የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo) @ethio_cairo Channel on Telegram

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

@ethio_cairo

ለኤምባሲው አገልግሎት ጠያቂዎች የተከፈተ ቻናል ሲሆን መረጃ ከዚህ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo) (Amharic)

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ የእኔዎን የአሜሪካ አምባሳደር ከበሬ በካይሮ በመጪው ኤምባሲ በኢትዮጵያ ድጋፍ እና አገልግሎት ለኢትዮጵያ በጋራ ነው። ስንት ሚሊዮን የዜግነት እና ኢኮኖሚክሽንን በቀጥታ በጤንሳይ አገልግሎት አቅብረው እንበለጋለን ። ethio_cairo እናንተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ ከፈፀሙ ሥራና ከእኔም ጋር በስምምነት እንደምደመስ እናወደምትገኘም አሁኑን ታሪክ ላይ እንቀናል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

21 Nov, 10:37

ስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

19 Nov, 19:23

ከላይ የተጠቀሰው ፓስፖርት ያለው ካሊድ አብዱ አባጋሮ የሚባሉት በኡማያት ኢምባባ ሆስፒታል በጠና በህመም ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ እርዳታ እና ድጋፍ የሚያደርግለት አካል የለም።  ስለዚህ እሱን በቅርብ የሚያቁት እና እሱን ለመርዳት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በሚከተለው አድራሻ ወደ ሆስፒታል በመሄድ መጠየቅ  እና አስፈላጊውን ድጋፍ  ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

https://maps.app.goo.gl/yuypcFEotPHhDb6v5?g_st=iwb

Namni paaspoortiin isaa armaan olitti argamu kun Kaalid Abdoo Abagaroo kan jedhamu dhukkubsatee mana yaalaa hospitaala Umayat Imbabaatti haala yaaddessaa keessa jira. Haa ta'u malee hanga ammaatti namni isa gargaaruu fi cinaa dhaabbatu hin jiru. Kanaafuu namoonni dhiyeenyaan isa beektanii fi fedhii keessaniin gargaaruu dandeessan teessoo armaan gadii kanaan gara mana yaalaa deemuun gargaaruu akka dandeessan isiin beeksifnaan.

https://maps.app.goo.gl/yuypcFEotPHhDb6v5?g_st=iwb

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

31 Oct, 05:46

https://www.facebook.com/share/v/XxosrfKxCgwDYdYY/

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

22 Oct, 12:44

ስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

22 Oct, 12:44

ስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

14 Oct, 17:17

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን በድምቀት አክብረዋል። በበአሉ ላይ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ እና የሰላምና የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

Ethiopian diplomats and staff members colorfully celebrated the 17th National Flag Day. During the occasion, they reiterated their commitment to maintain the unity, sovereignty, and territorial integrity and foster peace and development endeavors in Ethiopia.

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

08 Oct, 01:38

በሊባኖስ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ አገር ቤት የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በካይሮ ኤርፖርት በኩል ያደረጉት ትራንዚት የተቀላጠፈ እንዲሆን አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎ ወደ አገር ቤት ተሸኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

03 Oct, 14:59

አ.ኤ.አ ኦክቶበር 6 ቀን 2024 በግብጽ የሚከበረውን Armed Forces Day ክብረ በዓል ምክንያት ኤምባሲያችን እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ዝግ እንደሚሆን እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)

27 Sep, 10:54

የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት የመርሶ ህይወት መድኃኔዓለም ሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት የግብዣ ጥሪ መሰረት የኢፌድሪ ልዩ መልክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን ክቡር አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ሙሳን ጨምሮ ሌሎች የስራ ባልደረቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም በደማቅ ሁነት በካይሮ አባስያ ቤ/ክ ተከብሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ ክቡር አምባሳደር ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳቹ መልክት
አገራችን ያለፈው አመት ያስመዘገበችውን ስኬት በማስቀጠል ሰላሟን እና አንድነቷን ጠብቀን ለመጪው ትውልድ የማስረከብ አደራ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም ዜጎች በግብፅ የሚደርስባቸውን መንገላታት ለመፍታት ኤምባሲው ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን በመግለጽ ችግሩን ለማቃለል ከግብፅ መንግስት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጨረሻም ዜጎች ከኤምባሲው እና በቅርቡ ከተመሰረተው "በግብጽ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር" ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።