አሁኑኑ መቆም ስላለበት የተኩስ አቁም ስምምነት መደረግ አለበት ብዬ አምናለሁ። ከሁለቱም ወገን የሚያልቀዉ የኛዉ ዜጋ ነው፣ በከንቱ ተጨባጭ እመርታ ለሀገራችን የማያመጣ ጦርነት መቆም አለበት። ኢትዮጵያ ችግሯ መቼም በጦርነትና በጉልበት አይፈታም። ይባስ ብሎ ጦርነት የበለጠ ችግሩን የሚያባብስ እና ንጹሃንን የበለጠ ተጎጂ እያደረገ የሚሄድ ነው። ከሚያልቀዉ ወገናችን በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዉም ከባድ ነው።"

"የአማራ ሊህቃን በሐገር ዉስጥም በዉጪም ከስሜታዊነት ወጥተዉ መንገዳቸዉን መመርመር አለባቸው። ለአማራ ሕዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ ኃይሎች፣ አላማ እና እስትራቴጂያቸዉ የተለያዬ ነው፣ አንዱ ከተለያዩ አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት ይጥራል፤ ሌላዉ እነዛን አካላት እንደጠላት ፈርጆ ይንቀሳቀሳል።"

"በሐገሪቷ ስለሚገኙ ለተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችም ያላቸዉ አረዳድ የተለያዬ ነው። ይህ ኃይላቸዉ እንዲበታተንና በአነስተኛ ኪሳራ ምናልባትም በሰላማዊ መንገድ የሕዝቡን ጥያቄ እንዳያስመልሱ እንቅፋት ሆኗል ሰጥቶ የመቀበልን ፖለቲካ ለማካሄድ እንቅፋት ሆኗቿል። በተለይ የአማራ ሊህቃን የሕዝባችን ጥያቄ የሚሏቸዉ ነገሮች ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የተሳሰሩ መሆናቸዉንና ፖለቲካ ደግሞ በባህሪዉ ሰጥቶ መቀበልን የሚፈልግ መሆኑን አምኖ መንቀሳቀሱ ይበጃል ባይ ነኝ፣ እነሱም ቢሆን በጉልበት የሚሳካላቸዉ ነገር እንደሌላቸዉ ቢያዉቁ ጥሩ ነው።"

"ከሌሎች ብሔር ሊህቃንም ጋር ደግሞ ከመፈራረጅ ባለፈ የጋራ አጀንዳ ለመፍጠር መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፥ ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር እየበዛ የሚሄደዉን የሕዝቡንም ስቃይ ከግምት ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። ሰላም ይሻላል፣ ሁሉን አቀፍ ዉይይትና ድርድር ይሻላል።"

"በአማራ ሊህቃንም በኩል ደግሞ ለሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች እዉቅና ሰጥቶ በጋራ የመሥራትና የመታገል ክፍተት በዉስጥም በዉጭም ይታያል። የድሮ አገዛዞች ያደረሷቸዉን በደሎች መካድ አያስፈልግም፣ ስለነዛ አገዛዞች ጥብቅና መቆም አያስፈልግም፣ ይልቅ ያ ችግር ዛሬ የለምና የዛሬን ችግር በጋራ እንፈልግ የሚለዉ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል።"

"ፋኖም አንድ አደረጃጀት ፈጥሮ ወደ ድርድር ይምጣ። ከዛ ባለፈ የማምታታት አካሄዱ የትም ስለማያደርስ የመፍትሔው አካል ቢሆን ይመረጣል፣ ከዚህ በላይ የዉድመት መንገድ ላይ መቀጠል የለበትም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርድር የጋራ ነገር ከፈጠርን እንጂ፤ ማንም ማንንም ማንበርከክ አይችልም።"

"አንዳንድ የፋኖ ደጋፊዎች አሁን ያለዉን ጦር የብርሃኑ ጁላ ጦር፣ የኦሮሞ ጦር እያሉ ለማጠልሸት ይሞክራሉ፦ ይህ በፍጹም ትክክለኛ ካለመሆኑም በላይ አሰፈላጊም የሆነ አባባል አይደለም። መቼም ቢሆን መከላከያ ጠንካራ እንዲሆን ነው መፈለግ ያለብን፣ ጦሩን የሚከፋፍል መርዝ መርጨት ተገቢ አይደለም፤ መከላከያ ችግር ቢኖርበትም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ የሆነና ለሀገሪቷ ህልዉና አስፈላጊ ነው።"

"መከላከያ የበለጠ አካታች እና የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን እንፈልጋለን፣ ወንጀል የሠራ ይጠየቅ እንጂ ለመከላከያ መጥፎ በጅምላ አንመኝም። የእርስ በርስ ጦርነቶች የሀገር ጦሩን ያዳክማሉና መቆም አለባቸዉ፣ ችግራቸዉ ፖለቲካ ነዉና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋል፥ ጦሩ ላይ ከማነጣጠር በበለጠ የፖለቲካ አመራሮች ላይ ማነጣጠሩ ይጠቅማል።"

"ሌላዉ ደግሞ በተለይም ከሕገመንግስቱ ማዕቀፍ የሚወጡ ጥያቄዎች በፌደራል መንግሥትም ሆነ በፋኖ ብቻ ሊመለሱ አይችሉም፤ ሁለቱ ቢስማሙ እንኳን የሚቻልበት አግባብ የለም በሐገሪቷ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መሳተፍ አለባቸዉ ነው።"

"ጦርነት ደግሞ ወደ መፍትሄው እያቀረበን ሳይሆን እያራቀን ይሄዳል ነው። የፌደራል መንግስት የሐገሪቷን ሕገመንግሥት አክብሮ አይንቀሳቀስም ብለዉ ያኮረፉ ኃይሎች በብዛት ባሉበት ፋኖ ሕገመንግሥታዊ ሥርአቱን በሚያጠፋ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ለሁሉም ደግሞ ከጦርነት በሰላማዊ ድርድር ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀሱ ይበጃል ነው።"

"አንድ ግን አጽንኦት ሰጥቼ የምናገረዉ በኢትዮጵያዉያን መሐከል የሚደረግ ድርድር እንጂ ጦርነት አንደግፍም። በተለይ ፋኖ ከለዉጥ በኃላ የተደራጀ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከመንግስት ጎን የተሳተፈ እንዲሁም በመጀመሪያ ከነበረዉ የክልሉ መንግስት ጋር አብሮ የሚሰራ ኢ_መደበኛ የታጠቀ ቡድን የነበረ ሆኖ ሳለ አሁን ላይ "በደቡብ የፋኖ ብርጌድ ተመስርቶ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል" የሚለው ወሬ የአከባቢውን ህዝብ ስነልቦና ካለማወቅ የመነጨ ምኞት ነው፣ አብዛኛው የደቡብ አከባቢ ህዝብ የፋኖ እንቅስቃሴ ከደቡብ ህዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ጋር የማይገናኝ በመሆኑ የፋኖ ዕዝ መቋቋሙ ይቅርና ፋኖ መኖሩንም አያውቅም" ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተወጣጡ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት ከገጠሙት ምን ህብረት አለንና!?" ብሏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Amara #Fano #southethiopia

Wolaita Times

04 Feb, 18:03


የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተማፅነው

"የትግራይ ሕዝብ ካለፈው ቁስሉ ሳያገግም አሁንም በሌላ ጦርነት ስጋትና ሽብር ላይ ነው፤ የትግራይ ልሂቃን ልዩነታችሁን ፍቱ፤ እንዳለመታደል ሆኖ ግን ትግራይ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ባጋጠሙ ቅሬታዎች ምክንያት የትግራይ መሬት የጦርነት ምድር ሆኖ ቆይቷል፣ ከፌደራል መንግሥት እና ሌሎች ሐይሎች ጋር ያላችሁን ልዩነት በዴሞክራሲያዊ እና ሕገመንግሥታዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ሁኑ፥ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር በሕግ አግባብ እንድትነጋገሩም ጥሪ አቀርባለሁ"

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
በትናንትናው ዕለት ለትግራይ ሕዝብ በተለይም ለትግራይ ልሂቃን በትግረኛ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Tigray #TPLF

Wolaita Times

04 Feb, 13:02


የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ጋር ተወያዩ

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ጋር በፍሪታውን በሚገኘው ቤተመንግሥት ላይ ባደረጉት ውይይት የአገሪቱን የምግብ ዋስትና፣ የስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን የሚተገብር ፕሮግራም "ፊድ ሳሎኔ" (Feed Salone) ተነሳሽነት ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

አቶ ኃይለማርያም እንደገለጹት፣ "AGRA ከአፍሪካ መንግስታት ጋር በመተባበር የግብርና ልማትን ለማጎልበት እና የህዝብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ለዘርፉ ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ ቁርጠኛ ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም ሴራሊዮን በግብርና ምርታማነት ማሳደግ፣ የግብርና ሜካናይዝሽን አጠቃቀምን ማስፋፋት እና የምርት ሰንሰለቶችን በማጠናከር ራስን በራስ ለመቻል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለሌሎች ምሳሌያዊ እንደሆነም አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ጁሊየስ በበኩላቸው፣ "የ'ፊድ ሳሎኔ' ተነሳሽነት ለአገራችን ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው። በግብርና ውስጥ ያለውን ዘዴ በማዘመን፣ ለወጣቶች ስራ ለመፍጠር እና የገቢ ምንጮችን ያሳድጋል" ብለዋል።

የአገሪቱ መንግስት በግብርና ላይ ያተኮረው ይህ ስትራቴጂ የተለያዩ የልማት አጋሮችን፣ የቴክኖሎጂ አቅርቦቶችን እና የገንዘብ መድረኮችን በማስተባበር አገር አቀፍ የሆነ የምግብ ነፃነት እንዲዘረጋ እየተሰራ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማራመድ የሚደረጉ ስራዎችን የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #SierraLeone

Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5460

Wolaita Times

03 Feb, 14:55


በዎላይታ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ አርሶአደሮች ራሳቸውን እንዲያጠፋ ለምን?

አርሶአደሮች ለዘመናት አርሰው ከሚበሉበት ለም መሬታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ቤተሰቦቻቸው በመበተኑና ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ተስፋ ቆርጠው እስካሁን ከ4 በላይ አርሶአደሮች ራሳቸውን እስከማጥፋት መድረሱ ተገለፀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ አረካ ከተማ አቅራቢያ ሱማሞ ሜዳ ላይ ሊገነባ የታቀደው አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ መክፈል ባለመፈለጉ የግንባታ ሂደቱ ከመስተጓጎሉ በተጨማሪ የመሬታቸው የተነሱ አርሶአደሮች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው አሳሳቢ ስለመሆኑም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ከቦታው ለሚነሱ አርሶአደሮች ለመስጠት የተገመተው የካሳ ክፊያ መጠን በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ቅሬታ በሚያቀርቡ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ የግድያ፣ የእስርና የማስፈራራት ጥቃት እየደረሰባቸው እንዲሁም ለዘመናት አርሰው ከሚበሉበት ይዞታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በመበተኑና ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ተስፋ ቆርጠው እስካሁን ከ4 በላይ አርሶአደሮች ራሳቸውን እስከማጥፋት እንዳደረሱ በመጥቀስ ስለሆነ የፌደራል መንግስት ጠልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።

ከአስር ወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ለመንንባት አቅዶ የቦታ መረጣ በማድረግ በቅርቡ ወደ ስራ ለመግባት በፕላን መሰረት በይዞታ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውም ንብረቶች አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ በመፈፀም እና ከቦታው ለሚነሱ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተለዋጭ ቦታ በመስጠት ቦታውን ከይዞታ ነፃ ተደርጎ የይዞታ ማረጋገጫ በአስቸኳይ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሶ ለክልሉ በፃፉት ደብዳቤ ማሳሰባቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ሆኖም ግን እንደተባለውም ተቋራጮቹ ክልሉን "በአንድ አመት አጠናቀን እናስረክባለን ቦታውን ከይገባኛል ነፃ አድርጉልኝ" ካሉ 9 ወር አልፏል፤ ከክልሉ እንዲሸፈን የተጠየቀው 130 ሚሊየን ብር ብቻ የካሳ ገንዘብ ቢሆንም ትኩረት ተነፍጎ ክልሉ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ በጊዜው መክፈል ባለመፈለጉ ሂደቱ እንዲስተጓጎል ማድረጉ በአከባቢው ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠረ ስለመሆኑ ተገልጿል።

የግንባታ ሂደቱን ቶሎ ለማስጀመር የፕሮጀክቱ ስራ በሚከናወንበት አከባቢ ንብረትና ቤት ያላቸው አርሶአደሮችን ለማስነሳት ኮሚቴው ተዋቅሮ ስራ ውስጥ የገባ ቢሆንም ሆን ተብሎ በየትኛውም ቦታ ታይቶ የማያውቅ የአርሶአደሩን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ግምት ከ40ሺህ-140ሺህ ብር በሚገመትበት ሁኔታ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙትን መግደል፣ ማሰር እንዲሁም ከፍተኛ ማስፈራሪያ እያደረሱ ስለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አርሶአደር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

በርካታ የአከባቢው አርሶአደሮች ለዘመናት አርሶ ከሚበሉበት መሬታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ቤተሰቦቻቸው በመበተኑ ተስፋ በመቁረጥ እስካሁን ከአራት በላይ ራሳቸውን እስከማ'ጥፋት መድረሱንም አክለዋል።

ከሁለት አመት በፊት ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው አየር ማረፊያ ግንባታ እንዲቋረጥ ተደርገው በአንድ አመት ለማጠናቀቅ የተጀመረው ይሄው አዲሱ የሱማሞ አየር ማረፊያ ግንባታም በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ ክልሉ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር የካሳ ክፊያ ውዝግብ በመፍጠር እንዲሁም ትኩረት በመንፈግ የካሳ ክፊያ በመከልከል እንዲስተጓጎል እያደረገ ስለመሆኑ አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምሁር ለWT ጠቁመዋል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው የነበረ ሲሆን የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በ1999 የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉንም ምሁሩ ገልጸዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

ተጨማሪ ያንብቡ 👇https://wolaitatimes.com/?p=5455

Wolaita Times

02 Feb, 16:14


ታሪካዊ ለጠቅላላ እውቀት!

የኢትዮጵያ ዘውዳዊ አገዛዝ በመጣል ሀገሪቱን ለ 17 ዓመታት ያህል መርተው የነበሩት ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በ1937 በዎላይታ መወለዳቸውን ታዋቂው የአለምአቀፉ ሚዲያ ቢቢሲ ከ18 ዓመታት በፊት በሰራው ዝርዝር ዘገባው አመላክቷል።
የሙሉ ዘገባው Link ከታች በአስተያየት መስጫ ተቀምጧል።

በተጨማሪም አቡነ ጴጥሮስ (አላምቦ) በዎላይታ አውራጃ በኮይሻ ወረዳ በዋጪጋ መንደር የተወለዱ ቢሆንም አንዳንዶቹ ከሌላ ብሄር እንደወጡ በማስመሰል ለመፃፍ ይከጅላሉ በሚል ከፍተኛ ቅሬታ ይቀርብበታል።

ለመሆኑ በኢትዮጵያ ለምንድነው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች የወጡበት ብሄር እና አከባቢ ላይ የይገባኛል ሺምያ እና ክህደት የሚበዛው ይላሉ ?

https://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/6171927.stm?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR2gZ0KS0bzRD1lXIR6hjC312JpLpegY73xDFhrNJhQXol5HVJ5QLdTIe0U_aem_BpyrATF9S-6e8kCyoSquNA

Wolaita Times

02 Feb, 14:19


በየትኛውም መልኩ የሚቀርብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማህበራዊ መደራደሪያ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ለክልል ተጠሪነት አንጻር በፍጹም፣ በፍጹም ልዩንት እንዲያመጣ መፈቀድ የለበትም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #WolaitaSodo #Dilla #Arbaminch

ተጨማሪ በኦፊሼል ዌብሳይታችን ያንብቡ👇
https://wolaitatimes.com/?p=5444

Wolaita Times

02 Feb, 14:19


የዎላይታ ሶዶ ሪጂዮፖሊትትና የክልሉ ተጠርነት መዘዝ

የሪጂዮፖሊት ከተማ አደረጃጀትና የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

በዘርፉ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ልዩ ጥንቅር- ክፍል ሁለት

ውድ ተከታታዮች በጉዳዩ ላይ ባለፈው ቀን ባቀረብነው ክፍል አንድ ላአስተዳደራዊ አሉታዊ ጉዳዮች፣ ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይ፣ የክልሉ ፈርጅ አንድ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ? በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ማቅረባችን ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት በቀጠለው ክፍል ላይ ፖለቲካዊ አሉታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ (የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ፣ ኢኮኖሚዊ አሉታዊ ጉዳዮችን፤ ህጋዊ አሉታዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮች እንደሚከተለው ዝርዝር ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል።

ፖለቲካዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

👉 ለዎላይታ ዞን አጠቃላይ አመራር በዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ምንም ዕጣ ፈንታ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡ ይልቁንም የከተማው ዕጣ ፈንታ ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣቱ አመራሮች ለሚመሩት የክልሉ ቢሮዎች ይሠጠዋል፡፡

👉 የዎላይታ ዞን እና የዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገናኙበትን አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ገመድ ዳግም እንዳይገናኙ አድርጎ ይበጥሰዋል፡፡

👉 ለክልሉ አመራር ታማኝ የሆኑና ዎላይታ ዞን አመራር የተከፉ አልያም ስልጣን ፈላጊና ስልጣን ያጡ አካላትን ክልሉ መጠቀሚያ በማድረግ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ እንዲሾም በማድረግ በብሄሩ ዞንና በዎላይታ ሶዶ ከተማ አመራር መካከል ልዩነትና ተቃርኖ በመፍጠር የብሄሩን አንድነት እስከ ወዲያኛው ይበትነዋል።

👉 የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከተለያየ መዋቅር የሚሰየሙ በመሆናቸው ለየዞናቸው መዋቅራዊ ፍላጎት የከተማውን አመራር ሊጠቀሙበት መቻላቸው በክልሉ አመራር የፍላጎት ልዩነት መነሻ የከተማውን አመራር አንድነት ይሸረሽርና የአመራር ስርዓቱን ይበትነዋለወ፡፡ ይህም ለከፍተኛ ጣልቃ ገብነት በር ይከፍታል።

👉 የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች በዎላይታ ሶዶ ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ (ሹመት ቀርቶ) ያርቀዋል።

👉 የዎላይታ ዞን አስተዳደር የብሄሩ መሪ (የዎላይታ ህዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚያስፈጽም መዋቅር) ሆኖ ሳለ የዎላይታ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል በሆነችው እና በመላው ዎላይታውያን የለማችው ከተማ ላይ የመወሰን ምንም ዓይነት ዕጣ ፈንታ አይኖረውም፡፡

👉 አሁን ባለው ነባራዊ ሀገራዊ ሁኔታ የፌዴራል ከተሞች ተብለው ከተለዩ ሁለት ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ውጪ የብሄር ከተሞች ሆነው ለሌሎች የአስተዳደር እርከኖች ተላልፈው የተሰጡ ከተሞች አለመኖራቸው ( አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ሽሬ፣ ሀዋሳ ተጠሪነታቸው ለክልል ይሁን እንጂ ከተሞቹም ክልሉም የአንድ ብሄር መሆናቸው )፤

👉 የክልሉ መንግስት የወላይታ ሶዶ ከተማ በዋናነት በነዋሪዎቿ ጥረትና ድጋፍ ያደገች መሆኗ ይታወቃል፡፡ የክልሉ መንግስት የዎላይታ ሶዶ ከተማን ከብሄሩ ነጥሎ የመውሰድና የማስተዳደር ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት የብሄሩን አስተዳደርና የዞኑን ምክር ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ መሄዱ ልዩ አሻጥር ያለበት መሆኑ ( ምንም እንኳ እነዚህ አካላት ከተማዋን ከብሄሩ ቆርጠው ለሌላ አካል የማስተላለፍ ስልጣን ባይኖራቸውም)፤

👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉዳ የሁሉም የዎላይታ መዋቅሮች እና ህዝብ ጉዳይ ሆኖ ሳለ የተቀሩት 22 መዋቅሮችም ሆነ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም አጠቃላይ የዎላይታ ህዝብ እንዲያውቅ አለመደረጉ፤

ህጋዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

👉 በኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 የተቀመጠው የብሄር ብሄረሰቦችን ህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብትን የሚጻረር በመሆኑ፤

👉 የብሄር ብሄረሰቦችን ህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብት ብሄሩ በሚኖርበት ጂኦግራፊያዊ ድንበር ውስጥ የሚተገበር መሆኑና የዎላይታ ሶዶ ከተማ የዎላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር የጂኦግራፊ ወሰን ውጥ የምትገኝ በመሆኗ፤

👉 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደረጃጀት ( ማዕከላዊ ኢቲዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ ክልሎችን ይጨምራል ) ዞኖች ከሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች ማለትም ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ ወዘተ አንጻር የተለየ አደረጃጀት ያለውና በዞን ደረጃ ህግ አውጪ ክንፍ ያላቸው የብሄረሰብ ዞን መሆናቸው፤

👉 በዚህም የዎላይታ ዞን በዞን ደረጃ መንግስት ያለው የብሄረሰብ ዞን ( ሶስቱንም የመንግስት አካላትን ይዞ) እንጂ እንደ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል ዞኖች በዞን የአስተዳደር ዕርከን የሚመራ አለመሆኑ ( በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ዞኖች ዞኖች አስተዳደር የተሰየመላቸው የአስተዳደር ዕርከኖች እንጂ የህግ አውጪው ምክር ቤት የሌላቸው መሆኑን ልብ ይሏል)፤

👉 ከተማው ለክልል ተጠሪ እስከሆነ ድረስ የብሄሩን ፍላጎት ብቻ የሚከተል ሳይሆን በረጅም ጊዜ የክልሉና የሌሎች ነዋሪዎች ፍላጎት በሚል ሰበብ ከተማዋን ከብሄሩ እጅ እና ክትትል ለማውጣት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።

ኢኮኖሚዊ አሉታዊ ጉዳዮችስ?

👉 የከተሞች ፈርጅ የከተሞች የዕድገት ደረጃ መለኪያ እንጂ የከተሞች ተጠሪነት መወሰኛ አይደለም፡፡ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ እጅግ የሚበልጥ ዕድገት ላይ ያሉ ከተሞችም ጭምር ( አዋሳ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ ወዘተ) ከብሄር ተጠሪነት ባልወጡበት ክልል በሚል ካባ ብቻ ብሄሩ ብቻ ለማይመራው መዋቅር ተጠሪ ማድረግ ከተማዋን የመዋጥ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የከተሞች የእድገት ደረጃን በፖለቲካ ተጠሪነት ሰበብ ለመቸንከር የታቀደ ዓላማ ነው፤

👉 የክልሉ መንግስት ከተደራጀ ጀምሮ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ የመጣን ዕድል ከመቀማት ውጪ ለከተማው ያበረከተው አንዳች ልማት ስለሌለ ለከተማው እድገት የሚጨነቅ አይደለም፡፡ እንዲሁም ወደፊት ከተማው አቅዶ የሚሰራቸውን የልማት ፕሮጀክቶች መረጣ እና አካሄድ እንዲሁም ትግበራ ላይ በቀጥታ ጣልቃ እየገባ እንዲያሰናክል ዕድል ይሰጠዋል፤

👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ በልዩ ፍጥነት ካደጉ የኢትዮጵያ ከተሞች ( በተለይም ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት አመታት ) ተርታ የተሰለፈችው በብሄሩ እና ነዋሪ ህዝቦች ድጋፍ፣ መዋጮ እና ተሳትፎ እንዲሁም የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ድጋፍ ሆኖ ሳለ በከተማው እድገት ውስጥ እዚህ ግባ የማይባልና ብሄሩንም ጭምር ከፖለቲካ ስልጣኑ የሚገፋው የክልል መዋቅር የከተማውን ተጠሪነት ለክል ላድርገው ብሎ ለመወሰን መሄድ ለብሄሩ ይሁኝታ ያለውን ንቀት ማሳያ ነው፤

👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ ገቢ የሚተዳደር ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዎላይታ ዞን ዓመታዊ የበጀት ቀመር የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎችን የሚያካትትና ዞኑ በከተማው ነዋሪዎች ስም ጭምር የሚያገኘውን በጀት ከተማው በራሱ በጀት ስለሚተዳደር ለቀሪ ወረዳዎች በማከፋፈል ዞኑ ያለበትን የበጀት ጉድለት ይመራበታል፤

👉 ይሁን እንጂ አሁን በተያዘው ከተማዋን ለክልሉ ተጠሪ የማድረግ ሴራ በከተማው ህዝብ ቁጥር በጀት ከዞኑ ይቀነስና ከተማው ደግሞ ራሱን በራሱ ስለሚያስተዳድር ለክልሉ ፈሰስ እንዲደረግ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻውን ከወላይታ ዞን በጀት ብዙ መቶ ሚሊዮን ብሮች እንዲቀነሱ ያደርጋል፤

👉 የከተማው ሁለንተናዊ ዕድገትና እንቅስቃሴ ከወላይታ ብሄር ፍላጎትና ዕቅድ ውጪ የሚመራ ይሆናል።

ልዩ ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይስ ?

Wolaita Times

31 Jan, 15:42


የሪጂዮፖሊት ከተማ አደረጃጀትና የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

በዘርፉ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ልዩ ጥንቅር- ክፍል አንድ

መግቢያ

ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ፖሊቲካዊ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ የሚያቀርቡ እንደመሆናቸው በከተሞች ይህንን አገልግሎት የሚፈልግ ነዋሪ በተፈጥሮ እድገትን፤ ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረገው ስደት፤ በከተሞች ወሰን መስፋፋት እንዲሁም ከሌሎች ከተሞች የሚመጡ ነዋሪዎችን በመጨመር በህዝብ ብዛታቸው ላይ ተደማሪ ለውጦችን እያስመዘገቡ መሄዳቸው እይቀርም፡፡

የከተሞች የህዝብ ብዛት መጨመር ነባራዊ እውነታ ሆኖ ነገር ግን ወደ ከተሞች የሚካለለው ወይም የሚገባው ህዝብ ቁጥር የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን፤ የስራ ዕድሎችን፤ የአገልግሎት አሠጣጦችንና የዘመነ ህይወትን ፍለጋ የሚመጣውን ነዋሪ ፍላጎት ያማከለ የከተሞች ዕድገት የማይኖር ከሆነ ከተሞች ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ መሆናቸው ይቀርና የተፋፈጉ እና በነዋሪዎቻቸው የማይወደዱ ስለሚሆኑ ተጨማሪ ኃይል መሳብ ቀርቶ ያለውንም ማስቀጠል ስለ ሚያስቸግራቸው ማርጀት ይጀምራሉ፡፡

ይህንን የከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የከተሞችን ዕድገት ሁለንተናዊ ጤናማነት ማረጋገጥን የነዋሪዎችን የዚህ ዕድገት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከተሞችን ከሚመሩ አመራሮችና ከተሞችን ከሚመሩ በየደረጃው ካሉ ተቋማት ይጠበቃል፡፡

ለዚህ ግብ አፈጻጸም ይረዳ ዘንድ በየወቅቱ የከተሞችን ደረጃ እየፈተሹ በሚደረግላቸው ምዘና መነሻ በሚያስመዘግቡት ውጤት ከተሞች ደረጃ ይወጣላቸውና የከተማነት ፍርጃቸውን ባለበት እንዲያስጠብቁ፤ እንዲያሳድጉና ወደ ኋል እንዲያፈገፍጉ ይደረጋል፡፡

በክልላችንም ከተሞች በተደረገላቸው ጥናት መሠረት የፈርጅ ለውጥ ያደረጉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ ዓለማ ብቻ ሲባል ቀድሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በከተሞች የደረጃ ፍረጃ በፈርጅ አንድ ደረጃ ተመድበው የነበሩ የሶስት ከተሞችን ማለትም የዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና የዲላ ከተሞችን ወደ ሪጂዮፖሊት ከተማ አስተዳደርነት ያደረጉትን የከተማነት የፈርጅ ለውጥ መነሻ በማድረግ የዎላይታ ሶዶ ከተማን የከተማነት ፈርጅ ለውጥ ምንነት፣ ጠቀሜታ እና ጉዳት በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከዘርፉ ባለሙያዎች ያገኘውን ተጨባጭ እውነታዎችን እንደሚከተለው እንዳስሳለን፡፡

የክልሉ ፈርጅ አንድ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

አሁን በክልሉ በሪጂዮፖሊት ከተማ አስተዳደርነት የታጩት ከላይ የተገለጹ ሶስት ከተሞች ቀድመው ፈርጅ አንድ የከተማ አስተዳደር ከተሞች ተብለው የሚጠሩ የነበሩ ናቸው፡፡ አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተዋቀረ ከአንድ ዓመት በኋላ በከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተሞችን ፈርጅ ለመወሰን ባወጣው አዋጅ መሠረት ባጠናው የዳሰሳ ጥናት መሠረት እነዚህን ሶስት ከተሞች ( ዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ) በሪጂዮፖሊትነት ደረጃ እንዲፈረጁ እና በልዩ ሁኔታ እንዲያድጉ ለማድረግ በሚል ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ለትችት በማቅረብ ለክልሉ ምክር ቤት ለውሳኔ ለማቅረብ ዕቅድ ይዟል፡፡

ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይ ምንድነው ?

👉 እነዚህ ሶስቱም ከተሞች በጋራ ዕኩል ደረጃ (ፈርጅ አንድ) ደረጃ የሚገኙ የነበሩትን ብቻ አንድ ደረጃ በማሳደግ ሁሉንም ወደ ሪጂዮፖሊት የከተማ አስተዳደርነት ማሳደግ በከተሞቹ መካከል ለፈርጅ ለውጥ የተደረገውን ውድድር የይስሙላ ያደርገዋል፡፡

👉 ከዚህም በተጨማሪ የሪጂዮፖሊ ከተማ ላለበት አከባቢ ማዕከል ሆኖ በዙሪያው ያሉ ከተሞችን አስተሳስሮ የሚያሳድግ ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መስፈርት ስናይ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ውጪ ሌሎች ከተሞች በ20 ኪሎሜትር ራዲየስ እንኳ ሌላ የከተማ አስተዳደርም ሆነ የወረዳ ማዕከል እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ግን በ20 ኪሎ ሜትር ራዲየስ እንኳ ብቻ እንኳ 3 የከተማ አስተዳደርና 7 የማዘጋጃ ቤት ከተሞችን አቅፋለች፡፡

👉 ይህ እውነታ በከተማ ገቢ፣ በህዝብ ብዛት፣ በቆዳ ስፋት፣ በዕድገት ፍጥነት፣ በንግድና አገልግሎት ማዕከልነት፣ በቀጣይ የማደግ ዕድል ወዘተ ጉዳዮችም ጭምር በልዩነት የሚታይ ሆኖ ሳለ የዎላይታ ሶዶ ከተማን በዚህ ማዕቀፍ በልዩነት አለማየት እና ከላይ በተጠቀሱ መስፈርቶች በተመሳሳይ መዳኘት የፈርጅ አወጣጥ ስርዓቱን ወደ ፖለቲካዊ ውሳኔ የጎተተው ይመስላል፡፡

👉 በክልሉ በኩል ከዚህ ቀደም ለዎላይታ ሶዶ ከተማ የተሰጠው የከተማ ደረጃ ፍረጃ ምንም ያስገኘው ውጤት አልነበረውም፡፡ ክልሉም የፈርጅ አንድ ከተሞችን በልዩነት ለመደገፍና በሚየስመዘግቡት ውጤት ላይ ተንተርሶ የደረጃ ፍረጃ ለማከናወን የተጓዘበት ርቀት ባለመኖሬ ከተሞቹ ባሉበት ያለምንም ልዩነት የፈርጅ ለውጥ እንዲያደርጉ መደረጉ የስድስቱ የክልሉ ማዕከላት ከተሞች የዕኩልነት ውሳኔ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡

👉 በክልሉ ውስጥ ከዎላይታ ሶዶ የሚበልጥ ከተማ ባለመኖሩ የፈርጅ ለውጥ ይኑር ቢባል እንኳን ከዎላይታ ሶዶ የሚጀምር በመሆኑ በተለየ ሁኔታ ጠቃሚ አልያም ጎጂ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡

የዎላይታ ሶዶ ከተማ የፈርጅ ለውጥ ሂደት በአዎንታዊ እና በአሉታዊ እይታ፦ በአዋጁ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 3 ተራ ቁጥር 2 ላይ የተቀመጠው የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ እንመልከታቸው።

አስተዳደራዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

👉 የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ መሆኑ የዎላይታን ህዝብ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ የበላይ ባለቤትነት በማውጣት የከተማውን ተቋማት ከዞኑ አስተዳደር ይልቅ ለክልሉ የላይኛው ተቋማት በማድረግ በከተማው አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የዎላይታ ህዝብን ሚና ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋው ይሆናል።

👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ በቅርቡ በመስፋት ያካለላቸው 16 ቀበሌያት የዎላይታ ሶዶ ከተማን የወደፊት ዕድገት ያማከሉ ሆነው ሳለ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታነት የቀረቡ ያደርጋቸዋል።

👉 የከተሞች የፈርጅ ለውጥ የከተሞች የዕድገት መለኪያ እንጂ ከከተማው ፖለቲካዊ ተጠሪነት ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ ከተማዋ ባትወዳደርም በክልሉ ውስጥ በሁሉም መስፈርት የሚበልጣት ከተማ በሌለበት ተወዳድራ እንዳለፈች በማስመሠል የውድድሩን ውጤት በፖለቲካዊ ተጠሪነት ማባዛት ተገቢነት የሌለው አሠራር ነው።

👉 የኢትዮጵያ ከተሞች ዕድገት የከተሞቹ ነባራዊ ሁኔታ የፈጠረው ብቻ ሳይሆን የከተማው አካል የሆኑ ብሄሮች ሚናም ጭምር የታከለበት መሆኑ

👉 የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ በመሆኑ መነሻ ከከተማው የሚነሱ ይግባኞች እና ቅሬታዎች በዞኑ በኩል ስለማይታዩ ወደተበታተኑት ይክልሉ የማዕከል ከተሞች ነዋሪዎች እንዲጉላሉ ያደርጋል።

👉 ውሳኔዎች ቅሬታ ያለባቸው የብሄሩ ጥያቄዎች በሙሉ ወትሮም ስለ ብሄሩ ዕድገትና ለውጥ ግድ በማይላቸው የክልል መዋቅር አመራሮች እና ባለሙያዎች እጅ እንዲወድቅ ያደርጋል።

ውድ የሚዲያችን ወዳጆችና ተከታዮች በዚሁ ጉዳይ ላይ ቀጣዩንና ክፍል ሁለት ላይ ፖለቲካዊ አሉታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ (የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ (ሹመት ቀርቶ)፣ ኢኮኖሚዊ አሉታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ፤ ህጋዊ አሉታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ እንዲሁም ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮችን እናቀርባለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Wolaita Times

31 Jan, 15:42


#Ethiopia #southethiopia #WolaitaSodo #Dilla #Arbaminch

ተጨማሪ በኦፊሼል ዌብሳይታችን ያንብቡ 👇https://wolaitatimes.com/?p=5437

Wolaita Times

29 Jan, 17:43


የለውጡ ባለቤት የነበረውን ደቡብን የገፋው ኦሮ-ማራ አሁን የትነው ?

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር👇

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በቅርቡ በአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ከኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ጋር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ እና አቶ ዛዲግ አብርሃ ወደ አራት ሰዓት ገደማ የዘለቀ ቃለምልልስ ማድረጋቸዉ ይታወሳል። በቅድሚያ ስለ ቃለምልልሱ ምን አስተያዬት አልዎት ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ ብልጽግና ፓርቲ በማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ የተወሰደበትን ብልጫ ለመገዳደር ሪስክ ወስዶ ባልተለመደ አኳኃን በቁርጠኝነት መወሰኑ የሚደነቅ ነው... [ተከታታይ ምላሽ በሙሉ ተካትቷል👇

የተነሱ ዋና ዋና የውይይት ነጥቦች፦

👉 የብልጽግና ፓርቲ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው አጀንዳ፣
👉 የደቡብ ሕዝብ በፌደራል አስተዳደር ውስጥ ያለው ውክልና፣
👉 የሱማሌ ክልል ፖለቲካዊ ቁመና፣ የሕገመንግስታዊ አሰራር ጉዳዮች እና ሌሎች ጠቃሚ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተካቶበታል።

ሙሉውን ቃለመጠየቅ በኦፊሼል ዌብሳይታችን ያንብቡ👇https://wolaitatimes.com/?p=5433

Wolaita Times

29 Jan, 16:06


በጎፋ እርዳታ እንዳልደረሰ የተናገሩ ታሰሩ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ 627 አባወራዎች በቂ ሰብአዊ ድጋፍ አለመድረሱን ለብዙኅን መገናኛ የገለጹ ስምነት ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ቤተሰቦቻቸው እና የወረዳው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል። ከወረዳው እና ዞን ባለሥልጣናት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

https://youtu.be/ZWYnA6m0FSg?si=u2RxdUo_FHHWzcgt

Wolaita Times

29 Jan, 13:47


ከቀድሞ ደቡብ ክልል ጀምሮ ተሰራጭቶ የነበረው የወጣቶች ፈንድ የት ነው?

ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ በመታደግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቆመ!

ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበው የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ በቀድሞ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በአሁኑ ኦሞ ባንክ ገቢ ተደርጎ የተሰራጨው ሀብት ኦሞ ባንክ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ገንዘቡ ያለበት ሁኔታ ግልጽ አይደለም፡፡

ሀብቱ በአሰራሩ መሰረት ለስራ ዕድል ፈጠራ በግልጸኝነት እየዋለ እንዳይደለ ለሚድያው የቀረበው መረጃ ያሳያል፡፡

ሀብቱ በዋናነት በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የስራ ዕድል ፈጠራ ተቋም እንኳን ግልጽ መረጃ ኖሮት በክልሉ በሁሉም አከባቢ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥሩ እየጨመረ ላለው ስራ አጥ ወጣቶች በግልጸኝነት ማሰራጨት እንዳልቻለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በተለያዩት ጊዜያት ለተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ የተመደቡ ሀብቶች በጣም ከፍተኛ ብሆኑም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር ያሏቸዉ አስተዋጽኦ ስመዘን በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ከዓላማዉ ዉጭ የግለሰቦች ሀብት ምንጭ እንደሆኑ የዉስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል፡፡

ለአብነት በተለያዩ ጊዜያት ከመንግስት የተመደቡ የሀብት መጠኖች፡-

•  ከቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ለቀድሞ የገጠር ወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ከ500ሚሊዮን ብር በላይ በ2005 ዓ.ም የተመደበ፤
•  ከፌደራል መንግስት ለቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል 1.88 ቢሊዮን ብር ከ2009 ጀምሮ እስከ 2011 የተመደበ ለኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ የተላለፈ፤

• የቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል በመደበኛነት በየዓመቱ ከ100 ሚሊዮን እስከ 200 ሚሊዮን ብር ሲመደብ የነበረው፤
• በየዓመቱ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳዎች፣ ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች ለኦሞ ባንክ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተብሎ በቀጥታ የተላለፈ ለጊዜው ግምቱ የማይታወቅ ሀብት ይጠቀሳል፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት ሀብቶች መካከል የቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወደ ባንክ ደረጃ እንዲያድግ ስወስን መነሻ ካፒታል እንዲሆንለት 700 ሚሊዮን መወሰኑን ጭምር መሆኑን የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡

ከዚህ ውጪ በየደረጃው የተመደበውና ለኦሞ ተቋም የተላለፈው ሀብት ያለበት ደረጃ እንዲታወቅ እንደማይፈለግ የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ሀብቱን በአሁን ሰዓት እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ላለው ስራ አጥ ወጣቶች ለማሰራጨት ካለመቻሉም በላይ ገንዘቡ ለምዝበራና ለብክነት የተጋለጠበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡

ስለሆነም በቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ስር የነበሩ በአራቱም ክልሎች ውስጥ የሚገኙ የሚመለከታቸዉ አካላት በየአከባቢያቸው የተመደበውን የተዘዋዋሪ ብድር ገንዘብ ያለበትን ሁኔታ በመከታተልና በማረጋገጥ በዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ (በ10%) የብድር ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸዉ ተጠቁሟል፡፡

በጣም የሚያሳስዝነው ይህ ሀብት ኮሚሽን እየተወሰደ ለባለሀብቱ እና በአመራር ኔትወርክ ከአሰራር እና ከአግባብ ውጪ በብድር እየቀረበ እንደሚገኝ በቀረበዉ ጥቆማ ለማወቅ መቻሉ ነው፡፡

በተቋሙ ችግሩ ከተስተዋለ የቆየ ብሆንም በባለፉት አራት ዓመታት የግልጸኝነት ችግር እንዳይቀረፍ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ሚና የጎላ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።

የኦሞ ባንክ ቦርድ አባላትም ቢሆን ድርግቱን አርሞ የወጣቱን ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ይልቅ ወቅቷ መሻጋገሪያ ወቅት መሆኑዋን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመዉሰድ አይቶ እንዳለዬ፤ እያወቀም እንደማያዉቅ ሆኖ በመንቀሳቀስ ሀብቱ ከፍ ያለ በመሆኑ እስከ ቦርድ ሰብሳቢዉ ጭምር የግሉን ጥቅም ሊያስጠብቅ የምችል መንገድ ብቻ በመምረጥ ለማሳበብ ወቅቱን ለመጠቀም ወስኖ ቴክኒካል አመቻቾች ቡድኑ ጋር በመስማማት ከመስራት ዉጪ ከተሰጠዉ ኃላፊነት ከፍተኘነት አንፃር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዳልተወጣ የመረጃው ምንጫችን ያስረዳል።

በመሆኑም የፌደራል መንግስትና የሚመለከተዉ አካላት በተለያዩ ጊዜያት ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ያለበትን ደረጃ በማጣራት እዉነቱን በመለየት ተገብዉን የማስተካከያ እርምጃ በመዉሰድ ለህዝብ ይፋ እንድያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የብድሩ ተጠቃሚ መሆን የነበረበት ከነባሩ ደቡብ ክልል የወጡ የአሁኑ የአራቱ ክልሎች ወጣቶች ለወጣቱ ካለው ፋይዳ አንጻር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በየአካባቢው ከሚመለከተው ከመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፍትሀዊ ተጠቃሚነታችሁን እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።

ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ በመታደግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሊሠራ ይገባል!!!

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Omobank

ለመሆኑ ከቀድሞ ደቡብ ክልል ጀምሮ ተሰራጭቶ የነበረው ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ የት ነው? .... ተጨማሪ ያንብቡ 👇

https://wolaitatimes.com/?p=5428

Wolaita Times

28 Jan, 12:37


"የዎላይታ ዞን አስተዳደር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነት ለክልል አሳልፎ መስጠት ጭንቅላት የተቆረጠውን ሰውነት መሸከም ማለት ነው" - ባለሙያዎች

ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ከተሞች ሪጅዮፖሊታን ከተማ ሆኖ እንዲደራጁ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ተጠሪነታቸውም ለክልሉ ይሆናል መባሉን ተከትሎ ከተለያዩ አካላት ከፍተኛ ተቋውሞ እየተሰማ ይገኛል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ ከተለያዩ ባለሙያዎች እንዲሁም ሁኔታውን በቅርበት ከሚከታተሉ አመራሮችና ግለሰቦች ሀሳቦችንና መፍትሔ አቅጣጫዎችን አሰባስቧል።

በተለይም በክልሉ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ 100% በራሷ የውስጥ ገቢ የምትዳደር፣ በህዝብ ቁጥር ሆነ በኢኮኖሚያዊው አበርክቶ አንፃር ከፍተኛ ድርሻ ባለችው ዎላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ የጠየቅናቸው ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት "የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከፈርጀ አንድ ደረጃ ወደ ሪጅዮኦፖሊትነት ከፍ ማለቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ክርክር ባይነሳም በተቃራኒው በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠርነት ለክልሉ ነው የሚል ድንጋጌ መቀመጡ አዝማሚያው ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ኢህገመንግስታዊ ነው" ይላሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲደራጅ አደራጅ አካላት ትኩረት ያደረጉት እንዴት ዎላይታን እጅእግሩን በማሰር የነበሩ ልማቶችን እንደሚቀሙና ወደፊትም በምንም መልኩ እንዳይለማ እንዴት እንደሚሠሩ ተማምለው ነው። በመሐላቸው መሠረት ይህ ክልል ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ የቦዲቲ የአረካ ከተሞችን ከዓለም ባንክ ፕሮግራም ተጠቃሚነት ማስወጣት ጨምሮ ቀደም ሲል በእጁ የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ነጥቀው ለሌሎች አስተላልፈዋል ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁኔታዎችን በቅርበት የተከታተሉ አመራር አስረድተዋል።

በቢሮ ድልደላ እና በአመራር ምደባ ከፍተኛ በደል ተፈፅሟል አሁንም ቀጥሏል። ክልላዊና ሀገራዊ ዝግጅቶች በዎላይታ እንዳይደረጉ፣ በሶዶ ከተማ የተጀመረው መንገድ ፕሮጀክት እና የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት እንዲሰናከል ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ። የዎላይታ ተወላጅ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ቢሮዎች እንዳይመደቡ፣ የተመደቡትም ያለ ምክንያት እንዲፈናቀሉ በይፋ እየተሠራ እንደሚገኝ አስተያየት ሰጪ ጠቁመዋል።

ዎላይታ ከሰሜን ኦሞ ትብታብ ከተፈታ በኋላ ያለማንም ድጋፍ ከሕዝቡ በሰበሰበው እና በዎላይታዊያን ጥረትና ድካም ፈጣሪም ጥቂቱን ባርኮ ከተማ ሊመስል ችሏል። ይህ ያስቆጫቸው እና ሕዝቡን በጎሪጥ ሲመለከቱ የከረሙት የትኛውም ልማት በዎላይታ ሲሰራ የሚያንገበግባቸው አካላት ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመዘዋወር ሥልጣን ማግኘቱን አስታውሰዋል።

አክለውም፦ አሁን ደግሞ ይዘው የተነሱት የዎላይታ ሕዝብ የዓይኑ ብለን የሆነውን ከተማ በመንጠቅ ዳግማዊ ዎጋጎዳ ለማንሰራራተሰ ላይ ታች እያሉ ነው። ሪጂኦፖሊታን ለማወጅ የቸኮሉ አካላት የክልሉ መንግሥት መቀመጫ የሆነው የዎላይታ ሶዶ ከተማ ስሙ በክልሉ ሕገመንግስት በግልጽ እንዳይጠቀሰ ሽንጣቸው ገትሮ የሚሞግቱ፣ ዎላይታ ሶዶ ከተማ የክልሉ ዋና መቀመጫ ከሆነ የሐይቅ አዞ ይብላን ብለው የተገዘቱ፣ ከዎላይታ ጋር በሰማይ በምድር አንገናኝም ያሉ አካላት ናቸው" ብለዋል።

የሪጂዮፖሊታን ዋናው ውጥን የዎላይታ ሕዝብ የታሪኩ፣ የፖለቲካው፣ የእምነቱ፣ የተስፋው፣ የከፍታው ማዕከልና ማጠንጠኛ የሆነችውን የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነት ለክልሉ ማድረግ ከህዝብ እጁ በመንጠቅ ለሴራኞች የማስረከብ ግልጽ አጀንዳ ነው። በዚሁ አደረጃጀት ከጅምሩ ዎላይታ ጠል ክልላዊ ኃይላት በዎላይታ ጉዳይ እንደፈለጉ እጅ እየሰደዱ እንዲፈተፍቱና በሂደትም የዎላይታን ብሄርተኝነት፣ ቋንቋውን፣ ታሪኩንና ባህሉን በማክሰም ዎላይታነት ከምድረገፅ እንዲጠፋ የተወነጠ ፕሮጀክት እንደሆነም በማስረዳት።

"የሶዶ ከተማ የዎላይታ የሁሉም ነገር ማዕከል ነው። ከተማውን ከዎላይታ አመራር እጅ ነጥቀው ተጠሪነቷን ለጥላሁን እና ለብርሃኑ ለማድረግ ነው። ከዚህ በኋላ እያንዳንዱ የሶዶ ከተማ ጉዳይ የዞኑ ምክር ቤት ሳይወስነው በከተማ ልማት ይሁንታ የሚፈፀም ነው የሚሆነው። የዞኑ ምክር ቤት መክሮበት የወሰነው ነገር ሳይኖር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ለአደገኛው የክልል መዋቅር ማስረከብ መዘዙ ብዙ እንድምታዉ አደገኛ ነው" በማለትም አስረድተዋል።

"ዎላይታ ሶዶ ከተማ የመልማት ጭላንጭል የታየው ከሰሜን ኦሞዎቹ መዋቅር እጅ ከወጣች በኋላ ነው። አሁን መልሰው እያስረከቡ ነው። ምክያቱ ደግሞ ሶዶ ከተማ ከዞኑ ጋር ከኢኮኖሚው ሆነ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ አንፃር ዕኩል ስታተስ ስለሚኖረው ያንን ሥልጣን ለመቀራመት ነው። ይህ ጉዳይ እጅግ የሚያስብና ትኩረት የሚፈልግ ነው። ጥንቃቄ የሚሻ ጉዱይም ነው። በሂደትም የክልል ጥያቄአችን ላይ አደጋ የሚደቅን ነው። ምክያቱም የክልል ጥያቄ በሁለት የተለያየ መዋቅር ሆኖ አደራጅቶ ማስከሄድ አደጋም አለው" ይላሉ።

በተጨማሪም አልፎም ጥቂት የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም የዎላይታ ሕዝብና አመራሩን በመከፋፈል አከባቢው እንዳይረጋጋ፣ ምንም ዓይነት ክልላዊ ፕሮጀክት በዞኑ እንዳይሰራ ያለ ዕረፍት እየተጉ ይገኛሉ። የክልሉን በጀት ከሕግና አሠራር ውጭ በመጠቀም ለአንድ አከባቢ አድልተው እየሰሩ እየመዘበሩም እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ፦ "ችግሩ የሚመነጨው ከህገመንግስቱ ነው። የክልሉ ዋና ከተማ ያልሰየመ ብቸኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገመንግስት ነው። ስለ 6ቱ ማዕከላት እንጂ ስለ ዋና ከተማ አያወራም። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ ነው የተደረገው። የክልሉ "ዋና ከተማ" እና "ማዕከላት" በጽንጸ ሀሳብ ይለያያሉ። ሀገርም ይሁን ክልል ዋና ከተማ መሰየም ግዴታ ነው። ማእከላት በሚሰጡት አገልግሎት የተለያዩ እና ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ" ብሏል።

"ለምሳሌ በዚህ በጀት አመት 3ቱ ከተሞች እኩል ናቸው በሚል እሳቤ ካፒታል በጀት ተብሎ ለእያንዳንዳቸው 80 ሚሊዮን ነው የተመደበው። ይህ አግባቢ አይደለም። ዲላ በራሱ መጠን ማግኘት አለበት እንጂ ከአርባምንጭ ጋር እኩል ማግኘት የለበትም። የክልሉ ርዕሰ መዲናና ዋና ከተማ ከሆነች ተያይዞ የሚመጡ መዋቅሮችንም ሆነ አገለግሎቶች የማግኘት መብት መረጋገጥ አለበት። ማንም ይሁን ማን ክልሉ የሚታወቅ በህግ የተደነገገ አንድ ዋና ከተማ መኖር አለበት። ከዛ ውጪ የተለያዪ ማእከላትና የከተማ ፈርጆች ሊኖሩ ይችላሉ። ከተሞች የፋብሪካ ምርት አይደሉም። የራሳቸው ታርክ፣ ያከማቹት ሀብት፣ የተፈጥሮ ምቹነት፣ የነዋሪው ጥረትና መሪነት ሚና መጠን የእድገት ደረጃቸው ይለያያል። ይህን ሀቅ የማይቀበል ህዝብን መምራት የለበትም" ብሏል።

"በአለመአቀፍም ሆነ በአገርአቀፍ መስፈርቶች ዎላይታ ሶዶ በአዋጁ ከተጠቀሱ ከተሞች በብዙ ስለሚትበልጥ እና ይህንን ሀቅ የማይቀበሉ ፖለትከኞች ለጊዜው ባገኙት ስልጣን አድበስብሰው እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት እየሰሩ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው በሚል አክለዋል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነቱ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ለማድረግ ማሳብ የሀገሪቱን ሕገመንግስት የሚጻረርና የዎላይታን ሕዝብ የሚጎዳ አደገኛ ውሳኔ በመሆኑ ዳግም ሊጠን ይገባል፤ ምክንያቱም የከተማዋን መፃኢ ዕድል የመወሰን ስልጣኑ የዎላይታ ሕዝብ በተለይም የዞኑ፣ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ምክር ቤት እና የዎላይታ ብሔር ምክር ቤት እንጂ የክልሉ ካቢኔ ወይም ሌሎች ብሔረሰቦች ስለከተማችን ሊወስኑ አይገባም" ብሏል።

Wolaita Times

28 Jan, 12:37


በመሆኑም በአጠቃላይ ያነጋገርናቸው አካላት የሰጡት ማብራሪያ "የዎላይታ ዞን አስተዳደር የዎላይታ ከተማ ተጠሪነት ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠትን በአጭር ቃል ሲገለፅ፦ ጭንቅላት የተቆረጠው ሰውነትት መሸከም መሆኑን ተረድቶ ከተማውን አሳልፎ ከመስጠት መቆጠብ አለበት። ለችግሩ ዋነኛ መፍትሔ የራስን ክልላዊ መስተዳድር መመስረት ነው። የዞኑ አመራሮች ትግሉን ማቀጣጠል አለባቸው። መላው የዎላይታ ሕዝብ፣ ሲቢል ሰርቫንቱ፣ ወጣቱ፣ ምሁሩ፣ ነጋዴው አርሶ አደሩ በሀገር ውስጥ በውጭ ያለው ሁሉ ዎላይታ ዳግማዊ ዎጋጎዳ ከሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥፍነጋ እስር ቤት ወጥቶ የራሱን ክልል የመመስረት ትግል ዳግም አዲሶ እንዲጀምር ሕዝባዊ ጥሪ መቅረብ አለበትም ብለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከቀናት በፊት የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሥራ አስፈፃሚ በላከልን መግለጫ ክልሉ "እንደ ክልል በጋራ አጀንዳ ከመምከር እና ሕግ ከማውጣት ውጪ የአንድ ብሔርን የዘመናት ልፋት እና ጥረት የሆነውን ከተማ ተጠሪነቱን ከብሔሩ ምክር ቤት በመቀማት የክልሉ ምክር ቤት ለዚያውም የብሔሩ ውክልና በሌላቸው ተወካዮች ተጠሪነት ስር ማድረግ በሕገመንግስት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት የተደነገገውን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ከመቀማት ባሻገር የዴሞክራሲ ምሶሶ የሆነውን የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን እና የማስተዳደር የሕዝብ ልዕልናን የሚገረስስ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ መሆኑ አጽንኦት ልሰጥበት ይገባል" ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

መግለጫው በተጨማሪም የክልሉ መንግስት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ክትትል እና ድጋፍ ከማድረግ የዘለለ ያለ ብሔሩ ዕወቅና ያልተወከሉ የሌሎች ብሔር አባላት በጋራ ያቋቋሙት ምክር ቤት የተጠሪነት ሚና ሊኖረው የማይገባ መሆኑን በመግለፅ ጉዳይ በማንአለብኝነት እምቢ ተብሎ እንድሁም ይህ አዋጅ የፓርቲውን አስተያየት ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ሳይሻሻል የሚጸድቅ ከሆነ ፓርቲችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ የአዋጁ ሕጋዊነትን የማይቀበል ከመሆኑም ባለፈ የክልሉን ምክር ቤት እና ሕግ አውጪውን አካል በህግ የሚከስ መሆኑንና አዋጁም ከተፈጻሚነት ሊታገድ የሚችል መሆኑ ሊታወቅ የሚገባ መሆኑን በአንክሮ የምናስገነዝብ ሲሆን የአዋጁን ጉዳይ ፓርቲያችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ እስከመጨረሻው በአጽንኦት የሚከታተል መሆኑንም ጭምር አጥብቀን እንገልጻለን" በሚል ጠንካራ አቋም መያዙን ዘግበናል።

ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በጉዳዩ ዙሪያ የሶዶ ከተማ አመራሮች፣ የዞኑ አመራሮች እንዲሁም አንዳንድ በክልል ደረጃ የሚገኙም ባለመስማማት እሰጥአገባ ውስጥ እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን የተሟላ መረጃ እንዳገኘን እንደምናቀርብ ከወዲሁ ለመጠቆም እንወዳለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southernethiopia

... ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5422

Wolaita Times

27 Jan, 14:32


ገንደባ ቤቴል፣ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን የ2017 ኮንፈረንስ

ማስታወቂያ 👇

እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል። - ትንቢት ዘካሪያስ 14:9

ገንደባ ቤቴል፣ ዎላይታ ሶዶ - ኢትዮጵያ 🙏

“ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።” - 1 ዜና 16፥29

በኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን የዎላይታ ሰበካ ከጥር 22/17 እስከ ጥር 25/17 ዓ.ም ድረስ 18ኛው ዙር አመታዊ ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ያካሂዳል።

በዚሁ ኮንፍራንስ የሚሳተፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ሐሙስ ዕለት ከየአቅጣጫው በተመሳሳይ ሰዓት በከተማዋ በሁሉም መግቢያዎች በሰልፍ በመግባት እስከ ገንደባ ቤቴል ድረስ ለፈጣሪ ምስጋና፣ ዝማሬ እንዲሁም ፀሎት እያደረጉ በእግር ጉዞ ፕሮግራሙን እዚያው በይፍ ይጀምራሉ ተብሏል።

የሰላምና ለሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት በሆነችው #ዎላይታ #ሶዶ #ከተማ ላይ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዎላይታ ሰበካ ከጥር 22 እሰከ 25/17 ዓ.ም ድረስ በሚያካሂዱት ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ምዕመናንና ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች ከዎላይታ፣ አጎራባች ዞኖችና ክልሎች አንዲሁም ከተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ያለልዩነት ቀኑን በጉጉት ጠብቀው የሚሰበሰቡበት ጉባኤ ይካሄዳል።

በኮንፈረንሱም ምዕመናኑ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለፈጣሪያቸው ፀሎትና ምልጃ የሚያደረሱበት ዓመታዊ ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በየጊዜው የኃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በአከባቢው የሚያበረክቱት አውንታዊ ሚና ለኮንፍራንስ ቱሪዝም ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ ዜጎችን በመልካም ስነምግባር በማነፅ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

ኑ የበረከቱ ተካፋዮች ሁኑ፤ ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል 🙌

ከሐሙስ እስከ እሁድ ወንጌል በስልጣን ይሰበካል 🙌

በጉባኤው መንፈስ ቅዱስ በኃይል ይወርዳል፤ ኢየሱስ በእውነትና በመንፈስ ይመለካል 🙌

አድራሻ፡- ከዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 400 ሜትር ወረድ ብሎ ባለው በሰፊው ገንደባ ሜዳ ላይ🙏

#የኢትዮጵያ #ሐዋሪያዊት #ቤተክርስቲያን🙏
#Apostolic #Church of #Ethiopia 🙏

#GENDEBA #BETHEL #WOLAITA2025

Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5415

Wolaita Times

26 Jan, 19:04


ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የረጂዮፖሊስ ከተማ አወቃቀርን አስመልክቶ ካቢኔው የወሰነው ውሳኔ አስመልክቶ ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር/ዎሕዴግ/ የተሰጠ የአቋም መግለጫ፦

አንድ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት መሆን ሀገራችን ፈሪማ የተቀበለቻቸው ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ቃልኪዳን እንዲሁም በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት የተደነገገ እውነታ ነው።

ስለሆነም ሕገመንግስቱ በአንቀጽ 8 የሕዝብ ሉዓላዊነትን እንደሚከተለው ያብራራል።

1. የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡

2. ይህ ሕገ መንግሥት የሉዓላዊነታቸው መገለጫ ነው፡፡

3. ሉዓላዊነታቸውም የሚገለጸው በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 50 ስለ ሥልጣን አካላት አወቃቀር ክልሎች፤ በክልልነትና ክልሎች አስፈላጊ ሆነው በሚያገኙአቸው የአስተዳደር እርከኖች ይዋቀራሉ፡፡ ሕዝቡ በዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች በቀጥታ ይሳተፍ ዘንድ ለዝቅተኛ እርከኖች በቂ ሥልጣን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 52 የክልል ሥልጣንና ተግባር 2. ሀ/ ራስን በራስ ማስተዳደርን ዓላማ ያደረገ ክልላዊ መስተዳደር ያዋቅራል፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባል፤ ይህን ሕገ መንግሥት ይጠብቃል፤ ይከላከላል፤ በተመሳሳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት አንቀጽ 39 ስለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መብት በሚደነግገው ድንጋጌ ስር በራሱ መልከአ ምድራዊ ክልል ውስጥ የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን እና ራስን ማስተዳደር መብቶችን ያጎናጽፋል።

በተጨማሪም አንቀጽ 46 ስለሕግ አውጪ አካላት ስልጣን ሲደነግግም ቢሆን የክልሉ ሕግ አውጪ አካል የክልሉ ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱ ለወከለው ሕዝብ ነው። ይህም ማለት ተጠሪነቱ ለወከለው ብሔር/ብረሰብ ምክር ቤት ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤትን ከሌሎች ክልሎች ምክር ቤት ለየት የሚያደርገው ጉዳይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተወካይ ስብስብ መሆኑ ነው።

ይሁንና ይህ ስብስብ እንደ ክልል በጋራ አጀንዳ ከመምከር እና ሕግ ከማውጣት ውጪ የአንድ ብሔርን የዘመናት ልፋት እና ጥረት የሆነውን ከተማ ተጠሪነቱን ከብሔሩ ምክር ቤት በመቀማት የክልሉ ምክር ቤት ለዚያውም የብሔሩ ውክልና በሌላቸው ተወካዮች ተጠሪነት ስር ማድረግ በኢፌዴሪ ሕገመንግስት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት የተደነገገውን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ከመቀማት ባሻገር የዴሞክራሲ ምሶሶ የሆነውን የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን እና የማስተዳደር የሕዝብ ልዕልናን የሚገረስስ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ መሆኑ አጽንኦት ልሰጥበት ይገባል።

በመሆኑም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የራጂዮ ፖሊስ ከተሞችን ለማደራጀት የወጣ ረቂቅ አዋጅ በአንቀጽ 8(2) በክልሉ የተደራጁ የራጂዮፖሊስ ከተሞች ተጠራነቱ ለክልሉ መንግስት ነው የሚለው ተሻሽሎ ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ነው እንዲባልና የክልሉ መንግስት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ክትትል እና ድጋፍ ከማድረግ የዘለለ ያለ ብሔሩ ዕወቅና ያልተወከሉ የሌሎች ብሔር አባላት በጋራ ያቋቋሙት ምክር ቤት የተጠሪነት ሚና ሊኖረው የማይገባ መሆኑን ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እንፈልጋለን።

ይህ ጉዳይ በቸልተኝነትና በማንአለብኝነት እምቢ ተብሎ እንድሁም ይህ አዋጅ የፓርቲውን አስተያየት ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ሳይሻሻል የሚጸድቅ ከሆነ ፓርቲችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ የአዋጁ ሕጋዊነትን የማይቀበል ከመሆኑም ባለፈ የክልሉን ምክር ቤት እና ሕግ አውጪውን አካል በህግ የሚከስ መሆኑንና አዋጁም ከተፈጻሚነት ሊታገድ የሚችል መሆኑ ሊታወቅ የሚገባ መሆኑን በአንክሮ የምናስገነዝብ ሲሆን የአዋጁን ጉዳይ ፓርቲያችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ እስከመጨረሻው በአጽንኦት የሚከታተል መሆኑንም ጭምር አጥብቀን እንገልጻለን።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሥራ አስፈፃሚ

ጥር 18/2017 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ/ኢትዮጵያ

Wolaita Times

25 Jan, 16:22


ቤቶቻቸው ሲፈርስ ሆነ ሲያስረክቡ ካሳ አለመጠየቃቸውን ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ

የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ቤቶቻቸውን ሲያፈርሱም ሆነ ቦታዎችን ለልማቱ ሲያስረክቡ ካሳ አለመጠየቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከባለቤታቸው፣ ከሚኒስትሮች እና ከሌሎችም እንግዶች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በትላንትናው ዕለት ተዘዋውረው ጉብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ጉብኝት በኋላ በሰጡት ገለጻ፤ በጅማ ከተማ ለተከናወኑ “የገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ተናግረዋል።

በከተማይቱ የነበረ መስጂድ እና ከአንድ ሺህ በላይ የመቃብር ቦታ ቀድሞ ከነበሩባቸው ቦታዎች መነሳታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የጅማ ከተማ ነዋሪዎች “ቤቶቻቸውን ሲያፈርሱም” ሆነ ቦታዎችን ለፕሮጀክቶቹ ሲያስረክብ “ካሳ አለመጠየቃቸውን” ዶክተር ዐቢይ በአድናቆት አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተወለዱበት በሻሻ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የጅማ ከተማ ህዝብ፤ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ “ ‘እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው’ ያለው” ሲሉም በገለጻቸው ላይ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ እንሳይደር ዘገባ እንደዘገበው “የጅማ አካባቢ ማህበረሰብ ለእነዚህ ህልሞች፣ ለእነዚህ ሃሳቦች መወለድ የነበረው ሚና፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርት መሆን ያለበት ነው” ሲሉም አብይ በገለጻቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ጅማ፤ ከሌሎች ቦታዎች በተለየ መንግስት ለሚያፈልቀው ሃሳብ “የተከታይነት” አመለካከት እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Oromia #Jima

Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5411

Wolaita Times

23 Jan, 13:29


በዚሁ ስለ ሐገር አቀፉ ዎሕነን ስሔድ ፓርቲዉ አዲስ ከመሆኑ በተጨማሪም ሐሳቡም አዲስ ሆኖ አግንቼዋለሁ። ፓርቲዉ ዎላይታ ድንበሯ ና ሕዝቧ አሁን በዞን ደረጃ ያለዉ ብቻ አይደለም በድርድር ሰፊ አንድነት መፈጠር አለበት የሚል አቋም ያለዉ ነው። የፓርቲው አዲስነት እንዳለ ሆኖ ፓርቲው ከሌሎች የዎላይታ ፓርቲዎች ጋር መሥራት የሚችልበት አግባብ ካለም ከወዲሁ ቢጀምር ከዞኑ ዉጪም እንደቃሉ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግ ባይ ነኝ።

ምናልባት መሪዉ ወልደማርያም ልሳኑ አቅም ያለዉ ሰዉ ይመስላል፤ ግን ለዎላይታ ክልል በመታገሉ እና ፈደራል ሰርዓቱን በመከላከሉ አድንቀን ሳንጨርስ፣ በምርጫዉ እናት ፓርቲን ወክሎ የፈደራል ስርአቱ ከፋፍሎ ለመግዛት የተፈጠረ ነው ብሎ አስደንግጦኝ ነበረ። አቋም በዚህ ደረጃ መዋዥቅ ያለበት አይመስለኝም።

ሳጠቃልለዉ በሁሉም ፓርቲና ግለሰቦች ላይ የምናደርገዉ አስተያዬትና ትችት ከጥላቻ ሳይሆን የተሻሉ እንዲሆኑና ለሕዝባችንም ጥቅም በማለት ነው። በተረፈ በገዥዉም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፎ ፖለቲካ መሥራት ቀላል እንዳልሆነና ብዙ ዋጋ እንደሚያስፈልግ ስለምንገነዘብ ለእነሱ ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ አጠቃላይ በዎላይታም ሆነ በሐገር ደረጃ በፓርቲዎች አደረጃጀት ላይ ክፍተት የሚሉትን ነገር ቢጠቁሙንና ብንዘጋ?ማየት የሚፈልጉት ጥምረት ወይንም ፓርቲ ካለም ቢጠቁሙን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ በጋራ ያለመሥራት ችግር አንዱ ነው ። እነ ዎብንና ኦፈኮ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ ለምሳሌ ግምባር ቢፈጥሩ፣ አሁንም ያላቸዉን ኮከስ እንደቀላል ባይወስዱት እላለሁ። ሌላዉ በአደረጃጀት ደረጃ ኢፈፓ (የኢትዮጵያ ፈደራሊስት ፓርቲ) ቢደራጅ ትልቅ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ብዬ እገምታለሁ።

የፌደራል ሥርዓቱን የሚቀበል የትግራይን ግዛታዊ አንድነት ማስመለስ፣ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ማስከበር፣ የዎላይታን የክልል ጥያቄ መመለስ፣በአማራና ኦሮሚያ የሚደረጉ ጦርነቶችን የሚያስቆም ሐሳብ ማቅረብ፣ የመሰሉ አጀንዳዎችን ይዞ ቢወዳደር ቀላል ተቀባይነት የሚኖረዉ አይመስለኝም በመላዉ ኢትዮጵያ።

ሌላዉ ጥቆማዬ የቀድሞ የደቡብ ሕብረት አይነት ፓርቲም ተቋቁሞ ብናይ ባይ ነኝ። ሕገመንግሥታዊ ሥርአቱ ይቀጥል ሕገመንግሥት ይከበር የሚል ሁሉ ስለ ምርጫዉ ከወዲሁ ቢያስብበት መልካም ነው እላለሁ። ምርጫ ማሸነፍ ቢከብድም በምክር ቤቶች መቀመጫ ማግኘት በቀላሉ ሊታይ አይገባም።

ከተሞችን፣ ዞንና ክልሎችንም ማሸነፍ ከተቻለ ቀላል ነገር አይደለምና ቢታሰብበት እላለዉ። ሁለተኛው ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ አለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነዉና ሁሉም ተቃዋሚዎች ትኩረት ቢሰጡበት እላለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Politicalparty

ቆይ ፓርቲዎቹ በህዝብ ቁስል የሚነግዱ ሳይሆን የሚያክሙ በመሆን በብልፅግና ጨው ሳይታለሉ ለህዝብ ጥቅምና መብት እንዲቆሙ ማድረግ አይቻልም !?
Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5401

Wolaita Times

23 Jan, 13:29


በተለይም በዞኑ ሶስቱ ፓርቲዎች በብልፅግና ጨው ሳይታለሉ ለህዝብ ጥቅምና መብት እንዲቆሙ ማድረግ ይቻላል !? ለመሆኑ ፓርቲዎቹ በህዝብ ቁስል የሚነግዱ ሳይሆን የሚያክሙ መሆን የለባቸውም ወይ ?- የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ዛሬ የዎላይታ ፓርቲዎችን ወቅታዊ ቁመና ከሐሳብ ጥራት፣ ከአመራር ብቃት፣ ከአደረጃጀት ጥንካሬ እና ከሕዝብ ተቀባይነት እንዲሁም በሐገር ደረጃ ከተጽዕኖ አሳዳሪነታቸዉ አንጻር ግምገማ እናደርጋለን።

በዚህም አንጻር ቅርጫፍ ብቻ ቢሆንም የዎላይታ ብልጽግና፣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ እንዲሁም የዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄን እንዳስሳለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ሐገራዊ ምርጫዉም አንድ አመት ብቻ ስለቀረዉ፣ ትክክለኛ ርዕስ በትክክለኛ ሰአት ብያለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እሺ እናመሰግናለን። በቅድሚያ ከዎላይታዉ የብልጽግና ቅርንጫፍ ቢጀምሩልን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ እኔም አመሰግናለሁ። ያዉ ብልጽግና ወጥ ፓርቲ ስለሆነና በክልልም በዞንም ደረጃ መሰብሰብ የማይፈቀድለት ቅርንጫፍ ብቻ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ከትግራይ ክልል ዉጪ ገዥዉ ፓርቲ ብልጽግና ስለሆነ፣ በፓርቲው ዉስጥ ዎላይታ ምን ድርሻ አለዉ የሚለዉን መገምገም ይቻላል።

ብልጽግና ከጥንስሱም ለዎላይታ ሕዝብ ጥሩ አመለካከት አለዉ ማለት አልችልም፣ ፓርቲው በሐገር አቀፍ ደረጃም የሐሳብ ጥራት ብቻ ሳይሆን የወጥነትም ችግር ያለበት ነው። በተለይ ፓርቲውን በሐገር ደረጃ ከሚዘዉሩ ሰዎች ዉስጥ የዎላይታ ተወላጅ የለም።

ፓርቲዉ የሚሰጠዉ የመንግስት የስልጣን ሹመት ብሔሩን ወሳኝ ከሚባሉ ቦታዎች ማግለልን መሠረት ያደረገ ነው። በአቅም ደረጃ በብልጽግና ዉስጥ ብዙ የተሻለ አቅም ያላቸዉ ዎላይታዎች መኖራቸዉን መካድ እንደማይቻለዉ ሁሉ ፓርቲ ብለዉ ያሉበት ብልጽግና በብሄራቸዉ ምክንያት ቦታ እንደማይሰጣቸዉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

አደረጃጀቱ የመንግስትን መዋቅር ተከትሎ ብዙ ሰዎችን ቢያቅፍም፤ ፓርቲው ከልባቸዉ አምነዉ አባል የሆኑበት ነው ማለት አይቻልም። በተለይ ደኢህዴን የዎላይታን ሕዝብ በማስጠቃቱ ፊርማ አሰባስቦ ከድርጅቱ የወጣዉ ሕዝብ ልብ ዉስጥ ብልጽግና መልሶ ገብቷል ማለት ቀልድ ነው። በሐገር ደረጃም የዎላይታ ብልጽግናዎች ተጽዕኖ እምብዛም ነው።

ብሔሩ በክልልም በፈደራልም ሚዛናዊ የስልጣን ዉክልና መነፈጉም የችግሩ የአንዱ ሳንቲም ሁለተኛዉ ገጽታ ነው። ስለዚህ የዎላይታ ብልጽግናዎች፣ ፓርቲያቸዉ ስለሕዝባቸዉ ያለዉን የተዛባ እይታ መቀየር የቻሉበት አግባብ የለም፣ ስለዚህ በአፈናና በጉልበት ካልሆነ ብልጽግና በአካባቢው ብዙ ተቀባይነት አለዉ ማለት አይቻልም። ይሄንን ሁኔታ በማጤን ማስተካከል ከተቻለ መፍትሔ ሊኖር ይችላል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እሺ በመቀጠል ስለ ዎሕዴግ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ዎሕዴግ አንጋፋ ድርጅት ነው። ለዘመናት ለሕዝቡ ድምጽ በመሆን ያደረጋቸዉን ተጋድሎዎች አደንቃለሁ፣ በፓርቲው መስመር ለዎላይታ ለታገሉ ሁሉ ክብር አለኝ። ነገር ግን በዚህ ሁሉ አመታት ፓርቲው በዞኑ ምርጫ ለምን አላሸነፈም? የክልል ምክር ቤትም ሆነ የፌደራል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይ አባሎቹን ለምን ማስመረጥ አልቻለም የሚለዉ በራሳቸዉ መገምገም ና የመፍትሔ አቅጣጫም ሊያስቀምጡለት ይገባል።

በአመራር ደረጃ ጎልቶ የወጣ ነገር ባይስተዋልም፣ በፓርቲው ዉስጥ የተወሰኑ አቅም ያላቸዉ ግለሰቦች እንዳሉ ይስተዋላል ወደ ፊት አመራርነት መምጣት ያለባቸዉ ይመስለኛል። ፓርቲው በተለያዩ ሕዝቡን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በየጊዜዉ መግለጫ ማዉጣቱ የሚደነቅ ነው። ይሁን እንጂ ሐሳቡን በቋዋሚነት ለሕዝቡ በማህበራዊም ሆነ በmainstream ሚዲያ ለመሸጥ የሚያደርገዉ ጥረት ብዙ አይደለም።

ሕዝባዊ ስብሰባዎችን የምሁራን መድረኮችንም ሲያዘጋጅ አይስተዋልም። በሐገር አቀፍ ደረጃም ያለዉ ተጽዕኖ ከሚጠበቅበት በታች ነው ባይ ነኝ።

ዎሕዴግ በሐገራዊ ምክክሩ ተሳታፊ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይዞ የሚቀርባቸዉን አጀንዳዎች ለሕዝብ ይፋ ካለማድረጉም በተጨማሪ መጀመርያ አልሳተፍም ካለበት ምን ስለተቀየረ ለመሳተፍ እንደወሰነም ግልጽ አላደረገም። ፓርቲው አንጋፋ በመሆኑ በዎላይታም ሆነ በኢትዮጵያ ቢታወቅም ተጽዕኖዉን ለመጨመር ብዙ ሥራ ይጠበቅበታል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ስለ ዎብን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ዎብን ከለዉጡ በሁዋላ የተፈጠረ በወቅቱም ብዙ አቅም ያላቸዉ ወጣቶች የነበሩበት እና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያደረገ ቆይቶ የተቀዛቀዘ ፓርቲ ነው። በአመራር ደረጃ አሁን ከፊት ያለዉ አማኑኤል ሞጊሶ አቅም ያለዉና በተለያዩ ሚዲያዎችም ሐሳቦቹን በጥሩ ምሁራዊ አቅም ሲያስተዋዉቅ ታዝቢያለሁ። መሰል አቅም ያላቸዉ ምን ያህል ሰዎች ፓርቲዉ ዉስጥ አሉ የሚለዉን ለማየት አልቻልኩም።

ዎብን ከነኦፈኮ፣ ኦነግ እና ኦብነግ ጋር በጋራ ምክንያቱን ገልጾ ከሐገራዊ ምክክሩ እራሱን ማግለሉን አከብርለታለሁ፣ በዚህ ረገድ በሐገር አቀፍ ደረጃም ተጽዕኖዉ የሚናቅ አይደለም። ፓርቲዉ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ና የምሁራንን መድረኮች የማዘጋጀት ድክመት አለበት። ሐሳቡንም ለሕብረተሰቡ ለመሸጥ የበለጠ መትጋት ይጠበቅበታል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ስለ ዎሕነን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ምናልባት ከዛ በፊት ስለ ዎሕዴግና ዎብን አንድ ነጥብ መጨመር እፈልጋለሁ። ከፈቀዳችሁልኝ?

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እሺ ይቀጥሉ።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምናልባት ባለፈዉ ምርጫ ላይ የቱሳ ጥምረት በሚል ፓርቲዎቹ በጋራ እጩዎችን ለማቅረብም የተወሰነ ጥረት ማድረጋቸዉ ይታወሳል፣ ተግባራዊነቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነዉ። በፓርቲዎቹ መሐል በጋራ የቱሳ ጥምረትን ፈጥረዉ እንዳይሰሩ የሚከለክላቸዉ ልዩነት በግሌ ለእኔ ግልጽ አይደለም።

የሐሳብ ልዩነቶቻቸዉ አብሮ መታገልን የሚከለክሏቸዉ እስካልሆኑ ድረስ በጋራ ቢቀጥሉ የተሻለ ይመስለኛል። የደጋፊ ኃይል እንዳይበታተን በአመራር አቅምም በጋራ ቢሰባሰቡ በጣም የተሻለ ነገር የሚፈጠር ይመስለኛል። ድርጅታዊ አቅማቸዉም በጋራ ሲመጣ ትልቅ ነው። ተጽዕኖ አሳዳሪነታቸዉም ይጨምራል። ለሕዝብ ቸወካዮች ምክርቤትም ሆነ ለክልል ምክር ቤት የተሻሉ እጩዎችን ለመመልመልም ያግዛቿልና የተናጠል ጉዟቸዉ አያስደስተኝም።

በትንሹ ወንበሮችን በሁለቱም ምክር ቤቶች ለማሸነፍ ከፈለጉ ከወዲሁ ተጣምረዉ፣ ለምርጫዉ ይዘጋጁ እላለሁ፣ ምርጫዉ ሲደርስ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን። ሁለቱም አቅማቸዉን ለማጎልበት ብዙ ምሁራንን አባል ለማድረግ መጣር አለባቸዉ።

ገዥዉ ፓርቲ በግልጽ የዎላይታን ሕዝብ የሚገፋ በመሆኑ ብዙ ነጥብ ሊያስቆጥሩበትና የሕዝቡን ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ። ለምሳሌ የዎላይታ ዞን የሚያገኘዉ በጀት ከተገቢዉ በታች ነው። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሕዝቡ ጠይቆት የኢንዱስትሪ ዞን አንገነባም ብሏል መሰል ነጥቦችን መጠቀም ይችላሉ። ስለዚህ ጠንክረዉ ከሰሩ ዉጤት የማያመጡበት ምክንያት የለም።

Wolaita Times

22 Jan, 18:44


የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማሪያም በፕሬዝደንት ትራምፕ በዓለ ስምት የተናገሩት!

"... እኔ እዚህ የመጣሁት የዓለም ችግሮች እንዲፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ዋነኛ ሚና ስላላት ፕሬዝዳንት ትራምፕም የራሳቸውን ድርሻ መወጣት ስላለባቸው... በዚህ ረገድ [የዓለም] መሪዎች ሚና መወጣት ስላለባቸው... ፕረዚዳንት ትራምፕ በእግዚአብሔር ስለሚያምን እኔም ስለማምን ዓለም ሰላም እንድትሆን ለመፀለይ ነው።..."

Wolaita Times

21 Jan, 13:51


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ስብራትና ብልሽት በተመለከተ በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ባሉ 6 ምሁራን የተደረገ አጭር ጥናት ይፋ ሆነ

በወቅታዊና ክልላዊ ጉዳይ ላይ በዲላ በጂንካ በአርባምንጭ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ምሁራን በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ዳሰሳ የተካተቱ ወጣቶች መምህራን ነጋዴዎችና አርሶአደሮቹን በአጭር መጠይቅ ተዘጋጅቶ በምስጢር የተካሄደ ነው ተብሏል።

እኚህ ምሁራን በአከባቢያቸው ሆኖው ያጠኑ ሲሆን በጋራ የጥናቱን ውጤት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በኩል ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።

እነዚህ 6 ሙሁራን በአራቱ ዩኒቨርስቲ ያሉ በዶክትሬት ትምህርታቸው አብረው በዉጪ ሀገር ያሳለፉና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታን ተመልክተው መፍትሄ ለማስቀመጥ አልመው ያጠኑት እንደሆነ የጥናቱ አስተባባሪና በዲላ የኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ሲሆን ጉዳዩን በገለልተኝነት ለማድረግ እጅግ ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የክልሉን ብልሽት በአንድ ቃል ተጠያቂዎች ምላሻቸው ላይ አካተዋል። ብልሽቱን የከፋ ያደረገው ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በስነምግባር ብልሽት ውስጥ መግባትና በሌብነት ሰንሰለት ውስጥ መውደቃቸው ዋነኛ ነው ይላሉ አስተባባሪው።

በመቀጠል የክልሉ የመንግስትና የፓርቲ ስራ ሙሉ በሙሉ የወደቀ ሲሆን የክልሉ ህዝብም በመንግስትና በፓርቲ ላይ እምነት እንደሌላቸው በተቻለ መጠን ብልፅግናን ከክልሉ በቀጣይ ምርጫ ለማስወገድ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ከጥናቱ ማግኘታቸውን ይገልፃሉ።

እንደ ጥናቱ ውጤት የክልሉ ብልሽት በመንግስትም በፓርቲም ደረጃ እጅግ የከፋ ያደረገው የክልሉ የፓርቲና አመራርና ርዕሰ መስተዳድሩ በተመሳሳይ ብልሽት ውስጥ መውደቃቸው አንዱ አንዱን የመናቅና የሁለቱም ተግባር ከውጤት ይልቅ ለሌብነት ቅድሚያ መስጠታቸው ነው።

አቶ ጥላሁንና የእሳቸው ሎሌ በክልሉ ባሉ ዞኖች ውስጥ በእሳቸው በቀጥታ የተሾሙ የየዞኑ አስተባባሪዎች አቅም የሌላቸው ህዝቡን የሚያጉላሉ በሌብነት የተዘፈቁ መሆናቸው ምሬቱ ሀገራዊ ገፅታ እንዲይዝ አድርጓል።

በክልሉ ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎችን በቅርብ ዘመዳቸው ሹመት መስጠታቸውና በእሳቸው የተሾሙ ሁሉ በአለቃቸው በመተማመን የብልሽት ማዕከል ክልሉ እንዲሆን በማድረግ በእሳቸው የሚደገፍና በእሳቸው ትዕዛዝ የሚሰደዱ አመራርችም መኖሩ ክልሉ በሁለት ጎራ ተከፍሎ ወደ መበተን እየሄደ እንዳለም የጥናቱ አስተባባሪ ገልጿል።

በጥናቱ ያሉ መላ ምት ተብሎ የተቀመጡ ክልሉ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ እንዳለ ያገኙ ሲሆን ይህም የብልፅግና መንግስት ምናልባት ርዕሰ መስተዳድሩን አስቀርተው ሌሎችን አስተባባሪዎችን ብቻ በመበተን ሊወስዱ የሚችሉት እርምጃ መፍትሄ አካል ይሆናል የሚል አቅጣጫ ካለ በእርግጥ ህዝቡ ጥናቱ በተካሄደበት አከባቢ በከፊል አርባምንጭ ከተማን ጨምሮ እጅግ እሮሮ ባለበት በአስቸኳይ ሳይታረም የሚቀጥሉበት አዝማሚያ ካለ ክልሉ በእርግጠኝነት 100% የመፍረስ አደጋ እንደሚጋረጠው አረጋግጠናል ብለዋል።

አሁን ላይ በክልሉ ተንሰራፍቶ ያለው አድሎአዊ አሰራርና አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ አድርጎ የሚሄዱበት አግባብ እጅግ የሚያንገሸግሽና ህዝቡ አይቀጤ ቅጣት በምርጫ ብቻ ለመቅጣት ቀን እየጠበቁ እንዳለ ከዚሁ ጥናት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።

የጥናቱ አስተባባሪ በመጨረሻም በሰጠው አስተያየት፦ "ምናልባት የብልፅግና መንግስት በአቶ በአደም ፋራህ በብልፅግና ምክትል ፕሬዝዳነት የተመራ ልኡክ በቂ ግንዛቤ ጨብጠው የሄደ በመሆኑ የፓርቲ ውግንና ካለ የህዝብ ውግንና ካለ በእርግጥም ፓርቲው ሰው ተኮር ከሆነ የክልሉን የመንግስትና የፓርቲ 6ቱ አስተባባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት" ብለዋል።

"በክልሉ የተገፉ እና የጥላሁንን የተሳሳተ አካሄድ የታገሉ አመራሮች ወደ ፊት እንዲመጡ ጭምር ጥናቱ መረጃ ከህዝቡ ማግኘቱን ከአስተባባሪው አግኝተናል" በማለት አክለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southernethiopia

"ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ አመኔታ ከማጣቱ ባለፈ የመንግስትና የፓርቲ ስራ ሙሉ በሙሉ በስብሷል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምሁራን አጭር ውጤት ..
Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5397

Wolaita Times

20 Jan, 14:28


ከአፍሪካ የአንድም ሀገር መሪ ሳይጋበዙ የኃያላኗ አሜሪካ ፕረዚዳንት በዓለ ስመት ላይ የተጋበዙ ብቸኛው አፍሪካዊ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትኩረት ያገኙት በምን ይሁን ?

የአፍሪካ መሪዎች በአሜሪካ ጉዳይ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኩል መሄድ ይጠበቃል?!

በዚህ የአለም ትኩረት በሳበውና ለመካሄድ ደቂቃዎች በቀረው ትልቅ ኩነት ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሌጋሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በመምራት በበዓለ ስመታቸው ላይ በአካል ከተገኙ በተመራጩ ፕረዚዳንት ትራምፕ የተጠሩ አፍሪካውያን መሪዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል በቀዳሚነት መሆኑ ተገልጿል።

ከቀበሌ ልቀመንበርነት ወረድኩ ተብሎ በጥላቻ ለተቃውሞ ዘብመንጃ ተይዘው በሚወጣበት ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሠለ ስልጣን በክብር አሳልፈው ሰጥተው ዛሬም የሀገራችን፣ የአፍሪካ ሆነ የአለም ዕድገት በሚገኝበት ሁሉ ከፊት ናቸው።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲታወሱ 👇

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመሆናቸው በፊት ከዩኒቨርስቲ መምህርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ከአንዱ ወደሌላኛው ኃላፊነት ባላቸው በስራ ልምድና ክህሎት እንዲሁም ፍፁም ሌብነትን በመፀየፍ በማገልገል እየተሸጋገሩ አሁንም ያለስስት በተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት የአመራርነት ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ድንገት ወይንም በአጋጣሚ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነ የሚመስላቸዉ፣ አንዳንድ በብሄረተኝነት ተውጠው ኢትዮጵያዊነት ሲያሳድግ (ሲቀርጽ) የበደላቸዉ የዋህ ወገኖቻችንና የሐገሪቱን ችግሮች በባዶ አዕምሮአቸዉ ተሸክመዉ እነሆ መፍትሔ እያሉ ችግር ላይ ችግር የሚደርቡ የተወሰነ ጭብጥ እንዲያገኙ ይህቺ በአጭሩ የታሪክ ዳራ የዳሰሰች ፅሁፍ አስፈልጓል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ከማንሳታችን በፊት እርሳቸዉን ያፈራዉን ብሄር ዎላይታን ፖለቲካዊ ታሪክ ከእርሳቸዉ የሁዋላ ታሪክ ጋር በጥቂቱ መዳሰስ ያስፈልጋል። የዎላይታ ሕዝብ የኢትዮጵያ ኢምፓየር አካል የሆነዉ፣ ከአስደናቂ የሰባት ዓመት ትንቅንቅና ተጋድሎ በሁዋላ ሐገሩ ፈርሶበት መሆኑ መሠመር አለበት።

በአፀ ሚኒሊክ መሪነት ከሚመራዉ የኢትዮጵያ ጦርና በንጉስ ጦና በሚመራዉ የዎላይታ ጦር መሐከል ከተካሄዱ ሰባት አሰቃቂ ጦርነቶች ስድስቱ ላይ ጦናና ሕዝባዊ ጦሩ፣ በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ሐገርነቱን አስጠብቆ መቆየቱ በታሪክ ይታወቃል። ከሰባተኛዉ ወረራና ጭፍጨፋ ማለፍ ባይችልም።

እንግዲህ በዚህ መንገድ ወደ ኢምፓየሩ የተቀላቀለዉ ሕዝብ ከአዉዳሚ የሰባት ዓመት ጦርነት በሁዋላ፣ የጠበቀዉ ከጦርነቱ ጠባሳ ሊያገግም ይቅርና ጦርነቱ የቀጠለ የሚመስል ሁኔታ ነበርና። ለዛም ይመስላል ከምርኮ መልስ በተሰጠዉ ስልጣን ተጠቅሞ ራሱ ንጉስ ጦና መልሶ ያመጸዉ፣ ብዙ ባይሳካለትም።

በአድዋ ጦርነት ወቅት ከዎላይታ የዘመተዉን ጦር ከመሩት ጦር መሪዎች አንዱ ነው የሚባለዉ ሐጤሮ ሐንቼ ከብዙ ትልልቅ የዎላይታ ሰዎች ጋር በድጋሚ ሌላ አመጽ ካቀነባበረ በሁዋላ፣ አመጹ የታቀደበት ቀን ሳይደርስ በአጋጣሚ ብቻዉን በወሰደዉ እርምጃ ብዙ ዉጤት ሳያመጣ ከሽፎበት በአሰቃቂ ሁኔታ ለመሞት የተገደደዉ። እንደዉም ፊታውራሪ ገነሜ የተባለ በሚኒሊክ ዎላይታን እንዲገዛ የተሾመ ሰው ወደ ሰገሌ ጦርነት መሄዱን ተከትሎ ሕዝቡ አመጽ በመቀስቀሱ ከፍተኛ ቅጣት ደርሶበታል ።

የዎላይታ ሕዝብ ልጅ ኢያሱ ስልጣን ከሚኒሊክ ሲረከብ ጭቆና በዝቶብናልና መጥተህ ጎብኘን ብሎ መልዕክተኛ የላከና መልዕክቱም ተቀባይነት ያገኘለት ሕዝብ ነው፣ ጉብኝቱ ባይሳካም።

እናም ይህን ለመብቱና ለነጻነቱ ካለዉ ቀናኢነት የተነሳ ለበዝባዥ ሥርዓቶች የማይመቸዉን ሕዝብ ከመአከል ርቆ እንዲያስተዳድር የተወሰነበትና በአሜሪካ ሐገር ትምህርት ተከታትሎ የመጣዉ ተራማጁ ገርማሜ ነዋይ በዎላይታም ሆነ በኢትዮጵያ የለኮሰዉን የለዉጥ ችቦ የምንቃኝ ይሆናል።

ገርማሜ ነዋይን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ምን ያገናኘዋል

ተራማጁ ምሁር ገርማሜ ነዋይ የዎላይታ አዉራጃ አስተዳዳሪ ተደርጎ በአጼ ኃይለስላሴ መመደቡ በግፈኛ አገዛዝ ለሚማቅቀዉ የዎላይታ ሕዝብ መልካም እድል ነበረ። ገርማሜ በዎላይታ አዉራጃ ለዉጥ ለማምጣት ከግፈኛ መልከኞች ጋር የሚያደርገዉ ትንቅንቅ በንጉሱ አልተወደደምና ወደ ሌላኛዉ የባሰ ጠረፍ ኦጋዴን እንዲመደብ የተደረገ ቢሆንም እሱ ከዎላይታ ልጆች ጋር የማይበጠስ ትስስር ፈጥሮ ነበርና ለለዉጥ ሕልሙ ተግባራዊነት እሳት ፊት መቆም ሲኖርበት እርዳታቸዉ አስፈልጎታል።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መሪ የነበሩ ወቅት ለበዓል ከባለቤታቸው ጋር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተጋብዘዉ በነበራቸዉ ቆይታ እንደሚከተለዉ ይላሉ የአባታቸዉን ታሪክ ሲያወሩ "አባቴ በትምህርት በጣም በጣም ጎቦዝ ነበር። በነሱ ጊዜ በዎላይታ አካባቢ እስከስምንተኛ ክፍል ብቻ ነበር ትምህርት የነበረዉ። እና ተፈሪ መኮንን ነው እስከ አስራ አንደኛ የተማረዉ።

የ53ቱ የነገርማሜ ብጥብጥ ተሳታፊ ስለነበረ ነው ትምህርቱን አቋዋርጦ ገጠር የገባዉ። አባቴ ሸሽቶ ነው ገጠር የገባዉ፣ ትምህርቱን አልጨረሰም። ሸሽቶ ገጠር ገብቶ ...ገርማሜ ነዋይ የዎላይታ አዉራጃ አስተዳዳሪ ነበር እና ከእነዚህ ከዎላይታ ከመጡ ሐይስኩል ከሚማሩ ጋር ኔትዎርክ ፈጥሮ ነበር። ይሄ ነገር ሲነቃና የእነ ገርማሜው ሲከሽፍ አባቴና ጓዋደኞቹ መሸሽ ነበረባቸዉ። ሸሽቶ ገበሬ መስሎ ገጠር ገባ። "ኃይለማሪያም ደሳለኝ

በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዉ የተሳተፉና ያመለጡ የዎላይታ ተማሪዎች ጉዳይ አንደኛ ጀግንነት ሲሆን ፣ ሁለተኛ በወቅቱ ስዩመ እግዚአብሔር ነኝ የሚለዉን አስከፊ ንጉሳዊ ሥርዓት ለመገርሰስ ከተራማጅ ኃይሎች ጋር ተሰልፎ መንቀሳቀስ ቀድሞ መንቃትን ያመለክታል።

በወቅቱ በቁጥጥር ስር ዉሎ ተገድዶ በረዲዮ ለሕዝብ መልዕክት ያስተላለፈዉ ልዑል አልጋ ወራሸ አስፋወሰን እንደሚከተለዉ ብሎ ነበር፣ ለተማሩ ወጣቶች ተሳትፎም ጭምር እዉቅና የሚሰጥ ንግግር ያቀረበዉ“ የኢትዮጵያ ህዝብ ከ3000 አመታት በላይ የሚታወቅ ታሪክ አለው።

VOA ኃይለማርያም ደሳለኝ ከ2010 ጀምሮ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደነበሩ ጠቅሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ በወቅቱ ለተወሰኑ ዓመታት አብሯቸዉ የሰራዉን የአቶ ጌታቸው ረዳን ምስክርነት አቅርቦ "ኃይለማርያም የጥሩ ስብዕና ክህሎት ያለዉ መሪ ነው። በጣም ትሁትና፣ ከሰዎች ጋር ወዳጅነት መፍጠር የሚችል ሰዉ ነው። ከየትኛውም ሰዉ፣ ምናልባትም ከሳቸው በታች ካለ ሰዉም ቢሆን ትምህርት ከመቅሰም የማይቦዝን ሰዉ ነው" ሲል መስክሮአል።

ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ሲወርዱ የኢህአዴግ እና የህውሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ የነበሩት ጌታቸው ረዳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት "ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በነበረው የስልጣን ሽግግር ወቅት የወንበሩ ፈላጊ እና እኔ ነኝ አዋቂው የሚለው ሰው ቁጥር በመብዛቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስራቸውን በሚገባ እንዲሰሩ ከመርዳት ይልቅ ሙከራዎቻቸውንና እንቅስቃሴዎቻቸውን የመንቀፍ ነገር በዝቶ ነበር" ብለዋል።

Wolaita Times

20 Jan, 14:28


የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩበት ስድስት አመታት ለሀገሪቱ ሰላምና ዕድገት እንዲሁም አለምአቀፍ ተሰሚነት የተሻለ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ውጤታማ ስራ እየሰሩ በነበሩበት ወቅት በተገቢው ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ እንቅፋት በመፈጠሩ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣንን በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁ መሪ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከፓለቲካ በመውጣት በተለያዩ አለምአቀፋዊ ተቋማት ላይ የመሪነት ሚና በመጫወት እንዲሁም በሀገራችን የተለያዩ ልማት ስራዎች እንዲከናወኑ የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

ወደ ዋናው ነጥብ እንመልሳችሁና እንደሚታወቀው "ኢትዮጵያ ከተመሰረተች ጀምሮ አብዛኛው መሪዎቿ በሀይማኖት፣ በብሄር ወይንም በቡድን ውስጥ ተደብቀው መምራታቸው እስከ ዛሬ ከባድ ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል። ነገር ግን አሁንም ስልጣንን ከብሄር፣ ከሀይማኖትና፣ ከቡድን አስተሳሰብ የፀዳ፥ ያለ ማንም ድጋፍና በራሱ ጥረትና እግዚአብሔር በሰጠው እውቀትና ክህሎት እስከ ቤተመንግሥት ድረስ ጭንቅላት ብቻ ይዘው የመግባት አቅም ያላቸው እንደ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂነር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የሀይማኖት፣ የብሄር፣ የቡድን ኮታ ስልጣን ለመያዝ መስፈርት ማድረጓን ከቀጠለች፦ የእርስበርስ ጦርነት፣ ሁዋላ ቀርነትና ድህነት፣ ችግርና መከራ እየተፈራረቁ ይቀጥላሉ ... ለመሆኑ ልዩነቶችን በመቻቻል በማሸነፍ ኢትዮጵያን በጋራ ተባብረን ለማሳደግ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው ? የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር ምን ብለው ያስባሉ ? ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል?

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5392

Wolaita Times

19 Jan, 15:12


"የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን በእሳቸው መፈረም ያለበትን ጉዳይ በቀጥታ ህጋዊ አሰራር ተከትለው በመፈረም እንዲሁም ሪከርድ ተደርገው በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ተደርገው ደብዳቤዎች እንዲወጡ እየተደረገ ባለበት ሀገር ከዚህ አሰራር ባፈነገጠ መንገድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን በተቃራኒው የእሳቸውን ስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ይዘው በመዞር በህገወጥ መንገድ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ መቀጠሉ በክልሉ ያለው ህገወጥነት ያለበት ደረጃ አመላካች ነው" በማለት ህገወጥ አሰራርን ተችተዋል።

አክለውም "ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ጉዳዮችን አሠራርን ሳይጠብቅ በአቋራጭ የርዕሰ መስተዳድሩ ይሁንታን እንደ ህግ በመቁጠር ከአሠራር ዉጪ በርዕሰ መስተዳድሩ ማስታዉሻ ብቻ የተግባሩ ባለቤት የሆነዉ ተቋምም ሆነ የአሠራርና አፈፃፀም መመሪያ ሳይከተል በብጣሽ ማስታወሻ የሳቸዉ የስም ቲቴር እየተመታ የሚሰራዉ የማዕድን ሥራ ፈቃድም ሆነ የተለያዩ የኮንቶርባንድ ሥራ ህደቶችና በህገ ወጥነት የተያዙ ሰዎችም ሆነ ንብረቱ የማስለቀቅና ህገ ወጥ ሥራ የሚፈፀመዉ በዚሁ ማህተሙን በእጁ ይዞ በሚንቀሳቀሰዉና አብዛኛው ጊዜ ከአዲስአበባ ሆኖ የሚሰራው በአቶ ባህሩ ሙላቱ መሆኑ ሁሉ የክልላችን አመራር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ" ብለዋል።

"እናዉቃለን ነገር ግን ከተናገርን እንጠፋለን ብሎ ዝም የተባለበት የአደባባይ ምስጥር ነዉ፤ ሌላዉን ብልሽት ይሄን ሚዲያ ተከታይ የሆኑ የተከበሩ ህዝቦችን ስለማይመጥን ለራሱ እንዲታረም በማስታወስ የሚታለፍ ስለሆነ ክቡር ሚዲያ ተከታዮቻችን ከልታረመና በትላንቱ ሥራዓት አልበኝነት የሚቀጥል ከሆነ በምስል የተደገፈ የሱነትንና የአለቆቹንም ጭምር እዉነተኛ ማንነታቸዉን የሚያሳይ የብልሽት መረጃ ሊናቀርብ የሚንገደድ መሆናችን ጭምር ለማስታወቅ እንወዳለን" በማለት ብልሹ አሰራርን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛው በተለይም የሹመት፣ የሽረት እንዲሁም በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ገቢ አሰራር ያላለፉ ህገወጥ እንደሆኑና በዚሁም ምክንያት ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲 🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ 🙌

በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏

#Ethiopia #southethiopia

የርዕሰ መስተዳድሩ ደላላ👇
https://wolaitatimes.com/?p=5388

Wolaita Times

19 Jan, 15:12


እኚህ አመራር ምክንያቱን ሲያስቀምጡ "ርዕሰ መስተዳድሩ ከአመራር ብስለትና ምግባር ራቁ እንጅ ለሳቸዉ ደህንነትም ይሁን ለክልሉ ተረጋግቶ ለመቀጥልም በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በተለያዩ ሥራ ኃላፊነት ቦታ የሚሾሙ ሰዎች ከቦታዉ ሥራ ክብደትና ፍላጎት አንፃር በልዩ እይታ ከየትኛዉም ብሔር ይሁን ከይትኛዉ ማህበራዊ መሠረት ይሁን ውጤታማነታቸው ብቻ መስፈርት ተደርጎ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ በየዘርፉ የሚንመለከታቸዉ ለሰሚ ጆሮ ጭዉ የምል አሳፋሪ ሥራዎች ወይም ድርጊቶች ባልተፈፀሙ ነበር" በማለት ሁኔታውን አብራርተዋል።

ለአብነትም "የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፕሮቶኮልና ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ባህሩ ሙላቱ በሥራ ልምድም ይሁን ከቦታዉ ከፍተኛነት አንፃር የልጁ ስነ-ምግባር ጉዳይም ለዛ በፍፁም የሚያበቃና የሚታሰብ አልነበረም፤ ነገር ግን የአቶ ጥላሁን አክስት ልጅ መሆኑ ብቻ የቦታዉ መስፈርት አደረገዉ እንጅ፤ ልጁ የትም ሲዞር ፈላጭ ቆራጭ እሱ እንደሆነ እና በመጠጥ ቤት በጭፈራ ቦታ አመራርን ከሚሾምና ከሚያወርድ ፓርቲ ማዕል አመራር ጋር አብሮ በመሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ የስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ስላሌ አመራርን ከአመራር ምዘና እና ዲስፕሊን መመሪያ ዉጪ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ እየሰራ ነዉ የሚገኘዉ" ብለዋል።

"የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን በእሳቸው መፈረም ያለበትን ጉዳይ በቀጥታ ህጋዊ አሰራር ተከትለው በመፈረም እንዲሁም ሪከርድ ተደርገው በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ተደርገው ደብዳቤዎች እንዲወጡ እየተደረገ ባለበት ሀገር ከዚህ አሰራር ባፈነገጠ መንገድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን በተቃራኒው የእሳቸውን ስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ይዘው በመዞር በህገወጥ መንገድ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ መቀጠሉ በክልሉ ያለው ህገወጥነት ያለበት ደረጃ አመላካች ነው" በማለት ህገወጥ አሰራርን ተችተዋል።

አክለውም "ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ጉዳዮችን አሠራርን ሳይጠብቅ በአቋራጭ የርዕሰ መስተዳድሩ ይሁንታን እንደ ህግ በመቁጠር ከአሠራር ዉጪ በርዕሰ መስተዳድሩ ማስታዉሻ ብቻ የተግባሩ ባለቤት የሆነዉ ተቋምም ሆነ የአሠራርና አፈፃፀም መመሪያ ሳይከተል በብጣሽ ማስታወሻ የሳቸዉ የስም ቲቴር እየተመታ የሚሰራዉ የማዕድን ሥራ ፈቃድም ሆነ የተለያዩ የኮንቶርባንድ ሥራ ህደቶችና በህገ ወጥነት የተያዙ ሰዎችም ሆነ ንብረቱ የማስለቀቅና ህገ ወጥ ሥራ የሚፈፀመዉ በዚሁ ማህተሙን በእጁ ይዞ በሚንቀሳቀሰዉና አብዛኛው ጊዜ ከአዲስአበባ ሆኖ የሚሰራው በአቶ ባህሩ ሙላቱ መሆኑ ሁሉ የክልላችን አመራር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ" ብለዋል።

"እናዉቃለን ነገር ግን ከተናገርን እንጠፋለን ብሎ ዝም የተባለበት የአደባባይ ምስጥር ነዉ፤ ሌላዉን ብልሽት ይሄን ሚዲያ ተከታይ የሆኑ የተከበሩ ህዝቦችን ስለማይመጥን ለራሱ እንዲታረም በማስታወስ የሚታለፍ ስለሆነ ክቡር ሚዲያ ተከታዮቻችን ከልታረመና በትላንቱ ሥራዓት አልበኝነት የሚቀጥል ከሆነ በምስል የተደገፈ የሱነትንና የአለቆቹንም ጭምር እዉነተኛ ማንነታቸዉን የሚያሳይ የብልሽት መረጃ ሊናቀርብ የሚንገደድ መሆናችን ጭምር ለማስታወቅ እንወዳለን" በማለት ብልሹ አሰራርን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛው በተለይም የሹመት፣ የሽረት እንዲሁም በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ገቢ አሰራር ያላለፉ ህገወጥ እንደሆኑና በዚሁም ምክንያት ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲 🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ 🙌

በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏

#Ethiopia #southethiopia

የርዕሰ መስተዳድሩ ደላላ

የፕሬዘዳንቱን ስምና የፊርማ ቲቴር ይዘው የሹመት ሆነ ሌሎች ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ የሚያድል ግለሰብ



የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሁናዊ የአመራር ሥርዓት ሁኔታ እና እየሆነ ያለ ምግባር ቀዉስ ማን ያርመዉ ሁሉም ያዉ ነዉ!!ግለሰቡ "የርዕሰ መስተዳድሩን ስምና የፊርማ ቲቴር በቦርሳው ይዘው በመዞር የሹመት ሆነ ሌሎች ወሳኝ ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ እንደሚያወጣ" ተነገረ።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከዚሁ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በአሰራር ያላለፉ በመሆኑ ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን አረጋግጧል።

አንድ ሌለኛው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቅ ከፍተኛ አመራር እንደገለፁልን "አመራር ሲጀመር መሾም ያለበት የቤተሰብ ካምፓኒ ይመስል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የስጋ ዘመድ የሆኑ አካላት እየተፈለጉ በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት በልምድና በሙያ ብቃት በተለያዬ ቦታ በሀላፊነት የሰሩበትና በቦታዉ ሊኖራቸዉ የሚገባ ዲስፕሊን ማሟላትንም ጭምር በትርጉም ተመዝኖ ለክልሉ ዉጠታማነትና ቀጣይነት ፋይዳዉ ብዙ ስለሆነ መሾም እየተገባቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ የአክስት ልጅ፣ የአጎት ልጅ፣ የምስት ወንድም እና በመሳሰሉ በስጋ ዝምድና እና በማህበራዊ ቁርኝት መነሻ በአመራር መስፈርት ዉስጥ ሊገቡ የማይገቡ ሀሳቦችን የአመራር መመልመያ መስፈርት አድርጎ በማምጣቱ አሁን ላለዉ ለክልሉ ብልሽት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ማንም የምናገረዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ" ብለዋል።

እኚህ አመራር ምክንያቱን ሲያስቀምጡ "ርዕሰ መስተዳድሩ ከአመራር ብስለትና ምግባር ራቁ እንጅ ለሳቸዉ ደህንነትም ይሁን ለክልሉ ተረጋግቶ ለመቀጥልም በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በተለያዩ ሥራ ኃላፊነት ቦታ የሚሾሙ ሰዎች ከቦታዉ ሥራ ክብደትና ፍላጎት አንፃር በልዩ እይታ ከየትኛዉም ብሔር ይሁን ከይትኛዉ ማህበራዊ መሠረት ይሁን ውጤታማነታቸው ብቻ መስፈርት ተደርጎ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ በየዘርፉ የሚንመለከታቸዉ ለሰሚ ጆሮ ጭዉ የምል አሳፋሪ ሥራዎች ወይም ድርጊቶች ባልተፈፀሙ ነበር" በማለት ሁኔታውን አብራርተዋል።

ለአብነትም "የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፕሮቶኮልና ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ባህሩ ሙላቱ በሥራ ልምድም ይሁን ከቦታዉ ከፍተኛነት አንፃር የልጁ ስነ-ምግባር ጉዳይም ለዛ በፍፁም የሚያበቃና የሚታሰብ አልነበረም፤ ነገር ግን የአቶ ጥላሁን አክስት ልጅ መሆኑ ብቻ የቦታዉ መስፈርት አደረገዉ እንጅ፤ ልጁ የትም ሲዞር ፈላጭ ቆራጭ እሱ እንደሆነ እና በመጠጥ ቤት በጭፈራ ቦታ አመራርን ከሚሾምና ከሚያወርድ ፓርቲ ማዕል አመራር ጋር አብሮ በመሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ የስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ስላሌ አመራርን ከአመራር ምዘና እና ዲስፕሊን መመሪያ ዉጪ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ እየሰራ ነዉ የሚገኘዉ" ብለዋል።

Wolaita Times

19 Jan, 15:12


ግለሰቡ "የርዕሰ መስተዳድሩን ስምና የፊርማ ቲቴር በቦርሳው ይዘው በመዞር የሹመት ሆነ ሌሎች ወሳኝ ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ እንደሚያወጣ" ተነገረ።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከዚሁ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በአሰራር ያላለፉ በመሆኑ ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን አረጋግጧል።

አንድ ሌለኛው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቅ ከፍተኛ አመራር እንደገለፁልን "አመራር ሲጀመር መሾም ያለበት የቤተሰብ ካምፓኒ ይመስል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የስጋ ዘመድ የሆኑ አካላት እየተፈለጉ በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት በልምድና በሙያ ብቃት በተለያዬ ቦታ በሀላፊነት የሰሩበትና በቦታዉ ሊኖራቸዉ የሚገባ ዲስፕሊን ማሟላትንም ጭምር በትርጉም ተመዝኖ ለክልሉ ዉጠታማነትና ቀጣይነት ፋይዳዉ ብዙ ስለሆነ መሾም እየተገባቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ የአክስት ልጅ፣ የአጎት ልጅ፣ የምስት ወንድም እና በመሳሰሉ በስጋ ዝምድና እና በማህበራዊ ቁርኝት መነሻ በአመራር መስፈርት ዉስጥ ሊገቡ የማይገቡ ሀሳቦችን የአመራር መመልመያ መስፈርት አድርጎ በማምጣቱ አሁን ላለዉ ለክልሉ ብልሽት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ማንም የምናገረዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ" ብለዋል።

እኚህ አመራር ምክንያቱን ሲያስቀምጡ "ርዕሰ መስተዳድሩ ከአመራር ብስለትና ምግባር ራቁ እንጅ ለሳቸዉ ደህንነትም ይሁን ለክልሉ ተረጋግቶ ለመቀጥልም በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በተለያዩ ሥራ ኃላፊነት ቦታ የሚሾሙ ሰዎች ከቦታዉ ሥራ ክብደትና ፍላጎት አንፃር በልዩ እይታ ከየትኛዉም ብሔር ይሁን ከይትኛዉ ማህበራዊ መሠረት ይሁን ውጤታማነታቸው ብቻ መስፈርት ተደርጎ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ በየዘርፉ የሚንመለከታቸዉ ለሰሚ ጆሮ ጭዉ የምል አሳፋሪ ሥራዎች ወይም ድርጊቶች ባልተፈፀሙ ነበር" በማለት ሁኔታውን አብራርተዋል።

ለአብነትም "የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፕሮቶኮልና ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ባህሩ ሙላቱ በሥራ ልምድም ይሁን ከቦታዉ ከፍተኛነት አንፃር የልጁ ስነ-ምግባር ጉዳይም ለዛ በፍፁም የሚያበቃና የሚታሰብ አልነበረም፤ ነገር ግን የአቶ ጥላሁን አክስት ልጅ መሆኑ ብቻ የቦታዉ መስፈርት አደረገዉ እንጅ፤ ልጁ የትም ሲዞር ፈላጭ ቆራጭ እሱ እንደሆነ እና በመጠጥ ቤት በጭፈራ ቦታ አመራርን ከሚሾምና ከሚያወርድ ፓርቲ ማዕል አመራር ጋር አብሮ በመሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ የስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ስላሌ አመራርን ከአመራር ምዘና እና ዲስፕሊን መመሪያ ዉጪ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ እየሰራ ነዉ የሚገኘዉ" ብለዋል።

"የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን በእሳቸው መፈረም ያለበትን ጉዳይ በቀጥታ ህጋዊ አሰራር ተከትለው በመፈረም እንዲሁም ሪከርድ ተደርገው በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ተደርገው ደብዳቤዎች እንዲወጡ እየተደረገ ባለበት ሀገር ከዚህ አሰራር ባፈነገጠ መንገድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን በተቃራኒው የእሳቸውን ስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ይዘው በመዞር በህገወጥ መንገድ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ መቀጠሉ በክልሉ ያለው ህገወጥነት ያለበት ደረጃ አመላካች ነው" በማለት ህገወጥ አሰራርን ተችተዋል።

አክለውም "ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ጉዳዮችን አሠራርን ሳይጠብቅ በአቋራጭ የርዕሰ መስተዳድሩ ይሁንታን እንደ ህግ በመቁጠር ከአሠራር ዉጪ በርዕሰ መስተዳድሩ ማስታዉሻ ብቻ የተግባሩ ባለቤት የሆነዉ ተቋምም ሆነ የአሠራርና አፈፃፀም መመሪያ ሳይከተል በብጣሽ ማስታወሻ የሳቸዉ የስም ቲቴር እየተመታ የሚሰራዉ የማዕድን ሥራ ፈቃድም ሆነ የተለያዩ የኮንቶርባንድ ሥራ ህደቶችና በህገ ወጥነት የተያዙ ሰዎችም ሆነ ንብረቱ የማስለቀቅና ህገ ወጥ ሥራ የሚፈፀመዉ በዚሁ ማህተሙን በእጁ ይዞ በሚንቀሳቀሰዉና አብዛኛው ጊዜ ከአዲስአበባ ሆኖ የሚሰራው በአቶ ባህሩ ሙላቱ መሆኑ ሁሉ የክልላችን አመራር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ" ብለዋል።

"እናዉቃለን ነገር ግን ከተናገርን እንጠፋለን ብሎ ዝም የተባለበት የአደባባይ ምስጥር ነዉ፤ ሌላዉን ብልሽት ይሄን ሚዲያ ተከታይ የሆኑ የተከበሩ ህዝቦችን ስለማይመጥን ለራሱ እንዲታረም በማስታወስ የሚታለፍ ስለሆነ ክቡር ሚዲያ ተከታዮቻችን ከልታረመና በትላንቱ ሥራዓት አልበኝነት የሚቀጥል ከሆነ በምስል የተደገፈ የሱነትንና የአለቆቹንም ጭምር እዉነተኛ ማንነታቸዉን የሚያሳይ የብልሽት መረጃ ሊናቀርብ የሚንገደድ መሆናችን ጭምር ለማስታወቅ እንወዳለን" በማለት ብልሹ አሰራርን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛው በተለይም የሹመት፣ የሽረት እንዲሁም በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ገቢ አሰራር ያላለፉ ህገወጥ እንደሆኑና በዚሁም ምክንያት ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲 🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ 🙌

በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏

#Ethiopia #southethiopia

የርዕሰ መስተዳድሩ ደላላ

የፕሬዘዳንቱን ስምና የፊርማ ቲቴር ይዘው የሹመት ሆነ ሌሎች ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ የሚያድል ግለሰብ



የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሁናዊ የአመራር ሥርዓት ሁኔታ እና እየሆነ ያለ ምግባር ቀዉስ ማን ያርመዉ ሁሉም ያዉ ነዉ!!ግለሰቡ "የርዕሰ መስተዳድሩን ስምና የፊርማ ቲቴር በቦርሳው ይዘው በመዞር የሹመት ሆነ ሌሎች ወሳኝ ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ እንደሚያወጣ" ተነገረ።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከዚሁ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በአሰራር ያላለፉ በመሆኑ ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን አረጋግጧል።

አንድ ሌለኛው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቅ ከፍተኛ አመራር እንደገለፁልን "አመራር ሲጀመር መሾም ያለበት የቤተሰብ ካምፓኒ ይመስል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የስጋ ዘመድ የሆኑ አካላት እየተፈለጉ በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት በልምድና በሙያ ብቃት በተለያዬ ቦታ በሀላፊነት የሰሩበትና በቦታዉ ሊኖራቸዉ የሚገባ ዲስፕሊን ማሟላትንም ጭምር በትርጉም ተመዝኖ ለክልሉ ዉጠታማነትና ቀጣይነት ፋይዳዉ ብዙ ስለሆነ መሾም እየተገባቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ የአክስት ልጅ፣ የአጎት ልጅ፣ የምስት ወንድም እና በመሳሰሉ በስጋ ዝምድና እና በማህበራዊ ቁርኝት መነሻ በአመራር መስፈርት ዉስጥ ሊገቡ የማይገቡ ሀሳቦችን የአመራር መመልመያ መስፈርት አድርጎ በማምጣቱ አሁን ላለዉ ለክልሉ ብልሽት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ማንም የምናገረዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ" ብለዋል።

Wolaita Times

19 Jan, 13:05


በቅርቡ የኮዎ ጦና አለም አቀፍ ስቴዲየም እውን ይሆናል ?! እንዴት ? መፍትሔውስ ? ..... የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

በቅድሚያ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እንላለን🙏 መልካም ንባብ👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በቅርቡ የዎላይታ ዞን፣ አለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የእግርኳስ ሜዳና የመሮጫ track ያለዉን እንዲሁም ከ50ሺ በላይ ሰዉ የሚይዝ ስቴዲየም ለመገንባት አቅዶ የቀድሞ ዲዛይን ተሻሽሎ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል። በቅድሚያ ምን ተሰማዎት ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል። የአካባቢዉ ሕዝብ ያለዉ የስፖርት ፍቅርና የወጣቶቻችንም በእስፖርቱ ለዘመናት የዘለቀ ዉጤታማነትን ያገናዘበ ነው። ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አንዳች ትርጉም ያለዉ ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን አልጠራጠርም። ስቴዲየሙ ግን የሚይዘዉ ሰዉ ቁጥር ግን ከ60ሺ በላይ ቢሆን ባይ ነኝ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት ወደፊት ለግንባታዉ ቴሌቶን ማዘጋጀትን የመሳሰሉ ገቢ ለማሰባሰብ ብዙ ዘዴዎችን መጠቀም ሊኖርብን ቢችልም፣ አሁን እንደመነሻ ምልኣተ ሕዝቡን ለማሳተፍ መሰራት አለበት ብለዉ የሚጠቁሙን ነገር ካለ ቢገልጹልን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ዎላይታ ሶዶ የደቡብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ከተማ እንዲሁም የፖለቲካ እና የአስተዳደር ማዕከል፣ የሰፊዉ ደቡብም የታሪክና የኢኮኖሚ ማዕከል እንደመሆኑ ክልሉ ሆነ የፌደራሉ መንግስት አንዳች ደረጃ ፕሮጀክቱን የሚያደርስ መነሻ ገንዘብ መስጠት አለባቸዉ ብዬ አምናለሁ።

ከዛ ዉጪ ግን ሁሉም ሕዝባችንና የልማት አጋር ኢትዮጵያዉያንን ባሳተፈ መልኩ ትልቅ ገቢ ለመሰብሰብ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ ጋር በተለዬ ሁኔታ በመተባበር ከፍተኛ ና አጓዋጊ ሽልማቶችን የሚያስገኝ በ100ብር የሚሸጥ የቶምቦላ ሎተሪ በማዘጋጀት የተሻለ አማራጭ ይመስለኛል።

ሎተሪዉን፦ በ100ብር፦ 1 የእጣ ቁጥር ያለዉ
በ1ሺ ብር፦ 10 የእጣ ቁጥር ያለዉ
በ10ሺ ብር፦ 100የእጣቁጥር ያለዉ አድርጎ ማሳተም ይቻላል።

⨳⨳ባለ 100 ብሩን ለ1ሚሊየን ሰዉ ከሸጥን፣ 100 ሚሊየን ብር ይገኛል።
⨳ባለ 1ሺ ብሩን ለ 100ሺ ሰዉ ከሸጥን 100ሚሊየን ብር
⨳ባለ10 ሺ ብሩን ለ10ሺ ሰዉ ከሸጥን 100ሚሊየን ብር

⨳ባለ 10ሺ ብሩን 10በአንዴ በ100ሺ ብር የሚገዙ 500 ሰዎችን ካገኘን 50 ሚሊየን
⨳ባለ 10ሺ ብሩን 5በአንዴ በ50ሺ ብር የሚገዙ1000 ሰዎችን ካገኘን 50 ሚሊየን
⨳ባለ 10 ሺ ብሩን 100በአንዴ በ1 ሚሊየን ብር የሚገዙ 50 ሰዎች ካገኘን 50 ሚሊየን እናገኛለን።

በተጨማሪ ሎተሪዉ በዲጅታል አማራጭም ከተሸጠ ተጨማሪ ሰዉ የሚገዛዉ ይመስለኛል

ይህንን ካደረግን፣ በመላዉ ኢትዮጵያ ለሚኖረዉ ሕዝባችንና ለልማት ወዳድ ኢትዮጵያዉያ፣ ለዳያስፖራዉ፣ በከፍተኛ እርብርብ ከሸጥን በትንሹ፦ 350ሚሊየን ማሰባሰብ ይቻላል፣ የሕትመት ወጪዉ እንዳለ ሆኖ መንግስት ግብር እንዳይከፈልበት ብያግዝ፣ ከሽልማቱ በሁዋላ የተጣራ 300 ሚሊየን ብር ማሰባሰብ ይቻላል።

ሽልማት 10 ሚኒ ባስ፣ 10 የቤት መኪናና 30 ሞተር ሳይክል ቢደረግ፣ መንግስት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ካገዘ 50 የእድለኛ እጣ ይኖራል ማለት ነው። ባለሐብቶች ጀግሞ ለእጣ የሚሆኑ ነገሮችን በፈቃደኝነት ከለገሱ የእድለኛ ቁጥር መጨር ይቻላል። በዚህ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ በቴሌዠዥኖች አጠያይቆ በነጻ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ ከተደረገ፣ ከላይ ከተጠቀሰዉ በላይ ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል።

በተለይ ባለ 100ብሩን በብዙ ሚሊየን መሸጥ ይቻላል፣ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸዉን ደግሞ በቅድሚያ ሰዉ እየከፈለ የሚያገኝበት መንገድ ከተመቻቸ፣ በተለይ ተቋማት ወይንም በየተቋማቱ ያሉ ሰራተኞች እያዋጡ ከገዙ ብዙ መሸጥ የሚቻል ይመስለኛል።

በመላዉ ኢትዮጵያ ያለዉ የእስፖርቱ ማህበረሰብ ሎተሪዉን እንደየአቅሙ እንዲገዛ ቢደረግ፣ የተለያዩ ሚዲያ የእስፖርት ፕሮግራሞች ለአድማጭ ተመልካቶቻቸዉ እየገዙ በሽልማት መልክ ቢያስተላልፉ፣ በጥቂት ወራት ዉስጥ ግባችንን ማሳካት የሚቻል ይመስለኛል።

ይህ የሎተሪ ቲኬት ለእድል ብቻ የሚገዛ ሳይሆን በዎላይታ ሶዶ ለሚገነባዉ አለም አቀፍ ስቴዲየም የሚደረግ የአስተዋጽኦ ማረጋገጫ ሰነድም ስለሚሆን ታሪካዊ ነው። በባዶ ሰዉን ገንዘብ ለግሱ ከማለትም በሎተሪ መልክ መሸጡም የተሻለ ይመስለኛል። ይሕንን አሁኑኑ የዞኑ መንግስት ማድረግ የሚችል ይመስለኛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እንላለን🙏 በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Dichasport

Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5383

Wolaita Times

18 Jan, 16:11


የአሜሪካው ተመራጭ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሌጋሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በመምራት በበዓለ ስመታቸው እንዲገኙ መጋበዛቸው ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የምታደሙ የአፍሪካ መሪዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአዘጋጆቹ በኩል ይፋ ተደርጓል።

እንደ ደይሊትራስ ዘገባ ግብዣው በጥር 13 ቀን 2025 ለወጣቱ የናይጄሪያ የንግድ ሥራ መሪ ዶ / ር ኡዞቹክ በተላከ ደብዳቤ “ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕን በማክበር የመድብለ ባህላዊ ጥምረት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምረቃ ቦል አስተናጋጅ ኮሚቴን በመወከል እንዲገኙ ስንጋብዝ በታላቅ ክብር ነው ይላል ብሏል።

ይህ ታላቅ ዝግጅት በጥር 20፣ 2025 በዋሽንግተን የሚካሄድ ሲሆን በማዳም ፍራንያ ኢ ካብራል ሩዪዝ መሪነት ከአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት በቀረበው ሀሳብ እንደተገለጸው ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅዖ እና አመራር እውቅና በመስጠት፣ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ በመገኘታችን ታላቅ ክብር እንሰጣለን ብሏል።

በዚሁም የወቅቱን የአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በዩኤስ ፕሬዝዳንታዊ የትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የሚመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሆኑም ዘገባው ጠቅሷል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #USA #DonaldTrump #HailemariamDesalegn #Africa

Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5378

Wolaita Times

17 Jan, 13:22


የለውጥ ናፋቂዎች ይጠይቃሉ ......

መንግስትን፣ ህዝብንና ህሊናን በመዋሸት ለስልጣን ዕድሜ መስገብገብ ከነዉርም በላይ ሀጥያት መሆኑን ያዉቃሉ ክቡር ርዕሰ መስተዳድር ???

መንግስትን፣ ህዝብንና ህሊናን በመዋሸት ለስልጣን እድሜ መስገብገብ ከነዉርም በላይ ሀጥያት መሆኑን የማይገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩና ቡድኑ ሰሞኑን በሚድያ ጋጋታ መሬት ላይ ያለዉን ሀቅ ለመደበቅ ጥረት እያደረጉ ነዉ፡፡ ማህበራዊ ሚድያዉ የእርሻ ማሳ ብሆን ኖሮ እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚበለፅግ ክልል ያለ አይመስለንም፡፡

ክልሉ ዉስኑን በጀት ለህዝብ አንገብጋቢዉ ጉዳዮች ቅድሚያ ከማድረግ ይልቅ የመድረክ ድስኩርንና ማህበራዊ ሚድያን በተከፋይ ሰራዊት የርዕሰ መስተዳድሩን ገፅታ በመገንባት ላይ ተጠደምዷል፡፡

እንደ ሀገር ከተያዙ አቅጣጫዎች አንዱ በ2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገው “የሌማት ትሩፋት” መርሐ-ግብር የአገርን ጓዳ በእንስሳት፣ በዶሮ እና በማር ምርቶች በማትረፍረፍ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የተገኘውን ስኬት መድገም ነው።

ፕሮጀክቱ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊያን ሌማት ምሉዕ የማድረግ ትልም ያለዉና የዜጎችን ክብር የሚመልስ ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው።

ይህ ኢንሼትቭ ከክልሉ ካለዉ እምቅ ፀጋ ጋር ተዳምሮ ተገብዉን አመራር ብያገኝ ኖሮ የሀገርቱ ተሞክሮ ማዕከል የሚሆን ፕሮጀክት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ርዕሰ መስተዳድሩ የሀገርቱን መንግስትና ፓርቲ አቅጣጫ በአፍ የሚያወሩ እንጅ ከልብ ያልተቀበሉ በመሆናቸዉ በምትካቸዉ የራሳቸዉ ኢንሼትብ ቀርፀዉ ፕሮፖጋንዳ በማሰራት ብቻ ጊዜዉን አባክኗል፡፡

ለዚህ ማሳያ እንድሆን በደቡብ ኢት/ያ ክልል አገራዊና ክልላዊ ኢንሸትቮችን ለመገመገምና ያሉበት ደረጃ በማየት ለሚቀጥለዉ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ለመጣዉ ፌዴራል ሱፔርቭዥን ቡድን በማስመሰል ተግባር አቻ የማይገኝለት የክልላችን ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ በሳቸዉ አመራር ሰጪነት ተሰራ ተብሎ ያቀረቧቸዉ ልማቶች ዉስጥ አንደኛዉ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሙዝና የቲማትም ማሳ፤ የጨንቻ የወተት መንደር፤ የጌድዮ ቡና፤ በአሪ ዞን በግል ባለሀብት እየለሙ ያሉ የእርሻ ማሳ፤ በዩኒቨርስት ምሩቃን የተመሰረተዉ የዎላይታ ሶዶ ኤክሶዳስ ኢንተርፕራይዝ እና በግል ባለሀብት እየለማ የሚገኘዉን የብላቴ እርሻ ናቸዉ፡፡

በተጨማር ጠቅላይ ሚኒስተሩ በተደጋጋም አርባምንጭን ከተማ ስለሚጎበኙ እሳቸዉን ለማስደሰት ሲባል ከግንቦት 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2017 ዓ.ም ድረስ ልዩ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ስምርት ተሰቷቸዉ በዘመቻ መልክ ከክልሉ በጀት ተመድቦ በአርባምንጭ ከተማ የተሰራዉ የሌማት ትሩፋት ሞዴል ማሳያ የተሰራዉ ነዉ፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን በተለያዬ አጋጣም አብዘኛዉ ሰዉ ከመቼ ጀምሮ የተሰሩ ፕሮጀክቶችና የርዕሰ መስተዳድሩ አመራር ሚና ምን ያክል እንደሆነ የሚያዉቃቸዉ ስለሆነ ትዝብቱን ለህዝብ መተዉ ተገብ ነዉ፡፡

ክልሉ ከተመሰረተ በኋላ በክልሉ የጠቅላይ ሚኒስተሩ ኢንሸቲቭ ከክልሉ ካለዉ እምቅ አቅም አንፃር እንዴት እንደታቀደ፤ ፈጻሚዉን የማብቃትና ተገብዉ ክትትትልና ግብረመልስ የተሰጠበት አግባብ እንድሁም የአመራር ትኩረትና ክብደት ተሰጥቶ የተመራበት ሂደትና ምን ዉጤት አስገኘ የሚለዉን አንስቶ መፈተሽ በሚዛናዊነት ለመረዳት ያግዘናል፡፡

ከላይ ጉብኝት የተደረገባቸዉ ፕሮጀክቶች መቼም ይሰራ፤ በማንም ይሰሩ እስከተሰሩ ድረስ የህዝባችን ናቸዉና አሻራቸዉን ላኖሩት ምስጋናና ዕዉቅና መስጠት ጤናማነት ነዉ፡፡

ዋናዉ ቁም ነገሩ የአቶ ጥላሁን ከበደ አመራር ከዚህ በፍት የተጀመሩ ተግባራት ላይ ምርታማነትን ከማሻሻል፤ ጥራታቸዉ ተወዳዳሪ እንድሆን፤ ተደራሽነታቸዉን ከማስፋትና ከግብይት ሥርዓት ማነቆዎች ከመፍታት አንጻር አበርክቷቸዉ ምን ያክል ነዉ የሚለዉን መሰረታዊ ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነዉ፡፡

ከዛ ዉጭ በአጠቃላይ ክልሉ ከተደራጀ ወዲህ የተጀመሩ ጥረቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ግን የክልሉ የአመራር ሥርዓቱ በሚከተሉት ጥያቄዎች ከዉሸት ሪፖርትና ከሚዲያ ባሻገር ብፈተሽ በጣም ዝቀተኛ ደረጃ ላይ እንሚገኝ መሬት ላይ ካለዉ ሀቅ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

👉 እንደ ሀገር ተገቢዉን የአመራር ትኩረት ተሰጥቶና በጥብቅ ዲስፒሊን በንቅናቄ ተመርቶ ወጤት እንድመዘገቡ የተባሉ የሌማት ትሩፋት፤ የከተማና የገጠር ኮርደር ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መሬት ላይ ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ???

👉 እንደ ሀገር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ጫና ለመቀነስ ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት ለማስቀረት የተቀየሰዉ የበጋ ስንዴ እርሻ ልማት ሥራ የክልሉ ጥረትና ከተገኘዉ ዉጤት አንጻር ከሀገራዊዉ አፈጻጸም የክልሉ ድርሻው ምን ያክል ነዉ ???

👉  የአርሶ አደር የኩታ ገጠም እርሻ ሥራ ባህል የዕድገት ምጣኔና የተክኖሎጅ አጠቃቀም ክልሉ ካለዉ አቅምና ከክልሉ ከሚጠበቀዉ አንጻር አፈጻጸሙ እንዴት ይመዘናል ???

👉  የእርሻ ሥራን ከማዘመንና ሜካናይዘሽንን ከማስፋፋት አንጻር በክልሉ በሁለም አከባቢ ለእርሻ ስራ የምርትና የድህረ ምርት ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም አንጻር የተደረገዉ ጥረትም ሆነ የተመዘገበዉ ዉጤት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ???

👉 የኤክስፖርት ማዕድን ምርትና ግብይትን በማስፋፋት የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ከማሳደግ ይልቅ የክልሉ ባለስልጣናት ሀብት ማካበቻ ለሆነዉ ማዕድን ዘርፍ አፈጻጻም እንዴት እንገመግማለን ???

👉 የኢንቨስትመንት እና የንግድ ሴክተሮችን አሰራር በማዘመን ለተገልጋዮች ያልተንዛዛና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ማግኘት እንድችል የውስጥ አሰራሮችን ዲጂታላይዝድ ከማድረግ አንጻር ምን ዉጤት አስመዘገብን ???

👉 የክልሉን አንጻራዊ ሠላምን በመድረክ ከመናገር ባሻገር ለሀገር ዉስጥና ለዉጭ ባለሀብት የስበት ማዕከል በማድረግ ለዜጎች ሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ምን ተጨባጭ ዉጤት አስመዘገብን ???

👉 የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከመደገፍ፤ በግብዓት አቅርቦት ያለውን ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር ላይ የት ደረጃ ላይ እንገኛለን ???

👉  የክልሉን የቱሪዝም አለኝታዎች የመለየትና መዳረሻዎችን የማልማት እንድሁም በማስተዋወቅ ለኢኮኖሚያዊ ብልፅግና ያለዉን አበርክቶ በመረዳት ከመንቀሳቀስ ረገድ የት ላይ እንገኛለን ???

በመሆኑም እንደ ክልል ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚያስችል መልክ የተቀረፁ ኢንሼትቮችና ሪፎርሞች እንደ ሀገር ከተጣሉ ግቦች አንጻር የክልሉን እምቅ አቅምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ታቅዶ በጠንካራ አመራር ተመርቶ የተገኙ ዉጤቶች በተገቢዉ ተፈትሾ የአመራር ሽልማትና ተጠያቂነት ካልሰፈነ በስተቀር እዚም እዛም ባልተደራጀና ተቋማዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ የተገኙ ዉስን ዉጤቶችን በሚዲያ በመቀባባት የስልጣን ግዜ ለማራዘም የሚደረገዉ የሚዲያ ፖለቲካ ህዝብንም ሆነ የሚመራዉን መንግስት ስለማይጠቅም በጊዜ መቆም አለበት በሚል የለውጥ ናፋቂዎች ይጠይቃሉ።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia
ለመሆኑ በሰፍርተኝነት ሀገራዊ ተልዕኮ መጣል ይቻላል ?👇https://wolaitatimes.com/?p=5376

Wolaita Times

16 Jan, 16:04


በክልሉ ምስረታ ወቅት የተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ብር በላይ ከካቢኔ ውሳኔ ውጪ በክልሉ ፕረዚዳንት ትዕዛዝ ብቻ ወጪ ቢደረግም የገባበት እንደማይታወቅ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ወቅት ከተለያዩ መንግሥታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከታዋቂ ግለሰቦች ጭምር ከተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ በየወቅቱ ያለማንም ካቢኔ ሆነ አስተባባሪ ውሳኔ በክልሉ ፕረዚዳንት በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ አዛዥነት እና በአቶ ተፈሪ አባቴ (የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አማካይነት ወጪ የተደረገ ቢሆንም ያለበት ቦታም ሆነ ምን ያህሉ ጥቅም ላይ እንደዋለም እንደቀረም እንደማይታወቅ ያገኘነው የሰነድ መረጃ ያመለክታል፡፡

በክልሉ የካፒታል በጀት/ኘሮጀክት ከፍተኛ ችግር ያለበት ስሆን አጠቃቀሙም ቢሆን ምኑም ከምንም እንደሆነ የማይታወቅ በክልሉ ፕረዚዳንት በጎ ፍቃድ ብቻ የሆነበት ተጨባጭ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል።

ይህም እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ በቅርቡ በድጎማ እና በድጋፍ ስም ወደ አርባምንጭ እየፈሰሰ ያለው ስሆን ይህ ተቋም አርባምንጭ ላይ ቤት ስለምሰራ ብቻ ከክልሉ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖ ተልኳል፡፡

በክልሉ የዘላቂ ልማት በጀት አጠቃቀም የሀገሪቱን የፌደረሽን ም/ቤት ህግ ያከበረ እና የተቀመጠውን የበጀት ማከፋፈያ ቀመር የተከተለ አይደለም ብሏል።

የክልሉ ፕረዚዳንት ዎላይታ ሶዶ ከተማ የአስተዳደርና የፖለቲካ መቀመጫ መሆኗን ስለማያምን ህዝቦች አንድ ሆኖ እንዳይኖሩ በከፍተኛ ትጋትና ፍጥነት እየሰራ መሆኑ አንዱ መገለጫው በቀጥታ የኢምግሬሺን መ/ቤት ወደ አርባምንጭ እንድሄድ ማድረጉ እንቅስቃሴ ነው በማለት አስረድቷል።

"ወደ አርባምንጭ ለመውሰድ ለሎችም ተቋማትም እየተዘጋጁ የሚገኙ እንዳሉ መረጃዎቻች ያሳያሉ፡፡ ሌላው ከዚህ በፊት ተነግሮ እንደነበረው የፖሊስ ማሰልጠኛ ከእጃችን ወጥቷል ነገር ግን ለስሙ ፖሊስና ምልሻ ጽ/ቤት በድልድሉ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ናቸው" ብሏል።

ሌላኛው የመረጃ ምንጩ እንዳብራራው፦ "አቶ ጥላሁን ከበደ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንጅ በምንም መመዘኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት ልሆኑ አይችሉም ስንል ያለምክንያት አይደለም፡፡ ባለው ትንሽም ግንዛቤም ከፍተኛ የቅንነት ችግር ያለበት፤ እንደ ሰው ያለው እውቀት ለበቀል የሚጠቀም፤ ሌቦችን ለራስ አድቫንተጅ (ጥቅም) ቁጭ አድርጎ የሚጠቀም፤ "የአሁኑን እንጅ የነጌ ጉዳይ የማይታየው በመሆኑ ለአብነትም፡- ከህዝብ ለህዝብ ሰላማዊ ግንኙነት ጉዳዮችን አርቆ ከማየት ይልቅ የተገኘውን ሁሉ ወደ አርበምነጭ የሚል ጭፊን እይታ፤ ዎላይታንና ብልጽግናን የእንጀራ እናት ልጅ ሆኖ በመሀላቸው ጥርጣሬ እንድኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ጋርም በተቃራኒው እነደቆሙ አስመስሎ በማቅረብ ይህንንም አስተሳሰብ በእኔ አቶ አገኘው ተሻገር በኩል እንድሰርጽ በማድረግ ማስኬድን እንደ ብቸኛው አማራጭ የወሰደ ሴራ ሰው" ብሎታል።

በመሆኑም በክልል ምስረታ ወቅት ከተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ በየወቅቱ ያለማንም ካቢኔ ሆነ አስተባባሪ ውሳኔ በክልሉ ፕሬዝዳንት በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ አዛዥነት እና በአቶ ተፈሪ አባቴ (የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ታዛዥነት ወጪ የተደረገ ቢሆንም እስካሁን ያለበት ቦታም ሆነ ምን ያህሉ ጥቅም ላይ እንደዋለም አይታወቅምና የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርቧል።

ማሳሰቢያ፦ የተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ የሚመለከት ሰነድ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰ ቢሆንም ለሚመለከታቸው አካላት ምርመራ ሂደት እንዲያግዝና እንዳያደናቅፈው ይፋ አላደረግንም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አድራሻው ይጠፋና ያልታወቀውና 2 ቢሊዮን ገደማ ብር👇Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5372

Wolaita Times

16 Jan, 14:43


የአርሶአደሩን ገንዘብ የበላው ማነው ? ዕዳውን ለምን አይሰረዝም ?

በዎላይታ አርሶአደሮች ላይ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እዳ 120 ሚሊዮን ብር በላይ ወለድ እስኪቆጥር ለምን ? የውሸት ሰነድ ደረሰኝ ፈጥሮ የአርሶአደሩን ገንዘብ የበላው ማነው ?ተጠያቂውስ ? መፍትሔው ምንድነው?- የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ የዎላይታ ዞን በአሁኑ ሰአት በአፈር ማዳበሪያ ብድር ምክንያት የ520 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበትና ከዚህም በጊዜ ብድሩ ባለመከፈሉ 120 ሚሊየን ብር የሚሆነዉ እንደወለድ የቆጠረ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በቅድሚያ ይህ የእዳ ጫና እንዴት ሊፈጠር ቻለ ? ተጠያቂዉስ ማነዉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ የአፈር ማዳበርያዉ የዞኑ መንግስት በወረዳዎች በኩል ለአርሶ አደሩ በብድር ያደረሰዉ ነው። ገንዘቡ ተመላሽ መደረግ ያለበት፣ ቀጥታ ከአርሶ አደሩ በየወረዳ አመራሮች በኩል ሲሆን በዚህ መሐል እንግዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ገንዘቡ አልተመለሰም ማለት ነው።

ከባንክ የተወሰደ ገንዘብ ደግሞ ወለድ ስለሚቆጥር በየጊዜዉ ይጨምራል። የብር የመግዛት አቅምም በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መንግስት በወሰዳቸዉ እርምጃዎች በጣም ስለተዳከመ ትልቅ ኪሳራ ነው በወቅቱ ገንዘቡ አለመመለሱ። (ኪሳራዉ ለማነዉ የሚለዉ ሊለያይ ይችላል) ተጠያቂነትን በተመለከተ እንግዲህ የተለያዩ እና ብዙ አካላት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል።

በቀጥታ እዳዉን ያልከፈለ አርሶ አደር ካለ ተጠያቂ ነው፣ ተከታትሎ እዳ ያላስከፈለ አመራር ኃላፊነቱን ስላልተወጣ በቦታዉ መቀጠል የለበትም፣ ሌላዉ አርሶ አደሩ ከፍሎ በመሐል ገንዘቡን በየትኛውም መንገድ ወደኪሱ ያስገባ አመራር በሕግ ተጠያቂ ሊደረግ ይገባል።

ማንም የሕዝብን ገንዘብ ዘርፎ የሚፈነጭበት ሁኔታ መኖር የለበትም፣ በቀጥታ ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረግበት መንገድ ካለ ዞኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለበት፣ ያ ካልሆነ ወደተጠያቂነት መሔድ የግድ ነው። በጥቂቶች ጥፋት ጠቅላላ የዞኑ ሕዝብ መሰቃዬት የለበትም።

ከዛ ባለፈ ግን የአፈር ማዳበርያዉ የሚያስገኘዉ ዉጤት ከሚወጣበት ወጪ ጋር ይመጣጠናል ወይ የሚለዉም መጠናት አለበት። አለበቂ ጥናት ለአርሶ አደሮች ከአቅምና ከሚያገኙት ጥቅም በላይ እዳ ዉስጥ እንዲዘፈቁ የሚያደርግ አሰራር ካለም መፈተሽ አለበት።

በነገራችን ላይ በመላዉ ኢትዮጵያ በቂ የአፈር ማዳበሪያ አላገኘንም የሚል የአርሶ አደር እሮሮ መስማት የተለመደ ነው፣ በመንግሥት በኩል እንዲሰራጭ የመጣዉ፣ ተሰርቆ በነጋዴ በኩል በእጥፍ የሚሸጥበት የዝርፊያ ሰንሰለትም በብዙ አካባቢዎች እንዳለም ይነገራል።

ስለዚህ የዎላይታ ዞንም በዚህ እዳ የተዘፈቀበት ምክንያት መሰል ብልሹ አሰራሮች በመንሰራፋቱ ሊሆን ይችላል። ከለዉጡ በሁዋላ በተለይ በዎላይታ ዞን አመራር በየጥቂት ወራት ዉስጥ ሲቀያየር ስለነበረ እና ያልተረጋጋ መሆኑ የራሱ አበርክቶ ሊኖረዉም ይችላል። የአመራር መሳሳትና የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ለዘረፋ ምቹ ከባቢን ፈጥሮ ሊሆን ይችላል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ይህ የእዳ ጫና በዞኑ ላይ የሚያሳድረዉ ተጽዕኖ ምን ያህል ነው ? ከዚህስ የእዳ ጫና ለመዉጣት ዞኑ ከሕግ ተጠያቂነት ባለፈ ማድረግ አለበት የሚሉት ነገር ካለ ቢጠቁሙን ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምናልባት ከዛ በፊት ተጠያቂነት ላይ አንድ ነጥብ ለመጨመር፣ የዞኑ መንግስት ከእርምጃ በፊት ሰዎች አለጥፋታቸዉ እንዳይጉላሉ እና በትክክል ወንጀል የሰራ ሰዉ ብቻ እንዲጠየቅ ጉዳዩን በትኩረት ማጥናት አለበት የሚለዉን ለመጠቆም እወዳለሁ። ወደ እዳ ጫናዉ ተጽዕኖ ስንመጣ ለባንክ በጊዜ ገንዘብ ተከፍሎ ካልተዘጋ ወለድ ስለሚቆጥር፣ የእዳዉ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

በትክክል መሬት ላይ የተሰበሰበዉ ገንዘብም ላይከፍለዉ የሚችልበትም አግባብ አለ፣ ጊዜዉ በተራዘመ ቁጥር። ሌላዉ በተደጋጋሚ ደሞዝ ለመክፈል ዞኑ የሚቸገረዉ በዚህ የተነሳ ነው፣ ብቸኛ ምክንያት ባይሆንም። ከዛ ባለፈ ዞኑ በአቅሙ የረባ የ capital project አቅዶ እንዳይሰራ እጅና እግሩ በእዳ ታስሯል፥ ከዛ ባለፈ በሥራ እድል ፈጠራም ረገድ እዳ ዉስጥ የተዘፈቀ ዞን ከባድ ፈተና እንደሚገጥመዉ ግልጽ ነው።

ስለዚህ የዞኑ አመራሮች ከዚህ እዳ ዞኑን ለማላቀቅ በጣም ሕዝቡን ያሳተፈ ንቅናቄ መጀመር አለባቸዉ። በተለያዬ መንገድ ገንዘብ ከሕዝቡና ባለሐብቶች የሚሰበሰብበትን መንገዶች በመዘርጋት ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋል። ሕዝቡ "አመራር ዘርፎ እኛን አዋጡ ትላላቹ?" ማለቱ ስለማይቀር፣ ተጠያቂነትን ማስፈን የግድ ይላል።

እዳዉን ከፍሎ ዞኑን ነጻ ለማዉጣት፣ ገንዘብ በተለያዬ መንገድ ሰብስቦ ለመክፈል innovative መሆንን ይጠይቃል፣ አመራሩ ከዚህ እዳ ዞኑን በራሱ መንገድ ነጻ ማዉጣት አለበት፣ ገንዘቡን የማስመለስ ሥራ ከዛ በሁዋላም መቀጠል ይችላል። አቅም ካላቸዉ የዞኑ ተቋማት የተወሰነ ገንዘብ በመሰብሰብም እዳዉን ለመዝጋት መሞከር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

ለምሳሌ በአካባቢው በሕዝብ ጉልበት መሠራት የሚችልና ለዛ የተመደበን ገንዘብ ወደ ዞኑ ማዞር የሚቻልበት ፕሮጀክት ካለ፣ በበጎ ፈቃድ ሕዝብን በማንቀሳቀስ፣ ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት፣ ለእዳዉ የሚከፈል ገንዘብ ማግኘት ያስፈልጋል።

በተሳካ ሁኔታ እዳ ካስመለሱ ወረዳዎች ተሞክሮ በመቀመር ገንዘቡን ለማስመለስ ከመረባረብ በተጨማሪ ዞኑ በተለይ የባንክን እዳ ከወዲሁ ቢዘጋ መልካም ስለሚሆን አመራሩ የተለያዩ የገንዘብ ማግኛ ስልቶችን መቀየስ አለበት።

በሺያጭ ገቢ ማግኘት የምንችልባቸዉ ነገሮች ካሉ መሸጥ፣ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ መንቀሳቀስ። የተለያዩ ከፍተኛ ገቢ ሊሰበሰብባቸዉ የሚችሉ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ገቢ መሰብሰብ።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በመጨረሻም ምናልባት በተለያዩ ቦታዎች አርሶአደሮች ያልወሰዱትን ማዳበሪያ ወስዷል ተብሎ በውሸት ሰነድ እንዲከፍሉ የሚገደዱበትና በዚያ ምክንያት የተለያዩ ጫናዎች ሲደርስ ይስተዋላል። ምናልባት መንግስት ይሄንን ዕዳ መሠረዝ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር ምን ይመስላል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እውነት ነው ይሄ በአብዛኞቹ የሚሰማ ቅሬታ ነወሰ። ምክንያቱም ደሃዉ አርሶአደር ማዳበሪያ የወሰደዉ "የእርሻ መሬት የለኝም" ዕዳዉን መክፈል አልችልም በሚል ቅሬታ እያቀረቡ፣ ሌሎች አብዛኞቹ አርሶአደሮች ማዳበሪያ ሳይወስዱ የተጭበረበረ የዕዳ ደረሰኝ የቀረበባቸዉ ነው። ይሄ ብቻም ሳይሆን የተሰራጨዉ ማዳበሪያ ብልሽት የነበሩበት በመሆኑ አርሶአደሩ ዉዝፍ ዕዳዉን የመክፈል አቅም በማጣት ለችግር የተጋለጡ አሉና መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ መክሮና ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ዕዳ ቢሰርዝ ለአርሶአደሩ እፎይታ ይሰጣል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

16 Jan, 14:43


ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5366

Wolaita Times

15 Jan, 14:58


አፍሪካ ዋና ዋና እንቅፋቶቿንና ዕድሎቿን በመለየት መፍትሔ ለማመንጨት በዓላማና በእውቀት የሚመሩ መሪዎችን ማፍራት ወሳኝ እንደሆነ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገው የመጀመሪያው ተቋም በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አማካይነት ተቋቋመው ወደ ተግባር መግባቱ ተገልጿል።

የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ቤት (ASG)፣ በሕዝብ ፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ለማቅረብና ለመንደፍ ጥር 14 ቀን 2025 በሩዋንዳ በይፋ እንቅስቃሴውን መጀመሩ ተገልጿል።

ይሄንን በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገውንና በአፍሪካ የመጀመሪያው ተቋም የሆነውን የመሰረቱት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሲሆኑ በሩዋንዳ በሚገኘው ካምፓስ የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ማዕከል (ASG) በአፍሪካ አህጉር የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት በፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር አለም አቀፍ ደረጃ የተመረጡ ፕሮግራሞችን ከሁሉም አፍሪካ ሀገራት ለተመረጡ ተማሪዎች ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ AGRA የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተቋቋመው ተቋም የአፍሪካ ልዩ እውቀቶችን ከአለም አቀፋዊ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በማዋሃድ የአህጉሪቱን ዋና ዋና ተግዳሮቶችና ዕድሎች ለመቅረፍ በዓላማ የሚመሩ መሪዎችን ለማፍራት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

"አፍሪካ ታላቅነቷን ለማስመለስ የመጀመሪያው እርምጃ የታሪኳን፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚዋን እና የአመራርነት አስተሳሰቦችን በመሪዎቿ ውስጥ ግንዛቤ እና እውቀት በመገንባት ነው፥ ከዚያ ጠንካራ መሰረት በመነሳት መሪዎች የአፍሪካን ጉዞ ሊቀርጹ ይችላሉ" ሲሉም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።

የሩዋንዳ የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት ጆሴፍ ንሴንጊማና በበኩላቸው The African School of Governance (ASG) ለአፍሪካውያን ወደፊት የላቀ አመራር በማፍራት ወደ ዕድገት የመምራት አቅም እንዳለው እንዲሁም በአለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጠቁመዋል።

በዝግጅቱ ላይ የኤኤስጂ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኪንግስሊ ሞጓሉ እንዳሉት "ተቋሙ በአፍሪካ እውነታዎች ላይ የተመሰረተ ዘላቂ የአስተዳደር ሞዴል ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ በማብራራት ASG እውቅና ያለው የፓን አፍሪካ ድህረ ምረቃ-ደረጃ ተቋም በአፍሪካ ያለውን የአስተዳደር ለውጥ መፍትሄዎችን ለመምጣት ቁርጠኛ ነው" ብለዋል።

የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ማዕከል በ16 ኦክቶበር 2024 የጀመረ የድህረ ምረቃ ተቋም ሲሆን ካምፓሱ በኪጋሊ፣ ሩዋንዳ የሚገኝና በአፍሪካ አህጉር የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት በማቀድ በፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር አለም አቀፍ ደረጃ የተመረጡ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ አልሞ የተቋቋመ ነው።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Rwanda #Africa #ASG #AGRA

Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=5358

Wolaita Times

15 Jan, 05:53


#ሰበርመረጃ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "ሰማይ አይታረስም መንግስት አይከሰስም" ህግ በተግባር በርዕሰ መስተዳድሩ እየተፈጸመ መሆኑ ተገለፀ።

በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የገዥው ፓርቲ ም/ፕረዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ በተገኙበት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መድረክ በክልሉ ያለውን ተጨባጭ አድሏዊ አሰራር ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል የተባሉ ከአራት በላይ አመራሮችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ ከኃላፊነታቸው ማንሳታቸውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

"አምባገነናዊ ስረአት የክልሉ መገለጫ መሆኑ ማሳያ ይሄ ነው በቅርቡ በክልሉ በተደረገ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዶ በነበረው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መድረክ ላይ በአቶ ጥላሁን ከበደ ላይ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ እና አድሏዊ አሰራር በተመለከተ ከፍተኛ ትችት ያቀረቡት እና የገመገሙ የክልሉ አመራሮች ከግምገማው ማግስት በቂም በቀል ተነሳስተው አመራሮቹን የማባራር ስራቸውን ተያይዞታል" በሚል የመረጃ ምንጫችን አስረድተዋል።

ከኃላፊነታቸው የተነሱ የክልሉ አመራሮች፦ አቶ ብረጋ ብርሃኑ፣ አቶ ተገኑ ግርማ፣ አቶ ተፈሪ ሜንታ፣ ወይዘሮ አልማዝ ዘውዱ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደሆኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

"በብልፅግና ፓርቲ ም/ፕረዚዳንት በተመራው በዚሁ መድረክ ላይ በክልሉ ውስጥ የታዩት የፖለቲካ ብልሽቶችን እንድታረም በመረጃ አስደግፎ መታገሉ ብቻ ጀግናና ታታሪ የሆኑ አመራሮችን በማንአለብኝነት ከኃላፊነት እንዲነሱ አድርገዋል፤ እንግዲህ የግለሰቦች መጨዋቻ የሆነውን ፓርቲ ይዘን ነው፣ ክልሉ በብልፅግና ፓርቲ አይመራም ስንል በምክንያት ነው" በሚል አክለው ገልጸዋል።

ከሳምንት በፊት ለሁለት ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ብልሽት ዙሪያ የተካሄደው መድረክ የተዘጋጀው "ህዝብን ማገልገል ትተው በግሮሴሪና እና አልጋ ቤት" ውሏቸውን ያደረጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች በሚገባ ተገምግሞ እንዲቀርብ ተብለው ጠቅላይ ሚኒስትር በሰጡት አቅጣጫ መሠረት እንደሆነ ዘግበን ነበር።

በዋናነት ስር በሰደደው ሙስና፣ ስነምግባር ጉድለት፣ አድሏዊነት፣ ብልሹ አሰራር ዙሪያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ጥልቅ ግምገማ መድረክ ከፍተኛ ጥበቃ ተደርጎ መካሄዱን ከአንድ ተሰብሳቢ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በግምገማው በርካታ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በተለይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማንአለብኝነት በህገወጥ መንገድ ስለፈፀሙት አድሏዊነት፣ አግላይነት፣ ከፋፋይነት፣ ሴረኝነት፣ ቡድንተኝነት፣ ሆን ብሎ አሠራርን የሚጥሱና ብልሹ ተግባር የሚፈፅሙ የቡድኑ አደረጃጀት ዉስጥ ያሉ ግለሰቦችን ከለላ በመስጠት አገልግሎት ተቀባዩ ህዝብ ሲበደልና ቅሬታ ሲያቀርብ የባሰ በደል እንዲደርሳቸዉ ማድረግ ብሎም የፓርቲ መዋቅር ከኢትዮጵያ ባህል ያፈናገጠ ተግባር በህዝብ ዉስጥ ሲፈፅሙ ያለማረምና የመንግስት ሥራ ኃላፊዎችን ከፓርቲ መመሪያ ዉጪ በመጠጥ ቤት ሲሾሙና ሲያባርሩ የነሱን ተቀብሎ ማፅደቅ እንዲሁም ቅሬታንም ያለመቀበል ችግሮች በስፋት በመረጃ ተደግፎ ተገምግሞ ነበር።

በአብዛኞቹ ተሰብሳቢዎች በክልሉ የመንግስት አሰራር ሆነ የገዥው ፓርቲ ተግባርና ስልጣን በግለሰቦች እጅ በመውደቁ በየአካባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጥና ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል እንቅፋት የሆነ ክልሉ ሆኗል በሚልም ተገምግሟል።

በክልሉ አመራሮች መካከል በግልጽ የሙስና ተግባራቸው በመረጃና ማስረጃ ተደጎፎ የተነሳው ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አክሊሉ አዳኝ ከአስተዳደራዊ እርምጃ ባሻገር በህግ እንዲጠይቁ አቅጣጫ ተቀምጠው ነበር።

በመድረኩ የክልሉ አመራሮች የህዝብን አደራ ወደ ጎን በመተው በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል ያላቸውን ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ላይ በርካቶች ጥፋት ውሰጥ ተዘፍቀው መኖሩን በማብራራት በፌደራል ደረጃ የተመደቡ የክልሉ ተወካዮች የወከላቸውን ህዝብ እንዳይገናኙ በማድረግ ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ በእጅዙር የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር ጥፋት ለመሸፈን ጥረት አድርጓል በሚልም በመረጃ ከሷል።

የመድረክ መሪዎች በክልሉ ያለውን ከፍተኛ ብልሽት በተመለከተ የተነሱ ተጨባጭ መረጃዎችን በመውሰድ አስቸኳይ እርምት እርምጃ የሚያስፈልገው በመሆኑ በቦታው ምንም የውሳኔ ምላሽ ወይንም የማስተካከያ መመሪያም ሳይሰጡ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመለሳቸውና የእርምት እርምጃ እየተጠበቀ ስለመሆኑ መዘገባችንም ይታወሳል።

በተቃራኒው ግን የግምገማው ውጤት ከወዲሁ የከፋ እንደሆነባቸው የተረዱት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ ባለው ትንሽ ጊዜም ቢሆን የአጥፍቶ ማጥፋት አይነት አካሄድ ከህግና ከፓርቲው አሰራር ጭምር ባፈነገጠ አኳኋን በክልሉ ያለውን ተጨባጭ አድሏዊ አሰራር ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ከ4 በላይ የክልል ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው ማንሳታቸውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

14 Jan, 15:13


ከፍተኛ አመራሩ በአባታቸው ስም ከ120 ሄክታር መሬት በላይ ቢወስዱም ተጨማሪ ለማግኘት በአከባቢው የተደራጀ ህገወጥ ወረራ እየፈጸመ ስለመሆኑ ተነገረ።

"የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብርሃም ማርሻሎ ከሎካ አባያ ወረዳ በ2012 በአባታቸው አቶ ማርሻሎ ኢቲሶ ስም 120 ሄክታር መሬት ለኢንቨስትመንት የወሰዱ ሲሆን በጊዜው በህገውጥ መንገድ ነበር ያንን መሬት ለኢንቨስትመንት የወሰዱት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የራሳቸውን ቤተሰብ በማደራጀት በመላው ሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ብቻ በአከባቢው ተወላጆቹ ላይም ያለ ርህራሄ የጭካኔ የሌብነት በትሩን እያሳረፈ ይገኛል" በሚል ለደህንነታቸው ስም እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ገልጸዋል።

በተጨማሪም በክልሉ በዚሁ አመራር አማካይነት "በክስ ሂደት ላይ ያሉ የመሬት ጉዳዬችን ሰነዶችን ጭምር በማጥፋት ባደራጁት ቡድን በሐዋሳ እና አከባቢው ከተሞች ውስጥ ያሉ መሬቶች በህገወጥ በንግድ ለህግ ጥቅም እያዋሉ ታሪክ የማይረሳው በደል በህዝባችንን ላይ እየፈፀመ ነው፣ በአከባቢው የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችን በማሸማቀቅ ጭምር እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ ጉዳዩን የሚመለከተው አካል በትኩረት ማየት አለበት" ብለዋል።

ባለፈው ሰምንት በተካሄደው የሲዳማ ክልል አመራሮች መድረክ በሎካ አባያ ከዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ጉዳይ ክልሉ ለምን መግለጫ አልሰጠም? የተፈጠረዉ ነገር ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ሰዉ መኖሩ ተገቢ ቢሆንም ከአቶ አብርሃም ጋር አያይዞ የዉስጥ ባንዳ ከዎላይታ ጠላቶች ጋር በማበር ጓዱን ከስልጣን መነቅነቅ ስለ ጀመሩ አመራሮች በአንድ አቋም መታገል አለባችሁ" በሚል አንድ አመራር አስተያየት መስጠቱን የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃውን አጋርተው ነበር።

አክለውም "ይህ ነገር ሰፍቶ እስከ ፓርቲው ዋና ቢሮ ከደረሰ ጓዳችንን ልናጣው እንችላለን የሚል ሀሳብ በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ አንዳንድ አመራሮች "የዎላይታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ነዉ እየታገሉ ያሉት፣ ለኢንቬስትመንት የተሰጡ መሬቶችን በዞኑ በኩል እንደተሰጠ ጭምር በቂ መረጃ እያቀረቡ ነዉና በእኛ በኩል ምን አለ" የሚሉና ከአብርሃም፣ ከአባቱና ዘመድ አዝማዱ ጋር ተያይዞ በሎካ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታሮችን በጸጥታ ሀይል ጭምር በመታገዝ እየተወረረ ነዉ የሚል ወሬ በህዝቡ ዉስጥ እየሰፋ ነዉና ሀሳቡን የመመከት ስራ መስራት አለብን" በሚል አመራሩ የድጋፍ አስተያየት መስጠቱንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

እኚህ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጪ አመራር አክለውም፦ "አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይህንን የሚፈጽሙት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን (ይርጋለም ዞን) የሰላም፣ ጸጥታና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ባስቀመጠው በወንድሙ አማካኝነት በወታደር ጭምር ታግዞ ነዉ የሚል ወቀሳ በተጨባጭ የቀረበ ስሆን፣ ይህንን ችግር ሌላ ጊዜ በራሳችን መድረክ እናየዋለን አሁን ግን ለጠላታችን መጠቀሚያ ሳንሆን ከጓዱ ጋር መቆም አለብን፣ ሁሉም አመራር በአጠቃላይ ከአብርሃም ጎን እንደሆነ በማሳወቅ በዎላይታ በኩል የሚመጣዉን ጫና በተደራጀ መልኩ በፌስቡክ ዘመቻ፣ በሚዲያ ሰራዊት እንምራ በሚል ማሳሰቢያ ተዘግቶ ወደ ሰነዱ ንባብ እንደተገባ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት።

የመድረኩን መረጃ ያደረሱት እኚሁ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ስለ አቶ አብራሃም ሲገልፁ፦ "የማዕከላዊ ዞን የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ማርሻሎ (የአብርሃም ወንድም) ሎካ አባያ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነዉ፥ በተደራጀ መልኩ ነዉ ሲዳማንም ዎላይታንም እየበደሉ ያሉት። ወንድሙን በመሾሙ ምክንያት ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣ አስነስቶ ነበር" ብለዋል።

ባለስልጣኑ አክለውም፦ "በወንድሙ ትዕዛዝ መሰረት በሎካ ድንበር ንጹሀን ዎላይታዎችን ያስገ'ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ። ለዎላይታ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አብርሃምና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከእርሱ ጋር የተባበሩ አመራሮች ናቸው። አቶ አብርሃም የህዝብ ንቀቱ ጫፍ ወንድሙን ከወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኝነት ቀጥታ የዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አድርጎ በወታደር ሀይል የህዝብን መሬት እየወረረ ይገኛል" በሚል ገልፀው ነበር።

በመጨረሻም እኚሁ የመረጃ ምንጭ ባለስልጣን፦ "የሚገርመው አንድ የአቶ አብራሃም ደጋፊ ዘመድ የሆነ አመራር በዕለቱ ስብሰባ የዎላይታ አክቲቪስቶች አብርሃም ላይ ሲዘምቱ በሲዳማ ዉስጥ የሚገኙ የዎላይታ ተወላጆችን ቀብድ አስይዘው ነዉ የሚል አይነት እንድምታ ያለው ንግግር እየተናገሩ እንደ ነዉር እንኳን አይቆጠርም። ለአንድ ሌባ ሙሰኛ ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል ያን ያህል መላላጥና መጋጋጥ አሳፋሪ ነው ገዢው ፓርቲ በእነዚህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል እሳት በሚጨምሩት ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ተደራጅተን እየተንቀሳቀስን ነው" ብለዋል።

እንደሚታወቀው አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ባለሀብት ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ባለው ሳምንት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጨባጭ መረጃዎችን አስደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።

በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

በተጨማሪም "የብልጽግና ከፍተኛ አመራር አቶ አብራሃም ማርሻሎ የራሳቸውንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ" መሆኑም እንዲሁ።

ሰሞኑን በተፈጠረው የተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ያለበት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጉዳዩ ዙሪያ ጥፋተኞች ወደ ፍትህ እንዲቀርቡ ከመናገር ዝምታ መምረጡ ተጨማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ገልጿል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama

Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5350

Wolaita Times

14 Jan, 13:11


ለመሆኑ "ጃዋር በትግራይ ሻዕቢያ ያደረሰውን ጥቃት ለማዉገዝ ለምን ተቸገረ"?! "የጃዋር ኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራና ኦሮሚያ ብቻ ናት"?! "በሀገሪቱ ለተከሰተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ናቸው ተጠያቂ" ?- የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ፖለቲከኛ #ጃዋር #መሐመድ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ሰሞኑን በርዕዮት ሚዲያ ቃለምልልስ ማድረጋቸዉ ይታወሳል። አንዳንድ ነጥቦችን ከማንሳታችን በፊት አጠቃላይ ቃለምልልሱን እንዴት አገኙት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ያዉ በሩቅ ሆኖ ከመታኮስ ተቀራርቦ መነጋገር የሚበረታታ ነው። ቃለምልልሱ ከመስመር የወጡ እንካ ሰላሚትያዎች ሊያስተናግድ ይችላል ብዬ ፈርቼ የነበረ ቢሆንም፤ ከሞላ ጎደል ጥሩ በሚባል አኳሐን ተደርጓል። ለዚህ ሁለቱም መመስገን ያለባቸዉ ይመስለኛል። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ጥሩ ዝግጅት አድርጎ ነው የመጣዉ፣ ጃዋር መሐመድም ያመነባቸዉን ምላሾች ሰጥቷ ከሞላ ጎደል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በቃለ ምልልሱ አንዱ የተነታረኩበት ነጥብ የ state resiliance (የኢትዮጵያ ሐገረ መንግስት ፈረሳን የመቋቋም አቅም) ነው። በዚህ አርዕስት ያደረጉትን ምልልስ እንዴት ታዘቡት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ቴዲ ጃዋርን ከአመት በፊት ጥንታዊ ስለሆነ በቀላሉ አይፈርስም ያልከዉ ሐገረ መንግስት ምንም የተለዬ ነገር ባልተፈጠረበት የመፍረስ ስጋት ዉስጥ ገባ ያልከዉ እንዴት ነው ላለዉ ጃዋር የሰጠዉ መልስ አጥጋቢ አልነበረም። በተለይ ከ IMF ስምምነት በሁዋላ መንግስት አቋም ቀይሯል የሚለዉን በበኩሌ አጥጋቢ ምክንያት ሆኖ አላገኘሁትም።

በነገራችን ላይ ቴዲ አላነሳዉም እንጂ ጃዋር፣ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ማፍረስ እንችል ነበረ ስላልፈለግን ነው የተዉነዉ ያለበትንም ቢያነሳበት ጥሩ ነበረ። በዚህ ጉዳይ ላይ የጃዋር የ consistency ችግር ግልጽ ነው። በርግጥ ፈጽሞ የማይታረቁና የተራራቁ ነገሮችን በሐገረመንግስቱ ዘላቂነት ናፈረሳን የመቋቋም አቅም ላይ ተናግሯል በተለያዬ ጊዜ።

ከጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ጋር ባደረገዉ ቃለምልልስ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሐገረመንግስት ነች ብሏል። በርግጥ በአብዛኛው የብሔር ትግል ዘመናዊት ኢትዮጵያ ከሚኒሊክ ወዲህ የተፈጠረች ተደርጎ ይገለጻል፣ ነገሩ የጠራ አይደለም። በእዉነቱ የኢትዮጵያ ሐገረመንግስት ጥንካሬ ከሚመነጭባቸዉ ምክንያቶች አንዱ ጥንታዊነቱ ቢሆንም፤ የታሪክ ስርቆትና ድበቃ ያንን እዉነታ የደበቀብን ይመስለኛል።

በነገራችን ላይ OLA ከብልጽግና ጋር በታንዛንያ ሲደራደር referendum በኦሮሚያ ይደረግ የሚል ጥያቄ አንስቷል ተብሎ ነበር፣ ስለዚህ ጃዋር ኦሮሚያ ሐገር የምትሆንበት እድል አሁን የለም ብሎ ካመነ ስልጣን በእጁ ቢሆን ምን አድርጎ ግጭቱን እንደሚያስቆም ቴዲ ቢጠይቀዉ ጥሩ ነበረ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መንግስታትን ከዚህ በቀደም የአማራ እና የትግሬ እያልክ ፈርጀሐል፣ የአሁኑን የኦሮሞ ብላቹ አትፈርጁ ብለህ ምክንያት ደርድረሐል የሚል አንድምታ ያለዉ ጥያቄም ተነስቶ ነበር፣ ለዚህ ጃዋር የሰጠዉ መልስ አጥጋቢ ነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አይመስለኝም። በተለይ ከ1987 ሕገመንግሥት በሁዋላ ኢትዮጵያ የፈደራል ሥርዓት ስለምትከተል መንግሥት የአንድ ብሔር የተለጠጠ ዉግንና እንዳይኖረዉ አድርጓል ሥርአቱ። ስለዚህ ከዛ በሁዋላ መንግስትን ጠቅልሎ ወያኔ እያሉ መፈረጅ ስህተት ነው። ኢህአዴግ ህወሃት መራሽ ቢሆንም ለብአዴን ከመጀመሪያዉም የጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት፣ የአማራ ተወላጅ ጀነራሎችን በመከላከያ አመራርነት፣ አየር ኃይል አዛዥ እስከማድረግ አሳትፏል።

#ከዎላይታዉ #ዎጋጎዳ #ትግል በሁዋላ በዎላይታ አንስቶ ሌሎችንም የደቡብ ብሔሮች በከፍተኛ ስልጣን አሳትፏል። እዉነት ለመናገር ኦሮሞ በሚገባዉ ልክ ተገቢ ቦታ አልተሰጠዉም፤ ቢሆንም ጠቅልሎ መንግስትን ወያኔ ብሎ መፈረጅ ልክ አይደለም። ሌላዉ ወያኔ ማለት በትግራይ አልምበረከክም ባይነት እኩል ነኝ።

በሐገሬ ጉዳይ ባይተዋር ልታደርጉኝ አትችሉም ባይነትን የሚገልጽ ሕዝባዊ የትግልና የጀግንነት ስያሜ እንጂ የፓርቲ ስም አይደለም። ስለዚህ ወያኔ ይዉረድ ማለት የትግራይ ሕዝብ ታግሎ የተጎናጸፈው ራስን በራስ የማስተዳደርና በፈደራል ደረጃም ሚዛናዊ ዉክልናዉን አስጠብቆ የመዝለቅ ሕገመንግሥታዊ መብቱን የሚጋፋ ነው።

ትክክለኛዉ መንገድ ሕገመንግሥታዊዉ የኦሮሞ ሕዝብ ሚዛናዊ ዉክልና የማግኘት መብቱ ይከበር ማለት ነው የነበረዉ። አዉርዶ የመዉጣት ነባሩ የኢትዮጵያ የተቃዉሞ ፖለቲካ ቅኝት፣ ከፈደራል ሥርዓቱ እሴቶች ጋር የሚጣረስ ነው። ዛሬ ሐገሪቷን ወደዚህ ዉጥንቅጥ የከተታት በተለይ ኦሮ_ማራ የሚል የሌሎችን ሕዝቦች causes ችላ ያለ አካሄድ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በአቶ ኃይለማርያም ጊዜ ስልጣን ለመቀማት ጃዋር ባደረገው ቅስቀሳ አብዛኛው ቦታ በህወሓት ላይ ቢሆንም እነሱን ለመቃወም በተደረገው አንድም የትግራይ ተወላጅ በኦሮሚያ ክልል አልተገደለም አለ። ጋዜጠኛውም ያልተገደሉት በእናንተ ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ ቸርነት ነው በሚል ዘጋ። ነገር ግን በእሱ ምክንያት በመቂ፣ ዝዋይና መሠል በእዛ አከባቢ ምንም ፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ንፁሃን ዎላይታዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደል ያደረገው ማነው ? ቃለመጠይቁ ላይ ይሄንን ጉዳይ ጠያቂውም መላሹም አላነሳምና ምን ምላሽ አሎት ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ያዉ የዎላይታ ሕዝብ ላይ የደረሰዉ ጠቃት በቂ ትኩረት አላገኘም። ከለዉጡ በፊትም ሆነ ከለዉጡ በሁዋላ ሐገሪቷ የእልቂት ሜዳ እንድትሆን ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ይህ የዎላይታ ሕዝብ ላይ የደረሰዉ ጥቃት በቸልታ መታለፉ ነው። ያኔ ሁሉም ለምን ቢል ኖሮ ሐገሪቷ ለዚህ ሁሉ ፍጅት አትዳረግም ነበር። ግልጹም ነገር ቴዲ እንዳለዉ ጃዋር በዚህ ፍረጃ ላይ ከሚጠቀሱ ሰዎች ግምባር ቀደሙ ነው።

በአዋሳም የምታስታዉስ ከሆነ ከዎላይታዎች መጠቃት ቀናትን ቀድሞ ሲዳማን በጉልበትም ቢሆን ክልል እናደርጋለን ያለበት ይታወሳል። ጃዋር እንደሚለዉ በሁሉም መሥመር በጥላቻ ቅስቀሳዎች አልተሳተፈም ማለት ይከብዳል። ቴዲ የኦሮሞ ሕዝብ ቸርነት ያለዉ ባይሆን የወደድኩለት አገላለጽ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሌላዉ ነጥብ ጃዋር በትግራይ ጦርነት ሻዕቢያ መግባቱን ማዉገዝ ሲተናነቀዉ ተስተዉሏል። ይህንንስ እንዴት አዩት? የአማራ ክልልንም መግባት አድበስብሶ አልፏል? ይሄስ ከመርህና ከሕገመንግስት አንጻር እንዴት ይታያል? በርግጥ ጃዋር ለሕገመንግስቱ ታማኝ ከልሆነ እንዴት ሊታመን ይችላል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህ እንግዲህ መርህ አልባነት ነው። ጃዋር ታዲያ በጦርነቱ ጉዳይ ከብልጽግና አቋሙ በምን ይለያል የሚል ጥያቄም እንድናነሳ የሚያስገድድ ነው። የሻዕቢያም ሆነ፣ የአማራ ክልል ወደ ትግራይ ዘልቀዉ ገብተዉ መዉጋትና መሬት መቆጣጠራቸዉ፣ መንግስት "ሕግ ማስከበር "ያለዉን፣ ያከሸፈና ለጦርነቱ escalation (ወደ ሕዝባዊ የእርስበርስ ጦርነትነት) ደረጃ እንዲያድ ካደረጉ ምክንያቶች ዋነኞቹ እንደሆኑ ግልጽ ነው።

በእዉነቱ ይህ ጃዋር በምን ይገዛል፣ ሕገመንግሥት ካልገዛዉ የሚል ጥያቄ የሚያጭር ነው። ኢትዮጵያ አትፍረስ የሚል፣ ሰው ኢትዮጵያዉያን በባዕድ እና ሕገወጥ ሐገር በቀል ኃይሎች ሲበደሉ ካላወገዘ አስቸጋሪ ነው።

Wolaita Times

14 Jan, 13:11


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሌላዉ ነጥብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ የተለያዩ ሕገመንግሥታዊ መብቶቹ በተሻለ ሁኔታ እንዲከበሩ ከሚጠይቅበት ደረጃ ወደ ሕልዉና ጥያቄ በመዉረዱ ለምን አትጸጸትም ተብሎ ለተጠየቀዉ የሰጠዉስ መልስ ሚዛናዊ ነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አይመስለኝም። እኔ ወደዚህ ዉድቀት ያመራዉ መጀመሪያ ትግሉ የተመራበት ጃዋርም የተሳተፈበት ሥርዓት አፍራሽና የሌሎችን ሕዝቦች መብት የገፋ አካሄድ ይመስለኛል። ጃዋር አልጸጸትም ብሎ በቁጣ ወያኔ ምናምን ወደማለት ሄዶ በfalse equivalence እነ ሐየሎም ደርግን በመጣላቸዉና እነ ጌታቸዉ አሰፋ በሰሩት ወንጀል ምክንያት መጸጸት የለባቸዉም ብሏል፤ ብዙ ዉሃ የሚቋጥር ምክንያት አይመስለኝም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሌላዉ ሁለቱም የተስማሙበት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምንም ተስፋ ባለማድረግ ነው፤ ይህንንስ እንዴት ያዩታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔ እዛ ላይ ሁለቱም የተሳሳተ አቋም የያዙ ይመስለኛል። ጃዋር ግን አደገኛ ሐረግም አምልጦታል። በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ያሉ ሰዎች አዉቃቿለዉ፣ እርምጃ መዉሰዳቸዉ አይቀርም ያለዉ በጣም አደገኛ አባባል ይመስለኛል።

ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የፈረመዉን የፕሪቶሪያ ስምምነት ይተግብር፣ ከአማራና ኦሮም አማጽያን ጋር ሕገመንግሥቱን ያከበረ የሰላም ስምምነት ይፈራረም ቢሉ የተሻለ ነበረ። አጠቃላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ መልዕክት ማስተላለፋቸዉ ጥሩ አልመሰለኝም። እኔ ሲጀመርም ችግሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ነው በሚለዉ የጃዋር ሐሳብም ሆነ በቴዲ የኦሮሞ መንግስት ነው ዳርዳርታ አልስማማም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #JawarMohammed #oromo #Tigray

ለመሆኑ የጃዋር ኢትዮጵያ እስከየት ናት?
Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5346

Wolaita Times

13 Jan, 13:42


አቶ አገኘሁ ተሻገር በጋሞ ዞን ምን አላቸው ?

እንደሚታወቀው የፌደሬሽን ምክርቤት በሀገሪቱ ከብሄር ብሄረሰቦች መብት፣ ማንነት ጥያቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራ ቢሆንም በተቃራኒው የዚህ ተቋም መሪ የሆኑት አቶ #አገኘሁ #ተሻገር በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብሄረሰቦች በማንነታቸው ምክንያት ስቃይ እየደረሰባቸው ወደ ሚገኙበት ዞን በተደጋጋሚ እየመጡ ከስራቸው በማይገናኙ ጉዳዮች ላይ ከአከባቢው አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ መታየት የተለመደ እየሆነ ነው።

ለመሆኑ #የፌደሬሽን #ምክርቤት አፌ ጉባኤ ሆኖ በአከባቢው ብሄር ብሄረሰቦች በማንነታቸው ምክንያት ለሞት፣ ለእስር፣ ለስደት፣ ለውርደትና ለዘመናዊ ባርነት ተዳርገው የሚሰማ ህግ አጥቶ #ከፈጣሪ #ምላሽ በሚጠብቁበት ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞንና አከባቢው ላይ እየተመላለሰ ምን እየሰራ ይሁን ?

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #kuchazone #Zeyse #Dorze

Wolaita Times

12 Jan, 15:05


ተጠያቂነት ወዴት ነው? "ዎላይታ የራሱን ጉዳይ በክልሉ ተወካይ በኩል ሲዳማ ደግሞ ቀጥታ በራሱ ተወካይ የተሳተፈበት የዲላው መድረክ ምን ውጤት ያመጣል ? በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መሐከል የፖለቲካ ነጋዴዎች ጠልቃ እንዳይገቡ መፍትሔው ምንድነው ? ለመሆኑ ህዝቡ የራሱን ጉዳይ በቀጥታ በራሱ ተወካይ መነጋገር የሚጀምረው መቼ ?- የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በቅርቡ የሲዳማ ክልልንና የዎላይታ ዞንን በሚያዋስን አካባቢ የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት፣ ባልታጠቁ ወጣቶች ላይ በወሰዱት ሕገወጥ እርምጃ፣ በሰዉ ሕይወትና አካል ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ይታወሳል። በቅድሚያ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰማዎትን ነገር ቢገልጹልን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ። በመጀመሪያ ለሟቾች ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን፣ ለተጎዱ ደግሞ ፈዉስን እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው እመኛለሁ። በእዉነቱ የሲዳማ የጸጥታ አካላት ድርጊት ሕገወጥና የሁለቱን ሕዝቦች ወንድማማችነት የማይመጥን ተራ ተግባር ነው። ይህንን ጉዳት ያደረሱ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረክ እና ተጎጂዎችን ለመካስ የዎላይታ ዞን፣ የሲዳማ ክልልና የፌደራል መንግስት በጋራ መሥራት አለባቸዉ እላለሁ። በዚህም ረገድ በቅርቡ የሁለቱም ሕዝቦች ወዳጅና ወንድም የሆነዉ የጌዲኦ ሕዝብ መናገሻ በሆነችዉ፣ በዲላ ከተማ፣ የተደረገዉ ዉይይት ጥሩና የሚበረታታ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በጉዳዩ ዙሪያ በዲላ በተካሄደው ስብሰባ ሲዳማ ቀጥታ በራሱ አመራር ወክለው ተሳትፏል፣ ዎላይታ ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራር በኩል አንደ ተሳታፊ በመሆን እንጂ በቀጥታ ለመወያየት ዕድል አልነበረውም። ይሄን ሁኔታ እንዴት ተመለከትከው ? ከውይይቱ ለቅሶ መድረስና የህግ ተጠያቂነት ማስፈን አይቀድምም ወይ? ለምን መድረኩ በተጎጂ አከባቢ ልተካሄደም ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መድረኩ በዲላ መካሄዱ ጥሩ ነው። ጌዴኦ የሁለቱም ወንድም ሕዝብ ነዉና የአስታራቂነት ሚናን ሊወጣ ይችላል። የደቡብ ክልል መሳተፉ ጥሩ ሆኖ፣ ለዎላይታ ዞንና አመራሮች ቦታ መስጠት አለበት፣ የጉዳዩ ባለቤት ናቸዉና። ወንጀል የሰሩ ሰዎች ተጠያቂነት የግድ ነው፣ ያ ካልሆነማ መሰል ወንጀል ባህል ይሆናል፣ ስህተትን በስህተት ለማረም የሚፈልጉ ኃይሎችን ይፈጥራል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ የዎላይታ እና የሲዳማ ፖለቲካ በምን አግባብ መመራት አለበት ? የሕዝቦቹስ ትስስር እንዴት ይገለጻል? በርግጥ በሁለቱ ሕዝቦች መሐከል ወሰን ለግጭት የሚያበቃ ነገር መሆን አለበት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምንም ጥያቄ የሌለዉ ነገር የዎላይታና የሲዳማ ሕዝብ ወንድማማችነት ነው። እነኝህ ሁለቱ ሕዝቦች እጅግ በጣም የተጋመደ ጥቅም፣ ተቀራራቢ የፖለቲካ ታሪክ፣ በጋራና በተናጠል እየተደጋገፉ ጭቆናን ለማስወገድ የመታገል ታሪክ፣ በብዛት የተጋባና የተዋለደ ሕዝብ፣ ተቀራራቢ የሕዝብ ብዛት የሚጋሩት ሰፊ ወሰን አላቸዉ። እነዚህ ወንድማማች ሕዝቦች ከዚህ በመነሳት፣ የሚያራምዱት የፖለተካ ሐሳብ የሚደጋገፍና አንዱ ለአንዱ ደጀን የሚሆንበት መሆን አለበት።

ባለፈዉ በሐዋሳ ከተማ እና አካባቢዉ በዎላይታ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከደረሰ በሁዋላ፣ የዎላይታ ሕዝብ ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስበትም፤ ነገሩ በቀላሉ በሐገር ሽማግሌዎች እርቅ መብረድ የቻለዉ ሕዝቦቹ ለዘመናት ባዳበሩት የወንድማማችነት እሴት የተነሳ ነው። በርግጥ ግለሰቦች በወንጀላቸዉ መጠየቃቸዉ ግዴታ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝቦች ወንድማማችነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሠራት አለበት።

ሲዳማ በመላዉ ዎላይታ ይኖራል፣ ዎላይታም እንደዛዉ፣ ይህ የሕዝቦቹ ወንድማማችነት የፈጠረዉ ነው፣ ማንም ሊያለያዬዉ አይችልም፣ የሁለቱም አካባቢ ሊህቃን ደግሞ ይህንን ወንድማማችነት ለማጎልበት መሥራት አለባቸዉ። የሐዋሳ እና ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲዎች በጋራ የሁለቱን ሕዝቦች ወንድማማችነት ለማጠናከር ተቀናጅተዉ ቢሰሩ መልካም ነው።

ለምሳሌ የዎላይታና የሲዳማ ወንድማማችነት መድረክ፣ ሲምፖዚየም፣ ፈስቲባል፣ ንግድና ባዛር ወይንም አንዳች ትርጉም ያለዉ የወንድማማችነት ማጎልመቻ ዝግጅት በየአመቱ ቢካሄድ ጥሩ ነው። ሁለቱ ሕዝቦች መሐል ጸብ የለም፣ እያደገ የሚሄድ ወንድማማችነት እንዲኖር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። የጊፋታ እና የጫምባላላን በአል የልኡካን ቡድን እየላኩ በጋራ ማክበር ያስፈልጋል፣ በዉጪ የሚኖሩ የየብሄሩ ተወላጆችም በየአዲስ ዓመታቸዉ መገባበዝና በጋራ ማክበር አለባቸዉ።

ይህን ካደረግን ወሰን ዎላይታና ሲዳማን አያጣላም፣ በሌሎችም የፖለቲካ ጉዳዮችም እየተደጋገፉ በጋራ መሥራት ይቻላል። የዎላይታና የሲዳማ ተደጋግፎ መሥራት በኢትዮጵያ ፖለቲካም ላይ ተጨባጭ ለዉጥ ያመጣል። የወሰን ጉዳዮች በዉይይት እና በሰላማዊ መንገድ የሕዝቦቹን ወንድማማችነት በሚመጥን ጨዋነት መፈታት አለበት፣ በሲዳማ የሚኖር ዎላይታም፣ ሆነ በዎላይታ የሚኖር ሲዳማ፣ በወገኖቹ መሐል እንደሚኖር እንዲሰማዉ በሚያደርግ አግባብ እና ለሌሎችም አካባቢዎች ምሳሌ በሚሆን አግባብ መፈታት አለበት። የሲዳማ ክልል አመራሮችም፣ ከዎላይታ ዞን አመራሮች ጋር ሆነዉ፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን ማጽናናትና መደገፍ አለባቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama

"ዎላይታ የራሱን ጉዳይ በክልሉ ተወካይ በኩል ሲዳማ ደግሞ ቀጥታ በራሱ ተወካይ የተሳተፈበት የዲላው መድረክ ምን ውጤት ያመጣል ? በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መሐከል የፖለቲካ ነጋዴዎች ጠልቃ እንዳይገቡ መፍትሔው ምንድነው ? ለመሆኑ ህዝቡ የራሱን ጉዳይ በቀጥታ በራሱ ተወካይ መነጋገር የሚጀምረው መቼ ?-
Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5342

Wolaita Times

11 Jan, 14:05


በደቡብ ኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት በስድስቱ ማዕከላት የተካሄደው የአመራር ግምገማ እርስበርስ መጠቃቃት ላይ ያተኮረ እንደነበረ የፓርቲው አባላት ጠቆሙ።

"የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመሠረተው በብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ትኩረትና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ብርቱ ክትትልና በህዝቦች በጋራ መፈቃቀድ ላይ እንደሆነ ይታወቃል" ሲሉ በክልሉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ተናግሯል።

"ክልሉ እጅግ ሰላማዊ የሆኑ ህዝቦች መኖሪያ፣ ድልብ የተፈጥሮ ሀብት ያለበትና ብዝሃነት የምገለጽበት ትንሿ ኢትዮጵያ ተምሳሌት የሆነ ክልል ነው" በሚል አንድ በክልሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ገልጸዋል።

ነገር ግን ክልሉ አሁን ያለውን ቅርጽ ይዞ እንዳይደራጅ የብልጽግና ፓርቲ እሳቤና የመደመር መንገድን ያልተቀበሉ በሰማይና በምድር አንገናኝም የምል መፈክር ቀርጸው በተደራጀ መንገድ በህዝቦች መካከል ጸብን እየዘሩ የነበሩ ፀረ ብልጽግና እና ፀረ ሕዝብ በሆኑ ጽንፈኛ አካላት በክልሉ ምስረታ ወቅት ሥልጣን በመቆናጠጥ፤ የያዙትን ስልጣን መከታ በማድረግ ቀድሞም አቅደው ያልተሳካ ዕቅዳቸውን መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ለመፈጸም በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተውን ክልል ገና ሳይደራጅ ለመበተን እየሰሩ ይገኛሉ በማለት አስረድተዋል።

የፓርቲው አባል አክለውም "ይህ እውነት መሆኑ በባለፈው ሳምንት በዎላይታ ሶዶ ከተማ በጉተራ አደራሽ በብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚደንት በአቶ አደም ፋራህ የተመራው የፈደራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተደረገው ግምገማ ፍንትው አድርጎ አሳይቷል" ብሏል።

በመድረኩ በክልሉ ከብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤና መርሆዎችን ባፈነገጠ መልኩ ከከፍተኛ አመራር እስከ ዝቅተኛ አመራር ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንፀባረቅ ቡድንተኝነት፣ ሴረኝነት፣ አግላይነት፣ መጠቃቃት፣ በቀልተኝነት፣ የየአካባብ ገዥነት፣ ሌብነትና አድሎአዊነት መለያ ባህሪ መሆኑ ተለይቷል።

ይህንን ችግር በሚመጥን መልኩ ክልሉን በሚፈውስና ከነውር ተግባራቸው በሚያላቂቅ፤ ራሳቸውም ተፀፅቶ ሌሎችንም በተዋረድ የሚገኙ አመራሮችን ያርማሉ ተብሎ ብጠበቂም በተቃራኒው በመሪህ ላይ ቆሞ የታገሉትን የክልሉ አፍራሾች እንደሆኑ የተለመደውን እርካሽና የወረደ ተግባር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ።

ይህ ደግሞ የአመራሩ ስብስብ ምን ያህል ፀረ ብልፅግና እንደሆኑና በአፋቸው ብልፅግና በተግባራቸው ወያኔ እንደሆኑ ያሳያል ብሏል።

"በዚህ መድረክ ክፉኛ የቆሰሉ የሴራ ቡድኑና አመራሮች በተሰጠው ስምሪት በስድስቱ ክላስተር ማዕከላት የበቀል ብትራቸውን ገበናቸውን አጋልጠዋል ባሏቸው አመራሮች ላይ የግምገማ ናዳ በማውረድ በፓርቲው የተጎናጸፈውን የሀሳብ ልዕልናን በአደጋ ላይ ጥሎታል" በማለትም የለውጥ ደጋፊ ብልፅግና አባላት ገልጸዋል።

ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 2 በስድስቱ የክላስተር ማዕከላት በፓርቲው በባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል እንደ ሀገር በኢኮኖሚው፤ በማህበራዊ፤ በፖለቲካው እና በውጭ ጉዳዮች በተደረጉ ጥረቶች የተመዘገቡ ውጤቶች ዙርያ አመራሩ የጋራ ተግባቦት በማኖር ለቀጣይ ተለዕኮ የበለጠ እንድዘጋጅ ታስቦ የተካሄደውን ዉድ መድረክ ለእርካሽ ተለዕኳቸው ማሳኪያ መድረክ አድርጎ ተጠቅሟል።

በራሳቸው ጊዜ መከላከል ያልቻሉትን የአሰራር ጥሰትና ብልሹ አሰራርን ለመሸፈን ያለእንቅልፍ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪ ነውር ተግባራቸውን ማስተባበል የሚችሉ ለሆዳቸው የተገዙ ሽማግሌዎችን ከየዞኑ 2ት እንድመለመሉ በማድረግ አሰፈላጊ ወጭዎች ከክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ በሆኑት በአቶ ሃይለማሪያም ተስፋዬ ተመቻችቶ ወደ ፌዴራል ለመላክም ዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

ሌላው በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ከጥር 23 ጀምሮ በሚካሄደው በፓርቲው ጉባዔ ላይ ከየዞኑ መሳተፍ የሚገቡ አመራሮች፤ ተሳትፎ በማድረግ ማን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል መሆን እንዳለበት ልዬታ የማካሄድና ለሚመረጠው ሰው ገጽታ ግንባታ ዙሪያ ዕቅድ ወጥቶ እየተሰራ መሆኑ ነው።

እነዚህ ክፉኛ የቆሰሉ ሴራቸው የተጋለጠባቸው አካላት በህዝቦች መካከል ሌላ ግርግርና ሁከት ቀስቅሰው ለማለፍ ጭምር አደገኛ ዝግጅት እያደረጉ ስለሚገኙ፤ በቀጣይም ፓርቲያችንና ሀገራዊ ለውጡን ወደ ከፋ ፈተና ውስጥ ለመክተት ለአፍታም ስለማይቦዝኑ ተገቢው የእርምት እርምጃ ተወስዶ አካባቢው ከገዥዎች እጅ በማላቀቅ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ብልፅግና በሆኑ አመራሮች የሚመራበት ሥርዓት መዘርጋት ለፓርቲው ቀደሚ ተግባር መሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

Wolaita Times

09 Jan, 09:44


አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰበሰበው ሀብት ለተጎጂዎች ሳይደርስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች መሰወሩ ተነገረ።

በአሳዛኝ ክስተት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለማገዝና ለማማቋቋም ተብሎ ከሀገር ውስጥ እስክ የውጭ ሀገራት እንዲሁም ግለሰቦች ከተሀያዩ ቦታዎች ከ600 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ የተሰበሰበ ቢሆንም ገንዘቡ ለተጎጂዎች ሳይደርስ በክልሉና በአከባቢው ባለስልጣናት መሰወሩን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

እንደመረጃው ከሆነ "በክልሉ የማዕድን ሀብት በመስረቅ የሚታወቁት የክልሉ ምክትል ርዕሠ መሰተዳድር ማዕረግ የክልሉ ውሃ ቢር ኃላፊ አቶ አክሊሉ አዳኝ የክልሉ አደጋ ስራ አመራር ኮሚኒዩከሽን አቶ ጋንታ ጋምኣ በጋራ በመሆን በአርባምንጭ ፓራዳይዝ ሆቴል ሆኖ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመሆን የተጎጂዎችን ሀብት የማሸሽ ስራ ሰርቶዋል" ብለዋል።

እነኚህ በመሬት ናዳ የተፈናቀሉ ወገኖች አሁን በዚህ ሰዓት ከ500 በላይ ህዝብ በላስትክ በቶች በተጠለሉበት ምግብ ውሀ በለለት በራሀብና በችግር ይሰቃያሉ። ከተጎዎቹ የጉልበት ስራ መስራት የሚችሉት ወደ ሳውላ ከተማና ወደ አጎራባች ወረዳዎች በመሰደድ ላይ መሆናቸውንም የመረጃ ምንጭ ጠቁመዋል።

"በአከባቢው እስካሁን የአክሊሉ አዳኝ እና የጥላሁን ከበደ ቅጥረኛ ሙሰኞች የትኛው ሚዲያ እንዳይደርስ እና እንዳያገኛቸው ቀን ቀን ካሉበት ላስትክ ቤት በማውጣት ህዝቡን ጫካ ውስጥ እየደበቁ ናቸው" በማለትም ገልጸዋል።

"በአደጋው ሰዓት ዓለም ሁሉ ከጎናችን ነበር፡፡ ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋምም በጥሬ ገንዘብ ብዙ ሚሊዮን ብሮች እና በቁሳቁስና በዓይነትም ለመገመት የሚያዳግት መጠን ያለው ሀብት ተሰብስቧል፤ በስተመጨረሻም ለተጎጅዎች የሚሰሩ 200 መጠለያዎች በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍለው እንደተሰጡና በዋናነት በመዋቅሮቹ እየተገነቡ ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም "ቤቶች ተገንብተው እንዳለቁ ተደርጎ በዞኑ አስተዳደርና በገነቡ መዋቅሮች መካከል የእርክብክ ስነ-ሥርዓት የተከናወነ ቢሆንም አሁን ላይ በስፍራው የተገነቡ ቤቶች የእንጨት ቤቶች ሆነው በብዛት ጭቃ ያልተመረጉ ናቸው፤ ለተማሪዎች መማሪያ ክፍል ተብለው የተሰሩ ክፍሎችም የእንጨት ቤትና በአግባቡ ጭቃ ያልተመረጉ ናቸው፡፡ በአደጋው የተፈናቀሉ ወገኖችም ቁጥር በአባወራ መጠን ከ1000 ላይበልጥ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ወደ ግማሽ የሚሆን ሰው በሸራ በተወጠረ ዳስ ውስጥ ሆኖ የመከራ ኑሮ እየገፋ ነው ማለት ነው" ብለዋል።

"በአጠቃላይ ይህንን ያህል ሰው ሜዳ ላይ ከተጣለ፤ የተሰሩ ቤቶችም የእንጨት ቤትና በአግባቡ ጭቃ እንኳን ያልተመረጉ ከሆነ፤
*አከባቢው ንፁህ የመጠጥ ወሃና መብራት እንኳን ያላገኘ ከሆነ፤ ትምርት ቤት ተብሎ የተሰራው ዳስ እንጨቶች ብቻ የቆሙበትና በቂ የተማሪ ወንበር እንኳን የለላቸው ከሆኑ፤ የተሰበሰበው ገንዘብና ንብረት የት እንደገባ በአፋጣኝ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት" በሚልም ጉዳዩን በቅርበት የተከታተለና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

አመራሩ አክለውም "ገንዘቡ ሲሰበሰብ በአንድ ቋት መሆን ሲገባው ክልሉ ለላ አካውንት፣ ዞኑ ሌላ አካውንት፣ ወረዳውም ለተወሰኑ ቀናቶች የራሱን አካውንት ከፍቶ በተለያዬ አድራሻ የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ መጣራት አለበት፤ ሌብነትና ዘረፋ ውስጥ የገቡ አመራሮች ካሉም በአፋጣኝ ተጣርቶ በህግ ሊጠየቁና ውጤቱ ለህዝብም ይፋ መደረግ አለበት፥ ከህዝብ ለቅሶ ሳቅ አይዘረፍም!!! ይህ የዘመናችን ነውረኛ ተግባር ነው!! በጎፋዎችም ማሾ!! ማሾ!!! ይባላል" ብለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=5338

Wolaita Times

08 Jan, 14:48


ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የተሰጠ የአቋም መግለጫ፦

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የዎላይተ ሕዝብ ሁለንተናዊ ነፃነትነና ሰላም እንዲሁም ህገመንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ የሚገባውን ክብር እንዲያገኝና መብቱን እንዲጎናጸፍ የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን ሰሞኑን በሕዝባችን ላይ በተደራጀ መንገድ የተከፈተውን ጥቃት አስመልክቶ የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር (ዎህዴግ) እንደሚከተለው ባለሦሥት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፦

1. በአባያና ብላተ አከባቢ ተከስቶ የነበረው ጥቃት ውድ የሆነውን የሰው ሕይወት ባጠፋበት በዚህ ወቅት ከዚህ ሀዘን ሳንወጣ በዛሬ እለት ሀገር ሰላም ነው ብሎ ከዎላይታ ተነስቶ ወደ አርባምንጭና አከባቢው ለሥራ ጉዳይ በሚጓዙ በዎላይታ ተወላጆች ላይ በተደራጀ ጽንፈኛ ቡድን በተፈጸመው ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዎሕዴግ ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አስነዋሪ ድርጊት ለዘመናት ተቻችለውና እርስ በርሱ ተዋድደው የኖሩ ሁለቱ ሕዝቦችን ወደ ሌላ ቀውስ ብሎም ወደለየት አከባቢያዊ ትርምስ የሚያመራ በመሆኑ ድርጊቱን ያስጀመሩ አካላት በአስቸኳይ ከእንደዚህ ዓይነት አደገኛ አካሄድ እንድቆጠቡ በጥብቅ ዎህዴግ ያሳስባል።

በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስትም ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብታቸውን በጥቂት ፖለቲካ ነጋዴዎች ምክንያት እንዳያጡና ለከፋ ጥቃት ሕዝባችን እንዳይዳረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በጥብቅ አናስገነዝባለን።

2. በዎላይታና አከባቢው ባለፉት ሁለት ዓመታት የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ በማሳጣት ማስራብና ለከፋ ችግር መዳረግ አከባቢው እንዳይረጋጋ ሆን ተብሎ የሚሰራ የፖለቲካ ሸፍጥ መሆኑን ዎህዴግ ያምናል። በችግሩ ላይ በተለያዩ ጊዜያትም ይህንን የችግሩን አሳሳቢነትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ይሁንና ይህ ችግር ለአንድ ሁለት ወራት ለመቅረፍ የተሞከረ ቢሆንም አሁንም እንደገና አገርሽቶ የመንግስት ሠራተኛ በደመወዝ እጦት እየተሰቃዬ ይገኛል።

በመሆኑም ይህ በሕዝባችን ላይ በፖለቲካ ቅኝት ታቅዶ የሚሰራ ሴራ ለማናችንም የማይበጅ በመሆኑ በአስቸኳይ ሠራተኛው የላቡን ዋጋ ወቅቱን ጠብቆ የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲመቻችና ደመወዝ በጊዜ እንዲከፈል ዎህዴግ የሚመለከተውን የመንግስት አካላት በጥብቅ ያሳስባል።

3. መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከማድረጉ ጋር ተያይዞ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ያለውን ሕዝባችን በመንግስት ልማት ድርጅቶች በኩል ወቅቱን ያልጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት የሕዝቡ በሕይወት የመኖር ዋስትና እየተፈታተነ እንደሆነ ዎህዴግ ይገነዘባል።

ለዚህ ሁነት ማሳያ ትናንትና ማለትም ከታህሳስ 29/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ወቅቱን ያላገናዘበና የዜጎችን ስቃይ የሚያበዛ ከመሆኑም ባሻገር ነዳጅ በዓለም ገበያ 15% ቅናሽ በተረገበት ተመሳሳይ ወቅት ላይ በእኛ ሀገር የነዳጅ ዋጋ የጨመረበት ምክንያት በርግጥ መንግስት ለገበያ መረጋጋት ትኩረት አለመስጠቱን የሚያሳይ ምልክት በመሆኑ መንግስት የነዳጅ ድጎማ ስርዓቱን እንዲያሻሽል ዎህዴግ ጥሪ ያቀርባል።

በመጨረሻም ሕዝባችን ላይ እዛም እዚህም በተደራጀ መንገድ ከሚደርስበት ጥቃትና የፖለቲካ ወለድ ችግሮቹን የክልሉና የፌዴራሉ መንግስት እንዲከላከል ጥሪ እናቀርባለን።

የዎህዴግ ሥራ አስፈፃሚ
ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ/ኢትዮጵያ

Wolaita Times

08 Jan, 11:10


ትኩረት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

በዛሬው ዕለት መነሻውን ዎላይታ ሶዶ በማድረግ ወደ አርባምንጭ ከተማ እየተጓዙ በነበሩ የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች በጋሞ ዞን የትራፊክ ፖሊሶች በቆሙበት ቦታዎች ጭምር በንብረት ላይ ጉዳት፣ በተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ የስነልቦና ጉዳት መድረሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአይን እማኞቹ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረሱት መረጃ መሠረት፦ ተሳታፊዎቹ ሆነ ጥቃት የደረሰባቸው መኪኖች እንደወትሮው ሁሉ ለንግድና ለግል ጉዳያቸው የሚመላለሱ ቢሆንም በሚያሳፍር እንዲሁም በአከባቢው ህግ የለም በሚያስብል ሁኔታ የመኪና መስበር፣ በሰዎች ላይ ጥቃት ደርሷል።

በመሆኑም እንደዚህ አይነት አፀያፊ ድርጊት ወደ ሌላ መዘዝ ከመቀየሩ በፊት የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡበት አሳስበዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Gamo

Wolaita Times

06 Jan, 14:51


"ብልፅግና እንዳይመረጥ በማድረግ የብልጽግና ወንበር የተቆናጠጡ ቡድኖች"

"ዎላይታ እና ጋሞ በጉርብትና ቢሆን እንጂ በክልል መዋቅር አንድ ላይ በፍጹም አይደራጅም፣ የህዝብም ፍላጎት ያ ነው፣ ሳይደራጅ ለሚፈርሰው የብልፅግና መንግስት ህዝብን ባያስገድድ ይመረጣል" - አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የቀድሞ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብቸኛው ህብረተሰቡ በአመራሮች እየደረሰ ባለው ከፍተኛ በደል የተነሳ ብልፅግና ፓርቲውን በመጥላት ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ በመምረጥ ለክልልና ለፌደራል ፓርላማ ተወካዮቻቸውን መርጦ ካስገቡ ዞኖች አንዱ ጋሞ ዞን እንደሆነ ይታወቃል።

#Ethiopia #Gamo

Wolaita Times

05 Jan, 12:28


#ሰበርመረጃ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ብልሽቶችን በተመለከተ ከ12ቱ ዞኖች የተዉጣጡ ምሁራኖች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት መነሻ የተካሄደውን ጥልቅ ግምገማ በማመስገን ተገቢ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ይፋዊ ደብዳቤ አቀረቡ።

ከክልሉ ከሁሉም አከባቢ የተወጣጡ ምሁራኖቹ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ያቀረቡት የምስጋና እና ተገቢ ውሳኔ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደሚከተለው ደርሰዋል።

"ይድረስ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
-ለብልፅግና ፓርቲ ፕረዝዳንት
አዲስአበባ፤

ጉዳዩ፡- የክልሉን ችግር የሚመጥንና የሚፈዉስ፣ ህዝብን ማዕከል ያደረገና በእዉነተኛ ብልፅግና ዕሳቤ መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንድሰጥ ስለመጠየቅ

በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ከ12 ዞኖች የተዉጣጣን የክልሉ ምሁራን አድስ በተደራጀዉ ክልላችን የታዩ የፖለቲካ ብልሽቶችን በዝርዝር በማቅረብ ተጣርቶ ተገብዉ ማስተካከያ እንድያደርጉ ባቀረብነዉ ይፋዊ ጥያቄ ተቀብሎ በአጭር ጊዜ እንዲጣራ ስላደረጉ በክልላችን ሕዝቦች እና በራሳችን ስም የከበረ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንፈልጋለን፡፡

የሁላችንም ዓላማ በእርሶ መሪነት የበለፀገች ኢትዮጵያ ዕዉን እንድትሆን እኛም ሆነ ክልላችን የድርሻችን አሻራ ማኖርና የዉጤቱ የጋራ ተቋዳሽ መሆን ነዉ፡፡

ከዚህ ከተከበረ ዓላማ በተቃራኒዉ ክልላችን የራሱ አበርክቶ እንዳይኖር በእርሶ በተመደቡት በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቀን ማታ በተደራጀ መልኩ በአፋቸዉ ብልፅግና ተግባራቸዉና አስተሳሰባቸዉ የብልፅግና ተቃራኒ በሆኑት በአስመሳይ ማፊያ ቡድኖች እጅ በመውደቁ የክልሉ ህዝቦች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች አደጋ ዉስጥ እንድወድቅ ሆኗል፡፡

በመሆኑም በባለፈዉ ይፋዊ ደብዳቤ ለማብራራት እንደተሞከረዉና አሁን በአራት የግምገማ ቀናት ቆይታ እንደተረጋገጠዉ የክልሉ የፊት አመራሮች ብልሽቶች በዋናነት የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

👉 ፓርቲው የሚመራበት የመደመር እሳቤና የፖለቲካ ፕሮግራም ላይ የፀና አቋም ያልያዙ፤

👉 የአመለካከት ጥራትና የአሰላለፍ ግልጽነት የሌላቸዉ፤

👉 በክልሉ የሕዝቦች፣ የብሔር፣ የዕምነት፣ የጾታ፣ የአኗኗር ዘይቤና የአስተሳሰብ ልዩነት እውነታ መሆኑን ተቀብሎ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ እኩልነትና የጋራ ግብ የማይተጉ፣

👉 የሕዝቡን ህይወት ለመለወጥና ጠንካራ ተቋማዊ ስርዓት ለመገንባት በቁርጠኝነት የማይሰሩ፣

👉 እንዲሁም የፓርቲውን ዓላማ ከሚያደናቅፉ አመለካከቶችና ተግባሮች ነጻ ያልሆኑና የፓርቲን ተልዕኮ በብቃት መፈፀም የሚችል ሚዛናዊ እይታና ተግባር የሌላቸዉ፣

👉 የክልሉ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ቡድንተኛ፤የሴራ ፖለቲካ የሚጎንጎኑ፤ የመጠላለፍ፣ የመጠቃቃትና መጠቃቀም ልዩ ባህርና ተግባር የሆነበት፣

👉 የክልሉን ህዝብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ከመፍታትና ከማገልገል ይልቅ በተለያዩ ነጠላ ጉዳዮች ዙሪያ በጎራ በመከፋፈል በቡድንተኝነት ፖለቲካ በመተራመሳቸው ምክኒያት በሀዝቦች መካከልም አለመተማመን እና እርስ በእርስ መጠራጠር የፈጠሩ፣

👉 የፓርቲዉን እሳቤ ባፈነገጠ መልኩ በአካታችነትና አቃፊነት ተደምሮ ከመፈጸም ይልቅ በተቃራኒዉ ከመደመር ይልቅ በመከፋፈል፣

👉 ከመደጋገፍ ይልቅ በመገፋፋት፣ ከመተባበር ይልቅ በጎራ መቧደን፣ ከፍቅር ይልቅ በጥላቻ፣ ከአካታችነት ይልቅ በአግላይነት እሳቤ የተጠናወቱ፣

👉 በህዝቦች ይሁንታ የተደራጀዉ ክልል ህልዉና ከራሳቸዉ ስልጣን ጋር በማያያዝ እኛ ከተነሳን ክልሉ ይፈርሳል የሚሉ እና በእዉነትና ህዝብን ማዕከል በማድረግ ከሚታገሉ ዉስን አካላት ጋር የሚደረግ የክህደት ትግል የሚያካህዱ፣

👉 ከምንም በላይ እጅግ በጣም የሚያሳዝነዉ በክልሉ አመራር ላይ የታዩትን ብልሽቶችን ራሳቸዉንም ሆነ ክልሉን ልፈዉስ በሚችል መልኩ ዉስጣዊ አድርጎ ከመቀበልና ለቀጣይ ፈጥኖ ለመዉጣት በሚያስተምር መልኩ ያለመቀበላቸዉ ስሆን ይሄም አመራሮቹ ምን ያክል የብልፅግና ዋነኛ ጠላትና ፓርቲዉንና ህዝቡን ለመነጠል በዕዉቀት ከዉስጥ ሆኖ እየሰሩ እንደቆዩ በግላጭ ያረጋገጠ ስሆን፤

በአጠቃላይ የአራት ቀናት የክልሉ የከፍተኛ አመራሮች ግምገማ ሂደትና በመድረኩ የተንሸራሸሩ ሀሳቦች መረጃ በግልፅ የሚያመለክተዉ የብልሽቱ ሁኔታና ከችግሩ ለመማር ያለዉ ዳተኝነት በጣም አስደንጋጭ ስለሆነ ከመድረኩ ባለፈ ህዝቡ ዉስጥ የዘለቀ የመረጃ የማጥራት ሥራ በገለልተኝነትና ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ ተከዉኖ ክልሉንና ፓርቲዉን የሚያሻግር፤ ህዝቡን እርስበርስ በማባላት ለመኖር የሚፈልጉ የየአካባቢዉ ገዥዎች፤ ከፋፋይ ተግባራቸዉን በሚዲያ በመቀባት የስልጣን ጊዜያቸዉን በማራዘም ህዝቡንና ፓርቲዉን ለመነጠል የሚሰሩ ስዉር እጆችን፤ በመድረክ በፓርቲዉ ስም የሚተዉኑና የሚገዝቱ ከመድረክ ጀርባ ሆኖ ደግሞ የሴራ ንጉሰ ነገስቶች ለዚህ በማሳያነት የ12ቱ ዞን አስተዳዳሪዎችን ኦሪዬንቴሽን ሰጥተዉ በማስገባት እዉነታዉን ለማዛባት የተደረገዉ ሙከራ ታይቷል።

ይህም አስተባባሪዉ ኮሚቴ በጅምሩ ስደራጅ ጀምሮ የፈደራል መንግስትንም ጭምር በማሳሳት በዕዉቀት የተፈጠረ ክህደት እንዳለ በግልፅ የጠቆመ መሆኑን በማጤን ክቡር የፓርቲዉ ፕረዝዳንት ከጅምር ጀምሮ የነበረዉን ሂደትና አሁን የታየዉን ብልሽት በመፈተሸ በፍላጎቱ አንድ ሆኖ የተደራጀዉን ህዝባችንን ከመበተንና እርስበርስ ከማባላት አዉጥቶ አንድነታችንን፤ አብሮነታችንን፤ ወንድማማችነትን የሚያጎለብትና ወገን ዘለል ትስስር ላይ የሚያተኩር፤

እንዲሁም ሁሉንም ሕዝቦች እንደ ልጁ የሚመለከትና በአፍ የሚያወራዉን የሚፈጽም አስመሳይ ያልሆነ አባት መሪ የሚያስፈልግ መሆኑን በማመን ክልሉን ለዳግም ቀዉስ ዉስጥ በማያስገባ ሁኔታ የአመራር መልሶ የማደራጀት ሥራ እንዲታሰብ በትህትናና በታላቅ አክብሮት ጥሪያችን እያቀረብን እርስዎንና እኛን በመሀል ሆኖ የሚያጣሉትን ካሰወገዱልን የክልላችን ህዝቦች ከእርስዎና ከፓርቲዎ ጎን መሆኑን በድጋም ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!!"

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ብልሽቶችን በተመለከተ ከ12ቱ ዞኖች የተዉጣጡ ምሁራኖች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት መነሻ የተካሄደውን ጥልቅ ግምገማ በማመስገን ተገቢ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ይፋዊ ደብዳቤ

ታህሳስ /2017 ዓ.ም

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

Wolaita Times

04 Jan, 17:39


"ንጹሀን ወገኖችን ያስገ'ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ" - የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን

"በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል አመራሮች መድረክ ተጀምሯል። በቀድሞዉ የደኢህዴን አዳራሽ ዉስጥ። ርዕሱ ደግሞ የክልሉ የ6 ወራት የድርጅት እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸምና ወቅታዊ ጉዳዮችን መገምገም ይላል። የተጀመረው ደግሞ ቦና ወረዳ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነዉ" ስሉ አንድ የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ወደ ሰነዱ ይዘት ሳይገባ አስቀድሞ "ወቅታዊ ሁኔታዎች" ላይ የጋራ አቋም መያዝ አለብን በማለት በሁለት ሀሳቦች ላይ አስቀድሞ ዉይይት ተደርጎ እንደነበር አስረድተዋል።

"ባለፈው ሳምንት ቦና ወረዳ በተፈጠረውና ከ71 ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ በተመለከተ "ክልሉ ዝምታ መርጧል፣ ክልላዊ ሀዘን ማወጅ አለበት ተብሎ የሚናፈሰዉ ነገር ዉጪና ሀገር ዉስጥ የሚገኙ ጥገኞች የሚያናፍሱት ወሬና የፖለቲካ ቁማር ስለሆነ አስፈላጊ ምላሽ መስጠት አለብን፣ ፕሬዝዳንቱ ጭምር ሄዶ አስቀብ አጽናንቷል፣ የድጋፍ አካዉንት ተከፍቶ ድጋፍ እየተደረገ ነዉ" የሚል ሀሳብም መነሳቱን አክለዋል።

በመድረኩ በሎካ አባያ ከዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ጉዳይ ክልሉ ለምን መግለጫ አልሰጠም? የተፈጠረዉ ነገር ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ሰዉ መኖሩ ተገቢ ቢሆንም ከአቶ አብርሃም ጋር አያይዞ የዉስጥ ባንዳ ከዎላይታ ጠላቶች ጋር በማበር ጓዱን ከስልጣን መነቅነቅ ስለ ጀመሩ አመራሮች በአንድ አቋም መታገል አለባችሁ" በሚል አንድ አመራር አስተያየት መስጠቱን ተናግረዋል።

አክለውም "ይህ ነገር ሰፍቶ እስከ ፓርቲው ዋና ቢሮ ከደረሰ ጓዳችንን ልናጣው እንችላለን የሚል ሀሳብ በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ አንዳንድ አመራሮች "የዎላይታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ነዉ እየታገሉ ያሉት፣ ለኢንቬስትመንት የተሰጡ መሬቶችን በዞኑ በኩል እንደተሰጠ ጭምር በቂ መረጃ እያቀረቡ ነዉና በእኛ በኩል ምን አለ" የሚሉና ከአብርሃም፣ ከአባቱና ዘመድ አዝማዱ ጋር ተያይዞ በሎካ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታሮችን በጸጥታ ሀይል ጭምር በመታገዝ እየተወረረ ነዉ የሚል ወሬ በህዝቡ ዉስጥ እየሰፋ ነዉና ሀሳቡን የመመከት ስራ መስራት አለብን" በሚል አመራሩ የድጋፍ አስተያየት መስጠቱንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም እኚህ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጪ አመራር፦ "አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይህንን የሚፈጽሙት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን (ይርጋለም ዞን) የሰላም፣ ጸጥታና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ባስቀመጠው በወንድሙ አማካኝነት በወታደር ጭምር ታግዞ ነዉ የሚል ወቀሳ በተጨባጭ የቀረበ ስሆን፣ ይህንን ችግር ሌላ ጊዜ በራሳችን መድረክ እናየዋለን አሁን ግን ለጠላታችን መጠቀሚያ ሳንሆን ከጓዱ ጋር መቆም አለብን፣ ሁሉም አመራር በአጠቃላይ ከአብርሃም ጎን እንደሆነ በማሳወቅ በዎላይታ በኩል የሚመጣዉን ጫና በተደራጀ መልኩ በፌስቡክ ዘመቻ፣ በሚዲያ ሰራዊት እንምራ በሚል ማሳሰቢያ ተዘግቶ ወደ ሰነዱ ንባብ እንደተገባ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት።

በአቶ አብርሃም ጉዳይ ላይ በሚነሳው አጀንዳ ላይ በመድረክ ከአብርሃም ጋር የነበሩት የክልሉ ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ አንድም አስተያየት ያልሰጡ ሲሆን ስለ ቦና የትራፊክ አደጋ በተመለከተ በመፍትሔውና ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰብን በዘላቂነት ማጋዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ በስፋት እንደተናገሩም የመረጃ ምንጫችን ጠቁመዋል።

የመድረኩን መረጃ ያደረሱት እኚሁ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ስለ አቶ አብራሃም ሲገልፁ፦ "የማዕከላዊ ዞን የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ማርሻሎ (የአብርሃም ወንድም) ሎካ አባያ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነዉ፥ በተደራጀ መልኩ ነዉ ሲዳማንም ዎላይታንም እየበደሉ ያሉት። ወንድሙን በመሾሙ ምክንያት ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣ አስነስቶ ነበር" ብለዋል።

ባለስልጣኑ አክለውም፦ "በወንድሙ ትዕዛዝ መሰረት በሎካ ድንበር ንጹሀን ዎላይታዎችን ያስገ'ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ። ለዎላይታ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አብርሃምና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከእርሱ ጋር የተባበሩ አመራሮች ናቸው። አቶ አብርሃም የህዝብ ንቀቱ ጫፍ (ወንድሙን ከወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኝነት ቀጥታ የዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አድርጎ በወታደር ሀይል የህዝብን መሬት እየወረረ ይገኛል" በሚል ገልጸዋል።

በመጨረሻም እኚሁ የመረጃ ምንጭ ባለስልጣን፦ "የሚገርመው አንድ የአቶ አብራሃም ደጋፊ ዘመድ የሆነ አመራር በዛሬው ስብሰባ የዎላይታ አክቲቪስቶች አብርሃም ላይ ሲዘምቱ በሲዳማ ዉስጥ የሚገኙ የወላይታ ተወላጆችን ቀብድ አስይዘው ነዉ የሚል አይነት እንድምታ ያለው ንግግር እየተናገሩ እንደ ነዉር እንኳን አይቆጠርም። ለአንድ ሌባ ሙሰኛ ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል ያን ያህል መላላጥና መጋጋጥ አሳፋሪ ነው ገዢው ፓርቲ በእነዚህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል እሳት በሚጨምሩት ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ተደራጅተን እየተንቀሳቀስን ነው" ብለዋል።

እንደሚታወቀው አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ባለሀብት ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ባለው ሳምንት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጨባጭ መረጃዎችን አስደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።

በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

በተጨማሪም የብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑም እንዲሁም።

በተፈጠረው የተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ያለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ መምረጡ ተጨማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ገልጿል።

እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ የመረጠ ሲሆን በተፈጠረው በተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች ተገድለዋል፣ በርካቶች ቆስለው ጤና ተቋማት ላይ ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ የሰው ህይወት ሳይጠፋ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

Wolaita Times

04 Jan, 17:39


👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama
ሲዳማ ክልል የአባላ አባያ ጥቃት ምን አለ?
Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5331

Wolaita Times

03 Jan, 14:38


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከገቢ የሚገኘውን ገንዘብ አሰራርን ጥሶ ከመዝረፍ ባሻገር ቢሮው ከ45 በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ መቅጠሩ ተነገረ

የክልሉ ገቢ ቢሮ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ሰዎች ብቻ እንዲሰሩ በመደረጉ በተለያዩ ዞኖች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ መሆኑንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ በተለይም በዎላይታ ዞን፣ በጌዴኦ የሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ግብር ከፋይ የሆኑ ባለሀብቶች ላይ ያለአግባብ ጫና በመፍጠር ፋብሪካዎች እንዲዘጉ፣ ባለሀብቶች እንዲታሰሩ እና እንዲሸማቀቁ መደረጉም ተገልጿል።

በክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች ከግብር ከፋይ የተሰበሰበ ከፍተኛ ገንዘብ የተለያዩ ህገወጥ ዘዴዎችን በመጠቀም በክልሉ ርዕሰ መስተደድር አማካይነት ወጪ ተደርጎ እንዲወጣ ተደርጎ በኢፍትሃዊነት ለራሳቸው ለሚሉት ጥቅምና ፍላጎት መጠቀሚያነት እያዋሉ ስለመሆኑም የደረሰን ተጨባጭ የስነድ መረጃ ያመለክታል።

በተለይም የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የስነምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆነና የልጇን ባል ሾፌር በማድረግ ጭምር ከማህበረሰቡ እሴት ውጪ ባህሪ የሚያሳዩ እንዲሁም የሌሎች ብሄሮች ሰራተኛ አለአግባብ እንዲባረሩ በውድድርም እንዳይገቡ በማድረግ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ብቻ እንዲሆኑ በማድረግ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ግብር ከፋዮች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ እንደምትገኝ አንድ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተል አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግረዋል።

ከ 45 በላይ ስራተኞች የቢሮው የሰው ሀብት አመራሮችና ሰራተኞች ሳያውቁ በህገወጥ መንገድ በራሷ ፊርማ ብቻ ቅጥር መፈፀሟንም መረጃው አመላክቷል።

ለማሳያነት ከክልሉ ገቢዮች ቢሮ አመራርን ጨምረው አጠቃላይ 77 ሰራተኞች 88% ጋሞ፣ 6 የዎላይታ ተወላጆች (2 ሾፈሮች እና 4 ተራ ስራተኞች) እንዲሁም የተቀሩ ሰራተኞች 3% የማይሞሉ ከሌሎች ብሄሮች እንደሆኑ ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ይጠቁማል።

ፌደሬሽን ምክርቤት ባፀደቀው ህግ መሠረት በክልሉ በአንድ አከባቢ የሚገኝ የፈደራል ተቋም ለክልሉ በማሳወቅ ለፌደራል ገቢዎች ከከፈለ በኃላ በፐርሰንት ወደ ተቋሙ ያለበት ዞን የሚላክ "የጋራ ገቢ ህግ" መሠረት መላክ የነበረበትን በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ከግማሽ በታች እንዲሆን ማድረጓንና አለግባብ ገንዘቡ በህገወጥ አሰራር ወጪ እየተደረገ ስለመሆኑም ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አመራር መረጃ ከሆነ በህጉ መሠረት፦ ከጋራ ገቢ ከፌደራል ለሚመለከታቸው ዞኖች ለክልሉ የተላከውን በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ገንዘብ አለአግባብ ለአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ፣ ለአደባባይ ግንባታ፣ ለተለያዩ መስተንግዶ፣ ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሆነና ኦዲት እንዳይደረግ በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና መከልከሉንና እስካሁን ኦዲት ተደርጎ አለማወቁን አስረድተዋል።

በክልሉ ዎላይታ ዞን ከክልል ማዕከል ውጪ ባለው ዕቅድ 60% በመቶ በላይ ይይዛል፣ በ2016 በጀት አመት ዞኑ በክልሉ ከፍተኛ ገቢ ሰብስቧል፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 6.1 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በ6 ወር አፈፃፀም ብቻ ከ 3.9 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ በአፈፃፀም ከክልሉ ከፍተኛ አፈጻጸም አሳይቷል፣ በተቃራኒው በዘንድሮ በጀት ዓመት ጋሞ ዞን 5 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በስድስት ወር አፈፃፀም 1 ቢሊዮን ብቻ መሰብሰብ መቻሉን ከሪፖርቱ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

የመንግስት ስራተኞች ደመወዛቸውን በአግባቡ መክፈል እየተቸገሩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች የሚከፍሉትን ግብር ሰብስበው ለሰፈራቸው ልማትና ለግል ጥቅም እያዋሉ የሚገኙ የገቢ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አለመነሽ ደመቀ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው ስብሰባ ላይ ጥብቅ የጥቅም ግንኘነት ያለውን የክልሉን ርዕሰ መስተደድር ገበና ለመሸፈን እንዲሁም በቢሯቸው ከሰሩት ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂነት ለማምለጥ "ዎላይታ ዞን ግብር አይከፍልም" በሚል የውሸት ክስ ማቅረቧን ተከትሎ በርካቶች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

ለግንዛቤ ያህል፦ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገንዘብ በፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ለሁሉም ዞኖቹ በህጋዊ ቀመሩ መሠረት ገቢ ማድረግ ሲገባው በተቃራኒው ያንን ህጋዊ ቀመር በመጣስ ገንዘብ በክልሉ እንዲቀር በማድረግ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመመሳጠር አለአግባብ ወጪ እንዲሆን ያደርጋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

ለመሆኑ "88% የሰፈር ሰዎችን በመሰብሰብ የግብር ከፋዮች ገንዘብ መዝረፍና ለዝርፊያ እንዲያመች ከ45 በላይ ሰዎች ህገወጥ መንገድ ቅጥር ለምን አስፈለገ ?...... Read more on our official website 👇

https://wolaitatimes.com/?p=5324

Wolaita Times

03 Jan, 08:17


#ሰበርመረጃ

ላለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ብልሽት ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው ጥልቅ ግምገማ ማምሻውን ተጠናቀቀ

መድረኩ የተዘጋጀው "ህዝብን ማገልገል ትተው በግሮሴሪና እና አልጋ ቤት" ውሏቸውን ያደረጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች በሚገባ ተገምግሞ እንዲቀርብ ተብለው ጠቅላይ ሚኒስትር በሰጡት አቅጣጫ መሠረት እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

መድረኩን የመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የገዥው ፓርቲ ም/ፕረዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ሲሆኑ ሚኒስተሮች፣ በፌደራል በክልል ደረጃ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው የክልሉ ተወላጅ አመራሮች በተገኙበት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉተራ አዳራሽ ተካሂዷል።

በዋናነት ስር በሰደደው ሙስና፣ ስነምግባር ጉድለት፣ አድሏዊነት፣ ብልሹ አሰራር ዙሪያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ጥልቅ ግምገማ መድረክ ከፍተኛ ጥበቃ ተደርጎ መካሄዱን ከአንድ ተሰብሳቢ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በግምገማው በርካታ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በተለይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማንአለብኝነት በህገወጥ መንገድ ስለፈፀሙት አድሏዊነት፣ ሙስና፣ የአሰራር ጥሰት፣ ሰፈርተኝነትና ኢፍትሃዊነት በስፋት ተነስቷል።

በአብዛኞቹ ተሰብሳቢዎች በክልሉ የመንግስት አሰራር ሆነ የገዥው ፓርቲ ተግባርና ስልጣን በግለሰቦች እጅ በመውደቁ በየአካባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጥና ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል እንቅፋት በመሆን ከክልሉ ሆኗል በሚል ተገምግሟል።

በክልሉ አመራሮች መካከል በግልጽ የሙስና ተግባራቸው በመረጃና ማስረጃ ተደጎፎ የተነሳው ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አክሊሉ አዳኝ ከአስተዳደራዊ እርምጃ ባሻገር በህግ እንዲጠይቁ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመድረኩ የክልሉ አመራሮች የህዝብን አደራ ወደ ጎን በመተው በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል ያላቸውን ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ላይ በርካቶች ጥፋት ውሰጥ ተዘፍቀው መኖሩን በማብራራት በፌደራል ደረጃ የተመደቡ የክልሉ ተወካዮች የወከላቸውን ህዝብ እንዳይገናኙ በማድረግ ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ በእጅዙር የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር ጥፋት ለመሸፈን ጥረት አድርጓል በሚል በመረጃ ከሷል።

የመድረክ መሪዎች በክልሉ ያለውን ከፍተኛ ብልሽት በተመለከተ የተነሱ ተጨባጭ መረጃዎችን በመውሰድ አስቸኳይ እርምት እርምጃ የሚያስፈልገው በመሆኑ በቦታው ምንም የውሳኔ ምላሽ ወይንም የማስተካከያ መመሪያም ሳይሰጡ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመልሷል።

ነገር ግን ይሄንን የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምረው በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሳተፉበት ትልቅ መድረክ በክልሉ ሆኑ በክልሉ ባሉ መዋቅሮች ሚዲያዎች ላይ እስካሁን አልተገለፀም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

02 Jan, 12:42


ዞኑን ብቻውን ለመቆጣጠር ካለው ፍላጎት የተነሳ በክልል ደረጃ ከፍተኛ ስልጣን ካላቸው አንዳንዶቹን ከህገ- ወጥ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ባገኘው ገንዘብ አማካይነት ዞኑ ከእጁ እንዳይወጣ በእርሱ ሳንባ የሚተነፍሱ ሰዎች መንግስታዊና ፓርታዊ መደቦችን እንዲቆጣጠሩ የተላላኪነትንስ የአገናኝነት ሥራ ይሰራሉ።

እንኚህ ሁለት ግለሰቦች አንዱ በዲላ ከተማ የፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊነትን ይዞ ያለ ሲሆን አንደኛው ደግሞ እራሱን እንደ ስድስተኛ የዞን አስተባባሪ እየቆጠረ ካለው ጋር በኤኮኖሚ ሥራ እጅና ጓንት ሆኖ የምንቅሳቀስ ነው። ድብቁ ስድስተኛ አስተባባሪ በሁለቱ ታማኝ የመረጃ ጥንዶች አማካይነት ከአምስቱ አስተባባሪዎች ውስጥ ለዓላማው ምቹ በማይሆን ግለሰብ ብርቱ ክትትል ይደረጋል።

ከተማው ውስጥ ያለውን ከኮንትሮባንድ ንግድና ሌሎች ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ገንዘብ ይሰራል። የአምስቱ ጥምረት በዞኑ የፈለገውን ጥቅማ ጥቅም እንዳያስቀርበት የፓርቲ ጽ/ቤቱን ወይም አስተዳደሩን በመጫን የወረዳው መዋቅሮች ለእርሱ ድጋፍ በሚሰጡ ኃይሎች እንዲዋቀር ይሰራል። በቅርቡ እየሆነ ያለው አሿሿምም ለዚህ ጥሩ አስረጅ ነበር።

ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ዞኑን እንደስድስተኛ አስተባባሪ እየመራ ያለው ይህ ግለሰብ አባል ሆነን በተሰለፍንበት በራሳችን ብልፅግና መዋቅር ውስጥ ጠንካራ ግለሰቦች ወደፊት እንዳይወጡና ዞኑን እንዳይመሩ ከክራይ ሰብሳቢ ኃይሎች ጋር ሆኖ መስራቱ እስከመቼ ይቀጥላል በምል እንጠይቃለን። የክልል መንግስት የሰጠውን የግብርና ቢሮ ለራሱ ፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሙን የክልሉም ይሁን የፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ እያወቀ ዝምታን መምረጡ የበለጠ አግራሞትን ፈጥሮብናል።

በመሆኑም እውነተኛውን የብልፅግና መንገድ ለምንከተል ደጋፊዎች ይህ እንደ ካንሰር በአምስቱ ህጋዊ ሰውነት ላይ የተጣበቀው በሽታ ከወዲሁ መዲኃኒት ካልተበጀለት ብልፅግና ፓርቲ በህዝባችን መካከል ላሰበው ሁለገብ ዕድገት እንቅፋት እንደሚፈጥር ታውቆ ጉዳዩ የሚመለከተው አክስል ችግሩን ከሥሩ በማስጠናት መፍትሔ እንዲያስቀምጥ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።"

ከጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት የተላከ መልዕክት

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Gedio

Wolaita Times

02 Jan, 12:42


አስቸኳይ መልዕክት!

የደቡብ ክልል መንግስትን ግምገማ ለሚመራ አካል ከጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት

"በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ያለው ብልፅግና ሀገር አቀፍ ፓርቲውን በሚመሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድና ምክትላቸው አቶ አደም ፋራህ በሚያስቀምጡት አቅጣጫ ሳይሆን በብልፅግና ፓርቲ ሽፋን አድርገው ዞኑን የእነርሱ የግል ንብረት ለማድረግ ሌት-ተቀን በሚዳክሩ ጥቂት የፖለቲካ ተሿሚዎችና ከንግድ ማህበረሰብ ውስጥ ከወጡ ጥቂት ክራይ ሰብሳቢ ግለሰቦች በኩል አቅጣጫ እየተቀመጠ እንደሆነ ከውስጥ ሆነን ማየት ከጀመርን ሰነባብተናል።

አዎን አሁን ዞኑን እየመራ ያለው በዶ/ር ዝናቡ ወልዴ የሚመራ ካቢኔ እንደሆነ አልጠፋኝም። ሆኖም ዶ/ር ዝናቡ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህም ቢሆን ዶ/ሩ ያላቸውን ነፃነት ተጠቅመው ዞኑንና ህዝቡን በፈለጉት ልክ በነፃነት እየመሩ እንዳልሆነ ብዙ ምልክቶችን በቅርበት ማየት በመቻሌ ነው።

በሆነ ጫናና ቁጥጥር ውስጥ ዞኑን እየመሩ እንደሆነ ግንዛቤው ስላለኝ ነው። ሆኖም ዶ/ር ዝናቡ በዚህ ጫናና ቁጥጥር ውስጥ ሆነው የሚያደርጉትን ጥበብ የተላበሰ አመራር እያደነቅሁ ቢሆንም ይህንን የታወቀ ጫና ከሚመሩት ህዝባቸው ጋር ተቋቁመውና ተጋፍጠው የማለፍ አቅም እያላቸው ጫናውን ለማስታመም መፈለጋቸው ለዞናችን ፖለቲካ ዛሬም ፈውስን እንዳላጎናፀፈ ይሰማኛል።

ዛሬም ይህንን ያፈጠጠውን ተግባር ከላይ ያለው የፓርቲያችን ቤት መፍትሔ ያበጅለታል ብለን በትዕግሥት ብንጠብቅም እዚያው ነው። ብልፅግና ፓርቲያችን ከተመሰረተ አምስተኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ወቅት ላለፉት አምስት ዓመታት ከላይ ያለው የበላይ አካል በዝምታ ያያቸው ጉዳዮች ዛሬ ከመስመር ወጥተው ለዞኑ መጥፎ ድባብ ሰጥተዋል።

አሁንም አልመሸምና ህዝባችን ብልፅግናችን ላይ ያለው እምነት እንዳይሸረሽር አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ከመጠየቅ ጋር በዞናችን የነበረውን የአስተዳደርና የፖለቲካ ሥልጣን መዋቅር ችግር ከትዝብቴ ተነስቼ ማስቀመጥን ወደድኩ። ማን ያውቃል ዞን ያልቻለውን ክልል፣ ክልል አውቆ ያልፈታውን ችግር የፌዴራል ጆሮ ሰምቶ ትኩረት በመስጠት የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ዘመን ቢመጣ በምል ግምት!

የፖለቲካ ዓይን ቀጥተኛውን ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚካሄደውንና የሚያርፈውን ጫና በጥንቃቄ ያያል። ከዚህ በመነሳት ያለፊት አምስት የብልፅግና ዓመታት ዞኑ በተፈለገው ልክ እንዳያድግ እንቅፋት ሆነው ከቆዩ ጉዳዮች አንዱ በአመራር ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች ለአንዳንድ ኃይሎች ጥገኛ እንዲሆን አሳልፎ መስጠት ነበር።

እነኚህ ኃይሎች በንግድ ሽፋን ህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ስለሆኑ ጥገኛ ባለሥልጣናትን በገንዘባቸው ይዘውራሉ። በገንዘባቸው ለእነርሱ የሚመቸውን ወደ ሥልጣን ያስወጣሉ። እንቅፋት የሚሆኑ ካሉም በአስቸኳይ ከሥልጣን እንዲባረሩ ያስደርጋሉ።

ይህ የተለመደ የዞናችን የፖለቲካ ጫወታ ነበር ነውም። አምስተኛውን የፓርቲያችንን ምስረታ በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ላለፉት አምስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ከላይ በተቀመጠው ምክንያት ለዞኑ መቀጨጭ በበርካታዎቹ ውስጥ እንደ ሰበብ በዋናነት ስሙ የሚነሳውን ሰው ለማንሳት ዛሬ እንደፍራለን።

በመንግስት ደረጃ ዞኑን እንዲመራ የተቀመጡ ዶ/ር ዝናቡ እንደሆኑ በበርካታው የዞን ህዝብ ይታወቃል። እንዲሁም ፓርቲውን እንዲመሩ አቶ አበባየሁ ኢሳያስን። ዞኑን በሥራ አስፈፃሚነት ተያይዘው እንዲመሩ የተቀመጡት ደግሞ በድምሩ አምስት እንዳሉን ለሁላችንም ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ የዞኑ ፖለቲካ የሚዘወረው በአምስቱ ህጋዊያን ብቻ ሳይሆን ከፓርቲው ጀርባ ሆኖ ለስድስተኛነት እራሱን ካጨው አካል ጋር ነው።

መንግስት የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮን እንዲመራው ከተቀመጠው ሥልጣን ጋር በማዳበል ፓርቲውን ለመቆጣጠር በሚዳክረው አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ናቸው። ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ዞናችን በአምስት ሥራ አስፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆን ስድስት አስተባባሪ ሥራ አስፈፃሚ አካላት እንደሚመራት ማሳወቅ እወዳለሁ።

በእኔ የቅርብና የቆየ ትዝብት በአንድ ፖርቲ አባላት መካከል እርስ በርስ መጠራጠርና መጠላለፍ ከፍተኛ ሚና በመጫወት የታወቀውን ይህንን ግለሰብ የክልልም ይሁን የፌዴራል ብልፅግና ጽ/ቤት ለምን በእቅፉ እንደያዘ ግራ ይገባኛል።

በህዝብ የተመረጠ ነው እንዳልል በ2013 ዓ/ ም ብሄራዊ ምርጫ የአካባቢው ህዝብ በካርድ የቀጣው ነው፣ ዞኑን በፖለቲካ አዘምኖታል እንዳልል ደግሞ በዞኑ የፓርቲ አመራር አካላትን በሁለት ከፍሎ ጥርጣሬን የሚያነግስ ስብዕና የተላበሰ እንደሆነ እየታወቀ ለምን ማጀገን እንደፈለጉት ሊገባኝ አልቻለም።

ይህ ግለሰብ ዞኑን በጋራ መርተው ወደተፈለገው ውጤት እንዲያመጡ ፓርቲያችን ብልፅግና ያስቀመጣቸውን አመራሮች በመከፋፈል የውስጥ አንድነት እንዳይፈጠር ካደረጋቸውና ክልልና ፌዴራል ብልፅግና ጽ/ቤቶች ከሚያውቁት ጉዳዮች አንዱ ቢጠቅስ ደስ ይለኛል ይኸውም የደቡብ ክልል በአዲስ አወቃቀቅር በክልላዊ መንግስትነት ሲመሰረት ከአንድ ዞን ለጉባኤው በታደሙት የዞኑ ተወካዮች መካከል የተፈጠረው የአመለካከትና የአቋም ልዩነት ያሳረፈው ጫና ዛሬም በዞናችን ውስጥ ያለንን ድርጅታዊ ትስስር ፈታኝ እንዳደረገው ነው።

ከዞኑ ለጉባኤው ለታደምንም ይሁን ጉዳዩን በጥልቀት ለተከታተለው ሁሉ ትልቅ ጥያቄ የጫረብን በአቶ ኃይለ ማሪያም ተስፋዬ በኩል የተንፀባረቀው የክልሉ መንግስት መቀመጫ አርባ ምንጭ መሆን አለበት ብሎ ሽንጡን ገትሮ መከራከርና ከዶ/ር አበባየሁ ታደሰ በኩል የወከለውን የጌዴኦ ህዝብ ጂኦግራፍያዊ አቀማመጥ ከግንዛቤ በማስገባት ህዝቡን ቢያንስ ሊያማክል ይችላል በሚል ዋና መቀመጫ ዎላይታ ሶዶ ይሁን ብሎ ያቀረበው ሳይንሳዊ ትንታኔ ተቀባይነትን አግኝቶ መጽደቁ ነበር።

ለአቶ ኃይለማሪያም በእነ ጥላሁን ከበደ በኩል የተሰጠው አጀንዳና ተስፋ የፖርቲው አላፊ እንደሚሆን እንደነበረ ጭምጭምታዎች ነበሩ። ለእኔ ዛሬም ጥያቄ የምሆንብኝ ግን የአቶ ኃይለማሪያምን የውስጥ ስልጣንን ለማርካት የሄደበትን አካሄድና የዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ህዝብን ያስቀደመ ሳይንሳዊ ጥያቄ መሆኑን ያወቀው የፌዴራል የብልፅግን አመራር እስከዛሬ ዝምታን መምረጡ ነው።

በክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በኩል ግለሰቡ የተሰጠው ቦታና ጉዳዩን እያወቀ ዝምታን በመረጠው የፌዴራል ብልፅግና የተኮፈሰው ይህ ሰው ነው እንግዲህ እራሱን እንደ ስድስተኛ አካል አድርጎ ለዞኑ የሰየመው። በክልል መንግስት የተሰጠውን የግብርና ቢሮ በሚጠበቀው መልክ እንደመምራት በርካታ ጊዜውን ከዞናችን አመራር ጋር በአካልና በስልክ መገናኘትና ቀጭን አመራር መስጠትን ተያያዘው።

ግለሰቡ የዞኑ ፖለቲካ ለመቆጣጠርና በቀጣይ የዞኑ ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ ለመቅረብ ላለው ስውር ዓላማ የሚያስፈጽሙለትን ሁለት ግለሰቦች መድቦ ማሰራት ጀመሮ ይገኛል። እነኚህ ሁለቱ የመረጃ ኤጄንቶች ደግሞ የአምስቶቹን አስተባባሪዎች የየዕለት እንቅስቃሴ የሚከታተሉ፣ በየቢሮውም ይሁን ከቢሮ ውጪ በዲላ ከተማ ሃያ አራት ሰዓት የመንቀሳቀስ መብት የተጎናፀፉ ናቸው።

ሁሉም የመንግስትና የአስተዳደር ሠራተኞች ወደ ቤታቸው በገቡበት እነኚህ ሁለቱ ምሽት እስከፈለጉ ሰዓት ውጪ በመቆየት ስውሩ ስድስተኛ አስተባባሪ የሰጠውን ተልዕኮ ይፈጽማሉ፣ ክራይ ሰብሳቢ ከሆኑ ነጋዴዎች በኩል ያገኙትን መረጃ ያደርሳሉ፣ ነጋዴውንና ስድስተኛውን አስተባባሪ B -2 መዝናኛና ድብቅ ሆኖ በተዘጋጁ ሌሎች መዝናኛ ቦታዎች ላይ እንዲገናኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ።

Wolaita Times

01 Jan, 15:02


የዎላይታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ ልቦናዊ፤ ስነ ምህዳራዊ መጎሳቆል ከመቼ ይጀምራል? ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት በተለይም የአጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር ? - ከፈረንሳዊ አይን ምስክርነት

(ክፍል ሁለት)

ይህ ጸኁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ
#ቫንደራሂም /J.G Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደ ነው፡፡

ጹሑፉ ጉምቱ የዎላይታ ባህል አዋቂና ምሁር ለነበሩት ለክቡር ዶክተር ዘብድዎስ ጫማ በነጻ የተሰጠ ስጦታ አንደነበር በትርጉሙ ላይ ተብራርቷል፡፡

ጸሃፊው ስለ ዎላይታ እንደጻፈው ከወረራው በፊት ዎላይታ በፖለቲካው መስክ በራሱ ንጉስ ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ግዛት ነበር። ዎላይታ በኢኮኖሚው በለምነቱና በልምላሜ የሚታወቅ በመሆኑ ዎላይታዎች በምግብ ራሳቸውን ችለው ይተዳደሩ ነበር፡፡

በባህል ደግሞ ዎላይታዎች ድንቅ ባህልና ቅርስ አንዲሁም የራሳቸው የእምነት ተቋማት ነበራቸው፡፡ ዎላይታዎች እጅግ በጣም በጀግንት የአቢሲኒያ ወታደሮች ስለተቋቋሙ ንጉሳቸውን ጦና በቀላሉ ለመያዝ አልተቻለም፡፡
በስነ ልቦና ዎላይታዎች ደስተኞች፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ጀግና ተዋጊዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ ጠቢባን… እንደነበሩ እንመለከታለን፡፡

በክፍል አንድ ዎላይታ ከምኒክ ወረራ በፊት ምን ትመስል እንደነበር ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደት ምን እንደሚመስልና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል በተመለከተ ተቀንጭቦ ቀርቧል፡፡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የታሪክ ጥንቅር ላይ፦ ትርጉሙ ከዚህ በታች ቀርቧል መልካም ንባብ!

የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደትና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል ድፍን ሶስት ወራት ለዘመቻው ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ የጉዞ ቀን ህዳር መጀመሪያ አካባቢ መሆኑ ገልጽ እየሆነ መጣ፡፡ አዲስ አበባ ካለወትሮ በበለጠ ሽር ጉድ በዛ፡፡ ከንጉሱ ጋር እንዲሄዱ የተጠሩት ጀኔራሎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ፡፡ በጣም የተጠበቀውና ከሁሉም የላቀ እና ከራሱ ሰዎች ጋር 10000 (አስር ሺህ) ሰራዊት እንዲመራ የተመረጠ ራስ ሚካኤል ነው፡፡

ራስ ሚካኤል የጦር መሪ፣ የወሎ ኦሮሞች አገር ገዢ፣ የንጉስ ምኒልክ አማች፣ ደግሞም ሙስሊም፣ ታላቅ የባሪያ ውጪ ላኪ ነጋዴ፣ የሰበአዊ ፍጡርን በተከታታይ በኮንቮይ ወደ ቀይ ባህር ጠረፍ ከወሰደ በኋላ በእንግሊዝ ወይም በቱርክ መርከቦች አማካይነት ወደ የመን የሚልክ ነው፡፡ እሱ መጨረሻ ላይ ህዳር 1 ደረሰ፡፡

በሁለተኛው ቀን ማለቂያ የሌለው ጉዞ በሰልፍ ተጀመረ፡፡ ሴቶች በእግራቸው መጠጥ በገምቦ በጀርባቸው አዝለው፣ ማር ወይም ቅቤ ተሸክመው ከብቶችንና በጎችን እየነዱ ወደ መጀመሪያው ካምፕ አመሩ፡፡ በንግስት ጣይቱና በታላላቅ የቤተመነግስት አማካሪዎች ግፊት ህዳር 15 ቀን ጉዞ ተጀመረ…

ንጉሱ በሚያልፍባቸው በራሱ ግዛት የሚኖሩ አገረ-ገዢዎች ሁሉ ለንጉሱና ለሰራዊቱ ግብር እንዲያዘጋጁ አስቀድሞ ተነግሯቸዋል፡፡በኢትዮጵያ መንገዶች የሚሰሩት በሰው ጉልበት ነው፡፡ ይሄውም በደሃ ገበሬዎች ጉልበት (እጅ) ነው፡፡ እንጨቶችን ይቖርጣሉ፤ ግንዶችን ይነቅላሉ፣ ያቃጥላሉ፣ ወንዞችን ይሞላሉ፣ አፈር ይደለድላሉ፡፡ በጠላቱ (በወላሞ) አገር ግን ይህ ሁሉ የተከናወነው በራሱ በንጉሱ ወታደሮች ሲሆን በንጉሱ ጥብቅ ቁጥጥር ነበር፡፡

ይህን እስኪከወን ድረስ ለብዙ ሰአታት የጉዞአችን መስተጓጎል ግድ ነበር፡፡ እያንዳንዱ የስራ ድርሻውን ይወጣ ነበር፡፡ ይሄውም ድንጋይ ማንከባለል፣ የተቆረጡ እንጨቶችን መጎተት፣ የሳር ክምሮችን ወይም አፈር ማንሳት ሲሆን ንጉሱ በምሳሌነት ያሳዩ ነበር…

እያንዳንዱ የጦር መሪ እጅግ ብዙ ወታደሮችን ጋሻ አቀባዮችንና ለጌታው አስፈላጊ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙትን፣ በቀላል ምግቦች የተሞሉ አገልግሎችንና መጠጥ የያዙ ገንቦዎችን ሁሉም በጨርቅ የተሸፈኑትን አስይዞ አስከትሏል፡፡

ሰራዊቱ ስርአት ያጣና ስነ ምግባር የጎደለው ነበር፡፡ ዓላማቸው በአጠቃላይ አንድ መሆን ነበር፤ ይሄውም አለቆቻቸውን ብሎም ንጉሱን መከተል ነበር፡፡ ይህንን ትዕዛዝ መወጣት ይቸግራቸው ነበር፡፡ ይህ እጅግ ብዙ ህዝብ ጠመንጃ፣ ጦር፣ ዱላ፣ ጋሻ፣ የድንኳን ማቆሚያ ዋልታዎች የተሸከመው ሲሆን አብዛኛዎቹም ፈረሳቸውን እየጎተቱ ይጎርፉ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ወታደር ፈረሰኛ ወይንም እግረኛ በቀኝ ትከሻው ረጅም ከባድና በጣም ሹል ቆልመም ያለ ሰይፍ ከቆዳ በተሰፋ ሰገባ መያዝ ግድ ነበር…

ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት ንጉሱ ለዋና ዋና የጦር ጀኔራሎች በወረራው ወቅት ምን የት እንደሚወር ምድብ ሰጥቷቸው ነበር…አለቆቻቸው በሚያርፉባቸው ቦታዎች ሁሉ ተከታዮቻቸው በፍጥነት መጠለያ መስራት፣ ድንኳን መትከል፣ ትንንሽ ጎጀዎችን በጭራሮ መቀለስና በእንሰት ቅጠል መክደን ነው፡፡

የሴቶች የስራ ድርሻ ግን ወደ ወንዝ መውረድና ውሃ መቅዳት፣ የማገዶ እንጨት መሰብሰብ ነው፡፡ በሰፈርን በሁለት ሰአታት ውስጥ መካከለኛ ከተማ የሚያክል ካምፕ እንደ ማዕበል በሚጎርፍ ሰራዊት ከመቅጽበት ይመሰረታል …

በቀጣዩ ቀን ወደ ጉራጌ ሀገር ገባን፡፡ ጀኔራል ጎቤ የጉራጌ ሀገር ገዢ ንጉሱንና ሰራዊቱን ሊቀበል ወደ ቆንዳሊት ሲመጣ በቅርብ የተወለደ አንበሳ ግልገል ይዞ መጣ፡፡ ወደ አዲስ አበባ ካመጡ በኋላ ንጉሱ ለሚስተር ቺፊንግስ ሰጠው፡፡ እሱ እኔ ፓሪስ ስመለስ ከእኔ ጋር በመርከብ ልኮ የነበረ ቢሆንም በባህር ረጅም ጉዞ ተጎድታ ስለነበረ ጃርዲን ዴስ ፕላንትስ ዙ ከደረሰች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሞተች፡፡

እሁድ ቀን ጉዞ ስላልተደረገ ፊታውራሪ ጎቤ ከ600 በላይ የሆኑ አብዛኞቹ ከወገብ በላይ ራቁታቸውን የሆኑ ገበሬዎች ጋር ሰልፍ ካደረገ በኋላ እንጀራ፣ ማር፣ ቅቤ፣ ጠጅ፣ ጥራጥሬ እና ብዙ ከብቶችን እየጎተተ ለንጉሱ አመጣ፡፡ ታላቅ ግብዣም አደረገ፡፡

ቀጥሎ ጫካማ ወደሆነው ማረቆ ግዛት ተሸገርን…. ህዳር 26 ወደ ደጃዝማች በጫት አገር ደረስን፡፡ እሱም የንጉሱ የአጎቱ ልጅ ነው፡፡ የዚህ ግዛት ቄሶች አስደናቂ የሆነውን የሀር ልብስ ለብሰው ንጉሱን በጭፈራና በመዝሙር ተቀበሏቸው፡፡ ደጃዝማቹ 120 በ90 ጫማ ርዝመትና ከፍታ ያለውን ትልቅ ዳስ እንዲሰራ አዞ ቀኑን ሙሉ እየበላን የዋልነውን ምግብ አመጣልን፡፡

በቀጣዩ ቀን ወይሮ ወንዝ ተሻግረን በካንባታ ተራራ ጥግ ባለውና ሰፊ ቦታ በሚሸፍነው ፍል ውሃ አጠገብ ሰፈርን፡፡ ይህ ተራራ በኢትዮጵያ መንግስትና በጠላት (ዎላይታ) መንግስት መካከል የሚገኝ የተፈጥሮ ድንበር ነው፡፡

ህዳር 30… ብዙ ጊዜዎቻችንን ያጠፋው ዎላይታዎች የቆፈሩትንና በከባድ ጎርፍ የተቦረቦሩ ጉድጓዶችን መሙላት ነበር፡፡ በመጨረሻ ለጥ ያለና ሜዳማ ወደ ሆነው ቆርጋ ላይ ደረስን፡፡ ይህ ቦታ ቀድሞ በዎላይታዎችና በአቢሲኒያ መካከል በርካታ ውጊያዎች የተደረገበትና በተዳጋጋሚ የአቢሲኒያ ወታደሮች ተሸንፈው የተመለሱበት ቦታ ነው፡፡

ዘረፋ፣ ወረራ በዎላይታ አገር እና የዘመቻው ፍጻሜ በኋላም ወደ አዲስ አበባ መልስ ቀጥሎም ከአዲስ አበባ በረሃውን አቋርጬ ወደ ጅቡቲ ያደረግሁት ጉዞ ታህሳስ 1 ቀን ከስድስት ሰአታት አሰልቺ ጉዞ በኋላ መሃል ጠላት ሀገር (ዎላይታ) ገብተን ካምፓችንን ተከልን፡፡

Wolaita Times

01 Jan, 15:02


የራስ ሚካኤል ቀዳሚው ሰራዊት አስቀድሞ የተወራሪዎችን ቤት ማቃጠል ጀምሮ ነበር፡፡ በወረራው ጊዜ ንጉሱ በጦር ሜዳ መነጽር ተራራው ላይ ቆመው አሻግረው ይመለከቱ ነበር፡፡ በመጨረሻ ዎላይታ ቆንጦላ /ዳሞት ጋሌ/ደረስን፡፡ ውሃ ሊቀዱ ወንዝ የሚወርዱትን የአቢሲኒያ ሴቶች በጦር የሚያባርሯቸው ሰዎች ታስረው የሀገሩን ስፋት፣ ልማዳቸውን፣ ሐይማኖታቸውን መረጃ በግድ እንዲሰጡ ስለሚደረጉ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ተገድደው ይናገሩ ነበር …

ታህሳስ 15 ቀን ንጉሱ በዎላይታ የተገኘው ድል የልብ ልብ ስላገኘ ወረራውን የዎላይታ ድንበርተኛ ወደሆነው ወደ ገሙ (ቦሮዳ) ሀገር ለመቀጠል እቅድ ላይ እያለ የዚህ ሀገር አለቃ በቀጣዩ ቀን መጥቶ ለንጉሱ እጅ ሰጠ፡፡ በዚህን ቀን ምኒልክ የክቡር ዘውድ ደፍቶ በቀጥታ በውጊያ እየተሳተፈ በዊንቺስተሩ በ40 ሜት ርቀት ሆኖ ከረጅም ሳር ውስጥ ራሳቸውን ብቅ ለማድረግ የሚሞክሩትን ጠላቶቹን (ዎላይታዎችን) አነጣጥሮ እየተኮሰ በመግደሉ ደስታው ወሰን አልነበረውም፡፡

.... ይህ ከላይ በዎላይታ ታይምስ ታሪክ ጥንቅር ላይ የቀረበው ጽሁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ ቫንደራሂም /J.G
#Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ላይ የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደት ምን እንደሚመስልና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር የሚለው ተቀንጭቦ የቀረበ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደውን ለዛሬ ክፍል ሁለት አቀረብን ..... ክፍል ሶስት ይቀጥላል። በቀጣይ ክፍል ሶስት የምኒልክ ዘመቻ በዎላይታ ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ኢኮኖሚያዊ ሰብአዊ፣ ቁሳዊና ሞራላዊ ጉዳት እንመለከታለን፡፡ በቅርቡ ይጠብቁ 🙏

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #KingTONA #Minilik

ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት በተለይም የአጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር ? - ከፈረንሳዊ አይን ምስክርነት- ክፍል ሁለት .. Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5316

ማሳሰቢያ፦ የፅሁፉ ዋና አላማ ትውልድ የራሱን ትክክለኛ ታሪክ እንዲያውቅና በተቃራኒው ሌሎች ብሄረሰቦች አባል የሆኑም ከላይ በታሪክ ጥንቅራችን ስላቀረብነው ብሄር ትክክለኛ ማንነት እንዲያውቁ ነው። ይሄው አካሄድ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት በውጤት ሲለካ፦ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ሂደት ላይ የራሱ የሆነ ከፍተኛ የሆነ በጎ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል።

Wolaita Times

31 Dec, 13:35


"በመለስ የተከፈቱ ዩኒቨርስቲዎች በብርሀኑ ይዘጋሉ?!" - የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፖለቲካ ወጌሻ እንግዳ 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ከሰሞኑ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከ47 የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንቶችን ከየቦርድ ሰብሳቢዮቻቸዉ ጋር አዲስ በወጣዉ የዩኒቨርስቲ በጀት እና ቀጣይነት በዉጤት ብቻ የሚመዘንበትና ካልሆነ ወደ ማሰልጠኛነት የሚወርዱበት አሰራር የሚደነግግ ዉል እያፈራረሙ እንደሆነ በመንግሥት ሚዲያዎች ተዘግቧል።

ይህንን ሕግ እንዴት ያዩታል ? የእዉነት የትምህርት ጥራት ለማምጣት ነው ወይስ የድሮ ሥርዓቶች ተንኮል ለማጽናት? ሕጉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክና ሕገመንግሥት ያገናዘበ ነው ? በዚህ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ምልከታዎትን ቢያጋሩን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ በጣም ወሳኝና ታሪካዊ ጉዳይ ላይ አስተያዬት እንድሰጥ እድሉን ስላመቻቻችሁልኝ ሚዲያችሁን ከልብ አመሰግናለሁ። በመቀጠል ይህ አዲስ ወጣ የሚባለዉን ሕግ (ዉል) ከመገምገማችን በፊት ጥሩ ሕግ እራሱ ምን እንደሆነ በይነን ብንጀምር የተሻለ ይመስለኛል። ጥሩ ሕግ የሚባለዉ ጽንሰ ሐሳብ በሕግ ፍልስፍና ( Jurisprudence or philosophy of law ) ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚዉል ሐሳብ ነው።

የሕግ ፍልስፍና ማለት ደግሞ በራሱ ሰፊ ጽንሰ ሐሳብ ሲሆን በአጭሩ ሕጉ ምንድነዉ ምንስ መሆን አለበት። ምንንስ እንዲያመጣ ታልሞ ይቀረጻል፣ ምንንስ ከግምት ዉስጥ ማስገባት አለበት፣ የሚለዉንና የመሳሰሉትን ነገሮች የሚያመለክት ነው።

ወጥ ብያኔ ማስቀመጥ ባይቻልም፣ በአብዛኛው የሚያስማማዉ አንድ ሕግ ጥሩ የሚባለዉ የሚከተሉትን ሲያሟላ ነው ማለት ይቻላል፥ ሕጉ ለሕዝብ ጥቅም እንዲቆም ተደርጎ መቀረጽ አለበት፤ ሕጉ ማዳላት የለበትም ማለትም ለሁሉም በእኩልነት መተግበር አለበት፣ ሕጉ ምክንያታዊ መሆን አለበት፣ ለሕዝቡ ግልጽ መደረግ አለበት ቀጥሎ ሊተዳደርበት ስለሆነ ለሕዝቡ ( ለአካዳሚክ ማህበረሰብ ሊሆን ይችላል ) ግልጽ መደረጉ፣ መተግበር የሚችል፣ መቀየርም የሚችልና የመሳሰሉትን ጨምሮ መጥቀስ ይቻላል።

በተለይ ምክንያታዊ እና ፍትሐዊ ሕግ ነው ወይ የሚለዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሐገሪቷ ሕገመንግሥት መርሆዎች ጋር መጣረስ የለበተም። ይህ ሕግ ተቋማትን ያወዳድራል፣ እኩል ያልተከፈቱትን እኩል ያወዳድራል። ለምሳሌ ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እነ ፖልተር ጋትን የሚያሸንፈዉ ዉድድሩን እኩል ጀምሮ ነው።

በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች እኩል አልተከፈቱም፣ በሐገራችን ደግሞ እነዛ ነገሮች በብሔር ጭቆናና ሸፍጥ በመነዳት የተደረጉ ናቸዉ። የማደግ እድላቸዉም እኩል አልነበረም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ፣ እነዚህ ነገሮች ከግምት ዉስጥ መግባት አለባቸዉ። ያ ካልሆነ የቀደሙ መንግስታት የሰሯቸዉን ስህተቶች ማጽናት ነው የሕጉ አላማ የሚሆነዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ለምሳሌነት የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ወይንም አጠቃላይ የዎላይታ አካባቢ ላይ በቀደሙት መንግስታት ተፈጽሟል ብለዉ የሚያስቡት በደል አለ? አሁን የሚወጡ ሕጎች ታሳቢ ማድረግ የሚገባቸዉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በሚከፈትበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጥያቄ ቀረበላቸዉ፣ በፓርላማ "ለምን ዎላይታ ሶዶ ላይ ዩኒቨርስቲ ይከፈታል፣ አዋሳና አርባምንጭ ላይ በቅርበት እያለ ?" የሚል ነበር ጥያቄዉ። መለስ ዜናዊም "ዉሃ የሚቀዳዉ ከምንጩ ነው" በማለት የሐገሪቷን ሶስት መንግስታትን የዘለቀ እንቆቅልሽ የፈታበትን ምላሽ ሰጠ። በርግጥ ከዛ በፊት መለስ ዜናዊ በነ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ተሾመ ቶጋ ጋር ባለዉ ግንኙነት የእዉቀት ሰዎች መሆናቸዉ ተጽዕኖ አሳድሮበት ይሆናል።

በርግጥ በጀነራል ዊንጌት የሚያዉቃቸዉ በአጼ ኃይለስላሴ የተሸለሙት ጓደኞቹ እነ ቢሾፕ ዳዊት ጦሼ ትዝ ብለዉትም ይሆናል። በርግጥ በዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ግምባር ቀደም የነበሩት እነ ሰለሞን ዋዳ እና ሎንዶን ካንኮ ትዝ ብለዉት ይሆናል። በርግጥ በዘመነ ስልጣኑ እጅግ የፈተነዉ፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያስገደደዉ፣ በእዉቀት
የተመራዉ የዎጋጎዳ ትግል ትዝ ብሎትም ይሆናል ።

..... ነገር ግን የመለስ ዜናዊ መልስ ከዛ ያለፈ ትርጉም ያለዉ ነው የነበረዉ፣ በዉስጡም ለጠያቂዎቹ ብዙ መስቀለኛ ጥያቄ ያዘለ ነው። ቀድሞ ነገር በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሳይከፈት እስከ 1999 ዓ.ም የዘለቀዉ በፖለቲካ ሸፍጥ መሆኑን አታዉቁም ወይ የሚል ነው ? ጭሰኝነት ለማጥፋት ባበረከተዉ አስተዋጽኦ ቂም ተይዞበትና እና የነገ ተስፋዉ ተጠልቶ ዋዱ መዘጋቱን አታዉቁም ወይ የሚል ?

በዎላይታ የተጀመረዉን የግብርና ልማት ወደ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ዳዉሮና ኮንታ ለማስፋት ጥናቱ አልቆ በደርግ የሰብአዊ መብት ጥሰት ብዛት፣ ለጋሾች ገንዘብ በመከልከላቸዉ አለመተግበሩ በሚያስቆጭበት ደርግ ዎላይታ ብቻ ይለማል እንዴ ብሎ ዋዱን የዘጋዉ በጤናማ አስተሳሰብ ነበረ ወይ ?

በዎላይታ ዙሪያ ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ የነበሩት በዎላይታ እንዳይከፈት መሆኑን አታዉቁም ወይ? ዩኒቨርስቲዎቹንስ ሲያንቀሳቅስ የነበረዉ አብዛኛዉ ኃይል ከዎላይታ እየሄደ መሆኑ እየታወቀ በቀየዉ ያልተከፈተዉ በብሄር ጭቆና ምክንያት እንደሆነ አይገባችሁም ወይ ?

የኢትዮጵያ መንግሥታት ማስተማር የማይፈልጓቸዉን ብሄሮችና ብሄረሰቦች በእግራቸዉ እየኳተኑ ሲያስተምሩ የነበሩ ( ቦጋለ ዋለሉና ዋና ዋገሾን ልብ ይሉል ) ዎላይታዎች መንደር ዩኒቨርስቲ እስካሁን ያልተከፈተዉ በአጋጣሚ አለመሆኑን አታዉቁም ወይ ?

ይህ ከጥጥ ልብስን ቀድሞ የሸመነ መገበያያ ሳንቲም የፈበረከ ስልክ በአፍሪካ ቀድሞ ያስገባ ሕዝብ ወደ ሁዋላ የቀረዉ በብሄር ጭቆና ምክንያት መሆኑ ግልጽ አይደለም ወይ? እናንተ እራሱ በፓርላማ ከፈታዉን ለማጨናገፍ የምት ጠይቁት የአያትና አባቶቻችሁን ተንኮል ለማስቀጠል መሆኑን ሰው ይታዘባል አትሉም ወይ? የሚሉ ብዙ ጥያቄዎችን ያዘለ መልስ ነበር ብዬ አምናለሁ።

የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የወለጋንም ጉዳይ ብናነሳ አካባቢው ብዙ ምሁራንን ያፈራና በኢትዮጵያ በትምህርት ፈር ቀዳጅ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲ የተከፈተዉ እጅግ ዘግይቶ ነው የነበረዉ። ስለዚህ እነኝህ ነገሮች ከግምት ዉስጥ መግባት አለባቸዉ። ሆን ተብሎ ወደሁዋላ የቀሩ አካባቢዮችን ሆን ብሎ የማሳደግ እርምጃ መወሰድ አለበት ብዬ አምናለሁ።

የቀድሞ የፖለተካ በደሎች መቀልበስ አለባቸዉ። ለምሳሌ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ ደረጃ ላይ ነበረ፤ አሁን ግን የጦርነቱ ተጽዕኖ ወደሁዋላ ሊያስቀረዉ ይችላል የትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ በመቀስቀሱ። ተመራጭነቱን ቀንሶ ሊሆን ይችላል፣ ያም የተጠና አይመስለኝም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት በሕጉ (ዉል) ላይ የአካዳሚክ ማህበረሰቡ በቂ ዉይይት አድርጓል? ፖለቲከኞች እና የሚዲያ አካላትስ በቂ ትኩረት ሰጥተዉታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አይመስለኝም። በቂ ትኩረት ያላገኘ ጉዳይ ነው። የሐገሪቷን እጣፋንታ የሚወስን ጉዳይ እና የሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ የራሱ ተጽዕኖ የሚያሳድርም ጉዳይ ነው፤ ግን ትኩረት ተነፍጓል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ዩኒቨርሲቲ እንደስሙ universal ወይንም አለም አቀፍነቱ፣ አሁን ከምናነሳዉ አካባቢያዊ ቅሬታ ጋር እንዴት ይጣጣማል?

Wolaita Times

31 Dec, 13:35


ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህ ሰፊ ጉዳይ ነው። በአጭሩ በአንድ አካባቢ ዩኒቨርስቲ መኖሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት፣ በትንሹ የማህበረሰብ አገልግሎትን ብቻ እንኳን ብናይ ነገሩ ግልጽ ነው ጥቅሙ።

🎙💻 ዎላይላታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራሁ ነው ይላሉና፣ የእዉነት ሕጉ (ዉሉ) አላማዉ ይሄ ብቻ ነው ማለት ይቻላል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔ አሁንም የትምህርት ጥራት ደጋፊ ነኝ፤ ግን የኢትዮጵያን ዉስብስነት ከግምት እናስገባ ነው የምለዉ። በቂ ዉይይቶች ይደረጉ ሕግና አሰራሮች ከመዘርጋታቸዉ በፊት። ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ የእዉነት የዴሞክራሲ ሰዉ ከሆኑ በዚህ አዲሱ ዉል ላይ ዴሞክራሲያዊ ዉይይት በመክፈት ማረጋገጥ አለባቸዉ። ይህ ዉል ነባሮቹን ዩኒቨርሲቲዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፣ የተሻለ የተደራጁት፣ በጎበዝ ተማሪዎች ተመራጭ የሚሆኑት ነባሮቹ ናቸዉ፣ በጣም ጠንካራ ሥራ የሠራ ታዳጊ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ከነባሮቹ ጋር ተወዳድሮ መዝለቁ ያጠራጥራል። ጉዳዩ በቂ ትኩረት አልተሰጠዉም፣ በቂ ጥናትም የተካሄደበት አይመስለኝም፣ በቂ ዉይይትም የተደረገበት አይመስለኝም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት ሕጎች (ዉሎች) ፍትሐዊና ሐቀኛ እኩልነትን የሚያሰፍኑ መሆናቸዉ የሚኖረዉ ፋይዳ ምንድነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ፋይዳዉ ትልቅና ለሐገር አንድነትና ልማት የሚተርፍ ነው። አንድነት (cohesion ) የሚመጣዉ፣ ፍትሐዊ ሕግ ሲወጣና ወጥቶም ለሁሉም በወጥነት ሲተገበር ነው፣ ዳኛዉ ሕግ ነው፣ ሕጉም የቀደሙ ተንኮለኛ የፖለቲካ ዉሳኔዎችን ከግንዛቤ በማስገባት ሲረቀቅ ሕዝብ ሁላችንን የሚዳኘዉ ሕግ ነው ብሎ ሲያምን አንድ ይሆናል።


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromo

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።


Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5312

Wolaita Times

30 Dec, 15:59


የክልሉ መንግስት ከሌላ ክልል ዘልቀው በመግባት የዜጎች ህይወት እንዲጠፋና በርካቶች እንዲቆስሉ ያደረገበት የታጣቂዎች ጥቃት ማውገዝ አለመቻሉ ኃላፊነት የጎደለ ኢሰብአዊነት መሆኑ ተገለፀ።

በተፈጠረው የተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ያለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ መምረጡ ተጨማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ገልጿል።

እንደሚታወቀው አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ባለሀብት ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል።

በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

በተጨማሪም የብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑም እንዲሁም።

ባለሃብት ዳኜ ዳባ አባያ ብላቴ ከሚያለማው 500 ሄክታር ውስጥ 200 ሄክታሩ በምስጢር የተያዘው በሲዳማ ክልል ክፍተኛ አመራሩ በአቶ አብርሃም ማርሻሎ እና በቤተሰቦቹ ሲሆን በዚህ ምክንያት የመሬት ወረራ አባያ ብላቴ የተፈፀመ ያለው፡፡

አቶ በላይነህ ክንዴ በአባያ ብላቴ ቀበሌ የማገኘውን 550 ሄክታር የእርሻ ኢንቨስትመንት ይዞታ ካርታ እና ውል ከዎላይታ ዞን የወሰደ ቢሆንም ሌላ ተደራቢ ውል ከሲዳማ ክልል ሎክ አባያ ቀበሌ በመውሰድ ላለፉት ሦስት ዓመታት ዓመታዊ የመሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የገቢ ግብር ለሲዳማ ሎክ አባያ ወረዳ እየከፈለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት ከመፈጠሩ ከሰዓታት በፊት የታጠቁ ልዩ ኃይሎችን ከሎክ አባያ ወረዳ መሬራ ቀበሌ የአቶ በላይነህ ክንዴ ተሽከርካሪዎች ግጭቱ ወደተከሰተበት ቦታ ስያመላልሱ እንደነበረ በአከባቢው የሚኖሩ ዓይን እማኞች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።

"ጥቃቱ በተፈፀመበት ቀን ጥቃት አድራሽ ወታደሮች በበላይነህ ክንዴ እርሻ ውስጥ ባለው ምግብ ተመግበው፣ የእርሱ መኪኖችን ለዘመቻ ተጠቅሟል፣ የአብራም ማርሻሎ ወንድም በመኪናው ውስጥ ሆነው ኦፕሬሽን ሲመራ ነበር" ሲልም የአይን እማኝ ሁኔታውን አክለው ገልፀው ነበር።

በዚህ ሁሉ መሀል ባለሀብቶቹ አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ግለሰቦች በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ ግጭቱ እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ጋር በመሆን በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ የመረጠ ሲሆን በተፈጠረው በተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች ተገድለዋል፣ በርካቶች ቆስለው ጤና ተቋማት ላይ ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ የሰው ህይወት ሳይጠፋ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

በዛሬው ዕለት ከዎላይታ ከሁሉም አከባቢ የተወጣጡ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ወጣቶች እንዲሁም ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አካላት ግጭቱ በተከሰተበት አባላ አባያ ተገኝተው አጽናንተው መመለሳቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama

Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5307

Wolaita Times

30 Dec, 12:41


የዎላይታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ ልቦናዊ፤ ስነ ምህዳራዊ መጎሳቆል ከመቼ ይጀምራል? ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት ምን ይመስል ነበር ? - ከፈረንሳዊ አይን ምስክርነት

(ክፍል አንድ)

ይህ ጸኁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ #ቫንደራሂም /J.G Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደ ነው፡፡

ጹሑፉ ጉምቱ የዎላይታ ባህል አዋቂና ምሁር ለነበሩት ለአቶ ዘብድዎስ ጫማ በነጻ የተሰጠ ስጦታ አንደነበር በትርጉሙ ላይ ተብራርቷል፡፡

ጸሃፊው ስለ ዎላይታ እንደጻፈው ከወረራው በፊት ዎላይታ በፖለቲካው መስክ በራሱ ንጉስ ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ግዛት ነበር፡፡ ዎላይታ በኢኮኖሚው በለምነቱና በልምላሜ የሚታወቅ በመሆኑ ዎላይታዎች በምግብ ራሳቸውን ችለው ይተዳደሩ ነበር፡፡

በባህል ደግሞ ዎላይታዎች ድንቅ ባህልና ቅርስ አንዲሁም የራሳቸው የእምነት ተቋማት ነበራቸው፡፡ በስነ ልቦና ዎላይታዎች ደስተኞች፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ጀግና ተዋጊዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ ጠቢባን… እንደነበሩ እንመለከታለን፡፡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የታሪክ ጥንቅር ላይ፦ ትርጉሙ ከዚህ በታች ቀርቧል መልካም ንባብ!

እንደ ጀ.ግ ቫንደራሂም /J.G Vanderhem ምልከታ የዎላይታ ባህልና ስነ ምህዳር በምኒልክ ወረራ ወቅት ምን ይመስል ነበር?

የዎላይታ ሀገር በጣም ለም፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ተክሎች ያሉት፡- ስንዴ፣ ገብስ፣ ቡና፣ ትምባሆ፣ ጥጥና ማሽላ በጎጆአቸው ዙሪያ ተተክሎ ጎጆአቸውም እጅግ በጣም አስውበው ይገኛሉ፡፡ በየገጠሩ ትላልቅ እንጨቶች፣ ፍራፍሬ፣ ዘንባባ፣ ወይራ ስፔንድል ዛፎች በብዛት ይገኛሉ፡፡

በመንገዱ ግራና ቀኝ ከጎጆ እስከ ጎጆ ቆንጆና ውብ ዛፎች ተተክለው ይገኛሉ። ወንዞች በሀረጎች፣ በሚጣበቅ አረሞች እና ቀርከሃዎች መካከል ይፈሳሉ፡፡ የንብ ቀፍ ቅርጽ ያለው ቤቶቻቸው በጥሩ ሁኔታ የተሰራና በጣም ንጽህናቸው የተጠበቀ ነው፡፡

በህዝቡ የተሰሩ የተለያዩ ዕቃዎች ቤቱን አጨናንቀው ይታያሉ፡፡ እነዚህም በጣም ቆንጆ እንስራዎች፣ ከሸክላ የተሰሩ ከበሮ፣ከእንጨት የተሰሩ የቤት ቁሳቁሶች፣ በዶቃዎችና በዛጎሎች ያጌጡ እቃዎች፣ እጅግ ተውበው በቀጭን ሲባጎ መልክ ተወጥረው የተሰሩ የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ (ዲታ) በእህል የተሞሉ ጆኒያዎች፣ የተጠቀለሉ ቃንጫዎች፣ በነጭ ሽንኩርትና በበቆሎ የተሞሉ ከቆዳ የተሰሩ ስልቻዎች፣ ከብረት የተሰሩ ረዘም ያሉና ጠፍጣፋ በኮሮቻ ውስጥ የተሞሉ መነገጃ መሳሪያዎች (ማርጯ) ይገኛሉ፡፡ ይህ መሳሪያ (ገንዘብ) ዎላይታዎች ለንግድ ልውውጥ የሚገለገሉበት ነው፡፡ …. እነዚህ ቅርሶች ሁሉ የሚያመለክቱት ይህ ህዝብ ምን ያህል ጥንታዊና ነባር፣ መሰረታዊ ስልጣኔ ያለው መሆኑን ነው፡፡

በቤታቸው ውስጥ ለዕይታ በሚያመች መልክ በደረጃ በየአይነቱ ተደርድረውና ተሰቅለው የሚታዩ የአንበሳ፣ የነብር ወይም ሌሎች ቆዳዎች ለዚህ ህዝብ አደን ዋና ዋና ተግባሮች መሆኑን ነው፡፡

ሰዎቹ ደስተኞችና ብቃት ያላቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩና ህይወታቸውን በመንፈሳዊ ስርአት የሚመሩ ናቸው፡፡ ዎላይታዎች በካቶሊክ በካቶሊክ ሀይማኖት የሚያምኑ መሆናቸው ንጉሱን በጣም አስገርሟቸዋል፡፡ ንጉሱ ያስቡት የነበረው ዎላይታዎች እስላሞች እንደሆኑ ነበር፡፡ ለወረራ ካነሳሳቸው ምክንያቶች አንዱም ይሄው ነበር፡፡

ቅስና ከጥንት ከአባት ወደ ልጅ እየተላለፈ የመጣ ሲሆን ልማዳዊ (ባህላዊ ) ሀይማኖት ያሏቸው መሆኑን ተረዳን፡፡ አንዳንድ የንጉሱ ወታደሮች ለወረራ በተሰማሩበት ጫካ ውስጥ እንዲያውም ቤተክርስትያንና ምስጢራዊ ድንጋዮችን እንዳገኙ ገለጹልን፡፡

የዎላይታዎች የመቃብር ስርአት ዓይነት ከአቢሲኒያዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታወቅም፡፡ በርግጥም አንዳንድ ያየኋቸው የመቃብር ቦታዎች ቆንጆዎች ሲሆኑ በዙሪያቸው የጥላ እንጨቶች ተተክለው በዙሪያው ጉድጓድ ተቆፍሮ በእንጨት ጥላ ስር መሆኑ በርግጥም አስከሬኑን ለእርፍት የተጋደመ ያስመስለዋል፡፡

የሞተው ወንድ ከሆነ በህይወት በነበረ ጊዜ ሟቹ የሚጠቀማቸው መሳሪያዎች ከመቃብር አጠገብ እንጨት አቁመው ይሰቀላሉ፡፡ ሴት ከሆነች ግን ጌጣጌጦቿ በተመሳሳይ መልኩ ይሰቀላሉ፡፡ #ዎላይታዎች አዳኞችና ገበሬዎች ናቸው፡፡ እነሱ ለጦርነት የሚነሱት አገራቸው በወራሪዎች ሊወረር ብቻ ነው፡፡ ከኋላ ቀር መሳሪያዎች መካከል አዘውትረው የሚይዟቸው ሁለት ጦሮች ይገኝበታል፡፡ አንዱን ይዘው ሌላውን ይወረውራሉ፡፡ በወገባቸው የጠላቶቻቸውን አንገት መቀነጠስ የሚያስችል ከባድና በጣም ሹል ጎራዴ ይታጠቃሉ፡፡

የአለቆቻቸው መሳሪያዎች በመዳብና በብር ያጌጡ ሲሆን፣ አንዳንዱ ከባድና ከቆዳ የተሰራ ጋሻ ይይዛሉ፡፡ ዎላይታዎች ዝሆን ማደን ይወዳሉ፡፡ ይሄውም የሚከናወነው በጣም በተቀናጀ ወጥመድ ነው፡፡ ዝሆኑ በሚያልፍበት መንገድ ላይ በጣም የተሳለና ሹል ጦር ተወጥሮ በእንጨት ቅርንጫፎች የተሸፈነና ተስፈንጥሮ ሊወጋውና ሲወድቅ ይጠባበቁ የነበሩ አዳኞች ተረባርበው ይገድሉታል፡፡

የዎላይታ ወንዶች አጭር ቁምጣ (ሱሪ) ሲታጠቁ በወገባቸው ሸማ ያገድማሉ፡፡ ሸማቸው በወፍራም ማግና ድር የተሰራ ሲሆን ጥለቱም ጥቁር፣ ቀይ፣ ሰመያዊ ወይም አረንጓዴ መልክ ያለው ነው፡፡ ይህ ልብስ በአጠቃላይ ከአፈሩ መልክ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ የሀገሩ አፈር ነጣ ያለ ቀይ ነው፡፡
ሀብታቸው የእህል ምርት፣ ከብትና በአብዛኛው የባሪያዎች ብዛት ነው፡፡ እነዚህ ምርቶች ለንግድ ልውውጥ የሚጠቀሟቸው ናቸው፡፡ …

ዎላይታዎች እጅግ በጣም በጀግንት የአቢሲኒያ ወታደሮች ስለተቋቋሙ ንጉሳቸውን ጦና በቀላሉ ለመያዝ አልተቻለም፡፡ ጦርነቱ የተጠናቀቀው ንጉስ ጦና ክፉኛ ቆስሉ ከተያዘ በኋላ ነው፡፡ .........." ይቀጥላል።

ይህ ከላይ በዎላይታ ታይምስ ታሪክ ጥንቅር ላይ የቀረበው ጽሁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ ቫንደራሂም /J.G #Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ላይ ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት ምን ይመስል ነበር የሚለውን ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደውን ለዛሬ ክፍል አንድ አቀረብን ..... ክፍል ሁለት ይቀጥላል። በቅርቡ ይጠብቁ 🙏

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #KingTONA #Minilik

የዎላይታ ሀገር በጣም ለም፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ተክሎች ያሉት፡- ስንዴ፣ ገብስ፣ ቡና፣ ትምባሆ፣ ጥጥና ማሽላ በጎጆአቸው ዙሪያ ተተክሎ ጎጆአቸውም እጅግ በጣም አስውበው ይገኛሉ፡፡ በየገጠሩ ትላልቅ እንጨቶች፣ ፍራፍሬ፣ ዘንባባ፣ ወይራ ስፔንድል ዛፎች በብዛት ....... ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5300

Wolaita Times

29 Dec, 16:32


አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ

በሲዳማ ክልል ሰርገኞችን የጫነ መኪና ተገልብጦ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል በቦና ወረዳ በቁጥር ከ65 በላይ የሚሆኑ ሰርገኞች በአይሱዙ መኪና ተጭነው ወደ ባንሳ ዳዬ ሲሻገሩ በጋላና ወንዝ በተባለ ባለው ድልድይ ላይ በደረሰው አደጋ እስካሁን ከ60 በላይ የሚሆኑት ህይወት እንደቀጠፈ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸውን ላጡና ለተጎዱ ወዳጅ፣ ዘመድና አዝማድ መጽናናትን እንመኛለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን 🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Sidama

Wolaita Times

29 Dec, 12:02


#ሰበርመረጃ
ባለሀብቶቹ አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸው ተረጋገጠ።

በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሷል።

የብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑም ተገልጿል።

ባለሃብት ዳኜ ዳባ አባያ ብላቴ ከሚያለማው 500 ሄክታር ውስጥ 200 ሄክታሩ በምስጢር የተያዘው በሲዳማ ክልል ክፍተኛ አመራሩ በአቶ አብርሃም ማርሻሎ እና በቤተሰቦቹ ሲሆን በዚህ ምክንያት የመሬት ወረራ አባያ ብላቴ የተፈፀመ ያለው፡፡

አቶ በላይነህ ክንዴ በአባያ ብላቴ ቀበሌ የማገኘውን 550 ሄክታር የእርሻ ኢንቨስትመንት ይዞታ ካርታ እና ውል ከዎላይታ ዞን የወሰደ ቢሆንም ሌላ ተደራቢ ውል ከሲዳማ ክልል ሎክ አባያ ቀበሌ በመውሰድ ላለፉት ሦስት ዓመታት ዓመታዊ የመሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የገቢ ግብር ለሎክ አባያ ወረዳ እየከፈለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከትናንት በስቲያ የተቀሰቀሰው ግጭት ከመፈጠሩ ከሰዓታት በፊት የታጠቁ ልዩ ኃይሎችን ከሎክ አባያ ወረዳ መሬራ ቀበሌ የአቶ በላይነህ ክንዴ ተሽከርካሪዎች ግጭቱ ወደተከሰተበት ቦታ ስያመላልሱ እንደነበረ በአከባቢው የሚኖሩ ዓይን እማኞች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።

"ጥቃቱ በተፈፀመበት ቀን ጥቃት አድራሽ ወታደሮች በበላይነህ ክንዴ እርሻ ውስጥ ባለው ምግብ ተመግበው፣ የእርሱ መኪኖችን ለዘመቻ ተጠቅሟል፣ የአብራም ማርሻሎ ወንድም በመኪናው ውስጥ ሆነው ኦፕሬሽን ሲመራ ነበር" ሲልም የአይን እማኝ ሁኔታውን አክለው ገልጿል።

አንድ ሔክታር ለም መሬት ብርቅ በሆነበት በአበላ አባያ ወረዳ ብላቴ ቀበሌ ቢሊዮን የሙዝ ዘለላ ለዘመናት የሚያሳፍስ 550 ሔክታር የእንቨስትመንት መሬት አቶ በላይነህ ክንዴ የተባሉት ባለሀብት ለ45 ዓመት ለማልማት በሊዝ መረከባቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ በተጨበጠበት ከባለሀብቱ በኩል በተለያየ ግን ለበርካታ ሚዲያ መሬቱ የሚገኘው ዎላይታ ውስጥ መሆኑን የሚቃረን ተደጋጋሚ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ቦታው ከሲዳማ ጋር ያልተቋጭ የወሰን ውዝግብ ያለበት እንደመሆኑ በጉዳዩ ላይ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስከዛሬ ዝምታን መርጠዋል፡፡

የቀድሞ አባያ እርሻ ልማት ይዞታ 1,262 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 500 ሄክታር ይዞታን ለ25 ዓመት፣ አንድ ሄክታርን በ500 ብር ሂሳብ አከራይተዋል። (ዎልማ ለመንግስት ዓመታዊ የመሬት መጠቀሚያ ኪራይን በአንድ ሄክታር 1,000 ብር ይከፍላል፤ 500 ብር ከስሮ)። ነገር ግን ለአቶ ዳኜ ውል ይኑረው እንጂ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አልተሠራም፣ ወሰኑ አይታወቅም፣ ጎርፍ ያልገባበትንና አሲዳማ ያልሆነውን ቦታ በሙሉ እያማረጠ ሲያርስ ነበር። ይሁን እንጂ በ2014 ዓ.ም አንድ ዓመት ብቻ ከአባያ ወጣቶች ጋር በመጋጨቱ (የጉልበት ሠራተኛን፣ ጥበቃንም ጭምር ከኦሮሚያ ጭኖ በማምጣቱ) ከ2015 ጀምር ሥራ አቁመዋል።

ለችግሩ እንደመንስኤ የሚሆነው የዎላይታ ልማት ማህበር 1262 ሄክታር ይዞታን የሚያስተዳድርና የሚያለማ መዋቅር ቀርጾ፣ በየዘርፉ ሠራተኛ መቅጠር ሲገባው የድሮ አባያ እርሻ ልማት ጥበቃ የነበሩ 8 ሽማግሌ ጠባቂ ውጪ አንድም ሠራተኛ አልቀጠረም፤ ከሲቢክ ማህበራት ዘርፍ 3 ባለሙያ ደርቦ እንዲሠራ በማድረጉ ይዞታው ዳዋ ለብሶና መክኖ ተቀምጧል። ይህንን ምቹ ሁኔታን የተመለከቱ ሴራኛ አመራሮችና ባለሀብቶቹ ተመሳጥሮ በየቀኑ በከፍተኛ ፍጥነት ወረራ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በዚህ ሁሉ መሀል ባለሀብቶቹ አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ግለሰቦች በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ ግጭቱ እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ጋር በመሆን በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል
ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን ዝምታ የመረጠ ሲሆን በተፈጠረው የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን ተጨማሪ የሰው ህይወት ሳይጠፋ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama

"ጥቃቱ በተፈፀመበት ቀን ጥቃት አድራሽ ወታደሮች በበላይነህ ክንዴ እርሻ ውስጥ ባለው ምግብ ተመግበው፣ የእርሱ መኪኖችን ለዘመቻ ተጠቅሟል፣ የአብራም ማርሻሎ ወንድም በመኪናው ውስጥ ሆነው ኦፕሬሽን ሲመራ ነበር" ........ Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5296

Wolaita Times

28 Dec, 15:21


በጋሞ ዞን በቁጫ ህዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ተከታታይ ሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ እውቁ ፖለቲከኛ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ አሳዛኝ ታሪክ አጋሩ።

እኚሁ ገምቱ ፖለቲከኛ ዳንኤል በአከባቢው እየተካሄደ ያለውን ዘግናኝ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፦ "እየተፈጸመ ያለው ሁሉ ስሜትን ይረብሻል፤ ይፈታትናል። ቢሆንም ተረጋጉ፣ አይዟችሁ! ስብራታችሁ የሚጠገንበት፣ ቁስላችሁ የሚታከምበት፣ እምባችሁ የሚታበስበት ዘመን ይመጣል" በሚል የሚመለከታቸው አካላት ለጉዱዩ ትኩረት እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተለይም በቁጫ ህዝብ ላይ በዞኑ መንግስት መሪነት እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ ሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ከእውነተኛ ታሪካቸው ተነስተው እንደሚከተለው በአንደበታቸው አብራርተዋል።

"የማያልፍ መከራ፣ የማይነጋ ሌሊት የለም! ... የገራፍዎቹ ጥያቄ፣ የአስጨናቂዎቹ ምክንያት፦ "ለምን ብልጽግናን አልመረጣችሁም" የሚል ነው።

ከስር ባያያዝኳችሁ ቪዲዮ ፊለፊት ላይ የሚትታየው ሴት ወ/ሮ ሐረጓ ኃይሌ ትባላለች። የሰላምበር ከተማ ነዋሪ ናት። በቅርቡ ባሏን በሞት በመለየቷ በከባድ ሀዘን ውስጥ እንዳለች አውቃለሁ። ሁለቱም የልጅነት ጓደኞቼ ነበሩ። በጋቢቻቸውም እኔ 1ኛ ሚዜያቸው ነበርኩ። ነገር ግን በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ላለመነካካት ሲባል ከ22/23 እና በላይ ዓመታት ተገናኝተን አናውቅም።

የማልክደው ነገር ቢኖር በ2013ቱ ምርጫ ቅስቀሳ እኔና ፕ/ር #ብርሃኑ_ነጋ ወደዛች ከተማ በተጓዘንበት ወቅት ታሞ አልጋ ላይ የወደቀውን ወንድሜን በሩጫ እስከ ቤታቸው ሄጄ እግዚአብሔር ይማርህ! ብያለሁ።

ከዚያም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተል አንደ/ሁለተ? ተመላልሸ ጠይቅያለሁ፤ በመጨረሻም ከህልፈቱ በኋላ ከአዲስ አበባ ተነስቼ ለቅሶ ለመድረስ እስከ ቤታቸው መሄደን አስታውሳለሁ። በእኔ ምክንያት በደናቆርቶቹ ጥርስ ከሚገቡ እያልኩ ርቂያቸው ነበር፤ በሀገራችን ቆሻሻ ፖለቲካችን ምክንያት እነሱንም ጨምሮ ከብዙ አብሮ አደጎቼ መራቅ ግድ ነበር።

ዛሬ ላይ እሷ (ወ/ሮ ሐረጓ) ወልዳ፣ ድራ፣ ሀብት አፍርታ፣ ለብዙዎች ተርፋ፣ ከብዳ የሚትኖር እናት ናት። ይህንን ማለትም በስሱ (ተቀንጭቦ) በቪዲዮ ላይ የሚታየውን ጉድ ካየሁ በኋላ እንባዬን መቆጣጠር ተሳነኝ። በእንዲህ አይነት ጭቆና እንዴት አብሮ መኖር ይቻላል? እንዴት ጋሞና ቁጫ፣ ጋሞና ወላይታ፣ ወላይታና ሌላው፣ እንደ አዲስ የተፈለፈለው ክልል ወዘተረፈ እንዴት አብሮ መኖር ይችላል? እንዴት ሀገር ይገነባል? በጣም ማሰብ፣ ብዙ ማሰላሰል፣ እጅግ ማውራት፣ መጨነቅ፣ መጠበብ የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

በቅርቡ እነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደዛች ከተማ ተጉዘው እኔና አለቃዬ ንግግር ባደረንግባት በዛች ስቴዲየም ሸንግለው፣ ቀበጣጥረው መመለሳቸው አይዘነጋም። በሌላ ገጹ ይህ የመከራ ዶፍ በሕዝቡ ላይ እንዲዘንብ በጥቅሻም በውስጥ መስመርም ለማዘዛቸው ይህ ቪዲዮ ህያው ምስክር ነው። ለዚህ ውሳኔያቸው ደግሞ በዙሪያቸው ያሉ የአከባቢው ተሿሚዎች ሚና የአንበሳ ድርሻ መኖሩን እንካድ ብንል እንኳን የሚካድ አይደለም። ይመዝገብ!

የቁጫ ሕዝብ ወንጀሉ ምርጫውን መምረጡ ነው። ዴሞክራሲ ያለ መስሎት እንደ 1997ቱ በ2013ቱ ምርጫ በስፋት መሳተፉ፤ የፈለገውን መምረጡ ነው። እስከ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጌ፣ ጊዜና ጉልበት ሰጥቼ የፈጋሁት ቢሆንም ግን ሕዝቡ እኔን አልመረጠኝም። የተመረጠው ሌላ ፓርቲ ተወካይ ነበር፤ ሕዝቡ ልክ ነው። እኔም እጅግ ደስተኛ ነበርኩ።

የታገልኩለት ዓላማ ሁሉም ምርጫውን እንዲመርጥ ነበረና ተሳክቶልኛል። ደስም ብሎኝ ነበር። አዎን! ምርጫውን መርጧልና ሕዝቡም፣ ምርጫውም መከበር ነበርበት። ግን አልሆነም። ተመራጮች ከምክር ቤት አባልነት ያለ ሕጋዊ አሰራር ተባርሯዋል። ልክ በአማራና በትግራይ ኦሮሚያ ተወላጅ ሕዝብ ተወካዮች የተወሰደው አይነት ተመሳሳይ እርምጃ ... ተወሰደባቸው።

የዚህ ምክንያቱም በድንቁርናና በጨለማ ውስጥ ያሉ ልበ ስውራን መሆናቸው ነው። ለቁጫ ሕዝብ የምርጫው መዘዝ፣ 'የዴሞክራሲው' ጥማት የተረፈው ነገር ቢኖር ማንም በማይደርስበት ተሳቀው፣ ታስረው፣ ሞራላቸው፣ ክብራቸው፣ ስብዕናቸው ሁሉ ወድመው፣ በጥይት ከሚቆላ፣ በእስር ከሚማቀቅ ወይም አካል ጉዳተኛ ከሚሆን፣ ቢያንስ ለልጆቼ ልኑር ብለው ገዳዮችን መማጸን፣ መወትወት ነውና ውሳኔ ልክ ነበር።

በአፈሙዝ ፊት የየተሰየመ ግለሰብና ሕዝብ የተባለውን ከመፈፀም ውጭ ምንም ምርጫ የለውምና ፍርሃታችሁ ጭንቀታችሁ እጅግ ይገባናል። ይሄው ነው! It's so! የዛሬ ተጨቋኞች ሆይ ስሙኝ። ግድየለም! ለሁሉም ቀን አለው። ለሁሉም ዘመን አለው። አይዟችሁ! ከዚህ ማጥ፣ ከዝህ ቀን ጨለማ ለመውጣት ሰፊ ስራ እየተሰራ እንዳለ መረጃው አለኝ።

አይዟችሁ! አይዟችሁ! ዓለም ዝም ብል እንኳን፣ እኛም አቅም ብናጣ እንኳን፣ የሚሰራው ሁሉ ባይሳካልንም እንኳን እግዚአብሔር ደካማውን #ዳዊትን እንደሚያስነሳ ቅንጣት ታህል እንዳትጠራጠሩ። አይዟችሁ! ከቅመኝነትና ከብቀላ ርቃችሁ በለመዳችሁት ሰላማዊ መንገድ ኑሩ!

በመጨረሻም በሰውኛ ስነግራችሁ፦ ምንም ነገር በስሌት እንጂ በስሜት ከሆነ ወጤቱ ዜሮ ድምር ነው። ትዕግስትና ጽናት ግድ ነው!

አዎን! እየተፈጸመ ያለው ሁሉ ስሜትን ይረብሻል፤ ይፈታትናል። ቢሆንም ተረጋጉ፣ አይዟችሁ! ስብራታችሁ የሚጠገንበት፣ ቁስላችሁ የሚታከምበት፣ እምባችሁ የሚታበስበት ዘመን ይመጣል። ተስፋ አለኝ! ህልም አለኝ! ክብር አለኝ! ትግል አለኝ! እምነት አለኝ! ጽናት አለኝ! አይዟችሁ! ይህ ሁሉ እንደ ታሪክ የሚወራበት ዘመን ይመጣልና አይዟችሁ! የመንፈስ፣ የሞራል፣ የክብር ... ስብራታችሁ ይካሳል!

አይዟችሁ! ይህ ክፉ ቀን ያልፋል! ሁሉም ለበጎ ነው!!!" በሚል አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተለይም በቁጫ ህዝብ ላይ በዞኑ መንግስት መሪነት እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ ሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ከእውነተኛ ታሪካቸው ተነስተው በአንደበታቸው አብራርተዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከዚህ በፊት እንዲሁም ሰሞኑም በጋሞ ዞን በተለይም በቁጫ፣ በዘይሴ እና ሌሎች መዋቅሮች በአሳዛኝ ሁኔታ በህዝብ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #kuchazone #gamoworeda

Wolaita Times

27 Dec, 15:01


"ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው ዕለት የጋሞ አባቶች በውድድር ላይ እያሉ በዎላይታ ላይ በ3ቱ አቅጣጫ የተለመደውን ጦርነት በማወጅ የስድስት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ በርካቶች እንዲቆስሉ አድርጓል" - የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች

የአቶ ጥላሁን ከበደ ሴራ መጨረሻው መቼ ይሆን?

"በመጀመሪያ ደረጃ ንፁህ የጋሞ አባቶች ለሠላም ባበረከቱት አስተዋፅኦ ላገኙት ዕውቅና እንኳን ደስ አሎት ደስ አለን ለማለት እንፈልጋለን። እንግዲህ ይህ ትልቅ ዕውቅና በመሆኑ እናንተ እያላችሁ የዛይሴ፤ የዶርዜ፤ የቁጫ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሚድያ ብቻ የሠላም ተምሳሌት እየተባለ በእውኑ ዓለም እየተሰቃዩ መቀጠል የለባቸውም ብለን የሚናምን ስንሆን በተላይም ትክክለኛ ማንነት የማይታወቅ አፉ ቅቤ ተግባሩ ሰይጣን፤ በአፉ ብልፅግና በተግባሩ ሰይጣን የሆነው የአቶ ጥላሁን ከበደ የእናንተን ጭምብል ተጠቅሞ የሚያደርገውን አረመናዊ ድርግቱን ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል" በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

"በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ በሀገር ደረጃ የጋሞ አባቶች በውድድር ላይ እያሉ አቶ ጥላሁን ከበዴ ዎላይታ ላይ ደግሞ በ3ቱ አቅጣጫ የተለመደውን ጦርነት ማወጁን ከምንጮቻችን አረጋግጠናል" ብሏል።

ለአብነት ሲገልፁ፦ "ይኼውም በሠላምበር እና አካባብያዋ የሚኖሩ ዎላይታዎች እንድፈናቀል፤ በዳሞት ፑላሳ የአቶ ገብረመስቀል ጫላ ጎሳ እና የአቶ ሳሙኤል ፎላ ጎሳ እንድጋጬ በማድረግ የ2ት ሰው ሞት እና የበርካታዎቹ ከባድ ጉዳት እንድሁም ሲዳማንና ዎላይታ በሚያዋስነው ድንበር የ3ት ሰው ሞትና የበርካቶች አካል ጉዳት ያስከተለ ግጭት እንድፈጠር አድርጓል" ስሉ አብራርተዋል።

ይህንን ተልዕኮ ለጋሞ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ለሆኑት ለአቶ መኮንን እና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ለሆኑት ለፍሰሀ ጋረደው እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ተችሏል።

"ኮምነሽር ፍሳሃ ጋረደዉ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ የመምራትም ሆነ የማስጠበቅ ሥራ ሀላፊነትም፣ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት የለዉም፤ እሱ አቅሙንና ጊዜዉን ሰጥቶ የሚሰራዉ በዎላይታ ዉስጥ የራሱን አደረጃጀት ተጠናክሮ የምቀጥልበት እርካሽ ፖለቲካ ሥራ ዉስጥ ተጠደምዶ ነዉ ያለዉ" በሚል ተጠያቂ አድርጓቸዋል።

"ሲጀመር ኮ/ር ፍሳሃ ጋረደዉ ከዚህ ቀደምም በአዋሳ ከተማ የዎላይታ ተወላጆች ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም አይቶ እንዳላዬ ራሱንና ልጆቹን ይዞ አ/አበባ በመሸሹ ለዉለታዉ አ/አበባ ከተማ አስተዳደር ሹመት ተሰጥቶ ቆይቶ አሁንም ይሄን እሱ በስሜ ዎላይታነት የሚነግደዉን ህዝብ ለፍትህ እጦትና ለህይወት ማጣት ለመዳረግ ደቡብ ኢት/ያ የሚባል ክልል ሲዋቀር ከአቶ ጥላሁን ከበደ እና ከአቶ ተክለወልድ አጥናፉ ልዩ ተልዕኮ ይዞ ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዉ መጥተዋል" በሚል ሁኔታውን አስረድተዋል።

"ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የዎላይታ ዉስጥ ፖለቲካን በመበጣበጥና መረጋጋት እንዳይኖር በማድረግ የዎላይታ ህዝብ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ወድቀት ዉስጥ ሆኖ ለአቶ ጥላሁን ከበደ የእጁ ጦር መሣሪያ በመሆን እሱ የሚያሳድዳቸዉን የዎላይታ ጠቃሚ ፖለቲከኞችን በማፈንና በማሰር ተወጥሮ የዎላይታና የሲዳማ የድንበር ጉዳይ ለአንድ ቀንም እንኳን የህዝብ ሠላምና ፀጥታ ዘርፍ እንደምመራ ሰዉ ቅኝትም ይሁን ስምርት ሰጥቶ የፀጥታ ሁነታዊ ግምገማ አድርጎ አያዉቅም" በሚልም ተጠያቂ አድርጓቸዋል።

"ነገር ግን በሶዶ ከተማ ዉስጥ ያሉ ዜጎችን በየቀኑ የአቶ ጥላሁን ስዉር ተልዕኮን በመቀበል በማሰርና በማሰቃየት ሙሉ ጊዘዉን ያጠፋል፤ በዎላይታና ሲዳማ መካከል ያለዉ የድንበር አከባቢ ጉዳይ ፀጥታዉን በሚመራዉ አካል በልዩ ትኩረት ክትትል ተደርጎ ቢመራ ኖሮ ይሄን የህይወት ዋጋ የዎላይታ ህዝብ ባልከፈለ ነበር" ብሏል።

"ኮ/ር ፍሰሃ ጋረደዉ ለህሊና እና ለሙያ ዲስፕልን የሚገዛ ሰዉ መሆን የነበረበት ለአቶ ጥላሁን የመላላክና የኮንትሮባንድ ንግዱን በማጧጧፍ የአቶ ጥላሁን ከበደ ሴራ ዋና ዓላማ ህዝቡን በማማረር ወደ አመጽ ለማስገባትና የለውጡ አደናቃፊ ናቸው የሚለውን ድራማ ለማሳካት ነው። በአቶ ጥላሁን እና በአቶ ዓለማየሁ ባዉዲ ሴራ ምክንያት 38 ንፁሃን ዜጎች መጥፋቱን ህዝቡ እያወቀ በታጋሽነት ቀንና ማታ እንደፈለጋችሁ እንድትጨፍሩ አድርጓል" በማለት ገልጸዋል።

አስተባባሪዎቹ አክለው "ይህንን ታጋሽነት "ከሩቅ ስናያችሁ ጀግና ትመስሉን ነበር" ብሎ በየመጠጥ ቤት የሚያወራውን አቶ ዳዊት ገበዬሁንም ጭምር በሠላም አንከባክበን እያኖረ የሚገኝ ሲሆን በተደጋጋሚ ለፌዴራል መንግስት ጉዳዩን እንድያውቀው፤ እንድረዳና እንዲፈታ ጥረት ያደረግን ብሆንም መፍትሄ አልተገኘም" ብሏል።

"ሁላችንም እንደሚንገነዘበው ለትዕግስትም ልክና ገደብ ስላለው የሰው ህይወት ሳይጠፋ በዎላይታ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለው ሁሉ አቀፍ በደል እንድቆም ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለሞቱት ለንፁሃን ወንድሞቻችን ነፍሰ በሰላም ትረፍ እያልን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን" መልዕክት ገልጸዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama

"ፕሬዝዳንቱ የጋሞ አባቶች በውድድር ላይ እያሉ በዎላይታ ላይ በ3ቱ አቅጣጫ ጦርነት በማወጅ የ6 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ በርካቶች እንዲቆስሉ አድርጓል"

https://wolaitatimes.com/?p=5285

Wolaita Times

27 Dec, 13:55


"በጋሞ ዞን ፈጣሪ የለም" ያልተቋረጠው የቁጫ ስቃይ

ብልፅግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ በቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫውን በተሸነፈባቸው አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

በሀገራችን 2013 ዓ.ም በተካሄደው 6ተኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ካሸነፉባቸው የምርጫ ክልሎች የቁጫ ምርጫ ክልል አንዱ ነው።

በቁጫ ምርጫ ክልል ገዥውን ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ 7 ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን የተወዳደሩ ቢሆንም የቁጫ ምርጫ ክልል ሕዝብ ከቀረቡ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በአብላጫ ድምፅ የመረጠው በቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) መሆኑ ይታወቃል።

ይህም በመሆኑ ምርጫውን የተሸነፈው ብልፅግና በምርጫ ክልሉ በቁሕዴፓ አባላት፣ ደጋፊዎች እና በቁጫ ብሔር ተወላጆች ላይ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት አካላዊ ድብደባ፣ እስራት፣ የገንዘብ ቅጣት፣ ከሥራ ማፈናቀል እና ከአካባቢው ዜጎችን በማሳደድ አያሌ መከራዎችን በሕዝብ ላይ በማድረስ ላይ ይገኛል።

እነዚ በደሎች እንዲቆሙ በቁሕዴፓ እና በምርጫ ክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ለበርካታ ጊዜ ለሚመለከታቸው ተቋማት እና ለመንግሥት አካላት ተደጋጋሚ አቤቱታዎች የቀረቡ ቢሆኑም ተቋማት አንዳች ምላሽ ባለመስጠታቸው በቁጫ ምርጫ ክልል በዜጎች ህይወት ላይ የብልፅግና ፓርቲ መዋቅር እና በፀጥታ ኃይሉ በአስከፊ ሁኔታ የሚፈፀመው ሰብዓዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሕገ-መንግስታዊ መብት ጥሰት ተባብሶ ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው 6ኛ ዙር ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በቁጫ ምርጫ ክልል የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) ምርጫውን በማሸነፉ ምክንያት ያኮረፈው ብልፅግና ፓርቲ ከምርጫ ማግሥት ጀምሮ ላለፉት 3 ዓመታት መንግሥታዊ መዋቅሩንና ሠልጣኑን ተጠቅሞ በቁሕዴፓ አባላት፣ ደጋፊዎች እና በብሔር ተወላጆች ላይ ከምርጫ አዋጅ ሥነምግባር እና ከሕገ-መንግስቱ መርህ ባፈነገጠ መልኩ በዜጎችን በመደብደብ፣ በማሰር እና በገንዘብ በመቅጣት ለከፋ ጉዳት መዳረጉን ቀጥሏል።

"ብልጽግና ፓርቲን ተቃውማችሁ ፓርቲው ያቀረባቸውን እነ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች እጩዎችን መምረጥ እየተገባ ተቃዋሚ ፓርቲ የሆነውን ቁሕዴፓን እጩዎችን መረጣችሁታል" ያሏቸውን የቁሕዴፓ አባላት፣ ደጋፊዎች እና የቁጫ ብሔር ተወላጆችን የፀጥታ ኃይሉ በአሰቃቂ ሁኔታ እያስደቡደቡ በጠራራ ፀሐይ በመሬት እያንከባለሉ “ቁሕዴፓን ለምን መረጣችሁ? መንግሥትን ተቃውማችሁ ብልፅግና ፓርቲ እንዲሸነፍ በማድረጋችሁ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፌዴራል መንግሥት የተቆጡ ስለሆነ ይቅርታ ጠይቃችሁ ከቁሕዴፓ አባልነት በይፋ በመውጣት አሁኑኑ ወደ ብልፅግና ፓርቲ አባልነት ተቀላቀሉ!" እየተባለ የቁሕዴፓ አባላት፣ ደጋፊዎች እና የቁጫ ብሔር ተወላጆች በነፃ ፍላጎታቸው አባል ከሆኑበት ፓርቲያቸው በኃይልና በጉልበት ተገዶ እንዲወጡ በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ከሕግ አግባብ ውጭ በፖለቲካ አቋምና በብሔር ማንነት ልዩነት መነሻ በአስከፊ ሁኔታ አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ሥነልቦናዊ ጥቃቶች በአደባባይ ይፈፀማሉ።

በቁጫ ምርጫ ክልል የብልፅግና አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በቁሕዴፓ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ከምርጫ አዋጅ እና ከሕገ-መንግስታዊ አሰራር በተቃራኒ የመንግሥት ሥልጣንና መዋቅርን ተጠቅሞ የሚፈፀሙትን የፖለቲካ ወንጀል የሚሳዩ የቪዲዮ እና የምስል መረጃዎች በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉ ቢሆንም ከደረሱን መረጃዎች አንፃር ለሕዝብ ዕይታ እንዲበቁ የተደረጉ እጅግ ጥቅቶች ናቸው።

በዜጎች ህይወት ላይ በእብሪት የተፈፀመውን በደል ከሚያረጋግጡ የቪዲዮ እና የምስዕል መረጃዎች አስከፊነት የተነሳ ለማኅበራዊ ሚዲያ ሥርጭት፣ ለሀገሪቱ ገፅታ፣ ለሕዝብና ለግለሰቦች ሞራል እና ደኅንነት ስባል ለማኅበራዊ ሚዲያ ከማብቃት መቆጠብ አስፈላጊ እንደሆነ የታመኑባቸው በርካታ መረጃዎች በሚስጥር እንዲያዙ ተደርጓል።

በዚሁ ልጥፍ የቀረበው መረጃ "የፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ እምነት ጥሎባቸው በቁጫ ምርጫ ክልል እንዲያሸንፉ ያቀረባቸውን እነ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔዎች ጉዳይ ሚኒስትር አልመረጣችሁም" በማለት ያኮረፈው የብልፅግና ፓርቲ መዋቅር በፀጥታ ኃይሉ በቁሕዴፓ አባላት፣ደጋፊዎች እና የቁጫ ብሔር ተወላጆች ላይ በፖለቲካ አቋምና በብሔር ልዩነት መነሻ የሚፈፀሙ አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ሥነልቦናዊ ጥቃትና የፖለቲካ ጭቆና ነው።

ተጨማሪ የቪዲዮ እና የምስል መረጃዎች እንደ አስፈላጊነታቸው ለሚመለከተው አካል የሚቀርቡም ይሆናል። የዓለም ማኅበረሰብ፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተቋማት ይህን አስነዋሪ ድርጊት በማውገዝ ለቁጫ ሕዝብ ፍትህ ድምፅ እንድትሆኑ በሕዝቡ ስም እናመለክታለን።
ቁህዴፓ
ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

በቪዲዮ ተመልከቱ👇https://youtu.be/GsSVQ6Iaxmw?si=ZQDjb5ENvmxahXoc

Wolaita Times

26 Dec, 16:19


መንግስት በሕወሓት፣ በኦነግ ሸኔ በፋኖ ዎላይታ|ን ለምን ይከሳል?

የዎላይታም ሕዝብ በተደጋጋሚ የሕወሓትና የኦነግ ሸኔ ተባባሪ እየተባለ በብዙ የፈደራልና የክልል ብልጽግና ሹማምንት ተከሷል፣ ከፋኖ ጋር ይሰራል ተብሎም ተከሷልና ይሄ ከምን የመነጨ ነው?

ህዝቡ ማንም የሰጠዉ ተልዕኮ ኖሮ ሳይሆን መንግስት መመለስ ያለበት ሐቀኛ እና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ላለመመለስ ለምን የዳቦ ስም ይሰጣል ?በሄዱበት ቦታ ሁሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ስለህዝቡ ውሸት ለምን ያወራሉ ለምን ሀቅ ይደብቃሉ ? ለእነኚህና መሰል ጥያቄዎች የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፖለቲካ ወጌሻ መደበኛ ጥንቅር ምላሽ እንደሚከተለው አቅርቧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ማዲያ፦ አገዛዙ የዎላይታን ሕዝብ ለምን በተከታታይ በሐሰት ይከሳል፣ ከሕወሓትም፣ ከኦነግ ሸኔም፣ ከፋኖም ጋር ለምን ይፈርጃል ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ የሐሰት ክስ ለኢትዮጵያ ፖለተካ አዲስ ነገር አይደለም በተለይ መንግስት ትርጉም ያላቸዉን የፖለቲካ ጥያቄዎች የሚያነሱ አካላትን በሐሰት ሲከስ ኖሯል በኢትዮጵያ ታሪክ። በኢህአዴግ ጊዜም ለምሳሌ ግለሰቦችን አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ እያሉ ማሰር የተለመደ ነው በሐሰት።

ለምሳሌ እንደነ በቀለ ገርባ አይነት ሐቀኛ ፈደራሊስት ፖለቲከኞችንም ሳይቀር የሐሰት ምስክር በማዘጋጀት ፍርድ ይበየንባቸዉ ነበረ። በተለያዩ ግለሰቦችም ላይ ዶክመንተሪ በሐሰት እየተፈበረከ ይሰራ ነበር። አሁን የብልጽግናን ለየት የሚያደርገዉ ሕዝብን በሐሰት በጅምላ መክሰስ መጀመሩ ነው።

ለምሳሌ ከትግራይ ጦርነት በፊት "የትግርኛ ተናጋሪዎች" እየተባለ እጅግ አደገኛ የሆኑ በማረሚያ ቤት ተሰሩ የተባሉ ወንጀሎች በዶክመንተሪ መልክ በቴሌቪዥን ተሰራጭተዋል። የዎላይታም ሕዝብ በተደጋጋሚ የሕወሓትና የኦነግ ሸኔ ተላላኪ እየተባለ በብዙ የፈደራልና የክልል ብልጽግና ሹማምንት ተከሷል፣ ከፋኖ ጋር ይሰራል ተብሎም በዶክመንተሪ ተከሷል። እዉነታዉ መንግስት መመለስ የማይፈልጋቸዉ ሐቀኛ እና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎች የዎላይታ ሕዝብ አሉት እንጂ ማንም የሰጠዉ ተልዕኮ ኖሮ አይደለም።

በነገራችን ላይ ይህ ብቻ አይደለም የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በፌደሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከአወዛጋቢው የዎላይታ ሕዝበ ዉሳኔ በኃላ በተደረገ መድረክ ላይ በዎላይታ ላይ ሐሰተኛ ክስ በሕገወጥ መንገድ ፈብርኮ "እንደዉም በዎላይታ በተካሄደው ሕዝበ ዉሳኔ ሕዝቡ መታወቂያ ተከልክለን ነበር የኖርነዉ፣ አሁን ለሕዝበ ዉሳኔ ሲሉ አደሉ የሚል መረጃ ነው ያገኘነው" ብሎ ዋሽቷል።

እርሱ በሕጋዊነት መረጃ ማግኘት የሚችለዉ ከዎላይታ ዞን ብቻ ነው። የዎላይታ ዞን ደግሞ በሠጠዉ መግለጫ ዉስጥ እንደዛ አይነት ነገር የለም። ይህ የሐሰትና የጥላቻ ክስ ከግለሰቡ አልፎ የብልጽግና ፓሪቲም ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው።

ይህን ለማስረዳት አንዴ ወደሁዋላ ልመልሳቹ ለዉጡን ያመጣዉ አንዱ ህወሀት በኦሮሚያ ክልል ከኦህዴድ መዋቅር መዉሰድ እያለበት፤ የራሱን መረብ ዘርግቶ የሐሰት መረጃ እየተቀበለ በፈደራል መንግሥት ዉሳኔ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የሚለዉ ነበር። ብልጽግና ይህን አሰራር አስቀራለዉ ብሎ ነበር፤ ነገር ግን እነ አቶ ጥላሁን ከበደ የሐሰት መረጃ እየፈበረኩ በዎላይታ ሕዝብ ላይ ሴራ ሲጎነጉኑ ነበር።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እነዚህ እና የመሳሰሉት በተለይም ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ የሐሰት ክስና ፍረጃዎች ምክነያታቸዉ ምንድነው ? ተጽዕኗቸዉስ ምን ድረስ ነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምክንያቱ ፖለቲካዊ ግብ ነዉ፣ ማሳነስ የሚፈለጉ ብሔሮች አሉ፥ ቂም በቀል እየተፈጸመባቸው ያሉ ብሔሮች አሉ። በዋናነት ሐገሪቷን የሚመሩ ኃይሎች ካላቸዉ አላማ ይነሳል፣ በተለይ እነዚህ አይነት ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ ክስና ፍረጃዎች የበላይ አካላት ሳይፈቅዱ ይደረጋሉ ብሎ ማሰብ ቀልድ ነው። አላማዉ ክፉ ይሁን እንጂ ደረጃና አይነቱ ይለያያል በተለያዩ ሕዝቦች ላይ።

ተጽዕኖዉ ዘርፈ ብዙ ነው፤ በዋናነት በቀጥታ ከመንግሥት መዋቅሮችና ከመንግሥት ጋር በቅርበት በሚሰሩ አካላት ጀምሮ፣ በተዘዋዋሪ ወደ ግል ዘርፎችም ይዘልቃል። ሕዝብን ተጠርጣሪ ያደርጋል፣ ቦታ እንዳይሰጠዉ ያደርጋል፣ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በዛ አቅጣጫ ሥራቸዉን ይከዉናሉ።

በተጨባጭ ግን ነገሩ የዎላይታ ሕዝብ በመንግሥት መገፋቱንና እንደተገፋ እንዲቀጥል ፍላጎቶች መኖራቸዉን ያሳያል። ለምሳሌ በሁሉም ቦታ ጦርነት ሲካሄድ፣ በቀጥታ ከጦርነቱ ጋር የማይያያዝ ሕዝብ የሚከሰስበት ከሆነ፤ ተፈርጆ ከሚጎዳዉ በተጨማሪ፣ ጦርነቶቹ በሚያመጧቸዉ የአሰላለፍ ለዉጥም እየተጎዳና እየተገፋ እንዲሄድ ያደርጋል። ጉዳቱም ከፖለቲካ ዉክልና መነፈግ፣ ተደማጭነት መነፈግ እና የኢኮኖሚ ጥቅም መነፈግ ያስከትላል። የሕዝብን ገጽታና ስምንም ያጠለሻል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በጦርነቶች ጊዜ ሕዝብ ፈርጆ ከጎዱ በኃላ የሰላም ስምምነት ሲፈረምስ ያንን ሕዝብ ዞር ብሎ አለማዬት ልክ ነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የሚገርመዉ እሱኮነዉ ቀጥታ እንደሚታኮስ ቡድን ደርበዉ ይቀጡሐል፣ የሰላም ስምምነት ሲመጣም በተለይ ዎላይታን ገፍቶ የመቀጠል ፍላጎት አለ ያ የትም የሚያደርስ አይመስለኝም። በቀጥታ ጦርነት በሚካሄድበት ሰላም ሲመጣ በተመሳሳይ ተፈርጀዉ የተሰቃዩ የዎላይታ አይነት ሕዝቦችንም ጉዳይ ማየቱ ተገቢ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromo

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

ህዝቡ ማንም የሰጠዉ ተልዕኮ ኖሮ ሳይሆን መንግስት መመለስ ያለበት ሐቀኛ እና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ላለመመለስ ለምን የዳቦ ስም ይሰጣል ?በሄዱበት ቦታ ሁሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ስለህዝቡ ውሸት ለምን ያወራሉ ለምን ሀቅ ይደብቃሉ ? - Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5281

Wolaita Times

26 Dec, 13:45


ሰበር ዜና

ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በባላሃብቶች ታጅቦ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በተጨማሪ ለህግ ተገዢ ላለመሆን ላደረጉት ሙከራና እንቢተኝነት ሀምሳ ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሰሩት የሙስና ተግባር ህጋዊ የሆነው ማራ ማይነርስ የተባለ ድርጅት ከፍተኛ በደል መድረሱን በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፒያሳ ምድብ ችሎት ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 በዋለው የሙስና ክስ መዝገብ አመላክቷል።

በዚህ ችሎት የክልሉ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊና በም/ር/መ/ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ በአስገዳጅ ፍ/ቤት ትእዛዝ በችሎቱ ቀርቦ ምላሽ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህግና ሕገ መንግስታዊ አሰራር የለሌለው አደገኛ ማፈያ ቡድን የሚመራ ክልል መሆኑን የማራ ማይነርስ ድርጅት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረዳቱን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሌቦችና በኮንትሮባንዲስቶች የሚመራ ክልል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህ የማፍያ ቡድን በክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የሚመራ እንደሆነ ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

ፍትህ ለማግኘት እስከ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ድረስ አቤት ብሉም ምላሽ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ የከፈተው 'ማራ ማይነርስ' የተባለ ድርጅት በጋሞ ዞን ቦሮዳ ወረዳ ቦታ ተረክቦና በካዳስተር አስመዝግቦ ጥናት ሲደረግ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት መኖሩ መረጋገጡን የተረዱ የክልሉ ሙሰኛ አመራሮች በአንድ ጀምበር እነሱ የተካተቱበት አዲስ ማህበር በማደራጀት ማራ ማይነርስ ለተባለ ድርጅት በተሰጠው ቦታ ላይ ደርበው በማደራጀት ወረቀቶች ላይ ስርዝ ድልዝ በማድረግ ከስይስተም ውጭ በማኑዋል በመስራት ለራሳቸው መውሰድ መቻላቸው ህገ ወጥ መሆኑን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፒያሳ ምድብ ችሎት ባቀረቡበት የክስ መዝገብ መነበቡ ታውቋል፡፡

ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ፍ/ቤቱ የላከውን መጥሪያ ላለመቀበል በማስቸገሩ በፌደራል ፖሊስ ተገድዶ በአማካሪው በኩል የክስ ይዘትና መጥሪያ የደረሳቸው በመሆኑ ከፍተኛ አስፈጻሚ አካል ሆኖ ለህግ ተገዢ ላለመሆን ላደረጉት ሙከራና እንቢተኝነት 50000 ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

ሆኖም በህገ ወጥ መንገድ ባደራጃቸው ባለሃብቶች የታጀበው ችሎት ፍትህ ናፋቂና ጠያቂ በሆነው ድርጅትና ጠበቃቸው ላይ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡

በፍ/ቤቱ ጠንካራ አቋም የደነገጠው ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ደጋግሞ እኔ የክልል ም/ቤት አባል ነኝ ያሉት ሲሆን ፍ/ቤቱም የህዝብ ውክልናና ሃላፊነት ካለህ እንዴት ወንጀል ትፈጽማለህ በማለት ስርአት ማስያዙን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሙስና ወንጀል መረጃዎች በድምጽና በሰነድ ተደራጅቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ህገ ወጥ ተግባራቸውን ህጋዊ ለማድረግ ያለእንቅልፍ የምሰሩ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ በቅርቡ ለክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ በተሳሳተ መንገድ ሀሳብ አቅርቦ ካስወሰነ በኋላ የጋሞ ዞንና የቦረዳ ወረዳ መዋቅሮቹም የህገ ወጥ ተግባራቸው ተባባሪ ሆነው የክልል አስተባባሪ አቅጣጫ ነው በማለት ያለማመንታት ተቀብለው ፈጽመዋል፡፡

ክልሉ በአደገኛ ማፈያዎች ኔትወርክ የሚመራ ስለመሆኑ በቂ ማሳያም ነው ተብሏል፡፡የምደረአንፃር "በማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት በሕጉ መሠረት በቅድሚያ አንድ ባለሀብት የማዕድን ቅኝት (Exploration) ሕጋዊ ፈቃድ ከእነ coordinate ነጥቦች ጋር ከተሰጠ በኋላ፣ የፀደቀ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ፣ የአከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነድ፣ የማልማት አቅም፣ የንግድ ምዝገባ ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ አስቀድሞ የተፈቀደው ይዞታ መጠን ሊቀነስ እንደማይችል ሕጉ ይደነግጋል።

ነገር ግን ባለሀብቱ የማምረት አቅሙ ደካማ ከሆነ፣ በራሱ ፍላጎት ይዞታው ይቀነስልኝ የሚል ጥያቄ ካቀረበ፣ በአከባቢው ማህበረሰብና ሥነምህዳር ላይ የከፋ ጉዳት የምያደርስ መሆኑ በጥናት ከተረጋገጠ፣ ከይዞታው ሊቀነስ ይችላል።

ከዚህ ውጭ ከልማታዊ ባለሀብት ቀንሰው፣ በጥቅም ትስስር ለሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት ማስተላለፍ ሕጉ አይፈቅድም።

ሆኖም ከሕጋዊ አሰራር ውጭ ከማራ ማይነርስ ተቀንሶና እላዩ ላይ ሌላ ማህበር ተመስርቶ የነበረው ህገወጥ አሰራር በተመለከተ በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት እያለ ህግን በመጣስና የፍርድቤት ትዕዛዝ በመተላለፍ ከህጋዊ ማህበር በህገወጥ መንገድ ለሌሎች ለማስተላለፍ የተፈለገበትን የቢሮ ኃላፊው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን አጥብቆ በመያዙ ድንጋጤ ውስጥ የምገኙት የክልሉ ም/ር/መስተዳድር አክልሉ አዳኝ ከእሳቸው ጋር ተሳፍሮ የሄዱ የአዲሱ ማህበራቸው አባል የሆኑ ባለሃብቶች ጋር ምክክር በማድረግ የማራ ማይነርስ ድርጅት ጋር ለመደራደር እስከዛሬ በአዲስ አበባ እየተማጸነ እንደምገኝ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በባለሃብቶች የታጀበው ችሎት ጠንካራ ክርክር የተደረገበት ሲሆን በስይስተም የተሰራውን ቀይሮ በማኑዋል ለማስተካከል የተደረገው ጥረት ምንም ያህል ፍትህን ለማዛባት የሚደረግ ሙከራ ቢሆንም ጊዜውን ጠብቆ እውነቱ መውጣቱና ሙሰኞች ተገቢውን ቅጣት ማግኘታቸው እንደማይቀር አመላካች ነው እያልን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southernethiopia

በህጋዊ ስልጣን ህገወጥ ተግባር የተሰማራው ም/ርዕሰ መስተዳድር በፍርድቤቱ ህግ ተምረው ወጡ ?
Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5272

Wolaita Times

25 Dec, 14:43


ፕረዚዳንቱ "ተተቸው" በሚል ህግንም ሽማግሌዎችንም አልሰማም አሉ

የመብት ተሟጋችና የዩንቨርስቲ መምህር የሆነው "ፕረዚዳንቱን ተችቷል" በሚል በህገወጥ መንገድ ለአንድ ዓመት ያለቅጣት ውሳኔ በእስር እንዲቆይ መደረጉ በአከባቢው ቅሬታ ፈጠረ

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ መምህር መለሰ አብረሃም የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ መምህር እንዲሁም የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ ሚዲያ መስራች ሲሆን በሀገረ-ህንድ የዶክትሬት ትምህርቱን እየተከታተለ ካለበት ለምርምር ሥራ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ እንደሻው ጣሰውን "በማህበራዊ ሚዲያ ተችተሃል" በሚል ለአንድ ዓመት ሙሉ ያለ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ በእስር ቤት እያሳለፈ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

ቤተሰቦቹ መለሰ ከታህሳስ 2016 እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም ለ6 ወራት ያለምንም ክስ በሆሰዕና ማረሚያ ታስሮ እንድቆይ ከታደረገ በኃላ በ100 ሺ ብር ዋስ ተለቀው እንደነበር ተናግሯል።

ከእስር ስወጣ ወደ ህንድ ለመሄድና በማረሚያ ቤት በእስር ሆኖ የሰራውን የጥናት ውጤት አስረክቦ ለመመለስ ጉዞ ጀምሮ ኤርፖርት ገብቶ ሙሉ ህደቱን ካለፈ በኃላ ቀድሞ ከሀገር እንዳይወጣ እግድ ተቀምጦበት ስለነበር ማለፍ አትችልም ተብሎ መመለሱንም አክለዋል።

ከዛ በኃላ በሁለተኛ ቀንም በክልሉ ፕረዚዳንት እንዲታሰር ተደርጎ በመጀመሪያ ወደ ሆሳዕና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግዜ ቀጠሮ ስመላለስ ቆይቶ የነበረውን በዋስ ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሱን ያወቀው የክልል ፍትህ ቢሮ ዐ/ህግ ጉዳዩን ወደ ሀዲያ ዞን ከፈተኛ ፍ/ቤት ማዞሩን ቤተሰቦቹ አስረድቷል።

ከፈተኛ ፍ/ቤቱም የቀረበበት ክስ የዋስትና መብት የማያስከለክል መሆኑን ጠቅሶ በ200 ሺህ ብር ዋስ እንድፈታ በማዘዙ ቤተሰብ የፍርድቤቱን የባንክ አካውንት ቁጥርና የመዝገብ ቁጡር ለመቀበል ሄዶ እዛው እያለ ከህግ ውጪ የከፍተኛ ፍ/ቤት ፕረዚደንት በፍጥነት ወደ መዝገብ ቤት በመዝለቅ የመለሰ አብረሃምን መዝገብ ስጡኝ በመለት መዝገቡን ተቀብሎ በቢሮው አስቀምጦ መውጣቱን ቅሬታ ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንደለ መለሰ ለ4ተኛ ግዜ በመታሰሩ የሀዲያ የሁሉም ጎሳዎች ባህላዊ መሪዎችና የሁሉም የሀይማኖት አባቶች በመሆን ወደ ክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አቶ እንደሸው ጣሰው ቢሮ ሄደው መናገራቸውን ተናግሯል።

በዕለቱ የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪ የሆኑትን አቶ ንጉሴ አስረስን አግኝተው ተወያይተው አቶ ንጉሴ ለሀዲያ ሽመግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችን "የመለስን ጉዳይ ሀላፊነት የምትወስዱት ከሆነ ደብዳቤ ጽፋችሁ መለሰም ደብዳቤ ጽፎ ይዛችሁ ኑ" ብለው እንደነበር ገልጿል።

ሽመግሌዎቹም "ቀጥታ ወደ ሆሳዕና ማረሚያ በመውረድ መለስን አስጠርተው ይህንኑ ነግረውት ከዝህ በኃላ በምድያ ሥራ ከክልሉ መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ የሚያስገባ ነገር ውስጥ እንደማትገባ ለኛ ቃል ግባልን፣ ይቅሪታ ጠይቀህ ወደ ትምህርትህ ህድ አሉት። መለሰ "እኔ ያጣፈሁትና ያላወኩት ነገር ካለ ይቅርታ ይደረግልኝ" ብሎ ለክልል መንግስት ደብዳቤ ጽፎ ለሽማግሌዎች ሰጣቸው ብለዋል።

ሽማግሌዎቹም ደግሞ ሀላፊነት ወስደው ጉዳዩን እንደሚያዩ ገልጸው ጽፈው አንድ ላይ ለክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪ ሰጡት። እሱም ደብዳቤዎችን ለክልሉ ፕሬዚዳንት ማስረከቡን ነገሯቸው፣ እንጠራችኋለን ብሎ ሸኛቸው። ከዚያ ወድህ በተደጋጋሚ ሽመግሌዎች ቢሄዱም ከበረ እንዳያልፉ ጠባቂዎች እየከለከሏቸው ይይመለሳሉ" ሲሉ ቤተሰቦቹ በምሬት ይናገራሉ።

በዚሁ መሀል የሀድያ ዞን ከፈተኛ ፍ/ቤት መለሰን በዋስ እንድወጣ መፍቀዱን የተገለፀ ቢሆንም የክልል ፕሬዚዳንት ለዐ/ህጎችና ለደኞች በቀጥታ ስልክ እየደወለ እንዳትፈቱት እንደምላቸውና እምቢ ካሉ ስራቸውን እንደሚያጡ እያስጠነቀቃቸው እንደሆነ ከአንደበታቸው የሰማነው" በሚልም ቤተሰቦቹ የሁኔታውን ውስብስብነት በመግለፅ ለልጃቸው ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Hadiya #gurage

ፕረዚዳንቱ "ተተቸው" በሚል ህግንም ሽማግሌዎችንም አልሰማም አሉ
Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5267

Wolaita Times

23 Dec, 16:02


"ጃዋር የራሱን መንጋ ከብልፅግናው መቀማት የሚችልበት አቋም ላይ አይደለም" ደግሞ "ችግሩን የፈጠሩ ሶስቱ ብሄሮች ብቻቸውን መፍትሔ ይሰጣሉ ማለት በኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ቅዠት ነው"- የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፖለቲካ ወጌሻ እንግዳ

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ከሰሞኑ ከ BBC አማርኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ እንደነበረ ይታወቃል፣ በዝርዝር የተወሰኑ ነጥቦችን ቀጥለን ከማንሳታችን በፊት አጠቃላይ ቃለ ምልልሱን እንዴት አገኙት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በአጠቃለይ ቃለ ምልልሱ ብዙ ወሳኝ ጉዳዮች የተነሱበት ነው። ጃዋር መሐመድም በሚዲያ ቀርቦ በዚህ ሰዓት ሐሳቡን ማቅረቡ ጥሩ የሚባል ነው። በተለይ በዋናነት በሐገር ወይንም ኢትዮጵያ ላይ አተኩሮ አዉርቷል ያም መበረታታት ያለበት ይመስለኛል። እንደ ቅሬታ ደግሞ አሁንም ቀድሞም የነበረና የቀጠለዉ የጃዋር ችግር ኢትዮጵያን ከሶስቱ ብሔሮች ማለትም ኦሮሞ፣ አማራና ትግራይ ጋር ብቻ አያይዞ አዉርቷል። በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሱማሌን ጠርቷል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ጃዋር መሐመድ አሁን በጣም የሚያስጨንቀዉ የሐገር መፍረስ (state collapse ) እንደሆነ አንስቷል፣ በተጨማሪም ሐገሪቷ አሁን ከመስመር ለመዉጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ብቸኛ ተጠያቂ በማድረግ ማለትም ከአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ወደ ግለሰባዊ አምባገነንነት እንዳሸጋገሩ ምልከታዉን አጋርቷል፣ ይሄንን የጃዋርን ሐሳብ ይገዛሉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የተቀላቀለ ነው፤ እዉነትም፣ ዉሸትም የራሱ የግሉ ምልከታም እና ምርጫም ያለበት ነው አቋሙ በእኔ እይታ። ለምሳሌ የሐገር መፍረስ ስጋት በእዉነቱ ተጨባጭ ነው፣ ግን ጃዋር እራሱምኮ ለዚህ ከመስመር ለወጣ አካሄድ ትልቅ ድርሻ ነበረው። ኢህአዴግ ከፈረሰ በዛዉ ሐገር እንዳይፈርስ ጥንቃቄ አድርጌያለሁ ከ Arab spring በመማር የሚለዉ ጃዋር፣ ፈተና አዉጥቶ መበተን ፣ በሐገር ላይ የሚያስከትለዉን ተጽዕኖ የገመገመ አይመስልም።

ከለዉጡ በኃላ ኢትዮጵያ መጥቶ ፣አሁን በኢትዮጵያ ሁለት መንግስት ነው ያለዉ የዐብይና የቄሮ ሲልና መንግስት እሱን ሲፈራዉ ለሐገር ፈረሳ ጡብ እያቀበለ እንደነበረ የገባዉ አልመሰለኝም። ጃዋር በሚዲያ የዎልቃይትን ጉዳይ ባናነሳ የአማራ ብሔረተኝነት አይነሳም ነበረ እያለ በኩራት ሲያወራ ነበረ። ያ ችግር አሁን ለሐገር ፈረሳ ከሚያሰጉ ነገሮች አንዱ መሆኑን አሁንም አልገመገመም።

ሌላው ነጥብ በርግጥ ጃዋር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከመጀመሪያውም እንዳልወደደዉና ከኦህዴድ ዉስጥ ከማይመቹት ሰዎች አንዱ እንደነበረ ይነገራል። እንደ ፖለቲከኛ ግን ጃዋር የኦሮሞ ሊህቃንንና የኦህዴድ ሰዎችን ማሳመን ያልቻለዉ ሰዉዮ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መገንባት አይፈልግም፥ የግለሰብ አምባገነንነት ነው እያልኩ ነበረ የሚለዉ እዉነት አይመስለኝም። ባይሆን ጃዋር ለራሱ የነበረዉን የተሳሳተ ግምትም ሳያሳይ አይቀርም፤ በአክቲቨስትነት የኢትዮጵያን መሪ የሚሆን ሰዉ መርጣለሁ ማለቱ የሚገርም ነው (የጃዋር ሚና የሚናቅ ባይሆንም) ሌላዉ እነ ጃዋር በሚዲያ ከዉጭ ቢያስተባብሩትም፣ አመጹን በኦህዴድ ዉስጥ ሆኖ ይመራ የነበረው አንድ ቁጥር እራሱ አብይ አህመድ መሆኑን በልኩ የተገነዘበ አይመስለኝም።

አንድ ጃዋር ያስቀመጠዉ እዉነት የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ተገፎ የመድብለ ፓርቲ ሥርአት አለመምጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ብልጽግና ግን ኦሮ_ማራዊ የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ነው እንጂ የአንድ ግለሰብ ብቻ አይመስለኝም።

ለሐገሪቷ ዉድቀት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከብዙ ኃይሎች ጋር በጋራ ተጠያቂ ናቸዉ እንጂ ብቻቸዉን አይመስለኝም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፈ፦ ጃዋር በዚህ ቃለምልልሱ መንግስትን በ priority (ቅድሚያ መስጠት ላለበት ጉዳይ ቅድሚያ ባለመስጠት) ከሷል፣ ይሄንንስ እንዴት አዩት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሱ ሙሉ በሙሉ የምስማማበት ነው። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ችግሯ የቤተመንግሥት ግምባታ፣ ፓርክና መናፈሻ አይመስለኝም እኔም። በተለይ ጃዋር የስኳር ፋብሪካዎች በመለዋወጫ እቃ እጥረት ሥራ ማቆማቸዉ፣ የባቡርና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ቆመዉ መቅረታቸዉን በቁጭት ማንሳቱ ተገቢ ነው። ከዛዉ ጋር አያይዞ ዶላራችን ለድሮን መግዣ መዋለን የተቸበት መንገድም የሚያስመሰግነዉ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ አሁን ላይ ምርጫ በኢትዮጽያ ቅንጦት ነው ብሏል፣ የሐገራዊ ምክክሩም ላይ የሰላ ትችት ሰንዝሯል፥ ይሄንንስ እንዴት አዩት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በተለይ የሐገራዊ ምክክሩ ላይ ያቀረባቸዉ ሐሳቦች ዉሐ የሚቋጥሩ እና የእነ ጃዋር ፓርቲ ኦፈኮ እንዲሁም የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄም ጭምር የሚያራምዱት ምክንያታዊ አቋም ነው። ምርጫ ግን አንድ አመት ከምናምን ብቻ ስለሚቀረዉ እና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ መቀጠል ስላለበት ጃዋር በዚህ ደረጃ ባያጣጥለዉ ይመረጣል። ብልጽግና ከባህሪዉ እንደምንረዳዉ ምርጫዉ ጋር ከደረሰ በዉድም በግድም ምርጫ ማድረጉ አይቀሬ ነዉ። የሚሻለዉ ጃዋር የምርጫ ቦርድን ገለልተኛነት ቢተች ጥሩ ነበረ። ነገር ግን በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ያለዉን የጸጥታ ችግር በልኩ አስቀምጧል ለዚህም መመስገን አለበት። የሰላም ስምምነት መኖር እንዳለበትም ተናግሯል። እኔ ግን የበለጠ የሚያሳስበኝ ባለፈዉ ትግራይ ምርጫ እንዳለፋት በቀጣይ አማራ ክልል ምርጫ እንዳያልፍ ያሰጋል።

መንግስት በኦሮሚያ ምርጫ ማድረጉ የሚቀር አይመስለኝም። ግን በተለይ ሐገሪቷ ሰላም እንደሚያስፈልጋት በኢህአዴግ ጊዜ የሕዝቡ ጥያቄ የከተማ፣ የቋንቋና የመሳሰሉት እንደነበረ አሁን ግን የህልዉና መሆኑን መመስከሩ ያስመሰግነዋል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromo

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።
ለመሆኑ ጃዋር የራሱን መንጋ ከብልፅግና መቀማት መቀማት የሚችልበት አቋም ላይ ነው?
Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5263

Wolaita Times

23 Dec, 06:44


“የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝና የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈለን የዱቲ ሥራ ለማቆም ተገደናል” - ዎላይታ የሀላለ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች

“የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈላቸውም” - ሆስፒታሉ

“የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም” - የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ

በዎላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሀላለ ሆስፒታል የሚገኙ 78 ጤና ባለሞያዎችና ሌሎች ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዝና የ3 ዓመት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው የትርፍ ሰዓቱን ሥራ ለማቆም መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጤና ባለሞያዎቹ በሰጡን ቃል ምን አሉ?

“መንግስት ከሚመድበው በጀት ክፈሉ ብለን በደብዳቤ ብንጠይቅም ‘እንከፍላለን አሁን ግን የካሽ እጥረት አለብን’ አሉን። ከዚህ ባለፈ ማስፈራሪያ፣ እስራት፣ ድብደባ ይደርስብናል።

የመጀመሪያ የስምነት ወራት የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ተካስሰን ፍርድ ቤት እንዲከፈለን ውሳኔ ቢሰጠንም በፖለቲካ ሰዎች ጣልቃ ገብነት ውሳኔ ባለመከበሩ አልተከፈለንም።

ከዚያ ወዲህ የሰራነውን የ15 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያንም ቢሆን ባለመክፈላቸው፣ ለመክፈልም ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ኃላፊ ውጪ በአጠቃላይ ተፈራሪመን የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማቆም ተገደናል።

በደላችንን፣ ድምፃችንን ለህዝብ እና ለመንግስት አሰሙልን። ጤና ሚንስቴር በህይወት ካለ መብታችንን ያስከብርልን” ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የአንድ ወር ደመወዝና የ23 ወራት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተፈጸመበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ በረከት ሌራ ምን ምላሽ ሰጡ?

“የኛ ተቋም የሚያስተዳድረው ገንዘብ የለም ስራዎች ከተሰሩ በኋላ ለወረዳ ፋይናንስ ሪፓርት ቀርቦ ያንን መሠረት በማድረግ ነው ክፍያ የሚፈጸመው።

የ2016 ዓ/ም የሐምሌ ደመወዝ 13% ብቻ ነው የሚቀረው 87% ተከፍሏል። የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ሰፊ ነው ችግሩ። የካሽ እጥረት በሚል ብዙ ነገር እየተባለ ነበር።

የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ፍርድ ቤት ክፍያ እንዲፈጸም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። የወረዳው መንግስት ከክስ ሂደቱ በኋላ መክፈል ከጀመረ በኋላ ነው የቆመው።

‘በንግግር ችግሮችን እየፈታን እንመጣለን’ በሚል ቃል ከተገባልን በኋላ ነው በመካከል ክፍያው የቆመው። የሚያዚያ ወር በከፊል መከፈል ከተጀመረ በኋላ ነው ቆመ” ብለዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ በማታ የሚመጡ ወላድ እናቶችን ብቻቸውን እያከሙ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ባለሙያዎቹ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ቅሬታ አቅርበዋል፣ ሆስፒታሉም የ20 ወራት የዱቲ፣ የሐምሌ ደመወዝ 13 በመቶ ክፍያ አለመፈጸሙን ገልጿል፣ ይህ ለምን ሆነ? ጉዳዩን ተመልክታችሁት ነበር? ስንል ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።

የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ምን አለ?

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ፣ “የ23 ወራት እንዳልተከፈለ መረጃው የለኝም። ተከፍሎ ነው እየተሰራ ያለው። ትክክል ነው ለማለት እቸገራለሁ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ሆስፒታሉም እንዳረጋገጠ ስንገልጽላቸውም፣ “20 ወራት አይደርስም እኔ እንደማውቀው። ማጣራት ይጠይቃል” ነው ያሉት።

“የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም” ያሉት ኃላፊው፣ ጉዳዩን አጣርተው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ሆስፒታሉ ያልተከፈላችሁ የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ መሆኑን ገልጿል፣ እናንተ ደግሞ ያልተከፈላችሁ የ23 ወራት እንደሆነ ገልጻችኋል፣ የትኛው ነው ትክክል ? ስንል የጠየቅናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ከ23 ወራት የዱቲ የ3 ወሯን ለተወሰኑ ሰዎች ነበር የከፈሉት። በትምህርት፣ በዝውዝውር፣ ሥራ በመልቀቅ ሄዱት ሳይከፊሉ ነው ‘ከፍለናል’ የሚሉት ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ህብረተሰቡን እንዳገለገሉ መረሳት አልነበረበትም ” ነው ያሉት።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

Wolaita Times

22 Dec, 14:04


የአድልዎ አሰራርን በመዘርጋት የህዝቦች አደራ የበሉ የአንድ አከባቢ ርዕሰ መስተዳድር

"ካብኔዎች በሌሎች አከባቢዎች ስብሰባ ወይንም ፕሮጀክት ለመስራት ካቀዱ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ ይመስላቸዋል" - ጥናት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ አመት ተኩል እድሜ ከ80% በላይ ክልላዊና ሀገር አቀፋዊ ስብሰባ በአርባምንጭ ከተማ ብቻ ሲካሄድ እንደነበር አንድ ጥናት አመላክቷል።

አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ6 ማዕከል ተደራጅቶ በ6ቱም ማዕከል የክልሉ ቢሮዎች የሚገኙና የክልሉ አስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል ዎላይታ ሶዶ አድርጎ መደራጀቱ የሚታወቅ ቢሆንም የክልሉ ር/መስተደድር መቀመጫ አርባምንጭ እንደሆነ ሁሉም በአንድ አፍ የሚመሰክሩት ነው ይላል ጥናቱ።

አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ባለው አመራር የተካሄደው ይሄው ጥናት "በክልሉ 6ቱም ማዕከል የተደራጁ የቢሮ ኃላፊዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የክልሉን ፕሬዚዳንት ለማስደሰት በሚል ሁሉንም የክልሉን ካፒታል በጀት የክልሉ ፕሬዚዳንት ለሚፈልጉት ፕሮጀክት በአርባምንጭ ከተማ እንዲለማ ከማድረግ ባለፈ አንድም ከዞኑ ስብሰባ ውጪ በዲላ ክላስተር ተካሄዶ አያውቅም ሆቴሎችም ከዚሁ ስብሰባ ለከተማው በቂ ገቢ እያስገቡ አይደለም ሚዛናዊነቱ የተጠበቀ የስብሰባ ሆነ የበጀት የልማት ተደራሽነት የሌለው ክልል እንደሆነ የዲላ ግብርና ክላስተር 6% ያነሰ ክልላዊ ስብሰባ ማድረጉ ይገነዘባል" ሲል ያረጋግጣል።

"የክልሉ ፖለቲካና አስተዳደር ማዕከል 10% የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር ጂንካ 2% የክልሉ ፍትህ ክላስተር ጎፍ ሳውላ ከተማ 1% ኮንሶ ካራት 1% በድምሩ አጠቃላይ 6ቱ ክላስተር 100% የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰረት ያደረጉ ስብሰባዎች ተካሂደዋል" ብሏል።

ጥናቱ እንደሚያረጋግጠው "ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የክልሉ ር/መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ልማቶች ሁሉ ወደ አርባምንጭ ከተማ እንዲሆን ፍላጎት ስላላቸው የክልሉ ካቢኔም ስብሰባው አርባምንጭ ካልሆነ በሌሎች በክልሉ ክላስተር ከተሞች ካደረጉ ከአቶ ጥላሁን ከበደ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ ይመስላቸዋል" በሚል እንደሆነ ምክንያት ያብራራል።

"ስብሰባዎች ለምን ፍትሃዊነት የላቸውም ብቻ ሳይሆን አርባምንጭ ከተማ ላይ የተካሄዱ የክልሉ ፍሬ አልባ ስብሰባዎች ከ80% በላይ ናቸው አንድ አመራር በማዕከሉ በሳምንት አንድ ቀን አይገባም ባለጉዳይ ሲመጣ አርባምንጭ ሄዷል ነው የሚባለው ይህ ደግሞ ከፍተኛ ሀብት በነዳጅ በአልጋ በምግብ እየባከነ አዲሱ ክልል ለአንድ አከባቢ ዕድገት ሲሳይ እየሆነ ነው፤ ለዚህ ሁሉ ለማሳያነት በአንድ ቀን በአርባምንጭ ከተማ የተካሄዱ ሶስት ስብሰባዎችን በመረጃ አስደግፈን አቀረብንላችሁ" በሚል ያክላል።

"አቶ ጥላሁን ከበደ ሌሎች ከተሞችም በተለይ የክልሉ ክላስተር መቀመጫዎች በክልሉ በጀት ሊለሙ ይገባል ለአርባምንጭ ከተማ ልማት 500 ሚሊዮን ብር ያለ ካብኔ ውሳኔ የተሰጠው ለማዕከላቱም ሊሰጥ ይገባል። በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሜዳ 19ኛ የብሔረሰብች ቀን መከበሩ ቀድሞ እየታወቀ በበአል ስም የተወሰደው ለሁሉም ከተማ መሰጠት አለበት" በሚል ይጠቁማል።

በጥናቱ ቀሪ 5ቱ ማዕከላት በቂ ሆቴል የለም በሚል ሰበብ ሁሉም ስብሰባ በአንድ ማዕከል መሆን የለበትም ፍትህ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ለ5ቱ ማዕከላት ፍትህ በወሬ ብቻ ለሚያልቅ ከበቂ በላይ የሆነ የክልሉ ሀብት እየባከነ ነው ፍትህ ለውስን የክልሉ ሀብት ብክነት ከፍተኛ መሆኑም ተመላክቷል።

ከጥናቱ በተጨማሪ በጉዳዩ ዙሪያ በክልሉ ሀብት ብክነትና አንድ ማዕከል ብቻ እንዲለማ በርዕሰ መስተዳድሩ ከፍተኛ ፍላጎት አዲሱ ክልል በቅርቡ ወደ ለየለት ትርምስና ብጥብጥ ሊያመራ እንደሚችል አንድ የክልሉን ፖለቲካ በቅርበት የሚያወቅ የሚድያችን ተከታይ አስረድቶናል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

ለመሆኑ ሀሉንም በክልሉ የሚገኙ ህዝቦችን በእኩል ለማገልገል ቃል ገብተው ኢፍትሀዊነትንና የአድልዎ አሰራርን በመዘርጋት የህዝቦች አደራ ክደው የአንድ አከባቢ ርዕሰ መስተዳድር ለምን ሆኑ? ...
Read more on our official website
https://wolaitatimes.com/?p=5259

Wolaita Times

21 Dec, 14:32


የኦሮ-ማራ ጥምረት በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ያመጣው ቀውስ

ከዚህ በኃላ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማስተካከል አልረፈደም ? ምናልባት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት ጠልፈዉ የራሳቸዉን አላማ የሚያስፈጽሙ ኃይሎች ይኖሩ ይሁን ? ይሄ መንግስት የኦሮሞ መንግሥት ነው ማለት ይቻላል ? የትግራይ እና የዎላይታ ግንኙነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዴት እንደ ስጋት ታያቸው ? የኦሮ-ማራ ጥምረት በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ያመጣው ዳፋ እንዴት ይለካል ? በርካቶች እንደሚሉት የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ዳንኤል ክብረት ምክር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ስጋት እየፈጠረ ነውን ? ...... የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ያልተመለሱ ሀገራዊ ቀጠናዊ ጥያቄዎች ምላሽና ቁምነገሮችን ይዟል፤ ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ 👇

ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀ ታሪካዊ ጥንቅር ነውና በትዕግሥት እንድታነቡ እንጋብዝሃለን🙏

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ከለዉጡ በኃላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ስር የቀድሞ ደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ክልል ሕዝቦች፣ አመራሮች አሰላለፍ ምን ይመስላል ? እዉን ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ዎላይታን ስልጣን ከመያዛቸውም በፊት ይጠላሉ ? አሁን ኢትዮጵያ ለገባችበት ዉድቀት ሆነ ለዎላይታ ሕዝብ መገፋት የደቡብ አመራሮች ሚና ምንድነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሚያ ሰው ናቸው፣ እንደሚታወቀው ደግሞ በታሪክ አርሲና ጅማን ብንወስድ እንኳን ከዎላይታ ጋር ነገስታቶቻቸዉ በሰላም ለመኖር ልጆቻቸዉን ይድሩ ነበር። ከዛም መለስ ሲል ከሜጫና ቱለማ ማህበር ጀምሮ አብረዉ የሚታገሉ በመሆኑ አንዱ ለአንዱ ትግል እዉቅና የሚሰጡና አብሮ የመሥራትም ሆነ የመኖር ችግር የሌለበት ነው ማለት ይቻላል።

ለዚህ ማሳያዉ በኦሮሚያ የሚገኙ ዎላይታዎች ብዛት ነው፥ በዎላይታም ብዙ ኦሮሞዎች ይገኛሉ። ሕዝቦቹ በኢኮኖሚ ትስስር የተጋመዱ በብዛት የተጋቡና የተዋለዱ ናቸው። ለዛም ይመስላል አንድ ከኦሮሚያ የሚመጣ ሰው ከመሬት ተነስቶ ዎላይታን ይጠላል ብዬ የማላስበዉ። በነገራችን ላይ በአዋሳ እና አካባቢዉ በዎላይታ ተወላጆች ላይ ጥቃት በደረሰበት ወቅት ተፈናቃዮችን ሲጎበኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልቅሰው ነበረ።

ከዛን ጊዜ ጀምሮ በሐገሪቷ ከፍተኛ ትርምስ ነበር በየቦታው፣ በዚህ መሐል ቦታ ያገኙ የደቡብ አመራሮች የዎላይታ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መዉጋት የሚፈልግ፣ በሕወሓት የሚላክ፣ ጥያቄዎች የሚያነሳው ችግሩን ለመቅረፍ ሳይሆን ለዉጡን ለማደናቀፍ እንደሆነ እየተደረገ መረጃ ይሰጣቿል።

ታሪክ እየተጣመመ፣ መረጃ በተንኮል እየተቀመረ ይሰጣቿል። ለምሳሌ የዎላይታ ሐገር ሽማግሌዎች ሶስቴ ከቤተመንግስት በር የተመለሱት በዚሁ የደቡብ ሊህቃን ሕወሓት ነው የሚልካቸዉ በሚል ተንኮለኛ የሐሰት መረጃ ነው። እነኝህ በራሳቸዉ የማይተማመኑ insecure የደቡብ አመራሮች የዎላይታ ተወላጅ ከመጣ ያገኘነዉን ቦታ እናጣለን፣ አስፈላጊነታችን ያቆማል ብለዉ ያስባሉ።

እናም ሕዝቡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ስጋት እንደሆነ አድርገዉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባሉ፣ ለምሳሌ የዎላይታ ሕዝብ የሕወሓት፣ የሸኔ እና የፋኖ ተላላኪ ተብሎ ሶስት የተለያዬና የተራራቀ አላማ ካላቸዉ ኃይሎች ጋር እንዲፈረጅ አስደርገዋል። የዎላይታ ሕዝብ የሚያደርገውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመጥላት እንደሚያደርግ አድርገዉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባሉ።

በዋናነት ከዚህ የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ስለ ዎላይታ ሕዝብ ትክክለኛ ግምገማም ሆነ አመለካከት ያላቸዉ አይመስለኝም። ለሐገሪቷ ዉድቀት ደግሞ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ አካላት እነዚህ የደቡብ አመራሮች ይጠቀሳሉ፣ ምክንያቱም ከዎላይታ Phobiaቸዉ ተነስተዉ ከሚያቀርቡት በተንኮል የታጨቀ መረጃ ባለፈ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግምባሩን ከማንበብና መስማት የሚፈልገዉን ከመናገር የዘለለ ሚና የላቸዉም፤ የሚጠቅመዉ ግን ጠቅላይ ሚኒሰትሩን ሞግተው ሐሳብ እስከማስቀየር የሚደርስ ሰው ቢኖር ነበረ።

የደቡብ አመራሮች በዚህ ሁሉ ዉጥቅጥ ዉስጥ ፈሪ፣ አስመሳይ፣ በራሳቸዉ የማይተማመኑ፣ ተንኮለኞች፣ ግምባር አምባቢዎች፣ አቅመቢሶች በመሆናቸዉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙሪያ ላይ ከሚሆኑ ባይኖሩ የተሻለ ነው። ሌላዉ ከደቡብ አሁን ብልጽግና ዉስጥ ያሉ አቅም ያላቸዉ ግን ተገቢ ቦታ የተነፈጉ የሲዳማ፣ የስልጤ፣ የጉራጌ፣ የሐዲያ፣ የከምባታና የሌሎችም አመራሮች እንዳሉም መዘንጋት የለብንም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ይሄ መንግስት የኦሮሞ መንግሥት ነው ማለት ይቻላል ? ያልተመለሰ የኦሮሞ ጥያቄ የለም እነ ዳንኤል ክብረት የሚሉትን እንዴት ታዬዋለህ ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አየህ ይህ መንግስት የኦሮሞ አይደለም። ከጥንስሱም ኦሮ_ማራ በማለት የተዋቀረ ነው፣ ሐገሪቷን ለዚህ ሁሉ ቀዉስ የዳረጋትም በግምባር ቀደምትነት ይሄዉ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ መብት የሚከበረው ከብሔሮችና ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ መሆኑን ከእነ ጀግናዉ ባሮ ቱምሳ ጀምሮ የተናገሩት ሐቅ ነው። አሁን ኦሮሞዎችን ከፊት በማድረግና የተወሰኑ ጥያቄዎቹን በመመለስ፣ የተቀሩ ጭቁን ብሔሮችን ለዘዉድ ናፋቂዎች ቅዥት አሳልፎ የመስጠት አካሔድ ነው ያለዉ፣ ጫና ለማሳደርም የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ቅስቀሳ እንዲደርስበት እየተደረገ ይገኛል።

ዳንኤል ክብረት የዘዉድ ናፋቂነት መሰሪ አላማዉን ከጀርባ ሆኖ እያስፈጸመ ስለሆነ፣ ለዛ ነው በኦሮሞ መደበቅ የሚፈልገዉ። ሲጀመር ይህ ግለሰብ የትግራይን ሕዝብ እንደ ታዝሜኒያ (ከደቡብ አዉስትረሊያ ጥቂት ሰዎች ሲቀሩ የጠፋ ሕዝብ)፣ ለማጥፋት የሚመኝ ከንቱ ሰው ነው።

አንድ ድሮ የሮም ነጉስ ነበረ ካሊጉላ የሚባል ሰው ተናዶ፣ "ምን አለ የሮም ሕዝብ አንገት አንድ በሆነና በቀነጠስኩት" ብሏል ይባላል። ዳንኤል ክብረት ኢትዮጵያዊዉ ካሊጉላ ነው። ይህ ሰው ስለትግራይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤናማ ነገር ያማክራል ማለት እብደት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለትግራይ በትግራይ ሰዉ ጋር ነዉ መመካከር ያለበት። ሌላዉ ይህ ግለሰብ አሁን ኦነግ፣ በኦነግነቱ አያስፈልግም የሚል ለሕዝቡ እኔ አዉቅልሐለዉ የሚል መሰሪ ጸረ ዲሞክራሲያዊ አቋም ያለዉ ሰዉ ነው።

ግለሰቡ ስለዎላይታም አጠቃላይ ስለብሔሮች መብትም ጥሩ አመለካከት የለዉም። እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐገሪቷን ወደ ሰላም መመለስ ከፈለገ፣ እነኝህንና የመሳሰሉ ሰዎችን ከዙሪያዉ በማራቅ፣ ቀናነት፣ እዉቀትና ሕገመንግሥታዊ አመለካከት ባላቸዉ ሰዎች መተካት አለበት።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት ታዋቂዉ ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንደሚሉት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን መንግስት ጠልፈዉ የራሳቸዉን አላማ የሚያስፈጽሙ ኃይሎች አሉ ብለዉ እርሶም ያምናሉ ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በትክክል የእርሳቸዉን ሐሳብ እጋራለሁ። በነገራችን ላይ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከአገዛዙ ጋር ከሰላማዊ መድረክ ልዩነት እስከ ጫካ የዘለቀዉ ልዩነታቸዉም ላይ የኦሮ_ማራ የተቃወሰ የፖለቲካ አካሄድ አንዱ ምክንያት ነው። ይህ መንገድ ልክ ካለመሆኑም በተጨማሪ የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅምና መብት በዘላቂነት አያስጠብቅም ነው የሚሉት። በትንሹ የትግራይን ጦርነት ኦነግና ኦፌኮ አልደገፉም ይህ የኦሮሞ ሕዝብ ጦርነቱ አይጠቅመዉም ብሎ ከማመን የሚነሳ ነው።

Wolaita Times

21 Dec, 14:32


ጦርነቱን የፈጠሩ ኃይሎችን ክፉ አላማ ከመገንዘብ የሚነሳ ነው፤ ኢዜማና አብን ግን ከድጋፍ አልፈዉ ዘምተዋል። ይሄ ማለት ግን የኦሮሚያ ብልጽግና ከደሙ ንጹ ነው ማለት አይደለም፣ አምነዉበት እንጂ ምንም ተገደዉ የሚወስኑት ዉሳኔ የለም፣ አንዳንዴ የጠለፈዉ ማነዉ የሚያስብሉ ጉዳዮችም አሉ።

በዚህ መሐል ግን አሁንም የደቡብ አመራሮችን፣ ቦታ ይዘዉ ከዎላይታ ጥላቻ አንጻር ብቻ እየቀመሩ እና ኦሮ_ማራ ምን ብንል ይደሰታል እያሉ የሚያደርጉት ተንኮለኛ ተሳትፎ ሚናዉ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሁሉ ዉድቀት የዳረጉ አማካሪ ተብዬና አመራር ተብዬዎችን በጥልቀት በመገምገም የአቅጣጫና አካሄድ ለዉጥ ማድረግ አለበት። እስካሁን የተመጣበት መንገድ አያዋጣም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ከዚህ በኃላ አልረፈደም? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእንግዲህም እድል አላቸዉ ብለህ ታምናለህ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በሚገባ እድል አላቸዉ። ወደ ሕገመንግሥታዊዉ መንገድ መመለስ ነው፣ የተገፉ ሕዝቦችን ጉዳይ በአንክሮ ማጤን ነው። አጨብጫቢ ብቻ ሳይሆን ሞጋች ሰዎችን ቦታ እንዲይዙ ማድረግ ነው። መንግስት በግልጽ ወደ ሕገመንግሥታዊዉ አቅጣጫ ከተመለሰ ሐገሪቷም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም ተስፋም እድልም አላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈረሙትን የፕሪቶሪያ ስምምነት ይተግብሩት፣ ከሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ጋር ሕገመንግሥቱን ያከበረ የሰላም ስምምነት ለመፈራረም ቁርጠኛ ይሁን። ምርጫን አይፍሩ በየትኛውም ክልል ሕዝቡ የፈለገዉን እንዲመርጥ ይፈቀድለት፣ በተለይ ብልጽግና ቅሬታ ያላቸዉን ሕዝቦች ጉዳይ በድጋሚ ይመርምር።

በነገራችን ላይ አሁን ሁሉም ነገር ያበቃለት የሚያስመስሉ ኃይሎች አንደኛው፣ ሕገመንግሥቱን መናድ የሚፈልጉ ሲሆኑ፣ ሁለተኞቹ ደግሞ ሐሳባቸዉ ተሞክሮ የከሸፈባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ከቀየረ ተረሳን፣ አስታዉሱን ባዮች ናቸው። ኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ያላት ሐገር ነች፣ ሕገመንግሥቱ በተከበረበት ምንም መነጋገር ይቻላል፤ ከዛ ዉጪ የትም አያደርስም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromo

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን። 👇
Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5252

Wolaita Times

20 Dec, 18:42


"ከዚህ በፊት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን እንጨርሰዋለን እኛ አንድ ነን ደግፉን" የዎላይታ ዞን አስተባባሪ አካላት ተማፅኖ

በወቅታዊ ጉዳይ የዎላይታ ዞን ስራአስፈፃሚ አካላት በዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በኩል ማምሻውን መልዕክት እንደሚከተለው አውጥቷል።

"የዎላይታ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የዉስጥ አንድነቱን በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ እየሰራ ነው፡፡

በዞኑ ያሉ እምቅ ፀጋዎቻችንን እና ትልቁን የህዝብ አቅም በማቀናጀትና በማስተባበር በየደረጃው ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለመፍታት የወላይታ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አንድነቱን በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ በፊት ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሰሩ የቆሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጤን በየደረጃው ካሉ የተለያዩ አካላት ጋር በተደጋጋሚ በመወያየትና ማነቆዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመፍታት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት ለማጠናቀቅ እና ከህዝቡ የሚነሱ አንገብጋቢና መሠረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል የአመራር ሥምሪት በመስጠት ሁሉንም ተግባራት በዉጤት ለማሳጀብ የተጣለባቸዉን ታሪካዊ ኃላፊነት በሙሉ ቅንነትና ታማኝነት እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሴራ ፖለቲከኞች፣ ተናጠላዊ እውነቶች ላይ የቆሙና ተሻግረው የመመልከት አቅም የሌላቸዉ ተቸንካሪ ግለሰቦች በዞኑ አስተባባሪ አካላት ውስጥ አንድነት እንደሌለ በማስመሰልና የአመራር ሥምሪት ጋር በማያያዝ ጥላቻ ላይ የተመሠረቱ ሀሰተኛና የተቀነባበሩ መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ።

የአመራር ስምሪት በፓርቲዉ መመሪያ መስፈርት መሰረት የህዝብ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ማዕከል በማድረግ በየምዕራፉ የተግባር አፈፃፀም ዉጤታማነት፣ ግምገማና ምዘና ሂደትን ተከትሎ የሚፈፀም እንጂ በግለሰቦች ፍላጎት የተመሠረተ አይደለም፡፡

ስለሆነም በየማህበራዊ ሚዲያዎች ጭንብል አካውንቶችን በመክፈት የበሬ ወለደ እንቶ ፈንቶ መረጃን የሚያራግፉና ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከእኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የዞኑ አስተዳደር እያሳሰበ ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆኑ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑንም በጥብቅ ያሳስባል፡፡

የተከበረዉ የዎላይታ ህዝብም ለሀሰተኛ በሬ ወለደ ተረቶች ጆሮን ሳይሰጥ የተጀመሩ የተለያዩ የልማት ተግባራት ከግብ እንድደርሱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ይጠይቃል ሲል በዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በኩል ማምሻውን መልዕክት አስተላልፏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion

Wolaita Times

20 Dec, 12:58


የዲቻ መለያ በመልበስ "የጋሞ ሕዝብ ሞራል ነክታችኋል" በሚል እየታሰሩ ነው

በቁጫ የዎላይታ ዲቻ መለያ በመልበስ የጋሞ ሕዝብ ሞራል ነክታችኋል" በሚል በርካቶች እየታሰሩ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "የዎላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ መለያ ልብስ ለብሳችኋል፣ የጋሞን ሕዝብ ሞራል ነክታችኋል" በሚል ለጋሞ ሕዝብ መብት እንቆረቆራለን የሚሉ የአርባምንጭ ባለስልጣናት የሚያስተባብሯቸው ቡድኖች በቁጫ ሕዝብ መዋቅሮች ውስጥ በሚደግፉት የስፖርት ክለብ ምክንያት ብቻ የማሰር፣ የመደብደብና ከቤት ንብረት የማፈናቀል ዘመቻ ጀምረዋል" ሲል የቁጫ ህዝብ ደሞክራሲያዊ ፓርቲ አብራርተዋል።

ፓርቲው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ "በርካታ ወጣቶች ከእነ ማሊያቸው ተይዘው ልብሶቻቸውን አስወልቀው ራቁታቸውን እንዲቀሩ በፖሊስ በማስገደድ የለበሱትን ማሊያዎች ነዳጅ አርከፍክፈው ሰው በተሰባሰበበት የማቃጠል እርምጃ ወስደዋል" ብሏል።

"የአንድ ክለብ ደጋፊ መሆን አለመሆን ግለሰባዊ መብት ነው። የእኔን ክለብ ካልደገፍክ ብሎ ማስገደድ የትም የለለ ነው። ክለብህ ውጤታማ ሲሆን ስፖርት ይጣራል፤ ብዙ ደጋፊም ይኖርሀል። ስፖርት አለምን ባስተሳሰረበት በምንኖርበት ሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የራሱን ማንነት በታላቁ ቁጫ ህዝብ ቁጫዊ ማንነት ካልጫንኩ በሚለው እና የዛን አከባቢ ገፅታ እያበላሸ የቆየው በሁሉም ዘንድ የሚታወቀው ጎጠኛ ፅንፈኛ ቡድን እያከናወነው ያለው ይህ ተግባር ህገወጥ እና እጅግ አሳፋሪ ነው። ሸፍጡ የህዝቦችን ፖለታካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ለማቋረጥ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም እኛም ስንታገለው እና ስናጋልጠው የቆየነው ጉዳይ ነው" በሚል ጠቁሟል።

"ዋናው ዓላማቸው ግን ከስፖርት ዘለል ያለ መሆኑን ልብ ይሏል። ይኸውም ታላቆቹን የቁጫን እና የዎላይታን ህዝቦች በደም፣ በአጥንት፣ በጀግንነት እና በታላቁ እና ህያው ታሪካቸው ያላቸውን አንድነት ለመበጣጠስ የሚያደረጉት የቆዬ የጥላቻ ዘር ፍሬ በመሆኑ በዜጎች እና በአጎራባች ሕዝቦች ላይ ፀረ-ሰላም አጀንዳዎችን በመፍጠር አከባቢውን የስጋት ቀጠና ለማድረግ የሚደረገውን ሀይ ባይ ያጣውን ፖለቲካዊ ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል።

ሰሞኑን በቁጫ ወረዳ የዎላይታ ዲቻ መለያ ለብሳችኋል በሚል ከታሰሩት 72 ወጣቶች ጋር በተያያዘ፤ ለሚዲያ ዘመቻ መረጃ ስታቀብሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች ያለ በቂ ምክንያትና ያለ ፍ/ቤት እውቅና፤ በአመራሮቹ ትዕዛዝ መሰረት እየታፈሱ መሆኑን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከአከባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል።

ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውና በቤተሰብ እስካሁን ያልተጎበኙ መሆናቸውን ጭምር እየወጡ ባሉ ተጨማሪ መረጃዎች መሰረት ለማረጋገጥ ተችሏል።

የሠላምበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ጭምር በስራ ገበታ በማስተማር ሂደት ላይ እያሉ ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት በተማሪዎች ፊት ተይዘው ወደ ሠላምበር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንም ለማረጋገጥ ችለናል።

ይሄንን በዞኑ በየጊዜው በዞኑ በተደራጀ ሁኔታ የሚፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከትሎ በርካቶች በአከባቢው ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምሯል።

እነዚህ የጋሞ አባቶች አይደሉም ሚዲያ ጠርቶ በዎላይታ ላይ የጥላቻ መግለጫ ስሰጡ የነበሩት? 300 የሚደረስ ሰው ሸራ በተባለ አከባቢ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት የተጨፈጨፉት ?

ከ400 በላይ ትግራዋይን ምዕራብ አባያ አከባቢ ከታሠሩበት አውጥቶ የረሸነው የጋሞ ወጣትና አባቶች አይደሉም?

ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ለመግባት ለመወጣት የሚሸማቀቁባት (የዲቻ መለያ ለብሰሃል ተብሎ የምታሰርባት) አርባምንጭ ከተማ ላይ እነዚህ አባቶች ምን ሰሩ? ሰላም ስላሳጡ ነው? የሚል ሙግት እያሰሙ ይገኛሉ።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion

Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=5248

Wolaita Times

19 Dec, 14:37


"ርዕሰ መስተዳድሩ በህገወጥ መንገድ ተቋምን ወደ ሰፈራቸው ሊወስዱ ነው ተባለ"

ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑ ተቋማት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚገኝበት ከተማ እንዲሆን ህጉ የሚያስገድድ ቢሆንም በህገወጥ መንገድ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ ቅድመዝግጅት መጠናቁቀ ተገለፀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢምግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልሉ መቀመጫ በሆነችው ዎላይታ ሶዶ እንዲከፈት የተቋሙ ማኔጅመንት በመወሰን፣ በኦንላን የዎላይታ ሶዶ ስም ከተመዘገበ በኋላ ከነሃሴ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ ለመከራየት እንቅስቃሴ ተጀምሮ እነደነበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

ነገር ግን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጫና ተቋሙ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአርባ ምንጭ ከተማ እንድከፍት ውሳኔ በማስቀየራቸው፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የቀድሞ ስታትስቲክስ ግቢን ለኢምግሬሽን ጽ/ቤት እንዲውል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከታማኝ ምንጭ መረጃው ደርሷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ተጽፎ የወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ እንደሚያመላክተው ማንኛውም ዓይነት ስብሰባ፣ ጉባኤ፣ ስልጠና፣ ፎረም፣ ወዘተ ሴክተሩ/ቢሮው ባለበት ከተማ/ማዕከል እንዲደረግ ቀጭን ትዕዛዝ ተላልፏል።

ሰሞኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ እነ ዶ/ር ቀለሙ ደስታን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ የዎላይታ ተወላጆችን በቢሮአቸው ጠርተው ያናገሩ ሲሆን "በአርባምንጭ ከተማ ልማትና ዕድገት ሕዝባችሁ ለምን ይቀናል፤ የአርባምንጭ ከተማ አመራር በራሳቸው ሀብት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከጀመሩ በኋላ ድጋፍ ስለጠየቁን የክልሉ መንግስት እየደገፈ ይገኛል፣ ነገር የዎላይታ አመራሮች ምንም ሳይጀምሩና ሳይጠይቁን እንዴት ምን እንርዳቸው?" ማለታቸውን ከተሳታፊዎች መረጃው ደርሶናል።

ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑ ተቋማት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚገኝበት ከተማ መከፈት እንዳለበት በደንቡ የፀደቀ ቢሆንም ሕግን በመጣስ በማንአለብኝነት ወደ ሌላ ከተማ ማዛወር ፍጹም ተገቢነት የሌለው አምባገነነዊ አሠራር ማሳያ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት ይሰጣሉ።

ባለፈው ግንቦት ወር 2016 ዓ.ም የኢፌዲሪ ኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ዎላይታ ሶዶ ከተማ ሥራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እንደነበር ይታወሳል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲናዋ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ዓለምአቀፍ አገልግሎቶችን የሚሹ ተገልጋዮች፣ ኢንቨስተሮች፣ ቱርስቶች፣ ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ NGOs፣ ወዘተ የሚያዘውትሩባት ከተማ ሆናለችና ICS አገልግሎት መጀመር ፋይዳው የጎላ ይነገራል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion


Read more on our official website👇
https://wolaitatimes.com/?p=5244

Wolaita Times

18 Dec, 13:40


"ርዕሰ መስተዳድሩ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅ አስከልክሏል" በሚል የሀይማኖት አባቶች ከፍተኛ ቅሬታ አቀረቡ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የአቶ ጥላሁን ከበደ የፖለቲካ ሴራና ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት እየከፋ መምጣቱንም አባቶቹ ጠቁመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከአባ አልያስ የጋሞ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስርና ሀይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅና ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ማስከልከሉን የሀይማኖት አባቶች አክለው ተናግረዋል።

"ጠያቂ ያጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ሀይማኖታዊ መንግስት ምስረታ ብዙዎችን ለእስራትና ለእንግልት እየዳረገ ነው" ሲሉም ቅሬታ አቅርቧል።

"በከፋፋይነትና ከፋፍሎ በማጋጨት ስልጣን ላይ መቆየት እንደምቻል እንደሚያምኑ የሚገለፅላቸው አቶ ጥላሁን ከበደ በክልሉ ውስጥ የምኖሩ ህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራት ጥርጣሬና መከፋፈል ከፈጠሩ በኋላ ፊቱን ወደ ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት አዙሯል" ሲሉ አንዳንድ የአከባቢው ኦርቶዶክስ ሀይማኖት እምነት አባቶችና ተከታዮች ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በእያንዳንዱ ዞን አጀንዳ በመወርወር ዞኖችን እርስበርስ እና በውስጣቸውም አንድ እንዳይሆኑ ቡድኖችን በማደራጀት ለክልሉ ህዝብ ዕዳ መሆናቸውን በርካቶች እንደሚያውቁ ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወቃል።

"በዚህም አላማቸው እንደተሳካ በደስታ ስገልፁ ነበር። አገላለጹን በብልጽግና ፓርቲ ሽፋን አደረጉት እንጅ" ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

"በቀጣይ ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነትን በማስፋፋት ኃይማኖታዊ ግጭትን በመቀስቀስ ክልሉን ለመበተን እንደቁልፍ አጀንዳ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛልም" ብሏል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ እምነት የቀድሞ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብኬት የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ምዕመናን ባነሱት ጥያቄ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥያቄውን ተቀብሎ በሁለት ሀገረ ስብኬቶች እንዲደራጁ በ2016 ዓ.ም ወስኗል።

"ሆኖም በፎቶ መመልከት እንደምቻለው አቶ ጥላሁን ከበደ ከአባ አልያስ የጋሞ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስርና ሀይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅና ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት አስከልክሏል" በሚል የሀይማኖት አባቶች ቅሬታ አቅርቧል።

እነዚህ የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ጥያቄአቸውን በመያዝ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አቤት ለማለት ሲንቀሳቀሱ አቶ ጥላሁን ከበደ ለክልሉ ፖሊስ ቀጥታ ትዕዛዝ በመስጠት ምዕመናን መንገድ ላይ በማገት በበረሃ በረሃብና በውሀ ጥም እንዲቀጡ ማድረጋቸውንም በቅርቡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መዘገቡ የሚታወስ ነው።

"አቶ ጥላሁን ከበደ ዘርፈብዙ ብልሽቶችን ያለ ከልካይና በማን አለበኝነት የሚፈጽመው ለግል ጥቅምና ለቡድኑ የፖለቲካ ሴራ ስኬት እንጂ ለብዙሀኑ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው" ስሉ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ጠቁመዋል።

"በዚህ ግለሰብ ቅጥያጣ ብልሽት ክልሉ ወደ አላስፈላጊ ግጭትና መከራ ሳይገባ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ማበጀት አለበት" በሚልም ጥሪ አቅርበዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion


Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5237

"ርዕሰ መስተዳድሩ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅ አስከለከለ"

Wolaita Times

25 Nov, 13:30


"የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በብልፅግና ፓርቲ ሳይሆን በሰፈር ገዥዎች እየተመራ ነው" - ከፍተኛ ባለስልጣናት

"ክልሉ የፓርቲዉን 5ኛ ዓመት ጀምሮ ባጠናቀቃቸዉ ፕሮጀክቶች ሳይሆን በፈጻማቸዉ የሚድያ ኩኔቶችን በባህላዊ ልብስ በማታለል ለማክበር እየተዘጋጀ ነው" በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

"ብልፅግና ፓርቲ ሲመሰረት ከመከፋፈል እና ከአግላይ የፖለቲካ እሳቤ የወጣ አካታች፣ ሚዛናዊ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያፀና ለኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ የሰነቀ እንደሆነ ይታወቃል" ሲል ይጀመራል፡፡

አከለውም ፓርቲው ኢ-ፍትሀዊነት፣ አግላይነት፣ የነጠላ ትርክት የበላይነትና ሌሎች ችግሮችን በሀሳብ ልዕልና ለመፍታት በፅኑ መሰረት ላይ የጣለ እንደነበር ገልጿል።

ያልተገራ ስሜትና ፅንፈኝነት የሚገራው፤ ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው፣ የህዝብ ኑሮ የሚሻሻለው፣ ብሔራዊ ጥቅም የሚከበረው፣ የጥራትና የኢፍትሀዊነት ችግሮች የሚቀረፉት፣ ማህበራዊ ፍትህ የሚነግሰው በሀሳብ ልዕልና ብቻ እንደሆነም የሚያምን ነበር ይላል።

"በዚህም እንደ ሀገር በፈተና ዉስጥም የብልፅግና አመራሮች በሚያወሩት ልክ ባይሆንም ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ የፓርቲዉ ሊቀምበርና የሀገርቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በቁጥር ጥቂት አመራሮች ጋር የሀገርቷን ዕምቅ አቅም ከችግሮቿ በላይ በመመልከት ለብልፅግና እየተጉ እንደሚገኙ ለማንም ያልተደበቀ ሀቅ ነዉ" በሚል ያብራራል፡፡

"ሆኖም ግን ለዉጡን ከልብ ያልተቀበሉና በዉስጣቸዉ ላይ ነግሶ የቆየዉን ክፋትና ሰሬኝነት ማሸነፍ ያቃታቸዉ የራሱ የፓርቲዉ አመራር ለዉጡ የሰነቀዉን ግብ እንዳያሳካ አድርጎታል፡፡ የለዉጡ ትሩፋት ዉጤት እና የእዉነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ማሳያ ከሚጠቀሱት ክንዉኖች አንዱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ነበር" በማለትም ያስታውሳል።

"ይህ አደረጃጀት የህዝቦች የዘመናት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ቀስ በቀስ ይፈታል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ብሆንም በአንድ ዓመት ቆይታዉ ለህዝቦቿ ተጨማር ዕዳ እየሆነ ይገኛል" በሚል ሁኔታውን ይገልፃሉ፡፡

"የፓርቲዉን ምሶሶዎችን በተጻረረ መልኩ በተላይም መከፋፈልን እና አግላይ የፖለቲካ እሳቤ የወጣ አካታችነትን፣ ሚዛናዊነትን እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት ከማፅናት ይልቅ በተቃራኒዉ ቅመኝነት፣ በቀለኝነት፣ ቡድንተኝነት፣ ኢ-ፍትሀዊነት፣ አግላይነት፣ የየአካባብዉ ገዥነትና የነጠላ ትርክት የበላይነት ወዘተ የነገሰበት ክልል መሆኑንም በማስረጃ አረጋግጧል፡፡

ለማሳያነት፡- ዎላይታ ዞን ከ40 ዓመት በላይ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ ራሳቸዉ አባት እርሻ ማሳ ከአንዱ ስልጣን ወደ ሌላ ስልጣን በሚሽከረከሩ በአቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ እና በአቶ ገብረመስቀል ጫላ ዘመዶችና ጎሳዎች በተፈጠረዉ አደረጃጀትና ይሄን በሚቃወም ቡድን እየታመሰች ይገኛል ይላል መግለጫው፡፡

በተላይም ለቀጣይ የፓርቲ ጉባኤ ላይ የፓርቲዉ የሥራ አስፈጻም ኮሚቴ አባል ለመሆን ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ አድስ የአመራር አደረጃጀት በማዋቀር በየፍናዉ ሩጫ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋሞ ዞን በማንነት ቀዉስ ዉስጥ በሚገኝ በአቶ ጥላሁን ከበደ በሚመራ ቡድንና እዉነተኛ ጋሞዎች እኛ ነን በሚል ፍልምያ ዉስጥ ዉስጡን እየተናጠ ይገኛል፡፡

ጋሞነት እንደ አየር ሁኔታዉ የሚቀበሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በአሁናዊ ሁኔታቸዉ የጋሞ ልማት አርበኛ ነኝ ነጠላ ዜማ በኔትዎርካቸዉ አማካይነት እንድዘመር እያደረጉ በመሆናቸዉ ድል የቀናላቸዉ ይመስላል፡፡

ጌድኦ ዞን በአቶ ጥላሁን ከበደ ተላላክ በሆነዉ በአቶ ሃይለማሪያም ተስፋዬ የሚመራዉ ቡድን ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን የማጥፋት ሴራ ላይ ተጠምዷል፡፡

የቀድሞ ደቡብ ኦሞ ዞን በአሁኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዓለማየሁ ባዉድ በሚመራዉ ሰሬኛ ቡድን እና በአቶ ንጋቱ ዳንሳ በሚመራዉ ሚዛናዊ እይታ ባላቸዉ ቡድኖች ትግል ላይ ናቸዉ፡፡

ጎፋ ዞን ደግሞ በአቶ ጥላሁን ከበዴ የሴራ ልጅ በሆኑት በአቶ አክልሉ አዳኝ በሚመራዉ እና በእሱ በተገፉት የህዝብ ቅቡልነት ባለባቸዉ ወጣት ቡድኖች እየተናጠ ይገኛል፡፡

ኮንሶ ዞን ደግሞ በአቶ ጥላሁን ከበዴ ቀኝ እጅ በሆነዉ በአቶ ዳዊት ገበየሁ ሰሬኛ ቡድን እና በአቶ ሃልጋዮ ጅሎ በሚመራዉ ቡድን በየቀኑ የሰዉ ህይወት እየበላ ይገኛል፡፡

ሌሎች ቀሪ ዞኖችም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በሚደገፉ ትናንሽ ገዥዎች እጅ ወድቀዋል፡፡ በአጠቃላይ ክልሉ በብልፅግና ፓርቲ ሳይሆን በሰፈር ገዥዎች እየተመራ በመሆኑ ከሴራ ፖለቲካ ዉጭ እዝም እዛም በግለሰብ ደረጃ ከተሰሩ የልማት ሥራዎች በስተቀር በለዉጡ መንግስት ተጀምሮ የተጠናቀቁና እየለሙ ያሉ የልማት ዉጤቶችን ማሳየት አዳጋች አድርጓል" በሚል ያብራራሉ፡፡

በተቃራኒዉ የዜጎች ህገ-ወጥ እስራት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ ዕድል ሙሉ በሙሉ የተከለከለበት ክልል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡

ስለሆነም ክልሉ በአንድ ዓመት ቆይታዉ በአሰራርና በተቋም ሳይሆን በግለሰቦች ፍላጎትና እነዚህን ፍላጎቶችን ህጋዊ ለማስመሰል በተደረጉ የመድረክ ድስኩሮችና በሚዲያ ፖለቲካዎች ተጠማምደዉ ሰንብቷል፡፡

በመሆኑም "ክልሉ የተግባር ሳይሆን የሚድያ ክልል ስለሆነ የፓርቲዉን 5ኛዉን ዓመት የምስረታ በዓል በተደራጀ መልኩ ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ከማድረግ ይልቅ በ6ቱ ማዕከላት በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሳይሆን በባህላዊ አልባሳት ባሸበረቁ ኩኔቶች ኦዲት ዉጤቶች ዙርያ በ16/3/2017 ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል" በሚል ጠቁመዋል፡፡

ከምንም በላይ የሚያሳዝነዉ የለዉጡ ባለቤት በነበሩ ህዝቦች ይሁንታ የተመሰረተዉ ክልል በራሱ የፓርቲዉ አመራር ለዉጡ በመቀልበሱ ምክንያት የዳር ተመልካች መሆኑ ነዉ፡፡

የህዝቡ የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ የሚመለሰዉ መቼ ይሆን? ይህ የድብብቆሽ የሚዲያ ፖለቲካ ማብቂያዉ መቼ ይሆን? ይህ “የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ክልል” በሚዲያ ብቻ የሚናዉቀዉን በተግባር የሚናየዉ መቼ ይሆን? ብሎ ይጠይቃሉ። #Ethiopia #southethiopia


..... ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5140

Wolaita Times

24 Nov, 13:36


"ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዎላይታን ወግነዋል በሚል በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና እየደረሰበት ነው"- ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራር

"አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የዞኑ አስተዳደር ባለወቀበት መንገድ የምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ቤት እንዲታሸግ አድርጓል" በሚል አንድ የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን አድርሷል።

በየጊዜው በዞኑ ህገወጥ ተግባር እየፈጸመ እንደሆነ ያስረዱት እኚሁ የመረጃ ምንጫችን፦ "በሌብነት የፈረጠመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደም የክልል ማዕከል ውሳኔን ለዎላይታ ሶዶ ከተማ ወግነሃል በሚል የጌዴኦ ዞን የቀድሞ አስተዳዳሪን የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ር/መ ማዕረግ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን ከቀበሌ ቤት እንዲወጣ ቤተሰቦቹ ቤት ውስጥ እያሉ የዞኑ አስተዳደር ባለወቀበት በዲላ ከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅና በራሱ ተላላኪ በሆነው የክልል አንድ ቢሮ ኃላፊ በኩል ቤቱ በሰሞኑ ታሽጓል" ብለዋል።

በተጨማሪም "በአቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ የሚመራው የጌዴኦ ፖለቲካ በጥላሁን ከበደ ዘዋሪነት ለጋሞ ዞን ልማት የፈለገውን ገንዘብ ያለካቢኔ ውሳኔ በቅርቡ 60 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ ተሰጥቷል" ሲል ቅሬታ ገልጸዋል።

"የዞኑን ፖለቲካ በሩቁ እንዲከታተል እንኳን እድል ያልተሰጠው ዶ/ር አበባየሁ ለዎላይታ ይወግናል በሚል ብዙ ጫና እየደረሰበት ነው። በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማካኝነት የዲላ ከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅን እና የዲላ ከተማ ብልፅግና ኃላፊን አቶ አብነት አክሊሉን የራሱ ግሩፕ በማድረግ እና ከዞኑ አምስቱንም አስተባባሪዎችን በመያዝ የዞኑ ፖለቲካ በአቶ ጥላሁን ከበደ ፈላጭ ቆራጭነት በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማላጅነት የዞኑ ሀብት ህዝቡ እንዳይጠቀም በማድረግ ዞኑ የብልሽት ምንጭ ሆኗል" ሲሉም ከፍተኛ ባለስልጣኑ አስረድተዋል።

በተለይ በሁሉም መዋቅር በሚባል ደረጃ የአንድ ባች የሆኑትንና በጓደኝነት በጎሣ ትስስር በዘመድ አዝማድ በቀን ምድር ዝርፊያ እየተፈፀመ እንደሆነም ጠቁመዋል።

"የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን ቅጥ ያጣ ወዳጅነት ከአቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ የደቡብ ግብርና ኃላፊ ጋር በመፍጠር የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን ለዎላይታ ወግኗል በሚል ሰበብ የእነ አብዮት ደምሴ የደቡብ ቴክኒክ ሙያ ቢሮ ኃላፊ ለምለም ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ትራንስፖረት መንገድ ልማት ም/ኃላፊ ዘርሁን ማሞ ደቡብ ኢትዮጲያ የፐብሊክ ሰርቪስ ምክትል ኃላፊ የሆኑት የቀበሌ ቤታቸው ሳይነካ በአጠቃላይ የጌዴኦ ተወላጆች በአዲሱ ክልል ሹመት ያገኙት ሁሉ በተለምዶ 70 ቁጠባ በመባል የሚታወቀው የቀበሌ ቤት አላቸው፤ በጥላቻ ብቻ የዶ/ር አበባየሁ ታደሰን የዞኑ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ ባለወቀበት በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬና በጥላሁን ከበደ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ቤቱ መታሸጉ አግባብነት የለውም" በማለት አድሏዊ አሰራርን አጋልጠዋል።

"አቶ ጥላሁን ከበደ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማካኝነት የዞኑን ልማትና በማጓተት ከዞኑ ሀብት እንዲሸሽ የምልጃን ስራ እየሰራ የዞኑ አስተባባሪዎች የሰው ሀገር ልማት እንዲጎበኙ እየተደረገ በራሱ ውሳኔ እንዳይኖረው እየተደረገ ያለው የፖለቲካ ጫና እንዲሁም ጠልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል" ብለዋል። #Ethiopia #Gedio #southethiopia
https://wolaitatimes.com/?p=5135

"ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዎላይታን ወግነዋል በሚል በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና እየደረሰበት ነው"

Wolaita Times

23 Nov, 17:07


እንኳን ደስ አላችሁ 🙌

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ዶክተሬት በዛሬው ዕለት ካስመረቃቸው 120 ዎቹ መካከል 31ዱ የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ያፈራቸው ናቸው።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 67 ወንዶች እና 53 ሴቶች ማለትም 120 ጠቅላላ ሐኪሞችን ለ15ኛው ዙር በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

አጠቃላይ 120 ተመራቂዎች መካከል 31 የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ያፈራቸው የህክምና ዶክተሮች ሆነው ተመርቀዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ 🙌 #Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

23 Nov, 14:27


በዚህ የዎላይታ ሕዝብ የደቡብ ክልል እንዳይመሠረት የተቃወመ ብቻ ሳይሆን፤ ከተመሠረተም በኃላ ከክልሉ በመዉጣት ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የጠየቀ የመጀመሪያ ሕዝብ ያደርገዋል፤ ጥያቄዉ ምላሽ ባያገኝም።

ማስረጃ ካስፈለገ በወቅቱ ትግሉን የመሩት የሐገር ሽማግሌዎች ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በ2/2/ 1992 ዓ.ም በጻፉት የአቤቱታ ደብዳቤ ላይ የሚከተሉ ሐረጎች ይገኛሉ "...የዎላይታ ብሔር በራሱ መልከዓ ምድር የራሱ አስተዳደራዊ መዋቅር በክልል ደረጃ ...እንዲዋቀር ይፈልጋል።... በሽግግር መንግሥት ወቅት ክልል 9 ተብሎ በአዋጅ ቁጥር 7/84 መሠረት የዎላይታን ብሔር ማዕከል አድርጎ የተዋቀረዉ መዋቅር ብቸኛና ትክክለኛ ፍትሐዊ መዋቅር ነበር።

እናም ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት ሁዋላም ላይ የተነሳዉ የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ቢኖርም፤ ምላሹ እንደዎላይታዉ ሁሉ ክልከላ እንደነበረ ይታወሳል። በነገራችን ላይ የሁለቱም ሕዝቦች ጥያቄ ጠንካራና ሕዝባዊ መሠረት የነበረዉ በመሆኑ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ከህዝቡ ተወካዮች ጋር ቁጭ ብሎ ለመወያዬት እና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ተገዷል።

ለምሳሌ የዎላይታዉ ትግልና ዉይይት ከብሄራችን የሚወክሉን ምሁራን ይሁኑ የሚል አንድምታ ስለነበረዉ፤ በዚህም እድል ካገኙት መሐል አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ባሳዩት የአመራር ብቃትና ባመጡት ለዉጥ እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካሪ ሆነዉ በኢህአዴግ አደረጃጀት፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮችና በመሠረተ ልማት ግምባታዎች ባሳዩት ብቃት የሐገሪቷ መሪ ለመሆን በቅተዋል።

እንደኛው ጭቁን ከሆነዉ ወንድም የኦሮም ሕዝብ ለተገኙት ለእርስዎም ቢሆን ስልጣን ጨብጠዉ ያስረከቡት እርሳቸዉ መሆናቸዉን ማስታወስ ለቀባሪ ከማርዳትም በላይ ነውና ትቼዋለሁ። የሲዳማም ሕዝብ በወቅቱ በአዋሳ ከተማ ከመለስ ዜናዊ ጋር በካሄደዉ ዉይይት የክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ከሲዳማ ዉጪ እንደማይሰጥና አዋሳ ከተማ ላይ የሲዳማ ህዝብ ተጨባጭ demographic change ማምጣት ላይ አተኩሮ ወደፊት ክልል እንደሚሰጠዉ ቃል ገብተዉ ሄደዋል።

ለነዚህ ሁለቱ ክልከላዎች ዋነኛው ምክንያት የኢህአዴግ አደረጃጀት ሁኔታ እንደነበረ ማንም የተወሰነ የፖለቲካ ግንዛቤ ያለዉ ሰዉ ይረዳል። ከኢህአዴግ ምክር ቤት የደቡቡ ደኢህዴን 45 መቀመጫ እንዳለዉ ይታወቃል። እናም ዎላይታ ሆኑ ሲዳማ ደቡብ ታዳጊ እንዳይባል ካደረጉ ህዝቦች ግምባር ቀደም ናቸዉ፣ ክልል ቢሆኑ ታዳጊ ናችሁ ከእንግዲህ ቢባሉ ይቀበላሉ? ኢህአዴግስ 45 መቀመጫ እናንተም ያዙ ብሎ ይሰጣቸዋል ?

ወንበሩንስ ቀንሶ ከሰጣቸዉ ትግራይስ እንዴት 45 መቀመጫ በህወሃት በኩል አገኘች መባሉ ይቀራል ? ይህስ ጉዳይ በቀላሉ ይቋጫል ? ስልጣንስ በክልሎቹ ለተቃዋሚ አሳልፎ መስጠቱን ኢህአዴግ እንደ አማራጭ ይቆጥራል? ክቡርነትዎ ለነኚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ያቅትዎታል ብዬ አላምንም።

እናም ኢህአዴግን ዉህድ ፓርቲ የማድረጉ ስራስ ቀላል ተግባር አለመሆኑስ ይጠፋዎታል ? አሁንስ ብዙ ወገኖቻችንን የበላዉ ጦርነት መነሻ አንዱ ይህ ዉህድ ብልጽግና ሲፈጠር፣ አፈንግጠዉ ከወጡ ኃይሎች ጋር መሆኑስ እንዴት ይጠፋዎታል? ብዬ እጠይቃቸዋለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ አምስተኛው ክልል ሰለተሆነ ብቻ በጀት አይጨመርም፣ ያንኑ የዞኑን በጀት ነው የምናስቀጥለዉ፣ ክልሉ የሚደጉመዉን ያንኑ ብቻ የፈደራል መንግስት ይደጉማል ብለዉ ነበረ ለዚህስ ምላሽዎ ምንድነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህም በጣም ዉሸት ነው። ለምሳሌ ከዎላይታ ዞን ጋር በጣም ተቀራራቢ ሕዝብ ብዛት ያለዉና በጀቱም በትንሹ ይበልጥ የነበረዉ ሲዳማ ክልል ከሆነ በኃላ፣ በ2016 እና በ2017 ዓ.ም በተከታታይ 22.6 እና 23.4 ቢሊየን ብር ሲያገኝ፤ ዎላይታ 7.7 እና 9.6 ቢሊየን ብር ብቻ አግኝቷል። ይህ ልዩነት በዋናነት የዉስጥ ገቢ የፈጠረዉ ሳይሆን ድጎማዉ የፈጠረዉ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደማጠቃለያ የሚሉት ነገር ካለ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እነኚህ ምክንያቶች በአጠቃላይ ዉሸትና ዉሃም የማይቋጥሩ ሊባሉ የሚችሉ ናቸዉ። መንግሥት እነዚህን ችግሮች ቆም ብሎ ቢገመግም ይሻላል። በተለይ በዎላይታ ዞን ከክልል የሚደጎመዉ በጀት በማነሱ፣ ዞኑ ከባድ ችግር ዉስጥ ነው። የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አለመካሄዱ ትልቅ ችግር ሆኖ ቀጥሏል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን። 👇



ለመሆኑ የራሱን መብት ተገቢ ምላሽ አጥቶ ተገዶ በህግ ሳይሆን በከባድ መስዋዕትነት እያረጋገጠ የመጣው ህዝብ ጥያቄ ታፍኖ የሚቀር ይመስልዎታል ?
https://wolaitatimes.com/?p=5131

Wolaita Times

23 Nov, 14:27


መብቱን በህግ ሳይሆን በመስዋዕትነት እያረጋገጠ የመጣው ህዝብ ታፍኖ ይቀራል?

በየጊዜው የራሱን ህገመንግስት ያጎናጸፈውን ተቀዳሚ ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተገዶ በህግ ሳይሆን በከባድ መስዋዕትነት እያረጋገጠ የመጣው የዎላይታ ህዝብ የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ ሳይመለስ የሚተኛ ይመስልዎታል ? ሀገር የነበረ ዞንነቱን እንኳን ታግሎ ያስከበረና በመዋቅር ጭቆና ምክንያት ዘርፈብዙ ስቃይ ውስጥ የሚገኝ ብሄር ቢጠይቅ ኃጢያቱ ሆነ ልክ አለመሆኑ ምኑ ጋር ነው ክቡርነትዎ ? እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽና ቁምነገሮችን ይዘናል፤ ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ 👇

ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀ ጥንቅር ነውና በትዕግሥት እንድታነቡ እንጋብዝሃለን!

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) በዎላይታ ህዝብ ክልልነት ጥያቄ ላይ ክልከላ ባቀረቧቸዉ ምክንያቶች ላይ አስተያዬት እንዲሰጡበት ወድደናል፥ በቅድሚያ ሰላም ነው ፕሮፌሰር?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ሰላም ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። ቀጥታ ወደ ጥያቄዎችህ መግባት ትችላለህ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እሺ አመሰግናለሁ፥ እንግዲህ አንደኛዉ የሕዝብ ቁጥራቸው አምስት ሚሊየን ለማይሞሉ ብሄሮች ክልል መስጠት አያስፈልግም ያሉት ነው። እና በዚህ ምን አሰተያዬት አለዎት ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህ አስተሳሰብ ከሕገመንግስቱ ከቆመበት ፍልስፍና ( Jurisprudence) አንጻር ሲመዘን በመሠረታዊ ምክንያቶች ተቀባይነት የለዉም። ክልሎች የተዋቀሩት አምስት ሚሊየን ሕዝብ እየተሰበሰበ ከሆነ፣ ኦሮሚያና አማራ ወደ ሰላሳ ሚሊየን ሕዝብ ገደማ ያላቸዉ እንዴት ሊኖሩ ቻሉ፣ ለምን ወደ አምስትና ስድስት ክልልነት አልተሸነሸኑም ?

እነ ሐረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አፋርና ሲዳማ 6 ሚሊየን ሕዝብ ሳይኖራቸዉ እንዴት ክልል ሊሆኑ ቻሉ? ማለት የፈለግኩት የሕዝቦች ስነ ልቦና ( ከ political history ይመነጫል በዋናነት) መልከአም ምድር፣ አሰፋፈር፣ ከግምት ሳይገባ በቁጥር ብቻ የሚወሰን ከሆነ ከላይ ያነሳሁት ጥያቄ መልስ ሊሰጠዉ ይገባል። ካልሆነ ለዎላይታ ብቻ ሲሆን ቁጥር መመዘኛ ይሆናል ከተባለ የብሄር ጭቆና ነው። ምናልባት ይሄን ያሉት በጉራጌ ስለነበረ ለጉራጌም ብቻ ይህን ማለታቸዉ ተገቢ አይደለም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሁለተኛው ምክንያት ክልል ለእናንተ አይጠቅምም ብዙ ቦታ ተበታትናቹ ስለምትኖሩ የሚል ነው። ስለዚህ ምን የሚሉት ነገር አለ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይሄኛዉም ትክክለኛ ሐሳብ አይመስለኝም። የአሁኑ ግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር የዛኔ የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ግርማ አመንቴ በ2012 ዓ.ም የጊፋታ በአል ላይ ለኦሮሚያ ክልል በተደረገ ግብዣ መሠረት ተገኝተዉ የመልካም ምኞት መግለጫቸዉን ሲያቀርቡ "በኦሮሚያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ዎላይታዎች ይገኛሉ።" ብለዋል። እርሳቸዉ ፊንፊኔን የቆጠሩ አይመስለኝ።

ዎላይታዎች በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ በሲዳማ፣ በተለያዩ ደቡብ አካባቢዎች፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌና አፋር ክልልን ጨምሮ በመላዉ ኢትዮጵያ ማለት በሚቻል መልኩ በከፍተኛ ቁጥር እንደሚኖሩ ይታወቃል። ተበታትኖ ለመኖሩ ሕዝቡ industrious መሆኑ ብቸኛ ምክንያት ካለመሆኑም ባለፈ ዎላይታ ክልል በመሆኑ የሚያጡት ምንም ነገር ካለመኖሩም በላይ ዎላይታ ክልል ባለመሆኑም የሚጠቀሙት ነገር የለም።

የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ሰርተዉ ሐብት አፍርተዉ የመኖር ሕገመንግስታዊ መብታቸዉ የተጠበቀ ነው። በተመሳሳይ የዎላይታ ዞንም ክልል ሆኖ መደራጀት መፈለጉ ሕገመንግሥታዊ መብቱ ነው። ስለዚህ የዎላይታ ዞን ክልል ቢሆን ከአካባቢው ዉጪ የሚኖሩ ዎላይታዎች በሕገመንግስቱ መሠረት ከተመራን የሚያጡት ነገር የለም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሶስተኛው ምክንያት የሐገሪቷ አቅም (ኢኮኖሚዉ) አይፈቅድም የሚል ነው። ይሄኛዉስ ያስኬዳል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህም መከራከሪያ ዉሃ የማይቋዋጥር ከመሆኑም ባለፈ ሌላ የፍትሐዊ የሐብት ክፍፍል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በመጀመሪያ Budget ድልድል መካሄድ ያለበት ብቸኛ ባይሆንም ዋነኛዉ ምክንያት የሕዝብ ቁጥር መሆኑ እሙን ነው። ኢትዮጵያ ግን ከድሮዉ የደቡብ ክልል ጀምሮ አሁን ከሲዳማ ዉጪ በክላስተር እንዲዋቀሩ የተፈረደባቸዉ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ድህነቷን እንደሚሸከሙ የማህበር አህዮች ነው የምታያቸዉ።

ክልልነትን የተጎናጸፉ ብሄሮች በደቡብ ከሚገኙ ዞኖች የክልል በጀትንም ከግምት አስገብተን ማለት ነው። አንጻር በጀታቸዉ በብዙ እጥፍ መብለጡ ( የሕዝብ ቁጥራቸዉ ተመጣጣኝ አንዳንዴም የዞኖቹ እየበለጠ ) ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ተመሳሳይ ሕዝብ ቁጥር በመያዝ ክልል በመሆን የሚገኘዉ በጀት የበለጠ ከሆነ የትኛውም ብሄር ግልጽ ምክንያታዊና ሕገመንግሥታዊ ክልከላ እስከሌለ ድረስ ቢጠይቅ አይፈረድበትም!

የዎላይታ አይነት ሐገር የነበረ ከጭቆና ብዛት የተነሳ ዞንነቱን እንኳን ታግሎ የተጎናጸፈ ብሄር ቢጠይቅ ትክክለኛ እና ክልልም ከተፈቀደለት ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን የሚያጠናክር ነው። በተለይ የሐገሪቷ አቅም አይፈቅድም የሚለዉ መከራከሪያ ለዎላይታ አይሰራም! ቀድሞ ነገር የትኛዉ የሐገሪቷ ክልል ነው Autonomy ለማግኘት ከዎላይታ የበለጠ ምክንያት አቅርቦ ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚችለዉ? በሽግግር መንግስት እንደኔ እንደኔ ትልቁ ስህተት የነበረዉ ዎላይታ ክልል አንድ አለመባሉ ነዉ!

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶክተር) የክልል ጥያቄ የሚያነሱ የዎላይታ አመራሮችን "ለምን በእናንተ ልጅ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ጊዜ አልጠየቃችሁም" እያሉ አፍ ያስዘጋሉ ማብራሪያም እንዳይሰጡ ፊት በመንሳት ይከለክላሉ የሚል ጭምጭምታም ተሰምቶ ነበረና ለዚህስ የእርስዎ ምላሽ ምንድነዉ ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህ ጥያቄ ጥሩ ጥያቄ ነው። በቀናነት ማወቅ ለፈለገ፤ ግን ማብራሪያን ለመስማት ፈቃደኛ አለመሆን አፋኝነት ነው። እነሆ መልስ፦ የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተመሰረተዉ በ1983 ኢህአዴግ ደርግን አሸንፎ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ባረቀቀዉ የሽግግር ቻርተር ላይ ክልል 9 የነበረዉን ዎላይታን ከሌሎች 55 ብሄሮችና ብሄረሰቦች ጋር በመጨፍለቅ ነበር። በወቅቱ የክልሉን ምስረታ በእነ ወልደአማኑኤል ዱባለ የሚመራዉ የሲዳማ ልህቃን ቡድን፣ እነ ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስም የተቃወሙት ነበር፤ የዎላይታ ተቃዉሞ ግን ከሁሉም የጎላና፣ ታጋዮቻችንን እነ ሰለሞን ሴታን ለእስራትና ለከፍተኛ ድብደባ የዳረገ ነበር።

በወቅቱ ዎላይታን የወከሉ ሰዎች እንደታሰሩም ይታወቃል። በዚህ ምክንያት ታሰረዉ በእስር ቤት የሞቱም እንደነበሩ ይታወቃል። ኢህአዴግ አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) ሲገባ በወቅቱ የተቀሩትን ቋንቋዎች ጥናት አስጠንቼ ነው የምፈቅደዉ የእናንተ ግን የሚታወቅ ስለሆነ ያለጥናት ፈቅጃለሁ ልጆቻችሁንም አስተምሩበት ያለዉ ኦሮምኛ፣ ዎላይትኛ፣ ትግርኛ እና ሲዳምኛ ነበር።

በወቅቱ የተሻለ ዝግጅት ላይ የነበረዉ ኦነግ በኦሮሚያ 1984 ዓ/ም ላይ ሲያስጀምር፣ ዎላይታና ትግራይ 1985 ዓ/ም እንደጀመሩ መረጃዎች ያሳያሉ። እናም እንዲህ በጥዋቱ እዉቅና ያገኘዉን ዎላይትኛ ቋንቋ ለማጥፋት ዎጋጎዳ የሚባል አራት ቋንቋዎችን በመቀየጥ ተፈጥሮ እንዲጫን ሲወሰን ለተቃዉሞ የተነሳዉ የዎላይታ ሕዝብ ካነሳቸዉ ዘርፈ ብዙ እና ዘመን ተሻጋሪ ጥያቄዎች አንዱ የክልል ጥያቄ ነበር።

Wolaita Times

23 Nov, 08:14


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍላጎታቸው ውጪ ያለአግባብ ደሞዛቸው መቆረጡን የተቃወሙ በርካታ መምህራን መታሰራቸው ተገለፀ።

በክልሉ ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ያለአግባብ ደሞዛቸው መቆረጡን የተቃወሙ ከ60 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ሲሆን የመምህራኑ ደመወዝ ከነሐሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ መቆረጥ መጀመሩን እና እንዲመለስላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተከትሎ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የታሳሪ መምህራን ቤተሰቦች ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

ባለቤታቸው መታሰሩን እና እስሩ ከመምህራኑ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለጣቢያው የገለጹ ወ/ሮ አስቴር አበበ "ባለቤቴ ታስሮ ነው የሚገኘው፤ ወረዳው ደመወዛችን ይመለስ ብለን ብንጠይቅም እምቢ ብሎናል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህን ተከትሎ ባለቤታቸውን ጨምሮ የታሰሩ በርካታ መምህራን በፖሊሶች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ያስታወቁት ወ/ሮ አስቴር አበበ በድብደባው ቆስለው እስከአሁን ድረስ ህክምና ለማግኘት የተከለከሉ መምህራን መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በወረዳው መምህር የሆኑት አቶ ወረደ ዋኪሶ በበኩላቸው መምህራኑ ከደመወዛቸው ላይ እስከ 25 በመቶ ያለአግባብ መቆረጡን አስረድተዋል።

በዚህም ምክንያት መምህራኑ አቤቱታቸውን በመምህራን ማሕበር አማካኝነት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት እና ለወረዳው አስተዳደር ቢያቀርቡም "የምታመጡት ነገር የለም፤ እኛ የላክናቸው ካድሬዎች አስማምተው በመጡት መሰረት ነው ደመወዛችሁን የቆረጥነው።" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የሳርማሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጎሹ ጌታቸው የመምህራኑን መታሰር አረጋግጠው "መምህራኑ የታሰሩት ሌሎች መምህራን እንዳያስተምሩ በማሳመጻቸው" ነው ብለዋል። #Ethiopia #southethiopia #ኮሬ

Wolaita Times

22 Nov, 12:02


አስደንጋጭ ከፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ አሰራር በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ !!

ከ 2.4 ቢሊየን የሚበልጥ ሀብት ሕዝብ እንዳያውቀው ተሸሽጓል ምክንያቱ ምን ይሆን

በዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ ያልተደረገበትን የተሸሸገ ሴራ እና ሚስጢር በዛሬው ዘገባችን በትንታኔ እንዳስሳለን።

በስመ ትጥቅ ትግል በኤርትራ በርሃ በነበሩ በነጋ ልጅ ፕ/ር ብርሃኑ አድሮ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የጥልቁ ሸንቁጤ መንፈስ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አዘጋለሁ በማለት ሲጩህ መደመጡን በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የምክክር መድረክ የተሳተፉ የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል።

ወደ ዛሬው ትንታኔ ዜናችን ስንሻገር የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና የማፍያ ስብስብ ግብረ አበሮቹ ዩኒቨርሲቲውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማራቆት ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ባፈነገጠ መልኩ እያካሄዱት ያለውን ብልሹ ተግባር እንዳስሳለን።

ከጥቅምት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ የተመደቡት እና አሁንም ተጠባባቂ የሆኑት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና ግብረ አበሮቹ ዩኒቨርሲቲውን ለማራቆት ከትምህርት ሚ/ር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የተላኩ የማፍያ ስብስብ ስለመሆናቸው እየተነገረ ይገኛል።

ይህ የማፊያ ስብስብ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ገና ስራ በጀመሩበት ማግስት በተናጠል እያንዳንዳቸው ግማሽ ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቅንጡ ላፕቶፕ፣ እስከ 250 ሺህ ብር የሚያወጣ ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁም እስከ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ቅንጡ የውጭ ሀገር ሶፋ ጨምሮ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን በማግበስበስ እንደነበር የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በህግ እና ህጋዊ አሰራር ስም ተቋም የማራቆት ተልዕኮውን የጀመረው ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተደጋጋሚ የተረጋገጠውን የኦዲት ግኝት በማድበድበስ ወንጀልን በመሸሸግ እና ወንጀለኞች ለህግ ተላልፈው እንዳይሰጡ ጥብቅና በመቆም መሆኑን መረጃውን ያጋሩ ግለሰቦች ጥቆማ ሰጥተውናል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 4 ዓመታት ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት አስተያየት ውስጥ ያለፈ ተቋም መሆኑንና ይህንንም በትኩረት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተያየት የሰጡት የመረጃ ምንጮች፤ ዶ/ር ጉቼ እና አዲሱ የማፊያ ስብስብ አመራር ግን የባለፉትን ዓመታት ከፍተኛ የኦዲት ግኝት እንዲያርም የተሰጠውን ተልዕኮ በመተው ከፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ ተግባር ውስጥ መግባቱን ጠቁመዋል።

እንደ አስተያየት ሰጪዎች ጥቆማ ዶ/ር ጉቼ እና ግብረአበሮቹ ወደለየለት የተቋም ዝርፍያ ውስጥ ለመግባት ትራክ ላይ መሆናቸውን ማሳያ ያሉትን ፍንጭ ያመላከቱ ሲሆን፤ በዋናነት በዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ ያልተደረገበት የተሸሸገ ሴራ እና ሚስጢር መኖሩን አመላካች ነው ብለዋል።

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የልማት ዕቅድ ባለሙያ የሆኑት እና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት ግለሰብ "ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት በጀት ሲደለደል በግልጽ በቢል ቦርድ ማስታወቂያ ሰሌዳ፣ በተቋሙ ዌብሳይት እና ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ይደረግ እንደነበር ገልጸዋል።

ነገር ግን ይላሉ ባለሙያው፦ ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ እንዳይደረግ በተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ አቅጣጫ መቀመጡን እና አዲሱ ዓመት ከመግባቱ ጥቂት ቀናት በፊት በተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በዌብ ሳይት እና ሶሻል ሚዲያ በኩል ይፋ የተደረገው የበጀት ማስታወቂያ ከገጹ ላይ በአምስት ደቂቃ ልዩነት እንዲነሳ መደረጉን ጠቁመዋል።

ይህ ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ አሰራር መሆኑን የገለጹት ከፍተኛ ባለሙያው፤ የበጀት ማስታወቂያው ይፋ እንዳይሆን የተፈለገው ከዚህ ቀደም ታቅደው የተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች ሆን ተብሎ በጀት ስላልተያዘላቸው በተጠቃሚው ህዝብ ቅሬታ የሚፈጥር በመሆኑ እንዲሁም አዲስ ይጀመራሉ የተባሉት የልማት ፕሮጀክቶች እንዳይታወቁ በማድረግ የሀብት ምዝበራና ሌብነት ለመፈጸም በማቀድ መረጃውን ይፋ ለማድረግ እንዳልተፈለገ ጠቁመዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ በተያዘው በጀት ዓመት ገንዘብ ሚኒስትር ለዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 1,815,259,470 (አንድ ቢሊየን፣ ስምንት መቶ አስራ አምስት ሚሊዮን፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰባ) ብር መደበኛ በጀት እንዲሁም 650,000,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር ለካፒታል በጀት ተፈቅዷል።

በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲው ታቅዶ የተጠየቀና በገንዘብ ሚኒስትር የተፈቀደ የ2017 መደበኛ እና ካፒታል በጀት 2,465,259,470 (ሁለት ቢሊየን፣ አራት መቶ ስድሳ አምስት ሚሊዮን፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰባ) ብር መሆኑን የገለጹት ከፍተኛ ባለሙያው፤ ይህም ከባለፉት አምስት አመታት በጀት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ይላሉ ባለሙያው፦ ምክንያቱ ባልታወቀ አግባብ በዩኒቨርሲቲው ተጠይቆ በገንዘብ ሚኒስትር የተፈቀደው የ2017 በጀት ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ የቆዩትን የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ልዩ ልዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጨምሮ በዎላይታ ቦዲት ከተማ የተጀመረውን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል የመማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የአበላ ፋራቾ የመማሪያና የእንስሳት ሕክምና ሆስፒታል ቀሪ የግንባታ ስራዎችን፣ የዲምቱ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ህንጻ ግንባታ ማጠናቀቂያ እንዲሁም ሎሎች ትኩረት የሚፈልጉ ተግባራትን አላካተተም ብለዋል።

ሌላው ጉዳይ ይላሉ ባለሙያው፦ "ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማካሄድ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን ለመሥራት በተያዘው በጀት ዓመት 78,944,300 (ሰባ ስምንት ሚሊዮን፣ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ሺህ ሶስት መቶ) ብር በገንዘብ ሚኒስቴር የተመደበ ቢሆንም ማህበረሰብ ውስጥ የሚሰሩ ዝርዝር ተግባራት ምን እንደሆኑ አይታወቅም፤ የተመደበው በጀት ምንም ሳይሰራበት 1ኛ ሩብ ዓመት ተጠናቋል፤ ይህም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተቋሙ ምን እየተካሄደ ስለመሆኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ፣ አመራሩና ሠራተኛው ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንደተራራቁ፣ መድረክ ተፈጥሮ ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር የጋራ ምክክር እንደማይካሄድ፣ አመራሩ ለሠራተኞቻቸው የከለከሉትን ውሎ አበል እና ጥቅማጥቅም ይዘው በየሳምንቱ አዲስ አበባ እንደሚሄዱ እና ምን እንደሚሰሩ እንደማይታወቅ ይህም አንዳች የተሸሸገ ሴራና ሚስጢር ስለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ይኸው ባለሙያ ጠቁመዋል።

ውድ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተከታዮቻችን ለዛሬው ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ባፈነገጠ አግባብ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ያለውን ብልሹ አሰራር በተመለከተ ያዘጋጀነውን ትንታኔ ዜና በዚሁ ቋጨን።

በቀጣይ ትንታኔ ዘገባችን EBC እና FANA ያልነገሯችሁን እና በብዙ መቶ ሚልየኖች ሚቆጠር የህዝብ ሀብት የተመዘበረባቸውን ነገር ግን "የጨነገፉ የግንባታ ፕሮጀክቶችንና የተሸሸገውን ምትሃታዊ ሴራ እንዲሁም ከሴራው ጀርባ ያሉ ሥውር እጆችን" የሚዳስስ መረጃ ይኖረናል። ይጠብቁን

Wolaita Times

22 Nov, 12:02


👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #dawuro #Wolaita

"ብርሃኑ በጉቼ አማካይነት ዩንቨርስቲውን ለማዘጋት" ?👇

https://wolaitatimes.com/?p=5126

Wolaita Times

21 Nov, 15:36


Advertising ---- በቀጣዩ ልንክ በመግባት በቀላሉ እየተዝናኑ ገንዘብ ያገኙ 👇

https://t.me/bybit_spaces_bot/SpaceS?startapp=invite_9B6MVOHU_Gechonati
Blast off into the fun with SpaceS! 🚀

Join me through my link to earn 800 points instantly.

Invite to unlock more Boosters and join me in unboxing and sharing the limited Supply Box rewards!

Wolaita Times

21 Nov, 13:51


ጩሄት ክልሉ በወቅቱ ከነበረበት ከህዝብ መራራ ጩሄትና ጥያቄ መነሻ ከዞን አስተዳዳሪነት አንስቶ ክልል እንዲገባ ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ነዉ።

እሱም የዚያን ጊዜም አቶ ጥላሁን የተፈጥሮ ማንነቱን ክዶ ጋሞ ሆኖ የጋሞ ህዝብም ሆነ የአከባብዉ ሌሎች ብሔሮችን ለማሰቃየት እንደ ማደነጋገሪያ መስፈርት ተጠቅሞ ለማሳካት ያቀደዉ የጋሞ ህዝብን ከዎላይታ ህዝብ ጋር ማጣላት እና እሱ የጋሞ ህዝብ ብቸኛ ጠበቃና ተከራካሪ ራሱን አድርጎ ለማሳየት የሌለ አጀንዳ እየቀረፀ ሲንቀሳቀስ ዉሸትንና ቅጥፈትን የማይፈልገዉ የጋሞ ህዝብ ሴራዉን በመረዳት ከአከባብዉ ማበረሩ ይታወቃል።

በዛን ወቅት ደግሞ ሌላ ማንነት በፍጥነት በመፍጠር “እኔ የጋሞ ብሔረሰብ ስላይደለሁና የጋንታ ብሔረሰብ ባላባት የልጅ ልጅ ስለሆንኩ ነዉ ጋሞዎች ያባረሩኝ በማለት አ/ምንጭ ከተማ የጋንታ ብሔረሰብ ሀብት ናት እኔን ታድጉኝ” በማለቱ ከዚህ የዋህ ህዝብ እዉነትም የኛ ልጅ እንዴት ይገፋል የምል የዋህ እሳቢያቸዉ ከሌላ በማግኘት የጋሞንንና የጋንታ ህዝብ እንዲቃቃሩ ጭምር ምክንያት ሆኖ ማለፉ ይታወቃል።

በአጭሩ ጥላሁን የሚፈልገዉን ጉዳይ ለማሳካት የማይሄድበት ርቀት የለም፤ ምክንያቱም እሱ ሂሳብ ሰርቶ ነዉ፤ ያዉቅበታል ምክንያቱም ጥርስ የነቀለበት ስለሆነ!" በሚል
የሰሞኑ የሚዲያ ዘመቻ የፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት (ትንሹ አፀ ሚኒሊክ) ጉብኝትና የመሩት የዎላይታ ሶዶ መድረክ በተመለከተ ትዝብቱን ከስፍራው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን አድርሰውናል።
#southethiopia #Wolaita

ለመሆኑ ከኑዛዜዎቹ ባሻገር ፕረዚዳንቱ ሶዶ ላይ ስብሰባ አርባምንጭ ፕሮጀክትን ለምን ያበዛል?

https://wolaitatimes.com/?p=5121

Wolaita Times

21 Nov, 13:51


ለመሆኑ ፕረዚዳንቱ ሶዶ ላይ ስብሰባ አርባምንጭ ደግሞ ፕሮጀክት ያበዛል?

የርዕሰ መስተዳድሩ በባህላዊና በሃይማኖታዊ ልብሶች ያሸበረቁ የማደናገርያ መድረኮች ማብቅያቸዉ መቼ ይሆን ?

የሰሞኑ የሚዲያ ዘመቻ የፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት (ትንሹ አፀ ሚኒሊክ) ጉብኝትና የመሩት የዎላይታ ሶዶ መድረክ በተመለከተ ትዝብቱን ከስፍራው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃውን አድርሰውናል።

"ለእግዝአብሄርም ሆነ ለሾመዉ ለብልፅግና ፓርቲ ዴንታ የለሌዉ በአርቴፊሻል ማንነት በመገንባት ክልሉን ማተራመስ ዘዉትር ተግባር ያደረገዉ በተላይም የባለፉት ስድስት ወራት በብዙ ሀብት ተዉቦ በተደራጀዉ በዎላይታ ሶዶ ባለዉ ቤተመንግስት ከማደር የአርባምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ የሚቀናዉና ትንሽ ጊዜ ካገኘ ከEBC ስቱዲዮ ጋር ፎቶ ለመነሳት ብቻ ሶዶ የሚመጣዉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ትናንትና ለሆዳቸዉ ያደሩትን የከተማ፣ የዞን አመራሮችንና ስብሰባን ቋሚ የጡረታ ጊዜ መዋያ ያደረጉ ለአበላቸዉ ብቻ የሚኖሩ አስመሳይ ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ “ፈጣሪ ያያል፤ ፈጣሪ ይፈርዳል፤ የሚወራዉ ሁሉ የፈጠራ ወሬ ነዉ፤ እኛ ክልሉን የሰላም የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት እያደረግን እንገኛለን፤ እኔ ባልኖር ይሄ ክልል ይፈርስ ነበር”፤ ወዘተ በተለመዱ ቀልዶች የ3 ሰዓት የብቻዉን ኑዛዜ ይሁን ስብከት ወይ ስልጠና ወይ ቀልድ ብቻ ግልጽ ያልሆነ ድስኩር በማካሄድ መድረኩን አጠቃልሏል፡፡

የርዕሰ መስተዳድሩ የጥላቻ ማዕከል የሆነዉን ዎላይታን የማዳከም የመጀመርያ ስትራቴጅ ያደረገዉ ዎላይታን የሚወክሉ ሁለት የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከአንድ ቀበሌ የመመልመል፤ የጃላ ትርክት ማንዛት እና “እኔ አንተን በዚህ ቦታ የሾምኩትን ኤከለ የሚባል ግለሰብ ከልክሏል” በሚባሉ ትሪክቶች የዎላይታ አመራሮች እርስ በርስ በማፋጀት ለዘላለም እንዳይቀራረቡና እንዳይደማመጡ የማድረግ ሴራዉን በድል ተወጥቷል፡፡

በመቀጠልም በራሱ ብሄር ባደራጃቸዉ የፍትህ፣ የፖሊስ እና የፀረ-ሙስና ተቋማትን ሙስና በብቸኝነት ተወልዶ ያደገዉ በዎላይታ በሚመስል መልክ ለራሱ ተላላኪ አይሆኑም ብለዉ የገመታቸዉን የክልልና የዞን አመራሮችን የማሳደድ እንድሁም በነጋዴዎች ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ የመጣል እንቅስቃሴ አድርጓል፣ እያደረገም ይገኛል፡፡

በዚህም ለዘመናት በዎላይታ ላይ የተመኙትን ሁሉ አቀፍ ጉስቅልና በአንድ ዓመት የሥልጣን ጊዜያቸዉ ለማሳካት የቻሉ ከአፀ ሚኒልክ ቀጥሎ ሁለተኛ አምባገነን ገዥ ሆኖ በዎላይታ ታርክ ላይ ተመዝግቧል፡፡

በስተመጨረሻም ዞኑ ክልሉ ዉስጥ በመሆኑ ከዉጪ ሆኖ ለሚታዘብዉ አካልም ጭምር እስክታይ ድረስ የእሳቸዉ የሴራ ፖለቲካ ዞኑን ከልማት፣ መልካም አስተዳደርና ህግ በላይነት ዉጪ የሆነ ዞን እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት የህዝቦች እሩሮና ጩሄት እስከ ፌዴራል መንግስትም በየቀኑ በመዝለቁ የከተሞች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ንቅናቄ የሚል የማደናገርያ መድረክ እንድዘጋጅ አድርጎ ምንም ስብዕና የለሌዉ ሰዉ በመሆኑ ዓይኑን በጨዉ አጥቦ ከድምቱ ጀምሮ በእርጥብ ሳር በተቀበለዉ ህዝብ ላይ ለማፈዝ መድረኩን በራሱ መርቷል፡፡

የመድረኩ ዋና ዓላማ እዉነት የህዝቡ የፍትህ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጉዳይን ምላሽ ለመስጠት ነዉ? ወይስ አቶ ጥላሁን ዎላይታ ህዝብ ላይ የጀመረዉ የጥፋት አጀንዳ ሁለተኛ ምዕራፉን ለመጀመር ለቀጣይ ሴራ ህዝቡን ለማሳሳት ያቀደዉ እቅድ ማስፈፀሚያ መንገድ ለመጀመር ማህበረሰቡንና የአመራሩ ስሜትን ለማየት ነዉ?...ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በደንብ መታሰብ ያለበት ጉዳይ ብሆንም አብዘኛዉ የአቶ ጥላሁን ባህርን በቅርበት የሚያወቁ ሰዎች ለሚቀጥለዉ ሴራ የህዝቡ ሥነ-ልቦና ለመገምገም ነዉ ብሎ ይደመድማሉ፡፡

የመልካም አስተዳደር እና የህግ በላይነት ጉዳይ ቢቆረቁረዉና ሀላፊነት ቢሰማዉ አቶ ጥላሁን ማድረግ የነበረበት፡-

በነባሩ ክልልም ጭምር አገልግሎት እየሰጠ የነበረ በአድሱ ክልል ራሱ እንድዘጋ ያደረገዉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሶዶ ምድብ ችሎት ማስከፈት ነበር፤

በአንተ እጅ አዙር ትዕዛዝ በየቀኑ የሚፈፀሙ የጅምላ እስሮችን ታስቆም ነበር

በፍርድ ቤትም ጭምር እንድፈቱ ተወስኖ በየፖሊስ ጣቢያ እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን እንድፈቱ ማድረግ ነበር፤

ርዕሰ መስተዳድሩ ባለበት ልኖሩ የሚገቡ ተቋማት በአርባምንጭ እንድቋቋሙ አታደርግም ነበር፤

በዞኑ በየቀኑ የሚካሄደዉን ሹም ሽረት ማስቆም ነበር፤

የሀምሌ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸዉን የመምህራንና ሌሎች የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ማስከፈል ነበር፤

ለመ/ራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት የተዘጉ ት/ቤቶችን ማስከፈት ነበር

ለጤና ባለሙያዎች ደመወዝና ዲዩቲ ባለመከፈሉ ምክንያት በአግባቡ አገልግሎት የማይሰጠዉን ጤና ኬላዎችን፣ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎችን ችግር መፍታት ነበር፤

በወባ ወረርሽኝ እያለቁ ያሉትን ዜጎች ጉዳይ ያስጨንቅ ነበር

ያንተን አካሄድ የተቃወሙ አመራሮችን ከሀላፍነት የማንሳት፤ የማሳደድ እና ለብሄሩ ሳይሆን ለአንተ ሴራ የሚሆኑ አመራሮችን የማደራጀት ስራ ማቆም ነበር፤

በነሐሴ ወር በይፋ ግንባታ ይጀመራል የተባለዉን የአረካ አየር ማረፍያ ግንባታ ታስጀምር ነበር፤

የሶዶ ከተማ 10 ኪሜ የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት መንገድ ሥራ ለመስራት የተስማማዉን የአስፋልት ሥራ ድርጅት አስቁሜህ ወደ አርባምንጭ አትወስድም ነበር
ሌዊ ግብርና ኮሌጅ ያለዉ አስፋልት መንገድ ተዘግቶ አራት ወራት እንድቆይ አታደርግም ነበር፤

ያንተን ኮርደር ልማት በበጀት ታስደግፋለህ የእኛን 500 ካሜ በፎቶ ሾፒ አታደነጋግርም ነበር

103,410.3 ካሬ ሜትር የአርባምንጭ ከተማ ኢንቨስትመንት መሬት ህጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ለግል ባለሀብት በማስተላለፍ በምትኩ ሁለት መንታ የግል መኖሪያ ያሰራ የጋሞ ዞን የቀድሞ አስተዳድርን ከማስጠየቅ ፋንታ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ገጽታ ልቀይሩ የሚችሉ፤ ለበርካታ ዜጎች ሥራ ዕድል ልፈጥሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን አሰራርን ባልተከተለ መልኩ አታሳግድም ነበር

በክልሉ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጅ ቢሮ ክልላችን አንገት እንዲደፋና በህግና በአሰራር የማይመራ ክልል እስኪመስል የተሰራዉን ዝርፍያ እንድያጣራ ከማድረግ ይልቅ የዎላይታ አመራርን ልያሳስር የሚችል ወንጀል ፍለጋ ላይ ጊዜ አታጠፋም ነበር።

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ ከድርግቱ አስከፍነት የተነሳ በዞኑ እየተስተዋለ ያለዉን የህዝብ ቅሬታና ተቋዉሞ ለማደነጋገር ማሞ ሌላ መታወቂያዉ ሌላ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ራሱን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር፤ ህዝብ እንደ ሆነ እዉነት እና ፍትህ የማይሠራበት ክልል መሆኑን አረጋግጦ ፊትህን ለፈጣሪ ሰጥቶ ጊዜዉን እየጠበቀ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጅ ትልቁና አሳፋርዉ ነገር ሰዉ ተፈጥሮን ሲክድ ለራሱም ለአገሩም ከፍተኛ መከራና እርግማን እንደሚሆን የርዕሰ መስተዳድሩ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ ማሳያ ነዉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በተፈጥሮ ወደ ስልጣን መሄጃ መንገድ ሲመርጥ በነፍሱም፤ በማንነቱም ላይ ዴንታ የለዉም፤ ለአብነት አቶ ጥላሁን በብሔር ማንነቱ ጋሞ አይደለም፤ አለመሆኑ ደግሞ ኃጥያት አይደለም፤ መሆኑም በተለየ ፅድቅ አይደለም፤ ግን እሱ ጋሞ ላለመሆኑ ተጨባጭ እዉነታ ለማያዉቁና ይህን ሚዲያ ለሚከታተሉ ወገኖች 2005 እና 2006 “የአከባብዉ ጋሞ ማህረሰብ ህዝብ ጋሞ ሳይሆን ጋሞ ነኝ በማለት በልጆቻችን ላይ ከፍተኛ በደልና ስቃይ እየደረሰ ያለ አስመሳይ የዞናችን ዋና አስተዳዳር ይነሳልን ከልጆቻችን” ላይ በማለት እስከ ክልል ባሰሙት ቅሬታና

Wolaita Times

21 Nov, 08:36


የነብይ እዩ ጩፋ ወላጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ በየነች ዶጊሶ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህዳር 12 ማረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ፈጣሪ ለነብይ እዩ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። #Ethiopia

Wolaita Times

21 Nov, 06:17


ወደ አደባባይ የወጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገወጥ ተግባር - በመሠረት ሚዲያ

Wolaita Times

20 Nov, 14:49


የዎላይታ ህዝብ ከተጫነበት የመዋቅር እስርቤት መቼ ይወጣል?

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "በዎላይታ ሕዝብ ላይ ተጭኗል" ለማለት የሚያስችሉ ምክንያት የሚሏቸዉን ነገሮች ቢጠቅሱልን ? መንግስት የመዋቅር ጥያቄዎች በሙሉ ፈትችያለሁ እያለ ባለበት በአሁኑ ወቅት እየተካሄ ባለው ሀገራዊ ምክክሩ ላይ የዎላይታ ክልል ጥያቄ እንደ አጀንዳ ከእንደገና እንዴት ሊቀርብ ቻለ? ህዝቡ በግድ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጥሶ የተጫነበትን መዋቅር አስወግዶ ነፃነትን የሚያስከብረው መቼ ይሁን ?እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽና ቁምነገሮችን ይዘናል ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ👇

ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀ ጥንቅር ነውና በትዕግሥት እንድታነቡ እንጋብዝሃለን!

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ፕሮፌሰር እንግዲህ እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ እንላለን። ያዉ የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ ምላሽ እንግባ።

ለመሆኑ መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን የመዋቅር ጥያቄዎች በሙሉ ፈትችያለሁ እያለ ባለበት በሐገራዊ ምክክሩ የዎላይታ ክልል ጥያቄ እንደ አጀንዳ እንዴት ሊቀርብ ቻለ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መንግስት ሲያወራ የነበረዉ ዉሸት ስለነበረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ እንኳን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዛይሴ እና የቁጫ ተወካዮች ያነሷቸዉ ጥያቄዎች ዉሸት በአደባባይ ያረጋገጡ ናቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በአጭሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሕዝብ ላይ ተጭኗል ለማለት የሚያስችሉ ምክንያት የሚሏቸዉን ነገሮች ቢጠቅሱልን ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ክልሉን በተለይ በዎላይታ ሕዝብ ላይ ብልጽግና በጉልበት የመሰረተዉ የሚባለዉ በተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ በመመስረት ነዉ። ደግነቱ ጀግናው የዎላይታ ሕዝብ በቂ ትግል ከማድረጉም ባሻገር ብልጽግናን በሁሉም ግምባሮች ማኖ አስነክቷል።

1. ብልጽግና የክልል ጥያቄውን ለመቀልበስ አንድ አመት ሙሉ የደቡብ ክልል ምክር ቤት እንዳይሰበሰብ ከማድረጉም በላይ በዞኑ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዷል።

2. ሕዝበ ዉሳኔዉ ጸረ-ሕገመንግስታዊ ነበረ ምክንያቱም ትርጉሙ አይታወቅም ነበረ ለምሳሌ ( ጎጆ)። በአቶ አገኘሁ ተሻገር የሚመራዉ የፈደሬሽን ምክር ቤት በዚህ ተጠያቂ ነው።

3. በዎላይታ የሕዝበ ዉሳኔ አስፈጻሚነት የተመለመሉ ወጣቶች ባካሄዱት በሰላማዊ መንገድ የማደናቀፍ ትግል የተነሳ ሕዝበ ዉሳኔዉ ዉጤቱ እንዲሰረዝ ማድረግ ተችሏል። ብዙዎች ታስረዋል፤ ተሰደዋል።

4. በሁለተኛው ሕዝበዉሳኔ የሕዝቡ በቋንቋው የመገልገል ሕገመንግሥታዊ መብቱ ተጥሶ አስፈፃሚዎች ከአዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጓል።

5. ጎጆ የዎላይታን ክልል ይወክላል በሚል ሕጋዊ ትንታኔ ላይ የተመሠረተ ቅስቀሳ በተወሰኑ የዎላይታ ሊህቃን ተቀስቅሶ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ እንደሚያሸንፍ ምልክት ባሳየበት ሁኔታ የሕዝበ ዉሳኔዉን ዉጤት የሚያዛባ ዘገባ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተሠርቷል።

6. በወቅቱ የምርጫ ቦርድ ፕሬዚዳንት የነበረችዉ ብርቱካን ሚዴቅሳ በምርጫ ጣቢያ ተገኝታ አለስራዋ ከስድስት ወር በፊት ባልወጣ መታወቂያ መምረጥ አትችሉም ብላ ሕገመንግሥታዊ መብት እየጣሰች ዉላለች። ከዛም በተጨማሪ የጎጆን ትርጉም ተጠይቃ አላዉቅም የእኔ ሥራ ማስፈጸም ብቻ ነው ብላም ነበረ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሌላዉ ከነችግሩም ቢሆን ክልሉ ሲመሠረት ዎላይታ ሶዶ የመጀመሪያዋ ከተማ ተደርጋ ነበረ። በቅርቡ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለከፍተኛ አመራሮች በሰጠዉ ስልጠና ላይ ይሄንን ሽሯል፣ በተደጋጋሚ ስለ ኮሪደር ልማት ሲያወራ በቀጣይ በሁለተኛ ደረጃ ከተማነት ገሸሽ መደረጓን አስቀምጧል። ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን መቀየር ይችላሉ ? የዎላይታ ሕዝብስ የከተማ ጥያቄ እንዲሁ በቀላሉ የሚገፋ ነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ መብቱ ባይኖረዉም ያሻዉን እያደረገ ነው። የዎላይታ ሕዝብ ለዘመናት በቀየዉ ትልቅ ከተማ እንዳይሰራ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማስቀጠል ያሰበ ይመስላል። እንደለመደዉ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ሕገመንግሥት የጣሰ አካሄድ እየሔዱ ናቸው። የዎላይታ ሕዝብ በተለይ በቅርብ አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከደረሰበት ጥቃቶች በሁዋላ ይሄንን ግፈኛ ዉሳኔ ማሳለፍ በሕዝቡ ቁስል ላይ እንጨት መሥደድ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ለመሆኑ ዶክተር ዐብይ አህመድ እንዲህ በፈላጭ ቆራጭነት የሚወስነዉ ንጉስ ነው ወይስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንድ ተካልኝ ገዳሙ የሚባል ሰው ሰዉ ዘዉዳዊዉን አገዛዝ ገርስሰናል የሚሉ ቀጥለዉ የመጡ የኢትዮጵያን መሪዎች የሚተችበት መጽሐፍ ርዕስ ምን ይላል መሰለህ "The Republicans on the throne" እናም ፈላጭ ቆራጭነት በኢትዮጵያ የቀጠላ መራራ ሐቅ ነው።

ሕዝብን ከመጋረጃ ጀርባ የሚወሰኑ ተንኮለኛ ዉሳኔዎች መምራት ቀጥሏል፣ የሐገሪቷ ሕዝብ አንድነትም የማይመጣዉ ያለ መሥፈርት በሚወሰኑ ዉሳኔዎች ጭምር ነው፤ ዉስጣቸዉ የብሔር ጭቆና እርሾ ስላለ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት መንግስት በታሪክ ዎላይታ ሶዶ በአካባቢው ዋና ከተማ አልነበረችም የሚል መከራከሪያ ካቀረበስ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ የቀኝ ግዛት ዉሎችን አልቀበልም የሚል ትክክለኛ አቋም እንዳላት ይታወቃል። የዎላይተም ሕዝብ የብሔር ጭቆና በነበረባቸዉ እና እንደጠላት በሚታይበት ዘመን የተወሰኑ ዉሳኔዎችን አይቀበልም!!! በግልጽ ሕዝቡን ለመጉዳት የተወሰኑ ናቸዉና።

ሲጀመርኮ በአቶ አገኘሁ ተሻገር የሚመራዉ የፈደሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚያፍነዉ በተዘዋዋሪ የዎላይታን ሕዝብ ይጠቅማል ብሎ እንደሆነኮ የአደባባይ ሚስጢር ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መፍትሔ የሚሉትን ጠቁመዉን ብንጨርስ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ በሁሉም ግምባር በሰላማዊ መንገድ መታገል ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጀምሮ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎቻችንም ሆነ ሕዝባችን መብትና ጥቅሙን ለማስጠበቅ መታገል አለበት። ከእንግዲህ የዎላይታ ሕዝብ የሚገባዉን መብቱን ተነጥቆ ሌላ ከተማ አልምቶ እንደተለመደዉ ይባረራል ብዬ አላምንም። መፍትሔዉ ሰላማዊ እና ሕገመንግሥታዊ ትግል ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

19 Nov, 15:00


"የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች የዎላይታን ፖለቲካ የሚፈሩት ነፃ እየወጡ የቀሩ ብሄረሰቦች ነፃ የሚወጡበት ዕድል ያስገኛሉ በሚል ስጋትና ጭንቀት ነው" - የዎጋጎዳ ትግል መሪ አባል

ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የሰሜን ኦሞ መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣውን የሁለቱ አከባቢ ፖለቲካ ፉክክር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በመንግስት ደረጃ ካለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባሻገር መሠረታዊ የፉክክሩ መነሻ ምክንያት ምንድነው የሚለውን ምላሽ ለማግኘት በወቅቱ የነበረውን የጭቆና መዋቅር ለማፍረስ ታግለው ውጤት ካመጡት መካከል አንዱን ጠይቀን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እኚሁ አንቱ የተባሉ በአሁኑ ወቅት ወደ 65 ዕድሜ የተጠጉና ትግሉን የመሩና የተሳተፉ ሰዎች መካከል አንዱ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፁት "ጋሞ ማለት አርባምንጭና ዙሪያዋ ነች፥ ድሮ ከዎላይታ እስከ ዳውሮ ከኮንታ እስከ ጎፋ ብሔሮችን በሙሉ በመጠፈር ሰሜን ኦሞ በሚባል የጥርነፋ እስር ቤት ተደርጎ ያቺ በወበቅ ከአንድ ቀን በላይ ሰው ሊያሳልፋባት የማይችላትን ከተማ ብቻ አሳድገው በጀርባው ደግሞ ጋሞ የሚባልን ብሔር ብቻ የሰፋ አድርጎ በመሳል ከሁሉም በቁጥር የሚበልጠውን ዎላይታን በማሳነስ ሌሎቹንም ጭራሽ ደብዛቸውን በማጥፋት ጋሞን ብቻ የአካባቢው ትልቅ ብሔር የማስመሰል ሴራ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰራ ስለነበር ትግሉ የማይቀር የህልውና ጥያቄ በመሆኑ ለማቀጣጠል ወስነናል" በሚል ያስረዳሉ።

በዚህ የተበረታቱት የጋሞ ብሔረሰብ ፈጣሪ አባላት በወቅቱ የሌሎቹም ቋንቋ ጠፍቶ የጋሞ ቋንቋ የአካባቢው ቋንቋ መሆን አለበት በሚል ዎጋጎዳ የሚባል የፈጠራ ወፍኛ ቋንቋን እንደፈጠሩም ታጋዩ ያብራራሉ።

አክለውም አሁን ጋሞዎች በዎላይታ ሕዝብ ጥላቻ ተቃጥለው የሚንገበገቡት ዋንኛው ምክንያት ምንድነው ቢባል መልሱ ይህ ነው ይላሉ፦ "ትናንት በክልልነት ትግሉ ጊዜም የአካባቢው ሌላው ሁሉም ብሔር በኩሽና በተደበቀበት ወቅት ለመብቱ አደባባይ ወጥቶ በመታገል የፌዴራል መንግስቱን ጥይት ያስተናገደውና ውድ ልጆችን እስከመሰዋት ትግሉን በቁርጠኝነት ያከናወነው ዎላይታ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ቆራጥነቱን በ1992 ዓ.ም በተመሣሣይ ሁኔታ ዎላይታ ፈፅሞ ያንን የጋሞዎቹን የጥርነፋ እስር ቤት ሰባብሮ የወጣው ይሄው የጦና ሕዝብ አንበሳው ዎላይታ ብቻ ነበር" ብለዋል።

"ይሄውልህ ልጄ፦ በወቅቱ በዎላይታ ወደ አራት የሚሆኑ ምሁራን ተሰውተው መላ ዎላይታ ለትግል ተነስቶ ዎጋጎዳን ድባቅ መትተን በማስወገድ ብቻ አላበቃንም ነበር.... ጋሞ ይሁን ሌላ ብሔር ድጋሚ በሌላኛው የአካባቢው ብሔር እንዲህ ዓይነት የጭቆና ሃሳብ እንዳያስብ ለማድረግ አንድ መሠረታዊ ስራ መሠራት ነበረበት። እናም ያንን ስራ በወንድማችን በታላቁ ፍሬው አልታዬ የተመራው የዎላይታ ሕዝብ በመሠረታዊነት ለውጦ ሰርቶታል" በሚል ታሪክን በኩራት ያወሳሉ።

ይህም የመዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ነበረ.....በመሆኑም ዎላይታ ቀድሞ የዎላይታ ዞን የሚባል መዋቅር አቋቋመ (አልተፈቀደም እንጂ እሱማ በፍሬው አቅጣጫ አመላካችነትና በሃገር ሽማግሌዎቻችን አማካኝነት በወቅቱ ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩም ሆነ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ገብቶ የነበረው ደብዳቤ የክልልነት መዋቅር ነበር).....

.... ሆኖም ዎላይታ ዞንነትን አረጋገጠ። ልብ በል ልጄ፦ የዚህ ድል ፋይዳው ለዎላይታ ሕዝብ ብቻ አልነበረም። በወቅቱ ዎላይታ ሕይወቱን ሰውቶ ይሄንን ድል ያመጣው ሆኖ ያልታገሉትና አንዲት ጥይት ያልተተኮሰባቸው ወንድም የዳውሮ ሕዝብ የዎላይታ ትግል በቀደደላቸው ዕድል ተጠቅመው ምንም ዋጋ የሚያስከፍል ትግል ሳያካሄዱ በአርምንጭ ስር ከታሰሩበት እስር ቤት ከዎላይታ ጋር የራሳቸውን ዞን መዋቅር ተፈቅዶላቸው ነፃ ወጡ።

ዎላይታ በታገለው ለአካባቢው ሌሎችም ወንድም ሕዝቦች መንገድ ከፈተ። እኔ ሁሌም የምናደደው ይህ የዎላይታ ሕዝብ ውለታ በአግባቡ ያልተነገረና ዎላይታ ለአካባቢው ምን ያህል ጠቃሚ ሕዝብና የዲሞክራሲ መንገድ አለማማጅ የነበረ ሕዝብ መሆኑ ሁሌም እንደቆጨኝና ፀሐፊ ሆኜ ይህንን ውለታ በመፅሐፍ አሳትመው አሳትመውና አሰራጭ ያሰኘኛል በዕውነቱ።

ለዚህ የዎላይታ ሕዝብ ውለታ የመጀመሪያዎቹ የዳውሮ ዞን አስተዳዳሪዎች ዛሬም በሕይወት ያሉት እነ አቶ #ዳመነ_ዳሮታ ሕያው ምስክር ናቸው በዕውነቱ። እነ አቶ #ሳሙኤል_ሃላላ ህያው ምስክር ናቸው።

ቀጠለና ሌላኛው ብሔር የሆነው ኮንታም በልዩ ወረዳነት ቋንቋውን፥ አለባበሱን፥ ጭፈራውን.... ማንም ሳይጨፈልቅበት እንደያዘ ራሱን አስከብሮ ወጣ!! ለዚህ ድል የትግሉ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ዎላይታ ባይጀምረው እስካሁን የሌሎቹ ቋንቋ ጠፍቶ ጉዳያቸውን ለማስፀም ወደ አርባምንጭ እየተመላለሱ ይኖሩ እንደነበረ ግልፅ ነው።

ልጄ ዎላይታ|ኮ ባለውለታ እንጂ የዛሬ ተወላጆች የትናንቱን የዎላይታን ውለታ የማያውቁት ሌላ ነገር ሲያወሩ ስትሰማ የምታዝነው በባለማወቃቸው እንጂ በሌላ አደለም። ቀጠለና ጎረቤት ወንድሞች ጎፋ|ም ከትንሽ መዘግዬት በትግል በኋላ ራሱን ችሎ በዞንነት ወጣ።

ነገር ግን አሁንም በዞኑ በፊት ነፃ እየወጡ በጫና የቀሩ የተለያዩ ነባር ብሄር ብሄረሰቦች ለዘመናት ማንነታቸው ባልወከሉት ( ቁጫ፣ ቦሮዳ፣ ጋንታ፣ ዶርዜ፣ ዘይሴ፣ ካምባ፣ ቦንኬ፣ ኦቾሎ ብሄረሰቦች ) ታፍነውና ማንነታቸው ተደፍጥጠው የሚኖሩበት በዚህ እስርቤት ማንነታቸው እንዳይታወቅ ከፍተኛ ስቃይና አፈና እየተካሄደ መሆኑ የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች የዎላይታን ፖለቲካ የሚፈሩት ነፃ እየወጡ የቀሩ ብሄረሰቦች ነፃ የሚወጡበት ዕድል ያስገኛሉ በሚል ስጋትና ጭንቅ የመነጨ ነው" ሲሉም የዎጋጎዳ ትግል መሪ አባል ጠቁመዋል።

ታጋዩ ጨምረውም፦ "የትኛውም ብሄር አባል ለወጣበት ማህበረሰብ ከመታገል ባሻገር፦ እንዲህ በራሳቸው ማንነት የሚኮሩ እንዲሁም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚጠይቁትን ያፈነ ከድሮ ሴራኞች እጅ ያልወጣ ፀረ ፌደራሊዝም በሆኑ ሰዎች አስተሳሰብና ሴራ ተደራጅተው መብታቸውን የነፈጉትን ለማሸነፍ በሚደረገው ተፈጥሯዊ መብት ትግል ደጋፊ መሆን ወንጀል ወይም ጥላቻ ሳይሆን ለፍትህና ለሰብዓዊነት መቆም ስለሆነ በታሪክ አደባባይ ሁልጊዜ በኩራት እንናገራለን" ብለዋል።

"እንግዲህ በአጭር ቋንቋ ለምን የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች በዎላይታ ላይ ጥላቻን አተረፉ ካልከኝ መልሱ ይህ ነው ልጄ" በሚል ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የሰሜን ኦሞ መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣውን የሁለቱ አከባቢ ፖለቲካ ፉክክር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መሠረታዊ የፉክክሩ መነሻ ምክንያት ምንድነው የሚለውን ምላሽ ለማግኘት በወቅቱ የነበረውን የጭቆና መዋቅር ለማፍረስ ታግለው ውጤት ካመጡት መካከል አንድ ታጋይ ጋር ባደረግነው ቆይታ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #dawuro #konta #Wolaita #Gofa #Gamo #Kucazone

Wolaita Times

18 Nov, 14:45


"በዲላ ለድሆች በሴፍቲኔት በኩል የመጣው ገንዘብ የአመራሮቹ ገቢ ምንጭ ሆኗል"

በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ለድሃ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ወገኖች ከአለም ባንክ በድጋፍ የሚሰጠው ገንዘብ "ለድሆች ሳይሆን ለከተማ አመራሮች ገቢ ምንጭ ሆኗል" ተብሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ገንዘብ በስራ ለተሰማሩ ሰራተኞች ተገቢ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ከመስጠት ይልቅ የባለስልጣናቱ ጉድለት ማሟያ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከስፍራው ደርሷል።

መረጃ እንደሚያሳየው ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችና ለስራው አጋዥ ቁሳቁስ ገዢ ጨምሮ አስፈላጊ ጉዳዮች እንዲውል የሚላከው ሙሉ ፓኬጅ በማዘጋጃ ቤቱ ስራአስኪያጅ አማካኝነት በየሳምንቱ አንዳንዴ ደግሞ በሳምንት ሁለት ሶስት ግዜ ለከተማ ስራአስፈፃሚዎችና ለፋይናንስ ቁልፍ የስራ ባልደረቦቻቸው ከ10,000 እስከ 25,000 ሺ ብር አበልና የውሸት ስብሰባ እየተባለ እየተሰራ፣ በፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆን የማይችሉት እንዲገቡ እንዲሁም አድረሻ በማይታወቁ ተጠቃሚዎች ጭምር ደመወዝ መክፈልም እንደሚገኝበት ተገልጿል።

ለድሃ ከአለም ባንክ የሚሰጠው ገንዘብ ለባለስልጣናቱ ልዩ መቀለቢያ በመሆኑ በከተማ የፊት ስራአስፈፃሚ አመራሮች "የማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅና ሂሳብ ሰራተኞች የሚደረገው እንክብካቤ ከእንቁላሉ አስኳል በላይ ነው" ስሉ የመረጃ ምንጫችን ገልፀዋል።

እንደ አስተያየት ሰጭያችን መረጃ "ይህ ገደብ የሌለው የሴፍቲኔት ገንዘብ ብዝበዛ ከማዘጋጃ ውጪ ባሉ መስሪያቤቶች ሃላፊዎች ላይ አደጋ እንድደቀን ምክንያት ሆኗል" ስል ገልፀዋል።

ምን አይነት አደጋ ነው የሚደቀነው ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ "በተለይ ለዲላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ እና ሌሎች አስተባባሪ አካላት ልዩ ልዩ አስራትና በኩራት የማይሰጡ ሌሎች መስሪያቤቶች በማዘጋጃ ልክ ጥቅማጥቅም ስለማይሰጡ መስሪያቤቶችን የሚመሩ ሃላፊዎች ያለምንም ምክንያትና ያለ ምንም ጥፋት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ እየተደረጉ ይገኛሉ" በማለት ገልፀዋል።

ለእነኚህ የጉልበት ስራ ሰርተው ከሰፍቲኔት ፕሮግራም ጥቅም የሚያገኙ ድሆች "በሶስት አመት ውስጥ አንድ ግዜ ልብሳቸው እንደማይቀየርላቸው፤ የግብዓት ማሟያ ገንዘብ ለምን ጥቅም እንደሚውል እንደማይታወቅ እና በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ የከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራር እየተበዘበዘ ይገኛል" ስሉም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልፀዋል።

ባሳለፍነው ሳምንታት የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አባት ከነበረው ቀበሌ ቤት ወደተሻለ ቁጠባ ቤት አዘዋውረው ቤቱን አፍርሰው ለማሳደስ ለወጣው ወጪ በተለያዩ ሰዎች ስም ከዚህ ከሴፍቲኔት ገንዘብ በአበል መልክ ተሰርቶ የብሎኬት መግዣ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

በመሆኑም "በእነዚህ አጥፊዎች ላይ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ እርምጃ ተወስደው ለእነዚህ ለሴፍቲኔት ተጠቃሚ ድሃ ማህበረሰቦች ጥቅማቸው እንዲከበር በማድረግ ለከተማዋ ውበትና ዕድገት ወሳኝ የሆነው ሰፍቲኔት ፕሮግራም ከአላማው አንፃር በተገቢው መመራት አለበት" በሚልም የመረጃ ምንጫችን አሳስበዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita_sodo

"ለድሆች በሴፍቲኔት በኩል የመጣው ገንዘብ የአመራሮቹ ገቢ ምንጭ ሆኗል" ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5109

Wolaita Times

17 Nov, 14:52


የዞኑን ገጽታ ልቀይሩ እንዲሁም ለበርካቶች የስራ ዕድል ሊፈጥሩ የሚችሉ ኢንቨስሜንቶች በአድስ መልኩ እንዳይገቡ ስደረግና ነባር ተፈቅዶ እየተሰሩ ያሉ እንድቆም ስደረግ ያለመታገል የአቶ ገብረመስቀል ጫላ ትልቅ ድክመት ስለመሆኑም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ታዝቧል።

ሌላው በክልሉ ሕዝብ ዎላይታ ተመጣጣኝ የፖለቲካ ውክልና እንዳያገኝና በሴራ የተሸረበ የአቶ ጥላሁን በጎ ስጦታ ብቻ ድርሻ ስደረግ ያለመታገልና ህዝቦች በፍታሃዊ መንገድ የሚገባዉን የፖለቲካ ዉክልና እንዲያገኙ ብሎም የግለሰብ በጎ ስጦታ እንዳይሆን ተገቢዉን የአመራር ሚናን ያለመወጣትና ህዝቡ ተወካይ የሌለ እንዲሆን መንገዱን አመቻችቶና ፈቅደው ሰጥተዋል።

በዞኑ ዉስጥ ያሉ የትኛዉም የህብረተሰብ ክፍል በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለዉን በከፍተኛ አመራር ታቅዶ እየተሰራ የሚከናወነዉን ድርጊት ከተቃወመና ትክክል አይደለም ብሎ አስተያየት ከሰጠ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አማካይነት በሙስና ተጠረጥሮ በቁጥጥር ስር አዉለናል የሚል የዉሸት መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰጠ እንዲታሰርና ሌላዉ እንዲደናገጥ በሚል አቅጣጫ አስቀምጦ መምራት እንደጥሩ ስልት እየተጠቀመ ይገኛል።

በአጠቃላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እና በስልጣን ላይ ስለመኖሩ ማንም የማያስታዉሰዉ የክልሉ ፖለቲካና ሪዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዮሐንስ በየነ የዎላይታ ህዝብ ጥቅም ለማስከበርና መብቱን ከማስጠበቅ ይልቅ የግል ጥቅማቸዉን በማሳደድ ላይ የተጠመዱ በመሆናቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ ተላላኪ ከመሆን ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸዉ ብዙዎች ይስማሙበታል።

ይሄ ህዝብ በገዛ ልጆቹ እየተከዳ እስከ መቼ ይቀጥላል? የህዝቡ አንደበት ልሆን የሚችል አመራር መቼ ሊፈጠር ይችላል? የህዝቡን እዉነተኛ ስሜት ሊረዳ የሚችል አመራር መቼ ይኖረናል? የሆነ ሆኖ አሁን ዎላይታ የህልውና አደጋ ተጋርጦብናልና ከመቼዉም ጊዜ በላይ ሰላማዊ ትግል የሚያስፈልግበት ጊዜዉ አሁን ነዉ!!! ፍትህ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦችና ተወካይ ላጣዉ ለዎላይታ ህዝብ የሚሉ በርካታ ድምፆች በተጨባጭ ከፍ ብሎ ከየአቅጣጫው መሰማትና መፍለቅ ጀምሯል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita_sodo


ህዝቡ ከገጠመው አንገብጋቢ ምላሽ የሚሹ ችግሮች አንፃር ስለ "ተስፋ ተጥሎባቸው ተጨማሪ 17 ዕዳ የፈጠሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር" .... በWolaita Times official website ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://wolaitatimes.com/?p=5105

Wolaita Times

17 Nov, 14:52


"ተስፋ ተጥሎባቸው ተጨማሪ 17 በላይ ዕዳ የፈጠሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር" - የትዝብት ዘገባ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

ህዝቡ ከገጠመው አንገብጋቢ ምላሽ የሚሹ ችግሮች አንፃር ተስፋ የተጣለባቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተጨማሪ ዕዳ በመሆን “ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ” እንደሚባል ህዝብን የሚጠሉ ግለሰቦች በአደባባይ እንደፈለጉ መጨዋቻ እንዲያደርጉ መንገድ ከፍተውና አመቻችተው ሰጥተዋል!!

የዎላይታ ብሔር እንደ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ለመብቱና ለክብሩ እንድሁም ለማህበረዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ ዘመናትን የተሻገረ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኝና በሥራ ታታርነቱ የሚታወቅ ኩሩ ህዝብ ነዉ፡፡

ከምንም ነገር በላይ የኢኮኖሚ ጥያቄዉ ዛሬም ፋታ የማይሰጥ ነዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መዋቅራዊና ፓለቲካዊ ጫና በፈጠረው የመሬት ጥበትና የአካባቢዉም ሐብት ሊሸከም ባለመቻሉ ወደ መላዉ አገርቱ ያለማቋረጥ በመፍለስ ላይ ያሉ ታዳጊዎችና ወጣቶች ጉዳይ ጤናማ አስተሳሰብ ላለዉ ዜጋ እረፍት የሚነሳ ጉዳይ ነዉ፡፡

ዎላይታ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙትን አዉዳሚ ጦርነቶችንና በዝባዥ መዋቅራዊ ጭቆናዎችን አሸንፎ መዉጣት የቻለ ዛሬ ግን ዘመናዊ አስተሳሰብ አለ ተብሎ በሚገመቱ በዛሬዋ ልጆቿ በፈተና ዉስጥ ይገኛል፡፡

ዞኑ የምግብ ዋስትና ችግር፣ ከ300ሺህ የሚበልጡ ወጣት ልጆቿ በሥራ እጦት የሚሰቃዩባት፣ በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየተፈተነ ይገኛል፡፡

ይህንን ዉስብስብ ችግሯን ልፈታ የሚችል አመራር ጥያቄዋ ተስፋ ወደሚያስቆርጥ ደረጃ እንደተሸጋገረ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ችግሯን የሚመጥን እንቅስቃሴ ልያደርግ የሚችል ክልላዊ አደረጃጀት እንድፈጥር በቅንነት የተነሳዉ የክልል እንሁን ጥያቄዋ በሴራ ፖለቲካ ተቀልብሶ በልጆቿ ዉሸት ቅስቀሳ ተታልላ የታቀፈችዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሆድ ባደሩ በገዛ ልጆቿ አመቻችነት ዞኑን ከድጡ ወደ ማጡ አሽቆልቆሏል፡፡

ባላቸዉ የአመራር ልምድ ተጠቅመዉ ክልሉንና ዞኑን ያሻግራሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸዉ አቶ ገብረ-መስቀል ጫላ ተጨማሪ ዕዳ በመሆን ዞኑ የትርምስ ቀጠና እንድሆንና የዎላይታ ዕድገት ለሚጠሉ ግለሰቦች መጨዋቻ እንዲሆን አድርጓል፡፡

የተጣለባቸዉና የህዝብና የፓርቲ ሀደራ ወደ ጎን በመተዉ ለገዥነት የሚሆን የራሱን ዳይናስቲ በመምስረት ሥራ ላይ ተጠምዷል፡፡ የእሳቸው ትልቁ ግብ የህዝብን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት ሳይሆን የጡረታ መዉጫ ሀብት ለማካበት የሚያግዝ የተጠና ቤተሰባዊ አደረጃጀት መፍጠር እንደሆነ በጥቂት ጊዜ በአደባባይ እየታየ ይገኛል፡፡

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በተላይም የአከባቢው ጉዳይ በጥልቀት እየተከታተለ ለህብረተሰቡ መረጃ እንደሚያደርስ እንደ አንድ ሚዲያ ከላይ የጠቀስናቸው አቶ ገብረመስቀል ጫላ ለወከለዉ ለዎላይታ ህዝብ ተመጣጣኝና የሚገባዉን ጥቅም ለማስጠበቅ እንዳልቆመ በክልሉ በአጭር ጊዜ የተፈፀሙ ተጨባጭ ኢ-ፍትሃዊ ሥራዎች ዝርዝር በትንሹ እንደሚከተለው እናሳያለን።

በመረጃችን መሠረት አቶ ገብረመስቀል ዞናዊ አንድነት እንዳይኖርና አካባቢዉ ተረጋግቶ ልማት እንዳይሰሩ ቀን ማታ ከሚሰሩ አካላት ጋር በማበር እንደ አልፋ ትምህርት ከፓርቲ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ በየቀኑ ሹም ሽረት በማካሄድ የራሱን ዳይናሲቲ ማጠናከርን ትኩረት አድርገዋል።

ዎላይታን ለማዳከም፣ ለማሳሰር፣ ለማሸማቀቅና ለማዋከብ በዕዉቀት በፍትህ የምርመራና የፀረ-ሙስና ዘርፍ፤ በፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ፣ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ሌሎች ለዚህ ሥራ የሚያግዙ ቁልፍ ቦታዎች በርዕሰ መስተዳድሩ ብሄር በሆኑ ግለሰቦች ተደራጅተዉ ህጋዊ አስመስሎ የሚሰሩትን ሴራዎችን ታግሎ ያለማስቆም ደረጃ ደርሰዋል።

በዎላይታ ማዕከል ለሚገኘዉ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪ የሆነ ክልሉ ፖሊስ ኮሌጅ በአርባምንጭ ዙርያ ስቋቋም ምን አገባኝ በማለት ዝምታን መምረጥና ፍትህ ጥያቄን የምያነሱ ወገኖችን ማሳደድና ማሰር መደበኛ ተግባር አድርገዋል።

ህዝቡ በቀመር ከሚያገኘዉ በጀት በትንሹ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ከዞኑ መደበኛ በጀት ድርሻ እንድያጣ ስደረግ ተባባሪ መሆንን መረሰጠዋል

2ቱ የዎላይታ ከተሞች ከአለም ባንክ ድጋፍ በፖለቲካ ዉሳኔ ስዘረዙ፦ ለበርካታ ዓመታት በአለም ባንክ የሚደገፉ አረካ እና ቦዲቲ ከተሞችን በሕገወጥ እና በሴራ ፖለቲካ ውሳኔ ከድጋፍ ማዕቀፉ የሚሰረዙበትን ውሳኔ በማሳለፍ ከተሞችን ከልማትና ከዕድገት ጉዞ ውጭ አድርገዋል።

በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አማካይነት ከነባሩ ክልል ጀምሮ በአለም ባንክ ፕሮጀክት በዕዉቀታቸዉ ተወዳድሮ አልፎ እየሰሩ ያሉት ባለሙያዎች ዎላይታ በመሆናቸዉ ብቻ ከሥራ ስባረሩ ዝምታ መርጠዋል።

ከግብርና ኮሌጅ እስከ ሌዊ ያለዉን አስፋልት ሥራ የሚሰሩ ኮንትራክተሮች መንገዱን ዘግቶ ሥራዉን አቁሞ ወደ አ/ምንጭ ስታዲዬም ግንባታ እንድሄዱ ሲደረግ ዝም ብሎ ማየትና ለማስቆም ያለመቻሉም አቶ ገብረመስቀል በህዝብ ጉዳይ ደንታ የሌላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በክልሉ በለሎች አካባብዎች ባልተለመደ ሁኔታ በዞኑ ዉስጥ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አማካይነት የሚደረገዉን የበርካታ ዜጎች ህጋዊ ያልሆነ እስርና አፈና ያለማስቆም በፍርድ ቤትም ጭምር በዋስ እንድወጡ የተፈቀደላቸዉ ዜጎች የፍ/ቤት ትዕዛዝ ጭምር ስከለከሉ ያለማረም ዜጎችና በተሰቦቻቸዉ ስሰቃዬ በምን አገባኝ መንፈስ ማየትን መርጠዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ስልጣኑን ተጠቅሞ በህዝብ ስም የመጣዉን የህዝብ በጀት ያለ ህጋዊ አሰራር 500 ሚሊዮን ብር ለስታድየም ግንባታ እና 200 ሚሊዮን ብር ለአርባምንጭ ዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት ጥገና ድጋፍ ስሰጥ ለብሔር ዉግንናም ብቻ ሳይሆን ህግም እንዳይከበር ዝምታ መርጠው የተጣለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት ዘንግተዋል።

በዎላይታ በአረካ አካባቢ ለማሰራት የታሰበዉን ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ግንባታ በተለያዩ ሰበቦች ስጓተት መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ህዝብን ለማታለል ምንም ሥራ በማይሰራበት ፎቶ እየተነሱ ፌስ ቡክን ማጨናነቅ ሥራ አድርጎ አስቀጥለዋል።

አቶ ገብረመስቀል ጫላ በተጨማሪም የዎላይታ ተዎላጆች እንደማንኛዉም ዜጋ በክልሉ ባሉት ቢሮዎችና ሌሎች ቦታዎች በዕዉቀታቸዉ በክህሎታቸዉና በሥራ ልምዳቸዉ ተወዳድሮ እንዳይቀጠሩ እና እንዳይሰሩ በተጠና ሁኔታ መገለል ሲደረግባቸዉ ማረም ሲገባቸው የራሳቸውን ዳይነስቲ በመገንባት ላይ ተጠምደዋል።

በዞኑ ዉስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ መንግስታዊ ሥራዎች በአግባቡ የአመራር ክትትልና ድጋፍ ተደርጎ እንዳይመራ በመደረጉ ጤና ተቋማት ሥራ በማቆማቸዉ ምክንያት በርካታ ዜጎች በወባ ወረርሽኝ ህይዎታቸዉ እያለፈ ይገኛል፤ እንዲሁም በት/ቤቶች ተማሪዎች ትምህርታቸዉን በአግባቡ እየተማሩ አይደለም የሚለውን እውነተኛ የህዝብ ስቃይን በዉሸት ሪፖርት እንዲሸፈን አድርገዋል።

በቅርብ ጊዜ ደግሞ የኢምግረሽንና ዜግነት አገልግሎት በዎላይታ አካባብ ይጀምራል ተብሎ እየተጠበቀ በአቋራጭ ወደ አርባምንጭ ማዕከል እንድሆን ስሰራ ከአጨብጫብነት ዉጪ እንደ ህዝብ ተወካይ የሚገባዉንና ፍትሀዊ አሰራርን ተከትሎ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አለመስራትም የእሳቸው መገለጫ ሆነዋል።

ይህም ብቻ ሳይሆን በትልቅ ተስፋ እየተጠበቀ የነበረዉን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ዕድል በርዕሰ መስተዳድሩ አማካይነት ለአርባምንጭ ለማድረግ የሚሰራዉን ሴራ ለማስቆም ያለመታገልና ለሁሉም ጉዳይ ዝምታን መርጦ ቁጭ ብለዋል።

Wolaita Times

17 Nov, 14:11


የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አመራርና ተቋማዊ የእድገት ጉዞ ወደለየለት አዘቅት እየተንደረደረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው የተቋሙ ሠራተኞች ገለጹ።

"ከድጡ ወደ ማጡ" እንዲሉ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አመራር እና ተቋማዊ የእድገት ጉዞ ወደለየለት ከፍተኛ አዘቅት እየተንደረደረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ታማኝ የመረጃ ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ገልጸዋል።

በየኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ የሚመራው የአመራር ስብስብ "ስትራቴጂክ ጉዳዬች ላይ ትኩርት ሰጥቶ ከመስራት ይልቅ ለግል ጉዳዬቻቸው ቅድምያ የሰጡ ናቸው" ብለዋል የመረጃ ምንጮች።

ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በተጠባባቂነት የአመራር ምደባ ከተሰጣቸው ጊዜ ጀምሮ አንዳች ፋይዳ ያለው ተግባር ሳይሰሩ አንድ ዓመት ማለፉን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሌት ተቀን እረፍት ለሚነሳቸው እና ከእንቅልፍ ለሚያባንናቸው «የሙዝ እርሻ ልማት እና ንግድ ሥራ» እንጂ የዩኒቨርሲቲው ዋና ዋና ተግባራት ለሆኑት መማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት እንዲሁም አስተዳደራዊ እና ተቋማዊ የልማት ሥራዎች ግድ እንደማይላቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ጭምር ይናገራሉ።

የኢዜማው አለቃ እና የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምልምል የሆኑት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እርሳቸውም እንደ አለቃቻው ነፍጥ አንግባው ጫካ ባይገቡም ግንባር ቀደም አፍቃሪ ኢዜማ መሆናቸውንና በአርባ ምንጭና አካባቢው ባሉ ሰፋፊ የሙዝ እርሻ ጫካዎች ሙዝ ሲተክሉ እና ሲያስተክሉ የሰነበቱ “ምሁር ልማታዊ ባለሀብት” እንደሆኑ ይወራል።

ግለሰቡ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሀ ሀብት ምህንድስና መስክ በመምህርነት ቆይታቸው ከመንግስት ሰዓት ሰርቀውም ሆነ ትርፍ ሰዓታቸውን ተጠቅመው በግል ሀብት ማፍራታቸው በአንዳንድ ወዳጆቻቸው ሚደነቅ እና የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም፤ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ግን ስለሙዝ እርሻ እና የንግድ ስራዎቻቸው ስለሚቀላጠፍበት ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ከማውራት በስተቀር እንደ ተቋም በሁሉም ስትራቴጂያዊ የሥራ ዘርፎች አቅደው የፈጸሙት ተግባራት የለም፣ እንዲፈጸምም አመራር አልሰጡም፤ ይህም ተቋሙን በአፈጻጸም ከሚጠበቀው በታች እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል በማለት የመረጃ ምንጮቻችን በምሬት ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በግብርናው የልቀት ማእከል ለመሆን ራእይ መያዙን የዘነጉት ዶ/ር ጉቼ በተቋም ደረጃ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ የግብርና ልማት መልካም ስራዎች እንዲቆሙ በማድረግ «የግል እርሻ ልማት ስራ» ላይ ብቻ መጠመዳቻው ግን እጅጉን እንዳሳዘናቸው እና የተቋሙ መጻኢ ዕጣፈንታ እንደሚያሰጋቸው ምንጮቻችን ለሚዲያችን ገልጸዋል።

በኢዜማው አለቃ እና በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መታመናቸውን በሚያሳብቅ መልኩ ማንም ምንም እንደማያመጣ እና ከኃላፊነት እንደማይነሱ በተደጋጋሚ በገሀድ ሲናገሩ እንደሚደመጡ እንዲሁም "ከህግ አግባብ ውጪ ያለውድድር" የተሰየሙበት የፕሬዝዳንትነት ሹመት የማያስጨንቃቸውና ግድየለሽ መሆናቸው ተቋሙን ከያዘው ራእይ እና ተልዕኮ በማላቀቅ ከተወዳዳሪነት ውጪ እያደረገው ይገኛል ብለዋል ምንጮቻችን።

"ከድጡ ወደ ማጡ" እንዲሉ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አመራር እና ተቋማዊ የእድገት ጉዞ ወደለየለት አዘቅት እየተንደረደረ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ለሚዲያችን የገለጹት ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን፤ ግለሰቡ ግን አሁንም በግል ውጤታማ የሆኑበትን የሙዝ እርሻ ልማት እና ንግድ ሥራዎችን በተቋም ደረጃ ለማስፋት ዕቅድ መያዛቸውን ጠቁመዋል።

ለዚሁ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዲሆን በት/ት ሚኒስቴር እና በገንዘብ ሚንስትር ትዕዛዝ በቦዲቲ፣ በአበላ አባያ እና በአረካ ከተሞች የሕንጻ ግንባታቸው ተጀምሮ እንዲቋረጡ የተደረጉ የካምፓስ ማስፋፊያ ይዞታዎችንና አዲሱ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶቹ ተጠባባቂ ሆነው በዩኒቨርሲቲው ከተመደቡ ጊዜ ጀምሮ ስራ ያቆሙ የምርምር ማዕከላትን በኪራይ በመጠቀም መሆኑ ተመላክቷል።

የዳውሮ ታርጫ ካምፓስን ጨምሮ ከፍተኛ ቅሬታ የፈጠሩ ነባር ግንባታዎች ሆን ተብሎ ትኩረት እንዲነፈጋቸው እና እንዲቋረጡ መደረጉ ሳያንስ ገንዘብ ሚኒስትርን ሎቢ በማድረግ አዲስ ከሚጀመሩት የግንባታ ፕሮጀክቶች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት መመዝበር እና የግል ሙዝ እርሻን ማስፋፋት ሌላኛው ስውር የሀብት ምንጭ እንደሚሆን ተጠባቂ ነው ብለዋል መረጃውን ያጋሩን አካላት።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተቋም አፍራሽ ስውር ተልዕኮ አንግበው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ግድ የለሽ ተግባራቸው ያሳያል ያሉት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃ ምንጮቻችን፤ በትምህርት ሚኒስትር የከፍተኛ አመራሮች ምደባ እና ስምሪት መመሪያ መሰረት አስቸኳይ ውድድር ወጥቶ ህግ ተፈጻሚ እንዲሆንና ፕሬዚዳንቱ ወደሚወዱት የሙዝ እርሻ ልማት እና ንግድ ሥራቸው እንዲመለሱ የመረጃ ምንጮቻችን አስተያየት ሰጥተዋል።

በተግባር አፈጻጸም ተቋሙን የኋሊት እየጎተቱ ያሉ ምክትሎቻቸው፦ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በበርካታ ብልሹ አሰራር የሚታሙት የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተክሌ ሌዛ "በደባ እና በተሰረቀ የሴኔት ድምጽ" የያዙትን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲለቁ፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አክበር ጩፎ እንዲሁም የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውድነህ ቶማስ ተጠባባቂ ሆነን መስራት ከጀመርን ስድስት ወር አልፏል ያለ ውድድር ወደ ሙሉ ይጽደቅልን" የሚሉትን የቦርድ ተማጽኗቸውን ትተው በጊዜ ወደ መማር ማስተማር ሥራ እንዲመለሱ እንዲሁም የተቋሙ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ምሁራን ሁሉ ለህግ ተፈጻሚነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ከባለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በተቋሙ ሲፈጸም የቆየውን ከፍተኛ ምዝበራ እና ተቋም የማዳከም ስውር ሴራ በተጨባጭ መረጃዎች አስደግፈን “የምርመራ ዘገባ” በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita_sodo

ለመሆኑ ብልፅግና የራሱን አንስቶ በኢዜማ ሰው ተቋሙን ለመቅጣት ለምን ወሰነ? .... በWolaita Times official website ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://wolaitatimes.com/?p=5099

Wolaita Times

16 Nov, 16:04


አሳሳቢው አዲስ አበባ-ቡታጅራ-ሀላባ-ዎላይታ ሶዶ መንገድ ብልሽት እና የተጠቃሚዎቹ ቅሬታ

በተለምዶ ከአዲስ አበባ _ዎላይታ ሶዶ በመባል የሚታወቀዉ መንገድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ፣ ስልጤና ጉራጌ ዞኖች ዉስጥ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ተበላሽቷል። ይህ መንገድ የደበብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦችን እርስ በርስ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም ጋር የሚያገናኝ ዘርፈብዙ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያለው ወሳኝ መንገድ በመሆኑ ችግሩ በጣም አሳሳቢ ሆኗል።

አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ለአላስፈላጊ የመለዋወጫ ወጪ የመንገዱ ብልሽት እየዳረገን ነው ብለዋል። አንዳንዶቹ ተጨማሪ 60 ኪ.ሜ በሚያስኬደው የአዋሳ መንገድ መጓዝ መጀመራቸዉንም ገልጸዉልናል። በዛም ምክንያት አሁን ያለዉ ታሪፍ አያዋጣንም ብንልም የሚሰማን አካል አጥተናል ብለዋል።

አንዳንድ ያናገርናቸዉ ተሳፋሪዮች ደግሞ በበኩላቸዉ፣ የመንገዱ ብልሽት ጉዟቸዉን በማስተጓጎልና ምቾት በመንሳት እያማረራቸዉ መሆኑን ገልጸዋል። አሽከርካሪዎችም በአዋሳ መንገድ ለመሄድ ዋጋ እየጨመሩ እንደሚያስቸግሯቸዉ ጠቅሰዋል፤ ወዳሰቡበት በጊዜ መድረስንም አዳጋች ማድረጉንና የትራፊክ አደጋም እንዲከሰት ምክንያት እየሆነ መሆኑን ጠቁመዋል።

አንዳንድ በተበላሸዉ መንገድ አካባቢ የሚኖሩ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በበኩላቸዉ መንገዱ መበላሸት ከጀመረ የተወሰኑ አመታት ቢያልፉም አሁን ላይ ግን እጅግ አስከፊ በሚባል ሁኔታ መበላሸቱን ጠቁመዋል።

በዚህም ምክንያት የመኪና ፍሰት እንደቀነሰና ያም የንግድ እንቅስቃሴያቸዉን እንደጎዳ አንስተዋል። የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያናገራቸዉ አንድ የተሽከርካሪ ባለንብረት በበኩላቸዉ መንገዱ በከባድ ሁኔታ በመበላሸቱ ለመለዋወጫ እቃ አላስፈላጊ ወጪ ዳርጎናል ይህ ለእኛ ብቻ ሳይሆን በሌለ ዶላር በዉጭ ምንዛሪ የሚገዙ እቃዎች ፍላጎት እንዲጨምር ያደረገ ነው ስለዚህ በተዘዋዋሪ መንግስትንና ልማቱንም የሚጎዳ ነዉ ብለዋል።

በመሆኑም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የሚመለከተዉ አካል ይሄንን የደበብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦችን እርስ በርስ እንዲሁም ቀጥታ ወደ ሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ የሚያገናኝ ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያለው መንገድ መሆኑ ታሳቢ በማድረግ ለብልሽቱ እልባት እንዲሰጥ እናሳስባለን።


👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia

አሳሳቢው አዲስ አበባ-ቡታጅራ-ሀላባ-ዎላይታ ሶዶ መንገድ ብልሽት እና የተጠቃሚዎቹ ቅሬታ👇
https://wolaitatimes.com/?p=5095

Wolaita Times

15 Nov, 15:56


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ከሕገመንግስታዊነት አንጻር በኢሕአዴግ ዘመን የነበሩ ክፍተቶች እንደነበሩ እና በዋናነትም በብዙዎች ትግሎች ሲካሄዱ የነበረዉም ሕገመንግሥቱ እንዲከበር እንደነበረ ይታወሳል፣ የአሁኑ መንግስት ሕገመንግሥቱን ባልቀየረበት ሁኔታ በሪፎርም የሕዝቡን ጥያቄዎች እመልሳለሁ እያለ ሐገሪቷ በዚህ ደረጃ እንዴ በታሪኳ ያላየችዉ እልቂት እና መተላለቅ ሰፈነባት ? በዛዉም አያይዘዉ የነዚህ ሁሉ ችግሮች መነሻ ሕገመንግሥቱ ነው የሚሉ ሰዎች አሉና ለዚህ አስተያየቶት ምንድነው ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔ ሕገመንግሥቱን እንደ ቁራንና መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ነዉ ብለዉ ከሚያምኑ ተርታ ባልሰለፍም መከበር እንዳለበት ግን በጽኑ አምናለሁ። በኢትዮጵያ ታሪክ ሰላም የሚባለው በአንጻራዊነት ይህ ሕገመንግሥት የተተገበረበት የኢሕአዴግ ዘመን እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው።

ወደ ዘመነ ብልጽግና ቀዉሶች ስንመለስ፣ በመጀመሪያ ለለዉጡ መነሻ የሆነዉ የ
#Oromoprotest ምክንያታዊና ብሶቶቹም በተጨባጭ የኢሕአዴግ ኢ_ሕገመንግሥታዊ አካሄዶች ምክንያት የተፈጠረ ነው።

የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን መነሻ ይሁን እንጂ ብሶቱ ያደረ ነው። የኦነግ ተገፍቶ ከሽግግሩ መዉጣት፣ በጦሩ ላይ የተወሰደ ኢ_ሞራላዊ እርምጃ (ካምፕ የገባ ሠራዊት ላይ መተኮስ)፣ የኦሮሞ ተማሪዮችንና ሊህቃንን ማሳደድ (በስዬ አብርሃ ገለጻ የእስር ቤቶችን ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ መለወጥ)፣ ኦህዴድም ቢሆን ከኦሮሞ ሕዝብ ብዛት አንጻር በተለይ በፌደራል መንግስት ቁልፍ የሚባሉ ሥልጣኖችን (የፖለተካ፣ የመከላከያ እና የደኅንነት ስልጣን) አለማጋራት፣ አዲስ አበባ ፊንፊኔነቷን ጠብቃ አለመገንባቷ፣ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከአዲስ አበባ በጉልበት እንዲነሳ የተደረገበ እና ለይስሙላ የተመለሰበት አግባብ፣ እነዚህ እና የመሳሰሉ ምክንያት የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላዉ የበለጠ ተጨቁኛለሁ ብሎ ያምን ነበር፣ በአንጻራዊነት እዉነት እንደነበረዉም መካድ አይቻልም።

እናም ይህንን ሐቀኛ እና ምክንያታዊ የሕዝብ ብሶት የኦሮሞ ሊህቃን የመሩበት መንገድ የተሳሳተ ይመስለኛል፣ በተለይ የኦሮሞ ሕዝብ የፌደራል ስርዓቱን ታግሎ ማምጣቱንና የትግራይ እና የዎላይታም ሕዝብ በመርህ ደረጃ ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር ብዙ ነገሮችን የሚጋራ መሆኑን የዘነጉ አካሄዶች ተፋፋሙ። በተለይ በሕወሓት የደኅንነት ና በአንዳንድ የመከላከያ አመራሮች የሚወሰዱ ጸረ_ሕገመንግሥታዊ እርምጃዎች ማፈናቀልና የመሳሰሉት ነገሩን አባባሱት።

በዚህና በሌሎች ምክንያቶች የኦሮሞ ሊህቃን ኦሮ_ማራ የሚባል ጥምረት ለመመስረት ብዙ የቀኝ አክራሪ ኃይሎችን መቀስቀሻዎች ገዙ። የሚገባኝን ድርሻ ላግኝ ሕገመንግሥቱ ይከበር የሚለዉ የሕዝቡ ትግል ተጠልፎ እገሌ ይዉረድ፣ እገሌ ካልጠፋ፣
#ወያኔ ካልጠፋ ማለት ተጀመረ። በተለይ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመቻቹ ዴሞክራሲያዊ የዉይይት መድረኮችም ብዙ ቁም ነገሮች ቢነሱበትም አሁንም የመጠፋፋት ሱስ የተጠናወታቸዉ ኃይሎች እንቅፋትነት እርሳቸዉ ለሐገር ሰላም ብለዉ ስልጣን ለቀቁ።

የመጣዉም መንግስት ሪፎርም አደርጋለሁ በሚል ተስፋ እንዲሁም የቀድሞ መንግስት የሰራቸዉን ሥራዎች ሁሉ በመወንጀል ብዙ ደጋፊ አሰባሰበ (ያጠፉትንም፣ የተበደሉትንም፣ ሽብርተኞችንም ጭምር ያካትታል) ፣ በተለይ ኦሮ_ማራ የሚለዉ አሰራር ሁለቱም በየፊናቸዉ ያቀዱትን አቅደዉ ያዝረከረኩትን አዝረክርከዉ የሚያረጉት እንቅስቃሴ ሐገሪቷን በብርቱ ጎድቷል፣ ከፋፍሏል፣ አገዳድሏል።

በተለይ የትግራይ እና የዎላይታ ሰዎችን እንደ ጠላት በመፈረጅ የሚካሄደዉ ጸረ_ሕገመንግሥታዊ አካሄድ ሐገሪቷን ለእንዲህ አይነት ዉድቀት እና ድቀት እንደሚዳርግ ብዙዎች አልተገለጠላቸዉም ነበረ። ከተቋማት በዘረኛ መንገድ ሰዎችን መቀነስ ሐገርን ለዉድቀት ዳርጓል። የኦሮ_ማራ ኃይሎች በጋራ እና በተናጠል የጸረ_ትግራይ ኃይሎች የኩሽ ኃይሎች፣ በንግድ የተሻለ ተሳትፎ ያላቸዉ ኃይሎች (የኢኮኖሚ አሻጥር እንዳይሰሩ ሊሆን ይችላል) እና ጸረ_ዎላይታ ኃይሎችን አሰባስበዋል።

ስልጣን በዚህ ጸረ_ሕገመንግሥታዊ አግባብ ለማከፋፈል ሞክረዋል፣ ይህም ተቋማትን አሽመድምዶ ሕዝቡን ከፋፍሏል፣ በሐገሪቷ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ጥርጣሬና ጥላቻን አንግሷል፣ social fabric በጣጥሷል። በተለያዩ አካባቢዎች ግጭትና መፈናቀሎችን፣ መንግስታዊ ሽብሮችን እንዲሁም የእርስ በርስ ጦርነቶችን ወልዷል። በተለይም ኦሮ_ማራ አጋር አድርጎ ያሰባሰባቸዉ የአማራና የኦሮሞ ኃይሎች በመፎካከር በሚወስዷቸዉ እርምጃዎች በመንግሥት አመራሮች መሐል ከፍተኛ ጥርጣሬ ዘርቶ እስከማገዳደልም ደርሷል።

ይሕ ሕግ የማይገዛዉ አመራር ና አሰራር፣ በተለይ የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም ልዩነቱ ተካርሮ ብዙ የአማራ አመራሮች በመተፋታቸዉ ፣ክልሉ ወደ ጦር አዉድማነት ተቀይሯል። እንግዲህ ይሕ ከሕገመንግስቱ ያፈነገጠ የብልጽግና አካሄድ የፈጠረዉ ቀዉስ ነው። መርሕና ሕግ የማይገዛው ብልጽግና የኤርትራንም ጉዳይ በሴራናበደባ በመያዙ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዳለች።

የትግራይም ጦርነት ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ ወንጀሎች አደባባይ የተሰጡበት ነው የነበረዉ፣ የሕወሓት እብሪትና ወንጀል፣ የሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት፣ የጦሩ ሪፎርም ክሽፈት፣ የሕግ አስፈጻሚዉ አካል አግላይነት፣ የአማራ ክልል የሕገመንግስት ጥሰት፣ የመንግስት ሚዲያዎች እና ጀሌዎቻቸዉ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያደረጉት የጅምላ ፍጅት ቅስቀሳዎችን ማንሳት ይቻላል።

ከላይ የጠቀስናቸዉ የተለያዩ አካላት የሰሯቸዉ ወንጀሎች ሁሉ ሕገመንግስቱን በመጣስ የተደረጉ ናቸዉ ማለት ይቻላል። በተለይ ትግራይ ይህ የተለያዩ ብሔሮችን የሚያሳትፍና ሥልጣን የሚያጋራ ሥርዓት ለማምጣት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍላለች፤ የብልግና አካሄድ ይህንን መስዋዕትነት ከቁብ የሚቆጥር አልነበረም።

ዎላይታም ቢሆን በአንጻራዊነት ከተተገበረዉ ፌደራል ሥርዓት ከሌሎች የደቡብ ሕዝቦች ጋር በግምባር ቀደምነት ተቋዳሽ የሚሆንበት እድል ያገኘዉ ብዙ መስዋዕትነት ካስከፈለዉ የዎጋጎዳ ትግል በሁዋላ ነው፤ ብልጽግና ይህንንም ከቁብ አይቆጥረዉም በአካሄዱ። እነኝህ በብርቱ ትግል በኢትዮጵያ ሐገረመንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ የበኩላቸዉን የሚያበረክቱበትን መንገድ የተጎናጸፉ ሕዝቦችን ነጥሎ ማግለል፣ ለሐገሪቷ ውድቀት መነሻ ነው ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያ የበለጠ አካታች መሆን ሲገባት ብልጽግና የሰራዉ የበቀልና የንቀት እንዲሁም የጥላቻ መንገድ ሐገሪቷን እዚህ ቀዉስ ዉስጥ ከቷታል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህ መንግስት ሐቀኛ የፌደራል ሥርዓት ተግብሬአለሁ ይላል እና እንዳሉት የፌደራል ሥርዓቱን ትግበራ በብርቱ የሚሻዉ የዎላይታ ሕዝብ ከዚህ መንግስት የሚፈልገዉን አግኝቷል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በአጭሩ አላገኘም። ጭራሽ እንደጠላት ተፈርጇል፣ ተጠቅቷል። ለምሳሌ በፈለገዉ የሐገሪቷ ክፍል የመኖር መብቱ ተገፎ ተጠቅቷል፣ የክልል ጥያቄዉ ታፍኗል፣ በአዲሱ ክልል ያለ ድርድር በጫና እንዲገባ ተደርጓል። ከሥልጣን አንጻርም ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረ ብሔር ደህና የሚኒስቴር መስሪያ ቤት እንኳን እንዳይመራ ተደርጓል። በፈደራልም፣ በክልልም ሚዛናዊ ዉክልና ተነፍጓል (የትግራይም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው )።

Wolaita Times

15 Nov, 15:56


በዚህ መንግስት ዘመን በሐገሪቷ አቅጣጫ ላይ በዉሳኔ የሚሳተፍበት መስመር ተዘግቷል። ይህ ሁሉ ወድመትና እልቂት ሲካሄድ መተንፈሻ መንገድ እንዳይኖረዉ ተደርጓል። በነገራችን ላይ 40ሺ የዎላይታ ልጆች ከመከላከያ የተቀነሱት በትግራይ በሚካሄደዉ ጦርነት ላይ ጥያቄ የማያነሳ ጦር ለመፍጠርም ጭምር ነዉ፣ ሕወሓት በመከላከያ ተስፋ ከቆረጠባቸዉ ምክንያቶች አንዱ ያ ነው። ሌላዉ የትግራይ ተወላጆች ቅነሳና የጀነራል ሰአረ መኮንን ግዲያ ሊሆን ይችላል።

በዚህ በጉልበት በተመሠረተዉ ክልል እንኳን የመጀመሪያ ከተማ ተብሎ የነበረዉን መልሶ ብልጽግና ክዶታል፣ ክህደት ልማዱ ስለሆነ ብዙም አይገርምም። ስለዚህ በፍጹም ፍትሐዊ የፌደራል ሥርአቱ አተገባበር ሰፍኗል የሚባለዉ ተራ ቀልድ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደዉ በግርድፉ የዎላይታ ሕዝብ በሕገመንግስቱ ላይ ቢደረግ የሚደግፋቸዉ ማሻሻያዎች ምን አይነት ናቸዉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በጣም ብዙ ሊሆን ይችላል፣ እንደየ ሁኔታዉ ሰጥቶ በመቀበል መርሕ የሚቀየሩ አቋሞችም ስለሚኖሩ እሱን እንተወዉና ግን የእኛ ጥያቄ ከማሻሻያዉ በፊት ያለዉም ቢሆን በሐቀኛነት ይተግበር ነው። ፈላጭ ቆራጭነት እና አግላይነት እንዲሁም ለሕገመንግስት መንግስት አለመገዛቱ ከባድ ጥፋት አድርሷል።

አግላይነት እዉቀጥ እንደ ቁምጣ የሚያጥራቸዉን ሊህቃን የበቀል ጥም ሊያረካ ይችል ይሆናል፤ ሐገሪቷን ግን እያፈራረሰ ነው። ኢትዮጵያ ዉስጥ አንዱ የሠራዉን ሌላዉ የሚያጠለሸዉ ከዚህ መገለል ከሚፈጥረው የበቀል ስሜት የተነሳ ነው፣ የመበቃቀል አዙሪት ማብቃት አለበት፤ ዛሬ የሚሰራ ተንኮል ነገ ሌላ ተበቃይ ትዉልድ ይፈጥራልና። ማናችንም ማናችንንም በዘላቂነት ማንበርከክ አንችልምና የመናናቅ ፖለቲካ ቢያበቃ ይበጀናል።


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏

https://wolaitatimes.com/?p=5091

Wolaita Times

15 Nov, 15:56


የኦሮሞ ፌደራል ስርዓት አቀንቃኞች ሃዲዱን ስተው ይሁን ? የፈደራል ስርዓት እንዲከበር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉትን በመዘንጋት ታሪካዊ ስህተት አይሆንም ? እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽና ቁምነገሮችን ይዘናል ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ👇

ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀ ጥንቅር ነውና በትዕግሥት ያንብቡ!

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ፕሮፌሰር እንግዲህ እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ እንላለን። ያዉ ባለፈዉ እንዳሉት የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ እንግባ።

በዎላይታ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ጠንካራ ፌደራሊስት እንደሆኑ ይታወቃል፥ ለመሆኑ በሐሳብ ደረጃ የፌደራል ስርዓቱ በዎላይታ አካባቢ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበትን ምክንያቶች ምን ምን እንደሆኑ ቢጠቅሱልን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አሁን ኢትዮጵያ ለምትከተለዉ በዋናነት ቋንቋ እና ማንነትን መሠረት ላደረገዉ የፌደራል ሥርዓት በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ነገሮች መሀከል፦

👉ሐገሪቷ የሚንሊክን ወረራ እና ጭፍጨፋ ተከትሎ በጉልበት ተፈጥራ በጉልበት መቀጠሏ ጋር ተያይዘዉ የተፈጠሩ ችግሮችን በአሳታፊነት ለመፍታትና የጋራ ሐገር ለመፍጠር በተለይ የእርስ በርስ ጦርነቶችን ለመግታት።

👉 የአስተዳደር መዋቅሮች ማዕከላዊነትን ተከትለዉ ነባራዊዉ እና ታሪካዊዉ የሕዝቦች አሰፋፈር እንዲሁም ስነ ልቦና ሆን ተብሎ በሚቃረንና የገዢውን ክፍል ዘላለማዊ ስልጣን እና ጥቅም ለማስጠበቅ እንዲመች ተደርጎ እየተዋቀረ በመኖሩ ያንን ችግር ለመፍታት።

👉 የብሄሮች ቋንቋ ከጨዋታ ዉጪ የሚሆንበትን አወቃቀር መከተልና አይደለም በማዕከላዊ መንግሥት ተቋዋማት ፣ በየመንደሩም ቢሆን የሥራ ቋንቋ አለመሆናቸዉ (ቱርጁማን)፣ የፈጠረዉን ችግር ለመቅረፍና ዜጎች ከነቋንቋና ማንነታቸዉ ኢትዮጵያዉያን የሚሆኑበትን አዉድ ለመፍጠር።

👉 ኢትዮጵያ ከዜጎቿ ገሚሶቹ ልጆቿ፣ ቀሪዎቹ ጠላቶቿ፣ አንዳንዶች ደግሞ አጃቢዎቿ ሆነዉ መኖራቸዉን ለማስቀረትና ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ( በself rule )፣ እንዲሁም የማዕከላዊዉን መንግስት ስልጣንን እንዲጋሩ ( በshared rule ) ከእኔ አዉቅልሐለዉ ባይ ተንኮለኛ እና ወገንተኛ አሰራር ለማላቀቅ።

👉 ሕዝቦቿ ዉግንና በሌላቸዉ ጨቋኞች በየዘመኑ ሚዛን ለከፋ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ መዳረጋቸውን በማስቀረት የተሻለች ሐገር ለመፍጠር።

👉 የመሬት ቅርምትና ወረራ እንዲሁም ጭሰኝነት በብሄር ተለይተዉ መፈጸማቸዉ በተጨማሪ ሕዝቦች በአገዛዞች ሲስተናገዱበት እና ሲታዩበት የነበረዉ የተለያዬ ደረጃ ስለነበረ ያ የፈጠረዉን ልዩነት በዴሞክራሲያዊ አግባብ ለማስተካከል።

👉 በመንግሥታት ይፈጸም የነበረዉ የብሄር ጭቆና ከአገሪቷ አቅም ( Economic አቅም ) ከሚቀርበዉ ሁሉ እኩል ተቋዋዳሽነት ሆኖ ስላልኖረ ያንን ለማረቅ።

👉 ዜጎች በሐገሪቱ አቅጣጫ ላይ በሚጋሩት ስልጣን በኩል፣ የወሳኝነት ሚና ያላቸዉ ባለድርሻ እንዲሆኑ ለማስቻል ተቋማት ብዝሐነትን ታሳቢ አድርገዉ እንዲገነቡ ለማስቻል።

የብሄር የጭቆናዉን ቀምበር ለመሥበር ይካሄዱ የነበሩ ሐገሪቷን እስከማፍረስ በማለም የተደረጉ ትግሎች፣ በመፈቃቀድ ላይ በሚመሰረት ፌደራላዊ አንድነት እንዲስተናገዱ ለማስቻል እና የመሳሰሉት ምክንያቶች እንደሆኑ ግልጽ ነው።

በምክንያታዊነት ተመሥርተዉ በማስረጃ አስደግፈዉ ኢትዮጵያን እንደቀኝ ገዥ ከሚመለከቱ እስከ መለስተኛ የባህልና ቋንቋ መከበርን ጨምሮ የፖለቲካ ዉክልናን የሚጠይቁ ሐይሎችን ጥያቄ በመመለስ ሐገሪቷን ለማስቀጠልም በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ፈደራላዊ አንድነት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱም ጭምር መሆኑ እሙን ነው፤ በሐቀኝነት በሙላት ባይተገበርም።

ዎላይታንም በዚህ ማዕቀፍ ካየን ብዙ ነገሮች እጅግ በጣም አሳዛኝና የሚያስቆጭ ሆኖ እናገኛለን። ዎላይታ ከሚኒሊክ ወረራ በፊት ሐገር ነበር። እጅግ በጣም ጠንካራ ሐገር ለመሆኑ የሚንሊክን ጦር ስድስት ጊዜ ማሸነፉ እና ወረራዉን ለሰባት ዓመታት ተቋቁሞ ከመዝለቁ ባሻገር በተቻለ መጠን ከአለም ሥልጣኔ ጋር ለመራመድ ያለ ከልካይ ይታትር የነበረ ሐገርና ሕዝብ ነበር።

ለዚህ ማሳያነት ዳልቦ የነበረዉ ስልክና ራሱ የሕዝቡ የፈጠራ ዉጤት የሆነዉን ማርጯ የሚባለዉን የመገበያያ ገንዘቡን ብቻ መጥቀስ በቂ ይመስለኛል። ከጥጥ ልብስን የፈጠረ የመጀመሪያ ሕዝብ መሆኑን መጥቀስ ይቻላል። ዎላይታ ለሚኒሊክ ወረራ ዝም ብሎ አልገበረም። ሐገርነቱን ለማክሰም እና በባርነት ሊገዛዉ የመጣዉን ወራሪዉን የሚኒሊክ ጦር ለተከታታይ ሰባት ዓመታት በተካሄዱት እጅግ በጣም አሰቃቂ ጦርነቶች መሀል ስድስቱን በማሸነፍ ሐገርነቱን ማስጠበቅ ቢችልም በሚያሳዝን ሁኔታ በሰባተኛዉ ተሸንፎ ሐገርነቱን አጥቷል።

ከጦርነቱ በኃላ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በሚኒሊክ ጦር ተፈጽሞበታል፥ በባርነት ተቸርችራል፣ እንደ ከብት እየተነዳ መጥቶ በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተበትኖ በባርነት ለመኖር እና ለስልቀጣ ለመጋለጥ ተገዷል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ይህ ጀግናና ታላቅ ሕዝብ አንድም ቀን ባርነትን አሜን ብሎ ተቀብሎ አያዉቅም።

እራሱ ንጉስ ጦና ቆስሎ ከተማረከ በሁዋላ በተሰጠዉ ድጋሚ በሞግዚት ስር በተሰጠዉ ሹመት ተጠቅሞ ሕዝቡን ከአስከፊዉ የሚኒሊክ አገዛዝ ለማላቀቅ ድጋሚ አመጽ አካሂዶ ከሽፎበታል፤ ቀሪ ዕድሜዉን በግዞት ለማሳለፍ ተገዷል። ይህ በዘመናዊት ኢትዮጲያ የመጀመሪያ የተደራጀ በሐገረ መንግስቱ ላይ የተቃጣ አመጽ ነው ማለት የሚቻል ይመስለኛል። አጭበርባሪ የታሪክ ጸሐፍት ከሚሉት በተቃራኒው።

በአድዋ ጦርነት ከተሰለፉ የዎላይታ ጦር መሪዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሐጤሮ ሐኒቼ ሁዋላ ላይ ባስነሳዉ ግርግር ጨቋኙን ስርዓት ማስደንገጥ ቢችልም እሱንና ወገኖቹን ለከፋ መከራ ዳርጎ ወገኖቹን ለትግል አነሳስቶ ቢያልፍም ዋነኛ ህልሙ ሳይሳካለት ቀርቷል። ታዲያ እስከዛሬ ለሚደረገዉ የዎላይታ ሕዝብ ትግል እርሾ መሆኑ ሳይዘነጋ። ከዛን ጊዜም ጀምሮ የዎላይታ ሕዝብ ሲታገል ነው የኖረዉ ለብሔራዊ ክብር፣ ሕልዉና እና ለመብቱ።

የፌደራል ሥርዓቱን ጨምሮ አሁን ላለዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሠረት ነው በሚባለዉ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅትም ሰለሞን ዋዳ እና ለንደን ካንኮ የተባሉ ሁዋላ ላይ በደርግ የተቀጩት የዎላይታ ብርቅዬ ልጆች ግምባር ቀደም ተሳታፊ መሆናቸዉ በብዙዎች ተጠቅሷል። ከዛ በተረፈ በዎላይታ አካባቢ ለዘመናት በተንሰራፋው ድሕነት ምክንያት የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆን ብዙዎች የሚመርጡት የሥራ ዕድል ከመሆኑም ጋር ተያይዞ የሐገሪቷ አገዛዞች ብዝሐነትን ላለማስተናገድ ወይንም በሸፍጠኛ መንገድ በማስተናገድ በሚፈጥሯቸዉ የእርስ በርስ ጦርነቶችም ልጆቹ በማያምኑባቸዉ ጦርነቶች ሲማገዱ ኖረዋል።

መሰል ጦርነቶችም እንዲቀሩ፣ የፖለቲካ ጥያቄ የሚያነሱ ሕዝቦች በጨቋኝ አገዛዞች ሲቀጡ የኖሩበት ዘመን እንዲያበቃና እንዳይመለስም ጭምር ነው፤ የፌደራል ሥርአቱ በዎላይታ ድጋፍ ያገኘዉ ማለት ይቻላል። ይሄ ማለት ግን የፌደራል ስርዓት ከዎላይታ አንጻር በሙላት ካለመተግበሩም በተጨማሪ በከፊልም እንዲተገበር የተደረገዉ በዎጋጎዳ ጊዜ በተደረገ ብርቱ ትግል ነው። ከዛ ባለፈ ሥርዓቱ እንከን የለሽ ነው የሚል ገታራ አቋም ግን በዎላይታ በኩል የለም ማለት ይቻላል። ብዙ ማሻሻያዎች ያስፈልጉታል።

Wolaita Times

15 Nov, 13:35


"ከዎላይታ ጋር በሰማይ በምድር አንገናኝም" ያሉ ካድሬዎች ዎላይታ ላይ የጀመሩት የበቀል በትር ምክንያት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባታል ተባለ

የደቡብ ኢትዮጵያ ብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች መገለጫ እየሆነ የመጣዉ ሴራ ትንተና፤ ጠልፎ መጣልና የዜሮ ድምር ውጤት ነው፡፡

በእውነተኛ የግንኙነት መሰረት ላይ በመቆም ስልጣንን ተቀብሎ ህዝብን በቅንነትና በግልፅኝነት የማገልገል ባህል በጣም ደካማ በመሆኑ በሀዝቦች መካከልም አለመተማመን እና እርስ በእርስ መጠራጠር ውስጥ እንዲገቡ ካደረገ ሰነባብቷል፡፡

ይህ ደግሞ ለተመሳሳይ አላማ ህብረተሰቡን አንቀሳቅሶ አንድ ግብ ላይ ለመድረስ ፈታኝ ከባቢን ፈጥሯል፡፡ ይህም ደግሞ በክልሉ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰዉ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ እንቅስቃሴዋ የተገደበና ወደ መፍረስ የምትመራ ክልል እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ይህችን በተፈጥሮ ፀጋ የተቸረች ክልል በመፍጠርና በመፍጠን፤ በመፍጠንና በመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ወቅታዊና የተከማቹ ተግዳሮቶችን ተሻግራ ለመጓዝ ይቸግራታል፡፡

በክልሉ የአመራሩ በጠልፎ መጣል የፖለቲካ ባህል፤ በእግር ጎታች እና ከተለመደው ለመውጣት ያለው ዳተኝነት ከኤሊ ጉዞ ወጥታ የእንቁራሪት ዝላይ እንዳይኖራት አድርጓታል፡፡

ገና ከተመሰረተ አንድ ዓመት ተኩል ያልሞላው ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመፍረስ አደጋ እየገጠመው መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡

ለከልሉ የመፍረስ አደጋ ዋናው ምክኒያት ደግሞ ክልሉ አሁን በተደራጀው ቅርጽ እንዳይደራጅ ስሰሩ የነበሩ የሴራ ፖለቲካ አራማጅ ኃይሎች ተጠራርተው የፊት አመራር መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ሲዳማ ክልል ከቀድሞ ደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ክልል ተለይቶ ከወጣ በኃላ የቀሩ አከባቢዎችን በጋራ ለማደራጀት የፌዴራል መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጭ ስልጣን ለመያዝ በሚመች መንገድ ክልል ለማደራጀት የሞከሩ ኃይሎች ክልሉ አሁን በተደራጀው ቅርጽ እንዳይደራጅ ሴራ ፖለቲካ መሠራቱን ገልጸዋል።

በተለይ ደግሞ "ከዎላይታ ጋር አንደራጅም" የሚለዉ ዎላይታ ጠል ፖለቲካ አሁን ከፊት ሆኖ ክልሉን እየመሩ ባሉ አመራሮች እስከ ቀበሌና ጎጥ ድረስ መሠራቱን በማስታወስ ገልጸዋል።

በዚህም የወቅቱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የአሁኑ የክልሉ ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ኃላፊ ከዎላይታ ውጪ ከሌሎች ጋር እንደራጃለን የሚል አጀንዳ በመቅረጽ በካድሬዎቹ አማካኝነት እስከ ጎጥ ወርዶ ከማስተማሩም በተጨማሪ ሚዲያዎችን ጠርቶ የሰጡት መግለጫ ዛሬም በዩቱብ ይገኛል ብለዋል።

የአሁኑ ርዕሰ መስተዳድር ሴራ የሚጀምረዉ ክልሉ በአድስ መልክ ከመዋቀሩ በፊት ገና ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሲቋቋም ጉራጌንና ዎላይታን በማግለል ነበር፡፡ የአደረጃጀት ጥያቄ አልፋና ኦሜጋ ህዝብ ሆኖ እያለ የህዝብ ቁጥር ማንሳት ሀጥያት አድርጎ የሚያስቡ ግለሰቦችን በመፈለግ የተለያዩ ኮሚቴ አባል ሆኖ እንድሰሩ አደረገ፡፡

በኮሚቴ ዉስጥ ለሚሳተፉ እንደ አስተዋጽኦ ልክ ሹሜት እንደሚሰጥ ቃል ተገባላቸዉ፡፡ለአደረጃጀት ዉሳኔ ልያግዙ ይችላሉ ብሎ ለገመታቸዉ ለተወሰኑ የፌደራል ባለስልጣናት፣ ለአብዘኛዉ ክልል አመራሮች እና ለሁሉም በሚባል ደረጃ በደቡብ ኢት/ያ ዉስጥ ለሚገኙ የዞን/ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪና ፓርቲ ኃላፍዎች በአርባምንጭ ከተማ የመኖርያ ቤት እንድያገኙ ተደርጓል፡፡

የዎላይታ ሪፍረንዴም እንዲሰረዝ ተደርጎ ብዙም ሳይቆይ በአቶ ብርሃኑ ዘዉዴ በኩል ዎላይታ ሪፍረንዴሙን ለራሱ ብቻዉን ክልል ለመሆን ሆን ብሎ ያደረገዉ ስለሆነ ቀሪዎቻችን ወደ ክልል ምስረታ መግባት አለብን የሚል የሴራቸዉን ዉጤት ይፋ አስደረጉ፡፡

በመቀጠልም ለክልሉ ማዕከልነትም ዉድድር ሳያስፈልግ በዉሳኔ እንድሆንና ለዛ እንድያግዝ ቀደም ተብሎ በተሰጡ ስጦታዎችና ቃል በተገቡ ሹሜቶች የሰከሩ አካላት ነጠላ ዜማቸዉ እንድዘፍኑ ተደረገ፡፡ ሆኖም ግን በፌደራል መንግስት ብርቱ ክትትልና ድጋፍ አሁን ያለዉ አደረጃጀት ከኔ ዉስንነቱም ተፈጠረ፡፡

በአደረጃጀቱ አልሳካ የተባለላቸዉን በበቀል ለማካካስ የሚያስችል የስልጣን ክፍፍል እና የተቋማት ድልድል እንደፈለጉ አደረጉ፡፡
ከጋሞ ዞን ዎላይታ ጠል አመራሮች ጋር ጥብቅ ግንኙነት የፈጠሩት የወቅቱ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የአሁን የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የውሃ ማዕድንና እነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አዳኝ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ ፊት "ከዎላይታ ጋር በሰማይ በምድር አንገናኝም" እስከማለት ያሰሙትን የዎላይታ ጠልነት የነበረውን አገላለጽ በማሳያነት አንስተዋል።

በተጨማርም ከቀድሞ ደቡብ ኦሞ ዞን አሪ ዞንን ለመገንጠል በማሰብ ተዋልደዉና ተዋደዉ ለዘመናት አብሮ የኖሩ ህዝቦችን በማፋጀት በርካታ ንፁሃን ዜጎች በጠራራ ፀሀይ እንድሞቱና እንድፈናቀል እንድሁም ዎላይታ ከህወሀት ጋር አብረዋል በሚል ፈጠራ ወሬ 38 ንፁሃን ዜጎች እንድገደሉ ያደረገዉ የቀድሞ የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የአሁኑ የክልሉ ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ለማሳያነት ማቅረብ ይቻላል፡፡

በዚህም ከዎላይታ ውጭ ክልሉን ለማደራጀት ተማምሎ የሰሩ እና ያልተሳካላቸው የዎላይታ ጠል ጽንፈኛ ካድሬዎች እነሱ በማይፈልጉት መንገድ በብልጽግና እሳቤ የተደራጀውን ክልል ለመምራት ተጠራርቶ ራሳቸውን የፊት አመራር አድርገው ማደራጀታቸውን ገልጸዋል።

የአሁኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይህን ተግባር በመፈጸም የአምበሳ ድርሻውን ይወስዳል ብለዋል፡፡

በዚህም እነሱ በማይፈልጉት መንገድ የተደራጀውን ክልል አፍርሰው ቀደም ስል አስበውና አቅደው በመስራት ያልተሳካውን ከዎላይታ ውጭ ክልሉን አፍርሰው ለማደራጀት እየሠሩ መሆናቸውን አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል ሲሉም አስረድተዋል።

ዎላይታ ሶዶ የክልሉ የፖለቲካና አስተዳደር ማዕከል ቢሆንም ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም ሶዶ እንደማይቀመጥና ሁሉም ስብሰባዎችና ስራዎች አርባምንጭ ላይ እንድሆን መደረጉን እንደማሳያነት አንስተዋል።

አርባምንጭ ላይ የምገነቡ ግንባታዎች የበጀት ምንጩ የክልል ሆኖ ግን በጀቱን በቀጥታ ባልሆነ መንገድ ለጋሞ ዞን በመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ለዚህም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር 500 ሚሊዮን ብር በአደባባይ ቃል ገብቶ በመስጠት እየሰራ መሆኑንም አብራርቷል።

በተመሳሳይ መንገድ ከክልሉ ዋና ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥቶ በአርባምንጭ ከተማ ይከበራል የተባለው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ወጪው ከክልሉ ካዝና ሆኖ የጋሞ ዞን ተወላጅ የሆኑ የክልሉ አመራሮች ብቻ ተደራጅቶ እንድሰሩ መደረጉንም ክልሉን የጋሞ ዞን መዋቅር አድርጎ እየሠሩ መሆናቸውን ጠቅሷል።

የዚህ ሁሉ ችግር ክልሉ አሁን ከተደራጀበት ከብልጽግና እሳቤ አደረጃጀት ፈርሶ ቀደም ሲል ዎላይታ ጤል ካድሬዎች ባቀዱት ልክ ለማደራጀት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸው ይህ ሴራ በፌደራል መንግስት ጣልቃ ተገብቶ ካልተስተካከለ ክልሉ ላይ የመፍረስ አደጋ መጋረጡን የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሩና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምሁር በሰጠው ማብራሪያ ገልጸዋል።

https://wolaitatimes.com/?p=5087

Wolaita Times

13 Nov, 14:22


"በአጀቢዎች ጋጋታ ገዥ ለመሆን ይሰራሉ፤ እየዞሩ አበባ ይቀበላሉ፤ ሼፎችን ቀጥረው ይዞ ይዞራሉ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶክተር)

በማዕከላዊ መንግስት ትኩረት የተነፈገው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተጠቁሟል።

በደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ ሕዝብ በባህሉ ፈጣሪን የሚፈራ በመሆኑ እየደረሰበት ያለውን መንግስታዊ በደልና ጭቆና ጊዜ ይፍታ በሚል እምነታቸው ይግባኝ ለፈጣሪ ብለዋል፡፡

የዎላይታ ታይምስ በተለይም በዚሁ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስታዊ እንቅስቃሴዎችን ከፓለቲካ፣ ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከማህበራዊ ተግባር አንፃር በቅርበት እየተከታተለ መረጃዎችን እንደሚያቀርብ ሚዲያ አጠቃላይ የክልሉን የሩብ አመት ሪፓርቱን የተለያዩ መረጃ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ይሄንን ጥንቅር አሰናድቶ አቅርቧል።

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በዚሁ ጠያቂ የለሌው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እመራለዉ የምለዉ ሕዝብ በእርስበርስ ሹኩቻ በማከፋፈል ዞኖችንም ተከፋፍለው በመያዝ አጀንዳ ቀርጾ በመስጠት በተሰጡ አጀንዳዎች መዋቅሮችና አመራሩ ስወዛገቡና ስሻኮት ጥቂት በጥቅም የተሳሰሩ ሴረኛና አጀንዳ አከፋፋይ ቡድኖች የራሳቸዉን የሌብነት ሰንሰሌት በጽኑ በመዘርጋት በመንግስት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ሳይቀር እየተቀራመቱ ይገኛሉ፡፡

ለማሳያነት በክልሉ እንደ ፖለቲካ ስበት ማዕከል የሚትቆጠረዉ ዎላይታ በቀድሞ ባንክ ገዥ በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖም አማካሪ በሆኑት በአቶ ተክለወልድ አጥናፉ የበላይ ጣባቂነት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ገብረ-መስቀል ጫላ መሪነት ከ500 በላይ አመራሮች ከአመራርነት በማንሳት ለሌብነት በሚሆን መልኩ የጫላዝም አደረጃጀት (ልጅ፣ ወንድም/እህት፣ የአክስት/የአጎት ልጅ፣ አክቲቪስት፣ የራሳቸዉን ጎሳ ባካተተ መልኩ እንድሁም ከዚህ በፊት የነበሩ አመራሮችን የሚቃወም) ተፈጥሯል፡፡

ይህንን ፀረ-ብልፅግና አካሄድ የተቃወሙና ቅሬታቸዉን ለፈደራል ብልፅግና ፓርቲ ያቀረቡ አመራሮች "ሙስና" በሚባል ዳቦ ስም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በክልሉ በተለያዩ ዞኖች በስመ በሪፎርም ተግባር ከ1600 በላይ የተለያዩ የፓርቲ ስልጠና የወሰዱ ወጣት አመራሮች ከሃላፊነት እንድነሱ ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የመብት ጥያቄ ያቀረቡና ሥልጣን ላይ ላሉ ቡድኖች የማይመቹ ናቸዉ ተብሎ የሚገመቱት በጋሞ፣ በኮንሶ፣ በኮሬ፣ በደቡብ ኦሞ እና በጎፋ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ክልሉ የነዋሪዎች የሰብአዊና ድሞክራሲያዊ መብቶች በጠራራ ፀሐይ የምገፈፍበት፣ ሥር የሰደደ ጭቆናና ጸረ ድሞክራሲ የሰፈነበት ክልል ስለመሆኑ በየቀኑ በምደረገዉ እስራትና ግርፋት፤ ሞትና መፈናቀል ማወቅ ይቻላል፡፡

የህግ የበላይነት እዉቅናና ክብር የመስጠት ጉዳይ በክልልችን ነውር ሆኗል፣ ግለሰቦችን ሳይሆን ህግን ያከበሩ ዜጎች ባልታወቀና ለእሳቸው ሥራ በተዘጋጀዉ ህግና ለዛ ህግ አስከባሪዎች ቅጣትና እና የስቃይ ህይወት የሚገፉ ይሆናሉ፡፡

በከበሩ ማዕድናት ዙርያ ያለዉ እሽቅድምድም እና በስመ በኢንቨስትመንት ዘመድ አዝማድ በማደራጀት የከተማ መሬት ዝርፍያዎችን በዎላይታ ሶዶ እና በአርባ ምንጭ ከተሞች የሚያካህድ፤ የተፈቀደ በምመስል መንገድ ሕገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ (በተላይም የመድሀንት እና ጦር መሣሪያ) ዝዉዉር በዲላ እና በኮንሶ መግቢያ በመንግስት መኪኖች ተጭኖ በፖሊስ እጀባ ወደ መሀል አገር የምያስገባዉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዕዉቅና ነዉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም ወር መጀመሪያ በአዳማ ከተማ በተካሄደዉ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠቃለያ ተገኝተው አንዳንድ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ዋና ተግባራቸውን ዘንግተው በአጀቢዎች ብዛትና ጋጋታ ሕዝብን በማዋከብ ገዥ ለመሆን ይሰራሉ፤ ከቦታ ወደ ቦታ እየዞሩ አበባ ይቀበላሉ፤ ስዞሩም ምግብ የሚያበስልላቸው ሼፎችን ቀጥረው ይዞ ይዞራሉ ያሉት የደቡብ ኢት/ያ ክልል መንግስት ዋና መገለጫ ነዉ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ዉሎ አዳራቸዉ አለም አቀፍ ሆቴሎች ስሆን የክልሉን ፖለቲካ የሚመሩት በየሆቴሎቹ በሴተኛ አዳሪዎች ጋር ዉስኪ እየተራጩ እንደሆነ እስከ ፌዴራል መንግስት ድረስ የሚታወቅ ሐቅ ነዉ፡፡

ይህ ተግባር ደግሞ ከክልላችን ህዝቦች ባህልና ሃይማኖት ያፈነገጠና የብልፅግና አመራርን የማይመጥን ነዉረኛ ድርግት ነዉ፡፡

በአጠቃላይ የክልሉ ፊት አመራሮች ነባር ክልል እንዲፈርስ ገፍ የሆኑ ምክንያቶችን በተላይም ስልጣንን ለገዥነት መጠቀምን፣ የልማት ኢ-ፍትሃዊነት፣ አምባገነንትን፤ አሳታፍነትን፣ ግልፅኝነትን፣ የሀሳብ ነጻነትን፣ ፍትሀዊ እና ተመጣጣኝ የፖለቲካ ዉክልና…ወዘተ በመዘንጋት እንድሁም የሾመዉን የብልፅግና ፓርቲ መርሆችንና እሴቶችን ባፈነገጠ መልኩ ሴረኝነትን፤ ቅመኝነትንና በቀለኝነት መለያ ባህሪዉ ካደረገ ሰነባብቷል፡፡

ይህንን ነዉራቸዉን ለመሸፈን ብሎ በየቀኑ የሚደረገዉ የመድረክ ድስኩር እና በየማህበራዊ ሚድያ የሚደረገዉ የፎቶ ፖለቲካ ህዝቡን አንገሽግሾታልም ተስፋ ባደረጉት ፓርቲ ላይም ተስፋ አስቆርጧል፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ እያንዳንዱን ተግባር በጥልቀት የሚያዉቀዉ ማዕከላዊ መንግስት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁኔታ ከማረም ዝምታ መምረጡ ለብዙዎች ግርምትን ፈጥሯል፡፡

ፀለምት የዋጠዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካለበት ሁኔታ እንዲላቀቅ ማዕከላዊ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይቀይር ይሁን? ወይም ጠያቂ የለሌዉ አደረጃጀት ሆኖ ይቀጥላል? የዘዉትር ጥያቄያችን ነዉ፡፡

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia

https://wolaitatimes.com/?p=5078

Wolaita Times

13 Nov, 11:01


ርዕሰ መስተዳድሩ ለስራ ዕድል ፈጠራ የተሰራውን ህንፃ ቀምቶ ስቱዲዮ እየገነባ የሚገኘውን ኢቢሲ ለ5ኛ ጊዜ ጎበኙ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በዎላይታ ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የተሰራውን ህንፃ በመቀማት የራሱን ስቱዲዮ እየገነባ የሚገኘውን ርዕሰ መስተዳድሩ ለ5ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት ጉብኝት አድርገዋል።

ይህ ከታች በምስል የምትመለከቱት በተደጋጋሚ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ የሚጎበኙት ለወጣቶች አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸርንግ ኢንዱስትሪዎች "ምርት መሸጫና ሠርቶ ማሳያ" አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ነው።

ህንፃው የሚገኘው በዎላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ ጊዮርጊስ ሠፈር ሲሆን 100% ግንባታው አልቆ በ2014 ዓ.ም ርክክብ ከተደረገ በኋላ ከ41 ክፍሎች 12ቱ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በ2016 ዓ.ም ተላልፎም ነበር።

በአሁኑ ወቅት ይህ ሕንጻ #ለEBC ተላልፎ ተሰጥቷል፤ EBC አዲስ እየገነባ ያለው ሕንጻ በዎላይታ ውስጥ የለም። ይልቁንስ EBC 100% ያለቀውን ሕንጻ ተረክቦ፣ ለራሱ በሚፈልገው ቅርጽ ክፍሎቹን እያስፋፋ እና ቀለም እየቀባ ይገኛል።

ነገር ግን ከፍተኛ የሥራአጥነት ጫና ባለበት በዎላይታ ዞን፣ በማህበር የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ፣ የመሸጫና የሠርቶ ማሳያ ማዕከላትን አጥቶ በሚቸገሩበት በአሁኑ ወቅት፣ የገበያ ማዕከሉን ከታለመለት ዓላማ ውጪ ማዋል ተገቢነት የለውም ስሉ በርካቶች ይገልፃሉ።

በከተማዋ መንግስታዊ ተቋማት የራሳቸውን ሕንጻ ገንብተው አልያም ተከራይተው መንግስታዊ አገልግሎት መስጠት ሲገባቸው ለኢንተርፕራይዞች ገበያ ማዕከልነት የተገነባው በመንጠቅ እንደአዲስ ግንባታ ሚዲያ ላይ ማራገብ ክልሉን አይመጥንም ይላሉ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሄንን ለወጣቶች ስራ ዕድል በተሰራው ህንፃ ውስጥ ባለው አንድ ክፍል እየተገነባ የሚገኘውን መንግስታዊ ተግባርን በመተው በተደጋጋሚ ጉብኝት እያደረጉ ነው የሚል የፕሮፓጋንዳ ዜና ማሰራት ተገቢነት ላይ በርካቶች ጥያቄ እያነሱ ነው። #Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Etv

Wolaita Times

12 Nov, 15:19


ከ500 ሄክታር በላይ መሬት በህገወጥ ጥቅም ትስስር ለግለሰቦች ተላለፈ"

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ500 ሄክታር በላይ መሬት ከክልሉ ሆነ ከእንቨስትመንት አሰራር ውጪ በጥቅም ትስስር በአንድ ድጋፍ ደብዳቤ ለግለሰቦች እየተላለፈ እንደሆነ ሰነዱ አረጋገጠ።

ይሄንን ህግወጥ ትዕዛዝ በበላይነት የመሩት የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ እንዲሁም የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዱ የተባለ ግለሰብ እንደሆነ ከሰነዱ ለማወቅ ተችሏል።

ይሄንን ከ500 ሄክታር በላይ የማዕድን ልማት መሬት ከክልሉ ሆነ ከእንቨስትመንት አሰራር ውጪ በጥቅም ትስስር ለግለሰቦች በአንድ ደብዳቤ ትዕዛዝ ሲሰጥ "በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች የድንጋይ ከሰል ማዕድን ከምችት መኖሩ በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ በቦረዳ ወረዳ ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ለማምረት ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘው ማራ ማይንግ ኃላፊነት የተ/የግል ማህበር ለጥናት ይዞ ከነበረው 600 ሄክታር ላይ ለድርጅቱ 10 ሄክታር ብቻ በማስቀረት ሌላው ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም በዞኑ በግልም በማህበርም የድጋፍ ደብዳቤ ለወሰዱ ተሸንሽኖ እንድሰጣቸው የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤት ባደረገው ሰብሰባ መወሰኑ ይተወሳል ሲል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ይሄንን ተከትሎ በክልሉ በቦሮዳ ወረዳ ማራ ማይኒንግ ኃላፊነት የተወሰነ ማህበር በህጋዊ መንገድ የተረከበውን ቀጥታ በህግ ወጥ መንገድ ለሌሎች በመሸንሸን ለመስጠት በመሞከሩ ማህበሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘው በመሄድ በክርክር ሂደት እያለ ተጨማሪ ሽንሸና እና ዝርፊያ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉዳዩ ዙሪያ አንድ የዘርፉ ባለሙያ ከህግ አንፃር ጠይቀን ሲያስረዳ፦ "በማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ሕጉ መሠረት በቅድሚያ አንድ ባለሀብት የማዕድን ቅኝት (Exploration) ሕጋዊ ፈቃድ ከእነ ኮኦርድኔት ነጥቦች ጋር ከተሰጠ በኋላ፣ የፀደቀ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ፣ የአከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነድ፣ የማልማት አቅም፣ የንግድ ምዝገባ ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ አስቀድሞ የተፈቀደው የተፈቀደው ይዞታ መጠን ሊቀነስ አይችልም።

ነገር ግን ባለሀብቱ የማምረት አቅሙ ደካማ ከሆነ፣ በራሱ ፍላጎት ይዞታው ይቀነስልኝ የሚል ጥያቄ ካቀረበ፣ በአከባቢው ማህበረሰብና ሥነምህዳር ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ በጥናት ከተረጋገጠ፣ ከይዞታው ሊቀነስ ይችላል። ከዚህ ውጭ ከልማታዊ ባለሀብት ቀንሰው፣ በጥቅም ትስስር ለሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት ማስተላለፍን ሕጉ አይፈቅድም" በሚል አብራርተዋል።

ሰሞኑን በክልሉ በማዕድን ዘርፍ እየተደረገ የሚገኘውን ህገወጥ ዝርፊያና አሰራር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተከታታይ እያጋለጠ ሲሆን መረጃ አውጥቷል ያሏቸውን አመራሮች ጭምር ከኃላፊነት እያነሱ እንደሆነ መዘገቡም ይታወሳል።

ክልሉ የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት እያለ ህግን በመጣስና የፍርድቤት ትዕዛዝ በመናቅ ከህጋዊ ማህበር በህገወጥ መንገድ ለሌሎች በገንዘብና በጥቅም እያስተላለፉ የሚገኘውን የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ቅሌት በተመለከተ የሚመለከተው የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የህግ የበላይነት እንዲያስከብር እናሳስባለን።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳደሩ ደረጃ በየጊዜው በሚፈጠሩ ህገወጥ አሰራር ስንመለከት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሌሎች በመግፋት በአከባቢዊነት ግልጽ የመንግሥት አሰራር በመጣስ የዝርፊያ፣ የህገወጥ አሰራር መለማመጃ እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይቀር የማይከበርበት ጋጠወጥና ህግ የሌለበት ደረጃ ደርሷል።

ውድ ተከታዮች በዚሁ ጉዳይ ላይ እልባት እስኪገኝ ድረስ ዝርዝርና ተከታታይ መረጃ ማቅረባችን አጠናክረን እንቀጥላለን።
#Ethiopia #southethiopia #gamo #Wolaita
ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5071

Wolaita Times

12 Nov, 08:29


አስቸኳይ መልዕክት ለሚመለከታቸው-የሙስና ቅሌት‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የፍርድቤት ትዕዛዝ በመጣስ ህገወጥ የማዕድን ዝርፊያ እያካሄዱ መሆኑ ተገልጿል።

ህገወጥ ዝርፊያው በህጋዊ መንገድ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ መሬት ከተረከቡ ባለሀብቶች በመቀማት ጥቅም ትስስር ለፈጠሩት በመሸንሸን እየሰጡ ይገኛሉ።

ለአብነትም በክልሉ በቦሮዳ ወረዳ ማራ ማይኒንግ ኃላፊነት የተወሰነ ማህበር በህጋዊ መንገድ የተረከበውን ቀጥታ በህግ ወጥ መንገድ ለሌሎች በመሸንሸን ለመስጠት በመሞከሩ ማህበሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘው በመሄድ በክርክር ሂደት እያለ ተጨማሪ ሽንሸና እና ዝርፊያ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከደረሰን ሰነድ ማረጋገጥ ችለናል።

ሰሞኑን በክልሉ በማዕድን ዘርፍ እየተደረገ የሚገኘውን ህገወጥ ዝርፊያና አሰራር በተመለከተ በተከታታይ እያጋለጥን ሲሆን መረጃ አውጥቷል ያሏቸውን አመራሮች ጭምር ከኃላፊነት እያነሱ እንደሆነ መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በዛሬው በዚህ ዘገባ የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት እያለ ህግን በመጣስና የፍርድቤት ትዕዛዝ በመናቅ ከህጋዊ ማህበር በህገወጥ መንገድ ለሌሎች በገንዘብና በጥቅም እያስተላለፉ የሚገኘውን የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ቅሌት በተመለከተ የሚመለከተው የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ እርምት እንዲወስድ እናሳስባለን።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳደሩ ደረጃ በየጊዜው በሚፈጠሩ ህገወጥ አሰራር ስንመለከት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሌሎች በመግፋት በአከባቢዊነት ግልጽ የመንግሥት አሰራር በመጣስ የዝርፊያ፣ የህገወጥ አሰራር መለማመጃ እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይቀር የማይከበርበት ጋጠወጥና ህግ የሌለበት እየሆነ ይገኛል።

ውድ ተከታዮች በዚሁ ጉዳይ ላይ ዝርዝር መረጃ እናቀርባለን።
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita

Wolaita Times

11 Nov, 13:50


ከላይ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ምክንያቶች ማህበሩ እጅግ ደካማ የሚባል አፈጻጸም በማስመዝገቡ ከግብረሰናይ ፕሮጀክቶች፣ ከራሱ የንግድ ተቋማት፣ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድርሻ የሂሳብ አካውንቶች በሚልዮኖች የሚቆጠር ባለእዳ ሲሆን በወቅቱ ለሰራተኞች ደሞዝ መክፈል ወደ ማይችልበት ደረጃ የደረሰና ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መክፈል የሚገባቸውን ገንዘቦች አቅም እያጠረው መሆኑ በሰፊው ይነገራል፡፡

የልማት ማህበሩ አካል የሆነው የዎልማ ጋራዥ ምንም እንኳን አጀማመሩ ለዞኑም ሆነ ለክልሉ መልካም ቢሆንም እንደቀደሙት ተቋማት ጥልቅ ግሚገማዎች ባልተደረጉበት የተከፈተ በመሆኑ አሁናዊ አፈጻጸሙ የሚጠበቀውን ያህል ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ለአፈጻጸም ድክመቱ የልማት ማህበሩ በገንዘብ፣ በተሸከሪካሪዎች አካላት፣ በሰው ሀይል፣ በክህሎት… የመደገፍ ውስንነት ቢሆንም የተለያዩ አካላት ያስጠገናቸውን ተሸከሪካሪዎች ወጭ በወቅቱ ባለመክፈላቸው እና የቦርዱም ድጋፍ ባለመኖሩ ተቋሙ በተፈለገው ልክ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

በአጠቃላይ ልማት ማህበሩ ህዝቡ የሚጠብቀውን ያህል ካለመሆኑ ባሻገር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከህዝቡ እይታና ልብ እየራቀ የመጣ ስለመሆኑ ብዙዎች የሚስማሙት እየሆነ መጥቷል፡፡

በመሆኑም በልማት ማህበሩ የሚሰሩ ሰራተኞችም ሆኑ የማነጅመንት አካላት በመቀራረብ እና በቁጭት እንዳይሰሩ የስራ ኃላፊዎች የክትትል እና ግምገማ እና ቁጥጥር አድራጊ ክፍሎችን በጥቅምና በማስፈራራት የእርምት እርምጃዎች እንዳይወሰዱ በማድረግ ስያዘናጓቸው ይስተዋላል፡፡

በማህበሩ የጋራ እቅድ አለማድረግ፣ መተግበርና ተግባርን መገምገም እንደ ታርክ ማንሳት ከተጀመረ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡በተጨማሪም ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የስራ ውይይት እና ከህዝቡ ጋር ጭምር ምክክር ባለመደረጉ ክስተቶች እየሰፉና ውድቀት እየተፋጠነ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዎላይታ ልማት ማህበር (ዎልማ) የዎላይታ ሕዝብ ብቸኛ የልማት አለኝታ ነበር፣ ነዉ። የዎላይታ ሕዝብ የረጅም ዘመናት ታሪክ ባለቤት ቢሆንም የዘላቂ ልማት ፍላጎቱን የሚደግፍ ባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ የልማት ኮርፖሬሽን፣ ሁነኛ የቁጠባና ብድር ተቋም ወዘተ የለዉም።

በዎልማ ወርቃማ ዘመናት የነበረዉ የብሔሩን ምሁራን በማህበሩ አጠቃላይ ሁኔታዎች የማወያየት ገንቢ አስተያየቶችንና ምክሮችን የመቀበል አሰራር ሊዘረጋ እንደሚገባ በርካቶች ይስማሙበታል።

በመሆኑም ጊዜ ሳይወሰድ ስለ ጉዳዩ ያገባኛል/ይመለከተኛል የሚል አካል የማህበሩን አሁናዊ አቋም በቅርበት ሊከታተለውና እርምት እርማጃ ሊወስድበት እንዲሁም የማህበሩን ህልውና የማዳን ተግባር መስራት እንደማገባ ልናሳስብ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ይሄንን ምርመራ ዘገባ ለመስራት፦ ከህብረተሰቡ በተለይም ከተቋሙ ሰራተኞች፣ ማህበሩን በቅርበት ከሚከታተሉት እንዲሁም ከማህበሩ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ እየሰሩ ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች እና አመራሮች ያሰባሰበውን መረጃና ማስረጃ መነሻ በማድረግ እንደሆነ በቅድሚያ ለመጠቆም እንወዳለን።

በሌላ በኩል የተገኙ መረጃዎችን በሙሉ በዘፈቀደ እዚሁ ዘገባ ላይ አላቀረብንም። ምክንያቱም ምናልባት መረጃዎቹ ይፋ ከተደረጉ የማህበሩ ህልውናውን ይጎዳሉ ወይንም የህግ ተጠያቂነት ቀጥሎ የሚኖር ከሆነ ሂደቱን ያደናቅፋሉ ያልናቸውን ጥብቅ መረጃዎችን አለማቅረባችንን በድጋሚ እንገልፃለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀
#WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #WODA #ዎልማ
"ማህበሩ እንዴት ይታደግ?" Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=5066

Wolaita Times

11 Nov, 13:50


"የዎላይታ ልማት ማህበር ቁልቁል ጉዞ እና ሌብነት ሰንሰለት"- ምርመራ ዘገባ

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ይሄንን ምርመራ ዘገባ ለመስራት፦ ከህብረተሰቡ በተለይም ከተቋሙ ሰራተኞች፣ ማህበሩን በቅርበት ከሚከታተሉት እንዲሁም ከማህበሩ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ እየሰሩ ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች እና አመራሮች ያሰባሰበውን መረጃና ማስረጃ መነሻ በማድረግ እንደሆነ በቅድሚያ ለመጠቆም እንወዳለን።

በሌላ በኩል የተገኙ መረጃዎችን በሙሉ በዘፈቀደ እዚሁ ዘገባ ላይ አላቀረብንም። ምክንያቱም ምናልባት መረጃዎቹ ይፋ ከተደረጉ የማህበሩ ህልውናውን ይጎዳሉ ወይንም የህግ ተጠያቂነት ቀጥሎ የሚኖር ከሆነ ሂደቱን ያደናቅፋሉ ያልናቸውን ጥብቅ መረጃዎችን አላቀረብንም።

የዎላይታ ልማት ማህበሩ ከቀደምት አመራሮችና የልማት ስራዎች ብሎም በጎ ተጽእኖ ፈጣርነቱ፣ አለኝታነቱ እና ከአውራነቱ ቁልቁል ተፈጥፍጦ በዘረፋ፣ በስርቆት፣ በዘረኝነት፣ በብልሹ ስነምግበር እና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ግለኝነት የነገሰበት ተቋም እየሆነ ስለመምጣቱ ጥቂት ማሳያዎችን እንደሚከተለው በዝርዝር እናቀርባለን።

ላለፉት አራት አመታት በአንጻራዊነት ከቀደሙት የልማት ማህበሩ ተግባራትና ውጤት አንጻር ስታይ ይህ ነው የሚባል በየወረዳዎች የሚተገበሩ የልማት ስራ ካለመሰራቱም በላይ የህዝብን አጀንዳ ማስቀየርያነት መጠቀምያ ተቋም እየሆነ መጥቷል።

በሰው ሀይል አደረጃጀት በሰፈርና በጎሳ የተጠላለፈ ከመሆኑም ባሻገር በቅጥርና ዝውውር ላይ በሚደረጉ የጎሉ አድላዊ አሰራሮች ሰራተኞች የስራ ሞራላቸው በከፍተኛ ደረጃ ከመውደቁ ባሻገር ለስራ ትኩረታቸው እጅግ የቀነሰ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ከጥቂት አመታት ወዲህ የማህበሩ ማኔጅመንት አባላት ስራ ተኮር የስራ ግምገማ የማያደርጉና በውስጣቸው በጎራዎች/ቡድኖች ተከፋፍለው ከመናቆር ያለፈ በክልሉ ውስጥ አውራ ልማት ማህበርነቱን አስቀጥሎ የመሄድ ጉዳይ የተዘነጋ መሆኑ አሳይተዋል።

በጎራ ለመከፋፈላቸው የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ከችሎታ በታች በሆነ የስራ እና ተቋም አመራር ዘይቤ መያዛቸውና በመከተላቸው በተጨማሪ በግል ጥቅም ላይ ብቻ ያተኮሩ በመሆናቸው ማህበሩ ደካማ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በመሆኑም አድስ ከሚመጡ ስራ አስፈጻሚዎች ላይ መለጠፍን ዋና ተግባር በማድረግ የህዝቡንና የማህበሩን ተግባር በመዘንጋት ልማት ማህበሩን የቁልቁለት ጉዞ እንዲያፋጥን ያደረጉት በስራቸው ያሉ ም/ሥራ አስፈጻሚዎች መሆናቸው የማህበሩ ሰራተኞች ተጠያቂ ስያደርጉ ይታያሉ።

በልማት ማህበሩ ስር ከተደራጁ ተቋማት ውስጥ ዳሞታ ኮንስትራክሽን ስሆን በተለያዩ ቦታዎች በግንባታ ሳይቶችና ፑንዱንያ ከሚገኙ ግምጃ ቤቶች በሚልዮን ገንዘብ የሚገመቱ የተለያዩ ማሽኖች፣ የማሽን አካላቶች፣ ብረቶች ወዘተ በተደጋጋሚ ዝርፊያ የተካሄደባቸው ሲሆን ድርጊቱ ከውስጥና ከውጭ በተባበሩት ሌቦች ተፈፅሟል።

ከመሆኑም በላይ በሶዶ ከተማ ፖሊስ ስመረመር ቆይቶ ምክንያቱ በውል ባልታወቀበት መቋረጡ ለዘራፊዎች በጎ አጋጣሚ የፈጠረ በመሆኑ ቀጥለውም በተደጋጋም የህዝብ ሀብትና ንብረት በማባከንና ለግለሰቦች መበልጸጊያነተ እየዋለ ይገኛል፡፡

በሁምቦ ወረዳ በሀሚፖ ኮይሻ ቀበሌ የልማት ማህበሩ በግብርና ሰርቶ ማሳያነት በሚያገለግል ስፍራ የተለያዩ ስራስሮች፣ የማር፣ አትክልት፣ አዝርት፣ እንስታትና የእንስሳት ተዋጽኦዎችን የሚያመርት ሲሆን ጥቂት ከሚባሉት ውጭ ምርቶቻቸው አድራሸቸው የት እንደሚገቡ የማኔጅመንት አባላት ጭምር የማያውቃቸው ከመሆኑም በዘለለ ለአንዳንድ የመንግስት ሹመኞችን እንደእጅ መንሻነት እንደሚበረከቱ እና ለግል ጥቅም እንደሚውሉ ጭምር መስማታቸውን ያጋራሉ፡፡

ከዚህም አልፎ ተርፎ ስራ አስፈጻሚው አላማው በግልጽ በማይታወቅ ሁኔታ የተደራረቡ የውሎ አበሎችና ጥያቀ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ የነዳጅ አጠቃቀም ሂደታቸው ጥቅም ተኮር ስለመሆናቸው ያመላከተ ሆኖ ታይቷል፡፡

እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ የተገኘው ደግሞ ከልማት ማህበሩ ጋር የስራ እና የተግባር ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች በትውውቅና ቤተሰባዊ በሆኑ ግንኙነቶች አበሎችንና ልዩ ልዩ ጥቅሞችን መጋራታቸው መሆኑን ከምርመራ ሰነዶች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

በተመሳሳይ በአበላ አባያ ወረዳ የሚገኘውን የቀድሞ የመንግስት እርሻ ማህበሩ በመረከብ እየሰራበት እንደሚገኝ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ያየን ስሆን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት አግባቢነት ያላቸው የገቢና ወጭ ቁጥጥሮች በምርትም ላይ ይሁን በገንዘብ እንደማይካሄድና ከጥቂት ግለሰቦች ውጭ ስለጉዳዩ ማናቸውም ሰራተኞችም ይሁን ማነጅመንቱ ግንዛበ እንደለላቸው ይናገራሉ፡፡

ሥራ አስፈጻሚዎች የተገለገሉበት የመስተንግዶ ክፊያ ብር 3.5 ሚልዮን በላይ እንዲከፈል ከጉተራ ስልጠና ማዕከል ለዋና ጽ/ቤት በደብዳቤ የተጠየቀና ክፊያው በገንዘብና በተለያዩ እዳዎች የተሸፈነ መሆኑን የተረዳን ሲሆን ማህበሩ ከቀደመ የማህበሩ የቆጣቢነትና አግባቦችን መከተል ባህል እጅግ ያፈነገጠ መሆኑን ያሳያል፡፡

ልማት ማህበሩ የልማት ስራዎችን የሚሰራው ከአባላቱ በሚሰበስበው የአባልነት መዋጮ እና ካቋቋማቸው የንግድ ተቋማት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ማህበሩ አዳዲስ አባላትን በማደራጀት የጎላ ሥራዎችን መስራት ስገባው በዞኑ ውስጥ ካሉ ወረዳዎች በትንሹ ከአንድ አመት እስከ 34 ወራት ያልሰበሰባቸው ከ 20 ሚልዮን ብር በላይ እንዳለ በማስረጃ ጭምር ስቀመጥ ይታያል፡፡

በመሆኑም በቀደሙት ጊዜያት ከሚሰበሰቡ ገንዘቦች እያንዳንዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤ ወረዳዎች እኩለታውን ከልማት ማህበሩ ጋር በመሆን በማቀድ ለወረዳቸው የተለያዩ ግንባታዎችን መስራታቸው የሚታወስ ሲሆን ላለፉት አራት አመታት ግን ምንም አይነት ስራ ያልተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በልማት ማህበሩ የተቋቋሙ አዳዲስ ተቋማት በበቂ ጥናትና ትኩረት ባለመደራጀታቸው የተነሳ ላልተፈለገ ወጭ እና ኪሳራ በተደጋጋሚ በመዳረጋቸው እንዲታጠፉ በሚመለከታቸው ሀሳብ ቢሰጥም በቸልተኝነት በመያዝ ከቀን ወደ ቀን ማህበሩን እነደማህበር ዋጋ እያስከፈሉ ይገኛሉ፡፡

ዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የዎላይታ ኩራት የሆነ ተቋም ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትምህርት ቤቱን መርህና ደንብ በጣሰ መልኩ የተማሪዎችን ቅበላ የሚያደርግ፣ የትምህርት ቤቱ አመራሮች በማያውቋቸው አማካኝነት በተጽእኖ እንዲቀላቀሉ የሚደረጉ ተማሪዎች መኖራቸው የተፈለገውን ያህል ውጤት እንዳያመጡ ከማድረጉም ባሻገር ለቀጣይ የአሰራር ክፊተትን እንደሚፈጥር በቅርቡ በድንገት ውጤትን አስመልክቶ ለመገምገም ለሞከሩት ስራ አስፈጻሚ የት/ቤቱ ኃላፊዎች በአስተያየት መልኩ ተናግሯቸው እነደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በተመሳሳይ ባለፉት ጊዜያት ልማት ማህበሩ ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በመፈጸም በጤና፣ እርሻ፣ ትምህርት እና አካል ጉዳተኞች ላይ ከ 10 ከሚበልጡ ድርጅቶች ጋር ስሰራ የቆየ ቢሆንም በአሁን ወቅት ሁለት የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶችን ብቻ ይዞ መገኘቱ የዞኑን ህዝብ በአያለው ከመጉዳቱ ባለፈ የልማት ማህበሩን አሁናዊ አፈጻጸሚ ቆም ተብሎ እንዲገመገም የሚያስገድድ እንደሆነ አመላካች ወሳኝ ወቅት ላይ እንደምንገኝ የሚጠቁመን እንደሆነ ማነጅመንቱም ሆነ ሰራተኛው ስያነሱ ይስተዋላል፡፡

Wolaita Times

10 Nov, 13:54


Wolaytta Dichcha Amuwan merettida Maganxxuwa, Balibakkuwanne Wuussa xelliyagan gakkida mucura naqaasha hachchi ha macaran naagite!

Wolaita Times

10 Nov, 12:14


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአመራሮች ሙስና ቅሌት

ሰሞኑን ይፋ የተደረገውን ሙስና ቅሌት ለመሸፈን ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምረው እየተሯሯጡ እንደሚገኙ ተጠቆመ!

የህግ አካላትን አሰማርተው ተፈጽሟል የተባለውን የሙስና ተግባር ማጣራትን ትተው በነገው ዕለት በዲላ ማዕከል ያለዉ አመራርና አባላት አስቸኳይ ሰብሰባ መጠራታቸውም ተገልጿል።

ጠያቂ የሌለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከፋፋይ አጀንዳ በመቅረጽ እመራለዉ የምለውን ህዝብ በየግዜው እያዋከበ ቅጥ ያጣ ብልሽትና በሙስና ቅሌት ስለመዘፈቁ ባለፉት ሳምንታት ሙስናን በምጠየፉ ሠራተኞችና አመራሮች አማካይነት መረጃው ለሕዝብ በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በኩል ይፋ ሆኗል፡፡

ከፍተኛ የሙስና ተግባር ከሚፈጸምባቸው ቢሮዎች አንደኛው የዉሃ ማዕድንና ኢኔርጂ ቢሮ የማዕድን ሀብት ዘርፍ ሲሆን ይሄ ዝርፍያና ብዝበዛ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ብዙዎች የተሳተፉበት እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በመሆኑም "ይሄን ነዉር ዉጫዊ ለማድረግና የሌላ አካል ብልሽት ለማስመሰል ርዕሰ መስተዳድሩ ያልገባበት ቦታ የለም። ለማሳሳት ያልሞከረዉ አካልም ጥቂት ነዉ። የሆነ ሆኖ በእሳቸው ትዕዛዝና እውቅና የተመራዉን ብልሽት ወደ ሌላ ለማላከክ ከትዉልድ ቀያቸዉ እስከ አገር አቀፍ ቢሯሯጡም የማይመለስ ደረጃ ደርሷል። እሳቸዉንና ተባባሪዎችን ግልጥልጥ አድርጓል" ሲሉ ምንጮቻችን አረጋግጧል።

''ዉሸትና ዉፍረት ለባለቤቱ አይታወቅም'' እና እንደ መንግስት እጃቸው ንጹህ ከሆነ የህግ አካላትን አሰማርተው ተፈጽሟል የተባለውን የሙስና ተግባር በማጣራት ፈንታ ሰኞ በዲላ ማዕከል ያለዉ አመራርና አባላት አስቸኳይ ሰብሰባ ተጠርተዋል" በማለትም ስለሁኔታው አስረድቷል።

ሌላኛው ለእሳቸው ቅርብ የሆነ አንድ ከፍተኛ አመራር መረጃ እንዳጋሩት የስብሰባዉ አጀንዳ "የሌብነት ድርግት መረጃ ያወጡ አመራሮች ላይ እርምጃ ወስደናል። እኛ ከደሙ ነፃ ነን። ፈጣሪ ከሰማይ እንደምያየኝ ምንም ሙስና የለም። እኛ ክልሉን የሰላም የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች በፈጠራ ወሬና በሴራ ይዘምታሉ። እነዝያን ሚዲያዎች አትስሙ" የሚል እና ሌሎች ማደናገርያ ሀሳብ ለማሰማት እንደሆነ ታውቋል።

ይሄ የማደነጋገርያ እንቅስቃሴ ለሳቸዉ አይታወቅ ይሆናል እንጅ ለሰፍዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ የአደባባይ ምስጥር ነዉ።
ወይም እንደ ስብዕናቸው ራሳቸውን ነጻ በማውጣት ሥርአት አልበኛ የሆነውን ቢሮ ተጠያቂ ሊያድርጉ ይችላሉ? የምለው ዘውትር ጥያቄያችን ይሆናል። ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃ ማድረሱን ይቀጥላል።
#Ethiopia #southethiopia

በአሳሳቢ ሁኔታ የቀጠለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአመራሮች ሙስና ቅሌት👇
https://wolaitatimes.com/?p=5063

Wolaita Times

08 Nov, 11:25


በደቡብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን አስታወቀ።

ፋውንዴሽኑ ከአጋር አካላት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በደቡብ ኦሞ ዞን
#ሐመር፣ በ#ናፀማይ እና #ቱርሚ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ 10 የአርብቶ አደር ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በዚህ ወቅት የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ እንደገለጹት ድጋፉ በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚከናወኑ የትምህርት ስራዎችን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ፋውንዴሽኑ ያደረገው በአዲሱ የትምህርት ሥርዓት የተዘጋጁ 1 ሺህ 725 የማጣቀሻ መጽሐፍት፣ ስክሪፕቶና ወረቀት፣ የህትመት ቁሳቁሶች እንዲሁም ስድስት ሞተር ሳይክሎች መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የሚያገለግሉ የተለያዩ የማብሰያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

ድጋፉ በአርብቶ አደሩ አከባቢ በትምህርት ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣና የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚረዳ አስረድተዋል።

በተለይ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበልና ተሳትፎ ለማሳደግ ፋውንዴሽኑ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመው በዚህም በዞኑ ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው ቁርስና ምሳ እንዲመገቡ ማድረግ መቻሉን አውሰተዋል።

ፋውንዴሽኑ በአጠቃላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ጥራትና ተሳትፎን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት እየደገፈ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ይህንነ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ አስታውቀዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ጋያ ፋውንዴሽኑ በዞኑ በትምህርት መስክ ጠንካራ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ፋውንዴሽኑ በዛሬው ዕለት በዞኑ ለሚገኙ 10 ትምህርት ቤቶች ላደረገው የቁሳቁስ ድጋፍም አመስግነዋል።

የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ባለፉት አራት አመታት በተለያዩ የትኩረት መስኮች ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
#Ethiopia #debubomo

https://wolaitatimes.com/?p=5058

Wolaita Times

26 Oct, 14:25


"የዎላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲና የአረካ በጀታቸዉ ከንቲባቸውም ከአንድ ማዕከል ስር ይመራ"- ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና በቃለምልልሳቸው

"የዎላይታ ሶዶ፣ የቦዲቲና የአረካ የተናጠል ጉዞ ብዙ አዋጭ አይደለም ከተሞቹ በዙሪያው ያሉትን ቀበሌዎችን ጨምሮ ከሚሰፉ ይልቅ በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞች በማካተት አንድ ላይ የሚያድጉበት አሰራር መዘርጋት አለበት....
ከተሞቹ ለውጤታማነት በጀታቸዉ ከአንድ ማዕከል በአንድ አመራር ሥር ( ከንቲባ ስር ) በተቀናጀ ሁኔታ ይመራ" ------ እንዴት፣ ለምን፣ በማን፣ መቼ እና በምን ለሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ ይዘናል ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንግዳችን እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ። ያዉ ባለፈዉ እንዳሉት የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ እንግባ።

በቅርቡ በዎላይታ የሚገኙ ሶስት ትልልቅ ከተሞች፣ ዎላይታ ሶዶ፣ አረካ እና ቦዲቲ የተወሰኑ የገጠር ቀበሌዎችን በማካተት የቆዳ ሥፋታቸዉን ጨምረዋል። ይሄን እንዴት ያዩታል? ከዚህ የተሻለ የሚሉት ሌላ አማራጭ ሐሳብ ካሎትም መግለጽ ይችላሉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ አመሰግናለሁ። እነዚህ ሶስቱ ከተሞች ለየት የሚያደርጋቸዉ በጣም በቅርብ ርቀት የሚገኙ መሆናቸዉ ነው። የሚስፋፉበትም መንገድም የተቀናጀና ተገናኝቶ አንድ ትልቅ ከተማ መፍጠርን ያለመ መሆን አለበት ባይ ነኝ። አሁን ግን የተደረገዉ መስፋፋት አስፈላጊ ባልሆኑ አቅጣጫዎችም ጭምር የተደረገ ነው ሶስቱም ጋር።

በተናጠል ሶስት ትልቅ የተለያዬ ከተማ መፍጠር በነባራዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የሚቻል አይደለም። ለዎላይታ አይነት በሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ ልዩነት ላለዉ ብሔር አይመከርም። ከዛ ቀጥሎ ሶስቱም ከተሞች ከቋንቋ፣ ባህልና ማንነት ጀምሮ የእድገት ደረጃቸዉም ተመጣጣኝ እና የተያያዘ የሚባል ነው። ስለዚህ እነሱን አንድ ትልቅ ከተማ ለማድረግ አልሞ መንቀሳቀሱ አዋጭ ይመስለኛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በምን አይነት መንገድ ነው አንድ ከተማ አድርገን ልናደራጅ የምንችለዉ የሚለዉ ላይ በስፋትና በዝርዝር ቢሄዱበት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በርግጥ የተለያዩ ሰዎች የተለያዬ ሐሳብ ሊያመነጩበት እንደሚችሉና ያም በደምብ መደመጥና ለዉይይት ክፍት መሆን አለበት የሚለዉን እንየዝ። እኔ የከተማዉ ስም "ዎላይታ ሶዶ ከተማ!" መሆን አለበት ባይ ነኝ። ለምሳሌ ( ዳሞት፣ ጦና፣ ዲቻ፣ ቦዲቲ፣ አረካ፣ ጉኑኖ፣ ዳልቦ፣ ሁምቦ ) ክፍለ ከተሞች። ሆስፑን ዳናን ወይንም ላፑን ዎይሻን ለማስታወስ፣ በስምንት ወይንም ሰባት ከፍለ ከተማ ደረጃ ማደራጀት ይቻላል፣ ሌላም Symbolic ነገር መጠቀም ይቻላል።

የዎላይታ ዞን በገዥዎች ችሮታ ሳይሆን በሕዝባችን መራራ ትግል የተቋቋመ ነው። ይህ ዞን ሕዝቡንና ምሁራንን እያማከረ፣ ለሕዝቡ የሚጠቅሙ እርምጃዎችን መዉሰድ አለበት ብዬ አምናለሁ። በአሁኑ ሰአት ዎላይታ ሶዶ በራሷ እያደገች ነው፣ በጣም በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኙት ቦዲቲና አረካም በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ነው። በተናጠል እየወሰድን ግን ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ስናወዳድር ለዎላይታ ሊኖራት የሚገባትን ቦታ አያገኙም፣ የተናጠል ጉዟቸዉ ብዙ ርቀት አይወስድም።

በቅርቡ እንኳን የዎላይታ ሶስት ከተማ እንዴት ይገባል ተብሎ እየተገባቸዉ ከአለም ባንክ ድጋፍ አይናችን እያዬ ቦዲቲና አረካ ተገፍተዋል። በጋራ በአንድ ከተማ ዎላይታ ሶዶ ሥር ታሪካቸዉንና መረጃዎቻቸዉን እንደያዙ ክፍለከተማ ቢሆኑ የከተማዋ ሕዝብ ቁጥርም ሆነ የቆዳ ሥፋት ይጨምራል፥ በተናጠል ከተሞቹ የሚከብዳቸዉ ነገር በጋራ ቢደራጁ በጣም ቀላል ነው። በጋራ ቢደራጁ ዎላይታ ሶዶ ዉድድሯ ከነ አዲስ አበባ፣ ሸገር፣ መቐለ፣ ባሕር ዳር ጋር ይሆናል።

ይህ ሁሉ ሕዝብ ተሰባስቦ በጋራ የሚኖርባት አንድ ከተማ ስትሆን የሚገነባባት አየር ማረፊያ አለም አቀፍ መሆን አለበት። እንደ አንድ ከተማ በመሠረተ ልማት በመተሳሰር ከአንዱ ወደ ሌላዉ ለመጓጓዝ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ያስችላል። ዋናዉ Connectivity መጨመር ነው። እንደ አደጉ ሐገራት ወደፊት የዋሻ ሥር የሚሄድ ከተማ ባቡር metro በመሥራት ከአንዱ ወደ ሌላዉ የከተማ ክፍል በቀላሉ ሰዉ ተጉዞ ሰርቶ ዉሎ ሊመለስ ይችላል፣ ያም ከመኪና በፈጠነ ሰዓት በፍጥነት ለመጓጓዝ ያግዛል።

ከተቀሩ የዎላይታ ወረዳዎችም ለሚመጡ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የመጀመሪያ ምርጫ ትሆናለች። የአሁኗን ዎላይታ ሶዶ ለሁለት ብንከፍል ዳሞት ክፍለ ከተማ እና ጦና ክፍለከተማ ወይንም ዲቻ ክፍለ ከተማ በማለት። ቀጥሎ በተጨማሪ ቦዲቲ ክፍለከተማ፣ አረካ ክፍለከተማ፣ ዳልቦ ክፍለ ከተማ፣ ጉኑኖ ክፍለከተማ፣ ሁምቦ ከፍለ ከተማ በማለት ብንከፍል ( በጥናትና ዉይይት መዳበር ያለበት ሐሳብ ነው ) የተሻለ ይሆናል።

በሁሉም አቅጣጫ የሚሰሩ መንገዶች ይህንን ታሳቢ አድርገዉ ተገንብተዉ፣ የባስ ትራንስፖርት በስፋት እንዲጀመር፣ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች፣ መንግስታዊ ተቋዋማት ሲገነቡ ይህንን አንድ ከተማነት ታሳቢ አድርገዉ እንዲሰሩ ማድረግ። እንደ አዲስ አበባዉ ሁሉ በሁሉም ክፍለከተሞች ወደፊት ተመሳሳይ ሕንፃዎችን ገንብቶ የክፍለ ከተማ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ማድረግ።

በመንግስት በኩል የሚመቻቹ የብድር አቅርቦቶችን ከሁሉም የዎላይታ ወረዳዎች በተወሰነ መጠን ወጣቶችን እያመጡ በከተማዋ የሥራ ዕድል መፍጠር።

በኢትዮጵያ ዎላይታ ሶዶ ከ12ኛነት በተከታታይ ከ31ና 32 ያሉትን አረካ እና ቦዲቲን ከሁምቦና ጉኑኖ ጋር ይዛ በኢትዮጵያ ከ1-5 ካሉ ከተሞች ተርታ ትሰለፋለች። በዚህም የሚገባትን መሠረተ ልማት ለማግኘት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፤ ዎላይታ ደግሞ የሚገባት ያ ነው።

በየኢትዮጽያ ከተሞች ከተማረዉ እስካልተማረዉ እየተበተነ ከሚንገላታ የራሱን ቋንቋ እያወራ የሚኖርበት ከተማ መገንባት ለነገ ሊባል አይገባም። ከዚህ በላይ ማርፈድ የለብንም። እነ ገሱባ፣ ባዴሳ፣ ሻንቶ፣ በሌ እንዲሁም የመሳሰሉትም ከሌሎች የኢትዮጵያ ወረዳ ከተሞች ጋር እድገታቸዉን ይቀጥላሉ።

አርሶ አደሩ በቂ ካሳ አግኝቶ የከተማዉ ነዋሪ ሆኖ የሚቀጥልበት አሰራር ከተዘረጋ፣ የሕገወጥ ግምባታ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ከተደረገና ከተሞቹ የማስተሳሰር ዘመኑን የዋጀ ፕላን ከተነደፈ ታላቋ ዎላይታ ሶዶ እዉን የማትሆንበት ምክንያት የለም። አሁን ባለዉ ሁኔታ እንኳን ዎላይታ ሶዶ የዞንና በከፊልም የክልል ከተማ ነች፤ የሚቀላቀሉ ከተሞች የወረዳ መቀመጫነታቸዉ ሊቀጥልም ይችላል፦ የሸገር ቢሮዎች አዲስ አበባ ዉስጥ እንደተገነቡት ማለት ነው።

እነኝህ ከተሞች በጀታቸዉ ከአንድ ማዕከል በአንድ አመራር ሥር ( ከንቲባ ስር ) በተቀናጀ ሁኔታ ከተመራ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወጤታማ የመሆን እድሉ ይሰፋል። በዚህ ደረጃ ከወዲሁ ማሰብ አለብን፤ በተለይ የዎላይታ ሶዶ፣ የቦዲቲና የአረካ የተናጠል ጉዞ ብዙ አዋጭ አይደለም፣ በጋራ እንደ አንድ ከተማ በቀጣይ ቢጓዙ የተሻለ ይሆናል። ሕዝቡ የሚንቀሳቀሰዉ እንደ አንድ ከተማ እያሰበ ነው ማለት ይቻላል። በአንዱ ሰርቶ ሌላዉ ላይ ወዳለዉ ቤቱ ሄዶ ያድርራል። ዞኑ በዋናነት በዚህ ከተማ ላይ ትኩረት አድርጎ የከተማ ልማት ሥራን ቢያከናዉን የተሻለ ነዉ እላለሁ።

Wolaita Times

26 Oct, 14:25


የዳሞት ተራራንም የከተማዉ አካል በማድረግ በጣም በጥሩ ሁኔታ በማልማት የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ 5ጂ ኔትወርክ ማስፋፋት ቢካሄድ ዎላይታ ሶዶ እንደ ክልል ከተማ ቢካሄድባት ቦዲቲና አረካ የወረዳ ከተማ ተብለዉ ረዥም ጊዜ መጠበቃቸዉ አይቀርም። አንድ ከተማ ከሆኑ ግን በጋራ ያድጋሉ። በተለይ ይህ ብዙ ሕዝብ ቁጥር ያለዉ አንድ ትልቅ ከተማ የመፍጠሩ ነገርም በመንግስትም ሆነ በግል ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ስለ ጥልቅ ማብራሪያው እናመሰግናለን። ነገር ግን በፌደራል መንግስት በኩል ይህ ዘርፈብዙ ጥቅም ያለበት ግዙፍ አላማ በጥሩ አይን ይህ በጥሩ አይን ወይንም በአዎንታ የሚታይ ይመስልዎታል ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኛ እንግዲህ የምንመራዉ በሕገመንግስቱ ነው። ይህ የዎላይታ ዞን መብት ነዉ፥ የፈደራል ሥርአቱ የፈጠረዉ አንዱ እድል ይሄ ነው፤ ይሆነኛል የምትለዉን አጥንተህ ትወስናለህ። ከዛ ዉጪ ይሄ መንግስት "የሕልም ጉልበት፣ ለእመርታዊ እድገት" እያለ ይሄንን ሐሳብ ከተቃወመ የሚገርም ነው። የሚቃወምም አካል ካለ ሕገ መንግስታዊ መብታችን ነውና ለሰፊው ህዝብ ዘላቂ ጥቅም መፍተሔ ብለን መጋፈጥ አለብን። የዎላይታ ሕዝብ የሚበጀዉን አስቦ የመወሰን ሕገመንግሥታዊ መብቱን መጠቀም አለበት።


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

#WolaitaTimes ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏
#Ethiopia #southethiopia
https://wolaitatimes.com/?p=5003

Wolaita Times

25 Oct, 14:07


የብርሃኑ ነጋ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ተሿሚና ህገወጥ ሹመት

የብርሃኑ ነጋ ተሿሚ ፕረዚዳንት የ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ዘቻ እና ማስፈራሪያ ከምን የመነጨ ይሁን ? የትም ያልተሞከረ ሀገርአቀፍ አሰራር ያፈነገጠ የብርሃኑ ነጋ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አመራሮች ሹመትና ጠልቃ ገብነት ምን ታስቦ ነው? እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ምላሽ አላቸው

እንደተለመደው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የፓለቲካ ወጌሻ ልዩ እንግዳ ዝግጅት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ከፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ ማድረግ ልዩ ዝግጀት አሰናድተው እነሆ እንደሚከተለው አቅርቧል ተጋበዙልን🙏

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንግዳችን እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ። ያዉ ባለፈዉ እንዳሉት የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ መግባት እችላለሁ ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ተፈቅዷል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ዛሬ ስለ ዩንቨርስቲዎች እናወራለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መልካም ደስ ይለኛል።


🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንቶች በቀጥታ ከማዕከል የሚሾሙበት አሰራር ቀርቶ የአካዳሚክ ማህበረሰብ ጭምር በሚሳተፉበት ምርጫ እንዲሆን መደረጉ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ሀገር አቀፍ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ በብርሃኑ ነጋ የተሾሙ አካላት እያስተዳደሩ ቀጥለዋል፤ ይህ በዩኒቨርስቲው እና በዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጥረዉ ተፅዕኖ ይኖር ይሆን ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በሚገባ። በመጀመሪያ በሐገር አቀፍ ደረጃ ያለዉ አሰራር በወጥነት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መተግበር አለበት። ሌላዉ ይህ የምርጫ አሰራር በተቋም ደረጃ ዲሞክራሲን ለመለማመድ እድል የሚሰጥ ነው። ከዛ ባለፈ ለዩኒቨርስቲው እድገት ያለዉ ሚና ማሰብ ከሚቻለዉ በላይ ነው።

እጩዎቹ በዩኒቨርስቲው ለማምጣት ስላሰቡት እድገት በአጭርና በረዥም ጊዜ ግባቸዉ ምን እንደሆነ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመማር ማስተማር ላይ ሥራ ላይ እና በመሳሰሉት ምን ለመሥራት እንዳቀዱ የሚያቀርቡበትና የተሻለ ሰዉ እንዲመረጥ እድል የሚሰጥ ነው።

በዚህ አይነት ቀድሞ በፖለቲካ ዉግንና ይደረግ የነበረዉ ሹመት በተወሰነ ደረጃ የተሻለ አቅም ያላቸዉ ሰዎች ዩኒቨረስቲዎችን እንዲመሩ እድል የፈጠረ አሰራር ነው። ይህ ጥሩ አሰራር በዎላይታ ሶዶ ብቻ እንዲቋረጥ መደረጉ በጣም አሳዛኝ ነው። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ለሕግ የማይገዙ ፈላጭ ቆራጭነትን የሚሹ መሆናቸዉን ያሳያል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በእርግጥ የሹመት ደብዳቤ የጻፉት ብርሃኑ ነጋ ናቸዉ፣ ጊዜያዊ በሚል፤ የተሾመዉ ግለሰብስ ላይ ችግር የሚሉት ነገር አለ ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ጉዳዩ የግለሰብ አይደለም፥ የመርህ፣ የሕግና የአሰራር ነው። ምናልባት አንድ ዶክተር መድሕን ማርጮ የተባለ ምሁር በጉዳዩ ላይ አስተያዬት በመስጠቱ፣ የአሁኑ ፕሬዘዳንት በዉስጥ መሥመር "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ብሎ ጽፎለት፣ የለጠፈዉን አይቸዋለሁ። እንግዲህ በዚህ ደረጃ ምርጫም ቢደረግ ያለዉን አሰራር ጠልፎ አለአግባብም ቢሆን ያስመርጠኛል ብለዉ የሚያምኑት አካል ይኖር ይሆን የሚል ጥርጣሬም የሚያጭር ነው።

እኔ በበኩሌ ግን የአሁኑም ፕሬዘዳንት፣ እቅዳቸዉን አቅርበዉ እድሉ ተሰጥቷቸዉ በሐቀኛ መንገድ ቢወዳደሩ ችግር የለብኝም። ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን፣ የትዉልድ ተሻጋሪ ተቋም ግምባታ እና በሕግ የመመራት ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የምክትል ፕረዚዳንቶችም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህ የዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንቶችን በምርጫ የመሾም አሰራር በተጨባጭ ለዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሚፈይደዉ አሁናዊ ነገር ካለ ቢያስቀምጡልን ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የዎላይታ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ ባለ ያለመግባባት ምክንያት ለዘመናት ሲቀጣና ለተንኮለኛ አሰራሮች ተጋልጦ የኖረ ሕዝብ ነው። ይህን ዩኒቨርስቲ ማስከፈቱም ከብዙ ፈተናዎች በኃላ ነው የተቻለዉ። አሁን ደግሞ መንግስት የትምህርት ጥራት ወድቋል ብሎ ተማሪዮችን በገፍ እየጣለ ነው።

ስለዚህ ነገ ከነገ ወዲያ የዩኒቨስቲዎች መዘጋት እና የደረጃ ማዉረድ ሥራ ሊሰራ ይችላል። ስለዚህ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ብቁ ፕረዚዳንቶችን አግኝቶ እራሱን ማሳደግ አለበት። ይሄን የምለዉ ግጭትን ከማስወገድ፣ አቅምን ለእድገት አሟጦ ከመጠቀም አንጻር ነው እንጂ መቼስ የዛ አይነት ዉሳኔም ከመጣ በአካባቢው ሲሰራ ከኖረዉ የብሔር ጭቆና አንጻር በተለዬ ሁኔታ መታየቱ የግድ ነው። በዋናነት ግን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ እንዲያድግ፣ እንዲዘምንና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

#WolaitaTimes ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏
#Ethiopia #southethiopia



የብርሃኑ ነጋ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ተሿሚ፤ ከአሰራር ያፈነገጠ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አመራሮች ሹመት👇
https://wolaitatimes.com/?p=4998

Wolaita Times

25 Oct, 07:11


በዎላይታ ዞን በተለያዩ ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ አምስት አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በዞኑ በተለያዩ ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ አምስት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የመንግሥትንና የህዝብን አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በሙስና እና በተለያዩ ወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ፖሊስ የገለጸው።

በቁጥጥር ስር የዋሉት፦ 1ኛ. አቶ ተመስገን አለማየሁ የቀድሞ የዎላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ የነበሩ

2ኛ. አቶ መስፍን ዳዊት የቀድሞ የዎላይታ ዞን የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአረካ ከተማ ከንቲባ የነበሩ። 3ኛ. አቶ ማዕረጉ አስራት የቀድሞ የሆብቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ

4ኛ. ወ/ሮ ተዋበች ተረጬ የቀድሞ የአረካ ከተማ የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም 5ኛ. አቶ ከበደ ካንፌሶ የቀድሞ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

አያይዘዉም አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር ዉለዉ በህግ እንዲጠየቁ ምርመራ መጀመሩን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡ በሌሎች አካባቢዎችም በህገ ወጥ ወንጀል ድርጊቶች የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን መረጃ በመስጠት የተለመደዉን ትብብርና እገዛ እንዲያደርግ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ጥሪ አቅርበዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በአከባቢው ባለው ብልሹ አሰራሮች ዙሪያ በተደጋጋሚ ተጨባጭ መረጃዎችን ሲያቀርብ እንደነበር ይታወቃል። ዝርዝሩን እናቀርባለን!!

Wolaita Times

24 Oct, 18:39


"የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ሰራተኞች ስቃይና የአመራሮቹ ቀልድ እንደቀጠለ ነው" - ሰራተኞች

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ የመንግስት ሰራተኛውን ደሞዝ "በአግባቡ የማያስገቡ ዞኖች እና ወረዳዎች በመኖራቸው ከነሐሴ ወር ጀምሮ ቀጥታ የሰራተኞች ደሞዝ በባንክ አካውንቱ እንዲገባለት ማድረጉንና ይህ አሰራር በቀጣዩም ወር እንደሚቀጥል" በሚል ከዎላይታ ሶዶ ፋና 99.9 FM ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በዚህ ሳምንት ባደረጉት ቃለመጠይቅ አስታውቀዋል።

ኃላፊው በገለፃቸው ፦ "የመንግስት ሰራተኛውን ደሞዝ ሳይሸራረፍ ክልሉ ከዚህ ቀደምም ይልክ እንደነበረና ነገር ግን አንዳንድ ወረዳዎች ለሌላ አገልግሎቶች በመቁረጥ ሰራተኛውን ሲበድሉ ቆይተዋል ያሉት የቢሮው ሃላፊ በእነዚህ አካላት የተዝረከረከ አሰራር ክልሉ ደሞዝ መክፈል እንደማይችል ሲቆጠር ቆይቷል በማለት በጥቅምት ወርም የሰራተኛውን ደሞዝ እራሳችን በሙሉ ሃላፊነት ማስገባት የግድ ይለናልም" ብለው ተናግረዋል።

በተቃራኒው በዎላይታ ዞን የመምህራን ደሞዝ አሁንም አልተከፈለም፤ በአብዛኛው መዋቅር ትምህርትም አልተጀመረም፤ ደመወዝ የተከለከሉ መንግሥት ሠራተኞች ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ሲሉ ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኙትን ሁሉ እንደሚሰሩ ጠቅሰው "በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፤ በአንዳንድ መ/ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይታዩም፥ ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ተብሏል።

በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 የመማር ማስተማር ሥራ እንደተጎላላ ነው ዓመቱ ያለቀው፡፡ የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም ተሻግሯል መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም።

የቀጠለው የመምህራን ደሞዝ ጥያቄ በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 ዓም የመማር ማስተማር ሥራ እንደታጎለ ነው ዓመቱ ያለቀው። የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም መሻገሩ ነው የሚነገረው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አሁን ላይ በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም፡፡

በዎላይታ ዞን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የመምህራንም ሆነ የሌሎች መንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በወቅቱ አይከፈለም፡፡ ዘግይቶ ቢከፈልም የደሞዛቸው ከ20 እስከ 50 በመቶ ብቻ እየተሰላ እንደሚያገኙ ነው የሚነገረው፡፡ የዞኑ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ የመምህራን የደሞዝ ጥያቄ አለመፈታት የትምህርት ሥረዓቱን እየረበሸ ይገኛል ይላሉ፡፡

በመንግሥት ተቋማት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ በዎላይታ ዞን በሚገኙ 17 ወረዳዎች የሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ አለመፈጸም የጤና ተቋማትን ጨምሮ በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያቤቶች ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ አብዛኛው ሠራተኛ ተስፋ በመቁረጥ በሥራ ገበታው ላይ እንደማይገኝ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በዚህም የተነሳ አንዳንድ መሥሪያቤቶች በከፊል ሌሎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል፡፡

“ሠራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደር ሲል ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኘውን ሁሉ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ“ በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንድ መሥሪያቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይስተዋልባቸውም፡፡ ምክንያቱም ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ዞኑ ክልሉ በጀት ቶሎ አይለቀቅም ሲል ክልሉ ደግሞ ችግሩ እኔን አይመለከትም እያለ ነውና በመሀል የመንግስት ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ህይወት ኑሮ ውድነት ተጨምሮ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ቀጥሏል።

ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏

#Ethiopia #Wolaita #southethiopia #wolaitatimes

https://wolaitatimes.com/?p=4990

Wolaita Times

24 Oct, 15:17


የዎላይታና ጋሞ ንትርክ የታፈኑት ብሄሮች ማንነት ጭቆና መቼ ይቆማል? የዎላይታ እና ጋሞ ወዳጅነት ከፖለቲካ ባሻገር- የፖለቲካ ወጌሻ ዝግጅት ከፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ጋር🙏 ቀጥታ ወደ ዝግጅታችን👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ የዎላይታ እና የጋሞ ሕዝቦችን ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ምን መደረግ አለበት?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ መታወቅ ያለበት በሁለቱ ዞኖች የሚገኘዉ ሕዝብ ወንድማማችነት ዛሬ የጀመረ ወይንም የሚጀምር ሳይሆን ከጥንትም የነበረ ነው። የቋንቋዉ ተቀራራቢነት ይታወቃል፣ እንደዉም በቁጫ፣ ቦሮዳ እና ምዕራብ አባያ አካባቢ የሚነገረዉ ከዎላይትኛ ጋር በጠቅላላ አንድ አይነት ቋንቋ ነው። አንድ መታወቅ ያለበት ነገር የትኛዉም አይነት አወቃቀር ይምጣ አይምጣ ሕዝቦቹ አንድ ላይ እየኖሩ መቀጠላቸዉ አይቀሬ መሆኑን ነው። ስለዚህ በዚህ ቀጠና የሚኖረዉ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ከሶስተኛ ወገን ተጽዕኖ ዉጪ በመሆን ወንድማማችነቱን ማጠናከር እንዳለበት ማወቅ አለበት።

አሁን ላይ በተጨባጭ ወዳሉት ፈተናዎች ስንመጣ በዎላይታ በኩል የክልል ጥያቄዉ በጉልበት ታፍኗል፣ አለ በቂ ድርድር ክልል ተጭኖብኛል፣ በክልልም በፈደራልም ከስልጣን ሚዛናዊ ዉክልና አላገኘሁም የሚሉ ቅሬታዎች መኖራቸዉ ግልጽ ነው። ከዛ ዉጪ ግን በቀጥታ ይሄን የሚያደርገዉ የበላይ አካል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፣ ለራሱ አላማ።

በጋሞ ዞን ደግሞ በቁጫ እና ዶርዜ የማንነት እና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ደረጃ መድረሱ ይታወቃል፣ በርግጥ የሕዝቦች ሕገመንግሥታዊ መብት ላይ አስተያዬት መስጠት ድርሻችን ባይሆንም፤ አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ የአካባቢው ሕዝቦች እጣ ፋንታ የተጋመደና ነገ ከነገ ወዲያም አብሮ መኖርን የሚያስገድድ ነውና ሁሉም ነገሮች በሰላማዊ ዉይይት እና በወንድማማችነት መንፈስ መካሄድ አለባቸዉ።

ሶስተኛ ወገን ሳይገባ በአካባቢው ሊህቃን የሚደረግ የሰከነ ዉይይትና ድርድር መፍትሔ የሚወልድ ይመስለኛል። አሁን አንዳንድ ሊህቃን በጠላትነት የመተያዬትና በቃላት መጎሻሸሙ በፍጹም ተገቢ አይደለም፣ አዋጭም አይደለም። በተደጋጋሚ የሚታየዉ የአመራሮች ሽኩቻም፣ የፖለቲካ ዉሳኔዎች ላይ የሚታዩ ጥርጣሬዎች በምክክር የገራ አቅጣጫ ካለመቀመጡ የሚነሱ ናቸዉ፣ አንዳንድ ፓርቲዎችም በሕዝብና ግለሰቦች ላይ እያነጣጠሩ የሚያወጧቸዉ መግለጫዎች ከችግሩ የሚመነጩ ናቸዉ።

የቁጫ ፓርቲ በዎላይታ ሶዶ ይሰበሰባል፣ የጋሞ ፓርቲ ደግሞ በዎላይታ ላይ የክስ ናዳ ያወርዳል። እነኝህ ችግሮች ከአሁኑ ሁሉንም ባለ ድርሻ አካላት ባካተተ ምክክር መፍትሔ ካልተበጀላቸዉ የመሥፋት እድል አላቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በአሁኑ ሰአት በተጨባጭ በክልል ደረጃ መደረግ የሚችሉ ነገሮች ምንድናቸዉ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንዱ አንዱን መረዳት አለበት፥ ዎላይታ በክልልም ሆነ በፈደራልም ሚዛናዊ ዉክልና አለማግኘቱ ግልጽ ነው፥ ክልል በጉልበትም ተጭኖበታል፣ ይህን ያደረገዉ የበላይ አካል ነው።

ዎላይታ ክልልም ሆኖ ቢሆን ከአካባቢው ሕዝብ ጋር መኖሩ አይቀርም፣ ወንድማማችነቱ ከመዋቅር በላይ ነው። በጋሞ በኩል ከዎላይታ ጋር አንደራጅም ያሉ አመራሮች ነበሩ ያ አርቆ አሰተዋይ አለመሆንን ያሳያል፣ ዎላይታን የተሳደቡ ወጣቶች በተደጋጋሚ አይተናል፣ በሽማግሌዎች እና በአመራሮችም በፍጹም ከእነሱ የማይጠበቅ ነገር ሲባል ሰምተናል።

በዎላይታም በኩል አንዳንድ ምሁራን ከእነሱ የማይጠበቅ ነገር ሲሉ ተደምጠዋል፥ በማሕበራዊ ሚዲያም የቁጫና ዶርዜን ጉዳይ የሚያራግቡ አሉ። መሰል ነገሮች መፍትሔ የሚያመጡ አይመስለኝም። በተጨባጭ ለዉጥ የሚያመጣዉ ግን ሁሉን አቀፍ ዉይይትና ድርድር ነው፣ የዛኔ የሶስተኛ ወገን በመሓላችን በፍጹም ገብቶ የማያደፈርሰዉ፣ ዘላቂ ወዳጅነት እንመሰርታለን።

በተጨባጭ ዎላይታ ሶዶና አርባምንጭ በክልሉ የሚኖራቸዉ ቦታ እንዴት ተያይዘዉ ያድጋሉ የሚለዉንም መወሰን ይቻላል። በምክክር ጽኑ ወዳጅነት፣ የአንዱ ችግር የሌላዉ፤ የአንዱ ሰኬትም የሌላዉም የሚሆንበትን አዉድ መፍጠር እንችላለን። ይህ ሕዝብ ተለያይቶ መኖር አይችልም፣ ተጣልቶ ሳይሆን ሳይጣላ ተመካክሮ ወንድማማችነቱን በጽኑ አለት ላይ ይመስርት።

በአሁኑ ሰዓት የሚደረገዉ የእዉር ድምብር ጉዞ ነው፣ ግልጽ በጋራ የተስማማንበት አቅጣጫ ባለመኖሩ ጥርጣሬዎች እየሰፉ ናቸዉ። ክልሉም የተቋቋመዉ በምክክር ሳይሆን በመፋጠጥና በመፈራረጅ ዉስጥ ነው። የኢትዮጵያ ፖለተካ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ዛሬ በትንሹ እጃቸዉን የሰደዱ ሶስተኛ ወገኖች፣ ነገም ሌላ አተካራቸዉን አምጥተዉብን ይህንን ምስኪን ወንድማማች ሕዝብ እንዳይጎዱት እፈራለሁ።

ነገሮችን በምክክር መቋጨት ከተቻለ ደግሞ አንዱ ለአንዱ አለኝታ ይሆናል። ወደድንም ጠላንም በዚህ ወንድማማች ሕዝብ መሐል፣ በመፈራረጅና ጣት በመጠቋቆም የሚደረግ እንቅስቃሴ መጨረሻዉ ብቻ ሳይሆን መንገዱም እራሱ የዉድቀት ነው። ይህ ቋንቋ፣ ባሕልና መልከአ ምድር ያጋመደዉ ሕዝብ ግንኙነት፣ ዘላቂ ወንድማማችነትን ያማከለ መሆን አለበት።

በምክክር የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ከተቻለ፣ በጋራ በተሻለ ሁኔታ መልማትና አንዱ ለአንዱ ድጋፍ ሊሆን ይችላል፣ በጋራም በተናጠልም በወንድማማችነት መንፈስ መንቀሳቀስ ይቻላል፣ የሚጠቅመንም ያ ብቻ ነው። የዎላይታ እና ጋሞ ሕዝቦችን ዘላቂ ወንድማማችነት ያላገናዘበ የየትኛዉም ወገን አካሄድ አያዋጣም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

#WolaitaTimes ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ 🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን። #Gamozone #Wolaita #Ethiopia #southethiopia

በዎላይታና ጋሞ ንትርክ መሀል የታፈኑት ብሄሮች ማንነት ጭቆና መቼ ይቆማል?👇https://wolaitatimes.com/?p=4984

Wolaita Times

23 Oct, 15:00


የም/ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ሙስና ቅሌት የስልክ ንግግር

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ፀሃፊዋ አማካኝነት ለመንግስታዊ አገልግሎት በሚሊዮን ብር ከግለሰቦች ጋር የተደራደሩበት በምስጢር የወጣ የስልክ ንግግር ድምፅ ሙሉ ያድምጡ 👇
https://youtu.be/XSpU1peeU8c?si=X4JZVe2QAUIgWtBy

Wolaita Times

23 Oct, 12:15


በብልፅግና ጭምብል የምንቀሳቀሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ሙስና ቅሌት

በባለፈዉ ፅሁፍ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በምርመራ ዘገባው ለመጠቆም እንደተሞከረዉ የክልሉ ፖለቲካ ብልሽት በኢኮኖሚዉ ጠንካራ ሀብት ያካበተ ስሆን በዋናነት በዛሬዉ ስማቸዉ የማይጠቀሱ ከፍተኛ የፈደራል የመንግስትና የፓርት አመራሮችን ያካተተ ጠንካራ የጥቅም ሰንሰለት የክልሉ ሀብት እየተዘረፈ ይገኛል፡፡

በክልሉ ማዕድንና የመሬት ዉስጥ ሀብቶች ዝርፍያ የሚመራዉ በደቡብ ኢት/ያ ክልል ፊት አመራሮች ከርዕሰ መሰተዳደር ጀምሮ በተቀናጀ ሰንሰለት መሆኑ እዉነት ሲሆን በኢት/ያ የመሬት ዉስጥ ሀብትና ማዕድናት በአገርቱ ህግ መሠረት መመረት እየተገባዉ በታኝና ከፋፋይ ትርጉም በመስጠት ለዛ ሀሳብ የሚሆኑ ትፖዞዎችን በመሰብሰብ ልክ የህወሓትን ፈለግ በመከተል “ሳሮ” የሚባል ማህበር በርዕሰ መስተዳደሩ ሀሳብ አመንጭነት በማቋቋም ከአንድ ብሔር ብቻ እነዚህን የማህበሩ አባል የሆኑ ግለሰቦችን በመሰብሰብ ከማዕድናት ፊቃድ አሰጣጥ መመሪያ ዉጭ በርዕሰ መስተዳደሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ፊቃድ እንዲሰጥ በመደረጉ ህገ ወጥ ተግባር ጫፍ መዉጣቱ የሰለቻቸዉ አካላት በክልሉ ለሥራ የተሰጠዉ የመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር በመጠቀም የኮንትሮባንድ ነጋደ ለሆኑት ለክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠታቸዉ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያለ ወትሮ ጥቆማዉም ስለበዛባቸዉ የእገዳ ደብዳቤ ፅፈዋል፤ እገዳዉም ከርዕሰ መስተዳደሩ ጋር የተናበበ ነዉ፤ ይሁንና ግን እገዳ ነዉ።

እገዳዉ እንዳልኩት የተናበቡት ስለሆነ በቅጽበት የማህበሩ ስም በመቀየር 'ምንጭ' የሚባል ሌላ ከመጀመሪያዉ ስም ሀሳብ ጋር የሚገናኝ ስም በመስጠት ፈቃድ ይሰጣሉ፤ አሁንም በቢሮ ዉስጥ ያሉ ይህ ጫፍ የረገጠ ህገ-ወጥነት እጅግ ያንገሸገሻቸዉ ዜጎች ድጋምም መረር ያለ ጥቆማ ለኮሚሽኑ ያቀርባሉ፡፡

ኮሚሽኑ አሁንም ጉዳዩ እየከፋ መሄዱንና ከርዕሰ መስተዳደር ከሚሰጠዉ ትዕዛዝ ዉጭ እነሱንም ወደ ተጠያቅነት ሊወስድ እንደምችል በመገንዘብ ለአለቃቸዉ ድጋምም እገዳ እንደምፃፍ በማግባባት ድጋሚ ላደራጁት ህገ-ወጥ ማህበር እገዳ ፃፉበት ይሁን እንጅ እነዚህ ማህበራት ፊቃዳቸዉን ከሌላ አከባቢ በደላላ ለሚመጣዉ ባለሀብት በብዙ ሚሊዮን ይሸጡና ገንዘቡን ተከፋፍሎ ሌላ ማህበር ያደራጃሉ፤ ምክንያቱም ሰጪዎችም ነሽዎችም እነሱ ስለሆነ ጉዳዩ አልጋ በአልጋ ነዉና።

በቢሮዉ ሁኔታዉን የሚያመቻቹ አካላት ከአምስት መቶ ሺህ ብር በታች ጉቦ እንደማይወስዱ እና ለዛ ማሳያ ይሆን ዘንድ የምርመራ ሥራ በማያደናቅፍ መልኩ የተዘጋጀ በድምፅ የላክነዉ መረጃ ለእዉነታ ፍለጋዉ መነሻ ይሆናል።

ሌላዉ ይሄ ተቋም የሚያንቀሳቅሰዉ በጣም በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ፕሮጀክት ያለ ሲሆን እያንዳንዱ ፕሮጀክት በዚህ ሙስና ተግባር ምክንያት ሳይጠናቀቁ ተስተጓጉሎ ይቀራሉ፤ ግን ክፍያ ባልሰሩበት ይከፈልና ዉል እንዲቋረጥ ይደረጋል።

ለምሳሌ የባስኬቶ ዞን ላስካ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት እና የዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት እዉነተኛ ማሳያዎች ናቸዉ።

ሌላዉ አንገብጋቢዉና አሳሳቢዉ ትልቁ ችግር ህገ-ወጥነትን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት እንዲጠብቅና እንዲከላከል ሀላፊነትና ስልጣን የተሰጠዉ የክልላችን ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች ራሳቸዉ ኮንተርቫንድስቶች ከመሆናቸዉ ባሻገር የሙስና እና ሙሰኞች ቅንጅት በመፍራት የሙስና ጥቆማና አቤቱታም ጭምር ያለዉን ይዞ ከመከላከል ይልቅ ሙሰኞችን በእናንተ ላይ ጥቆማ እየመጣ ስለሆነ በጥንቃቄ ሥራችሁን ሥሩ ብሎ መንገድ ለሙሰኞች በመስጠት መደላደልን መፍጠር በክላላችን የሙስኛ ተግባርና አድራጊዎች በቀላሉ ጠቋሚዎችን በመጉዳት ተፈርቶ እንዲኖሩ የሚያደርግ አደገኛ ሁኔታ መኖሩን ለማሳያነት እየጠቆምን በክልሉ የኮንትሮባንድ፣ የድንጋይ ከሰል እና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሚመለከታቸዉ አካላት የተጀመረዉ የምርመራ ሥራ ተጠናክሮ እንድቀጥል እና ለዛ አጋዥ መረጃዎች የማጋለጥ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለጽን ዝርዝር መረጃ ለህዝብ ይፋ ካደረግን በምርመራ ሥራ ጫና እንዳይፈጥር ታስቦ ለማሳያ የተላከ መረጃ ነዉ፡፡

በተያያዘ ከዚህ መረጃ ጋር በተያያዘ የክልሉ ውሃ ማዕድንና ማዕድን ኢኒርጂ ቢሮ ለመንግስታዊ አገልግሎት በሚሊዮን ብር ከግለሰቦች ጋር የተደራደሩበት የስልክ ንግግር ድምፅ ከሰዓታት በኃላ እናቀርባለን።
#Ethiopia #southernethiopiaregion

https://wolaitatimes.com/?p=4981

Wolaita Times

22 Oct, 17:52


"ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማህበራዊ መድልዎ በጋሞ አመራሮች እየደረሰብን ነው"- ቁህዴፓ

"ዘርፈብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማህበራዊ መድልዎ በጋሞ ዞን አመራሮች እየደረሰ ነው" ስል ቁህዴፓ ከሰሰ

ፓርቲው በዛሬው ዕለት ባወጣው አጭር መግለጫ "በጋሞ ዞን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አበረታችነት በቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) አባላት ላይ በፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝታችኋል በሚል የበቀል ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል" በሚል ገልጿል።

ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፓርቲው በላከው በዚህ መግለጫ፦ "አብነቶቹ ብዙ ቢሆኑም በአንዳንድ የፓርቲያችን አባላት ላይ የተፈጸሙት ተግባራት አስቀያሚና በብርቱ መወገዝ ያለባቸው ናቸው" ብሏል።

"በቁጫ ወረዳ ጎይላ ቀበሌ አቶ ደረጀ ዳንጋሮ የተባሉት የፓርቲያችን አባል በደረቅ ጣቢያ ላይ በቀበሌው ሚሊሺያ አባላት ታግተው ለረዥም ጊዜያት እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን ለዚህ የቀረበውም ምክንያት የቁሕዴፓን ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካፍለሃል የሚል ነው፥ አቶ ደረጀ ዕሁድ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በቀበሌው ሊቀመንበር እና በሚሊሺያ አባላት በጋራ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከፍለህ መውጣት ካልቻልክ እንገድልሃላለን የሚል ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል፤ ዎላይታና ጋሞ ወደ ጦርነት እንዲገቡ አድርገሃል የሚል የቧልት ዓይነት ውንጀላም ቀርቦባቸዋል" ስል መግለጫው ያትታል።

ፓርቲው አክለውም "በክልላችን የአስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችው ዎላይታ ሶዶ ከተማ መስከረም 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የቁሕዴፓ ጠቅላላ ጉባኤ ከቁጫ ገላ እና ጎይላ ቀበሌዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፈዋል ብለው የአካባቢው ገዢዎች በጠረጠሩአቸው ግለሰቦች ላይ ቀጥሎ የተዘረዘሩት አስነዋሪ ተግባራት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ" በሚል ጋሞ ዞን አመራሮችን ከሷቸዋል።

መግለጫው ለአብነት በዚህ ምክንያት ሰብዓዊ ጥሰትና ህገወጥ ድርጊት የተፈፀመባቸውን አባላትን ስጠቅስ፦ አቶ ለማ መንገሻ ታስረው 50 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተጠየቁ ሲሆን ለጊዜዉ 4 ሺህ ብር፤ አቶ ደምሴ ዳንጋሮ 100 ሺህ ብር እንዲቀጡ፤ ወጣት እንድሪያስ ኢያሱ ታስሮ 12 ሺህ ብር እንዲቀጣ፤ አቶ በላይ በለጠ ታስረው 16 ሺህ ብር እንዲቀጡ፤ አቶ ዳኜ ዳርጋሶ ታስረው 1 ሺህ ብር፤ ወጣት ታምራት ዘለቀ ታስሮ 2 ሺህ ብር፤ አቶ ስምኦን ደግሰው ታስረው 2 ሺህ 7 መቶ ብር፤አቶ ዝናቡ መኩሪያ ታስረው 1 ሺህ 1 መቶ ብር፤ አቶ ስንታየሁ ሼንደሮ ታስረው 4 መቶ ብር፤ አቶ ታረቀኝ ዳታ ታስረው 1 ሺህ ብር ተቀጥተዋል፤ አቶ ዛሳ ዛማላ ታስረው 2 መቶ ብር፤ ወጣት ቶማስ እስራኤል ታስሮ 2 መቶ ብር ተቀጥቷል" በማለት እያንዳንዱን ዘርዝሯል።

ክስተቱን ፓርቲው እንደመረመረው፦"አብዘኞችን ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች እና የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ ለማሰር እና ለመቅጣት እየፈለጓቸው እንደሆነ በመግለፅ የብዙዎቹ የሐሰት ክስ ርዕሶች የሚከተሉት እንደሆኑም አረጋግጠናል በሚል ሲያብራራ፥ በዎላይታ እና ጋሞ መካከል ጦርነት አውጃችኋል እንዲሁም የዎለይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን T-Shirt ማሊያ ለብሳችኋል" የሚል እንደሆነ አስረድቷል።

ፓርቲው በመግለጫው "የአካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ ኃላፊዎች፣ በነዚህ ውንጀላዎች ሰዉ ከቤት ውጪ የትም እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ የፓርቲያችንን አባላት፣ ደጋፊዎችና የቁጫ ብሔረሰብ አባላትን ብቻ በመነጠል የመንቀሳቀስ ነጻነታቸውን በመንፈግ ላይ ናቸው፤ በተጨማሪም፣ በሦስቱም የቁጫ ሕዝብ መዋቅሮች በሚገኙ ቀበሌያት ተመሳሳይ ወንጀሎች በሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ይገኛሉ" ብሏል።

በመጨረሻም "ቁሕዴፓ እንደዚህ ዓይነቱን ከባድ የአስተዳደር መላሸቅና የሥርዓተ መታጣት እየኮነነ ለችግሮች መፍትሔ እንዲመጣና ሕግ እንዲከበር እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ እንደሚቀጥልና ለቁጫ ሕዝብም አለኝታነቱን በድጋሚ እንደሚያስመሰክር ቃል በመግባት አምባገነንነትንና ሥርዓት አልበኝነትን በብርቱ እንደሚዋጋ በመግለጫው አረጋግጧል። #Ethiopia #Kuchazone #Gamozone
https://wolaitatimes.com/?p=4975

Wolaita Times

22 Oct, 14:17


ምርጫ ቦርድ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ጨምሮ በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የእግድ ውሳኔ ተላለፈ

በሌላ በኩል አገዳ የተጣለባቸው ፓርቲዎቹ እርምጃው "በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ፓርቲዎችን ከሰላማዊ ትግል ለማውጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው” በሚል ተቃውሞ አስገብተዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

የዕግድ ውሳኔ የተሰጣባቸው ፓርቲዎች የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ናቸው ።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለጊዜው ፓርቲዎችን ከማናቸውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

የዚህን የኮሚሽኑ ውስኔ ተከትሎ እገዳ ከተጣለባቸው ፓርቲዎቹ አንዱ የሆነው የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን ፍሰሃ፤ በፓርቲያቸው ላይ ውሳኔው የተላለፈው “የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች አባላትን መረጃ አላቀረበም” በሚል ምክንያት መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ይህን መረጃ እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ ደብዳቤ በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም እንደደረሳቸው የገለጹት አቶ ሰለሞን፤ ሆኖም ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የአባላቱን መረጃ ለመሰብሰብ “በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳልፈቀደለት” አስረድተዋል። ፓርቲው ይህንኑ ችግሩን ለምርጫ ቦርድ ማሳወቁንም አመልክተዋል።

“ፓርቲው ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው። ሰዎች ተንቀሳቅሰው፤ አባሎቻችን ጋር ሄደው መረጃ አሰባስበው ነው ይዘው የሚመጡት። ‘አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ አይፈቅድልንም፤ የሁለት ዓመት ጊዜ ይሰጠን። ሀገሪቷ ከተረጋጋች በኋላ እናመጣለን። የቦርዱን ትእዛዝ እና መመሪያ እንቀበላለን’ብለናቸዋል”ሲሉም አዲስ ትውልድ ፓርቲ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ማብራሪያ አስታውሰዋል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምርጫ ቦርድ የእገዳ ውሳኔ ማስተላለፉ፤ “በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ፓርቲዎችን ከሰላማዊ ትግል ለማውጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው” ሲሉ አቶ ሰለሞን ተችተዋል። የገዳ ስርአት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሮበሌ ታደሰም የምርጫ ቦርድ ውሳኔ “የሰላም ትግሉ ላይ በር መዝጋት ነው” በማለት የተቃውሞ አስተያየታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ሰጥተዋል።

ፓርቲያቸው ግንቦት 20፤ 2015 ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉን የሚገልጹት አቶ ሮበሌ፤“ለፓርቲው 12 አመራር ለመምረጥ 30 እጩ ማቅረባችሁ ተገቢ አይደለም” በሚል ምክንያት ፓርቲው በድጋሚ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ ማሳለፉን አስረድተዋል። አቶ ሮበሌ ይህንን የምርጫ ቦርድ ውሳኔ“ትክክል ያልሆነ”ሲሉ ነቅፈውታል።

አቶ ሮበሌ የሚመሩት የገዳ ስርአት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ እና የአገው ለፍትህ እና ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 12፤ 2017 ዓ.ም የምርጫ ቦርድን የእግድ ውሳኔ በመቃወም ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ደብዳቤ ማስገባታቸውን ገልጸዋል። ሶስቱ ፓርቲዎች ለምክር ቤቱ ያስገቡት ደብዳቤ፤ የእግድ ደብዳቤው መስከረም 26፤ 2017 እንደደረሳቸው ይገልጻል።

ምርጫ ቦርድ “ወቅቱን ባልጠበቀ እና ጊዜን በማይዋጅ ሁኔታ ደብዳቤዎችን እየጸፈ በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ ችግር እየፈጠረብን ድርጅታዊ ስራዎችን ለመስራት ተቸግረናል” ሲሉም ፓርቲዎቹ በደብዳቤያቸው ላይ አስፍረዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “መድረክ በመፍጠር” ከቦርዱ ጋር “መፍትሔ እንዲያፈላልግ” ፓርቲዎቹ በደብዳቤው ጠይቀዋል።

የሶስቱ ፓርቲዎች ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መድረሱን፤ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። የጋራ ምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ከሶስቱ ፓርቲዎች የቀረበለትን አቤቱታ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍም ሰብሳቢው ጠቁመዋል።
#Ethiopia
https://wolaitatimes.com/?p=4972

Wolaita Times

21 Oct, 17:16


በዎላይታ ዞን የመምህራን ደሞዝ አሁንም አልተከፈለም፤ ትምህርትም አልተጀመረም ቢባልም "ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን ነው የምናውቀው" ሲሉ አቶ ጎበዜ ጎዳና ምላሽ ሰጡ

በሌላ በኩል ደመወዝ የተከለከሉ መንግሥት ሠራተኞች ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ሲል ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኙትን ሁሉ እንደሚሰሩ ጠቅሰው "በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፤ በአንዳንድ መ/ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይታዩም፥ ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ብለዋል።

በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 የመማር ማስተማር ሥራ እንደታጎለ ነው ዓመቱ ያለቀው፡፡ የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም ተሻግሯል መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም።

የቀጠለው የመምህራን ደሞዝ ጥያቄ በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 ዓም የመማር ማስተማር ሥራ እንደታጎለ ነው ዓመቱ ያለቀው። የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም መሻገሩ ነው የሚነገረው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አሁን ላይ በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም፡፡

ዶቼ ቬሌ ያነጋገራቸው በዞኑ ዳሞት ወይዴ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ሁለት የተማሪ ወላጆች በወረዳው በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርት አለመጀመሩን አረጋግጠዋል። አንዳንዴ ተማሪዎች ቤት አንቀመጠም በሚል ትምህርት ቤት ደርሰው እንደሚመለሱ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ “ነገር ግን መምህራኑ ባለመግባታቸው ልጆቻችን ትምህርት ሊጀምሩ አልቻሉም፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም ትምህርት እስኪጀመር በማለት የቀን ሥራ ፍለጋ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ብለዋል፡፡

በዎላይታ ዞን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የመምህራንም ሆነ የሌሎች መንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በወቅቱ አይከፈለም፡፡ ዘግይቶ ቢከፈልም የደሞዛቸው ከ20 እስከ 50 በመቶ ብቻ እየተሰላ እንደሚያገኙ ነው የሚነገረው፡፡ የዞኑ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ የመምህራን የደሞዝ ጥያቄ አለመፈታት የትምህርት ሥረዓቱን እየረበሸ ይገኛል ይላሉ፡፡

የመምህራን ደሞዝ በመቶኛ ተቆራርጦ መከፈሉ አግባብ እንዳልሆነ የጠቀሱት ሊቀመንበሯ“ ይህ ሠላሳ ቀን የሚመገብ ገንዘብ አይደለም፡፡ ሥለሆንም ቶሎ መፈታት ይገበዋል“ ብለዋል።

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የዎላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጎበዜ ጎዳና የመምህራኑ ጥያቄ ተገቢነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ እኛ እንደመምሪያ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን ነው የምናውቀው ያሉት ሃላፊው“ ነገር ግን እስከአሁን ትምህርት ቤቶች አልተከፈቱም በሚል በሪፖርት የደረሰን ነገር የለም ብሏል፡፡

አቶ ታደሰ ሻንካ በዎላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ላለፉት 26 ዓመታት በወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በድጋፍ ሰጪ ሠራተኛነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡ “የሚከፈለኝ ደሞዝ አሁን ካለው የኑሮ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው“ የሚሉት አቶ ታደሰ“ እሱንም ቢሆን በወቅቱ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ከአምስት ቤተሰቦቼ ጋር ችግር ውስጥ እገኛለሁ፡፡ ቤተሰቦቼን ለመመገብ ለጊዜው የመንግሥት ሥራውን በመተውና ወደ ገጠር በመግባት የጉልበት ሥራን አማራጭ አድርጌ እየሠራሁ እገኛለሁ” ብለዋል፡፡

በዚሁ የዎላይታ ዞን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት ደምሴ ቶጋ በወረዳው ለሦስት ወራትና ከዚያ በላይ ደሞዝ ሳይከፈል እንደሚቆይ ይናገራሉ፡፡ ደሞዝ ቢከፈልም በመቶኛ ተሰልቶ በግማሽና ከዚያ በታች እንደሚደርሳቸው የጠቀሱት ደምሴ“ አሁን ላይ እኔን ጨምሮ አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኛ አማራጭ ኑሮ ለመፈለግ ተገዷል፡፡ እኔም የቤተሰቤን ረሀብ ለማስታገስ ስል ገጠር ገብቼ ካዛቫ መትከል ጀምሪያለሁ ” ብለዋል ፡፡

በመንግሥት ተቋማት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ
በዎላይታ ዞን በሚገኙ 17 ወረዳዎች የሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ አለመፈጸም የጤና ተቋማትን ጨምሮ በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያቤቶች ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ አብዛኛው ሠራተኛ ተስፋ በመቁረጥ በሥራ ገበታው ላይ እንደማይገኝ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በዚህም የተነሳ አንዳንድ መሥሪያቤቶች በከፊል ሌሎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል ብለዋል፡፡

“ሠራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደር ሲል ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኘውን ሁሉ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ“ በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንድ መሥሪያቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይስተዋልባቸውም፡፡ ምክንያቱም ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ብለዋል፡፡ #Ethiopia #Wolaita

"ትምህርት አልተጀመረም ቢባልም ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን ነው የምናውቀው"

https://wolaitatimes.com/?p=4969

Wolaita Times

21 Oct, 15:44


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመረጃ ነፃነት የተከፈተው ልዩ አፈና ዘመቻ ከሸፈ

2 መቶ ሺህ በላይ ተከታይ ለማፍራት ዘመቻ ተከፍቶ የነበረው ለምን ተዘጋ ?

የዎላይታ ብልጽግና ፓርቲ አምና ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፌስቡክ ገጽ ተከታይ ቁጥር ወደ 200ሽህ ተከታይ ለማድረስ በአቅጣጫና በቀጭን ትዕዛዝ በዞን ደረጃ ሼርና ላይክ እንዲያደርጉ ለአመራሩ አስገዳጅ አቅጣጫ ተቀምጠው ዘመቻ ተከፍቶ ከ47 ሽህ ተከታይ ማለፍ ያልቻለው ፌስቡክ ገፃቸው ከወራት በፊት የፌስቡክ ህግና ደንብ በመጣሱ ሊዘጋ መቻሉን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

አንድ የቀድሞ የፓርቲ ከፍተኛ አመራር ስለሁኔታው ሲገልፅ፦ "በዞኑ ሁሉም የፓርቲውን ፌስቡክ ገፅ ላይክም ሆነ ሼር በዞኑ ፓርቲ ኮማንድፖስት ስለሚቆጣጠር የዞንና የወረዳ አመራሮች ከሁለት ጊዜ በላይ ሼር እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። ይህን የማያደርግ አመራር በአመራርነቱ እንደማይቀጥል ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጣል" ይላል።

"ይህን ፔጅ ሼርና ላይክ የማያደርግ እንዲሁም በጎ ሀሳብ የማይሰጥ አመራር በኮማንድፖስት በኩል ለሚመለከተው ቀርቦ ከሥልጣን እንዲባረር የሚደረግበት ዋነኛው መስፈርት ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም እኚሁ የቀድሞ አመራር "የዞን ፓርቲ ፌስቡክ ገጽ ላይክና ሼር ለማድረግ እንዲሁም በዞኑ ውስጥ የመልካም አስተዳደር እጦት ስከሰት በመቃወም የሚጽፉትን ማህበራዊ ሚደያዎችን ለማጠልሸት ፌክ/የውሸት አካውንቶች ከዞን እስከ ወረዳ ተከፍቶ እየተሠራ ይገኛል" ሲሉ አስረድተዋል።

አመራሩ ለአብነት ሲጠቅሱ "በማንኛውም በዞኑ ተሿሚ በፌስቡክ በግል አካውንታቸው ብንመለከት የፓርቲውን ዜና ጥሩ ሆነ መጥፎ መጋራትና ላይክ ማድረግ የሹመቱ አንዱ መሥፈርት ነው። ውጤቱ ይሰጣል ተግባራዊ የማያደርጉት ከሥልጣን ይነሳሉ። በእያንዳንዱ ዜና ላይክና ሼር የሚያደርጉ አመራር በኮማንድፖስት አማካይነት ይቆጠራል" በሚል አብራርተዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ፌስቡክ ገጽ የተከታይ ቁጥር ወደ 200ሽህ ተከታይ ለማድረስ በአቅጣጫና በጥብቅ ትዕዛዝ ለወራት በዞን ደረጃ ብሠራም ከ47ሽህ ተከታይ በላይ ማለፍ ያልቻለው ፌስቡክ ገፃቸው በዞን ደረጃ በአዋጅ ሼርና ላይክ እንዲያደርጉ ለአመራሩ አስገዳጅ አቅጣጫ ተቀምጠው ስሰራበት የፌስቡክ ህግና ደንብ በመጣሱ ተዘግቶ አዲሱ 12 ሺህ የደረሰውን በተመሳሳይ መንገድ በማሳደግ ዘመቻ ላይ እንደሚገኙ ተመልክተናል (ዜናቸውን ብንመለከት ከላይክ በላይ ሼር ይበልጣል)።

አጠቃላይ የዞኑ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በፓርቲው ኮማንድፖስት ሀሳብን በነፃናት የመግልፅ መብት በሚጥስ መንገድ እንደሚጠረነፍ የተገለፀ ሲሆን የዚህ ጉዳይ ዋነኛው ማሳያ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ያለውን አመነታ ከማጠልሸት በላይ የመረጃ ነፃነት፣ ታአማንነትና ተደራሽነት እውነታውን ሸፍነው በላይክና በሼር ሥራ የተሠራ የሚመስለው የዞን ፓርቲ ቀጣዩ ዕጣ ፈንታው ምን እንደሚመስ መገመት ይቻላል ያስብላል።

በተያያዘ ዜና ይሄው በመረጃ ነፃነት ላይ የተከፈተው አፈና ዘመቻ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አምና ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፌስቡክ ገጽ የተከታይ ቁጥር ወደ 450 ሽህ ለማድረስ በአቅጣጫና በቀጭን ትዕዛዝ ለወራት በክልል ደረጃ ብሠራም በአሁኑ ወቅት ከ13 ሽህ በላይ ተከታይ ማግኘት እንዳልቻለ ተመልክተናል።

ለመሆኑ በመቶ ሺህዎች ተከታይ ለማፍራት ዘመቻ ተከፍቶ የነበረው ዘመቻ እንዴት ከሸፈ ?
https://wolaitatimes.com/?p=4962

Wolaita Times

21 Oct, 12:21


በፕሬዝዳንቱ የተሰረቀዉ ስታዲየም

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በዎላይታ ሶዶ ይገነባል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ ስታዲየም ተሰርቆ ወደ አርባምንጭ የሄደበትን አጋጣሚ እናስታዉስ እስቲ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አዉ እንግዲህ አጋጣሚዉ የተፈጠረዉ አቶ ተስፋዬ ይገዙን የክልሉ አመራሮች ከአርባ ምንጭ ያባሩበት ወቅት ነው። በዚች ዉዝግብ መሐል ነው። እንግዲህ አቶ ጥላሁን ከበደ ያለ ምንም መሥፈርትና ዉይይት ስታዲየሙን በአርባምንጭ ያስጀመረዉ። አሳቻ ሰአት ጠብቆ ነው የዎላይታ ተወካይ በሌለበት፣ እርምጃዉን የወሰደዉ። ኢትዮጵያ በ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ እየተንቀሳቀሰች ነው፣ እንግዲህ ለዚህ ይመስላል፣ አድሎዉ የተፈጸመዉ። ያ የኢኮኖሚ ጥቅም ይኖረዋል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በመሥፈርት ላይ የተመሠረተ ዉይይት ቢደረግ ኖሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ሶዶ እስቴዲየም ይገባታል፣ ብለን ለማለት የሚያስችሉ መከራከሪያዎችን ቢያቀርቡልን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ የዎላይታ ሶዶ ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማነት፣ ብዙ ሊጎበኙ የሚችሉ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች በቅርብ ርቀት ትገኛለች። ከ67ሺ አመታት በፊት ሰዉ የኖረበት የአፍሪካን ጥንታዊ ስልጣኔ ያስመሰከረዉ ሞቼና በራጎ ዋሻ በጉያዋ ነዉ። ከተማዋ በትንሽ ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት የመብቃት እድሏ ሰፊ ነዉ።

በሕዝብ ብዛት የዎላይታ ሕዝብ ከክልሉ ሕዝቦች አንደኛ ነዉ ብዙ ሚሊዮን በልጦ፣ ለዛዉም በሌሎች አካባቢ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ታፍኖ ባለበትም። በአካባቢዉ በቂ ደረጃቸዉን የጠበቁ ሆቴሎች አሉ። ለልምምድ ከተባለም በትንሽ ዝግጅት ለልምምድ ሜዳነት ዝግጁ መሆን የሚችሎ በዎላይታ ሶዶ የአሁኑ ስታዲየም እና በዩኒቨርስቲዉ ጫፍ የሚገኘዉን መዉሰድ ይቻላል።

በቦዲቲና በአረካ ያሉ ስታዲየሞች ዝግጁ ናቸዉ። አለምንን ተጨማሪ የመለማመጃ ሜዳ ግምባታ፣ ያለምንም ካሳ ክፍያ በአንድ ምድብ የሚገኙ አራት ቡድኖችን ማስተናገድ የሚችሉ አራት ደረጃቸዉን የጠበቁ ስታዲየሞች አሉ። የእግር ኳስ ተሳትፎና ዉጤትን ካየን በደርግ ጊዜ በተጀመሩት መላዉን ኢትዮጵያ በሚያሳትፉ የእግር ኳስ ዉድድሮች ዎላይታ ደማቅ ነበረች፣ ለብሄራዊ ቡድን አራትና አምስት ተጨዋቾች ታስመርጥ ነበረ።

ዎላይታ ቱሳ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ያሸነፈ የመጀመሪያው የደቡባዊዉ ኢትዮጵያ ክፍል ክለብ ነበረ፥ በአፍሪካ ኮንፈደሬሽንም በመሳተፍ የመጀመሪያዉ ክለብ ነው። ከ31 አመት በሁዋላ ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስትመለስ ወቅቱ የአቶ ኃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ተከትሎ ለደቡብ ከወትሮዉ የተለዬ የእኩልነት ቦታ የሚሰጥበት ነበረና አቶ ሳህሉ ገብረወልድ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ጀግናዉና ከወገንተኝነት የጸዳዉ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ከመረጣቸዉ የአርባምንጭ እና የአዋሳ ልጆች ብዙዎቹ የዎላይታዎች ልጆች ነበሩ፥ አበባዉ ቡጣቆ፣ ሲሳይ ባንጫ፣ ባህሉ አሰፋ ቱሳ|ን መጥቀስ ይቻላል።

ዎላይታ ዲቻ ከመጣ በሁዋላ ደግሞ በሊጉ ተፎካኳሪ ሆኖ ከመዝለቁም ባሻገር ለብሔራዊ ቡድን እንቁ ልጆችን ከማፍራቱ በተጨማሪ በአፍሪካ ኮንፈደሬሽን ካፕ የግብጹን ኃያል ክለብ ዛማሌክ ጥሎ በማለፍ ለመላዉ ኢትዮጵያውያን ኩራት መሆኑ CGTN ን በመሰሉ አለም አቀፍ ሚዲያዎች የተዘገበ ነበረ። በወቅቱ በዎላይታ እቴዲየም ባለመኖሩ ቡድኑ በአዋሳ ጨዋታዎችን ያደርግ ነበረ። በአሁኑ ሰአት የዎላይታ ዲቻ አካዳሚ በታዳጊዮች ዉድድር ለተከታታይ አመታት ሻምፒዮን ከመሆኑም ባለፈ ፍሬዎቹ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንጀምረዉ የፕሪሚየር ሊግና የብሄራዊ ሊግ ክለቦችን ከቦዲቲ ከነማና ከአረካ ከነማ ፍሬዎች ጋር ተደምረዉ አጥለቅልቀዋል።

በደጋፊው ብዛትም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተመርጦ የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ ተጫዉቶ ማሸነፉም ይታወሳል። በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በአዋሳ በሚደረገዉ የሊጉ ጨዋታዎች ስታዲየሞችን የሚሞላዉ የዲቻ ደጋፊ ነው። በዎላይታ ሶዶማ ጨዋታ ሲደረግ በኢትዮጵያ ከየትኛውም ከተማ የበለጠ ደጋፊ እስቴዲየም የሚገባበት፣ በየሕንጻዉ ጫፍ ተንጠልጥሎ፣ ከገባዉ በላይ እስቴዲየሙ በመሙላቱ ስታዲየሙ ዙሪያ ላይ ቆሞ እንደሚጠባበቅ ያዬ ሁሉ የሚመሰክረዉ ነው።

እስከ አምና መጨረሻ በክልሉ ብቸኛ የፕሪምር ሊግ ተወካይ ዲቻ ሲሆን፣ ዎላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲና አረካም በብሄራዊ ሊግ አሉ። ስለዚህ የቀድሞ ደቡብ ክልልን እንኳን ብንወስድ፣ በአፍሪካ መጀመሪያ የተሳተፈዉ ዎላይታ ቱሳ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ አዋሳ ከነማ ነበረ፣ ቀጥሎም ዎላይታ ዲቻ ነው። መሥፈርት ቢኖር የምትመረጠዉ ዎላይታ ሶዶ እንደምትሆን ግልጽ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህንን አድሏዊ ዉሳኔ ግን አቶ ጥላሁን ብቻዉን ደፍሮ ይወስናል? ከጀርባ ሌሎች አካላት ያሉ አይመስልዎትም?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ያዉ ይህ መንግስት የዎላይታን ሕዝብ በበቀልና በተንኮል እንደሚያስተዳድር የአደባባይ ሚስጢር ነው ። ከጀርባ ሌሎች አካላት እንደሚኖሩ ግልጽ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህንን የዎላይታ ተወካዮች በካቢኔ ስብሰባዎች፣ በክልል ምክር ቤትም ሆነ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለምን አያነሱም ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንደኛዉ ተጋፋጭ በነበረዉ የነዳጋቶ ኩምቤ አስተዳደር ወቅት ብልጽግና በዞኑ ላይ ያደረገዉ መፈንቅለ መንግስት ብዙ ዞኑን ጎድቷል። አብዛኛው አመራር መንግስት በዎላይታ ሕዝብ ላይ ጤናማ አመለካከት እንደሌለዉ አምኖ የተቀበለ ይመስላል። በጣም ያሳዝናል። ሌላዉ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ዎላይታ በፌደራልም፣ በክልልም የሚገባትን ሚዛናዊ ዉክልና ተነፍጋለች፣ ስለዚህ ለዘርፈ ብዙ ተንኮሎች ዞኑ ተጋልጧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

በተያያዘ አርባምንጭ ከተማ እያስገነባ ላለው ስታዲየም ግንባታ ሁሉም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ በአንድ አባወራ 1000 ብር እንዲያዋጣ ሊደረግ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ቃል በቃል ለጠቅላላ አማራሩ በዎላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከል መዝጊያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት መናገራቸውን ከስብሰባው ተሳታፊዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአርባምንጭ ስታድየም ተገንብቶ እስከሚያልቅም አንድም ሜጋ ፕሮጀክት የትኛውም ዞን ሆነ ልዩ ወረዳ ህዝብ አስተባብሮ ለማሰራት ቢያቅድ አመራሩ ተጠያቂ እንደሚሆንና ክልሉም ለሚሰራው ስራ እውቅና እንደማይሰጥ ተነግሯል።

ለአፈጻጸሙ ከጋሞ ዞን አመራሮች ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ወደ ተግባር እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፏል።

በቅርብ ጊዜ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ለትውልድ አካባቢያቸው በክልሉ ካብኔ የጋራ ውሳኔ ባልተሰጠበት ለአርባምንጭ ከተማ ስታዲየም ግንባታ በሚል ከመንግሥት በጀት 500 ሚሊዮን ብር መስጠታቸው ጫፍ የወጡ አድሏዊ አሰራሮች አንዱ ማሳያ በሚል በርካቶች ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል።

#WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Etv #Ebc
https://wolaitatimes.com/?p=4959

Wolaita Times

20 Oct, 13:40


የብልጽግና ከፍተኛ አመራር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ብልሽት ምን አሉ? - በምስጢራዊ መረጃ - "የክልሉ ህዝብ ሰላምና ልማት እንድያገኝ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው እንድመለስላቸው ከሁሉ በላይ የህዝቦች አንድነት ተጠብቆና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይህ ፀረ ህዝብ፣ ጸረ ለውጥ፣ ፀረ ብልጽግና ፀረ-ህብረትና ፀረ-አንድነት የሆነ ሴረኛ ሃይል ልስተካከል ይገባል፡፡ ካልሆነ….. ጨው ለራስ ካለ ይጣፍጥ!"........ይቀጥላል 👇
https://wolaitatimes.com/?p=4955

Wolaita Times

20 Oct, 13:40


የብልጽግና ከፍተኛ አመራር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ብልሽት ምን አሉ? - ምስጢራዊ መረጃ ከፓርቲው አመራር

የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ስለ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የፖለቲካ ብልሽት ምን ይላሉ ?

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለህዝብ፣ ለመንግሥትና ለፖርቲ ህልውና ለማስጠበቅ በሚል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አጠቃላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተስተዋለ የሚገኘውን የፖለቲካ ብልሽት በተመለከተ ይፋ እንዲደረግ በዝርዝር መረጃዎችን አድርሰዋል። ለዝርዝር መረጃዎች አመራሩን በሚዲያችንና በተከታዮቻችን እያመሰገንን ቀጥታ ወደ ጉዳዩ እንግባ።

መረጃው "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን ከማፍረስ አደጋ ማዳን ይቻል ይሆን?" እያለ ይጀመራል።

"የቀድሞ ደቡብ ክልል ከፈረሰ በኃላ የተደራጀው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እድሜው አንድ ዓመት ነው፡፡ በዚህ ክልል የሚኖረው ህዝብ በክልል አደረጃጀት ጥያቄ ምክንያት ላለፉት 5 ዓመታት ምንም አይነት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ጥያቄዎች ሰሚ ጠፍቶ የቆየ ህዝብ ነው" ሲል ያስረዳል፡፡

እኚሁ ከፍተኛ አመራር "የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ከተመለሰ የእናንተ ጥያቄ ይመለሳል፤ ልማት ይሰራል ተብሎ በየአካባብዉ በይደር የቆዩ አጀንዳዎች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ አዲስ የተደራጀው ክልል ጤናማ፣ ብቃትና ስነ ምግባር ባላቸው አመራሮች የተደራጀና የተመራ ቢሆን ኖሮ ክልሉ ለአገር የሚበቃ ድልብ አቅም ያለው ክልል ነበር" ይላል፡፡

"በሴራ ለእኩይ አላማ የተደራጁ ወንበዴና ስነ ምግባር የጎደላቸው አመራሮች ግን ከአገራዊ ራእይ በተቃራኒ ስለቆሙ የክልሉ ህዝብ ገና ሳይደራጅ ሌላ ሀሳብ ውስጥ እንዲገባ ተስፋ እንድቆርጥ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በይደር የቆዩ አጀንዳዎች ባለቤት የላቸውም፡፡ አሁንም በየቀኑ ሌላ ተቃራኒ አጀንዳ በመፍጠር ክልሉን የትርምስ ቀጠና እያደረጉ ናቸው፡፡ በየዞኑ አጀንዳ ተፈብርኮ የሚሰጠው በክልሉ ቁልፍ አመራሮች ነው፡፡ በአንድ ዞን ሁለት ቡድን በማደራጀት አንዱ አንዱን እየመረጀ አከባቢዎች በሙሉ የትርምስ ቀጠና ሆነዋል" በማለት የሴራ ወጥመድ አብራርተዋል፡፡

የመረጃ ምንጫችን ጨምሮ ሲያስረዳ "ለአብነት ጋሞ ዞን፣ ኮንሶ ዞን፤ ዎላይታ ዞን፣ ደቡብ አሞ ዞን፣ ጎፋ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን፣ ቡርጂ ዞን፣ ጌዴኦ ዞን… ሁሉም ዞን ውጥረት ውስጥ ናቸው። ለዘመናት አብሮ በአንድ ዞን ተደራጅቶ የኖሩ ያሁኖቹ የአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በጦርነት ውስጥ ናቸው፡፡ የአጀንዳው ባለቤት የክልሉ ፓርቲ ሃላፊ ነው፡፡ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሪነት በጋሞ ዞን የዜይሰ እና የቁጫ ህዝቦች የመብት ጥያቄ ለማፈን በሚደረገዉ አመፃ ፖለቲካ በርካታ ንፁሃን ዘጎች ሞትና እስራት እየተሰቃዩ ይገኛሉ" ብለው ያብራራሉ፡፡

አክለውም "የቀድሞ ሰገን ዞን ተብሎ የሚታወቁ አከባቢዎች በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ናቸው፡፡ የግጭቱ መሪ ስነ ምግባር የጎደለው ሴተኛ አዳሪዎችን ይዞ በየመጠጥ ቤት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሽጉጥ እያወጣና እየተኮሰ ዓመት ሙሉን የከረመዉ የክልሉ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ነው፡፡ የጎፋ ዞን በእርስበርስ ግጭትና መከፋፈል እየተተራመሰ ይገኛል፡፡ መሪ ተዋናዩ በሰማይ በምድር ከዎላይታ ጋር አንደራጅም ያለው አሁን የዲላ ክላስተር አስተባባሪ የሆነ ግለሰብ ነው" ብለዋል።

"ጌዲኦ ዞን ለሁለት ተከፍሎ እየተናጠ ነው፡፡ መሪው የክልሉ ፕረዝዳንት ሲሆኑ በህዝብ ተጠልቶ በምርጫ ጭምር ተሸንፎ ብልጽግናን የጣላውና ያዋረደው አቶ ሃይለማርም ተስፋየን አስተባባሪ አደርጋለሁ በሚል እና በህዝብ ቅቡልነቱና በእውቀቱ ተወዳዳሪ የለሌለው ዶ/ር አባባዬሁ ታደሰን "አነሳለሁ" በሚል ቅዠት ጌዴኦን እያበጣበጠ ይገኛል፡፡ በቅርቡ የክልሉ ምክትል ፕረዝዳንት ሆኖ የመጣው ሽማግሌም ገና ከመምጣቱ እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የጎሳና የቤተሰብ አደረጃጀት ፈጥሮ ዎላይታ ዞንን እያተራመሰ" እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

"እነዚህ አካላት ጸረ ብልጽግና ናቸው ሲባል በብዙ ማሳያ ስሆን በቀን 8/02/2017 የተጠቃለለው የብልጽግና ፓርቲ ሥልጠና በክልሉ ሶዶ ማዕከል የተጠቃለለ ብሆንም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዳይቀይሩ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሰጠው ማጠቃለያና ከስራ ስምሪት ተቃራኒ በሆነ መልኩ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አሰልቺና ከስልጠና ርዕስ ጋር የማይሄድ ማጠቃለያ በመስጠት ሀገራዊ የፓርቲ ስልጠና አቅጣጫውን ስቶ እንድጠናቀቅ አድርገዋል" በማለት ትዝብታቸውን አጋርተዋል፡፡

"በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ በተለይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመሩ ኢንሼቲቦች አንድ እንኳን በክልሉ ዉጤታማ ልሆኑ አልቻለም፡፡ በግል ባለሀብቶች ደረጃ የተሰራውን የእርሻ ልማቶች መጎበኘት ማንን ለመሸወድ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ይህ የሽወዳ ፖሌቲካ ዲስኩር ህዝቡን ከደኢህደን ፖለቲካ በላይ አንገሽግሾታል" ብለዋል፡፡

እኚሁ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለህዝብ፣ ለመንግሥትና ለፖርቲ ህልውና ለማስጠበቅ በሚል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እየተስተዋለ የሚገኘውን የፖለቲካ ብልሽት ይፋ እንዲደረግ በላከልን መረጃ፦ "የኮንትሮቫንድ ንግድ ቀጥተኛ ተሳትፎ፣ በከበሩ ማዕድናት (በድንጋይ ከሰል) እና በሌሎች ኢንቨስትመንት ዘርፎ የሚታየው ሌብነት፣ ዝርፍያና መሰል ተግባራት በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርና በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ቅንጅት በዲላና በኮንሶ መስመር ዋነኛ የገቢ ምንጫቸው ሆኗል፡፡ በከፍተኛ አመራሩ አማካይነት በየሆቴሉ የሚደረገው ብልግና ለማንም የተሰወረ አይደለም" በሚል ገልፆታል፡፡

"በክልሉ ህዝብ ዘንድ መጠራጠር፣ መተማማትና የባለቤትነት ስሜት እንዳይሰማቸው ፍትሃዊነት የጎደለ ውሳኔዎች፣ ግልጸኝነት የጎደለው አሰራር የራስ ቡድን በማደራጀት በቡድን አማካኝነት የደቦ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መቃቃርን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርጉት በአንድ በኩል የራሳቸውን የግል ጥቅም ለማግበስበስ፣ በሌላ በኩል አገራዊ ሪፎርም ወደ መሬት እንዳይወርድና ተንገራግጮ እንዲቆም የተሰለፈ ብልፅግና ፓርቲ አደራና ሹመት የተሰጠዉ ግን አደራዉን ከነመፈጠሩ የዘነጋዉ የደቡብ ክንፍ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም" በማለት አረጋግጠዋል፡፡

በማጠቃለያው ሀሳባቸውም፦ "የክልሉ ህዝብ ሰላምና ልማት እንድያገኝ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው እንድመለስላቸው ከሁሉ በላይ የህዝቦች አንድነት ተጠብቆና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይህ ፀረ ህዝብ፣ ጸረ ለውጥ፣ ፀረ ብልጽግና ፀረ-ህብረትና ፀረ-አንድነት የሆነ ሴረኛ ሃይል ልስተካከል ይገባል፡፡ ካልሆነ….. ጨው ለራስ ካለ ይጣፍጥ!" የሚል የማሳሰቢያ፣ የማንቂያ እንዲሁም በክልሉ እየተስተዋለ ያለው ሁኔታ በአስቸኳይ በሚመለከታቸው አካላት ማስተካከያ እርምጃ እንዲደረግበት ለህዝብም ለመንግሥትም ወደ አደባባይ አውጥተዋል።
#Ethiopia #SouthernEthiopiaregion #Wolaita #Gofa #Gedio #Gamo #Burji #Konso #Arizone #Kore #Alezone #Basketo

Wolaita Times

19 Oct, 17:58


"ከባድ ዱብዳ በኢቲቪ ከመዘገቡ በፊት ተስፋዉ ለምልሞ የነበረዉ ሕዝብ፤ ኩምሽሽ አለ" - ፕሮፌሰሩ ስለ ኢቢሲ ምን አሉ?

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ Ethiopian broadcasting corporation በቅርቡ በዎላይታ ሶዶ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ቅርንጫፍ እየከፈተ ነው። Etv አፋን ኦሮሞም ሥራ ጀምሯል ይህን እንዴት ይመለከቱታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ጥሩ ነው። በሚዲያ መሰረተ ልማት ደረጃ ከዛ ዉጪ ግን ጣቢያዉ ፍጹም የካድሬነት ሥራ የሚሰራና ሐቀኛ የሕዝብ ድምጽ የማይደመጥበት መሆኑ ላይ የሚቀይረዉ ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እስቲ ሚዲያዉ በዎላይታ በድጋሚ በተደረገዉ ሕዝበ ዉሳኔ ዋዜማ ላይ የሠራዉን እና ተድበስብሶ ያለፈዉን ከባድ ወንጀል እናስታዉስ፥ በተጨማሪም ማን አደረገዉ ብለዉ እንደሚያምኑ ሐሳቦትን ቢያጋሩን?

ፕሮፈሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ በጣም ደስ ይለኛል፥ ይህ በብሔሮችና ብሔረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን ሕገመንግስታዊ መብት ላይ የተፈጸመ አደገኛ ወንጀል ተረስቶ እንዳይቀር በማስታወስህ አመሰግናለሁ። በዎላይታ ዞን ድጋሚ ሕዝበ ዉሳኔ ሊካሄድ በዋዜማው ማታ የተሰራዉን ወንጀል ክብደት እና አዉድ ለመረዳት የሕዝበ ዉሳኔዉን ዳራ እንደሚከተለዉ አስቀምጣለሁ።

የዎላይታ ሕዝብ ክልል ጥያቄ ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑ ቢታወቅም ስለዛ ዝርዝር ጉዳይ ማንሳት የዛሬ ርዕስ ስላልሆነ እዘለዋለሁ። ብቻ ከለዉጡ በሁዋላ በሐገሪቱ ከብደዉ ከተነሱ የፖለቲካ ጥያቄዎች አንዱ የውላይታ ክልልነት ጥያቄ እንደሆነ ግልፅ ነው።

ይህን ጥያቄ ላለማስተናገድ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አንድ ዓመት ሙሉ ሥራ ሳይሰራ ደሞወዝ ከመብላቱ በተጨማሪ የፌደራሉ መንግሥት በዎላይታ ዞን ላይ መፈንቅለ መንግሥት እስከ ማድረግ መድረሱ እና ብዙ ንጹሐን ምትክ የለሽ ሕይወታቸውን ሲያጡ ብዙዎች አካላቸዉ እንደጎደለም ይታወሳል፣ ይህም የዚሁ ጥያቄ አፈና አካል ነው።

ከዛ ሁሉ በኃላ መንግሥት በጫና የደቡብ ኢትዮጵያን ክልል ለመመሥረት፣ እርግብ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን አደረጃጀት እደግፋለሁ፤ ጎጆ ደግሞ አልደግፍም በሚል ባካሄደዉ ሕዝበዉሳኔ የዎላይታ ዞን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝና ድጋሚ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል።

በዚህ ሁሉ ሂደት እንግዲህ የዎላይታ ፓርቲዎች፣ ብዙ ሊህቃንና አክቲቪስቶች በሙሉ ከተወሰኑ የብልጽግና ካድሬዎች ዉጪ ለሕዝበ ዉሳኔዉ ሂደትም ሆነ ዉጤት እዉቅና እንደማይሰጡ አሳዉቀዉ፣ አባሎቻቸዉም ሕዝቡም እንዳይሳተፍ በመቀስቀሳቸዉ በጣም ብዙ ሰዉ እነሱን ሰምቶ በመጀመሪያዉ ሕዝበ ዉሳኔ አልተሳተፈም። ፓርቲዎቹም ለዎላይታ የክልልነት አማራጭ ካላካተተ እንደማይሳተፉ ገልጸዉ ቆይተዋል ።

ነገር ግን በሕዝበ ዉሳኔዉ ጎጆ ምንን ይወክላል የሚለዉ ጥያቄ ለሕዝቡ ምንን እንደሚወክል እንዲገለጽ ቢጠየቅም መልሥ የሰጠ የመንግሥት አካል አልነበረም። በዚህ መሐል የዎላይታ ሕዝበ ወሳኔ ድጋሚ ይካሄድ ብሎ ምርጫ ቦርድ በወሰነ እና ቀን ከቆረጠ በኃላ፣ በሕግ አግባብ ጎጆ በዉስጠ ታዋቂነት የዎላይታን ክልልነት ትወክላለች የሚል መከራከሪያ ማንሳት በተወሰኑ የዎላይታ ሊህቃን ዘንድ ተፈጠረ።

በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ሐሳቡ በመዛመቱ እና ብዙ አክቲቪስቶች በመጨመራቸዉ ከፍተኛ ተቀባይነት አገኘ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክልል መሆን በእጃችሁ ነው ብለዉ እንደነበረም እያመሳከሩ የሚቀሰቅሱ ሰዎች ነበሩና እዉነትም ጎጆ መዉጫ መንገድ ነው የሚለዉ በብዙ የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ ተቀባይነት አገኘ።

የዎላይታ ክልልነት ጥያቄ ታፍኗል ብለዉ አኩርፈዉ የነበሩ ብዙ ሰዎችም ወደ ጎጆ መሰባሰብ ጀመሩ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ተቃዉሟቸዉን ቢቀጥሉም የተወሰነ ደጋፊያቸዉ ካለመሳተፍ ወደ ጎጆ መራጭ ተቀላቀለ፣ ብዙ እርግብን በመጀመሪያዉ የመረጠ ሰዉ የጎጆ ቀስቃሽ ሆኖ ተገኘ። በሚገርም ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ ጎጆ ወደ ዎላይታ ክልል ለመድረስ ሰላማዊ የትግል መንገድ ነው ብሎ አምኖ ቀሰቀሰ።

በሚገርም ሁኔታ አትሳተፉ ከሚሉ ሊህቃንም የተወሰኑት በመጨረሻ የሕዝቡን ሁኔታ በማየት አቋዋማቸዉን በማሻሻል "አትሳተፉ! ከተሳተፋቹ ጎጆን ምረጡ !" ወደሚል ቀየሩ።
በጣም በሚገርም ሁኔታ በዋዜማው ጎጆ ያሸንፋል የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚያደፋፍር ሁኔታ ተፈጠረ በሕዝቡ ዘንድ።

በሕዝበ ዉሳኔዉ ዋዜማ ምሽት ሕዝቡ ጎጆ የዎላይታን ክልል ያስገኛል ብሎ በተዘጋጀበት አስደንጋጭ፣ ሕገወጥ፣ የብሄር ጭቆና መኖሩን ያስመሠከረ፣ ብሄሮችንና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲሁም ሕገመንግሥቱን የናቀ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንኳን ጎጆ ምንን እንደሚያመለክት ለመግለጽ ፈቃደኛ ባልነበሩበት፣ አቲቪ በምርጫዉ ቅድመ ዝግጅት ላይ የምርጫ አስፈጻሚ ቃለመጠይቅ አስታኮ ጎጆ የሚወክለዉ በቀድሞዉ ክልል መቀጠልን እንደሆነ የሚገልጽ ዘገባ በመዘገብ ለሕዝበ ዉሳኔዉ የተዘጋጀዉን ሕዝብ ተስፋ አስቆረጠ።

ይህ ከባድ ዱብዳ በኢቲቪ ከመዘገቡ በፊት ተስፋዉ ለምልሞ የነበረዉ ሕዝብ፤ ኩምሽሽ አለ። የሕዝበ ዉሳኔዉ ተቃዋሚ ዎላይታዎች ብለን ነበር ሲሉ የጎጆ ቀስቃሾች አንገታቸዉን ደፉ። ምርጫ ቦርድ ዘገባው የሕዝበ ዉሳኔዉ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሎ ከኢቲቪ ገጽ ከተወሰነ ቆይታ በሁዋላ እንዲነሳ ቢያስደርግም ያመጣዉ ለዉጥ የለም። በወቅቱ በሕዝቡ ዘንድ የተፈጠረዉ ተስፋ መቁረጥ አስደንጋጭ ነበረ።

ይህን ያደረገዉ ማነዉ ? ያዉ scenarios የሚለዉ ቃል ወደፊት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን መላምት ማስቀመጫ ካልሆነ በፊልምና ድራሜ አልያም በስነ ጽሑፍ ሥራዎች ላይ ተፈጽመዉ አድራጊያቸዉን መለየት ሳይቻል ሲቀር ደራሲዉ በምዕናቡ ሊያስብ የሚችላቸዉን ነገሮች ለመገመትም ጥቅም ላይ ይዉላል። እንግዲህ የኢትዮጵያ ፖለቲካም ድራማ ነውና የተወሰኑ senarios አስቀምጠን እንይ፦

1. ኢቲቪ ዉስጥ የሚገኝ deep state ነው?

deep state which acts as state with in state. ይህ ሊሆን እንደሚችል ለመጠራጠር በቂ ምክንያቶች አሉን። ለምሳሌ ያዉ የሐገራችን ተቋዋማት ፈደራል ሥርዓት እንከተል እንጂ አካታችነት በዞረበትም አያልፉምና አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ቋንቋቸዉ በዋናነት የአማርኛ ከመሆኑና በሌሎች ምክንያቶች የአሀዳዊነት ፖለቲካአራማጆች የተሞሉ መሆናቸዉ ይታወቃል። ለአሃዳዉያን ካምፕ ደግሞ የዎላይታ ኦቶኖሚ ማግነት የእግር እሳት ነው።

ሌላዉ ከዚህ በፊት ለምሳሌ "ንጉስ ጦና አድዋ አልዘመተም መሀል ሐገሩን ሲጠበቅ ነበር" ተብሎ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተዘግቦ ነበር፤ ሆኖም ከፍተኛ ተቃዉሞና ብዙ ጥያቄ በማስነሳቱ፣ በ2014 ዓ.ም ዘምቷል ብለዉ ወደ ዎላይታ ሶዶ መጥተው ሌላ ዘገባ ሰርተዋል። እንግዲህ ይህ በመንግሥት ተቋዋም በመሠግሠግ የሚሰራ ሸፍጥ ነው።

2. ብልጽግና ፓርቲ መራሹን መንግሥትን ወይንም የአስፈጻሚዉ አካል ቁንጮዎችን ነው?

ለዚህ ጥርጣሬ የሚዳርገን አንድ ተራ ጋዜጠኛ ደፍሮ እንደዚህ አይነት ከባድ ወንጀል የሆነ ዘገባ ይሰራል ወይ? የጣቢያዉስ አሰራር ዘገባዉ ከመቅረቡ በፊት ዉድቅ ያላደረገዉ ለምንድነው?

የጋዜጠኛዉ ሆነ ጣቢያዉ ምንም አይነት ተጠያቂነት ባለመኖሩ፣ በነጻ መቀጠላቸዉም ይህን ጥርጣሬያችንን ያጎላል።

3. በምርጫ ቦርድ እራሱ ?

Wolaita Times

19 Oct, 17:58


በሁለቱም ሕዝበ ዉሳኔዎች ምርጫ ቦርድ ያፈጠጡና ያገጠጡ የብሄር ጭቆናዎችን ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ከመቆየቱም ባሻገር የዎላይታን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት ከፍተኛ አድሎዎችን ሲፈጽምና እና መሰረተ ቢስ ዉጀላዎችን ሲያሰራጭ ነበር። ለምሳሌ ሕዝበ ዉሳኔዉ ትርጉም የለሽ መሆኑን እያወቁ ማስፈጸም፣ ፈደሬሽን ምክር ቤትን መጠየቅ የሚችሉትን ጥያቄ መጠየቅ አለመፈለግ፣ ሕዝቡ ቋንቋዉን በሚችሉ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንዳይ ገለገል መከልከል፣ አለሥራቸዉ መታወቂያ ፈታሽ መሆንና የያዛችሁት ስድስት ወር ያልሞላዉ አዲስ መታወቂያ ነው በማለት እንዳይመርጡ መከልከል። ሌላዉ ቃለመጠይቅ የተደረገለት ግለሰብ የምርጫ ቦርድ አስፈጻሚ የሆነ መሆኑ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

#WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Etv #Ebc

"ከባድ ዱብዳ በኢቲቪ ከመዘገቡ በፊት ተስፋዉ ለምልሞ የነበረዉ ሕዝብ፤ ኩምሽሽ አለ" - ፕሮፌሰሩ ስለ ኢቢሲ ምን አሉ?
ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።👇
https://wolaitatimes.com/?p=4950

Wolaita Times

19 Oct, 15:24


የሙስና ቅሌት በጠበላ አመራሮች

ከታች በፎቶ የሚታየው በዎላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ስሙ ዮሐንስ ቡናሮ ይባላል። ከታች በፎቶ የተያያዙ የመሬት ካርታ ባለቤቶች በቡናሮ ስም የሚጠሩ ነገር ግን የጠበላ ከተማ ነዋሪ ያልሆኑ ግለሰቦች የከንቲባዉ ቤተሰብ ተደርገዉ ከማዘጋጃ ሳይት ፕላን የተሰራላቸዉ ናቸው።

በእነዚህ ግለሰቦች ስም ጠበላ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ባሉ ቀበሌያት ምንም አይነት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ማረጋገጫ የለለ ሲሆን ከንቲባዉ በእነዚህ ስም የተሰሩ መሬቶችን ቀስ በቀስ እየሸጠ ገንዘቡን እየተቀበለ እንዳለ ከማዛጋጃ ቤታዊ ጽ/ቤት አመራር የነበረ ግለሰብ አረጋግጦልናል።

5 የሚሆኑትን መሬቶች ሽጦ ከንግድ ባንክ በምስቱ ስም ብሩን ትራንስፈር የተደረገ ሲሆን የተቀሩትንም ለመሸጥ በመሬት ደላሎች ጋር በወኪሉ በኩል እየጨረሰ ስለመሆኑ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው ስነድ መረጃ ያመለክታል።

ሰነዱ ከንቲባዉ አሳትሞ ባሰራጨዉ የተባለው ሃሰተኛ ደረሰኝ ከ800 ሺህ ብር በላይ የገቢ እና የሊዝ ግብር ተሰብስቦ በከንቲባዉና በተወሰኑ ግለሰቦች ስም መከፋፈሉን ይጠቁማል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ሌላው "2016 ዓ.ም የጠበላ አንደኛው ደረጃ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪወች ለት/ቤቱ አጥር ግንባታ በሚል ከሃገር ዉጭ እና ዉስጥ የቀድሞ ተማሪዎች፣ የከተማዉ ባለሃብቶችና ሌሎች አካላት የተሰበሰበውን 10 ሚሊዮን ብር ምንም ሳይሰራ ከወቅቱ ት/ቤት ሃላፊና ርዕሰ መምህሩ ጋር ተሻርከዉ አጥፍቷል" የሚል መረጃ አድርሰውናል።

የመንግስት ሰራተኞች የሰሩበትን ደመወዝ ማግኘት አለመቻል ብቻ ሳይሆን ለምን ብለው የሚጠይቅ በሚታሰርበት ዞን እንደዚህ አይነት የሙስና ቅሌት በየአካባቢው በአመራሮቹ ደረጃ እየተፈፀመ እንደሆነ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታል።

ለዛሬው ከላይ በዎላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዮሐንስ ቡናሮ እና አባሪዎቹ በተደራጀ መንገድ ሌብነት ተፈፅሟል ተብሎ በመጠርጠር በሰነድ ተደግፎ የተደረሰው መረጃ የፍርድቤት ሂደት ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት ለመስጠት በሚል የተወሰነ ሰነድ ብቻ ያቀረብን ሲሆን ጉዳዩ የደረሰበትን ተከታትለን እናቀርባለን። #Ethiopia #Wolaita

Wolaita Times

19 Oct, 14:22


በደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ዞን የሰሩበትን ደመወዝ የጠየቁ መምህራን መታሰራቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን በዳሞት ወይዴ ወረዳ ሶስት መምህራን የሐምሌ ወር ደሞዛቸውን ስለጠየቁ ብቻ ትላንት ሐሙስ 7/2/2017 ከሌሉት 9:00 አካባቢ ከቤታቸው በፀጥታ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ቤተሰቦቻቸው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

እንደ ቤተሰቦቻቸው ገለፃ በፀጥታ ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት መምህራን በአከባቢያቸው ባለው ፓሊስ ጣቢያ ሳይሆን ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ሰሊሆም ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ አስረድተዋል።

እነኚህ የሰሩበትን ደመወዝ የጠየቁ መምህራን፦ መ/ር ወንድምዓለም ሙላቱ፣ መ/ር ዳንኤል ፋልታሞ እና መ/ር መስፍን ዳዊት ስለመሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባገኘው መረጃ መሰረት፦ በዞኑ የከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ትግቢውን አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህም ምክንያት በተለይም በግል የጤና ተቋማት ለመታከም ዐቅም የሌላቸውና ከዚህ በፊት በማኅበረሰብ ጤና መድኅን ሽፋን በነዚህ ተቋማት አገልግሎት ሲያገኙ የቆዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በከፋ የጤና ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

በዞኑ በሚገኙ ወረዳ ውስጥ ለመምህራኑ ተገቢው ደመወዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ከ65 በመቶ በላይ መማር ማስተማር ስራ ተቋርጧል፡፡

የመንግስት ሰራተኛ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት ተነፍጎ በዞን ውስጥ የሚሠሩ ብዙ ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች በተቆራረጠ ክፍያ እና ደመወዝ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምክንያት ለከፋ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች ተጋልጠዋል።

ሠራተኞቹ ሌላ ገቢ እንደሌላቸውና ደመወዝ በመቋረጡ ምክንያት ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የዕለት ጉርስ ለማግኘት እንደተቸገሩ፣ የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ፣ ከደመወዝ ጋር በተያያዘ በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ብድርም ማግኘት ስላልቻሉ ሕይወታቸውን ለማቆየት የቤት እቃ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

አሁን አሁን በአከባቢው ደመወዝ መጠየቅ ወንጀል እስኪመስል ድረስ ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ የደመወዝ ክፍያ በፈለገበት ሰዓት ቆራርጦ መክፈል የተለመደ እና ህጋዊ አሰራር ከሆነ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡

ከዚህም የተነሳ የሰራተኛው ህይወት ከድጡ ወደማጡ እንዲገባ በመዳረጉ አቤቱታቸውን እንኳን የሚሰማ ጠፍቶ ችግሮች እየተባባሱ ከዕለት ወደዕለት ወደ ባሰ ድህነት ውስጥ ሰራተኛው እንዲገባ ተዳርጓል፡፡

ከሁሉም በላይ ከደመወዝ አለመከፈል ጋር ተያይዞ ቅሬታ እና ተቃውሞ ባሰሙ፤ ፍትህ በጠየቁ ግለሰቦች ላይ ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ ጭምር እየደረሰባቸው የሚገኝ ስለሆነ የፌዴራል የመንግሥት፤ የክልል የመንግሥት እና የዞን የመንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እርምጃዎችን በመውሰድ ለሠራተኞች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ መከፈሉን እና ሰብአዊ መብቶቹ መከበራቸውንና መጠበቃቸውን እነዲያረጋግጡ ጥሪ ቀርቧል።

የሥራ መብት በተለያዩ ዓለምአቀፍና አህጉርአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ዕውቅና ካገኙ መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች አንዱ ሲሆን የሥራ መብት የሠራተኞች ደመወዛቸውን በሙሉና በወቅቱ የማግኘት መብትንም የሚጨምር ሲሆን ለሠራተኞች ተገቢውን ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያዎችን በወቅቱ አለመክፈል ሠራተኞች እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር የሚችሉበትን መንገድ የሚገድብ እና የሥራ መብት ጥሰት ሆኖ የሚቆጠር ነው ይላል፡፡

የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በደመወዝ ጥበቃ ስምምነት 1949 (ቁጥር 95) አንቀጽ 12 እና በደመወዝ ጥበቃ ምክረ ሐሳብ 1949 (ቁጥር 85) አንቀጽ 4 ሥር የደመወዝ ክፍያ በመደበኛነት ሊከፈል እንደሚገባና በተለይም ደመወዛቸው በየወሩ ወይም በዓመት ተወስኖ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ የደመወዝ ክፍያ ሊፈጸም እንደሚገባ ይደነግጋሉ።

ይህ መብት በሀገራዊ ሕጎች ዕውቅና ያገኘ እና በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2017 እና በደቡብ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 175/2011 ጭምርም የተደነገገ ቢሆንም በአከባቢው በተቃራኒው ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
#Ethiopia #Wolaita

https://wolaitatimes.com/?p=4947

Wolaita Times

19 Oct, 10:53


ህብረተሰቡ በወረርሽኝ በሽታ እየተሰቃየ የተጠራው ድግስና የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች ወግ

በዞኑ ሰሞኑን በተከሰተው ወረርሽኝ በሽታ የበርካቶች ህይወት እያለቀ እንደሆነ ከየወረዳው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በየዕለቱ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ህብረተሰቡ በአከባቢው በቂ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ በቀላሉ ልድኑ በሚችሉ በሽታ ምክንያት እየተቀጠፈ ነው። ህዝቡና በአከባቢው የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች አስቸኳይ ድጋፍ ከሚመለከታቸው አካላት እንዲደረግ እየወተወቱ ይገኛሉ።

በተቃራኒው የህዝብ ሞትና ስቃይ ግድ የማይሰጣቸው የሚመስሉ የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች የህዝብ ሞት እንዲቀጥል በትንሹም የተከሰተውን ወረርሽኝ የመከላከል እርብርብ እያደረጉ የሚገኙትን የምን ስልጠና እንደሆነ ባይታወቅም ከ1500 በላይ ለሆኑት ለህብረተሰቡ በሽታ ለመከላከል የመጣውን ገንዘብ ወደ ድግስ ቀይሮ ለመሰባሰብ ቀጠሮው መያዙን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ለመሆኑ ከህዝብ ሞትና ስቃይ በላይ ሆኖ የተዘጋጀው የምን ስልጠና ይሁን ? ትዝብታችሁን አካፍሉን🙏 Wolaita Times #Ethiopia #health

https://wolaitatimes.com/?p=4944

Wolaita Times

18 Oct, 17:03


Urgent Call to Address the Malaria Epidemic in South and Southwest Ethiopia 🦟

Dear Community,

As a dedicated medical professionals in southern and southwestern Ethiopia—including Wolaita, Dawro, Konta, Gamo, and Mizan Teferi—We are sounding the alarm on an escalating malaria crisis in these regions.

Over the past five years, the halt in indoor residual spraying (IRS) has exposed millions of households to malaria, dramatically increasing cases.

Research from The Lancet Global Health (2022) indicates that consistent IRS coverage can reduce malaria incidence by 62% over five years. Without this critical intervention, our local health systems are overwhelmed.

We urgently need to reinstate IRS, especially during peak transmission seasons. We also call upon the World Health Organization and leadership from Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus to support this crucial effort.

Let’s come together to protect our communities and save lives. Your voice can make a difference. 🌍

#MalariaAwareness #Health #Ethiopia #PublicHealth

Thank you for joining this vital cause.

The Statement sent from medical professionals in southern and southwestern Ethiopia to Wolaita Times media.

https://wolaitatimes.com/?p=4941

Wolaita Times

18 Oct, 15:36


ህዝቡ መንግስት የሚጀመረውን እንጂ የሚያጠናቅቀውን ልማት ማየት ለምን አልቻለም ?

ላለፉት ስድስት አመታት ጀምሮ መንግስት በዎላይታ የሚጀመረውን እንጂ የሚጨርሰውን ልማት ለምን ማየት አልተቻለም ? መንግስት በዎላይታ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከሕዝቡ ፖለቲካዊ ምክንያቶችና ከመልማት ፍላጎቱ ጋር በፍጹም የሚጣጣም አለመሆኑ ለምን ይሁን ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባይጠሩም አዲሱ ፕሬዘዳንት ታዬ አስቀስላሴ የዎላይታ ሶዶን ስም በአንደኛ የጠሩት በባለፈው ቅሬታ ይሁን ? እና በሌሎች እንደወትሮው ሁሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለተነሱ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል፥ ዘገባውም ቀጥታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ ይገነባል ተብሎ የዉሃ ሽታ ስለሆነዉ የአስፋልት መንገድ ጉዳይ ሐሳቦትን ቢያጋሩን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አዎ ሁሌ የሚያንገበግበኝን ጉዳይ ነዉ ያነሳሄዉ። በዎላይታ ሶዶ እንደ ዋና ጎዳና የሚታየዉ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ የሚዘልቀዉና ከዛም በዩኒቨርስቲው በር አድርጎ የሚዘልቀዉ መንገድ ነው። ለዘመናት ሕዝቡ ደረጃዉን ጠብቆ እንዲሰራ ሲጠይቅ ከርሞ ከቅርብ አመታት ወዲህ በተደጋጋሚ ይጀመራል ተብሎ ሲጓተት ከርሞ አምና ዲዛይኑ ሳይቀር በዎላይታ ቴሌብዥን ከመተላለፉ በተጨማሪ የተለዋጭ መንገድ ዝግጅት መደረጉም ተዘግቦ እንደነበረ ይታወሳል።

አሁንም በተግባር ግን ምንም የተጀመረ ነገር የለም። አንዴ በመንገዱ የሚገኝ አንድ ተቋም መነሳት የሚገባቸዉን ሱቆች ለማንሳት ካሳ ተከፍሎም ዳተኝነት በማሳየቱ ነው የተስተጓጎለዉ የሚሉ ጭምጭምታዎች ነበሩ። አሁን ደግሞ የተለያዩ የመንግስት አካላት የዉሃ እና የመብራት መስመሮች የማንሳት ጉዳይ ያንተ ነው፣ ያንተነዉ እየተባባሉ መስማማት ባለመቻላቸው ተስተጓጉሏል ተብሎ በሕዝቡ ዘንድ ይወራል።

በግሌ ተጨባጭ ምክንያቱን ባላዉቅም መንገዱ ባለመሠራቱ የከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት እየተስተጓጎለ ነው። በእዉነቱ አሁን መንገዱ ያለበት ደረጃ ከተማዋን ካለመመጠኑም በተጨማሪ አሳፋሪ ነው። መንገዱ ተሠርቶ ማለቅ በነበረበት በዚህ ሰዓት ስለአለመጀመሩ ማዉራት በጣም ያሳዝናል። በየደረጃው ያለዉ አመራር ይህ ጉዳይ ሊያንገበግበዉ ይገባል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ምናልባት ከቦዲቲ በሌዊ በኩል የሚያስገባዉ መንገድ ዳልቦ ላይ ከተዘጋ ቆይቷል፣ እሱስ መንገድ ካነሳነዉ መንገድ ጋር የተያያዘ ይሁን በአጠቃላይ በዎላይታ የአዳዲስ ፕሮጀክቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖርና ቃል የተገቡቱም ከሌሎች አካባቢዎች በተለዬ ሁኔታ መስተጓጎላቸዉን እንዴት ያዩታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አዎ በተጨባጭ የሚታዩ ችግሮችን ነው ያነሳው። የጠቀስከዉ መንገድ መዘጋቱን እንጂ ስለመጀመሩም ይሁን ከጠቀስነዉ መንገድ ጋር የዲዛይን ማሻሻያ ተደርጎ አብሮ ሊሰራ ስለመሆን አለመሆኑ መረጃዉ የለኝም።

ይህ መንግስት ለዉጡ አስፈልጓል ብሎ ከሚሰጣቸዉ ምክንያቶች አንዱ ፕሮጀክቶች በጊዜ አለማለቃቸዉ ነው ብሎ ሲያበቃ፤ በዎላይታ ግን የአየር ማረፊያዉንና የጠቀስነዉን መንገድ መስተጓጎል አይነት ነገር ከለዉጡ በፊት አልነበረም ማለት ይቻላል። በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። በዎላይታ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ከሕዝቡ ፖለቲካዊ ምክንያቶች እና ከመልማት ፍላጎቱ ጋር በፍጹም የሚጣጣም አይደለም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባይጠሩም ፕሬዘዳንት ታዬ አስቀስላሴ የዎላይታ ሶዶን ስም በአንደኛ ጠርተዉ በአዲስ አበባ የተጀመረዉ ኮሪደር ልማት እንደሚቀጥልባት አስታዉቀዋል። በአሁኑ ሰዓት ለዚህ ዝግጁ የሆነ መንገድ ከተማዋ ያላት ይመስልዎታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በብዛት አላት ግን የአጭርነትና የ topographic ችግሮች የሚስተዋልባቸዉ ይመስለኛል። በጣም ጥሩ የሚሆነዉ ግን ይሄዉ የሌዊ ግብርና ኮሌጅ መንገድ ተሰርቶ የሳይክልና የእግረኛ መሄጃ ቢሰራለት የበለጠ ጥሩ ይመስለኛል። ለዚህ ተብሎ ግን ቀድሞ በወጣዉ ዲዛይን ላይ የነበረዉ የመንገድ ስፋት ወይንም የ lane ብዛት መቀነስ የለበትም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ አሁን ለዚህ ወሳኝ መንገድ ግምባታ ማን ምን ያድርግ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ይህ በወሳኝ ጀረጃ የከተማዋን ገጽታ የሚቀይር መንገድ ነዉና ባለድርሻ አካላት ሥራቸዉን በአግባቡ መሥራት አለባቸዉ። ሕዝቡም በየመድረኩ መወትወት አለበት። በተለይ በመንገዱ የሚገኙ ተቋማትና ግለሰቦች መነሳት ያለበት ንብረት ካላቸዉ ልማቱ የነሱም ነውና ተባባሪ መሆን አለባቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በግምባታዉ ሂደት መወሰድ ያለባቸዉ ጥንቃቄዎች ካሉ አንስተን ብንቋጭስ?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ ጥሩ። መንገዱ ብዙ የተለያዩ አይነትና ደረጃ ያላቸዉ መጋቢ መንገዶች የሚገናኙት ስለሆነ በተቻለ መጠን ሌላ ተጨማሪ ወጪ እንዳይበዛ ከመንገዶቹ ጋር ከፍና ዝቅ እንዳይል ጥንቃቄ ይፈልጋል።

ሌላዉ ወደፊት የሚለሙ የታጠሩ ቦታዎችና አሮጌ ቤቶች ጉዳይ ብዙ ባያስጨንቅም በተለይ አሁን ላይ የተገነቡ ተቋማትና ሕንጻዎች በተጋነነ ሁኔታ እንዳይሰቀሉ፣ አልያም እንዳይቀበሩ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ ቢደረግ እላለሁ።

ከዛ በተረፈ በአንዴ ሁሉንም መቆፈር ስለማያስፈልግ በደምብ ተጠንቶ በሁለት ወይንም በሶስት ቦታ ተከፍሎ መንገዱ ቢሰራ ችግር ያለዉ አይመስለኝም። መንገዱ ሲያልቅ ከግብርና ኮሌጅ በዩኒቨረስቲ አድርግ እስከ ሁምቦ መዉጫ ወደፊት በተመሳሳይ ስፋት መቀጠል ያለበት ይመስለኛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

#WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromia #addisababa

በዎላይታ የሚጀመር እንጂ የሚጠናቀቅ ልማት ለምን ጠፋ ? የመንግስት ምላሽ ከሕዝቡ ከመልማት ፍላጎቱ ጋር በፍጹም ለምን አልተጣጣመም?👇
https://wolaitatimes.com/?p=4937

Wolaita Times

17 Oct, 16:14


Facebook's Removal Delays Critical Disease Alert in Ethiopia's Wolaita.

Facebook's Wrongful Removal of Post Delays Critical Disease Alert in Ethiopia's Wolaita Area

The Company's Erroneous Removal of Wolaita Times Media Post on Deadly Disease Sparks Outcry Over Freedom of Speech and Accountability.

Wolaita Times, a media organization dedicated to professional journalism since 2019, has been broadcasting from exile since December 19, 2022, due to the arrest and harsh persecution of its journalists in Ethiopia and the lack of free press. Despite these challenges, Wolaita Times continues to bring crucial news to its audience through social media platforms, including Facebook. However, recent actions by
#Facebook have raised serious concerns about freedom of speech and platform accountability.

One day ago,
#Facebook wrongly removed a post by Wolaita Times that reported on an unknown disease killing many people in Ethiopia, particularly in the Wolaita area. Upon realizing the error, Wolaita Times Media Chief editor Journalist Natnael Gecho promptly responded to Facebook, asserting that the post did not contravene any of Facebook's community standards.

In a concerning incident,
#Facebook wrongly took down a crucial media post highlighting a deadly disease outbreak in Ethiopia's Wolaita area. The post, intended to draw urgent attention and aid from relevant authorities, was removed without valid justification, resulting in a significant delay in the dissemination of life-saving information.

This critical post aimed to alert concerned bodies and prompt immediate intervention. Despite Wolaita Times contesting the removal and affirming that the content did not violate any community standards,
#Facebook restored the post only after more than 10 hours, without issuing an apology or providing an official reason for the error.

"The wrongful removal of our post delayed essential information from reaching authorities who could have acted to mitigate the health crisis in Wolaita. Facebook's lack of transparency and accountability in this matter is deeply concerning," stated a chief editor from Wolaita Times.

This incident is not isolated. Last year, starting from February 18, 2023, Facebook imposed multiple restrictions on the Wolaita Times page, alleging a violation of community standards. The content in question was a photo posted on August 16, 2021, depicting Afghans and American military personnel at an airport in Afghanistan.

Despite being in circulation for more than two years and originating from another media source, the photo led to the imposition of these restrictions. Multiple attempts to report complaints and seek clarification from Facebook went unanswered, leaving the unjust restrictions in place.

"The ongoing restrictions and lack of response from Facebook not only compromise the dissemination of critical information but also undermine the principles of free speech.

It is imperative for social media platforms to ensure that valid and relevant information is not censored unjustly, as the public's right to know must be protected," the representative added.

These incidents underline the broader issues related to the content review processes of social media companies. The ability to share accurate and timely information, especially during crises, is vital. Erroneous actions by platforms can have severe repercussions, hindering necessary support and response efforts.

The recurring wrongful actions by Facebook highlight the urgent need for more reliable and transparent content moderation policies. Social media platforms must ensure the swift and accurate dissemination of information, particularly during emergencies when timely intervention can save lives.

Wolaita Times Media calls for
#Facebook to review and improve its moderation policies, upholding the principles of free speech and ensuring accountability for its actions. As more communities depend on social media for real-time updates, it is paramount that critical information is not obstructed due to preventable errors.

Wolaita Times

17 Oct, 16:14


በተጨማሪም በአከባቢው በርከት ያሉ አዋቂዎችና ህፃናት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ህክምና የሚከታተሉ፣ የሞቱ እንዲሁም ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉት በየቤታቸው እንዳሉ በመግለፅ በወረርሽኙ ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጂት፣ ሚዲያዎችና ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርባ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም በዎላይታ የህብረተሰቡን ጤና "አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር" በሚል በመቶ ሚሊዮኖች ከዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ እየዋለ በመሆኑ የወባ፣ የኩፍኝ እና ሌሎች የወረርሽኝ በሽታዎችን መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገና በርካቶች እንዲሞቱ እያደረገ ስለመሆኑ በዎላይታ ዞን በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ ከማድረጉ ባለፈ ከዞን ባለሙያዎች ጭምር ወረርሽኝ ወደተከሰተበት አከባቢ በጊዜው ለመሄድ የተመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ በመዋሉ በየአካባቢው የሚከሰቱ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እያደረገ እንደሆነም የጤና ባለሙያዎች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ሰሞኑን በዞኑ በተለይም በቦሎሶ ቦምቤ፣ ክንዶ ኮይሻ፣ ክንዶ ዲዳዬ፣ በዳሞት ፑላሳ፣ ሁምቦና አባላ፣ ቦሎሶ ሶሬ እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ ወረዳዎች ስለተከሰተው ያልተረጋገጠ ወባ መሠል ወረርሽኝ በተመለከተ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚመለከታቸውን አካላት ለማግኘት በድጋሚ ያደረገው ጥረት ያልተሳካ ቢሆን ምላሽ እንዳገኘን እንመለስበታለን።

ያም ሆነ ይህ በዞኑ የተከሰተው አስደንጋጭና ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ በቀላሉ መቆጣጠርና መከላከል እየተቻለ በርካቶችን ለሞት እየዳረገ ነውና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ትኩረት ይሻል።
#Ethiopia #Wolaita #Malariaoutbreak #WHO #Freepress

Facebook's Wrongful Removal of Post Delays Critical Disease Alert in Ethiopia's Wolaita Area 👇
https://wolaitatimes.com/?p=4927

Wolaita Times

17 Oct, 16:14


ፌስቡክ በዎላይታ ታይምስ ፖስቶች ላይ የወሰደው የተሳሳተ እርምጃ የንግግር ነፃነት እና ተጠያቂነት ላይ ስጋት ፈጥሯል።

ከአንድ ቀን በፊት ፌስቡክ በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተፃፈውን ጽሁፍ በስህተት አስወግዶታል። ዘገባው ያልታወቀ በሽታ በኢትዮጵያ በተለይም በዎላይታ አካባቢ ብዙ ሰዎችን እንደገደለ የሚገልጽ ነበር። የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ዋና አዘጋጆች ስህተቱን እንደተረዱት ወዲያው ለፌስቡክ ምላሽ ሰጡ፣ ፖስቱም ከፌስቡክ የማህበረሰብ መስፈርቶች ጋር እንደማይጋጭ አስረድተዋል።

ይሄንን መነሻ በማድረግ ፌስቡክ በስህተት ያጠፋውን በኢትዮጵያ ዎላይታ አካባቢ ገዳይ የሆነ በሽታ መከሰቱን የሚገልጽ ወሳኝ የሚዲያ ጽሁፍ ወደቦታው መልሷል።

ይህ ወሳኝ ልጥፍ የሚመለከታቸው አካላትን ለማስጠንቀቅ እና አፋጣኝ ድጋፍ እና ጣልቃ ገብነትን ለመጠየቅ ያለመ ነው። ዎላይታ ታይምስ እገዳ እንዲነሳ ተከራክሮ እና ይዘቱ የትኛውንም የማህበረሰብ እሴት የማይጥስ መሆኑን በመግለፁ እገዳው የተነሳ ቢሆንም ፌስቡክ ይቅርታ ሳይጠይቅ እና ለስህተቱ ይፋዊ ምክንያት ሳይሰጥ ከ10 ሰአት በላይ በኋላ ወደነበረበት እንዲመለስ አድርጓል።

የዎላይታ ታይምስ ዋና ኤዲተር ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ "በዎላይታ ያለውን የጤና ችግር ለመቅረፍ እርምጃ ሊወስዱ ለሚችሉ አካላት የኛን ልጥፍ በስህተት መውጣታችን አስፈላጊ መረጃ ዘግይቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ የፌስቡክ ግልፅነት እና ተጠያቂነት በጣም አሳሳቢ ነው" ብለዋል።

ጋዜጠኛ ናትናኤል አክለውም "በፌስቡክ እየታዩ ያሉት እገዳዎች እና ምላሽ ማጣት ወሳኝ መረጃዎችን ስርጭትን ከማስተላለፍ ባለፈ የመናገር የነጻነት መርሆችን ይጎዳል፤ ፌስቡክ ፖሊሲዎችን እንዲገመግም እና እንዲያሻሽል፣ የመናገርን ነፃነት መርሆዎችን እንዲያከብር እና ለድርጊቶቹ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርቧል።

ብዙ ማህበረሰቦች ለእውነተኛ ጊዜ ዝመናዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ወሳኝ መረጃ ሊከለከሉ በሚችሉ ስህተቶች ምክንያት አለመታገዱ በጣም አስፈላጊ ነው ብሏል።

ለመሆኑ ፌስቡክ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ካነሳ በኃላ መልሶ የለጠፈው ዘገባ ምን ይላል? 👇

"በአሁኑ ወቅት የህብረተሰቡን ህይወት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀጠፈ የሚገኘው እውነትም የወባ ወረርሽኝ ስለመሆኑ በገለልተኛ የአለም ጤና ተቋም ወይንም በሲዲሲ ምርመራ ተደርጎ መረጋገጥ መቻል አለበት። በጣም አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ ደርሷል። በዎላይታ የአሁኑ ዓይነት የወባ ወረርሽኝ የተከሰተው ከሚኒሊክ ወረራ ማግስት እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ" ስል በዞኑ ተዘዋውረው ትዝብቱን እንዲያካፍል የተባበሩ አንድ ግለሰብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የጉዳቱን መጠን ጠቁመዋል።

ግለሰቡ አክለውም "ይህ በዎላይታ ደጋማው ክፍልን ጨምሮ በተለምዶ ወባ በብዛት ተከስቶ በማይታወቅ አከባቢዎች ተሰራጭቶ ሕዝቡን እየጨረሰ የሚገኘው በትክክል ወባ ብቻ ነው ለማለት እቸገራለሁ። በክስተቱም የሰው እጅ ስላለመኖሩ እየተጠራጠርኩ ነው" በሚልም ስጋቱን ገልጸዋል።

"ሰዎች በበሽታው እየሞቱ በአይኔ ተመልክቻለሁ፥ በአከባቢው ያሉ አብዛኞቹ ህብረተሰብ ክፍሎች መጠቃታቸውን እንዲሁ፦ በሽታው ራሱ ወባ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በልዩ ሁኔታ በዎላይታ ዞን ብቻ እንዴት ሊከፋ ቻለ የሚለው ጥያቄ የሚጭር ነው" ስልም ሁኔታውን አብራርተዋል።

ሌላኛው በዞኑ በስራ ምክንያት በየአካባቢው በዞረበት ወቅት የታዘበውን ለWT ሲያስረዳ "በዎላይታ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ላይ አደገኛ ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት ህብረተሰቡ በበሽታው መሰቃየትና በሺዎች የሚቆጠሩት ህይወት መቅጠፍ ከጀመረ ወራቶች ከተጎጂ ሰዎች አረጋግጫለሁ።

ነገር ግን እስካሁን ዞኑ ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሽታውን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረትም እንቅስቃሴ ካለመኖሩ ባሻገር የመንግስት ጤና ጣቢያዎች ባዶ ናቸው፤ መድኃኒት የላቸውም በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች ደሞወዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ያልተከፈለላቸው በስራ ገበታቸው ላይ ስለማይገኙ ህብረተሰቡ በወረርሽኙ በመታመሙ ወደ ጤና ጣቢያ እየጎረፈ ቢሆንም የሚያስተናግድ የለም።

ህብረተሰቡ በዚህ ክፉ ወረርሽኝ ህይወቱ ተቀጥፈው ከማለቁ በፊት የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምላሽ መስጠት አለባቸው" በሚል ተማፅነዋል።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሥራ አስፈፃሚ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በላከው መግለጫ ላይ በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የተከሰተው የወባ ወረርሽኝ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈና የበርካቶች ህይወት እንዲናጋ ምክንያት መሆኑን እንዳሳሰበው የዎህዴግ የሥራ አስፈፃሚ ገልጾ መንግስት የሚከተለው የጤና ፖሊሲ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ እንኳን የሚያስችል አቅም የሌለው መሆኑ ማሳያ ነው" በሚል መተቸታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም መንግስት የጤና ባለሙያ ደመወዝና ጥቅማጥቅም በጊዜ ባለመክፈሉ፣ ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢዎችና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፊታሎች ምንም ዓይነት መድኃኒት ባለመኖራቸው ምክንያት በበሽታው የተያዙ ሰዎች መዳን እየቻሉ በመድኃኒት እጥረት እየሞቱ መሆኑ እጅግ በጣም እንደሚያሳዝንና እንደሚያሳፍርም በመግለፅ መንግስት በአስቸኳይ የህዝባችን ሕይወት እንዲታደግ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከዚህ ውጭ በህዝባችን ላይ በሚደርሰው አደጋ መንግስት ራሱ ተጠያቂ መሆኑንም እንዲሁ ዎህዴግ አሳስቧል።

"እባካችሁ በዎላይታ ባልታወቀ በሽታ በየአካባቢው ህዝብ እያለቀ ነው። ባለፈው በእናንተ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በአከባቢያችን የወባ ወረርሽኝ ህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ መዘገቡን ተከትለው የተወሰኑ የሚመለከታቸው አካላት የሁለት ቀን ዘመቻ ያደረጉ ቢሆንም አሁን ላይ ህብረተሰቡ ባለቤት አጥተው በበሽታው በየቀኑ እየሞተ ነው እባካችሁ አሁንም እንደወትሮው ድምፅ ሁኑልን" በሚል የአከባቢው ነዋሪዎች ተማፅነዋል።

አክለውም "ለሌላው ደግሞ አያይዘን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ የምንፈልገው ህብረተሰቡ ወደ ግል ጤና ጣቢያዎች በውድ ዋጋ ለመታከምና የወባ መድሀኒት ለመግዛት ሲሄዱ አብዛኞቹ የተሳሳተ መድኃኒት በእርካሸ እንሸጣለን በሚሉ ተታልለው ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ። እባካችሁ ህብረተሰቡ እያለቀ ነው ድምፃችን አሰሙልን" በሚልም አሳስበዋል።

ሌላኛው አንድ የአከባቢው ነዋሪ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ሁኔታውን ሲገልፅ "በሚያሳዝን ሁኔታ በአከባቢው ዘንድሮ በበሽታው ተጠቅተው ከሁለት ጊዜ ያላነሰ ሀኪም ቤት ያልገባ ሰው የለም፥ ሁሉም ጋ ለቅሶ አለ፣ አሁን ደግሞ ብዙ ሰዎች በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው እየሞቱ ነው እባካችሁ ይሄንን የህዝብ ስቃይ ይፋ ተደርጎ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጉ" ሲል ተማፅነዋል።

በዞኑ ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አንድ ጤና ጣቢያ ባለሙያ በማገልገል ላይ የምትገኝና ስሜ አይጠቀስ ያለች የህክምና ባለሙያ" በጤናው ዘርፍ መረጃ በየጊዜው ሪፖርት የሚደረግ ቢሆንም መንግሥት አስፈላጊውን የጤና ግብዓት እያቀረበ ወረርሽኙ ለምን ተከሰተ የሚል ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሲባል በወረርሽኝ የተጠቁ ህብረተሰብ ክፍሎች በሽታና ሞት በበላይ አካላት እንዲሰወሩ ተደርጓል" ስትል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልፃ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

Wolaita Times

16 Oct, 14:51


ብልፅግና ዜጎችን ለምን ያሳድዳል? ዜጋህን እስከመቼ ? ወዴትስ ታባርረዋለህ?

ለመሆኑ ዜጋህን እስከመቼ ታባርራለህ ? ወዴትስ ታባርረዋለህ? ዜጋ ተኮር የተባለ የብልፅግና ፖሊስ በመዋቅራዊ ጫና የሚንከራተቱ ዜጎችን ለምን ያሳድዳል? በሀገራቸው ስደተኛ ስለሆኑ ዎላይታዎች እና ለሌሎች እንደወትሮው ሁሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለተነሱ ለዚሁ እና ለተያያዥ ጉዳዮች ምላሽ አላቸው፥ ዘገባውም ቀጥታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በስፋት ሕገወጥ የጎዳና ንግድ ይስተዋላል። በዚህም በብዛት የዎላይታ ልጆች ይሳተፋሉ ስለዚህ ጉዳይ ያሉዎትን ምልከታ ቢያጋሩን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አዎ እንዳልከዉ አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ የኢትዮጵያ ከተሞች ሕገወጥ የጎዳና ንግድ ይስተዋላል፥ የዎላይታም ልጆች በስፋት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከሌሎች በበለጠ ሁኔታ ይሳተፋሉ። በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የዎላይታ ልጆች ቁጥር በ100ሺዎች እስከ ሚሊየን ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በግርድፉ ስናስቀምጥ ንግዱ ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ ጸሐይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸዉ የፖሊስ ዱላ እና የንብረት ነጠቃ እየደረሰ፣ በሽሽትም ሲሮጡ ከመንገድ ላይ ጉድጓዶችና አደጋ ሊያስከትል ከሚችል መኪና ጋር የሚጋፈጡበት ፈታኝ ሥራ ነው።

አንዳንዶቹ የሚሸጧቸዉን በራሳቸዉ ገዝተዉ ለትርፍ ሲሸጡ፣ ሌሎች ደግሞ የሌሎች ነጋዴዎችን እቃ በአነስተኛ ክፍያ በየጎዳናው እያዞሩ ይሸጣሉ። በርግጥ ስራዉ ሕገወጥ እና ግብር የማይከፈልበት ነው። መንግስትም ግብር ከፍለዉ የሚሰሩ ሕጋዊ ነጋዴዎችን ይጎዳል ብሎ ለመከላከል መንቀሳቀሱ በመሠረታዊነት ከሕግ አንጻር ካየነዉ ልክ ነው። ነገር ግን ይህ በሚሊየን የሚቆጠረዉ በየከተሞቹ በሕገወጥ የጎዳና ንግድ ላይ የሚሳተፈዉስ ዜጋ አይደለም ወይ? እንደ ዜጋ በሕጋዊ ንግድ እንዲሳተፉ ምን የተመቻቸ ነገር አለ የሚለዉ መጠየቅ አለበት?

በነገራችን ላይ ከዜግነትም አንጻር በተለይ የዎላይታ ልጆች ነገር ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በአዲስ አበባ በዚህ ደረጃ በቁጥር በዝተዉ ያሉት የዎላይታ ልጆች የከተማው ነዋሪነት መታወቂያ የላቸዉም፣ በምርጫ አይሳተፉም ማለት ነው ጉዳያቸዉን እንደአጀንዳ የሚያነሳ ፓርቲም የለም። በጣም የሚገርመዉ እነዚህ በየከተማዉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚኖሩ የዎላይታ ልጆች በቅርቡ በዎላይታ በተካሄደዉ "ሕዝበ ዉሳኔ" አልተሳተፉም።

በሚኖሩበትም በዎላይታ ዞንም በኩል የዜግነት መብታቸዉን የሚጠቀሙበት እድል የላቸዉም፣ ይህ እንግዲህ "ማነዉ ኢትዮጵያዊ?" የሚለዉን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በሌላዉ አለም Absentee voting የሚባል አሰራር አለ ዜጋ መሰል መብቶቹን እንዲጠቀም የሚደረግበት አሰራር፤ በእኔ እምነት እነኝህ በየከተማዉ እንደሁለተኛ ዜጋ የሚኖሩ የዎላይታ ልጆች የእዉነትም ዜጋ ናቸዉ ተብሎ ከታመነ ወይ በሚኖሩበት መታወቂያ እና የሥራ ቦታ የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣ ካልሆነም የዎላይታ ዞን ነዋሪ ከተባሉ በምርጫም ሆነ በሕዝበ ዉሳኔ መሳተፍ አለባቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህ መጥፎ እጣ ለምን በብዛት የዎላይታ ልጆች ላይ የወደቀ ይመስልዎታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ነገሩ ሰፊ ና ጥልቅ ጥናት የሚፈልግ ነው ፣በየከተሞቹ በብዛት የዎላይታ ልጆች በመሰል ሥራዎች ላይ መሰማራታቸዉ አዉነት ነው። በአዲስ አበባም ከፖሊስና ደምቦች ዱላ ሽሽት ሲሮጡ ብዙዎቹ ዎላይትኛ ሲነጋገሩ መስማት የተለመደ ነው። የዎላይታ ልጆች በዘርፉ ስለመብዛታቸዉ በግሌ ግን የተለያዩ መላምታዊ ግምቶችን ማስቀመጥ የሚቻል ይመስለኛል።

ያዉ እኔ የዎላይታ ሕዝብ በሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ ከጥንት ጀምሮ ባለዉ ልዩነት ምክንያት ሲቀጣ የኖረና አሁንም የሚቀጣ ሕዝብ ነው ብዬ አምናለሁ። ሕዝቡ ለዘመናት ብዙ ፖለቲካዊ ተንኮሎች ተሰርተዉበት፣ ለዘመናት ለፖሊሲ ክፍተት ተጋልጦ ኖሯል።

የአስተዳደር መዋቅሮች ሆን ተብለዉ ሕዝቡን ለመጉዳት በማለም ይደራጃሉ፣ የሕዝብ ብዛቱን በሚቃረን መልኩ በቀየዉ ሕዝቡ ትልቅ ከተማ እንዳይሰራ ለዘመናት የዘለቀ ጫና አለ፣ የመንግስታቶቻችን አግላይነትም ድርሻዉ ብዙ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ መንግስታት የሚጠቀሙት የሕዝቡ ቁጥርም ከጥንትም አጠራጣሪ ነገሮች የሚበዙበት (በማስረጃ የተደገፉ) ነው። ሌላዉ ደግሞ የብሔር ጭቆና መልክና ደረጃዉን ቀይሮ የመቀጠል እድሉ ሰፊ ከመሆኑን በላይ ሕዝባዊ ጠባሳዉም በቀላሉ ከትዉልድ ትዉልድ ሊሸጋገር ይችላል።

በአካባቢው ለድሕነት ቅነሳ በቂ ትኩረት አለመሰጠቱ ካለዉ ሕዝብ ብዛት አንጻር የሥራ እድል አለመኖሩ። በተለይ መንግስት አንድን ችግር አይቶ በሚመጥን ደረጃ ትኩረት አለመስጠቱ፣ መዋቅራዊ ጫና፣ የኢኮኖሚ አቅም ጉዳይ እና የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላል። ነገሩ ሰፊና ጥልቅ ጥናት ይፈልጋል አዝማሚያዉም እየተባባሰ የመሄድ ነገር ይታይበታል።

አንድ ግን አጽንኦት ሰጥቼ ማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት ዜጋን ማሳደድ ተገቢ አይደለም!! መፍትሔም አይደለም!! መንግሥት ይሄ ሁሉ የኔ ዜጋ የተሠማራበት ዘርፍ አንዳች ወደ ሕጋዊ መሥመር የሚመጣበትን አግባብ መፍጠር አለብኝ የሚል አስተሳሰብ ሊኖረዉ ይገባል። ይሄን ሁሉ ሰዉ የደምብ ቁጥር በማብዛት እቆጣጠራለሁ ማለትም ስህተት ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ባለድርሻ አካላትንና መፍትሔዎች የሚሏቸዉን ነገሮች ቢጠቁሙን?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የዞኑ፣ የክልሉና የፈደራል መንግስት፣ ሚዲያዎች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣ የፖለተካ ፓርቲዎች እና የመሳሰሉት ጉዳዩን የኔ ሊሉት ይገባል። በተረፈ ይህ በጣም ሰፊ እና ጥልቅ ጥናት ላይ የተመሠረተ እርምጃ የሚፈልግ ነው። ይሕ ጉዳይ አጀንዳ መሆን አለበት፣ መንግስት ይሄ ሁሉ ዜጋ የተሠማራበትን ዘርፍ በደምብ አስከባሪዮች እቆጣጠራለሁ አጠፋለሁ ብሎ ካሰበ ስህተት ብቻ ሳይሆን ዜጋ ተኮር ያልሆነ አካሄድ ነው።

በእዉነት ደምቦች ሲያባርሯቸዉ ልጆቹ ላይ የመኪና አደጋ እንዳይደርስም በጣም ያሰጋል። መንግስት በጥብቅ የሚያስጠብቃቸዉ አካባቢዎች ላይ ሲጠፋ ቀንሶ ሳይሆን ቦታ ቀይሮ ንግዱ ቀጥሏል። መዝግቦ አደራጅቶ ወደ ሕጋዊ መሥመር ማስገባቱ አስፈላጊ እርምጃ ነው። ተጨማሪ ወጣቶች ደግሞ ወደ ዘርፉ እንዳይቀላቀሉም፤ በተለይ በዎላይታ አይነት አካባቢዎች የድኅነት ቅነሳ ፖሊሲዎች በትኩረት ተነድፈዉ ወደ ሥራ መግባት አለባቸዉ። ዜጋህን እስከመቼ ታባርራለህ ? ወዴት ታባርረዋለህ?

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

#WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromia #addisababa

Wolaita Times

16 Oct, 14:51


ለምን ያሳድዳል? ዜጋህን እስከመቼ ? ወዴትስ ታባርረዋለህ? 👇https://wolaitatimes.com/?p=4921

Wolaita Times

15 Oct, 15:37


በዎላይታ ከጦርነት በላይ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘው አስደንጋጩ በሽታ ምን እንደሆነ ጥናት ተደርጎ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ።

"በአሁኑ ወቅት የህብረተሰቡን ህይወት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀጠፈ የሚገኘው እውነትም የወባ ወረርሽኝ ስለመሆኑ በገለልተኛ የአለም ጤና ተቋም ወይንም በሲዲሲ ምርመራ ተደርጎ መረጋገጥ መቻል አለበት። በጣም አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ ደርሷል። በዎላይታ የአሁኑ ዓይነት የወባ ወረርሽኝ የተከሰተው ከሚኒሊክ ወረራ ማግስት እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ" ስል በዞኑ ተዘዋውረው ትዝብቱን እንዲያካፍል የተባበሩ አንድ ግለሰብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የጉዳቱን መጠን ጠቁመዋል።

ግለሰቡ አክለውም "ይህ በዎላይታ ደጋማው ክፍልን ጨምሮ በተለምዶ ወባ በብዛት ተከስቶ በማይታወቅ አከባቢዎች ተሰራጭቶ ሕዝቡን እየጨረሰ የሚገኘው በትክክል ወባ ብቻ ነው ለማለት እቸገራለሁ። በክስተቱም የሰው እጅ ስላለመኖሩ እየተጠራጠርኩ ነው" በሚልም ስጋቱን ገልጸዋል።

"ሰዎች በበሽታው እየሞቱ በአይኔ ተመልክቻለሁ፥ በአከባቢው ያሉ አብዛኞቹ ህብረተሰብ ክፍሎች መጠቃታቸውን እንዲሁ፦ በሽታው ራሱ ወባ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በልዩ ሁኔታ በዎላይታ ዞን ብቻ እንዴት ሊከፋ ቻለ የሚለው ጥያቄ የሚጭር ነው" ስልም ሁኔታውን አብራርተዋል።

ሌላኛው በዞኑ በስራ ምክንያት በየአካባቢው በዞረበት ወቅት የታዘበውን ለWT ሲያስረዳ "በዎላይታ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ላይ አደገኛ ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት ህብረተሰቡ በበሽታው መሰቃየትና በሺዎች የሚቆጠሩት ህይወት መቅጠፍ ከጀመረ ወራቶች ከተጎጂ ሰዎች አረጋግጫለሁ። ነገር ግን እስካሁን ዞኑ ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሽታውን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረትም እንቅስቃሴ ካለመኖሩ ባሻገር የመንግስት ጤና ጣቢያዎች ባዶ ናቸው፤ መድኃኒት የላቸውም በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች ደሞወዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ያልተከፈለላቸው በስራ ገበታቸው ላይ ስለማይገኙ ህብረተሰቡ በወረርሽኙ በመታመሙ ወደ ጤና ጣቢያ እየጎረፈ ቢሆንም የሚያስተናግድ የለም። ህብረተሰቡ በዚህ ክፉ ወረርሽኝ ህይወቱ ተቀጥፈው ከማለቁ በፊት የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምላሽ መስጠት አለባቸው" በሚል ተማፅነዋል።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሥራ አስፈፃሚ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በላከው መግለጫ ላይ በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የተከሰተው የወባ ወረርሽኝ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈና የበርካቶች ህይወት እንዲናጋ ምክንያት መሆኑን እንዳሳሰበው የዎህዴግ የሥራ አስፈፃሚ ገልጾ መንግስት የሚከተለው የጤና ፖሊሲ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ እንኳን የሚያስችል አቅም የሌለው መሆኑ ማሳያ ነው" በሚል መተቸታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም መንግስት የጤና ባለሙያ ደመወዝና ጥቅማጥቅም በጊዜ ባለመክፈሉ፣ ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢዎችና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፊታሎች ምንም ዓይነት መድኃኒት ባለመኖራቸው ምክንያት በበሽታው የተያዙ ሰዎች መዳን እየቻሉ በመድኃኒት እጥረት እየሞቱ መሆኑ እጅግ በጣም እንደሚያሳዝንና እንደሚያሳፍርም በመግለፅ መንግስት በአስቸኳይ የህዝባችን ሕይወት እንዲታደግ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከዚህ ውጭ በህዝባችን ላይ በሚደርሰው አደጋ መንግስት ራሱ ተጠያቂ መሆኑንም እንዲሁ ዎህዴግ አሳስቧል።

"እባካችሁ በዎላይታ ባልታወቀ በሽታ በየአካባቢው ህዝብ እያለቀ ነው። ባለፈው በእናንተ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በአከባቢያችን የወባ ወረርሽኝ ህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ መዘገቡን ተከትለው የተወሰኑ የሚመለከታቸው አካላት የሁለት ቀን ዘመቻ ያደረጉ ቢሆንም አሁን ላይ ህብረተሰቡ ባለቤት አጥተው በበሽታው በየቀኑ እየሞተ ነው እባካችሁ አሁንም እንደወትሮው ድምፅ ሁኑልን" በሚል የአከባቢው ነዋሪዎች ተማፅነዋል።

አክለውም "ለሌላው ደግሞ አያይዘን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ የምንፈልገው ህብረተሰቡ ወደ ግል ጤና ጣቢያዎች በውድ ዋጋ ለመታከምና የወባ መድሀኒት ለመግዛት ሲሄዱ አብዛኞቹ የተሳሳተ መድኃኒት በእርካሸ እንሸጣለን በሚሉ ተታልለው ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ። እባካችሁ ህብረተሰቡ እያለቀ ነው ድምፃችን አሰሙልን" በሚልም አሳስበዋል።

ሌላኛው አንድ የአከባቢው ነዋሪ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ሁኔታውን ሲገልፅ "በሚያሳዝን ሁኔታ በአከባቢው ዘንድሮ በበሽታው ተጠቅተው ከሁለት ጊዜ ያላነሰ ሀኪም ቤት ያልገባ ሰው የለም፥ ሁሉም ጋ ለቅሶ አለ፣ አሁን ደግሞ ብዙ ሰዎች በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው እየሞቱ ነው እባካችሁ ይሄንን የህዝብ ስቃይ ይፋ ተደርጎ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጉ" ሲል ተማፅነዋል።

በዞኑ ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አንድ ጤና ጣቢያ ባለሙያ በማገልገል ላይ የምትገኝና ስሜ አይጠቀስ ያለች የህክምና ባለሙያ" በጤናው ዘርፍ መረጃ በየጊዜው ሪፖርት የሚደረግ ቢሆንም መንግሥት አስፈላጊውን የጤና ግብዓት እያቀረበ ወረርሽኙ ለምን ተከሰተ የሚል ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሲባል በወረርሽኝ የተጠቁ ህብረተሰብ ክፍሎች በሽታና ሞት በበላይ አካላት እንዲሰወሩ ተደርጓል" ስትል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልፃ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በተጨማሪም በአከባቢው በርከት ያሉ አዋቂዎችና ህፃናት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ህክምና የሚከታተሉ፣ የሞቱ እንዲሁም ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉት በየቤታቸው እንዳሉ በመግለፅ በወረርሽኙ ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጂት፣ ሚዲያዎችና ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርባ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም በዎላይታ የህብረተሰቡን ጤና "አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር" በሚል በመቶ ሚሊዮኖች ከዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ እየዋለ በመሆኑ የወባ፣ የኩፍኝ እና ሌሎች የወረርሽኝ በሽታዎችን መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገና በርካቶች እንዲሞቱ እያደረገ ስለመሆኑ በዎላይታ ዞን በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ ከማድረጉ ባለፈ ከዞን ባለሙያዎች ጭምር ወረርሽኝ ወደተከሰተበት አከባቢ በጊዜው ለመሄድ የተመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ በመዋሉ በየአካባቢው የሚከሰቱ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እያደረገ እንደሆነም የጤና ባለሙያዎች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ሰሞኑን በዞኑ በተለይም በቦሎሶ ቦምቤ፣ ክንዶ ኮይሻ፣ ክንዶ ዲዳዬ፣ በዳሞት ፑላሳ፣ ሁምቦና አባላ፣ ቦሎሶ ሶሬ እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ ወረዳዎች ስለተከሰተው ያልተረጋገጠ ወባ መሠል ወረርሽኝ በተመለከተ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚመለከታቸውን አካላት ለማግኘት በድጋሚ ያደረገው ጥረት ያልተሳካ ቢሆን ምላሽ እንዳገኘን እንመለስበታለን።

ያም ሆነ ይህ በዞኑ የተከሰተው አስደንጋጭና ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ በቀላሉ መቆጣጠርና መከላከል እየተቻለ በርካቶችን ለሞት እየዳረገ ነውና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ትኩረት ይሻል። #Ethiopia #Wolaita #Malariaoutbreak #WHO

በዎላይታ አስደንጋጩ ገዳይ በሽታ ምን እንደሆነ ጥናት እንዲደረግ ተጠይቋል👇https://wolaitatimes.com/?p=4918

Wolaita Times

15 Oct, 13:01


ፋኖ ዉስጥ የጦና ብርጌድ ተቋቁሟል? ወደ ታጠቀ አመጽ ለምን ተሸጋገረ ? - ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ለWolaita Times ሚዲያ ምላሽ አላቸው

ፋኖ ዉስጥ "የጦና ብርጌድ ተቋቁሟል" ተብሎ በቀጥታ በአማራ ታጣቂዎች ጉዳይ ዎላይታ ብቸኛ ግብረ አበር ተደርጎ ተጠቅሷል ይሄን እንዴት ያዩታል? የአማራ ሕዝብ ከዎላይታ ወንድሞቹ ጋር የሚጋራቸዉ ጥያቄዎች የሉትም? በጦርነቱ ምክንያት መሄድ ያልቻሉ በዎላይታ አስፈላጊ ድጋፍ ተደርጎላቸው ስለሚገኙት የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ምን ይላሉ? እንደወትሮው ሁሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለተነሱ ለዚሁ እና ለተያያዥ ጉዳዮች ምላሽ አላቸው፥ ዘገባውም ቀጥታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ዛሬ ባለፈዉ የአማራ ክልሉን ግጭት አስመልክቶ ካደረግነዉ ቃለ ምልልስ በሁዋላ ከሚዲያችን ተከታዮች የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎች ተነስተዋል፥ እነሱን ይዘን ቀርበናል።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ደስ ይለኛል የሚዲያውን ተከታዮች ማሳተፍ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ፋኖ ወደ ታጠቀ አመጽ እንዲሸጋገር ያደረጉ ዉለዉ ያደሩ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች የሉም ወይ ? በርግጥ በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ መቀየር የሚቻል ነገር ቢኖር ፋኖ ጦርነትን ይመርጣል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የእኔ መከራከሪያ የሕዝብ ጥያቄ የለም አይደለም። ጦርነት ችግሮችን እያባባሰ ይሄዳል ነው። መፍትሔም አያመጣም፥ በተለይ ደግሞ የእርስ በርስ ጦርነት ሲደረግ በስሜት ብዙዎች የሚገቡበት ሲጠናቀቅ የሚጸጸቱበት ነው። ሌላዉ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ አንስቶ ማስመለስ አይቻልም ለሚለዉ ያም ካልሆነ እኔ ሰላማዊ ትግል ይሻላል ባይ ነኝ።

ሌላዉ ደግሞ በተለይ ከሕገመንግስቱ ማዕቀፍ የሚወጡ ጥያቄዎች በፈደራል መንግሥትም ሆነ በፋኖ ብቻ ሊመለሱ አይችሉም፤ ሁለቱ ቢስማሙ እንኳን የሚቻልበት አግባብ የለም በሐገሪቷ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መሳተፍ አለባቸዉ ነው።

ጦርነት ደግሞ ወደ መፍትሄው እያቀረበን ሳይሆን እያራቀን ይሄዳል ነው። የፈደራል መንግስት የሐገሪቷን ሕገመንግሥት አክብሮ አይንቀሳቀስም ብለዉ ያኮረፉ ኃይሎች በብዛት ባሉበት ፋኖ ሕገመንግሥታዊ ሥርአቱን በሚያጠፋ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ለሁሉም ደግሞ ከጦርነት በሰላማዊ ድርድር ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀሱ ይበጃል ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ፋኖ በአንድ ወጥ አደረጃጀት አለመታቀፉ የችግሩን እድሜ ያራዝማል ብለሃል። አንድነቱ ጥሩ ሆኖ ነገር ግን ለአንድ ወጥ አደረጃጀት የሰጠሄዉ ግምት አልበዛም?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ለምን መሰለህ ፋኖ አመራሮቹ ታዉቀዉ የሚያራምደዉ የትግል አላማ ታዉቆ ጥያቄዎቼ እነዚህ ናቸዉ ብሎ ዝርዝሩን ቢያስቀምጥ በጣም ጥሩ ነው። አሁን ባለዉ ግን የተለያዩ የፋኖ አመራሮች የሚያወሩት የተለያዬ ነገር ነው። አንዱ ሕገመንግሥት የሚያከብር ነገር ይናገራል፣ አንዱ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ማፍረስ አለብን ይላል፣ አንዱ ብሔረሰቦችን ወዳጆቼ ናቸዉ ይላል፣ አንዱ ይዝታል፣ አንዱ ስለአማራ እና አማራ ብቻ ያወራል፣ አንዱ ስለኢትዮጵያ ያወራል።

ይህ ዉዝግብ የሚያልቀዉ ፋኖ አንድ ሆኖ አላማዉን ግልጽ ሲያደርግ ነው። ሌላዉ መንግስትስ ከየትኛው ፋኖ ጋር ተደራድሮ፣ የትኛውን ይተዉ። ለፋኖምኮ የኃይል መበታተን ጥሩ አይደለም አንዳች ትልቅ ግብ አሳካለሁ ካለ ትልቅ አደረጃጀት ይጠይቃል።

እኛ ግን የምናበረታታዉ ጦርነትን ሳይሆን ድርድርን ነው። የአማራዉ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ወንድማማች ነው። የወንድማማች መገዳደል ሊቆም ይገባል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ የአማራ ሕዝብ ከዎላይታ ወንድሞቹ ጋር የሚጋራቸዉ ጥያቄዎች የሉትም? እንደዉም ከዚህ ጋር ተያይዞ በአማራ ክልል ባለዉ ጦርነት ምክንያት ወደቤተሰቦቻቸዉ መሔድ ያልቻሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተማሪዮችን፣ ብሔረ ዎላይታዉ የዎላይታ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እየተንከባከቡ የሚያስፈልጋቸዉን እያቀረቡ አቆይተዋል። በተለያዬ ቦታዎች የሚደረገዉ የብሔር ጥቃት በዎላይታ ታይቶ አይታወቅም። እንደዉ የአማራን ሕዝብና የዎላይታን ሕዝብ ወንድማማችነት እንዴት ይገልጹታል?

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የአማራ ሕዝብና የዎላይታ ሕዝብ ወንድማማችነት ዘመናትን የተሻገረ ነው፥ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። ሐገር እየተጋራን የሕዝብ ጥያቄ መጋራታችንን የሚጠበቅ ነው። በተለይ የአማራና የዎላይታን ሕዝብ የሚያመሳስላቸው ሁለቱም በመላዉ ኢትዮጵያ በስፋት ተሰራጭተዉ የሚኖሩ መሆናቸዉ አንዱ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች በሚደርሱ የብሔር ተኮር ጥቃቶች በጋራም በተናጠልም ሰለባ ሲሆኑ ታይቷል።

በተደጋጋሚ ስለዚህ ሁለቱም ሕዝቦች በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተንቀሳቅሶ የመሥራት፣ ሐብት ንብረት የማፍራት ሕገመንግሥታዊ መብታቸዉ መከበሩ የጋራ ጥያቄያቸዉ ነው። በነገራችን ላይ ከራሳቸዉ ክልል እና ዞን ዉጪ በብዛት የሚኖሩ እንደ አማራ፣ ዎላይታ፣ ትግራይ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ኦሮሞ፣ ሐዲያ፣ ካምባታ እና የመሳሰሉት ስለነዚህ ወገኖቻቸዉ እጣ ፋንታ ተወያይተዉ የጋራ አቋም መያዝ አለባቸዉ።

የአቡነ ይስሐቅ ተግባር በእዉነቱ ሐቀኛ የሐይማኖት አባትነት የታዬበትና የአማራንና የዎላይታን ዘላቂ ወንድማማችነት ያረጋገጠ እጅግ የሚያስመሰግን ተግባር ነው። ስለ ጥቃት ያነሳሄዉ የዎላይታ ሕዝብ አብሮ በመኖር የሚያምንና ለዛም ከሱ የሚጠበቀዉን የሚወጣ ነው፤ ወንድማማች ሕዝብ በእዉነቱ መጠቃቃት የለበትም።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በቅርቡ በመንግሥት ሚዲያዎች በተላለፈዉ ዶክመንተሪ ፋኖ ዉስጥ የጦና ብርጌድ ተቋቁሟል ተብሎ በቀጥታ በአማራ ታጣቂዎች ጉዳይ ዎላይታ ብቸኛ ግብረ አበር ተደርጎ ተጠቅሷል ይሄን እንዴት ያዩታል? እርስዎ ፋኖ በሌሎች ክልሎች ብዙ ደጋፊ የለዉም ብለዋልና።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በርግጥ መንግስት የሕወሓት ና ኦነግ_ሸኔ ግብረ አበር ሲለን ከርሞ አሁን ደግሞ የፋኖ ማለቱ በአገዛዙ ዎላይታ ተፈርጆ መቀጠሉን ያሳያል ባይ ነኝ። ብዙ ደጋፊ ፋኖ የለዉም ያልኩት ፋኖ አንድ ወጥ አደረጃጀት ፈጥሮ አቋሙን ግልጽ ባለማድረጉና የተለያዩ አመራሮች የማይናበብ ነገር ስለሚያወሩ ነው። ከዛ በተረፈ በፋኖ በኩል የጦና ብርጌድ የሚባል የዎላይታ ልጆች ያሉበት ጦር አለ ስለሚባለዉ እዉነቱን ፋኖ ያዉቃል እኔ አላዉቅም።

አንድ ግን አጽንኦት ሰጥቼ የምናገረዉ በኢትዮጵያዉያን መሐከል የሚደረግ ድርድር እንጂ ጦርነት አልደግፍም። የአማራ ሕዝብና የዎላይታ ሕዝብ ወንድማማችነት ግን ያለ እና ተጠናክሮ መቀጠልም ያለበት ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ "የፖለቲካ ወጌሻ" መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

Wolaita Times

15 Oct, 13:01


#WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromia👇


ፋኖ ዉስጥ የጦና ብርጌድ ተቋቁሟል? ወደ ታጠቀ አመጽ ለምን ተሸጋገረ ? - ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ለWolaita Times ሚዲያ ምላሽ አላቸው 👇
https://wolaitatimes.com/?p=4913

Wolaita Times

14 Oct, 11:06


በብልፅግና አስገዳጅ ህግ፣ በወባ ወረርሽኝ ሞት እንዲሁም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዎህዴግ መግለጫ አወጣ።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሥራ አስፈፃሚ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በሦሥት የተለያዩ አንኳር ጉዳዮች የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1. በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የተከሰተው የወባ ወረርሽኝ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈና የበርካቶች ህይወት እንዲናጋ ምክንያት መሆኑን እንዳሳሰበው የዎህዴግ የሥራ አስፈፃሚ ገልጾ መንግስት የሚከተለው የጤና ፖሊሲ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ እንኳን የሚያስችል አቅም የሌለው መሆኑ ማሳያ ነው።

በተጨማሪም መንግስት የጤና ባለሙያ ደመወዝና ጥቅማጥቅም በጊዜ ባለመክፈሉ፣ ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢዎችና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፊታሎች ምንም ዓይነት መድኃኒት ባለመኖራቸው ምክንያት በወባ የተያዙ ሰዎች መዳን እየቻሉ በመድኃኒት እጥረት እየሞቱ መሆኑ እጅግ በጣም ያሳዝናል ያሳፍራልም። ስለሆነም መንግስት በአስቸኳይ የህዝባችን ሕይወት እንዲታደግ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከዚህ ውጭ በህዝባችን ላይ በሚደርሰው አደጋ መንግስት ራሱ ተጠያቂ መሆኑን ዎህዴግ ያስገነዝባል።

2. ትምህርት ለአንድ ሀገርና አከባቢ እድገት ወሳኝ ሲሆን በአግባቡ ካልተያዘ ለውድቀትም መነሻ በመሆን የሚያገለግል መሳሪያ መሆኑ ይታወቃል ይሁንና ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት በዎላይታና አከባቢው የተማረ ኃይል እንዳይፈጠር ታቅዶ የሚሰራ በሚመስል መልኩ የትምህርት ሥራ ከመውደቁም በላይ የ2017 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ በከተሞች ከሚገኙ ከግል ትምህርት ቤቶች ውጭ እስካሁን አለመጀመሩ እጅግ የሚያስደነግጥና የሚዘገንን ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ዎላይታ ከዚህ በፊት የሚታወቀው "ትምህርት ለልጄ" ፕሮጀክት ከሽፎ ትውልድ እየጠፋ መሆኑ እና በትውልድ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ ዎህዴግ በጽኑ ያሳስባል።

3.ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ግንባታ ተብሎ ዎላይታ 350 ሚሊዮን ብር እንዲያዋጣ ግዴታ ተጥሎብናል ያሉ የዎላይታ ዞን አመራርና የወረዳ አመራሮች በእያንዳንዱ አርሶ አደር ላይ 1200 ብር እንዲከፍል አስገዳጅ ህግ በማውጣት ብሎም ትዕዛዝ ተቀብሎ የማይሰጠውን ግለሰብ እስከማሰር የደረሱበት መንገድ ፓርቲው ከአባላቱ ሰብስበው መገንባት የሚገባውን ህንፃ በመላው ዎላይታ ላይ እንደ ሜዶንና ፋሪስ ህግ ጭኖ አርሶ አደሮቻችንን በቁጣ አለንጋ መግረፍ ከሞራልም ከሰብዓዊነትም ያፈነገጠ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ፓርቲው ከአባላቶቹ ብቻ ድጋፍ እንዲሰበስብ እንዲደረግ ዎህዴግ በጥብቅ ያሳውቃል።

በመጨረሻም ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮች ለነገ የማይባሉ እና ህዝባችንን ለከፋ አደጋ የሚዳርጉ አደገኛ ድርጊቶች በመሆኑ መንግስትና የሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ የእርምት እርምጃ ወስዶ ሕዝባችንን እንዲታደግ እየጠየቅን በአንጻሩ ህዝቡም ለመብቱ መከበር ከራሱ የሚጠበቅበትን ሰላማዊ ትግል እንድያደርግ ዎህዴግ ያሳስባል።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሥራ አስፈፃሚ

ጥቅምት 03/2017 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ/ኢትዮጵያ

5,304

subscribers

3,536

photos

29

videos