አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-
“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምራሉ፡፡
ትንሽ ተራምደው ያልጠበቁት ሁኔታ ሲገጥማቸው ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚለው የጥርጣሬ ዘር ወዳለበት እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡
ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው ደከም ወዳለ እሳቤ ይንሸራተታሉ፡፡
በመጨረሻ “አልችል” በማለት ጭራሹኑ ያቆሙታል፡፡
አንባቢዎቼ!!! ይህ ለብዙዎች ውድቀት ምክንያት የሆነ የእሳቤ ሂደት ለእናንተ አልተፈቀደላችሁም፡፡
እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!
በርቱና . . .
1. አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ደካማ ጎናችሁ ላይ ሳይሆን ዝንባሌያችሁና ብርቱ ጎናችሁ ላይ አተኩሩ፡፡
2. የምትጀምሩት ነገር ውጤታማ የሚያደርጋችሁ እስከሆነ ድረስ እንቅፋት እንደሚያጋጥማችሁ አትዘንጉ፡፡
3. ካለማቋረጥ ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡
4. ስትወድቁም ሆነ ስትሳሳቱ ከልምምዱ የምታገኙትን ትምህርታችሁን ያዙና ወደፊት ቀጥሉ፡፡
5. በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፡፡
ዶር አዮብ ማሞ
ነብዩ ስነ አእምሮ E-CLINIC
ከውደዱት ያጋሩ ይቀላቀሉን 👇👇
@Psychiatry1 @Psychiatry1
@Psychiatry1 @Psychiatry1