አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥) @oneamhra Channel on Telegram

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

@oneamhra


አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️

https://t.me/OneAmhra

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥) (Amharic)

አንድ አማራ የሁሉም አማራውን ለመምረጥ የተከታተለው እና በአንድ አማራውም የሚደውሉ አማራዎችን መምረጥ እንዴት መነሻ እንደሚከተሉ እንደሚቀርብ ነው። ይህን በከባድ ሊገኝ ይችላል። ስለዚህ እናመልከቱ። አዎንቸው በማድረግ ለአማርኛ ቋንቋ በሚከናወነው ጽሁፍ በተለያዩ ልዩነትና ተንቀፅኦ አሳምነን ሊነበብ ይችላል። ያቀረበውን ጀርባውን በማድረግ ከእዚህ ወደቀጥታ ቦታ በመሄድ ወዳለበትን ገፅ እናሳይን። በዚህ ቦታ የተለጠፍነው ሰብሳቢዎችን ለመቅረብ ማምረጥ የሚያስከፍል ነው። ያልተገኘና ጠላቱን ለመለወጥ አሳልፈኑልን እናመሰግናለን። የተቀናጀ ክፍሎችን ለማየት ከበላይ ተላክለናል። ለእኛ በልክላለን! አማራን በዚህ ቦታ ለመቅረብ እና ለመግባት ለኢቤል ኦሪንና አወርሳለን።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

14 Jan, 08:06


🔥#መረጃ_ሰከላ‼️
 
#ግሽ_ዓባይ_ነፃ_ወጣለች‼️

ከአዴት በብር አዳማ ወደ ሰከላ እየመጣ ያለ
የጠላት ሀይል አለ።እሱን ለመቀበል ሰከላ ግሽ አባይ የነበረው በኮሎኔል ድባቤ የሚመራው የብልፅና ጦር ወደ አብስከን ሂዶ ዙሪያውን በሞርተር እየደበደበ ነው። የአብስከን ፋኖም ተጋድሎ እያደረገ ነው።

አምቢስ የነበረው ፋኖ ደሞ የሰከላ ወረዳ ግሽ ዓባይ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን አድማ ብተናና ሚኒሻ ግሽ ተራራ ሰፍሯል።

በዚህ ተጋድሎ ወራሪው የብልጽግና መከላከያ ሰራዊት በአፈና አስሯቸዉ የነበሩ ንፁሐን በግዮን ብርጌድ ነበልባሎች ከእስር ነፃ ሆነዋል።እስረኞችን አስለቅቀዋል💪


ግሽ አባይ ሰከላ በአናብስቱ ፋኖ ቁጥጥር ስር ሆናለች። ተጨማሪ መረጃ ከግዬን ብርጌድ ቃል አቃባይ ይዘን የምንመለስ ይሆናል‼️

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

06/05/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

14 Jan, 06:24


🔥#አበስከን_ሰከላ‼️

የሽብር ቡድኑ ዛሬ በጥዋት በሰከላ ወረዳ አበስከን ላይ ተኩስ ከፍቷል። በአካባቢው የሚንቀሳቀስ የወገን ሀይል አራዊት ሰራዊቱን በተገቢው ቋንቋ ያናግረው ዘንድ መረጃው ይዳረስ‼️

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

06/05/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

13 Jan, 15:25


🔥#ጠንካራ_ጦር_እየተገነባ_ነው💪

ፋኖ በአራቱም አቅጣጫ በሰው ሀይል ሆኖ በመሳሪያ እና በአደረጃጄት ራሱን እያዘመነና በሪፎርም እያጠነከረ ይገኛል።

  ለአብነትም የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር ባህርዳር ብርጌድ በአዲስ መልኩ ራሱን አደራጅቶ ተሞሽሮ መጥቷል ሲሉ የብርጌዱ ቃል አቀባይ ፋኖ ሀብታሙ የሱፍ ከንስር አማራ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል‼️

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/05/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

13 Jan, 11:31


ሰበር
ስናን ሮብ ገበያ ከተማ ተጨብጣለች!
የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ክ/ጦር  የስናን ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን እሮብ ገበያን ተቆጣጠረ።


ድል ለአማራ ፋኖ💪

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

13 Jan, 10:12


ሰበር ዜና!

መቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች ድንበር አቅራቢያ የአማራ ፋኖ በወሎ ድል ተጎናፅፏል።

ለምስር ወጥ ብለው ህዝባቸውን በመጨፍጨፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የከረሙ ሚሊሻዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል::

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው ቴዎድሮስ ሻለቃ በትናንትናው ዕለት መቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ውስጥ ፀረ ባንዳ ዘመቻ ከፍቶ ሚሊሻዎችን አይቀጡ ቅጣት የቀጣ ሲሆን በዚህ ፀረ ባንዳ ዘመቻ 3 የሚሆኑት ሚሊሻዎች በአልሞ ተኳሽ ጀግኖች ተመትተው ከመካከላቸው አቶ ገዛኸኝ የተባለው ሚሊሻ ወዲያው ተደምስሶ በዛሬው እለት የቀብር ስነስርአቱ እየተፈፀመ ሲሆን ሌሎች 2 ግብረአበሮቹ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል::

ከእነዚህ በተጨማሪ ቁስለኛ እና ሟች ሊኖር እንደሚችል ቢገመትም ለማረጋገጥ ስላልተቻለ ይሄነው ብሎ ለመናገር ቢከብድም ሚሊሻዎች ያላሰቡትን ኪሳራ ሲያስተናግዱ ከወገን ኃይል በኩል ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል:: ከትናንቱ ውርጅብኝ በሙልጭልጭ የተረፉ የጥምር ጦሩ አባላት በሰላም እጃቸውን ለቴዎድሮስ ብርጌድ ሰጥተው ህይወታችሁን ያትርፉ ሲልም ክፍለ ጦሩ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌለኛው የክፍለ ጦሩ ክንፍ የሆነው የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ አርብ ዕለት በመቅደላ ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ደብረዘይት ከተማን አመሻሽ ላይ መቆጣጠሩን መግለጻችን ይታወሳል፤ የደብረዘይቱን ኦፕሬሽን ውጤት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንደምናቀርብ በገባነው ቃል መሰረት የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ በርከት ያለ የነፍስ ወከፍ ትጥቅ መማረኩንና ቁጥሩ በውል ያልተገለፀ ጠላትን እስከወዲያኛው መሸኘቱን ለማወቅ ችለናል።

በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱንም የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የደብረዘይቱ ኦፕሬሽን በብርጌዱ አዛዥ ፋኖ በለጠ ምትክ (ድሮን) እና በክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ፋኖ ሙሀመድ አሊ (ጭንቅየለሽ) የተመራ ስለመሆኑም ነው የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል የገለፀው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዞኑ ምዕራባዊ ቀጠና ተንታ እና መቅደላ ወረዳዎች አዋሳኝ የሚንቀሳቀሰው ቴዎድሮስ ሻለቃ ወደ ብርጌድ ማደጉ ይፋ ሆኗል::

የሰው ኃይል እና የመሳሪያ አቅሙ ተገምግሞ የሻለቃው ደረጃ መሻሻሉንና ቴዎድሮስ ብርጌድ ተብሎ መሰየሙን ዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አውጇል::

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የሚዲያ ባለሙያዎች የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ቴዎድሮስ ብርጌድ የሚለውን ስያሜ እንድጠቀሙ እናሳስባለን::


ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
ወሎ ቤተ - አምሓራ
ጥር 5/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

12 Jan, 17:30


ይኼ ጥርስ ዛሬ የለም!

አዎ ይኼ የጋሼ ሃጫ በረዶ የመሰለ ጥርስ አሁን የለም 😁🤣 እናልህ እንዲህ ሆነልህ…

ጋሼ የቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ የመሰረተ ልማት አማካሪ ናቸው፤ ስማቸውም አቶ አስናቀ ይርጉ ይባላሉ።

ጥቂት ቀደም ብሎ በዳንግላ ወህኒ ቤት ታጉረው የሚገኙ ታሳሪዎችን ለሚሊሽያነት ሲያሰለጥን ሰንብቶ፣ ኮብራ መኪናው በነበልባሎቻችን ስትማረክ፣ እሱ አምልጦ ባህርዳር ገባ።

ባህርዳር ገብቶም ሌላ የመንግሥት መኪና ያዘ። ይህችን መኪና ይዞ ብዙም ሳይቆይ ግን ከሰሞኑን ባህርዳር ቀበሌ 14 ልደታ አካባቢ ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየሄደ እያለ የአገዛዙ ሚሊሽያዎች አስቁመው ከመኪናው በማወረድ ትጥቁንና የመኪናውን ቁልፍ ከቀሙት በኋላ በለብለብ ስልጣናቸው ያልጨረሱትን ካራቴ አስኔ ላይ ጨረሱት።

አስኔም በሚሊሽያ ተመቶ የሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ የብልጽግና አመራር በሚል ስሙ የክብር መዝገብ ላይ ሰፍሯል፤
               ጥርሱ ግን ተርፏል? 😁

በነገራችን ላይ አንድ ቀን ድንገት ተኝተን ስንነሳ "አረጋ ከበደን ሳንገለው ሞተ (ተገደለ)" የሚል መጣጥፍ የምንጥፍ ይመስለናል። ጭሶቹ 😉

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

12 Jan, 06:29


ህይወት በምንገብርበት ትግል አንባልግም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የተሸከምነው የአማራን ህዝብ ከመጥፋት አደጋ በንፅፅር ቢታይ እየጠፋ ያለውን ህዝብ የመታደግ ግዙፍ አላማ ነው።

"ጊዜው ሲፈቅድ የአማራ ህዝብ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ አጣቅሰን ማስረጃዎችን አቅርበን የትግላችንን መነሻ ምክንያት እንከልሳለን።

አሁን ግን በመጥፋት ላይ ባለና ግልፅ መንግስታዊ የዘር ማፅዳት የታወጀበትን የአማራን ህዝብ እየታደግን የተጋረጠበትንም አደጋ እየመከትን ስርዓቱን እያሸነፍነው እንገኛለን።
በዚህ ታሪካዊ የትውልድ አደራ ና ታሪካዊ እዳ ላይ በፍፁም አንባልግም ስንዝር ታክል ስህተትም ለራሳችን አንፈቅድም።
-በአጥቢያ ማግስት በጭካኔ በሚገደሉ ወገኖቻችን፣አናቶቻችን፣አባቶቻችን፣ወንድም እህቶቻችን፣ጨቅላ ህፃነት ህይወት ላይ የሚጨክን ልቦና ስሌለለን በዚህ ትግል አንባልግም።
- ይህንን የህዝብ እልቂት ለመታደግ በእየ ዕለቱ ዋጋ በከፈሉበት ጓዶቻችን ደም ላይ ቁመን በፍፁም አንባልግም ይልቁን አደራቸውን እናሻግራለን እንጅ።
-በየ ደቂቃው በቃላት የማይገለፅ ዋጋ ለሚከፍሉበት ቤተሰቦቻችን እህቶቻችን ወንድሞቻችን ልጆቻችን ሚስቶቻችን እንባና ሰቀቀንን ገፍትረን በፍፁም በዚህ ትግል አንባልግም።
-ውድ ህይወታቸውን ገብረው ልጆቻቸውን በትነውባቸው ማዕቅ ለብሰው በሚተክዙት የጓዶቻችን ቤተሰቦች ሀዘን ላይ ቁመን በጭራሽ አንባልግም።
- በየ ሰከንዷ የምንተነፍሳት ትንፋሽ ዋጋ ይከፈልባታል፣  እያንዳዷ ንጋት ብዙ  ይለፋባታል፣ አዳራችንና ውሏችን ሁሌም ከጠላት ጋር ተፋጠን ነው በዚህ አውድስ እንዴት ይባለጋል?

-ገንዘብ እያለን ሁሉን ትተን ለመነንበት ትግል፦
-ህይወት እያለን ለሞት በተዘጋጀንበት ትግል፦
-ምቾት እያለን በምንጎሳቆልበት ትግል፦
-ቤተሰብ እያለን ቤተሰብ በበተንበት ትግል፦
-ስራ እያለን ስራችንን ሞት ባደረግንበት ትግል፦
ምን ለማትረፍ? ምንስ ለማግኘት? እንባልጋለን፤ እንደሚወራውም ሳይሆን እንደሚታየው ፎቶ ና video ሳይሆን በማይታይ በማይዳሰስ በአይን ጥቅሻ በፈጠነ ፍጥነት ሁሉም የአማራ ፋኖ ተመሳሳይ መስዋትነት ይከፍላል።
ስለዚህ የአተረፈ መስሎት በዚህ ትግል ከሚባልገው ማንኛውም አካል ጋር ህብረትም አንድነትም አይኖረንም ይልቁንም ሁለንተናችንን ሰጠን ከጠላታችን እኩል እንታገለዋለን ።
ይህ የተቀደሰ ዋጋ የሚከፈልበት ትግል  ለመሪዎቻችንና ለትግሉ በዋናነት ለአማራ ህዝብ እስከ ደም ጠብታ ታምነናል እንታመናለንም።
በዚህ ፍፁም እርግጠኛ ሁኑ በምትሰሙት የባለጌዎች ጩህት አትናወጡ!!

ፋኖ ባየ ደስት የአማራ ፋኖ በጎጃም 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ

04:05/2017

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

11 Jan, 19:08


🔥#አገው_ምድር_ትንቅንቁ_ተጧጥፏል💪

የአማራ ፋኖ በጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ግዮን ሰከላ ብርጌድ በዚህ ሰዓት ጠላትን በጨለማው እየለቀመው ይገኛል።
ከሰከላ የተነሳውን አራጅ ቡድን መንገድ ላይ ይዞ አበሳዉን እያሳየው ነው።አሁን አይናችንን ጨፍነን መግጠም ላይ ነን︎

ለብልበው አገው ምድር ክፍለ ጦር የጠላት እራስ ምታት💪

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

03/05/2017 ዓ.ም


   

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

08 Jan, 17:26


ሰበር ዜና!

64ኛ ክፍለጦር ተደመሰሰ!

በዛሬው ዕለት ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11:30 እስከ 9:00 ድረስ በዘለቀ ትንቅንቅ ደቡብ ጎንደር ቀጠና ክምር ድንጋይ ላይ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱት ራስ ጉና ብርጌድ ፣ ጄነራል ነጋ ተገኝ ክፍለጦር እና አንበሳው ጋይንት ክፍለጦር በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ 303ኛ ኮር 64ኛ ክፍለጦር 500 ሰራዊት ይዞ ቢገባም 50 ሰራዊት ብቻ ይዞ መውጣት እንደቻለና ቀሪው የብልጽግና ሰራዊት ግን ክምር ድንጋይ ላይ ሬሳውን ውሻ እየጎተተው እንደሚገኝ የራስ ጉና ብርጌድ አዛዥ ፋኖ አማኑኤል ሞላ  ገልጿል።

በዚህ ውጊያ ራስ ጉና ብርጌድ እቅዱን በማቀድ ከ500 ሰራዊት 50 ብቻ ይዞ ሲወጣ፤ መቶ አለቃን ጨምሮ ተደምስሷል፤ 7 መከላከያ ሰራዊት፣ 2 ፖሊስ፣ ሚኒሻዎች እጅ ሰጥተዋል፤ እስካሁን በተሰበሰበ መረጃ 4 ብሬንና 97 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ተማርኳል። ገና የለቀማ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲል ፋኖ አማኑኤል ሞላ  ገልጿል።

303ኛ 64ኛ ክፍለጦር በኮ/ል አሰጋ እየተመራ ቢገባም ኮሎኔል አሰጋ የተሸከመው ስናይፕር ጥሎና ሰራዊቱን አሰጨፍጭፎ ፈርጥጧል፤ ይህ ኮሎኔል በዚህ ውጊያ ላይ ኃይል ጨምሩልኝ እያለ ቢውልም ከጋይንት ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም አንበሳው ጋይንት ክፍለጦር መንገድ ላይ ዘግቶ ሲፋለመው ሲውል፣ በሻለቃ ሀብታሙ የሚመራው ሻለቃ ጦርም ከደብረታቦር ለመግባት ጋሳይ ላይ ሲፋለመው ውሏል። አገዛዙ መቀናጀት እንዳይችል አድርገን ፋኖዎች ግን በጋራ ቅንጅት 64ኛ ክፍለጦር ከዚህ በፊት በአንድም በሌላም መንገድ ሲዳከም የነበረ ኃይል ነው፤ ዛሬም ቀሪውን የመፈጻጸም ስራ ሰርተናል ሲል የራስ ጉና ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ አማኑኤል ሞላ  ገልጿል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

07 Jan, 05:45


ድሮኗ አሰሳ ጀምራለች:: ደሴ ጦሳ ተራራ ላይ ያለው ስቴሽን ከተጠገነ ወዲህ ወሎ ውስጥ ቦንብ ከሰማይ መዝነብ ጀምሮ በካስታ እና ሳይንት እንድሁም መቅደላ አካባቢዎች ጥቃት መፈፀሙ የቅርብ ትዝታችን ነው:: ዛሬም በአራቱም የክልላችን ክፍሎች ድሮኗ ፎቶ ልታነሳ መብረር መጀመሯ ታውቋል:: መልክአምድሩን እና ፋኖዎች ያሉበትን ቦታ ፎቶ አንስታ ስትመጣ ፋኖዎች የታጠቁትን መሳሪያ ጭምር ለመለየት ይቻላል አሉ!

መረጃውን ገቢ አድርጋ ስታበቃ ጥቃት ሊፈፀም ሲል የኮር ወይም ዕዝ አመራሮች የሚፈርሙት ፊርማ አለ:: ፊርማው ዌብሳይት ነው:: ይህ ፊርማ "በለው ምናባቱንስ" ማለት ነው::

ስለዚህ ፊርማው እስኪፈረም ፋኖ ወደ ጫካ ገብቶ ራሱን መደበቅ ነው ያለበት:: ይህ ስልት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ምንጃር ውስጥ ውጤት አስገኝቷል:: ይልማ መርዳሳ የራሱን ሰራዊት ሙክክ አድርጎታል:: ፋኖዎች ቦታ ቀይረው የእነሱን የጦር ሰፈር ወዲያው ጠላት ሰፍሮበት ድሮኗ ቦንብ ስትጥል የራሷን ምድራዊ ሀይል ጭዳ አድርጋው አስከሬን ሲጋዝ ውሏል:: ታህሳስ 21 ቀን ነው ይህ የሆነው:: ውሸት ከመሰላችሁ አጣርታችሁ ውቀሱኝ::

ጓዶች: ዛሬ በምንም ተአምር ሜዳ ላይ እንዳትሰባሰቡ:: ወደ ጫካ ተሰወሩ ወይም ተበታትናችሁ በአልን አሳልፉ!!

በላይነህ ሰጣርጌ እሳቱ ብዕረኛ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

06 Jan, 18:04


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።

የህዝባችንን ህልውና ለማረጋገጥ በአራቱም ማዕዘን በዱር በገደል የተግባር መስዕዋትነት እየከፈላችሁልን ላላችሁ ፋኖዎቻችን እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።

በዓሉን ስታከብሩም መዘናጋት ይኖራል በሚል ከጠላት በኩል ሊፈፀም የሚችልን የአየርና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ታሳቢ እንድታደርጉ መልዕክታችን ነው። መልካም በዓል!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

06 Jan, 08:18


10ኛው ሺ

በአላዋቂዎች እጅ የወደቀችው ጦቢያ አግድምና አስቂኝ አካሄድ ቀጥሏል። "መንግሥት" ተብየው የጨቅላው አብይ አህመድ አገዛዝ፣ በአራዊት ሰራዊቱ ይጠበቃል፤ በአማራ ክልል ደግሞ አራዊት ሰራዊቱን በሚሊሽያ ኃይል ለመጠበቅ መከራ እያዮ ነው። ይህ ዘመንማ አስረኛው ሺ ነው።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በጎንደርና በጎጃም በርካታ ቁጥር ያለው የአራዊት ሰራዊቱ ጠባቂ ሚሊሽያ ከአፈር ተቀላቅሏል፤ ለዚህም የእብናትና የዳንግላ ዙሪያ ወረዳዎች ብቻ ምስክሮች ናቸው። የአማራን ሕዝብ መጠበቅ ሲገባው የአንድ ጨቅላ ወፈፌን ስልጣንና ጨፍጫፊ ሰራዊትን ለመጠበቅ ለተሰለፈ ሁለት የግራ እግር ባይሆን ብለን ቢቆጨንም ለማዘን ግን ጊዜው አልፏል።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

06 Jan, 06:24


የገና ስጦታ ድል ታሕሳስ 28 ቀን 2017 ዓ. ም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የ3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር የዳንግላው ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ዛሬ አነጋግ ላይ በፈፀመው አስደናቂ ኦፕሬሽን ምርጥ የገና ስጦታ እንካችሁ ብሏል።

ብልፅግና ከየወረዳው አሰባስቦ ዳንግላ ዙሪያ-ጊሳ ያሰፈረውን ከአንድ መቶ በላይ የምሊሻ እና አድማ ብተና አባላት ከበርካታ ተሽከርካሪወቻቸው ጋር በብርጌዳችን ልጆች ተማርከዋል።

እስካሁን 110 (አንድ መቶ አስር ) ክላሾች ከበርካታ ተተኳሾች እና ካዝና ጋር ገቢ ተደርጓል፤  የቡድን መሳሪያወች ተገኝተዋል።

የዳንግላ ወረዳ አስተዳዳሪ ጌትነት ማረልኝን ጨምሮ በርካታ የጠላት ካድሬወችም ከጠላት ሰራዊት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ በጀግኖች ተጨብጠዋል።

ካድሬ እና ኮሎኔልን በጋራ አጣምሮ የጀመረው አዲሱ የጠላት እቅድ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል። ጦርነቱ ወደ ሌላ ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ ነው። ይቀጥላል..

✍️አሥረስ ማረ ዳምጤ

    ድል ለአማራ ህዝብ
     ድል አማራ ለፋኖ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Jan, 18:49


ታሕሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም! ምሽት!
````````````````````````````````````
እስከ ምሽት በደረሰን ሪፖርት መሰረት ስናን አባ ጅሜ ብርጌድ ከንጉስ ተክለ ኃይማኖት ብርጌድ ጋር በመቀናጀት ባደረገችዉ ተጋድሎ 04 (አራት) ብሬን፤ 105 (አንድ መቶ አምስት) ክላሽ፤ 02 (ሁለት) ሞርተር፤ አንድ የድሽቃ ሸንሸል እና አፈሙዝ፤ 01 (አንድ) ስናይፐር እንዲሁም በርካታ የክላሽ፣ የብሬን እና የዱሽቃ ጥይት ከሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋር ተረክባለች።

በሌላ መረጃ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በተደረገ ውጊያ በሻለቃ ሰንደቁ የሚመራው ታሪካዊው የቀስተ ደመና ብርጌድ ደብረ-ኤልያስ የሰፈረውን ግዙፍ የጠላት ኃይል በሚገባ እያስተናገደዉ ይገናኛል።

ከትላትንት በፊት ታሕሳስ 22/2017 ዓ.ም በተደረገ ውጊያ 310 የጠላት ኃይል የተሸኘ ሲሆን የደብረ ኤልያስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ ግቢው ወደ ጠላት መካነ መቃብርነት ተለውጧል። 60 ያህክሉ ደግሞ ደብረ ኤልያስ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ።

ዛሬም ታሕሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የደብረ-ኤልያሱ ቀስተ ደመና ብርጌድ እና የደምበጫው ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ ሰባት ያህክል የጠላት ወታደራዊ መኮንኖች ተሸኝተዋል።

በነገራችን ላይ በዚህ ቀጠና የዓለም ብርሃን የሚባል እንቅስቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚገለፀው የጠላት በሬ ወለደ ወሬ ሲሆን በ2015 ዓ.ም የነበረው እንዲህ ዓይነት ችግር ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ ህዝብ እና ፋኖ እጅ እና ጓንት ሆኖ ብርጌዱም ከ6ኛ ክፍለ ጦር አመራር ጋር ተመካክሮ ተዓምራዊ ተጋድሎ እያደረገበት ያለ ቀጠና ነው።

አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

✍️አስረስ ማረ ዳምጤ

ታህሳስ24/2017

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Jan, 14:46


-------------
የቀጠለው የዛሬ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የድል ዜና

''ነጥሎ ሚጥል ፈሪና ጀግና
የግዮን ፍሬ የአማራው ደጀን
ቆለኛው ሶማ የበረሃው ጭስ
ጠላት ይሮጣል ገና ሳይተኩስ።

እረ አሳምነው አንዴ ተነሳ
በስሙ ቆሟል ፋኖ እያገሳ።

ደባይ ጠላትግን ደገኛው ጮቄ
እያባረረ እንደጉም ሲያበን
እናርጅ እናውጋ ጉባያ ደጀን
ኤልያስ ጠላቱ እንደ እሳት ፈጀን
ጎዛምን ዋበል ደግሞም ከአነደድ
የስናን ጀግና ጠላቱን ሲያነድ
በላይ በጮቄ አቋርጦ ዘልቆ
አርበተበተው ሱሪ አስወልቆ።

የአማራን ህዝብ ስነ ልቦና ያልተረዳው የአብይ አህመድ ቡድን ጎጃም እየዘለለ እየገባ በብርሐን ፍጥነት በዘመነው ትውልድ እያለቀ ነው።ታሪክ በእጃችን እየፃፍን እንዘልቃለን።የአማራ ታሪክ በእኛ በልጆቹ ይመለሳል ያሉት የዮፍታሔ የበኸር ልጆች ዛሬም እንደትናንቱ ጠላትን ሲያረግፉት ዋሉ።

ስናን አባጅሜ፣ቀስተ ደመና፣ ንጉስ ተክለሐይማኖት፣ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ዛሬ ድል ቀንቷቸው ውሏል ነው የምላችሁ።
ደብረ ማርቆስ የሚገኘው የቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ ካድሬዎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ ገብተዋል።ምክንያቱ ምንድን ነው ከተባለ መከላከያ ጥሎን ከክልሉ ከወጣ ፋኖ በየከተማው ገብቶ ከእነ ዘራችን ያጠፋናል በሚል ነው።
እና የህልውና ትግል ጀምረን ባንዳን ከመቅጣት የምንቦዝን ይመስልሀል እንዴ?
ይሔው ዛሬ የዘሜ ትንፋሽ እያለ የሚዋጋው የስናን አባ ጅሜ እና የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ በጋራ መስታዎት ላይ ባደረጉት ውጊያ የተገኘውን ድል ያዬ ካድሬ አድለም አዲስ አበባ ሲኦልስ ቢገባ ይፈርድበታል እንዴ?

የእስካሁኑ ቆጠራ ተጠናቆ አሁን ባለን መረጃ መሰረት
1, ሁለት(2) ሞርተር ከእነ በርካታ ተተኳሹ
2, ሶስት(3) ብሬን ከእነ ሙሉ ሸንሸሉና በርካታ ተተኳሹ
3, አንድ (1) እስናይፐር ከእነ ተተኳሹ
4, ሰማንያ(80) የነፍስ ወከፍ ጥቁርና ኮፍ ብሎም የኮሪያ ክላሾች
5, ሁለት(2) መገናኛ ራዲዮኖች
6, አንድ(1) የጦር ሜዳ መነፅር
7, ሙሉ የወታደሩ ዶክሜንቶች
8, ሁለት(2) መቶ አለቆች የጦር አዛዦች
9, በርካታ የድሽቃ ተተኳሾች
10, ተቆጥሮ ያላለቀ የእጅ f1 ቦንቦች
11, በርካታ ካዘናዎች

የሩጫውን ነገር ያየሰው ይናገር
የውጊያውን ነገር ንጉሷ ትመስክር
የምርኮውን ነገር ስናኑ ያመስጢር
የዛሬውን ጀብድስ አዋጊው ይናገር
ጠላት ከመስታዎት እዛው ወድቆ ሲቀር።

የምትሏን ስንኝ ከታች ጣል ላርግና የቀስተ ደመናው ፣የኢንጅነር ክበሩ የዚያ የጀግና ዘር ጠላትን በጡሀት ያርበደብድ ጀመር።
ከየሳሰር ማዶ ከአቡዬ ታቦቱ
የመሸገው ጠላት ጠፍቶበት በሀቱ
ያበራየው ገባ ቀስተኛው እሳቱ
ይገርፈው ጀመረ የይርሳው አፎቱ።
እረ ምን ተሻለኝ ምንስ መሔጃ አለኝ
ከእንግዲህስ ወዲያ ማምለጫ ከሌለኝ
አስረክቤው ልግባ አክብሮ ቢተወኝ።
ጠላት በዛሬው እለት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ከእየ አካባቢው ከህብረተሰቡ ይነበቡ የነበሩ ደስታዎችን በስንኝ ቋጠሮ ለመጨመር ያክል ነው።
ጀግናማ ጎጃም ይወለድ።አገርን ለመጠበቅ ጀግኖች ከእየ ቀየው እንደ እሳት የሚጋረፉ ልቦቸው በወኔ የተሞላ ከኃላቸው ስትሔድ ወንድነት የሚሰማህ ከፋኖ ጎን ስትቆም ነው።
የዚህ ዘመን ትውልድ አካል የሆናችሁ ሁሉ ድሉ ቅርብ ነውና እንበርታ።
አማራነት ተዳፍኖ የተቀጣጠለ እሳት ነው።አማራነት በክብሩ ከመጣህበት ረመጨት ነው።
አዲስ አብዮት
አዲስ ድል
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ፋኖ ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)


#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/04/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Jan, 06:16


🔥#ባህርዳር_ብርጌድ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር ባህርዳር ብርጌድ ፏፏቴው ገብርኤል ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት 14ቱን በማሰናበት 5ቱን ክራንች አንጋችና የአልጋ ደምበኛ አድርጎታል💪

©ሀብታሙ የሱፍ የባህርዳር ብርጌድ ቃል አቀባይ

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/04/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Jan, 17:23


ታሕሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
`````````````````````````
ባሕርዳር ዙሪያ ሰባታሚት ሁለት ሻምበል መሪዎች ከጠላት ከድተው የወገንን ኃይል ተቀላቅለዋል።

ደጋ ዳሞት ወረዳ ዳማ ቀጠና በተደረገ ተጋድሎ የ25ኛ ክፍለ ጦር መገናኛ ሬዲዮ ኦፕሬተር አስር አለቃ ገለታ አከለ ከነመገናኛው ተማርኳል። ወደ ቀጠናው የተንቀሳቀሰው ጠላትም ተገርፎ ተመልሷል።

በዚሁ የደጋ ዳሞት ቀጠና የ601ኛ ኮር 25ኛ ክፍለጦር ሎጀስቲክ ኮሎኔል ብርሃኔ ሁለት አጃወች ከድተው የደጋዳሞትን ብርጌድ ተቀላቅለዋል።

ዳንግላ ከሰፈረው የጠላት ኃይል 1 ብሬን፣ 2 ክላሽ፣ 685 የብሬን ጥይት፣ 8 ካዝና እና 253 የክላሽ ጥይት የታጠቁ እና የአብይ አህመድን የእብደት ወረራ የተቃወሙ ወታደሮች የቤትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድን ተቀላቅለው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ከቁይ ከተማ ተነስቶ የጮቄን ተራራማ ቦታዎች ለመያዝ የተንቀሳቀሰውን የአብይ አህመድ ሰራዊት አባኮስትር ብርጌድ እና ደባይጮቄ ብርጌድ በጋራ ባደረጉት ብታትነውታል። ናብራ ስላሴ ቤተክርስቲያን መሽጎ ከነበረው መካከል ከሽኝት የተረፉ 11(አስራ አንድ) የጠላት ኃይል ከበርካታ የድሽቃ እና ብሬን ጥይቶች ጋር እጅ ሰጥተዋል።

እረፍት አልባዋ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ከዳንግላ ግራ ና ቀኝ ዋናው አስፋልት ላይ የተዘረጋውን የጠላት ኃይል ሙሉ በሙሉ አፅድታለች። ... ይቀጥላል‼️

አስረስ ማረ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Jan, 16:07


አራዊቱ እየተወቃ ነው!

አራዊት ሰራዊቱ ለብልፅግና ክብረበዓላትና ድግሶች ድምቀት የሚተኩሱት መሳሪያ እንኳን ሳያስቀሩ እያስረከቡ እየፈረጠጡና አፈር እየቀመሱ ነው። ከአጅሬ ጃኖራ እስከ ጮቄ ተራራና ከዞብል አምባ ድረስ በፋኖዎቻችን የተጠናከረ ዘመቻ የጨቅላው አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ሲወቃ ውሏል።

በቀጣይ ጊዜያትም የመውቃት ስራው አድማሱን አስፍቶ የአራዊቶችን መሳሪያ እኛ፣ ነፍሳቸውን ደግሞ ፈጣሪ የሚቀበላቸው ይሆናል። ነበልባሎቻችን እየወቃችሁ!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Jan, 09:17


ሰበር ዜና!

የአራዊት ሰራዊቱ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድ ተነደለ። በእነ ማን ካላችሁ በቤተ አማራ ነበልባሎቻችን በእነ ምሬ ወዳጆ በዞብል አምባ ክፍለጦር የሚል መልስ ታገኛላችሁ። ከሌ/ኮሎኔሉ በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ አራዊት ሰራዊቶች አፈር መቅመሳቸውን ከአማራ ፋኖ በወሎ ያገኘው መረጃ ያስረዳል።

አንተ ማን ነህህህ? ሌ/ኮሎኔል!
አሁን ምንድን ነህህህ? አስክሬን! 😁

ቻው ሌ/ኮሎኔሎ!

(እስኪ ደንበኛ ግጥም ወዲህ በሉልን)

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Dec, 10:37


በባህርዳር ከተማ ዛሬ ረፋድ አባይ ማዶ አካባቢ የአራዊት ሰራዊቱ አባላት በነበልባሎቻችን ወደ ላይ እንዲጎኑ ተደርገዋል። በምን ካላችሁ - በድንች 💣💣! ይቀጥላል!

ቻው አራዊት!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Dec, 09:22


""በሚስጥር የሚደረጉ የኦሮሙማ ስብሰባዎች" ከተሰብሳቢ አንደበት ጥብቅ ሚስጥር

በፋኖ ዙሪያ ሁሌም ቀን በቀን ስብሰባ የሚያካሂድ እና ፋኖ ያለበትን አቋም የሚገመግም ራሱን የቻለ ግብረ ሐይል አለ።ብዙ ግዜ ስብሰባዎች የሚደረጉት አዳማ ከተማ ነው።በዚህ ግብረ ሐይል ውስጥ ከሁሉም የአማራ ክልል ወረዳዎች የተመለመሉ አማራን ለኦሮሙማ አሳልፈው የሚሸጡ ባንዳዎች አሉበት፤በየ ሁለት ሳምንቱ ፋኖ ያለበትን ደረጃ  ከቦታው ድረስ በመሄድ እና መረጃዎችን በመሰብሰብ ሪፖርት ያቀርባሉ።

ሰኞ በ14/04/17 በነበረው ስብሰባ ሰፋ ያለ ሪፖርት የቀረበው ስለ ጎንደር ፋኖ ነው።ሪፖር አቅራቢው እንደሚለው እኔ ተወልጄ ባደኩበት ማዕከላዊ ጎንደር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ሰሞኑን የጎንደርን ፋኖ አንድ ለማድረግ እየለፉ ነው፤በነገራችን ላይ ብልፅግናን አማራ ክልል ውስጥ እንዲቆይ ያደረገው ፋኖ ነው፤ፋኖ ያኔ 2015 መጨረሻ አካባቢ እንደነበረው ቢቀጥል ኖሮ እስካሁን ብልፅግና ታሪክ ሁኖ ነበር፤ያኔ ፋኖ የሚታገለው ለህልውና ነበር ዛሬ ግን ለስልጣን ነው።ፋኖ ወደ 4ኪሎ እንዳያስብ ከተፈለገ አማራን በጣም ህልውናውን ሳትጋፋ ነፃነትም ሳትሰጠው እየረገጥክ ብትገዛው ቀና ብሎ አይመለከትህም እያለ ይቀጥልና።

ፋኖም የህልውና አደጋው የተቀለበሰ ሲመስለው እርስበርሱ ሲታኮስ ነው የሚውለው ለብልፅግና ስጋት አይሆነም እናንተ አማራን አታውቁትም መሰለኝ።ለምሳሌ ጎንደር ገና ፋኖ ያሸንፋል በማለት በስልጣን እየተጣሉ ነው የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አንድ ልነሆን ነው አሉ እስካሁን ግን ምንም ነገር የለም፤እንደውም ከነዚህ ከሁለቱ ዕዞች የተውጣጣ"የጎንደር ክፍለ ሀገር ጠቅላይ ግዛት ፋኖ ዕዝ የሚል ሌላ ተቋም ፈጥረዋል፤በዚህ ከቀጠሉ ሌላ ተቋም ያዋልዳሉ።ስለዚህ በጎንደር በኩል ለመንግስት ብዙም ስጋት አይደለም ሲል በጎንደር ፋኖ ዙሪያ የሰራውን ሪፖርት አቀረበ።


ሌላኛው ደግሞ በቅርቡ ስለተመሰረተው የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ ዕዝ(ቢዛሞ) ስለዚህ ዕዝ ያቀረው ልጅ ደግሞ ወለጋ ላይ  የሸኔ አባል ሁኖ ወለጋ ላይ ሁለት አመት አማራን የጨፈጨፈ ነው።በሪፖርቱ ላይ እንደተናገረው ወለጋ ላይ በዕዝ ደረጃ የሚሆን አማራ የለም።አሁን ያለው ፋኖ ከጎጃም የተሻገረ 1 ክ/ጦር ነው ከአሁን በፊትም 2013 ላይ እኛን ሲዋጉን የነበሩት ከጎጃም የመጡ ሚሊሻ እና ልዩ ሐይል ናቸው ይላል ሌለኛው የኦሮሙማ መረጃና ደህንነት።

እንግዲህ ጎንደር ቶሎ የቤት ስራህን ጨርሰህ ጎንደርን በእውነተኛ የጎንደር ልጆች አስመራ።ለደንቆሮ ፖለቲከኞች ቤታችሁን ዝጉና የፖለቲካ ስራውንም መሬት ላይ ያላችሁት ስሩ ለማንም ዩቱበር አትስጡ፤መሬት ላይ ብዙ ምሁራን አሏቹህ ከነሱ ጋር በደንብ ምከሩ ፖለቲካው ከአካባቢያቹህ ወግ እና ባህል ከማህበረሰብ ስነ-ልቦና አንፃር ራሳቹህ አጣጥማችሁ ምሩት፥ቶሎ የአንድነታችሁን ጉዳይ ጨርሱ።

ወለጋ ላይ ማንም ምንም ያውራ ማህበረሰቡ ከነፍጡ ውጭ ሌላ መዳኛ እንደሌለው ያለፉት አራት አመታት ምስክር ናቸው አሁን ታግሎ የሚያታግል ተቋም ተመስርቶልሐል።የተቋሙን መርህ በመከተል ጠላትን የመመከት እና መታገል የሚያስፈልግበት ግዜ አሁን ነው።ጠላት ከእስከ ዛሬው በበለጠ የወለጋ አማራን ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሰራነው።ካለፈው የሚመጣው የከፋነውና ዝግጁ እንሁን።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ
ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ

20/04/2017

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Dec, 19:46


ደራ አርብ ገበያ አስደናቂ የምሽት ኦፕሬሽን ተሠራ

ዛሬ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር አርብ ገበያ ከተማ ላይ የመሸገውን ወራሪ ሠራዊትና ተላላኪ ባንዳ ላይ ውጤታማ ቀዶ መጣል አከናውነዋል።

ከምሽቱ 2:30 ላይ በ30 የተመረጡ የክ/ጦሩ ባለ ልዩ ተልዕኮ ነበልባል አርበኞች አማካይነት ለ30 ደቂቃ በቆዬ ኦፕሬሽን እቅዳችንን አሳክተን ወጥተናል።

በዚህ ኦፕሬሽን ስምሪት ሲሰጡ የነበሩ ሁለት ወታደራዊ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የሚሊሻና የወራሪ ሠራዊቱ አባላት ተሸኝተዋል።

እጅግ በጣም አስደናቂው ጉዳይ ደግሞ የአገዛዙ ጦር ኦፕሬሽናችንን ፈጽመን ወጥተንም እንኳን በባዶ ሜዳ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ሞርተርና ዲሽቃ እየወረወረ  ይገኛል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
      አርበኛ ባዬ ቀናዉ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Dec, 19:00


ዳንግላ‼️

በዚህ ስአት ዳንግላ ከተማና ጫራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአገዛዙ ሰራዊት እየተገረፈ ይገኛል።በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት🔥

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

27 Dec, 17:47


የአማራ ፋኖ በጎጃም ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም
==============================
#የ1ኛ ክፍለ ጦር #ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ለ3 ቀን የቆየ አውደ ውጊያ በማድረግ ጠላትን በቆራጥነት በመፋለም ብራቃትን፣አማሪትና፣ጨንታንና ዳጊን ከጠላት ሙሉ በሙሉ ነጻ ማድረግ ችሏል።ዛሬ ደግሞ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ዋና ከተማ #መራዊ ላይ መሽጎ የሚገኘውን የአብይ ገዳይ ቡድን ቻይና ካምፕና አስተዳደር ላይ በመክበብ በርካታውን ሙትና ቁስለኛ አድርጎ 15 የጠላት ኃይል፣17 የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ቁጥሩ ያልታወቀ ተተኳሽ ማርከዋል ።መራዊ ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ቢቻልም ገዳይ ቡድኑ በእግረኛ አልችል ሲል ከባህር ዳር መኮድ ወታደራዊ ካምፕ ጀነራል መድፍ በመተኮስ የከተማውን ነዋሪ በመደንደቡ ቅድሚያ ለወገናችን በማለት ፋኖ ከተማውን ለቆ ወጥቷል።

#የ3ኛ(ጎጃም አገው ምድር) ክፍለ ጦር አካል የሆነው       የዳንግላው #ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ ትናንት ምሽት #ዳንግላ ከተማ ላይ ዛሬ ደግሞ #አሸር መስክ ላይ የብርሃኑ ጁላን ቱልቱላ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲያደርገው ውሏል።
    #ዘንገና ብርጌድ ቲሊሊ ከተማ በመግባት ጠላትን ዶግ አመድ ሲያደርገው ውሏል።
    #ዘንገና ብርጌድ
    #ግዮን ብርጌድና
     #ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ በጥምረት የጠላት መቀበሪያ በሆነችው #አሽፋ መገንጠያ ላይ የአብይን ጅምላ ገዳይ ሲረፈርፉት ውለዋል።ጠላት ያሰበውን ሳያሳካ እንዲመለስ ተደርጓል።
    #የደቡብ አቸፈሩ #አቤ ጉበኛ ብርጌድ በደቡብ አሸፈር ወረዳ ዋና ከተማ ዱር ቤቴ ላይ የመሸገውን ጠላት መድረሻው እስኪጠፋው ድረስ እያባረረ ሲለበልበው ውሏል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ በጎጃም ለ5 ተከታታይ ቀናት ለክፍለ ጦር አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቋል።ከስልጠናው ጎን ለጎን የትግሉን ግምገማና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ረገድ ትልቅ ስራ ተሰርቷል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣
አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ዮሀንስ አለማየሁ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

27 Dec, 11:38


🔥#ጎጃም
ሜጫ፥መራዊ ከተማ በጀግኖች የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ ክ/ጦር የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አናብስቶች  ቁጥጥር ውስጥ ገብታለች!!



#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

18/04/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

27 Dec, 09:32


<<ለአማራ ህዝብ ትግል የሚዲያዎች ሚና>> በሚል ቀናዎችን የሚያሰባስብ አንድ ዓለምአቀፍ የውይይትና ግምገማ መድረክ መዘጋጀት ቢችል መልካም ነው። ወገን ግድ የላችሁም "የእኔ አሸናፊነት" ጉዞ፣ ውሎ አድሮ የወል ኪሳራን ያመጣል፤ ከጊዜያዊ ስሜት ወጥተን ለትግላችን የሚጠቅም፣ የህዝባችንን አንገት ቀና የሚያደርግ ስራን እንስራ።

ትናንት ከመሬት ተነስተው በጠሉት ወንድማቸው ላይ ጭቃ ሲወረውሩ ውለው፣ አመሻሹ ላይ ደግሞ "የእኛ ብቻ" የሚሉት ሲጠለሽ ሲያዮ እየየው ማለት ከጎደሎ የሚዲያ ተዋናዮች የምናየው የተለመደ አካሄድ ሆኗል። የወል ድልን ቢያመጣልንማ መዘርጠጥና የተካበን መናድ መች ከባድ ነበር።

ተወደደም ተጠላም፣ ሳይነጋገሩና ሳይመካከሩ አንድነትና አሸናፊነት አይመጣም፤ ነገ የምርም የሚገደን ከሆነ በቀናዒ የሚዲያ ሰዎች መካከልም ብቻ ሳይሆን በአደረጃጀት ልዮነት ላይ ያሉ ወንድሞቻችን እንዲመክሩ መስራት አለብን። ብንመክርና የሚበጀውን ብናልም መልካም ነው።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

26 Dec, 15:32


ሁለተኛውና ዝቅ ብለን በዝርዝር እንደምናየው ሌላው ትልቅ ችግር ከድርጅት ግንባታና አመራር ጋር ያለው ድክመት ነው፡፡ ትግሉ በፖለቲካ ሃይል ካልተመራ ከሽፍታና የጦር አበጋዝ እንቅስቃሴነት ያለፈ ሊሆን እንደማይችል ቢታወቅም፣ ይህን መሰረታዊ እውነታ በልኩ ያለመገንዘብ ድክመት አለ፡፡ ታጋዩ ብሄርተኝነት ያልሰረፀው በመሆኑ፣ በተጋዮች መካከል ያለው ጓዳዊ መተማመን፣ መከባበር እና መደጋገፍ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጠንካራ ድርጅት የመገንባቱን ሂደት ፈታኝ ያደረገው አንዱ ችግርም ይኸው የፋኖ አርበኞች ያላቸው ዝቅተኛ የሆነ የብሄርተኝነትና የድርጅት ግንባታና አመራር ግንዛቤ ነው፡፡ ስለሆነም በብሄርተኝነት ርእዮት የሚመራ ጠንካራ የፖለቲካ ሃይል ለመገንባት መላው የፋኖ ታጋይ ስለ ብሄርተኝነት የጠራ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሦስተኛው ችግር ስለ ትግሉ አብዮታዊ ባህሪ ያለው ግንዛቤ ውስንነት ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ችግር በብልፅግና አገዛዝ የተጀመረ አይደለም፡፡ ችግራችን በብልፅግና ፋሽስታዊ ቡድን መወገድ የሚቀረፍም አይደለም፡፡ የአማራ ህዝብ ችግር ከፋሽስት ጣልያን የግፍ ወረራ ጀምሮ እየተንከባለለ እና እየተደራረበ የመጣ ነው፡፡ የቁልቁለት ጉዞው ለረጅም ዘመናት የተካሄደ በመሆኑ፣ እንደ ህዝብ ከገባንበት አሳፋሪ አረንቋ ለመውጣት የምንችለው ትግሉ አብዮታዊ ባህሪ የተላበሰ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

የአማራ ጥያቄ “ተራ የፖለቲካ ጥያቄ” አይደለም፡፡ ስለሆነም የአማራ ህዝብ ትግል “ተራ የፖለቲካ ትግል” ሊሆን አይችልም፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል አማራ እንደ ህዝብ ሲታይበት የኖረውን ትርክት ከመሰረቱ የመቀየር ትግል ነው፡፡ የአማራ ህዝብ በፖለቲካ፣ በባህል፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎችም መስኮች በተጠና ሁኔታ እንዲዳከምና እንዲንበረከክ ሲደረግበት የኖረውን ትርክት እና በዚያ ትርክት ላይ የቆመውን መዋቅራዊና ሥርዓታዊ አገዛዝ ከመሰረቱ የመቀየር ትግልም ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል አብዮታዊ ባህሪ ያለው መሆን ይኖርበታል ማለት የህዝቡን የሥራ ባህል፣ የእርስ በርስ መስተጋብሩን፣ ከመንግሥት ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት (state-society relations) በተመለከተ ከመሰረቱ መቀየር ይገባል ማለት ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ ረገድ ሲገመገም አሁን ያለው የፋኖ የአርበኝነት ትግል ብዙ ድክመት ያለበት ነው፡፡ ታጋዩ ስለ አብዮት ያለው ግንዛቤ ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡ ትግሉ አብዮታዊ ነው ብሎ የሚያምን አለ ለማለትም አያስደፍርም፡፡ ትግሉ አሸናፊ እና ዘላቂ ውጤት ማምጣት ካለበት የግድ አብዮታዊ ባህሪ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡

ልብ እንበል!
➢ የትግሉ ግብ በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ መቀልበስ እና የህዝባችን ዘላቂ ነፃነት ማረጋገጥ ነው!
➢ ትግሉ መራራ ነው፡፡ መስዋእትነትን ይጠይቃል፡፡ ትግሉን በአሸናፊነት ልንወጣው የምንችለው በታገልነው መጠን ነው!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

#ማስታወሻ:- ከላይ ያነበባችሁት የአማራ ምሁራን የጥናትና ምርምር ቡድን ያሰናዱት ሰነድ ነው፣ በተከታታይ ወደ እናንተም ይደርሳል!

ይቀጥላል

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

26 Dec, 15:32


📌የፋኖ አርበኝነት ትግል፡- ወቅታዊ ሁኔታዎች

1. እንደ መግቢያ

የአማራ ፋኖ የአርበኝነት ተጋድሎ የተጀመረው ታጋዮች ለተራዘመ የትጥቅ ትግል ተዘጋጅተው ከወጡ በኋላ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በውስን አካባቢዎች የተወሰኑ ዝግጅቶች መደረጋቸው ባይካድም፣ በአብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢ ግን ትግሉ ግብታዊ ባህሪ ይዞ የተቀሰቀሰ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ወደሜዳ የወጣው ሃይል በትግሉ መነሻና መድረሻ ላይ ግልጽ የሆነ የጋራ ግንዛቤ አልነበረውም፤ ዛሬም ይህ ችግር አልተቀረፈም፡፡ በፋኖው ውስጥ ቀደም ሲል በሽፍታነት፣ በነብሰ-አዳይነትና በሌብነት የሚታወቁ አካላትም አሉ፡፡ በዚያው ልክ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ በርከት ያሉ የተማሩ የአማራ ልጆችም የህልውናና የነፃነት ትግሉን ተቀላቅለዋል፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያው ተጽእኖ ምክንያት ብዙው ታጋይ ትግሉ በቀላሉ የሚጠናቀቅና አገዛዙም በአጭር ጊዜ የሚፈርስ ይመስለው እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትግሉ ያለ እድሜውና ያለ ዝግጅቱ የመጋለብና የመንቦጅቦጅ ነገር ነበር፤ ዛሬም አለ፡፡ በሂደቱም ያልተገባ ዋጋ ተከፍሏል፤ እየተከፈለም ነው፡፡ 

ዝቅ ብለን በዝርዝር እንደምናየው በርእዮተ-ዓለም ጥራት ችግር ምክንያት ጠንካራ የፖለቲካ ሃይል ፈጥሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄድ የአርበኝነት ትግል ማካሄድ አልተቻለም፡፡ ወደፊትም ቢሆን የሐሳብ/ርእዮት ጥራት ካልተፈጠረ ጠንካራ የፖለቲካ ሃይል መገንባት አይቻልም፡፡ በጠራ ርእዮት የሚመራ ጠንካራ የፖለቲካ ሃይል መፍጠር ካልተቻለ ደግሞ ጠንካራና አሸናፊ ሠራዊት መገንባት አይቻልም፡፡ ጠንካራ የፖለቲካ ሃይል ከሌለ ውጤታማ አደረጃጀቶችን መፍጠር አይቻልም፡፡ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት አይቻልም፡፡

ስለሆነም ወደ የመፍትሄ ሃሳቦች ለመግባት መጀመሪያ ፋኖ አሁን ያለበትን ቁመና በልኩ መገምገም ያስፈልጋል፡፡ ለውይይት መነሻ እንዲሆን በእኛ በኩል የታዘብናቸውን ሁኔታዎች እንደሚከተለው አስቀምጠናቸዋል፡-

2) የትግሉን ምንነትና ባህሪ በልኩ ከመገንዘብ አንጻር የሚታዩ ድክመቶች

የአማራ ህዝብ ከፋሽስት ጣልያን የግፍ ወረራ ጀምሮ በተከታታይ አገዛዞች በደረሰበት በደል ምክንያት ያጋጠመውን የዘመናት የውርደት ማቅ ቀልብሶ የህዝቡን ህልውና ለማስከበርና ነፃነቱን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ መካሄድ ያለበት ትግል በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት ላይ በተመሠረተ የፖለቲካ ድርጅት/ሃይል መሪነት የሚካሄድ አብዮታዊ ትግል መሆን ይገባዋል፡፡

ከላይ የቀረበውን አንቀጽ ዘርዘር አድርጎ ለማስቀመጥ ያክል ትግሉ፡-

✓ በአማራ ብሄርተኝነት መመራት አለበት ማለት መላው ህዝባችን (ከልሂቅ እስከ ሰፊው ህዝብ/ከሊቅ እስከ ደቂቅ) አማራዊ ማንነቱን እንዲገነዘብና እንዲነቃ፣ በአማራዊ ማንነቱ እንዲደራጅ እና ለአማራዊ ማንነቱ እንዲታገልና መስዋእትነት እንዲከፍል መደረግ አለበት ማለት ነው፡፡ የትኛውም ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት መስዋእትነት በሚያስከፍል ትግል ውስጥ ለመሳተፍ የሚነሳሳውና ወደተግባራዊ እርምጃ ውስጥ የሚገባው የሚያታግለው ርእዮት ሲኖረው ነው፡፡ እያንዳንዱን ታጋይ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የሚያጣብቀው፣ የትግሉን መነሻና መዳረሻ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው ፍኖት ወይም ርእዮት ያስፈልገዋል፡፡ በእኛ ሁኔታ ዋነኛው የመታገያ ርእዮታችን ሃይማኖት ሊሆን አይችልም፡፡ የምናካሂደው የመደብ ትግል ወይም በአካባቢ ላይ የተመሠረተ ትግልም አይደለም፡፡ ዋነኛው የመታገያ ርእዮታችን የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ የአማራ ህዝብ በተከታታይ አገዛዞች የደረሰበትን መገፋትና በዚህ ምክንያት የገባበትን የቁልቁለት ጉዞ ቀልብሶ ህልውናውንና ነጻነቱን ለማስከበር ያለው ትልቁ ሀብቱ ብሄርተኝነቱ መሆኑን ሁልጊዜም ደግሞ ደጋግሞ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ከድሮንም፣ ከኒውክሌርም በላይ ትልቁ መሳሪያ የተደራጀ ህዝባዊ ሃይል ነው፡፡ የአማራ ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን እንደ ብረት የጠነከረ አንድነትና የተደራጀ አቅም ሊፈጥር የሚችለው ደግሞ በአማራ ብሄርተኝነት አማካኝነት ብቻ ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ብሄርተኝነቱን አጥብቆ ካልያዘ አይነሳም!

✓ ትግሉ ‹መሪ ድርጅት› ያስፈልገዋል፡፡ የአማራ ህዝብ ህልውናውን ሊያስከብርና ነጻነቱን ሊያረጋግጥ የሚችለው በትጥቅ ትግል በታጀበ አብዮታዊ ትግል ነው፡፡ ይህን አብዮታዊ ትግል በድል ለመወጣት ደግሞ ሃሳብ የሚቀምር፣ ስትራቴጅ የሚቀርጽ፣ ድርጅታዊ አመራር የሚሰጥ፣ የዲፕሎማሲና ፕሮፓጋንዳ ሥራውን በተደራጀ አግባብ የሚመራ ወዘተ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት/ሃይል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ሠራዊቱም ሆነ ሌላው በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኘው ታጋይ በዚህ የፖለቲካ ድርጅት አማካኝነት መመራት ይኖርበታል፡፡ በጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት የማይመራ ሠራዊት ከሽፍታ ወይም ከጦር አበጋዝ የዘለለ ሚና ሊኖር አይችልም፡፡ ስለሆነም ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት መገንባት እና ይህን ድርጅት በዲሞክራሰያዊ አግባብ መምራት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡

✓ ትግሉ አብዮታዊ ትግል ነው፡፡ ይህም ሲባል ህዝባችንን ጠፍረው የያዙት ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች (ጥቁር ደም፣ ስንፍና፣ ማይምነት ወዘተ) ከመሰረታቸው እንዲቀየሩ፣ ህዝባችን የራሱን ጉዳይ በራሱ መፍታትን እንዲለማመድ፣ የዲሞክራሲና የተጠያቂነት ባሕል እንዲሰርጽ፣ ታታሪነትና ዲሲፕሊን የህዝቡ ዋነኛ መገለጫ እንዲሆን ወዘተ… መታገል ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ ትግሉ አብዮታዊ ትግል ነው ማለት በህዝቡና በሚገነባቸው አስተዳደሮች መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማና የሰመረ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ በየደረጃው የሚዋቀሩት አስተዳደሮች ህዝቡን በፍፁም ወገናዊነት፣ በቁጭት እና በተጠያዊነት መንፈስ እንዲያገለግሉት ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ በሀገር ደረጃ የሚመጣው ለውጥም በተመሳሳይ የፖለቲካና የማህበራዊ ጉዳዮችን በመሰረታዊነት የሚቀይር መሆን አለበት ማለት ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ታዲያ ታጋዩ ራሱ ታታሪ፣ በዲሲፕሊን የሚመራ፣ አቅዶ የሚሰራ፣ ህዝባዊነትን የተላበሰ ወዘተ… መሆን ይኖርበታል፡፡ ታጋዩ ህዝቡን አስተባብሮ አብዮታዊ ለውጥ ለማምጣት መጀመሪያ በራሱ ላይ አብዮት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡ የትግሉ ተዋናዮች እነማን እንደሆኑ፣ ትግሉ የት እንደሚካሄድ እና ትግሉ እስከመቼ እንደሚቀጥል ጠንቅቆ መገንዘብም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ከላይ ከቀረቡት ነጥቦች አንጻር የፋኖ አርበኝነት ተጋድሎ ያለበትን ሁኔታ ስንገመግመው፣ አንደኛ የፋኖ ትግል በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት እየተመራ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ የሚበዛው ታጋይ ስለ ብሄርተኝነት ያለው ግንዛቤ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአመራር ደረጃ ያሉት ወገኖችም ስለ ብሄርተኝነት ምንነት፣ ስለ ብሄርተኝነት አቅም እና ስለ አማራ ብሄርተኝነት መለዮዎች ያላቸው ግንዛቤ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የተሻለ ግንዛቤ ያላቸው ታጋዮች ቢኖሩም፣ አብዛኛው ታጋይ ብሄርተኝነትን በውል ያውቀዋል ለማለት አይቻልም፡፡ ይህ ትልቅ ችግር ነው፡፡ በፍጥነት መታረም የሚገባው ትልቅ ችግር!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

26 Dec, 12:55


ጎንደር

በዳባት ከባድ ውጊያ በመካሄድላይ ሲሆን ደባርቅ አካባቢ ትናንት በተካሄደው ውጊያ 400 የሚሆን ወራሪ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል 20 ወራሪ ገደል ገብቶ ሞቷል 6 መስመራዊ መኮንኖች ተደምስሰዋል 19 ብሬንና 19 ስናይፐር ከጥላት ሲማረክ በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና 70 ወራሪ ተማርኳል።

ታሕሳስ 17/04/2017 ዓ.ም
 

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

25 Dec, 18:55


አብይ አህመድ በሚመራው መከላከያ ሚኒስቴር ውሰጥ ስራ ላይ ያሉ 105 ጄኔራሎች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 31ዱ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩ ናቸው። በዚህም መነሻ 105 ሲቀነስ 31 ቀሪ 74 ይሆናል። 74ቱ ጄኔራሎች የሚያዋጉ ጄኔራሎች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 44 ያህሎቹ ከጥር ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የአማራ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ እና ጥቃት ለማድረስ በቋሚ ወይም በጊዚያዊነት የቆዩ ሲሆኑ እነሱም ፦

1ኛ. ፊ/ማርሻል ብርሃኑ ጁላ (ኢታማዦር ሹም )
2ኛ.ጄነራል አበባው ታደሰ (ም/ል ኢታማዦር እና የአማራ ክልል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ )
3ኛ. ሌ/ጄ ጌታቸው ጉዲና (የመከላከያ መረጃ ዋና መመሪያ )
4ኛ. ሌ/ጄ በላይ ስዩም (የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ኃላፊ
5ኛ. ሜ/ጄ ሙሉዓለም አድማሱ (የመከላከያ ሜካናይዝድ ዕዝ ዋና መመሪያ ኃላፊ)
6ኛ. ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ (የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ )
7ኛ. ሌ/ጄ ክንዱ ገዙ (የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ )
8ኛ. ------የመከላከያ የሎጅስቲክ ዋና መምሪያ ኃላፊ
9ኛ. ------- የኢንፎርሜሽን ዋርፌር ኃላፊ
10ኛ. ሌ/ጄ ብርሃኑ በቀለ (የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ )
11ኛ. ሌ/ጄ መሀመድ ተሰማ (የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ )
12ኛ. ሌ/ጄ አሰፋ ቸኮል (የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ )
13ኛ. ሌ/ጄ ሹማ አብደታ (የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ፣የኮማንዶ እና አየር ወለድ አዛዥ )
14ኛ. ሌ/ጄ ጥጋቡ ይልማ
15ኛ. ሜ/ጄ ሰለሞን ቦጋለ
16ኛ. ብ/ጄ ዋኘው ዓለሜ
17ኛ. ብ/ጄ ማርዬ በየነ
18ኛ. ሜ/ጄ አዳምነህ መንግሥቴ
19ኛ. ብ/ጄ ተሰማ አናጋው
20ኛ. ብ/ጄ አዘዘው መኮንን
21ኛ. ሜ/ጄ ጥሩዬ አሰፋ
22ኛ. ሜ/ጄ መሰለ በለጠ
23ኛ. ብ/ጄ ዘውዱ ሰጥአርጌ
24ኛ. ብ/ጄ ደረበ መኩሪያ
25ኛ. ሌ/ጄ ይመር መኮንን
26ኛ. ብ/ጄ አበባው ሰይድ
27ኛ. ብ/ጄ አበባው መንግሥቴ
28ኛ. ብ/ጄ ማርዬ መንግሥቴ
29ኛ. ብ/ጄ ሐሽም (ከደባርቅ እስከ ማይጠብሪ መከላከያን የሚመራ )
30ኛ. ብ/ጄ ሞሲሳ (የሸዋን ኮማንዶ የሚመራ )
31ኛ. ሜ/ጄ ሰይድ እንድሪስ (ወሎ 5ተኛ ሻለቃ ኮማንዶ የሚመራ )
32ኛ. ብ/ጄ እርቂያለሁ (ደቡብ ጎንደር ያለውን መከላከያ የሚመራ )
33ኛ. ብ/ጄ ጠቅለው ክብረት
34ኛ. ብ/ጄ አዲሱ መሀመድ
35ኛ. ሌ/ጄ ሰለሞን ኢተፋን (የደቡብ ዕዝ አዛዥ )
36ኛ. ሜ/ጄ አማረ ገብሩ
37ኛ. ሌ/ጄ መሰለ መሰረት (የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ )
39ኛ. ብ/ጄ አብደላ መሀመድ
39ኛ. ብ/ጄ መለሰ መንግሥቴ
40ኛ. ብ/ጄ ያሬድ አበበ (የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የባሕርዳር ከተማ ኦፕሬሽን ምድብ )
41ኛ. ሜ/ጄ ግዛው ኡማ (የምስራቅ ዕዝ ም/ል አዛዥ )
42ኛ. ብ/ጄ ሶፍያ መሀመድ (602ኛ ኮር አዛዥ )
43ኛ. ብ/ጄ ተሾመ ይመር
44ኛ. ሌ/ጄ አሸናፊ ብርቄ እና ከዚህ ውጭ ስማቸው ያልተዘረዘሩ በቀጣይ የሚገለፁ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል ።

በዚህ የአማራ የዘር ጭፍጨፋ እውነታውን በመደበቅ እና የብልጽግናን ሕገወጥ ድርጊት እንደ ሕጋዊ ዕርምጃ በመሸፈን ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ:-

1ኛ. የአማራ ክልል የመገናኛ ብዙሃን የቦርድ ሰብሳቢዎች ።
2ኛ. የአማራ ክልል ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች
3ኛ. የአማራ ክልል ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች
4ኛ. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እና የቦርድ ሰብሳቢዎች
5ኛ. የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የባሕርዳር ስቲዲዮ ጨምሮ በሁሉ ዞኖችና ከተሞች የሚገኙ ጋዜጠኞች ።
6ኛ. የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እና ጋዜጠኞች
7ኛ. በለገሰ ቱሉ የሚመራው የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር
8ኛ. በሚኒስትር መስሪያ ቤት የሚገኙ የፌደራል ተቋማት ፦
  ሀ) የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት
ለ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መስሪያ ቤት
ሐ) የፌዴራል ፍትሕ ሚኒስትር ዓቃብያን ሕጎች እና ኃላፊዎች
መ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ)
ሠ) አርቲፊሻል ኢንቴሌጄንስ (ሰው ሰራሽ አስታውሎት)
ረ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ሰ) የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን
ሸ) የአቢሲኒያ አየር ትራንስፖርት አገልግሎት ናቸው።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

25 Dec, 15:09


''60 ወታደር እና 200 መሳሪያ ሲማረክ ከ150 በላይ ሙት ሆኗል'' የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ።

3 ክፍለጦር፣ 3 ጀንበር እልፍ ድል በጎንደር ምድር !

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ 3 ክፍለጦሮች 72 ሰዓታትን ከጠላት ጋር እያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ከፍተኛ ድልና ጀብዱ አስመዝግበዋል።

እስካሁን ተጠናክሮ በቀጠለው  ይህ ትንቅንቅ የአገዛዙን 68ኛ ክፍለጦር በጥራሂናና ወገዳ ቀጣናዎች በመግጠም ከፍተኛ የመሳሪያና ወታደር ምርኮ ያገኙበትና ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የአገዛዙን ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል ያስመዘገቡበት፤ አሁንም እየተፋለሙበት ያለ ሆኗል።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር፣ ጭና ክፍለጦርና ሰሜን አምባራስ ክፍለጦሮች እያደረጉት ባለው ትንቅንቅና ድል በተጎናፀፉበት ተጋድሎ ከ200 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ከ60 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች እንደዚሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብሬንና ስናይፐር ምርኮም በወገን ሀይል ተገኝቷል።

በትንቅንቁ እድል የቀናቸው የአገዛዙ ሀይሎች በቀላልና ከባድ ቁስለትም ውስጥ ሆነው ለሽሽት ሲበቁ ከ150 በላይ የሚሆኑት በውጊያው ተገድለዋል ሲል የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዮሀንስ ንጉሱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።

ይህ የመረጃ ቅብብል ቃለምልልስ እየተደረገ ባለበት ጊዜም ውጊያው በከፍተኛ ሁነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ፋኖ ዮሀንስ አንስቷል።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

25 Dec, 14:17


የጀነራሉ አጃቢዎች መክዳት

የጀነራሉ አጃቢ ኮማንዶዎች ስርዓቱን ከድተው ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ
በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የሚከዱና የሚጠፉ ወታደሮች ቁጥርም እየጨመረ ነው፡፡
በባህርዳር ቅርብ ርቀት ላይ ባሉ የጎጃም አካባቢዎች ትናንት ከባድ ውጊያ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን ብራቃትና አማሪት ደግሞ ይህ ውጊያ የተካሄደባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡
በአካባቢዎቹ በተካሄደው ውጊያ በፋኖ ሽንፈት ያስተናገደው የአገዛዙ ጦር በንጹሃን መኖሪያ መንደሮች ላይ ዙ 23ን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ሲወረውር ነበር፡፡
በተመሳሳይ እነ አበባው ታደሰ ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ሚሊሻን በሚመለከት አንድ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ውሳኔያቸውም ወጣቱን ለሚሊሻነት ማስታጠቅ አደጋ ያመጣብናል ብለዋል፡፡ ስለሆነም ወጣቱ ለእኛ ስለማይታመን ለሚሊሻነት ሲመለመል መሳሪያ ማስታጠቅ አያስፈልግም ፣ ሌላ መፍትሄ ፈልጉ መባሉ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም እነ አበባው ታደሰ የመሳሪያ እጥረት እንደገጠማቸው ነው የተነገረው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ የሚደረጉ ወታደራዊ ስምሪቶች በመከላከያ እንዲመሩና ሚሊሻና አድማ ብተና በራሳቸው ሥምሪት እንዳይሰጡ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በሌላ በኩል ከሰሞኑ በርካታ ወታደሮች ከስምሪት ቦታቸው ጠፈተዋል ፣ ለፋኖ እጃቸውን ሰጥተዋል ፣ ተማርከዋል ፣ ወደ ፋኖ በፍቃዳቸው ተቀላቅለዋል፡፡
ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በምዕራብ ጎንደር መተማ ከ34 በላይ ወታደሮች በፋኖ ተይዘዋል፡፡ የጦር መሪያቸውን ጨምሮ 29 የሚሆኑት ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ በበለሳ የሚሊሻ ሃላፊውን ጨምሮ ከ33 በላይ የሚሆኑት የአገዛዙ ሃይሎች በፋኖ ተይዘዋል ፣ በመንዝ ደግሞ ድሽቃ ይዘው ቁጥራቸው ያልታወቀ ኮማንዶዎች ፋኖን ተቀላቅለዋል፡፡
በፍኖተ ሰላም 8 ወታደሮች በፋኖ ሲያዙ ፣ 37 የሚሆኑት ደግሞ ጠፍተው በፈቃዳቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል፡፡
በደብረማርቆስ ፣ ደብረኤሊያስ ፣ ጎዛመንና ቢቸና ቀጠናዎች አጠቃላይ ከ41 በላይ ወታደሮች ከስምሪት ቀጠና ጠፍተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ጎንደር ጋይንት የጀነራሉ አጃቢዎች ፋኖን መቀላቀላቸው ነው የተሰማው፡፡ የብርጋዴር ጀነራል መላኩ ገላነህ አጃቢዎች ናቸው ፋኖን የተቀላቀሉት ተብሏል፡፡
እነዚህ አጃቢዎች የሲዳማና የኦሮሞ ተወላጅ ኮማንዶዎች መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡ በአካባቢው ያሉ የፋኖ ሃይሎችም ቃለ መጠይቅ እንዳደረጉላቸው ነው የተነገረው፡፡
roha

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

25 Dec, 11:05


ቤተ አማራ ወሎ💪

#ላስታ_አሳምነው_ኮር፦ የአማራ ፋኖ በወሎ የላስታ አሳመነው ኮር ትልቅ ፊልሚያ እያደረገ ይገኛል።

ዛሬ ማለትም 16/04/2017 ዓ.ም የጠላት ሀይል ጀግናወቹን የአሳመነው ልጆች አገኛለሁ በሚል ተልካሻ ምክንያት ከጋሸና ወደ ድብኮ ማሪያም ከባድ መሳሪ በመተኮስ ንጹሀንን እየጨፈጨፈ ሲሆን እስከ አሁን ከ3 ጊዜ ያላነሰ ከባድ መሳሪያ ከጋሸና ወደ ድብኮ ማሪያም ተተኩሷል። በተጨማሪ ከወደ ላሊበላ የመጣው የጠላት ሀይል ዶግ ሜዳ አካባቢ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን እየተኮሰ ቢሆንም የበረሀወቹ የአሳመነው ልጆች እንኳን የምድር ሀይል የድሮንን ሀይል ከጉዳይ የማይቆጥሩት ይምጣ አይመለስም ብለው ግምባር ግምባሩን እየነደሉት ይገኛሉ።

የመጣው ሀይል ከጉድጓዷ ገብታ የማታመልጥ  አይጥ እንደማለት ነው በማለት ኮማዶ ፍቅሩ ሀይሉን አጠናክሮ እየጠበሰው ይገኛል ሲሉ  ምንጮች ገልፀዋል

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 14:08


🔥#አሁና_መረጃ_ፋግታ

በገፍ ይራገፋሉ እንደቅጠል ይረግፋሉ!!

አብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ከኢትዮጵያ ድሀ እናት እቅፍ እየፈለቀቁ በግድ አፍሰዉ የሚሰበስቡትን ምስኪን ለብለብ የማይሰነብት ሰራዊታቸዉን እያመጡ ከሚያራግፉበት የአማራ ምድር አንዷ የእኔዋ አዲስ ቅዳም ከተማ ከሆነች ቆይታለች።  አዲስ ቅዳም ከተማ ቀን በቀን ከእየ አቅጣጫዉ በመቶወች አለፍ ሲል በሽዎች የሚቆጠር የጠላት ጦር ሲገባ እናያለን ይሁንም እንጅ የጠላት ጦር ቁጥር ግን ከነበረበት አንድስ እንኳ ጨምሮ አያዉቅም እንዲያዉም እያደር ሲሳሳ እንጂ ይህ የሆነዉ ካለምክኒያት አይደለም ምክኒያት አለዉ። አወ! ምክኒያቱም ፋግታ ለኮማ ወረዳ (አዲስ ቅዳም) ማለት የእነዚያ የአናብስቶቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በፋ/ለ/ወ  የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ  መገኛ ከባድ  የጠላት ፔርሙዳ የተባለለት አደገኛ ቀጠና በመሆኑ ነዉ።

ዛሬ 24/03/2017 ዓ/ም  የዉሎ ሁኔታ ስመለስ ጠላት 23 ለ 24 ለሊት 6:00  ከአዲስ ቅዳም ከተማ ተነስቶ  በምዕራቡ አቅጣጫ ከዚህ ቀደም ከ22 ጊዜ በላይ ሞክሮ  እንደ እባብ አናት አናቱን ተቀጥቅጦ የተመለሰባትን ድማማ ደለከስ ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን ከአንገት በታች መምታትን እንደ ዉርደት በሚቆጥሩት አናብስቶቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፋኖዎች መንገድ እስኪጠፋዉ ቅንድብ ቅንድቡን ተብሎ መድረሻ ነጥቡ የነበረችዉን  ደለከስን ሳይረግጥ ከድማማ ዙሮ አብላ ቀበሌን አቋርጦ አሽዋ በመድረስ አስፓልት መንገዱን በመጠቀም እንደተለመደዉ ከሁዋላ እንደ እብድ ዉሻ እያባረሩ ለሚነድፉት የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ እስትንፋሶች የሚያስረክበዉን አስረክቦ ከቀኑ 7:30 አካባቢ ሲሆን አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት አድጓሚ ተራራ እንደ ኤሊ አንገቱን ቀብሮ መቀመጡን የአሻራ ምንጮች ገልፀዋል ።

በተመሳሳይ ለሊት 7:00 ስዓት 1ኛዉ ከአዲስ ቅዳም በመነሳት
#በመርፊ-ሚኬኤል #ቅላጅስታን አድርጎ ፋግታን በማለም  ከሁለት ቀን በፊት ማለትም በ21/03/2017 ዓ/ም በአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር ብርጌዶች ጥምረት በመቶወች የሚቆጠሩ ጓዶቹን በገበረበት እና በመቶወች የጦር መሳሪያ ወደ ተማረከባት #ደብረ_ዘይት እየተንፏቀቀ ሲሆን ባለ ንስር አይኖቹ የስቦ መምታት ጠበብቶች የ፲/አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ እስትንፋሶችም ቀለበታቸዉ ዉስጥ እስኪገባ እያባበሉት ይገኛል።

ከእንጅባራ በመነሳት አሰራን አቋርጦ በአሰም ስላሴ በማለፍ ያችን የባለ ሱሪዎችን አገር የወንዶችን መፍለቂያ ፋግታን ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን የአይደፈሬዎቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በሳትማ ዳንጊያ ቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ግስሎች የደፈጣ ሲሳይ ሁኖ "አሰራ" ተራራን ሙጥኝ ብሎ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማ እንደሚገኝ አሻራ ሚዲያ አረጋግጧል።

©ፋኖ ተሻገር አደመ ከ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 13:04


በድሮን ጥቃት ጭፍጨፋ ተፈፀመ !

የአገዛዙ ሀይል በሸዋ 2 የድሮን ጥቃቶችን ፈፅሞ በርካቶች መጎዳታቸው ተሰምቷል።

በሸዋ ክፍለ ሀገር መርሀቤቴ አውራጃ ሬማ ከተማንና አካባቢውን የተቆጣጠረውን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ አፄ ዳዊት ክፍለጦር ማስለቀቅ የከበደው የአገዛዙ ሀይል በፈፀመው የድሮን ጥቃት ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

በሬማ ንዑስ ወረዳ ቢራባ በተባለ ስፍራ በተፈፀመው ይህ የድሮን ጥቃት በርካቶች መጎዳታቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።
ጥቃቶች ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ተፈፅመዋል ብለዋል የአካባቢው ምንጮች።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 09:45


🔥#ጎንደር ‼️

አዞዞ ኢምባሲ በሚባል ቦታ ሮዚኦ ሆቴል አጠገብ  እና 18 ቀበሌ ጊዮርጊስ አደባባይ ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን ከ10 በላይ ሚኒሻ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 09:44


ባንነቃና:–
> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው የድሮ ስርአት የማስመለስ ጥያቄ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው ሀይማኖት ጨቋኝ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው የአሀዳዊነት ጥያቄ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

ምናልባት በዚህ ዘመንም የቀጠለው አማራ ጠሉ ትርክታችሁ ውዝንብር በፈጠረብን ነበር።

ችግሩ ~ አማራ አሁን ነቃ፣ አይኑን ገለጠ!!!

በእርግጥ አማራ እንዳይነቃ ሆኖ የኖረበት ዘመን ለብዙ የምርምርና የጥናት ስራ የሚገፋና ለወደፊት ትውልድ የሚሆን የማስተማሪያ ስራ የሚወጣው የቤት ስራችን ቢሆንም ለዛሬ አማራ በላዩ ላይ የተናዘበትን ጭቃና አቧራ አራግፎ የተነሳበት አዲስ የአማራነት መንፈስ፣የትውልድ ንቃት በአማራ ህዝብ ፖለቲካ ውስጥ በድሮ በሬያችሁ አርሳችሁ ፣በድሮ ትርክታችሁ ናውዛችሁ ልትዘሩት ያቀዳችሁትን፣ያሰባችሁትን ነገር ሁሉ ፉርሽ አብልቷል።

Whatever you could say or peddle against us, It doesn't ring a bell in our ears.

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 08:09


ቲሊሊ‼️

ከቲሊሊ ወደ ሰከላ ወረዳ ግሽ ዓባይ ከተማ ጀሚያገናኘውን መስመር ሙሉ በሙሉ ይዘጋ ብሎ ትዛዝ በማስተላለፉ የተሸጡ ሸቀጦችን ጨምሮ የተጫኑ እቃዎንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አግዷቼዋል።
በ100 ተራሮች ዘመቻ 75ኛ ክፍለ ጦር በቅርቡ ደግሞ 73ኛ ክፍለ ጦር የተደመሰሰበት ሰከላ ወረዳ ምንም አይነት የሸቀጣ ሸቀጥ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተከለከለ።

#የሰከላ _ወረዳ ባንኮችም ከመስከረም 29/2017ዓ.ም ጀምረው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌላቼው በተደጋጋሚ መዘገባችን አይረሳም። ባንኮች አሁንም ሰራተኞችን ወደሌሎች ቅርንጫፎች እየላኳቼው መሆኑን ተጨባጭ የሆነ መረጃ አድርሰውናል።

የሰከላ ወረዳ ማኅበረሰብ የባንኩን ሁኔታ ምንም ያልመሰለው አሁን ደግሞ ሸቀጣ ሸቀጥ አይደለም ምንም አይነት መኪና እንዳይንቀሳቀስ አግደዋቸዋል።
በአሁኑ ሰዓትም በአዲስ ቅዳም በኩል ባለው መስመር ከባባድ መሳሪያ እየተተኮሰ ነው።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Dec, 04:39


🔥#ጥንቃቄ_መልዕክት‼️

በዚህ ሰአት ከባህርዳር በላይ ዘለቀ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ተደጋጋሚ የድሮን በረራ እየተደረገ እንደሆነ ጥቆማዎች አሉ ስለሆነም ጥንቃቄ ይደረግ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Dec, 16:28


ሰበር ዜና!

የመከላከያው ከፍተኛ አዛዥ ኮሎኔል አበራ  በይፋ ፋኖን መቀላቀሉን ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ ገለፀ።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Dec, 05:23


የኦሮሞ ወጣት ሸኔን ለመዋጋት ወደ መከላካያ እየተመዘገበ ነው ~ የሚል ዜና ሲሰሩ በብዛት አይስተዋሉም።

ለምን:–
አብይ አህመድ ከዚህ በፊት ናዝሬት ላይ በነበረ ስብሰባ የሆነ ፕሮጀክት ለማስመረቅ ወለጋ ያልሄድኩት ምናልባት ኦነጎች እኔን ለመግደል ቢሞክሩ ወይም መግደል ቢችሉ ኦሮሞን ኦሮሞ ገደለው የሚባል ታሪክ በኔ ሰበብ እንዳይፃፍና በወለጋና በጅማ አካባቢ ኦሮሞ የታሪክ ቁርሾ እንዲቀመጥ ሰላልፈለኩ ነበር የሚል አንደምታ ያለው ንግግር በድብቅ ከስብሰባው ላይ ተቀርፆ ሰምተን ነበር።

ከሰሞኑ:–
የግዴታ አፈሳው ሀቅ እንዳለ ሆነ በመንግስት በኩል ግን የአማራ ክልል ወጣቶች ፋኖዎችን ለመግጠም ወደ መከላከያ አረየተመዘገቡ ነው ብለው ዜና ሲለቁ ያለማፈራቸውና ያለመሳቀቃቸው ነገር በብልፅግና ቤት ውስጥ ~ #Thought_Disorder የከፋ መሆኑን አሰረጂ ነው።

Imagine?
ስለ ኦሮሞነት ያን ያክል ርቀት የተጓዘው መሪ የአማራ ወጣት የጥንፈኛው ቡድን ለመግጠም ለመከላከያ እየተመዘገበ ነው ሲልህ ሰዎቹ ምን ያክል የአስተሳሰብ እክል፣የአስተሳስብ ዝቅጠት ላይ እንደደረሱ ማሳያ ነው።

የሚያጨሱት ነገር እማ አለ!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Dec, 12:59


🔥#መረጃ_ደብረኤልያስ‼️
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም ትንቅንቁ ቀጥሏል‼️

ከአራት ቀን የእጅ ለእጅ ሙሉ ውጊያ ተርፎ እና ሌላ ሐይል ጨምሮ ደብረ ኤልያስ የገባው የአብይ ቡችላ ዛሬ በነበረው ኦፕሬሽን ታሪክ ነው የተሰራው።
በስድስት አቅጣጫ የገባው የፋኖ ሐይል ጠላትን እንደ ቅጠል ሲያረግፈው ውሏል።የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ክፍለ ጦር ዛሬ በደብረ ኤልያስ ባደረገው ውጊያ የተገኙ ድሎች እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ናቸው።

የቤተክርስቲያን አባቶችን ሰብስቦ አስታርቁኝ ሲል የሰነበተው የአብይ ወንበዴ ቡድን እንደዛሬውስ ተመቶም አያቅ!!

👉በውጊያው ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ሆኗል
👉የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከአስታጥቄዎች መረከብ ተችሏል
👉ሬሳው በየመንገዱ ወድቆ ቀርቷል
👉ሙሉ ከተማውን ለሰባት ሰዓት ያክል ተቆጣጥሮ ውሎ አሁን ላይ ፋኖ ቦታውን ይዟል።
ሌላውን በዝርዝር እንመለስበታለን!!!

አዲስ አብዮት ፣አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ

በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

22/03/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Dec, 08:25


#ትናንት

በዘመቻ መቶ ተራሮች አንደኛ ደረጃ እንደወጣ በአፋጎ ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የተመሰከረለት ፫ኛ ክፍለ ጦር ጎጃም አገው ምድር
የመከላከያን 73ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ደምስሷል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ህዳር 21/2017 ዓ.ም
ጀብደኛው #የ3ኛ(የጎጃም አገው ምድር) ክፍለ ጦር እንደዚህ ቀደሙ ትናንትም በጠላት ላይ ባደረገው ትንቅንቅ ጠላትን አሳሩን ሲያበላው ውሏል።
አብይ አህመድ "አንድ ሺ ዓመትም ቢሆን እንዋጋቸዋለን" እያለ እየቀባጠረ ባለበት ሰዓት ጀግናው የ3ኛ(የጎጃም አገው ምድር) ክፍለ ጦር ጠላትን በመረፍረፍ የጠላትን ቅስም የሰበረ ወገንን ያኮራና የወገንን ልብ ሞቅ የሚያደርግ ጀብዱ ፈጽሟል።
ጠላት እርም የለውምና በፋግታ ለኮማ ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ፋግታ ከተማን ለመያዝ ጭፍራውን አግተልትሎ ቢመጣም #ደብር ዘይት መገንጠያ ላይ ጠላት እንደእባብ ሲቀጠቀጥ ውሏል።
  ባለድሎቹ
#የፋግታ ለኮማው ~፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
#የዳንግላው ~ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ
#የሰከላው ~ጊዮን ብርጌድ እና
#የእንጅባራው(ሳጥሚያ ድንጋይ) ~ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ እንዲሁም ከዘንገና ብርጌድ የተወሰነ ኃይል በጥምረት ባደረጉት የከበባ ውጊያ
    ከ300 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ
     ቁጥሩ ያልታወቀ ጠላት ተማርኳል
     6 ብሬል(መትረጊስ)
      3 ስናይፐር
      137 ክላሸንኮቭና
በርካታ ቁጥር ያለው ተተኳሽ ተማርኳል።

ጠላት ከእንጅባራ በBM ወደ ፋግታ ከተማ በመተኮስ ሽፋን ለመስጠት ቢሞክርም የፋኖን ስነ- ልቡና መስበር አልቻለም።መጨረሻ ላይ ዙ 23ና ፔምፔ በማምጣት ከፋኖ ጥይት የተረፉ ትንሽ ኃይሉን እንዲሁም ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ተመልሷል።
በሌላ ግንባር ይሄው 3ኛ ክፍለ ጦር ከቲሊሊ ወጥቶ ወደ ሰከላ አቅጣጫ እየተጓዘ እያለ #አሽፋ መገንጠጠያ(ስላሴ) ላይ በቲሊሊው #ዘንገና ብርጌድ ሲረፈረፍ ውሎ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ፈርጥጦ በመመለሱ ሙሉ በሙሉ ከመደምሰስ ተርፏል። ዘንገና ብርጌድ በሌላ በኩል #ቲሊሊ ከተማ በመግባት ጠላትን ሲፋለመው ውሏል።ቲሊሊ ከተማን ለረጅም ሰዓት በወገን እጅ ማስገባት ችሏል።
አሽፋ መገንጠያ(ስላሴ) ከዚህ በፊት በርካታ የጠላት የተደመሰሰበትና እነኮሎኔል ያሬድን ጨምሮ በርካታ ጠላትና የጠላት መሳሪያ የተማረከበት ቦታ ነው።

#የ8ኛ(በላይ ዘለቀ) ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ በእነማይ ወረዳ #ወይራ ቀበሌ ላይ በጠላት ካምፕ ውስጥ በመግባት ባደረገው ድንገተኛ ጥቃት 9ሙትና ከ10 በላይ የጠላት ኃይልን ቁስለኛ ማድረግ ችሏል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Nov, 16:03


ቃላት ያልደበቁት ሽንፈት

"ከ15 ቀናት ወደ 1ሺ ዓመታት…"

የ4ኛ ጨ ምሩቁ ጨቅላው አብይ አህመድ "በ15 ቀናት እደመስሰዋለሁ፤ እንኳን ትጥቁን ሱሪውን አስፈታዋለሁ" በማለት ጦርነት ከፈተብን፣ ከሁለት ዓመታት ውጊያ በኋላ ዛሬ ግን "በአንድ ሺ ዓመትም አታሸንፉንም፤ ስለዚህ እንደራደር" ሲል ተደመጠ።

እዚህ ጋር የጨቅላው ድንፋታ በሁለት መልኩ ማፈግፈግን አሳይቷል፦ A) የመጀመሪያ ወደል ማፈግፈግ ከ15 ቀናት ወደ አንድ ሺ ዓመት ሲሆን B) ሁለተኛው ደግሞ የ"አጠፋችሁኋለሁ" ድንፋታ ወደ "አታሸንፉንም" የሚል ሆኖ እናገኘዋለን። "እዚህ ና፣ እዛም ና" የተባለለት ሰራዊት የወንዶቹን ሱሪ ለማስወለቅ 1000ሺ ዓመታትን እንደሚፈልግ ወይም የራሱን ማውለቅ እንደሚቀለው በእቅድ ክለሳው ነገረነ 🤣🤣  በጥቅሉ የዚህ ፊደል ያልዘለቀው ወደል ጨቅላ ከንግግሩ ይልቅ ለቅሶው ዘልቆ ይሰማናል።

የዚህን ጨቅላ ረብ የለሽ ዲስኩር ወደ ጋርቤጅ ቢን ወርውረን - አገዛዙ በየጊዜው ኤሊትፎርስ፣ ባህር ኃይል፣ መደበኛ ወታደር ወዘተ እያለ ሲያሰለጥናቸው የኖሩት አራዊት ሰራዊቶች በሙሉ የት ገብተው ይሆን አሁን በድጋሚ በገፍና በስፋት አፈሳና አስገዳጅ ውትድርና የተጀምረው? መልሱ ቀላል ነው - ባለፉት ሁለት ዓመታት ስለቀለጡ ነው። በግዳጅ የሚዘምተውም ይህንን ፋሽስታዊ ስርዓት ከመቅለጥ አያድነውም።

ለማንኛውም አንድ ሺ ዓመታት አይደለም አንድ ዓመት ከቆየህ በአንተ ጥንካሬ ሳይሆን በእኛ ችግርና ድክመት ብቻ ይሆናል። ከእነ ድንቁርና አፈር ትለብሳለህ - ይህ ይመዝገብልን።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Nov, 11:27


የድል ዜና !!!

የአማራ ፋኖ በጎጃም የ3ኛ ክፍለ ጦር በፋግታ ለኮማ ወረዳ በደብረ ዘይት መገንጠያ አከባቢ ማታ ሰርጎ የገባው የአብይ አህመድ ስርዓት አጠባቂ ሀይል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ።

💪💪💪💪💪

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Nov, 11:27


🔥#ላስታ_ግዳን_ወረዳ_ሙጃ_ከተማ‼️

ዛሬ ጀግኖቹ የአሳመነው ልጆች ከሌቱ 11:00 ጀምረው ላስታ አውራጃ ግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ላይ ጠላትን ድባቅ መተዋል።
#ዙ23_አውድመዋል ሶስት ሙሉ መኪና ወድሟል ሚኒሻ ጸድቷል ድሉን የላስታ ጀነራል አሳመነው ጽጌ ልጆች ተጎናጽፈዋል፣ የምርኮኛው የብርሃኑ ጁላ ልጆች #የምድር_ድሮኖቹን መቋቋም ሲያቅተው #ይልማ መርዳሳ ሽፋን ሰጭነት #በድሮን የታገዘ ውጊያ እያደረገ ይገኛል።

ከዚህም በተጨማሪ ከደሴ በቅርብ እርቀት ላይ የምትገኜው
#ኩታበር ከተማ ላይ ከባድ ትንቅንቅ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️

21/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Nov, 08:21


🔥#ሰበር_ዜና!

በዳውንት ወረዳ ገበያ ገብይተው ሲመለሱ በነበሩ  ንፁኋኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት መገደላቸው ታወቀ!

በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ህዳር 19/2017 ዓ/ም ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ በነበሩ ንፁኋን ወገኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸው ማለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በወረዳው ሰጎራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን፣ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ በርካቶች ቆስለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸውን ነው የመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል የአይን እማኞችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።

ጥቃቱ የተፈፀመው ለደላንታ ወረዳ አዋሳኝ በሆነችው ልዩ ስሟ ሾጋ ተብላ በምትጠራ ቀበሌ ሀሙሲት ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች ላይ ነው ብለዋል ጣቢያችን ያነጋገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል  የሸቀጣሸቀጥ ነጋዴዎች፣ ገበያ ለመገብየት የመጡ እናቶችን ጨምሮ አርሶ አደሮችና መምህራን እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑት ወዲያውኑ ነው ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል።

ህዳር 20/2016 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ ላይ በተፈፀመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወላድ እናቶች አምቡላንስ አሽከርካሪን ጨምሮ ሌሎች አምስት የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች መገደላቸው ይታወሳል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ ተሽከርካሪ አምቡላንሱ እና በተሽከርካሪው ላይ ተጭኖ የነበረ መድሃኒት ሙሉ በሙሉ መውደሙ የሚታወቅ ሲሆን፡ በተመሣሣይ በዓመቱ ከዚኸው ቀጠና በቅርብ ርቀት በንፁኋኖች ላይ ከፍተኛ እልቂት ያደረሰ ጥቃት ነው የተፈፀመው።

የአማራ ፋኖ በወሎ
ድል አለማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

21/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Nov, 18:58


ብልፅግና ከስሯል ስልህ በምክንያት ነው!  አለም ወደ ጀግናው የአማራ ፋኖ እየመጣች ነው። ቦታውን መጥቀስ የማልፈልገው ቦታ ላይ እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሳይመን ቬራ ውብ ጊዜን አብሮን አሳልፏል።የምርኮኛ አያያዛችንን ከቦታው ተገኝቶ በአይኑም በካሜራውና በድምፀ መቅረፁ ተመልክቷል።የአሸባሪው ብልፅግና ድሮኖች በንፁሀንን እና በተቋማት ላይ ያደረሱትን ጉዳት በቦታው ተገኝቶ አይቶ ታዝቧል።እኔም ከመሪዎቸ ጋር የሚያደርጋትን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በካሜራየ ከተብኩ።ከምርኮኞች ጋር የነበረውን ቆይታ በፎቶ ላስቃኛችሁ።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Nov, 12:11


🔥#አስቸኳይ_መረጃ‼️

ዛሬ ማለትም 20/03/2017 ዓ ም ከሰሜን ሸዋ  ደብረ ብርሃን ከየወረዳው የታፈኑ ወጣቶች  ከ60 በላይ አውቶብስ ተጭነው ወደ ብርሸለቆ ማሰልጠኛ በዙ 23 እና መሰል ከባድ መሳሪያ ታጅበው እየሄዱ ነው።
በለሚ መስመር ቅርብ ያላችሁ ፋኖዎች ልጆችን ነፃ ታወጡ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል‼️

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Nov, 10:42


🔥#ደንበጫ_የጠላት_መቅጫ‼️
~

፲፩ኛው ቀን የተጋድሎ ውሎ
~

በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሳምንት አለፈው ያለማቋረጥ ውጊያ ማድረግ ከጀመረ!!
ይህም ሆኖ ግን ጠላት እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው።
አስራ አንድ ቀን ሙሉ የእጅ በእጅ ውጊያ ሲያደርግ የነበረው የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ትናንት ምሽት እስከ አንድ ሰዓት ድረስ ሲፋለሙት አምሽተው ጠላት በየጫካው ከተበተነ በኃላ ለአይን ሲነሳ ፋኖ ከምሽጉ ወጥቶ ቦታውን ሲይዝ ጠላት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈረጠጠ።

ዙ23 ካልመጣና ሽፋን ካልተሰጠን ተከበናል አድኑን ያለው የወንበዴው ቡድን ከየጨረቃ ተነስቶ አንድ ዙ 23 አስከትሎ የተመታበትን ኃይሉን ሊያወጣ ቢመጣም ያሰበው አልተሳካለትም!!!

ዙ-23 የተበተነን ጦር ማስለቀቅ አይችልም።ይህንም በተግባር ደንበጫ ላይ አይተናል።

አንድ ጀግና ከእነ ጓዶቹ ጋር በጨለማ ተስቦ ዙ 23ቱን ዶግ አመድ አርጎ ሹፌርና ረዳቱንም እስከወዲያኛው አሰናበታቸው።

ጠላት ተደናግጦ ዙ-23 ሲቃጠል እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ፈረጠጠ።ቀኑን ሙሉ ሲመታ የዋለው ኃይልም ከተበታተነበት ተለቃቅሞ የያዘውን ሸንሸል ተተኳሽ ሁሉ በየቦታው እየጣለ ራሱን ለማዳን ፈረጠጠ።
እጅግ ብዛት ያለው ተተኳሽና የቡድን መሳሪያ ከአነ ሸንሸሉ ተተኳሹን ጥሎ ፈረጠጠ።
ተመቶ የተቃጠለው ዙ 23 ከጥቅም ውጭ ሆኖ እየጎተተ ይዞት ተመልሷል።

#በሺ አለቃ ይርሳው ደምስ የሚመራው የደንበጫ ፋኖ ግን #ምድራዊ_ድሮን በመባል ቢጠራ ያንስበታል ይሆን? እረ አያንስበትም አስራ አንድ ቀን ሁሉ ባደረገው ውጊያ  ኮለኔሎችን፤ሻለቃዎችን፣
ሻምበሎችን፣ኮማንደሮችን ሁሉ ደምስሷል።

በርካታ ተተኳሾችንም ለመማረክ ችሏል።
ታሪክ በእጃቸው መስራት ልማዳቸው የሆኑት የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ዛሬ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው እይዘዋለሁ ያለውን ቦታም ሳያየው አብዛኛውን ደምስሰው የተረፈውን መልሰው  ልከውታል።

በየመንገዱ እየፈረጠጠ ሳለ የቆሰለበትን እየረሸነ ይጓዝ ነበር።ሬሳውንም የሚያነሳበት መኪና ስላልነበረው በየቦታው  ወድቆ ቀርቷል።
ድል በድል የሆነው የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድን አስራ አንድ ቀን ተዋግቶ ዛሬም ሌላ ስራ ላይ ነው።

ይሔ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ግን ምን አይነት ብርጌዶችን ነው በውስጡ የሰበሰበው አለኝ አንድ ወዳጄ በውስጥ መስመር መጥቶ?

አይ ወንድሜ ታቃለህ ያኔ መስከረም 21/01/2016 ዓም ከተመሰረቱት ክፍለ ጦሮች ከተመሰረተበት ቀን አንስቶ ያለምንም ማመንታት ራሱን በብዙ ነገር ሲያደራጅ የነበረ ክፍለ ጦር በኃላም ጥር ሶስት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የውስጥ አደረጃጀቶችን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በመርህ የሚሰራ ጦር ለመገንባት ቃል ገብቶ ወደ ስራ ከገቡት ጠንካራ ክፍለ ጦር አንዱ ነው።

በዚህ ደግሞ ከፊት ያሉት መሪዎች እንደ ወርቅ በእሳት የተፈተኑ የረዥም ጊዜ የትግል ልምድ ያላቸው ጀግና መሪዎች ያሉበት ዳሩ ግን በጀግንነታቸው ልክ ስራቸውን ለአዓለም ያልታወቀላቸው በስራ ብቻ የሚታወቁ
#ዝምኛ ገዳይ የሚባሉ አናብስቶች የበዙበት ስለሆነ በስሩ ያሉ ብርጌዶችንም እንዲሁ መንፈሰ ጠንካራ ናቸው ስለው በደስታ ወደቀ።
ገና ታሪክ በክንዳችን እና በፈጣሪ እረዳትነት እንሰራለን።ይሔ ክፍለ ጦር ታምረኛ ነው።የአራት ኪሎው ባንዳ አጥብቆ ከሚፈራቸው ክፍለ ጦሮች ግንባር ቀደሙ ነው ማለት እችላለሁ።

ደብረ ማርቆስ ላይ ወሽቆ የሚገኘው የካድሬ ስብስብ ሲተኛም ሲነሳም ሲበላም ሲራመድም በአዕምሮው የሚመጣበት የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ነው።
በዚህ ክፍለ ጦር ውስጥ ስድስት ብርጌዶች አሉ።ሁሉም ግን እጅን በአፍ የሚያስጭን ታሪክ በየቀኑ ይሰራሉ።ፈክረው ገብተው ያሰቡትን ጀብድ የሚፈፅሙ የድንቅ ብርጌዶች ስብስብ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር።

ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድን አለማድነቅ ማለት የአማራን ትግል እንዳለመደገፍ ይቆጠራል።
ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌዶችን አመስግኑልኝ!!!

አዲስ አብዮት፣አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ

በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

#ላንጨርስ_አልጀመርነውም
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Nov, 07:43


🔥#የምልምል_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️

#ሰቆጣ
ሰሞኑን በሰቆጣ ከተማ ለበርካታ ቀናት የምልምል ምዝገባ ተደርጓልተ። በአሁን  ሰዓት በርካታ  ምልምል ሠልጣኞችን ወደ ማሰልጠኛ ለመወሰድ አንድ ቦታ ላይ ተሰብስበዋል። ይህ ሀይል የሚንሳቀስበት ከሰቆጣ ሦስት መንገዶች ያሉ ሲሆን እነሱም
👉 ከሰቆጣ ኮረም አላማጣ ወደ ቆቦ
👉ከሰቆጣ ከተማ ላሊበላ ወደ ባህር ዳር
👉ከሰቆጣ ደሃና እብናት ወደ ባህርዳረ

ዛሬ ወይ ነገ ይጓዛሉ በዙርያው ያሉ ፋኖዎች መረጃው ይዳረስ‼️

#ባህርዳር

ባህርዳር ከተማ አመዶ አካባቢ  ያለው ፖሊስ ጣቢያው እስቴድየሙ ፊትለፊት  4 የህዝብ ቅጥቅጥ መኪና ወጣት በአሁኑ ሰዓት እየተጫኑ ነው‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

29 Nov, 05:23


አስቸኳይ መረጃ‼️


መነሻውን ባህር ዳር መኮድ ያደረገ የአራዊት ሠራዊት ሎጅስቲክ ወደ ጎንደር አሁን አቅንቷል።

✍️ከ100 በላይ ተሳቢዎች ሬሽንና ተተኳሽ ጭነዋል። በዚህ ጉዟቸው አዲስ ባስ የከተማ አውቶቢስ አብሮ ሔዷል በዚህ ስዓት ዘንዘልማ ይደርሳሉ።

✍️አንድ ዙ-23 አጅቧቸዋል፣ የተወሰኑ መኪኖች ከፊት አራዊቱን የያዙ አሉ።
መረጃው በፍጥነት ይድረስ።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Nov, 11:52


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለጦር የባህርዳር ብርጌድ እና የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በጋራ ጥምረት በመፍጠር ጠላት ከአዴት ወደ ክልልት ሰራዊት ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እንዳለ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ገዥ ቦታወችን በመቆጣጠር ምንም እንኳን መንግስት ነኝ የሚለው አካል ፋኖ እጅ እየሰጠነው እያለ ቢነዛም እኛ በተቃራኒው እጅ እንዲሰጡ በየቀኑ  የማጥቃት ስራችን እየሰራን እንገኛለን።

በዛሬው እለት በቀን 19-03-2017ዓ.ም
በየትኛው አቅጣጫ ቢሆን ባህርዳር ብርጌድ ጠላት ባለበት አቅጣጫ በመንቀሳቀስ ከሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ጋር ጥምረት በመፍጠር አይበገሬወች የደጉ በላይ ሻለቃ እና የአሳምነው ሻለቃ ጨጨ በር ጎንጅ መገንጠያ፣ ደጋፊት ተራራ ከጠዋቱ ከ12 ጀምሮ ለ5 ሰዓት ያህል ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ 47 የጠላት ኃይል የተደመሠሠ ሲሆን አንድ ኦባማ የጠላት ሰራዊት እንደያዘ  ክልልት ጮጮበር መገንጠያ ላይ በደፈጣ እና በከባድ መሳሪያ የተመታ ሲሆን መኪናው ላይ የነበሩትን በርካቶች ቁስለኛ ሁነዋል። በተሽከርካሪው ላይም ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ ተችሏል ሲሉ የባህርዳር ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ ሐብታሙ የሡፍና የአንሙት ያዛቸው ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ አማረ ጌታቸው  ገልጸዋል።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Nov, 11:03


ሰላም ውድ ቤተሰቦች አገዛዙ ከ 11 ሺ በላይ ተከታይ የነበረውን የፌስቡክ ገፅ አዘግቶብኛል በዚህ መጥቻለሁ 🔥🔥አማራ ስትሆን በህይወት እንድትኖር አይፈቀድልህም፣የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንዳትሆን ትደረጋለህ።በአጠቃላይ ስለ አማራ ህዝብ ድምፅ መሆን ወንጀል ነው።እኔም እላለሁ ስለ አማራ ህዝብ ድምፅ ለመሆን ሰው መሆን በቂ ነው።👇👇👇👇አዲሱ #የፌስቡክ ገፅ

https://www.facebook.com/profile.php?id=61569062925374

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Nov, 09:28


🔥#አስቸኳይ_መረጃ_ጨጨሆ‼️
.
አሁን በዚህ ስአት ከንፋስ መውጫ ወደ ጨጨሆ የጠላት ሀይል በሰልፍ እየሄደ ነው እዛ ላሉ ፋኖዎች መረጃዉን  አድርሱ አስቸኳይ ነው።ሊቀመንበሩ ነው ከፊት እየመራ ያለው በግምት እሰከ 100  ይሆናሉ‼️


#ሼርርርርር ይደረግ

#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

19/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Nov, 08:19


🔥#11ኛ_ቀን_የያዘው_ውጊያ_በደምበጫ‼️

የደምበጫ ፋኖ (የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛ ክ/ጦር እንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ) ለተከታታይ 11 ቀን ያለ ዕረፍት እየተዎጋ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የደምበጫ ክፍል ቆላማው ክፍል ላይ ዎየምን አቦ ቀጠና
#የጨበጣ_ውጊያ እየተደረገ ይገኛል። በዚህ 11ኛ ቀኑን በያዘው በርካታ ድሎችን እያስመዘገበው ያለውን እንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ምት መቋቋም ያልቻለው የሽብር ቡድን ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ በመሆን ደምበጫ ወረዳን #በመድፍ እየደበደበ ሲሆን ምንም ውጊያ በሌለበት ቀጠና #ዎድ ላይ ቤቶችን አውድሟል፣ንፁሀኖች ተጎድተዎል፣ እንስሳቶች ተገድለዎል ሲሉ ለንስር አማራ ገልፀዎል‼️

#ደምበጫ_የጠላት_መቅጫ_ወጥር💪


#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

19/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

28 Nov, 05:21


ሰበር- ዜና

የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ በአገዛዙ  ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት አባላት ላይ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ አንድ ሻለቃ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ።

የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ሻለቃ ቢራራ እንደገለፁት  ዛሬ ሕዳር 18/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት በርካታ ወጣቶችን ከስማዳ ወረዳ አፍሶ እስቴ ላለው ሃይል ካስረከበ በኋላ የእስቴው ሃይል የታፈኑትን ወጣቶች ተቀብሎ በሚመጣበት ሰአት የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ  ከበባ በማድረግ በአገዛዙ እግረኛ ሰራዊት ላይ በወሰደው  መብረቃዊ ጥቃት አንድ ሻለቃ ጦር ሙሉ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት መደምሰስ መቻሉን አስታውቀዋል።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

21 Nov, 18:32


🔥#እጅ_የሰጡ_ህይወታቸው_ተርፏል‼️
 
#ስናን💪

ስናን አባጅሜ ብርጌድ ዛሬ ህዳር 12 በጠሗቱ ታሪክ ሰራ!!
በአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛ ክፍለጦር ስናን አባጅሜ ብርጌድ ታሪካዊ ገድል ሰራ!!ከመዲናዋ ረ/ገበያ ተነስቶ የጮቄን ሰንሰለታማ ተራራ ለመያዝ ከሌሊቱ 10:00 የተነሳዉ የብርሃኑ ጁላን ጦር በአናብስቶች ስናን ሲወቃ ዉሏል!!

    የተገኘ ድል:-
1:- ከ30 በላይ ሙት
2:- 8 የአብይ ወታደር የተማረከ
3:-  ከ20 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ
4:- ሶስት ብሬን
5:- ከ120 በላይ የክላሽ ጥይት
6:- 2 ካዘና የዲሽቃ ጥይት
7:- 1 የብሬን ሸንሸል
8:-  18 የወታደር ቦርሳ እንዲሁም ለቁጥር የሚያታክት ሬሽን በአናብስቶች የስናን አባጅሜ ብርጌድ  እጅ ገቢ ሆኗል!!

ከፊሉ በፎቶ ተገልጿል💪

#እጅ_በመስጠት ህይዎታችሁን እንድታድኑ ጥሪ እናስተላልፋለን‼️


✍️ ንስር አማራ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

21 Nov, 11:38


🔥#የድሮን_ጥቃት_ወሎ‼️

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ጭንጓ ቀበሌና ዶሽት ቀበሌ በዛሬው ዕለት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት በዘፈቀደ በመጣል በትምርት ቤትና በግለሠብ ቤት ላይ ውድመት አድርሷል።የፋኖ አባላት ንአገኛለሁ በሚል በዘፈቀደ የሚተኮስ የድሮን ጥቃት ንጹሃንን ከመጨፍጨፍ የዘለለ ምንም አይነት የተለየ ነገር የሚያመጣው የለም ከድሮን ጥቃት በተጨማሪ ተደጋጋሚ የሞርታርና የሌሎች ከባድ መሣሪያ ቅንቡላዎችን ወደ ንጹሃን እየተኮሰ ይገኛል ሲሉ የአማራ ፋኖ በወሎ አምሃራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ ሰይድ ከንስር አማራ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዎል‼️

©መቅደላ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ


#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

12/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

21 Nov, 10:57


የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታፍታሄ ንጉሴ ክ/ር  ስናን አባጅሜ ብርጌድ በዛሬው ዕለት ዕለህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አድርጎ በምርኮ ገቢ ያደረጋቸው መሳርያዎች
17 ክላሽ
3 ብሬን
1 ስናይፐር
6 የሰዉ ምርኮኛ

ፋኖ አበባየሁ ባንተአምላክ

12/03/2017

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

20 Nov, 17:29


🔥#የድል_ዜና‼️

     የአገዛዙ ኃይል በሌሊት ኦፕሬሽን እወስዳለሁ ብሎ ፋኖ የያዘው ምሽግ ላይ ዘሎ የገባው  የሌሊት መዓት ወረደበት💪

ህዳር 10/2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ላይ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ የፋኖ አባላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም  የማታ ሞቱን ተሸክሞ ከጊና አገር ከተማ ተነስቶ ወደ ታሞ ቀበሌ ያመራው  የአገዛዙ ቡድን በጀግናው የአስማረ ዳኜ ብርጌድ የፋኖ አባላት ተቀጥቅጦ በርካታ የሞቱበትን ሳያነሳ ቁስለኛውን ብቻ ይዞ በጨለማ ፈርጥጧል ።

ፋኖዎች ይተኛሉ በሚል የጅል ግምገማ የተሸወደው የአብይ አህመድ ምስለኔ ከሌሊቱ 9:00 ላይ ሰይጣናዊ ተለዕኮ ለመፈፀም አስቦ ቢንቀሳቀስም ለአማራ ህዝብ ሲሉ ለሰከንድ እንኳን የማይተኙት የፊታውራሪ አስማረ ዳኜ ልጆች በወሰዱት ፈጣን እና መብረቃዊ ጥቃት ጠላት ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ የያዘውን ትጥቅ ለፋኖ አስረክቦ ወደ መጣበት መፈርጠጡን ለአሻራ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

                 ድል ለአማራ ፋኖ
      © የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

11/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

20 Nov, 11:06


ሰበር ዜና
አርማጭሆ

መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ አባላት እርስ በእርስ ተጋድለዋል ‼️

በዛሬዉ ዕለት መነሻቸዉን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ  ከተማ ያደረጉ የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ አባላት በቅንጅት አሰሳ በሚል ምክንያት ወደ ጅንግር ቀበሌ ለመግባት በጉዞ ላይ እያሉ ባለመተማመናቸዉና ባለመግባታቸዉ ምክንያት እርስ በእርስ የተጋደሉ ሲሆን በዚህም ከ20 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 8 የሚሆኑ የሚሊሻ አባላትም ሞተዋል።

የተቀሩት የሚሊሻ አባላትም ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ወደጫካ መግባታቸዉ ተረጋግጧል‼️

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

20 Nov, 10:59


በጎጃም ቀጠና የግንባር ተጋድሎዎች ሲቀጥሉ የአገዛዙ የጥፋት ተግባራትም በትምህርት ቤቶችና መሠል ተቋማት ላይ ቀጥሏል።

በጭንባ የትምህርት ተቋማት በአገዛዙ ኃይል ሲወድሙና ሲዘረፉ አገዛዙ በቆየባቸው ጊዜያት የማህበረሰብ እንግልት ሲፈጥር እንደነበረም ተገልጿል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የቢትወደድ አያሌው መኮንን ብርጌድ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ካሳሁን አድማሱ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

20 Nov, 04:33


ሰበር ዜና -ደብረማርቆስ ከተማ ታሪክ ተሰራ
ዛሬ ሌሊት ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ፣ንስር ልዩ ኮማንዶ እና በረኸኘው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረማርቆስ ከተማ ታሪክ ሲሰሩ አድረዋል።
10/03/2017ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር!!!!

@እንጅነር እስቲበል አለሙ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

20 Nov, 02:16


የአማራ ፋኖ በጎጃም ከ19 አውደ ውጊያዎች በላይ በአንድ ጀንበር
ኮሶ በር ረቡ ገበያ ምርክታ አዲስ ቅዳም፣ ጉደር፣ አምሳልታ፣ ቲሊሊ፣ ዳንግላ፣ ጃዊ፣ አዞሬ፣ ሉባ ቢሮ፣ ሀሙስ ገበያ(አረፋ)፣ ድግድግ፣ደንበጫ፣እምቡሊ፣ፈንድቃ፣እነሞጨራ፣አመሻና ቀኘ አቦ እና የቦቅላ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች ናቸው ።

የጎጃም አገው ምድር(3ኛ) ክፍለ ጦር በስሩ ያሉትን ብርጌዶች በማስተባበር የጠላትን ኃይል ጠላት ባለበት ሁሉ ቦታ በመክበብ መምታት ተችሏል። ክፍለ ጦሩ በቅንጅት እንጅባራ ከተማ ላይ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ እንጅባራና አካባቢው ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፋግታ ለኮማ ወረዳ ፣ጊዮን ብርጌድ ሰከላ
ዘንገና ብርጌድ ቲሊሊና አካባቢው በጥምረት እንጅባራ ከተማ ላይ ያለውን ጠላት እጅግ ከባድ ምት ሲፈጽምበት ውሏል።

በጎጃም አገው ምድር(3ኛ) ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ወደ ፋግታ ከተማ መጥቶ የነበረውን ጠላት ጉደር አምሳልታ ላይ እንዲሁም ጠላት ወደ ፋኖ ሲመጣ ፋኖ ወደ ጠላት ቀጠና በመሄድ አዲስ ቅዳም ላይ ጠላትን ሲቀጠቅጠው ውሏል።
፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ በሶስቱም ቦታ ላይ ባደረገው ውጊያ ከ50 በለይ የጠላት ኃይልን መደምሰስ ችሏል።

የጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ዘንገና ብርጌድ ቲሊሊ ከተማ ላይ የነበረን የጠላት ኃይል በርካታውን በመደምሰስ ጠላትን አባሮ አሁን ላይ ቲሊሊ ከተማን ከጠላት ነጻ ማድረግ ችሏል። የ4ኛ ጃዊ ክፍለ ጦር የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር 7 ልጆችን ጃዊ ከተማ በማስገባት በጠላት ላይ ባደረሱት ጥቃት 9 ሙትና 3 ቁስለኛ ተደርጓል።

የ2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ ቢቡኝ ወረዳ ከዲጎ ፂዮን 2 ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ በሚገኘው አዞሬ ሉባ ቢሮ ወይም እግዜር አብ ከሚባል ቦታ ላይ የብርሃኑ ጁላን ጦር መግጠም ተችሏል።

2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ ከወይን ውሃ ወጥቶ ወደ አረፋ ሀሙስ ገበያ ሲንቀሳቀስ የነበረን የብርሃኑ ጁላን ፈርጣጭ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገው ከሞት የተረፈውን በመጣበት እግሩ መልሰው ሰደውታል።

የ9ኛ የሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር መዝገበ ጮቄ ብርጌድ ሰዴ ወረዳ ድግድግ ከሚባል ጫካ ላይ በመያዝ 28 ሙት 16 ቁስለኛ በድምሩ 34 የጠላት ኃይልን የፋኖን ጥይት ግተውታል። የ6ኛ(ቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ደንበጫ በላይ ዘለቀ ብርጌድ(ማቻከል) ከአቻ ጓዳቸው ከ2ኛ ክፍለ ጦሩ ደጋ ዳሞት ብርጌድ ጋር በጥምረት ደንበጫ ከተማ ላይ ያለውን የ25ኛና 75 ክፍለ ጦር የጠላት ኃይልን ሲቀጠቅጡት ውለዋል።በርካታ የጠላት ኃይልን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።16 የጠላት ኃይል 3 ክላሸንኮቭ መሳሪያ ተማርኳል። ትናንት ዳባ ላይ በነበረው ውጊያ ብቻ ከ162 በላይ የጠላት ኃይል ተደምሷል። የ6ኛ(ቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር በላይ ዘለቀ ብርጌድ (ማቻከል ወረዳ) እምቡሉና ፈንድቃ ውጊያ ተደርጓል ።

የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር የክፍለ ጦሩ ልዩ ኮማንዶ (ጥቁር አንበሳ) የቦቅላ አባይ ብርጌድ (ጎዛምን ወረዳ)መብረቁ ብርጌድ አዋበል ወረዳ)- እነሞጨራ ሻለቃ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ከትናንት የቀጠለውን ውጊያ የቦቅላ ቀኝ አቦ፣እነሞጨራ፣ አመሻ ላይ ጠላትን መውጫ መግቢያ በማሳጣት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ውለዋል። በርካታ የጠላት ኃይልን መደምሰስ ችለዋል።

    በዚህ የተበሳጨው የጠላት ኃይል የቁጣው መወጫ የሆነውን ንጹሃንን ሲጨፈጭፍ ውሏል። 7 ንጹሃንን ገድሏል።
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት
  የ2ኛ ክፍለ ጦር
  የ3ኛ ክፍለ ጦር
   የ4ኛ ክፍለ ጦር
    የ6ኛ ክፍለ ጦር
     7ኛ ክፍለ ጦር
    የ9ኛ ክፍለ ጦር

በ19 ቦታዎች ላይ ጠላትን ሲደመስሱት ውለዋል።

Amhara Fanno In Gojjam

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

19 Nov, 11:44


🔥#የድሮን_ጥቃት_ደምበጫ‼️

ነበልባሉ ፋኖ ደምበጫ ላይ አስደማሚ ስራ እየሰራ እንደሆነ እና የድሮን ቅኝት እንዳለ መዘገባችን ይታወቃል። ውጊያው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አናብስቱ ፋኖ 1 #ዙ23 መሳሪያቸውን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ያደረጉት ሲሆን አንደኛው ዙ23 መጠነኛ ጉዳት አስተናግዶ አምልጧል። ፋኖ እየገሰገሰ ሲሆን በዚህ የተደናገጠው ይልማ መርዳሳ ደምበጫ ላይ #3 ጊዜ #የድሮን_ጥቃት ፈፅሟል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዎል‼️

10/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

19 Nov, 09:25


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ተኛ አገው ምድር ክፍለጦር ፲ አለቃ ኤፍሬፍ አጥፉ ብርጌድ አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ አዲስ ቅዳም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በዚህ አውደ ውጊያ ከ20 የማያንስ መከላከያ ተማርከዋል፣ ከሙትና ከመማረክ የተረፈው የብልጽግና ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሚኒሻ እና መከላከያ ተብዬው ወደ ኮሶበር ፈርጥጧል።

በዝርዝር መረጃዎች እንመለሳለን!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

19 Nov, 07:25


🔥#ደምበጫ‼️

ደምበጫ ትናት የጀመረው ውጊያ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ተጠናክሮ ቀጥሏል💪 ስቦ መምታትና፣ስቦ ማስከዳት በሚለው መርህ መሰረት ከደምበጫ ወደ ኪስ ቀጠና ዳባ በርካታ ሀይል ስቦ በመውሰድ ትናት ሲለበልቡት አምሽተው የተረፈውን ከበው በማሳደር ትራፊውን ውሰዱ በሚል መልዕክት ከ100 በላይ እግረኛ በድጋሚ ስበው ወስደዎል💪

በማመንመን የጠላትን እስትንፋስ
#ሲጥ ማድረግ በሚለው መርህ መሰረት ከተማ ላይ የቀረውን ሀይል ደግሞ አናብስቱ  ከተማ በመግባት #እየለበለበው ይገኛል💪

ይህ ውጊያ አስደማሚ ጀብድ፣ቅንጅትና መናበብ የተሰራበት ውጊያ ነው በአሁኑ ሰዓት
#ደምበጫ ከተማ በከበባድ መሳሪያዎች ተኩስ እየተናጠች ሲሆን ይልማ መርዳሳም ሽፋን ለመስጠት #ድሮን ልኳል ህዝቡ እና አናብስቱ በጥንቃቄ ይንቀሳቀስ ሲሉ ነበልባሎች ለንስር አማራ ገልፀዎል ‼️

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

19 Nov, 06:24


🔥#የድል_መረጃ_ጎንደር‼️

መነሻውን ከአለፋ ወረዳ አፀደ ማርያም ከተማ በማድረግ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሃይል ላይ በተደረገው ጥቃት አስደናቂ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ፋኖ በጎንደር የአድዋ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ተስፋ ጌታሁን ገለፀ።

በአርበኛ ሳሙኤል ባለድል የሚመራው የአድዋ ክፍለጦር በቀጠናው በስፋት በመንቀሳቀስ እየወሰደ ባለው የመልሶ ማጥቃት ኦፕሬሽን የጠላትን አከርካሪ መምታቱ ተነግሯል።

በዚህም በዛሬው ትናንትናው የአገዛዙ ሃይል በቀጠናው በምትገኘው አፀደ ማርያም ከተማ ተነስቶ በመንቀሳቀስ የንጋት ጮራ ብርጌድ ሻለቃ አንድን ለማፈን ሙከራ ቢያደርግም የአፀፋ ምላሽ በማድረግ ዋጋውን ሰጥተውታል ብሏል ቃል አቀባዩ::

©️ ሞገሴ ሽፈራው

#እናሸንፋለን 💪💪
#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

10/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

18 Nov, 20:08


የብልፅግና ሰራዊት ምልመላ እቅድና አፈፃፅም አማራ ክልል!!!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

18 Nov, 18:10


9 አውደ ውጊያ በአንድ ቀን የአማራ ፋኖ በጎጃም
=================================
ህዳር 9/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም
     ረቡዕ ገበያ፣ምርክታ፣ደንበጫ ከተማ፣ዳባ፣ቀኝ አቦ፣እነጋትራ፣አጋምና፣የሺሚት፣የሰንበት ላይ ከባድ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል።

√#ረቡዕ ገበያና #ምርከታ ላይ የ3ኛ( ጎጃም አገው ምድር)ክፍለ ጦር ለ2 ቀን ያክል ጠላትን ሲቀጠቅጠው ውሏል።
   የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር
       #ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ(እንጅባራና አካባቢው)
       #ዘንገና ብርጌድ (ቲሊሊና አካባቢው)
       #ጊዮን ብርጌድ (ሰከላና አካባቢው)
       #፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ (ፋግታ ለኮማና አካባቢው)
በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ ቁጥሩ ያልታወቀ የብርሃኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
√ #ደንበጫ ከተማ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክ/ጦር #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ 2 ሻለቃ ጦር በማስገባት ጠላትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ደንበጫ ከተማን ለረጅም ሰዓት መቆጣጠር ችሏል።

√#ዳባ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር
      #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ
       #በላይ ዘለቀ ብርጌድ እንዲሁም
     #ከ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ) ክፍለ ጦር #መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ
  በጥምረት ባደረጉት ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።ከሞት የተረፈው የጠላት ኃይል እስከምሽት ድረስ ሙትና ቁለኛውን እያነሳ ይገኛል።

√#ቀኝ አቦ(ቢሮ) ከሚባል ቦታ ላይ የ6ኛ(ቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር #ንጉስ ተ/ሃይማኖት ብርጌድ ና ከ7ኛ(ሐዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #የየቦቅላ አባይ ብርጌድ በጥምረት የአብይን ገዳይ ቡድን ከደብረ ዘይት ተነስቶ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ እያደረገ እያለ በከበባ ሲቀጠቀጥ ውሏል።በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።

በዛሬው እለት ከአምስት አቅጣጫ (ከደ/ማርቆስ፣ከሉማሜ፣ከአምበር፣ከደብረ ዘይት) ብዙ ቁጥር ያለው የአብይ ጭፍራ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ ያደረገው የጠላት ኃይል በጀግኖቹ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ተቀጥቅጦ ያሰበውን ሳያሳካ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ተመልሷል።

√#እነጋትራ ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #መብረቁ ብርጌድ 2ኛና 3ኛ ሻለቆች ጠላትን በደፈጣ በመያዝ እያባረሩ ሲረፈርፉት ውለዋል።

√#የሻሚትና #አጋምና ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #ደባይ ጮቄ ብርጌድ ወደ ቀኝ አቦ በመሄድ ላይ የነበረን ጠላት ከበባ ውስጥ በማስገባት ሲለበልበው ውሏል።

√#የሰንበት ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር
       #የቦቅላ አባይ ብርጌድና
       #መብረቁ ብርጌድ
በጥምረት የብርሃኑ ጁላን ጨፍጫፊ ቡድን እያባረሩ ሲደመስሱት ውለዋል።
ሲጠቃለል እጅግ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

   የአብይ ገዳይ ቡድን እንደተለመደው የንጹኃን ግድያ፣የንብረት ውድመት፣የአርሶሩን ሰብል በከባድ መሳሪያ ሲያቃጥል ውሏል።የየሰንበት 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን ንብረት በሙሉ ጭኖ ወስዶታል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

ዮሐንስ አለማየሁ (የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ቃል አቀባይ)

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

18 Nov, 17:37


🔥#የድል_ዜና‼️
=======
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ የሚገኙት ሶስቱ ብርጌዶች ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ይገኛሉ።
፩, የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ ~~~በቀኝ አቦ
፪, ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ~~~በደንበጫና በዳባ
፫, በላይ ዘለቀ ብርጌድ~~~ በደንበጫና በዳባ

ታሪክ መስራት ልማዱ የሆነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም እንደ ትናንቱ  ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ውለዋል።ለአስራ ሁለት ሰዓት ቀጥሎ የዋለው ውጊያ እጅን በአፍ የሚያስጭን ገድል አሁንም ድረስ እየሰራ ነው።

ጠላት ወሽቆበት ከነበረው የደብረዘይት ቀበሌ ተነስቶ የንጉስ ተክለሐይማኖት ፋኖ ይገኝበታል ያለውን ቀኝ አቦን ለመያዝ በጡሀቱ ቢንቀሳቀስም እንደ ተርብ የሚናደፉት የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድና የየቦቅላ አባይ ብርጌድ ፋኖዎች የብርሐኑን አራዊት ሰራዊት ጦር ዶግ አመድ ሲያረጉት ከደብረ ማርቆስ በመነሳት ፔንፔ እና ዙ-23በመያዝ የተከበበውን ኃይሉን ለማሰለቀቅ ከአራት መቶ በላይ ኃይሉን ጭኖ በመግባት ቢያስለቅቀውም፤ አሁን በዚህ ሰዓት ከየሰንበት፣ከቁይ፣ከደብረ ማርቆስ እንዲሁም ከፋኖ ቅጥቀጣ ያመለጠው ኃይል የቦቅላ ላይ ተሰብስቦ ተከማችቷል።

ይሁንምና ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ እና ከሀዲስ አለማየሁ ፯ኛ ክፍለ ጦር  የየቦቅላ አባይ ብርጌድ፣የተድላ ጓሎ ብርጌድ፣ተከቦ ጠላት መውጫ መግቢያ አጥቶ የተፈጠረበትን ቀን እየረገመ ይገኛል።

በደንበጫ ወረዳ እየተካሔደ ባለው ውጊያ ደንበጫ ከተማ እና ዳባ ላይም ጠላት ባደረገው እንቅስቃሴ ጠላት እንደ ቅጠል እስካሁኑ ሰዓት ድረስ እየረገፈ ነው።

በዳባ ላይ በሚደረገው ውጊያ ከቢቡኝ ወረዳ የኮረብታ ፋኖ እንዲሁም ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር በላይ ዘለቀ ብርጌድ እንዲሁም የደንበጫ ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረጉ ይገኛሉ።ቀኑን ሙሉ በቀጠለው ውጊያ ጠላት ሬሳውን እና ቁስለኛውን ማንሳት አልችል ብሎ እየፈረጠጠ ይገኛል።
ደንበጫ ከተማንም ከፊሉ ፋኖ ተቆጣጥሮ ከጠላት ጋር እየተፋለመ ነው።
ብርሐኑ ጁላ በባህርዳር ከተማ ተገኝቶ የተሸለመው ካባ አዲስ አበባ ሳይደርስ እንዲሁም ያቀደውን እቅድ ለነፍስ አባቱ አብይ ሳይነግረው ያሰማራው ጦር እግር በእግር እየተመታና እየተሸነፈ ነው።
ዝርዝር መረጃዎችን በነገው እለት እንቀጥላለን----------//
አዲስ አብዮት ፣አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ

በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

#እናሸንፋለን 💪💪
#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

9/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

18 Nov, 12:27


የድሮን ጥቃት በአማራ ሳይንት ተፈፀመ ።

ዛሬም ማለትም ህዳር 9 ረፋዱ አካባቢ ሽንፈቱን ማመን የተሳነው የአገዛዙ ሰራዊት በአማራ ሳይንት ወረዳ ዋሮ  ሺዎት ቀበሌ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል::
የተጎዳ ሰው ባይኖርም የግለሰብ ቤት ሙሉ በሙሉ አዉድሟል::

ድል ለአማራ
ፋኖ ድል ለጭቁን አማራ ሕዝብ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

18 Nov, 04:03


#ሰላም
በሰሜን አቸፈር ወረዳ ጭምባ የምትባል ከተማ ላይ መሽጎ የነበረው ሰው በላ ሰራዊት በ 07 03 2017 ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት እቃቸውን ሸክፈው ቁንዝላ ወደ ሚባል ቦታ ሂደዋል ቦታውን ሲለቁ አንድ highschool ትምህርት ሙሉ በሙሉ አውድመውት ሂደዋል አላማቸው ትውልድን ማጥፋት እንደሆነ አሳይተውናል

via inbox

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

17 Nov, 17:24


~ የአማራ ትግል ያሸንፋል!

በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጡት የሕልውና እንዲሁም የፍትሕ ርትዕ ጥቃቶች የአማራን ሕዝብ አሳምነው አስነስተዋል።

በጥቃቶቹ እውንነትና በጉዳቶቹ የተመረረ ሕዝብ ለአመታት ያደረገውን  "አታጥቁን" ጥሪና ሰልፍ አጥቂዎቹና አስጠቂዎቹ ሲቀልዱበት ፣ ሲያሳንሱትና ሲያመካኙበት ኖረዋል።

ያ ሕዝብ አሁን ከላይ እስከታች፣ ከሩቅ እስከቅርብ ተነስቷል። ይሔንን አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፎች "በቃ" ሲል እንደነበረው ብረት አንስቶ "በቃኝ" ብሏል።

ስለሆነም ድል ያደርጋል!

➡️ አሳማኝና ትክክለኛ ጥቃቶችን መሠረት አድርጎ ስለተነሳ

➡️ በአመት ከመንፈቅ ልዩ አቅም የፈጠረ ፣ በሰው ኃይልና በመሣሪያ የደረጀ ሠራዊት ተገንብቷል፤

➡️ አያሌ ወታደራዊ ልምድ ያላቸውና ውጊያን በብቃት የሚመሩ አዋጊዎችና ተዋጊዎች ተሰልፈውበታል።

➡️ ውጊያዎችን አሸንፎ ያረጋገጠና የሚያሸንፍ፣ የሚዋጋበትን ምክንያት በውል ተገንዝቦ በቆራጥነት የተሰለፈ ሠራዊት ተገንብቷል።

➡️ አቅሙ እያደገ ያለ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የውጊያ፣ የስልጠና ፣ የሽምቅ ትግል ልምድ እየተገነባ ነው።

➡️ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቀባይነትና ድጋፍ ያለው ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነ ሕዝብ ተሰልፏል።

➡️ በአለም ጫፍ ሁሉ ያለ የአማራ ልጅ (ተሳትፎው ጠንካራም ይሁን ደካማ) ከትግሉ ጎን ቆሟል።

➡️ በርካታ ምሑራን (ከሁለተኛ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ባለቤት የሆኑ) የትግሉ መሪዎችና አካል ሆነዋል።

➡️ አገዛዙን በመጨረሻ ተስፋነት የድርድር ጠያቂና ተለማማጭ አድርጎታል።

➡️ በቀጠለ አገዛዛዊ በደል እየተቆጣ የትግሉ አካል የሚሆን ኃይል እየሰፋ ቀጥሏል።

➡️ አለም አቀፉ ማሕበረሠብ የፋኖን ተጋድሎ በወል እየተረዳው ነው።

ስለሆነም ፍትሐዊና ሐቀኛ ትግል አሸናፊ ነው!

አዲሱ ደረበ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

17 Nov, 16:34


📌ጥብቅ መረጃ!

ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ እና ባንዳው አረጋ ከበደ የመሩት ስብሰባ እና ግምገማ መጠናቀቁ ታውቋል። ተሰብሳቢዎች የእዝ መሪ ጀነራሎች ሲሆኑ ብርሃኑ ጁላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች በግልፅ አስቀምጧል።

1) እስከ ታህሳስ 30- 2017 አም ጦርነቱን ማጠናቀቅ ካልተቻለ መከላከያውን እናስወጣለን የሚል የውሳኔ ሃሳብ በግልፅ አስቀምጧል።

2) ማሸነፍ ያልቻልነው በአረጋ አመራሮች ምክንያት ስለሆነ አረጋ አመራርህ ላይ እርምጃ ውሰድ የሚል ጥብቅ መመሪያ ሰጧል።

3) አንድ ኮር ከወለጋ ተንቀሳቅሶ ወሎና ጎጃም እንደሚሰፍርም ውሳኔው ተነግሯቸዋል።

በመጨረሻም ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ እነ አረጋ ከበደን መንግስት ከዚህ በላይ ሊዋጋላችሁ አይችልም:: እንደ ብልፅግና ከጎናችን ቁማችሁ መታገል ካልቻላችሁ የክልሉን ስልጣን ለፋኖ አስረክቡትና ከወላዋዮች ከእናንተ ይልቅ በግልፅ አቋም ካላቸው ከእነሱ ጋር አጋር ብንሆን ይሻላል ሲል ተደምጧል።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

17 Nov, 11:15


ሰበር !!

ሁለተኛው የአማራ ፋኖ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም የሚደንቅ ግኝት ማምረቱ ተነግሯል::

በአማራ ልጆች የተፈጠረው ድንቅ መሳሪያ የመጀመሪያ ሙከራው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ሲበሰር በቅርቡ ይፋ የሚደረግ ይሆናል::

ይህ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም ከዘሪሁን 13 የጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም ተጨማሪ ሲሆን በሌላ የአማራ ቀጠና እንደሚገኝም ተገልፃል::

©️ ሞገሴ ሽፈራው

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

10 Nov, 08:53


🔥#ሰበር_ዜና‼️

የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባለሙያው ፋኖን ተቀላቀለ !

         " ጀ/ል አሳምነው ፅጌ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉን አማራን እንዲጠብቅ  ቃለ መሀላ ሲያስገባው ኤፍሬም አጥናፉ ደግሞ የአማራ ህዝብን እንድጠብቅ አሰልጥኖ ቃለ መሀላ አስገብቶኛን። በመሆኑም የልቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፕሬሽን የሚከፍለኝ 13685 ብር ደሞዝ  ከሚፈናቀለው፣ ከሚታረ*ደው፣ አርሶ እንዳይበላ ማሳው በወራሪ ታንክ ከሚነዳበት፣ ከገዛ ቀየው በድሮን ከሚጨ*ፈጨፈውና እንደ ሰው መኖር ከተነፈገው የአማራ ህዝብ አይበልጥብኝም። ደግሞም እኮ ሰው ለሆዱ አይኖርም ለአላማና ለነፃነት ጭምር እንጅ። "  የሚለው የሰሜን አቸፈሩ ግስላ ቻላቸው መንግስቱ ፋኖን ተቀላቅሏል።

         ቻላቸው መንግስቱ ደፋርና ጀግና ነው የባህር ዳርን ፋኖን እየመራ የጋሸናን ምሽግ ሲሰብሩ ቆስሎ ነበር ይታወቃል።

መልካም ትግል ጓድ !

©ይኸነው የሸበሉ


#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

1/3/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

09 Nov, 13:56


አገዛዙ ከግንባር ውጊያ ወደ ፎቶ ሾፕ ወርዷል!

ከታች በምስሉ የሚታየው የአርበኛ ዘመነ ካሴን ምስል የብልጽግና አመራሩ፣ የሚዲያ ሰራዊት በግል ፔጅ ፖስቱ ተብሎ አብዛኛው አመራር አልፖስትም ብሎ እርምጃ እንወስዳለን፤ የማትፖስቱት ፅንፈኛን ስለምትደግፉ ነው ተብሎ የግል ስልክ እየተፈተሸ ነው።

ገ*ድለነዋል ሲሉ የነበረውን ውሸታቸውን ለመሸፈን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በግንባር ያልቻላችሁትን በፎቶ ሾፕ አታሸንፉም!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

09 Nov, 03:57


ሰበር

ጎጃም አገው ምድር ዳንግላ ከተማ በልጆቿ እዬተሞሸረች ነው

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

08 Nov, 19:26


እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠንን እንዋጋለን !

እነሆ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ ለስድስት (6)ወር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ ስርዓት አስመርቋል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ጠላትን ድል እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት የምናደርገውን የህልውና ትግል በድል ለመቋጨት የሚያስችሉ ተተኪ ተዋጊዎችን እያበቃ ይገኛል።

በምርቃት ስነ ሰዓት ላይ በእንግድነት የተገኙ የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ለተመራቂዎች ቀጣይ ተልዕኮዎችንም ሰተዋል።

አርበኛ Tilahun Abeje

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

08 Nov, 15:18


የጀነራሎቹ የዕርስ በዕርስ ተኩስ በወልድያ !

የአብይ የግል ጀነራሎች የግል ተኩስ ከፍተዋል።

ትላንትና ቃሊም ላይ በተደረገ ውጊያ በርካታ ሰራዊቱ ሙትና ምርኮኛ የሆነበት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጀነራሎች እርስ በእርስ እንደገጠሙ የአይን እማኞች ገልፀዋል።

ወልድያ እንጨት ተራ አርሶ አደር ህንፃ ሆቴል በብስጭት ሲጠጡ ያደሩት ጀነራሎቹ ትናንት በደረሰባቸው ከፍተኛ ምርኮና የግንባር ሽንፈት ሲጨቃጨቁ ካደሩፐ በኋላ ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ "ሀይል ጨምርልኝ ስልህ አልጨመርክልኝም"  "ብጨምርልህም አስማርከህ ነው የምትመጣው፤ መድፍ ሳስተኩስልህ አልነበር ወይ" በሚል እርስ በእርስ ከቃል ወደ መሳርያ ተሸጋግረው እንደገጠሙ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የጀነራሎቹ ግብግብ ወደ አጃቢዎቻቸውም ወርዶ እስካሁን አምስት አጃቢዎቻቸውን እርስ በእርስ አስተኳኩሰው እንዳገዳደሉ የአይን እማኞቹ ገልፀዋል።

የዓይን እማኞች የነበረውን ሒደት ሲገልፁም ግማሾቹ እዚያው ያደሩ ሲሆን  የተወሰኑት ጄነራሎች ደግሞ ንጋት አካባቢ ወደ ሆቴሉ እንደመጡና ሆቴል ላይ ከሴት ጋር ሲያገኟቸው " እናንተ ሴት ጭን ስር ሆናችሁ ሰራዊቱ ያልቃል" በሚል ነው ጭቅጭቁ የተነሳውና ወደ መገዳደል ያመራው ሲሉ በቦታው ላይ የነበሩ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።

እርስ በእርስ መገዳደሉና የቡድን ተኩሱ ለፍተኛ ውጥረቱ ወደታችኛው ሰራዊት እየወረደ በመምጣቱ ሀራ የሚኘው የሰሜን ምስራቅ እዝ አዛዥ ጀነራል አሰፋ ቸኮል ነገሩን ለማርገብ እየከነፈ ወደ ወልድያ እያቀና እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ethio 251 media

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

07 Nov, 16:39


🔥#ሰበር_ዜና‼️

ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣዕመ በጀግኖቹ ተጋድሎ ተደመሰሰ!

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ የቃሊሙ ታላቅ ድል በዛሬው እለትም ተደግሟል::

የበላጎው ባለታሪኮች ዞብል አምባ ክፍለጦርና አሳምነው ክፍለጦር ታጠቅ ክፍለጦርን ተጠባባቂ አድርገው በጋራ በፈፀሙት ታላቅ ተጋድሎ ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው የራያ ቆቦዋ
#ቃሊም_ከተማን ለመቆጣጠር የመጣው ጠላት በጀግኖቹ በርካታ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ሆኗል::

ከበላጎ ተራራ ስር የምትገኘዉን ቃሊም ከተማ ለመቆጣጠር አስቦ የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ አዲስ ምልምል ሰራዊት በጀግኖቹ የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጆች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ 48ተኛ ክፍለጦር 5ተኛ እና 2ተኛ ሻለቆች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተደምስሰዋል:: በአዲሱ አመት 2017 አ.ም መባቻ ቃሊም ከተማና አካባቢው ላይ 48ተኛ ክፍለጦር 4ተኛ ሻለቃ በብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ክፍለጦር የጊራናው ባለሽርጡና ታጠቅ ክፍለጦር ሙሉ ለሙሉ መማረኳና መደምሰሷ የሚታወቅ ነው::

በጀኔራል አሰፋ ቸኮል የሚመራው ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ
#ኮሎኔል_ጣእመ በጀግኖቹ ተጋድሎ #የተደመሰሰ ሲሆን ሁሉም #አጃቢዎቹ_እጅ ሰጥተው ይገኛሉ::

በተጋድሎው በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ከምርኮ የተረፈዉም ፈርጥጦ ወልድያ ከተማ ገብቷል:: በርካታ ቁጥር ያለው ምርኮኛ በእጃችን ያለ ሲሆን በቀጣይ ይፋ የምናደርግም ይሆናል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦርና የአሳምነው ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነቶች ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ እና ፋኖ ንጉስ አበራ ገልፀዋል::

በምርኮ የተገኙ ድሎች

-ስናይፐርና ብሬን
-ለጊዜው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ነፍስ ወከፍ ክላሽ
-ለጊዜው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የብሬንና የክላሽ እንዲሁም የዲሽቃ ተተኳሽ

የህልዉና ተጋድሎው እስከ ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል::

©የአማራ ፋኖ በወሎ ቃል አቀባይ ፋኖ አበበ ፋንታው

#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/2/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

07 Nov, 16:25


🔥#ሰበር_ዜና_ወሎ‼️

ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣዕመ ዎርካው ምሬ ወዳጆ በሚመራው በአማራ ፋኖ በወሎ አናብስቶች ተጋድሎ ከእነ በርካታ ጦሩ
#ቃሊም ላይ ባለው ውጊያ ተደመሰሰ‼️

ፎቶው የተደመሰሰው  ኮረኔል ነው💪
#ዋርካውና_ጦሩ_ይችላሉ💪

#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/2/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

06 Nov, 18:15


#መረጃ!

የአማራ ክልል ጤና ም/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጋሹ ክንዱ የአማራ ፋኖን ተቀላቀሉ።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

05 Nov, 18:04


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ሙጃ ከተማን ተቆጣጥሮ በርካታ ድሎችን ተጎናፀፈ።

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ዛሬ ጥቅምት 26/ 2017 አ.ም ማለዳ ላይ በተጀመረ መደበኛ ዉጊያ በቀላል መስዋዕትነትና ባጭር ሰአት ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ፖሊስ ጣቢያዉንና የተለያዩ የጠላት መሰረት የሆኑ ቦታዎችን ሰብሮ በመግባት በርካታ ድሎችን ተጎናጽፏል።

የጠላት ቁልፍና መሰረት የሆነዉን ወታደራዊ ቦታ የሰሜን ወሎ ዞን ጊዳን ወረዳን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የአማራ ፋኖ በወሎ በዛሬው እለት ደግሞ የከተማ መቀመጫው የሆነችዉን ሙጃ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ጠላት ላይ ከባድ ዉጊያ በመክፈት በርካታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በመማረክ ሰብአዊና ቁሳቂ ኪሳራ አድርሶበታል።

በኮማንዶ ዘላለም የሚመራው ተከዜ ክ/ጦር በሻለቃ ብርሃን የሚመራው ጥራሪ ክ/ጦር እንዲሁም ከማረጉ ተማረ ክ/ጦር በፋኖ ምስጋን የሚመራ ሻለቃ በአጠቃላይ በላስታ አሳምነው ኮር ስር ያሉ ግዳጁ ላይ አሃዶቻቸዉን ያሳተፉ ክፍለጦሮች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በፋኖ ካሳ አበበ የሚመራው ሃውጃኖ ክፍለጦርና በፋኖ ጌታሁን ሲሳይ የሚመራው አሳምነው ክፍለጦርን ጨምሮ ከሁሉም አሃዶች የተውጣጡ ሻለቆች በጋራ የፈፀሙት ግዳጅ ነው።

ከጠላት ኪሳራ አኳያ

1. እስካሁን በቁጥር ያልታወቀ በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

2. ሁለት የጠላት መኪና የተቃጠለና አንድ የጠላት ዲሽቃ ከጥራሪ ክፍለጦር መካናይዝድ ቡድን በተወነጨፈ ሞርታር ሙሉ ለሙሉ ወድሟል::

3. ብልፅግና የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የሚጠቀማቸዉ የቢሮ ሰነዶች ከምንፈልጋቸው ዉጭ ያሉት ፖሊስ ጣቢያዉን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

ምርኮን በተመለከተ
1. ጥራሪ ክ/ጦር 22 ከላሽ አንድ ጂመስሪ በምርኮ አግኝታለች::

2. ተከዜ ክ/ጦር ከአስር በላይ ከላሾችን በምርኮ አግኝታለች::

3. ከ20 በላይ  ሆድ አደር ሚሊሻ ተማርኳል::
4. የአሳምነው እና ሃውጃኖ ክፍለጦር አሃዶች ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ ክላሽ ማርከዋል::

ሌላው አስገራሚ ነገር የተከበበዉን የጠላት ሃይል ለማዉጣት ከድልብ በኩል የመጣው ዙ23 የራሱን ወገን መትቷል: ይህ የሆነው ደግሞ ፋኖዎች በጥበብ የነበሩበትን ቦታ ለቀው ለጠላት ቦታዉን በመስጠታቸዉ ነው። በዚህም ዙ23ቱ የራሱን ወገን በርካታዉን ጨፍጭፎታል።


በሌላ መረጃ
የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ክንፍ የሆነው አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ጀብዱ መፈፀሙ ተገልጿል።

የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር አካል የሆነው በመቅደላ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው በፋኖ በለጠ ምትክ የሚመራው ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ባንዳዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

አድማ ብተና ጋር ተጠርንፈዉ የነበሩ የብልፅግና ባንዳዎች ጤፍ ሊያሳጭዱ  አስፈቅደው ወደ ቤተሰብ እንደመጡነው  እርምጃ የወሰድንባቸዉ ሲል የሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ገልጿል።  ደጋግመን ጥሪ አድርገን ስለነበር ጥሪያችንን ሳይቀበሉ በመቅረታቸውና ወደወጡበት ማህበረሰብ ተመልሰው የመምጣት ፍላጎት ስለሌላቸው  የማያደግም እርምጃ ለመውሰድ ተገደናል ሲል ብርጌዱ አክሎም ገልጿል።

በሌላ ምእራብ ወሎ ኮር ተጋድሎ መሃል ሳይንት ወረዳ ደንሳ ከተማ ዛሬ አዳሩን ማለትም ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ለአንድ ቡድን አገዛዙና ለሆዳቸው አድረው ህዝባቸውን ሲጨፈጭፉና ሲያስጨፈጭፉ የከረመው ሆድ አምላኩ የሆኑ ሚሊሻዎች አዳሩን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው አድረዋል። በርካታ የጠላት ሃይልም ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል::

የህልዉና ተጋድሎው እስከ ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ገልጿል።

@የአማራ ፋኖ በወሎ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

05 Nov, 16:39


የአውደ ውጊያ መረጃ ጎጃም

ዛሬ ውሎውን የአማራ ፋኖ በጎጃም ስድስት(6) ቦታዎች ላይ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። 5ኛ ክፍለ ጦር ጅጋ ፣ማንኩሳ ፣ቡሬ እና ፍኖተሰላም ከተማ ላይ ከባድ ውጊያ አድርጎ ጠላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ጠዋት 2ሰዓት የጀመረው ውጊያ አሁን አመሻሽ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ፍኖተ ሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ አድርጓል ።በአሁኑ ሰዓት ጠላት ከተማውን ለቆ ከከተማው ውጭ ያሰራው የኮንክሪት ምሽግ ውስጥ ገብቷል። የ3ኛ ክ/ጦር ሙሉ ኃይል እና የሰከላው ጊዮን ብርጌድ በጋራ  የጠላትን ምሽግ በሞርተር እየደበደበ ይገኛል።

በሌላ በኩል የ3ኛ ክ/ጦሩ ዘንገና ብርጌድ እና ብይን ብርጌድ በጋራ ባደረጉት ውጊያ ቲሊሊ ከተማን ተቆጣጥሯል።በተመሳሳይ አዴት ዙሪያ አንሙት ያዛቸው ብርጌድም ውጊያ ላይ ውሏል።

አርበኛ ጥላሁን አበጀ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

05 Nov, 15:59


በንፁሃን ደም የሰከረው የአብይ አህመድ ቡድን እብደቱን ቀጥሎበታል።

ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በደቡብ አቸፈር ወረዳ በዝብስት ንዑስ ከተማ 43 ሲቪሊያንን በጅምላ ጨፍጭፏል። 21 ያህክሉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢወች በተከታታይነት በተደረገ የድሮን ጥቃት ጤናጣቢያ እና ትምህርት ቤትን ጨምሮ በርካታ የግለሰብ ቤቶችም ወድመዋል።

ከዚህ በፊት በዚሁ ደቡብ አቸፈር ወረዳ ዲላሞ (ላሊበላ) ላይ አምስት ንፁሃንን መጨፍጨፉ ይታወቃል::

የአማራ ህዝብ ይሔን ኢትኖ ፋሽስት ቡድን አምርሮ መታገል እና ማስወገድ ታሪካዊ ግዴታው ነው።

ፋኖ Asres Mare Damtie
የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

04 Nov, 09:01


የባንዳዉ ይርጋ ሲሳይ  እና የሰማ ጥሩነህ
የአገው ሸንጎ  አዲስ እቅድ በባሕርዳር !!

በባሕርዳር ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የስርዓቱ ሰራዊት መኖሩ ይታወቃል። በብርሃኑ ጁላ የሚመራው ወራሪ ሰራዊት ፣ በኮሚሸነር ደስየ ደጀን የሚመራው አድማ ብተና ፣ ሚኒሻ እና ፖሊስ እንዲሁም በደሳለኝ ጣሰው የሚመራው ሰላምና ደህንነት ቢሮ  በአሁኑ ወቅት ከሞትና ኩብለላ የቀራቸውን ጥቂት ኃይል አሟጠው የፋኖን ትግል ለመግታትና ለመቋቋም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።

ጎን ለጎን ያወጡት እቅድ ግን በሁሉም አደረጃጀት ውስጥ ካላቸው ገዳይ ቡድኖች በተጨማሪ ከዚህ በፊት በኮሚሽነር ደስየ ደጀን ቡድን የተዘጋጁ የጥበቃ ኤጀንሲዎችን ባሕርዳር ከተማ ውስጥ ባሉ ትልልቅ የግል ድርጅቶች ፣ ፋብሪካዎች ፣ የንግድ ተቋማት ፣ ሪልስቴቶች እና ትልልቅ የመኖሪያ መንደሮች ላይ በማሰማራት የ Community Intelligence በማጠናከር የፋኖን ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ሚስጥራዊ ግንኙነት መረጃ በመሰብሰብ የሥርዓቱ ድጋፍ ሲጨ ሃይል ለማድረግ ታቅዷል።

በዚህ እቅድ ውስጥ ሚኒሻውን እና አድማ ብተናው ወስጥ ልዩ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ጥቂት ወታደሮች ወደ  የጥበቃ ኤጀንሲዎች ሄደው የተቀላቀሉ ሲሆን ፤ወደ ሚመደቡበት ማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ተመሳስለው የፋኖን የከተማ እንቅስቃሴ መረጃ እየሰበሰቡ ፋኖ በከተማ ያለውን ሴል ሲያውቁ እና ሲያገኙ ከአድማ ብተናው እና ከብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ጋር በመሆን እርምጃ ለማስወሰድ የተዘጋጀ ነው።

በባሕርዳር ከተማ ማህበረሰብ ውስጥ የጥበቃ ኤጀኒሲዎች ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ ሆነ ተብሎ በሰላምና ደህንነት ቢሮ በአድማ ብተና ፈጻሚነት የተዘጋጀ የሰው ፣ የህጻናት ፣የሴቶች ፣ የንብረት እገታ አፈናዎች የተሰላቸው የነጋዴው እና መካከለኛ ኑሮ ነዋሪው የማህበረሰብ ክፍል እንዲማረር ከአደረጉ በኋላ የጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲመደቡላቸው ያደርጋሉ በመቀጠልም የራሳቸውን ገዳይ ቡድኖች እና መረጃዎችን ለማሰማራት መሆኑ ታውቋል።

በዚህ እንቅስቃሴ እና እቅድ ውስጥ ስርዓቱ ባህርዳር ከተማ ላይ ብቻ ለግዜው ያቅደው እንጂ በሌሎች ትልልቅ የአማራ ከተሞች ተሞክሮውን ለመተግበር የወደፊት እቅድ ተደርጓል ። አገዛዙ አካሄዱንየመረጡበት ምክንያትም ፋኖ የከተማ ሴሉን በማሳደጉ እና በከተሞች ሰርጎ ገብቶ የሚፈፅማቸው ኦፕሬሾኖችን ለመግታት በየቦታው የራሱን የመንግሥት ሴል ለማስቀመጥ እንደሆነ ታውቋል።

በባህርዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኙት የባሕርዳር ብርጌድ ሻለቆች እንደ ደጉ በላይ ሻለቃ ፣ግዬን ሻለቃ ፣ አራራት ሻለቃ ፣አሳምነው ሻለቃ እና አራራት ሻለቃ ወደ ከተማው ሰርገው በመግባት የስርዓቱ ሎሌና ባንዳዎችን አንጠልጥለው በመውሰዳቸው አሁን በጥበቃ ኤጀንሲ ስም የመንግሥት ሃይል በማስቀመጥ ፋኖ ጥበቃ ናቸው ብሎ ተዘናግቶ ኦፕሬሽን በሚከውንበት ወቅት መረጃ በመስጠትና  ከጀርባ ጭምር በመውጋት ከተማ ውስጥ የሚደረገው ኦፕሬሽን ስኬታማ እንዳይሆን የታቀደ አዲስ እቅድ ነው።

ለባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕት የፋኖኦፕሬሽኖች ባንዳ እና የስርዓቱ አዳሪዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድና ታንቀው ሲወሰዱ ጥቂቶች ተመልክታችኋል። ይሁን እንጅ ከዚኽ በተቃራኒ እገታ ፣አፍኖ ገንዘብ ድርድር በከተማው የሚፈጽመው ሆነ ተብሎ የሥርዓቱ አፋኝና ዘራፊ ቡድን መሆኑን በጥቂቱም ቢሆን የምትረዱት ሃቅ ነው።

ስለሆነም አገዛዙ አሁን ተቋማትን በስውር ለማስጠበቅ የጥበቃ ሽፋን ኤጀንሲን አመጣለሁ እያለ በየአካባቢው የሚወተውተው ሁሉ ከጀርባው የተሸከመው የስርዓቱ ተልዕኮ መሆኑን ቀድማችሁ እንድታውቁና በአጠቃላይ የጥበቃ ኤጀንሲዎች በማን እንደሚዘወሩ ሴራቸውን  ልትገነዘቡ ይገባል እንላለን ።

ይህንን የአገዛዙ ተንኮልና ሴራ እያዎቀ የአገዛዙን ሴራ በጥበቃ ኤጄንሲ ሥምና ሽፋን የተቋማት የጥበቃ ኤጀንሲ ይመደብልን ብሎ የሚያስተባብርና የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በየአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል ለማስጠቃት ከአገዛዙ ጋር ተናቦና ተባብሮ እየሰራ እንደሆነ በውስጥ አርበኞች መረጃ ደርሶናል ።

 በዚህ መሰረት የአገዛዙ ተባባሪ በመሆንም ሆነ፤ ሴራውን ባለማወቅ የትኛውንም የጥበቃ ኤጀንሲ አዲስ ቅጥር የምትፈጽሙ ድርጅቶች ፣ ንግድ ተቋማት ፣ ፋብሪካዎች ፣ ሪልስቴቶች በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልዕክት በአዲስ የቅጥር ውል የቀጠራችሁት የጥበቃ ኤጀንሲ አባል ከአገዛዙ ጋር በማበር ለሚፈጽመው ማንኛውም ፀረ-ፋኖ እንቅስቃሴ እና አገዛዙ ላቀደው አዲስ የፋኖ ጥቃት ሙሉ ሃላፊነት ትወስዳላችሁ። ይህንንም ተከትሎ የፋኖ ለሚወስደው ሴራውን የማክሸፍና የበቀል እርምጃ በጥበቃ ኤጀንሲ ድርጅቱ  ብቻ ሳይሆን በቀጣሪ ድርጅቱ ጭምር ይሆናል።

✍️የአማራ ፋኖ በጎጃም በባሕርዳር ከተማ
የውስጥ ሸማቂ ኃይል የተላከ መልዕክት!!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

04 Nov, 08:53


271 የአብይ ሰራዊት በ10 ቀን መክዳቱ ተነገረ::

ስቦ ማስከዳት እና ስቦ መምታት ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው የአማራ ፋኖ በጎጃም የሚዲያ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ ጥላሁን አበጀ በዚህ መሰረት ከጠላት ካምፕ ከድተው የወጡ የአብይ አሕመድ ስልጣን አስጠባቂ ጦር የአማራ ፋኖ በጎጃምን ተቀላቅለዋል ብላል::

በዚህም...
1ኛ ክ/ጦር = 37
2ኛ ክ/ጦር መብረቁ ተፈራ ዳምጤ  32
3ኛ ክ/ጦር ጎጃም አገው ምድር  =84
4ኛ ክ/ጦር ጃዊ =30
5ኛ ክ/ጦር ራስ መንገሻ ቲከም  34
6ኛ ክ/ጦር ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ  17
8ኛ ክ/ጦር በላይ ዘለቀ  22
9ኛ ክ/ጦር ሳሙኤል አወቀ 15 በአጠቃላይ 271 ገቢ ሆኗል ሲል ገልጿል::

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Nov, 17:32


ሪፖርተር!

“10.8 ሚሊዮን ህዝቦች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል!

5566 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል!

በአማራ ክልል 85 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል!

ሱፍ ለባሹ ኋላቀር አምባገነን!
ሚልዮን ገ ዳ ይ አቢይ አህመድ
ውሸቱ በሀገር ውስጥ ጋዜጣ ሲሰጣ!

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

03 Nov, 10:07


"...የአገዛዙን ሞት ማፋጠን ይኖርብናል.."
     ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
👇በዛብህ በላቸው

1) በምኒልክ ቤተ-መንግስት  ደጃፍ የነበረውን ባለ ግርማ ሞገስ የአንበሳ ምስል አፍርሶ ፒኮክ ያስቀረጸው በውበቷ ማልሎ ወይም ፒኮኳ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስተሳስራት ለቁምነገር የሚበቃ ጉዳይ በመኖሩ አይደለም።
2) አዲስ አበባን የኮሪዶር ልማት በሚል የዳቦ ስም የሚንዳት የከተማው ህዝብ ኑሮ መሻሻል አስጨንቆት አይደለም።
3) በአዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ የኦሮሞ-ጠል ኃይሎች አሉ በሚል ግጭት ቀስቃሽ ንግግር  ያደረገው  ለኦሮሞ  የሚራራ አንጀት ስላለው ወይም የፍቅር ሰው ከመሆኑ የተነሳ ጥላቻን በማነወሩ አይደለም።
4) ቤተ-መንግስቱን በሚያብለጨልጩ  ቁሳቁሶች አሽሞንሙኖ ይዘቱንም ስሙንም የለወጠው  ለማስመሰል እንደሚጥረው የኢትዮጵያን ትናንት ለመዘከር ፈጽሞ አይደለም።
5) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታን በመወሰን ረገድ የማይተካ ሚና ያለውን የዓባይ ተፋሰስ በመጣልና በማሳነስ በአዋሽ ተፋሰስ ተክቶ የሚዳክረው ለኢትዮጵያ ደቡብ የተለዬ ውግንና ስላለው አይደለም።
6) እኔ ጎርጎራን ስሰራላችሁ የጎጃም ሰዎች ግን ተቃወሙኝ የሚል አሳፋሪ  ግጭት ቀስቃሽ ንግግር የሚያደርገው ለጎንደር የተለዬ ፍቅር ስላለው ከቶ አይደለም።
7) በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ሌቦች ዳኞች ናቸው የሚል አዋጅ በፓርላማው ፊት የተናገረው የሙስና ጉዳይ አሳስቦት ወይም የፍትህ ነገር አስጨንቆት አልነበረም።
8)  የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መዝሙር እንዲቀየር ትእዛዝ ያስተላለፈው መዝሙሩ  እንከን ኖሮበት አይደለም። 
9) በአረብ ኤምሬቶች በኩል ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አባል ለማድረግ እየደከመ ያለው ማህበሩ የሚያስገኘው ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ አሳስቦት አይደለም።
10) የአበባየሁሽን መዝሙር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አዲስ ዓመትም የሚቀይር አዋጅ ይዞ መምጣቱ የማይቀር የሚሆነውም  የዘመን ቀመራችን ለእድገታችን ጸር ስለሆነ ከቶ አይደለም።
11) የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልን ወደ አራት የበተነው ስለ ራስን ማስተዳደር ግድ ኖሮት ወይም ለአስተዳደር ምቹነት በማሰብ አይደለም።
ምክንያትቹ ምንድን ናቸው? አደራረጉስ እንዴት ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ማድረግ አለበት? ምን ማድረግስ የለበትም ? የሚሉትን ነጥብች በአጭሩ እንመለከታለን።
ሀ) የነገረ-ስልጣን ክፍፍል ሊቅ የሆነው ጀምስ ማዲሰን እንደሚለው አምባገነንነት አንድ ሰው ሁሉንም የማድረግ ስልጣን ሲኖረው የሚፈጠር ነው። [ If all the three powers of a government  lays in one organ that is the definituon of tyranny]. አብይ አህመድ አሊ በህግ ተወስኖ የተሰጠውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን እንኳን ለመሸከምና ለመፈጸም የሚበቃ የትምህርት ዝግጅት፣ ልምድ እና የሞራል ብቃት የሌለው ሆኖ ሳለ  ሁሉንም ጉዳዮች  የሚወስን ንጉስ መሆንን መረጠ። የኢትዮጵያ የተቋማት ግንባታ ድክመት በአጉራዘለል እርምጃዎቹ ላይ ገደብ ለማኖር የሚያስችል አልሆነም።  የላቀና የደረጀ ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ቢሆን እንኳን  ፓርላማውንም ፍርድ ቤቱንም አስፈጻሚውንም ተክቶና እንኳን መዋቅርና ተቋማትን የግለሰብ ምክር እንኳን የማይሰማ እስከሆነ ድረስ ሁሉንም የኢትዮጵያ ጉዳዮች የሚወስን ሆኖ ከጦርነትና ከእልቂት በቀር የሚያመጣው ብለጽግና የለም። 
ለ) አብይ አህመድ አሊ ካድሬዎቹን የሚገዛበት ስልቱ ለተቀመጠበት ኃላፊነት የማይመጥን ወሬን በማመላለስ ነው።  ለምሳሌ በመጋቢት 2014 ዓ/ም በተካሄደው የብልጽግና ጉባዔ ወቅት ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚደንት የማደርግህ አንተን ነው ተዘጋጅ ደመቀ አልለቅም ብሎ እያስቸገረኝ ነው ካለው በኃላ ደመቀ መኮንንን ደግሞ በሽማግሌና በቤተሰቦቹ  ጭምር  ማልዶ ያለ አንተ ለውጡ ቀጣይነት አይኖረውም ተመስገን ግን እኔ ልሁን የሚል ቅሬታ አለው በማለት በሁለቱ መካከል እስከዛሬ የቀጠለን ጠብ ፈጥሯል።  እነዚህ ሁለቱን ጨምሮ በስሩ የሰበሰባቸው ሰነፎች ደግሞ በእሱ ዘንድ የበለጠ ለመወደድ  በመላላክ ብርቱ ውድድር ውስጥ ያልፋሉ።  አብይ አህመድ እንዲህ ያለውን አፋፍሎ፣ አጋጭቶና መልሶ አስታራቂ ሆኖ የመቅረብን ስልት በብሄሮች መካከል፣ በክፍለ-ሃገሮችም መካከል ደጋግሞ ሞክሮታል።
መ) እሱና በዙሪያው የሰበሰበው የፖለቲካ ቡድን የኢትዮጵያን ፍሬ-ነገር በመለወጥ በአዲስ የመተካት ፕሮጀክት አለው። የኦነግ ሽማግሎች፣ የኦህዴድ ጎረምሶች በምኒልክ ቤተ-መንግስት የሚዶልቱት ይህንኑ ጉዳይ ነው። የምንመራው መንግስት የኦሮሞ መንግስት ነው የሚሉት በይፋና በአደባባይ ነው። ኦሮሞን በሰማይም በምድርም ሲወጋ የሚውለው የእነ ብርሃኑ ጁላ ቡድን እንዴት ሆኖ ለኦሮሞ ጥቅም የቆመ መንግስት ይሆናል? ብሎ የሚጠይቅ ያለ አይመስላቸውም።

አገዛዙ  በብሄር ወይም በሀይማኖት ለመጠለል የሚያደርገው ሙከራ አይሳካለትም። ኢትዮጵያን የመበተን ህልሙም ይመክናል። የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲህ ያለውን ነውረኛ ስርዓት በጋራ እንዲታገሉት የሚያደርግ ተጨባጭ የታሪክ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ምክንያቶች አሏቸው። ስለሆነም ትግላችንን ፈርጀ-ብዙ በማድረግና በማስፋት የአገዛዙን ሞት ማፋጠን ይኖርብናል።

   ©አስረስ ማረ ዳምጤ


#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/2/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Nov, 13:21


የጀነራሎቹ ፕርፓጋንዳና ደብረማርቆስ

የብልጽግና ጀነራሎች እያካሄዱት ባለው የአማራ ክልል ስብሰባ “ፋኖን አጥፍተነዋል” የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ነው
የዋሺንግተን ግዛት የተወሰኑ የብሔራዊ ጥበቃ አባላቱ በተጠንቀቅ እንዲሆኑ ማዘዙን አስታወቀ
የብልጽግና የጦር አዛዦችና ካቢኔዎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ስብሰባ ማካሄዳቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ በደሴና በኮምቦልቻ ጀነራል በላይ ስዩም በደብረማርቆስ ጀነራል መሃመድ ተሰማ የመሯቸው ስብሰባዎች ተካሂደዋል፡፡
በደሴና በኮምቦልቻው ስብሰባ የተገኙት ጀነራል በላይ ስዩም ለአመራሩ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ይህም መመሪያ ፋኖ መጥፋት አለበት ለዚህም ህዝቡ ይተባበር የሚል ሲሆን ዛቻ የተቀላቀለበት እንደነበርም ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ጀነራል መሃመድ ተሰማ የዛሬ ዓመት ጥቅምት ወር ገደማ የተናገረውን ንግግር በዛው ከተማ ደግሞታል፡፡
ጀነራሉ “ፋኖን አጥፍተናል ፣ በትነነዋል ፣ አዳክመነዋል ፣ከፍተኛ ውጊያ አያካሄድን ነው፣ በአየር ሃይል ጥቃት እየፈጸምን ነው” ሲል ነው የተሰማው፡፡ ይህን የሰሙት ተስብሳቢዎች አብዛኛዎቹ የብልጽግና ካድሬዎች ስለሆኑ የዛሬ ዓመትም እኮ እንዲህ ተብለን ነበር አላሉም፡፡
ይሁን እንጂ መሃመድ ተሰማ የዛሬ ዓመትም በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ፋኖን አጥፍተነዋል ማለቱ ይታወሳል፡፡
ጀነራሎቹ ይህን ቢሉም የአማራ ክልል አብዛኛው አካባቢ በፋኖ ቁጥጥር ስር መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የብልጽግናው ሃይል አዲስ የውጊያ ዘመቻ ይዞ የመጣ ሲሆን ይህ ስልትም የክላስተር / የኩታ ገጠም/ ዘመቻ ለማድረግ መወሰኑ ነው የተሰማው፡፡
በዚህ በኩታ ገጠም ውጊያ አንድን ዞን ከሌላ ዞን ጋር የሚያዋስነውን ቦታ በመናበብ ውጊያውን እንዲመሩና የመረጃ ልውውጥ እያደረጉ እንዲዋጉ የሚል ነው፡፡
ብልጽግና ከፋኖ ጋር እያካሄደ ባለው ውጊያ ያልተገበረው የዘመቻ አይነትና ያልቆረጠው የመጨረሻ ዘመቻ የለም ፣ ይሁን እንጂ ሁሉም ዘምቻና እቅዶች ፋኖን የበለጠ እያስታጠቁትና እያደራጁት አልፈዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዐቢይ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ያደረጓቸው ለገሰ ቱሉ በእነ ዳንኤል ክብረት የተደረሰውን አዲስ የፕሮፓጋንዳ ስልት ተቀላቅለዋል፡፡
እኒህ ጥላቻና ፍረጃን በመቀስቀስ የሚታወቁት የብልጽግናው ሹም በስተርጅና እድሜያቸው ለብልጽግና በሆዳቸው አድረው በአማራ ህዝብ ላይ ጦር ካወጁት መካከል ናቸው፡፡
በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “ፅንፈኛው ቡድን በምንም መመዘኛ ቢለካ ለአማራ ህዝብ ጥቅም የሚሆን አንግቦ የተነሳው ዓላማም ሆነ ዕቅድ የለውም” ሲሉ ለአማራ ከፋኖ ይልቅ ዐቢይና ሽመልስ አብዲሳ ይጨነቁለታል ብለዋል።
ፋኖ የሆነው ራሱ የአማራ ህዝብ መሆኑ ቢታወቅም ፣ የተሰቃየውና ግፍ የተፈጸመበት ራሱ አማራ መሆኑ ሃቅ ቢሆንም እነ ለገሰ ቱሉ ግን ይህን ሃቅ መካድ ዋነኛ ስራቸው ነው፡፡
ክልሉን በድሮን ፣ በከባድ መሳሪያ ፣ በሄሊኮፕተር እያወደመ ያለውን የብልጽግና ስብስብ በሚኒስትርነት የሚያገለግሉት እኒህ ሰው ፋኖን ክልሉን በማውደም ሲከሱት ተስተውለዋል፡፡

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Nov, 12:18


አማራ ክልል ኢንተርኔት መለቀቁን ተከተሎ ስትጠቀሙ  VPN ማብራታቹህን አረጋግጡ በተለይ ፋኖዎች።እስኪ የብልጽግናው አገዛዝ ምን ድራማ ይዞ መጦ ይሆን በቀጣይ የምንጠብቀው ይሆናል

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Nov, 04:33


🔥#መረጃ_ደብረማርቆስ‼️

ነበልባሎች ዛሬ ንጋት ጀምሮ ደብረማርቆስ ከተማ መምህራን ኮሌጅ እና ሌሎች ቀጠናዎች ኦፕሬሽን እያካሄደ መሆኑን የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዎል‼️

ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን...

#አማራ_ታሪኩን_ይድሳል💪
#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

23/2/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

02 Nov, 03:22


ሰላም አማራዊያን እንደምን አላችሁ የፌስቡክ አካውንቴ #ንስር_አማራ(አሳምነው ጽጌ) በዚህ ጹሑፍ እስከ ጥር 30,2025 ድረስ ዘግተውታል። ያው አማራ ስትሆን ፣ለአማራዊያን ግፍ እና በደል ድምጽ መሆን በአገዛዙ በኩል ትሳደዳለህ ምንም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንድትሆን አይፈቀድልህም ፣በህይወት የመኖር እድልህ በነሱ እጅ ነው።even if totally privacy የሚባል ነገር የለህም ።ይህንን ስርዓት ለመታገል ሰው መሆን በቂ ነው አማራዊያን🔥🔥💪

ድል ለባለ ድል ሱሰኛው ለአማራ ህዝብ ይሁን💪🔥🔥

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

01 Nov, 04:40


ጠ/ሚ #አብይ _አህመድ_የአዕምሮ እንከን እንደገጠማቸው የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ግን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደረሰዋል። ለዚህም በትናንትናው ዕለት የምክር ቤት ውሎ ላይ ከምክር ቤት አባላት ከተነሳላቸው ጥያቄዎች መካከል የሰጡት መልስ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።ከዚህ የተለየ ክትትል የሚሻ በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ካልተደረገላቸውም ኢትዮጵያን ከዚህ የከፋ ችግር ላይ እንደሚጥሏት የግድ #ነብይ መሆን አይጠበቅብንም በማለትም ምክራዊ ሀሳባቸውን ጣል አድርገዋል

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

31 Oct, 22:17


አሳዛኝ ዜና!

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

ጥቃቱ የደረሰው በዞኑ የሶዶ ወረዳ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ ቢርቢርሳና ጋሌ ቀበሌ  ልዩ ስሙ ''ኩሬ'' እንዲሁም ''ቢጢሲ'' ተብለው እስከሚጠሩ ስፍራዎች ነው።

በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ዛሬ ከስፍራው የደረሱን ተደጋጋሚ መረጃዎች አመላክተዋል።

ጥቃቱ ትላንት ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መራዘሙን የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟቾች ቤተሰቦች በጥቃቱ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተናግረዋል።

የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በአካባቢው የመንግሥት መዋቅሮች በኩል እስካሁን ስለጉዳዩ ግልፅ መረጃም ሆነ ድርጊቱን የሚያወግዝ መግለጫ አልተሰጠም።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

31 Oct, 17:13


የምዕራብ ወሎ ኮር ምስረታን በተመለከተ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም

የአማራ ፋኖ በወሎ ካሉት ክፍለ ጦሮች መካከል ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በኩል የሚንቀሳቀሱት 3 ክፍለ ጦሮች በአንድ ወታደራዊ ኮር እንዲታቀፉ መደረጉን ድርጅታችን እየገለጸ:-

1. የንጉሥ ሚካኤል አሊ ክፍለ ጦር፣

2. የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣

እና

3. ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር

ቀጠናዊ የክፍለ ጦር ለክፍለ ጦር ግንኙነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል ግዳጅ የመፈጸም አቅማቸውን ማሳደግ እና የትግሉን ዙር ማክረር እንዲችሉ ማድረግ በማስፈለጉ የተነሳ በቀጠናው ያሉት እነዚህ 3 ክፍለ ጦሮች በአማራ ፋኖ በወሎ ስር ምዕራብ ወሎ ኮር በሚል ስያሜ ተደራጅተዋል::

ለዕዝ ሰንሰለት ስምረት እና ለአስተዳደራዊ አመችነት ሲባል ክፍለ ጦሮችን በኮር የማደራጀት እንቅስቃሴ ከተጀመረ የሰነበተ ሲሆን የአማራ ፋኖ በወሎ በያዘው እቅድ መሰረት የምዕራቡን ክፍል በኮር የማደራጀት ስራውን በዛሬው እለት አጠናቋል::

የምዕራብ ወሎ ኮር ከደሴ እስከ ሳይንት ጫፍ በሽሎ ወንዝ ድንበር ድረስ የሚያካልል የፋኖ ሀይልን ያቀፈ ሲሆን የአፄ ቴዎድሮስ አጽመ እርስት ከሚገኝበት መቅደላ አምባ እስከ ጌታው ሸህዬ ሀገር ደገር የሚዘረጋ ግዙፍ ኮር ነው:: ከሸዋ ድንበር በቶ እና ወለቃ ወንዞች እስከ ጎንደር ድንበር በሽሎ ወንዝ እንድሁም የጎጃም እና ወሎ መዘያየሪያ የሆነው አባይ ወንዝ ድልድይ ድረስ የሚወነጨፍ የፋኖ ሀይል በኮሩ ስር የተሰበሰበ ሲሆን የኮሩ መስራች የሆኑት 3 ክፍለ ጦሮች ያቀፏቸው ብርጌዶች፣ ሻለቃዎች እና ሻምበሎች ከምዕራብ ወሎ ቀጠና ባሻገር ወደ ጎንደር፣ ጎጃም እና ሸዋ በመወርወር ግዳጅ መወጣት እንደሚችሉ ተደርገው የተደራጁ መሆናቸውን እየገለፅን የቀጠናው ፋኖዎች ወንዝ ተሻግረው እና ጎራ ዙረው ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችላቸውን ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ጭምር በቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ስም ሰይመው ለሰማዕተ ጓዳችን እና ወንድማችን ማስታወሻ የሚሆን የተቋም ሀውልት እንዲቆምለት ማድረግ ተችሏል::

የምዕራብ ወሎ ኮርን በዋና ሰብሳቢ/ዋና አዛዥ የሚመራው ስመጥሩው አርበኛ ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ሲሆን በጥብቅ ወታደራዊ ዲስፕሊን የታነፀ እና ግዳጅ የመፈፀም ብቃቱ አኩሪ መሆኑ የተረጋገጠ ሰራዊትን ያቀፈ ኮር ነው:: አርበኛ ሳጅን አደም አሊ ጋር ኮሩን በመምራት ትግሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ያሸጋግራሉ ተብለው የታመነባቸው የኮሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ስም እና ኃላፊነት ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ለታጋይ ሰራዊታችንና ለህዝባችን ይፋ የምናደርግና የምናሳውቅ ይሆናል::

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

31 Oct, 09:46


መረጃ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ አየር ክልል እንዳይበር መከልከሉ ታውቋል። ምክንያቱ ከ20 ዓመታት በፊት ለሠጠሁት አገልግሎት ከአየር መንገዱ አልተከፈለኝም የሚል ነው።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

31 Oct, 07:47


‹‹ በአማራ ክልል ንጹኃን በድሮን እያለቁ ነው ››
‹‹ በሁለት ወራት ይጠናቀቃል የተባለው የአማራ ክልል ዘመቻ ከአንድ ዓመት በላይ ወስዷል ››

‹‹ በአማራ ክልል ያለው ችግር እየተባበሰ ሄደ እንጂ እየተፈታ አልሄደም ››
‹‹ ሲቪል ተቋማት ፣ት/ቤቶች ጤና ጣቢያዎች እየወደሙ ነው ››
‹‹ በአዲስ አበባ፣  በአማራ ክልል እና በተለያዩ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ››

‹‹ የእኛ የምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለፍርድ እየተመላለሱ ነው !>>

‹‹ ከዚህም የሚብሱ አሉ፤ ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት [በወህኒ ቤቶች]  ያህል ያለፍርድ የተቀመጡ አሉ ›› የሚሉት አበባው ‹‹ በሁለት ወራት ይጠናቀቃል የተባለው የአማራ ክልሉ ዘመቻ ከአንድ ዓመት በላይ ማስቆጠሩን ››

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ዶ/ር አበባው ደሳለው  ለጠቅላይ ሚነስትሩ ያቀረባቸው እውነታዎች 💪

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Oct, 17:23


በአማራ ሰማይ ስር

ገናም ይቀጥላል🙉🙉 ትገባለህ አትወጣም ምድረ ገልቱ😏

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Oct, 17:13


🔥ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ💪

~ ትንሽ ሲጠፋ ገደልነው አሉ ጮቤ ረገጡ
መቶ ሲናገር ውሸት ነው አሉ ተደናገጡ
መቸም ጀግና ነው ሲያታልላቸው
ዝሆን ነኝ ብሎ ታንኳ አሳያቸው
ደግሞ መጣና በእጁ ቀለበት አሰጠማቸው💪

ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ(ቅኔው)

#አማራ_ታሪኩን_ይድሳል💪
#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/2/17 ዓ.ም

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Sep, 06:44


🛑ሰበር ባህርዳር የጦር ጄት‼️

አገዛዙ ብልፅግና መንግስት በአሁኑ ሰዓት  ከባህርዳር ወደ ደቡብ ጎንደር አንድ የጦር ጄት ለመላክ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አሁን ከባህርዳር ምንጮች የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በጎንደር ቀጠና የምትገኙ የወገን ሀይሎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል። መረጃው በአስቸኳይ ሼር ይደረግ ይዛመት።

አንድ አማራ (አሳምነው ጽጌ🔥)

30 Sep, 05:12


መንገድ ያሰባችሁ ሰዎች ከወዲሁ ቀጠሯችሁን አስተካክሉ ከመስከረም 23 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መንገድ ዝግ መሆኑ ታውጇል !!በሁሉም አማራ ክልል