Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ @tjmma Channel on Telegram

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

@tjmma


I didn't bit the land that feeds you!

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ (Amharic)

ታላቁ ልጅ፣ ቶማስ ጀጃው ሞላ በስም እና ተከብቤው የሚጠቅመው ወይም በስምተከብቤው የተጠቅመው ታላቁ ልጅ፣ ይህ እንግሊዝ ቻናል በመከባበር ይገበያል። ልጅ ሆይ፣ ይህ ቻናል እንግሊዝ ፊኖችን እንዴት በዚህ ቻናል እንደሚገባለን ለማስተናገድ ይህን ቻናል በመጠቀም እንዲሁም ጥቅም ተጨምሯል። በቃላችን ዘራግን በመተንበረከን የታላቁ ልጁ ታሪክን ለመተንበረከን የተጋበውን መምህር ቻናሎችን ለመመልከት ይገባል። ታሪኩን ከዝግጅት እቅዱን እንድራቅል፣ ሰዎቹም በተጠቀሰው የትምህርት ዳይሬክች ማግኘት ይሰጣል።

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

20 Nov, 16:01


የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

19 Nov, 14:13


በጎንደር ዳንሻ ተንጠባጥበው በረሃ የነበሩ ታጣቂዎች ቀድመው የገቡ ወንድሞቻቸውን የሰላም መንገድ በመከተል የወጡበትን ማህበረሰብ ለመካስ በሰላም ገብተዋል። የጀግና መንገድ መርጣችኋልና ልትመሰገኑ ይገባል።

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

19 Nov, 13:39


ስሙት የጃውሳ አመራር የሚሰጠውን ትዕዛዝ። ፖሊስ ከሆነ ጨርሰው ይላል።

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

18 Nov, 11:30


የጥፋት እቅዷ በሶማሊያ በኩል ያልተሳካላት ግብፅ በሻዕቢያ በኩል ይሳካላት ዘንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ቆሞ ሊመለከት አይገባም። የሁለቱም የጥፋት ሃይሎች እቅድ ቃታ ከመሳቡ በፊት መምከን አለበት። ወደ አሰብ በገፍ እየገባ የሚገኘው የጦር መሳሪያ ለግብር ልማት ወይም በኤርትራ የሚገኙ ፍየሎችን ለመጠበቅ የሚውል ይደለም።አላማው ግልጽ ነው።

ወንድም የኤርትራ ሕዝብም በአሰብ ጉዳይ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ቆሞ ለጋራ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለሁለንተናዊ ብልጽግና ላቡን እንጅ በግብጽ ሴራ በሻዕቢያ ተላላኪነት ለውድቀት ለድህነት የሚዳርገውን የሞት መንገድ የሆነውን ጦርነት በሜዳው እንዲሆን መርጦ ከኢትዮጵያ በመቃረን ደሙን ለማፍሰስ ይሞክራል ብለን አናስብም። እንዲያውም ከባርነት ቀንበር ነፃ ወጥቶ ወደተሻለ ሕይወት ለመሸጋገር የጥፋት የድህነት ተላላኪውን ሻዕቢያ ታሪክ ለማድረግ አጋጣሚውን እንደ መልካም ዕድል ቆርጦ ከወንድም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ ታሪካዊ ኋላፊነቱን ይወጣል ብለን እናሰሰባለን። ከሻዕቢያ በላይ ጠላት የለውምና የኤርትራ ሕዝብ።

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

17 Nov, 09:10


ሐገር ወዳዱና ስልጥኑ አዲስ አበቤ 🇪🇹

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

16 Nov, 17:51


ኧሯ😂
የሆነው ሆኖ ምዕመናን ሆይ፣ በጀት በሄሊኮፕተር እንዳትደነቁ ሰማዩ በፋኖ ተመትቶ ሊወድቅ ስለሚችል እባካችሁ በያላችሁበት ሆናችሁ ባላ ይዛችሁ ትቆሙ ዘንድ በትህትና ትጠየቃላችሁ።

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

15 Nov, 12:31


በሰሜን ሸዋ በጠላት ፕሮፖጋንዳ ተደናግረው ወደ በረሃ ወጥተው የነበሩ ታጣቂዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪን በመቀበል ወደወጡበት ማህበረሰብ በሰላም ከመመለስ ባሻገር የጃውሳውን አላማ እውነቱን ለሕዝቡ እያስተማሩ ነው። ከእነዚህ መካከል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አጊራጥ ቀበሌ ሕዝባዊ መድረክ ላይ የተገኙት ታጣቂዎች ስለ ጃውሳ የሚሉትን ስሙ!

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

14 Nov, 13:28


በሙሐዘ ጥበባት Daniel Kibret

በድሮ ዘመን ሙንጣዝ የሚባል ወጠጤ ነበረ። አንዷን ልጅ በግድ ካላገባሁ ብሎ ሠፈር በጠበጠ። እሷ ደግሞ ሞቼ እገኛለሁ አላገባውም። አይመጥነኝም አለች። ዘመዶቿም በግድ አይሆንም አሉት።
ሙንጣዝም የጣልያን ዘመን ቆመህ ጠብቀኝ ይዞ ሸፈተ። እሱ በረሃ ገባ ልጂቱም አገባች።
በዚህም በዚያም እየሄደ ይበጠብጥ ጀመር። ወንድሞቿም ዙሪያውን ከብበው ከጫካ አላስወጣው አሉት።
ልጂቱም ወለደች።
ሙንጣዝም ያደዘድዝ ጀመር።
ልጂቱም ልጇን አሳድጋ ዳረች።
ሙንጣዝም ከብት ይዘርፋል፤ ሰው ይገፋል።
የልጅ ልጇም በተራዋ ልጇን አሳድጋ ዳረች።
ሙንጣዝም በንዴት ሰው ይገድላል፤ እሷን ለማግባት ሲል ሕጻናት ይደፍራል።
የልጂቱም የልጅ ልጇ በተራዋ ወለደች።
ሙንጣዝም ይፎክራል፤ ይረብሻል፤ ይበጠብጣል። መጣሁ፤ ደረስኩ፤ ላገባት ነው ይላል፡፡
የልጂቱ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጇ አገባች።
ሙንጣዝ አረረ፤ ደበነ፤ ጎፈየ፡፡ ትግሉን እየረሳ በረሃ ያገኛቸውን ሦስት አራት ሚስቶች አገባ፡፡
ሙንጣዝም ለሚስቶቹ “እናንተን ያገባሁት እርሷን ለማግባት ብዬ ነው” አዠብሎ ደሰኮረ፡፡
የልጂቱ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጇ ወለደች።
የልጅ ልጅ፣ ልጆችም እንዲህ ብለው ዘፈኑበት
ሙንጣዜ ሙንጣዜ የኔ ድብልብል
ጥጆቹ የሚያሥሩት የብረት ቃጭል