ሰዋሰዉ @sewasewsemay Channel on Telegram

ሰዋሰዉ

@sewasewsemay


ይህ ሰዋሰዉ የተስኘዉ ቻናል ሰለ ሀገራችን የበፊት ድርሰቶ ች: ግጥሞች: ወግ: ባህል:ስርዓት:አኖኖር:ክስተቶች የሚያትት: ምን ተብሎ ነበር ብሎ ሚተይቅ: ምንስ ሆነ ብሎ ሚመርም: ወደፊትስ ምን የሆናል የሚለውን የሚያወራ ቻናል ነዉ::
ለተጨማሪ መረጃ @ሰዋሰውሰማይ ያነጋግሩን::

ሰዋሰዉ (Amharic)

ሰዋሰዉ የተስኘዉ ቻናል ሰለ ሀገራችን የበፊት ድርሰቶ ችቶ ማተሚያዎችን ያነጋግሩን እና ምስክሮችን እንዲያትትሩ የቀረበ የቻናል ነው። ወግን፣ ባህልን፣ ስርዓትን፣ አኖኖርን፣ ክስተትን፣ ወደፊትም ሆነ ሚተይቅን፣ ሚመርምን የሚለውን ምንድን ነው የሚያወራዉን መረጃን ይከታተላል። ለተጨማሪ መረጃ ከተናጋሩ @ሰዋሰውሰማይ ያነጋግሩን።

ሰዋሰዉ

22 Jul, 02:52


https://vm.tiktok.com/ZMrumTrWE/

ሰዋሰዉ

20 Jul, 04:23


Dr Alemayehu Wassie ስለ ምንኩሰና ምንነት አና ትርጉም በ ደጃፍ poadcast ያቀረቡት ሃሳብ::

@ደጃፍ ፖድካስት/ dejaf podcast #ethiopia #ethioart
Link: https://vm.tiktok.com/ZMrm4ud2J/

ሰዋሰዉ

28 Nov, 06:12


Title: መግባት እና መውጣት 🖊: በውቀቱ ስዩም 🔊: በአንዷለም ተስፋዬ 💾: 44.8MB : 18:40Min Sheger Shelf

ሰዋሰዉ

14 Jul, 12:13


Title: “የጠላት ትንሽ የለውም” 🖊: ከስብሃት ገብረእግዚአብሔር 🔊: ግሩም ተበጀ 💾: 6.8MB : 12:34Min suggestedBy:Abusha Shukuru Sheger Shelf

ሰዋሰዉ

14 Jul, 12:13


Title: የዛሬው ቀን “ጨለማው ሐምሌ ሰባት” 📚: ታሪክን የኋሊት 🔊: በእሸቴ አሰፋ 💾: 6.8MB : 2:49Min Sheger Shelf

ሰዋሰዉ

02 Jul, 15:27


Title: የአፄ ቴዎድሮስ ፍርዶች : 5:17Min 💾: 12.7MB 🖊: በኪዳኔ መካሻ 📚: ከወይ አዲስ አበባ መጽሔት 🔊: በግሩም ተበጀ Sheger Shelf

ሰዋሰዉ

26 Jun, 15:29


Title: የካድሬው የፍቅር ደብዳቤ : 6:46Min 💾: 16.3MB 🖊: አቤ ቶኪቻው Sheger Shelf suggested by: @Abusha5 Abusha Shukuru

ሰዋሰዉ

25 Jun, 14:54


ሌተና ኮሎኔል ጃጋማ ኬሎ በማዕረግ ልብሳቸው::

በዚሁ አንድ ጊዜ ሳነብ ያገኘሁትን ቅኔ ልጋብዛችሁ ነው:: በአንኮበር አንድ ኢትዮጵያዊ በኦሮሚኛ ወልደ ጻዲቅ ለተባለ የእርስ ቤት አዛዥ የተቀኘው ቅኔ ነው::

ናገርሰሲ ከራ ሐዘሎ:
ዒጃ ሚኒሊክ ወልደ ጻዲቅ
አኒ ቤኪ ኢንጂሩ ጎፍታኮ:
ከራ ሐዘሎ ሁንዱማ
ዱቢን ኬቲ ዳዲ: አፋን ኬቲ ደማ
ሌንጫ ጎፍታኮ: አርካ ምኒሊክ ይልማ
ኦሮሞ አቡልቱ ምስለ ሲዳማ:
ዒጃ ጎፍታ ኬኛ ኩኖቲ : ቢፍቱ ዲረማ
አዕየንተ ይሰብር በግርማ::

የኦሮምኛ ቋንቋ የምትችሉ ትርጉሙን አስተያየት መስጫው ላይ ሞክሩ::
-------- ------- -------
ምንጭ:- ''አራዳ'': ፊታውራሪ ገ/ሕይወት ወ/ሐዋርያት

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

24 Jun, 09:25


ልጅ ጃጋማ ኬሎ ከወንድማቸው ከልጅ ጠንቄሳ ኬሎ ጋር በአርበኝነት ዘመን::

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

23 Jun, 06:23


ሀይልን መልሶ በእጅ ለማድረግ ትዕግስት እንደሚጠይቅ የተረዱት ንጉሰነገስቱ ሀገራቸውን ከወራሪው ፋሽስት ኢጣልያ ነፃ ለማድረግ ፖለቲካዊ ግንኙነቶችንና የምዕራባውያን ወዳጆቻቸውን የጦር ድጋፍ አቀናጅተው ተጠቅመዋል። በርግጥ የኢትዮጵያ ነፃነት በአምስቱ የጦርነት አመታት እንግሊዝ ምንም አይነት ድጋፍ ባለማድረጓ የመከዳት ስሜት ተሰምቷቸው ንጉሰነገስቱ ወደ ሀገራቸው በመዲናዋ በተደረገው የአቀባበል ስነ ስርዐት ለመገኘት አሻፈረኝ እንዳሉት ጃጋማ ኬሎና መሰሎቻቸው ትግል እውን አይሆንም ነበር። በወቅቱ ከነበሩት የኢትዮጵያ የሚዲያ ዘገባዎች መረዳት እንደሚቻለው ንጉሰነገስቱ ሸዋ ውስጥ ወደምትገኘው የጃጋማ መኖሪያ ጊምጪ ከተማ ጉዞ አድረገው የነበረ ሲሆን ጃጋማም ወደ 3,500 የሚደርሱትን ወታደሮቻቸውን አሰልፈው ተቀብለዋቸዋል። ከመሞታቸው ጥቂት ግዜያት በፊት ተደርጎላቸው በነበረ ቃለመጠይቅ ጃጋማ ከሰልፉ በኋላ ንጉሰነገስቱ ጃጋማን በራሳቸው መኪና ወደ ቤተ መንግስታቸው የወሰዷቸው ሲሆን በዚያም ገበርዲን ኮት እና የወርቅ የእጅ ሰዐት እንደሸለሟቸው ጠቅሰዋል። ጅማ ከተማ በኢጣልያ ቁጥጥር ስር የነበረች በመሆኗ የነፃነት ትግሉ ሙሉ ለሙሉ አልተደመደመም ነበር። በመሆኑም እርዳታቸውን በንጉሰነገስቱ የተጠየቁት አርበኛው ጃጋማ ወታደሮቻቸውን ወደ ጦርነቱ በማሳተፍ 500 የኢጣልያ ወታደሮችን ማርከው ለእንግሊዝ ጦር አስረክበዋል።

ያለ ሸጉጥ ትግሉን የጀመረው ወጣቱ አርበኛ ከጦርነቱ መጠናቀቅ በኋላ በብሔራዊው ጦር ሰራዊት ውስጥ በመቆየት እስከ ሌተናንት ጀነራል የማዕረግ ደረጃ አድጓል። በ1950ዎቹ መግቢያ ላይም በባሌ የተነሳውን አመፅ በመቆጣጠሩ የአውራጃ ጦር አዛዥነትን ማዕረግ ተሸልሞ ከፍተኛ ሹመት ሊያገኝ ቾሏል። ጃጋማ በነበረው አፍሮ ፀጉር የተነሳ ጠላቶቹ ይፈሩት እንደነበርና ለስኬቱም አንድ አስተዋፅዖ እንደነበረው ያምናል። ለዚህም ነው በአንድ ወቅት በከፋ የወባ በሽታ ተጠቅቶ ሊያክመው በነበረው እንግሊዛዊ ዶክተር አፍሮ ፀጉሩን መቆረጥ እንዳለበት ሲጠየቅ አልቆረጥም በማለት የመለሰው።

በወቅቱም በአዲስ አበባ የነበረው ሆስፒታል ጃጋማ ፀጉሩን እስካልተቆረጠ እንደማያክመው ቢገልፅም ጃጋማም ከኢጣልያ ወታደሮች ጋር በዱር በገደሉ በነበረው ውጊያ የጠላት ወታደሮችን በፍርሃት እንዲርዱ ያደረገልኝን ፀጉሬን አልቆረጠውም በማለት በእምቢተኝነቱ ፀንቷል። በመጨረሻም ንጉሰነገስቱ በጉዳዩ ገብተው ባቀረቡት ተማፅኖ ጃጋማ ተሸንፎ ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል። በአፄ ኃይለሥላሴና በጃጋማ መካከል የነበረው ግንኙነት እንዲህ የጠለቀ ነበርና ንጉሰነገስቱ በታህሳስ 1953 ብራዚል በሄዱበት ወቅት በተቃዋሚዎቻቸው በተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ካልተሳተፉት የጦር አመራሮች አንዱ ጃጋማ ኬሎ ነበሩ። የመፈንቅለ መንግሰቱ ሙከራ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ካወረዳቸው የ1966ቱ አብዮት በቀር በዘመናቸው ካጋጠሟቸው አደጋዎች ሁሉ የከፋው ነበር።

ጃጋማ ኬሎ በ96 አመታቸው መጋቢት 29/2009 በአዲሲ አበባ የሚገኝ ሆስፒታል ሞቱ በህይወት የነበሩት የመጨረሻው የአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የጦር ጀነራል ነበሩ። ከሄሊኮፕተር አደጋ ለተረፈ እና በጦርነቶች ብዙ ጉዳቶችን ላስተናገደ ሰው፤ ጃጋማ ኬሎ የደርግ መንግሥት በ1983 በወደቀ ማግስት የኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ በመሆን በሽምግልና ዕድሜያቸው እንኳን ንቁ እና ለኢትዮጵያ ሀገራቸው ታታሪ ሰው እንደነበሩ አስመስክረዋል። ጃጋማ ኬሎ የካርታ ጨዋታ አጥብቀው ይወዱ እንደነበርና እስከለተሞታቸውም ድረስ ይጫወቱ እንደነበር የተለያዩ የኢትዮጵያ ሚድያ ዘገባዎች ያስረዳሉ።

ምንጭ፡ www.face2faceafrica.com
ብሩክ አያሌው

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

22 Jun, 09:29


በ15 አመቱ ሀገሩን ከወራሪ ፋሽስት ኢጣልያ ጦር ነፃ ያወጣው ባለ አፍሮ ፀጉሩ ወጣት አርበኛ: ጃጋማ ኬሎ

ጃጋማ ኬሎ ሀገሩ ኢትዮጵያን ከ1928ቱ የኢጣሊያ ወረራ ለመከላከል ወደ ጫካ በመግባት መዋጋት ሲጀምር ዕድሜው ገና 15 ብቻ ነበር። በመስከረም 1928 ኢጣልያዊው ፋሽስት የጦር መሪ ቤኔቶ ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ ወረራ ጀመረ። በንጉሰነገስት ኃይለሥላሴ ጦር ዙርያውን ተከቦም ቢሆን የኋላ ኋላ ሙሶሎኒ ሚያዚያ 27/1928 አዲስ አበባ ገብቶ ኢትዮጵያ የኢጣሊያ እና የኢጣልያ የምስራቅ አፍሪካ ግዛት አካል ሆናለች በማለት አወጀ። ንጉሰነገስቱም የኢጣልያ ወረራ ተከትሎ ወደ ፈረንሳይ ሱማሌላንድ አቀኑ።

የባለፀጋ ባላባት ልጅ የነበረው ጃጋማ የኢጣልያ ጦር በወረራው እየገፋ ሲመጣ ከገበሬ አስከ ታዋቂ ሰዎች በመሰባሰብ እንደ ህዝብ ወራሪውን ጦር ለመመከት ጫካ ገብተው የተደራጁትን አርበኞች የጦር መሳሪያ በመያዝ ከወንድሙ ጋር በመሆን ቤታቸውን ጥለው ተቀላቀሉ። በወቅቱ የጃጋማ ወንድም ሽጉጥ የነበረው ሲሆን ጃጋማ ግን ምንም መሳሪያ አልነበረውም። ያም ሆኖ ተደብቀው የኢጣልያ ወታደሮች ላይ አደጋ በመጣል በፍጥነት ራሳቸውን ማስታጠቅ ጀመሩ። ሌሎችም በሂደት ትግሉን የተቀላቀሉ ሲሆን በጦርነቱ መጨረሻ ጃጋማና ታላቅ ወንድሙ ከ3,000 በላይ በስራቸው የሚታዘዙ የአርበኞች ጦር ነበራቸው።

በአንድ ወቅት በተደረገ ቃለ መጠይቅ ጃጋማ ካደረጓቸው ጦርነቶች ሁሉ ከአዲስ አበባ 55ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው በስዩመ ማርያም ላይ ያደረጉት እንደነበር ያስታውሳሉ። በጦርነቱ አንዲት ሴት አርበኛ ለጃጋማና ለአርበኞቹ የኢጣልያ ወታደሮች የት እንደሚገኙ በነገረቻቸው መሰረት በኢጣልያ ጦር ላይ የድንገት ጥቃት በመሰንዘር 72 የኢጣልያ ወታደሮችን ገድለው 3,000 ጠብመንጃዎችን መማረክ ችለው ነበር። ንጉሰነገስት ኃይለሥላሴ ከአምስት አመት የብሪታንያ የግዞት ቆይታቸው በኋላ በ27/08/1933 ወደ ሀገራቸው መዲና አዲስ አበባ ተመለሱ::

ይቀጥላል

ሰዋሰዉ

13 Jun, 15:39


ብላቴን ጌታ ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል የጸሐፌትዕዛዝ ወልደመስቀል ታሪኩ ልጅ ናቸው:: ብላቴን ጌታ እንቅልፍ ለምኔ የተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል:-

''እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችን ጥንታዊት መሆኗን ሥልጣኔም በመሻት ዐዋቆችና አስተዋዮች አባቶቻችን በብዙ የደከሙ መሆናቸውን በመገንዘብ ላገራችን ወጣቶችም ሆነ ወይም ለውጭ አገር ሰዎች እውነተኛውንና ምስክርም ሊሆን የሚገባውን ሁሉ እየሰበሰብን ማዘጋጀት፤ ለመጭውም ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ አለብን::''

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

13 Jun, 15:39


ብላቴን ጌታ ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል እኚህ ነበሩ:: ብላቴን ጌታ ከሚታወቁበት ነገር አንዱ ሰውን መርዳት የሚወዱ: ልጆችን ሰብስበው ማሳደግ ማስተማር የሚወዱና እጅግ በጣም ደግ ሰው ነበሩ ይላሉ የቅርብ ወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው::

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

06 Jun, 14:44


ብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአገራችን ኢትዮጵያ ያሉትን ባህል በመሰብሰብ: በማጥናት: በመመርመርና በመጻፍ ትልቅ እውቅና አላቸው:: የኢትዮጵያ እርሻ ኮሌጅን (አምቦ እርሻ ኮሌጅ) እንዲከፈት በማድረግና እርሻ ሚኒስትር በመሆን በጣም ሰፊ ስራ ሰርተዋል:: 'ዝክረ ነገር' : 'ያባቶች ቅርስ': 'እንቅልፍ ለምኔ': 'የአማርኛ ቅኔ': 'ባለን እንወቅበት': 'ያገር ባህል(ቡልጋ)': 'ቼ በለው': 'ጥበበ ገራህት' :'ብዕለ ገራህት': 'ስም ከመቃብር በላይ' ና : 'ሰዋሰወ ሰማይ' ከፃፏቸው መጽሐፍቶች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው::

ብላቴን ጌታ የአማርኛ ቅኔ የተሰኘውን መጽሐፍ እንደገና ከነመፍቻው ጽፈውልናል:: እርሳቸውም እንዲሁ የህዝብና ታሪካዊ ቅኔዎችን ከመሰብሰብ በላይ እጅግ ባለቅኔና የስነ-ጽሑፍ ሰው ነበሩ:: ይህ ክፍል ብላቴን ጌታ ካሰባሰቡት ቅኔ እንዲሁም የታዋቂ ሰዎችና ራሳቸውም ከተቀኙት ቅኔ የምናይበት ክፍል ነው::

ከብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ቅኔዎች ለምሳሌ ያህል:- - እስከዛሬ:ድረስ: ዶፋ: ነበረች:
ኧረ: ለምን: አሁን: ጠብ: አዝላ: መጣች::
ሰሙ- እስከዛሬ ጭቅጭቅ በመጥላት ራቅ ብላ ዶፋ ቀበሌ ትኖር ነበር : ዛሬ ለምን ይሆን ጠባዝላ(የቦታ ስም) የመጣችው
ወርቁ:- ሽማግሌዎች ለማስማማት ቢደክሙ እምቢ አለች: በሆዷ ቂም ያዘች

- እንዲያ: ስናፍቅሽ: በጣም: ስወደሽ:
ምስጢሩ: ምን: ይሆን: ሳላይሽ: ቀረሽ::
ሰሙ:- እህቴ ሳላይሽ ዘመዴ እያልኩ ስጨነቅ
ወርቅ:- ዐፄ ምኒልክ በአቀማመጥሽ ተገርመው ያውቁሽ በመኖራቸው ተጸጽተው '' ሳላይሽ'' ያሉሽ የማትደፈሪ የኮረማሽ አምባ ለምን ይሆን እንዲህ ወድቀሽ የቀረሺው? በጊዜሽ የመሳሪያ ማከማቻ ማኖሪያ ሆነሽ አልነበረምን?

የአማርኛ ቅኔ በዋነኝነት በሶሰት መንገድ ይገጠማል::
1.ቃላቶችን በማጥበቅና በማላላት:-
አገውን: በቁርበት: ጎዣምን: በከብት:
በመላ: ፈጃቸው: አንድ: ሰው: ሳይሞት::
(ወርቁ:- በመላ ወይም በዘዴ)
2.አንዱን ቃል ከሌላው ጋር በማያያዝ ፍቺ የሚሰጥ
አዳራሹ: ሰፊ: በሩ: አልጠበባችሁ:
በተራ: በተራ: ምነው: መግባታችሁ::
(ወርቅ:- በተራበ ተራ)
3.በላንቃ ልዩ አነባበብና ድምፅ ሁለት ፍቺ የሚሰጥ
በታንኳ: በመርከብ: ሲገቡ: ብታይ:
እረ: አባይን: በግር: ትገባለህ: ወይ::
4.በቃላቶቹ ሁለት አይነት ትርጉም(አገባብ) የሚፈቱ
በሬዬ: ጠፍቶብኝ: ስፈልግ: ስባጅ:
እውነት: ከጠፋማ: አምላክ: ይፍረድ: እንጅ::
(ወርቅ:- እውነት(የሐሰት ተቃዋሚ) ከጠፋ)
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በቦታ ስም: በሰው ስም: ታሪክን የተመለከቱ: ቅኔዎችም አሉ:: ካልታወቁ በስተቀር ለመፍታት ያስቸግራሉ:: ለምሳሌ:-

**በቦታ:-
እሱ: ምን: ቸገረው: ሰው: ሁሉ: ቡጉላላ:
መርጦ: ከተማውን: ከያዘ: በኃላ::
(ወርቁ:- መርጦ የተባለውን ከተማ)
**በስም:-
የቀረበው: ጮማ: ምንም: ጣሙ: ቢጥም:
ያገራችን: ጀግና: ያላዋዜ: አይቆርጥም::
(ወርቁ:- አልዋዜ የተባለውን የጠላት ጦር መሪ)
**በታሪክ:-
ዐፄ: ቴዎድሮስ: እጅግ: ተዋረዱ:
የሸዋን: መኳንንት: እጅ: ነስተውት: ሄዱ::
(ወርቁ:- እጁን ቆርጠውት ሄዱ) ይህም ዐፄ ቴዎድሮስና አቤቶ ሰይፉ ተዋግተው: ዐፄ ቴዎድሮስ ድል ካደረጉ በኃላ ምርኮኛውን እጅና እግሩን ስላስቆረጡት ባሏ የሞተባት የሸዋ ሴት ያለቀሰችው ቅኔ ነው::

ከዚህም ባሻገር የፍቅር: የልቅሶ: ዘለሰኛ ቅኔዎችም አሉ:: ማህበረሰቡ በስልጣኔውና በአስተሳሰቡ ከፍ ያለ መሆኑንም ያሳያል:: ኢትዮጵያ በስልጣኔዎቿ እጅግ የተለየችና ውብ መሆኗን የስነጽሁፍና ኪነጥበብ ቅርሶች ዋነኛ ከሚባሉት ምሳሌዎች ናቸው:: ይህ ደግሞ በራሷ ቋንቋና ፊደል በመሆኑ የተለየና ግዙፍ ያደርገዋል:: በኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች አሉ:: ሁሉም የራሳቸው ውበትና ቅርጽ ያላቸው ናቸው:: በሌላ ጊዜ ይህንን ርዕስ በሌሎች ቋንቋዎች እንመለስበታለን:: በዚህ ክፍል የህዝብ ግጥሞችን እና ቅኔዎችን ለአብነት ያህል አይተናል:: እንዲሁም ሶስት አንጋፋና ኩሩ ኢትዮጵያውያንን ምሳሌ አደርገን ስራዎቻቸውን ለማየት ሞክረናል::

ቸር ያቆየን!

ሰዋሰዉ

01 Jun, 18:55


ነጋድራስ ተስማ እሸቴ ቀይስርን በኢትዮጵያ ያስገቡት ሳይሆኑ እንደማይቀሩ እገምታለሁ:: ይህ የምትመለከቱት ደብረዘይት ካስተከሉት ቀይስሮች 5 ኪሎ ከ 300 ግራም የሚመዝነውን ቀይስር ንጉሱ አይተው ፎቶ እንዲነሱ አድርገው የተነሱት ፎቶግራፍ ነው::

@RWESTIFANOS

ሰዋሰዉ

30 May, 11:34


የታዋቂው ስፖርተኛ: ኳስ ተጫዋች በኃላም የኢትዮጵያ ስፖርት ማህበር መስራች: የአፍሪካ ዋንጫን መስራች ከነበሩት አነዱ የነበሩት የይድነቃቸው አባት ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እኚህ ነበሩ::

@RWESTIFANOS