“ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ዐይነ ስውሩም፣ “ጌታ ሆይ፤ ማየት እፈልጋለሁ” አለው።
ሉቃስ 18:41
📖 በአዲስአበባ ጎዳናዎች ላይ በጣም ብዙ የተቸገሩ እና የተቸገሩ የሚመስሉ ሰዎች በልመና እንደ ሚተዳደሩ ይታወቃል። አንድ አንድ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን በቋሚነት ለመርዳት እና ከልመና ህይወት እንዲወጡ ለመርዳት ይሰራሉ። አስገራሚ የሚሆነው አንድ አንድ ግለሰቦች ከንደዚህ አይነት እርዳታ ይልቅ ልመናውን ይበልጥ ይፈልጉታል። ከዚህም የተነሳ ጎዳና ላይ ከመለመን የሚያስቀር ርዳታን አይፈልጉም ሲባል ሰማለሁ።
📖በአይሁድ ምድር በተለይ ጌታችን በነበረበት ዘመን ሰዎች ዝም ብለው ወጥተው አይለምኑም። ለመለመን የሚያበቃ ትክክለኛ ምክንያት እንዳላቸው ታውቆ ይፈቀድላቸዋል። ይህም ምክንያት ስራ ለመስራት የማያስችል እንደሆነ ሲታወቅ ብቻ ከቤተሰቡ ወንዶች ብቻ ወደ ልመና ይወጣሉ። ስለዚህ ልመናው ማህበረሰቡ ያመነበት ነገር ይሆናል። ሰዎቹም ይህን በማድረግ አይሸማቀቁም። ህዝቡም የሕጉን ግዴታ በአግባቡ ይወጣላቸዋል።እንድያውም ከሌላው ማህበረሰብ የተሻለ የሚመገቡ እና የሚኖሩ እንዳሉ ይነገራል። ስማቸው እና የሚለምኑበት ስፍራ ሁሉ የታወቀ ሰዎች ናቸው።
📖ኢየሱስ በሚያልፍበት ጊዜ አጥብቆ የጮሄው የኢያሪኮ ሰው ለምን የጮኸ ይመስላችኋል? በመታወር ካለ ትርፍ ብርሃንን አስበልጧል። የብርሀን ዋጋ ገብቶታል። የማየት ክብር ምን አንደሆነ አውቋል። ማየት ለሱ ታምራት ብቻ ከይደለም። የለመደውን ያለ ድካሞ የሚገኝ ገቢውንም የሚያጣበት ነው። ኢየሱስ ምን ላድርግልህ አለው። ሌላ ነገር መጠየቅ ይችል ነበር። የጠየቀው ጥያቄ መልስ የሚያሳጣው ነገር አለ። ሆኖም ጠየቀው ፤ ተቀበለም።
📖ብዙ ሰዎች ብርሃንን የሚጠሉት የሚያሳጣቸውን የጨለማ ትርፍ መናቅ ተስኗቸው ነው። የስጋ አይን ቢታወር ከሚሆነው በላይ የመንፈስ አይን መታወር ታላቅ ውድቀት አለው። ይህም የዘላለም ክብር የሆነውን እግዚአብሔር እንዳናውቅ የሚያደርግ ፤ በመዘዙም ህይወት እንዳናገኝ እና ወደ ዘላለማዊ ኪሳራ የሚመራን ነው።
📖እውነተኛ ብርሃን ወደ ሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስትመጣ ብርሃን ይሆንልሃል። ከምንም በላይ እግዚአብሔርን ማወቅ ይሆንልሀል። ነገር ግን አለምንና ትርፏን ፥ ኀጢአትንና ደስታውን ሁሉ አስጥሎ ፤ በማየት የሚገኘውን ደስታ እንድትቀበል የሚያደርግ ነው። መዳን የሚሰጥህ የዘላለም ክብር አለ ፤ በተመሳሳይ ጊዜ የሚያስጥልህ ብዙ ኮተት አለ። ማየት ይሻላል!! የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ብሎ እንደጮኸው አንተም ወደርሱ ጩኽ ይሰማሀልና።
ጸሎት: ጌታ ሆይ አንተ እውነተኛ የአለም ብርሃን ነህ። ካንተ ውጪ ሁሉም ጨለማ ነው። አንተን ማወቅ እሻለሁ። አንተን ማወቅ ልያሳጣኝ የሚችለውን የማይጠቅም ትርፍ ሁሉ ለመጣል ፈቃደኛ ነኝ። ቃልህን ሳጠናው እና ስማረው ራስህን ግለጥልኝ። ስለ ስምህም በጽድቅ መንገድ ምራኝ። አሜን!!
አገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ
ሄቨን አርሚ
🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀
ይቀላቀሉን
🔻🔻
@heavenarmyy
@heavenarmyy
@heavenarmyy
🔺🔺
Join