DeepThingsOfGod @thedeepthingsofgod Channel on Telegram

DeepThingsOfGod

@thedeepthingsofgod


Glorious Church the bride of Christ.
Rapture ready!

DeepThingsOfGod (English)

Are you searching for a place where you can deepen your understanding of God and His teachings? Look no further! Welcome to 'DeepThingsOfGod', a Telegram channel dedicated to sharing the profound mysteries and wonders of the divine. Our username, @thedeepthingsofgod, reflects our mission to explore the depths of God's word and unravel the mysteries of faith. Who are we? We are a community of believers who are passionate about diving into the deep things of God. Our channel is a place where you can find insightful discussions, inspiring messages, and reflections on the scriptures. Whether you are a seasoned Christian or a new believer, there is something here for everyone who seeks a deeper connection with God. What is 'DeepThingsOfGod'? It is a space where we come together to study the Bible, share our thoughts and experiences, and grow in our faith. Our goal is to provide a platform for believers to explore the profound truths of the Word of God and deepen their relationship with Him. From discussions on prophecy to reflections on the nature of God's love, there is always something thought-provoking and inspiring to discover in our channel. The title 'DeepThingsOfGod' encapsulates the essence of what we are all about - delving into the depths of God's wisdom and uncovering the hidden treasures of His word. We believe that the more we seek Him, the more we will find, and our channel is a place where you can embark on this journey of discovery and revelation. So, if you are rapture ready and eager to explore the wonders of God's mysteries, join us on 'DeepThingsOfGod' today. Together, let us uncover the deep things of God and grow in the knowledge and grace of our Lord and Savior, Jesus Christ.

DeepThingsOfGod

26 Dec, 05:42


The wait is over and the surprise is here!

እግዚአብሔር ይመስገን።

🎊🎉🎈አመሰግናለሁ 🎊🎉🎈

DeepThingsOfGod

21 Dec, 10:31


The highest science, the loftiest speculation, the mightiest philosophy, which can ever engage the attention of a child of God, is THE NAME, THE NATURE, THE PERSON, THE WORK, THE DOINGS, and THE EXISTENCE OF THE GREAT GOD whom he calls his Father.

ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ልጆች ትኩረት የሚገዛው እጅግ የላቀ ሳይንስ፣ ከፍ ያለ መላምት፣ የገዘፈ ፍልስፍና፥ አባታችን ብለው የምጠሩት የታላቁ አምላክ ስም፣ በሕሪይ፣ ማንነት፣ ስራ፣ አደራራግ እና ሕልውና ነው።

-C. H. Spurgeon

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

11 Dec, 04:12


ስለ እግዚአብሔር ከማወቅ...እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ
ይብዛም ይነስም ብዙዎቻችን ስለ እግዚአብሔር እናውቃለን።

እንደውም አንዳንዶቻችን ስልታዊ ነገረ መለኮትን ያጠናን እና ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ የሆነ ቲዮሎጂካል እውቀት ያከማችንም እንሆን ይሆናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን እናውቀው ይሆን?

ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ "በጆሮዎቻችን የሰማነውን፣ በአይኖቻችንም ያየነውን፣ የተመለከትነውን፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራላችሁለን" እንዳለ፥ እግዚአብሔርን ማወቃችን በዚሂ ደረጃ የጠለቀ ይሆን? ድምጹን ሰምተነው ይሆን? መልኩን (በሕሪዪን) በመጽሐፍ ከማንበብ ያለፈ አይተነው ይሆን? በልብ ዓይኖቻችን ተመልክተነው ይሆን? በእጆቻችንስ ደሰነው ይሆን?
እኔ እራሴን እጠይቃለሁ፥ ሁልጊዜም እፈልጋለሁ።
በተለያየ መንገድ ስለ እግዚአብሔር ያከማቸነውን እውቀት እንዴት ነው ወደ እግዚአብሔር እውቀት ይምንለውጠው? እንዴትስ ነው የራሳችን (Personal) የምናደርገው?
ትልቁ መልስ ማሰላሰል (Meditation) ነው። ያነበብነውን ወይም የሰማነውን ቃል "በልባችን መሸሸግ" ማሰላሰል ቤተ-ክርስትያን በዚህ ዘመን የተሰረቀችው ሃብት ነው።

መጽሐፈ ምሳሌ 2:1 ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥........... 2:5 የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

07 Dec, 04:30


ምህረት የገነነለት
እግዚአብሔር የሚጠብቀው
ይቅርታን የሚያረግለት
እንደኔ ያለ ሰው ማነው?

ሊሊ 🥰

DeepThingsOfGod

05 Dec, 04:16


Who is God —-be blessed!

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

04 Dec, 07:43


በእድል አላምንም፥ በእግዚአብሔር በረከት ግን አምናለሁ።

እዚህ ቤት ነበር የተወለድነው😊

DeepThingsOfGod

03 Dec, 04:21


መጽሐፈ ኢዮብ። 28:28 ፤

ሰውንም። እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው። And unto man he said, Behold, the fear of the Lord, that is wisdom; and to depart from evil is understanding.

DeepThingsOfGod

30 Nov, 03:11


The fear of the Lord is your access to the knowledge of God, without the fear of the Lord you're qualified to know nothing about God!
-Victor
.

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

26 Nov, 17:54


እግዚአብሔር ያስቃችኃል!!!

DeepThingsOfGod

22 Nov, 06:37


“Knowing about God is crucially important for the living of our lives. As it would be cruel to an Amazonian tribesman to fly him to London, put him down without explanation in Trafalgar Square and leave him, as one who knew nothing of English or England, to fend for himself, so we are cruel to ourselves if we try to live in this world without knowing about the God whose world it is and who runs it.” Knowing God - by J. I. Packer

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

19 Nov, 14:11


“Destroyed for lack of knowledge”😭

ትንቢተ ሆሴዕ 4:6 ፤ ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። My people are destroyed for lack of knowledge: because thou hast rejected knowledge, I will also reject thee, that thou shalt be no priest to me: seeing thou hast forgotten the law of thy God, I will also forget thy children.

DeepThingsOfGod

18 Nov, 08:40


ትልቅ ነው.....እኛም አናዉቀውም

በሰውኛ ትልቅ ነገር ይታወቃል።
በዓለም ብዙ ተራሮች አሉ ሰዎች ግን በጋራ የምናውቀው ትልቁን ወይም የተወሰኑ ትልልቅ ተራሮችን ብቻ ነው።

በዓለም ብዙ ሰዎች አሉ ሰዎች ግን በጋራ የምናውቃቸው ጥቂት ትልልቅ ሰዎች ነው።

በዓለም ብዙ ሃገራት አሉ ሰዎች ግን በጋራ የምናዉቀው ትልልቆቹን ጥቂት ሃገራት ነው። እነዚህን ያነሳሁን ለምሳሌ ነው እንጂ በሁሉም ነገር ወይም ዘርፍ ትልቅ የሆነ በብዙሃኑ ይታወቃል።

ትልቅ የሆነ እሩቅም ቅርብም ያለ ያየዋል፥ ያውቀዋል። ነገር ግን በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ኢዮብ 36:26 ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም። ይላል። ትልቅ ነው! ተብሎ እንዴት አናውቀውም ይባላል? ትልቅ ነገር እኮ በቀላሉ ይታያል፥ ይታወቃል።

እግዚአብሔር ግን ልበ ንጹሐን ብቻ የሚያዩት ትልቅ አምላክ ነው።

ንጹሕ ልብ፥ የክርስቶስ ልብ እንዲበዛልን እጸልያለሁ።

@TheDeePThingsOfGod

DeepThingsOfGod

15 Nov, 05:10


በእቅድ መኖር

ዓለም በብዙ ሰውች፣ ፍላጎቶች፣ ሃሳቦች፣ መዳረሻዎች...ወዘተ የተሞላች ናት። እያንዳንዱ ቀን የተለያዩ እድሎች እና ክፋቶች ይዞ ይመጣል፥ እቅድ ከሌለን እድሎችን ወደድል መለወጥ፥ ፈተናዎችን ማለፍ ይሳነናል።
ብዙዎች እምቅ አቅም አለን ነገር ግን እቅድ ከሌለን አቅም ለብክነት ይዳረጋል፥ ያለ ውጤት ይፈጃል።

እቅድ ከሁሉ በላይ ውድ የሆነውን ሃብታችንን ይሀውም ጊዜን በተገባው ቦታ ለተገቢው ነገር እንድናውል ይረዳናል።
እቅድ አልቦ መሆን በተለያዩ ሰዎች፣ ፍላጎቶች፣ መንገዶች፣ መዳረሻዎች...ወዘተ ይከፋፍለናል እናም ሃይል አልባ ያደርገናል።
ከእቅድ አልቦነት መላቀቅ እና ሕይወትን በእቅድ በመኖር እግዚኣብሔር የሰጠንን ውድ የጊዜ ስጦታ በልኩ እንድንጠቀም አበረታታለሁ። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

14 Nov, 14:20


ሕይወትን እንዴት ነው የምትኖሩት? How do you live your life?

እያንዳንዱን ቀናችሁን፥ እያንዳንዱን የምታደርጉትን ነገር አስቀድማችሁ አቅዳችሁ ነው? Every day, every detail of your day is planned and you just implement your plan?

ወይስ በዘፈቀደ ቀኑ ይዞ በምመጣው አቅጣጫ ነው የምትሄዱት? Randomly doing things and letting the day pass like that ?

ወይስ በእቅድ ለመኖር እና እያንዳንዱን ነገር በእቅድ ለማድረግ እየሞከራችሁ ነው? Trying my best to plan out my day and live accordingly.

ወይስ በእቅድ መኖር መጨናነቅ ይመስላችሃል? እና ዝም ብሎ መኖር ነጻነት? ከየትኛው ወገን ናችሁ? እስኪ እናውራ... @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

12 Nov, 05:53


እግዚአብሔርን ማወቅ?

“እግዚአብሔርን ማግኘት የሕይወት ትልቁ ግኝት ነው" -ቅዱስ ኦግስቲን

አባቶች፣ ነቢያት፣ ሐዋሪያት እና ቅዱሳን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር እግዚአብሔርን ለማወቅ የነበራቸው ጥልቅ ፍላጎት እና ትጋት ነው።

የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ እና ፍጥረትን ሁሉ እየመገበ የሚያኖር፣ ዘላለማዊ፣ ሁሉን የምችል፣ ሁሉን የምያውቅ እና በሁሉ ቦታ የምኖር፣ በሕሪዩ ፍጹም የሆነ አሃዱ-ስሉስ መንፈስ እጅግ አስደናቂ ነው፥ የሰው አእምሮ ሊረዳው ከምችለው በላይ ነው: ይህንን አምላክ በሁለት ጆሮ መካከል ባለ ትንሽ አእምሮ ማወቅ የሚቻል አይደለም።

እርሱን ማወቅ የሚቻለው በማግኘት ብቻ ነው፣ የአምላክ እውቀት ይገኛል እንጂ አይመረመርም። ለሚወደው ራሱን ያስገኝለታል፥ ይገልጥለታል እንጂ የትኛውም ምጡቅ ቢሆን ረቂቅ ሊያውቀው አይችልም።

እውቀት ሰይሆን ፍቅር፥ ብዙ ምርምር ሰይሆን መታዘዝ ወደዚህ ሕያው አምላክ ያስጠጉናል። ከአባቶች የምንማረው ይሄንን ነው፥ የአምላክን እውቀት በዚህ መልኩ መፈለግ፥ ማልቀስ፥ ማፍቀር እና መታዘዝ።

ኦ የአምላክን እውቀት ማግኘት ይሁንልን።
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

06 Nov, 15:40


እግዚአብሔር ይመስገን።

DeepThingsOfGod

06 Nov, 06:50


Donald Trump has won the election, Gods will is done. Pray for better future of the world.

የአሜሪካውን ምርጫ Donald Trump አሸንፎል።

DeepThingsOfGod

03 Nov, 16:22


እግዚአብሔር

ዘላለማዊ: (Eternal)

ፍጹም: (Morally perfect, perfect in every respect and perfect in every aspect)

ሁሉን ቻይ: ( omnipotent)

ሁሉን አዋቂ:(omniscient)

በሁሉም ቦታ ያለ :(omnipresent)

የፍጥረት ፈጣሪ: (The Creator of creator)

የፍጥረት መጋቢ:( Sustainer of creation)

አሓዱ-ስሉስ መንፈስ ነው: (A Tri-une Spirit.)

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

31 Oct, 04:38


በዚህ ሕይወት የሰው ትርፉ እግዚአብሔርን ማወቅ ፈቃዱንም ማድረግ ነው።

መጽሐፈ መክብብ 12:13 ፤ የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። Let us hear the conclusion of the whole matter: Fear God, and keep his commandments: for this is the whole duty of man.

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

30 Oct, 16:27


ዛሬ ልደቴ ነው😁 እግዚአብሔር ይመስገን ስለሰጠኝ አዲስ ዘመን፥ እስኪ ልደቴን በማስመልከት ከላይ ላለው ጥያቄ መልስ አስቀምጡልኝ። I LOVE YOU ALL!

DeepThingsOfGod

30 Oct, 16:05


ጥያቄ?

መጽሐፈ መክብብ 1:3 ፤ ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው? What profit hath a man of all his labour which he taketh under the sun?

DeepThingsOfGod

28 Oct, 05:03


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለእግዚአብሔር እንድናውቅ ያደርገናል፥ መታዘዝ ግን እግዚአብሔርን እንድናውቅ ያደርገናል።

Bible study gives us knowledge about God, but obedience gives us THE KNOWLEDGE OF GOD.

መጽሐፍ ቅዱስን እያጠኑ ስለ እግዚአብሔር ብዙ እውቀት ማግኘት መልካም ቢሆንም በቂ ግን
አይደለም፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ፍጹም የሚሆነው እና ትክክለኛውን ግብ የሚመታው ስንታዘዝ ነው፥ መታዘዝ እግዚአብሔርን እራሱን በግላችን እንድናውቀው ያደርገናል። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

26 Oct, 17:20


Jesus in all the Bible.
ኢየሱስ በእያንዳንዱ መጽሐፍ። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

19 Oct, 17:19


እግዚአብሔርን ማወቅ
"ማወቅ" የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው -ዘፍጥረት 4፥1 ላይ የአዳምን ወደሚስቱ መቅረብን እና አንድ ስጋ መሆንን ለማሳየት ነበር የዚህም መቀራረብ (intimacy) ውጤት ልጆች ይፈጥራል። ታዲያ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ልክ እንደዚሁ ገብራዊ እና ውጤት ያለው እንጂ ምእናባዊ ብቻ አይደለም፥ በአእምሮ ውስጥ የሚኖር እውቀት ብቻ ሳይሆን መላው ማንነታችንን የሚነካ እና የሚለውጥ ልምምድ (Experience) ነው። የሚሰማ: የሚታይ እና የሚዳሰስ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅ የማያሻማ (decisive) ውጤት በሕይወታችን ይኖረዋል፥ የእርሱ በሕሪይ በእኛ ይወለዳል። ኦ ጌታ ሆይ እንደገና ተገለጥልን!

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

17 Oct, 13:06


"Loving God is the greatest romance, seeking him is the greatest adventure and finding him is the greatest achievement.” -Saint Augustine
Oh lord who art thou? 😭
ጌታ ሆይ አንተ ማን ነህ? 😭

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

14 Oct, 02:43


የማርቆስ ወንጌል 10:38
"ኢየሱስ ግን። የምትለምኑትን አታውቁም።..."

ጥያቄዎቻችን ትክክል ይሆኑ? መጠየቅ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው? ወይስ ትክክለኛ ያልሆኑ ጥያቄዎች በመጠየቅ እየሳትን እና እየባከንን ነው? ሰዎች አንዱ ትልቁ ችግራችን ትክክለኛው ጥያቄ ምንድነው የሚለውን አለማወቃችን ነው፥ ምን መጠየቅ እንዳለብን እንድናውቅ እግዚአብሔር የፉቃዱን እውቀት በጥበብና በመንፈሳዊ አእምሮ ሁሉ እንዲሞላን እጸልያለሁ።

ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:9 ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም። For this cause we also, since the day we heard it, do not cease to pray for you, and to desire that ye might be filled with the knowledge of his will in all wisdom and spiritual understanding;

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

13 Oct, 15:01


1-55% - ጌታ ሆይ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?
2-27% ጌታ ሆይ አንተ ማን ነህ?
3-14% ጌታ ሆይ ጥበብና እውቀት ስጠኝ? ሌሎች ጥያቄዎች 2% እና ከዛ በታች ነው የተጠየቁት።

ጌታ ግን አሁን ከእኛ ጋር እንደለ እናውቅ ይሆን? እናምንስ ይሆን? የማቴዎስ ወንጌል 28:20...እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ለጸሎታችን Effectiveness የመጀመሪያው አስፈላጊ ነገር ይሄ እምነት ነው፥ ጌታ አሁን ከእኔ ጋር ነው፥ ቅርብ ነው ይሰማኛል የሚል እምነት። በእምነት ጌታ ከኛ ጋር እንዳለ በማወቅ ጥያቄዎቻችንን እናቅርብ ይሰማናል ደግሞ ይመልስልናል። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

12 Oct, 04:16


DeepThingsOfGod pinned «ጥያቄ: ጌታ ኢየሱስ አሁን ያላችሁበት ፊትለፊታችሁ ቢቆም እና አንድ ጥያቄ እንድትጠይቁት ቢጠይቃችሁ፥ ጥያቄችሁ ምን ይሆናል? »

DeepThingsOfGod

10 Oct, 23:38


“For the seek of a suffering and dying world, I will count the cost, pay the price and be used by God to set the captive free.” -unknown

DeepThingsOfGod

09 Oct, 04:36


Giving yourself to God without reservation, will result in receiving his fullness. Saul was a chief sinner, but by the strength of surrender he was transformed into Paul, the mighty apostle of God who is the writer of roughly half the books of the New Testament.
-victor
ሙሉበሙሉ ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት የእግዚአብሔርን ሙላት እንድንቀበል ያደርገናል። ሳውል ከኃጢአተኞች ሁሉ ዋነኛ የነበር ነው፥ ነገር ግን ፍጹም በሆነ መሰጠት ምክንያት የአዲስ ኪዳንን ግማሽ ያክል ቅዱሳት መጽሐፍት የጻፋ ታላቅ ሐዋሪያ ጳውሎስ ለመሆን ተችሎታል። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

08 Oct, 03:39


ኦሪት ዘፍጥረት 3:9 ፤ እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። And the LORD God called unto Adam, and said unto him, Where art thou?

እግዚአብሔር ከዚህ ጊዜ (moment) ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሰው እየፈለገ ነው፥ ማነው የሚገኝለት? @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

06 Oct, 17:19


በእምነታቸው የተመሰከረላቸው አባቶች ሩጫውን ቢፈጽሙም ተስፋውን ግን አልተቀበሉም: በጣም ይገርማል! ተስፋ በሌለቤት ተስፋ ይዘው ያመኑ (Who against hope believed in hope) ሮሜ 4፥18--የእምነት አበቶች ናቸው፥ እኛ ግን ተስፋው ተሰጥቶናል: የተስፋው ቃል የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦልናል: እንዴት ይልቅ ልናምን ይገባናል? እንደደመና የከበቡን ጻድቃን መናፍስት: ተስፋ በሌለቤት በተስፋ ያመኑ የእምነት አርበኞች ናቸው: እኛ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱት የተባልን: የተስፋው ቃል የተሰጠን ብሩካን ነን።

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

06 Oct, 02:31


1-የክርስቲያን ሕይወት እንደ ሩጫ ነው፥ ይሄ ሩጫ ግን የአጭር ርቀት ሰይሆን እንደ ማራቶን ረዘም ያለ ሩጫ ነው።

2-ይህንን ሩጫ በትክክል ለመሮጥ እና በድል ለማጠናቀቅ መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተዘርዝረዋል፥ የመጀመሪያው ኃጢአትን ማስወገድ ( eliminating sin of off our lives) እንደዚሁም ሸክም የምሆንብንን የትኛውንም ነገር ማስወገድ (lay aside every weight )
አንዳንድ ነገሮች አሉ ኃጢአት ያልሆኑ ነገር ግን ሸክም የሚሆኑ፥ ሸክም ተሸክሞ ሩጫን በድል ማጠናቀቅ ደግሞ የማይታሰብ ነው: በመሆኑም ፈጽሞ ሸክምን ሁሉ ማስወገድ ያስፈልጋል።

3-ይሄንን ሩጫ በስኬት እንድንሮጠው እና በድል እንድናጠናቅቀው የሚያነሳሳን ትልቁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ አይናችንን በእርሱ ላይ ማድረግ ያስፈልጋል (Keep your eyes on Jesus) ብዙ ጊዜ ሰዎች "በእከሌ ምክንያት ተሰናክዬ ከእምነት አፈገፈኩ" ስሉ ይደመጣል፥ አዎ እውነት ነው አይናችንን ከኢየሱስ ላይ አንስተን ሰዎች ላይ ካደረግን እንሰናከላለን፥ ስለዚህ ለአንድም ሰከንድ አይናችንን ከኢየሱስ ላይ ማንሳት ሩጫውን በረስኬት እንደንሮጥ በድልም እንዳንፈጽም እንቀፋት መሆኑን ተረድተን ኢየሱስ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባናል።

4-ይሄንን ሩጫ በስኬት ለመሮጥ እና በድል ለማጠናቀቅ የምያስፈልገን ኢየሱስ ክርስቶስ የኃይማኖቶችን ጀማሪ እና ፍጹም አድራጊ መሆኑን ማወቅ ነው። ይሄንን ሩጫ ጀምሮ በድል ያጠናቀቀ ሞዴል አለን፥ የሚጀምረውን ሁሉ የሚፈጽም ታማኝ ጌታ እንዳለን ማወቅ ትልቅ ብርታት የሚለግስ ይሆናል።

5-ሌላው እጅግ አስፈላጊ የሆነው ትዕግስት (perseverance) ነው፥ ሩጫው ረጅም ነው: የመቶ ሜትር አይነት ሩጫ አይደለም ይሄ እጅግ ፈታኝ ያደርገዋል: በተጨማሪም ብዙ አይነት ፈተናዎች ይኖረሉ: ጌታችን ነውር የሆነውን የመስቀል ሞትም ጭምር ተቀብሎ ነው በድል የፈጸመው፥ መጽናት የግድ ነው።

ይሄ ሁሉ ለምን?...በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር አብርን እንድንገዛ መጽናት ይገባናል።

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

05 Oct, 04:19


የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ ተወዳጆች፥ አንድ ክፍል ከእግዚአብሔር ቃል እንመልከት። ወደ ዕብራውያን 12:2
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
Looking unto Jesus the author and finisher of our faith; who for the joy that was set before him endured the cross, despising the shame, and is set down at the right hand of the throne of God.
ምን ትራዳላችሁ? መልሳችሁን በኮመንት መስጫ ጻፉልኝ?

@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

04 Oct, 06:04


ሰይጣን ከፍተኛ የማሳት ዘመቻ ላይ ነው፥ ጥቂት ጊዜ እንዳለው አውቆ የመጨረሻ የሚለውን ስርቆት፣ ማጥፋት እና ግድያ ለመፈጸም በዓለም ሁሉ ተሰማርቶ እንዳለ እየተመለከትን ነው፥ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የእግዚአብሔርን ቃል በልባችን መያዝ ያለብን ጊዜ ነው፥ ምክንያቱም ከመሳት የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው (The word of God is our only guard against deception)
እንንቃ፥ እንጸልይ፥ እንዘጋጅ፥ ወንጌል እንስራ። @TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

04 Oct, 03:49


ኢየሱስ በቶሎ ይመጣል!

DeepThingsOfGod

02 Oct, 05:34


ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ፥

በድንግል ተጸንሶ በድንግልና እንደተወለደ፥ በዚህም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ እንደተገለጠ አምናለሁ፥

በመንፈስ ቅዱስና በሃይል ተቀብቶ የሰውን ልጅ እንዳገለገል፥
ኃጢአትና ሕጸጽ የሌለበት ፍጹም ሕይወት እንደኖረ አምናለሁ፥

በኃጢአተኞች ምትክ መከራን እንደተቀበለ፥ በእንጨት እንደተሰቀለ እና እንደሞተ እንደተቀበረም አምናለሁ፥ ነገር ግን መጽሐፍ እንደሚል በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደተነሳ አምናለሁ፥

ወደሰማይ እንደወጣ፥ ሁለተኛም በክብር ተመልሶ እንደሚመጣ፥ ዘላለማዊ መንግስትም እንደሚመሰርት አምናለሁ።

አሜን።
ይሄ ሁልጊዜ የማደርገው ኑዛዜ (Confession) ነው፥ በእያንዳንዱ ጊዜ እምነቴን አጠናክሮታል።

@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod

DeepThingsOfGod

01 Oct, 19:30


ትንቢተ ዘካርያስ 12:1-14
ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል። በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ። በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፤ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ። የይሁዳም አለቆች በልባቸው። በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ። በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፤ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።
እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፤ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።
በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።
በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።
ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የቀሩት ወገኖች ሁሉ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።

DeepThingsOfGod

01 Oct, 18:42


IDF ኢራን የሚሳኤል ጥቃቱን አቁማለች ብሎል
What’s next? Are we close to world war 3 and the return of Jesus Christ?

DeepThingsOfGod

01 Oct, 17:27


መዝሙረ ዳዊት 122:6

ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፤ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን። Pray for the peace of Jerusalem: they shall prosper that love thee.

DeepThingsOfGod

01 Oct, 17:05


Now in Israel