WCU_Evange_Moblizers @wcuevang Channel on Telegram

WCU_Evange_Moblizers

@wcuevang


Gospel for all Student's!

WCU_Evange_Moblizers (English)

Are you a student looking for a place to connect with like-minded individuals and deepen your faith? Look no further than the WCU_Evange_Moblizers Telegram channel, also known as @wcuevang! With the tagline 'Gospel for all Students!', this channel is dedicated to spreading the word of God and building a community of young believers. The WCU_Evange_Moblizers channel is a platform where students can come together to share their love for God, discuss scripture, and support one another on their spiritual journeys. Whether you're looking for daily devotions, inspirational messages, or simply a virtual space to connect with fellow students, this channel has something for everyone. Led by a group of dedicated mobilizers, the WCU_Evange_Moblizers channel provides a safe and welcoming environment for students to explore their faith and grow in their relationship with God. Through a combination of prayer requests, Bible studies, and uplifting content, members of this channel are encouraged to strengthen their faith and spread the message of the Gospel to others. So, who is this channel for? The WCU_Evange_Moblizers channel is designed for students of all backgrounds who are passionate about their faith and eager to connect with other like-minded individuals. Whether you are a seasoned believer or just starting to explore your spirituality, this channel welcomes you with open arms. What is the channel all about? The WCU_Evange_Moblizers channel is a virtual hub for students to come together, share their faith, and support one another in their spiritual journeys. From daily reflections to group discussions, this channel offers a variety of resources and activities to help students grow in their relationship with God and each other. If you're a student looking to deepen your faith, connect with a supportive community, and spread the message of the Gospel, the WCU_Evange_Moblizers Telegram channel is the perfect place for you. Join @wcuevang today and start your journey towards a stronger, more vibrant relationship with God.

WCU_Evange_Moblizers

02 Jan, 11:56


የ 3 ቀን ቻሌንጅ (3 Days Challenge).

ሁላችሁም ለ 20 ክርስቲያን ጓደኞቻችሁ Share በማድረግ Pp እና Story ማስደረግ ዘወትር እሁድ 3:00 Liv እንዲቀላቀሉ መጋበዝ በመቀጠል 👇
#Subscribe
#Follow
#Join
በማድረግ ከታች ያሉትን አካውንቶቹን ከፍ በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቀለን!
🙌Youtube
https://youtube.com/@apolomics?si=om9_3tvl2Iy2E58_

🙌Tiktok
Sahih Iman👇
https://www.tiktok.com/@sahihiman7?_t=ZM-8sjG2dbWUEw&_r=1

https://www.tiktok.com/@apolomics?_t=ZM-8sjG6aZMlqn&_r=1


Telegram
@YEA_2016
@apolomics

አብረውን የእግዚአብሔርን መንግስት ስላገለገሉ ጌታ ይባርኮት🙌

WCU_Evange_Moblizers

30 Dec, 20:57


ሰላም 🙌 ወንጌላዊያን የሚቀጥለው እሮብ የዚህን #ሴሚስተር_የመዝጊያ ፕሮግራም እናደርጋለን በመሆኑም ሁላችንም በሴሚስተሩ ሁሉ የረዳንን #እግዚአብሔር የምናመሰግንበት እንዲሁም #ለአንዱ_አምላክ ለእግዚአብሔር #ክብርን የምንሰጥበት ጊዜ በመሆኑ ሁላችሁም @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት እንገናኝ!!
ተወዳችኋል❤️❤️❤️

WCU_Evange_Moblizers

29 Dec, 04:26


ሁላችሁም በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የ Live Program በ Tiktok እና Telegram
😍ዛሬ ማታ 3:00 የተደበቀው እውነት መፅሀፍ ግምገማ ክፍል 2 #በሳሂህ ኢማን ይቀጥላል።
#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል.

🤝ለአገልግሎቱ ተደራሽነት ሁላችሁም ለ 10 ሰው Share  አርጉ።

@YEA_2016
@apolomics

WCU_Evange_Moblizers

28 Dec, 12:57


ባለፈዉ የዉሰድነዉ የ"only jesus training "ሳዘጋ የተጠቀምኳቸዉ መፅሐፍት ናቸዉ ።እነዚህን መፅሃፊት ብታነቡ ይበልጥ የሰፋና የተጠለቀ ነገር ታገኛላችሁ የሚል እምነት አለኝ። የጌታ ፀጋ ይብዛላችሁ !! በጌታም በእኛም ተወዳችሁኋል!!😍😍

WCU_Evange_Moblizers

21 Dec, 06:18


የሚቀጥለው ሰኞ እለት ከባለፈው የቀጠለ #Only_Jesus ትምህርት ስለሚኖረን በጊዜ @11:00 ላይ እንገናኝ።

ወንጌልን #በመንፈስ_ቅዱስ ሀይል እንዲሁም #በእውቀት እንሰብካለን!!!


“ በእናንተ ስላለ #ተስፋ ምክንያትን #ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ #መልስ ለመስጠት ዘወትር #የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 3፥15

WCU_Evange_Moblizers

18 Dec, 04:22


🙌በፍፁም አይቀርም

ይህንን PP በማድረግ አብረውን የጌታን መንግስት ያገልግሉ!

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ🙏

የመወያያ ስፍራ👇
Tiktok = @apolomics
Telegram =@Yea_2016


join us
@apolomics

WCU_Evange_Moblizers

18 Dec, 04:22


🙌በፍፁም አይቀርም

ይህንን Story በማድረግ አብረውን የጌታን መንግስት ያገልግሉ!

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ🙏

የመወያያ ስፍራ👇
Tiktok = @apolomics
Telegram =@Yea_2016


join us
@apolomics

WCU_Evange_Moblizers

18 Dec, 04:22


በኡስታዝ ወሂድ የተፃፈው የተደበቀው እውነት የተሰኘው መፅሀፍ ይተቻል, ይገመገማል!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🙏

WCU_Evange_Moblizers

17 Dec, 19:35


ነገ ማለትም ዕሮብ @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት ተገኝተን በደንብ #የምንፀልይበት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ #በወንጌል በአገልግሎታችን ይበልጥኑ #አቅጣጫዎችን እንዲያሳየን #በጊቢ #ያልዳኑ_ተማሪዎችን ቤዛ አድርጎ እንዲሰጠን በፀሎት የምንጋደልበት ጊዜ ስለሚኖረን ሁላችሁም ይህ ልብ ያላችሁ #ወንጌላውያን ተገኝተን እንድንፀልይ ይሁን።

📌ስንፀልይ #እግዚአብሔር ይሰራል መፀለይ ስናቆም ጉልበታችን ይሰራል!!!
እግዚአብሔር በሙላት እንዲሰራ እንፍቀድለት።


ሐዋርያት 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ወደ #እግዚአብሔር ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ እንዲህም አሉ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ፥


³¹ #ከጸለዩም በኋላ #ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ #የእግዚአብሔርንም #ቃል በግልጥ ተናገሩ።

WCU_Evange_Moblizers

11 Dec, 11:38


❇️ ማሳሰቢያ!
****
➲ ባላፈው ጊዜ ከEvang week በፊት እንደ ሰኞ ዕለት የEvent Organizers መጥተው ማስታወቂያ ስናገሩ #ለትሻርት ተመዝግባችሁ #ቀብድም ሆነ #መሉ ብር የሰጣችሁ የevang ልጆች! ከታች በላው username communicate እንድታደርጉ የEvent organizers በጥብቅ ይፈልጋሉ!!
👇👇
▸@Degife_Dawit

WCU_Evange_Moblizers

11 Dec, 11:27


WCU_Evange_Moblizers pinned «💢 የዛሬ ፕሮግራም እንደተጠበቀ ነው! ልክ #11:00 ሰዓት በጊዜ ተገናኝተን 🔈#ወንጌል እንሰራለን! ማናችሁም እንዳትቀሩ!!»

WCU_Evange_Moblizers

11 Dec, 11:26


💢 የዛሬ ፕሮግራም እንደተጠበቀ ነው! ልክ #11:00 ሰዓት በጊዜ ተገናኝተን 🔈#ወንጌል እንሰራለን! ማናችሁም እንዳትቀሩ!!

WCU_Evange_Moblizers

08 Dec, 12:10


WCU_Evange_Moblizers pinned «❇️ notice      **** ▸እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነገ ሰኞ ዕለት ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ እግዚአብሔር በሳምንቱ ስላደረገልን ነገር #ሁሉ የምናመሰግንበት፣ስለ #ዳኑት ነብሰት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፣#ተስፋ ስለሰጡት ነብሰት የምንጸልይበት፣#በንስሐ ስለተመለሱ ሰዎች የምናመሰግንበት፣#ስለሰሙ ነብሰት ወደ እግዚአብሔር የሚንቃትትበት! ▸እንድሁም በሳምንቱ ለይ የነበረውን አጠቃላይ #ሪፖርት የምንሰማበት…»

WCU_Evange_Moblizers

08 Dec, 12:10


❇️ notice
     ****
▸እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነገ ሰኞ ዕለት ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ እግዚአብሔር በሳምንቱ ስላደረገልን ነገር #ሁሉ የምናመሰግንበት፣ስለ #ዳኑት ነብሰት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፣#ተስፋ ስለሰጡት ነብሰት የምንጸልይበት፣#በንስሐ ስለተመለሱ ሰዎች የምናመሰግንበት፣#ስለሰሙ ነብሰት ወደ እግዚአብሔር የሚንቃትትበት!
▸እንድሁም በሳምንቱ ለይ የነበረውን አጠቃላይ #ሪፖርት የምንሰማበት ጥሩ ጊዜ ይኖረናል!
❗️ስለሆነም ማናችንም ሰንቀር በጊዜ እንድንመጣ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን!
    ...የጌታ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን...

1ኛ ተሰሎንቄ 1
2-3: በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤

#አዳኙን ማወቅ፣መታዘዝ እና ማረፍ ይሁንልን!

WCU_Evange_Moblizers

08 Dec, 11:59


WCU_Evange_Moblizers pinned Deleted message

WCU_Evange_Moblizers

07 Dec, 06:38


WCU_Evange_Moblizers pinned «✴️ Notice የዛሬውን #city #mission ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ ነው የምንወጣው!»

WCU_Evange_Moblizers

07 Dec, 06:38


✴️ Notice

የዛሬውን #city #mission ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ ነው የምንወጣው!

WCU_Evange_Moblizers

07 Dec, 05:07


💥Evange week Day-6
የዛሬው ነው ሁሉም ሰው profile እና share ያድርገው::

“የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።”
ማቴዎስ 12፥8

#እረፍት በኢየሱስ ብቻ ነው!

WCU_Evange_Moblizers

06 Dec, 04:59


#Notice

በዛሬው ጥቅስ ላይ የቁጥር ስህተት ስለተፈጠረው በዚህ channel ላይ ብቻ የተለጠፈውን አድርጉ

WCU_Evange_Moblizers

06 Dec, 04:41


💥Evange week Day-5
የዛሬው ነው ሁሉም ሰው profile እና share ያድርገው::

“የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?”
ዮሐንስ 10፥36

screen shoot በዚህ ላኩልን
👇👇
@BaruchNeriah

WCU_Evange_Moblizers

05 Dec, 09:17


አዳኙን ማወቅ ማላጅነቱን ማወቅ ነው!!!
የኢየሱስ ክርስቶስን  አማላጅነት (ሊቀ-ክህነት) በሚመለከት በሀይማኖተኛው አለም ብዙ ግራ መጋባቶችን እንመለከታለን።
"ማማለድ/መማለድ" የሚለውን የቃል ትርጉም እንመልከት። "የሚማልድ" የሚለውን ቃል በግዕዙ "ወይትዋቀሥ በእንቲአነ" ስለኛ የሚከራከር ፣ እንዲሁም "ወይተነብል ሎሙ" ስለነሱ የሚለምን ይለዋል፣ ይህም "ተዋቀሠ" እና "ተንበለ" ከሚለው ግስ የመጣ ቃል ሲሆን፣ ተሟገተ፥ ተከራከረ፣ ለመነ፣ ጥብቅና ቆመ የሚል ትርጓሜን ይይዛል። በእንግሊዝኛውም "Intercession" ይለዋል።
የአዲስ ኪዳን ሊቀ- ካህናት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ  በሰው እጅ ወደተሰራችው ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን በእግዚአብሔር ፊት አሁን ስለእኛ ይታይልን ዘንድ ወደ እርሷ ገባ ይላል ዕብ 9፣24።
በዚህ ጥቅስ ውስጥም “አሁን” የሚለውን ቃል ማስተዋል አለብን ምክንያቱም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ስለእኛ የሚታይልን የአዲስ ኪዳኑ ሊቀ-ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
እንደዚሁም ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 8፣34 ኢየሱስ ካረገ በኋላ ስለምልጃው ስለሚናገረው ነገር ላይ ማስተማል ያለብን ነገር ፣የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሐላፊ ግዜን ሲሆን ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ፣ የሚለው ግን የአሁን_ጊዜን አመላካች ነው፡፡  በዚህም ላይ ጨምሮ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይላል እንጅ ማርያም ወይንም ሌሎች ናቸው አይልም፡፡
ሐዋርያው በዕብ 9፣24 አሁን ስለእኛ ይታያል እንዳለው ሁሉ በአብ ዘንድ ጠበቃችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ መልዕክቱ 2፣1-2 ሐዋርያው ጳውሎስም የኢየሱስ ክርስቶስን መካከለኛነት ይናገራል በ1ኛ ጢሞቲዮስ 2፣5 ስለዚህም ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ዋስ ሆኗል ዕብ7፣22
ስለ ምልጃ ስናነሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መስፈርቶችን እና እውነታወችን መቀበል ግድ ይላል። አንድ ያላመነ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅነት (ሊቀ ክህነት) ከመጠቀሙ በፊት በመስዋዕትነቱ ማለት በመስቀሉ ስራ ማመን አለበት ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የመስዋዕትነት ስራ (በመስቀሉ ስራ) ያመኑ እና የተጠቀሙ ሁሉ ካህናት ይሆናሉ። ራዕይ 1:5-6
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያማልደዉ አምላክም ሰውም ስለሆነም ነው።ኢየሱስ በፍፁም አምላክነቱ ከአምላክ ስለሚስተካከል ቦታውን መያዝ ይችላል  በፍፁም ሰውነቱ የሰው ልጆች ሁሉ ችግር የሚገባው በነገር ሁሉ የሚራራልን ብቸኛው የአዲሱ ኪዳን ሊቀ-ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እና ብቻ ነው።
      ለማማለድ_መስፈርቶች፦
👉 በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ሴት መወለድ ያስፈልጋል ኢሳ 7:14, ማቴ 1:23
👉ሰው መሆን፦ ዕብ 5:1፤
👉ከሰውም + ወንድ ኢሳ.9:6፤
👉ከወንድም + ሊቀ ካህናት መሆን ዕብ.5:3
👉ከሊቀ ካህምናትም + ነውር የሌለበት፦ዕብ.7:26፤
👉ነውር ከሌለበትም +የሚያቀርበው ብቁ መሥዋእት ያለው፤ዕብ.8:3
👉ብቁ መሥዋእት ካለውም  +  የማይሞትና ዘላለማዊ መሆን አለበት።ዕብ.7:23-24  ይህን መስፈርት በሟሟላት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው አንድ ነው ....ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል ።
1 ጢሞቴዎስ 2:5
አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ስለዚህ እስከዛሬ ያማልዳሉ ያልናቸው ሰዎች እና መላእክት፦
1) ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ስለማይችሉ
2) መካከለኛውን ማለት (የኢየሱስን) ቦታ መያዝም ስለማይችሉ
3) አምላክም ሰውም(God-Man) መሆን ስለማይችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍም ስለሌላቸው፣ አንድ ብቻ አማላጅ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተመለሱ!!!

WCU_Evange_Moblizers

05 Dec, 05:06


💥Evange week Day-4
የዛሬው ነው ሁሉም ሰው profile እና share ያድርገው::

screen shoot በዚህ ላኩልን👇👇
@BaruchNeriah

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 20:29


WCU_Evange_Moblizers pinned «ከነገ ጀምሮ አንብቾ ላይ በህብረት የምንሰራውን የሚቀረን አንድ ቀን ስለሚሆን ሁላችሁም ነገ 📌devotion ፀሎት @12:00 📌ምሳ ሰዓት @6:00 📌አመሻሽ @11:00 ላይ በደንብ #የንጉሳችንን #የኢየሱስን ስም ከፍ አድርገን የምንናገርበት ቀን ስለሚሆን ሁላችሁም እንድትገኙ እንዲሁም #ጓደኞቻችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ ይሁን!!! 💥 ስለወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ!!!💪💪🔥🔥»

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 20:24


ከነገ ጀምሮ አንብቾ ላይ በህብረት የምንሰራውን የሚቀረን አንድ ቀን ስለሚሆን ሁላችሁም ነገ
📌devotion ፀሎት @12:00
📌ምሳ ሰዓት @6:00
📌አመሻሽ @11:00
ላይ በደንብ #የንጉሳችንን #የኢየሱስን ስም ከፍ አድርገን የምንናገርበት ቀን ስለሚሆን ሁላችሁም እንድትገኙ እንዲሁም #ጓደኞቻችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ ይሁን!!!

💥 ስለወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ!!!💪💪🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 19:57


¤ Evang week #Day-3💥
   #Pictures!
        👇👇
#አዳኙን ማወቅ!
በመጽሐፍ ቅዱስ #እውነት ነው!!

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 19:56


¤ Evang week #Day-3💥
   #Pictures!
        👇👇
#አዳኙን ማወቅ!
በመጽሐፍ ቅዱስ #እውነት ነው!!

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 11:18


WCU_Evange_Moblizers pinned «አዳኙን ማወቅ በመፅሐፍ ቅዱስ እውነት ነው!!! ~ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች እምነት ,ሕይወትና ድነትን መስጠት የሚችል እስትንፋስ መለኮት ያለበት ስተት አልባ ግልጽና ብቁ የሆነ ሥልጣን ያለው የአማኞችን እና የሚያምኑትን  እምነትና ልምምድ የሚጋራ  የሕይወታቸው  መመሪያ  መጻሕፍ ቅዱስ  ብቻ ነው                   ለምን ቃሉ ብቻ? 1.እስትንፋሰ መለኮት ስለሆነ :- የመለኮት እስትንፋስ…»

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 11:12


አዳኙን ማወቅ በመፅሐፍ ቅዱስ እውነት ነው!!!

~ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች እምነት ,ሕይወትና ድነትን መስጠት የሚችል እስትንፋስ መለኮት ያለበት ስተት አልባ ግልጽና ብቁ የሆነ ሥልጣን ያለው የአማኞችን እና የሚያምኑትን  እምነትና ልምምድ የሚጋራ  የሕይወታቸው  መመሪያ  መጻሕፍ ቅዱስ  ብቻ ነው
                  ለምን ቃሉ ብቻ?

1.እስትንፋሰ መለኮት ስለሆነ :-
የመለኮት እስትንፋስ ያለበትና የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሀፍት በእግዚአብሔር መንፈስ በመነዳት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለባቸውን መፅሀፍት ሊፅፉ ችለዋል። በሌላ አገላለፅ ምን መፃፍ እንዳለባው ይመራ የነበረው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ለዚህም 2ዜና 18:13 እንዲህ ይላል
“ሚክያስም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! አምላኬ የሚለውን እርሱን እናገራለሁ አለ።” 2 ዜና 18፥13
2ጢሞ 3:16  ላይ "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው" የሚለውን ለማመልከት በጥቅም ላይ የዋለው የግሪክ ቃል (θεόπνευστος) theh-op'-nyoo-stos የሚል ሲሆን በቃል በቃል ሲፈታ "እግዚአብሔር የተነፈሳቸው/የተናገራቸው" ማለት ነው።
የመፅሐፍ ቅዱስ መፅሐፍት በጠቅላላው የእግዚአብሔር መንፈስ ወይም እስትንፋስ አለባቸው።
2.ስህተት/ሕጸጽ አልባ ስለሆነ፦
መፅሐፍ ቅዱስ ስህተት አልባና ሙሉ በሙሉ እውነት የሆነ መጽሀፍ ነው።
መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሆኑ መጠን ምንም ስህተት ወይም ህፅፅ የለበትም።በመሆኑም የሚያስተላልፋቸው መረጃዎች በሙሉ ትክክል ናቸው።(ቲቶ 1:2፤ ዮሐ 17:17)
3.ግልጽነት ስለሆነ፦
መፅሐፍ ቅዱስ ተራ ሰዎች ጭምር መረዳት በሚችሉት ልክ ግልፅና ያልተወሳሰበ መፅሐፍ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ሰዎች መረዳት እስከማይችሉ ድረስ ረቂቅ አይደለም።
የብሉይ ኪዳን ሰዎች መፅሐፍ ቅዱስን ያነብቡ ነበር አስተሳሰባቸውም በዚያ መልኩ እንዲቀረፅ ይጠበቅ ነበር። (መዝ 1:1-3 ፤ዘዳ 6:6-7 1ዮሐ 2:27 ዮሐ 16:13)
   መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያለበት ማን ነው?

👉 ባሎች ኤፌ 5:25-28
👉 ሚስቶች ኤፌ 5:22-24
👉 ልጆች      ኤፌ 6:1-3
"መፅሐፍ ቅዱስ የሰው ሁሉ መፅሐፍ ነው"
3.በቂነት ስለሆነ ፦
መፅሐፍ ቅዱስ ብቻውን ለክርስትና ልምምድ በቂ ነው።መፅሐፍ ቅዱስ  የሰው ልጆች ሊያወሰቁት የተገባቸውን እውነትና የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሙሉ ይዟል።መፅሐፍ ቅዱስ እንዴት አማኝ መሆን እንደሚቻልና ይህንን በእምነት የተገኘውን የፅድቅና የቅድስና ህይወት እንዴት መኖር እንደምንችል በቂ ዕውቀት ያስጨብጣል።(2ጢሞ 3:16 ፤ሐዋ 20:32፤ሉቃ 16:27-29፤መዝ 19:7-8 )
4.ስልጣን ያለው ስለሆነ ፦
መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ የእምነትና የልምምዳችን የበላይ ባለስልጣን ነው።እስትንፋስ መለኮት የሆነው ስህተት አልባው፣ዕውቀት ያለበትና ለሁሉም በቂ የሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ለእምነትና ለህይወታችን ርሱ ብቻ መመሪያ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰይጣን ጋር የነበረውን ጦርነት ለማሸነፍ ምን መሳሪያ ነበር የተጠቀመው? ህይወቱን በምን አይነት መርህ ይመራ  ነበር?
መልሱ "የተፃፈው የእግዚአብሔር ቃል ማለትም መፅሐፍ ቅዱስ" የሚል ነው።(ማቴ 4:4:7:10)

    "መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ" ማለት ምን ማለት አይደለም?
ብዙ ሰዎች መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ስንል "መፅሐፍ ቅዱስ በነጠላው" ማለት ይመስላቸዋል። ነገር ግን
👉 መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች መፅሀፍትን ማንበብ የለብንም ማለት አይደለም።
ኢያ 10:13 ሀዋ 17:28 ቲቶ 1:12 2ጢሞ 4:13
👉 ሌሎች መፅሀፍት አጋዠ የሚሆኑት መስፈርታቸው መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ሲሆን ነው።
👉 መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት ትውፊት ሁልጊዜ ስህተት ነው ማለትም አይደለም።ከእኛ በፊት የተነሱ አባዎቸች ልዩ የሆነን መረዳት ጨብጠዋል በመፅሐፍ ቅዱስ በማመሳከር እንቀበለዋለን።
👉 የመንፈስ ቅዱስ እርዳታን እንፈልግም ማለትም አይደለም፡፡

      እውነተኛው አዳኝ የሚታወቀው በመጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው!!!!
       ወደ እዚህ አዳኝ ኑ፡፡

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 06:30


የዛሬ ከሰዓቱ silent witness እንደተጠበቀ ነው ልክ @6:00 ሲል MKC እንገናኝ።

#ወንጌልን ሊያቆም የሚችልም ምንም ሀይል የለም🔥🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

04 Dec, 04:13


#አዳኙን ማወቅ! Day-3💥
በመጽሐፍ ቅዱስ #እውነት ነው!!
       👇👇
2ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
¹⁶-¹⁷ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

Evange week Day-3 🔥🔥🔥
ሁሉም profile picture ያድርገው
screenshots ደግሞ በዚህ ላኩልን
  👇👇👇
@BaruchNeriah

WCU_Evange_Moblizers

03 Dec, 21:07


WCU_Evange_Moblizers pinned «ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው!!! =================== 📌 መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ #አምላክ መሆኑን በግልጽና በስፋት የሚያስተምር ቢሆንም አንዳንድ ወገኖቻችን ኢየሱስ ቃል በቃል በራሱ አንደበት "እኔ #አምላክ ነኝ #አምልኩኝ" አላለም ስለዚህ አምላክ አይደለም የሚል #ሙግት ያቀርባሉ። በመሠረቱ #በሐዲስ ኪዳን መፃፍ  ይህ ዐይነቱ ንግግር ቃል በቃል ተጠቅሶ አለመገኘቱ እውን ቢሆንም መጽሐፍ…»

WCU_Evange_Moblizers

03 Dec, 20:38


በhard copy ላጣችሁ ይህንን መጠቀም ትችላላችሁ።

WCU_Evange_Moblizers

03 Dec, 20:37


ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው!!!
===================
📌 መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ #አምላክ መሆኑን በግልጽና በስፋት የሚያስተምር ቢሆንም አንዳንድ ወገኖቻችን ኢየሱስ ቃል በቃል በራሱ አንደበት "እኔ #አምላክ ነኝ #አምልኩኝ" አላለም ስለዚህ አምላክ አይደለም የሚል #ሙግት ያቀርባሉ። በመሠረቱ #በሐዲስ ኪዳን መፃፍ  ይህ ዐይነቱ ንግግር ቃል በቃል ተጠቅሶ አለመገኘቱ እውን ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ በራሱ #የአገላለጽ መንገድ #የኢየሱስ ክርስቶስን #አምላክነት በግልጽና በጥልቀት #ያስተምራል።
📌 አንድ #አካል #አምላክ ነው የሚባለው ወይም እንደ አምላክ ሊመለክ የሚገባው "እኔ #አምላክ ነኝ #አምልኩኝ" ብሎ በራሱ አንደበት ስለተናገረ ብቻ አይደለም።
ለምሳሌ በቁርአን ሱራ 28:38 ላይ ፈርኦን እኔ አምላክ ነኝ ብሎ እንደተናገረ እንመለከታለን።
#ፈርዖንም «እናንተ ጭፍሮች ሆይ! #ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላወቅሁም፡፡....... ሱራ 28:38።
📌 ስለዚህ ፈርኦን እኔ #አምላክ ነኝ ብሎ #ስለተናገረ ብቻ #አምላክ ነው ብሎ መደምደም እንደማይቻል ሁሉ አንድ አካል አምላክ ነኝ ስላለ ወይም ብዙዎች አምላክነቱን ስላወጁለት ብቻ አምላክ ሊሆን በፍጹም አይችልም።
👉አምላክነት ባህሪ ነው። ባህሪ ደግሞ የሚገለጠው በንግግር ብቻ ሳይሆን #በተግባር እንደሆነ መረዳት አለብን። ስለዚህ አንድ አካል አምላክ ነኝ ብሎ መናገሩ ብቻ አምላክ ነው ሊያስብለው አይችልም አምላክነቱን በተግባር መግለጥ አለበት።
✍️ ስለዚህ የኢየሱስ የአምላክነት መገለጫ ወይም (ባህሪያት) በመለኮት ባህሪያት ውስጥ ታቅፎ እናገኛለን።
መለኮታዊ ባህሪያት ስንል ፍፁም አምላክ ከሆነው #ከእግዚአብሔር(አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ ) በስተቀር  ማንም ፍጡር በራሱ ሊኖረው የማይችሏቸው ናቸው(ገላ 4:8)።
እነዚህም ባህሪያት የሚከተሉት ናቸው

1.ሁሉን ማወቅ(omniscience)
📌ኢየሱስ ሁሉን ያውቃል!!
✍️ሁሉን ማወቅ አምላክ ብቻ ሊኖረው የሚችል ባህሪይ ነው ኢየሱስ ደግሞ ይህንን ሲያሟላ እንመለከታለን።
ዮሐ2:24-25 ዮሐ 16:30
2.ሁሉን ማድረግ መቻል (omnipotent)
“ሁሉ #በእርሱ_ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”
  — ዮሐንስ 1፥3
3.በሁሉ ቦታ መገኘት (omnipresence)
📌ኢየሱስ በሁሉ ቦታ ይገኛል!!!
✍️ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር የሚሆው በሁሉ ቦታ ስለሚገኝ ነው።(ማቴ 28:20 ማቴ 18:20 ዮሐ 14:18)
✍️ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ስለሆነ በዚህ ምድር ሲመላለስ እንደ ሰው በተወሰነ ስፍራ ቢገኝም እንደ እግዚአብሔር ግን በአንድ ጊዜ በሁሉ ቦታ ይገኛል።
4.ፈጣሪነት (creator)
📌 ኢየሱስ ፈጣሪ ነው!!
“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ #ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
  — ዮሐንስ 1፥1
“ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ #ከጥንት_ምድርን_መሠረትህ፥ #ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤”
  — ዕብራውያን 1፥10
5.ዘላለማዊነት (Eternal)
✍️  ዘላለማዊነት አምላክ ብቻ ያለው ባህሪይ ነው።
📌እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ማለት #ጅማሬም_ፍፃሜም የለውም ማለት ነው።
📌 ኢየሱስ ዘላለማዊ ነው(ራዕ 1:17 ፣ ራዕ 22:13)
📌 በተጨማሪም #ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ለመሆኑ የአምላክነት ግብሩ ባህሪዎቱንና ሐልዎቱን #በተለያየ መንገድ ሲያሳይና ሲገልጽ የነበረበትን የመፃፍ ቅዱስ ክፍሎች እንመልከት:-
📌ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ አንደበት ‹‹ጌታ ነኝ›› ብሎ መናገሩን በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተጽፎ እናገኛለን፡-
ኢየሱስ “ጌታ #(ኩሪዮስ)” የተባለው #አምላክ በመኾኑ እንጂ ለነገሥታት በሚኾን መንገድ በማዕርግ አጠራር አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ የተባለው በክብር ጌትነት ወይም እነ አብርሃም ጌታ በተባሉበት መንገድ ሳይሆን #በአምላክነት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ጌታ ነኝ ሲል ያህዌ ነኝ አምላክ ነኝ እያለ እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል።
(ማቴ 21፡3፤በማር 5:19 ማቴ 12፥8 ዮሐ 13:13) 
📌ኢየሱስ ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› ያለውን ቃል የተናገረው  ፊሊጶስ ‹‹አብን አሳየንና ይበቃናል›› ስላለው ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ የፊሊጶስ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እንዲህ ነው ያለው፡- ‹‹አንተ ፊልጶስ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ አንተ ‹አብን አሳየን› ትላለህ?› እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል፡፡ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ፡፡››
ዮሐ 14፡8-10፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ‹‹እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ›› ማለቱኮ ከአብ ጋር ፍጹም አንድ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ለመሆኑ ራሱ አምላክ ካልሆነ በቀር የትኛው ፍጡር ነው ራሱን ከአምላኩ ጋር አንድ አድርጎ እንዲህ ማለት የሚችለው ??
📌አይሁድ  ኢየሱስ ‹‹ራሱን አምላክ አድርጓል›› የሚለውን ክሳቸው ይዘው ኢየሱስን እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከወሰዱት በኋላ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው።” ማቴዎስ 26፥63  ጌታችን የሰጠው መልስ "አንተ አልህ" ብሎ ነው። «አንተ አልህ» የሚለው አገላለጽ አንተ እንዳልከው እንደዛው ነው ማለት ነው፡፡  በዚህም ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ ራሳችን ከአፉ ሰምተናል ከእንግዲህ ወዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል ሞት ይገባዋል በማለት ስቅላት እንደተፈረደበት እንመለከታለን።
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነኝ ብሏል ለሚለው ለአይሁዳውያን ክስ ይቅርታ አለመጠየቁ ወይም አለማስተባበሉ አምላክ መሆኑን ማረጋገጡ እንደነበር ግልፁ ማሳያ ነው።

📌 ከዚህም በተጨማሪ #ከኢየሱስ ጋር አብሮ  የነበረው #የአይን እማኝ ሆነው ስለ ኢየሱስ አምላክነት በግልፅ፤በማያሻማ መልኩ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ.... እርሱም ልጁ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ነው። እርሱ #እውነተኛ #አምላክና #የዘላለም #ሕይወት ነው።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 5፥20
✍️ #የኢየሱስን_አምላክነት ማወቅ ለደህንነት አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን እውነት በማመን ህይወት እንዲሆንላችሁ
    በእርሱ እመኑ!!!!

WCU_Evange_Moblizers

30 Nov, 10:57


#የወንጌልን_ልብ በይበልጥ እንዲኖራችሁ እና በዚህ ይህወት ጥሞና ለመቀጠል የምትወዱ ዛሬ ማታ #የኮንፍራንሱ አካል እንድትሆኑ።በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን🙏🙏 እንደ አንድ #ወንጌላዊ ይህ #ትምህርት ያስፈልገናል!!!

📌 ታተርፉበታላችሁ @11:30 MKC እንገናኝ

WCU_Evange_Moblizers

29 Nov, 18:53


“አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”
— ሉቃስ 10፥2


#EVANGE MOBILIZERS
#EVANGE MOBILIZERS

👨‍🚀ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት
👨‍💻 MEDIA Team👩‍💻
🔖እርስዎ  አስተያየት አሎት?
👇👇👇
📨 @Wcu_EvaSUE

WCU_Evange_Moblizers

29 Nov, 07:54


📣ተዘጋጁ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ትልቅ #የወንጌል_ድግስ አለ🔥🔥🔥 የፋሲካው በግ #ክርስቶስ_ኢየሱስ በጊቢያችን ከፍ ብሎ የሚታይበት ጊዜ ነው።

💥ይህንን #ድንቅ_ስም 🗣ለማወጅ ማን ነው የተዘጋጀው?🙌

WCU_Evange_Moblizers

26 Nov, 17:34


ነገ #የወንጌል ቀን ነው ሁላችሁም 11:00 እንገናኝ🙌 ጌታ መልካም ነገርን ያደርጋል!🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

26 Nov, 10:47


Mission Conference

አርብ ህዳር  20 ከ 11፡30 ጀመሮ እና ቅዳሜ ህዳር 21 ሙሉ ቀን ከ አገልጋይ ኤልያስ ጌታቸው እና ዘማሪ ሙሴ ጋር  በ  አምብቾ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

“አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”
  — ሉቃስ 10፥2

መቅረት አይችልም!!!

WCU_Evange_Moblizers

25 Nov, 16:59


የዛሬው ነው በደንብ አንብቡት

የተኛውንም ጥያቄ ካላችሁ👇👇👇
@christaloneeee

WCU_Evange_Moblizers

22 Nov, 14:53


የሚቀጥለው #ሰኞ የመጨረሻው ክፍል #five_sola ይቀጥላል ሁላችሁም @11:00 መገኘት አለባችሁ @11:30 ትምህርቱ ይጀምራል!!

📌 #መፅሐፍ ቅዱስና #ማሳታወሻ እንዳይረሳ🙏

WCU_Evange_Moblizers

20 Nov, 07:17


ዛሬ #ወንጌልን በህብረት የምንሰራበት ቀን ነው ማንም ሰው #እንዳይቀር! @11:00 ፌሎ የተከራየበት እንገናኝ😍

ልጆችን #የቀጠራችሁ መጣችሁ በጊዜ ፀልየን እንመለሳለን!!

WCU_Evange_Moblizers

19 Nov, 15:20


Part#2 ነው

WCU_Evange_Moblizers

18 Nov, 08:38


WCU_Evange_Moblizers pinned «ሰላም ወንጌላዊያን ሰኞ እለት ከባለፈው የቀጠለ Orthodox evangelism and the five's sola part 2 ይቀጥላል. ባለፈው #ጊዜ ሳይበቃን ቀርቶ #አቋርጠን ነበር ይህ ነገር አሁንም እንዳይከሰት ልክ @11:00 ሲል #ትምህርት እንጀምራለን ስለዚህ በጊዜ እንድትመጡ❗️ Notice:- መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ያልያዘ ሰው እንዳይመጣ!!»

WCU_Evange_Moblizers

17 Nov, 12:15


ሰላም ወንጌላዊያን ሰኞ እለት ከባለፈው የቀጠለ Orthodox evangelism and the five's sola part 2 ይቀጥላል.
ባለፈው #ጊዜ ሳይበቃን ቀርቶ #አቋርጠን ነበር ይህ ነገር አሁንም እንዳይከሰት ልክ @11:00 ሲል #ትምህርት እንጀምራለን ስለዚህ በጊዜ እንድትመጡ❗️

Notice:- መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ያልያዘ ሰው እንዳይመጣ!!

WCU_Evange_Moblizers

16 Nov, 17:27


ከ ፊታችን እሁድ ህዳር 8 ጀምሮ ለ ሶስት ተከታታይ ሳምንታት spritual maturity በሚል ርዕስ ከ ቴዎድሮስ ተሾመ ጋር በ pray mobilizers የተዘጋጀ የትምህርት ጊዜ። ቦታ ፌሎ የተከራየቤት ቤት ከ 11፡00 ጀምሮ።

መቅረት አይቻልም!!!

WCU_Evange_Moblizers

13 Nov, 17:28


ዛሬ ስለነበረን ጊዜ #እግዚአብሔር ይመስገን🙌 እግዚአብሔር በነፍሳት #መዳን ባርኮናል🔥 ቀጣይ #ሳምንት ደግሞ ከዚህ በሚበልጥ ጌታ ይረዳናል እስቲ ደስ ያለው እግዚአብሔርን በያለበት #ያመስግን🙏

WCU_Evange_Moblizers

13 Nov, 05:24


የዛሬው የወንጌል ቀን እንደተጠበቀ ነው ሁላቹም @11:00 ሲል እንገናኛለን ልጆችን #የቀጠርን መጥተን ፀልየን እንሄዳለን ውጭ ላይ የምንሰራም አብረን #የክርስቶስን_ወንጌል #በሀይል እንናገራለን እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን ያደርጋል🔥🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

11 Nov, 18:49


ይህቺ መፅሐፍ በብዙ ትጠቅማችኃለች ጊዜ ወስዳችሁ ለማንበብ ሞክሩ

WCU_Evange_Moblizers

10 Nov, 05:57


ነገ ሰኞ #ኦርቶዶክስ እና #አምስቱ #ብቻዎች(The five sola's) በሚል በevange mobilizer የተዘጋጀ #ትምህርት ስለሚኖር ሁላችሁ @11:00 ላይ chapel እንገናኝ

📌መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ!!

WCU_Evange_Moblizers

08 Nov, 10:21


ነገ #ቅዳሜ MKC ከጠዋቱ 2:30 ላይ እንገናኝ🔥🔥
📌 ማንም #መቅረት የሌለበት ስልጠና ነው!!

WCU_Evange_Moblizers

07 Nov, 05:49


ሰላም እንዴት ናችሁ #ወንጌላውያን የሚቀጥለው ቅዳሜ ማለትም 30/02/2017 በተጋባዥ #አገልጋዮች የተዘጋጀ #የእግዚአብሔር_ተልዕኮ በሚል #የትምህርት እና #ስልጠና ጊዜ ይኖረናል በመሆኑም ከጠዋቱ @2:30 ላይ #አንቢቾ #MKC እንገናኝ💥

WCU_Evange_Moblizers

05 Nov, 19:33


ትንቢተ ኤርምያስ
20፥9
እኔም፦ የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
ሰላም ወንጌላዉያን ሰላም ይብዛላችሁ ነገ የሚኖረን ወንጌልን የመመስከር ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው ማንም እንዳይቀር

WCU_Evange_Moblizers

04 Nov, 02:06


WCU_Evange_Moblizers pinned «ነገ ማለትም ሰኞ Evangelism in small Group የሚል አዲስ #የትምህርት ጊዜ ይኖረናል በመሆኑም @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት በጊዜ እንገናኝ ። 📌 #በsmall_group ወንጌልን መስራት የምትወዱ እና ፍላጎቱ ያላችሁ እንዳትቀሩ»

WCU_Evange_Moblizers

03 Nov, 06:16


ነገ ማለትም ሰኞ Evangelism in small Group የሚል አዲስ #የትምህርት ጊዜ ይኖረናል በመሆኑም @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት በጊዜ እንገናኝ ።

📌 #በsmall_group ወንጌልን መስራት የምትወዱ እና ፍላጎቱ ያላችሁ እንዳትቀሩ

WCU_Evange_Moblizers

02 Nov, 10:42


Channel photo updated

WCU_Evange_Moblizers

01 Nov, 10:32


እንዴት ናችሁ ወንጌላውያን ባለፈው #እሮብ እለት #in_reach የሰራቹ ወገኖች ሪፖርታችሁን በዚህ link ላኩልን👇👇👇
@christaloneeee

WCU_Evange_Moblizers

31 Oct, 05:59


የፕሮግራም መሪ ሐሳብ ንጉሱን መከተል
📍ማወቅ
📍መታዘዝ
📍ማረፍ
አርብ ጥቅምት 22 ከ 11፡30 ጀመሮ እና ቅዳሜ ጥቅምት 23 ሙሉ ቀን ከ ፓስተር አቤኔዘር ታደሰ እና ዘማሪ ምናሴ ጋር በ አምብቾ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

መቅረት አይችልም!!!

WCU_Evange_Moblizers

30 Oct, 06:31


ሰላማችሁ ይብዛ🙌 እንዴት ናችሁ #ወንጌላውያን ዛሬ ማለትም #ዕሮብ እለት #ወንጌልን፦
👉 in reach
👉በጀማ
👉 #አንድ_ለአንድ
👉 ወረቀቶችን በመያዝ
የምንሰራበት ቀን ስለሆነ ሁላችንም @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት እንገናኝ🥰


“ሕይወትም ተገለጠ #አይተንማል #እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን #የዘላለምን_ሕይወት እናወራላችኋለን፤”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥2

WCU_Evange_Moblizers

28 Oct, 21:01


የዛሬ ትምህርት ነዉ 🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

26 Oct, 13:52


#መቅረት #አይታሰብም!!💥💥🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

26 Oct, 09:54


ሰላም mibilizers በሚቀጥለው #ሰኞ #እንዴት_ወንጌልን ማዳረስ እንችላለን በሚል መደበኛ #የትምህርት ጊዜ ይጀምራል @11:00 ፌሎ የተከራየበት ጊቢ

#Notice:-
1ኛ አመት ተማሪዎች ለእናንተ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ መምጣት ይኖርባችኋል።

📌 ስትመጡ #ማስታወሻ እና #መፅሐፍ_ቅዱስ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ🙏

WCU_Evange_Moblizers

22 Oct, 21:20


ሰላማችሁ ይብዛ🙌 እንዴት ናችሁ #ወንጌላውያን ነገ ማለትም #ዕሮብ እለት #ወንጌልን፦
👉በጀማ
👉 #አንድ_ለአንድ
👉 ወረቀቶችን በመያዝ
የምንሰራበት ቀን ስለሆነ ሁላችንም @11:00 ላይ ፌሎ የተከራየበት እንገናኝ🥰


“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ #ለሚያምኑ ሁሉ #የእግዚአብሔር_ኃይል #ለማዳን ነውና።”
— ሮሜ 1፥16

WCU_Evange_Moblizers

20 Oct, 05:58


📌በብዙ ስለ እስልምና እንድናወቅ መጽሐፍት የጻፈ አሁንም እየተጋ #ያለ_ዐቃቤ ክርስቲያን
#Sahih #Iman
በቴሌግራም መጥቶል
#ሁላችሁም በዚህ link Join አድርጉ ለሌሎችም share አድርጉ👇👇👇

#
@Sahih Iman

https://t.me/YEA_2016

WCU_Evange_Moblizers

19 Oct, 16:10


💥💥#Announcement❗️❗️
ሰላም🙌 #ወንጌላውያን እንዴት ቆያችሁ በሚቀጥለው #ሰኞ ማለትም 11/02/2017 የEvange mobilizer #የመክፈቻ ፕሮግራም ስለሚኖረን ሁላችንም ልክ ሰኞ #@11:00 ላይ ፌሎ #የተከራየበት (Chapel) በጊዜ እንገናኝ

📌እግዚአብሔር በጊቢያችን ያስጀመረውን #የወንጌል_ሀይል ዘንድሮም #በክብር ያስቀጥለዋል💪💪

WCU_Evange_Moblizers

13 Oct, 19:37


የቀጠለ.....

“ተሓድሶና ቃሉ”
በአውሮፓ በ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረው ተሓድሶ፥ ቤተ ክርስቲያንን ከአደገኛ የሞት እንቅልፍ አባንኗታል ።
✍️ #አዳሽነት ባህሪው የኾነው #አሐዱ-ሥሉስ አምላክ በደካማ ሰዎች በኩል ቤተ ክርስቲያኑን ጎብኝቷታል ። ክስተቱ ቁልፍ #ነገረ_ መለኮታዊ ዕሳቤዎች የተነቀነቁበት ብቻ አልነበረም ። የአገሮቹን ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ጭምር ትልቅ ለውጥ ያመጣ ነበር ።
👉የቤተ ክርስቲያን ተሓድሶ ያልነበረውን አላመጣም ፤ ዐዲስ ነገር አልጀመረም ። #መሰረቱ ላይ #የተከመረውን_አቧራ አራገፈ እንጂ! ድንግዝግዝ ጭጋግ ላይ ብርሃን ፈነጠቀ እንጂ!
📌የቤተ ክርስቲያን ተሓድሶ በቀላል ቋንቋ እውነተኛውን የወንጌል ብርሃንና እርሱን የሚመጥን ኑሮ መልሶ መቀዳጀት ማለት ነው ። ወደ ቀደመው ርቱዕ መንገድ መመለስ ነው ።
✍️ #እግዚአብሔር በደካማ ሰው በኩል የቤተ ክርስቲያኑን የፊት መጨማደድ #በቃሉ_ሂጶብ የሚያጸዳበት፥ በጸጋው ዘይት ዝገቷን የሚያራግፍበት ሂደትም ነው ።
✍️ምክንያቱም #በጎሎጎታ የተመረቀው የሰማያዊው መንግሥት አብዮት ጥልቀቱና ኅይሉ መታወቅ ስላለበት ። የመስቀሉ ሥራ ሁሌም ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች ሞኝነት እንደሆነ መቀጠል አለበት ።
📌ሰው በራሱ ሞራላዊ ጥረትና የአዕምሮ ልህቀት አምላክን ማወቅና ከኅጢአት በሽታው መገላገል እንደማይችል ሊገባው ያስፈልጋል ። ባጠቃላይ የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ !
📌ተሓድሶው ሲጀመር እጅግ አወዛጋቢ ነበር ። በክርስትና ስም በተደላደለው የሰው ሥርዐትና ወግ ላይ የተወረወረ ቦንብ ነው ። ፍንዳታው ከሩቅ ተሰምቶ በየቦታው ሲብላሉ የነበሩ ተመሳሳይ ጩኸቶች እንዲሰሙ አስችሏል ። እስከዛሬም ድረስ ‹ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት› የሚለው የተሓድሶ ጩኸት ለአንዳንዶች ጆሮ የማይስማማ እንግዳ ድምጽ ነው ። ጥቂቶችን ያስቆጣል ፤ በሌሎች ዘንድ ግርታንና ፌዝ ይፈጥራል ። አወዛጋቢነቱ በከፊል የሚመነጨው ሰው ጒረኛና ጥቅመኛ ስለሆነ ነው ። ትህትናንና ዝቅ ማለትን ፣ በየትኛውም ጉዳይ 'አስተዋፆ የለህም ወይም አትችልም' መባልን አይፈልግም ። ተሓድሶ ደግሞ የሰውን ጥበብና ችሎታ አሳንሶ የእግዚአብሔርን ጥበብ [መሲሑን] የማላቅ ፕሮጀክት ነው ።
📌በተሓድሶ #ነገረ-መለኮት ውስጥ የሰው ትምክህት ቅንጣት ቦታ የለውም ። ተሓድሶን መናፈቅ ማለትም ይኼንን “መራራ”
እውነት ዐውቆና ፈቅዶ መቀበል ማለት ነው ። ሰው ድነቱን — ወይም ስለ እግዚአብሔር ያለውን ልከኛ እውቀትና ምልልስ — በራሱ ማስተዋል ፣ በመልካም ሥነ ምግባር ወይም በኅይማኖት ድርጅት አባልነት ማግኘት አይችልም ። ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት የሰማዩ መንግሥት ጉዳይ ከሀ እስከ ፐ ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ነው ። ማንም በመልካም ሥራው እንዳይመካ!
👉 #ማዳን የእግዚአብሔር ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? እግዜሩ የሰውን ድነትና ዋስትና በተመለከተ ኪዳን #የገባውም_ የፈጸመውም #ብቻውን ነው እያልን ። ይኼም ዘላቂና አስተማማኝ አምላካዊ ኪዳን ነው ።
✍️በብሉይ ኪዳን ለአብርሃም የተገባለት የተስፋ ቃል የተፈጸመው በዐዲሱ ኪዳን በመሲሑ ደም ነው ።
📌ከኅጢአት በሽታ መዳን ፣ በትንሣኤው ኅይል መጽደቅ ፣ ዐዲስ ፍጥረት መኾን ፣ መላ-ዐለሙን በሚያድስበት ድንቅ አሠራሩ ከርሱ ጋር አብሮ ሠራተኛነት ፣ በዐዲሱ ሰማይና ምድር ከንጉሡ ጋር በትንሣኤ አካል መክበር ... ተጀምሮ እስከሚያልቅ #በእግዚአብሔር_ ጸጋ ላይ ብቻ ከተመሠረተ - ክብሩም ምስጋናውም ለእርሱ ብቻ ይገባል ። “የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ” እንዲል ቃሉ!
📌ይኼን እውነት ሓዳሲያኑ ከየትም አላገኙትም ። ልዩ ፍጥረት አልሰበከላቸውም ፤ ልዩ መገለጥም አልመጣላቸውም ። በእጃቸው የነበረውን ቅዱሳት መጻሕፍትን አክብረው ሲገልጡትና ሲያጠኑ - እውነቱ በራላቸው ። ለአስተምህሮም ሆነ ለምልልስ ቃሉን ቀዳሚ ባለስልጣን አድርገው ሲሾሙ - ለእግራቸው መብራት ለመንገዳቸው ብርሃን ሆነላቸው ። ከቆየ የቤተ ክርስቲያን ልማድም ሆነ የሰው ወግ ቃሉን ሲያስበልጡ — የጸጋው ጉልበትና የሰው ድሽቀት ታያቸው ።
“#ቅዱሳት_መጻሕፍት ብቻ” ብለው ሲጸኑ — ሁሉም ጉዳይ ቦታ ቦታውን ያዘላቸው ።
በOctober 31, 1517 ፣ 95ቱን አንቀፆች በቪተንበርግ ካቴድራል ማስታወቂያ ሰሌዳ በመለጠፍ የተሓድሶን እሳት በመለኮስ ፈር ቀዳጅ የሆነው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር፥ ስለተቀጣጠለው እንቅስቃሴ ሲናገር #“I did_ nothing; the Word did everything.
- እኔ ምንም አላደረኩም፤ ሁሉን ያደረገው ቃሉ (የእግዚአብሔር) ነው!” እንዳለው ነው!
ክብር #ለአዳሹ_ያሕዌ ይሁን!፡


ይቀጥላል....

WCU_Evange_Moblizers

12 Oct, 13:42


ሰላም ወንጌላዊያን አንድ ወዳጄ በፅሁፍ ያጋራኝን ላጋራችሁ🙏 ነገር ግን ይህንን #ትምህርት በ Evange mobilizer በዚህ አመት ሰፋ ባለ መልኩ እንሰጣለን ስለዚህ እያነበባችሁ ቆዩልን😍


የተሓድሶው «ብቻዎች»

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና፥ የእምነት መርኾቹን ያለደባል የሚያስኬድ «አጥላይ» (Exclusive) እምነት ነው። ለሰው ድነትና ለአምልኮተ እግዚአብሔር ብዙ የሙከራ ዕድልና ምርጫ አይሰጥም ። መንገዱ አንድ ፣ ግቡም አንድ ነው ይለናል ።
👉አጥላይ ስለሆነ #«ብቻ» በሚሉ መርኾች ይመራል። እነዚህ «ብቻዎች» #የእምነቱ-መሠረታዊያን ፣ #የአስተምኀሮው-ምሠሶዎችና የተሓድሶ ምንጮች ናቸው።
ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስን በማወቅ እንዲድኑ፣ ወደ እውነት የሚመራ ግልጽ መንገድ ለመጠቈም እግዚአብሔር #«ብቻዎችን» ተጠቅሟል ማለት እንችላለን። ይኼም ከብዙ #መወዛገብ ጠብቆናል ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቂት ማስረጃዎችን እንመልከት፤
• «ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም #[ብቻ] አምልክ» ሲል ስግደትና አምልኮ የሚገባው አምላክ እርሱ ያሕዌ #ብቻ መሆኑን ያስረግጣል።
📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ ከቶ የለም» ሲል «አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው—እርሱም እኔ ነኝ» ማለቱ ነው።
📌 ሐዋርያው ጴጥሮስ «መዳን #በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ሌላ ስም የለምና» ሲል ሰውን ከኅጢአት ሞት ሰውን የሚያድን «አንድ #ስም ብቻ» አለ ማለቱ ነበር።
📌ሃዋሪያው ጳውሎስም “ጸጋው #በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ #ከእናንተ አይደለም” ሲል ደኅንነት ከእግዚአብሔር ለእናንተ የሆነው እንዲያው #በጸጋው-ብቻ ነው ማለቱ ነበር።
📌እንዲሁም፤  “ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለን” ሲል በጻዲቁ እግዚአብሄር ፊት ሃጢው የእርሱን ጽድቅ ለመቀበል #እምነት ብቻውን በቂ እንደሆነ ያረጋግጥልናል።
✍️በመካከለኛው ዘመን የተነሱት የተሓድሶ መሪዎች ከሮሟ ቤተ ክርስቲያን ያልተስማሙትም ልዩ ትምህርት ስላመጡ አልነበረም ። #ሰውኛ የሆኑ ተጨማሪ ነገሮችን አንቀበልም በማለታቸው እንጂ ። ቤተ ክርስቲያኗ የምታራምዳቸውን ደባል አስተምኅሮዎችና ልምምዶች #በመጽሐፍ _ቅዱሳዊ ብቻዎች አጥብቀው ተቃወሙ ። ብልሹ የሰው ወግና አሰራርን እየሞገቱ ፃፉ ፤ አስተማሩ። በዚህም በብዙ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ ሆነዋል።

✍️ #የተሓድሶው እሳት ምንጩ ግን ከምድር ስላልሆነ ሊጠፋ አልቻለም!
አምስቱ ብቻዎች (The Five Solas) ተብለው የሚታወቁት መርኾች፣ ክርስትናን ወደ ቀደመው መንገድ ለማደስ የነጠሩ መሣሪያ ሆነው አገልግለዋል ። የወንጌልን እውነት ዳግም አጽንተዋል ። 📌ዛሬም እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በሰው ልማድ ቆሽሻ ተሓድሶ ሲያሻት እንደ #ሰንደቅ ከፍ አድርጋ የምታነሳቸው፣ እንደ አዋጅ ጮክ ብላ የምታውጃቸው እውነቶች ሆነዋል። የወንጌላዊው ክርስትና አንኳርና ልዩት መለያም ናቸው።

እነዚህም «አምስቱ ብቻዎች»፡
📌በክርስቶስ ብቻ (#Solus_Christus) - ብቸኛው አዳኝ
📌መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (#Sola_Scriptura) - ብቸኛው ላእላይ የሥልጣን ምንጭ
📌በጸጋ ብቻ (#Sola_Gratia) - ብቸኛው የድነት መንገድ
📌በእምነት ብቻ (#Sola_Fide) - ብቸኛው የድነት ዘዴ
📌ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ (#Soli_Deo_Gloria)- ብቸኛው የድነት ዓላማ
እዚህ ጋር አንድ እውነት ልብ ማለት ያስፈልጋል።
✍️የወንጌል እውነት #አጥላይ ነው ሲባል አትጠጉኝ፣ አትንኩኝ ባይ ነው ማለት አይደለም። እውነት ፣ ሕይወትና መንገድ አንድ ብቻ ቢሆንም - ብዙዎች ወደዚህ መንገድ ተጋብዘዋል። ሰዎች እንዲድኑ የውድ ልጁን ዋጋ የከፈለው እጅግ አፍቃሪው አምላክ ፥ የግብዣው ጥሪ ካርድ «ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ» የሚል ነው። መጋቢ ቲሞቲ ኬለር ባንድ ወቅት ስለወንጌል አጥላይነትና አካታችነት አያዎ በአንድ አረፍተ ነገር ሲገልጹ

«The gospel is an exclusive truth but it's the most inclusive 'exclusive truth' in the world.» በግርድፍ ትርጉም ወንጌል በዐለም ውስጥ የሚገኝ እጅግ አካታች የሆነ 'አጥላይ እውነት" ነው።

WCU_Evange_Moblizers

10 Oct, 15:39


ልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የመክፈቻ ፕሮግራም የፊታችን አርብ ጥቅምት 01 ይደረጋል !!

በዕለቱ በ 11፡30 በመገኘት አብረውን እግዘብሔርን ያምልኩ!!

“አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።”
— መዝሙር 145፥10

የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት !!

WCU_Evange_Moblizers

04 Oct, 08:17


የአፖሎሚክስ ኦንላይን ትምህርት ቤት ልዩ የክረምት ሰልጣኞ የምርቃት መርሀ ግብር

በአፖሎሚክስ ኦንላይን ትምህርት ቤት በክረምት መርሀግብር በ “Apologetics” (አቅብተ እምነት ) እና በ “Polemics” (መሞገት ) ሲሰለጥኑ የቆዩ ተማሪዎች መስከረም 26/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በሰርተፊኬት መርሀግብር የምናስመርቅ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው።

በ “Apolomics Online School” የተማሩ ተማሪዎች :-
 
ክርስትናን የሚያውቁ እና የሚከላከሉ
ከክርስትና ውጪ ያሉትን በራሳቸው አስተምሮ በእውቀት የሚያፈርሱ
ለወንጌል አገልግሎት የታጠቁ ናቸው።

🎓በሀይማኖት ንፅፅር | Comparative   Religion የወሰዷቸው ኮርሶች
✝️ስነ ሥላሴ Trinity
✝️ነገረ ክርስቶስ Christology + Soteriology
✝️ስነ መጵሐፍ ቅዱስ Bibliology
💪እስልምናን ማጥናት Islamic study
🤗ስነ አምንዮ Logic
😍የወንጌል ስርጭት Evangelism


በእለቱ :-
👉እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት
👉ተማሪዎች ውጤት እና ሰርተፍኬታችሁን የምታገኙበት
👉የተጋበዙ አገልጋዮች የሚገኙበት
👉እንዲሁም ስለ የወደፊት #ፕሮጀክቶቻችንን ለተማሪዎች የምናሳውቅበት  መርሀግብር ይኖረናል።

እሁድ መስከረም 26/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ አይቀርም

የአገልግሎቱ ተደራሽነት ይሰፋ ዘንድ  
#Share
#Share
#Share

አድርጉ!!

Join our channel
🎓🎓🎓🎓 @apolomics

WCU_Evange_Moblizers

29 Sep, 18:25


“A farmer plows his field, sows the seed, and fertilizes and cultivates—all the while knowing that in the final analysis he is utterly dependent on forces outside of himself. He knows he cannot cause the seed to germinate, nor can he produce the rain and sunshine for growing and harvesting the crop. For a successful harvest, he is dependent on these things from God. Yet the farmer knows that unless he diligently pursues his responsibilities to plow, plant, fertilize, and cultivate, he cannot expect a harvest at the end of the season. In a sense he is in a partnership with God, and he will reap its benefits only when he has fulfilled his own responsibilities.
Farming is a joint venture between God and the farmer. The farmer cannot do what God must do, and God will not do what the farmer should do.
We can say just as accurately that the pursuit of holiness is a joint venture between God and the Christian. No one can attain any degree of holiness without God working in his life, but just as surely no one will attain it without effort on his own part. God has made it possible for us to walk in holiness. But He has given to us the responsibility of doing the walking; He does not do that for us.” ( Jerry Bridges, The Pursuit of Holiness)

WCU_Evange_Moblizers

09 Sep, 18:14


selam wongelawuyan yihenin youtube channel subscribe enditaderguna tmrtun enditketatelu adera lemalet ewodalew..mechem beki malet man malet endehone swur ayhonbachihum💥💥🔥🔥

WCU_Evange_Moblizers

09 Sep, 18:12


https://youtu.be/poR_n-pkiAg?si=fSw8FElQX_CXCVbO

WCU_Evange_Moblizers

28 Aug, 08:28


“እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ #በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።”
  — መዝሙር 27፥4


📌ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት መኖርንና መቅደሱን ያይ ዘንድ ለመነ! ይህ በሱ ዘንድ #ትልቅ መሻቱ ነበር።

✍️ሚያስደንቀው ነገር ግን ዳዊት ሊያየው ያሻው ያ #የእግዚአብሔር መኖሪያ #መቅደስ እኛ ሆንን! እግዜሩ ሰው በሰራው ውስጥ ያድር ዘንድ #አልወደደም! እኛን መረጠ! አፅናፈ አለሙን የመላው ገደብ #የለሽ(infinite) አምላክ በዚህ ደካማና ደቃቅ ብላቴና ውስጥ አደረ ...

ክብር ለስሙ ይሁን!🙌

“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16

“ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20

WCU_Evange_Moblizers

23 Aug, 11:55


[መስቀሉ የእምነታችን ጅማሬና ፍጻሜ የተሸመነበት  ሰማያዊ ጥበብ ነው።]

°°°°
እምነታችን የጀመረው ከእናታችን ማህፀን የተወለድን ቀን አይደለም ፤ እምነታችን የጀመረው ከመስቀሉ ስር በፈሰሰው ክቡር የልጁ ደም ላይ ባለ መታመናቸንና መደገፋቸን ላይ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ እምነታችን ያረፈበት መነሻ ነውና መዳረሻ አለው ።
ይህም መዳረሻ ከእምነታችን ጀምሮ በህይወታችን በተከወኑ ትሩፋቶች ላይ የሚቀር ሳይሆን እዛው መስቀሉ ላይ የተመረኮዘ ነው። እምነታችን የተጀመረበት  የመስቀሉ ቦታ የምንጨርስበት መዳረሻችንም ነው ። የእምነታችን መጀመሪያና መጨረሻ በመስቀሉ ማለትም ስለ ኃጢአታችን በፈሰሰው ክቡር የኢየሱሰሰ ደም ላይና ራሱን ምትክ ባደረገበት የቤዝሆት ጎዳና ላይ ያረፈ ነው።
°
ለዛም ነው ለራሳችንና በዚህ ክቡር ደም ለተዋጁ “ ... እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ... ።”[ዕብ 12፥1-2] በሚል ህያው ቃል የምንተናነጸው ። አዎ በመስቀሉ ላይ የተሰራውን የድህነት ሥራ በማመን የጀመርነው መንገድ መጨረሻ አለው ፥ ያም መጨረሻ ለመዳን መስቀሉን እንዳየነው እስክንጨርስም ድረስ ትኩር ብለን እያየን መንገዳችንን በትዕግስት እንድንሮጥ የሚያዝ ነው።
°
ስለዚህም በእምነት የጀመርነው መንገድ የክብር ፍጻሜን  የሚያገኘው ፥ በመስቀሉ ስራ ለኛ የሆነልንን በማሰብና በዛም ሀሴት እያደረጉ ባለመቀጠል ሳይሆን ፤ መስቀሉን ዘወትር እየተመለከትን ፈለጉን በተወበት አካሄድ ሩጫችንን በትዕግስት በመሮጥ ነው። ቻርልስ ሰፐርጀን በአንድ ስብከቱ ላይ  ይህንኑ ሃሳብ ሲያደረጅ " የእምነትህን ራሰና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንጂ እምነትህን አትመልከት ። ምክንያቱም ጸሎትህን ፣ ቃለ እግዚአብሔርን ስታካፍል ያለ እይታህን ፣ መልካም ተግባርህን ፣ ወይም ትጋትህን በማየት ደስታን አታገኝም። ለነፍስህ እረፍት የሚሰጣት አንተ ያለህ ሳይሆን ኢየሱስ ላንተ የሆነው ነው።" ብሏል ።
°
ሩጫችንን በትዕግስት የምንሮጠው አንድም እንዳንዘገይ ሁለትም ተሰነካክለን እንዳንቀር ነው። መስቀሉን ስናይ ፈለጉን በተወልን መንገድ ላይ ነንና በነፍሳችን ዝለን  እንዳንደክም ፣ ጽናቱም ጽናታችን እየሆነ ያግዘናል ፣ በመልካም እጁም እየደገፈና እየሸላለመ ይመራናል። አዎ መስቀሉ የዳንንበት ብቻ ሳይሆን እስከፍጻሜም የምንጠብቅበት መመካታችን ፤ ደግሞም ስለዘላለሙ ህይወት እርግጠኛ የሆንንበት መተማመኛችን ነው።
°
እናማ አይናችንን ዛሬም በመስቀሉ ላይ በማድረግ ፥ ሞቱንና  መከራውን ስናስብ የክብር ፍጻሜያችን ህያው ተስፋ ፥ ያለድንግዝግዝ ወገግ ብሎ ይታየናል። ደግሞም ጎዳናውን በማሰብና በመመልከት እንጽና ፤ ያኔ  የማጽናናቱ ደመና በመስቀሉ ስራ ለተጠለልን ለኛ [ ለጥገኞቹ ] የየዕለት ጠል በመሆን ያረሰርሰናል።

📌ምክንያቱም መስቀሉ #የእምነታችን ጅማሬና ፍጻሜ የተሸመነበት  #ሰማያዊ #ጥበብ ነውና ነው።

✍️ ነገረ-ወንጌላውያን

WCU_Evange_Moblizers

11 Aug, 13:01


ጋይስ እስቲ ማታ ማታ መዝሙረ ዳዊትን እያነበብን የግላችን ጸሎት ጨምረንበት እንተኛ😣😣
መዝሙረ ዳዊት እጅግ አጽናኝ የሆኑ  መዝሙሮችን በክምችት የያዘ ነው። በጥልቅ ሥነ-መለኮትና በግጥም ያለንበትን ስሜቶቻችንን የሚገልጡ መልእክቶችን በመያዝ በእውነቱ ተወዳዳሪ የለውም። ይህንን በመረዳት ታላላቅ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ስለ መዝሙረ ዳዊት ብዙ ነገር ብሏል።
ቅዱስ አውገስጢን መዝሙረ ዳዊትን የነፍስ መስታወት ነው ይላል።  የተጻፉ መዝሙራት የእግዚአብሄር ምርጦች ደስታ፣ ሀዘን፣ ተስፋና ሌሎች አሉታዊ ልምምዶች በህይወታቸው ውስጥ ሲገጥሟቸው እራሳቸውን እንዲያዩ የሚረዳቸው መስታወት  እንደሆነ ይናገራል።
ጋሽ ሉተርም መዝሙረ ዳዊት የቅዱሳን ሁሉ መጽሐፍ ነውና እያንዳንዱ ሰው የራሱ ቅጂ ሊኖረው ይገባል ይላሉ። አማኞች መጸሃፉን ሲያነቡ ይጽናናሉ፣ ትምህርቶችን ያገኛሉ፣ የጸሎት ህይወታቸውንም ያሻሽሉበታል በማለት ይመክራሉ
ወንድማችን ካልቪንም መዝሙረ ዳዊትን የነፍሳችን ስሪት አድርጎ ያቀርባል። በዚህም መሰረት መዝሙረ ዳዊት የጸሎትና የአምልኮ ምንጭ እንደሆነ ያስተምር ነበር። በቤተክርስቲያንም ውስጥ መዘመር ያለበት በመጸሃፉ ውስጥ የተዘመሩ መዝሙሮች ብቻ ናቸው ብሎ ያምናል
አጎታችንም ሲኤስ ሊዊስ መዝሙረ ዳዊትን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት፣ ስሜቶቻችንና አሳቦቻችንን የሚገልጽ ትክክለኛ የጸሎት ቋንቋ ነው ብሎ ያምን ነበር። ፓስተራችንም እስፐርጀን መዝሙረ ዳዊት የዳዊት የጸሎት ግምጃ ቤት ስለሆነ አማኞች ከዚህ ግምጃቤት  ለጸሎታቸው መመሪያ እንዲወስዱ ያበረታታ ነበር።
ስለዚህ ተወዳጆች በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ የሚገኙትን መንፈሳዊ ሀብቶች ተገንዝበን በጸሎታችን እንድናሰላስልና በህይወታችን እንድንተገብር አበረታታችኋለሁ። ጥልቅ የመጽናናት፣ የጥበብ እና የአምልኮ ምንጭ ሆኖን በቤተክርስቲያን ህይወትና በግላችን እንድንለማመድ ጌታ ሁላችንን ይርዳን

WCU_Evange_Moblizers

03 Aug, 08:14


"ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና #አዘነላቸው።" (ማቴ. 9፥36)

"ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና #አዘነላቸው ድውዮቻቸውንም ፈወሰ።" (ማቴ. 14፥14)

"ኢየሱስም #አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፥ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።" (ማቴ. 20፥34)

"ኢየሱስም #አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ “እወድዳለሁ ንጻ” አለው።" (ማር. 1፥41)

"ጌታም ባያት ጊዜ #አዘነላትና፦ “አታልቅሽ” አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ ... የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ፤ ሊናገርም ጀመረ፥ ለእናቱም ሰጣት።" (ሉቃ. 7፥13-15)

📌 #የሚያዝን፣#የሚራራ፣ለሁሉም #የሚያስብ ድንቅ #ጌታ  #ኢየሱስ #ክርስቶስ🙏🙏

WCU_Evange_Moblizers

27 Jul, 08:16


"ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ_ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡

"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

WCU_Evange_Moblizers

24 Jul, 13:26


ይህንን አስቡ #በምትንበረከኩበት ጊዜ እግዚአብሔር #እንደሚሰማችሁ እንዲሁም #ቃሉን በምታነቡበት ጊዜ እርሱ #እንደሚናገራችሁ አስቡ።

WCU_Evange_Moblizers

24 Jul, 13:26


"For this reason I bow my knees before the Father, from whom every family in heaven and on earth is named, that according to the riches of his glory he may grant you to be strengthened with power through his Spirit in your inner being, so that Christ may dwell in your hearts through faith - that you, being rooted and grounded in love"
"ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥"

Ephesians 3:14-17

WCU_Evange_Moblizers

12 Jul, 11:10


🦻አስደሳች ዜና🗣🗣 ለመላው ክርስቲያኖች በሙሉ ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ! የሰርተፊኬት (Certificate ) ትምህርት

🗣አሁኑኑ ይመዝገቡ!!  ፈጥነው ለሚመዘገቡ 70 ሰዎች ብቻ

🎓ልዩ የሆነ የክረምት ትምህርት Online በ አፓሎሚክስ |Apolomics ይጀመራል

የሚሰጡ ኮርሶች

💪በ አቀብተ እምነት |Apologetics ዘርፍ
1.ነገረ ስላሴ |Trinity
2.ነገረ ክርስቶስ |Christology
3.ስነ መፅሀፍ ቅዱስ | Bibliology
4.ነገረ ድህነት |Soteriology

💪በ ማጥቃት |polemics ዘርፍ
1.ስነ እስልምና |About Islam
      ኢስላም ምንድነው?
      ሰነ መሐመድ
      ኢስላማዊ መፅሀፍት (ቁራን, ሀዲስ ,ተፍሲር..
     ድነት በእስልምና
     የኢስላም ጀነተ
     ሴቶች በእስልምና እና ሌሎች...
2.መሠረታዊ የወንጌል ስርጭት ስልጠና |     Evangelism Training

ተጨማሪ አስፈላጊና ጠቃሚ ኮርሶች
1.ስነ አመክንዮ እና ሙግት |Logic and Argument
2.ሳይኮሎጂ |Psychology


🛑ለመመዝገብ
1.ማንነታችሁን ሊገልፅ የሚችል መታወቂያ |የቀበሌ, መንጃ ፈቃድ, ፓስፓርት በ ፎቶ መላክ ይኖርባችኋል
2.ሙሉ ስምና ስልክ የምታገለግሉበት ቤተክርስቲያን ስም መሙላት ይጠበቅባችኋል
3.የኢንተርኔት (Internet)አገልግሎት ማግኘት የሚችል በ ዋነኝነት Telegram


ለመመዝገብ👇
Googe form
https://forms.gle/StfUrKx8LrrEWzXG6


◀️Telegram User name
@tojosh
@bamzoe

📱Phone
0915618227
0941167314



❤️‍🔥ለሁሉም ክርስቲያኖች ይህንን እድል እንዲጠቀሙ አጋሩአቸው
#Share
#Forward
👇ይቀላቀሉን |Join our channel
@apolomics

WCU_Evange_Moblizers

08 Jun, 07:37


WCU_Evange_Moblizers pinned «ሰላም mobilzers እንዴት ናችሁ የ evange mobilizers member የሆናችሁ ሁላችሁ ከታች በምልክላችሁ link በመግባት formu በሚያዛችሁ መሰረት register እንድታደርጉ ይሁን🙏 NOTICE:- ይህ ምዝገባ የዘንድሮ #GCዎችም የሚመለከት እንዲሁም በጊቢ ውስጥ ያላችሁ ልጆችንም የሚያካትት ነው። ያልገባችሁ ነገር ካለ contact👇👇👇 @Birukforjesus7 @christaloneeee»

WCU_Evange_Moblizers

08 Jun, 07:36


Link👇👇👇

https://forms.gle/4VzmPpoNcFXM2v1J7