የፍልስፍና አለም @philosophyworld1 Channel on Telegram

የፍልስፍና አለም

@philosophyworld1


“የማያነብ ሰው እና ማንበብ የማይችል ሰው ልዩነት የላቸውም” ይህ ቻናል ማንኛውም ፍልስፍና ተኮር የሆኑ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ነው ። ፍልስፍናን እንደነብሴ እወዳለሁ ያለ ሁሉ ይቀላቀለንና አብሮን ፍልስፍናን ይኮምኩም... @Philosophyworld1

ግሩፓችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @Philosophyworldd

ለአስታየት እና ለCross @fear121

የፍልስፍና አለም (Amharic)

የፍልስፍና አለም በአሁኑ በታች ለፍላፍናውን ለእጁን ለልዩነት ማዕጠን እና ማንበብ ሌላውን ሁኔታ መመለስ የሚችል ልዩነትን እና በፍልስፍና ያስከተለለና የፍልስፍና ጽሑፎችን ማካሄድ የሚችል ሰባት ፋይለዉቋል። ይህ በሰባት ፃላት ልናሳድድ እንደነብሴ መከራት እና ፍልስፍናን በመቀላቀል እንደምትወዳል የሚችል መረጃ ነው። @Philosophyworld1 ከተወዳጆች ይልቁ ፧ ያብሮን እንደምጥንታይ፤ ፍልስፍናን እንደፎቶ ይኮምኩት። ግሩፓችንን መቀላቀል ለማድረግ ወይም ሌሎች ውድቀትም በሚፈልጉ @Philosophyworldd ወደኛ እንድትፈልጉ የሚችሉ ምርቶችን ይመልከቱ። ለጠቃሚው እና ለCross @fear121 በመሆኑ እንቀላቅል።

የፍልስፍና አለም

21 Oct, 19:17


በእርግጥም ስንቶቻችን ነን የአለማችን አስፈሪ ፊልም ተብለው ከሚጠቀሱት መሀከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው "The Cconjuring" እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እንደተሰራ ምናውቀው? የዚ ፊልም የተሰራበት እውነተኛ ታሪክስ ምንድነው?

በእርግጥም ፊልሙን አይተውት ካልሆነ ብቻቹን ሆናቹ ባታዩት ይመረጣል።ብዙ ሰዎች ይሄ ፊልም የተጋነነ ማስፈራርያ ገብቶበታል ብለው ሲያሙት ቢደመጡም የእውነተኛ ታሪኩ ባለቤቶች በእውነት የተከሰተው የፊልሙን እጥፍ ያህል እንደሚያስፈራ ገልፀዋ ታሪኩ እንዲ ነው...

በ1971 አንድ ቤተሰብ Harrisville, Rhode Island ውስጥ የሚገኝ ባለ 14 ክፍል መኖርያ ቤት ገዝተው ለመኖር ይገባሉ እነዚ ጥንዶች Carolyn እና Roger የሚባሉ ሲሆን 5 ሴት ልጆች አሏቸው።የሚገርመው እዚህ ቤት ገና አንድ እግራቸውን ከማስገባታቸው ነበር እንግዳ ነገር መፈጠር የጀመረው...

ማንም ሳይኖር ኩሽናው ይኮሻኮሻል መብራቶች በራሳቸው ጊዜ ይበራሉ ይጠፋሉ ነገሩ እንግዳ ቢሆንባቸውም መኖር ይጀምራሉ እዚህ ቤት ውስጥ አንድ ብቻ ሳይሆን ብዙ መንፈሶች ነበር የሚኖሩበት ጥሩም በጣም መጥፎም መንፈሶች ነበሩ።እናም Roger ነገሩን ሲያጣራ እዚ ቤት ለ5 ክፍለዘመን ያህል የተለያየ ቤተሰብ የኖረ ሲሆን አብዛኛዎቹ እርስ በእርስ እዚ ቤት ውስጥ ተገዳድለዋል ወንድም እህቱን ጣቷን ቆርጦ በልቷል ብቻ ብዙ መጥፎ ነገር ተከስቷል ከቤቱ ጀርባ እዛው ቤት ይኖሩ የነበሩ ብዙ ህፃናት መቃብር አለ ይሄን ሁሉ ከድሮ የቤቱ መዝገብ ላይ አንብቦ ተረዳ እዚ ቤት ውስጥ ከባድ 9 አመት አሳልፈዋል ፊልሙም በዚ እውነታ ላይ ተመስርቶ ነው የተሰራው።

እስቲ እዚ ፊልም ላይ ስለሚገኙ አንዳንድ አስፈሪ መንፈሶች መረጃ ልስጣቹ.. ከላይ ምስሉ ላይ የምትመለከቷት bathsheba ትባላለች ፊልሙ ላይ ካሉት አስፈሪ መንፈሶች ሁሉ የከፋችዋ ናት ታድያ የbathsheba
እውነተኛ ታሪክ ምንድነው?

Bathsheba sherma Rhode Island ውስጥ 1812 የተወለደች በmarch 10 1844 አንድ Thompson የተባለ ግለሰብ አግብታ የምትኖር የቤት እመቤት ነበረች በ37 ዐመቷ Herbert የተባለ የመጀመርያ ልጇን ወለደች ሌላም 3 ልጆችን ብትወልድም ሁሉም 7ኛ እድሜያቸው ላይ ይሞታሉ።

ይቺ ሴት ጠንቋይ ናት ጎረቤት የነበረን አንድ ህፃን ወስዳ እንደበላች የሚያሳይ ግልፅ ማስረጃ አለ።ቤቷ ውስጥ ብዙ ሰው እንደቀበረች ይነገርላታል።

ተጋብተው ብዙ ከቆዩ ቡኋላ ሞተ እሱ ከሞተ 4 ዐመት ቡኋላ እሷም ሞተች ከሞተች ቡኋላ የሷ ክፉ መንፈስ እዛው ቤት ውስጥ ቀርቷል በጣም ሀይል ያላት መንፈስ ስትሆን አለማችን ላይ ታዋቂ ከሆኑ መንፈሶች መሀል በግንባር ቀደም ደረጃ ትቀመጣለች (ማን ያውቃል አሁን ሁላ እናንተ ጋር ትሆናለች) በሰዎች ዘንድ ስለምትገለል ቤቷ ጀርባ ቀበሯት። Googel ላይ ስለሷ ብትፈልጉ ብዙ መረጃ ታገኛላቹ ይቺ መንፈስ በየትኛውም ሰዐት የትም የመገኘት አቅሙ እንዳላት ይነገራል።

የፍልስፍና አለም

19 Sep, 19:54


የሃዲያ ፈርጦች
የሁለት ወንድማማቾችገድል

#Ethiopia | ታናሹ ጀግና የጀግና ዉሃ ልክ ነዉ።ሀገር በተጨነቀች፣ዳር ድንበሯ ተጥሶ፣በወራሪዎች በተደፈረች ሰዓት አለሁ ያለ ተዋጊ፣ተምዛግዛጊ ፣አየሩን ሰንጥቆ ጠላትን የሚያርበደብድ፣ሰማዩን አራሽ፣ምድሩን በቦምብ የሚያደባይ፣አልሞ የማይስት፣ለነፍሱ የማይሳሳ ደፋር ጀግና ነዉ።

የዚያድባሬን እብሪት ያስታገሰ፣የእምዬን ክብር ያስጠበቀ፣ሉዓላዊነቷን ያስከበረ ሳተና ነዉ-ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ

ደግሞም በ90ዎቹ መጀመሪያ ሸኣቢያ ኢትዮጵያን በደፈረ ሰዓት የሀገርን ጥሪ ተቀብሎ ቀድሞ የተሰለፈ፣በጠላት ሰማይ ተመላልሶ በነበልባል የቀጣ፣ለሀገር ሲል እዚያው የቀረ፣በዋጋ የማይተመን፣በቃላት የማይገለጽ መስዋዕትነት የከፈለ የምንጊዜም ጀግና፣ስሙ ሲጠራ ባላንጣዎች የሚርዱለት ነበልባል ነዉ።

ታላቁ፣ የቀለም ቀንድ ነዉ።የምጡቅ አዕምሮ ባለቤት ነዉ።ለብዙዎች ዛሬ፣ ትናንታቸዉ ያሳመረ የትዉልዶች መሠረት- ገራድ ሀንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሎዳሞ

እርሱ ከሀገር አልፎ በሠለጠነው ዓለም ጭምር የናኘ ስም አለዉ።በሰዉነት የሚያምን፣ለሁሉም በሁሉም ጉዳይ የሚደርስ ምክንያታዊ እና ሚዛናዊ ሰዉ ነዉ።ከራሱ ይልቅ ለህዝብ፣ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ በመታገል ዘመኑን የቋጨ ተምሳሌት ነዉ።

ድፍረት መለያዉ፣ፅናት መታወቂያው ነዉ።ተጋፍጦ ለማሸነፍ፣ተናግሮ ለማሳመን የሚቸግረዉ ሰዉ አይደለም።በአምባገነን ዘመን ዴሞክራሲን ያለማመደ፣ብቻዉን ታግሎ ያሸነፈ፣ህዝቡን ያለማመንታት ማስከተል የቻለ፣ለተከታታይ ዓመታት እንደራሴ መሆን የቻለ ኮከብ ነዉ።

ችግርን በመሸሽ ሳይሆን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ማሸነፍ እንደሚቻል ያሳየ፣የሀገር ፍቅሩን ሀገሩ ዉስጥ ሆኖ ስለ ሀገር በመታገል ያስመሰከረ፣ለሠላማዊ ትግል ፊት-አዉራሪ የዘመናችን ጀግና ነዉ-ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ።

በአንድ ወቅት ስለ ታናሽ ወንድማቸው የሚያዉቁት ካለ ብዬ ጠየኳቸው።በረጅሙ ወደ ዉስጥ ተነፈሱና "እኔም መንግስትን እየጠየኩ ነዉ" የሚል ምላሽ ስጡኝ።ከዚያ በላይ መጠየቅ አልቻልኩም።እናም እስከ ዛሬ ስለወንድማቸዉ እያሰቡ፣ነገር ግን ማንንም ተወቃሽና ተጠያቂ ሳያደርጉ ይህችን ምድር ተሰናበቱ -ፕሮፌሰር በየነ።

እነዚህ ሁለቱ የሀዲያ ፈርጦች፣የደቡብ ኢትዮጵያ ጀግኖች የኢትዮጵያ ባለዉታዎች ናቸው።ሁለቱም በየፊናቸው ዘመን ተሻጋሪ ገድል ፈፅመዉ፣ታሪክ ፅፈዉ አለፉ።በትዉልዶች ጅረት እየታወሱ ዝንታለም የሚኖሩ ህያዉ ሰዎች፣የሀገር ካስማ ፣የትዉልድ ባለዉለታ ጀግኖች ናቸዉ-ኮሎኔል በዛብህ እና ገራድ ሀንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሎዳሞ

መልካም እረፍት
ጋዜጠኛ ደስታ ወ/ሰንበት

የፍልስፍና አለም

24 Jun, 10:52


የሠው ልጅ ትንቢት፦

ባለ ብሩህ ጭንቅላቶች ይተነብያሉ ትንቢታቸውንም ተግባራዊ ያደርጋሉ። ይህ ጋዜጣ ለንባብ የበቃው በፈሬንጆች አቆጣጠር April18,1963 ከዛሬ 60 አመት በፊት ነበር። ጋዜጣው ትንሽ የግንኙነት ማሽን በኪሳችን እንይዛለን፣ ሰዎችም በመተያዬት እርስ በርሳቸው በዚህ የግንኙነት መሣሪያ ሀሳባቸውን ይለዋወጣሉ።

ይህ የሚሆን ነገር ነው። ነገ ይሆናል፣ ቶሎ ይሆናል ብለን አንጠብቅም ግን ከረዥም ግዜ በኋላ እውን ይሆናል ብለን እናስባለን።

ታስቦ አልቀረም እውን ሆነ። የዚያን ግዜ በላቦራቶሪ ምርምር ደረጃ ላይ ነበር፣ አሁን ግን በባለ ብሩኅ ጭንቅላቶች እውን ሆነ ። ሁሉም በውጤቱ እየተጠቀመ ነው ። የሚቆጨው ግን የሠው ልጅ ወደ ሥልጣኔ ሲገስግስና አለምን ባያሌው ሲለውጥ እዚህ አንሰን በዘረኝነት ስንናቆር መታዬታችን ነው፣ ሥልጣኔ የሸሸንና የምናሳዝን የምድር ጉዶች።

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

26 May, 10:03


https://www.binance.com/en/activity/referral-entry/CPA/together-v3?ref=CPA_007K3Z5BHX

የፍልስፍና አለም

25 Feb, 06:53


ዲዎጋን

📖📜📖📜📖

ዲዎጋን የተባለው የግሪክ ፈላስፋ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ413 ዓ.ዓ ተወለደ። ይኽ ፈላስፋ የዓለምን ክብርና ደስታ የናቀ፣ ከሕይወት ተድላ የራቀ ፈላስፋ ነበር። ቀን ያለ ጫማ ባዶ እግሩን ይሄዳል ፤ ሌሊትም ቀን ለብሶት የሚውለውን ካባ ደርቦ በአንድ ዋሻ ውስጥ ያድር ነበር።
አንድ ቅልና አንድ ዋሻ ነበሩት፤ የሚከተለውም አንድ ውሻ ነበር። ዋሻው ቤቴ ነው፣ ውሻው የማይከዳኝ ታማኝ ወዳጄ፣ ቅሉም ውሃ ቀድቶ የሚያጠጣኝ አገልጋዬ ነው ይል ነበር።
አንድ ቀን አንድ ህፃን ልጅ ከምንጭ ዳር ሆኖ በእፍኙ ውሃ እየቀዳ ሲጠጣ ዲዮጋን አይቶት "ይህ ልጅ እስከ ዛሬ ሳልረዳው የነበረውን ዕውቀት አስተማረኝ፤ ይህ ይዤ የምዞረው ቅል ለካስ ትርፍ ነገር ነው።" ብሎ ወረወረውና ከዚያ በኋላ ውሃ በእፍኙ እየቀዳ ሲጠጣ ኖረ።

📖📖📖

አንድ ቀን ደግሞ በቀትር ሰዓት ዲዎጋን ፋኖስ አብርቶ በገበያ መካከል ሲመላለስ አንድ ሰው ወደሱ መጥቶ "በእኩለ ቀን ፋኖስ አብርተህ የምትሄደው በምን ምክንያት ነው?" ብሎ ጠየቀው። ዲዮጋንም "ሰው አጥቼ እፈልጋለሁ" አለው። ሰውየውም "ይህ የምታየው ሁሉ ሰው አይደለምን?" ብሎ ቢጠይቀው "ይህን የማየውን ሁሉ ሰው ነው አልልም። ይህ የምትመለከተው ህዝብ እውነተኛን ነገር ትቶ ሁሉም የየራሱን ጥቅም የሚሻና ለግል ምኞቱ የሚገዛ ፍጡር ነው። እነዚህ የሰው አካል የለበሱ፤ ውስጣቸው ግን እንስሶች ናቸው። እውነተኛ ሰው ማለት አእምሮው ትክክል የሆነ፣ እውነትን የሚሻ ፍጡር ነው።" ብሎ ዲዎጋን መለሰለት።

📜📜📜

ዲዎጋን አንድ ቀን ፀሀይ ሲሞቅ ታላቁ እስክንድር መጥቶ አጠገቡ ቆመና "የምትፈልገውን ነገር ጠይቀኝና ልስጥህ" አለው። ዲዎጋንም "እኔ የምለምንህ ፀሀይዋን እንድሞቅ ዞር እንድትልልኝ ብቻ ነው"ብሎ መለሰለት።
ታላቁ እስክንድርም "እኔ እስክንድር ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር።" ብሎ አብረውት ለነበሩ ሰዎች ነገራቸው ይባላል።
ዲዎጋን በእርጅና እድሜው ሳለ አንድ ሰው "እንግዲህ አረጀህ ስራ ትተህ እረፍት ብታደርግ መልካም ነው" አለው። ዲዮጋን ግን "ሰው የሚፈልገውን ነገር ሲያገኝ ደስ ይለዋል እንጂ ወደኋላው አይሸሽም። እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ ሞትን ስከተለው ኖርኩ አሁን ስደርስበት እቸኩላለሁ እንጂ ለምን እረፍት አደርጋለሁ" ብሎ መለሰለት።
ዲዎጋን በ323 ዓ.ዓ ሞተ።

📖📖📖

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

22 Feb, 15:31


ትምህርት ለእውቀት ወይስ....?

📖📜📜📖

ትምህርት ለእውቀት ሳይሆን ትምህርት ለሥራ የሚል ነገር የፈጠሩት ጥቅመኛ ሰዎች ይመስሉኛል ። የሰውን ልጅ እንደመሳሪያ የሚያዩና የተሻለ መሳሪያ እንዲሆን የሚፈልጉ ናቸው ትምህርትን ለሥራ ያሉት ። በዚህ የተነሳ ትምህርት አንዱ የጭቆና መሳርያ ሆኗል ። ሰዎች በትምህርት ሽፋን የበሰበሰ አስተሳሰባቸውን ፣ ምክንያት የለሽ እምነታቸውንና ጠባቸውንም ጭምር ይጭኑብሃል ። ትምህርት ዋና ግቡ መሆኑ የነበረበት እውቀት፣ ነጻነት፣ ምርምርና ራስህን ለማወቅ ነው ። እንደዚያ ሲሆን ነው ጥሩ የሚሆነው ።

📜📜📜

በጥንት ዘመን ትምህርት የተጀመረው፣ ለማወቅ ለመመራመር፣ ለመደነቅ ብቻ ነበር ። አንድ ሰው በራሱ መንገድ ተመራምሮ የደረሰበትን የእውቀት ደረጃ ለሌሎች በነፃነት ያካፍላል፤ ያስተምራል ። ሆኖም በመጀመርያ ሶፊስቶች የሚባሉ መጡና ጥበብን፣ እውቀትን፣ ትምህርትን ገበያ ለማዋል ሙከራ አደረጉ ። እነ ሶቅራጥስ መጥተው ወደ ቀደመው ክብሩ መለሱት ። በዚህ መንገድ ብዙ ዘመንም ተኖረ ።

📖📖📖

በመጨረሻ ዘመነ ካፒታሊዝም መጣ! የሰውን ክብር በሚያወጣው ዋጋ ብቻ የሚመዝን፣ ሌላው የባርነት ዘመን መልኩን ቀይሮ መጣ ። በባርነት ዘመን የሰው ልጅ ተገዶ በኃይል እየተያዘ ነበር የሚሸጠው ። በአሁን በካፒታሊዝሙ ዘመን ግን የሰው ልጅ በራስ ተነሳሽነት ፣ ከአስፈሪው የኑሮ መከራ ለማምለጥ በፈቃደኝነት፣ ራሱን ለገበያ ያወጣል ። ደሞዝ በሚል ስምም ይሸጣል ።

📜📜📜

እንዲህ አይነቱ መሄጃ ያጣ ሰው የኮርፖሬት ድርጅቶች በርካሽ ዋጋ ይገዙታል ። እድሜውን፣ ችሎታውን፣ ጉልበቱን መዝነው አውርደው አውጥተው ይገዙታል ። ስሙን ግን ቅጥር ነው የሚሉት፣ ግዢ አይሉም ። በእግር ኳስ፣ በእስፖርቱ አካባቢ ነው በእውነተኛ ስሙ ሲጠራ አልፎ አልፎ የምንመለከተው ። በዘመነ ካፒታሊዝም ሁሉም ነገር ወደ ገበያ ነው ። ሽንትና ሰገራም ወደ ኃይል ማመንጫነት ወደ ማዳበሪያነት ተቀይረው ገበያ ውለዋል ። ሁሉም ነገር ወደ ገበያ በሚለው ሰው በላ የካፒታሊዝም ሕግ ጥበብም ትንህርትም እንዲሁ የገበያ ሸቀጦች ሆኑ ።

📖📖📖

ምንጭ 👉 " የፍልስፍና መንገድ " ገጽ 17-18
ደራሲ 👉 መጽሐፈ ኦዜል
ኅትመት 👉 2010

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

21 Dec, 20:14


ትምህርት ለእውቀት ወይስ....?

📖📜📜📖

ትምህርት ለእውቀት ሳይሆን ትምህርት ለሥራ የሚል ነገር የፈጠሩት ጥቅመኛ ሰዎች ይመስሉኛል ። የሰውን ልጅ እንደመሳሪያ የሚያዩና የተሻለ መሳሪያ እንዲሆን የሚፈልጉ ናቸው ትምህርትን ለሥራ ያሉት ። በዚህ የተነሳ ትምህርት አንዱ የጭቆና መሳርያ ሆኗል ። ሰዎች በትምህርት ሽፋን የበሰበሰ አስተሳሰባቸውን ፣ ምክንያት የለሽ እምነታቸውንና ጠባቸውንም ጭምር ይጭኑብሃል ። ትምህርት ዋና ግቡ መሆኑ የነበረበት እውቀት፣ ነጻነት፣ ምርምርና ራስህን ለማወቅ ነው ። እንደዚያ ሲሆን ነው ጥሩ የሚሆነው ።

📜📜📜

በጥንት ዘመን ትምህርት የተጀመረው፣ ለማወቅ ለመመራመር፣ ለመደነቅ ብቻ ነበር ። አንድ ሰው በራሱ መንገድ ተመራምሮ የደረሰበትን የእውቀት ደረጃ ለሌሎች በነፃነት ያካፍላል፤ ያስተምራል ። ሆኖም በመጀመርያ ሶፊስቶች የሚባሉ መጡና ጥበብን፣ እውቀትን፣ ትምህርትን ገበያ ለማዋል ሙከራ አደረጉ ። እነ ሶቅራጥስ መጥተው ወደ ቀደመው ክብሩ መለሱት ። በዚህ መንገድ ብዙ ዘመንም ተኖረ ።

📖📖📖

በመጨረሻ ዘመነ ካፒታሊዝም መጣ! የሰውን ክብር በሚያወጣው ዋጋ ብቻ የሚመዝን፣ ሌላው የባርነት ዘመን መልኩን ቀይሮ መጣ ። በባርነት ዘመን የሰው ልጅ ተገዶ በኃይል እየተያዘ ነበር የሚሸጠው ። በአሁን በካፒታሊዝሙ ዘመን ግን የሰው ልጅ በራስ ተነሳሽነት ፣ ከአስፈሪው የኑሮ መከራ ለማምለጥ በፈቃደኝነት፣ ራሱን ለገበያ ያወጣል ። ደሞዝ በሚል ስምም ይሸጣል ።

📜📜📜

እንዲህ አይነቱ መሄጃ ያጣ ሰው የኮርፖሬት ድርጅቶች በርካሽ ዋጋ ይገዙታል ። እድሜውን፣ ችሎታውን፣ ጉልበቱን መዝነው አውርደው አውጥተው ይገዙታል ። ስሙን ግን ቅጥር ነው የሚሉት፣ ግዢ አይሉም ። በእግር ኳስ፣ በእስፖርቱ አካባቢ ነው በእውነተኛ ስሙ ሲጠራ አልፎ አልፎ የምንመለከተው ። በዘመነ ካፒታሊዝም ሁሉም ነገር ወደ ገበያ ነው ። ሽንትና ሰገራም ወደ ኃይል ማመንጫነት ወደ ማዳበሪያነት ተቀይረው ገበያ ውለዋል ። ሁሉም ነገር ወደ ገበያ በሚለው ሰው በላ የካፒታሊዝም ሕግ ጥበብም ትንህርትም እንዲሁ የገበያ ሸቀጦች ሆኑ ።

📖📖📖

ምንጭ 👉 " የፍልስፍና መንገድ " ገጽ 17-18
ደራሲ 👉 መጽሐፈ ኦዜል
ኅትመት 👉 2010

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

04 Dec, 03:46


ዕውቀት እና ፍላጎት

📜📜📜

የሾፐንሀወር ፍልስፍና በጥቂቱ...

የምትዋሸው በፍላጎትህ እንጂ በእውቀትህ አይደለም ። ስለዚህም ማወቅህ እንዳትዋሽ ካላደረገህ ፍላጎትህ የእውቀትህ አዛዥ ሆኗል ማለት ነው ። ለዚህ ነው ሃይማኖቶች በላይኛው ቤት ዋጋ ታገኝበታለህ የሚሉት የእውቀትህን ሳይሆን የፍላጎትህን ሥራ ነው ። ማመንዘር ብትፈልግ በዕውቀትህ ሳይሆን በፍላጎትህ ነው ። ጥላቻንም ብናይ ሰው በእውቀቱ አይጠላም፤ በፍላጎቱ እንጂ...ወዘተ...በአጭሩ ማወቅህ ፍላጎትህን ካልገዛ፤ ፍላጎትህ የዕውቀትህ ገዢ ሆኗል ።

📖📖📖

"...እውቀት ይደክማል፤ ፍላጎት ግን ዘወትር አዲስ ነው ። አዋቂነትህ አንተ ስትተኛ አብሮህ ያንቀላፋል፤ ፍላጎትህ ግን በሕልምህም ከአንተ ጋር ይሠራል ። እንግዲያማ ፍላጎትህ የማይደክምና የማያንቀላፋ ከሆነ ማወቅህ የፍላጎትህ ተገዢ ሆኗል ማለት አይደል? ሰው የቱንም ያህል ቢያውቅ እንስሳነቱ አይቀየርም የሚለው ያስማማን ይሆን ።

ለምሳሌ ፦
ከየትም ሃገር ስትነዳ ያመጣህውን ዝሆን በአንዲት ድልድይ ላይ ደርሰህ ተሻገር ብትለው በጄ አይልም፤ ዝሆኑ ድልድዩ የእሱን ክብደት እንደማይችል ግን ተምሮት አላወቀውም ፤ ውሻህን ከጠረጴዛ ላይ ዝለል ብትለውም እንዲሁ አይዘልልህም፤ እሱም ቢሆን ሲወድቅ እንደሚሰበር ተምሮ አላገኘውም....እንዲሁ ሰው ሳያውቅ የሚፈልገውና ሕይወቱን የሚመራበት ነገር እጅግ ብዙ ነው....

📜📜📜

ምንጭ 👉 ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩ (4በ1)
ገጽ 👉 83
ደራሲ 👉 ኃይለጊዮርጊስ ማሞ

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

19 Nov, 19:12


የሆነም ያልሆነም!
/ ክፍል 3/
(ስብሀት ገብረእግዚአብሔር)
የመጨረሻው ክፍል
📗📒📕

ቻይናዊው ፈላስፋ ጁዋንግ ዱ እንዲህ ይላል ። "ቢራቢሮ ሆኜ ስበር - ስበር - ስበር እነቃለሁ - ታድያ፣ ለካ በሕልሜ ኖሯል ። ሰው ነኝ ።...ግን ምን ይታወቃል ። ሰው ስሆን ቆይቼ በኋላ እነቃና አያለሁ ። ለካ በሕልሜ ኖሯል? በውን ግን ቢራቢሮ ነ ኝ ። አይቻልም አይባልም ። ሕልምህ እስከቀጠለ ድረስ እውን የሚመስልህ ስለሆነ፣ ያቺ ያሁኗ ደቂቃ በውንህ ለመሆኗ ማረጋገጫ የለህም ።

📖📖📖

ኧሃ! በዚህ አካሄድማ እርግጠኛ የምንሆንበት ነገር ላይኖር ይችላል ። ምናልባት እስቲ እንፈላሰፍ፤ ሃሳብን እያነሳን እንጣል ።

🔴 እግዚአብሔር ነው የፈጠረኝ፤ እርግጠኛ ነኝ ።

🔵 ሲሉ ሰምተህ?

🔴 አረ መጽሐፉን አንብቤ!

🔵 ማን የጻፈውን?

🔴 ሰዎች ናቸው የጻፉት፤ እርግጥ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ እየነገራቸው ነው የጻፉት ።

🔵 እንዴት አወቅህ? እዚያ አልነበርክ?

🔴 እንዴ? ሸረሪት ድሯን ስታደራ፣ ቢራቢሮ ስትበር ፣ ጽጌረዳ ስትፈነዳ ፣ ፀሃይ ስትወጣ ይህን ይህን እያየህ ፈጣሪ የለም ትላለህ?

🔵 አልወጣኝም!

🔴 እንግዲያው አለ ማለት ነዋ!

🔵 አላልኩም!

🔴 እንግዲያው ምንድነው የምትለው?

🔵 እግዚአብሔር ሊኖርም ይችላል ፤ ላይኖርም ይችላል ።

🔴 እምነትና ሃይማኖት ሌላ ፣ በሎጂክ መፈላሰፍ ሌላ!

📖📖📖

እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ነገር አለ ወይ? አሁን ያለሁት በሕልሜ ውስጥ ልሁን ወይስ በውኔ ውስጥ ልሁን ምን ማረጋገጫ አለኝ? ምንም ።
ደግሞ ሕጻን ነበርኩ - ብይ የምጫወት ፤
ጎረምሳ ነበርኩ - ሴቶቹ ትኩሳቴን የሚቀሰቅሱብኝ፤
ሽማግሌ ነኝ -ኑሮን እየታዘብኳት ነው ።
እነኚህን ሦስቱን ነኝ እንዴ? ያ ሕጻን አሁን የታለ? ያ ጎረምሳስ? የለም፤ እኔ የለሁም፤ እያለሁ የለሁም ፤ ስለ አንድ ነገር ብቻ እርግጠኛ ነኝ ። እያሰብኩ ነው ።

📖📖📖

" እያሰብኩ ነው፤ ስለዚህ አለሁ " አለ ሬኔ ዲካርት ። መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ መፈላሰፉን ቀጠለበት ።

ተፈፀመ

ያነበቡትን ለወዳጅዎም ያጋሩ

ምንጭ 👉 ("ደቦ ቅጽ አንድ" በ 60 ነባርና አዳዲስ ጸሐፍት)

የጋሽ ስብሀትን ፍልስፍና ተኮር ወግ እንዴት አገኛችሁት..?

አስቂኝ ነበር (😁)
ግራ አጋቢ ነበር (🤷‍♂)
መጠይቃዊ ነበር (🤔)

የተሰማችሁን አጋሩን እናመሰግናለን

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

13 Nov, 13:41


የሆነም ያልሆነ!
/ክፍል 2/
ስብሀት ገብረእግዚአብሔር

📗📒📕

ከክፍል 1 የቀጠለ...

ግን እዚህ ውስጥ ያልተመለከትነው ነገር አለ ። ይኸውም እነዚያን ሁሉ እኔዎች የሚያገናኘው አለ ። ትውስታ ወይም ማስታወስ ። እሱ ነው፣ ብዙዎቹን እኔዎች አንድ አጠቃላይ እኔ የሚያደርጋቸው ። ትውስታዬና ማኅበረሰቡ ናቸው - እንግዲህ አንድ እገሌ የሚባል ስሙ አለ የሚሉት ። አሉ ካሉ እንግዲህ ይኑሩላቸዋ!

📖📖📖

...ሌላ መንገድ እንሞክር መሰለኝ ። አንባቢ ሆይ! ወጠሰሪ ዶሮን እንደምትበልተው አይነት ዓይነት ሃሳብን እንበልታት ። ለካስ ሃሳብ ከቃላት ነው የተገነባችው ። በቋንቋ ነው የምናስበው ። ከሌላ ሰው ጋር ለመነጋገር ስንፈልግ፣ ከውስጣችን ለሁኔታው የሚሆን የሚመስለን ሃሳብ በድምጽ አውጥተን እንነግረዋለን ። እንግዲህ ግን ለኔ መናገር ነው እንጂ መወያየት የለም ። እኔ ይህን የጻፍኩት አንተን የምታነበውን ልሰማህ አልችልም ። ቢሆንም ከባዶ ግማሹ ስለሚሻል፣ እኔም ልጻፍልህ አንተም አንብብልኝ ። እንዲሁም አንቺ ። (አንተ ማለት የምናበዛው በብዛት ከወንድ ጋር ስለምንውል ነው ።)

📖📖📖

ግን እኔስ ለምን መጻፍ አስፈለገኝ፤ አንተስ ለምን ማንበብ አስፈለገህ? ኧሃ! እዚህ ላይ ደግሞ ሃሳብን ሳይሆን የሰው ልጅን እንበልተው ። አንድ ሁለት ብልት ያህል ብቻ ። ምክንያቱም የሰው ልጅ ማለቅያ የለውም ። ይሞታል እንጂ አያልቅም(አለች አባባል!)

📖📖📖

የሠው ልጅ እንግዲህ በማኅበር የሚኖርና የሚሰራ ነው ። ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው ደግሞ ቋንቋ ነው ። ቋንቋ ማሰቢያ፣ መነጋገርያ፣ መግባብያ፣ ግለሰቦችን በማኅበራዊ ገመዶች ማስተሳሰርያ - ትልቅ ተዐምር ። እንግዲህ ሰው በሃሳብ የሚጓዘው ራሱን ፍለጋ ነው ። አዎና! (እዚህ ላይ አንባቢት ቆም ትላለች)

📖📖📖

ያን የስፋት ስፋት ከየት አምጥተን እንድረስበት? ኧሃ አሁንስ በዛ ባይደረስ አይቀርም ። ጤዛ ነን ። ሰማይ ከነስፋቱ በእኛ ውስጥ ነው ። ወደ ውስጣችን ብንመለከት አንባቢ ሆይ አሁን የሃሳብ አዙሪት፣ ሽክርክሪት ላይ ደርሰናል ። ከእንግዲህ እንኳን በጽሑፍና ንባብ የኤሊ ጎታታነት ቀርቶ በንግግር ፈጣን ሩጫ ችለን አንደርስበትም ። በሃሳብ በረራ ነው ። እዚያ ብቻ ለብቻ ነው ። ከአንባቢዬ ጋር የማወራ መስሎኝ ነበር ። ብቻዬን ነኝ ለካ! ሲያስፈራ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ደስ ሲል ፤ ሲያስፈነጥዝ ። የሃሳብ ክር ቢመዙት ቢመዙት አያልቅም ። እኛ የፈጣሪ ክሮች ስንበጠስ አብሮን ይበጣጠሳል እንጂ ። አሜን አሜን!

📖📖📖

መፈላሰፋችንን እንቀጥለው ከተባለ፣ አስቀድመን የጥንት ግሪካውያንን በኅሊና እንባርካቸዋለን ። በእነሱ በኩል ነዋ ፍልስፍና የበቀለችው ። በአምስተኛው ምዕተ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ። ማንም ሰው ይፈላሰፋል ። ግሪኮች ግን ፍልስፍናን ሳይንሳዊ ቅርጽ አስያዟት ። ዘመናትን እንዝለልና በፈረንሳይ ሀገር ሬኔ ዴካርት (1596 - 1650 እ.ኤ.አ) ሲፈላሰፍ እናገኘዋለን ። ለዴካርት እጅ ነስተን እሱ ባመነጨው ዘዴ እንፈላሰፋለን ።

📖📖📖

ቻይናዊው ፈላስፋ ጁዋንግ ዱ እንዲህ ይላል...

📜📜📜

ይቀጥላል....
( ምንጭ 👉 " ደቦ ቅጽ አንድ " 60 ነባርና አዳዲስ ጸሐፍት )
/ ክፍል 3 / የመጨረሻው ክፍል ይቀርብ ዘንድ በንባብ አብሮነታችሁን አሳዩን 10 (📖) ሲደርስ ቀጣዩን ክፍል እንለቃለን ።

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

09 Nov, 19:22


የሆነም ያልሆነም!
/ ክፍል 1 /
(ስብሀት ገብረእግዚአብሔር)

📗📒📕

እንፈላሰፍ እንግዲህ እንዳመጣብን!
መፈላሰፍ ማለት ከሃሳባችን ጋር መጫወት ማለት ነው ። <እንዳመጣብን> ያልኩት ላለማሰብ ስለማንችል ነው ። ላለመተንፈስ የማንችለውን ያህል ። ከሃሳባችንማ መውጣት ብንችል ኧይ እንዴት ያለ እረፍት ነበር! እፎይ! አንድ ብቻ ሳይሆን ሃሳብ ረገፈ ። ግና ከቆዳችን መውጣት እንችላለን?

📖📖📖

ማሰብ ካልቀረልን እንግዲያው፣ የማይቀርልህን እንግዳ አጥብቀህ ሳመው ። ይሁንና እንደ ልማዱ፣ እኛ ተዝናንተን እናስብ ። እንመቻች ። ሃሳባችንን እንሳፈረውና እሱ ይዞን ሲሄድ ተጓዦች ዙርያውን እንመለካከት....

ለመሆኑ ማነው የሚያስበው?....
እኔ ነኛ!
እኔ ማለት ይህንን የጻፈውም፣ ይህንን የሚያነበውም ። ይሁን...እኔ ማን ነኝ? እንዴ፣ ምንስ ቢሆን ሃሳብኮ አሳቢውን ይጨምራል ። ማለት አሰቢው ከሌለ ሃሳቡ ከየት ይመጣል? ማን ያስበዋል? እኔ ። እኔ እገሌ!

📖📖📖

እገሌ ማን ነው? ያ ማሕጸን ውስጥ የነበረው ነው? ያ ኩኩሉ ሲጫወት የነበረው ነው? ጎረምሳ ፍቅር የሚባል እብደት አይሉት ተአምር የደረሰበት ነው? ወይስ ያ ወልዶ በልጆቹ ተደንቆ የማያባራው ሰውዬ ነው?
እነዚህ እኔዎች ሁሉ አንድ እኔ ናቸው ለማለት እችላለሁ? ወይስ ስሜ ክር ይመስል እንደ ዶቃዎች እነዚህን ሁሉ እኔዎች አያይዞ ነው?

📖📖📖

(ለወጣት ደራስያን እቺ የክርና የዶቃዎች አባባል ከነሃሳቧ የሩቅ ምስራቅ የቡድሂዝም ናት) ስሜ ነኝ እንጂ እኔ የለሁም፣ እኔዎች ነን ያለነው ። ያለሁትማ እኔ ያሁኑ እኔ ነኝ ። የቀድሞዎቹ እኔዎች የሉም ። አልፈዋል ። እኔም ይኸው እያለፍኩ ነው ።

📖📖📖

ያ ግዜ እሚሉት አይናገሬ መጣንግዲህ ። ያለፈው ፣ ያሁኑ ፣ የሚመጣው ። ትናንት የለችም ፤ አልፋለች ። የትናንትናው እኔም የለም አልፏል ኧረ የቀድሞው እኔም የለም ። ከአንድ ሰከንድ በፊት የነበረው እኔም የለም ። በዚች የአሁኗ ቅጽበት እኔ ብቻ ነው ያለው ። እሱም ያውና አለፈ ።

📖📖📖

በዚህ አካሄዳችን ጊዜም የለም-እኔም የለሁም ። ሂደት ብቻ ነው ያለው እልፈት ። ግን እዚህ ውስጥ ያልተመለከትነው ነገር አለ ። ይኸውም....

📜📜📜

ይቀጥላል...
(ምንጭ 👉 "ደቦ ቅጽ አንድ" 60 ነባርና አዳዲስ ጸሐፍት)
/ ክፍል 2 /ይቀጥል ዘንድ በንባብ አብራችሁን መሆናችሁን አሳዩን 10 (📖)ሲሆን እንቀጥላለን

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

07 Nov, 04:12


ፍልስፍና ምንድነው?

📖📖📜📜📖📖

"ፍልስፍና" ቃሉ "የጥበብ ፍቅር"(Love of wisdom) ማለት ነው ። ከዚህ ስንነሳ ፍልስፍና የጥሬ እውቀት ማካበቻም ሆነ ማስተላለፍያ ዘርፍ ሳይሆን በጥበብ ስለጥበብ የሚደረግ ከፍተኛ መነሳሳት እና መጠየቅ ነው ። ሶቅራጥስ እንዳመለከተው ፈላስፋ ጥበብን ለማፍቀር እንጂ የራሱ ለማድረግ ማጠየቅ የለበትም ።

📜📖📜

ሶቅራጥስ ፤ ምርምራችን የትም ያድርሰን የትም ፤ ያልተመረመረ ህይወት እርባና የለውም በማለቱ የፈላስፎችን መንገድ እንደጠረገና እንደ ደለደለ ተደርጎ ተቆጥሮለታል ። አባባሉ ለፍልስፍና የመመርመር ግንዛቤና የመጠየቅ ባህሪይ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳል ። በተጨማሪም የመልካም ህይወት ስነ-ምግባራዊ ግንዛቤን መልሶ መላልሶ በፍልስፍና የመመርመር ትኩረትን እንደሚሻ ይጠቁማል ።

📖📜📖

አርስቶትል ታላላቅ የሚባሉ ስራዎችን በማጥናት የፍልስፍናን ጭብጦች ከፋፍሎ ለማስቀመጥ ሞክሯል ። ከዚህ ተነስቶ ፍልስፍናን በብዙ ዘርፎች ከፋፍሏል ። አርስቶትል "ቀደምቱ ፍልስፍና" ለሚለው "ዲበአካል" (Metaphysics) የመጀመርያውን ስፍራ ይሰጣል ። ዲበ አካላዊነት የመሰረታዊ መርህ እና ምንጭም እውቀት ስለሆነ ነው ቅድሚያውን የሰጠው ። ለዲበ አካል ትኩረት መስጠቱ በፍልስፍናእ ዘርፍ የሚጫወተው ከፍተኛ ሚናም ይኖረዋል ።

📜📖📜

ወደ ዘመናዊናቱ ስንመጣ ሙሉ ትኩረት የሚያገኘው የእውቀት ምንነትና እውቀትን ስለሚያውቀው አእምሮ መዋቅር ነው ። ኢማኑኤል ካንት የዚህ ዝንባሌ በር ከፋች ነበር ። ካንት ለተፈጥሮ ሳይንስ ግልጋሎት በሚውለው በ "ዳሰሳዊ እውቀት" (empirical knowledge) እና በ"ምክንያታዊ እውቀት" (Rational knowledge) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ፍልስፍና በማስተዋወቅ የዘመናዊውን አዲስ አቅጣጫ በር ከፈተ ። በዚህም አሁን ድረስ ስለፍልስፍና እና ሳይንስ አንፃራዊ ሚና የጦፈ ክርክሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ ። በግልፅ መመልከት እንደምንችለው የዘመናችን ሰዎች መሰረታዊ እውቀትን የሚሹት ከፍልስፍና ሳይሆን ከሳይንስ እየሆነ መጥቷል ። ለምሳሌ በጊዜአችን ጠንካራ አስተሳሰብ እየሆኑ ከመጡት ዘመናዊ ፍልስፍናዎች ውስጥ "ተጨባጫዊነት" (Positivism) አንዱ ነው ። በዚህ ፍልስፍና መሰረት "ዳሰሳዊ ሳይንስ" (empirical science) ብቻ ትክክለኛ የእውቀት ምንጭ ተደርጎ ሲወሰድ የፍልስፍና አስተዋፅኦ ይሄንኑ ሳይንስ መተንተንና መሔስ ብቻ እንደሆነ ተደምድሟል ።

📖📜📖

ፍልስፍና የጥበብን ልዕልና የሚያስመሰክሩ የነጠሩ እውቀቶች የሚገኙበት ዘርፍ ነው ። ስለሰው ልጅ ስለአለምና ስለፈጣሪ የሚያትቱ ጥበቦች ከፍልስፍና ይቀርብልናል ። ስለ መልካም ህይወትና ጥሩ ማህበረሰብ የሚተነትን ጥበብም የሚገኘው ከፍልስፍና እንደሆነ መዘንጋት አይገባም ። ከዚህ አመለካከት አንፃር ካየነው ፍልስፍና የሰው ልጆች ሁሉ ግድ እንጂ የልሂቃን ጉዳይ አይደለም ።

📜📖📜

ፍልስፍና እንደ ፊዚክስ ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የቤተሙከራ ተረጋጋጭ ሳይንስ አይደለም ። ተውጠንጣኝ ምክንያታዊ ሳይንስ ነው ብንል ያስኬዳል ። ልክ እንደ ሂሳብ ደርዝ-ደርዝ ባለው እሳቦት ውስጥ በትንተና እየበለፀገ ይመጣል ። የሂሳብ ሊቅም ሆነ ፈላስፋ ከተለምዷዊ እውቀት ውጪ የተጨባጭ ማስረጃ ጥገኛ አይደለም ። ፍልስፍና ፤ ስነ-ፅሁፍ ፣ ስነ ጥበብ የሚወክለው ቱባ ጥበብ አይደለም ። ነገር ግን ከቱባ ጥበብ ይልቅ ነፃውን ጥበብ በተለይም የክርክር ጥበብን ይጠቀማል ።

📖📖📖

(( ምንጭ 👉 " የፍልስፍና አፅናፍ " ከሚለው የዓለማየሁ ገላጋይ ትርጉም መጽሐፍ ላይ የተቀነጨበ ))

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

07 Aug, 07:01


ታኦኢዝም
(ከላይኛው የቀጠለ)

📜📖📜

በቻይና ታኦኢዝምን የሚከተሉ እምብዛም አይደሉም ። በምንም ማመንና "ምንም" መከተል ይከብዳል ይላሉ ። የጃፓኑ ዜን ግን በታኦኢዝም አስተሳሰብ ተወስዶ እንደነበር እንረዳለን ። ለዚህም ነው የጃፓን ቅርፃ ቅርጽ የሰው እጅ ሳይነካቸው በተፈጥሮ ቅርፃቸው ብቻ መደነቅን እንዲያተርፉ አድርጎ አልፏል የሚባለው ።

📖📜📖

የታኦኢስት ዋነኛ መገለጫቸው ባላቸው ነገር ረክተው መገኘታቸው ነው ።ይኸ ደግሞ ኮንሺፊየዝምን የሚቃወሙበት ዋነኛው ነገር ነው ። ከዚሁ ጋር የተገናኘ የአንድ የኮንፊሽየስ አስተሳሰብ ተከታይ የሆነ ሰዓሊን ታሪክ ቻይናውያን ይነግሩናል ። ይኽ ሰዓሊ የእባብ ስዕልን መሳል ይጀምርና ስዕሉ በእውነታው የምናየውን እባብ አልመስል እያለ ያስቸግረዋል፤ ይኸን ግዜ ሰዓሊው ለእባቡ አራት እግሮች ማበጀት ይጀምራል ፦ "ለእባብ እግር መሳል" ይላሉ ታኦኢስቶች "የሌለን ነገር እንደማሳየት(መግለጽ) ነው ፤ አልያም ተፈጥሮን በሥልጣኔ እንደመተካት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል" ይላሉ ። በሕፃንነት የጀመርነውን ሕይወት በሕፃንነት እንጨርሰው እንደማለት ነው ።

📜📖📜

ታኦኢስቶች ለራስ መብቃት እምነታቸው ነው ። "ዉ ዊ" ይሉታል ።
"የምድርን አበቦች ተመልከቱ ... አያርሱም፣ አይዘሩም... ሰለሞን እንኳን በዚያ ሁሉ ክብሩ እንደ እነሱ አላጌጠም" ። ይኽን ምክር ታኦኢስቶች የሚቀበሉት በከፊል ነው ። " አትረስ ፣ አትዝራ... " ይላሉ ታኦኢስቶች

" ነገር ግን ይኸን የማታደርገው የሰማዩ አባት ስለሚያቀርብልህ አይደለም፤ አንተ ለራስህ ማቅረብ ስለምትችል እንጂ ። የምታርሰውና የምትዘራው ሁሉ ለአንተ መታሰርያ ነው፤ ይልቁንስ ታኦ ነፃና ግልጽ እንዲሁም ባዶ ነውና በዚያ ተመላለስ ...." ይላሉ ።

📖📜📖

በመጨረሻም ስለሰው ልጅ ይመክሩናል ፦

"የሰው ልብ እንደተወጠረ ሽቦ ነው ፤ ብትጫነው ተመልሶ ይዘላል ። እናም ሰውን ከመጨቆን ራቅ " ነው ምክራቸው ። ዳሩ ታኦ ስትሆን አንተስ ሰው ጋ ምን ልታደርግ ትደርሳለህ?

ለዚህም ነው ቻይናውያን ከሁለቱ አስተሳሰቦች አንዳንድ ነገር ወስደዋል የሚባለው ፦

" ቻይናዊ ሲሳካለት ኮንፊሽየስ ፤ ሲወድቅ ደግሞ ታኦኢስት ይሆናል " ይባላል ።

📜📖📖📜

ምንጭ 👉 ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩(4ቱን በ1)
ደራ ሲ 👉 ኃይለጎርጊስ ማሞ
ከገጽ 44-46 ካለው የተወሰደ

ስለ ኮንፊሽየስ አስተምህሮዎች ሌላ ግዜ የምናቀርብላችሁ ይሆናል ።

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

04 Aug, 20:14


የጥበብ ቅምሻ...

ታኦኢዝም

📗📒📕

በቻይናውያን ፍልስፍና ከኮንሺፊየኒዝም ቀጥሎ ሁለተኛውን መስመር የያዘው ታኦኢዝም ነው ። የታኦኢዝም ፍልስፍና በላኦትዙ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው ። ላኦትዙ ማለት "Old Master" ማለት ነው የሚሉ አሉ ። በእርግጥም ከጥንታዊነቱ ጋር ሲነፃፀር ትርጉሙ ተቀባይነትን ሊያገኝ ይገባዋል ። ላኦትዙ በኮንፊሽየስ ዘመን የነረም ነበር ይባላል ። በአንዳንድ አፈታሪክ ላኦትዙና ኮንፊሽየስ በመንገድ ላይ ተገናኝተውም ነበር ይላሉ ፤ ይሁንና አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያወሩት ስላልነበራቸው በዝምታ ተላልፈዋል ይባላል ።

📜📖📜

የላኦትዙ ተቀዳሚና ዋነኛ ፍልስፍናዊ እሳቤና ሥራ ደግሞ "ታኦ ቲ ቺንግ ይባላል" ። "መንገዱና የመንገዱ ኃይል" እንደማለት ነው ይላሉ ። ይኽ እሳቤ ከኤሽያ ፍልስፍናዎች ሁሉ ጣፋጭና የተዋበው ነው የሚሉም ምዕራባውያን ፈላስፎች አልጠፉም ። ከእነዚህም አንዱ ጆርጅ ሳንታያና ነው ። እንደሌላው ፍልስፍና ሁሉ የታኦኢዝም መሠረቱ ውስጣዊ ማንነታችን ነው ። ታኦ ምክንያታዊና ሞራላዊ የሆነው ተፈጥሮአዊ አስተሳሰባችን ሲሆን ይኸ አስተሳሰብ ደግሞ በውስጡ "ባዶነትን" ያዘለ ሆኖ እናገኘዋለን ።

📖📜📖

ታኦ ምንም እንኳን ሲተረጎም "መንገድ" እንደማለት ቢሆንም ይኽ መንገድ ግን ራሱን ወደ ባዶነት (ምንምነት) መውሰጃ ነው ። በብዙዎች የቻይና መልክዓምድራዊ ሥዕሎች ውስጥ የምናየው ባዶነት የታኦኢዝም ፍልስፍና ተፅዕኖ ነው የሚሉ አሉ ። ታኦኢስቶች ከሰው ተነጥለው ወደተራራ ጫፍ ይወጡና በደመና መካከል ይቀመጡ ነበር ይባላል ። ባዶነትን ፍለጋ ነው ። ታኦኢስቱ ቹ ኦንግ ዙ ይመክረናል ፦
"ሌሎችን ለባልንጀራነት የሚፈልግ እሱ ለዘላለም በሰንሰለት እንደታሰረ ሰው ነው፤ በሌሎች አጥብቆ የሚፈለግ ደግሞ እሱ ለዘላለም እንዳዘነ ይኖራል፤ ሰንሰለቱን አውልቀህ ጣል ፤ ማዘንህንም አስወግድ ፤ ከታኦም ጋር በታላቁ የባዶነት መንግስት ውስጥ ተመላለስበት ።"
ይኽን የሰሙ ምዕራባውያን ፈላስፎች
" ታኦኢስት ማለት ለማንም የትም እንደማይሄድ ፈጽሞ ቃል የማይገባና ፤ ነገር ግን የሚሄድበትም የሌለው ነው " ይላሉ..

ይቀጥላል...

በንባብ አብራችሁን መሆናችሁን እቺን 👉 (📜) በመጫን አሳዩን...

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

31 Jul, 20:35


ፍቅር በፍልስፍና እይታ

ንፅረተ-ፍቅር

📖📜📜📖

አብዛኞቻችን "ፍቅር" ሲባል ከሰማን እዝነልቦናችን ላይ የሚመጣብን በወንድና በሴት መካከል ያለው የመቀራረብ ስሜት ነው ። በእርግጥም እንዲህ ያለው ፍቅር ተጨባጭና ለተመልካች ግንዛቤ የማያዳግት ነው ። ተጨባጭነቱንና ግልፅነቱን ያገኘው በቴአትሮች ፣ በሆሊውድ ፊልሞች ወይም በፍቅር ልቦለዶች ብርታት ነው ማለት አይቻልም ። በነባሩ ባህል ውስጥ ስንመለከት የኖርነው እንዲህ ያለው የወንድና የሴት ፍቅር ወደ አንድ አካልና አንድ አምሳልነት ሲያመራ ነው ።

📖📜📖

ፍቅር አይነቱ ብዙ ነው ። በፆታዊ ፍቅር ብቻ አይገደብም ። የመጽሐፍ ቅዱሱ ንጉስ ዳዊት ቤርሳቤህን በማፍቀር ብቻ እሷን አግኝቶ አልተገታም ። በህይወቱ ውስጥ ሌላም አይነት ፍቅር እንዳለ አሳይቷል ። ለምሳሌ ለዮናታን ከፍተኛ ፍቅር ነበረው ከዚህም ባሻገር ልጁ አቢሴሎም ሲሞትም "አቢሴሎም ልጄ ልጄ" ሲል በተሰበረ ልብ ፍቅሩን ገልጿል ። ስለዚህ የጓደኝነትና የስጋ ዝምድና ፍቅር እንዳለ በዚህ እንረዳለን ። በፕሌቶና በሶቅራጥስ እንዲሁም በኢየሱስና በደቀመዛሙርቱ መካከል የነበረው ደግሞ እውቀትን ወይም ሃይማኖትን ተንተርሶ የሚመጣውን ፍቅር ይገልፅልናል ። በዚህ አይገታም የሰው ልጅ አገሩን፣ ወገኑን ፣ አቋሙን ፣ ቤተሰቡን ፣ አምላኩን በማፍቀር የተለያየ ፍቅር መኖሩን አሳይቷል ።

📖📜📖

የተለያዩ ግንኙነቶችን እራሳቸውን አስችለን የምንወክልበት መጠርያ ስለምናጣላቸው በጋራ ስያሜ የምንደፈጥጥበት ግዜ ብዙ ነው ። ፍቅርም አይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን ካንዱ የሚለይ ስም ግን ሲውጣለት አይታይም ። ይሄንን ክፍተት ተመልክተው ለፍቅር አይነቶች ሶስት መጠርያ ያዘጋጁ ግሪኮች ናቸው ። "ፊልያ" (Philia) ፣ "ኢሮስ" (Eros) ፣ እና "አጋፔ" (Agape) ይሏቸዋል ። ምናልባት በጥሬው ብንተረጉማቸው "የወዳጅነት" ፣ "የምኞት" እና "የልግስና" የፍቅር አይነቶች ልንላቸው እንችላለን ። ፊልያ በንጉስ ዳዊትና በዮናታን መካከል የነበረውን የጓደኝነት ፍቅር ይወክላል ። ኢሮስ ደግሞ አፍቃሪው ተፈቃሪውን በማግኘት እርካታን የሚቃብዝበት አይነቱ ነው ። በወንድና በሴት መካከል የሚከሰተውን ማለታችን ነው ። አጋፔ ደግሞ መንፈሳዊ ፍቅር ሆኖ በሰውና በፈጣሪው ወይም በሰዎች መካከል ይከሰታል ። በቅዱሳት መጻህፍት አማካኝነት አምላክ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር በአጋፔ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። በአፀፋው ሰዎች ስለፈጣሪያቸው የሚቀበሉት መከራና ሞት የዚሁ የፍቅር አይነት ውጤት ነው ።

📖📜📖

ምኞት ያለበት ኢሮስን ጨምሮ ሶስቱም አይነት ፍቅሮች የተሸጋጋሪነት ጠባይ አላቸው ። ስለዚህ ፍቅር ሁልግዜም ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያነጣጥር ጥልቅ ስሜት ነው ለማለት ተገደናል ። ነገር ግን እራስ አፍቃሪነትስ? የት ይመደባል? "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለው የአምላክ ትእዛዝ ለእራስ አፍቃሪነት እውቅና አይሰጥም? የስነ-ምግባር ሰዎች እና የስነ-ልቦና ምሁራን እራስን ማዕከል ያደረገ ፍቅርን ጤናማ ያልሆነ ስሜትና ያለመብሰል ምልክት አድርገው በመፈረጅ ያጥላሉታል ። የሃይማኖት ጉባኤዎችም ለራሳችን እራሳችን የምናሳየውን ፍቅር ያወግዙታል

ምንጭ 👉 " የፍልስፍና አፅናፍ "
ደራሲ 👉 ዶክተር ሞርቲመር ጄሮም
ትርጉም 👉 ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ

፨ በነገራችን ላይ ባሁን ሰአት ግሪኮች ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስቱ የፍቅር አይነቶች በተጨማሪ አራተኛ ስተሪጅ(Sturige) ወይም "ቤተሰባዊ ፍቅር" የሚሉት አይነት ፍቅር እንዳለም ያምናሉ አንዳንድ መጽሀፍትም በዛ መነሻነት ፍቅርን በአራት ከፍለው ይገልጹታል ።

For any comments:- @fear121

JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Join our group:-👇👇👇👇👇👇@philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

የፍልስፍና አለም

25 Jul, 18:53


💡'እኔ ማን እንደሆንኩኝ አታውቅም, ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ'

'She doesn't know who I am, but I know who she is

💎 የ85 አመት አዛውንት ናቸው ከ 60 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ጋር በትዳር ኖረዋል, ባለቤታቸውን በሄዱበት ሁሉ እጃቸውን አጥብቃ እንድትይዛቸው ባለመሰልቸት ይጠይቋታል, ስትቆም ቆመው ስትቀመጥ ተቀምጠው ስታስቸግር አብረው ተቸግረው . . . ሳይሰለቹ የድሮ ፍቅራቸውን ሳይቀንሱ በ 85 ዓመት የአዛውንት ጉልበታቸው አሁንም በትዕግስት አብረዋት አሉ :: ሰዎች ሚስታቸው ምን ሆና እንዲህ እንደሆነች ይጠይቃሉ “አልዛይመርስ' የመርሳት በሽታ አለባት” ሲሉ ይመልሱላቸዋል

💡እና ምንም አታስታውስም ? ምንም !ያን ሁሉ ዓመት የሕይወት ውጣውረዳችንን,ደስታችንን ሀዘናችንን ወልደን ኩለን መዳራችንን ዘመድ አዝማድን ኧረ እኔንም ዘንግታኛለች
እናም "ሚስትህ እጅህን ብትለቅህ ትጨነቃለህ ማለት ነው ?" ለምን አልጨነቅም ምንም ነገር ማንንም አታስታውስም እኮ በዚህ ዓለም ያላትን ነገሮች ሁሉ ረስታለች እኔንም ጭምር , ለብዙ አመታት አላወቀችኝም እና ያለኔ ማን አላትና ነው የማልጨነቀው ?!

💎 "እናም አንተን ባታውቅህም በየቀኑ መንገድ ላይ እየመራሃት ትቀጥላለህ" ማለት ነው ,
ፈገግ አሉና አይኖቼን እምባ ባቀረሩ አይናቸው እየተመለከቱ. "እኔ ማን እንደ ሆንኩኝ አታውቅም ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ " ውዷ ከ 60 ዓመት በላይ ብዙ ነገር የሰጠችኝ ሕይወቴ ናት " እናም ሕይወቴን ሙሉ በሄደችበት ሁሉ አብሪያት አለሁ , ሰው ካለ ህይወቱ ምን ሕይወት አለው .. እከተላታለሁ።

መልካሞችን ሁሌም ያብዛልን።

ውብ አዳር❤️

For any comments:- @fear121
@Philosophyworld1
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊