መጽሐፈ ምሳሌ 6
32፤ ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤
እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
33፤ ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥
ስድቡም አይደመሰስም።
ካላገባሃት ሴት ጋር ምታመነዝር ከሆነ አእምሮ የጎደለህ ነህ እያለህ ነው ቃሉ.. ኧረ ወራዳም ብሎሃል እና ደግሞ ለዘላለም ማይደመሰስ ስድብ ነው በአንተ ላይ ያለው.. በዚህም ነፍስህን ታጠፋለህ ይልሃል..
እንዲህ የጎደለ አእምሮ ይዘን እንዳንኖርና ነፍሳችንንም እንዳናጠፋ ጌታ ይጠብቀን.. የሳትንም ጌታ በምህርቱ ይቀበለን ዘንድ ንስሐ እንግባ..
@Apostolic_Answers