AASTU-ECSF @aastuecsf Channel on Telegram

AASTU-ECSF

@aastuecsf


The Official Telegram Channel Of Evangelical Christian Students Fellowship at AASTU.

Acc no: 1000656422959 Daniel Kebede and/or Samuel Tesfaye

Stay tuned via:
@galleryaastuecsfBot
@souceoflifeBot
@AASTU_Anony_Counseling_bot
@i4u_contact_bot

AASTU-ECSF (English)

Welcome to AASTU-ECSF, the official Telegram channel of the Evangelical Christian Students Fellowship at AASTU! If you are a student at AASTU looking to connect with like-minded individuals who share your faith and values, then this is the place for you. Our channel provides a platform for students to come together, share their thoughts, and engage in meaningful discussions about their Christian beliefs.

The Evangelical Christian Students Fellowship at AASTU is dedicated to fostering a strong sense of community among students who are passionate about their faith. By joining our channel, you will have access to a supportive network of fellow students who are committed to growing in their relationship with God and living out their faith on campus.

For those interested in getting involved with the fellowship, we offer opportunities for Bible study, prayer groups, community service projects, and more. Our goal is to create a welcoming and inclusive environment where students can explore their faith, deepen their spiritual life, and make lasting connections with others.

To stay updated on all our events and activities, be sure to follow us on our other channels as well: @galleryaastuecsfBot, @souceoflifeBot, @AASTU_Anony_Counseling_bot.

If you have any questions or would like to learn more about the Evangelical Christian Students Fellowship at AASTU, feel free to contact us at the provided account number: AMANUEL KETEMA AND/OR SELIHOM DEMEKE 1000510257492 or give us a call at +251907743926. We look forward to welcoming you to our community of faith! God bless.

AASTU-ECSF

18 Feb, 15:33


#Morning_Prayer

ሰላም እንዴት ናችሁ? ዘወትር ረቡዕ ጠዋት 12:00 ጀምሮ የሚኖረን የማለዳ ፀሎት በዚህም ሴሚስተር የሚቀጥል ስለሆነ ከነገ ጀምሮ ሁላችንም እየተገኘን እንድንፀልይ ይሁን።

🛐 ቂሊንጦ መካነ ኢየሱስ
🕛 12:00

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

18 Feb, 14:07


https://youtu.be/016vLvB4cng?si=mFWrKB9lYIdfZO99

AASTU-ECSF

17 Feb, 03:05


ትርፍ👇

ሰዎች ከባንክ አክስዮን ሲገዙ በተወሰነ ያህል ጊዜ ወደ ባንክ ገንዘብ ያስገባሉ። ባንኩም ከእነርሱ ባገኘው ገንዘብ ያተርፍበታል።ከዛም ካገኘው ትርፍ ለአክስዮን ገዣዎቹ ገንዘብ ያስገባል። ነገርግን ባንኩ አንድ ቀን ተነስቶ “ያስገባችሁት ገንዘብ ትንሽ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ተቆራጭ አልከፍልም” ወይም “እስከዛሬ የተቀመጠው ገንዘባችሁ ይኸው ሌላ ነገር የለም” ቢል አክስዮን ገዢዎቹ ይከሱታል። ምክንያቱም ባንኩ ከሰዎቹ ጋር በተፈራረሙት ውል ላይ ይህን እንዲያደርግ ስለማይፈቅድለት ። ገንዘቡን የወሰደው ሊያተርፍበት ከዛም ገንዘቡን አክስዮን ገዢዎቹ የትርፉ የረጅም ጊዜ ተካፋይ እንዲሆኑ ነውና።

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

16 Feb, 17:53


ሰላም ውድ የAASTU ECSF ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያቹ?😊

እረፍት መልካም እንደነበርና ጌታ በብዙ እያገዛችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን። እንደሚታወቀው አብዛኞቻችን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ክላስ በአግባቡ እንደምንጀምር ይታወቃል። በመሆኑም አብዛኞቻችን ለአዲሱ ሴሚስተር የሚሆኑ የትምህርት መሳሪያዎችን በመግዛት እራሳችህንን የምናዘጋጅበት ጊዜ ነው። ነገር ግን የትምህርት መሳርያዎች የመግዛት አቅም ምን አልባት የሌለን ወንድሞች/እህቶች ካለን ጌታ በረዳንና አቅማችን በፈቀደው መጠን እኛ ጋር ያዘጋጀን ስለሆነ በነጻነት እና ፍጹም ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ መውሰድ እንደምትችሉ እና በ @i4u_contact_bot በኩል እንድታወሩን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በጌታ ሃልዎት ተባረኩ!

#I4U_Mobilizers_Team
#CARING_HEARTS_SHARING_HANDS

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

14 Feb, 17:01


የመጀመሪያዎቹ አመታት የግቢ ቆይታ እንዴት ነበር? ከትምህርት አንፃር እንድሁም ከfellowship አንፃር ? ...

በዛሬው የሃላቅ ፓድካስት ዝግጅታችን ክርስቲያን ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ስለሚያሳልፉት ህይወት ከ መጨረሻ አመት ተማሪዎች (GC) ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] ሰባተኛ ክፍል [seventh Episode] ነው።

ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣ ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስተ‍ኣችንን ማግኘት ይችላሉ።
Spotify
Apple Podcasts
Teraki
RSS Feed
YouTube

እኛን ማግኘት ከፈለጉ እነዚህን በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡-
Anonymous Counseling bot
Telegram channel

AASTU-ECSF

10 Feb, 03:02


ልዉጠት👇

እንበልና አጠገባችን ያለ ሰው በትከሻችን ላይ አባ ጨጓሬ አየሄደ መሆኑን ቢነግረን ወዲያውኑ ምን ይሰማን ይሆን?

ደስ አንደማይለን መገመት አያሰቸግርም። እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ይህ ሲነገራቸው ሊጮሁ ወይም አርምጃ ያልተጠበቀ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። አሁን አባ ጨጓሬ ምኑ ደስ ይላል?
↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

07 Feb, 20:16


የመጀመሪያዎቹ አመታት የግቢ ቆይታ እንዴት ነበር? ከትምህርት አንፃር እንድሁም ከfellowship አንፃር ? ...

በዛሬው የሃላቅ ፓድካስት ዝግጅታችን ክርስቲያን ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ስለሚያሳልፉት ህይወት ከ መጨረሻ አመት ተማሪዎች (GC) ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] ስድስተኛ ክፍል [sixth Episode] ነው።

ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣ ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስተ‍ኣችንን ማግኘት ይችላሉ።
Spotify
Apple Podcasts
Teraki
RSS Feed
YouTube

እኛን ማግኘት ከፈለጉ እነዚህን በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡-
Anonymous Counseling bot
Telegram channel

AASTU-ECSF

06 Feb, 12:22


ሰላም እንዴት ናችሁ?

ከፊታችን እሁድ የካቲት 2 - ሐሙስ የካቲት 6 #Break_Mission በዱከም እና በሞጆ ከተሞች ላይ እንደሚኖረን ተናግረን እንዲሁም ምዝገባ ላይ ነበርን።

ነገር ግን እነዛ ከተሞች ላይ የምናርፍባቸው  እና አብረናቸው ወንጌል ከምንሰራባቸው ቤተ ክርስቲያኖች ጋር በነበረን ግንኙነት ከነሱ ከምንገኛቸው አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ እነዛን ግልጋሎቶች ማቅረብ እንደማይችሉ በቅርቡ ገልፀውልናል።

ያለ ቤተ ክርስቲያናቱ አገልግሎቶች ወደነዚህ ከተሞች ሄደን ፕሮግራም ማደረግ አስቸጋሪ ስለሚሆን የ2017 Break Mission የማይኖር መሆኑን  ከታላቅ ይቅርታ ጋር እንገልፃለን።

ለዚህ የወንጌል ስርጭት የተመዘገባችሁ ፣ ስትፀልዩ የቆያችሁ እንዲሁም በብዙ የደከማችሁ በሙሉ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንደገጠመን እንድትረዱን በጌታ ፍቅር እየገለፅን ስለድካማችሁ በሙሉ ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ።

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 19:00


ማስታወቂያ

📌 የተወደዳችሁ የአንደኛ አመት ተማሪዎች Retreat የካቲት 21 - 23 ስለሚሆን ካሁኑ እንድትዘጋጁ ይሁን።

📌 ከቤት ስትመጡ ለBook Club መፅሃፍት ያላችሁ ይዛችሁ እንድትመጡ አደራ እንላለን።

📌 Half Life & GC Coupons የወሰዳችሁ ሸጣችሁ እንድትመጡ Committees ያሳስቧችኋል።

📌 ቀጣይ ሳምንት ጀምሮ መደበኛ የ2nd Semester ፕሮግራሞች (Small Group, General Fellowship, Morning Prayer, Team...) ስለሚጀምሩ ሁላችሁም እንድትገኙ ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:57


#QandA

የዛሬው የጥያቄና መልስ አሸናፊዋቻችን 🥁🥁🥁

🥇Bitanya Kibru 3rd Elctrical
🥈Samuel Waktassu 3rd Electromechanical
🥉Kalkidan Bantewesen 5th Architecture

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:49


🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁

የዛሬውን የጥያቄ መልስ እና አሸናፊዎችን ይፋ እናደርጋለን። 🎉🎉🎉

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:46


#QandA

መልሶች
1. D
2. C
3. D
4. A
5. B
6. C
7. Matthew 22:1-14
8. Unknown (Matthew 2)
9. አጋቦስ (Acts 21:10-11)
10. ሚክያስ (Micah 5:2)

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:42


#QandA

ሰዓት አልቋል

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:27


#QandA

1. የዚህ አመት Theme ንጉሱን መከተል እንደሆነ ይታወቃል እናም ከማቴዎስ ወንጌል ስለ ንጉሱ የተለያዩ ትምህርቶችን በ1st Semester General Fellowship ላይ ስንማር ቆይተናል ከነዛ ርዕሶች ውስጥ ያልተማርነው የቱን ነው?
A. የንጉሱ ግብዣ      C. የንጉሱ አደራ
B. በክብር የሚመለሰው ንጉስ D. ትሁቱ ንጉስ

2. የስሙ ትርጉም "እግዚአብሔርን ማክበር (Honoring God)" የሆነው ማነው?
A. ሳሙኤል  C. ጢሞቴዎስ  
B. ኢዩኤል     D. ቴዎፍሎስ

3. በማቴዎስ 1 ላይ ባለው የንጉሱ የዘር ሃረግ ውስጥ ማቴዎስ ስሙን ያልጠቀሰው ማነው?
A. ሰልሞን      C. አሣፍ
B. ሰሎሞን     D. አካዝያስ

4. የብሉይ ኪዳን መፅሃፍ ቅዱስ በአጠቃላይ ስንት ህጎችን ይዟል?
A. 613   B. 623   C.  633   D. 603

5. ህጉን እና የአባቶችን ወግ በመጠበቅና ንፁህ በመሆን ነው እረፍትን ማግኘት የሚቻለው ብለው የሚያምኑት የሃይማኖት ቡድን የቱ ነው?
A. ኢሴናውያን    C. ሄሮዳውያን
B. ፈሪሳውያን     D. ቀናተኞች

6. በእስራኤል ላይ ትፈርድ የነበረች ሴት ማናት?
A. ሩት       C. ዲቦራ
B. አስቴር   D. ሊዲያ

7. በ1st Semester በነበረን General Fellowship ላይ የንጉሱ ግብዣ በሚል ርዕስ ተምረን ነበር የትምህርቱ መነሻ የሆነው የመፅሃፍ ቅዱስ መፅሃፍ እና ምዕራፍ ምን ነበር?

8. ኢየሱስን ለማየት ከምስራቅ የመጡት ጠቢባን (ሰብአ ሰገል) ቁጥር ስንት ነበር?

9. የጳውሎስን መታጠቂያ በመውሰድ በኢየሩሳሌም እስር እንደሚጠብቀው የተናገረው ነቢይ ማነው ?

10. ኢየሱስ በቤተልሔም እንደሚወለድ የተናገረው ነብይ ማን ነው ?

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:25


#QandA

      የጥያቄ እና መልስ ጊዜ

👮‍♂️ የውድድር ህግ ⚖️

🙅‍♂ አንዴ የተላከን መልስ ባለበት Edit ማድረግ ፈጽሞ አይቻልም 🚫
ውድድሩ የ15 ደቂቃ ቆይታ ብቻ ይኖረዋል
🥇🥈🥉 አሸናፊዎች በፕሮግራማችን መጨረሻ ላይ ይገለፃሉ

👉 መልሶችን የምትልኩት በ @SamiSTR10 ብቻ ነው።

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:23


#QandA

በቀጣይ ደግሞ አጓጊው የጥያቄና መልስ ጊዜ ይሆናል🥳🥳🥳

ዝግጁ የሆነ እና በንቃት እየተሳተፈ ያለ እዚህ ላይ በemoji React እናደርጋለን 😍

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 18:18


#የመባ_ጊዜ

አሁን ደግሞ ህብረታችንን ለመደገፍ የምንችለውን ያህል መባ እንሰጣለን።

👇 Click to Copy 
1000656422959 CBE
Daniel Kebede and/or Samuel Tesfaye

ተባረኩ 🙏

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:40


#Sermon 🎤

ቃለ እግዚአብሔር 📖
ርዕስ - እውነተኛ ደቀመዝሙር

Jitu Tesfaye
5th Year
Software Engineering
Choir Team


Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:39


#Sermon 🎤

አሁን ደግሞ የተወደደውን የእግዚአብሔርን ቃል 📖 የምንሰማበት ጊዜ ይሆናል። ሁላችንም በትኩረት ቃሉን ለመማር በሚፈልግ ልብ ሆነን እንማራለን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:34


#Gift 🎁

98127-7184-27945

Take Screenshot and post on the Comment below 👇👇👇

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:32


#Gift 🎁

እስካሁን የነበሩትን ፕሮግራሞች በትኩረት እየተከታተላችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።

በቀጣይ ደግሞ የካርድ ስጦታ ጊዜ 🎁🎁🎁

ሁላችሁም ተዘጋጁ 📲

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:31


#Worship

ደስ የሚል ዝማሬ ነበር 😊 ያፊ እግዚአብሔር ይባርክህ
ሁላችንም ተባረክ እንበለው

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:19


#Worship 🎶

የዝማሬ ጊዜ 🎧🎸🎸
አብረን እናመልካለን

ያፌት ኤልያስ
2nd Year
Mining Engineering
Choir Team


Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:18


#Worship 🎶

ፕሮግራማችን አሁንም ይቀጥላል። አሁን ደግሞ እግዚአብሔርን በዝማሬ የምናመልክበት ጊዜ ነው። 🎸

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:17


#Prayer

አሜን አማኑኤል ስለሆነልን እግዚአብሔር ከኛ ጋር ስለሆነልን እግዚአብሄር ይመስገን🙏

ወንድማችን ያብ ተባረክልን😊 እግዚአብሔር ይባርክህ በሉት

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

05 Feb, 17:01


#Prayer

የፀሎት ጊዜ 🙏🙏🙏
ከወንድማችን ጋር አብረን እንፀልይ

Yeabsira Abinet
4th Year
Chemical Engineering

Counseling Team

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

01 Feb, 17:01


⚠️ Urgent Notice ⚠️

#Break_Mission_2017

ሰላም የተወደዳቹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ከጌታ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለሁላችሁም በያላችሁበት ይሁን።

📌በሚቀጥለው ሳምንት ከዕረቡ - እሁድ ማለትም ከጥር 28 እስከ የካቲት 02 የነበረው
የወንጌል ስርጭት (Break Mission) ጊዜ ዩኒቨርስቲያችን ባደረገው የመመዝገቢያ ቀናት ለውጥ ምክንያት እኛም የወንጌል ስርጭቱን ቀናቶች ለማሸጋገር ተገደናል።

📌 በዚህም ምክንያት ከዕረቡ - እሁድ ማለትም ከጥር 28 - የካቲት 02 ሊደረግ የነበረው የወንጌል ስርጭት ጊዜ ወደ እሁድ ማለትም ከየካቲት 02 እስከ የካቲት 06(ሀሙስ) የሚቆይ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን።

📌 አብራችሁን ልትወጡ የተመዘገባቹ ወንድምና እህቶች የ 2nd Semester ምዝገባ በጊዜ አርብ(ጥር 30) እንድትጨርሱ ይሁን!!!

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on:
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

31 Jan, 17:01


የመጀመሪያዎቹ አመታት የግቢ ቆይታ እንዴት ነበር? ከትምህርት አንፃር እንድሁም ከfellowship አንፃር ? ...

በዛሬው የሃላቅ ፓድካስት ዝግጅታችን ክርስቲያን ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ስለሚያሳልፉት ህይወት ከ መጨረሻ አመት ተማሪዎች (GC) ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] አምስተኛ ክፍል [Fifth Episode] ነው።
ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣ ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስተ‍ኣችንን ማግኘት ይችላሉ።
Spotify
Apple Podcasts
Teraki
RSS Feed
YouTube

እኛን ማግኘት ከፈለጉ እነዚህን በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡-
Anonymous Counseling bot
Telegram channel

AASTU-ECSF

29 Jan, 07:25


#General_Fellowship


ሰላም እንዴት ናችሁ? 😊 የእረፍት ሁለተኛ ሳምንታችሁ እንዴት ነው? በነገር ሁሉ ጌታ አብሯችሁ እንዳለ እናምናለን። አንደኛ አመቶችም ፈተና ጥሩ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።

ዛሬም ሁላችንም የምንወደው የረቡዕ የአምልኮ እና የህብረት ጊዜያችን የሚቀጥል ይሆናል ።

በፕሮግራማችንም ላይ :
     🙏የምንፀልይበት
     🎹 በጋራ ጌታን በዝማሬ የምናመልክበት እና
     📖 ከእግዚአብሔር ቃል የምንካፈልበት ጊዜ ይኖረናል ።


ስለዚህ በግቢ ውስጥ ያለን ሁላችንም በጊዜ 12:00 ላይ :
      👉 መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻችንን ይዘን ፣
      👉 ሌሎች የምናውቃቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ወደ ምንናፍቀው ህብረታችን እንምጣ።



#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on:
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

27 Jan, 03:04


መጽናናት ከየት ይገኛል?👇

ይሄ ማለት እግዚአብሔር እንደምናዝን ያውቃል? እናም ምንም እያደረገ አይደለም? በሰው ልጅ የሕይወት ኡደት ውስጥ ከማይቀሩት አላባውያን መካከል አንዱ ሀዘን እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱስ በግልፅ ይነግረናል። ሰው በመሆናችንም የዚህ ስሜት ተካፋዮች ነን ......

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

24 Jan, 19:15


ሰላም ውድ የሃላቅ ፖድካስት ቤተሰቦች በዛሬው ዝግጅታችን እንዴት መፀለይ እንዳለብን ከእግዚአብሔር ቃል አንስተን ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛቿለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] ክፍል 4 [4th Episode] ነው።

ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣

AASTU-ECSF

22 Jan, 07:49


#General_Fellowship


ሰላም ሰላም በጌታ የተወደዳችሁ ቤተሰቦች 🤗
እንዴት ናችሁ? 😊 እረፍት በጥሩ ሁኔታ እያሳለፋችሁ እንዳለ ተስፋ እናደርጋለን። በፈተና ላይ ያላችሁም አንደኛ አመቶች ጌታ እየረዳችሁ ነው ብለን እናምናለን።

ዛሬ ሁላችንም የምንወደው የረቡዕ የአምልኮ እና የህብረት ጊዜያችን የሚቀጥል ይሆናል ።

በፕሮግራማችንም ላይ :
     🙏የምንፀልይበት
     🎹 በጋራ ጌታን በዝማሬ የምናመልክበት እና
     📖 ከእግዚአብሔር ቃል የምንካፈልበት ጊዜ ይኖረናል ።


ስለዚህ በግቢ ውስጥ ያለን ሁላችንም በጊዜ 12:00 ላይ :
      👉 መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻችንን ይዘን ፣
      👉 ሌሎች የምናውቃቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ወደ ምንናፍቀው ህብረታችን እንምጣ።


የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on:
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

20 Jan, 04:04


አልፈረደብኝም👇

እኔ ከመቸኮሌ ብዛት እነርሱን ትዕቢተኛ አድርጌ መውሰዴ አሳፈረኝ፣  ዓይነ ስውር  ነበርና :: አብሮት ያለው ልጅም  እያገዘው እንደነበር ሲገባኝ ተሸማቀኩ አይገልፀውም። ምን አለ ዝም ብል እንኳን አስባለኝ። ሰውን እንዲህ ነው ብሎ ለመናገር ከባድ ሆነብኝ።
በዚህ ምድር ባለን መንፈሳዊ ህይወትም የቱንም ያህል ጥሩና መልካም እንደሆንን ብናስብ .......

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

17 Jan, 17:06


ሰላም ውድ የሃላቅ ፖድካስት ቤተሰቦች በዛሬው ዝግጅታችን እንዴት መፀለይ እንዳለብን ከእግዚአብሔር ቃል አንስተን ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛቿለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] ሶስተኛው ክፍል [Third Episode] ነው።

ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣ ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስታችንን ማግኘት ይችላሉ።

Spotify
Apple Podcasts
Teraki
RSS Feed
YouTube

እኛን ማግኘት ከፈለጉ እነዚህን በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡-

Anonymous Counseling bot
Telegram channel

AASTU-ECSF

13 Jan, 05:05


ብልህ ገበሬ👇

በአንድ አከባቢ በሚደረግ የገበሬዎች ውድድር  ላይ በየዓመቱ የሚያሸንፈው አንድ ገበሬ ነበር በዚህም የተደነቀ ጋዜጠኛ ስለ ገበሬው አንዳንድ ነገሮች ማጣራት ይጀምራል ይህም ገበሬ ምርጥ የበቅሎ ዘር እንዳለው እና ምርጡንም ዘር ለተፎካካሪዎቹ እንደሚሰጥ ይሰማል። በአንድ ወቅት በተዘጋጀ ዉድድር ላይ አሽናፊውን እንዲ በማለት መጠይቁን ይጀምራል.....

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

07 Jan, 12:08


https://youtu.be/bwFb66glLRE?si=ZR7yQFXMi4Wd44Nc

AASTU-ECSF

07 Jan, 12:08


https://youtu.be/U5VvGXxTghw?si=-u-yjKhf-O2yRmgi

AASTU-ECSF

07 Jan, 11:01


ሰላም የተወደዳችሁ ጥሩ የበዓል ውሎ ላይ እንዳላችሁ ተስፋ እናደርጋለን። ልዩ የበዓል ፕሮግራም በተስፋ ቲቪ ላይ አሁን እየተላለፈ ስለሚገኝ የምትችሉ መከታተል ትችላላችሁ ከቲቪ በተጨማሪም በYouTube ማየትም ትችላላችሁ። መልካም በዓል 🎉

https://youtu.be/U4nDMDTDaAM?si=VMbld30HIsnAOkUX

AASTU-ECSF

06 Jan, 03:03


ሉአላዊ አምላክ👇

አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሄር ዝምታ ከፈተና አንፃር ሊገለጥ ይችላል፡፡ ምናልባትም ልባችን በተሰበረበት፤ ባዘነበት ሁኔታ ለእርሱ ያለንን ቦታ ለማወቅ፡ ካደረገው ነገር ይልቅ እርሱን እንደምትወዱት ሊያውቅ ወዶ አድርጎ እደሆነስ ማን ያውቃል? ዝምታው በተፈጠረው ነገር ወደ እርሱ ለመቅረብ ወይስ ለመራቅ እርሱን ለማመን ወይስ ለመካድ ቢሆንስ......

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

01 Jan, 19:51


👑The King Is Born 👑


#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

01 Jan, 17:32


#HappeningNow

WORD OF GOD

👑The King Is Born 👑


#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

01 Jan, 16:24


#HappeningNow

WORSHIP TIME

👑The King Is Born 👑


#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

01 Jan, 16:04


#HappeningNow

WORSHIP TIME

👑The King Is Born 👑


#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

01 Jan, 14:44


“ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።”
— ማቴዎስ 2፥11

👑The King Is Born

📌 ስንመጣ በጌታ ያልሆኑ ጓደኞቻችንን ሁሉ እየጋበዝን አብረናቸው እንምጣ 😊

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

01 Jan, 07:06


https://maps.app.goo.gl/ZFRTrdwAXGrW2mxg7

📍#Feche_Tulu_Dimtu_Mulu_Wengel is next to Tulu Dimtu Taxi Tera

AASTU-ECSF

30 Dec, 07:01


#First_Year_Batch_Program

ሰላም ሰላም የተወደዳችሁ የአንደኛ አመት ቤተሰቦቻችን🤗🤗🤗 እግዚአብሔር ረድቷችሁ ዛሬ ለዚህ ሴሚስተር የመጨረሻ Batch ፕሮግራም ደርሳችኋል። 🎉🎉🎉

በእስካሁኖቹ ፕሮግራሞች ሁሉ በብዙ እንደተጠቀማችሁ ተስፋ እያደረግን ዛሬ በአይነቱ ለየት ያለ የጨዋታ ጊዜ ይኖረናል በዚህም ደግሞ የምትጫወቱበት ፣ የምትዝናኑበት ከዛም ባለፈ የምትማሩባቸው ጨዋታዎች ይኖራሉ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ 🙏 አብረንም በፀሎት የምንሆንበት እና 🎹እግዚአብሔርን በዝማሬ የምናመልክበትም ጊዜያት አሉ።

ስለዚህ በሰዓቱ 12:00 🕛 ላይ ጓደኞቻችሁን ፣ ወንድምና እህቶቻችሁን ይዛችሁ ፌሎ እንገናኝ።

መቅረትም ማርፈድም ያስቆጫል

የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

30 Dec, 05:33


ሚስጥሩ👇

ድሮ ልጆች እያለን የምናየው ፊልም ትዝ ይልሻል?” ስል ጠየኳት። “የትኛው ነበር?” አለችኝ። “Superman፣ ትዝ ካለሽ እርሱ የመጣው ክሪፕቶን ከተባለችው ፕላኔት ነበር እና ያ ሁሉ ጉልበትና ጥንካሬ የመጣው ከመጣበት ስፍራ ከተካፈለው ማንነት የተነሳ ነው እንደውም ካየሽው The daily planet የሚባል company ውስጥ ጋዜጠኛ ሆኖ ይሰራ አልነበር? ታዲያ ከሰው የሚለየው ነገር አልነበረውም ግን ካየሽው የችግር ቀን ራሱን ቀይሮ ይገኛል። ልክ እንደዚሁ......

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

27 Dec, 17:00


እንደ ክርስቲያን ድጋፍን(እርዳታ) ከሰዎች መጠየቅ አስፈላጊ ነው? መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ድጋፍ ምን ይላል? ድጋፍን መጠየቅ ደካማ ጎንን ማሳያ ነው?
በዛሬው የሃላቅ ዝግጅታችን ድጋፍን ወይም እርዳታን ስለመጠየቅ አስፈላጊነት እና ምንነት ከ counseling team አባላት ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንድትከታተሉ እንጋብዛቿለን።

ይህ የምእራፍ 2 [Season 2] ሁለተኛ ክፍል [Second Episode] ነው።

ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣
ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስተ‍ኣችንን ማግኘት ይችላሉ።

Spotify
Apple Podcasts
Teraki
RSS Feed
YouTube

እኛን ማግኘት ከፈለጉ እነዚህን በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡-
Anonymous Counseling bot
Telegram channel

AASTU-ECSF

25 Dec, 06:14


#CHRISTMAS_CARNIVAL


Location: kilinto primary school
Map: https://maps.app.goo.gl/cshXNpv9HRnSDtqn7

+251961099526 Gedion
+251983354799 Dagmawit


#I4U_TEAM
#CARING_HEARTS_SHARING_HANDS

AASTU-ECSF

24 Dec, 08:54


ሰላማችሁ ይብዛ ተወዳጆች Christmas Ticket Lottery የምትገዙ ከFund Coordinators ማግኘት ስለምትችሉ እየደወላችሁ ከእነሱ እንድትወስዱ እንላለን።

🎁 1ኛ ዕጣ AirPod Pro🎁 100Br
🎁 2ኛ ዕጣ Hoodie 🎁 50Br
🎁 3ኛ ዕጣ ስዕል 🎁 50Br
🎁 4ኛ ዕጣ KK for 5 days🎁 50Br
🎁 5ኛ ዕጣ እርጥብ for 5 Days🎁 30Br
🎁 6ኛ ዕጣ Mystery Box 🎁 50Br

Fund Coordinators
አብርሃም - +251965461076
ብፁአን - +251996717744
ቤተልሔም - +251978142393
ፍሬው - +251954726441
በረከት - +251953757720
በእምነት - +251941780781
ኢዮሲያስ - +251900289463
ክብሮም - +251901529464
አማኑኤል - +251965461112
ናትናኤል - +251985361110

#Fund_Coordinators

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

24 Dec, 08:34


🎓#GC_Batch_Program🎓

ሰላም እንዴት ናችሁ🤗 GC ተማሪዎቻችን🧑‍🎓 ዛሬም አብረን የምንፀልይበት ፣ በዝማሬ የምናመልክበት እና ከእግዚአብሔር ቃልም የምንማርበት GC Batch ፕሮግራም ዛሬም ከ12:00 ጀምሮ ስለሚቀጥል GC የሆንን ሁላችንም በጊዜ ሳናረፍድ ፣ ወንድም እህቶቻችን ጋር ተጠራርተን በጊዜ እንገኝ።


For more info contact the GC Committees :
👉 Saron - 0912443297
👉 Yoska - 0961096978
👉 Sofonias - 0964345393
👉 Abigail - 0915007965
👉 Bemnet - 0916514667
👉 Amanuel - 0953387761
👉 Yabets - 0940136512
👉 Yoseph - 0962323563


የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Follow AASTU ECSF on :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

24 Dec, 03:15


#I4U_TEAM
#CARING_HEARTS_SHARING_HANDS
#CHRISTMAS_CARNIVAL

AASTU-ECSF

23 Dec, 03:15


#I4U_TEAM
#CARING_HEARTS_SHARING_HANDS
#CHRISTMAS_CARNIVAL

AASTU-ECSF

23 Dec, 03:02


መከተል👇

በእስራኤላውያን ልማድ አንድ እረኛ ከበጎቹ ፊት በመቅደም የእረኝነቱን ተግባር ይወጣል :: ወደ እኛ ሀገር ልማድ ስናመጣው ደግሞ እረኛው ከማስከተል ይልቅ በጎቹን ከፊት አስቀድሞ እርሱ ከኋላ በመሆን የእረኝነቱን ሚና ይፈፅማል።

ሁለቱም በግ የማሰማሪያ መንገዶች ቢሆኑም መሰረታዊ ልዩነት አላቸው። ይኸውም .......

↪️ ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

Article By Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

22 Dec, 19:48


https://youtu.be/Cqo87LSFfzg?si=aQvabjkPmAvtN2xJ

SHARE || SUBSCRIBE

Follow AASTU ECSF on :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

22 Dec, 05:39


#CHRISTMAS_CARNIVAL

የተወደዳችሁ የAASTU fellowship ተማሪዎች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ።

ዕሮብ በማስታወቂያ ሲነገር እንደነበረው I4U የሚያዘጋጀዉ የCHRISTMAS CARNIVAL መጪው ዕሮብ ታህሳስ 16 ከ7:30 ጀምሮ በቂሊንጦ primary school የምናከብር ይሆናል

የክርስቶስ ኢየሱስን ልደትን እያሰብን ለ50 ህጻናት ስጦታ የምንሰጥበት እንዲሁም ከልጆቹ ጋር የምንተዋወቅበት እና የምንጫወትበት ጊዜ ይኖረናል። 

ስለዚህ የምንችል ሁላችን መተን ከልጆቹ ጋር መልካምን ጊዜ እናሳልፍ

❗️ብር ሰብስባችሁ ያላስገባችሁ small group ማስገባታችሁን እንዳትዘነጉ አደራ

Stay blessed!
#I4U
#caring_hearts_sharing_hands

AASTU-ECSF

21 Dec, 07:04


#digital_mission_week
#gospel_week
#DAY_6
#wallpaper

AASTU-ECSF

07 Dec, 12:46


https://youtu.be/ztqeJ0ZWNKg?si=j3XMsOinNBG9YRG4

Watch | SHARE | SUBSCRIBE

 
#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

30 Nov, 03:49


ሰላም ቅዱሳን የጌታ ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ

እንደሚታወቀው ዛሬ የወንጌል ስርጭት ስላለን ሁሌችንም #2:00 ፌሎ እንድንገኝ ይሁን።
የምናውቃቸውን እየጠራን እንምጣ።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ድል አድርጓል አሁንም ያደርጋል ወደፊትም ብቻውን ድል ያደርጋል!!!

ተባረኩ🙌

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

25 Nov, 03:00


በጌታ ተደስቶ መኖር

በማላውቀው ሁኔታ ትልቅ ገደል ውስጥ ገብቻለሁ። ለመውጣት ብዙ እታጋላለሁ ነገር ግን ተመልሼ እውዳቃለሁ፥ እርዳታን ፈልጌ ብዙ እጣራለሁ የሚሰማኝ ግን አልነበረም አሁንም ተመልሼ ሀይሌን አሰባስቤ ለመውጣት እታጋላለሁ ነገር ግን አሁንም መውደቄ አልቀረም። ጥሬቴን አላቆምኩም እየታጋልኩ ነው ።

በክርስትና ህይወታችን ጌታ የሚፈልገውን ህይወት መኖር የአብዛኞቻችን ፍላጎት ነው። በምንኖረው ህይወት ጌታን ለማስደሰት እናሞክራለን ነገር ግን ያቅተናል ተመልሰን እንወድቃለን። ብዙ ጊዜ በራሳችን ጥረት መልካም ሰው ለመሆን እንጋጋጣለን፥ እግዚአብሔርን ለማስደስት ትግል ውስጥ እንገባለን ነገር ግን አይሳካልንም። የምንፈልገውን ህይወት ሳይሆን የማንፈልገውን ህይወት ስንኖር ራሳችንን እናገኘዋለን ።

በቃ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ህይወት እኖራለሁ ብለን ቃል እንገባለን ፣እንጥራለን ፣እንታገላለን እንደዛ ብለን ሳንቆይ የማንፈልገውን ህይወት ስኖንር ራሳችንን እናገኘዋለን።

ጌታ ህይወታችን ፈፅሞ እርሱ ላይ እንዲደገፍ ይፈልጋል እርሱን ለማስደሰት ከመትጋታችን በፊት በእርሱ እንድንደሰት ይፈልጋል። ምን አልባት አሁን እያለፍንበት ያለው መንገድ በቡዙ ድካም እና ዝለት ውስጥ ይሆናል ተስፋ የሚያስቆርጡ የህይወት ምዕራፎችን እያለፍን ይሆናል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን አይናችንን ከራሳችን ከሁኔታዎች ካለን ነገር ሁሉ ላይ አንስተን በመስቀል ላይ የሞተለን ጌታ ላይ ማድረግ ያስፈልጋል ።

የጌታ ደስታ እርሱን በማወቅ እንድንደሰት እና ህይወታችንን በእርሱ የሚገኘውን ዕረፍት በማረፍ እንድንጀምር ነው።

#ተባረኩ

Article@Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

20 Nov, 09:36


#General_Fellowship
#Panel_Discussion


ሰላም ሰላም በጌታ የተወደዳችሁ ቤተሰቦች 🤗
እንዴት ናችሁ? 😊 ሁሉ ሰላም እንደሆነ እና መልካም ሳምንት እንደነበር ተስፋ እናደርጋለን ።

ዛሬ ሁላችንም የምንወደው የረቡዕ የአምልኮ እና የህብረት ጊዜያችን የሚቀጥል ይሆናል ።

ዛሬ በሚኖረን የህብረት ጊዜ :-
📌 አብረን የምንጸልይበት ፣
📌 አብረን የምናመልክበት ፣
📌 ጥያቄዎቻችን የሚመለሱበት እና የምንወያይበት የ Panel Discussion ጊዜ ይኖረናል።


ስለዚህ ሁላችንም በጊዜ 12:00 ላይ :
      👉 መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻችንን ይዘን ፣
      👉 ሌሎች የምናውቃቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ወደ ምንናፍቀው ህብረታችን እንምጣ።


የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

Telegram | YouTube | Instagram | TikTok

AASTU-ECSF

13 Nov, 12:35


#ደም_ልገሳ
#Blood_Donation
#Happening_Now

AASTU-ECSF

13 Nov, 11:11


#ደም_ልገሳ
#Blood_Donation
#Happening_Now

AASTU-ECSF

12 Nov, 06:01


ታስታውሳላችሁ የደጉን ሳምራዊ ታሪክ በመንገድ ላይ ላገኘው ችግረኛ ራራለት አያቹ? ልክ እንደዚሁ እኛም የክርስቶስን ፈለግ እንድንከተል ተጠርተናል። ለዚህም ነው አምላክ ከሰጠን ስጦታዎች መካከል አንዱ የሆነው ደማችን በመስጠት የምናገለግለው። ማቴዎስ 5:14 ላይ እኛ የዓለም ብርሀን እንደሆንን ይናገራል። ታዲያ ይህ ደም የመስጠት ተግባር ብርሀናችን ከፍ ብሎ ለሌሎች እንዲበራ የሚያስችል ነው። ተስፋ አጥተው የተቀመጡ አሉና የክርስቶስን ፈለግ በመከተል በፍቅር በመስጠት ለሌሎች እንኑር።ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለእኛ ያሳየንን ፍቅር ለዓለም የምንገልጽበት ተጨባጭ መንገድም ነው።

❗️እያንዳንዱ የምንሰጠው የደም ጠብታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚፈስ ፍቅር እና እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር መገለጫ እንደሆነ እናስታውስ።


AASTU_ECSF


#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

11 Nov, 06:00


ደም መለገስ ለእኛ ምን ይጠቅመናል?

ከመንፈሳዊ ሽልማቶች በተጨማሪ ተግባራዊ ጥቅሞችም አሉ፡-

ግላዊ እድገት፡ ማመንታትን ማሸነፍ እና ከምቾት ዞናችን መውጣት ቁርጠኝነታችንን ያጠናክራል እናም በራስ መተማመንን ያዳብራል። እያንዳንዱ ልገሳ ለድፍረት እና ለአገልግሎት ያለን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ይሆናል።

የአትራፊነት ስሜት፡- ደማችን ሕይወትን እንደሚያድን ማወቃችን ኃይለኛ ማበረታቻ ነው። የአንድን ሰው ህይወት ትርጉም ይሰጠዋል፣የእግዚአብሔር ፀጋ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን በስራው ንቁ ተሳታፊዎች መሆናችንን ያስታውሰናል።

AASTU_ECSF

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

11 Nov, 05:31


ጊዜን የመጠቀም ጥበብ

የጊዜ ዋጋ
ጊዜ ምን ማለት ነዉ?
የተሳሳቱ የጊዜ አጠቃቀም መንገዶች
ጊዜን እንዴት እንጠቀም?


በ2022 በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት መሰረት 82% የሚሆኑ ሰዎች የተወሰነ የጊዜ አጠቃቀም ስርዓት የላቸዉም። 33% የሚሆኑ ሰዎች ብቻ *to-do-list* ይጠቀማሉ። የዕቅድ ስርዓት የሚጠቀሙት ደግሞ 12% የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸዉ።

በእጃችን ላይ ሰዓት ማድረጋችንና በስልካችንም መኖሩ ፣ በሁሉም ነገር ከጊዜ ጋር መቆራኘታችንም የጊዜን አስፈላጊነት ለመረዳታችን እንደማሳያ መወሰድ ይችላሉ። በጊዜ የተሳሰርን ብቻ ሳንሆን በጊዜ የምንመራ ፣ ከጊዜ ዉጭ መሆን የማንችል ፍጥረቶች ነን። ታዲያ ጥያቄዉ ፤ የጊዜን አስፈላጊነት ያለማንም አስረጅ በራሳችን የምንረዳዉ ነገር ሆኖ ሳለ ለምንድን ነዉ በስርዓት ልንጠብቀና ልናስተዳድረዉ ያልቻልነዉ? መፍትሄዉስ ምንድን ነዉ? እነዚህን ጥያቄዎች ጨምሮ ጊዜን በተሻለ እንድንጠቀም ሊረዱን የሚችሉ ሃሳቦችን ከማየታችን በፊት ስለ ጊዜ ምንነት በሚከተለዉ ትግበራ በጥቂቱ ለመረዳት በመሞከር እንጀምር።

ጊዜን ስታስቡ ስለጊዜ ምን ማለት ትችላላችሁ? ለማሰብ ሞክሩ እስኪ…። ለምሳሌ እኔ ስለጊዜ ሳስብ የሚመጡልኝ ሃሶቦች ቢኖሩ ፤
1.ጊዜ የማይተካ ሃብቴ ነዉ።
2.ጊዜን በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ከላይ በተቀመጠዉ ምሳሌ መሰረት የቻላችሁትን ያክል ለመፃፍ ሞክሩ። ፅፋችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ‹‹ጊዜ›› በሚሉት ቃሎች ምትክ ‹‹ህይወት›› የሚለዉን አስገቡ።
1.ህይወት የማይተካ ሃብት ነዉ።
2.ህይወት በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ከላይ የተቀመጠዉ ትግበራ ለጊዜ የምንሰጠዉን ትርጉም ደግመን እንድናስብ ያስረዳል። ይህም ፤ ጊዜ ህይወት ነዉ ፣ ህይወት ደግሞ ጊዜ ለሚለዉ አፅንዖት ይሰጣል። ስለዚህ ጊዜን ማስተዳደር ወይም የጊዜ አጠቃቀም ስንል በሌላ አባባል ህይወትን ማስተዳደር ወይም የህይወት አጠቃቀም እያልን። ጊዜን መጠቀም/ማስተዳደር ደግሞ መስራት ባሉብን ስራዎች መሰረት ጊዜን መከፋፈል ማለት ነዉ።

ነገር ግን ብዙዎች (82% የሚሆን የአለም ህዝብ) ይህን የከበረ ዉድ ሃብት እንዴት በተወሰነ የማስተዳደር ጥበብ እንደሚጠቀሙበትና እንደሚያተርፉበት አያዉቁም። ይሁንና በተወሰነም ቢሆን ጊዜአቸዉን እየተቆጣጠሩ እንዳለ እንዲሰማቸዉ የሚያደርጓቸዉን ፤ ነገር ግን ትርፋማነታቸዉን የሚቀንሱ የጊዜ አጠቃቀም ልማዶችን ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ፤ ዛሬ መስራት የነበረባቸዉን ስራ ራሳቸዉን በማባበል መሰራት ከነበረበት ጊዜ ቆይቶ መስራት (Procrastination) ፣ ሁለት ስራ በተመሳሳይ ጊዜ መስራት (Multitasking) ፣ ግልፅ ያለሆኑ ግቦችን ማስቀመጥ ፣ ቅድሚያ ሊሰጠዉ ለሚገባዉ ነገር ቅድሚያ አለመስጠት ፣ ዝቅተኛ የሆነ የዕቅድ ልማድና የመሳሰሉት ሊረዱ የሚችሉ ቢመስሉም ዕገዛቸዉ ዘላቂነት የለዉም።

ስለዚህ ይህን ጊዜ የተባለ ወሳኝ ነገር እንዴት በጥበብ ፤ ለዉጤታማነት መጠቀም እንችላለን?
እንግዲህ በምድር ላይ ባሉ ሰዎች መካከል ልዩነት እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል አንዱ የጊዜ አጠቃቀም ነዉ ማለት ይቻላል። የጊዜ አጠቃቀማችን ነዉ አትራፊም ፣ ብኩንም እንድንሆን የሚያደርገን። ገንዘብ ያለዉ ሰዉ ሌላ ገንዘብ ለመስራት ሲያስብ ለመስረቅ ሳይሆን የሚሄደዉ ያለዉን ገንዘብ ትርፋማ ሊያደርገኝ ይችላል ብሎ ባሰበዉ ነገር ላይ አዉጥቶ ትርፍ ለማግኘት ነዉ የሚሰራዉ። ለዚህም ደግሞ አትራፊ እንዲሆን ሊያደርገዉ የሚችለዉን ነገር ለይቶ ማወቁ ይቀድማል። ጊዜም በዚህ መሰረት ነዉ የሚሰራዉ። በመጀመሪያ ጊዜአችንን ምን ላይ ማዋል እንዳለብን ማወቅ ፤ ከዛም የትኩረት አቅጣጫዎችን በዛ መሰረት ማስቀመጥ ስኬታማ የሆነ የጊዜ አጠቃቀም መጀመሪያ ነዉ። ስኬታማ የሚባሉ ሰዎችን የጊዜ አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ ወስዶ ለራስ ማድረግ በተወሰነ መልኩ ይረዳ ይሆናል እንጂ ጥቅሙ ዕምብዛም ነዉ።

ጊዜዉን በአግባቡ መጠቀም የሚፈልግ ማንኛዉም ሰዉ ከየትኛዉም ነገር በላይ የህይወቱን የትኩረት አቅጣጫ/ዓላማ ለይቶ ማወቅ ዓለበት። ከዛ ፣ እያንዳንዱን ሰዓት (ሽርፍራፊ ሰከንዶች ሳይቀሩ) በጥበብ መጠቀም መጀመር አለበት። ጊዜን በጥበብ እንደሚጠቀሙ በእግዚአብሄር የተመሰከረላቸዉ ወታደሮች በመፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ተጠቅሰዉ እናያለን። እኚህ ወታደሮች በምሳሌ መፅሐፍ 30 ፤ 25 ላይ ይገኛሉ። ገብረ ጉንዳኖች ፤ ምን መቼ መስራት እንዳለባቸዉ ያዉቃሉ ፣ መስራት ያለባቸዉንም ነገር መስራት ባለባቸዉ ጊዜ ይሰሩ ነበር። ጊዜን መጠቀም መቻል ጥበብን የሚሻ ነገር ነዉ። ጥበብን ደግሞ እግዚአብሄር ነዉ የሚሰጠዉ። በምሳሌ 2 ፤ 6 ‹‹እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና ፤ ከአፉም እዉቀትና ማስተዋል ይወጣሉ›› ተብሎ እንደተፃፈ።


Article@Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

10 Nov, 06:01


ደም መለገስ ህይወትን ለማዳን ማንነታችንን ከመስጠት የበለጠ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ተግባር ምን ሊሆን ይችላል?

ደም በመለገስ፣ ጠቃሚ ሃብትን ማካፈል ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን የመስዋዕትነት መንፈስ እንለብሳለን ። ተስፋ ለሚያስፈልጋቸው የሕይወት መስመርን በማስቀጠል የክርስቶስ የፍቅሩ መርከቦች እንሆናለን።

አንዳንዶች እንዲህ ያለው ድርጊት ከእምነታቸው ጋር ይስማማል ወይ ብለው ይጠራጠሩ ይሆናል።

ነገር ግን "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" – 1ኛ ዮሐ 15:13 - የሚለውን የዮሐንስ መልእክት እናስታውስ።  ደም መለገስ ህይወታችንን በእጃችን ማሳለፍ አይደለም፣ ይልቁንስ ከራሳችን ትንሽ ክፍል በመስጠት በሚዛን ላይ የተንጠለጠለን ህይወት ወደ መኖር እንዲያዘነብል መርዳት ነው። ባልንጀራችንን እንደራሳችን የምንወድበት፣ የክርስቶስን ትምህርቶች ተግባራዊ የምናደርግበት ነው።
በተጨማሪም የደጉ ሳምራዊን ታሪክ ምሳሌነት ፍቅር ድንበር እንደሚሻገር እና ርህራሄያችን ለተቸገሩ ሁሉ እንዲደርስ ያስተምረናል።

ደም ልገሳ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ብሔር አያውቅም።  እሱ የሕይወትን ምንነት ይዞ የተገነባ ዓለም አቀፋዊ የሰው ልጅ የደግነት ድልድይ ነው።


AASTU_ECSF

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

09 Nov, 06:05


ደም እንደ መጽሃፍ ቅዱስ:

በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ፣ የደምን ቅድስና ማየት እንችላለን። የእግዚአብሔርን እስትንፋስ እንደሚሸከም ወንዝ በደም ሥር የሚፈስ የሕይወት ምንነት ነው።
“...የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና...”    በ ዘሌዋውያን 17:11
ይህ ጥቅስ በደም እና በፍጡር ማንነት መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት ያጎላል።

ከዚህም ባለፈ መጽሐፍ ቅዱስ ደም የሕይወት ምልክነትነቱን ብቻ ሳይሆን የመስዋዕትነት መልክትነቱንም ይናገራል።
ወደ እግዚአብሔር ከሚጮኸው ከአቤል ደም ጀምሮ ፣ እስከ ፋሲካው የመስዋዕት በግ፣  በመስቀል ላይ እስከ ቀረበው የመጨረሻው መስዋዕት ኢየሱስ ክርስቶስ ድረስ፣ ደም በእምነታችን ማሰሪያ ውስጥ ተሸምኖ ራስን ስለሌላው አሳልፎ የመስጠት ፅኑ ውክልና ሆኗል።


AASTU_ECSF

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

06 Nov, 18:00


AASTU-ECSF pinned «#Dorm_To_Dorm_Prayer ሰላም እንዴት ናችሁ የማክሰኞ ጠዋት Dorm to Dorm ፀሎት እንደተጀመረ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ጠዋት 12:00 ጀምሮ በየብሎኮቻችን ባሉ የሚፀለዩባቸው ዶርሞች እየሄድን እንድንፀልይ ይሁን። ከዚህም በተጨማሪ በዶርም 3 እና 4 ክርስቲያን ተማሪ ያለባቸው ዶርሞችን እንድታስመዘግቡ እና እንዲፀለይባቸው ይሁን። ለወንዶች ዶርም ለማስመዝገብ ጌታነህ - 0968756958…»

AASTU-ECSF

04 Nov, 19:40


#Dorm_To_Dorm_Prayer

ሰላም እንዴት ናችሁ የማክሰኞ ጠዋት Dorm to Dorm ፀሎት እንደተጀመረ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ጠዋት 12:00 ጀምሮ በየብሎኮቻችን ባሉ የሚፀለዩባቸው ዶርሞች እየሄድን እንድንፀልይ ይሁን። ከዚህም በተጨማሪ በዶርም 3 እና 4 ክርስቲያን ተማሪ ያለባቸው ዶርሞችን እንድታስመዘግቡ እና እንዲፀለይባቸው ይሁን።

ለወንዶች ዶርም ለማስመዝገብ
ጌታነህ - 0968756958
ዳግማዊ - 0974382519

ለሴቶች ዶርም ለማስመዝገብ
ዲቦራ - 0939608990

#Prayer_Team

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

On Telegram 👉 AASTU-ECSF
On YouTube 👉 AASTU ECSF

AASTU-ECSF

04 Nov, 05:34


ፍርሃት

ከሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ባህሪ አንዱ ፍርሃት ነው። ብዙ ሰዎች የሚፈሩት የተለያየ ነገር ሊሆን ይችላል ለምሳሌ ጨለማ ፤ ብዙ ሰው ፊት ቆመው ሀሳባቸውን መግለጽ ፤ ከሰው መግባባት .....በጥቂቱ ነው። ፍርሃት ተፈጥሯዊ ቢሆኑም ግን አንድአንድ ፍርሃቶች ምንጫቸው ከሴይጣን ነው ፍርሃት እግዚኣብሄር ያሰበልንን ህይወት እንዳንኖርና እግዚአብሔርን እንዳናምነው እንደሚችል ልናውቅ ይገባል።

ፍርሃታችን ዓይኖቻችንን ከጌታ ላይ አንስተን ነገሮች ላይ ስናደርግ እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል።

ጴጥሮስ አይኖቹን ከጌታ ላይ አንስቶ ነፋሱ ላይ ሲያደርግ መስጠም እንደጀመረ እንመለከታለን ።ጌታ እንድናምነው ይፈልጋል የምንራመድበት መሬት አንድ ቀን ሰምጦ ይውጥናል ብለን አስብን አናውቅም ምክንያቱም መሬቱን እናምነዋለን ጌታ በዚህ ልክ እንድናምነው ይፈልጋል።

ፍርሃት ማለት በሙሉ ልባችን ጌታ ላይ አለመደገፍ እና እርሱን አለመታመን ነው ጌታ ይህንን አይፈልግም ። እግዚአብሔር እንዲሰራብን ከፈለገን እርሱን ማመን ያስፈልጋል

ፍርሃታችንን እንዴት እናስወግድ?


“ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።”
1ኛ ዮሐ 4፥18

ፍፁም ፍቅር ኢየሱስ ነው ኢየሱስን ማወቅ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከፍርሃታችን ነፃ ያወጣናል እኛ የምናውቃቸው እና የምናምናቸው ጓደኞች ይኖሩናል ከእነሱ ጋር ስንሆን ሚስጥራችንን እንነግራቸዋለን ይህን እምነታችንን ያመጣነው ከእነርሱ ጋር ጊዜ ስላሳለፍን ነው ከጌታ ጋር ጊዜ ስናሳልፍ አይኖቻንን ከነገሮቻችንን ይልቅ እርሱ ላይ ይሆናሉ ስለዚህ አይኖቻችንን ከሁኔታዎች አንስተን ጌታ ላይ ማድረግ ያስፈልጋል።

“ኢየሱስ ግን ሰዎቹ የተናገሩትን ችላ በማለት የምኵራቡን አለቃ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፤” አለው።”
ማር 5፥36

እርሱ ከምንሰማው፤ ከምናየው ፤ ከሚሆነው ነገር በላይ እንደሚያደርግ እንድናምነው ይፈልጋል። ስለዚህ እርሱን ታምነን እንኑር።



Article@Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

31 Oct, 14:45


ሰላም በጌታ የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን እንዴት አላችሁ😊

➡️ ማታ በማስታወቂያ ለመናገር እንደሞከርነው I4U team contact bot አዘጋጅተናል ይሄም bot የትኛውንም አይነት ድጋፍ የምትሹ እህት ወንድሞቻችን እኛን የምታገኙበት bot ነው።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች በዝርዝር ቦቱ ላይ ያለ ስለሆነ start ሚለውን button በመንካት ዝርዝሩን እንዲሁም እኛን ማግኘት እንደምትችሉ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። በጣም በናፍቆት እንጠብቃቹሀለን ተባረኩ!🙌🏼

Link : @i4u_contact_bot

Gedion 0961099526
Yamrot  0940178048
Nathnael 0966000160
Samuel   0940829420
Bitaniya 0994265687

#I4U
#Caring_Hearts_Sharing_Hands

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

On Telegram 👉 AASTU-ECSF
On YouTube 👉 AASTU ECSF

AASTU-ECSF

28 Oct, 03:02


📌 ከማማከር አገልግሎት ዘርፍ (Counseling Team)

ከማማከር አገልግሎት ዘርፍ (Counseling team) አባላት ጋር በግል (ONE TO ONE) ምክክርን የምትፈልጉ ወይም በተለየዩ ጉዳዬች /ርዕሶች ማዉራት ፣ መወያየት ወይም በምክር.. የሚደግፉአችሁ ሰዉ ከፈለጋችሁ:

በተጨማሪም ከጓደኞቻችሁም እንዲህ አይነት አገልግሎት የሚፈልጉ ወይም የሚያስፈልጋቸው  ተማሪዎች ካሉ በዚህ ስልክ ይደዉሉ።

☎️  ሄማን(ለወንዶች) - 0901000052
       ሊድያ(ለሴቶች) - 0968201667

በተጨማሪም ማንነታቹ ሳይታወቅ የምክክር አገልግሎት ምትፈልጉ በanonymous counseling ቦትአችን ማግኘት ትችላለቹ።

@AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

28 Oct, 03:01


መጨነቅ

ሰዎች በመሆናችን ፤ ነገ ምን እንሆናለን?
ያሰብነው ነገር ባይሳካ ምን ይውጠን ይሆን?  እግዚአብሔር የተወን ሲመስለን፤ የምንወደውን ጓደኛ ብናጣ ምን እንሆናለን? ብሞትስ ወዴት እንሄድ ይሁን? ...... ብለን በብዙ እናስባለን። ብቻ ምን አለፋችሁ በብዙ ነገር እንጨነቃለን።

በአንድ ወቅት የአለማችን ሀብታም የነበረ አንድ ክርስቲያን ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር " ሁሉ ነገር ቢኖረኝም አለመጨነቅ አልቻልኩም። ኢየሱስ እንኳን አምላክ ሆኖ ምንም ማድረግ እየቻለ ከተጨነቀ እኔ እንዴት"  ይህን በማለት የጭንቀት ስሜት ተፈጥሯዊ መሆኑን ይነግረናል።

የጭንቀት ስሜት መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አለ።  ኢየሱስ እንደ እኛ ሰው ስለነበር ይህን ስሜት ተጋርቶታል ስለዚህ ጭንቀት በማንኛውም ክርስቲያን ውስጥ ሊከሰት የሚችል ነገር ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ እንዲህ ይለናል

“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።”
        ዮሐ 14፥1

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”     ፊል 4፥6


ኢየሱስ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሊሰማን ካለንበት ጭንቀት ሀዘን እና መከፋት ነፃ ሊያወጣን አጠገባችን ነው ። የሚስጨንቀንን ነገር በእርሱ ላይ መጣል እንዳለብን እና የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለእርሱ ማስታወቅ / መናገር እንዳለብን ይነገርናል ።

ይህንን የምታነቡ ወዳጆቼ በህይወታችሁ ደክሞችሁ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ገጥሟችሁ፤  እግዚአብሔር እንደሚፈልገው እየተመላለሳችሁ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ኢየሱስ ዛሬም ከሚያስጨንቃችሁ ነገር ነፃ ሊያወጣችሁ እና ሊያሳርፋችሁ እጆቹን ዘርግቶ ይጠብቅችኋል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ በመጨነቃችን አንዲት ስንዝር አንጨምርምና ሁሉን ለእርሱ እንተው።

“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”          1ኛ ጴጥ 5፥7


Article@Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

AASTU-ECSF

25 Oct, 09:25


#2nd Years Small Group Formation Retreat

ውድ የAASTU ECSF የ2ተኛ ዓመት ቤተሰቦቻችን በያላችሁበት ሰላም ለእናንተ ይሁን🤗።  

እንደሚታወቀው #ዛሬ ዕለተ አርብ እንደ Batch በጉጉት የምንጠብቀው የSmall Group Formation Retreat ይጀምራል።

ጌታ ረድቷችሁ ሁላችሁም ዲፓርትመንት ተመድባችኋል፤ ስለዚህም በየዲፓርትመንታችሁ በየክፍሎቻችሁ የSmall Group ፋሚሊይ ይኖራችኃል ማለት ነው።

በዚህም Retreat ትምህርት የምንማርበት፣ ስለ Small Group ምንነት እና ጠቀሜታ የምናውቅበት፣ ጌታን በዝማሬ የምናመልክበት እንዲሁም በዲፓርትመንታችን ጌሞችን የምንጫወትበት ጊዜ ይኖረናል።
ስለዚህም፡ - መጽሐፍ ቅዱስ፣
               ማስታወሻ ደብተር፣ እስኪርቢቶ
            - አንሶላ፣ ብርድልብስ እና
            - መውጫ ካርድ ከፕሮክተሮች
                በማፃፍና በመያዝ፣ እራታችንን በጊዜ በመመገብ እና ከጓደኞቻችን ጋር በመደዋወል ልክ 12:00 ሲል #በቂሊንጦ በር እንገናኝ።
ማሳሰቢያ፡- ማርፈድም ሆነ መቅረት አይፈቀድም!!

#እንወዳችዋለን_ተባረኩ

#AASTU_ECSF_COORDINATORS

AASTU-ECSF

21 Oct, 19:16


#Small_Group_Prayer_Week

ሰላም እንደምን አመሻችሁ ከነገ ጀምሮ የSmall Group ፀሎት ስለሚጀምር ከጠዋቱ 12:00 ላይ እየተደዋወልን እና እየተጠራራን መጥተን እንድንፀልይ ይሁን።

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

On Telegram 👉 AASTU-ECSF
On YouTube 👉 AASTU ECSF

AASTU-ECSF

21 Oct, 18:51


https://t.me/+wGbMBnYdUrUzZmFk
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በጌታ የተወደዳችሁ የመጀመሪያ አመት ወንድም እህቶቻችን ፤ ይህ ለእናንተ የከፈትነው የBatch Family Group ነው።

AASTU-ECSF

21 Oct, 02:59


የፀሀፊው እውነት

የደሙ ዋጋ
በየ ዕለቱ ይፈስለት ከነበረው ደም የተነሳ የአለምን ህዝብ ሁሉ ለወዲያኛው እንዳይኖር እየማረካቸው ሲሰዋቸው ኖሯል።
እርሱ ካለው አቅም እኛ ደግሞ ካለን ድካም ይህ እጣ ተፈረደብን ተማረክንም።

ለጨለማው አለም ገዢ የእርድ መስዋዕት እንድንሆን ሁላችንንም ራቁታችንን አድርገው በረጃጅም እንጨት በሰንሰለት አንገታችንን አስረው የምርኮኝነታችንን ምልክት ቀለምን ቀብተውን እንደ በግ ለመስዋዕትነት ወደ ሚሰዉበት ይጎትቱን ጀመር።

ይበልጥ ወደ ስፍራው በቀረብን ጊዜ በግራና በቀኝ የተሳሉ የግድግዳ ምስሎች ስለ ምንሄድበት እና ከፊታችን ስላለው የእርድ መስዋዕት በስዕል ይገልፃል።

አሁን አረጋገጥኩ ምንም ተስፋ እንደሌለኝ ወደ እዛ ቅጥር የገባ እንኳን አይደለም መትረፍ ሳይሰዋ እንደማይቀር አረጋገጡልኝ። ብወራጭ ብታገል መሞቴ ግልፅ ነው። ተራዬም እየደረሰ ነበርና ልቤ በውስጤ እየሞተ መጣ። በቃ ምድር እንኳ ብትናወጥ ሚለወጥ ነገር እንደሌለ ስላወቅሁ ማን ያድነኝ ይሁን?? የሚለው ጥያቄ ከአዕምሮዬ ጠፋ።

በጣም እየቀረብኩ ስመጣ አጥፊውን አየሁና ፤ "ምነው ልቡ በራራልኝ" እልና "ውይ ለእኔ ብቻ እንዴት? እንዲያው በጎና ጥሩ ሰው አይደለሁ፤ ብሆንም እንኳን መች አውቆኝ? "እልና "ሞቴስ አይቀር" እላለሁ።

ወንድሞቼና እህቶቼ በዚህ ስፍራ ሆኜ እውነት ሚያተርፈኝ እንዳለ ተስፋ ማድረግ እችል ነበርን?

ዛሬ በህይወት አለሁ አልሞትኩም ፤ ምን መጥቶ እንዴት ያስብላል። ይህ እውነት ነው ፊልም ወይም ልብ ወለድ አይደለም፤ ብቻ አመለጥኩ ከሞት አፋፍ ፤ ከእስራቴ፣ ከምርኮኝነቴ ተፈታሁ።

አስቡት እስቲ በዚያ በመሰዊያው ስፍራ ተራዬ ሆኖ ስሜ ተጠርቶ" አምጡትና እረዱት" በሚባልበት ስፍራ " አንተ ነፃ ነህ ተፈትተሀል፤"_ " እርሱን ተውት" ስትባሉ ምን እንደሚሰማቹ?

ይህ ሁሉ ግን በምክንያት ሆነ። ተፈታሁ ፣ ነፃ ሆንኩ ብዬ በደስታ ዘለልኩ። ምክንያቱን ለማወቅ ወዲያ ወዲህ ብዬ ስመለከት አሁንም ደም ይፈስ ጀመር ፤ "እንዴ አልቆመም?" ስል ለካ በእኔ ተራ ለእኔ የተሰዋልኝ ሰው ደም ነበር። እኔን ንፁህና የምጠቅም አድርጎ ቆጥሮኝ እርሱ ለእኔ ራሱን ሰጠ።

እርሱም ኢየሱስ ይባላል በሞቱ ህይወትን በመስዋዕትነቱ ነፃነትን ያወጀልኝ። እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ ለማይገባኝ ለእኔ ህይወትን፤ ሞት የተፈረደብኝን እኔን ለዘላለም እንድኖር ፍፁም ነፃ አደረገኝ።
ዛሬ ባሪያ አይደለሁም፤ ዛሬ ምርኮኛ አይደለሁም በተከፈለልኝ የንፁህ ሰው ደም ደግሞም በጣም ትልቅ ዋጋ በህይወት አለሁኝ።

ወንድሞቼና እህቶቼ እንደዚሁ እንድንድን ክርስቶስ የከፈለልን ዋጋ በአጭሩ የሚገለፅ አይደለም ።

ነገር ግን ሁላችንንም በሀጢአታችን ምክንያት ወደ ሞት ሰይጣን ሲመራን እርሱ እንዴት በደሙ እንዳዳነን እናስብ ፤ እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ ማንም ማዳን የማይቻለውን፣ ማንም ሊፈታ የማይቻለውን እስራት እንደፈታልን፤ ይህም እንዲሁ ብቻ አይደለም በስቃዩበስቅላቱና በሞቱ እንደሆነና በጣም ትልቅ የደም ዋጋ እንደከፈለልን እናስተውል።

ይህም ከወደደን ከታላቅ ፍቅር እንደሆነ በተግባር አረጋግጦአል።

ለመኖራችን ደም ተከፍሎበታል።

Article@Counseling

Contact us: @AASTU_Anony_Counseling_bot

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

AASTU-ECSF

19 Oct, 14:09


#Small_Group_Prayer_Week

ሰላም እንደምን ናችሁ በህብረት በጌታ ፊት የምንሆንበት ሳምንት ደረሰ። በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም ማክሰኞ ፣ እሮብና ሐሙስ የንዑስ ቡድን (Small Group) ወርሃዊ የፀሎት ጊዜ ስለሚኖረን በማለዳ እርስ በእርስ እየተጠራራን አብረን በመምጣት እንድንፀልይ ይሁን።

📌 የአንደኛ አመት ተማሪ የሆናችሁ በሙሉ በፈለጋችሁባቸው ቀናት ሁሉ መጥታችሁ አብራችሁን መፀለይ እንደምትችሉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

📍ቂሊንጦ መካነ ኢየሱስ
🕛 12:00 ጠዋት

#FOLLOWING_THE_KING
#Know #Obey #Rest

On YouTube 👉 AASTU ECSF
On Telegram 👉 AASTU-ECSF

AASTU-ECSF

09 Oct, 10:39


የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኃላ እንደገና ልንገናኝ ነው። የእረፍት ቆይታችሁ መልካም እንደነበር ተስፋ እናደርጋለን።

ዛሬ ልዩ የ'welcome' ፕሮግራም ይኖረናል

በሚኖረንም የህብረት ጊዜ :
📌 አመታችንን በምስጋና እንጀምራለን
📌 የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን

#ተባረኩ

#FAITHFUL_SERVANTS_OF_THE_KINGDOM
#KINGDOM
AASTU ECSF