ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] @bethel_orthodox Channel on Telegram

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

@bethel_orthodox


TELEGRAM - t.me/Bethel_Orthodox
INSTAGRAM - https://instagram.com/BethelOrthodox?igshid=MzMyNGUyNmU2YQ==

"ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የምታደርገን የልዑል እግዚአብሔር ደጅ ናት፡፡"

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] (Amharic)

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] ትክክለኛ መረጃዎችን ጥቅምት ከተለያዩ እና ከፍተኛ ታሪኮች አዳምጧል፡፡nnቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] አካባቢ በTelegram የሚከተሉ ልዩ ሰዎችን የሚያሳይ ተመልከት የሚለዋወጥ ማወቅ ያለው ቡድን ነው፡፡ ይህም በምሳሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካሉ ሰዎች ጋር በሥራ ሳይኖሩ ያለ ቡድን ነው፡፡nnቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] እንደተንኮል በTelegram ዘመን እንደሚሮጥ እና ከራስን ወደ ፍጥረቱን የሚምር በሽታችን ነው፡፡nnበጣም በቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ] እንኳን እንጠይቃለን ፡፡

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

28 Dec, 06:54


በቅርቡ ተከፍቶ የስንቱን ቀልብ 😱የሳበው የምንጊዜም ምርጡ  የኦርቶዶክስ ቻናል ❤️

እኔ ተቀላቅዬ ወድጄዋለው እናንተም ተቀላቀሉ ትወዱታላቹ❤️

https://t.me/+05s9XgAljNBiNDRk

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

28 Dec, 03:30


በቴሌግራም የቱን ማግኘት ይፈልጋሉ

🎧ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች🎧

📖የቅዱሳን ታሪክ📖

🎤ኦርቶዶክሳዊ ስብከት🎤

📖የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ 📖

መናፍቃን ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው🎯

👳‍♂የአባቶች ምክር እና ተግፃፅ 👳‍♂

ሁሉንም ለማግኘት

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 20:06


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 19:49


📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 19:31


ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ ሠለስቱ ደቂቅን ከነደደው እሳት ሊያድናቸው ከአምላኩ ተልኮ ወደ እቶኑ ሲገባ "ለሠለስቱ ደቂቅ ዘአውረድከ ጠለ" ይለዋል እሳቱ ውኃ ሆነላቸው እርሱም በዚያ አብሯቸው ታይቷል ነገር ግን "ገብርኤል ነደ ወነበልባለ" እንዲለው እሳታዊ ልብሱ በውሃ ቢታጠብ አልቋልና [እሳት ውሃ ቢነካው እንዲጠፋ] ..... ይህስ የልብሱ ማለቅ "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ...." ይባላልና ..... ምን ለብሼ እታያለሁ ብሎ አይጨንቀውም ከጥምቀቱ አስቀድሞ ታህሳስ ፳፪ ጽንሰት[ብሥራት] ይታሰባልና "ተፈስሒ" ብሎ ያበሰራት እመቤቱ ድንግል በእሳት ቢፈተን የሚነጥረውን ወርቅ ፈትላ ታለብሰዋለች

"አስተርአያ ገብርኤል ግብተ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ" ይላል ..... ጌታውም ቢሆን "እለ ይትለአክዎ መባርቅት ወየአውድዎ ነጎድጓድ" የተባለለት መብረቅን ያለብሰዋል....መልአኩን "ልብሱ ዘመብረቅ" ይለዋልና ለተልእኮ እንደመብረቅ የሚፋጠን ስለሆነ አንድም ዜና ብስራቱ እንደመብረቅ ስለሚሰማ ..... ለዚያ ነው በዚህ ክብር ተገልጾ በትንሳኤው ያየነው፡፡

"እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።" [ማቴ. ፳፰፥፪ ]

መልካም በዓል ይሁንላችሁ

ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 13:58


t.me/seed_coin_bot/app?startapp=1405012211

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 13:58


ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 13:01


ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 11:02


የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት ተጀምሯል።

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት ይቀላቀሉን!
👇👇
📎 https://t.me/+TmIvFjW58AliNmE0
📎 https://t.me/+TmIvFjW58AliNmE0

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

27 Dec, 10:05


✞ጥያቄ✞✞

➥ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው ጉባኤ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቱ ነው?

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

25 Dec, 13:36


ELOHE PICTURE

“ ኪዳንኪ ግን ለኃጥአን ቤዛነ ፤ ኪዳንኪ ኮነ ኪዳንኪ ኮነ ፤ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ ። ”

♡ ㅤ  ⎙ㅤ    ⌲        ✉️    Lᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
     ➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ

🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗
https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

07 Dec, 19:34


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

07 Dec, 18:16


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

07 Dec, 17:30


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

04 Dec, 17:30


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

04 Dec, 17:02


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

04 Dec, 12:48


አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

🕊

[   † ኅዳር ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ [ወላጆቹ]
፫. ቅዱስ ሮማኖስ

[   † ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ]
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
፮. ታላቁ አባ ቢጻርዮን

" የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . ." [ዕብ.፲፩፥፴፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

04 Dec, 12:48


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[  ✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ [ ፒሉፓዴር ]" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]


🕊  † ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል †  🕊

ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ [ሁለተኛው] ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ [አስሌጥ] ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: ፪ ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና :- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ ፪ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር [ፒሉፓተር] ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና ፪ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን ፪ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ፭ ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ [አብሮት ያደገ ነው] ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

በ፫ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: [ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ]" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት :-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ፪ መቶ ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ፪ መቶ ፳ ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ፪፻፳፭ ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::

"የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው"

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

01 Dec, 06:43


በቴሌግራም የቱን ማግኘት ይፈልጋሉ

🎧ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች🎧

📖የቅዱሳን ታሪክ📖

🎤ኦርቶዶክሳዊ ስብከት🎤

📖የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ 📖

መናፍቃን ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው🎯

👳‍♂የአባቶች ምክር እና ተግፃፅ 👳‍♂

ሁሉንም ለማግኘት

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

30 Nov, 19:10


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

30 Nov, 18:12


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

26 Nov, 04:04


#ጥያቄ ✞✞✞
==========

5⃣.በብሉይ ኪዳን ሕግ ሰው ካለው ላይ ከአስር አንድ ይስጥ ይላል። ይህ ከአስር አንድ የምንሰጠው ምን ይባላል?

-----------------------------------------------

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

25 Nov, 20:04


🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █          
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

21 Nov, 17:18


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

21 Nov, 17:06


👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

20 Nov, 09:31


#ሕዳር_ሚካኤል !

#እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን !

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12)


ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡

በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

20 Nov, 08:00


"መጻጉዕ" የአብይ ጾም ስንተኛ ሳምንት ነው?

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

19 Nov, 18:30


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

18 Nov, 15:35


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

18 Nov, 14:59


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

13 Nov, 19:58


᭙ꪖꪜꫀ በ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ላይ መግባት የምትፈልጉ @kingo08bot ላይ መመዝገብ ትችላላቹ

over 3k

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

13 Nov, 19:30


አዲስ የአእላፋት መርሙር ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@janyared

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

13 Nov, 19:05


የመጥምቁ ዩሐንስ አባት ስም ማን ይባላል?

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

09 Nov, 03:45


👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

https://t.me/addlist/Hnzdad45XskzMTM8

https://t.me/addlist/Hnzdad45XskzMTM8

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

06 Nov, 13:33


https://vm.tiktok.com/ZMhVrCxdB/

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

02 Nov, 19:30


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

02 Nov, 18:37


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

26 Oct, 16:01


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት ቅዱስ መላዕክ ማን ይባላል?

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

26 Oct, 15:01


💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን  እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

22 Oct, 19:11


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

22 Oct, 19:00


የመጥምቁ ዩሐንስ አባት ስም ማን ይባላል?

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

19 Oct, 12:13


https://vm.tiktok.com/ZMh5AHypy/

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

16 Oct, 14:37


https://vm.tiktok.com/ZMhfp4Tqs/

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

06 Oct, 17:19


ወርኃ ጽጌ
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን ዘመነ ጽጌን ታከብራለች ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ

በዚህ በወርኃ ጽጌ በዘመነ ጽጌ የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ.7፡47) እንዲል

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸው የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

10 Sep, 19:55


"የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡

በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡

ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡

ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

08 Sep, 08:53


እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

"እውነት እውነት እላችኋለሁ:: ሰማይ ሲከፈት: የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ::" †††
(ዮሐ. ፩፥፶፪)

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

08 Sep, 08:53


ርኅወተ ሰማይ


ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን::" ትባላለች::

አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም:: የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ::

እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት: ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል:: በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል::

ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ:: በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል::
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን::

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

22 Aug, 06:26


#ዕርገተ_ማርያም (#ነሐሴ_16)

ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።

የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ።

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ።

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው ። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።

ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።

በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ።

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

21 Aug, 08:32


https://youtu.be/mMULw02FyCE?si=ZD9RYq3NzVoczYv1

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

19 Aug, 06:48


https://youtu.be/Dno-zrsgRcY?si=LkTlXKcYvAoL-MM7

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

18 Aug, 15:52


​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ቤቴል [ ቤተ - እግዚአብሔር ]

18 Aug, 15:51


መዝ 88፥12-14
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

27,830

subscribers

68

photos

21

videos