ሕያው ቃል @hiyaw_qal Channel on Telegram

ሕያው ቃል

@hiyaw_qal


''ነዋ ወንጌል መንግሠተ ሰማያት "፦ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል እንሆ። "

ሕያው ቃል (Amharic)

ሕያው ቃል በተለያዩ እና በመንግስት ሠኞችን በራሱ ያወዳናቸው መዝገበ ቃሉን የምንቀናው ነው። እንደምዕራፍ እና ህዝቦች አንድም የሞባይል የቃል ቋንቋ አንዳንድ በሽታየሚኖሮት እና በምወድበው የሚቀጥሉ ተግባሪነትን መጻፍ የሚያስፈልግ መሆኑን ይመስላን። እንደምንከተለው ማንኛውንም ወንጌላቸውን ስታስረገመው ቃለምልልስ መሆን ሲያስነሳ ይመስላል። ሕያው ቃል የመጽናናትና የጽሁፍ ገዳኝ ያሉ ግንኙነቶችን እንዲሁም ህብረተሰብሆችን እንቀላጥ።

ሕያው ቃል

03 Mar, 20:25


ይሄን ሊንክ በመንካት ቀጥታ ወደ ፌስቡክ አካውንታችን በመግባት ፎሎው ያድርጉን ። በአዲስ መልኩ የተከፈተ ነው አዳዲስ ነገር ያገኙበታል ።
👇👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=100090438198637

ሕያው ቃል

03 Mar, 20:08


ከመታወቅ በላይ!

እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ታዉቆ ይኖራል እንጂ በፍጡር አዕምሮ የማይደረስበት ትልቅ አምላክ ነዉ።
እግዚአብሔርን ያወቅነው እርሱ የሆነውን ያህል ሳይሆን እኛ ለማወቅ የቻልነውን መጠን ነው።  እርሱ ከቃላችን ከስብከታችን በላይ ነው።  ቃላት እርሱን ለመግለጥ ያነክሳሉ፣ አሳብም እርሱን ለማጠናቀቅ ይብረከረካል፣ እንዳይጠፋ ይሰጋል።  እግዚዓብሔር ከመታወቅ በላይ ቢሆንም እውነት ነውና እንድናውቀው ይፈልጋል። እርሱ
ጨለማ የሌለበት ብርሃን ነው።  እንኳን እግዚዓብሔር የሰማይ ስፋት፣ የባህር ጥልቀት እንኳን አልተደረሰበትም።

የፈጠረዉ ካልተደረሰበት ፈጣሪው ባይደረስበት ምን ይደንቃል! እግዚአብሔር ህልውናው ምክንያት የለውም፣ ለመኖሩም በማንም አይደገፍም፣ በራሱ ሕይወተ ባህርይ ይኖራል። ምሳሌ አልባ፣ ድካም የሌለበት አምላክ ነው።

አባቶች እንደተናገሩለት ኃይሉ በመብረቅ፣ ፍጥነቱ በነፋስ፣ ልዕልናው በሰማይ፣ ስፋቱ በምድር፣ አስፈሪነቱ በእሳት፣
ጥልቀቱ በባህር አይመሰልም። ከፍጡራን አስረጅነት በላይ የሆነ በራሱ ታውቆ የሚኖር የእውቀት እውቀት ነው።  ጎዶሎው ሰው ፍፁሙን አምላክ በሙሉነት ማወቅ አይችልም። እግዚአብሔር ስለራሱ የገለጸልንን
አለማወቅም ተገቢ አይደለም። እርሱ ግን በራሱ ታውቆ፣ ባሕርይው ባሕርዩን አክብሮት ይኖራል። በመታወቅም
ባለመታወቅም ያስደስታል።

ፅንፍ የለሽ ክብሩ ይወደስ!!!!!!!!!!!!

ሕያው ቃል

26 Feb, 11:56


ኀጢአተኞች ኹሉ ምሕረት ያገኘንበት አዲሱ ኪዳናችን፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ የምሕረት ኪዳኑም ላይሻር በቅዱስ ደሙ ታትሞአል! አሜን።

ሕያው ቃል

20 Feb, 14:44


አቤቱ ጾም አስለምደኝ
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፦ ጾም ምግብን ከሥጋ ከመከልከል እንደሚጀመር አውቃለሁ። የሰባውን መተው እንደሆነም ተምሬአለሁ። ምግቤን በመቀየር መጾም አስቸግሮኝ አያውቅም። ነገር ግን እንዳንተ ወደ ምድረ በዳ መውረድን አልለመድኩም። ስሜቶቼን ከመብላቸው ልከለክላቸው አልቻልኩም። አርባ ቀን እስክትራብ ጾመሃል። ከዓለም ጫጫታ ተሰውረህ ብቻህን ከርመሃል። ሰይጣን መራብህን አይቶ የዘረጋውን የፈተና ወጥመድ ሰብረሃል። ልጅህ ግን ከምግብ ለውጥ ያለፈ የጾም ማዕረግ የለኝም። በተራብኩ ጊዜ ለብዙ ፈተና እጋለጣለሁ። ንዴት፣ ፍርድ፣ ስንፍና፣ ፌዝ የተባለ የሰባማዕድ ዛሬም ከፊቴ አልተነሳም። የምወደውን ለመጨበጥ ያለኝ ጉጉት ሰከን አላለም። ያየሁት ሲያምረኝ ሰውነቴ ሆይ ጾም ላይ ነህ! አልለውም። ከንፈሬ እስኪደርቅ ከውሃ እከለከላለሁ። ስንፍናን ለመናገር ግን መልሼ ከንፈሬን በምላሴ አረጥባለሁ። መልሼ ጾመኛ መሆኔን እናገራለሁ። አየህ ጌታዬ ያልተማርኩት ብዙ ጥበብ አለ። ያልደስረኩበት ብዙ መንፈሳዊ ማዕረግ አለ። ከነርሱ አንዱ መንፈሳዊ ጾም ነው። መጾምን እንድታስተምረኝ አለምናለሁ። ሁል ጊዜ በፊትህ የእውነት መኖርን እንድትሰጠኝ እለምናለሁ። የማያድግና በልማድ ዓለም የተዋጠ ህይወት እንዲኖረኝ አልሻም። እንደትንሽ ዘለላ በወደቀበት አድጎ የሚነሳ ታደርገኝ ዘንድ ከልቤ እጸልያለሁ።
ተባረኩበት።

ሕያው ቃል

17 Feb, 18:55


አሳርፎናል!

ለዘላለም ሕይወት ሰው ለእግዚአብሔር የሚሠራለት ምንም ነገር የለም፡፡ የኃጢአታችን ደመወዝ ሞት እንደ ሆነ ሁሉ፤ የዘላለም ሕይወት ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው (ሮሜ 6፥23)፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚድኑበት የእግዚአብሔር ጸጋ፤ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት የሚያስክድ ጸጋ ከእግዚአብሔር ለእኛ ተገልጦአል፡፡

     ክርስቲያን ስላመነ እንዳመነ ሰው በእምነት ይኖራል (ሮሜ 1፥17) እንጂ ለዘላለም ደኅንነት እግዚአብሔር ከተግባሩና ከእጅ ሥራው (ከሰው) የሚፈልገው ምንም ነገር የለም፡፡ ጌታችን "እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ . . " /ዮሐ. 17፥4/ እንዳለ፤ "ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፡- ተፈፀመ አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ. 19፥30)፡፡

🙏 የፈፀመው ጌታ አሳርፎናል!

ሕያው ቃል

08 Feb, 19:39


"የኢየሱስ ክርስቶስ ደም አገልግሎት"
***

“ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ”(1 ዮሐ .1÷9)

“ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን የሚታይ” (ዕብ .9÷24)

“በቅዱስ ደሙ ኃጢአታችንን የሻረ” ( ትምህርተ ኅቡዐት)

“ መዓዛው የጣፈጠ ንጹህ መስዋዕት”(ቅዱስ ቄርሎስ)

>ፊተኛው የደም አገልግሎት ኃጢአትን ከመቀነስ ይልቅ
እየጨመረ ፣ከማንጻት ይልቅ እያዳፈነ የኃጢአት ፍህም
በየማለዳው አዲስ እየሆነ ምድርን በእድፈትና በርኩሰት ስላካለለ ኢየሱስ ከዕድፈትና ከርኩሰት ፣ከፊት መጨማደድም ንጹህ የሆነች (ኤፌ .5÷27) ቤተ ክርስቲያንን ያዘጋጅና ይሞሽር ዘንድ ወደደ፡፡ስለዚህም በገዛ ደሙ የዋጃትንና ያነጻትን ቤተ ክርስቲያን እርሱ በገዛ ፈቃዱ መሠረተልን፡፡ ( ሐዋ.20÷28) ቤተ ክርስቲያን የደሙን አገልግሎት ፍጹም ታምናለች፡፡ የደመቀችበት ፣ያጌጠችበት ለሙሽራው ኢየሱስ የተሞሸረችበትና ሙሽሪት ሆና የቀረበችበት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው፡፡ የደሙን አገልግሎት የማታምን ቤተ ክርስቲያንና የማያምን አማኝ ፈጽሞ ክርስቶሳዊ ክርስቲያን መሆን አይችልም፡፡የኢየሱስ የደሙ አገልግሎት ዛሬም ያላቋረጠ፤የደሙን መስዋዕት አቅራቢው ሊቀ ካህን ክርስቶስ ኢየሱስም የማይለወጥና የዘላለም ክህነት ያለው ነው፡፡(ዕብ .7÷24)
© አስተውሉ!!! የታረደው በግ ዛሬም በዙፋኑ ህያው ሆኖ አለ፤በእግዚአብሔር አሁን ውስጥ ሆኖም በዙፋኑ የሚታየው
እንደታረደ ሆኖ ነው፡፡በዳግም ምጽአቱ የሚመጣው እንኳ
የታረደበትን ችንካር እያሳየ ነው፡፡
(ራዕ .5÷9 ፤ማቴ.24÷30 ፤ራዕ.1÷7) ፡፡በጉ ሊታረድ ግድ የሆነው ምንም ኃጢአት የሌለበት ሆኖ ለኃጢአተኛው አዳም ሊሞት በሥላሴ ዘንድ ምክሩ ስለፀና ነው፡፡የሞተውንና የወደቀውን ሊያነሳ የማይሞተው ሞቶ ፤እንደታረደም ሆኖ ታየ፡፡

#የታረደው በግ ደም ዋና አገልግሎት፦

#1- ደሙ አዲሱን ኪዳንና ህያውን መንገድ መርቆ የከፈተ ነው፡፡
ፊተኛው ኪዳን እንኳ ያለደም አልተመረቀም፡፡ጌታ ደካማዋንና
ሙት የነበረችዋን የኩነኔ አገልግሎት መንገዷን መርቆ
የከፈተውና ሊቀ ካህኑ ወደቅድስቱ ሊገባ ድፍረት የሆነው
በእግዚብሔር ፊት የሚያቀርበውና በእጁ የያዘው ደም ነው፡፡
ያለደም ወደቅድስት ፈጽሞ መግባት አይቻልም፡፡
በአንድ ሐገር የሚሰሩ ታላላቅ የመንገድ ሥራዎች የምረቃ
ሥርዐታቸው የሚከናወነው በሐገሪቱ ዋና ባዕለሥልጣን (መሪ ) ነው፡፡ዋናው ባዕለሥልጣን የምረቃዋን ሪባን ገመድ ቆርጦ በመንገዱ ከተራመደበት በኋላ ሌሎች እርሱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ ከዚያ ቀንም ጀምሮ መንገዱ ለሁሉም አካላት ክፍት ይሆናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በር ሆኖ በደሙ መርቆ የከፈተልን አዲስና ህያው መንገድ እርሱ የምህረቱ ዓመት አዲስ ኪዳን ነው፡፡“በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት … ”አለን፡፡ (ዕብ .10÷19) ፡፡ምንም እንኳ ኃጢአተኞችና በደለኞች ብንሆን በልጁ በኩል የምንገባው ወደዘላለም ክብሩ ፤የምንወርሰውም የዘላለም ህይወትን ነው፡፡(ቆላ .2÷13 ፤ ዮሐ.3÷15) ሕይወታችን የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት በዚያን ጊዜ እኛም ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር እንገለጣለን፡፡
(ቆላ .3÷4 ፤ 1ተሰ .4÷17)  “ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእኛ አይደለም … ”(ኤፌ .2÷8) ፡፡ያለእርሱ ጸጋና ያለእርሱ መንገድነት ወደአብ መድረስ አይቻልም፡፡ (ዮሐ .14÷6) ፡፡ቅዱሳን ሁሉ የሄዱበት መንገድ እርሱ መርቆ በከፈተው ቅዱስና ህያው መንገድ ነው፡፡ ወደአብ የሚያደርሰው ይህ መንገድ የማያሳስት መንገድ ነው፡፡
በደሙ ተመርቆ ከተከፈተውም መንገድ በቀር ሌላ
ወደህይወትና ወደእረፍት የሚያደርስ መንገድ ፈጽሞ የለም፡፡ደሙ የከፈተልን መንገድ የህይወትና የልምላሜ መንገድ ነው፡፡ክርስትና የሚለው አዲስ መንገድ ላይ መጓዝ የጀመርነው ክርስቶስ መርቆ ከከፈተው በኋላ ነው፡፡አዲሱም ኪዳን ላያረጅ ፍጹም የታተመበት ህትመት ህያውና ለዘላለም ትኩስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው፡፡

#2- ደሙ ቤዛችን ነው፡፡

“ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ
የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”(ኤፌ .1÷7)

“ በኋለኛው ዘመን የምክርህን አበጋዝ መድኀኒት ቤዛ የሚሆን
ልጅህን ሰደድህልን፡፡” ( የሐዋርያት ቅዳሴ )

" ስለፍጥረትህ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በእግዚአብሔር ቸርነት በሥጋ
ሞተ" ( ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ ምዕ.70 ክ.1 ቁጥር
10)

“ከአዳም ጀምሮ እስከዛሬ ከተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ማንም
ማን ሊያድነን አልቻለም፤ ከእግዚአብሔር ቃል በቀር በሰው ቢሆን አለኝታችን ከንቱ እንዳይሆን የባህርይ አምላክ እርሱ ሰው ኾነ እንጂ፡፡ከሰው ወገን የሚሾም ሊቀ ካህናት ሁሉ በመጽሐፍ እንደተነገረ ስለሰው ይሾማል፤ስለዚህም ጌታ ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከሰው ወገን ተወለደ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ፤ አምላክ በመሆኑ ያድነን ዘንድ ሰው በመሆኑም ለእኛ ቤዛ ሆኖ ይሞትልን ዘንድ፡፡( ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ ምዕ.58 ቁ .49-50)

“ ቤዛ” የሚለውን ቃል “ አዳኝ፣መድኃኒት ዋቢ፣ሃላፊ፣መድህን፡፡በካሳ መልክ ወይም እንደምትክ
፣እንደመለወጫ፣እንደመያዣ የሚቀርብ…” ብሎ ይፈታዋል፡፡
(ኣማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡ (2001) ፤አዲስ አበባ፣አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ማተሚያ ቤት፡፡ገጽ .243) በሌላ ትርጉም ደግሞ
“የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ
፣ካሳ ፣ለውጥ … ” ነው ይለናል፡፡(
በሞቱ ለሚያምንበት ሁሉ ቤዛ ሆኖ በእግረ አጋንንት ፤በሞት
ይገዛ የነበረውን አዳምንና ዘሩን በሞቱ ካሳ ክሶ ፤ደሙን አፍስሶ በመከራና በሐዘኑ ሁሉ ምትክ ሆኖ ወደቀደመና ህያው ክብሩ የመለሰው ሥጋ የለበሰው ክርስቶስ ነው፡፡ጌታ ነፍሱን በቤዛነቱ ላመኑበት ለብዙዎች ራሱን የሰጠ ነው፡፡
(ማር .10÷45 ፤1 ጢሞ.2÷5)

#ኢትዮጲያውያን ገበሬዎች በልዩ የሥነ መለኰት የእምነት
እውቀታቸው “ ቤዛነት አምላክነት ያሻዋል” ይላሉ፡፡ክርስቶስን
ቤዛችን ነው የምንለው የእኛ ምትክ ሆኖ ከታላቅ የፍቅሩ
ባዕለጠግነቱ የተነሳ እኛን ተገብቶ፤ዕዳችንን ሁሉ ከፍሎ በመቤዥ በደሙ ነጻ ስላወጣን ነው፡፡ቤዛነት የክርስቶስ ብቻ ነው፤ከፍጡር ወገን ቤዛ መሆን የሚቻለው ማንም የለም፡፡ዋጋ የሚከፍል አካል እርሱ ቀድሞ ከዕዳ ነጻ መሆን መቻል አለበት፤ከክርስቶስም በቀር ከአዳም በደልና ዕድፈት ነጻ ሆኖ ዕዳችንን ከፍሎ መድኃኒትና ቤዛ የሆነን የለም፡፡እርሱ በንጹህ ደሙ ለበደለኛው የሰው ዘር ሁሉ ዋጋ የሆነና በዋጋውም ገዝቶን የዋጀን ነው፡፡“ ቤዛነት አምላክነት ያሻዋል” የሚባለው ከአምላክ በቀር ፍጹምና ንጹህ ቤዛ ፈጽሞ ስለሌለ ነው፡፡ምክንያቱም ሰው የማይበድል አይደለምና፤በተጨማሪም “ ጻድቅ አንድስ እንኳ የለም” (2 ዜና .6÷36 ፤ ሮሜ .3÷11) በማለት ቃሉ ስለደመደመ ንጹህና ፍጹም ቤዛ መሆን የሚቻለው ከብርሐን የተገኘው ብርሐን፣ከእውነተኛው አምላክ የተገኘው እውነተኛው አምላክ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ፍጹም ሥጋን የነሳውና ዘመዳችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡እርሱ አምላክ የሆነ ሰው፤ሰው የሆነ አምላክ ነውና፡፡ ክርስቶስ የመጣበት ዋና ዓላማው “ ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ” እንደሆነ ተገልጧል፡፡ (ማቴ .20÷28 ፤ማር.10÷45) አዎ! ከአምላክ በቀር ሰው ስለራሱ ነፍስ ቤዛ መሆን

ሕያው ቃል

08 Feb, 19:39


መስጠት አይችልም፡፡( ማቴ .16÷26) ፡፡ ቤዛነት ምትክ ሆኖ ከእስራት ነጻ ለማውጣት የሚከፈል ዋጋ ከሆነ፤ኢየሱስ ብዙዎች ስለሆንነው ስለሁላችን ነፍሱን ቤዛ አድርጎ ከኃጢአትና ከዘላለም ሞት ነጻ ሊያወጣን ህይወቱን አሳልፎ ሰጠ፡፡አምላክ ለፍጡር እንጂ ፍጡር ለፍጡር ቤዛ መሆን ከቶ አይቻለውም፡፡ኃጢአት ላረከሰው የሰውልጅ ኃጢአትና ዕድፍ ፈጽሞ የሌለበት የእግዚአብሔር በግ
ኢየሱስ ያስፈለገው ለዚህ ነው፡፡
ስለዚህ የኃጢአት ክስ ያለበት የትኛውም አዳማዊ ፍጡር መዳን የሚችለው በአንዱ ቤዛ በተሰቀለው መድኃኒት ማመን ሲቻለው ብቻ ነው፡፡እስከዛሬ ለበደለ ባርያ የሞተ ጌታ ወይም
አንድ የስስት ልጁን የሰጠ ጌታ አልሰማንም፡፡ጌታ አብ ግን ልጁን እስኪሰጠን በእንዲሁ ፍቅር ወደደን ( ዮሐ .3÷16) ፤ ወልድም ገና ደካሞች ሳለን ቤዛ ሆኖ በሞቱ ሊታረቀንና ሊያስታርቀን ወደእኛ መጣ፡፡( ሮሜ፣5÷6) እኛ ወደእርሱ የሚያቀርብ ምንም ነገር ስለሌለንና የህይወት በራችንን በራሳችን ላይ ስለዘጋን እርሱ ወደ እኛ የተዘጋውን በር ከፍቶ መጥቶ ተቤዠን፡፡ፍቅሩ ከህሊና መረዳት ከማስተዋል ይረቃል!!! ተመርቆ የተከፈተውን ህያውና አዲስ መንገድ የሚያስተዋውቀውና የሞቱን ነገር በልባችን የሚስለውም መንፈስ ቅዱስ ድንቅና ፍቅር ነው፡፡ አዎ ! ኢየሱስ መስዋዕት ሆኖ ባፈሰሰልን ደሙ ቤዛችን ሆነልን፡፡ከእርሱ በቀርም ማንም፤ምንም ቤዛ የለንም፡፡.በቤዛችን እንዲህ ተወደናልና ደስ ይበለን፡፡

ለሌሎች አጋሩ

Facebook :https://m.facebook.com/103351765227313

ሕያው ቃል

07 Feb, 07:34


https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid02e42JRmxa1JpDWaM5bXjZQ9jqsCjBz9udvowDbedHNivwA1184jrr3ka9Y6X9gnwjl/?app=fbl

ሕያው ቃል

06 Feb, 16:12


የሚበልጠው ኪዳን

“አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።”
  — ዕብራውያን 8፥6

በዚህ ከፍል ላይ ጸሐፊው ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ማለትም በበለጠና በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሰረተ ኪዳን መካከለኛ መሆኑን ይናገራል  ።  ከአይሁዳውያን ካህናት አገልግሎት ይልቅ የኢየሱስ ክህነት አገልግሎት እንደሚበልጥ ሁሉ አዲስ ኪዳን ከአሮጌው ኪዳን ይልጣል ።

ለመሆኑ አሮጌው ኪዳን ምንድነው ?

ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካካል የሚደረግ ውል ወይም ስምምነት ማለት ነው ። በአሮጌው ኪዳን መሰረት እግዚአብሔር  የአብርሃም ዘሮች (አይሁዳውያን ) የእርሱ የተለየ ሕዝብ እንደሚያደርጋቸውና እንደሚባርካቸው ተስፉ ሰቶአቸው ነበር ። (ዘፍ 12÷1-3)  ይህም በእግዚአብሔር በኩል ያለ ውል ነው ።  በአይሁዳውያን በኩል ያለ ውል ደግም ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ መታዘዝ ነበር ። ዘጸ19÷51 ። አይሁዳውያን ካልታዘዝ በእግዚአብሔር የነበረው  ኪዳኑ ይፈርስ ነበር ።  አይሁዳውያን ለእግዚአብሔር አልታዘዙም እና አሮጌው ኪዳን ተገቢውን ውጤት አላስገኘም ። (ኤር 7÷24-26) ። አይሁዳውያን ለገቡት ውል ታማኝ አልሆኑም ። ስለዚህም እግዚአብሔር እኔም ችላ አልኩአቸው አለው ።  ለአሮጌው ኪዳን ለመታዘዝ ብርታቱም ሆነ ፍቃደኝነቱ አልነበራቸውምና ከኃጢአት ባርነት ነፃ አልሆኑም  ። ምንም እንኳን ካህኑ ለሕዝቡ ኃጢአት በየአመቱ መሥዋዕት ቢያቀርብም የሕዝቡ ልብ ግን አልነፃም አልተቀደሰም ። ሰለዚም ቅድስናና ጽድቅ የጎደላቸው በመሆናቸው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አልቻሉም ።

አሁን ግን በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የተደረገ አዲስ ኪዳን የኢየሱስ ክርስቶስ ኪዳን ነው ።  የዕብራውያን ጸሐፊው ኢየሱስ ክርስቶስንና የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ይለዋል ። እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን የሰጠው ተስፋ የምንቀበለው በኢየሱስ አማካኝነት ነው ። እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ብታምኑ ድህነትንና የዘለዓለም ሕይወትን ትበቀላላችሁ ብሎ ቃል ገብቷል  ። ይህ የሚሰጠው የእርሱ ድርሻ ነው የእኛ ድርሻ ግን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ብቻ ነው ። በዚህ ክፍል ላይ ጸሐፊው አዲሱ ኪዳን ከአሮጌው ኪዳን የበለጠ በተሻለ ተስፋ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ይናገራል ። ከነብዩ ኤርምያስ መጸሐፍ በመጥቀስ ከተሰጡት የተሻሉ ተስፋዎች ሶስት ያቀርባል ።

የመጀመሪያ እኔ ሕጌን ብልባችሁ አኖራለው ፣ በአእምሮአችሁ እጽፋለው ። 

ሁለተኛው ተስፋ  ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቀኛል  ይላል ።

ሦሶተኛው በደላችሁን ይቅር እላችዋለው ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲ አላስታውስባቸውም ይላል ።

የእነዚህ ሶስት ተስፋዎች በአጭሩ ስናጠቃልለው በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ እግዚአብሔር አዲስ ፍጥረት ያደርገዋል ማለት ነው ። በእያንዳንዱ ክርስቲያን ልብ ውስጥ እንዲኖር መንፈስ ቅዱስ ይልካል  ። እግዚአብሔር እንዲህ አለ « አዲስ ልብና አዲስ አእምሮ እሰጣቸዋለሁ ፣ እልኸኛ የሆነውን የድንጋይ ልብ ከእነርሱ አውጥቼ የሚታዘዝ ልብ እሰጣችዋለው ። በዚያው ጊዜ ሕግን ይፈጽማሉ ትዕዛዛቴንም ሁሉ ያከብራሉ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ እኔም አምላካቸው እሆናለው አለው ።

ስለዚህም በእግዚአብሔር እና በሰው መካክል የተደረገው አዲስ ኪዳን ይህ ነው ። በመንግሰተ ሰማያ የዘለአለም ሕይወት ተስፉ እግዚአብሔር ሰቶናል ። ከዚህም ጋር አብሮ ኃጢአት የምናሸንፍበት እርሱን የምናውቅበትና የምንታዘዝበትን አዲስ መንፈስ ይሰጠናል ።ኪዳኑ እንዲፈጸም ከተፈለገ አንድ ነገር ብቻ  አስፈላጊ ነው ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ፣ እግዚአብሔር የሰጠውንም ትዕዛዙንም መጠበቅ ነው ። በእርግጥ አዲሱ ኪዳን ከአሮጌው ኪዳን እጅግ በጣም ይበልጣል ።

@hiyaw_qal
@hiyaw_qal

ሕያው ቃል

06 Feb, 15:28


..ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”  / ዮሐ  20፥26/

በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብቶ ሰላምን ያወጀ ጌታ፥ ዛሬም በታወከችው ምድራችን፣ ባዘነው ልባችን የሰላም እጁ ትዘርጋ! ፈውስ ለምድራችን ይሁን!!!

ሕያው ቃል

05 Feb, 19:31


መዝሙር

ያለም ቤዛ ኢየሱስ ነው የፈወዜ ጌታ ነው።
መዳን በሌላ የለመ እኔ አምናለው ዘላለም ።

▸ በሞግዚቱ(በሕግ) ሥራት ፍጥረት ስላልዳነ
ለሚሻለው ኪዳን ኢየሱስ ዋስ ሆነ ።
ከባርነት ቀንበር ተቤዠኝ በደሙ
ያዳነኝ እሱ ነው ይስማልኝ አለሙ ።

▸አንዴ ለዘላለም ደሙ ፈሶልኛል
አሁን ያለ ኃጢአት ውዴ ይታይልኛል ።
ነፍሴን እንዲያነጻ ታርዷል ፋሲካዬ
በር ሆኖኝ ወደክብር አስገባኝ ቤዛዬ

▸የዘላለም ርስትን የተናዘዘልኝ
መቃብሬን ቀብሮ በሰማይ ያለልኝ
ሞቶ በመስቀሉ ስላምያደረገው
እሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።

▸እንድንበት ዘንድ ተሰቶናል ስሙ
አማራጭ የሌለው መዳኛ ነው ደሙ።
ሞትን በሞት እንጂ መግደል የተቻለው
ከኢየሱስ በቀር ለሌላ ጌታ ማነው ።

▸ የመቅደስ አዛዦች እጅ ቢጫንብኝ
ከክርስቶስ ፍቅር መቼም ላይበልጥብኝ
በልቤ ያመንኩትን ልመስክረው ባፌ
አልችልም ዝምታ በሞቱ ተርፌ ።

ከወደዳችሁት ለሌሎች አጋሩ ።

ሕያው ቃል

05 Feb, 19:08


እባካችሁ ይህን መዝሙር በተከፈተ ልብ አዳምጡት ።

ሕያው ቃል

05 Feb, 09:27


ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር?

ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣ ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡ ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”

እግዚአብሔር ጸሎታችንንና ጾማችንን ይቀበልልን ።"ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት"

ለሌሎች አካፍሉ
Telegram: https://t.me/Hiyaw_qal
Facebook :https://m.facebook.com/103351765227313/

ሕያው ቃል

04 Feb, 20:28


እባካችሁ አዳምጣት

ሕያው ቃል

04 Feb, 09:21


ሁላችሁም ይህን ሊንክ በመንካት ፔጁን ሼር አድርጉ ። ድምጻችሁን አሰሙ

https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid0JoTWvkFSbDWRJVHqYRoLFF4XuuDXo52azGczptF2Hje3RyB6pGBwK9XpWP9vPPK5l/?app=fbl

ሕያው ቃል

04 Feb, 08:47


በኦርቶዶክስ ላይ የሚደረግን ጫና እቃወማለሁ። በውስጥዋ የተፈጠረውን ችግር/ ሁኔታ በሰላሞ እንዲፈታ እጸልያለሁ። !!

ሕያው ቃል

04 Feb, 07:29


+++ "ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት" +++