በስዊዘርላንድ የምትገኝ አንዲት ቤ/ክ “AI ኢየሱስን” ለኑዛዜ አገልግሎት አቅርባለች።
'Deus in Machina' ወይም “አምላክ በማሽን ውስጥ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክቱን ያስተዋወቀችው በስዊዘርላንድ ሉሰርን ከተማ የምትገኝ የቅዱስ ጴጥሮስ ቤ/ክ ናት። አላማውም ሰዎች ኢየሱስን በአካል (“”) ያናግሩት ዘንድ በማሰብ ነው፣ ምንም እንኳን በAI ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቢሆንም።
ሂደቱ እንዲህ ነው፣ ምንም ጉዳይ ወይም ጥያቄ ያለው ሰው፣ ወደ “AI ኢየሱስ” ሄዶ ይተነፍሳል፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎቱም በድምጽ የፊልሙን ኢየሱስ ጭምብል አድርጎ ሰዎችን ያናግራል።
ማሽኑ በሙከራ ወቅት የገጠመው ፈተና ኦንላይን የሚገኙ የአሜሪካ ወንጌላዊያንን መረጃ በመሆኑ የያዘው፣ የሉሰርን ቅዱስ ጴጥሮስ ቤ/ክን አቋም የማያንጸባርቅ መልሶችንም መልሷል። ይሁን እንጂ ይላሉ የቤ/ክኗ መሪዎች ፕሮጀክቱ AI በሃይማኖት ውስጥ የሚኖረውን ሚና ማስጀመሪያ ይሆናል ብለውታል።
በዚያው የሉሰርን ዩኒቨርሲቲ የስነ መልኮት ፕሮፌሰር፣ ስለ እምነት፣ መጋቢያዊ አገልግሎት እና በሃይማኖት ውስጥ የህይወትን ትርጉም ስናወራ፣ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን” ብለዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎቱ (Chat Boot) ለጊዜያዊነት ሙከራ ላይ ያለ ቢሆንም፣ የሙከራ ጊዜውን አልፎ በትክክል መስራት የጀመረ ቀን የቤ/ክ አግልጋዮችን ስራ ሊተካ ይችላል ተብሏል። ፕሮጀክቱ ከነሃሴ - ጥቅምት በነበሩት ወራቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆኖ ቆይቷል ሲል ያስነበበው ዘ ደይሊሜይል ነው።