አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች @so_funy Channel on Telegram

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

@so_funy


No Matter what language you speak. ☞This channel will make reader .

➡️Some time i have to post ads to Grow the channel.
➡️If you have Some Gifs or Videos or FEED BACK then Feel Free to Share With
👉some Funny pic ,Videos & GIFs.

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች (Amharic)

የተጫጭሩት አስተያየቶቻችን በአጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች እንዴት እንደሚሸጥ እና እንደሚሰራ ሆነ በአረንጓዴ ላይ ለመሆን እያየን ነን። ይህ ቦታ የታወቀ የሚሆንን ፅሁፍና እንስሶች ከገበያ በላይ እንዲታይ ላይ ያደረጉ መረጃዎች ይጠቀሙበታል። ከምን ሄዳችሁ እናገራለን፣ ማስታወቂያ ወደ ዓረቢያ ዋና ምርጫዎቹ እያወገዱ ነው። በአጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች የተለያዩ ስልኩቶችና ቪድዮዎች ለጠቃሚው በእምነት የታዩ ከተጫጭሩበት ወዲህ ያልተካሄደ አድራጊ ስልኩትን እና ቪድዮዎችን ይቀንስበዋል።

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

20 Nov, 10:29


https://aaaonline.info/pjFkbB

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

20 Nov, 08:44


የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=1191684771456103&language=am&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

07 Nov, 02:45


1. አልበርት አንስታይን፡-

አንስታይን ከ1879-1955 የኖረ ታላቅ የሳይንስ ሊቅ ነበር። በተለይ ሁለት ግኝቶቹ የሳይንስ እይታችንን በእጅጉ የቀየሩ ሲሆን አንስታይን ምድራችን ካፈራቻቸው የሳይንስ ሊቆች ውስጥም ሆነ ወደፊት ከሚወለዱት ውስጥ ተወዳዳሪ አይገኝለትም የሚባል ብርቅዬ ሳይንቲስት ነው።

አንስታይን በልጅነቱ ዳይስሌክሊስ (ሲያነቡ ወደ ግራ የሚያነቡ) የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ አስተማሪዎቹ ደደብ አድርገው ይገምቱት ነበር።

በ15 ዓመቱ ትምህርቱን አቁሞ ከዓመት በኋላ ዙሪክ የሚገኝ አንድ ፖሊ ቴክኒክ ለመግባት አመልክቶ የመግቢያ ፈተናውን ወድቋል።

ይህ ሰው ግን በፊዚክስ ንድፈ ሃሳብ ዓለምን በመቀየሩ የኖቬል ሽልማት ለመሸለም የበቃ ድንቅ ሳይንቲስት ነው።

2. ቶማስ ኤዲሰን፡

ይህ ታላቅ ፈላስፋ ትምህርት ቤት የሄደው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር። ምክንያቱም በስምንት ዓመቱ አስተማሪው "ደደብ" ብሎ ስለሰደበው እናቱ ከትምህርት ቤት አውጥታ ቤት ውስጥ አስተማረችው። በዘጠኝ ዓመቱ ይሞክራቸው የነበሩት ነገሮች ከእናቱ አቅም በላይ ሆኖ ተገኝቷል።

ቶማስ ኤድሰን በህይወት ዘመኑ አንድ ሺህ አዳዲስ ግኝቶችን የፈለሰፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የኤሌክትሪክ ብርሃን እና ሸክላ ማዘፈኛ ሲኖሩበት ያሻሻላቸው ነገሮች ደግሞ ፊልም ማሳያ፣ ቴሌፎን ይገኙበታል።

3. ሰር ዊንስተን ቸርችል፡

ይህ ሰው ታላቅ እንግሊዛዊ ፖለቲከኛ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ሰዓሊ ሲሆን እንግሊዝን በአንደኛ እና ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በተለያየ የመንግስት ስልጣን ደረጃ የመራ ታላቅ የፖለቲካ ሰው ነው። (በአገራችን መዲና አዲስአበባ ጎዳና በስሙ ተሰይሞለታል)

ቸርችል ይህቺ ምድር ካፈራቻቸው ድንቅ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ቢሆንም በትምህቱ ደካማ ስለነበር ሮያል የውትድርና ኮሌጅ ለመግባት ከአንዴም ሁለት ግዜ ተፈትኖ በመውደቁ መግባት አልቻለም ነበር።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ቸርችል በአመራር እና በንግግር ችሎታው ለሃገሩ ትልቅ ሚና ተጫውቶ ያለፈ መሪ ነው።

4. ሪቻርድ ብራንሰን፡

የVirgin Group መስራች የሆነው ብራንሰን የዲስሌክሲያ (dyslexia) ችግር የነበረበትና ደካማ የአካዳሚክ ብቃት ነበረው። በ 16 ዓመቱ ትምህርቱን ያቋረጠ ነገር ግን ዓለም አቀፍ የሆነ የንግድ ኢምፓየር መገንባት የቻለ ስኬታማ ሰው መሆን ችሏል።

5. አይዛክ ኒውተን፡-

ኒውተን በልጅነቱ ቸልተኛ እና ሰነፍ ተማሪ እንደሆነ ይቆጠር ነበር። በመጨረሻም ሰዋሰው ወደሚያስተምር ትምህርት  ቤት ተላከ። እዚያም እውነተኛ እምቅ ችሎታውን ማሳየት ጀመረ፤ በኋላም ደካማ ውጤቶች ስለነበሩት ከትሪንቲ ኮሌጅ ሆነ ከካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ የክብር ወይም የማዕረግ ተመራቂ አልነበረም።

ነገር ግን በታሪክ ከታወቁት ታላላቅ የሳይንስ ፈጣሪዎች አንዱ በመሆን የዘመኑ ሳይንስ በእርሱ ስራዎች ላይ ለመመርኮዝ በቅተዋል።

6. ቻርለስ ዳርዊን፡

በዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ የሚታወቀው ዳርዊን እንደ መካከለኛ ተማሪ ይቆጠር ነበር። ከትምህርቱ ይልቅ ከቤት ውጭ እንቅስቃሴዎችን እና ናሙናዎችን መሰብሰብን ይመርጥ ነበር።

ወጣቱ ዳርዊን በትምህርቱ በመድከሙ አባቱ "አንተ ከአደን እና ውሻ በስተቀር የምትወደው ነገር የለም፤ ስለዚህ ለራስህም ሆነ ለቤተሰብ ውርደት እንዳትሆን" ብሎ ከትምህርት ቤት አስወጣው።

የህክምና ትምህርት ሞከረ አስጠላው። የሃይማኖት ትምህርትም ሞክሮ ነበር አልሆነለትም። ብዙውን ግዜውን ግን ከስፖርተኞች ጋር ነበር የሚያጠፋው።
ይህ ሰው ግን በመጨረሻ አጠቃላይ የስነ-ህይወት ሳይንስን ለመቀየር ችሏል።

7. ፓብሎ ፒካሶ፡-

ታዋቂው አርቲስት ለመደበኛ ትምህርት አነስተኛ ፍላጎት የነበረው ሲሆን ብዙ ጊዜ እንደ ደካማ ተማሪ ይቆጠር ነበር። የጥበብ ተሰጥኦው ግን የማይካድ ነበር እናም በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከፍተኛ ተደማጭነት ካላቸው አርቲስቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል።

8. ስቲቭ ጆብስ፡

የአፕል ካምፓኒ መስራች የሆነው ጆብስ፣ በአመፀኛ ተፈጥሮው እና በመደበኛ ትምህርት ላይ ፍላጎት በማጣት ይታወቅ ነበር። ነገር ግን የእሱ የፈጠራ ራዕይ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪውን ለውጦታል።

9. ቢል ጌትስ፡-

የማይክሮሶፍት መስራች የሆነው ጌትስ ጎበዝ ግን ብዙ ጊዜ ስልቹ የሚባል ተማሪ ነበር። ለሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ያለውን ፍቅር ለማሳካት ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አቋርጧል፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ እንዲፈጠር አድርጓል።

10. ማርክ ትዌይን፡-

የ"The Adventures of Tom Sawyer" and "Adventures of Huckleberry Finn" ፀሃፊ የሆነው ይህ ታዋቂ ደራሲ እንደ ሰነፍ ተማሪ ይቆጠር ነበር። ብልህነቱ እና የመተረክ ችሎታው ግን ከአሜሪካ ታላላቅ ጸሐፊዎች አንዱ አድርጎታል።

11. ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ይህ ሰው የሂሳብ ትምህርት አይሆነውም ነበር። እናም አባቱ ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ሻማና ጧፍ ሲያሰራው አደገ። ነገር ግን ይህ ሰው አሜሪካ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ በመሆን ታዋቂ ፖለቲከኛ፣ ሳይንቲስት፣ ጸሐፊ እና የፔንሲልቫኒያ ፕሬዚዳንትና የአሜሪካ መስራች አባት ለመባል የበቃ ሰው ነው።

12. ሴናተር ኤድዋርድ ኤም ኬኔዲ

ይህ የማሳቹሴትስ ሴናተር በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሁሉ ተወዳድሯል። ግን ፈተናውን ጓደኛው ሲፈተንለት ተይዞ ከሚማርበት ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተባርሮ ነበር።
------------------------------
እነዚህ ታሪኮች ያቀረብነው መደበኛ ትምህርት እንደማያስፈልግ ሳይሆን በቀደምት የትምህርት ህይወታችን ውጤታማ መሆን አለመቻላችን የግድ የወደፊትን ስኬት የሚወስን አለመሆኑን ለማሳየት ብቻ ነው።

እነዚህን ግለሰቦች ወደ ታላቅነት የመራቸው ልዩ ባህሪያቸው እና ጽናታቸው ነው።
------------------------------
ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ከእናንተ ወይም ከልጆቻችሁ/ከእህት-ወንድሞቻችሁ ጋር የሚመሳሰለው የትኛው ነው?

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

07 Nov, 02:39


☑️ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች😁

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው።
Via:Ayuzehabesha
መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

07 Nov, 02:36


1. መቆጣጠር የማትችለውን ነገር ተቀበል!

ሁልጊዜ የሚደርስብንን ነገር መቆጣጠር ባንችልም ምላሽ የምንሰጥበትን መንገድ ግን መቆጣጠር እንችላለን።

2. ስኬት የራዕይ ውጤት ነው!

ሁሉንም ጊዜህን እና ጉልበትህን ስኬታማ ለመሆን ከማዋል ይልቅ እሴት ለመፍጠር፣ ከራስህ በላይ ትልቅ ለሆነ ነገር አውለው። ይህን ስታደርግ ስኬት በራሱ ጊዜ ፈልጎህ ይመጣል።

3. በመከራ/ስቃይ ውስጥ ትርጉም አለ!

መከራ/ስቃይ የህይወት ክፍል የሆነና የማይቀር ነው።

ስለዚህ በህይወት ውስጥ ትርጉም ካለ በመከራ ውስጥም ትርጉም አለ።

"ያለ መከራ/ስቃይ የሰው ህይወት ሙሉ አይደለም"

4. መከራ/ስቃይ ለዘላለም አይቆይም!

መከራ/ስቃይ የማይቀር ቢሆንም - ቋሚ ግን አይደለም።
የነጻነት ጊዜ ይመጣል፣ መከራ የሚቆምበት ጊዜ ይመጣል። ያ ጊዜ የሚመጣው ከስቃይህ ጀርባ ያለውን ትርጉም ስታገኘው ወይም ስትፈጥረው ነው።

5. አቅምን ሙሉ በሙሉ መገንዘብ ከራስ አልፎ ለሌሎች የመኖር ውጤት ነው።

ሰው ራሱን ለአላማው ሙሉ በሙሉ መስጠት አለበት። ይህን ሲያደርግ ከሚያስበው በላይ ሰው ይሆናል፣ የበለጠ ሰው በሆነ መጠን ራሱን በተግባር እያሳየ እና አቅሙን እየተጠቀመ ይመጣል።

6. ዓላማ በሕይወት እንድንኖር ያደርገናል!

ተስፋ የቆረጡ፣ የመኖር ዓላማቸውን (Purpose) ያልፈጠሩ፣ በህይወት የመቆየት እድላቸው አነስተኛ ነው።

ነገር ግን አንድ የሚያበረክቱት ነገር እንዳለ የሚያውቁ ሰዎች ማንኛውንም መከራ/ስቃይ ተሻግረው በህይወት የመኖር እድላቸው ሰፊ ነው።

7. ሰው አላማውን ይፈጥራል!

"የሰው ልጅ የህይወቱ ትርጉም ምን እንደሆነ ሌሎችን መጠየቅ የለበትም፣ ይልቅ ሲጠየቅ መመለስ ያለበት እሱ መሆኑን ማወቅ አለበት።

ሕይወት ትጠይቃለች፣ ትሞግታለች፣ እናም ጥያቄውን መመለስ፣ ተግዳሮትን አልፎ መነሳት እና ለህይወታችን ትርጉም መስጠት የእኛ ድርሻ ነው።

8. በፍቅር የተነቃቃህ ሁን!

በሄድክበት ቦታ ሁሉ ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ።

የአለም ጨለማ ብርሃንህን እንዲያደበዝዝ አትፍቀድ።

የሌሎች ክፋት ክፉ እንዲያደርግህ አትፍቀድ።
—————————————————

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ
#like
#copylink
#share
ማድረግን አትርሱ 🙏
——————————————

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

07 Nov, 02:25


ማነው የወደቀው ?
****💡💡💡

ስለ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ትምህርት ብዙዎች ብዙ ብለዋል ፤ ብዙ ፅፈዋል ። ከእነዚህም መካከል  ፕ/ር ኧረነስት ዎርክ አንዱ ናቸው በጥናታቸውም  " ... ነፃይቱ ኢትዮዽያ ውስጥ ያለው የትምህርት ስርዓት ቅኝ ከተያዙት የአፍሪካ አገሮች የማይለይ በመሆኑ በጣም አደገኛ እንደሆነ ይገልፃሉ። "

ይህም  የሚሼል ፉ ኮ አባባል " ... የቅኝ ግዛት የመጨረሻው ደረጃው ትምህርትና ተቋማትን መቆጣጠር ነው  :: " የሚለው ሀሳብ ይበልጥ ያጠናክረዋል :: የዎርክ የጥናት ሪፖርት በ1924 ዓ.ም በቀረበበት   ወቅት   " የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት የምዕራቡን  አለም መምሰል የለበትም ፤   መሆን ያለበት "የኢትዮጵያ " ነው የሚል ነበር ::

  ሌላኛዋ አሜሪካዊቷ የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የነበረችው ዶ/ር ኤዲት ሎርድም 1954 ዓ.ም በፅሁፏ ላይ  ስለ ኢትዮጲያ የትምህርት ቤቶች ካሪኩለም ታዝበው  “ ... ካሪኩለም ማዘጋጀት ያለብን የተማሩ ኢትዮጵያውያንን በተማሩ እንግሊዛውያን ፣ ፈረንሳውያን ወይም አሜሪካዊያን ሞዴል ለመቅረፅ ነዉ? ወይስ ሊፈቱ የሚገባቸው የዚህች አገር ችግሮች ምንድን ናቸው? የሕዝቡ ፍላጎትስ ምንድን ነው ? ብለን ጠይቀን ነው? የአሁኑ የትምህርት ፕሮግራም እንዴት ነው እነዚህን ችግሮች የሚፈታው ? እንዴትስ ነው የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟላው ? “ ብለዉ  ነበር ::

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት መሰረታዊ ችግሮች በዚህ ጥናት ውስጥ በግልፅ ተቀምጠዋል። ትምህርት ዝግ ሆኖ ሀገር በቀል ይሁን የሚባል ጉዳይ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ነገር ግን የማህበረሰቡን  እሳቤ ኋላ ቀር ብሎ የውጭውን ከእነ ምናምኑ መጫን ትልቅ ስህተት ነው ።

ብራዚላዊው የትምህርት ፈላስፋ ፖሎ ፌሬሬ አባባል ከሆነ ትምህርት ችግር ፈቺ የሚሆነው  ከሽምደዳ  (Banking (deposite) system ) ወጥቶ ለማህበረሰብ ችግር መፍትሄ ፈላጊ ሆኖ ሲቀርብ ነው ይህም( problem posing  and  problem Solving system) ይሉታል ::

ሊቁ ፕ/ር ማዕምር  የኢትዮጵያ ትምህርት የራስ እውቀት ነፃነት (ሉዓላዊነት)  የለውም  ይላሉ :: ይህም በፅንሰ ሃሳብም ፣ በስነ ዘዴውም እንዲሁም  በማስተማሪያ ቋንቋው ምዕራባዊ በመሆኑ  ደመነፍሳዊ  (zombie concept) ነው ይላሉ ።

ይህም ትምህርቱ የራሱን ፍኖት መፈንጠቅ እንዳይችል አድርጎታል፤ ምሁራዊ አድር ባይነት እና የተበላሽ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ እንድንዘፈቅ አድርጎናል ይላሉ።  በመሆኑም ሃገርና ማህበረሰብን ከማልማትና ከማሳደግ ይልቅ የውድቀት ምንጭ ነው ይላሉ። 

እንደ አብሪ ኮከቡ ገ/ህይወት ባይከዳኝ አባባል " ... አንድ ህዝብ አርነት ሊኖረው የሚችለው በሁሉም ነገር ራሱን ሲችል ነው ። አርነት የሌለው ህዝብ ውሎ አድሮ የሌሎች ተገዥ ይሆናል። የፖለቲካ ነፃነት ብቻውን ምንም ነው ። 

እንደ ዶ/ር ይርጋ ገላው ምልከታ ደግሞ  የትምህርት  ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ከውጪ የተቀዳ በመሆኑ ሃገር በቀል ቅኝ ግዛትን (native colonization) እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ይላሉ ። ይህም ማህበረሰቡ በገዛ ሃገር ባይተዋር ፣ እሴት አልባ ፣ ትርጉም አልባ አድርጎታል ይላሉ። ይህም የተማሩ የተባሉ ሽሚዝ ለባሾች (ቢሮክራት) ህዝቡን በተበላሽና በጭቆና ቀንበር ውስጥ እንዲዘፈቅ አድርገውታል።

የክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ የትምህርቱን ስርዓት አምርረው በተቹበት " የልም ዣት " በተሰኘው ብሉይ ረጅም የልቦለድ መጽሐፋቸው መግቢያ  ላይ  “ትምርት ለሰው ሁለተኛ ፈጣሪው” ነው ይላሉ :: አክለውም “ ...እቤቴ እንግዳ ቢመጣ ተቀብዬ ማስተናገድ አለብኝ እንጂ እንዴት ቤቱን ትቼለት እወጣለሁ ይላሉ (ቃል በቃል አይደለም የተወሰደው ) ከውጪ በመጣውና በሀገር በቀሉ ትምህርት መካከል የሆነው ይህ ነው።

ለማሳያ በዚሁ መፅሀፋቸው ውስጥ ባሉት ሁለት ወካይ ገጸ ባህርያት አማካይነት ማለትም በተዋበችና በልጇ በተከስተ መካከል  የተፈጠረውን የእሴት ልዩነት ፣ የስነ ልቦና መፈርቃት ወዘተ ... ጥሩ ማሳያ ነው ።

በስንት ጥረትና ልፋት  ያስተማረችው  እናቱን ፤ አንድ ቀን ምሳ ቋጥራለት ስትሄድ በጓደኛው ምንህ ናት ተብሎ ሲጠየቅ" ገረዳችን ናት " ብሎ  ሲያፍርባት ታዝበናል። 
ቆይቶ ቆይቶ  ባህር ማዶ ሲሻገር ሊሰናበታት እንኳን አይፈቅድም ። እንዳልተፈጠረች ጥሏት  ይጠፋል። ከዚህ የተሻለ ማሳያ ምን አለ?

ትምህርቱ የፈጠራቸው ተከስታውያንን ፕ/ር ማዕምር  " የስርዓታዊ ና መዋቅራዊ ድህነት አዋላጆች (Midwifery of the systematic living poverty) ።

ዛሬስ ? በቂ የትምህርት ፍልስፍና ፣ ስነ - ዘዴ ፣ መፅሀፍ ፣ ት/ቤት፣ ወዘተ የሉንም ።  እነዚህ ነገሮች በአግባቡ ባልተሰሩበት ሁኔት  የተወሰደው እርምጃ ልክነት አጠያያቂ ነው። ትምህርት ላይ የሚፈረገውን ሸፍጥ እዚህ አልዘበዝ ብም። ነገር ግን  ትምህርት የፖለቲካ መሳሪያ መሆን የለበትም ።Alas!

© Teshale Kebede Bedriya

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

31 Aug, 22:49


የምድር ና የሰማይ ልዩነት የስጋና የነብስ መኖሪያ ያክል አድማሰ ህላዌ ጥልቅ እሳቤ መሠረተ ሰብዓዊ ና ተግባረ ምግባር ና ስብእና የገነባ ና የተገነባ ዘርፈ ብዙ ችግር ፈቺ የሆነ ኪህለ ጠቢባን የምናዳብር ና የምንተገብር ጀግና ዜጋ የምንፈጥርበት የአገር ኢኮኖሚ ከቤተሰብ ምጣኔ ስሌት የተቆራኘ እንደሆነ አውቀን ልእለ ኃያል ኢትዮጵያዊነትን የምንገነባበት እንዲሆን እመኛለሁ

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

18 Aug, 12:54


መጪዉ ዘመን ለሀገሬ የምመኝላት

መልካም የሆነ የጎላ #የተግባር ዘመን እንዲሆንላት ነው ።

...
የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለጸው #በተግባሩ እንጂ #በንግግሩ አይደለም ።
የተግባር መሰረቱ ደግሞ #ጽኑ_ፍላጎት ነው !

ችግሮችን ከመቅረፍ ችግሮቹን የሚያላዝኑ ና ልማታዊ እንቅፋቶችን ከሚፈጥሩ ሀሳቦች የምንወጣበት፣

መጪው ዘመን ጠቃሚውን የምናስቀጥልበት፣

ችግሮቻችንን ለይተን የምንቀርፍበት ፣

የመነጣጠልና የመለያየት እሳቤዎችን የምንገራበት ፣

ገናና ና ልእለ ኃያል የሆነች አገራችንን አጥብቀን የምንፈጥርበት ና የምናስቀጥልበት ፣

የአገር ፍቅር መሰረት ያለው ና ለአገር ፍቅር ተግባራዊ የሆኑ እሳቤዎችን ና ተግባሮችን የምናለማበት ና የምናስቀጥልበት ፣


አገር የሚገነባ፣ የሚያለማ፣ የሚያበለፅግ፣ ከራሱ በፊት ለአገሩ ክብር ዘብ የቆመ ዜጋ የምንቀርፅበት፣

ፍፁም #ሰላማዊ ና #የተረጋጋ ቤተሰብ፤ማህበረሰብ ፤ዜጋ፣ሀገር ፣ አገር ና አህጉር የምንፈጥርበት ፣

እርሃብ ፣ ጠኔ ፣መከራ፣እንግልት ፣አምጪ የሆነውን #ጦርነት የምናስቀርበት፣

ከንቱ ና እርባነቢስ ከሆነ ፀብ ፣ ንትርክ፣ ሙግት ና ክርክር ከንቱነት የምንረዳበት ፣

ባልተጋገረ ና ባልዳበረ ዳቦ ተጠቃሚነት ወይም ባል ተገነባ ሀብት እኩል የሀብት ና የልማት ተጠቃሚነት ከሚል እሳቤ ወጥተን ትልቁ ና የደረጀውን ለሁላችንም የሚበቃ ፣ የሚመጥን ና የሚገባ ልማትን አጥብቀን የምንገነባበት ፣

ለመልካም እሳቤ ና ተግባር ዘብ የምንቆምበት ፣

ለአገሩ ልማት ተቆርቋሪ አሳቢ ቀማሪ ና ጦማሪ (ፀኃፊ) የምንፈጥርበት፣

በሀሳብ ና በብዕር የሚያምን ትውልድ የምንገነባበት ፣

መዋጋት ካለብን ዋነኛ ጠላታችን ድህነት ነው! (የቀድሞው ክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ )
የሚያባላን ቃታ የሚያማዝዘን ችግር ውስጥ የሚከተን መልካሙን ከክፉ ለይተን እንዳናቅ ና እንዳንለይ የሚያደርገን ድህነታችን ነው ።

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:26


ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!!

፨፨፨

<< አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >>

/ ሶቅራጥስ /

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:26


የፈላስፋው ፍርድ

"የሰው ልጅ #ለተፈጥሯዊው_ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ #በዓለማዊው_ሕግ በከለው"

/ ላኦ-ዙ /

📚📚📚

.....ላዎ-ዙ በመላዋ ቻይና ጠቢብ ለመሆኑ በተመሰከረለት ዘመን ላይ ቆሞ ነበር ። ይኸን የሰማው የቻይና ንጉስ ላኦ-ዙን አስጠርቶ በታላቅ ትህትና ከተቀበለው በኋላ ..."እባክህ!የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ እንድትሆን እለምንሀለሁ?"ሲል የሹመት ጥያቄ አቀረበለት ።
፨ ላኦ-ዙ ግን "ንጉስ ሆይ! ተሳስተሀል!ለዚህ ቦታ የሚሆን ትክክለኛው ሰው እኔ አይደለሁም ፤ ልቅርብህ...ሌላ ሰው ፈልግ!" አለው ።
ንጉሱ ግን የላዎ-ዙን እምቢታ መቀበል ቀርቶ መስማት እንደማይፈልግ ነገረው፦"ከአንተ በቀር ማንንም ሰው በዚህ ወንበር ላይ ማስቀመጥ አይቻልምና የሰጠሁህን ሥልጣን ግድ መቀበል አለብህ"ሲል ወተወተው ።



፨ ላዎ-ዙም፦ "እንግዲ አልሰማህም የምትል ከሆነ በመጀመሪያው ቀን ችሎት የምፈፅመውን ስትመለከት መሳሳትህ ይገባሀል ። ከትህትና በመነጨ ወይም ለአንተ ካለኝ አክብሮት ለቦታው የምገባ አለመሆኔን ነገርኩህ እንጂ ፣ እውነቱ ግን መንግስትህ የዘረጋው ሥርዓት የተሳሳተ መሆኑን ማወቄ ነው!እናም በቦታው ላይ ወይ እኔ እኖራለው ፤ ወይም ደግሞ የአንተ ህግና ሥርዓት። ፣ እንዲሁም እሱን የሚከተለው ሕዝብህ ይኖራል"በማለት ሥልጣኑን ለመቀበል ተስማማ ።
፨ ላዎ-ዙ ጊዜ ሳያባክን በነጋታው ችሎት ተቀመጠ ። ተከሻሱ ሰው በቻይና ዝነኛ ከነበረ ሀብታም ብዙ ገንዘብ ዘርፏል ተብሎ ከፊቱ ቀረበ። ላዎ-ዙ የተከሳሹን ወንጀል አድምጦ ሲያበቃ ፍርድ ሰጠ ። "ከሳሽም ተከሳሽም እያንዳንዳቸው በስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፈርጃለሁ"።



ከሳሽ የሰማውን ማመን አልቻለም ። ምናልባት ላኦ-ዙ ክሱ አልገባው ይሆናል ፤ አልያም እርጅና እየተጫጫነው ስለሆነ መርሳት ጀምሮት ይሆናል ፥ ወይም ደግሞ ለስራው አዲስ ስለሆነ ...ብቻ አስቦ ሲጨርስ ፈገግ ብሎ፦"ክቡር ዳኛ!ምን እያሉ ነው? ገንዘቤን የተዘረፍኩት እኮ እኔ ነኝ ፤ ይሄ ምን አይነት ፍርድ ነው? ሀብቴን ተዘርፌ እንዴት እንደገና ከዘረፈህ ሰው ጋር አብረህ ወህኒ ውረድ እባላለው ? ግዴለም የሆነ ቦታ አልገባዎትምና ያልተገባ ፍርድዎን ያስተካክሉልኝ!"

፨ላዎ-ዙ ፈገግ ብሎ ምክንያቱን አስረዳው፦"ይልቁንስ ያልገባህ አንተ ነህ!ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁ መስሎህ ከታየህ ምናልባት ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁትም ገንዘብህን ዘርፏል በተባለው ሰው ላይ ነው ። የአንተ ወህኒ መውረድ ግን ከሌባው በላይ የተገባ ሆኖ አግኝቼዋለው ። ምክንያቱም አንተ የበዛ ሀብት ለራስህ ያከማቸኽው ፥ ሌላው ሰው ማግኘት የሚገባውን እያሳጣህ ነው...ብዙዎች በችግር የሚማቅቁባት በዚህች ሀገር አንተ ገንዘብ በገንዘብ ላይ ታከማቻለህ ። ለምን ይሆን? አየህ! የአንተ ከልክ ያለፈ ስግብግብ ባህሪህ እነዚህን ሌቦች ፈጠረ! ስለሆነም ሌባው በድርጊቱ ፤ አንተ ደግሞ ሌባ በመፍጠርህ እኩል ፍርድ ይገባችኋል ! የመጀመሪያው ወንጀል ፈጣሪ ግን አንተ ነህ ።



ላዎ-ዙ፦"የሰውን ልጅ ዓለማዊው እውቀትና ሕግ ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግ ሊገዛው ይገባዋል" የሚለው ለዚህ ይመስላል ። ይህ ከላይ የተሰጠው ፍርድ መለስ ብለን ብንቃኝ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በውስጡ ያስቀመጠችውን የእኩልነት ፣ የመፋቀር ፣ የመተሳሰብ ፡ባህሪይ እንዲጥል ያደረገው ራስ ወዳድነት በመስፈኑ ነው ። የራስ ወዳድነት ምንጩ ደግሞ ይህንን ስሜቱን የሚጠብቅለት ሰው ሰራሽ ሕግ መፈጠሩ ነው ። ሀብትን ለማንም ሳታካፍል ማከማቸት እንደምትችል እርግጠኛ ያደረገህ ማንም እንደማይወስድብህ የሚጠብቅልህ ሰው ሰራሽ ሕግ መኖሩ ነው ። ለዚያም ነው "የሰው ልጅ ለተፈጥሯዊው ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ በዓለማዊው ሕግ በከለው/corrupt አደረገው" የሚለን ላዎ-ዙ ።

📚📚📚

ምንጭ ፦ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ-ፍትህ መፅሔት ቁ.57(የተወሰደ)

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:25


መሳጭ ከሆኑ የፈላስፋው #ኮንፊሽየስ ንግግሮች በጥቂቱ...

<< የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለጸው #በተግባሩ እንጂ #በንግግሩ አይደለም። የተግባር መሰረቱ ደግሞ #ጽኑ_ፍላጎት ነው።....የአንድን ተራ ሰው ጽኑ ፍላ ፍላጎት ከውስጡ ከመውሰድ፣ የአንድን ታላቅ ሃገርን የጦር አዛዥ መማረክ ይቀላል። >>



<< ሰዎች እያወሳሰቧት እንጂ ሕይወት ቀላል ናት...ሰዎች በጨለማው ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሻማ ቢለኩሱ ለጨለማው ችግራቸው በቀላሉ መፍትሄ ያገኛሉ። >>



<< ታላቅ ሰው ችሎታውን ለማሳየት አይሽቀዳደምም...የአላዋቂን ሰው ስንፍና ልኩን የሚያውቅ አዋቂ ሰው ብቻ ነው። እናም በሌሎች ዘንድ ለመታወቅ ከመድከም ይልቅ ልታወቅ የሚገባኝ ነኝ በሚለው እምነት ውስጥ ሞልተህ ተቀመጥ። የእውቀቱ አንዱ ጥቅሙ በራስ መተማመንን ማምጣቱ ነውና።...ታላቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ታላቅነቱ ባለመታወቁ የማይናደድ ሰው እሱ በእርግጥ ታላቅ ነው። >>



<< አንድን ነገር መቼም ላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ ስታውቀው ደግሞ ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው። >>

ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ...ቅጽ ፩

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


<< ፍልስፍና በመጪው ዘመን የሰው ልጅ የሚመራባት ትሆናለች ብዬ አልገምትም፣ ለጥቂቶችና የላቀ አዕምሮ ላላቸው ግን ማረፊያ ቤተ መቅደስ እንደምትሆን አምናለሁ >>
/ አልበርት አንስታይን /

የታላቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን እይታ...#ጥበብ_ከጲላጦስ ገጽ 246 ላይ ይሄ ንግግሩ ሰፍሯል።

መፈላሰፍ የሚጀምረው እንግዲህ ከማሰብ እንዲሁም እያሰቡ መሆኑን ከማወቅ ነው። አሳቢያን ደግሞ ከሃሳቦቻቸው ጋር የሚነጋገሩ እና ከራሳቸው ጋር ተሟግተው መፍትሄ ጋር የሚደርሱ ናቸው። ፈላስፋን ከማክበር ይልቅ ሃሳቡ ከሰፊው ሕዝብ ጋር ስላልተመሳሰለ ማውገዝ በሚቀናው ማኅበረሰብ ውስጥ የፍልስፍና ህልውና የጥቂት አሳብያን ጭንቅላት ውስጥ ብቻ ይቀራል። ነብይ መሆን ሳያስፈልገው አልበርት ያህንን ቀድሞ ማወቅ ችሏል።

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


እውነት...?
(በፍልስፍና...!)

፨፨፨

ሱፊስቶች ስለ እውነት ይህንን እይታ ያስቀምጣሉ
<< እውነት የሚመጣው ከስሜት ነው። ስለዚህም የእውነት ጥያቄ ምላሹ ስሜትህ ነው።...ስለዚህም እውነት ማለት የምትቀምሰው፣ የምታሸተው፣ የምትነካው፣ የምትሰማውና የምታየው ነገር ነው። >> ይላሉ
ይህንን እይታ ካልተቀበሉት ፈላስፎች ግንባር ቀደሙ ፕሌቶ ነበር እሱም እንዲህ አለ...
<< እውነት ማለት ሱፊስቶች እንደሚሉት ስሜትህ ከሆነ እውነት የለም ማለት ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር የሚያሸተው፣ የሚነካው፣ የሚቀምሰው፣ ወዘተ...በተለያየ መንገድ ነውና። >>

፨ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች በሁለት መንገድ ከሰማው ወይም ካየው ነገሩ አንድ መሆኑ አብቅቷል፤ ስለዚህ ነገሩ በራሱ እውነት አይደለም! እያለን ነው እንግዲህ ፕሎቶ...!

<< ስለሆነም የእውነት ጥያቄ የሚመለሰው በምክንያታዊ ማሰብ(Reasoning) እንጂ በስሜት አይደለም።...አንድን ነገር ለማየት ማሰብ ያስፈልጋል። አስቀድመህ የምታስበው ነገር ወደ አይንህ መልእክት አስተላልፎ የምታየውን ማየት ቻልክ፤ በሌላ አባባል የምታየው እውነት መሆኑን በማሰብህ ነው፤ ስለዚህ እውነት ማለት 'ማሰብ' ነው ። >> ይላል ፕሉቶ



የጠርጣሪነት ፍልስፍና መስራች የሆነው #ፊሮ ደግሞ የሱፊንም ሆነ የፕሌቶን አስተሳሰብ አይቀበልም ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል...
ስለ ሱፊዎች እምነት...
<< የምታየውን እንዴት ማመን ትችላለህ?...ፀሐይ ከመሬት እጅግ ብዙ እጥፍ ግዙፍ እንደሆነች እናውቃለን። ነገር ግን መሬት ላይ ቆመን ፀሐይን ስናያት ትንሽዬ ነች። ስለዚህ የምናየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም ማለት ነው። >>
ስለ ፕሎቶ እና አርስቶትል እይታ...
<< እንግዲህ አንድን ነገር እውነት የሚያደርገው ማሰብ ስለቻልን ከሆነ፦ ሰው የሚያስብ ፍጡር ነው፤ ሶቅራጥስ ደግሞ ሰው ነው፤ ስለዚህም ሶቅራጥስ ሰው ስለሆነ ማሰብ ይችላል ማለት ነው። ይኽ ደግሞ ሁልጊዜ አይሠራም ምክንያቱም ሰው ሁሉ ማሰብ ይችላል ማለት ሞኝነት ነውና። >> ይለናል ፊሮ



ከሁሉም በተለየ መልኩ የሱፊ እምነት ተከታይ የነበረው ጎርጂያስ ደግሞ እውነትን በተናጋሪው የንግግር እና የማሳመን ችሎታ ይመነዋል ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል...
<< እውነት የሚባል ነገር የለም፤ ቢኖር እንኳን ነገሩን ነገሩን እውነት የሚያደርገው የአንተ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ እንጂ የነገሩ እውነትነት አይደለም >> ይላል ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክልበታል...
<< ምንም ነገር የለም፤ አንድ ነገር ቢኖር እንኳን መኖሩን ማወቅ አንችልም፤ ማወቅ ብንችል እንኳን ስለዚያ ነገር ማስረዳት አንችልም፤ ምክንያቱም አለ ብለን የምናስበው ነገር የለምና፤ ስለዚህም አለ ብለን ነገሩን ስላሰብን ብቻ እንዴት በድፍረት አለ ብለን እንፈርዳለን>> ይለናል...
በምሳሌ ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክላል...
<< ለምሳሌ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች እንዴት እንደሚያዩት ብትጠይቅ በጣም የተለያየ መልስ ታገኛለህ፤ ስለነገሩ አስረዱኝ ብትላቸው ደግሞ ከሁለቱ ሰዎች የአንዱ ንግግር ስለነገሩ የበለጠ ሊያሳምንህ ይችላል። ለዚህም ነው ነገሮች እውነት ናቸው ብለን እንድናምን የተሻለ ተናጋሪ ሰው መፍጠር አለብን የምንለው...>>



ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩ ( 4 በ 1)
፨ መቼም በፍልስፍናው ዓለም እውነትን በተመለከተ ዛሬም ድረስ የሚያስማማ እይታ ማግኘት አልተቻለም...በርግጥም የፍልስፍና አላማው መስማማት አይደለምና...ዛሬ ላይ #እውነትን በተመለከተ ያሉት እይታዎችም በዚህ ዙርያ የሚሽከረከሩ ይመስለኛል...
፩, እውነት አለ #ፍጹማዊም ነው
፪, እውነት አለ ግን #አንፃራዊ ነው
፫, እውነት ብሎ ነገር #የለም...!!

ከፍልስፍና ዓለም

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


እውቁ ቻይናዊ ፈላስፋ ኮንፊሽየስ እንዲህ ይለናል...

" ጥበብን ከተግባር መማር ጥሩ ነው። ነገር ግን ረጅምና መራራ ነው። ጥበብን ከሰው በመኮረጅም መማር ይቻላል። ነገር ግን ቀላልና ርካሽ ነው። ጥበብን በልቦና መርምሮ መማር ከባድ ነው። ነገር ግን ከዘዴዎች ሁሉ እጅግ የተከበረው ዘዴ ነው። "
/ ኮንፊሽየስ /

በኔ አረዳድ...
ልቦናውን መመርመር ያልቻለ ሰው ወይ ልቦናውን ደፍኖ ከተግባር መማርን ይመርጣል በዛም ረጅም እና መራራ ትግልን እና ትምህርትን ይጎነጫል አልያም በመኮረጅ እራሱን ለማስተማር ይሞክራል ግን ዘወትር ተከታይ ብቻ ይሆናል አልያም የሚከተላቸው በቀደዱለት ቦይ ብቻ የሚፈስ ውሃ ይሆናል...

እናንተስ እንዴት ተረዳችሁት...?

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ምክረ ኦሾ...

፨፨፨

<<… ስግብግብ ሀሳብ በአእምሮአችሁ ውስጥ እያለፈ ከሆነ፣ እንዲያልፍ ፍቀዱለት፤ ብስጭት እያለፈ ከሆነም ይለፍ፣ ምን የሚያገባችሁ ነገር አለ? ደግሞስ ማን ሆናችሁ ነው ጣልቃ የምትገቡት? ለምንስ ነው ከአእምሯችሁ ጋር በሀይል የምትጎዳኙት? ለምን  ' እኔ ስግብግብ ነኝ፣ እኔ ተበሳጭቻለሁ.....'  ብላችሁ ማሰብ ትጀምራላችሁ? በአእምሯችሁ ውስጥ እያለፈ ያለው አንድ የብስጭት ሀሳብ ብቻ ነው። ሀሳቡ ይለፍ፣ እናንተ ደግሞ አስተውላችሁ ተመልከቱት! >>

፨፨፨

ምንጭ ፦ " ብርሃነ ኅሊና...ገጽ 62 "
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ከአርተር ሾፐንሐወር ፍልስናዎች በጥቂቱ እንጋብዛችሁ...

( አርተር ሾፐንሐወር ሥለ ሰው ልጅ የፍላጎቱ ሎሌነት እና ሥለ ጥበብ በሰጠው ትንታኔ እንዲሁም የ #ኒርቫና እሳቤ አድናቂ እንደነበር በሱ ዙርያ የተፃፉ ጽሑፎች ያስነብቡናል )

፨ ከሚታወቁ እና ከሚደነቁለት የሱ እሳቤዎች ጥቂቶቹን ጀባ እንበላችሁ...

፩, " አጭር በሆነችው ሕይወት ውስጥ እውነት ረዥም ዕድሜና ተግባር አላት፤ ስለዚህም እውነትን ብቻ እንናገር "

፪, " ይኽ ዓለም የእኔ(የእኛ) ሀሳብ ነው። ከእኛ ውጪ ያለው ማንኛውም ነገር ሁሉ መኖሩን የምናውቀው በስሜት ሕዋሳታችንና በሐሳባችን ውስጥ በተላለፈልን መልዕክት ብቻ ነው። "

፫, " አንድን ቁስ አካል ከውጭ በምናየው ነገር ላይ ተመስርተን የተፈጥሮውን እውነታ አውቀነዋል ብንል ራሳችንን እንደማሞኘት ነው። ደረስንበት የምንለው እውነታም ከምስል እና ስም ያለፈ ነገር የለውም። በአጭሩ ነገሮችን ከውጭ ባለው ገጽታቸው በዓይናችን ስለተመለከትናቸው ወይም በእጃችን ስለነካናቸው አወቅናቸው የሚል ድፍረት ባይወጣንስ? "

፬, " አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀት እና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል።"

፭, " እብደት የሚመጣው የስቃይን ትዝታ ለመርሳት በሚደረግ ሂደት ነው፤...ፍርሃቶቻችንን እና ልማዶቻችንን መቋቋም የምንችለው በመርሳት ብቻ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ለመርሳት ደግሞ የተሻለው መንገድ እብደት ነው። ካላበድክ ክፉውን ነገር መርሳት የምትችለው ራስህን በመግደል ብቻ ነው። "

፮, "ብዙውን ጊዜ ከጥበብ የራቁ ሰዎች ምሉዕነት የሚመጣው ከገንዘብ ይመስላቸዋል። ሁሉም ነገር የተሟላለት ሰው ጥበብ ከጎደለችው እንደሱ መከራን የሚቀበል ሰው ያለ አይመስለኝም። የሕይወት መንገድ ሀብት ሳትሆን ጥበብ ነች። "

፯, " ...ፍላጎቶቻችንን ይበልጥ ባወቅናቸው ቁጥር እኛን የመቆጣጠር ብቃታቸውም እንዲሁ ይደክማል፤ ዓለምን ማሸነፍ ከውስጣዊ ማንነት ይጀምራል የምንለውም ይህንኑ እውነታ ለማሳየት ነው። "

፰," የብዙዎቹ ምሁራን ችግር የራሳቸው የአስተሳሰብ ድህነት የሚፈጥረው ነው፤ ይኽ ድህነት ደግሞ የሚመጣው የራስን ሀሳብ ጥሎ የሌሎችን ሐሳብ ለመረዳት ከሚደረግ መፍጨርጨር ይሆናል። ስለአንድ ነገር በራሳችን አእምሮ አስበን ሳይሆን ከመጽሐፍት ላይ በማንበብ እንዲገባን ለማድረግ ስንሞክር ሌላው ሰው ስለነገሩ እንዲያስብልን እንደማድረግ ሆኖ ይቆጠራል፤ በዚህም ሂደት የእሱን ሐሳብ በእኛ አዕምሮ እየደገምነው እንገኛለን ማለት ነው።..."

፱, " አንድ ሰው በማንኛውም መንገድ ለሌላው መስሎ የሚታየው ወይም ለመምሰል የሚሞክረው ነገር ሁሉ እሱ ቁምነገር አይደለም፤ማንኛችንም ብንሆን ለብቻችን ቆመን የምንታይበት ጊዜ ይመጣል፤ ጥያቄው ግን በዚያ ጊዜ ብቻውን ብቻውን ለመቆም ብቃት የሚኖረው ማን ነው? የሚለው ይሆናል። ደስታ ማለት ከራሳችን የምናገኘው እንጂ ከሌሎች የምንቀበለው አይደለም፤ የሰውን ልጅ አእምሮ የሚቀርፀውም ዓለም ሳይሆን ነገር ግን እሱ ዓለምን የሚመለከትበት ዓይን ነው። ስለዚህም በዓለም ላይ የሚኖረውና የሚሆነው ነገር ሁሉ በሰው አእምሮ ቅድሚያ የሚሆን ከሆነ እጅግ አስፈላጊው ነገር የአእምሮ እሳቤ ደረጃን በማሳደግ ይሆናል ማለት ነው። "

፲, " ያልገባህን እና ያልተረዳህውን ነገር ለማድነቅም ሆነ ለመተቸት አትቸኩል፤ ስራህን ካልተረዳ ሰው የሚሰነዘር አድናቆት ከስድብ አይሻልም። አንድ ዘፋኝ ለደንቆሮዎች በመድረክ ላይ ሲዘፍን ቆይቶ ሲወርድ ቢያጨበጭቡለት ሰደቡት እንጂ አደነቁት አይባልም። አንተም ያልተረዳህውን ነገር ስታደንቅም ሆነ ስትተች ትርጉሙ ይህ ነው። "

ምንጭ ፦ " ጥበብ ከጲላጦስ " እንዲሁም  "የፍልስፍና መንግድ "መጽሐፍት...

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ባብዛኛው ስለ #ፍላጎት እና #እውቀት በሰጣቸው ትንታኔዎች የማታወቀው ፈላስፋው አርተር ሾፐንሀወር እንዲህ ይለናል..


"ፍላጎት ማብቂያ የለውም፤ ስኬት ግን ማቆሚያ አለው"

" ለለማኝ በየእለቱ የምትሰጠውን ምፅዋት ምሳሌ አድርገህ ውሰደው...የምትሰጠው ምፅዋት የለማኙን ሕይወት ብቻ ሳይሆን እግረ መንገዱን ስቃዩንም ማራዘሚያ መንገድ መሆኑን አትዘንጋ። ለዚህም ነው ንቃተ ኅሊናችን በምኞታችን እስከተሞላች ድረስ፣ እያንዳንዱ ምኞታችንም ለተስፋና ለፍርሀት አሳልፎ እስከሰጠን ድረስ ዘላለማዊ ደስታና ሰላም የሚባሉት ጉዳዮች ከእኛ የራቁ ሆነው የምናገኛቸው...ስኬትም በራሱ እርካታ የለውም፤ የሰው ልጅ እንዲያውም የተመኘው ሲሳካለት ከስኬቱ ይልቅ ስኬቱን ለማግኘት የከፈለው መስዋዕትነት ያሳዝነዋል "

፨፨፨

፨ ብዙውን ጊዜ ፈልገን ባገኘነው ነገር ላይ እርካታችን ከቀናት ወይም ከሳምንታት በላይ የማይዘልቀው ከላይ የተነሳውን ፍልስፍና ሳናስበው እየኖርነው ሥለሆነ ይሆን...?

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ብዙዎቻችን ስንሰማው ያደግነው የአልበርት አንስታይን የንፅፅር ሕግ (Theory of Relativity)...

ብዙዎች በጊዜው በቀላሉ ሊረዱት ባለመቻላቸው በቀላል ምሳሌ እንዲህ ብሎ አስረድቷቸዋል...

" ከቆንጆ ሴት ጋር በሚያምር አትክልት ቦታ ለአንድ ሰዓት ተቀመጥ፤ አንዱ ሰዓት እንደ አንድ ደቂቃ ይሆንብሃል። በጋለ ምድጃ ላይ ደግሞ ሱሪህን አውልቀህ ለአንድ ደቂቃ ተቀመጥ፤ አንዱ ደቂቃ አንደ አንድ ሰዓት ይሆንብሀል። የንፅፅር ሕግም ይኸው ነው። "

ከፍልስፍና ዓለም

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


" ታላቅ ስልጣኔ የሚመጣው በሰው አእምሮ ውስጥ በሚገኝ ነፃነት ነው። "

/ ፍሬድሪክ ኒቼ /

ይህ ነፃነት ደግሞ ከሰው ልጅ ፍላጎት ውጪ የሚሆንበት አንዳች ምክንያት የለም...ከዚህ በተጨማሪ ሕይወትን ያለአንዳች #የሞራልና #የወግ ገደብ የሚኖራት ሰው ደስታውም እንዲሁ ሙሉ እንደሚሆንና እንዲህ ዓይነቱ ደስታ ደግሞ ለጊዜው አስደስቶ  የሚሰወር ሳይሆን በምድራዊ ሕይወት እስካለ ድረስ የሚከተል ነው ።

እያለ ያወጋናል #ኒቼ



ሞራልን እና ወግን እንደ ነፃነት ገዳቢ ማነቆ አድርጎ ይወስዳቸዋል ኒቼ ትክክል ነው ማለት ይቻል ይሆን ግን...? ከራስ ጋር መነጋገር ነው እንግዲህ...!!

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ካታርሲስ(Catharsis)

፨፨፨

የአሪስቶትል የፍልስፍና ሃሳብ ካታርሲስ /ስሜትን ማጥለል / ይባላል ። የካታሪስ ቲዎሪ ባጭሩ ሲቀመጥ ይህንን ይመስላል...

" አንድ ሰው የቅርብ የሆነ ዘመዱ ወይም ወዳጁ ሲሞት የሚያለቅሰው ለሟቹ ሰው በማዘን ሳይሆን በማዘኑና በማልቀሱ ግን ራሱ የሚያገኘው እፎይታ(relief) ስላለ ነው። በለቅሶውም የራሱ ሃጢያትና ክፋት ካሳ እንደሚያገኝለት ያምናል። "

በሌላ አገላለጽ አሪስቶትል ይህንኑ ሲያስረዳን...

"አንድ ንፁህ ሰው በሞት ሲቀጣ ብትመለከትና ብታለቅስ፤ ንፁህ ሰው ያለጥፋቱ በመሞቱ ሳይሆን ያለቀስከው ራስህን በሰውዬው ቦታ በማስቀመጥ 'እኔ በዚህ ሰው ቦታ ብሆንስ?' በሚል ስሜት ስለምትንገላታ ነው። እንግዲህ በሰው ሞት ውስጥ የራስህን ሞት ማየት ካታርሲስ ይባላል" ይለናል ።

ምንጭ ፦ "ጥበብ ከጲላጦስ"

፨ የካታርሲስ ፍልስፍና ግን ምን ያህል ቅቡል ነው በእኛ ዘንድ...?

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

12 Jul, 21:21


ፈገግ ከሚያደርጉ የዲዮጋን ምላሾች መሀከል...

🐓 የፕሌቶ ሰው ይኸውላችሁ 🐓

፨፨፨፨

ፕሌቶ እንዲህ የሚል ፍልስፍና ነበረው

"ሰው ማለት ሁለት እግር ያለው እና መብረር የማይችል እንስሳ ነው" እያለ ለተከታዮቹ(ለተማሪዎቹ) ይነግር ነበር...

ይህንን የሰማው ዲዮጋን በማግስቱ ፕሌቶ ተማሪዎቹን ወደሚያስተምርበት ቤት አንፍ #ዶሮ ይዞ በመሄድ ለተማሪዎቹ ፦

"የፕሌቶ ሰው ይኸውላችሁ!" በማለት አስቋቸዋል ።

ሌላ ፈላስፋ...

"እንቅስቃሴ የሚባል ነገር የለም"

ሲል በሰማ ጊዜም ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደቤቱ በመሄድ እንቅስቃሴ መኖሩን አሳይቶታል...!

📜

1,431

subscribers

78

photos

5

videos