🇪🇹 ኢትዮ Students @ethiostudents Channel on Telegram

🇪🇹 ኢትዮ Students

@ethiostudents


Our Bot :
@EthioExamBot

Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

🇪🇹 ኢትዮ Students (Amharic)

ኢትዮ Students ተያይዞ እንዴት ነዉ? ኢትዮ Students ለምን እንዴት ነዉ? እና ኢትዮ Students ምንድንዉ ነዉ? ኢትዮ Students ለስለስ በትክክል መረጃ በትክክል ከበለዉ! ለምሳሌ ኢትዮ Students መረጃን ማሰማጠን ይችላሉ። የእንግሊዝ ኦንላይን ስነ-ስራሹ እና ለመማቭ ይህንን ላይ ተመለሱ። እናም በዚህ ቦታ በምርጫ ምዝገባ ጊዜ አቅምን። ኢትዮ Students ለመረጃ በትክክል እና እው ለተከፍተበት ጊዜ አቅምን። ግን ኢትዮ Students ምንድንዉ ነዉ? ኢትዮ Students የምንወድቅ ነዉ? ኢትዮ Students የመረጃ ማስገባት እንዴት ነዉ? ኢትዮ Students ለዚህ ስራ ብቅ ብቅ ብቅ! ኢትዮ Students ለማቀናበን እባኮትን ለመቆም ተጠቃን።

🇪🇹 ኢትዮ Students

07 Jan, 07:59


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዬች እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🌐 @ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

04 Jan, 20:47


እንደተለመደው ዛሬም በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበረ እየተነገረ ይገኛል ከደቂቃዎች በፊትም ዛሬ ከነበሩት ከፍተኛው እንደነበር ታይቷል

🇪🇹 ኢትዮ Students

04 Jan, 04:05


የለሊቱ መሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ያሳየው ሁኔታ:: የዛሬው እጅግ ከበድ ያለ ንዝረት እንደነበር ታውቋል;:

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Jan, 18:28


ሳዑዲ ዓረቢያ ስድስት ኢራናውያንን ሺሻ በድብቅ ሲያዘዋውሩ አግኝቻለው በማለት በስቅላት እንዲቀጡ ማድረጓን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Jan, 12:21


🔔🌐ሰላም የኢትዮ STUDENTS ቻናል ቤተሰቦች በሚያስገርም ሁኔታ ይሄ ቻናል ከተከፈተ ከ7 ዓመት በላይ አልፎታል ።

🖕 እስካሁን አብራችሁን ለነበራችሁ እናመሰግናለን። በእስካሁኑ ቆይታችን ለእናንተ የሚመጥኑ እና የተመረጡ አለማቀፋዊ ሀገራቀፋዊ እና ትምህርታዊ መረጃዎችን እያደረስንላችሁ እንገኛለን እና እስከዛሬ በነበራችሁ ቆይታ ያላችሁን ሀሳብ እና አስተያየት በComment ስር አስቀምጡልን።

😘 በተጨማሪም  በReaction አብሮነታችሁን ግለፁልን ።

🥂መልካም ቀን ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Jan, 07:53


በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣  የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።

ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል። ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

31 Dec, 19:31


#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።

በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል።

ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች በተለይ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች መልዕክቶችን ተቀብለናል።

#tikvahethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

29 Dec, 10:36


ስዊድን ጦርነት ይከሰታል በሚል ለብዙ ሰዎች የቀብር ቦታ ማዘጋጀት ጀመረች‼️
ኔቶን በቅርቡ የተቀላቀለችው ስዊድን በሩሲያ ምክንያት ብዙ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ውስጥ ነች
አሁን ደግሞ ከሩሲያ ሊሰነዘር በሚችል ጥቃት ምክንያት ሰዎች በብዛት ሊሞቱ ይችላሉ በሚል የቀብር ቦታ ማዘጋጀት ጀምራለች ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።
በስዊድን ካሉ ከተሞች መካከል በግዙፍነቱ ሁለተኛው የሆነው ጎትቦርግ ከተማ ብቻ በድንገት በሚከሰት ጦርነት ለሚሞቱ ሰዎች አራት ሄክታር መሬት ለቀብር አዘጋጅቷል።
የሀገሪቱ ከተሞች የቀብር ቦታ በስፋት ወደማፈላለግ የገቡት የስዊድን ጦር እና ሌሎች ተቋማት ጦርነት ሊኖር ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ካሰሙ በኋላ ነው።
ከአንድ ወር በፊት ሩሲያ ኦሬሽኒክ የተሰኘውን የኑክሌር ሚሳኤል ወደ ዩክሬን መተኮሷን ተከትሎ ስዊድን ዜጎቿን ከኑክሌር ጦርነት ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ማስተማር ጀምራ ነበር።
ከስዊድን በተጨማሪም ፊንላንድ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ዜጎቻቸውን በጦርነት ወቅት እንዴት ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ በማስተማር ላይ ናቸው።
ዴንማርክ እና ኖርዌይ ጦርነት ሊከሰት ይችላል ከሚል ስጋት ውጪ በሚያስተምሩት የቅድመ ጥንቃቄ ማስተማሪያ ይዘቶች ላይ የሩሲያን ስም አልጠቀሱም ተብሏል።
ሶስት ዓመት የሆነው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ሲሆን ምዕራባውያን ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያዎች በማስታጠቅ ላይ ናቸው።
ዩክሬን ከኔቶ አባል ሀገራት በምታገኛቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሩሲያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ ናት።
ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚሰጡ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎች ሶስተኛው የዓለም ጦርነትን ሊቀሰቅስ እንደሚችል በተደጋጋሚ አስጠንቅቃለች።

#ayuzehabesha

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

29 Dec, 09:16


ቪድዮ፦ በአስደንጋጩ አውሮፕላን አደጋ እስካሁን 151 ሰዎች ሞቱ።

በደቡብ ኮሪያ ውስጥ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ እስካሁን ድረስ 151 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

" ጄጁ " የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባንግኮክ መጥቶ በደቡብ ኮሪያው ሙዋን አየር ማረፊያ ሲያርፍ ነበር መንገዱን ስቶ የአውሮፕላኑ የፊተኛው ክፍል በእሣት ሲያያዝ የታየው።

ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የአደጋው መንስዔ ባይታወቅም የእሣት አደጋ አገልግሎት " ምናልባት ከወፍ ተጋጭቶ አሊያም ባለው ከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብሏል።

አውሮፕላኑ 181 ሰዎች አሳፍሮ ነው ከታይላንድ የተነሳው።

አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያዊያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እስካሁን አንድ ተሳፋሪና አንድ የበረራ ሠራተኛ በሕይወት ሲተርፉ ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማዳን ሥራው መቀጠሉን ቢቢሲ ኒውስ ፣ ቲአርቲ ወርልድና ሮይተርስ ዘግበዋል።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

#tikvahethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

28 Dec, 20:30


የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች

• የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር - ኤላ ትሪክ
• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ
• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi
• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ
• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮንቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ
• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ /Miss Fendisha/
• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ - ጃዝሚን/jazmin_hope1/
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት - ኤላ Review
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ - Baes
• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ
• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ
• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu
• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ
• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ /Elatick/
• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ - I did it በዘነዘና
• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ - አቤል ብርሃኑ
• የዓመቱ ምርጥ ኢንፎርማቲቭ ኮንቴንት አዋርድ- ሙሴ ሰለሞን
• የዓመቱ ምርጥ ኢመርጂንግ ኮንቴንት አዋርድ-ስኬት ቤስት ሾርት ሙቪ ቪዲዮ አዋርድ
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በወንድ አሸናፊ- ከርተንኮል
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በሴት አሸናፊ - ማሂልት ኢብራለም

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

08 Dec, 17:55


በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ         

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል። 

የታጣቂ  ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል። 

በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል።

ኀዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Dec, 13:42


ምክትል ፕሬዝዳንቷ በኃላፊነታቸው ይቀጥላሉ !!

የኣዲስ ኣበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለዛሬ የጠራው ስብሰባ ኣዲስ የተመረጠው ስራ ኣስፈፃሚ ለትውውቅ የጠራው እንጂ ምንም ሹም ሽር ሀላፊነት መልቀቅ ምናምን የለውም ፤ ትናንት የተመረጡት ይቀጥላሉ በሀረገወይን ቦታ ብቻ ሰው ሊተካ ይችላል።

[ኤርምያስ በላይነህ]

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Dec, 10:06


ወጣቷ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ አካሂዷል።

ኢ/ር ሃይለእየሱስ ፍስሀ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው ሲመረጡ፤ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።

ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጊዮን ሆቴል ሲያካሂድ ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩትን ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚዎችንም መርጧል።

አንጋፋዋ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ፣አቶ ሲሳይ ዳኜ ፣ደ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ፣አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ፣አቶ ሸሀመለ በቀለ፣አቶ በለጠ ወልዴ፣ ወ/ሮ አሰፋሽን ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ተካተዋል።

ፌዴሬሽኑ አለብኝ የሚለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ አርቲስቶችን ወደ ስራ አስፈፃሚ በማምጣት የማርኬቲንግ ስራዎችን ለመስራት እንዳሰበ ለማወቅ ተችሏል።

ቀደም ተብሎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ላይ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ግብዣ ቀርቦለት ሳይቀበለው እንደቀረም ከታማኝ ምንጭ ለመረዳት ተችሏል።

በቀጣይ ተመራጮችን በባላገሩ ሜዳ ፕሮግራም ላይ ይዘን እንቀርባለን።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

03 Dec, 10:08


" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! "

" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል።

ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር ያጣመሩ ናቸው።

በተለይም የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳይቀር እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውና ብዙ ተመልካች ያለው ነው።

ከህጻን እስከ አዋቂ፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ ነው ፍልሚያውን የሚከታተሉት።

ነገር ግን በየዓመቱ ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ የሚደራበት ወር በተለይም ሃይማኖተኛ የሆኑ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የሚያስቀይም ነው።

ምክንያት ? ሊጉ ውስጥ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ ሲባል ዘመቻ ስለሚካሄድበት ነው።

ሰዎቹ " እኩልነትን ለማምጣት " ይበሉት እንጂ በበርካታ ሃይማኖተኛ እግር ኳስ ተመልካቾች እና ተጫዋቾች ዘንድ የሚወገዝ ተግባር ነው የሚፈጽሙት።

የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለግበረሰዶማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው የግብረሰዶማውያኑን መለያ ምልክት ክንዳቸው ላይ እንዲያጠልቁ ያደርጋሉ።

ይህን ዘመቻ የሚያደርጉትም እኤአ ከኅዳር 29 እስከ ታኅሣሥ 5 ነው።

ከቀናት በፊት በነበረ አንድ ጨዋታ ላይ ግን የአንድ ክለብ አምበል " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ምልክቱን ሳያድረግ ቀርቷል።

የተጨዋቹ ስም ሳም ሞርሲ ይባላል ፤ ኢፕስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል ነው።

በእምነቱም የእስላም እምነት ተከታይ ሲሆን የግብፅ ዜጋ ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ቡድኑ ኖቲንግሃም ፎረስት ከተባለው ቡድን ጋር በተጫወተበት ወቅት ክንዱ ላይ ምልክቱን " አላጠልቅም " ብሎ ጨዋታውን ያካሄደው።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ ምልክቱን ያላደረገው " በሃይማኖቱ ምክንያት ነው ፤ ውሳኔውን እናከብራለን " ብሏል።

ክለቡ አክሎም ፤ የግብረሰዶማውያኑን ምልክት የሚያሳየውን የአምበሎች መለያ በኩራት እንደሚደግፍ ፤ ከግብረሰዶማውያን ማኅበረሰብ ጋር አብሮ እንደሚቆም ፤ እኩልነት እና ተቀባይነት እንዲንሰራፋ እንደሚሰራ ገልጿል።

ከሳም ሞርሲ በስተቀር ሌሎች የፕሪሚዬር ሊጉ አምበሎች የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ አጥልቀው ሲጫወቱ ነበር።

#SamMorsy #PremierLeague #Muslim

#tikvahethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

30 Nov, 07:00


ብሪታኒያ ህመምተኛች ስቃያቸው ከበዛ በህክምና እርዳታ በፍቃደኝነት እንዲሞቱ ለማገዝ የሚያስችል ህግ ልታፀድቅ ማቀዷ ተሰምቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

29 Nov, 12:00


የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት
አሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያለው 10 ብር የትኬት ዋጋ ወደ 20 ብር ጭማሪ እንዳሳደገው አሳውቋል።

የታሪፍ ጭማሪው ከታኅሣስ 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል ።

🇪🇹 ኢትዮ Students

27 Nov, 09:41


ቢሊየነሮች "የዘላለም ሕይወት" ምስጢር እየፈለጉ ነው::ግባቸው በባዮሎጂካል ተሃድሶ ሴሎችን በማደስ እርጅናን ማስቀረት ነው

የፔይፓል መስራች ፒተር ቲኤል፣ የኦፕን ኤአይ መስራች ሳም አልትማን፣ የአማዞን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄፍ ቤዞስ እና ሌሎች የተሃድሶ ክኒን እያለሙ ያሉ ሀብታሞች በአልቶስ ላብስ ፕሮጀክት ላይ ገንዘብ ፈሰስ አድርገዋል።

የአልቶስ ላብስ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዳሉት ሀብታሞችን ወደ " እርጅናን የማይቀምሱ ከሰው ወጣ ያለ ሰው ይሄ ክኒን ይለውጣቸዋል “

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

25 Nov, 08:15


ዶናልድ ትረምፕ በመጪው ጥር ስልጣን ላይ ሲወጡ ፆታቸውን የቀየሩ 15 ሺ የአሜሪካ ወታደር አባላትን ከስራ እንደሚያባሩ ይጠበቃል ሲል አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

17 Nov, 09:40


ተያዙ‼️
በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ‼️
በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።
ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አጋርቶ ነበር ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

07 Nov, 03:37


በአዳማ ከተማ የተፈፀመ አሰቃቂ ወንጀል‼️

በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ማናጀርነት ተቀጥራ ምትኖር ሴት ተናግራኛለች በሚል ምክንያት በምግብ ቤቱ ፍየል የሚያርደው ልጅ የልጅቱ ቢሮ ገብቶ 4ጊዜ ልቧን ወግቶ አንገቷን አርዶ ቢሮዋን እራሷ ላይ ቆልፎ ተሰወረ።

በአዳማ ከተማ  ወንጂ ማዞሪያ  እቴቴ ሬስቶራንት በተባለ ጊቢ ውስጥ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው ከቀኑ  7:33 በጠራራ ፀሐይ ሲሆን እድሜዋ 20 መጨረሻዎች የምትገኝ ወጣት ናት።

በሆቴሉም ገንዘብ ያዢነትና  የሂሳብ  ሰራተኞችን  የመቆጣጠር ሃላፊነት ነበራት። ጥቃት  የፈፀመባት ከትላንት በስቲያ  አብሯት በሚሰራ ሰራተኛ ነው። ግለሰቡ ለሬስቶራንቱ ፍየል አራጅ  ሲሆን "ቀን አብረው ገበያ ውለው መተዋል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ታዲያ  በሩን ሰብሮ  እርዳታ  ለመስጠት የፖሊስ የአንቡላንስ አገልግሎት ማግኘት  የተቻለው  ከአንድ ሰዓት በኃላ ህይወቷ ካለፈ በኃላ ነበር።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 09:07


#USA

ስደተኞች በትራምፕ የስልጣን ዘመን ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ዶላንድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር።

ትራምፕ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ነበር ያሉት።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁንም ፕሬዜዳንት ሲሆኑ እንደሚያጠናክሩት ነው በዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ቃል የገቡት።

ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ነው የሚባለው።

ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር ግን እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻቸው ወቅት ፥ ለ4 አመት በስልጣን ሲቆዩ ህገወጥ ስደትን ከማስቆም ባለፈ በህጋዊ ስደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ፥ " ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ፣ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ፤ ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ስደተኞችን " #የሀገራችንን_ደም_እየበከሉ_ነው " በማለት ተናግረውም ብዙዎችን አስቆጥተው ነበር።

በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።

Dv 😁

#TikvahEthiopia
#USA #deport

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 08:47


🇪🇹🇺🇸ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በእርስዎ የስልጣን ዘመን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ብዬ እጠብቃለሁ” ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTYDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 08:08


🇺🇸Us election

ትራምፕ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የተለያዩ የሀገር ባለስልጣናት የእንኳን ደስ አልዖት መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ይገኛል ከነዚህም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና የኤልሳልቫዶር ፕረዚዳንት ናይብ ቡኬሌ በቀዳሚነት ይገኙበታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 06:27


BREAKING: 🇺🇸 Donald Trump officially elected President of the United States of America.

© WatcherGuru

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 05:39


የዶላንድ ትራምፑ ፓርቲ ሪፐብሊካኖች የዩኤስ ሴኔት አብላጫ ድምፅን አሸንፈው ከ4 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ  ምክር ቤቱን መቆጣጠራቸውን ሲል አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 03:15


ዶናልድ ትራምፕ በድምፅ ቆጠራ መሰረት በአራት ሚሊዮን የድምፅ ልዩነት እየመሩ ይገኛል። የቁልፍ ግዛቶች ውጤት እየተጠበቀ ይገኛል።

#ዳጉ_ጆርናል

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Nov, 03:10


⚡️⚡️ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ካሸነፉ ነገውኑ የሩስያው መሪ ለቭላድሚር ፑቲን ጋር 'ሊደውሉ ' ይችላሉ - CNBC

🇪🇹 ኢትዮ Students

04 Nov, 07:53


የአሜሪካ ጦር ለኒውክለር ጦርነት ብቻ ይዘጋጀውን B-52 ኒውክለር ቦምበር ወደ ኢራን እና እስራኤል መገኛ መካከለኛው ምስራቅ መላኩን አሳውቋል‼️

አለም አቀፍ የዜና ቋቶች የተፈራው ደረሰ በመማለት በሰበር ባስተጋቡት ዜና ላይ አሜሪካ ይሄን ተንቀሳቃጭ የጦር ማዘዣ የሚባለውን የሞት እጅ ወደ ቀጠናው የላከችው ኢራን እስራኤል ካጠቃች በቀጥታ ኢራንን ለመደብደብ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሄ በ ስድስት ፓይለቶች የሚዘወረው ግዙፍ ኒውክለር ቦምበር አውሮፕላን አየር ላይ ለመምታት የማይቻል እና አሜሪካ ለሩሲያው የሞት እጅ የምድራችን ሃይል ለሚባለው Tu-95ms ኒውክለር ቦምበር ታሳቢ አድርጋ የሰራችው የመጨረሻው የኒውክለር ቦምበር ነው።

አሜሪካ በዚህ ልክ ለአርማጌዶን ያዘጋጀችውን ጦር ወደ እስራኤል መገኛ የላከችው ኢራን ምን አይነት ጥቃት ብታስብ ነው የሚል ከባድ ጥያቄን አስነስቷል።

©ayuzehabesha

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Nov, 05:36


በምስራቅ ስፔን በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 158 ደርሷል።

የጠፉ ሰዎች እየተፈለጉ መሆናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ለተጎጂ ቤተሰቦች ሪያል ማድሪድ የእግር ኳስ ክለብ አንድ ሚልየን ዪሮ እርዳታ ሰጥቷል።

🧐 እነዚህን ሁሉ ስታዪ ( ጦርነት,ጎርፍ,የመሬት መንቀጥቀጥ....) ምን ታስተውላላችሁ ?

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

24 Oct, 19:38


ከዚህ በፊት ለሪሚዲያል ተማሪች በተቋማት የሚሰጠው ውጤት 30% ሲሆን 70% ደግሞ የሚሰጠው ከት/ት ሚኒስቴር ነበር ። አሁን ግን ይህ አሠራር ተሻሽሎ 100% ከማዕከል(በትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጡ ምዘናዎች) በኩል እንዲሰጥ ተወስኗል። ተማሪዎች በሚማሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው 30% የውጤት ምዘና  አሰጣጡ ወጥነት ስለሚጎድለው ይሄን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።

@ETHIOSTUDNETS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

22 Oct, 03:32


🔈#መርካቶ

" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንድ ሰው በዚህ የከፋ ጊዜ አብሮ ተጋግዞ እሳቱን ማጥፋት ሲገባው የራሱ ያልሆነን ንብረት ለመዝረፍ ሲሯሯጥ ማየት እጅግ ያሳዝናል።

ሌላው በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተከታይ ለማፍራት ሲባል ያልተባለውን በማለት፣ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ' ላይክ ፣ ሼር ፣ ፎሎው ' አድርጉን እያሉ በዚህ የችግር ወቅት ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን መመልከቴ አሳስዝኖኛል።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)

#tikvahethiopia

🇪🇹 ኢትዮ Students

17 Oct, 03:19


#BreakingNews በአዲስ አበባ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ተሰማ

ለሰከንዶች በቆየዉ ይህ የመሬት ንዝረት በከተማዋ በተወሰኑ አከባቢዎች መሰማቱ ተነግሯል ።

በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ፣ ሰሚት ፣ጀሞ ፣  መካኒሳ እንዲሁም ከክልል አዋሽ 40 ላይ ከምሽቱ 5 ሰዓት 10 ገደማ ለሰከንዶች የቆየ ንዝረት ማጋጠሙን ለካፒታል ከነዋሪዎች የደረሰው መረጃ ያመላክታል ።
Capital

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

13 Oct, 06:22


የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ዳግም መሰማቱን ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ አረጋገጡ!!


በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሊ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

10 Oct, 10:18


አስፈሪው የተፈጥሮ ክስተት‼️

ሚልተን የተሰኘው አውሎ ነፋስ በፍሎሪዳ ስቴት አካባቢ 15 ጫማ የሚደረስ ማዕበል ሊያመጣ እንደሚችል ተጠቁሟል። ይህንንም ተከትሎ ከላይ በቪድዬ እንደምትመለከቱት በፍሎሪዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ ከተማዋ በዚህ ሰዓት ዝምታ ወርሷታል ።

እ.ኤ.አ በ 2022 በፎርት ማየርስ ከተማ ተከስቶ ከነበረው ኢያን አውሎ ነፋስ በበለጠ አደገኛ እንደሆነ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል። ሀገሪቱ የተፈጥሮን አደጋ ለመቋቋም ዝግጅት ላይ ነች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዚሁ ነፋስ ምክንያት ጉዟቸውን መሰረዛቸው ተሰምቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Oct, 18:39


#Update: " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Oct, 17:35


ሰበር ዜና ‼️

የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል

ከምሽቱ 2:10 ሰዓት ላይ በዓደይ አበባ ኖህ ረሪል ስቴት አራብሳ መንገድ ላይ ፣ ሃያት፣ ሲኤሚሲ ፣ ሜክሲኮ ፣ በንዝረቱ ሰዎች ከቤታቸው ወጥተዋል

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Oct, 13:05


🇵🇸🇺🇸 ዋይት ሀውስ አቅራቢያ በተካሄደ የፍልስጤም ድጋፍ ሰልፍ ላይ አንድ ሰልፈኛ እራሱን አቃጠለ

ክስተቱ የተፈጠረው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደችው ያለው ጦርነት የተጀመረበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ዋይት ሀውስ አቅራቢያ ቅዳሜ እለት በወጡበት ወቅት ነው። እንደ የጋዛ ባለስልጣናት ገለጻ በእስራኤል ጥቃት ከ41,000 በላይ ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ ወደ 97,000 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል።

እራሱን ያቃጠለው ሰልፈኛ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል እንደተወሰደ እና ለህይወት አስጊ የሆነ የአካል ጉዳት ስላልደረሰበት ጤንነቱ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

1,000 የሚጠጉ ሰዎች በተሳተፉበት ሰልፍ የፍልስጤምን ነጻነት የሚጠይቁ እና እስራኤል የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጥሪ የሚያቀርቡ ድምጾች የተሰሙ ሲህን የፍልስጤም ባንዲራም ሲውለበለብ ታይቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

06 Oct, 12:14


እስራኤል የመበቀል ውሳኔ አሳልፋለች‼️

በዚህም መሰረት እስራኤል ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ በኢራን ላይ የበቀል ጥቃት ለመፈፀም ወስናለች።
የበቀል እርምጃው ከባድ እንደሚሆን ቤኒያሚን ኔታኒሁ ገልጿል።

"የመኖራችን ብቸኛ ስጋት ኢራን ናት " ያለው ኔታኒያሁ እስራኤል ኢራንን ታጠቃለች ብሏል።

እስራኤል በዜጎቿ ላይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። የኢራን ዳግም አፀፋ በመፍራትም ዜጎቿ ከመሰባሰብ እንዲቆጠቡ አዛለች። የሀገሪቱ አየር ክልልም የሚዘጋ ይሆናል።

የእስራኤል የጥቃት ኢላማዎች በዋናነት ሁለት ናቸው አንድ የኢራን የኑክሌያር ፋሲሊቲ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የነዳጅ ጣቢያዎቿ ናቸው።

በኢራን ኑክሌየር ፋሲሊቲ ላይ እስራኤል ጥቃት ብትፈፅም ያን ያክል ጉዳት ታደርሳለች ተብሎ አይታሰብም። ምክንያቱም የኢራን ኑክሌየር ማብላያዎች እነዚህን የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃቶችን ታሳቢ በማድረግ ከመሬት በታች በጥልቅ የተገነቡ ናቸው ። የነዳጅ ጣቢያዎቿ ግን ተጋላጭ ናቸው።

ኢራን በበኩሏ የነዳጅ ጣቢያየ በእስራኤል የሚመታ ከሆነ እስራኤል አንድም የሀይል ጣቢያ አይኖራትም ሁሉንም አጠፋቸዋለሁ ብላለች። የዳግም በቀል እርምጃዋም ከእስካሁኑ ሁሉ የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቃለች።

🇪🇹 ኢትዮ Students

02 Oct, 06:41


በአሜሪካ ኒዮርክ የአይጦችን ቁጥር ለመቀንሰ የእርግዝና መከላከያ እንክብል ሊስጣቸው ነው

አይጦቹን ቁጥር ለመቀነስ በመርዝ መግደል ቢታሰብም ከእንሰሳት መብት ጋር አብሮ የሚሄድ ስላልሆነ በእርግዝና መከላከያ እንክብሉ ቁጥራቸውን ለመቀነስ መታቀዱን ተነግሯል::

በኒዮርክ ከ3 ሚልየን በላይ አይጦች አሉ::

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Oct, 17:48


የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ እስራኤል ለኢራን ጥቃት ምላሽ ከሰጠች "አስከፊ ጥቃት" እንደሚደርስባት አስጠንቅቋል

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Oct, 17:48


እስራኤላውያን የኢራንን ጥቃት በመስጋት ቤት የተሸሸጉ ሰዎች  ለቀው እንዲወጡ ተፈቅዶላቸዋል።ከእንግዲህ ኢራን ስጋት አይደለችም  - ወታደራዊ ቃለ አቀባይ

ሀገሪቱ የአየር ክልሏንም ከፍታለች።

🇪🇹 ኢትዮ Students

01 Oct, 17:04


ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤል መተኮስ ጀመረች።

ኢራን ዛሬ ምሽት የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል እያዘነበች ነው።

እስካሁን ባለው 200 ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን ታይንስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

የሀገሪቱ ዜጎች በአደጋ መጠለያ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

በተያያዘ ሁሉም የ DIGITAL CURRENCY (CRYPTO) በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለም ይገኛል

🇪🇹 ኢትዮ Students

30 Sep, 04:57


አንድ የሩሲያ ቱሪስት በጆርጂያ ውስጥ በጓደኛዋ ሞባይል ቪዲዮ እየተቀረጸች እየተራመደች ሳለ መሻገሪያ የመሬት ድልድይ ውስጥ በመግባቷ ወድቃ ሞተች።

ሰሞኑ አሪና እና ጓደኛዋ በምሽት በተብሊሲ ዙሪያ እየተዘዋወሩ ፣ ዘፈኖችን እየዘፈኑ እና እየተዝናኑ በሞባይላቸውም ቪዲዮ እየተቀረፁ ነበር ።

አሪና ተሰናክላ ወደ መሻገሪያ የመሬት ድልድዩ እስክትወድቅ ድረስ እየዘፈኑ ነበር።

። አሪና የራስ ቅል ላይ በደረሰባት ጉዳት ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ከአደጋው በፊት ሟቿ "ለመጨረሻ ጊዜ" የተሰኘ ዘፈን እየዘፈነች ነበር ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

🇪🇹 ኢትዮ Students

26 Sep, 10:52


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የጥንቃቄ መልዕክት

ሰሞኑን የተለያዩ የዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም ሽልማቶችን ለመሸለም በሚመስል መልኩ የኢትዮ-ቴሌኮም ነጻ የዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አረጋግጧል።

ይህ መልዕክትም የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎች የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

በጥቃት አድራሾቹ ለተጠቃሚዎች አጓጊ የሚመስሉ ሆነዉ ከኋላቸዉ የሳይበር ጥቃት የያዙ ሲሆን የተጠቃሚዎችን ቀልብ ለመሳብ የኢትዮ ቴሌኮም ረጅም ጊዜ ተጠቃሚ በሚል በሲም ካርድ የቆይታ ጊዜ የሚል ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል፡-

• 6 ወር የቆየ ሲም- 10GB

• 1 አመት እና ከዚያ በላይ- 20GB

• 5 አመት እና ከዚያ በላይ- 50GB እንሽልማለን የሚሉ ናቸዉ።

ነገር ግን ያቀረቡት ማታለያ እንጂ ምንም አይነት ሽልማት እንደማይሰጡ ማህበረሰቡ እንዲያዉቅና ሊንክ ተጠቃሚዎችን ለማጥመድ ታስቦ የተዘጋጀ በመሆኑ ሊንኩን እንዳይከፍቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳስቧል፡፡

እንደዚህ አይነት የማጭበርበር ሁኔታዎች በበዓል ወቅቶች በስፋት የሚከሰቱ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

🇪🇹 ኢትዮ Students

17 Sep, 06:29


ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።

Professor Beyene Petros embodied the spirit of peaceful political struggle, playing a pivotal role in fostering a culture of non-violence and constructive political dialogue in Ethiopia. I am deeply saddened to hear of his passing after a prolonged period of medical care. May his legacy endure, and may he rest in eternal peace.

🇪🇹 ኢትዮ Students

09 Sep, 20:06


ተፈታኝ ለሆናችሁ እና የ12 ተኛ ውጤት እንደተለቀቀ ማየት ለምትፈልጉ ከታች ያለውን Link ተጠቅማችሁ ማየት ትችላላችሁ ለጓደኞቻችሁም ሼር አርጉላቸው

@Dotpayet_bot
@Dotpayet_bot
@Dotpayet_bot

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

🇪🇹 ኢትዮ Students

08 Sep, 19:36


«ጥሩ ዜና ይዤ እመለሳለሁ ብዬ ነበር አልተሳካም» እናት

የእነ ህፃን ሶሊያና እና ሄራን የህክምና ጉዳይ በደቡብ አፍሪካ ሆስፒታል ተስፋ አላቸው ተብሎ ተነግሯቸው ተስፋው ወደ እውነት እንዲቀየር ገንዘብ ተሰብስቦ ወደ ባንኮክ በማቅናት በባንኮክ በተደረገ ምርመራ ተስፋ ቢኖራቸውም በመጨረሻ የተደረገው ህክምና እንደማይሆን እንዳልተሳካ ተነግሮን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰናል ስትል እናታቸው በሰይፉ በኢቢኤስ ቀርባ ተናግራለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS