Tiriyachen | ጥሪያችን @tiriyachen Channel on Telegram

Tiriyachen | ጥሪያችን

@tiriyachen


Tiriyachen | ጥሪያችን (Amharic)

እንፀልይ! ከመሰረታዊ እንዴት አገር እየሞተ የጥሪያችን ቻናል የሚሆነውን በቀላሉ ያወቅናል? ብዙ አማርኛ ቅንጅትን ማንበብ መማር በአስተያየት ከአማራ ወጪ ጋር እንዳስተካከላቸው ይሆን? ለበአታችን ሐምሌ መሃሎትን እና ማፅዳትን ባአንቺ መሃሎት እንደሚወርድ ይገኛል! ይህ ቻናል የአማርኛ ትምህርት እንዴትንም እንጀምራለን ጥሪያችን! እባኮት አድማስ ወይም አልባስ በጣም አዳዲስ ኡናዳማችንን እና ቭኖችን ለማድረግ እንደገና ሂደቱን ሚመደብቶን ለመረቦቹ እንተኛለን። በዚህ ትምህርት ነዋሪነትን እና ሎክናውን መጠቅላችንን እንሮጣለን! እባኮትን እና ሊንክን ለመሳብ እንደሞከረ ቻናልን ለትምህርት መንስኤ እንደገና እንር ይመልከቱ! በሚል ጡመራ ፅንሆ ትምህርት እና ሎክንን ለማገኘት ሁለት ውጤትን እንጠቀማለን ወይም ጥሪትን እና ልምናትን ይሻላል።

Tiriyachen | ጥሪያችን

14 Feb, 14:48


ሦስቱ መልእክተኞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ
📜 ቁርኣን 40፥78

አምላካችን አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል። ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ አሉ፥ ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦

ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ
📜 ቁርኣን 40፥78

ስማቸው ካልተተረኩት መልእክተኞች መካከል ሦስት መልእክተኞች ወደ አንዲት ከተማ ልኳል፦

ሙሉውን ለማንበብ 👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ሦስቱ-መልእክተኞች/

Tiriyachen | ጥሪያችን

13 Feb, 16:17


አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦
”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። እነርሱም፦ "ይህ እንዴት ይሆናል? የአላህ መልእክተኛም፦ ሆይ!" አሉ። እርሳቸው፦ "ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፣ እናቶቻቸው ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው። በእኔ እና በእርሱ መካከል አንድም ነቢይ የለም" አሉ"።

📚ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 190
---------------------------------------------------------------------
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

12 Feb, 15:32


https://tiriyachen.org/ፈጣሪ-አይተኛም-አያንቀላፋም/

Tiriyachen | ጥሪያችን

12 Feb, 15:24


የአላህ ባሕርይ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 21፥22

"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ባሕርይ" ወይም "መገለጫ"description" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር "ሲፋት" صِفَات‎ ነው፦

የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 21፥22

የሰማያትና ምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ።

سُبْحَانَ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 43፥82

የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 37፥180

"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው “የሲፉነ” يَصِفُونَ ሲሆን “ባሕርይ ካደረጉለት”they attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን ከወሰፉት ሲፋህ ሁሉ የጠራ ነው። “ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስብሐት” ማለት ነው፥ “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ሲሆን አላህ ከወሰፉት የነውርና የጎደሎ ባሕርይ ማጥራት ነው። አላህ እራሱ በራሱ የእኔ ሲፋህ ይህ ነው ብሎ ከተናገረበት ውጪ ውድቅ ማድረግ ተስቢሕ ነው። እራሱን በራሱ ከገለጣቸው .....

ሊንኩን ተክተው ያንብቡ👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የአላህ-ባሕርይ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

10 Feb, 15:13


የቁርኣን አወራረድ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው።

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا
📜 ቁርኣን 17፥106

“ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ሲሆን “ተንዚል” تَنزِيل ማለት ደግሞ “የተወረደ”Revelation” ማለት ነው፤ ሁለቱም ቃላት “አንዘለ” أَنْزَلَ ወይም “ነዝዘለ” نَزَّلَ ማለትም “አወረደ” ወይም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጡ ናቸው። የቁርኣን አወራረዱ ሁለት አይነት ነው፤ አንዱ በጠቅላላ አንድ ጊዜ ከለውሐል መሕፉዝ ማለትም ከተጠበቀው ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ሲሆን ሁለተኛው ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ ቀስ በቀስ ለ 23 ዓመት ወረደ፤ ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እንመልከት።
የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወደ እልቅና ቤት የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ቁርኣን በዚህ ወር ውስጥ በአንድ በተባረከች ሌሊት በጠቅላላ አንድ ጊዜ ወርዷል፥ ይህም አወራረድ “ጁምለተን ዋሒዳህ” جُمْلَةً وَاحِدَةً ይባላል፦

ሙሉወን ያንብቡ ይማርበታል👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የቁርኣን-አወራረድ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Feb, 14:22


ሐዲስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
📜ቁርኣን 59፥7

"ሐዲስ" حَدِيث የሚለው ቃል "ሐደሰ" حَدَّثَ‎ ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንግግር" ማለት ነው፦

"ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?"

أَفَمِنْ هَـٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ
📜ቁርኣን 53፥59

እዚህ አንቀጽ ላይ "ንግግር" ለሚለው የተቀመጠው ቃል "ሐዲስ" حَدِيث መሆኑ ልብ በል። እዚህ ድረስ የሐዲስ ቃል ምን ማለት እንሆነ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ነቢያችን"ﷺ" በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ወሕይ ነው፦

ሙሉውን ያንብቡ
https://tiriyachen.org/ሐዲስ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

07 Feb, 15:25


ኢሥቲሥላም


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

"በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"

أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ
📜 ቁርኣን 3፥83

"ኢሥቲሥላም" اِسْتِسْلَام የሚለው ቃል "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" ለሚለው መስደር ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” ማለት ነው። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦

"በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"

أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ
📜 ቁርኣን 3፥83


ገበተው ሙሉውን ያንብቡት 👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ኢሥቲሥላም/

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Feb, 14:51


መገለጥ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡

إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
ቁርኣን 20፥14

“ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት” አሊያም "መለኮታዊ ራእይ"Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ለነቢያት ግልጠት ይገልጥላቸዋል፦

"እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም "አወረድን"፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም "አወረድን"፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
ቁርኣን 4፥163

"አወረድን" ለሚለው ቃል የገባው "አውሐይና" أَوْحَيْنَا ሲሆን "አውሓ” أَوْحَىٰٓ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ገለጥን" ማለት ነው። አላህ ለነቢያት ስለራሱ ማንነት የሚገልጠው ........

ሙሉውን ያንብቡ 👇🏻
https://tiriyachen.org/መገለጥ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

05 Feb, 16:29


https://tiriyachen.org/የነቢያችንﷺ-ነቢይነት/

Tiriyachen | ጥሪያችን

05 Feb, 14:35


7. አሳማ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ *የአሳማንም* ስጋ፣ ያንንም በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ አመጸኛም ወሰን አላፊም ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ ۖ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

8. አሳ
37፥142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን *አሳው* ዋጠው፡፡ فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ

ሐ. በራሪ ፍጥረት

1. ሁድሁድ
27፥20 በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም *«ሁድሁድን* ለምን አላየውም! በእውነቱ ከራቁት ነበርን፡፡ وَتَفَقَّدَ الطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِيَ لَا أَرَى الْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ الْغَائِبِينَ

2. ወፍ
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ *ወፍ* ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

3. ቁራ
5፥31 የወንድሙንም ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር *ቁራን* ላከለት፡፡ «ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ከጸጸተኞችም ኾነ፡፡ فَبَعَثَ اللَّهُ غُرَابًا يَبْحَثُ فِي الْأَرْضِ لِيُرِيَهُ كَيْفَ يُوَارِي سَوْءَةَ أَخِيهِ ۚ قَالَ يَا وَيْلَتَىٰ أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَـٰذَا الْغُرَابِ فَأُوَارِيَ سَوْءَةَ أَخِي ۖ فَأَصْبَحَ مِنَ النَّادِمِينَ

4. ቢራቢሮ
101፥4 ሰዎች እንደ ተበታተነ *ቢራቢሮ* በሚኾኑበት ቀን። يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوث

5. ንብ
16፥68 ጌታህም ወደ *ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

6. ዝንብ
22፥73 እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው ጣዖታት *ዝንብን* ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን ለመፍጠር ቢሰበሰቡም እንኳን አይችሉም፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَن يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ

7. አንበጣ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ *አንበጣንም* ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

8. ትንኝ
2፥26 አላህ ማንኛውንም ነገር *ትንኝንም* ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

መ. ነፍሳት

1. ነቀዝ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም *ነቀዝንም* እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

2. ሸረሪት
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን ጣዖታትን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች *ሸረሪት* ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

3. ጉንዳን
27፥18 በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ *ጉንዳኖች* ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

4. እንቁራሪት
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም *እንቁራሪቶችንም* ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

05 Feb, 14:35


እንስሳት እና ነፍሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥26 *”አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

አምላካችን አላህ እኛም ለማስተማር የቤት እንስሳትን፣ የዱር እንስሳትን በራሪ ፍጥረትን፣ ነፍሳትን በቅዱስ ቃሉ አውስቷል። ከትንሿ ትንኝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ዝሆን ድረስ ምሳሌ እያደረገ አውስቷል፦
2፥26 *አላህ ማንኛውንም ነገር “ትንኝንም” ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

ሀ. የቤት እንስሳት

1. ፈረስ
38፥32 አለም «እኔ ፀሐይ በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ *ፈረስን*! መውደድን መረጥኩ፡፡» فَقَالَ إِنِّي أَحْبَبْتُ حُبَّ الْخَيْرِ عَن ذِكْرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتْ بِالْحِجَابِ

2. አህያ
62፥5 የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት ያልሠሩባት ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም *አህያ* ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ حُمِّلُوا التَّوْرَاةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ الْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًا ۚ بِئْسَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

3. በቅሎ
16፥8 ፈረሶችንም፣ *በቅሎዎችንም*፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

4. ላም
2፥69 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ *ላም* ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا لَوْنُهَا ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ صَفْرَاءُ فَاقِعٌ لَّوْنُهَا تَسُرُّ النَّاظِرِينَ

5. ግመል
88፥17 ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ *ግመል* እንዴት እነደተፈጠረች! أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

6. ከብት(በሬ)
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ *የከብት*፣ የበግና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

7. በግ
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ *የበግ* እና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

8. ፍየል
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ የበግና *የፍየል* እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

9. ውሻ
7፥176 በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ *ውሻ* ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡ وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَـٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ለ. የዱር እንስሳት

1. ዝሆን
105፥1 *በዝሆኑ* ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ

2. አንበሳ
74፥51 *ከአንበሳ* የሸሹ፡፡ فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍ

3. ተኩላ
12፥13 «እኔ እርሱን ዩሱፍን ይዛችሁ መሌዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡ እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ *ተኩላ* ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ» አላቸው፡፡ قَالَ إِنِّي لَيَحْزُنُنِي أَن تَذْهَبُوا بِهِ وَأَخَافُ أَن يَأْكُلَهُ الذِّئْبُ وَأَنتُمْ عَنْهُ غَافِلُون

4. የሜዳ አህያ
74፥50 እነርሱ ልክ ደንባሪዎች *የሜዳ አህዮች* ይመስላሉ፡፡ كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ

5. እባብ
7፥107 በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ *እባብ* ኾነች፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

6. ዝንጀሮ
7፥166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች *ዝንጀሮች* ኹኑ አልን፤» ኾኑም፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ

Tiriyachen | ጥሪያችን

04 Feb, 15:15


የመላእክት ጋብቻ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውኃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ
📜 ቁርኣን 29፥14

አምላካችን አላህ”ﷻ” ኑሕ የሚባለውን መልእክተኛ የላከው፥ የኑሕ ሕዝቦች ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም የተባሉትን አማልክት ያመልኩ ስለነበር እና ያንን ሺርክ ትተው እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ ጥሪ እንዲያደርግ ነው፦

ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! “አላህን አምልኩ፡፡ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም”፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»

لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
📜 ቁርኣን 7፥59

አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡

وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا
📜 ቁርኣን 71፥23

ሙሉውን ያንብቡ
https://tiriyachen.org/የመላእክት-ጋብቻ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

03 Feb, 16:19


የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም)
ከርሱ የሆነ መንፈስ
------------------------------
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡ (አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

🔹ከርሱ የኾነ መንፈስ፡-

"እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው…"
📜 (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡171)

ባለፈው ‹‹ከርሱ በሆነው ቃል›› የሚለውን አንስተን፡ በዚህ ዙሪያ የሚነሱ ብዥታዎችን በአላህ ፈቃድ ለማጥራት የተወሰነ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ዛሬም የአላህ ፈቃዱ ከሆነ ‹‹ከርሱ የሆነ መንፈስ›› በሚለው ላይ መጠነኛ ቆይታ እናደርጋለን ኢንሻአላህ፡፡


ገብተው ሙሉውን ያንብቡ ይማሩበታል
https://tiriyachen.org/የመርየም-ልጅ-ዒሳ-ዐለይሂ-ሰላም-2/

Tiriyachen | ጥሪያችን

02 Feb, 16:26


የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም)
"ከርሱ በሆነ ቃል"

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡
📜 (አል-ፋቲሓ 2)

ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ
📜 (አል-አሕዛብ 56)

ለመላው የአላህ መልክተኞች
📜 (አል-ሷፍፋት 181)

የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን
📜 (ጣሀ 47)

1/ ከርሱ በሆነው ቃል፡-

"መላእክት ያሉትን (አስታዉስ) ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ (ልጅ) ያበስረሻል"
📜 (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 45)፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ ‹‹ከርሱ በሆነ ቃል›› የሚለውን በመምዘዝ፡ ወገኖቻችን:- ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) የአላህ ቃል ነውና አምላክ መሆን አለበት ይሉናል፡፡ ለዚህ የተሳሳተ ግንዛቤ የምንሰጠው ምላሽ የሚከተለው ይሆናል፡-
ሀ/ አምላካችን አላህ ማንኛውንምን ነገር መፍጠር ከፈለገ፡ ‹‹ሁን›› በሚለው መለኮታዊ ቃሉ አማካኝነት መፍጠርና ማስገኘት ይችላል፡፡ ይህ ፍጥረትና ግኝት ግን የ ”ይሁን” ቃሉ ውጤት እንጂ: እራሱ ቃል ተብሎ አይጠራም፡፡ ምክንያቱም የተገኘው ‹‹ሁን›› በሚለው መለኮታዊ ቃል አማካኝነት በመሆኑ!!
አላህ በመለኮታዊ ቃሉ አማካኝነት አንድን ነገር ይፈጥራል፣ ያስገኛል፣ ይሰራል እንጂ፡ ይህ መለኮታዊ ቃል እራሱ የተፈለገውን ነገር ሁኖ አይፈጠርም፣ አይሰራም፣ አይገኝምም፡፡ የአላህ ቃል፡ የራሱ የአላህ አንድ መለኮታዊ ባሕሪ እንጂ: ፍጥረትና ግኝት አይደለምና፡፡ ይህንን ሀሳብ የሚገልጹ የተወሰኑ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችን እንመልከት፡-

ሙሉዉን ለማንበብ 👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የመርየም-ልጅ-ዒሳ-ዐለይሂ-ሰላም/

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Feb, 16:03


2. ተቅሊድ
‎ “ተቅሊድ” تَقْلِيد ማለት ዐላዋቂ የሆነ ሰው ከዐዋቂዎች የሚወስደው ነገር “ተቅሊድ” ይባላል፤ ይህ ሰው ደግሞ “ሙቀሊድ” مُقَلِّد ይባላል።

3. ተክሊፍ
“ተክሊፍ” تَكْلِيف‎ ማለት ቁርኣንን እና ሐዲስን መመሪያ አድርጎ የሚሠራ፥ በእነርሱ ትእዛዝ አዛዡንም ለይቶ ማወቅ ነው። ለምሳሌ ሶላት ስገድ ከተባለ ሰላት ትእዛዝ ነው ይተገብራል፥ ስለዚህ የታዘዘውን መተግበር እንጂ የራሱን ጥረት አያደርግም ሌላ ተጨማሬ ነገር ለማወቅ።

4. ተክፊር
“ተክፊር” تَكْفِير‎ ማለት ከእሥልምና ማስወጣት ሲሆን የተለያየ ሁጃ ደሊል ሊገኝበት ከቻለ አህሉል ዒልም የሚወስነው እርምጃ ነው። እርምጃውን የሚወስነው አካል “ሙከፊር” مكفر‌‎ ሲባል የካደው ሰው “ካፊር” كَافِر‎ በብዜት “ኩፋር” كُفَّار ይባላል። ድርጊቱ “ኩፍር” كُفْر‎ ይሰኛል።

5. ፈትዋ
“ፈትዋ” فَتْوَى‎ የሚለው ቃል “አፍታ” أَفْتَى ማለትም “አደረሰ” ወይም”ወሰነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መደበኛ ውሳኔ” ማለት ሲሆን ይህንን ብይን የሚሰጥ አካል “ሙፍቲ” مُفْتٍ‎ ይባላል።

6. ዓዳህ
“ዓዳህ” عَادَة የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ‎ ማለትም “ለመደ” “አወጋ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ልምድ” “ባህል” “ወግ” ማለት ነው። “ዓዳት” عَادَات‎ ደግሞ የዓዳህ ብዙ ቁጥር ነው። በፊቅህ ነጥብ ውስጥ “ዓዳህ” የሚባል እሳቤ አለ። በአንተ እና በአላህ መካከል ያለው አምልኮ ውስጥ አዲስ ነገር ከጨመርን ቢድዓ ይባላል። በእኔ እና በአንተ መካከል ግን ምንም አዲስ ነገር ጥሩ ከሆነ ዓዳህ ነው።

7. ኢሥትድላል
“ደሊል” دَلِيل ማለት “ማስረጃ” ማለት ሲሆን ይህ ሂደት “ኢሥትድላል” اِسْتِدْلَال ይባላል። ቁርኣንን እና ሐዲስ ማስረጃ አርጎ ማስረዳት ኢሥትድላል ነው።

8. ኢሥቲሕሣን
“ኢሥቲሕሣን” ‏اِسْتِحْسَان‎ ማለት ደግሞ መዝሀቦችን መርጦ ሐሰን የሆኑትን ነገሮች በቂያሥ ወስዶ እና በጥሩ መልኩው በራሳቸው ማስቀመጥ ነው። የሚያስቀምጡ እነዚህ የመዝሀብ ሰዎች ናቸው። “መዝሀብ” مَذْهَب‎ ማለት በነጠላ ሲሆን በብዜት “መዛሂብ” مذاهب ሲሆን “የድርጊት መንገድ”school of thought” ማለት ነው። ልክ አንድ ጥጃ ከአራት ጡቶች መርጦ እንደሚጠባ ሁሉ ይህም ሰው አንዱን ወስዶ ይቀስማል፥ እነዚህ መዛሂብ፦
1. የኢማም አቡ ሃኒፋን ግንዛቤ የሚከተል “ሐነፊይ” حنفي‌‎ መዝሃብ ነው።
2. የኢማም ኢብኑ ኢድሪስ ሻፊዕ ግንዛቤ የሚከተል “ሻፊዕይ” شافعي‌‎ መዝሃብ ነው።
3.የኢማም ማሊክ ኢብኑ አነሥ ግንዛቤ የሚከተል “ማሊኪይ” مالكي‌‎ መዝሃብ ነው።
4. የኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ግንዛቤ የሚከተል “ሐንበሊይ” حنبلي መዝሃብ ነው።

ይህንን የፊቂህ እሳቤ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ለማስቀመጥ ሳይሆን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል መሰናዶ ነው። አምላካችን አላህ"ﷻ" እርሱ ባወረደው ሑክም የምንመራና የምፈርድ ያድርገን! አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Feb, 16:03


ፊቅህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

"ፊቅህ" فِقْه‎ የሚለው ቃል "ፈቂሀ" فَقِهَ‎ ማለትም "ተረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥልቅ መረዳት" ማለት ነው፦
6፥98 እርሱም ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ ነው፡፡ በማሕፀን መርጊያና በጀርባ መቀመጫም አላችሁ፡፡ *"ለሚያወቁ" ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ فَمُسْتَقَرٌّ وَمُسْتَوْدَعٌ ۗ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَفْقَهُونَ

“ሚያወቁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የፍቀሁነ” يَفْقَهُونَ ሲሆን “ሚረዱ” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ነው። "ፊቅህ" فِقْه‎ የሚለው እሳቤ ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ማለት ነው። ይህንን ሕግ የሚያጠና ምሁር በነጠላ "ፈቂህ" فَقِيه‎ ሲባል በብዜት "ፉቀሃእ" فُقَهَاء‎ ይባላል። አንድ ዐሊም የሚያጠናው ሕግ "ሸሪዓህ" ይባላል፥ "ሸሪዓህ" شَرِيعَة ማለት "ትክክለኛ ሕግ" ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ *በትክክለኛይቱ ሕግ* ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُون

"ትክክለኛይቱ ሕግ" ለሚለው ቃል የገባው "ሸሪዓህ" شَرِيعَة የሚል ነው፥ ይህም ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም "ሕግ" ከሚል ቃል የመጣ ነው፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” مَنْهَج ማለት ነው። አምላካችን አላህ"ﷻ" ለሁሉም መልእክተኞች በዘመናቸው ሸሪዓህ እና መንሃጅ ማድረጉን ያሳያል። “ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፥ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው። “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን "ሕግጋት" ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።

እነዚህ ሕግጋት ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መሠረት ብቻ ዒባዳህ ይፈጸማል። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” اِتِّبَاع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን "ተከተሉ"*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” اِتِّبَاع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፥ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒሕ ሐዲስ ነው። “ቢድዓህ” بِدْعَة ማለት ደግሞ “ኢብተደዐ” ٱبْتَدَعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቢድዓህ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው።

እነዚህ አምስቱ ሕግጋት የተዋቀረበት ውቅር ደግሞ አራት ናቸው፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ቁርኣን” قُرْءَان የአምላካችን የአላህ"ﷻ" ንግግር ነው።
2ኛ. “ሡናህ” سُنَّة‎ የነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ ነው።
3ኛ. “ቂያሥ” قِيَاس ዐሊሞች የሚያመዛዝኑበት “ማመጣጠን”Analogy” ነው።
4ኛ. “ኢጅማዕ” إِجْمَاع‎ የምሁራን ስምምነት “ሲኖዶስ”acadamic agreement” ነው።

አንድ ነገር ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ፈርድ ነው? ሙስተሐብ ነው? ሙባሕ ነው? መክሩህ ነው? ሐራም ነው? የሚለው ይታያል። እዚያ ላይ ከሌለ በቂያሥ ይታያል፥ ለምሳሌ "ቢራ" የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ባይኖርም ሐራም መሆኑ "ኸምር" በሚል ቂያሥ ይደረጋል። ቂያስ ማድረጉ በግል ደረጃ ከከበደ በኢጅማዕ በያን ይደረጋል።
ምን አለፋን “ፊቅህ” ሰፊ አርስት ነው፥ በውስጡ፦ ኢጅቲሀድ፣ ተቅሊድ፣ ተክሊፍ፣ ተክፊር፣ ፈትዋ፣ ዓዳህ፣ ኢሥትድላል፣ ኢሥቲሕሣን የመሳሰሉትን ከባባድ እሳቦት ይዟል። እነዚህን በግርድፉና በሌጣው እንያቸው፦

1. ኢጅቲሀድ
“ኢጅቲሀድ” اِجْتِهَاد‎ ማለት ቁርኣንን እና ሡናን ባማከለ ሁኔታ የሚደረግ “ፍለጋ” “ጥረት” ወይም “ግኝት” ኢጅቲሀድ ይባላል፥ ዐዋቂ ሆኖ የሚጥረው፣ የሚፈልገው፣ የሚያስሰው ሰው ደግሞ “ሙጅተሂድ” مُجْتَهِد ይባላል።

Tiriyachen | ጥሪያችን

31 Jan, 17:02


የኢሥላም መልእክት ላልደረሳቸው በሙሉ!!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡
📜 (አል-ፋቲሓ 2)

የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ
📜 (አል-አሕዛብ 56)

ለመላው የአላህ መልክተኞች
📜 (አል-ሷፍፋት 181)

የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን
📜 (ጣሀ 47)

ሙሉውን ያንብቡ👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የኢሥላም-መልእክት-ላልደረሳቸው-በሙሉ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

31 Jan, 16:11


በህይወት ያለው ከሞተው አይበልጥም!!


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
የማያጠግብ እንጀራ ባይበላ ይቅር! እንዲሉ ሆነና፡ እንኳን በአላህ አንድነት ላይ እምነቱን ላጸናው ሙስሊም ይቅርና ከሃይማኖት እሳቤ ገለልተኛ ሆኖ በንጹህ ህሊናው የሚያስብን ሰው ማሳመን የማችል የወረደ አስተሳሰብ ነው፡፡
እሱም፡- የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሙስሊሞች እንደምትሉት ካልሞተና አላህ ወደራሱ ከወሰደው፡ በዛው ተቃራኒ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሞቱና ከተቀበሩ፡ በርግጥም ዒሳ በደረጃ ይበልጣቸዋል ማለት ነው!!፡፡ እንደገናም እሱ የአላህ ልጅ መሆን አለበት ማለት ነው! የሚል ነው፡፡ ለዚህ የተሳሳተ አስተሳሰብ እርምትን ለሚሻ ሰው በአላህ ፈቃድ መጠነኛ ምላሽን እንካችሁ ብያለሁ፡፡ ወማ ተውፊቂ ኢልላ ቢላህ (የመልካም ነገር ሁሉ ገጠመኝ ከአላህ እንጂ ከማንም አይደለም)፡፡

ሙሉውን ያንብቡ👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/በህይወት-ያለው-ከሞተው-አይበልጥም/

Tiriyachen | ጥሪያችን

29 Jan, 16:24


ውሸት ይፈቀዳልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡

فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ
📜 ቁርኣን 22፥30


ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፥ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትንም ቃል መራቅ አለበት፦

እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ።

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
📜 ቁርኣን 33:70

ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡.......

ሙሉውን ያንብቡ👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ውሸት-ይፈቀዳልን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

28 Jan, 15:15


የአላህ ዙፋን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር።

وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍۢ وَكَانَ عَرْشُهُۥ عَلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۗ وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِنۢ بَعْدِ ٱلْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ
📜 ቁርኣን 11፥7

መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ተስተምህሮት ዶግ አመድ ቢሆንላቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነው፤ ሂስ የሙግት አንዱ ክፍል ቢሆንም የሚሽነሪዎች ሂስ ግን ማሸሞር፣ ማነወር እና ስላቅ ነው፤ ይህ ደግሞ ጡዘቱ ጣራ የነካና ዙሪያ ገባ ነው፤ ከእነርሱ ቅንነት የተሞላው መልስ መጠበቅ ማለት ከጅብ አፍ ላይ ስጋ እንደመጠበቅ ነው። እነርሱ የሚሰጡት ትችት እኛ ሙስሊሞችን የሚያፍረከርክ ሳይሆን ከእለት ወደ እለት የሚያጀግን ነው፤ ለማንኛውም የተነሳውን ትችት አብጠርጥረን እና አንጠርጥረን እንመልከት፦ “የአላህ ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ የሰይጣንም ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ ስለዚህ የሁለቱም ዙፋን አንድ ነው” በማለት ሊያምታቱ ይሞክራሉ።..............


ሙሉውን ለማንበብ 👇🏻
https://tiriyachen.org/የአላህ-ዙፋን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

27 Jan, 15:13


ጀነት የሚገቡት እነማን ናቸው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“እነዚያ ያመኑ፣ እነዚያም ይሁዳውያን የኾኑ፣ ክርስቲያኖችም፣ ሳቢያኖችም ”በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው”፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፡፡

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالنَّصَارَىٰ وَالصَّابِئِينَ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَعَمِلَ صَالِحًا فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
📜ቁርኣን 2፥62

በጌታቸው ዘንድ ምንዳ ያላቸው ይሁዳውያን፣ ክርስቲያን እና ሳቢያን “መን” مَنْ በሚል አንጻራዊ ተውላጠ-ስም ተለይተዋል። እነዚህም በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመኑና መልካምንም ሥራ የሠሩ ናቸው። “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን” ማመን የኢማን ማዕዘናትን ያቅፋል፥ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ማመን መካከል በመላእክቱም፣.....

ሙሉውን ለማንበብ 👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ጀነት-የሚገቡት-እነማን-ናቸው/

Tiriyachen | ጥሪያችን

26 Jan, 15:34


ቀሪን
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል"፡፡

إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ
📜ቁርኣን 15፥95

የአእምሮ ስንኩላን ከትልቅ እስለ ደቂቅ ያለ አንዳች ከልካይ የባልቴት የቡና ወሬ ሲነዙ ማየት ዐላዋቂነትን ከማሳበቅ ውጪ አንዳች የሚፈይዱት ነገር የለም። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ስለ ቀሪን የተነሳውን የወይዛዝርት የቡና ወሬ በትክክለኛ የአስተላለፍና የአስነዛዘር ሙግት እንሞግታለን። "ቀሪን" قَرِين የሚለው ቃል 8 ጊዜ በቁርኣን የተጠቀሰ ሲሆን "ጓደኛ" ማለት ነው፦

ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል፦ "እኔ ጓደኛ ነበረኝ"፡፡

قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ
📜ቁርኣን 37፥51

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሪን" قَرِين የተባለበው ሰው ለሰው "ጓደኛ" በሚሆንበት ስሌት ነው። ስለዚህ "ቀሪን" ማለት "ሸይጧን" ማለት ሳይሆን "ጓደኛ" ማለት ብቻ ነው። ለምሳሌ ሥራችንን የሚመዘግቡ መልአክ "ቀሪን" قَرِين ተብለዋል፦ ........

ሙሉውን ለማንበብ 👇🏻
https://tiriyachen.org/ቀሪን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

25 Jan, 14:47


ሰባው ሱባዔ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡

وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
📜 ቁርኣን 3፥78

ነጥብ ሦስት
“አንድ ሱባዔ”

“እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል”።
📜 ዳንኤል 9፥27

“እርሱም” የሚለው ተውላጠ-ስም “የሚመጣው አለቃ” የሚለውን ተክቶ የመጣ ተውላጠ-ስም ነው፦ ........

ሙሉውን ያንብቡ 👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ሰባው-ሱባዔ-2/

Tiriyachen | ጥሪያችን

25 Jan, 14:30


ሰባው ሱባዔ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡

وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

📜 ቁርኣን 3፥78
ነቢዩ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ ያህዌህ በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋለ፦ ......

ሙሉውን ለማንበብ
https://tiriyachen.org/ሰባው-ሱባዔ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

24 Jan, 16:02


8+11=19 ይሆናል። ከምርኮ መጀመር ከ 605 ላይ19 ዓመት ሲቀነስ 586 ይሆናል፥ 605−19=586 ይሆናል። በዚህ ጊዜ ኢየሩሳሌምን ስለ መጠገን እና ስለ መሥራት ቃሉ ወደ ኤርሚያስ መጣ፦
ኤርምያስ 1፥3 በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ *"አሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ *"የእግዚአብሔር ቃል መጣ"*።

ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ቃሉ የመጣው ከተማይቱ በፈረሰችበት በ 586 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ቃሉ ከመጣበት እስከ አለቃው መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል፥ ቅድሚያ ለምን 7 ሱባዔ እንደቀደመ እና እንደተቀመጠ የክርስትና ምሁራን አጥጋቢ መልስ የላቸውም። አንድ ሱባዔ 7 ዓመት ከሆነ 7 ሱባዔ 49 ዓመት ይሆናል። 7×7=49 ይሆናል። ከ 586 ቅድመ-ልደት"BC" 49 ዓመት ስንቆጥር 537 ይሆናል፥ 586-49= 537 ይመጣል።
በ 537 ቅድመ-ልደት"BC" እግዚአብሔር በኤርምያስም አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ ቂሮስን አስነሣ፦
ዕዝራ 1፥1 *"በኤርምያስም አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ"*።

ይህ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ከመወለዱ ከ 200 ዓመት በፊት ያህዌህ የሚቀባው መሢሕ እንደሆነ ተተንብዮለታል፦
ኢሳይያስ 45፥1 *"እግዚአብሔር፦ "ለመሢሑ לִמְשִׁיחוֹ֮ ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ "አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት"*።
"This is what the LORD says to his anointed, to Cyrus, whose right hand I take hold of to subdue nations before him and to strip kings of their armor, to open doors before him so that gates will not be shut: NIV

"መሺሆው" ִמְשִׁיחוֹ֮ ማለት "የእርሱ መሢሕ" ማለት ነው፥ ይህም የሚያሳየው አለቃው ቂሮስ የያህዌህ መሢሕ መሆኑን ነው። አለቃውም መሢሕም እርሱ ነው።

ነጥብ ሁለት
"ስድሳ ሁለት ሱባዔ"
ዳንኤል 9፥25 *ከዚያም በስድሳ ሁለት ሱባዔ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ጎዳና እና ከቅጥር ጋር ትሠራለች"*። וְשָׁבֻעִים שִׁשִּׁים וּשְׁנַיִם, תָּשׁוּב וְנִבְנְתָה רְחוֹב וְחָרוּץ, וּבְצוֹק, הָעִתִּים.

"ከዚያም" የሚለው ቅድመ ተከተል የጊዜ ሳይሆን የንግግር ቅድመ ተከተል ነው። "የጭንቀ ዘመን" የተባለው ምርኮ የሚጀምርበት ቀን ነው፥ ይህ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን ነው፥ በዚህ የጭንቀት ዘመን ከተማይቱ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት፦
ሶፎንያስ 1፥15 ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን።
ሰቆቃው ኤርምያስ 1፥1 አሌፍ። *"ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች"*!
ሰቆቃው ኤርምያስ 1፥3 ጋሜል። *"ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች"*፤ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፤ *"የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት"*።

"ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" ከተማይቱ ተማረከች፥ የጭንቀቱ ዘመኗ ጀመረ። ከ 605 ጀምረን 62 ሱባዔ ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት"BC" ይሆናል። ቅድሚያ 62 ሱባዔ 434 ዓመት ነው፥ 62×7=434 ይሆናል።
እንግዲህ ከምርኮ 605 ጀምሮ 434 ዓመት ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። 605-434=171 ይሆናል። በዚህ ጊዜ የተገደለ መሢሕ አለ፦
ዳንኤል 9፥26 *"ከስድሳ ሁለት ጊዜ በኋላ መሢሕ ይገደላል"*፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም።

ዳንኤል 9፥26 ላይ "ሰባት" የሚል ቃል የለም። የዕብራይስጡን ማየት ይቻላል። ስድሳ ሁለት ሱባዔ ሲያልቅ የተቀባው ሊቀ-ካህን ሣልሳዊ "አንያስ" ተገሏል፦
ዳንኤል 11፥22 የሚጐርፍም ሠራዊት ከፊቱ ይወሰዳል፥ እርሱ እና *"የቃል ኪዳኑ አለቃ ይሰበራሉ"*።

አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ በ 171 ቅድመ-ልደት የተቀባው ሊቀ-ካህን ሣልሳዊ "አንያስን" አስገድሎታል። "ማሺአሕ" מָשִׁ֣יחַ ማለት "የተቀባ" ማለት ሲሆን ይህ ቃል 39 ጊዜ ብሉይ ኪዳን ላይ ለተለያየ ካህን፣ ንጉሥ እና ነቢይ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ዘሌዋውያን 4፥3 *የተቀባውም* הַמָּשִׁ֛יחַ ካህን በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኃጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።

"ማሺአሕ" מָשִׁ֣יחַ የሚል ቃል በተገኘ ቁጥር ለወደፊት ከዳዊት ቤት ለሚመጣው ንጉሥና ነቢይ ነው ብሎ ማለት ቂልነት ነው። ኢንሻላህ ይቀጥላል......

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

24 Jan, 16:02


ሰባው ሱባዔ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ነቢዩ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ ያህዌህ በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋለ፦
ዳንኤል 9፥2 እኔ ዳንኤል *የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ እግዚአብሔር በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋልሁ*።

የባቢሎን ምርኮ 70 ዓመት የሚጀምረው በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ዮአኪንንን እና የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር ባስወሰደ ጊዜ ነው፦
2 ዜና 36፥9-10 *"ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአሥራ ስምንት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ። ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ"*።

ከዚህ ከ 605 ጀምረን 70 ዓመት ስንቆጥር 535 ቅድመ-ልደት"BC" ይሆናል፥ ከዚያ በኃላ ነቢዩ ዳንኤል የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋለ። በዚህ ጊዜ ገብርኤል ለዳንኤል፦ "በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል" አለው፦
ዳንኤል 9፥24 ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ *"በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል"*።

"ሱባዔ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ሻቡኢም" שָׁבֻעִ֨ים ሲሆን "ሳምንታት" ማለት ነው፥ "ሻቡአ" שְׁבוּעַ ማለት "ሳምንት" ወይም "ሰባት" ማለት ነው። "ሰባ ሱባዔ" ማለት "ሰባ ሳምንት" ማለት ነው፥ አንድ ሳምንት ሰባት ቀናት ናቸው። ስለዚህ 70×7= 490 ይሆናል። ይህ ሰባ ሱባዔ በዳንኤል ሕዝብ እና በቅድስት ከተማ ላይ የተቆጠረ ስሌት ነው። ይህ ሰባ ሱባዔ ለሦስት ይከፈላል፥ እነርሱም 7 ሱባዔ፣ 62 ሱባዔ እና 1 ሱባዔ ይሆናል። ይህ 7+62+1=70 ሱባዔ ይሆናል። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሰባት ሱባዔ"
ስለ ኢየሩሳሌምን መጠገን እና መሥራት ቃሉ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል፦
ዳንኤል 9፥25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ *"ኢየሩሳሌምን ስለ መጠገን እና ስለ መሥራት ቃሉ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል"*። ከዚያም በስድሳ ሁለት ሱባዔ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ጎዳና እና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
וְתֵדַע וְתַשְׂכֵּל מִן-מֹצָא דָבָר, לְהָשִׁיב וְלִבְנוֹת יְרוּשָׁלִַם עַד-מָשִׁיחַ נָגִיד--שָׁבֻעִים, שִׁבְעָה; וְשָׁבֻעִים שִׁשִּׁים וּשְׁנַיִם, תָּשׁוּב וְנִבְנְתָה רְחוֹב וְחָרוּץ, וּבְצוֹק, הָעִתִּים.
English Standard Version
Know therefore and understand that from the going out of the word to restore and build Jerusalem to the coming of an anointed one, a prince, there shall be seven weeks. Then for sixty-two weeks it shall be built again with squares and moat, but in a troubled time.

የዕብራይስጡን ያመጣሁት ምክንያት 7 እና 62 ቁልጭ አርጎ ስለሚለይ ነው። "ሌ" לְ ማለት "ስለ" ማለት ነው፥ ስለ ኢየሩሳሌምን መጠገን እና መሥራት ቃሉ ወጥቷል። "ዳባር" דָבָ֗ר ማለት "ቃል" ማለት ነው። ይህ ቃል የወጣው ከፈጣሪ ሲሆን በነቢዩ ኤርሚያስ በኩል ነው፦
ኤርምያስ 29፥10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ *"ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ *"እመልሳችሁ"* הָשִׁיב֙ ዘንድ መልካሚቱን "ቃሌን" דְּבָרִ֣י እፈጽምላችኋለሁ።

"ቃሌ" ለሚለው ቃል የገባው "ዳባሪ" דְּבָרִ֣י ሲሆን "የዳባር አገናዛቢ መደብ ነው። "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ማለት "እመልሳለው" ማለት ሲሆን ዳንኤል ላይ "መጠገን" ለሚለው የገባው ቃል "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ነው፥ "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ማለት "ሹብ" שׁוּב "መመለስ" ማለት ነው፦
ኤርሚያስ 29፥14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም *"እመልሳለሁ"* וְשַׁבְתִּ֣י ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ "እመልሳችኋለሁ" הֲשִׁבֹתִ֣י ።

"እመልሳለሁ" ለሚለው ቃል "ሸብቲ" שַׁבְתִּ֣י የሚለው ቃል መግባቱ አስተውል። "እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ "እመልሳችኋለሁ" የሚለው ይህንኑ ታሳቢ ያረገ ነው።
ኢየሩሳሌምን "መሥራት" ለሚለው ቃል የገባው "ሊብኖውት" לִבְנ֤וֹת ሲሆን ይህም ቃል በኤርሚያስ በኩል ወጥቷል፦
ኤርምያስ 30፥18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ *"ትሠራለች"* נִבְנְתָ֥ה ፥ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።

"ኒብናታህ" נִבְנְתָ֥ה ማለት "ትሠራለች" ማለት ነው። እዚህ ጋር መያዝ ያለብን ነጥብ በነቢዩ ኤርሚያስ ስለ መመለስ እና ስለ መሥራት ቃል ከያህዌህ የመጣበት ጊዜ በ 586 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" ዮአኪንን ማርኮ ከ 8 ዓመት በኃላ ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የአሻንጉሊት መንግሥት አነገሠ፥ ሴዴቅያስ በነገሠ በ 11 ዓመት ኢየሩሳሌም አፈረሱ፦
2 ነገሥት 25፥2 *ከተማይቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ አሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር*።
2 ነገሥት 25፥8 *በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በአሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባሪያ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ*።
2 ነገሥት 25፥10 *ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ዙሪያዋን አፈረሱ*።

Tiriyachen | ጥሪያችን

23 Jan, 15:05


https://tiriyachen.org/የዒሣ-አፈጣጠር/

Tiriyachen | ጥሪያችን

22 Jan, 15:51


https://tiriyachen.org/መምህር-እና-ጌታ-ትሉኛላችህ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

22 Jan, 14:50


ፈጣሪ ፍጡር አይደለም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
ቁርኣን 13፥16

አምላካችን አላህ የሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው፥ አላህ በፈጣሪነቱ ላይ ፍጡርነት የሚባል የነውር እና የጎደሎ ባሕርይ የለውም። አላህ ሁለመናው ፈጣሪ ነው፥ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦

አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፥ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው" በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
ቁርኣን 13፥16

ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
📜ቁርኣን 2፥117

ሙሉውን ለማንበብ
https://tiriyachen.org/ፈጣሪ-ፍጡር-አይደለም/

Tiriyachen | ጥሪያችን

21 Jan, 15:20


ያህዌህ እና መሢሑ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡

مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل
ቁርኣን 5፥75

“አል-መሢሕ” الْمَسِيح የሚለው የዐረቢኛው ቃል “መሠሓ” مسح ማለትም “አበሰ” አሸ” “ቀባ” ከሚል ሥርወ-ግንድ የተገኘ ሲሆን “የቀባ” አሊያም “የተቀባ” ወይንም “የሚያብስ” አሊያም “የታበሰ” ወይንም “የሚያሽ” አሊያም “የሚታሽ” የሚል ፍቺ አለው፤ ዒሣ ኢብኑ መርየም በሽተኞችን፣ ህሙማንን እና ሙታንን በማበስ፣ በማሸት እና በመቀባት ከበሽታቸው በአላህ ፈቃድ ያሽራቸው ስለነበረ እና በአላህ የተሾመ(የተቀባ) ነቢይ ስለሆነ “አል-መሢሕ” ተብሏል። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል። ይህ መሢሕ አስተምረው ካለፉት መልእክተኞች አንዱ የአላህ ባሪያ ነው፦


ሙሉውን ለማንበብ
https://tiriyachen.org/ያህዌህ-እና-መሢሑ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

20 Jan, 16:19


ኢየሱስ ይመለካልን ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

«በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡

مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
ቁርኣን 5፥117

“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ አላህ ዒሳን በል ብሎ ያዘዘው ቃል፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦

«በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡

مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
ቁርኣን 5፥117

ነገር ግን በተቃራኒው ክርስቲያኖች ኢየሱስን በቀጥታ ያመልካሉ፤ “አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አባድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ኢየሱስ፦ አምልኩኝ ያለበት፣ ሀዋርያት እና ነብያት፦ ኢየሱስን አምልኩ ያለበት እና ሰዎች ኢየሱስን ያመለኩበት አንድ አንቀጽ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ የሚመለክ መሆኑን የሚጠቁሙ ጥቅሶች አሉ ይላሉ፤ እውን ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ይመለካል ይላልን? እስቲ ጥቅሱን እንየው፦

ሙሉን ለማንበብ
https://tiriyachen.org/ኢየሱስ-ይመለካልን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

19 Jan, 18:09


በስጋ ተገለጠ | ዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/1dzFncAMy44

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

19 Jan, 15:00


አሐዳዊያን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

«ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ ”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» በላቸው፡፡

قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
ቁርኣን 21፥108

በሥነ-መለኮት ጥናት ክርስትና፣ አይሁድ እና እስልምና አሐዳዊ ሃይማኖት"monotheistic Religion" ተብለው ይመደባሉ፤ ክርስቲያን፣ አይሁዳውያን እና ሙስሊም አሐዳውያን"Monotheism" ይባላሉ፤ ምክንያቱም ፈጣሪ በህላዌ ማለትም በምንነት አንድ ኑባሬ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።

ነገር ግን የክርስትና አሐዳውያን በሥስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ አሓዳውያን“Unitarian” ሲሆኑ፤ “uni” ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት እና በማንነት አንድ ስለሆነ አምላካቸውን “mono-une God” ይሉታል፤ እነዚህ የመጀመሪያ መቶ ክፍለ-ዘመን የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ነበሩ።
2ኛ ደግሞ ክሌታውያ“Binitarian” ይባላል፤ “Bini” ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ደግሞ ሁለቱ አብና ወልድ ናቸው፤ አምላካቸውን “Bini-une God” ይሉት ነበር፤ ይህ ትምህርት ሁለተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።
3ኛ ሥላሴአዊያን“Trinitarian” ይባላሉ፤ “Tri” ማለት "ሶስት" ማለት ነው፤ ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ሶስት ስለሆነ አምላካቸው “Tri-une God” ይባላል፤ ይህ በአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።

ሙሉን ለማንበብ
https://tiriyachen.org/አሐዳዊያን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

18 Jan, 15:24


7፥52 *ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው*፡፡ وَلَقَدْ جِئْنَٰهُم بِكِتَٰبٍۢ فَصَّلْنَٰهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًۭى وَرَحْمَةًۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
4፥114 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፤ የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا
55፥1-2 *አል-ረሕማን ቁርኣንን አሳወቀ*፡፡ ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَّمَ ٱلْقُرْءَانَ
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ነጥብ ሶስት
"ሥነ-አመክንዮ"
"የሥነ-አመክንዮ"Logic" ምሁራን "ሙግት"argument" በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ስሙር ሙግት"valid argument" ሲሆን ይህ ሙግት በእማኝነትና በአስረጂነት ጠቅሶና አጣቅሶ መሟገት ነው፤ በትክክለኛው የአስተላለፍ ስልትና አወቃቀር ስለተዋቀረ የራሱ የሆነ መንደርደሪ፣ የሙግት ነጥብ"premise"፣ መደምደሚያ ያለው ነው፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ በአጽንኦትና በአንክሮት ለማዳመጥ ጥልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ነው፤ ይህን ሙግት አምላካችን አላህ መልካም ክርክር ይለዋል፤ ይህ ዘዴ ርቱዕ አካሄድ"optimistic approach" ነው፦
16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ *መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ*፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ሁለተኛው ሙግት ደግሞ "ስሁት ሙግት"Invalid argument" ሲሆን ይህ ሙግት ያለ ዕውቀትና ያለ መረጃ እውርር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ ሙግት ነው፤ ሰው ሱሪ በአንገቴ ካለ ዓይን ያስፈጠጠ እውነት ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ የጨባራ ለቅሶ ውስጥ እርርና ምርር ብሎ የሚንጨረጨረውና የሚንተከተከው በዚህ ሙግት ነው፤ ይህ አካሄድ ኢርቱዕ አካሄድ"pessimistic approach" ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ጉዳይ የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍۢ وَلَا هُدًۭى وَلَا كِتَٰبٍۢ مُّنِيرٍۢ

በድርቅና ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም የሚከራከርን ሰው መሃይምነት ስላጠቃው መሃይማን በክፉ ሲያነጋግሩን በሰላም ውይይቱን መተው ነው፤ ምክንያቱም ወደ ብሽሽቅ ስለሚያስገባ ነው፤ ብሽሽቅ ውስጥ መልካም የሆነችውን ቃል ስለማንናገር ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፦
7:199 “ገርን ጠባይ ያዝ”፤ በመልካምም እዘዝ “መሃይማንን” الْجَاهِلِينَ ተዋቸው። خُذِ ٱلْعَفْوَ وَأْمُرْ بِٱلْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْجَٰهِلِينَ
25:63 የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ “በዝግታ የሚኼዱት”፣ “መሃይማን” الْجَاهِلُونَ በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ “ሰላም” የሚሉት ናቸው። وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًۭا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًۭا
17:53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ “መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

18 Jan, 15:24


ውይይት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

"ውይይት" በተቃናቃኝ እና በአቀንቃኝ አሊያም በአውንታዊ እና በአሉታዊ አመለካከት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ሙግት ብቻ ሳይሆን ችግር ሲመጣ የመጣው ችግር ለማንበብ፣ ለመረዳት፣ ለመፍታት አይነተኛ ቁልፍ ነው፤ ማንኛውም ውይይት አላህ ይሰማዋል፣ ያውቀዋል፣ የቂያማ ቀን በቀኝና በግራ ያሉት መላእክትም ውይይታችንን ጽፈውት ያስጠይቀናል፦
9፥78 አላህ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የሚያውቅ መኾኑን* አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መኾኑን አያውቁምን? أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
43፥80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

ስለዚህ ውይይት ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚቀርብ የማስተማሪያ ጥበብ እንጂ የሌላውን ሰው ሃሳብና ስሜት ለማብጠልጠል፣ ለማጠልሸት፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማነወር፣ ተብሎ የሚደረግ ንትርክ ወይም እሰጣገባ አይደለም። ለውይይት ምህዳር የሚሆኑ ቅድመ-ሁኔታ እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሥነ-እውነት"
የሥነ-እውነት ጥናት"metaphysics" ምሁራን እንደሚያትቱት እውነት አንድ ሲሆን ሁለት ገፅታዎች አሉት፤ አንዱ "ውሳጣዊ እውነታ"subjective truth" ሲሆን ለምሳሌ እኔ አሳ መብላት እወዳለው ብል፤ ሌላ ሰው አልወድም ብንል ሁለታችንም ትክክል ነን፤ ይህ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ እውነታ"objective truth" ሲሆን ለምሳሌ ቢጫ ቀለም በየትኛውም ቋንቋ ስሙ ይቀያየር እንጂ ቢጫ ቀይ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ አይደለም፤ ይህ "ውጫዊ እውነታ" ይባላል፤ አንድ ሰው ይህንን እውነታ ሲቃረን ዕውቀት ጎድሎት በመሃይምነት እንዳለ ያሳብቅበታል። አምላካችን አላህ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር፦ "ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ" "ሐሰትንም ቃል ራቁ" ይለናል፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

እውነትን ለመግለጥ ሃሰትን ለማጋለጥ እውነቱ ምንድን ነው? ሃሰቱ ምንድን ነው? ብሎ መሞገት እንጂ እውነተኛው ማን ነው? ሃሰተኛው ማነው? ካልክ ሰውዬው ወደ ግትረኛነት ወይም ወደ መበሻሸቅ ይሄዳል፤ ስለዚህ ውይይት ለማድረግ ሃቅ መያዝ አይነተኛ ሚና ነው፤ አንድ ሰው እውነተኛ ለመሆን ማስረጃ ማቅረብ አለበት፤ ሁሌም ማስረጃ ከያዙ እውነተኞች ጋር መሆን አለብን፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

የተሟላ ማስረጃ ማለት ደግሞ ከአላህ የሚመጣው የአላህ ንግግር ነው፦
6፥149 *የተሟላው ማስረጃ የአላህ ነው*፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» *በላቸው*፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ ٱلْحُجَّةُ ٱلْبَٰلِغَةُ ۖ فَلَوْ شَآءَ لَهَدَىٰكُمْ أَجْمَعِينَ
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ*? تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ ۖ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤْمِنُونَ

ነጥብ ሁለት
"ሥነ-ዕውቀት"
"የሥነ-ዕውቀት ጥናት"epistemology" ምሁራን ዕውቀት በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ውሳጣዊ ዕውቀት"Rational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ከውስጥ የሚመጣ እሳቤ፣ ፈጠራ፣ መፍትሔ ወዘተ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ ዕውቀት"Irational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ልምድ፣ ተሞርኮ፣ ሰርቶ ማሳያ ወዘተ "ውጫዊ ዕውቀት" ይባላል፤ ዕውቀት ለብዙ ነገር ማስረጃ ነው፤ እውነተኛ ሰው በዕውቀት ይናገራል፤ ያለ ዕውቀት አንድን እምነት መከተል ያስጠይቃል፦
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል*፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ ۚ إِنَّ ٱلسَّمْعَ وَٱلْبَصَرَ وَٱلْفُؤَادَ كُلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْـُٔولًۭا

አንድ ነገረኛ ወሬን ቢያመጣልን በስሕተት ላይ ሆነን ሕዝቦችን እንዳንጎዳ እና በሠራነው ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳንሆን በዕውቀት በተደገፈ ማስረጃ ማረጋገጥ አለብን፦
49:6 እላንተ ያመናችሁ ሆይ ነገረኛ *ወሬን ቢያመጣላችሁ” በስሕተት ላይ ሆናችሁ “ሕዝቦችን እንዳትጎዱ” እና በሠራችሁት ነገር ላይ “ተጸጻቾች” እንዳትሆኑ ”አረጋግጡ”*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍۢ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍۢ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ

ዕውቀት ከሰው ልጅ አዕምሮ ሲመጣ "ዐቅል" عقل ሲባል ወሕይ ሆኖ ወደ ነብያት ሲመጣ ደግሞ "ነቅል" نفل ይባላል፤ ለምሳሌ ቁርአን ከዕውቀት ጋርም የተዘረዘረ መጽሐፍ ነው፤ ነብያችን"ﷺ" የማያውቁት እና ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቃቸው አላህ ነው፦

Tiriyachen | ጥሪያችን

15 Jan, 14:38


አሁንም ልብ አድርጉ በመከራ መጠመቅ ፍካሬአዊ እንደሆነ እንጂ እማሬአዊ እንዳሆነ እሙን ነው።
ከላይ የደረደርኳቸው የሙግት ነጥቦችpremises" በኢስላም ጥምቀት እንዳለ ለማሳየት ነው፥ ሙሥሊም ሲፈጠር የሚጠመቅበት የሃይማኖት ጥምቀት ኢሥላም ነው። ይህ ጥምቀት በ 40 ቀን ወይም በ 80 ቀን አሊያም ለአቅመ ኣደምና ሐዋ ስንደርስ የምንጠመቀው ሳይሆን በተፈጥሮ የምንጠመቀው ጥምቀት ነው፥ አጥማቂውን ቄስ አሊያም ፓስተር ሳይሆን የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፦
2፥138َ Our religion is the Baptism of Allah: And who can baptize better than Allah? And it is He Whom we worship. Yusuf Ali
*የአላህን የተፈጥሮ ጥምቀት ያዙ፡፡ በማጥመቅም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን በሉ*። صِبْغَةَ اللَّـهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّـهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُون

አምላካችን አላህ ሰዎችን የፈጠረው እርሱን እንዲያመልኩና እንዲታዘዙ ስለሆነ ኢሥላም አላህ ሰዎችን የፈጠረበት ሃይማኖት ነው፦
30፥30 ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን *”አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት”*፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًۭا ۚ فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

“ሙስሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አስለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፥ “ኢስላም” إِسْلَٰم ደግሞ ሃይማኖቱ ነው። አላህ ሰውን ሲፈጥር በተፈጥሮ ጥምቀት ሲሆን የህፃኑ ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል፦
ኢማም ቡኻርይ መፅሐፍ 23, ሐዲስ 138
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“ማንም የሚወለድ ሰው “በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም”። ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ያደርጉታል ወይም ክርስቲያን ያደርጉታል አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል እንጂ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كُلُّ مَوْلُودٍ يُولَدُ عَلَى الْفِطْرَةِ، فَأَبَوَاهُ يُهَوِّدَانِهِ أَوْ يُنَصِّرَانِهِ أَوْ يُمَجِّسَانِهِ

“አል-ፊጥራህ” الْفِطْرَةِ ማለት “ተፈጥሮ” ማለት ነው። አንድ ሰው ከከሐዲያን ቤተሰብ ተወልዶ ወላጆቹ እስከሚያከፍሩት ወይም በአንደበቱ እኔ የዚህ እምነት ተከታይ ነኝ እስከሚል ድረስ በኢሥላም ሥር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 38
አቢ ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም የሚወለድ ሰው በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም፥ በአንደበቱ እስከሚል ድረስ”*። لَيْسَ مِنْ مَوْلُودٍ يُولَدُ إِلاَّ عَلَى هَذِهِ الْفِطْرَةِ حَتَّى يُعَبِّرَ عَنْهُ لِسَانُهُ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *”ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ “እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው”*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏”‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

ስንቋጨው ይህንን የተፈጥሮ ጥምቀት ልክ እንደ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ የእሳት ጥምቀት፣ የመከራ ጥምቀት በፍካሬአዊ እንረዳዋለን እንጂ ልክ እንደ የውኃ ጥምቀት በእማሬአዊ አንረዳውም። አላህ በተፈጥሮ ጥምቀት ፀንተው ከሚሞቱ ሙሥሊም ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

14 Jan, 15:22


የአላህ ይቅርታ እና ምሕረት በአላህ ስም
እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”፡፡

نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
📜ቁርኣን 15፥49

በቁርኣን ከተጠቀሱ ዘጠና ዘጠኝ ከአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ገፋር” الغَفَّار ወይም “አል-ገፉር” الغَفُور ሲሆን “ይቅርባዩ” ማለት ነው። “መግፊራህ” مَّغْفِرَة ማለት “ይቅርታ” ማለት ሲሆን የእርሱ ባሕርይ ነው። እንዲሁ በቁርኣን ከተጠቀሱ ዘጠና ዘጠኝ ከአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አር-ረሒም” ٱلرَّحِيمِ ማለት ደግሞ “እጅግ በጣም መሓሪ” ማለት ነው፥ የአር-ረሕማን ባሕርይ ደግሞ “ረሕማህ” رَّحْمَةً ማለትም “ምሕረት ነው። አምላካችን አላህ በመጀመሪያ መደብ እና በሦስተኛ መደብ፦ “እኔ ይቅርባዩ መሓሪው ነኝ” ይላል፦

“ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”፡፡

نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
📜ቁርኣን 15፥49

ሙሉውን ለማንበብ ....
https://tiriyachen.org/የአላህ-ይቅርታ-እና-ምሕረት/

Tiriyachen | ጥሪያችን

13 Jan, 16:07


https://tiriyachen.org/ኅሊና/

Tiriyachen | ጥሪያችን

13 Jan, 13:29


አላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
📜ቁርኣን 59፥7

"ዐቂቃህ" عَقِيقه ማለት አዲስ ለተወለደ ሕፃን ልጅ የሚታረድ መስዋዕት የሚደረግ እርድ ነው። የተወደደ እና የተፀና የተከበደ ነቢያዊ"ﷺ" ፈለግ የሆነ እርድ ነው። ዐቂቃህ ማረድ "ማሱና ሙአከዳ" ማለትም በጣም የጠበቀ እና የተወደደ ሱናህ ነው። የዐቂቃህ ዓላማው የተደነገገበት ምክንያት ለአላህ ምስጋና ለማድረስ ነው። ይህም አንድ ሰው ልጅ ስለተወለደለት በመደሰት በ 7ኛው ቀን ደስታውን ለመግለፅ፣ ይህንንም ደስታውን ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ እና የተወለደውም ልጅ የማን እንደሆነ ለማሣወቅ ነውና። አላህ ደግሞ ልጁን እንደሚጠብቀው፥ እንዲሁ ሷሊህ ልጅ እንዲሆንለት ምክንያትም እንዲሆነው የሚደረግ አርዶ ሰውን የማብላት ሥርዓት ዐቂቃህ ይባላል፦

ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ዐቂቃህ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

12 Jan, 15:29


ድነሃልን ?

አላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡

وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
📜ቁርኣን (3፥103)

በየመንገዱ፣ በየትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ከክርስቲያኖች ወገኖች በተለይ ከፕሮቴስታንት አንጃ፦ “ድነሃልን? የሚል ዋስትና የሌለው ጥያቄ ተደጋግሞ ሲመጣ ይጤናል። ነገር ግን ከምን እንደሚዳን ጠቅሰውና አጣቅሰው በማስረጃ አይሞግቱም፥ አይሟገቱም። ከዚያ ይልቅ ስሜታውያን በመሆን ስሜታዊ ቃላት ይጠቀማሉ። አንዱ አምላክ አመጸኞችን በገሃነም ያጠፋል፥ ከዚህ ጥፋት የሚያድነውም እርሱ ነው፦

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።


https://tiriyachen.org/ድነሃልን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

10 Jan, 17:09


መሐላ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ፡፡
ቁርኣን (21፥23)

“ቀሠም” قَسَم የሚለው ቃል “ቃሠመ” قَاسَمَ ማለትም “ማለ” “አጸና” “አሳመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መሐላ” “አጽንዖት” “መተማመኛ” ማለት ነው። አማንያን አንድን ነገር አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት አስፈላጊ ከሆነ በአሏህ ስም “ወሏሂ” وَٱللّٰه “ቢሏሂ” بِاللَّهِ በማለት ይምላሉ። ከአላህ ውጪ በሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መማል ግን አይቻልም፦

ሠዕድ ኢብኑ ዑበይዳህ እንደተረከው፦
“አንድ ሰው፦ “በከዕባህ እምላለው” ብሎ ሲናገር ኢብኑ ዑመር ሰምቶ እንዲህ አለ፦ “ከአላህ ውጪ በሌላ መማል ከንቱነት ነው፥ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ “ማንም ይሁን ከአላህ ውጪ በሌላ የማለ ከፍሯል ወይም አሻርኳል”።

📚ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 13

እዚህ ሐዲስ ላይ “መን” مَنْ የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ከአላህ ውጪ የሆነን ምንነት ነው፥ ይህ ከአላህ ውጪ የሆነ ማንም ፍጡር በአላህ ስም ብቻ እንጂ በፍጡራን መማሉ ኩፍርና ሺርክ ነው። ነገር ግን ምን አይነት ኩፍርና ሺርክ? ይህንን ለመረዳት ስለ ኩፍርና ሺርክ በግርድፉና በሌጣው እንይ፦

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።

https://tiriyachen.org/መሐላ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

10 Jan, 15:49


ነጻ ፈቃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“ሻእ” شَآء ማለት “ፈቃድ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ በፍጥረተ-ዓለማት ውስጥ የሚሻውን ይፈጥራል፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
86፥16 *የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው*፡፡ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
3፥47 *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"የሚሻውን" ለሚለው ቃል የገባው "የሻኡ" يَشَاءُ ማለትም "የሚፈቅደውን" ነው። ማንኛውም ነገር ሲከሰት፣ ሲከናወንና ሲሆን አላህ ፈቅዶ ነው፥ ያለ አላህ ፈቃድ ምንም እኩይ ወይም ሰናይ ነገር አይከሰትም፤ አይከናወንም፣ አይሆንም። የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ሆኗል፥ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው።

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።

https://tiriyachen.org/ነጻ-ፈቃድ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Jan, 15:04


ዒባዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" ማለት ነው። ዒባዳህ ማለት በቀልብያ፣ በቀውልያ፣ በዐመልያ ለአንድ ምንነት እና ማንነት የሚደረግ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ ነው። የመስኩ ልሂቃን፦ "አምልኮ" ማለት "ለአንድ ምንነትና ማንነት በፍጹም ሁለንተናዊነት ማለትም በኃልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር መገዛት ነው" ይላሉ።
ዒባዳህ በተመላኪ እና በአምላኪ መካከል ያለ መርሕ ነው፥ "መዕቡድ" مَعْبُد ማለት "ተመላኪ" ማንነት ማለት ሲሆን “ዐብድ” عَبْد ወይም “ዐቢድ” عَابِد ደግሞ "አምላኪ" ማንነት ነው። አምላካችን አላህ በመጀመሪያ መደብ ብዙ ቦታ "አምልኩኝ" እያለ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِ

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ዒባዳህ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Jan, 14:13


🎙 የድምፅ ትምህርት | 7.3 MB

አዲስ አመት

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

ከዓቃቢ ኢስላም ወሒድ

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃኑአርይ ነው። “ጃኑአርይ” ማለት “ጃኑስ” የተባለው ጣዖት የሚመለክበት ወር ነው። ይህ በዓል ጁለስ ቄሳር በ 46 ቅድመ-ልደት ስለጀመረው በዚህ ወር ዓመቱ ስለሚቀየር ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ይባላል።

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

08 Jan, 16:19


ይፍረዱ

አምላካችን አላህ ለዒሣ ወንጌልን ሰጠው፤ በዚያ ወንጌል ውስጥ፦ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” የሚል መመሪያ አለ፦

5፥46 በፈለጎቻቸውም ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን *አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው*። وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًۭى وَنُورٌۭ وَمُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًۭى وَمَوْعِظَةًۭ لِّلْمُتَّقِينَ

5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ *አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ*። وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ይፍረዱ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

08 Jan, 15:21


የሥላሴ አማንያን ከባይብል የሥላሴ እሳቤ ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። በተለይ የሥላሴ ሽታው እንኳን ከማይሸተው ከብሉይ ኪዳን ፍንጭ ለማግኘት ሲዳዱ ማየት ፈገግ ያሰኛል። የብሉይ ኪዳን ቀዳማይ ተዳራሲያን አይሁዳውያን እንጂ ክርስቲያኖች አይደሉም። ክርስቲያኖች ደኃራይ ተዳራሲያን እንደመሆናችሁ መጠን አይሁዳውያን ከሙሴ ጀምሮ ሥላሴ የሚባል አምላክ ሰብከው እንደማያውቁ ከባለቤቶቹ ቀረብ ብሎ መጠየቅ ነው። እስቲ ለዛሬ ሥላሴን ያሳያል ብለው ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው ጥቅሶች አንዱ እንይ፦

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ልከውኛል-ወይስ-ልኮኛል/

Tiriyachen | ጥሪያችን

07 Jan, 16:50


ልከውኛል ወይስ ልኮኛል?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

የሥላሴ አማንያን ከባይብል የሥላሴ እሳቤ ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። በተለይ የሥላሴ ሽታው እንኳን ከማይሸተው ከብሉይ ኪዳን ፍንጭ ለማግኘት ሲዳዱ ማየት ፈገግ ያሰኛል። የብሉይ ኪዳን ቀዳማይ ተዳራሲያን አይሁዳውያን እንጂ ክርስቲያኖች አይደሉም። ክርስቲያኖች ደኃራይ ተዳራሲያን እንደመሆናችሁ መጠን አይሁዳውያን ከሙሴ ጀምሮ ሥላሴ የሚባል አምላክ ሰብከው እንደማያውቁ ከባለቤቶቹ ቀረብ ብሎ መጠየቅ ነው። እስቲ ለዛሬ ሥላሴን ያሳያል ብለው ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው ጥቅሶች አንዱ እንይ፦
ኢሳይያስ 48፥16 ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም *"አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል"*። NET Bible
ዕብራይስጥ ማሶሬቲክ፦
אֲדֹנָי יְהוִה שְׁלָחַנִי--וְרוּחו
ግሪክ ሰፕቱጀንት፦
καὶ νῦν Κύριος ἀπέστειλέ με καὶ τὸ πνεῦμα αὐτοῦ.

የዕብራይስጡ ማሶሬቲክ እና ግሪክ ሰፕቱጀንት(LXX)፦ "አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል" ብለው አስቀምጠውት ሳለ ሥላሴአውያን፦ "አዶናይ ያህዌህ እና መንፈሱ ልከውኛል" በማለት ሥላሴ ለመስራት ሞክረዋል።
"ሠላሐኒ" שְׁלָחַ֖נִי ማለት "ልኮኛል" ነው እንጂ "ልከውኛል" ማለት አይደለም። "ሠላሐ" שְׁלָחַ֖ ማለት "ላከ" ማለት ሲሆን ነጠላ ግስ ነው፥ ይህ ግስ በተመሳሳይ ነቢያት "ላከኝ" ላሉበት ግስ የተጠቀሙት ይህንን ግስ ነው፦
ዘፍጥረት 45፥5 አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ፥ አትቈርቈሩም፤ እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי ።
2 ነገሥት 2፥2 ኤልያስም ኤልሳዕን፦ ያህዌህ ወደ ቤቴል *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי በዚህ ቆይ፡ አለው።
ኤርምያስ 26፥12 ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ በሰማችሁት ቃል ሁሉ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ ያህዌህ *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי ።

ብሉይ ላይ "ሠላሐኒ" שְׁלָחַ֖נִי የሚለው ቃል 26 ቦታ አለ፥ ሁሉም ጋር "ልኮኛል" ለማለት እንጂ "ልከውኛል" ለማለት በፍጹም አልተጠቀሙበት። ኢሳይያስ ላይ ግን የሥላሴ አማንያን ትርጉም ላይ ሆን ብለው የሥላሴን እሳቤ ለማዳበር የጨመሯት ነው። የላከ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት "ላኩ" ነው፥ "ላኩ" ደግሞ "ሣላሁ" שָׁלְח֖וּ ነው፦
ኤርምያስ 14፥3 ታላላቆችም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ *"ላኩ"* שָׁלְח֖וּ ።

ኢሳይያስ "ልከውኛል" ለማለት ቢፈልግ ኖሮ "ሣላሁኒ" שָׁלְח֖וּנִי ይል ነበር፥ ቅሉ ግን አላለም። የያህዌህ መንፈሱ ከአፉ እና ከአፍንጫው የሚወጣ እስትንፋ ነው፦
ዘጸአት 15፥8 *”በአፍንጫህ እስትንፋስ”* ውኆች ተከመሩ፥ ፈሳሾችም እንደ ክምር ቆሙ፤ ሞገዱም በባሕር ውስጥ ረጋ፡፡
መዝሙር 33፥6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ *”በአፉ እስትንፋስ”*።

የያህዌህ እስትንፋስ ከያህዌህ በተለይ መልኩ እንደ ያህዌህ እራሱ የቻለ ማንነት"person" ከሆነ እርሱ ማን ነው? ያህዌህስ ከራሱ አፍ እና አፍንጫ ተሸንሽኖ የሚወጣ ሌላ ማንነት ካለው ያህዌህ አንድ ነው ከሚለው ትምህርት ጋር ይጣረሳል። ሲቀጥል አፍንጭ እና አፍ ሁለት ስለሆኑ ሁለት እስትንፋሶች ከወጡ በኃላ ተገጣጥመው ነው ወይስ ተለያይተው ነው ማንነት የሚሆኑት?
ሢሰልስ ኢሳይያስን የያህዌህ እስትንፋስ አላከውም፥ ግን ላከው ቢባል የሚያስደንቅ አይደለም። ምክንያቱም ከያህዌህ አፍ የምትወጣ ጥበብ ትልካለች፦
ምሳሌ 9፥1 *"ጥበብ ቤትዋን ሠራች"*፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።
ምሳሌ 9 3፤ *"ባሪያዎችዋን ልካ"* በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።
ሉቃስ 11፥49 ስለዚህ ደግሞ *የእግዚአብሔር ጥበብ* እንዲህ አለች፦ ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን *እልካለሁ*፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥

ያህዌህ መልእክቱን ለነቢያት የሚያስተላልፈው በመንፈሱ ነው፦
ዘካርያስ7፥12 የሠራዊትም ጌታ ያህዌህ *"በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉን እና ቃሉን"* እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ።

ላኪ ያህዌህ በመንፈሱ ከሆነ የተላከው ማን ነው? የተላከው ኢሳይያስ ነው። ዐውዱ ላይ፦ "ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ" የሚለው ያህዌህ ነው። ከዚያ ኢሳይያስ፦ "አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል" ይላል። ይህ የተለመደ አነጋገር በኢሳይያስ መጽሐፍ እንይ፦
ኢሳይያስ 50፥3-4 *"ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፥ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ። የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ አዶናይ ያህዌህ የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል"*።

"ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፥ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ" የሚለው ያህዌህ ሆኖ ሳለ እዛው ዐውድ ላይ፦ "የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ አዶናይ ያህዌህ የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል" የሚለው ኢሳይያስ ነው። መቼም፦ "አንዱ ያህዌህ ለሌላው ያህዌህ የተማረ ምላስ ሰጥቷል፣ ማለዳ ማለዳ ያነቃዋል፣ ጆሮውን ያነቃቃዋል" የሚል ቂል ያለ አይመስለኝም። ስለዚህ ከላይ ያለውን ጥቅስ በዚህ ስሌት ተረዱት። የሚያጅበው እኮ ኣ “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢሳይያስ 48፥16 እና 50፥4 ላይ "ጌታዬ" የሚለው ኢሳይያስ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። ሲቀጥል “አዶኒም” אֲדֹנִ֣ים የብዙ ቁጥር ሆኖ ሲመጣ "ጌቶች" ማለት ከሆነ ሥላሴን ያሳያል ካላችሁ እንግዲያውስ መንፈሱ እና የተላከው ከሥላሴ ውጪ ነው። ቅሉ ግን "ጌታዬ" ያህዌህ ልኮኛል የሚለው ኢሳይያስ ሲሆን ላኪው ደግሞ ያህዌህ በመንፈሱ ነው።

በወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Jan, 11:22


ወርቃማው ሕግ | ዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/NNLigt9FCkA

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

05 Jan, 16:00


25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *”ፉርቃንንም አወረደ”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَان
5፥48 *”ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን”*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

“ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለት “አረጋጋጭ” ማለት ሲሆን ቁርኣን ከወረደበት አላማ እና ኢላማ አንዱ ከአላህ የወረደውን እውነት ለማረጋገጥ ነው፥ ከአላህ የወረደውን እውነት ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” ይባላል። “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለት ደግሞ “አራሚ” corrector” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” ማለት ነው፦
Arabic-English Lexicon volume 1 page 147 Edited by Edward William Lane.

በተወረደው ላይ ቀጥፈው የጨመሩትን ውሸት ስለሚያርም “ሙሃይሚን” ይባላል።
የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያለው የተበረዘ መፅሐፍ ነው ማለት ወተት ከቡና ጋር ሲቀላቀል ኦርጂናሉ ወተት ተበርዟል ማለት ነው። ነገር ግን የወተት ቅሪት በማኪያቶ ላይ አለ። በተመሳሳይ የአላህ ንግግር የወረደበት ቋንቋ ሥረ-መሠረቱና የቃሉ አንጓ ባይኖርም መልእክቱ እና ሃሳቡ በቅሪት ደረጃ አለ። የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያሉት መጽሐፍት ሙሉ ለሙሉ እውነትን ነው ብለን እንደማንቀበል ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው ብለን አናስተባብልም። ዋናው ከአላህ የወረደውን እውነት ሰዎች ከጨመሩበት ሐሰት የምንለይበት ፉርቃን ቁርኣን ነው። ቁርኣን ያረጋገጠውን እሳቤ በማረጋገጥ ያረመውን ደግሞ በመተው እንመዝናለን። ለምሳሌ ቁርኣን ከበፊቱ የወረደውን በመግለጽ እና በመዘርዘር አረጋግጧል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ከገለጻቸውና ከዘረዘራቸው መካለል በዐቂዳህ ነጥብ፦ አላህ “እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” በማለት ወደ ነቢያቱ ማውረዱ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ *”እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

በፊቅህ ነጥብ ደግሞ አላህ ስለ “ጾምን፣ መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን” ማውረዱን ነው፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

05 Jan, 16:00


ሙሰዲቃን እና ሙሃይሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥48 *”ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን”*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

አምላካችን አላህ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ቁርኣንን በእውነት አወረደ፥ ከቁርኣን በፊት ተውራትንና ኢንጂልን ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፦
3፥3 *”ከእርሱ በፊት ያሉትን የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል”*፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *”ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ

“የደይ” يَدَيْ ማለት “ፊት” ማለት ሲሆን “ኃላ” ለሚል ተቃራኒ ሆኖ የመጣ ነው፥ “ቀብል” قَبْل ማለት “ፊት” ማለት ሲሆን የየደይ ተመሳሳይ ትርጉም ነው። “የደይ-ሂ” يَدَيْهِ ማለት እና “ቀብሉ” قَبْلُ ማለት “ከበፊቱ” ማለት ነው፥ “ሂ” هِ ወይም “ሁ” هُ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ቁርኣንን ያሳያል። ከቁርኣን በፊት የወረዱትን ተውራትና ኢንጅልን ሊያረጋግጥ ቁርኣን ወርዷል። “ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አምላካችን አላህ፦ “እመኑ” ያለን ከቁርኣን በፊት ባወረደው ወሕይ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው፤ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፤ በዚያም *”ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ

“ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። እንግዲህ አምላካችን አላህ ተውራትና ኢንጅል የሚላቸው ወደ ሙሳ እና ወደ ዒሣ የወረዱትን ወሕይ ብቻና ብቻ ነው። አምላካችን አላህ ከራሱ የሚያወርደው ወሕይ እውነት ይለዋል፦
34፥48 ፦ጌታዬ *“እውነትን ያወርዳል”*፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው *በላቸው*። قُلْ إِنَّ رَبِّى يَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ

ይህ ከአላህ የወረደውን እውነት የመጽሐፉ ሰዎች ከውሸት ማለት ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለውታል፦
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

ይህ የሰው ንግግር “ውሸት” ለምን ተባለ? ምክንያቱም የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ስለሆነ ነው፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

እዚው ዐውድ ላይ ስንመለከት ከመጽሐፉ ሰዎች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

“የሚለውጡት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሐረፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን “የሚበርዙት” ማለት ነው፤ “ዩሐረፉ” يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “በረዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ የሚበርዙት ፊደሉ “ሐርፍ” حَرْف ሲባል፥ በራዡ “ሙተሐሪፍ” مُتَحَرِّف ሲልባ፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ “ተሕሪፍ” تَحريف ይባላል፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
በተጨማሪም ከቀደምት የነቢያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባሥ”ረ.ዐ” የሱረቱል በቀራ 2፥79 አንቀጽን በሰሒሕ ሐዲስ ሲፈሥረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ሲናገር፦ *ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ”ﷺ” የተወረደው ወቅታቂ መረጃ እና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ

ተውራትንና ኢንጂልን ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ ቢያወርዳቸውም ቁርኣን ግን ከእርሱ በፊት ያሉትን ተውራትንና ኢንጂልን የሚያረጋግጥ እና የተቀላቀለው እውነት ከውሸት የሚለይ ነው፥ የመጽሐፉ ሰዎች እዉነቱን በዉሸት በመቀላቀል ሲበረዙት አምላካችን አላህ ቁርኣንን ፉርቃን በማድረግ አውርዷል። “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከውሸት የሚለይ” ማለት ነው፦

Tiriyachen | ጥሪያችን

04 Jan, 14:38


መርየም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?*» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

አላህ ዒሳን እዲናገር ያዘዘው ቃል፦ “አላህ ጌታዬ ጌታችሁ ነው፤ በብቸኝነት አምልኩት” የሚል ሲሆን ነገር ግን ነሳራዎች እርሱ እና እናቱን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው ይዘዋል፤ “አምላክ አድርጎ መያዝ” ምን ማለት ነው? አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 *ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን?* አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሰዎች ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው የያዙት ዒሳን እና እናቱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ ባሮች የሆኑትንም መላእክት እና ነብያትንም ጭምር ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا ፡፡
3:80 *መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ* ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን? وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَن تَتَّخِذُوا الْمَلَائِكَةَ وَالنَّبِيِّينَ أَرْبَابًا ۗ أَيَأْمُرُكُم بِالْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ይህንን ከተረዳን “ኢላሀይኒ” إِلَٰهَيْنِ ለኢሳ እና ለመርየም በሙተና የገባ ነው፤ በሙፍረድ ሲሆን ደግሞ “ኢላህ” إِلَٰه ማለትም “የሚመለክ” ማለት ነው፣ “አምልኮ” የሚለው ቃል “መለከ” ማለትም “ገዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ለምንነት መገዛት” ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

አምልኮ በውስጡ ልመና፣ ስግደት፣ ስለት መሳል እጣን ማጨስ መስዋዕት ማቅረብ ይይዛል። “አምላክ” የሚለውም ቃል “መለከ” ከሚል ስርወ ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው፣ ነገር ግን የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ፣ የሚያውቅበት አንጎል በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም፣ ዐያውቅም።
በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ስለት መሳል፣ እጣን ማጨስ እና መስዋዕት ማቅረብ ይደረጋል፤ ታዲያ ማርያም በሌለችበት ይህን ማድረግ አምልኮ አይደለምን? አዎ ከተባለ እንግዲያውስ አግባብ አይደለም፤ አይ ከተባል ለምን ወደ ማርያም ይህ ሁሉ ይደረጋል? ማርያም በምኗ ትሰማለች? ታያለች? ታውቃለች? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሽርክ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር በጊዜና በቦታ ሳይገደብ ማወቅ፣ ማየት እና መስማት የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
46:5 *እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው*። وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ

ማርያም በሌለችበት እንዲህ ጸሎት፣ ስግደት እና መገዛት ይቀርብላታል፦
ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144
“ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ”
መጽሐፈ ሰአታት ገፅ 31
፦ “በብርሃን ጌጥ ያጌጥሽ ወርቅ ዘቦ ግምጃን የተጎናፀፍሽ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ተገዛንልሽ ለአንቺ እንገዛለን”
፦ “አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ብርሌ ካህናት የሚያሹትሽ የሽቱ ሙዳይ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺን ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “የታተምሽ የውሃ ጉድጓድ የተዘጋሽ የተክል ቦታ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ የነብያት ልጆቻቸው አንች ነሽና ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “በብርና በወርቅ የተሸለምሽ አዲስ የጣሪያ ዋልታ ሚስጥር ማደሪያ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንሰግዳለን”

ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል? አላህ የትንሳኤ ቀን ከእርሱ ሌላ አምልኮ የሚደረግላቸውን አካላት እንዲህ በማለት እያወቀ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17 *እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَقُولُ أَأَنتُمْ أَضْلَلْتُمْ عِبَادِي هَـٰؤُلَاءِ أَمْ هُمْ ضَلُّوا السَّبِيلَ

ነገር ግን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81-82 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ* وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا ፡፡
ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል* كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا ፡፡

በካቶሊክ ማርያም፦ “ሰማይ ላይ ኖራ በኃላ ስጋ የለበሰች አርያማዊት ማለትም ሰማያዊት ናት፤ ከዚያም ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል፤ በኦርቶዶክስና በአንግሊካንም፦ “ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል።
በ 375 AD የተነሱት ኮላደሪያን ክርስቲያኖች ማርያምን በግልጽ፦ “ቴአ” Θεία ማለትም “ሴት አምላክ” ብለው ይጥሩአት ነበር።

Tiriyachen | ጥሪያችን

04 Jan, 14:38


በ 431 AD የኤፌሶን ጉባኤ ማርያምን “ቴኦቶኮስ” Θεοτόκος ማለትም “የአምላክ እናት” ብለዋታል።
ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን በግሪክ “ኪርያ” κυρία ማለትም “ሴት ጌታ” ይሉአታል፣ “ኪርዮስ” κύριος ማለት “ወንድ ጌታ” ማለት ነው። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚኢት” ትባላለች፤ “እግዚኢት” ማለት “ሴት ጌታ” ማለት ሲሆን “እግዚእ” ደግሞ “ወንዱ ጌታ” ማለት ነው፤ ኢየሱስን “እግዚኢነ” ማለትም “ጌታችን” እንደሚሉት ሁሉ ማርያም “እግዚኢትነ” ማለትም “ጌታችን” ይሉአታል። ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ነሳራዎች ሆይ! ዒሳን በቀጥታ መርየምን ደግሞ በተዘዋዋሪ እያመለካችሁ ትገኛላችሁ፤ እናማ በእኛ እና በእናንተ የጋራ የሆነው ቃል አንድ አምላክ ብቻ ማምለክ የሚል ነውና ከአንዱ አምላክ ሌላ ከፍጡራን ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው*፤ በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

03 Jan, 15:27


https://tiriyachen.org/ፈጣሪ-ፆታ-አለውን/

Tiriyachen | ጥሪያችን

03 Jan, 14:42


ፈጣሪ ፆታ አለውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ፈጣሪአችን አላህ የሚመስለው ምንም ሆነ ማንም የለም፥ ፍጡራንም እርሱን አይመስሉትም፤ አላህም ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል የራሱ ስምና ባህርይ አለው፤ ይህንን ስምና ባህርይ ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስልና ሳናወዳድር እራሱ ዕውቅና በመሰጠበት መሠረት እንቀበላለን፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

አላህ ፈጣሪ ነው ፍጡርን አይመስልም ከተባለ ታዲያ ለምንድን ነው በቁርአን እራሱ “እርሱ” እና “አንተ” በሚል ተባዕታይ ፆታ የሚጠራው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ በማድረግ በዐረቢኛ ሰዋስው አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“ነሕው” نَحْو ማለት “ሰዋስው” ማለት ሲሆን “ጂንሥ” جِنْس ማለት ደግሞ “ፆታ”gender” ማለት ነው፥ የሰዋስው ፆታ በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ “ሙዘከር” مُذَكَّر ማለትም “ተባዕታይ”masculine” ሲሆን ሁለተኛው “ሙአነስ” مُؤَنَّث ማለትም “አንስታይ”feminine” ነው፤ ከዚህ ውጪ ልክ እንደ ኢንዶ-ኤሮፕያን ሰዋስው ግዑዝ ፆታ”neutral gender” የሚባል ዐረብኛ ሰዋስው ውስጥ የለም። ታዲያ ፆታ የሌላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ምን ብለን እንጠራቸዋለን? ከተባለ አሁንም ለዐረቢኛው ሰዋስው መድረኩን መልቀቅ ነው። አሁንም በዚሁ የሰዋስው ሙግት ስንሄድ ከሁለቱም ማለትም ከሴትና ወንድ ፆታ ውጪ ያለ ማንነት ሆነ ምንነት ሲሆን “ሙፍረድ” مُفْرَد ማለትም ነጠላ”singular” ከሆነ ተባታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሁወ” هُوَ ማለትም “እርሱ” የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንተ” أَنْتَ ማለትም “አንተ” የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ “ዋሒድ” وَٰحِد ማለት “አንድ” ማለት ሲሆን ተዕባታይ መደብ ነው።
ከአንድ በላይ የሆነ ማንነት ሆነ ምንነት “ጀመዕ” جَمَع ማለትም “ብዜት”plurar” ከሆኑ አንስታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሂየ” هِيَ ማለትም “እርሷ” የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንቲ” أنتِ ማለትም “አንቺ” የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ “ሰላሳህ” ثَلَٰثَة ማለትም “ሦስት” አንስታይ ናት፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ልብ አድርግ አላህ አንድ ስለሆነ “ዋሒድ” ብለክ “ሁወ” እንጂ “ሂየ” አትልም። የሚያጅበው “ሰላሳ” ثَلَٰثَة በሚለው ቃል መጨረሻ ላይ “ታ” ة የሚባለው “ታእ-መርቡጧህ” መሆኑ በራሱ ቃሉን አንስታይ ያደርገዋል። ለምሳሌ “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” በነጠላ ሙዘከር ነው፥ ነገር ግን በብዜት “መላኢካ-ህ” مَلَائِكَة ማለትም “መላእክት” ሙዐነስ ነው። “መላኢካ” በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች “ታ” ة የምትባለው “ታእ-መርቡጧህ” ሙአነስ ናት፥ ለዚያ ነው እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “ናደት” نَادَتْ ማለትም “ጠራች” የሚል ያለው፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት *”ጠሩት”*፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

“ጠሩት” ለሚለው ቃል “ናደት-ሁ” َنَادَتْهُ መሆኑን አንስታይ መሆኑን ያሳያል፥ “ቃለ” قَالَ ማለት “አለ” ማለት ሲሆን ተባዕታይ ነው፥ “ቃለት” قَالَت ደግሞ “አለች” ማለት ሲሆን አንስታይ ነው። ይህ ቃል ለመላእክት ጥቅም ላይ ውሏል፦
3፥42 *”መላእክትም ያሉትን”* አስታውስ፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ

“ያሉት” ለሚለው “ቃለት” قَالَت በሚል መምጥቷል፥ “ቃለ” በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች “ታ” ت “ታእ-መፍቱሓህ” تَاء مَفْتُوحَة‎ የምትባለው ሙአነስ ናት፥ ስለዚህ “ቃለት” የሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለትም “አሉ” ለማለት ተፈልጎ ነው፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ *”እነርሱም”*፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» *”አሉ”*፡፡ አላህ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون

Tiriyachen | ጥሪያችን

03 Jan, 14:42


እዚህ አንቀጽ ላይ “አሉ” ለሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለቱን አስተውል። መላእክት ፆታ የሌላቸው ሴትም ወንድም አይደሉም። ለምን በአንስታይ መደብ ተጠቀመ? ስልን መላእክት ብዙ ማንነቶች ስለሆኑ ሲሆን አላህ ደግሞ አንድ ማንነት ስለሆነ በተባታይ መደብ “እርሱ” “አንተ” “አለ” ተብሎ ተገልጿል። ልብ አድርግ ሂየ” هِيَ የሚለው አንስታይ መደብ “እነርሱ” የሚለውን ብዜት ለማመልከት ይመጣል፦
6፥78 ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ *«አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?»* አለ፡፡ وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ ۖ قَالَ مَن يُحْيِي الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ

“ዐዝም” عَظْم በነጠላ “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ “ዒዛም” عِظَام ደግሞ የዐዝም ብዜት ሲሆን “አጥንቶች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ አጥንቶች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በሙዐነስ “ሂየ” هِيَ ነው። በተጨማሪ፦
27፥88 *”ጋራዎችንም እርሷ” እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ*፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ

“ጀበል” جَبَلْ በነጠላ “ጋራ” ማለት ነው፤ “ጂባል” جِبَالْ ደግሞ የጀበል ብዜት ሲሆን “ጋራዎች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ጋራዎች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም አሁንም በሙዐነስ “ሂየ” هِيَ ነው።

እሩቅ ሳንሄድ በዐረቢኛ ድምጽ ያላቸው ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ ከእነርሱ ውጥስ 14 ሐርፎች “ሑሩፉል ቀመሪያህ” حُرُوف القَمَرِيَّة ማለትም “የጨረቃ ፊደሎች”lunar letters” ተባታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ء ﺏ ﺝ ﺡ ﺥ ﻉ ﻍ ﻑ ﻕ ﻙ ﻡ ﻭ ﻱ ه
የቀሩት 14 ሐርፎች “ሁሩፉ አሽ-ሸምሢያህ” حُرُوف الشَمْسِيَّة ማለትም “የፀሐይ ፊደሎች”solar letters” አንስታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ﺕ ﺙ ﺩ ﺫ ﺭ ﺯ ﺱ ﺵ ﺹ ﺽ ﻁ ﻅ ﻝ ﻥ
ያ ማለት አስራ አራቱ ቀመሪያህ ሙዘከር ስለሆኑ ወንዶች ናቸውን? አስራ አራቱ ሸምሲያህ ሙዐነስ ስለሆኑ ሴቶች ናቸውን? መልሱ አይ ይህ የዐረቢኛ ሰዋስው ላይ የተለመደ ነው። ፀሐይ “ሂየ” هِيَ ትባላለች፥ ጨረቃ ደግሞ “ሁወ” هُوَ ይባላል፤ እና ፀሐይ ሴት ጨረቃ ወንድ ነውን? ፀሐይ በአንስታይ መደብ ነው የተጠራችው፦
81፥1 *”ፀሐይ “በተጠቀለለች” ጊዜ”*። إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

“ተጠቀለለች” ለሚለው ቃል የገባው “ከወረት” كُوِّرَتْ የሚለው ሙዐነስ እንጂ “ከወረ” كُوِّرَ የሚለው ሙዘከር አይደለም፦
75፥8 *”ጨረቃም “በጨለመ” ጊዜ”*፡፡ وَخَسَفَ الْقَمَر

“ጨለመ” ለሚለው ቃል የገባው “ኸሠፈ” خَسَفَ የሚለው ሙዘከር እንጂ “ኸሠፈት” خَسَفَتْ የሚለው ሙዐነስ አይደለም።
ስለዚህ አላህ “አንተ” እና “እርሱ” ስለተባለ ፈጣሪ ፆታ አለው ብሎ መደምደም ስህተት ነው። ባይሆን በባይብል እግዚአብሔር ፆታ ከሌለው ወንድም ሴትም ካልሆነ ለምን “አንተ” እና “እርሱ” እንደሚባል የቤት ሥራ ሰጥተናችኃል።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

02 Jan, 14:37


አንዱ አምላክ እና በጉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

አንዱ አምላክ አላህ ኢየሱስን ሲልከው፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” እንዲል ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን ሰዎች ዛሬ ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን ሲያመልኩ ይታያል። ይህ ስህተት ቢሆንም ኢየሱስ አምልኮ ይገባዋል ብለው ድምዳሜ ላይ ከአደረሳቸው አናቅጽ መካከል አንዱ እንይ፦
ራእይ 5፥13 *”በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ። አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት”*።
καὶ πᾶν κτίσμα ὃ ἐν τῷοὐρανῷ καὶ ἐπὶ τῆςγῆς καὶ ὑποκάτω τῆςγῆς καὶ ἐπὶ τῆςθαλάσσης, καὶ τὰ ἐναὐτοῖς πάντα, ἤκουσαλέγοντας, Τῷκαθημένῳ ἐπὶ τῷθρόνῳ καὶ τῷ ἀρνίῳ ἡεὐλογία καὶ ἡ τιμὴ καὶἡ δόξα καὶ τὸ κράτοςεἰς τοὺς αἰῶνας τῶναἰώνων. καὶ τὰ τέσσαρα ζῷαἔλεγον, Ἀμήν: καὶ οἱπρεσβύτεροι ἔπεσανκαὶ προσεκύνησαν.

እዚህ አንቀጽ ላይ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም” በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአንድ አምላክ እና ለበጉ ቀርቧል። ግን “አምልኮ” ቀርቧል የሚል ሽታው የለም። ይልቁንም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ለመለየት “ካይ” καὶ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር ይጠቀማል። ሲጀመር ምስጋና የተገባው ማንነት ሁሉ አምልኮ ቀረበለት ብሎ መደምደም ስህተት ነው፥ ምስጋና የሚገባው ያህዌህ ቢሆንም ለቅኖች እና በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባቸዋል፦
መዝሙር 18፥3 *”ምስጋና የሚገባውን ያህዌህ እጠራለሁ”*፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
መዝሙር 33፥1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ *”ለቅኖች ምስጋና ይገባል”*።
1ኛ ጴጥሮስ 2፥19 በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ *”ምስጋና ይገባዋልና”*።

በጉ ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ተገባው ማለት ትህትና ተገባው ማለት ነው፥ ምክንያቱም ትሕትናና ባለጠግነት፣ ክብር፣ ሕይወትም ነው፦
ምሳሌ 22፥4 *”ትሕትና እና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው*።

ክብር ለነገሥታት የሚሰጥ አንድ አምላክ ነው፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ተብሏል፦
ዳንኤል 2፥37 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና *”ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ”* የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።
ሮሜ 13፥7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ *”ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ”*።

እንግዲህ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው እነዚህ አካላት እየተመለኩ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ሲቀጥል አንድ ነቢይ ከአንዱ አምላክ ጋር ምስጋና ክብር ተቀበለ ማለት ያን ነቢይ መመለክ ይገባዋል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከተቻለ ዳዊት ተመላኪ ነበር ማለት ነው፦
1 ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ አምላካችሁን ያህዌህን ባርኩ፡ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ ያህዌህን ባረኩ፥ *”ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ”*።

ጉባኤውን ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ ማለት ዳዊት ከያህዌህ ጋር ተሰግዶለታል። እና ዳዊት አምልኮ ተቀብሏልን? አይ፦ “ስግደት የአምልኮ ክፍል እንጂ ስግደት በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ሲሆን ለዳዊት የጸጋ ነው” ከተባለ እንግዲያውስ ምስጋና ክብር የአምልኮ ክፍል እንጂ ምስጋና ክብር በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ምስጋና ክብር ሲሆን ለበጉ የጸጋ ምስጋና ክብር ነው።
ሢሰልስ “ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት” ይላል፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለአብና ለወልድ ቢሆን ኖሮ “ሰገዱላቸው” ይባል ነበር። ነገር ግን ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለበጉ ሳይሆን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 19፥4 ሀያ *”አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ፡ እያሉ ሰገዱለት”*።
ራእይ 4፥10 *”ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ*።
ራእይ 11፥16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ *”ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ”*፡

ሲያረብብ በጉ መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጽሐፍ መቀበሉ በራሱ በጉ እና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ናቸው፦
ራእይ 5፥7 *”መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው”*።
ራእይ 5፥13 *”በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና καὶ ለበጉ”* ይሁን ሲሉ ሰማሁ።

“ካይ” καὶ ማለት “እና” ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 6፥16 ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ *”በዙፋንም “ከ”ተቀመጠው ፊት እና “ከ”በጉም ቍጣ ሰውሩን፤
ራእይ 7፥10 በታላቅም ድምፅ እየጮሁ፦ *”በዙፋኑ ላይ “ለ”ተቀመጠው ለአምላካችን እና “ለ”በጉ ማዳን ነው”* አሉ።

“ከ” እና “ለ” የሚለው መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ በተባለው እና በጉ በሚለው መነሻ ቅጥያ ሆኖ ሁለቴ መምጣቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉ ሁለት ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ምንነቱ ጌታ አምላክ መባሉ ኢየሱስ ደግሞ በግ መባሉ ሁለት ምነነቶች እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 21፥22 *”ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና”* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ “ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እና “በጉ” ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት “ናቸው” በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም “እና” በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እና “በጉ” ሁለት ኑባሬ ናቸው። እንደ ባይብሉ በግ የሚታረድ ስጋ ስለሆነ ስጋ ደግሞ አምልኮ አይገባው። በነገራችን ላይ “በግ” የሚለውን ተርም እኛ ሙሥሊሞች አንቀበለም። ዋናው ነጥባችን ኢየሱስ አምልኮ አይገባውም ነው።

ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Jan, 16:56


https://tiriyachen.org/አንዱ-ተመላኪ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Jan, 14:48


Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Jan, 14:48


አንዱ ተመላኪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ኢየሱስ ለሰይጣን፦ "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና" ብሎታል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው፦
ራእይ 5፥12 በታላቅም ድምፅ፦ *"የታረደው በግ"* ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፥ አሉ።

መለኮት የሆነው ጌታ አምላክ ስጋ ስላልሆነ መቼም አይታረድም። እንደ ባይብሉ የታረደው በግ ሰው የሆነው ኢየሱስ ከሆነ ሰው አይመለክም፦
ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦
ራእይ 7፥15 ስለዚህ *"በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል"*።
ራእይ 7፥17 በዙፋኑ መካከል ያለው *"በጉ እረኛቸው ይሆናልና"*።

ልብ አድርግ "አውቶ" αὐτῷ ማለትም "እርሱ"him" የሚለው ተክቶ የመጣው "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል ነው፥ "ያመልኩታል" የተባለው በግልጽና በማያሻማ "እግዚአብሔርን" ነው። በጉ ከእግዚአብሔር በሰዋሰው አቀማመጥ ተነጥሎ "እረኛቸው ይሆናልና" የተባለው።
አንዳንድ ቂሎች፦ "የእግዚአብሔር እና የበጉ ዙፋን አንድ ዙፋን ነው፥ ስለዚህ በጉ ይመለካል" ይላሉ፥ ለመሆኑ ሰለሞን የተቀመጠበት ዙፋን የማን ነው የእግዚአብሔር ወይስ የዳዊት? እስቲ እንመልከት፦
1ኛ ዜና 28፥5 *በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን* ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
1ኛ ዜና 29፥23 *"ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ"*፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

የዳዊት ዙፋን የእግዚአብሔር ዙፋን ነው፥ ዳዊትም ሆነ ሰለሞን የተቀመጡት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ነው። ታዲያ የእግዚአብሔር እና የዳዊት ዙፋን አንድ ስለሆነ ዳዊት ይመለካልን? እንደ ባይብሉ ኢየሱስም የተሰጠው ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

በእግዚአብሔር እና በበጉ ዙፋን ላይ ከኢየሱስ ጋር የሚቀመጡ አማንያንም ጭምር ናቸው፦
ራእይ 3፥21 እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ *"ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ"*፥ ድል ለነሣው *"ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ"* ዘንድ እሰጠዋለሁ።

በዙፋኑ ላይ የሚቀመጡት አማንያንስ ይመለካሉን? ሲጀመር ኢየሱስ ዙፋኑን ከጌታ አምላክ በስጦታ ያገኘው ነው፥ ሲቀጥል እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውን ነገር ሁሉ ለአማንያንም ይሰጣል፦
ሮሜ 8፥32 *"ከእርሱ ጋር ደግሞ "ሁሉን ነገር" እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?*

"ሁሉን ነገር" የሚለው ይሰመርበት። ለወልድ የተሰጠው "ሁሉ ነገር" እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ሁሉን ነገር ለአማንያን ይሰጣል። ለምሳሌ ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን ወዘተ። ኢየሱስ ምንም የራሱ ነገር የለውም። ሁሉንም በስጦታ ያገኘው ነው፦
ሉቃስ 10፥22 *"ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል"*።
ዮሐንስ 17፥10 *"የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፥ የአንተውም የእኔ ነው"*፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።

የኢየሱስ የሆነ ሁሉ ከአብ የተሰጠው ስለሆነ "የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው" አለ፥ ግን የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ የኢየሱስ ስላልሆነ "የአንተውም የእኔ ነው" አለ እንጂ "የአንተ "ሁሉ" የእኔ ነው" አላለም። የአንተ ዙፋን የእኔ ነው ማለቱ ነው፥ የእግዚአብሔር ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው እንደማለት ነው። ከሌላ ማንነት ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን እረ ሕይወትም ሳይቀር የተሰጠው ማንነት በፍጹም አይመለክም፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ *"ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና"*።

ሕይወት አልባ የነበረውን የኢየሱስን ማንነት ሕይወት በመስጠት ወደ ህልውና ያመጣ ማንነት በእውነት ሊመለክ ይገባዋል።
ኢየሱስ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

ስለዚህ አንድ ተመላኪ አለ እርሱም ኢየሱስን መልእክተኛ አድርጎ የላከ አላህ ብቻ ነው። እርሱም፦ "እኔን ብቻ አምልኩኝ" ይላል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Tiriyachen | ጥሪያችን

31 Dec, 15:56


https://tiriyachen.org/የኢብራሂም-መንገድ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

31 Dec, 15:07


“ቀጥ ይሉ ነበር” ለሚለው የግስ መደብ የገባው “የተሐነሱ” يَتَحَنَّثُ ሲሆን ኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ በፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ ሐዲስ 3 ላይ፦ “የተሐነሱ” يَتَحَنَّثُ ማለት “የተሐነፉ” يَتَحَنَّفُ ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል፦
قوله : ( فيتحنث ) ‏
‏هي بمعنى يتحنف ، أي : يتبع الحنفية وهي دين إبراهيم ، والفاء تبدل ثاء في كثير من كلامهم . وقد وقع في رواية ابن هشام في السيرة ” يتحنف ” بالفاء أو التحنث إلقاء الحنث وهو الإثم ، كما قيل يتأثم ويتحرج ونحوهما .

ልብ አድርግ የኢብራሂም መንገድ አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ኢሥላም ነው፥ ሲቀጥል አላህ በኢብራሂም ዝርዮች ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አድርጓል፦
43፥28 *”በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት”*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ የኢብራሂም ዝርያ ናቸው። ከዚያ በኃላ አላህ ቁርኣንን በማውረድ “ቁል” قُلْ በሚል ትእዛዝ የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን መራቸው፦
6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት “ቀጥተኛ” ሲኾን የኢብራሂምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል”*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
10፥105 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ”*፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ይህ ዲን ሐኒፋ የሆነው ኢሥላም እንደሆነ እና ኢሥላም ማለት መታዘዝ ማለት እንደሆነ ከላይ አይተናል፥ ቁርኣን ደግሞ “ትእዛዝ” ሆኖ ወደ እርሳቸው ወርዷል፦
65፥5 *”ይህ “የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው”*። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ

ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
6፥14 *«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ*”፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት። “ትእዛዝን የተቀበለ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ “አወል” أَوَّل ማለትም “መጀመሪያ” በአንጻራዊነት ደረጃ የመጣ ገላጭ ነው። እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ ከሠለሙት ሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን”ﷺ” ናቸው ማለት ነው፦
6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *”«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ»* በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

“ሰጠሁ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ሲሆን እርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው ሁለንተናቸውን ለአላህ ያሠለሙ መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ነቢያችን”ﷺ” ከአላህ ወደ እርሳቸው በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፥ ተከታዮቻቸውም እንደዚሁ አመኑ፦
2፥285 *”መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ”*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

“ሙዕሚኑን” مُؤْمِنُون ማለት አማኞች ማለት ነው። “ኢማን” إِيمَان ማለት “አመነ” آمَنَ ማለትም “አመነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እምነት” ማለት ነው። ቁርኣን ትእዛዝ ሆኖ ወደ ነቢያችን”ﷺ” ከመውረዱ በፊት ቁርኣንን ሆነ በቁርኣን ላይ እምነቱ ምን እንደሆነ ዐያውቁም ነበር፦
42፥52 እንደዚሁም *”ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም”*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيم

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

31 Dec, 15:07


የኢብራሂም መንገድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥123 *ከዚያም ወደ አንተ፦ “የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል! ከአጋሪዎቹም አልነበረም” ማለት አወረድን*፡፡ ثُمَّ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ أَنِ اتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለትም “መታዘዝ” ወይም “መገዛት” ማለት ሲሆን አላህ ዘንድ ዕውቅና ያለ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *”አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው”*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም ነው፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አምላካችን አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፥ ኢብራሂም ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ፦
2፥131 *”ጌታው ለእርሱ “ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ”*፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
3፥67 *”ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን “ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ”፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም”*፡፡ مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” ማለት ነው፥ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ነው። “ሐኒፍ” حَنِيف ማለት “ቀጥተኛ” ማለት ሲሆን ለአላህ ቀጥ ያሉ “ቀጥተኞች” ደግሞ “ሑነፋ” حُنَفَاءَ ይባላሉ፦
22፥31 *”ለአላህ ቀጥተኞች በእርሱ የማታገሩ ሆናችሁ ከሐሰት ራቁ”*፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡ حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ
98፥5 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ *”ቀጥተኞች ኾነው ሊያመልኩት”*፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ተለያዩ፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌ ነው፡፡ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَة

ኢብራሂም እራሱ ሐኒፍ ሲሆን እርሱ የተጓዘበት መንገድ ደግሞ ሐኒፋ ነው፦
2፥135 አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ! ቅኑን መንገድ ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም *”የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን”*፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡፡ وَقَالُوا كُونُوا هُودًا أَوْ نَصَارَىٰ تَهْتَدُوا ۗ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሚላህ” مِلَّة ማለት “መንገድ” ማለት ነው፥ ይህም የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ነው፦
3፥95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ *”የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉ”*፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين
4፥125 *”እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው”*፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا
6፥79 *«እኔ ለእዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ*፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ሲሆን አላማው ሁለንተናን ለአላህ መስጠት ነው፥ “የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ ነው።
ነቢያችን”ﷺ” ወደ እርሳቸው ወሕይ ከመውረዱ ይህንን የኢብራሂም መንገድ ይተገብሩ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3
የምዕመናን እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *”ከወሕይ ጅማሬ ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ልክ እንደ ጎህ ንጋት ደማቅ ሆኖ በሰናይ ህልም ሁኔታ ነበር። ከዚያም የተማልሎ ውዴታ በእርሷቸው ላይ ነበር። በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና “ቀጥ ይሉ ነበር”። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህ ያመልኩ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ

Tiriyachen | ጥሪያችን

30 Dec, 17:43


https://tiriyachen.org/ሣሚሪይ/

Tiriyachen | ጥሪያችን

30 Dec, 17:43


አይ ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ቁርአን እየነገረን ያለው በሙሳ ጊዜ ስለነበረ ክስተት እንጂ በሰማርያውን ስለተከሰተው ክስተት አይደለም።
ሁለት ክስተት በተለያዩ ጊዜ ሲከናወኑ ታሪኩ አንድ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ለምሳሌ በሉጥ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
ዘፍጥረት 19፥5-9 *ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው*። *ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው*፤
እንዲህም አለ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ *ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው*፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።

ይህ ድርጊት በመሳፍንቱ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
መሣፍንት 19፥22-25 ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ *የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን፡ አሉት። ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ፡ አላቸው። ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት*።

ያ ማለት ሁለት ተመሳሳይ ክስተት ግን በተለያየ ጊዜ የሆኑ ክንውኖች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክና ልክ ተረዱት።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

30 Dec, 17:43


ሣሚሪይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ

"ሣሚሪይ" سَّامِرِىّ በሙሳ ዘመን ለእስራኢል ልጆች በእሳት አቅልጦ ወይፈን የሰራላቸው ሰው ነው፦
20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ
20:87 ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም፤ ግን እኛ ከሕዝቦቹ ጌጥ፣ ሸክሞችን ተጫን በእሳት ላይ ጣልናትም፤ *ሳምራዊውም* እንደዚሁ ጣለ አሉት። قَالُوا مَا أَخْلَفْنَا مَوْعِدَكَ بِمَلْكِنَا وَلَـٰكِنَّا حُمِّلْنَا أَوْزَارًا مِّن زِينَةِ الْقَوْمِ فَقَذَفْنَاهَا فَكَذَٰلِكَ أَلْقَى السَّامِرِيُّ
20:95 ሙሳ *ሳምራዊው* ሆይ ነገርህም ምንድነው? አለ። قَالَ فَمَا خَطْبُكَ يَا سَامِرِيُّ

እሱም የሰራላቸው አንድ ወይፈን የሆነ ጥጃ ነው፦
20፥88 ለእነሱም አካል የኾነ *ጥጃን* ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡ فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَـٰذَا إِلَـٰهُكُمْ وَإِلَـٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ
7፥148 የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው *ወይፈንን አካልን ለእርሱ ማግሳት ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን?* አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ

ይህን ትረካ በመጠኑም ቢሆን ከፔንታተች ጋር ይመሳሰላል፦
ዘጸአት 32፥7-8 ያህዌህም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ *ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም*፤፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ* ሲል ተናገረው።
ዘጸአት 32፥20 *የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው*፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።

እዚህ ጋር የተሰራው ጥጃ አንድ ጥጃ እንደሆነ ይናገራል፤ ሰሪውም አሮን ነው ብሎ ያስቀምጣል፤ "ሣሚሪይ" سَّامِرِىّ በዕብራይስጥ "ሳንበርይ" זִמְרִי በአማርኛ "ዘንበሪ" የተባለው ሰው ነው፦
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች ሁለት የተለያዩ ታሪኮችን በማታታት ቁርአን የታሪክ ግድፈት እንዳለበት ለማሳየት ሲያምታቱ ይገኛሉ። "ሳንበርይ" זִמְרִי ማለትም "ዘንበሪ" የተባለውን ስም "ሰማሪይ" שומרון‎ ማለትም "ሰማሪያ" ጋር ደባልቀው ቁርኣን፦ "በሙሳ ዘመን ጥጃ ሰራ የሚለው ግለሰብ የሰማሪያ ሰዎችን ነው" ብለው ለመጠምዘዝ ይሞክራሉ፤ በ 930 BC በአስሩ ነገድ ይኖር የነበረው ዘንበሪ የተባለው ንጉሥ ሳምርም ከሚባል ሰው በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው፦
1ኛ ነገሥት 16፥24 *ከሳምርም* በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት *በሳምር* ስም *ሰማርያ* ብሎ ጠራው።

ከዚያ በኃላ ያሉ ሕዝቦች "ሳምራውያን" ሲባሉ ወንዱ "ሳምራዊ" ሴቷ "ሳምራዊት" ይባላሉ፦
ሉቃስ10፥33 አንድ *ሳምራዊ* ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
ሉቃስ 17፥16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም *ሳምራዊ* ነበረ።
ዮሐንስ 4፥9 ስለዚህ *ሳምራዊቲቱ*፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን *ሳምራዊት* ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ *ከሳምራውያን* ጋር አይተባበሩም ነበርና።
ዮሐንስ 8፥48 አይሁድ መልሰው፦ *ሳምራዊ* እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን? አሉት።

ይህንን እሳቤ ከያዝን ሳምራውያን ከጊዜ በኃላ የአስሩ ነገዶች መጠሪያ ሆነ፤ ሳምራውያን ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ በኣልንም አመለኩ፤ የሰሯቸው አማልክት ብዙ ናቸው፦
2 ነገሥት 17፥16 የአምላካቸውንም የያህዌን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፥ *ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ*፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ *በኣልንም አመለኩ*።
2 ነገሥት 17፥29 *በየሕዝባቸውም አምላካቸውን አደረጉ፥ ሰምራውያንም በሠሩት በኮረብታው መስገጃዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚኖሩበት ከተሞቻቸው አኖሩአቸው*።

ታዲያ ይህ ታሪክ በየትኛው ቀመርና ስሌት ነው ከቁርአን ጋር የሚመሳሰለው? ሲጀመር ከመነሻው "ሳንበርይ" זִמְרִי የተባለውን ስም እና "ሰማሪይ" שומרון‎ የተባለው ስም አንድ ነውን? ሲቀጥል በሙሳ ጊዜ የነበረው ሳንበርይ አንድ ግለሰብ ሲሆን ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ በኃላ አማልክት የሰሩት ሳምራውያን ደግሞ ሕዝብ ናቸው፤ ሲሠልስ ቁርኣን ልክ እንደ ዘጸአት በሙሴ ጊዜ ተሰራ የሚለን አንድ ጥጃ ነው፤ ነገር ግን በተቃራኒው ሳምራውያን የሰሩት የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች ናቸው።

ጥያቄ፦ እስራኤላውያው በምድረ በዳ ያሉት የቱን ነው? "ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው" ወይስ "ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው" ?
ነህምያ 9፥18 ቀልጦ የተሠራውንም እምቦሳ አድርገው፡— *ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው* ባሉ ጊዜ፥ እጅግም ባስቈጡህ ጊዜ፥
ዘጸአት 32፥4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው*፡ አላቸው።

ዘንበሪ ይኖር የነበረው በማን ዘመን ነው? በሙሴ ወይስ በይሁዳ ንጉሥ በአሳ?
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤
1ኛ ነገሥት 16፥23 በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት *ዘንበሪ* በእስራኤል ላይ አሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ።

Tiriyachen | ጥሪያችን

18 Nov, 05:25


🎙 የድምፅ ትምህርት | 11 MB

ተጸጸተ

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

በዓቃቢ ኢስላም ወሒድ

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

17 Nov, 17:52


አባት እና ልጅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ኣብ” אַבָּא ማለት በዕብራይስጥ “አስገኚ”orginator” ማለት ሲሆን በግዕዝ “አብ” ማለት “አባት” ማለት ነው፤ የአብ ተመሳሳይ ትርጉም “አባ” ሲሆን “አባት” ማለት ነው፤ “አበው” የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን “አባቶች” ማለት ነው።
በመጀመሪያ መደብ፦
“አቡየ” ማለት ነጠላ ሲሆን “አባቴ” ማለት ነው፤ “አቡነ” ማለት “አባታችን” ማለት ነው።
ሁለተኛ መደብ፦
“አቡከ” ለወንድ ሲሆን “አባትህ” ማለት ነው፤ “አቡኪ” ለሴት “አባትሽ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡክሙ” ማለት “አባታችሁ” ሲሆን ለሴት “አቡክን” ማለት “አባታችሁ” ነው።
ሦስተኛ መደብ፦
“አቡሁ” ለወንድ ሲሆን “አባቱ” ማለት ነው፤ “አቡሃ” ለሴት “አባቷ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡሆሙ” ማለት “አባታቸው” ሲሆን ለሴት “አቡሆን” ማለት “አባታቸው” ነው። ይህንን ካየን ዘንዳ የሚገርመው አበይት ክርስቲያኖች ማለትም ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና አንግሊካን፦ “ኢየሱስ አብ ሳይሆን ወልድ ብቻ ነው” ይላሉ፤ ትክክል! ምክንያቱም ኢየሱስ የእራሱን ማንነት ከአብ ነጥሎ አስቀምጧል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም*፤ ስለ እኔ የሚመሰክር *ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።
ዮሐንስ 12፥49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*።

ወልድ ማን ነው? ስንል ኢየሱስ ይሉናል፤ አብ ማን ነው? አብ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ቆላስይስ 1፥3 *የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን* ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤
ሮሜ 15፥5 *እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ቆሮንቶስ 15፥24 በኋላም፥ መንግሥቱን *ለእግዚአብሔር ለአባቱ* አሳልፎ በሰጠ ጊዜ፤
ዮሐንስ 5፥18 *እግዚአብሔር አባቴ ነው* ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።

የኢየሱስ አባት እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፤ ምክንያቱም አብ እግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ነው፤ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት አንዱን እግዚአብሔር ነው፣ ኢየሱስም፦ “እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው” ብሏል፦
ዘዳ.6:4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው*፤
ዮሐ.8:54 *እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው*፤

ይህ አንድ አምላክ የሁሉም አንድ አባት ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ማቴዎስ 23፥9 *አባታችሁ አንዱ* እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ *ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ*።
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ* ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

አባትና ልጅ ለኢየሱስ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለመላእክት ልጅነት እና ለእግዚአብሔር አባትነት አገልግሎት ላይ ውሏል። መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስትም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር በሚል ስሌት ኢየሱስን እግዚአብሔር ካረግን መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና እግዚአብሔሮች መሆን ነበረባቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “የእግዚአብሔር አባት”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ 42 ቦታ ላይ “የእግዚአብሔር ልጅ” ብቻ ተብሏል፦
ሉቃስ 1፥35 ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ *የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “እግዚአብሔር ወልድ”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ እግዚአብሔር የሚባለው አብ ብቻ ስለሆነ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃላት 13 ቦታ እናገኛለን፦
ያዕቆብ 1፥27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ *በእግዚአብሔር አብ* ዘንድ ይህ ነው፤

ባይብሉ እግዚአብሔር እና ኢየሱስን አባት እና ልጅ አርጎ ነው የሚያስቀምጠው፤ አባት ልጅ አይደለም ልጅም አባት አይደለም ካላችሁ እግዚአብሔር ኢየሱስ አይደለም፤ ኢየሱስም እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ግህደተ-መለኮት”revelation” ማለትም “ወሕይ” ሰቶቷል፦
ራእይ 1፥1 *እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ግልጠት በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው*፥ The Revelation of Jesus Christ, which God gave unto him,
ዮሐንስ 7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ *ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ* የምናገር ብሆን ያውቃል።

“ከእግዚአብሔር ወይም እኔ ከራሴ” የሚለው ይሰመርበት፤ የሚገርመው እራሱን ከእግዚአብሔር በመለየት “እራሴ” በሚል ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun ” ተጠቅሟል፤ ትምህርቱ ከላከው ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሱ አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ግልጠት በግሪክ “አፓልካሊፕስ” Ἀποκάλυψις ይባላል፤ ኢየሱስ በአንድ እግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል እየሰማ የሚናገር ሰው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5፤ *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ሐዋ ሥራ 2፥22 *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ*፤

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገር ከአንድ እግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛና አገልጋይ ነው፦
ዮሐንስ 3፥34 *እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና*፤
ሐዋ ሥራ 3፥26፤ ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር አገልጋዩን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ላከው*። NIV

Tiriyachen | ጥሪያችን

17 Nov, 17:52


እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ ሌሊቱንም ሁሉ ሲጸልይ ያደረው ወደዚህ ወደ አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ይህ አንድ እግዚአብሔር ኢየሱስን ቀብቶታል፤ ለዲያብሎስም የተገዙትን እንዲፈውስ እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ነበረ፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ *ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።
ሐዋ ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ *እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና*፤

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ ማለትም የበላይ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1 ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለምትሉ አልቆላችኃል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት ነው ተብላችኃል፤ ኢየሱስ ደግሞ አብ አይደለም ብላችኃል።
ስለዚህ ኢየሱስ አብ ማለትም እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርም ወልድ ማለትም ኢየሱስ ሳይሆን አብ”አባት” ነው።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

15 Nov, 13:01


አባት እና ልጅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ዋሊዳእ” وَٰلِدَي ማለት “ወላጅ” ማለት ነው፤ አባት የሆነ ወላጅ “ዋሊድ” وَالِد ወይም “መውሉድ” مَوْلُود ሲባል እናት የሆነች ወላጅ ደግሞ “ዋሊዳ” وَٰلِدَٰت ወይም “ዋሊደ” وَٰلِدَة ትባላለች፤ ከወላጅ የሚገኝ ልጅ ደግሞ “ወለድ” وَلَد ወይም “ወሊድ” وَلِيد ይባላል፤ ሁሉም የስም መደብ የመጡት “ወለደ” وَلَدَ ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው። አላህ ፃታ የለውም፤ ወንድም ሴትም አይደለም፤ አባት ሆኖ አልወለደም ልጅ ሆኖ አልተወለደም፦
112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስ ልጅ ሲሆን አባቱ እግዚአብሔር ነው ይላሉ፤ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው የሚል እሳቤ አላቸው፤ “ተወለደ” ሲባል “ተገኘ” ማለት ነው ይሉናል፤ አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ማለት ነው፤ በ 325 AD የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
በግሪክ፦
Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,
በግዕዝ፦
“ብርሃን ዘእም-ብርሃን፤ አምላክ ዘእም-አምላክ”
በአማርኛ፦
*“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ”* ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።
የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”
ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*
ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በገቢር ሁለት አብ ማን ነው? ወልድ ማን ነው? የሚለውን እናብራራለን።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

14 Nov, 18:20


የነብያችን "ﷺ" ስርወ ግንድ | ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/l8fAobLra5o

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

14 Nov, 08:09


https://tiriyachen.org/hijab/

Tiriyachen | ጥሪያችን

13 Nov, 19:58


ሒጃብ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡
ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡
وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

"ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ" "መሸፋፈኛ" "መጋረጃ" "ግርዶ" ማለት ነው፦
19፥17 ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች፡፡
فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا
እዚህ አንቀጽ ላይ መርየም እንዳያዩአት ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሎ ተቀምጧል። ሒጃብ ሙሥሊም ሴት የምትሰተርበት ኺማር እና ጂልባብ ነው፦
24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡
وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ
"ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው። ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759
ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንደተረከችው፦ "ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንዲህ ትል ነበር፦ "ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"።
عَنْ صَفِيَّةَ بِنْتِ شَيْبَةَ، أَنَّ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقُولُ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ‏}‏ أَخَذْنَ أُزْرَهُنَّ فَشَقَّقْنَهَا مِنْ قِبَلِ الْحَوَاشِي فَاخْتَمَرْنَ بِهَا‏.‏

"ኒቃብ" نِقَاب ማለት "መሸፈኛ" ማለት ሲሆን "ጉፍታዎች" በሌላ አንቀጽ "መከናነቢያዎች" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
እዚህ አንቀጽ ላይ "መከናነቢያዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ጀላቢብ" جَلَٰبِيب ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ጂልባብ" جِلْبَاب‎ ነው።
በባይብል ውስጥ ይስሐቅም ርብቃን ከማግባቱ በፊት አጅነቢይ ስለነበረ እንዳያያት ኺማር ወስዳ ተከናነበች፦
ዘፍጥረት 24፥65  "እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች"።
فَأخَذَتْ رِفقَةُ الخِمارَ وَغَطَّتْ وَجهَها

እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ኺማር" خِمارَ ሲሆን "ፊቷን" ለሚለው የገባው ቃል "ወጀሀሃ" وَجهَها ነው፥ ርብቃ በሒጃብ የተሰተረችው ፊቷን ነው። በእስራኤል ሴቶቹ ዓይናቸውን በኒቃብ ይሸፈኑ ነበር፥ ንጉሥ ሰለሞን የሱላማጢስ ልጃገረድን በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖች እና ጕንጭና ጕንጯ እንዳሉ መናገሩ በኒቃብ ፊታቸው እና ዓይናቸው ይሰተሩ እንደነበር አመላካች ነው፦
መኃልይ 4፥1 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው።
عَيْنَاكِ حَمَامَتَانِ مِنْ تَحْتِ نَقَابِكِ
አንቀጹ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ነቃቢኪ" نَقَابِكِ ሲሆን "ኒቃብ" نِقَاب በጥንትም ፊትን መሸፈኛ ነው፥ እዚሁ ዐውድ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ሒማሪኪ" خِمارِكِ ነው፦
መኃልይ 4፥3 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
كَفَلَقَةِ رُمّانَةٍ هُوَ خَدُّكِ تَحتَ خِمارِكِ
የሱላማጢስ ልጃገረድን ሒጃቧትን ልክ እንደ ኢትዮጵያዊያን ሴት ሙሥሊሞች ቅጥር ጠባቂዎች እንደወሰዱባት መናገሯ በራሱ ሒጃብ ታደርግ እንደነበር ማሳያ ነው፦
መኃልይ 5፥7 ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።
وَنَزَعَ حُرّاسُ الأسوارِ خِمارِي عَنِّي
እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ኺማር" خِمَار እንደሆነ ልብ አድርግ! ሴት ራስዋን በኺማር ሳትሸፍን ወደ ፈጣሪ ልትጸልይ አይገባትም፥ ሴት አማኝ ሁሉም ቦታ እንድትከናነብ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥13 በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት "ራስዋን ሳትሸፍን" ወደ አምላክ ልትጸልይ ይገባታልን?
ዲድስቅልያ 3፥32 ነገር ግን ላመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽህና “ሊከናነቡ” ይገባል። እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ!።
በግዕዝ "ዲድስቅሊያ" በውጪው ዓለም "ዲዳኬ"Didache" ከ 60-85 ድኅረ ልደት የተዘጋጀ የሐዋርያት ትምህርት ነው፥ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን 35 ከምትላቸው የቀኖና መጻሕፍት አንዱ ነው። "እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ" የሚለው ይሰመርበት! ታዲያ ለምን ይሆን ክርስቲያን ሴት ተገላልጣ በጎዳና ላይ የምትሄደው? መልሱ መጽሐፉን ለትራስነት እንጂ አያነቡትም፥ ያነበቡትም የሚከተሉት መጽሐፉን ሳይሆን የምዕራቡን ርዕዮት እና እሳቦት ነው። መራቆትን እንደ መሰልጠን መሰተርን እንደ ኃላ ቀርነት ለሚቆጥሩት አሏህ ቀልብ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍️ በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
Telegram፦https://t.me/tiriyachen
Facebook፦https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩምወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

01 Nov, 17:38


የማይተኛ አምላክ | ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/PI_hNh4DJWQ

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

19 Oct, 16:52


ዕሩቅ ብእሲ | ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/F_j1TQZK0_o

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

26 Sep, 15:39


የመስቀል አምልኮ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ! እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ዘርዓ ያዕቆብ ከደረሳቸው መጻሕፍት አንዱ መስተብቁዕ ዘመስቀል ነው፥ መስተብቁዕ ዘመስቀል ላይ መስቀል እና ማርያም ከፈጣሪ ጋር ተካክለው ምስጋና እንደሚቀርብላቸው ይናገራል፦
መስተብቁዕ ዘመስቀል ቁጥር 8
"ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተዐረዩ በክብሮሙ"

"ለእነዚህ ሁለት ፍጥረታት የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል፥ በክብር ተካክለዋልና"

"ሁለቱ" የተባሉት "መስቀል እና ማርያም" ሲሆኑ እነዚህ ሁለት ፍጡራን ከፈጣሪ ጋር "በክብር ተካክለዋል" ይለናል፥ ኢየሱስን፦ "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ(በባሕይርው ከአብ ጋር የሚተካከል)" ሲሉት ሲገርመን ማርያም እና መስቀልን "እስመ ተዐረዩ በክብሮሙ(በክብር ተካክለዋል)" ሲሏቸው አስደመመን። ስለተስተካከሉ ለፈጣሪ የሚገባው የፈጣሪ ምስጋና "ይገባቸዋል" ብለው አረፉት፥ ይህ እልም ያለ ሺርክ ነው። ስብሐት ለሦስቱ ማለትም ለእግዚአብሔር፣ ለድንግል እና ለመስቀል እንደሚገባ የዘወትር ጸሎት ላይ ተገልጿል፦
የዘወትር ጸሎት ቁጥር 9
"ስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር"

ትርጉም፦ "ለእግዚአብሔር፣ ለወለደችው ለድንግል እና ለክቡር መስቀሉ ምስጋና ይገባል"

መስቀል ከመመስገንም አልፎ ይሰገድለታል፦
የዘወትር ጸሎት ቁጥር 8
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”

ትርጉም፦ “በደሙ ክቡር “ለ”ተሰቀለበት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እሰግዳለው”

እንደ ትምህርታቸው ኢየሱስ የተሰቀለበት እና ደሙን ያፈሰሰበት እንጨት እኮ አንድ ነው፥ ዛሬ በእጃቸው የሚያሳልሙበት እና በጉልላት ላይ የሚሰቅሏቸው መስቀሎች የተሰቀለባቸው፣ ደም የፈሰሰባቸው እና ወዝ የተንጠፈጠፈባቸው ስላልሆኑ በምንም ሒሣብ ክቡር አይደሉም።
የሚገርመው መስከረም 17 ቀን "ዮም መስቀል ተሰብሐ" ማለትም "ዛሬ መስቀል ተመሰገነ" በማለት ካመሰገኑት በኃላ መልሰው በደመራ ያቃጥሉታል። "የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፣ አታምልካቸውምም" እየተባለ ለማይሰማ እና ለማይለማ፥ ለማይናገር እና ለማይጋገር ለግዑዝ እንጨት የጸጋ ስግደት መስገድ አግባብ አይደለም፥ ይህ ድርጊት አሳፋሪ እንደሆነም ተገልጿል፦
ዘጸአት 20፥4 የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ! አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም።
መዝሙር 97፥7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ።

"ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" የሚለው ይሰመርበት! እኛም ሙሥሊሞች የምንለው ደግሞ "የፈጠራችሁን አሏህን ብቻ አምልኩ" ነው፦
11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ! እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

የፈጠረንን አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
Telegram፦https://t.me/tiriyachen
Facebook፦https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

21 Sep, 13:44


5፥91 ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፤ አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን ተከልከሉ፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ

"ነቢዝ" نَّبِيذ ማለት ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚጠጣ ጭማቂ"juice" ነው፥ እርሱን መጠጣት ሐላል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 81
ዐብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህ አባቱ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ "በኮዳ በስተቀር ከነቢዝ የሚዘጋጅ ነገር እንዳትጠጡ ከልክያችሁ ነበር፥ ግን አሁን በሁሉም ሰፍነግ መጠጣት ትችላላችሁ። ነገር ግን አስካሪ መጠጥ እንዳትጠጡ። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُرَيْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَهَيْتُكُمْ عَنِ النَّبِيذِ إِلاَّ فِي سِقَاءٍ فَاشْرَبُوا فِي الأَسْقِيَةِ كُلِّهَا وَلاَ تَشْرَبُوا مُسْكِرًا ‏”‏

ይህ ጭማቂ ከሁለት ቀናት አሊያም ከሦስት ቀናት በኃላ ስለሚቆመጥጥ ሙሥኪር ይሆናል፥ ሙሥኪር መጠጣት ሐራም ነው። አይደለም ኸምር ጠጪው ይቅርና ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፦
ሡነንን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 6:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ ኸምርን ጠጪውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ረግሟቸዋል"። أَنَّهُمَا سَمِعَا ابْنَ عُمَرَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَعَنَ اللَّهُ الْخَمْرَ وَشَارِبَهَا وَسَاقِيَهَا وَبَائِعَهَا وَمُبْتَاعَهَا وَعَاصِرَهَا وَمُعْتَصِرَهَا وَحَامِلَهَا وَالْمَحْمُولَةَ إِلَيْهِ ‏”‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 1:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "የሚያሰክር ነገር ሁሉ ኸምር ነው፤ የሚያሰክር ነገር ሁሉ ሐራም ነው፡፡ በዱኒያህ ኸምርን የጠጣ እና በእሷም ላይ ዘውትሮ ሳይቶብት የሞተ ሰው በአኺራ የጀነቷን አይጠጣትም"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ شَرِبَ الْخَمْرَ فِي الدُّنْيَا، ثُمَّ لَمْ يَتُبْ مِنْهَا، حُرِمَهَا فِي الآخِرَةِ ‏”‌‏.‏

አሏህ ከአስካሪ መጠጥ እና በአስካሪ መጠጥ ከሚመጣ ጥፋት ይጠብቀን! አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

21 Sep, 13:44


አስካሪ መጠጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

"ኸምር" خَمْرየሚለው ቃል "ኸመረ" خَمَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ "የሚሸፍን" "የሚደብቅ" "የሚሰውር" ማለት ነው፥ እኅቶቻችን ከሚሰተሩበት ሒጃብ መካከል "ጉፍታ" እራሱ በቁርኣን "ኺማር" خِمَار ይባላል፦
24፥31 ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ። وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም አስካሪ መጠጥ”alcohol" ሁሉ “ኸምር” خَمْر ይባላል፦
2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ስለሆነ ለሰዎች ጥቅም አለው፥ አስካሪ መጠጥ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው፥ አስካሪ መጠጥ ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ዑመር በአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ ”ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የሚሰውር” ለሚለው የገባው ቃል “ኻመረ” خَامَرَ መሆኑ ልብ አድርግ! አስካሪ መጠጥ አእምሮን የሚያስት እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ”፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው” ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ ‏”‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው”። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ ‏”‏

“ሙሥኪር” مُسْكِر የሚለው ቃል “ሠኪረ” سَكِرَ
ማለትም "ሰከረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሚያሰክር" "የሚያነፍዝ" ማለት ነው፥ “ሠከር” سَكَر እራሱ “አስካሪ”intoxicant” ማለት ሲሆን “ሡክር” سُكْر ደግሞ “አስካሪነት”intoxication” ማለት ነው። ኸምር ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚሠራ ጠጅ ነው፦
16፥67 ከዘምባባዎች እና ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፡፡ ከእርሱ ጠጅን እና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ፡፡ وَمِن ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

አሏህ ከዘንባባ እና ከወይን ፍሬ ማብቀሉ በእርግጥ ታምር አለበት፥ ከዚህም ሰው በሠናይ መልካም ምግብ ማለትም ጭማቂ ሲሠራ በተቃራኒው እኩይ የሆነውን አስካሪ ጠጅን ይሠራል። "ዛሊከ" ذَٰلِكَ ማለትም "በዚህም" የተባለው ኢሥሙል ኢሻራህ ከበፊቱ ያለው "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የተባለው ዶሚሩል ሙንተሲል የሚያመለክት ነው፥ ይህም "እርሱ" የተባለው ፍራፍሬው ነው፦
16፥11 "በ"-"እርሱ" ለእናንተ አዝመራን፣ ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ። يُنبِتُ لَكُم بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ የተባለው የአዝመራን፣ የወይራንም፣ የዘምባባዎችንም፣ የወይኖችንም ፍራፍሬ ነው። ተጨማሪ አናቅጽ፦ 6፥99 13፥3 ይመልከቱ!
ፍራፍሬ ሲቆይ ስኳርነቱ ወደ አሲድ ይቀየርና ቆምጣጣነት"Fermentation" ሢሠራ ወይም ጌሾና ብቅል ሲቀላቀልበት ፓስቸራዜሽን”Pasteurization” እና ኒዩትራላይዜሽን”Neutralization” በመሆን ያሰክራል፥ ቢራ ፣ ቮድካ፣ ውስኪ የመሳሰሉት የዛ ውጤት ናቸው። አስካሪ መጠጥ አዕምሮን የሚያደንዝ እና ለጥል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለጣዖት አምልኮ የሚዳርግ፣ ከሶላት እና አሏህ ከማውሳት የሚያዘናጋ እኩይ ነገር ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Sep, 15:17


🎙 የድምፅ ትምህርት | 7 MB

የማይተኛው አምላክ

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

በዓቃቢ ኢስላም ወሒድ

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Sep, 13:32


لاَ يُؤْمِنُونَ حَتَّى يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ‏}‌‏.‏

ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው በፍትሓዊነት የመስኖ ባለቤቱ ከተጠቀመ በኃላ ተፋሰሱን ለጎረቤት መልቀቅ እንዳለበት ነው። ይህንን ይዘን እኛ ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልገንን የኃይድሮ ኤሌትሪክ ሆነ የአግሮ ኢንዱስትሪ ግድብ ተጠቅመን ማንንም ሳንጎዳ ለጎረቤታችን ለግብጽ መልቀቅ ፍትሓዊነት እና ሐዲሳዊ ሡናህ ነው። አምላካችን አላህ በሰዎችም መካከል በፈረድን ጊዜ በትክክል እንድንፈርድ ስላዘዘን ይህንን ፈርደናል፦
4፥58 *"አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:

https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachenn

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

09 Sep, 13:32


የዐባይ ወንዝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥58 *"አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا

“ዐድል” عَدْل የሚለው ቃል “ዐደለ” عَدَلَ ማለትም “አስተካከለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስተካከል” “ፍርድ” “ፍትሕ” ማለት ነው፥ “ዐዲል” عَادِل‎ ማለት “ፍትሓዊ” ማለት ሲሆን “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለት ደግሞ “ፍትሐዊነት” ማለት ነው። አምላካችን አላህ በፍትሕ ያዛል፥ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ማስተካከል” ለሚለው ቃል የገባው “ዐድል” عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። የፍትሕ ተቃራኒ ዙልም ነው፥ “ዙልም” ظُلْم የሚለው ቃል “ዞለመ” ظَلَمَ ማለትም “በደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በደል” ማለት ነው። “ከሚጠላ ነገር ሁሉ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አላህ ዘንድ የሚጠላ ነገር ሺርክ፣ ኩፍር፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ብሔርተኝነት፣ ዘውገኝነት ነው። የአንድን ሰው ዘውግ፣ ብሔር፣ ዘር መጥላት በራሱ በደል ነው። ሰውን በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በዘውጉ፣ በብሔሩ መጥላት የፍትሕ ተቃራኒ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

አሁንም “አስተካክሉ” ለሚለው የገባው ቃል “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا መሆኑ ልብ በል። “ሕዝቦችን መጥላት” ወደ ፍትሕ አልባ ይገፋፋል፥ ፍትሕ ግን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። በፍትሕ የሚጠላ ነገር ሁሉ ለአላህ ብሎ ጠልቶ መከልከል ከመበደል ይታደጋል። ክፉ ነገር ከልባችን መጥላት ፍትሓዊነት ነው፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ቁርኣንን እና ሐዲስን ሚዛን ይዘን ስለ ዐባይ ወንዝ ጉዳይ እየመጣ ያለውን እኩይ ነገር በአፋችን እናወግዛን አሊያም በልባችን እንጠላዋለን።
“ግዮን” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ጊሖን” גִּיח֑וֹן ሲሆን “ፏፏቴ” ማለት ነው፥ ይህንን የግዮን ወንዝ በአገራችን “ዐባይ” ማለትም “ታላቅ” ይሉታል። ግሪኮች ይህንን ወንዝ “ኒሉስ” Νεῖλος ይሉታል፥ “የወንዝ አምላክ” ማለት ነው። ነጭ ዐባይ ከኡጋንዳ ቪክቶሪያ ከሚባል ሃይቅ ይመነጫል፥ ጥቁር ዐባይ ከኢትዮጵያ ጣና ከሚባል ሃይቅ ይመነጫል። ሁለቱም ካርቱም ሱዳን ላይ ይገናኙና ሱዳንን ይከብና በግብጽ ካይሮ ሜድትራኒያን ባሕር ይገባል። የዐባይ ተፋሰስ ወንዝ ለግብጽ መጠቀሚያ ነው፥ ነገር ግን ሰሞኑን በዚህ ዙሪያ የይገባኛል ጉዳይ ትልቅ የፓለቲካ ውጥረት በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል አለ። ይህንን ነጥብ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ እናቅርበው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 8
ዐብደሏህ ኢብኑ አዝ-ዙበይር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"የአንሷር ሰው በነቢዩ"ﷺ" ፊት ስለ የዘንባባ መስኖ ስለሚያጠጡ የኸራህ ቦዮች ከአዝ-ዙበይር ጋር ተጨቃጨቀ። ጭቅጭቁ፦ የአንሷር ሰው ለአዝ-ዙበይር፦ "ውኃው ይለፍ" አለው፥ ነገር ግን አዝ-ዙበይር ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። ጉዳዩ ወደ ነቢዩ"ﷺ" ሲቀርብ እሳቸው ለአዝ-ዙበይር፦ "አዝ-ዙበይር ሆይ! መስኖህን አጠጣ ከዚያ ለጎረቤትህ ልቀቅ" አሉት። በጉዳዩ የአንሷሩ ሰው ተቆጣና ለእርሳቸው፦ "እርሱ(አዝ-ዙበይር) የአክስትህ ልጅ ነውን? አላቸው፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" የፊታቸው ከለር ተቀየረ። እርሳቸውም ለአዝ-ዙበይር፦ "አዝ-ዙበይር ሆይ! መስኖህን አጠጣ ከዚያ በዛፎቹ ጉድጓድ መካከል ግድግዳው እስኪሞላ ድረስ ውኃውን ያዘው" አሉት"*። አዝ-ዙበይር ሲናገር፦ "ወሏሂ ስለዚህ ጉዳይ፦ 4፥65 "በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ አያምኑም" የሚለው አንቀጽ ወረደ" አለ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ الزُّبَيْرِ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّهُ حَدَّثَهُ أَنَّ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ خَاصَمَ الزُّبَيْرَ عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي شِرَاجِ الْحَرَّةِ الَّتِي يَسْقُونَ بِهَا النَّخْلَ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ سَرِّحِ الْمَاءَ يَمُرُّ فَأَبَى عَلَيْهِ، فَاخْتَصَمَا عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لِلزُّبَيْرِ ‏"‏ اسْقِ يَا زُبَيْرُ، ثُمَّ أَرْسِلِ الْمَاء إِلَى جَارِكَ ‏"‌‏.‏ فَغَضِبَ الأَنْصَارِيُّ، فَقَالَ أَنْ كَانَ ابْنَ عَمَّتِكَ‏.‏ فَتَلَوَّنَ وَجْهُ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ثُمَّ قَالَ ‏"‏ اسْقِ يَا زُبَيْرُ، ثُمَّ احْبِسِ الْمَاءَ، حَتَّى يَرْجِعَ إِلَى الْجَدْرِ ‏"‌‏.‏ فَقَالَ الزُّبَيْرُ وَاللَّهِ إِنِّي لأَحْسِبُ هَذِهِ الآيَةَ نَزَلَتْ فِي ذَلِكَ ‏{‏فَلاَ وَرَبِّكَ

Tiriyachen | ጥሪያችን

08 Sep, 14:19


እንቁጣጣሽ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ጳጉሜ” የሚለው ቃል “ኤፓጎሜኖይ” ἐπαγόμενοι ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው፥ ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው። ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው፤ ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ሉቃስ ስድስት ቀናት ሲኖሩር በዘመነ ዮሐንስ፣ በዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት ቀናት ይሆናል። ልብ በሉ! ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም ጊዜ ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ 12 ወራት ብቻ ነው ያለው። አምላካችን አሏህ የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር እንደሆነ ነግሮናል፦
9፥36 አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአሏህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው። إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًۭا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ

ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም። ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሠራሽ ቢድዓ ነው፥ ዓመተ ምሕረትን ያማከለ ዘመነ ሉቃስ፣ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ሰው ሠራሽ ሃይማኖታዊ ትምህርት ነው። በዛ ላይ የባዕድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው፥ በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፥ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።

ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ ተጓግቶ ስለሚመጣ “እንቁ” ተባለ፥ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ “ጣጣሽ” ተባለ። በጥቅሉ “እንቁ ጣጣሽ” ተባለ፥ ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የአሏህን ሐቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው። እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊ መሠረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባዕድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሠራሽ በዓል እራሳችንን እንጠብቅ! ይህ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ስንል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው ዐወቁ። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፥ "ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ ”አሏህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን አሏቸው”። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ ከተከተልን ሁለት በዓል ብቻ አለን፦
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት "ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል" ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል። ስለዚህ "እንቁጣጣሽ" ስንባል "እንኳን ደህና መጣሽ" ከማለት ይልቅ "ማን አመጣሽ" ብለህ በታሪካዊ ዳራ እና ፍሰት እንሞግታለን። በዓሉን ባለማወቅ ለሚያከብሩ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:

https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

28 Aug, 16:38


እየሱስ ጌታ ነውን? | ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/OqGFB_kWlSQ

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

Tiriyachen | ጥሪያችን

08 Aug, 14:55


#ኅሊና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

“ኅሊና"Conscience" የሚለው ቃል “ኀለየ” ማለትም “አሰበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማሰቢያ” ማለት ነው። ኅሊና በሦስት ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1. ታህታይ ኅሊና"sub-Conscience
2. መደበኛ ኅሊና"normal-Conscience
3. ላዕላይ ኅሊና"super-Conscience

ነጥብ አንድ
"ታህታይ ኅሊና"
ታህታይ ኅሊና ማለት ከተፈጠርንበት ጊዜ ጀምሮ በስሜት የምናውቃቸው ግን በትውስታ ትዝ የማይሉን ነገር በኅሊና ተደብቀው የሚኖሩ ነገር፥ ለምሳሌ እናታችን ማህጸን ውስጥ እያለን የምንሰማው ድምጽ፣ ሕጻን ሆነን የምናየው ነገር ወዘተ ያጠቃልለ። ለምሳሌ አላህ ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣ ጊዜ «ጌታችሁ አይደለሁምን?» በማለት ጥያቄ ያቀርባል፤ እኛም «ጌታችን ነህ መሰከርን» በማለት መልስ የሰጠንበት ነው፦
7:172 ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው *ዘሮቻቸውን ባወጣ”* እና «ጌታችሁ አይደለሁምን» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ *”ባስመሰከራቸው”* ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ *«ጌታችን ነህ መሰከርን»* አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡» وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِنۢ بَنِىٓ ءَادَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا۟ بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَآ ۛ أَن تَقُولُوا۟ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَٰذَا غَٰفِلِينَ

ይህ ማንም ትዝ የሚለው የለም። ይህ የተነጋገርንበት የምናስታውሰው "በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ" ነው ይለናል። በትንሳኤ ቀን ይህ ውስጣችን ያለው ሚስጥር ይገለጻል፦
100፥10 *"በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚኾን"*፡፡ وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ
86፥9 *"ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን"*፡፡ يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ

ነጥብ ሁለት
"መደበኛ ኅሊና"
መደበኛ ኅሊና ማለት በስሜት ሕዋሳት የምንረዳው ውጫዊና ውስጣዊ ነው፥ ለምሳሌ "ሕውስታ"sensation" የሚባለው ነው፦
16፥78 አላህም *"ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ"*፡፡ وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

በመደበኛ ኅሊና ምንም ሳናውቅ እንወለዳለን። "ሕዋስ"Sense" ከውጪ ማየትና መስማት ሲሆኑ ከውስጥ ደግሞ ልብ ነው፥ “ልብ” የሚለው ቃል “ለበወ” ማለትም “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመዛዘኛ” ማለት ነው። ይህ ዕውቀት በእርጅና ምንንም ነገር ወደ ዐለማወቅ ይሄዳል፦
16፥70 አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ *"ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ"*፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّاكُمْ ۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰ أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ قَدِيرٌ

ነጥብ ሦስት
"ላዕላይ ኅሊና"
ላዕላይ ኅሊና ከሰው በተለየ መልኩ የሚያሳውቀው ዕውቀት ነው፥ ለምሳሌ ነቅል ነው። “ነቅል” نقل ማለት "ግልጠተ-መለኮት" ማለት ነው፥ ለምሳሌ ቁርኣን ነቅል ነው፦
55፥2 *"ቁርኣንን ዐሳወቀው"*፡፡ عَلَّمَ الْقُرْآنَ
96፥5 *"ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን"*፡፡ عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

“ዐቅል” عقل ማለት ከእንስሳ በተለየ መልኩ በውስጣዊ ስሜት የምንረዳው አእምሮ ነው፥ “አእምሮ” የሚለው ቃል “አእመረ” ማለትም “ዐወቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማወቂያ” ማለት ነው። ነቅል ግን ከአላህ ዘንድ የሚወርድ ዕውቀት ነው፦
4፥113 አላህም *"በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ "የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ"*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا

"የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ" የሚለው ይሰመርበት። ይህንን ዕውቀት የተረዳ ላዕላይ ኅሊና አለው። ሰው በውስጡ ያለውን ውሳጣዊ ተፈጥሮ ሰፊ ነው። ሙሉውን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው፦
17፥25 *ጌታችሁ በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው*፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ በመሳሳትም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው፡፡ رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا

ይህንን ውሳጣዊ ማንነት በማጥራት ማስተንተን “አት-ተሰዉፍ” الْتَّصَوُّف‎ ይባላል፤ በማጥራት የሚያስተነትነው ሰው ደግሞ “ሙተሰዉፍ” مُتَصَوُّف‎ ይባላል። በራሳችን ውስጥ ያለው ውሳጣዊ ምልክትቶች ብዙ ናቸው፥ አላህ ይህንን ውሳጣዊ ነገር አትመለከቱምን? ይለናል፦
51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Aug, 15:09


ነጥብ ሰባት
"ነብያችን"
አምላካችን አላህ በነብያችን"ﷺ” ለእኛ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዘበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቋሙ ብሏል፤ ይህም ሃይማኖት ኢስላም ነው፦
42:13 ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዘበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቋሙ፣ በእርሱ አትለያዩ ማለትን ደነገግን። شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحًۭا وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِۦٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓ ۖ أَنْ أَقِيمُوا۟ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا۟

አላህ ለራሱ "ታዛዦች" ነን በሉ ብሏል፤ "ታዛዦች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙስሊሚን" مُّسْلِمِين እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
2፥136 «በአላህ እና ወደኛ በተወረደው ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ *"ታዛዦች"* ነን» በሉ፡፡ قُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَآ أُوتِىَ ٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ *"ታዛዦች"* ነን» በል፡፡ قُلْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
29:46 ሲቀር *"በሉም"* ፦ በዚያ ወደ እኛ በተወረደው፣ ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም *"ለእርሱ ታዛዦች"* ነን። وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

መደምደሚያ
ታዲያ ከላይ የተዘረዘሩት ነብያት አስተምህሮቻቸው ኢስላም እነርሱ ሙስሊም ከተባሉ ለምንድን ነው አላህ ነብያችንን"ﷺ” "እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ በል" ያላቸው? ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እስቲ እንየው፦
6፥163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም *የሙስሊሞች መጀመሪያ* ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
39፥11-12 በል «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡ «*የሙስሊሞችም መጀመሪያ* እንድኾን ታዘዝኩ፡፡» وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ ٱلْمُسْلِمِينَ

"መጀመሪያ" የሚለው የአረቢኛ ቃል "አወል" أَوَّل ሲሆን በሁለት ይከፈላል፦ አንደኛው "አወሉል ሙብተዳ" ሲሆን አወሉል ሙብተዳ ማለት መጀመሪያነት “መርፉዕ” مرفوع ማለትም "ባለቤት ሙያ"nominative case" ሆኖ ሲመጣ "ሙጥለቅ" مطلق ማለትም "ፍጹማዊ መጀመሪያ"Absolute first" ይባላል። ሁለተኛው "አወሉል ዘርፉል ዘመን" ሲሆን መጀመሪያነት "መንሱብ" منصوب "ተሳቢ ሙያ"accusative case" ሆኖ ሲመጣ "ቀሪብ" قريب ማለትም "አንጻራዊ መጀመሪያ"Relative first" ይባላል። ይህ የሥነ-ሰዋስውና የቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ አድርገን የነብያችን"ﷺ” የሙስሊሞች መጀመሪያ መሆን በአንጻራዊ መጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠ እንጂ በፍጹማዊ መጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠ አይደለም። ይህን ሙግት ከተረዳን ነብያችን"ﷺ” የመጀመሪያው ሙስሊም ሳይሆኑ የሙስሊሞች መጀመሪያ ናቸው፣ አላህ በሁለተኛ መደብ "እናንተ" ሙስሊሞች እያለ የሚያነጋግረው የነብያችንን"ﷺ” ኡማ ነው፦
3:102 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢዉን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፤ *እናንተም ሙስሊሞች* ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

ታዲያ አንጻራዊነት ከምን አኳያ? ካልን የቁርአን ትእዛዝ ተቀብሎ የታዘዘ ከኡማው መጀመሪያው እሳቸው ናቸው፦
6:14 «እኔ *መጀመሪያ ትእዛዝን* ከተቀበለ ሰው ልኾን *ታዘዝኩ*፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

"ትእዛዝን ከተቀበለ" የሚለው ይሰመርበት፣ ይህም ትእዛዝ በእሳቸው ላይ የተወረደው ቁርአን ነው፦
65:5 ይህ *"የአላህ ትእዛዝ ነው"*። ወደ *እናንተም* አወረደው፤ ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ
42:15 በላቸውም፦ ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፤ በመካከላችሁም ላስተካክል *"ታዘዝኩ"*፤ وَقُلْ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٍۢ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ

ከሐዲ የሙስሊም ተቃራኒ ሆኖ አገልግሏል ፣ የሙስሊም መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ እንደተጠቀመ ሁሉ የከሐዲ መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ ተቀምጧል፦
68:35 *ሙስሊሞቹን እንደ ከሐዲዎች* እናደርጋለን?
2:41 ከእናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም ቁርኣን እመኑ፡፡ በእርሱም *"የመጀመሪያ ከሓዲ"* አትሁኑ፡፡ وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًۭا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ

በእርሱ የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ የሚለው ይሰመርበት፣ በቁርአን ማመን የመጀመሪያው ታዛዥ ነብያችን"ﷺ” እንደሆኑ ሁሉ በቁርአን የመጀመሪያው ከሓዲ እነርሱ ናቸው፤ እኔ የሞባይል የመጀመሪያው ተጠቃሚ ነኝ ብል፤ መጀመሪያነት ከምን አንጻር? ከቤተሰብ? ከከተማ? ከአገር ወይስ ከዓለም? ይህ ቅድሚያ መጠየቅ አለበት፤ ስለ መጀመሪያነት ብዙ ናሙናዎችን መጥቀስ ይቻላል፤ ሙሳ፦ የምእምናን መጀመሪያ ነኝ ብሏል፤ ያ ማለት የሙሳ መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፤ የፈርኦን ደጋሚዎች፦ የምእምናን መጀመሪያ ነን ብለዋል፤ ያ ማለት የፈርኦን ደጋሚዎች

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Aug, 15:09


መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእነርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፦
7፥143 «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም *የምእምናን መጀመሪያ* ነኝ» አለ፡፡ قَالَ سُبْحَٰنَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُؤْمِنِينَ
26፥51 «እኛ *የምእምናን መጀመሪያ* በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡» إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ

https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Aug, 15:09


ኢስላም እና ነብያት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *"ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ"* በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

መግቢያ
የኢስላምን መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” لا اله الاّ الله ነው፣ የነብያት ዐቂዳህ አስኳሉ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ነው፤ አላህ ጥንት ለነበሩት ነቢያቱ ወሕይ የሚያወርድላቸው የነበረው “ላ ኢላሃ ኢልላ አና” لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا ማለትም "ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" የሚል ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *"ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ"* በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ *"ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም"* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

ወደ ሰዎች ሲልካቸውም "ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ" مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ማለትም "ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም" ብለው እንዲናገሩ ነው፦
23:32 በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ አላህን አምልኩ *"ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም"* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፤ ለእናንተ *ከእርሱ በቀር ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን አምልኩ *ከእርሱ ሌላ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን አምልኩ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤

ለናሙና ያክል ከላይ ያሉትን ጠቀስን እንጂ አላህ በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ እርሱን እንዲያመልኩ እና ጣዖትንም እንዲርቁ መልክተኛን በእርግጥ ልኳል፤ ከእነርሱ አላህ ለእኛ አስፈላጊ ያላቸውን በነብያችን"ﷺ” ላይ የተረካቸው አሉ፤ ከእነርሱም ለእኛ አስፈላጊ ያልሆኑትን በነብያችን"ﷺ” ላይ ያልተረካቸው አሉ፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ *"አላህን አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ"*፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوتَ
40:78 *"ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፤ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፤ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ"*፤ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًۭا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

እነዚህ ነብያት አምላካችን አላህ ወሕይ የሚያወርድላቸው ጭብጥ ይህ እስልምና ነው፤ እስቲ እነዚህ ነብያት በተናጥል እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"አደም"
አላህ ወደ አደም ወህይ አውርዷል፤ አደምም ከእርሱ ቃላት ተቀብሏል፦
20:115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት *“ኪዳንን በእርግጥ አወረድን”*፤ ረሳም፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِىَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُۥ عَزْمًۭا ፡፡
2:37 አደምም *“ከጌታው ቃላትን ተቀበለ”*፡፡ በርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና فَتَلَقَّىٰٓ ءَادَمُ مِن رَّبِّهِۦ كَلِمَٰتٍۢ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ ፡፡

ወደ ነብያት የሚወርደው የኢስላም አስኳሉ የሆነው “ላ ኢላሃ ኢልላ አና” ከሆነ ነብያችንም"ﷺ” በግልፅና በማያሻማ አደም የመጀመሪያው ነብይ መሆኑን ነግረውናል፦
ሙስነድ አህመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1781
አቡ ዘር ነብዩን የአላህ ነብይ”ﷺ” ሆይ የመጀመሪያው ነብይ ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው፤ ነብዩም አደም”አ.ሰ.” ነው አሉ፤ እርሱም፦ እርሱ ነብይ ነበረ? ብሎ ጠየቀ፤ ነብዩም፦ አዎ አላህ በእጁ የፈጠረውና ሩህ የነፋበት ነበር፤ አሉት قال : قلت : يا نبي الله ! فأي الأنبياء كان أول ? قال : آدم عليه السلام . قال : قلت : يا نبي الله ! أو نبي كان آدم ? قال : نعم , نبي مكلم , خلقه الله بيده , ثم نفخ فيه من روحه ።

ነጥብ ሁለት
"ኑሕ"
የኑሕ ጥሪ "ወገኖቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፤ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም" ማለት ነበረ፦
23:23 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ ወገኖቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፤ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እኔ በናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።

ልብ አድርግ የኑሕ የመልእክቱ ጭብጥ ከአንዱ አምላክ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለምና አምልኩት የሚል ነው፤ ይህንን አንድ አምላክ በብቸኝነት ስለሚያመልክ "ከሙስሊሞችም እሆን ዘንድ ታዝዣለሁኝ" ብሏል፦
10፥72 “ብትሸሹም አትጎዱኝም ፣ከምንዳም ምንንም አለምናችሁም፡፡ምንዳዬም በአላህ ላይ እንጂ በሌላ አይደለም፣*"ከሙስሊሞችም እሆን ዘንድ ታዝዣለሁኝ"*” فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ

Tiriyachen | ጥሪያችን

06 Aug, 15:09


ነጥብ ሶስት
"ኢብራሂም"
የዐረቦች አባታቸው ኢብራሂም ሲሆን የኢብራሂምን ሃይማኖት ደግሞ ኢስላም ነው፤ አላህ ከነብያችን"ﷺ” በፊት "ታዛዦች" ብሎ ሰይሟቸዋል፦
22:78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፤ እርሱ መርጧችኃል፤ በእናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ ከዚህ በፊት *"ሙስሊሞች"* ብሎ ሰይሟችኋል፤ وَجَٰهِدُوا۟ فِى ٱللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِۦ ۚ هُوَ ٱجْتَبَىٰكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلدِّينِ مِنْ حَرَجٍۢ ۚ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَٰهِيمَ ۚ هُوَ سَمَّىٰكُمُ ٱلْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

"ሙስሊም" مُسْلِم “ታዛዥ” ማለት ነው፤ አላህ ለኢብራሂም "አስሊም" أَسْلِمْ "ታዘዝ" ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ "አስለምቱ" أَسْلَمْتُ "ታዘዝኩ" አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ *"ታዘዝ"* ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ *"ታዘዝኩ"* አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ስለዚህ ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፦
3:67 ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ *"ሙስሊም ነበረ"*፤ ከአጋሪዋችም አልነበረም። مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّۭا وَلَا نَصْرَانِيًّۭا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًۭا مُّسْلِمًۭا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

ነጥብ አራት
"ያዕቁብ"
ያዕቁብም ልጆቹን እናንተ "ሙስሊሞች" ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው፤ እነርሱም አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም "ታዛዦች" አሉ፦
2:132 በእርሷም በሕግጋቲቱ ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ ያዕቁብም እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ፡፡ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ *"ሙስሊሞች"* ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው፡፡ وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
2:133 ያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም *"ታዛዦች"* ኾነን እናመልካለን አሉ፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَآءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ ٱلْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِنۢ بَعْدِى قَالُوا۟ نَعْبُدُ إِلَٰهَكَ وَإِلَٰهَ ءَابَآئِكَ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ إِلَٰهًۭا وَٰحِدًۭا وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ነጥብ አምስት
"ሙሳ"
ሙሳም ለሕዝቦቹ "ታዛዦች" እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ አለ፤ "ታዛዦች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙስሊሚን" مُّسْلِمِين እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
10:84 ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ *"ታዛዦች"* እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ፡፡» وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوْمِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ

ነጥብ ስድስት
"ዒሳ"
ዒሳ የትምህርቱ ጭብጥ፦ "አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት" የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 «*"አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት"*፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
5፥72 እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! *"ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ"*፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
19፥36 ዒሳ አለ፦ «*"አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት"*፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

የዒሳ ሐዋርያትም ይህንን ቃል አምነው ሙስሊሞች መሆናቸውን አስመስክረዋል፦
5:111 ወደ ሐዋርያትም በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፤ አመንን፣ እኛም *"ሙስሊሞች"* መሆናችንን መስክር አሉ።وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى ٱلْحَوَارِيِّـۧنَ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِى وَبِرَسُولِى قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَٱشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
3:52 ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ *"ታዛዦች"* መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ። فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

3,159

subscribers

557

photos

69

videos