M.O.R East Addis Ababa Branch @moreastaa Channel on Telegram

M.O.R East Addis Ababa Branch

@moreastaa


East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.

M.O.R East Addis Ababa Branch (English)

Welcome to M.O.R East Addis Ababa Branch! This Telegram channel, with the username @moreastaa, serves as a platform for the East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office, which is part of the Ministry of Revenues in Addis Ababa. This branch is dedicated to collecting revenue from customs duties and domestic taxes from individuals and businesses in the area. They play a crucial role in ensuring that the government receives the necessary funds to provide essential services and support economic development in the region. By joining this channel, you will stay updated on important announcements, changes in tax regulations, and valuable resources to help you navigate the tax system effectively. Whether you are a small business owner or an individual taxpayer, M.O.R East Addis Ababa Branch is here to support you every step of the way. Join @moreastaa today to connect with the branch office, ask questions, and access the information you need to fulfill your tax obligations accurately and efficiently. Let us work together towards a prosperous and compliant tax environment in East Addis Ababa!

M.O.R East Addis Ababa Branch

14 Jan, 11:10


የበጀት ዓመቱ የጥር ወር የሞጁላር ስልጠና ተጀመረ !!!
..............................
ጥር 6/2017 /ምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
በገቢዎች ሚኒስቴር የምሥራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱ የጥር ወር የሞጁላር ስልጠና ተጀመረ ፡፡
የስልጠናውን መጀመር አስመልክተው አቶ እሸቱ ኢራጎ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ታክስ ከፋዮች በቂ የታክስ ዕውቀት ኖሯቸው ግብራቸውን በሃላፊነት ፣ አዋጅ ፣ህግንና መመርያን ተከትለው መክፈል እንዲችሉ ታሰቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል ።አያይዘዉም ከሰልጣኞች የሚጠበቀው በአግባቡ በመከታተል ያገኙትን ስልጠና ተገባር ላይ ማዋል መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው አጠናቀው የሚሰጠውን ፈተና ማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች ሰርተፊኬት እንደሚዘጋጅና በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል ፡፡
ወ/ሮ እታፈራው ወርቁ የታክስ ከፋዮች ትምህርት መሪ ባለሙያ የእለቱን ስልጠና የሰጡ ሲሆኑ በመጀመሪያ ሴምስተር ከሚሰጠው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚለውን ርእስ አንስተዋል ፡፡
በሌላ በኩልም የርቀት የሞጁላል ሰልጣኞችም በዛሬው እለት የክፍል አንድ ሞጁላር ገለጻ ተደርጎላቸዋል ስልጠናውንም ገለጻ ያደረጉት ወ/ሮ ይልፋሸዋ ይርጋ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው፡፡ ለድርጅት ስራ አስኪያጆችና ምክትል ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀ ስልጠና ነው ፡፡
በታክስ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡
……….

M.O.R East Addis Ababa Branch

14 Jan, 07:48


እንኳን ደህና መጣችሁ
ትክክለኛውን የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችን ይወዳጁ፤ የታክስ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ ታክሳዊ መረጃዎችን ይከታተሉ!!
M.O.R East Addis Ababa Branch
ቴሌ ግራም https//t.me/moreastaa
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCaS60GHxhnCrPTcIjsd6nbw
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Moreastaddisababa
Telegram (https://t.me/moreastaa
ለአስተያትዎ ሃሳብ መስጫ ቴሌግራም https://t.me/EastTaxPayersGroup
የእውቀት አድማስዎን በማሰፋት ግብርዎን በህግንና ደንብን መሰረት በማድረግ በጊዜው ለማሳወቅ፣ ለመክፈል እንዲችሉና ካላስፈላጊ ቅጣትና ወጪ ለመዳን በእውቀት የታገዘ ስራ ለመስራት የሞጁላር ስልጠናን ይመዝገቡ !!
የድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትት ስራ አስኪያጅ ከሆኑና ጊዜ ከሌለዎት የርቀት ትምህርት በመመዝገብ ይማሩ !

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Jan, 12:50


“1165 ሃሰተኛ ደረሰኞች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ውድቅ ተደርጓል” - የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ

ጥር 05/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ባለፉት ስድስት ወራት የህግ ተገዢነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት 1165 ሃሰተኛ ደረሰኝ ጥቅም ላይ እንዳይውል መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገለጹ፡፡

ደረሰኞቹ በ153 ድርጅቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበር ሲሆን በዚሁም 1,210,091,184 ብር ሃሰተኛ ግብይት ለታክስ ዓላማ እንዳይውሉ ውድቅ መደረጉም ተመላክቷል፡፡

የህግ ተገዢነትን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም እንዲህ ባለ አላስፈላጊ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላትም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡

በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ፡- እስካለም ሰፊው

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Jan, 12:50


ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገው ጥረት ከሀገር ውስጥ ታክስ 247.7 ቢሊዮን ብር ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 203.8 ቢሊዮን ብር ገቢ መስብሰቡ ተገለፀ

ጥር 05/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እንደ ሀገር አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ መስረት በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩም እኛ የትልቅ ሀገር ባለቤት ነን ያሉት ሚኒስትሯ ሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅነቷን የሚመጥን አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ወሳኝ የለውጥ ሂደት ውስጥ እያለፈች ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም የለውጥ ሂደቱን ለማስቀጠል የመንግስት ብቸኛና ተቀዳሚ ተግባር የሆነው ታክስ የመጣል እና የመሰብስብ ተግባርን በብቃት ለመወጣት ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገው ጥረት ከሀገር ውስጥ ታክስ 254.9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 247.7 ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዱን 97.2 በመቶ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ይህ የገቢ አሰባሰብ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ79.4 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ብር 190.9 ቢሊዮን ለማሰብስብ ታቅዶ 203.8 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 106.7 በመቶ መሰብስብ ስለመቻሉ ጥቅስዋል፡፡

እንደ ጉምሩክ ዘርፍ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሰነፃፀር የ106.7 ቢሊዮን ብር ወይም የ110 በመቶ ብልጫ መመዝገብ መቻሉን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ተናግረዋል፡፡

በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፡-እስካልም ሰፊው

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Jan, 07:25


ለክፍል 3 ሞጁላር ሰልጣኞች

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Jan, 07:14


ለክፍል 2 ሞጁላር ሰልጣኞች

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Jan, 07:12


የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄ ይገኛል

ጥር 05/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩም የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ መስከረም ደበበ፣ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ምክትል ኮሚሽነር ክበርት ምስራቅ ማሞ፣ ምክትል ኮሚሽነር ክብርት ሙሉወርቅ ደረሰ፣ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አዝዘው ጫኔ፣ የሁለቱ ተቋማት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች እና ምክትል ስራ አስኪያጆች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

መድረኩ በአባገዳ እና አደስንቄ ምረቃ የተጀመረ ሲሆን እንደ 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በታክስ እና ጉምሩክ ተግባራት አፈፃፀም በታዩ ውጤታማ አፈፃፀሞች እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ተጠቅሷል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፡- እስካለም ሰፊው

M.O.R East Addis Ababa Branch

10 Jan, 11:54


ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ ስልጠና መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
...........................
ጥር 2 /2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ አዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና መሰጠቱን ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ አላዓዛር መልካሙ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ባለሙያ ሲሆኑ በስልጠናው ላይም በቅድመ ግብር ታክስ፣ተርን ኦቨር ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ፡፡ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም አሰልጣኙ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል ።
የስልጠናው ዋና ዓላማ አዳዲስ ግብር ከፋዮች መሰረታዊ የታክስ ህጉን እንዲረዱ በማድረግ ካላስፈላጊ ቅጣት ማዳን ፣ግብርን በመክፈል ሀገራዊ ሀላፊነትን እንዲወጡ ማሰቻል ነው ፡፡
…………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

10 Jan, 11:16


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ስኬታማነት ለማስቀጠል ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ ተገለጸ

ጥር 02/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ስኬታማነት ለማስቀጠል የታክስ መሰረቱን በማስፋት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

የፌደራልና የክልል የፋይናንስ፣ የገቢዎች እና የፕላን መስሪያ ቤቶች የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በመድረኩ እንደገለፁት፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት በተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራ ጠንካራ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/71589

M.O.R East Addis Ababa Branch

10 Jan, 08:14


እንኳን ደህና መጣችሁ
ትክክለኛውን የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችን ይወዳጁ፤ የታክስ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ ታክሳዊ መረጃዎችን ይከታተሉ!!
M.O.R East Addis Ababa Branch
ቴሌ ግራም https//t.me/moreastaa
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCaS60GHxhnCrPTcIjsd6nbw
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Moreastaddisababa
Telegram (https://t.me/moreastaa
ለአስተያትዎ ሃሳብ መስጫ ቴሌግራም https://t.me/EastTaxPayersGroup
የእውቀት አድማስዎን በማሰፋት ግብርዎን በህግንና ደንብን መሰረት በማድረግ በጊዜው ለማሳወቅ፣ ለመክፈል እንዲችሉና ካላስፈላጊ ቅጣትና ወጪ ለመዳን በእውቀት የታገዘ ስራ ለመስራት የሞጁላር ስልጠናን ይመዝገቡ !!
የድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትት ስራ አስኪያጅ ከሆኑና ጊዜ ከሌለዎት የርቀት ትምህርት በመመዝገብ ይማሩ !

M.O.R East Addis Ababa Branch

09 Jan, 07:39


https://youtu.be/BMFgC4BiGeI?si=L1jZEy36BrVecr-h

M.O.R East Addis Ababa Branch

09 Jan, 07:38


https://youtu.be/ls4ZCRawy20?si=cSSwikibmc5-7Obg

M.O.R East Addis Ababa Branch

09 Jan, 07:28


የመጀመሪያ ሴምስተር የሞጁላር ስልጠኞች መመዘኛ ፈተና ተሰጠ ፡፡
……………………………………………………
ጥር 1/2017
የምስራቅ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ በታኅሣሥ ወር ሞጁላር ስልጠና ለመከታተል የተመዘገቡ ሰልጣኞች የመጀመሪያ ሴምስተር ትምህርታቸወን አጠናቀው የመዘኛኛ ፈተና ወስደዋል ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታም የሴምስተር ሁለት እና ሶስት ሰልጣኞች ባለፈው ሳምንት የተፈተኑ ሲሆን ሰልጣኞቹም የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ሲረጋገጥ ወደ ቀጣይ ሴምስተር የሚዘዋወሩ ሲሆን የሴመስተር ሶስት ሰልጣኞን በተቋም ደረጃ በሚወጣ መርሐ ግብር የሚመረቁ ይሆናል ፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ጉዳዮችን በማሰልጠን ግብር ከፋዮች መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲሁም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ከሚያረግባቸው መንገዶች አንዱ 13 ሞጁሎችን በማዘጋጀት በሶስት ክፍል ሞጁላራዊ ስልጠና በመደበኛና በርቀት መስጠትና መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ የእውቅና ሰርተፊኬት አንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

06 Jan, 09:31


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታኅሣሥ ወር የገቢ እቅዱ እንዲሳካ አመራሩና ሰራተኛው ተግቶ እየሰራ ይገኛል
…………….ታኅሣሥ 28/2017
የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀሩት ሁለት የስራ ቀናት የታኅሣሥ ወር የገቢ እቅዱ እንዲሳካ አመራሩና ሰራተኛው ተግቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡ በዚህም የገቢው መሳካት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ግብር ከፋዩ ግብሩን እያሳወቀና እየከፈለ ነው ፡፡በሌላ በኩል ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማግኘት ግብራቸውን አሳውቀው ያጠናቀቁ ግብር ከፋዮች የክሊራንስ አገልግሎትም በማግኘት ላይ ይገኛሉ ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከገቢዎች ሚኒሰቴር የመጡ ዳይሬክተሮቶች የገቢ እቅዱ ለማሳካት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን የአገልግሎት አሰጣጡም ምን እንደሚመስል ምልከታ በማድረግ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ አድርገዋል ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል ፡፡
………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

04 Jan, 12:40


የጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ባለ 6 ወለል የቢሮና የመጋዘን ህንጻ ግንባታው ተጠናቆ ተመረቀ

ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የጉምሩክ ኮሚሽን ለኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በኮምቦልቻ ከተማ ያስገነባው ባለ 6 ወለል የቢሮ ህንጻ ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት  ተመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ የሀገር ልማትና እድገት እንዲፋጠን ብሎም ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና አድርጋ እንድትቆም የኢኮኖሚ የደም ሥር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ መሆኑን ገልጸው ትልቁ አላማችንም አገልግሎት አሰጣጣችን የዘመነና ኢኮኖሚውን የሚደግፍ ተቋም መገንባት ስለሆነ ህንፃው ለአገልግሎት በመብቃቱ እኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ::

አክለውም ኮምቦልቻ ትልቅ የኢንዱስትሪ መዳረሻ እየሆነች የመጣች እና በደንብ የመልማት እድል ያላት ከተማ እንደመሆኗ የኮሚሽኑ ህንፃውን በዚህ መልክ ማስገንባቱ የወደፊት የለውጥ ተስፋዋን የሚያሳይ ነው ብለዋል ::

ለአገልግሎት የበቃው ህንጻ ከቢሮ አገልግሎት በተጨማሪ በውስጡ የህፃናት ማቆያ፣ ጅምናዚየም እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የሰራተኞች መመገቢያ አዳራሽ ያካተተ ሲሆን ይህም ሰራተኞች ደንበኞቻቸውን በብቃት አንዲያገለግሉ  እና ተወዳዳሪ  ተቋም እንዲሆን ያስችላል ብለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በ 2023 ደረጃውን የጠበቀ የኢትዮጵያውያንን የመልማት ፍላጎት የሚያሟላ አገልግሎት የመስጠት ራእይ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል::

ከእነዚህ ስራዎች መካከል የስራ አካባቢን ምቹ ማድረግ አንዱ ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ
ኢትዮጵያ ያለባትን የተቋም ስብራት ጠግኖ ኢትዮጵያውያንን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ከዋናው መስሪያ ቤት ጀምሮ እስከ ቅ/ጽ/ቤቶች እና  ኮሚሽኑ አገልግሎት በሚሰጥባቸው በሌሎች አካባቢዎች  ተመሳሳይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ከቢሮ ግንባታው በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡ ዘመኑን የዋጀ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ህንጻው የተገነባው የጉምሩክ ኮሚሽንን ራእይ እና ተልእኮ ለማሳካት ለሰራተኞቻችን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ደንበኞቻችንን በዘመነ መንገድ ለማገልገል እንዲሁም ወጭ አና ገቢ እቃዎችን በብቃት በማስተናገድ የከተማውን እድገት ለማፋጠን አና ኮንትሮባንድ ለመከላከል  በሚያስችል መልኩ ለመስራት በማቀድ ነው ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ ደርሴ የጉምሩክ ኮሚሽን በከተዋ  ያስገነባው ህንጻ ከተማዋ እያከናወነችው ላለው የእድገት ጉዞ ተጨማሪ አቅም ነው ብለዋል።

በአዳነ ውበት
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ

M.O.R East Addis Ababa Branch

04 Jan, 11:45


በታክስና ጉምሩክ ህጎች ፣ደንቦችና መመሪያዎች ዙርያ ግንዛቤ መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
………….
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በታክስና ጉምሩክ ህጎች ፣ደንቦችና መመሪያዎች ዙርያ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጫበጥ ስራን አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም በሶስቱ ክፍለ ከተማዎች የካ ፣ቦሌ እና ለሚ ኩራ ከሚገኙ 8 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመጡ ርዕሰ መምህራንና አበቂ መምህራን ግንዛቤውን ሰጥቷል ፡፡
አቶ ሬድዋን ከድር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የግንዛቤው ማስጨበጫ አላማ ሲናገሩ መንግሥት የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ፣ህዝቡን ለማስተዳደር እና ልማቱን ለማፋጠን ታክስ ያስፈልገዋል ፤ ታክስ ከሌለለ ሀገር የለም፡፡ ለዚህም ታክስ በፈቃደኝነት የሚከፍል ሀላፊነቱን የሚወጣ ትውልድ ለማፍራት ትውልዱን የምትቀርጹ መምህራን ሚና ከፍተኛ ነው ፡፡ በመሆኑም ዓላማው ግቡን እንዲመታ ስልጠናው ተዘጋጅተዋል ፡፡ በሌላ በኩል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ወክለው የሚወዳደሩ ተማሪዎችንም በበቂ ሁኔታ ለማዘጋጀትም ይረዳል ፡፡ብለዋል
አቶ እሸቱ ኢራጎ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ እና ወ/ሮ ስንታየሁ ዘውዴ የጉሙሩክ ከሚሽን የህዝብ ግንኙነት አመራር በታክስና ጉምሩክ ህጎች ፣ደንቦችና መመሪያዎች ዙርያ ስልጠናውን ሰጥተዋል ፡፡
ስልጠናውም የተሰጠው ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት እና በጉሙሩክ ከሚሽን ጋር በመተባበር ነው፡፡
………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

02 Jan, 08:18


የታክስ ህግ ተገዢነታቸው ዝቅተኛ ከሆኑ ግብር ከፋዮች ጋር ወደ ተሻለ የታክስ ሥርዓት ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
………………
ታህሳስ 24 /2017
በገቢዎቸው ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ህግ ተገዢነታቸው ዝቅተኛ ከሆኑ ግብር ከፋዮች ጋር ወደ ተሻለ የታክስ ሥርዓት ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና ዓ.ም ተሰጠ፡፡
አቶ ሴናማል አብዲሳ የታክስ ህግ ተገዢነት ጥናትና ስትራቴጂክ ዝግጅት ቡድን አስተባባሪ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን የህግ ተገዥነት ምንነት፣ለህግ ተገዢ ያልሆኑ ግብር ከፋዮች መገለጫ ባህርያት እንዲሁም ወደ ታክስ ህግ ተገዢነት እንዴት መመለስ ይቻላል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የተገኙ ተሳታፊ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው የአሰራር ክፍተቶች በማየት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ወደ ቅጣት ከማምራቱ በፊት ጠርቶ ስልጠና መስጠቱና በግልጽ እንድንወያይ ማድረጉ ወደ ታክስ ህግ ተገዥነት እንድንመለስና በቀጣይ እራሳችንን ለመፈተሸ ያግዘናል ብለዋል፡፡
…………….

M.O.R East Addis Ababa Branch

31 Dec, 09:01


ምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የአራተኛ ዙር የርቀት ሞጁላር ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡
..............................
ታኅሣሥ 22/2017 /ምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
የምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ለአራተኛ ዙር ሞጁላር የርቀት ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡
ይህ የርቀት የሞጁላል ስልጠና በኦን ላይን በተዘረጋ አሰራር ለተመዘገቡ የድርጅት ስራ አስኪያጆችና ምክትል ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀ ስልጠና ነው ፡፡እነዚህ ኋላፊዎች ካለባቸው የስራ ጫና አንጻር ገጽ ለገጽ ወይም በተከታታይ ቀናት በመገኘት መሰልጠን ለማይችሉ ስራቸውን በማይጎዳ መልኩ በአጭር ጊዜ ሁሉንም የታክስ የህጎች ተምረው እንዲመረቁ ታሰቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ወ/ሮ የሺወርቅ ተጫነ የቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ የአራተኛ ዙር ርቀት ሞጁላር ስልጠና መጀመሩን አስመልክቶ ስልጠናው በምን መልኩ መሄድ እንደሚገባ መርሐ ግብሩን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ አጠቃላይ የስልጠናው ይዘት ምን እንደሚመስል ሰነድ በማቅረብ ለሰልጣኞቹ ገለጻ አድርገዋል ፡፡
አያይዘውም የሞጁላር ስልጠና መዘጋጀቱ የግብር መክፈል ጠቀሜታን አውቃችሁ በተገቢ መልኩ ግብራችሁን እንድትከፍሉ ፣ ባለመክፈል ከሚገጥማችሁ የህግ ጥሰት እንድትጠበቁ ፣ሀገራዊ ሀላፊነት እንድትወጡ ማስቻል አንዱ ጠቀሜታው ነው ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች ይህን ስልጠና ከወሰዳችሁ በኋላ የህግ ተገዥነት ደረጃችሁ ከፍ ብሎ በህግና በመመሪያ መሰረት በታማኝነት ፣በጊዜ የምትከፍሉ፣ለውጥን በወቅቱ የምታሳውቁ ግብር ከፋዮቻችን እንድትሆኑ እንፈልጋለን በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል ፡፡
የምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የመጀመሪያ ዙር የርቀት ሞጁላር ስልጠና መጋቢት 19/2016 ዓ.ም መስጠት መጀመሩ ይታወሳል ፡፡
…………

M.O.R East Addis Ababa Branch

28 Dec, 06:40


“በቀጣይ ሰባት ወራት እቅድ እንዲሳካ በየጊዜው ስራዎችን መፈተሸና ተግባር ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል” //አቶ ሬድዋን ከድር የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ//
………………………..


በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የህዳር ወር አፈጻጸምና የቀጣይ ሰባት ወር የእቅድ ክለሳ ዙርያ ከቅ/ጽ/ቤቱ ማኔጅመንት ጋር ግምገማና ውይይት ታህሳስ 18 /2017 ዓ.ም አድርጓል፡፡
የቅ/ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ቡድን አሰተባባሪ አቶ ገንዘብ መካሻ የህዳር ወር የስራ አፈፃፀም አቅርበዋል ፡፡
በሪፖርታቸውም ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 378.22 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 532.04 ሚሊዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 140.67% መሆኑ ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 532.04 ሚሊዮን መካከል ብር 294.13 ሚሊዮን ከቀጥታ ታክሶች ፣ ብር 236.40 ሚሊዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 1.51 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ ነው፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአምስት ወራት ውስጥም 2,963.87 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 3,596.32 ሚሊዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 121.34% አድርሷል፡፡
በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 2,963.87 ሚሊዮን መካከል ብር 1,713.47 ሚሊዮን ከቀጥታ ታክሶች ፣ ብር 1,860.66 ሚሊዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 22.19 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ ነው፡፡
አቶ ሬድዋን ከድር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሰበሰበው ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም አመራሩ እና ሠራተኛው ተናቦ በመስራቱ፣ ከምንጊዜውም በላይ ሰራተኛ ስራውን ለማከናወን ያለው የስራ ተነሳሽነት፣ ግብራቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት በከፈሉ ግብር ከፋዮች የተገኘ በመሆኑ አመራሮች እና ሠራተኞች፣ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡ ባሉፉት ወራት በነበረ ጠንካራ የስራ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በቀጣይ ሰባት ወራት የእቅድ ክለሳ የተደረገ ሲሆን ይህን እቅድ ማሳካት እንዲቻል ተጨማሪ የፊዚካል ስራዎች መሰራት እንዳለበት በመግለጽ ከታህሳስ-ሰኔ 30/2017 የገቢ ዕቅድ መሳኪያ ሥራዎች ይፋ አድርገዋል ፡፡ በመሆኑም የተጨመረው እቅድ እንዲሳካ ሁልጊዜ ስራዎችን መፈተሸና ተግባር ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል ፡፡
በህዳር ወር በነበረ አፈጻጸም፣ በተጨማሪ የፊዚካል ስራዎች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ሰባት ወራት ለሚኖረው የእቅድ አፈጻጸም ዙርያ ለተነሱ ጥያቄዎች ምክትል ስራ አስኪያጆች ከዘርፋቸው አንጻር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የማኔጅመን አባላትም እቅዱን ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ፡፡
በማጠቃለያም በቀጣይ ወራት የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ሁሉም አመራርና ፈጻሚ ሙስናን በመዋጋት፣ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል እና ገቢ ሊያስገኙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ወቅቱን የጠበቀ የክልሎች የጋራ ገቢ ትልልፍ ማከናወን፣ ዲፖዚት ኢንትራንዚቶች እንዲቀንሱ ማድረግ፣ የሞጁላር ስልጠና አጠናክሮ መቀጠል፣ ኢ-ፋይል አድርገው ያልከፈሉት ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት እንዲከፍሉ ማድረግ፣ የኢ-ክፍያ፣ የቴሌ ብር ክፍያን እና የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን ማጠናከር፣ ተጨማሪ የገቢ ዕቅድን አጠናክሮ መቀጠልና የገቢ ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ መሰብሰብ እንደሚገባ አቅጣጫ በመስጠት ሰብሰባው ተጠናቋል፡፡


……………………….

M.O.R East Addis Ababa Branch

27 Dec, 10:13


ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ ስልጠና መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
...........................
ታኅሳስ 18/2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ አዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና መሰጠቱን ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ አላዓዛር መልካሙ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ባለሙያ ሲሆኑ በስልጠናው ላይም በቅድመ ግብር ታክስ፣ተርን ኦቨር ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ፡፡ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም አሰልጣኙ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል ።
የስልጠናው ዋና ዓላማ አዳዲስ ግብር ከፋዮች መሰረታዊ የታክስ ህጉን እንዲረዱ በማድረግ ካላስፈላጊ ቅጣት ማዳን ፣ግብርን በመክፈል ሀገራዊ ሀላፊነትን እንዲወጡ ማሰቻል ነው ፡፡
…………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

06 Dec, 12:51


በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች ስልጠና ተሰጠ፡
...........................
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ህዳር27 /2017 ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ባለሙያ ሲሆኑ በስልጠናው ላይም በቅድመ ግብር ታክስ፣ተርን ኦቨር ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ፡፡ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም አሰልጣኙ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል ።
ስልጠናው ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው አዳዲስ ግብር ከፋዮች መሰረታዊ የታክስ ህጉን እንዲረዱ በማድረግ ካላስፈላጊ ቅጣት ማዳን ፣ግብርን በመክፈል ሀገራዊ ሀላፊነትን እንዲወጡ ማሰቻል ነው ፡፡
………………

M.O.R East Addis Ababa Branch

06 Dec, 10:54


https://youtu.be/ZbPlkDylSk0?si=MWP2x7D8y3Lgc6C1

M.O.R East Addis Ababa Branch

06 Dec, 09:59


ቅ/ጽ/ቤቱ በህዳር ወር በዓለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ በዓላት አከበረ
……………….
በምስራቅ አ/አ/አነ/ግ /ከ/ቅ/ጽ/ቤት ህዳር 26 /2017 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን ፣የሕጻናት ቀን ፣የኤች አይቪ ኤድስ ቀን እና የአካል ጉዳተኞች ቀን አከበረ ፡፡
በእለቱም የቅ/ጽ/ቤቱ ተቋማዊ አቅም ድጋፍ ዘርፍ ምከትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሁዳ አሊ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፏል ፡፡
ወሮ ኑሪያ አሊ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቡድን አስተባባሪ የአራቱን በዓል መሪ ቃል በመግለጽ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል ፡፡ በገለጻቸዉም በተለይ በሴቶችና ህጻናት ላይ ከጊዜ ወደጊዜ መልኮቻቸውን ቀይረው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ከመከላከል አኳያ ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ግልጸዋል ፡፡
በሴቶችና በህጻናት የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል የወንዶች ሀላፊነት ከፍተኛ መሆኑና በተጨማሪም የህግ ማዕቀፎቹ ሊጠናከር እንደሚገባ የቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራአስኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ ገልጸዋል ፡፡
ከዚህም ጋር በቅ/ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ዘጠኝ አባዎራዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቿል ፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

05 Dec, 05:54


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መካከለኛ የታክስ ተገዢ ለሆኑ ግብር ከፋዮች ስልጠና ሰጠ
…………..
በገቢዎቸው ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ የታክስ ህግ ተገዢነታቸው መካከለኛ ከሆኑ ግብር ከፋዮች ጋር ወደ ከፍተኛ የህግ የታክስ ሥርዓት ተገዢ መኆን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና ህዳር 25 /2017 ዓ.ም ሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ እሸቱ ኢራጎ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ የህግ ተገዥነት ምንነት፣ለህግ ተገዢ ያልሆኑ ግብር ከፋዮች መገለጫ ባህርያት እንዲሁም ወደ ታክስ ህግ ተገዢነት እንዴት መመለስ ይቻላል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስጋትና ህግ ተገዢነት ስትራቴጂ የስራ ሂደት አሰተባባሪ ና ሙያተኞች መገኘት ውይይት ያደረጉ ሲሆን ያሉትን ጥቃቅን ስህተቶች በማረምና የበለጠ ለህግ ተገዢነቱ ትኩረት በመስጠት ወደ ከፍተኛ የህግ ተገዢ ማደግ እንደሚቻልና የበለጠ በመቀራረብ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል ፡፡
በስልጠናው የተገኙ ተሳታፊ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው የአሰራር ክፍተቶች በማየት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጠርቶ ስልጠና መስጠቱና በግልጽ እንድንወያይ ማድረጉ ወደ ከፍተኛ የታክስ ህግ ተገዥነት እንድንመለስና በቀጣይ እራሳችንን ለመፈተሸ ያግዘናል ብለዋል፡፡
…………

M.O.R East Addis Ababa Branch

29 Nov, 12:30


ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ፡
...........................
ህዳር 20/2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ አዳዲስ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ፣ መመሪያ እና ደንቦች ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡የስልጠናው ዋና ዓላማ አዳዲስ ግብር ከፋዮች መሰረታዊ የታክስ ህጉን እንዲረዱ በማድረግ ካላስፈላጊ ቅጣት ማዳን ፣ግብርን በመክፈል ሀገራዊ ሀላፊነትን እንዲወጡ ማሰቻል ነው ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ አላዓዛር መልካሙ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ባለሙያ ሲሆኑ በስልጠናው ላይም በቅድመ ግብር ታክስ፣ተርን ኦቨር ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ፡፡ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም አሰልጣኙ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል ።
ከዚህም ጋር ግብር ከፋዮች የበለጠ ህግን ተከትለው ግብራቸውን አንዲያሳውቁና እንዲከፍሉ የሚረዳቸው ሥነምግባራዊ መርህና የጥቆማ ሰርዓት ግንዛቤ እዲወስዱ ተደርጓል ፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫው የሰጡት አቶ ተስፋዬ ግርማ የተቋሟዊ ስጋት ስራ አመራርና ስነምገባር ቡድን አስተባባሪ ሲሆኑ ንግድና ስነምግባር ፣ታክስና ስወራ ፣ የህግ ተገዥነት እና ሙስና እንዲሁም ስለጥቆማ አቀራረብ ገለጻ አድርገዋል ፡፡ ለሚገጥማቸው ማንኛውም የስነምግባር ጥሰት ጥቆማ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸዋል ።
ስልጠናው በወር ሁለት ጊዜ ለአዳዲስ ግብር ከፋዮች የሚሰጥ ነው

M.O.R East Addis Ababa Branch

29 Nov, 07:32


እንኳን ደህና መጣችሁ
ትክክለኛውን የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችን ይወዳጁ፤ የታክስ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ ታክሳዊ መረጃዎችን ይከታተሉ!!
M.O.R East Addis Ababa Branch
ቴሌ ግራም https//t.me/moreastaa
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCaS60GHxhnCrPTcIjsd6nbw
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Moreastaddisababa
Telegram (https://t.me/moreastaa
ለአስተያትዎ ሃሳብ መስጫ ቴሌግራም https://t.me/EastTaxPayersGroup
የእውቀት አድማስዎን በማሰፋት ግብርዎን በህግንና ደንብን መሰረት በማድረግ በጊዜው ለማሳወቅ፣ ለመክፈል እንዲችሉና ካላስፈላጊ ቅጣትና ወጪ ለመዳን በእውቀት የታገዘ ስራ ለመስራት የሞጁላር ስልጠናን ይመዝገቡ !!
የድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትት ስራ አስኪያጅ ከሆኑና ጊዜ ከሌለዎት የርቀት ትምህርት በመመዝገብ ይማሩ !

M.O.R East Addis Ababa Branch

25 Nov, 13:59


በአራት ወራት ውስጥ ከ312 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል
ሕዳር 16/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የአራት ወራት የገቢ እና የዋና ዋና ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ባለፉት አራት ወራት ብር 311.56 ቢሊዮን ጥቅል ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 312.56 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 100.3 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ118.58 ቢሊዮን ብር ብልጫ እና የ61 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/rO1Me

M.O.R East Addis Ababa Branch

20 Nov, 11:01


ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቅርብ ጊዜ በቅጥር ለተቀላቀሉ ሰራተኞች የማስታወቂያ ስልጠና( Ineduction )ተሰጠ
....................
ኅዳር 11/2017 /የምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቅርብ ጊዜ በቅጥር ለተቀላቀሉ ሰራተኞች የማስታወቂያ ስልጠና( Ineduction )ዛሬ ኅዳር 11/2017 ተሰጠ ።
ስለጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ስራ ሂደት አሰተባባሪነት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሆን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ስልጠናውን በመስጠት ተሳትፈውበታል ፡፡አቶ ጌታቸው አጽብሐ የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ስራ ሂደት አሰተባባሪ የተቋሙ መዋቅራዊ አደረጃጃት የፍቃድ አሰጣጥ ሁኔታ እንዲሁም ዋስ የመሆን መብት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በማንሳት ግንዛቤ አሰጨብጠዋል ፡፡
ወ/ሮ ኑርያ አሊ የ/ቅ/ ጽ/ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቡድን መሪ በሴቶችና ወጣቶች ፎረም ፣ ማስገንዘቢያ ስልጠና ሰጥተዋል ።
ከዚህም ጋር ተያያዞ የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ ምግባር ቡድን አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ግርማ በሰራተኞች ደንብ ዙርያ ፣የስነ ምግባር ጽንሰ ሀሳብ አስፈላጊነት እና የሞያ ሰነምግባር በተመለከተ ለሰራተኞቹ ግንዛቤ ሰጥተዋል ፡፡
ስልጠናውም የወሰዱት ሰራተኞች ስልጠናው የበለጠ ለስራቸው የሚደግፋቸውና ለስራ መነሳሳት የበለጠ እድልም እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል።
………………………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

14 Nov, 16:48


#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/JNqW7

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Nov, 07:07


የአራት ወራት አፈጻጸማችን ውጤታማ እና ትምህርት ያገኘንበት ነው
- ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የጥቅምት ወር እና የአራት ወር አቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል ::

በግምገማው ሶስት ዋና ዋና ጉዳይች የተነሱ ሲሆን የጥቅምት ወር እና የአራቱ ወራት የገቢ አሰባሰብ ምን እንደሚመስል፣ በበጀት ዓመቱ ኦዲት የሚደረጉ ግብር ከፋዮች ትንተናን በተመለከተና የገቢ አሰባሰቡን ለመደገፋ የተደረገው የሰው ኃይል ስምሪት ውጤታማነት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል::

በመድረኩ የጥቅምት ወር እና የአራቱ ወራት የገቢ አሰባሰብ ውጤታማ ሥራ መሰራቱን እና የተገኘውም ውጤት የሚያኮራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ተናግረዋል:: ለዚህም ውጤት መገኘት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተጣላባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሰሩት ጠንካራ ሥራ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ በሚኒስቴሩ በልዩ ሁኔታ የተዋቀረውና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በገቢ አሰባሰብ ሲደግፍ እና ክትትል ሲያደርግ የነበረው ቡድን የሰራው ሥራ የሚጠቀስ ነው ብለዋል ::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- http://tiny.cc/ov2vzz

M.O.R East Addis Ababa Branch

13 Nov, 05:52


https://youtu.be/8yRZDS7z1Dw?si=Za9mmEhr9QLnOnn1https://youtu.be/8yRZDS7z1Dw?si=Za9mmEhr9QLnOnn1

M.O.R East Addis Ababa Branch

12 Nov, 08:31


https://youtu.be/YsN_sVtTEOg?si=vGGnZj80NrLHMyWR

M.O.R East Addis Ababa Branch

11 Nov, 08:46


የ2016 ዓ.ም የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት ዛሬ የመጨረሻ ቀን
……………………..
ከሐምሌ1 ቀን እስከ ሰኔ 30 የሒሳብ ዓመት መዝጊያ የሆኑ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ የሒሳብ ማሳወቂያ ጊዜ ይጠናቀቃል ፡፡ ነገር ግን በታክስ አሰተዳደር አዋጅ 83/2008 አንቀጽ 83 መሰረት ሰነድ የማቅረቢያ ወይም የመክፈያ ጊዜ ቅዳሜ ፣እሁድ ወይም በኢትዮጵያ የሕዝብ በዓል ቀን ላይ ከዋለ ሰነዱ የሚቀርብበት ፣ክፍያው የሚፈጸምበት ወይም በታክስ ህግ መሰረት ሌላ ማንኛውም እርምጃ የሚወሰድበት ቀን የሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ፡፡የሚል ተደንግጓል ፡፡
ይህን ተከትሎ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዛሬ ሕዳር 2 /20017 ግብራቸውን ለማሳወቅና ለመክፈል የመጡ ግብር ከፋዮችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ግብር ለሀገር ክብር!!

M.O.R East Addis Ababa Branch

11 Nov, 07:38


ለክፍል ሁለት ሞጁላር ሰልጣኞች

M.O.R East Addis Ababa Branch

11 Nov, 07:35


ለክፍል ሶስት ሞጁላር ሰልጣኞች

M.O.R East Addis Ababa Branch

11 Nov, 06:31


#ዛሬ_ሙሉ_ቀን_አገልግሎት_ይሰጣል

ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብር የመክፈያ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

ይህንኑ ምክንያት በማድረግ የገቢዎች ሚኒስቴር በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ዛሬ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

09 Nov, 09:18


https://youtu.be/AWhq4ZfrLbU?si=rreoClVRihExLxUZ

M.O.R East Addis Ababa Branch

08 Nov, 06:10


የቅስቀሳ መርሀ ግብር ቀጥሏል
…………..
የ2016 ዓ.ም የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት ምክንያት በማድረግ ቅንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር በሚሰበስብባቸው በቦሌ ፣በለሚ ኩራ እና በየካ ክፍለ ከተማ ቅስቀሳው እየተካሄደ ይገኛል

M.O.R East Addis Ababa Branch

07 Nov, 14:12


የጥቅምት ወር ግብር አሰባሰብ ሂደቱና የመስተንግዶ ሁኔታ
……………..
የ2016 ዓ.ም የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት ሊጠናቀቅ የቀሩት 3 ቀን ብቻ ናቸው ፡፡
ቀናቱ ከመጠናቀቃቸው አሰቀድሞ ባሉት ቀናት ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል ላይ ያሉ ግብር ከፋዮች በአግባቡ መስተናገድ እንዲችሉ ፣በታቀደቀው ልክ ገቢው እንዲሰበሰብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አበክሮ እየሰራ ይገኛል ፡፡
ይህን ተከትሎ በየደረጃ ያሉ ሀላፊዎች ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ ነው ፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

05 Nov, 09:53


ለመጀመሪያና ለሶስተኛ ሴምስተር የሞጁላር ስልጠኞች መመዘኛ ፈተና ተሰጠ ፡፡
……………………………………………………
ጥቅምት 26/2017
የምስራቅ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ለሶስት ወር ወይም ለ90 ሰዓታት የሞጁላር ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ሠልጣኞች የመመዘኛ ፈተና ወስደው ስልጠናውን አጠናቀዋል ፡፡
ይህ በንዲህ እንዳለ ቅ/ጽ/ቤቱ በጥቅምት ወር አዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ሰልጣኞች የሞጁላር ስልጠናውን እየተከታተሉ ሲሆን ወደ ክፍል ሁለት መሸጋገር የሚያስችላቸውን ፈተናም ወስደዋል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ጉዳዮችን በማሰልጠን ግብር ከፋዮች መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲሁም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ከሚያረግባቸው መንገዶች አንዱ 13 ሞጁሎችን በማዘጋጀት በሶስት ክፍል ሞጁላራዊ ስልጠና በመደበኛና በርቀት መስጠትና መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ የእውቅና ሰርተፊኬት አንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

04 Nov, 10:45


የበጀት ዓመቱ የጥቅምት ወር የሁለተኛ ሴምስተር የሞጁላር ስልጠና መመዘኛ ፈተና ተሰጠ ፡፡
……………………………………………………
ጥቅምት 25/2017
የምስራቅ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱ የጥቅምት ወር ሁለተኛ ሴምስተር የሞጁላር ስልጠና መመዘኛ ፈተና ሰጠ ፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ጉዳዮችን በማሰልጠን ግብር ከፋዮች መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲሁም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ከሚያረግባቸው መንገዶች አንዱ 13 ሞጁሎችን በማዘጋጀት በሶስት ክፍል ሞጁላራዊ ስልጠና በመደበኛና በርቀት መስጠትና መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ የእውቅና ሰርተፊኬት አንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡
ፈተናውን የወሰዱ ሰልጣኞች ወደቀጣዩ ሴምስቴር የሚሻገሩ ይሆናል

M.O.R East Addis Ababa Branch

04 Nov, 10:34


https://youtu.be/xfKw7sR5qlU?si=ot3J4x196Clw_Dyy

M.O.R East Addis Ababa Branch

04 Nov, 09:05


በገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀጽ 83 መሰረት ግብር ማሳወቅ
1/ አንድ ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ለሆኑ ቀጣርዮች የማይሰራ ወይም ግብርን ቀንሶ ገቢ የማድረግ ግዴታ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ግብሩን የማስታወቅ ግዴታ የለበትም ፡፡
2/ አንድ ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ቀጣርዎች ያሉት ወይም ከራስ ገቢ ላይ ግብርን ቀንሶ የመያዝ ግዴታ ያለበት እንደሆነ ፣ተቀጣሪው ከየሶስት ወሩ መጨረሻ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የግብር ማስታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
3/ አንድ ተቀጣሪ ግብር የማሳወቅ ግዴታ የሌለበት ሲሆን ቀጣሪው በአንቀጽ 96 መሰረት ለተቀጣሪው የሚሰጠው ግብር ተቀንሶ ቀሪ መሆኑን የሚያሳየው ደረሰኝ ለዚህ አዋጅና ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አላማ ሲባል ቀጣሪው በየወሩ መክፈል በሚኖርበት ግብር ላይ የግብር ውሳኔ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
4/ የደረጃ ”ሀ” እና “ለ’’ ግብር ከፋዮች የግብር ዓመቱን ግብር የሚያሳውቁት በሚከተሉት ጊዚያት ይሆናል፣
ሀ የደረጃ “ሀ“ግብር ከፋዮች የግብር ዓመቱ ከተጠናቀቀበት ጊዜ አነስቶ በሉት የአራት ወራት ጊዜ ውስጥ፤
ለ የደረጃ “ለ“ ግብር ከፋዮች የግብር ዓመቱ ከተጠናቀቀበት ጊዜ አነስቶ በሉት የሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ
5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት የሚቀርብ የግብር ማስታወቂ የሚከተሉት የግብር ማስታወቂያ የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል ፣
ሀ የደረጃ“ ሀ“ ግብር ከፋዮች የግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩን የግብር ዓመቱን ትርፍና ኪሳራ ሂሳብ መግለጫ
ለ የደረጃ“ ሀ “ግብር ከፋዮች የግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩን የግብር ዓመቱን ትርፍና ኪሳራ መግለጫ እና የሀብትና እዳ መግለጫ ወይም
6/ የደረጃ “ሐ“ ግብር በዚህ አዋጅ አንቀጽ 84 በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የግብር ማስታወቂያውን ማቅረብ አለበት
7/ካገኘው ገቢ ላይ ግብሩ ተቀናሽ የተደረገ በመሆኑ ምክንያት ነጻ ካልተደረገ በስተቀር የሰንረዥ
“መ“ ገቢ ያለው ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ገቢውን ያስገኘው ግብይት ከተደረገ ጀምሮ ባሉት
ሁለት ወራት ውስጥ የግብር ማስታወቂ የማቅረብ ግዴታ አለበት ፡፡
ትክክለኛውን የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችንን ይወዳጁ፤ የታክስ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ ታክሳዊ መረጃዎችን ይከታተሉ
ቴሌ ግራም https//t.me/moreastaa
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCaS60GHxhnCrPTcIjsd6nbw
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Moreastaddisababa

Telegram (http://t.me/moreastaa)

Telegram
M.O.R East Addis Ababa Branch
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for c

M.O.R East Addis Ababa Branch

02 Nov, 11:35


የግብር አሰባሰብ ሂደቱ ስነምግባርን የተከተለና ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ እንዲሆን የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ስነምግባር ቡድን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል
……………..
የ2016 ዓ.ም የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት እየተገባደደና የቀሩት ቀናትም ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡
ይህንንም አስመልክቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ስነምግባር ቡድን ቅኝት በማድረግ የግብር አሰባሰቡ ሂደት ቀልጣፋ መሆኑ ፣ለስነምግባር ግድፈትም ተጋላጭ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ለሙያተኞች የቅርብ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ስራውን ለማቀላጠፍ ከተቋቋመ ኮሚቴ ጋር በየእለቱ ቅኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ግብር ከፋዩም በቀሩት ቀናት የወረፋና የሲስተም መጨናነቅ እንዳይገጥም ግብራቸውን እየከፈሉ መሆናቸውን ለማየት ተችሏል ፡፡

………..

M.O.R East Addis Ababa Branch

01 Nov, 13:41


በገቢዎች ሚኒስቴር ለምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች በሙሉ
ውድ ግብር ከፋዮቻችኝ
ከሐምሌ 1 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ የሒሳብ ማሳወቂያና መክፈያ ጊዜ መሆኑን ይታወቃል ፡፡
ስለሆነም ውድ ግብር ከፋዮቻችን ወቅቱን ጠብቃችሁ በማሳወቅ እና በመክፈል ከአላስፈላጊ ወልድና ቅጣት ድርጅታችሁን እንድታድኑ፣ መብታችሁን በማስጠበቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡
ወደቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዓመታዊ ንግድ ትርፍ ግብር ለማሳቀወቅ ስትቀርቡ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ዝርዝር በጥንቃቄ በመመልከት አሟልታችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን ፡፡
****ማሳሰቢያ፡- ሂሳቡ ሲመረመር የድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ሰው መቅረብ ግደታ አለበት!!

M.O.R East Addis Ababa Branch

29 Oct, 14:23


እናስታውስዎ
ውድ ግብር ከፋዮቻችኝ
ከሐምሌ1 ቀን አስከ ሰኔ 30 የሒሳብ ዓመት መዝጊያችሁ የሆነ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 ቀን 20116 እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ የሒሳብ ማሳወቂያ ጊዜ መሆኑን ይታወቃል ፡፡
ስለሆነም ውድ ግብር ከፋዮቻችን ወቅቱን ጠብቃችሁ በማሳወቅ እና በመክፈል ከአላስፈላጊ ወልድና ቅጣት ድርጅታችሁን እንድታድኑ፣ መብታችሁን በማስጠበቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡
ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታም ፣ክብርም ነው!!

M.O.R East Addis Ababa Branch

28 Oct, 14:16


3ኛሴምስቴር የሞጁላር ሰልጣኞች  ስልጠኛቸውን አጠናቀቁ 
……………
የም/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች  የግብር መክፈል ጠቀሜታን አውቀው በተገቢ መልኩ ግብራቸውን  እንዲከፍሉ፣ ባለመክፈል  ከሚገጥማቸው የህግ ጥሰት  አንዲጠበቁ ፣ሀገራዊ ሀላፊነት እንዲወጡ  ከሚያረጋቸው ተግባራት  አንዱ ሞጁላር ስልጠና በማዘጋጀት  በተለያዩ ዙር ለ90 ሰዓት ግብር ከፋዮቹን ማሰልጠን ነው፡፡
ይህን ተከትሎ ጥቅምት በበጀት ዓመቱ ወርሃዊ የሞጁላር ስልጠና እየወሰዱ ለነበሩ የሶስተኛ ሰሚስተር ሰልጣኞች በታክስ የአስተደርና የወንጀል ቅጣቶች ዙሪያ የማጠቃለያ ሰልጠና ጥቅምት 18 /2017 ተሰጥቷል ፡፡
ወ/ሮ የሺወርቅ የቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ስልጠናው ሰጥተዋል ፡፡ 
ሰልጣኞችም የሞጁላር ስልጠና  አሰጣጥ በጣም ጥሩ እንደነበር ገንቢ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን ለሙያቸው እና  ለተቋሙ ያለው ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ  እንደሆነ ተናግረዋል።  
……………………………………………

M.O.R East Addis Ababa Branch

26 Oct, 12:10


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1.81 ቢሊዮን የታክስ ገቢ ሰበሰበ
………………………..
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ከቅ/ጽ/ቤቱ ማኔጅመንት ጋር ግምገማ ጥቅምት 14 /2017 ዓ.ም አድርጓል፡፡

ወ/ሮ ገነት አዳሙ ተፈራ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ውይይቱን ያስጀመሩ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የገቢ አሰባሰቡ 110.03% አፈጻጸም መድረሱን ጠቅሰው ለአፈጻጸሙ ስኬት በየደረጃ ያሉ ሀላፊዎችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል ፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ቡድን አሰተባባሪ አቶ ገንዘብ መካሻ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም የስራ አፈፃፀም አቅርበዋል ፡፡
በሪፖርታቸውም ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 1.65 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 1.81 ቢሊዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 110.03% መሆኑ ግልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 1.81 ቢሊዮን መካከል ብር 710.59 ሚሊዮን ከቀጥታ ታክሶች ፣ ብር 1.09 ቢሊዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 5.93 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ ነው፡፡

በግምገማውም የዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጆች ከዘርፋቸው አንጻር ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡
አቶ ሬድዋን ከድር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በሩብ ዓመቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሰበሰበው ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም አመራሩ እና ሠራተኛው ተናቦ በመስራቱ፣ ከምንጊዜውም በላይ ሰራተኛ ስራውን ለማከናወን ያለው የስራ ተነሳሽነት፣ ግብራቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት በከፈሉ ግብር ከፋዮች የተገኘ በመሆኑ አመራሮች እና ሠራተኞች፣ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
ስራ አስኪያጁ አያይዘው ያለንበት ወቅትም የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት በመሆኑ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰበስብ በሚደረግ ጥረት አሁንም በቀሩት ውስን ቀናት የሚፈለገውን ገቢ ሆነ ሌሎች ስራዎች በጥብቅ ዲሲፒሊን መሰራት እንዳለበት አሳስበው የግብር አሰባሰብ ሂደት ከብልሹ አሰራር የጸዳ በማድረግ፣ አገልግሎቱ የላቀ መሆን እንዳለበትና የተቋሙን ሆነ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በሀገር ደረጃ የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት ገቢን በብቃት መሰብሰብ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት ቅንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ የህግ ተገዢነት የነበራቸውን እና ለገቢው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ 13 ግብር ከፋይ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገ የዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1 የወርቅ እና 12 የብር ያገኙ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡ በዚህም የተሻለ የህግ ተገዢነት ያላቸው ዜጎችን ለማብዛትና የሀገርን ገቢ ለማሳደግ የበለጠ ጥረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
በማጠቃለያም በቀጣይ ሩብ ዓመት የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ሁሉም አመራርና ፈጻሚ ሙስናን በመዋጋት፣ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል እና ገቢ ሊያስገኙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ወቅቱን የጠበቀ የክልሎች የጋራ ገቢ ትልልፍ ማከናወን፣ ዲፖዚት ኢንትራንዚቶች እንዲቀንሱ ማድረግ፣ የሞጁላር ስልጠና አጠናክሮ መቀጠል፣ ኢ-ፋይል አድርገው ያልከፈሉት ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት እንዲከፍሉ ማድረግ፣ የኢ-ክፍያ፣ የቴሌ ብር ክፍያን እና የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን ማጠናከር፣ ተጨማሪ የገቢ ዕቅድን አጠናክሮ መቀጠልና የገቢ ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ መሰብሰብ እንደሚገባ አቅጣጫ በመስጠት ሰብሰባው ተጠናቋል፡፡
……………………….

M.O.R East Addis Ababa Branch

22 Oct, 11:51


በገቢዎች ሚኒስቴር ለምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች በሙሉ
ውድ ግብር ከፋዮቻችኝ
ከሐምሌ 1 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ የሒሳብ ማሳወቂያና መክፈያ ጊዜ መሆኑን ይታወቃል ፡፡
ስለሆነም ውድ ግብር ከፋዮቻችን ወቅቱን ጠብቃችሁ በማሳወቅ እና በመክፈል ከአላስፈላጊ ወልድና ቅጣት ድርጅታችሁን እንድታድኑ፣ መብታችሁን በማስጠበቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡
ወደቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዓመታዊ ንግድ ትርፍ ግብር ለማሳቀወቅ ስትቀርቡ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ዝርዝር በጥንቃቄ በመመልከት አሟልታችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን ፡፡
****ማሳሰቢያ፡- ሂሳቡ ሲመረመር የድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ሰው መቅረብ ግደታ አለበት!!

M.O.R East Addis Ababa Branch

22 Oct, 07:13


የሚንስተሮች ምክር ቤት የፌደራል የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 በማለት ያሻሻላው አንቀጾች ለውድ ግብር ከፋዮቻችን ለግንዛቤና ለማስታወስ እንዲረዳ ደንቡ እነሆ፡፡

M.O.R East Addis Ababa Branch

21 Oct, 11:28


የታክሥ ሥርዓት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ ::
………………….
በምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ካሉት የስራ ዘርፎች የታክስ ሥርዓት ዘርፍ አንዱ ነው ፡፡ይህን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 11/2017 በዘርፉ የሚገኙ የስራ ሂደት አሰተባባሪዎች እና ሌሎች በየደረጃው ካሉ መሪዎች ጋር የ2017 ዓ.ም የየመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል፡፡
አቶ ያዕቆብ ሽፋረ የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ስራአስኪያጅ ተወካይና የታክስ መረጃና ሽ/መ/መ/አስተዳደር የስራ ሂደት አስተባባሪ የእቅድ አፈጻጸሙን አቅርበዋል ፡፡
ከመሪ እቅዱ አንጻር ስራዎች የተገመገመ ሲሆን እንደ ዘርፍ የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች፤ ክፍተቶች እንዲሁም ተግዳሮት ተለይቶለውይትም ቀርቧል ፡፡
በቀጣይ ወራትም በ2017 በጀት ዓመት በተቋም ደረጃ የተቀመጠውን የመደበኛ እና የገቢ ማሳደጊያ እቅዶችን ለማሳካት በሚዘጋጀው የድርጊት መርሀ ግብር መሰረት ስራውን በጥብቅ ዲሲፕለን መመራት፣ ከመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ያልተጠናቀቁ ማህደራት ላይ ቅድሚያ በመስጠት እንዲጠናቀቁ ማድረግ፣የኦዲት አፈጻጸምን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ ፣ የታክስ ኦዲት አሰራር ስርአት በጥብቅ ድሲፕሊን እንዲተገበር ማስቻል ፣የስራ ክፍሉ ፈጻሚ እና ቡድን አመራር የመፈጸም አቅሙን እንዲያጎለብት የሚያስችሉ ስልጠናዎች እንዲያገኙ ማድረግ የሚሉና ሌሎችንም የስራ ከንውኖች በቀጣይ እንዲተገበሩ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል ፡፡
በቀጣይ ቀናትም እንደ ቅርንጫ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ውይይት የሚያካሄድ ይሆናል፡፡
…………………….
.

M.O.R East Addis Ababa Branch

21 Oct, 06:45


ለክፍል ሶስት ሰልጣኞች

M.O.R East Addis Ababa Branch

21 Oct, 06:39


ለክፍል ሁለት ሰልጣኞች