ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

@referal_gibi


🖋️✍️ ይህ ቻናል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ጉባኤ የተከፈተና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶች፣ ወቅታዊ መረጃዎች፣ ኪነጥበባዊ ፅሁፎች፣ ዝማሬዎች የሚለቀቁበት ነው።

ጽሑፎቹን ለጓደኞችዎ share በማድረግ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ! ያሎትን ጥያቄ ሀሳብ አስተያየት በ @referal_gibi_gubae ያድርሱን። 🙏

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

21 Oct, 09:38


"ወትትሐሠይ ነፍስየ በእግዚአብሔር እስመ አልበሰኒ ልብሰ ሕይወት ወከደነኒ ክዳነ ሐሤት ከመ ትርሲተ መርዓዊ ወከመ ሰርጐ መርዓት"

ትንቢተ ኢሳይያስ ፷፩÷፲

ከእርሷ ተጠግተን በክርስቶስ ፍቅር የኖርንባት ፤ በቃሉ ትምህርት ሐሴት ያደረግንባት ፤ በዝማሬ ነፍሳችን የረካችባት እመ ኲሉ አርድእት ግቢ ጉባኤ ክርስቶስ ኢየሱስ የማዳንን ልብስ እንዳለበሰን ትእምርት ይሆን ዘንድ የልደት በዓል ቲሸርቴን ልበሱ ተጎናፀፉ ትለናለች ።

“ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን...  ።” መክ 9፥8 ነጩን ልብስ ለብሰን አክሊል እንደ ለበሰ ሙሽራ እንዳጌጠችም ሙሽሪት ደምቀን የእናታችንን ልደት እናከብር ዘንድ ቲሸርቱን እንግዛ ።

💰 ዋጋ     : # 300 ብር
📍 አድራሻ ፡ ሐመር ሱቅ
💎 ከአስተማማኝ የብድር አማራጭ ጋር !

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

20 Oct, 07:00


" መሳለቂያ እንዳንሆን ኢየሩሳሌምን እንቅጠር "
ንህምያ 2:17

እስራኤላውያን በታሪካቼው ከባቢሎን ምርኮ ቀጥሎ ትልቁ በፋርስ የተማረኩበት ጊዜ ነበር ። የ እስራኤል ዘሥጋ ቁልፉ የሚባሉ ሰዎችን ማርከው ፤ ቤተ መቅደሱን ፤ አጥር ቅጥራቼውን አፈረሱ ።

ከምርኮኞቹ አንዱ የነበረው ንህምያ ከብዙ ጊዜ ምርኮ በኋላ በንጉሡ ፈቃድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ " መሳለቂያ እንዳንሆን ኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ " አለ ። የፈረሰውን ቅጥርም በ 52 ቀናት ሠርተው አጠናቀቁ ።

ተወዳጆች እኛም መሳለቂያ እንዳንሆን ኢየሩሳሌምን እንቅጠር ። ኢየሩሳሌም ግቢ ጉባኤን እንቅጠር ። የክርስቶስ ፍቅር የተገለጠባት ፤ የቃሉን ወተት የጠጣንባት ፤ ከእርሷ ተማርከን መሄድ የማንፈልግባት ግቢ ጉባኤ ለእኛ ኢየሩሳሌም ናት ።

እናም እኛ እንደ እስራኤላውያን የእናታችንን ቅጥር የምንሰራው በዲንጋይ በአሸዋ አይደለም የግቢ ጉባኤ ቅጥሮች እኛ ነን እንጅ ። ሁላችንም ከያለንበት ለእናታችን ፲፱ ኛ ዓመት በመሰብሰብ ቅጥር እንሁናት ። ግቢ ጉባኤአችን ከበን በዙሪያዋ እንመላለስ ።

የቀደመውን ጊዜ እናስብ ፤ ከግቢ ጉባኤ ያላገኘነው ምን አለ ? በማይመች ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳ ስለ ፍቅሯ እንሰብሰብ ። መሳለቂያ እንዳንሆን ግቢ ጉባኤን እንቅጠር ። በስራ ላይ የምትገኙ ወንድም እኅቶቻችን ከ ጥቅምት 15-17 በእናታችሁ ቤት እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል ።


በእናታችን ቤት እንሰብሰብ !
እግዚአብሔር በሰላም ያገናኘን !

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

18 Oct, 16:44


ማኅሌተ ጽጌ ፫ ኛ ሳምንት

በቀደመው ሳምንት እንዘ ተሐቅፊዮ ሲባል ለምን ዲያቆናት ምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ይዘው ካህናት ማዕጠንት ያጥናሉ ?


የማኅሌተ ጽጌ ደራሲዎች አባ ጽጌ ድንግል እና አባ ገብረ ማርያም የጽጌዋ ምስጋና የተገለጠላቼው ከ ፱ ዓመታት ጸሎት በኋላ ነበር ። በየዓመቱ መስከረም 26 ሲደርስ በጋራ የአበባዋን ምስጋና በጋራ ያደርሱ ነበር ።

እንዘ ተሐቅፊዮ ሲሉ የእመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር ያለውን ሥዕለ አድኅኖ ይዘው ሲያመሰግኗት እመቤታችን ተገልጣ ትባርካቼው ነበር ። ስለዚህም ነው ምስለ ፍቁር ወልዳን መያዛቼው ። ዛሬም ልጅሽን ይዘሽ ነይ እያልን ስሟን ስንጠራት ትባርከናለችና ።

ማኅሌተ ጽጌ 🌷

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።

ትርጉም 🌷

አበባ እና ብርህት የዓለም ፀሐይ የወለደች
ማርያም እናትሽ ሐና ሶሥተኛዋን እና
አራተኛዋን ዕለት ትመስላለች ፤ ዳግመኛም ሰባተኛዋን ዕለት ትመስላለች በሰማይና በምድር ላሉ እረፍት የሆንሽ የነጻነት ምልክት
ሰንበት አንችን አፍርታለች ።

ምስጢር 🌷

እመቤታችን በሰባቱ ዕለታት ትመሰላለች ፤ የፍጥረት የመጀመሪያ ቀን እሑድ ነው ደራሲው እናትሽ ሐና ሦስተኛዋን ዕለት ማክሰኞን ትመስላለች ማለቱ እንደምን ነው ቢሉ በሦስተኛው ቀን አዝዕርት ፣ አበባዎች ፣ፅጽዋት ተገኝተዋል ከእናታችን ሐናም የፈካች አበባ ፍሬዋ ክርስቶስ የሆነ እመቤታችን ተገኝታለችና ሦስተኛዋን ዕለት ትመስላለች አለ ።

ወራብዕተ አለ የፍጥረት አራተኛ ቀን ረቡዕ ነው በዚህ ቀን ፀሐይ ፣ ጨረቃ ፣ ከዋክብት ተገኝተዋል ፀዓዳ የሆነች አማናዊት ፀሐይ ካንች ተገኝታለችና ሲል መስሏታል ። “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”ራእይ 12፥1

ሰባቸኛዋን ቀንም ትመስላለች አለ ቀዳሚት ሰንበት ናት በዚች ዕለት አምላካችን ከሥራው ሁሉ ያረፈባት ዕለት ናት እመቤታችንም በሰማይና በምድር ላሉ ፍጥረታት ዕረፍት ናትና አንችን ያስገኘች ሐና ሰባተኛዋን ዕለት ትመስላለች ይላል ።

ጥያቄ ?

አዳም በገነት ለምን ያህል ጊዜ ኖረ ?
ከነ ቀኑ ድረስ መናገር አሸናፊ ያደርጋል ።
በሰው ልቦና ያልታሰበ ልዩ ሽልማት ያስገኛል ።


በማኅሌት ከእመቤታችን በረከት እንሳተፍ ! 🌷

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

15 Oct, 09:25


እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕየወት) ዓመታዊ የእረፍት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

#ጥቅምት_5

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዕረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ በዐቢይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሐዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሐዘን እንጂ። የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


https://t.me/referal_gibi

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

13 Oct, 12:08


" የሞትክለት እንዴት ይሙት ?! "
...
        

🔘 ውብ ምስጢር የቋጠሩ ሀረጋት ፣ በጋራ የመደርደራቼው አንዳች ፍቺ ፣ የመዋሀዳቼው ረብ ትርጉም ፤ የቅኔአቼው ሰም እና ወርቅ ሲተረጎም ፤ ያዘሉት ምስጢር ሲደላደል ፤ ዕደ ሕሊና ሰማያትን ይጨብጣል ። እግረ ልቦና በጥበብ ተመልቶ ይረማመዳል ።

🔘 " የሞትክለት እንዴት ይሙት " ደጋግመው ቢሰሙት ንቃተ መንፈስን የሚያድል ፤ ልብን ዘልቆ የሚፈስ የግጥም ውሃ ! ሁላችሁም ጠጥታችሁ ትረኩ ዘንድ የተጠማ ሁሉ ይጠጣ እንላለን !

🎤 "....መቆም ከብዶት ሲንገዳገድ
የዓለም ፍቅር እየገዛው
ቁልቁል ሲወርድ ከጸጋህ ላይ
የዘመኑ ደዌ ስቦት
ከአባቱ ቤት ጠፍቶ ሄዶ
የሞትክለት እንዴት ይሙት
የሞትክለት ለምን ይሙት "

👤 በገጣሚት ፡ ዕሌኒ መኮነን

| ከግጥሙ የተወሰደ |

ይኸን ድንቅ ግጥም በሪፈራል ግቢ ጉባኤ የዩቲዩብ ገጽ ይመልከቱ !


https://www.youtube.com/watch?v=p9vyeXU5pic

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

11 Oct, 19:01


#ስለ_ጽዮን_ዝም_አልልም ኢሳ 62 : 1

✝️ ቤተ አብርሃም ለ ፲፱ ዓመታት ✝️

አብርሃም በዘመኑ ድንኳኑን አቁሞ በአራቱም አቅጣጫ የሚመጡ እንግዶችን እየተቀበለ ከድካማቸው እንዲበረቱ እግራቸውን አጥቦ ፤ ለሰውነታቸው ኃይል ለመንገዳቸው ስንቅ ይሆን ዘንድ መልካሙን ፍሬዳ ጥሎ ያስተናግድ ነበር።
እነሆ የኛዋ ቤተ አብርሃምም ከምሥረታዋ ጀምሮ በዓራቱ አቅጣጫ የሚመጡ ልጆቿን ከድካማችሁ እረፉ እያለች እግሮቻችን አጥባ ተቀብላ ለመንፈሳችን ብርታት የሕይወታችን ስንቅ የሚሆነንን መልካሙን የእውቀትና መንፈሳዊ መዕድ እየመገበች እነሆ ፲፱ ዓመት ሆናት ።
እኛም "ወኢያረምም በእንተ ጽየን" የበላነውን የጠጣነውን ስለአገኘንባት ስለ እናታችን ስለ፦

  📍ድንግል ማርያም
  📍ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
  📍ግቢ ጉባያችን


ዝም አንልም ልደቷ ልደታችን ነው ብለን ለማክበር ጥቅምት 15 - 17 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ይዘናል።
እናታችን የሐዋሳ ዩ/ሪ/ግ/ግ/ጉ እናንተ ልጆቿን የትናችሁ በላ እየተጣራች ዝግጅቷን እያጠናቀች ትገኛለት።
እናት ጠርታ መቅረት አይታሰብምና ከወዲሁ እንድትዘጋጁ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።

https://t.me/referal_gibi

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

11 Oct, 15:27


እንኳን ለእመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር
ለተሰደደችበት ለዘመነ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ ! የእመቤታችን ምስጋና ሁለተኛ ሳምንት ትርጓሜ ! 🌷


| ፩ |ማኅሌተ ጽጌ፦ 🌷

ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ

ትርጉም

ማርያም ሆይ! በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንደ ተሸለመ (ተለበጠ) ታቦት በድንግልና ጌጥ በነፍስ በሥጋሽ የተሸለምሽ ነሽ ሀና እና ኢያቄም ሽቶዎች ካበቡሽ ( አበባ ካረጉሽ) በኋላ በሦስት ዓመትሽ የመቀመጥ ተአምርን በቤተ መቅደስ ዓሳየሽ


አንድምታ

ይህ ክፍል በ ሦስት ዓመቷ የእመቤታችንን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ይናገራል ፤ በዚህ እድሜ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ለቅጽበት መለየት የማይፈልጉበት ሲሆን አንች ግን እመቤታችን ቤተ መቅደስ ከ ኢያቄም አባትሽ ከሐና እናትሽ ተለይተሽ ተቀመጥሽ እያለ ይደነቃል ።


| ፪ |ማኅሌተ ጽጌ | የዘወትር ቀለም | 🌷

እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ትርጉም

ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ
ወደ ቤተመቅደስ እንደገባሽበት ተአምርና ንጹሕ ጊዜ ሁሉ ደስ ካለው ከገብርኤልና  እንደ አንቺ ርኅሩህ ከሆነው ከሚካኤል ጋር ከኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ።


አንድምታ

ነጭ እና ቀይ መልክ ያለው አበባ ማለቱ ወልድ እኁየ ፀዓዳ ወቀይህ እንዲል ፀዓዳ በመለኮቱ ወቀይህ በትስብእቱ ሲል ነው ይኸም ፍጹም ሰው ፍጹም
አምላክ የሆነ ልጅሽን ይዘሽ ነይ ።

ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብስራት ለገብርኤል እንዲል ቅዳሴአችን አብሳሪ ( ደስተኛ ) ከሆነው
ከቅዱስ ገብርኤል ሩኅሩኅ ከሆነው ከሚካኤል ጋር ከሀዘኔ ከጭንቀቴ ታረጋጊኝ ዘንድ ወደ እኔ ነይ ።


| ፫ |ማኅሌተ ጽጌ | የዘወትር ቀለም | 🌷

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ትርጉም

ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት፣
(የጊዮርጊስ) የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፣
ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ፣
አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፣
እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።


አንድምታ

የስሙ መታሰቢያ ማለቱ ማርያም ከሚለው ስም 'ማር ' የሚለውን ወስዶ ማር ጊዮርጊስ ይላልና ትርጓሜውም ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ጊዜ ሞቶ በአራተኛው የሕይወት አክሊል እንደተቀበለ ማርያም የሚለው አራት ፊደል መሆኑ በዚህ ወክሎ የሞቱ መታሰቢያ ማለቱ ለዚህ ነው ።


የጊዮርጊስ የአበባ አክሊል ማርያም ማለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎውን እንደፈጸመ የሕይወት አክሊል ተቀብሏል እመቤታችንም ዕፀ ሕይወት ናትና የጊዮርጊስ አክሊሉ ነሽ ይላታል ።

በደብረ ቁስቋም እመቤታችን ለግብፅ ምእመናን ተገልጣ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ በምስራቅ ተገልጦ ለእመቤታችን እሰግድ ለኪ እያለ ሲሰግድ አንች ደግሞ እነሱን ታሰግጅለታለሽ ሲል ነው ።


ጥያቄ | Comment ላይ ይመልሱ |
| ቀድሞ ለመለሰ ..............|

ለምን እንዘ ተሐቅፊዮ ሲባል ዲያቆናት ምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ይዘው ካህናት ማዕጠንት ያጥናሉ ? ትርጓሜው ምንድን ነው ?


“እናትህ እነኋት አለው ። ” ዮሐ 19፥27 ወደ እናታችን ምስጋና ማኅሌተ ጽጌ !

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

11 Oct, 06:31


ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL) pinned Deleted message

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

11 Oct, 05:08


እሴብሕ ጸጋኪ ኦ እግዝእትየ ማርያም ዕፅ ልምልምት ወፍሬ ጥዕምት፤ እምሐና ወኢያቄም ዘሠረፀት። 
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም 

ትመስሊ ፊደለ፤ ወትወልዲ ወንጌለ፤ ወታገምሪ መስቀለ።
🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ሰማየ፤ ወትልዲ ፀሐየ፤ ወታገምሪ አዶናየ። 
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ መሶበ፤ ወትወልዲ ኮከበ፤ ወታጸግቢ ርኁበ።
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ መቅደሰ፤ ወትወልዲ ንጉሠ፤ ወታገምሪ መንፈስ ቅዱሰ።
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ጽላተ፤ ወትወልዲ ታቦተ፤ ወታገምሪ መለኮተ።
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ደመና፤ ወትወልዲ ኅብስተ መና፤ ወታገምሪ ጥዒና። 
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ገራህተ፤ ወታፈርዪ ሰዊተ፤ ወታጸግቢ ነፍሳተ።
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ስኂነ፤ ወትወልዲ መድኅነ፤ ወትፌውሲ ቁሱላነ።
🌷🌷 ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም

ትመስሊ ምሥራቀ፤ ወትወልዲ መብረቀ፤ ወታለብሲ ዕሩቀ።
🌷🌷ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ሐረገ (ዐፀደ) ወይን አንቲ ማርያም
ለአብ መርዓቱ ለወልድ ወላዲቱ ወለመንፈስ ቅዱስ ጽርሐ ቤቱ

ስብሐት ለኪ፤ እምዘበላዕነ ሥጋ ወልድኪ፤ ወእምዘሰተይነ ደመ መሢሕኪ፤ አግብርትኪ ወአእማትኪ ለዓለመ ዓለም። አሜን።

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

10 Oct, 15:05


ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL) pinned «»