#ክፍል_3
አላህ እንዲህ ብሏል፦
“እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር።” (ሙሐመድ፡ 21)
#ሐዲሥ 4 / 56
አቡ ሱፍያን ሶኸር ኢብኑ ሐርብ (ረ.ዐ) ስለ ሂረቅል በተረኩት ረዥም ትረካቸው እንዳወሱት፦ ሂረቅል፦ “የሚያዛችሁ ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው -ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) መሆኑ ነው። “እንዲህ አልኩት” ይላል አቡ ሱፍያን፦ “አላህን ብቻ አምልኩ። በርሱ ላይ ማንንም አታጋሩ። አባቶቻችሁ የሚሉትን ነገር ተዉ፤” ይላል። “ሶላት እንድንሰግድ፤ እውነት እንዲንናገር፤ ሐራም ከሆኑና ክብርን ከሚያጎድፉ ጸያፍ ተግባራት እንድንቆጠብና ዝምድናን እንድንቀጥል ያዘናል።”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እውነተኝነት ባሕሪያቸው እንደሆነና በዚህ ባሕሪያቸው ከሰዎች ዘንድ እንደሚታወቁ፤ ጠላትም እንደመሰከረላቸው ይህ ዘገባ ያመለክታል።
2/ የዚህ “ዲን” መሠረት አላህን በብቸኝነት ማምለክና በርሱ ላይ የትኛውንም አካል “አለማሻረክ” (አላማጋራት) ነው። ይህ ነው የመልካም ሥነ-ምግባር ሁሉ በላጭ።
3/ ሌሎችን በጭፍኑ የመከተል አደገኛነት -በተለይም በዲን ጉዳይ ላይ።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1