የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን በክልሉ ማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ማአሾ ላይ ተፈጸመ የተባለውን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰጠ ያለው ጽንፍ የያዘ መረጃ ማሰራጨት እንዲቆም አሳሰበ።የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ከትግራይ ፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር ወንጀሉ ተፈጽሟል ከተባለበት ግዜ አንስቶ አንድ ቡድን አቋቁሞ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ፖሊስ ትላንት ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠቁሞ የምርመራ ውጤቱን በቀጣይ እንደሚያስታውቅም አመላክቷል።
በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን መዓሾ እሁድ ኅዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሰአት በኋላ በሥራ ምክንያት ከ #አክሱም ወደ #መቀለ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ‘የግድያ ሙከራ’ መትረፋቸውን መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።በእርሳቸው ላይም ሆነ አብሯቸው በመኪናው ውስጥ የነበሩት የግል ጠባቂያቸው እና ሹፌራቸው ምንም ዓይነት ጉዳት ባይደርስባቸውም፣ መኪናቸው አራት ቦታ በጥይት እንደተመታ ለቢቢሲ ማረጋገጣቸውን በዘገባው ተካቷል።
ጥቃቱን በሚመለከት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚወጡ አንዳንድ መረጃዎች በአስተዳዳሪው ላይ ያነጣጠረ የግድያ ሙከራው እንዳልተፈጸመ ገልጸው ነበር፤ ይህንን አስመልክቶ አቶ ሰለሞን ሲናገሩ “ምንም እንዳልተከሰተ የሚቀርቡ ነገሮች ሕብረተሰቡን ለማደናገር ያለሙ ናቸው” ብለዋል።አቶ ሰለሞን በህወሓት ሊቀመንበር የሚመራው ቡድን “የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም በእኛ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ ነው” ያሉ ሲሆን፣ “አሁን ያጋጠመው ክስተት ውሸት ነው እያሉ ያሉት እነሱ ናቸው” ብለዋል።የክልሉ ፖሊስ በዞን አስተዳዳሪው የግድያ ሙከራ ዙሪያ በማህበራዊ ሚዲያ በመሰጠት ላይ ያሉት ጽንፍ የያዙ አስተያየቶች አሁንም እንደቀጠሉ መሆኑን ጠቁሞ እንዲቆሙ ሲል በትላንቱ መግለጫው አሳስቧል።
Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa