MOR North West STO @northwestmor Channel on Telegram

MOR North West STO

@northwestmor


ይህ ገፅ የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አ/ግ/ከ/ቅ/ፅ/ቤት  የቴሌግራም ቻናል ነው።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን 
https://shorturl.at/l988k
☎️ +251115574182

MOR North West STO (Amharic)

በተጨማሪም የሰሜን ምዕራብ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ፅ/ቤት የታክስ ትምህርትና መረጃ የሚሰጥበት አዳዲስ ቻናል በሚባለው ምህዳር ውስጥ ነው። 'MOR North West STO' ብሔራዊ ችግር፣ ትላንት፣ ተረካችሁ፣ ህዝቦችን እና ለውጥቶችን የተለያዩ መረጃዎችን ባይታወቅንም እንቅስቃሴ በማስጨበጥ የተለያዩ መረጃዎችን እንባዳለን። ከዚህ በታች ሰሞኑ 'MOR North West STO' በዚህ ችግርትና መረጃዎችን ስንት እናገለገላለን? እባኮት እንባዝናለን እንባዝንና ላይ ስለ እንባዝን እናዳልገዋለን።

MOR North West STO

02 Dec, 11:48


የክፍል አንድ ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ፡፡

ህዳር 23-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሶስተኛ ዙር የታክስ ትምህርት ሞጁላር ሰልጣኞችን በዛሬው እለት የክፍል አንድ ማጠቃለያ ፈተና ሰጠ፡፡

በክፍል አንድ ሰልጣኞች ቀጥተኛ ታክስ በተመለከተ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት ፣ከቤት ኪራይ እና ከንግድ ሥራ የሚገኝ ገቢ ግብር ፣ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት አስተዳደር ስርዓት (Withholding Tax) ላይ ያተኮረ ሰፊ ስልጠና ወስደዋል ።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን 
https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

29 Nov, 11:18


የክፍል ሁለት ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ።

ህዳር 20-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ዙር የርቀት ታክስ ትምህርት ሞጁላር ሰልጣኞች በዛሬው እለት የክፍል ሁለት ማጠቃለያ ፈተና ሰጠ፡፡  

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

29 Nov, 06:11


በተሻሻለዉ የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ቁ. 188/2017 መሠረት የተካተቱና የተደረጉ ለዉጦች ፦

1.እያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ሲታተም ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) ተካቶ ካልታተመ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
2.ከአንድ በላይ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ ያለዉ ታክስ ከፋይ
ሀ) ድርጅት ከሆነ ፡-
(1) የማንዋል ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄ ሲያቀርብ ለእያንዳንዱ ቅርንጫፍ የሚያስፈልገዉን የጥራዝ ብዛት መግለጽ አለበት ፤
(2) ከዋናዉ አድራሻ በተጨማሪ ደረሰኙ ሊታተምለት የተፈለገዉ የንግድ ዘርፍና የቅርንጫፍ አድራሻዉ ተገልጾ መታተም አለበት 
ለ) ግለሰብ ከሆነ ፡-
(1) የማንዋል ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄ ሲያቀርብ እያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ ለሚካሄድበት ቦታ የሚያስፈልገዉን የጥራዝ ብዛት መግለጽ አለበት ፡፡
(2) ከዋናዉ አድራሻ በተጨማሪ ደረሰኙ ሊታተምለት የተፈለገዉ የንግድ ዘርፍ እና የንግድ ሥራ ዘርፉ የሚካሄድበት ቦታ  ወይም አድራሻ ተገልጾ መታተም አለበት ፡፡

መሸጋገሪያ
1.ማንኛዉም ታክስ ከፋይ ይህ የማሻሻያ መመሪያ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አሳትሞ ያልተጠቀመባቸዉን ደረሰኞች መጠቀም የሚችለዉ የማሻሻያ መመሪያዉ ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባለዉ ለሶስት ወር ጊዜ ብቻ ነዉ ፡፡
2.በተሰጠዉ በሶስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ደረሰኞችን በተመለከተ ታክስ ከፋዩ ተመዝጋቢ ለሆነበት የታክስ ባለሥልጣኑ ቅ/ጽ/ቤት ሪፖርት በማደረግ ደረሰኞቹ እንዲወገዱ የማድረግ ግዴታ አለበት ፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

28 Nov, 12:26


ውድ ግብር ከፋዮቻችን

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 7 ማናቸውም የፌደራል እና የክልል መንግሥት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ ኤጀንሲ ወይም ሌላ አካል፣ የአካባቢ አስተዳደሮች፣ ማህበራት፣ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የታክስ ሕጎችን በማስፈፀም ረገድ ከባለሥልጣኑ ጋር የመተባበር ግዴታ አለባቸው በሚል ተደንግጓል፡፡
ሰለሆነም ድርጅትዎ በየወሩ የፈጸማቸውን የግዥና ሽያጭ መረጃዎችን ወር በገባ ከ1-30 ባሉት ቀናት ማሳወቅ የሚጠበቅበት ሲሆን የጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም የግዥና ሽያጭ መረጃ ከህዳር 01-30/03/2017 ዓ/ም ድረስ የሚታወቅ በመሆኑ ደርጅትዎ የታስ ሲስተም ተጠቃሚ ከሆነ በታስ ሲስተም መረጃውን እንዲልክ የታስ ሲስተም ተጠቃሚ ካልሆነ በታክስ መረጃ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ላይ በመምጣት መረጃችሁን  እንድትሳወቁ  እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 114/7/መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እየገለጽን የታስ ሲስተም ተጠቃሚ  የሆናችሁ ግብር ከፋዮች ምንም አይነት ግዥና ሽያጭ ከሌላችሁ በኢሜል [email protected] በሚል መረጃውን እንድትልኩልን ስንል እናሳስባለን፡፡

ከታክስ መረጃና ሽ/መ/መ አስ/የስራ ሂደት
ሰ/ም/አ/አ/አ/ግ/ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

MOR North West STO

28 Nov, 12:00


የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች

ሕዳር 19/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነጻ የሚሆነው፡-

1. በስራ ባህሪው ምክንያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2,200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

2. አንድ ተቀጣሪ በስራ ባህሪው ምክንያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

3. አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስርያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም ባይቀርብም ለዚህ ዓይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/F9ahO

MOR North West STO

27 Nov, 11:57


የክፍል አንድ የምጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ህዳር 18-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን መሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሠራሮች እንዲሁም አዋጆች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ ለ2017 በጀት አመት ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች በክፍል አንድ ቀጥተኛ በሆኑ ታክሶች ማለትም ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና ወጪ፣ ከንግድ ስራ እና ኪራይ ገቢ የሚገኝ ገቢ እንዲሁም ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ስለማስቀረት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረው የምጅላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

25 Nov, 11:10


በአራት ወራት ውስጥ ከ312 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል
ሕዳር 16/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የአራት ወራት የገቢ እና የዋና ዋና ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ባለፉት አራት ወራት ብር 311.56 ቢሊዮን ጥቅል ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 312.56 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 100.3 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ118.58 ቢሊዮን ብር ብልጫ እና የ61 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/rO1Me

MOR North West STO

16 Nov, 07:27


የክፍል አንድ ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ።

ህዳር 7-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ዙር የርቀት ታክስ ትምህርት ሞጁላር ሰልጣኞች በዛሬው እለት የአንደኛ ሴሚስትር ማጠቃለያ ፈተና ሰጠ፡፡  

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

14 Nov, 08:29


#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/JNqW7

MOR North West STO

13 Nov, 07:10


የአራት ወራት አፈጻጸማችን ውጤታማ እና ትምህርት ያገኘንበት ነው
- ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የጥቅምት ወር እና የአራት ወር አቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል ::

በግምገማው ሶስት ዋና ዋና ጉዳይች የተነሱ ሲሆን የጥቅምት ወር እና የአራቱ ወራት የገቢ አሰባሰብ ምን እንደሚመስል፣ በበጀት ዓመቱ ኦዲት የሚደረጉ ግብር ከፋዮች ትንተናን በተመለከተና የገቢ አሰባሰቡን ለመደገፋ የተደረገው የሰው ኃይል ስምሪት ውጤታማነት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል::

በመድረኩ የጥቅምት ወር እና የአራቱ ወራት የገቢ አሰባሰብ ውጤታማ ሥራ መሰራቱን እና የተገኘውም ውጤት የሚያኮራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ተናግረዋል:: ለዚህም ውጤት መገኘት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተጣላባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሰሩት ጠንካራ ሥራ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ በሚኒስቴሩ በልዩ ሁኔታ የተዋቀረውና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በገቢ አሰባሰብ ሲደግፍ እና ክትትል ሲያደርግ የነበረው ቡድን የሰራው ሥራ የሚጠቀስ ነው ብለዋል ::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- http://tiny.cc/ov2vzz

MOR North West STO

12 Nov, 09:03


ውድ የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብራችሁን በወቅቱ አሳወቃችሁ ለከፈላችሁ ታማኝ ግብር ካፋዮቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብን የቅ/ፅ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በጥቅምት ወር እንድንሰበስብ የተሰጠንን እቅድ ለማሳካት ባደረጋችሁት ርብርብ 672 ሚሊየን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን የእቅዱ 168% በላይ ማሳካት በመቻላችን የተሰማኝን ደስታ እየገለፅኩ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማመስገን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።

MOR North West STO

11 Nov, 10:56


የ 2017 በጀት አመት የሶስተኛ ዙር የሞጁላር ትምህርት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

ህዳር 2-2017 ዓ/ም አ.አ
በገቢዎች ሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት  የ2017 በጀት አመት የሶስተኛ ዙር የታክስ ትምህርት ሞጁላር ሰልጣኞችን ማሰልጠን ጀመረ።

ስልጠናው የታክስ ህግ፣ደንብና መመሪያ  ለግብር ከፋዮች ግንዛቤ ለመስጠት ያለመ ነው ሲሉ በእለቱ ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ናርዶስ ብርሃኑ ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ሴምስትር የታክስ ትምህርት ሞጁላር ትምህርቱም ሲጀምር ትኩረቱን ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ላይ ያደረገውን የመጀመሪያ ሞጁል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

10 Nov, 14:28


ውድ ግብር ከፋዮቻችን

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ  የመክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30 /2017 ዓ.ም ቅዳሜ ቀን ስለዋለ ነገ ሰኞ ህዳር 2/2017 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12፡30 ድረስ አገልግሎት የምንሰጥ በመሆኑ ግብርዎን በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣ ቅጣትና ወለድ ለመዳን ነገውኑ ግብርዎን አሳውቀው ይክፈሉ!

ግብር ለሀገር ክብር!

የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

MOR North West STO

09 Nov, 08:38


ካሉበት ቦታ ሆነው ግብርዎን የሚያሳውቁበት እና የሚከፍሉበት መንገድ

ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)

ኢታክስ የሚያጠቃልላቸው የአገልግሎት ዓይነቶች

ኢ-ፋይሊንግ ፦
ግብርን ወደ ታክስ ባለስልጣኑ መቅረብ ሳያስፈልግ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የማስታወቅ አሠራር ሥርዓት ነው፡፡

ኢ-ፔይመንት ፦
ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ቀደም ሲል በኢ-ፋይሊንግ በላከው መረጃ ክፍያውን እንዲያስተናግዱ ውል በተፈራረሙ ባንኮች በኩል ክፍያውን የሚከፍልበት ስርዓት ነው፡፡

ኢ-ክሊራንስ፦
ግብር ከፋዪ ድርጅት የሚኒስቴር መ/ቤት ድረ-ገጽ በመጠቀም የታክስ ክሊራንስ ለመጠየቅ የሚያስችለው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ግብሩን የከፈለ እና ምንም ዓይነት የታክስ ክፍያ የሌለው ግብር ከፋይ በቀላል መንገድ የዓመታዊ ንግድ ፈቃድ ማደሻም ሆነ ሌሎች ክሊራንሶች በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት የአሠራር ሥርአት ነው፡፡

የታክስ ነክ መረጃ አገልግሎት፦
ኢ-ታክስን ተጠቅሞ አንድ ግብር ከፋይ መጠየቅ የሚፈልጋቸውን ታክስ ነክ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ሲሆን ግብር ከፋዪች የሥርዓቱ ተጠቃሚ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኝነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የአሠራር ሥርዓት ነው፡፡

MOR North West STO

08 Nov, 13:02


የጥቅምት ወር ገቢ አሰባሰብ የመጨረሻ ቀናት

ጥቅምት 29-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 በጀት አመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ማሳወቂያ ጊዜ 1 ቀን ብቻ የቀረውት በመሆኑ ግብር ከፍዮች እያሳወቁና እየከፈሉ ይገኛሉ። መስተንግዶውም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

08 Nov, 06:54


ውድ ግብር ከፈዮቻችን

የ2016 ግብር ዘመን ዓመታዊ ግብራችሁን አሳውቃችሁ የምትከፍሉበት ጊዜ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ግብርዎን አሳወቀው ሚከፍሉበት የመጨረሻ ቀናት ዛሬና ነገ ብቻ ስለሆነ በወቅቱ ካለመክፈል ከሚመጣ ቅጣትና ወለድ ለመዳን ዛሬውኑ ግብርዎን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ።

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

07 Nov, 10:53


ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦
ሀ) ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
ለ) ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
▫️  የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
▫️  መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
▫️ ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

MOR North West STO

07 Nov, 05:01


2 ቀን ቀረው!

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብር የመክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ስለሆነም ግብርን በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣ ቅጣትና ወለድ ለመዳን ዛሬውኑ አሳውቀው ይክፈሉ!

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

06 Nov, 13:18


የታክስ ንቅናቄ የመኪና ላይ ቅስቀሳው ተጠናክሮ ጥሏል

ጥቅምት 27-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሊጠናቀቅ ሶስት ቀናት በቀሩት የግብር ማሳወቂያ ቀናት ግብር ከፋዮች ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈል በመጨረሻ ሰዓት ከሚያጋጥም የሲስተም መጨናነቅ እንዲድኑ የሚያሳስብ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ሲሆን አመታዊ ሪፖርት ሲቀርብ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን የያዘ ብሮሸርም በተለያዮ ክፍለ ከተማዎች እና ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች ላይ ስርጭት አካሂዷል ፡፡

ቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

05 Nov, 14:57


የሻይ ቡና መስተንግዶ ዛሬም ሲቀጥል ግብር ከፍዮች የ2016 በጀት አመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ማሳወቂያ ጊዜ 4 ቀናት ብቻ የቀሩት በመሆኑ እያሳወቁና እየከፈሉ ይገኛሉ።

እስካሁን ያላሳወቃችሁ ግብር ከፍዮች የማሳወቂያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊትና በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብርዎን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን 
https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

05 Nov, 13:03


የመኪና ላይ ቅስቀሳው ዛሬም ቀጥሏል

ጥቅምት 26-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች በቀሩት ጥቂት ቀናት ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈል በመጨረሻ ሰዓት ከሚያጋጥም የሲስተም መጨናነቅ እንዲድኑ የሚያሳስብ ቅስቀሳ በተለያዮ ክፍለ ከተማዎች እና ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች ላይ አካሂዷል ፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

05 Nov, 12:30


የክፍል ሦስት ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ

ጥቅምት 26-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮችን ግንዛቤ በማሳደግ ግብር ከፋዮች የታክስ ህጎችን አውቀው ግዴታቸውን በመወጣት መብታቸውን እንዲጠይቁ ለማድረግ የተዘጋጀውን ተከታታይ ስልጠና ለወሰዱ የ2017 ዓ.ም 1ኛ ዙር ሰልጣኞች የ3ኛ ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና ሰጠ፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

05 Nov, 09:51


#4_ቀን_ቀረው!

ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብር የመክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በቀሩት ጥቂት ቀናት ሊያጋጥም ከሚችል የሲሰተም መጨናነቅ፣ ወረፋ፣ እንዲሁም በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣ ቅጣትና ወለድ ለመዳን ግብሮዎን ዛሬውኑ አሳውቀው ይክፈሉ!

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

04 Nov, 12:57


ለግብር ከፋዮች የሻይ ቡና መስተንግዶ ተደረገ።

ጥቅምት 25-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአመታዊ የንግድ ትርፋቸውን አሳውቀው ለሚከፈሉ ግብር ከፋዮቹ የሻይ ቡና መስተንግዶ እያካሄደ ነው።

ግብር ከፍዮች የ2016 በጀት አመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ማሳወቂያ ጊዜ 5 ቀናት ብቻ የቀሩት በመሆኑ የማሳወቂያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊትና በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብርዎን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ ።

ቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን  https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

01 Nov, 14:42


ውድ ግብር ከፋዮቻችን

ግብር ከፋዮች በታክስ ህግ ላይ ግንዛቤያቸው ከፍ እንዲል በማድረግ መብታቸውና ግዴታቸው እንዲያውቁ በገቢዎች ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ አዲስ ኣበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የታክስ አዋጅ ደንብና መመሪያ ያካተተ ሰነድ በማዘጋጀት ለተከታታይ ቀናት በነፃ ስልጠናው በመስጠት በሰርተፊኬት እያስመረቀ ይገኛል፡፡
ስለሆነም እርስዎ ስልጠናውን ለመውሰድ 6ኛ ፎቅ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ስራ ሂደት መጣችሁ መረጃ በመጠየቅ እንድትመዘገቡ  እናሳስባለን፡፡
   ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251115574182 ይደውሉ

የታክስ ህግን በማወቅ መብታችንን በማስከበር ግዴታችን እንወጣ !!

MOR North West STO

01 Nov, 12:00


ለ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ዙር የርቀት ትምህርት ሰልጣኞች  የማጠናከሪያ ትምህርት ተሰጠ።

ጥቅምት 22-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 የመጀመሪያ ዙር የርቀት ሞጁላር ትምህርት ለሚከታተሉ ግብር ከፋዮች ቀጥተኛ ታክሶች ላይ ያተኮረ የግማሽ ቀን የማጠናከሪያ ትምህርት(ቲቶር) ሰጠ።

የርቀት ትምህርቱ ከመደበኛው የሞጁላር ትምህርት በተጨማሪ ስልጠናውን በአካል ተገኝተው መውሰድ ለማይችሉ የድርጅት ስራ አስኪያጆች እና ም/ስራ አስኪያጆች እንደ አማራጭ የተጀመረ ሲሆን ሰልጣኞችም ካላቸው የስራ ሁኔታ እና ጊዜን ያገናዘበ ነው ሲሉ ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ናርዶስ ብርሃኑ ገልፀዋል።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

01 Nov, 07:31


#8_ቀን_ቀረው!
ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብርን የመክፈያ ወቅት ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡
በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብሮዎን አሳውቀው ይከፈሉ!
የገቢዎች ሚኒስቴር
ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

31 Oct, 14:31


አመታዊ ግብር መክፈያ ወቅትን መሰረት ያደረገ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ተካሄደ፡፡

የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ለማቀላጠፍ እና ተደራሽ ለማድረግ ከጥቅምት 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሰኞ እሰከ አርብ እስከ ምሽቱ 12፡30 ሰዓት ቅዳሜን ደግሞ እስከቀኑ 10፡00 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጎን ለጎን ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ የመኪና ላይ ቅሰቀሳ አካሂዷል፡፡
ለተከታታይ ቀናት በቆየው ቅስቀሳም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ብዛት ያላቸው ግብር ከፋዮች በሚገኙበት ክፍለ ከተሞች እና ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች ላይ ቅስቀሳ የተደገ ሲሆን  ቅስቀሳውም እስከ ጥቅምት 30/2017 ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

31 Oct, 13:19


9 ቀን ቀረው!

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብርን የመክፈያ ወቅት ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብሮን አሳውቀው ይከፈሉ!

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

30 Oct, 14:16


https://youtu.be/IrOqI50u9sI?si=axSJcnIFykH8nimz

MOR North West STO

30 Oct, 12:57


የክፍል ሦስት ስልጠና ተሰጠ

ጥቅምት 20-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች የታክስ ስሌትና የታክስ ማሳወቅ ላይ ያተኮረ ተሰጧል፡፡ ስልጠናዉን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ናርዶስ ብርሃኑ ሲሆኑ የታክስ ስሌትን ማወቅ ችግሮችን ለመፍታትና ለንግድ ያለው ጠቀሜታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

29 Oct, 11:58


የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ

ጥቅምት 19-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ድጋፍ እና ክትትል ቡድን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ስራተኞች በማስተባበር በዛሬው እለት በጌርጌሴኖ የአእምሮ ሕሙማን እና ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት ከሰራተኛው የተሰበሰበ የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ድጋፍ እና ክትትል ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ አበባ መኮንን የቅ/ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው የተደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ገልፀዋል ።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

29 Oct, 11:34


ውድ ግብር ከፋዮቻችን

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ዓ.ም  አንቀጽ 7 ማናቸውም የፌደራል እና የክልል መንግሥት፣የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ኤጀንሲ ወይም ሌላ አካል፣ የአካባቢ አስተዳደሮች፣ማህበራት፣ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የታክስ ሕጎችን በማስፈፀም ረገድ ከባለሥልጣኑ ጋር የመተባበር ግዴታ አለባቸው በሚል ተደንግጓል፡፡

ሰለሆነም ድርጅትዎ በየወሩ የፈጸማቸውን የግዥና ሽያጭ መረጃዎችን ወር በገባ ከ1-30 ባሉት ቀናት ማሳወቅ የሚጠበቅበት ሲሆን የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የግዥና ሽያጭ መረጃም ከጥቅምት 01- 30/02/2017 ዓ/ም ድረስ የሚታወቅ በመሆኑ ደርጅትዎ የታስ ሲስተም ተጠቃሚ ከሆነ በታስ ሲስተም መረጃውን እንዲልክ  የታስ ሲስተም ተጠቃሚ ካልሆነ በታክስ መረጃ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ላይ በመምጣት መረጃችሁን  እንድትሳወቁ  እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 114/7/መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እየገለጽን የታስ ሲስተም ተጠቃሚ የሆናችሁ ግብር ከፋዮች ምንም አይነት ግዥና ሽያጭ ከሌላችሁ ኢሜል [email protected]   መረጃ እንድትልኩልን ስንል እንጠይቃለን፡፡

የታክስ መረጃና ሽ/መ/መ አስ/የስራ ሂደት

ስ/ም/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት

MOR North West STO

28 Oct, 10:38


#12_ቀን_ቀረው!

ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብርን የመክፈያ ወቅት ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብሮን አሳውቀው ይከፈሉ!

የገቢዎች ሚኒስቴር

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

26 Oct, 14:06


የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

ጥቅምት 16-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ671.49 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት በዛሬው እለት የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማን ያካሄደ ሲሆን በሩብ አመቱ 562.97 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 671.49 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 119.28% ማሳካት መቻሉን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእቅድ አፈጻጸም ክትትል ቡድን መሪ ወ/ሮ ሮማን አለባቸው የሩብ አመት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል ። እንዲሁም አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 82.63% በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ ደበሱ በሩብ ዓመቱ ለተመዘገበው ስኬት አመራሩን እና ሰራተኛውን አመስግነው በመጪው የጥቅምት ከፍተኛ ገቢ የሚሰበሰብበት ወቅት እንደመሆኑ በሩብ አመቱ የነበሩንን ጥንካሬዎቻችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በመሙላት ከተያዘው እቅድ በላይ ማሳካት እንደሚገባና ለዚህም በየደረጃው ያለው አመራር እና ሰራተኛ የራሱን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል።

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን 
https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

26 Oct, 09:00


በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ  እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብሮን አሳውቀው ይከፈሉ!

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

26 Oct, 07:53


የታክስ ሕግ-ተገዥነት ጠቀሜታዎች
ለመንግስት፦
👉የሀገርን ወጪ በሀገር ገቢ ለመሸፈን ያስችላል፣
👉የሀገር ዕድገትና ልማትን ለማፋጠን ይረዳል፣
👉የማህበረሰብን ስልጣኔ ለማጎልበት ፣
👉የመንግስትን ገቢ እና ማህበራዊ ልማትን ለማሳደግ፣
👉የሚጠበቀውን ገቢ ለመሰብሰብ ያስችላል፣
👉የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ይረዳል፣
👉ለሕግ ማስከበር እና ቀረጡን ለመሰብሰብ የሚወጡ ወጪዎችን ይቀንሳል፣
👉የሀገር እድገት ያፋጥናል እና ሌሎችም፣
ለግብር ከፋዩ፦
👉የግብር ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ፣
👉መብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ፣
👉ጊዜንና ገንዘብ ይቆጥባል፣
👉ከአላስፈላጊ ወጪ ይድናል፣
👉መስተንግዶን ያቀላጥፋል፣
👉መልካም ስምን ያተርፋል፣ እና ሌሎችንም ጠቀሜታዎች ያስገኛል።

MOR North West STO

24 Oct, 11:07


16 ቀን ቀረው!

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብርን የመክፈያ ወቅት ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲሰተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብሮን አሳውቀው ይከፈሉ!

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር

ግብር ለሀገር ክብር!

MOR North West STO

23 Oct, 14:36


17 ቀን ቀረው!

የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ አስታውቆ የመክፈያ ወቅት ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል::

በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ እና እንግልት፣ የሲስተም መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብርዎን አስታውቀው ይክፈሉ!

MOR North West STO

22 Oct, 13:29


ለሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ

እንደሚታወቀው የሃገራችን ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ገቢ ለመሰብሰብ የእናንተ ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡በመሆኑም የ2016 ግብር ዘመን ዓመታዊ ግብራችሁን አሳውቀውቃችሁ የምትከፍሉበት ጊዜ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም እስካሁን ግብራችሁን አሳውቃችሁ የከፈላችሁ ግብር ከፋዮች ከፍ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን ነገር ግን እስካሁን ያላሳወቃችሁ ግብር ከፋዮች በቀሩት ውስን ቀናት ውስጥ ግብራችሁን አሳወቃችሁ እንትከፍሉና በመጨረሻ ቀናት ከሚያጋጥም የኔትወርክ መጨናነቅና ቅጣት እንድትድኑ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ 

                 “ ግብር ለሃገር ክብር ”

MOR North West STO

22 Oct, 12:56


ማካካሻ፣ተመላሽ እና ከታክስ ዕዳ ነፃ ስለመሆን

በታክስ አስተዳዳር አዋጅ 983/2008 መሰረት ለታክስ ክፍያዎች የሚሰጥ ማካካሻ

1. ታክስ ከፋዩ በታክስ ዓመቱ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ለቀረበት  ታክስ እና በቅድሚ ለከፈለው ታክስ ሊያገኝ የሚገባው ማካካሻ ታክስ
ከፋዩ በታክስ ዓመቱ ከሚፈለግበት  የገቢ ግብር ዕዳ በሚበልጥበት ጊዜ፣ ባለስልጣኑ በብልጫ የታየውን ገንዘብ በሚከተለው ቅደም ተከተል ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤

      ሀ) በመጀመሪያ(ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የሚቀርን ታክስ ሳይጨምር) ታክስ ከፋዩ በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት
የሚፈለግበትን ማንኛውንም ታክስ ለመክፈል ይውላል፣

      ለ) ቀሪው ታክስ ከፋዩ በሌላ በማንኛውም የታክስ ሕግ የሚፈለግበትን ታክስ ለመከፈል ይውላል፣

     ሐ) የዚህ  አንቅፅ ንዑስ አንቀፅ (2) እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ተራፊ ገንዘብ ካለም ታክስ ከፋዩ በጽሁፍ የተመላሽ ጥያቄ ካቀረበቡት ቀን
ጀምሮ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ ለታክስ ከፋዩ ይመለስለታል፡፡

2. ታክስ ከፋዩ በፅሁፍ ስምምነቱን ከገለፅ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(1)(ሐ) የተመለከተው ገንዘብ ወደፊት ለሚመጣ ማንኛውም የታክስ እዳ መክፈያነት ሊሸጋገር ይችላል፡፡

3. ባለስልጣኑ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(1)(ሐ) በተደነገገው መሰረት ተራፊውን ገንዘብ ለታክስ ከፋዩ ካልከፈለ፣ ዘጠናው ቀን ካለቀ ጀምሮ ተራፊው ገንዘብ እስከሚመለስበት ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ ወለድ የማግኘት መብት አለው፡፡

4. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(3) መሰረት የሚከፈለው ወለድ ምጣኔ በንዑስ አንቀፅ የተመለከተው ጊዜ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ባለው ሩብ  ዓመት በንግድ ባንኮች ሥራ ላይ የዋለው ከፍተኛው የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ይሆናል፡፡

MOR North West STO

21 Oct, 10:32


የክፋል ሁለት ማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ፡፡

ጥቅምት 11-2017 ዓ/ም አ.አ
የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት  ለሁለተኛ ዙር የታክስ ትምህርት ሞጁላር ሰልጣኞችን በዛሬው እለት የሁለተኛ ሴሚስትር ማጠቃለያ ፈተና ሰጠ፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን https://shorturl.at/l988k

MOR North West STO

17 Oct, 08:41


ኢታክስ የሚያጠቃልላቸው የአገልግሎት ዓይነቶች

▫️ኢ-ፋይሊንግ ፦

ግብርን ወደ ታክስ ባለስልጣኑ መቅረብ ሳያስፈልግ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የማስታወቅ አሠራር ሥርዓት ነው፡፡

▫️ኢ-ፔይመንት ፦

ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ቀደም ሲል በኢ-ፋይሊንግ በላከው መረጃ ክፍያውን እንዲያስተናግዱ ውል በተፈራረሙ ባንኮች በኩል ክፍያውን የሚከፍልበት ስርዓት ነው፡፡

▫️ኢ-ክሊራንስ፦

ግብር ከፋዪ ድርጅት የሚኒስቴር መ/ቤት ድረ-ገጽ በመጠቀም የታክስ ክሊራንስ ለመጠየቅ የሚያስችለው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ግብሩን የከፈለ እና ምንም ዓይነት የታክስ ክፍያ የሌለው ግብር ከፋይ በቀላል መንገድ የዓመታዊ ንግድ ፈቃድ ማደሻም ሆነ ሌሎች ክሊራንሶች በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት የአሠራር ሥርአት ነው፡፡

▫️የታክስ ነክ መረጃ አገልግሎት፦

ኢ-ታክስን ተጠቅሞ አንድ ግብር ከፋይ መጠየቅ የሚፈልጋቸውን ታክስ ነክ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ሲሆን ግብር ከፋዪች የሥርዓቱ ተጠቃሚ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኝነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የአሠራር ሥርዓት ነው፡፡

ዩቱዩብ   https://shorturl.at/EyUPI
ቴሌግራም  @northwestMOR
ፌስቡክ   https://shorturl.at/UQjxc
ተከታታይ እና የርቀት ስልጠና በነጻ ለመሰልጠን 
https://shorturl.at/l988k

2,271

subscribers

2,090

photos

29

videos