MOR Large Taxpayers Office @morlargetaxpayersbranchoffice Channel on Telegram

MOR Large Taxpayers Office

@morlargetaxpayersbranchoffice


This is the official telegram channel of ministry of revenue large taxpayers branch office. Join our channel and gets up-to-date information regarding Tax affairs and tax education.

MOR Large Taxpayers Office (English)

Welcome to the MOR Large Taxpayers Office Telegram channel! Are you looking for reliable and up-to-date information on tax affairs and tax education? Look no further, as this is the official channel of the Ministry of Revenue's Large Taxpayers Branch Office. Here, you will find valuable insights, updates, and resources to help you navigate the complex world of taxation.

Who are we? We are a dedicated team of tax experts and professionals working under the Ministry of Revenue to serve large taxpayers. Whether you are an individual taxpayer or a corporation, our goal is to provide you with the support and information you need to fulfill your tax obligations and make informed decisions.

What do we offer? By joining our channel, you will have access to a wealth of information on tax laws, regulations, and best practices. Stay informed about important deadlines, changes in tax policies, and opportunities for tax savings. We also provide educational resources to help you better understand your tax responsibilities and rights.

Why should you join us? As a large taxpayer, it is crucial to stay informed and compliant with tax laws to avoid penalties and optimize your tax strategy. Our channel offers a convenient way to access reliable information and connect with tax experts who can answer your questions and address your concerns.

Don't miss out on the latest updates and insights from the Ministry of Revenue's Large Taxpayers Branch Office. Join our Telegram channel today and take control of your tax affairs with confidence!

MOR Large Taxpayers Office

12 Feb, 13:13


ታክስ ሞራል ላይ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ (05/06/2017ዓ.ም)፡- 31ኛው ዙር የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች እየተሰጠ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና ታክስ ሞራል እና ታክስ ማስታወቅና ቅጾች ላይ ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና፤ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ ታክስ ሞራል ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ከህግ ተገዥነት ወደ ተነሳሽነት ከተገዥነት ወደ ታዛዥነት በሚል ስልጠናቸው ታክስ ሞራልና ህግ ተገዥነት፣ ግብር ከፋዩ ለታክስ ህጉ ተገዥ በሚሆንባቸው ነጥቦች፣ ታክስ ሞራልና ዘመናዊ ማህበረሰብ፣ የታክስ ሞራል ምንነት፣ የታክስ ሞራል አለመኖር በሀገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፣ ታክስ ሞራልና ህግ ተገዥነትና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች ላይ ወ/ሪት ራሔል ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ታክስ ማስታወቅና ቅጾች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቅ፣ ኤክሳይዝ ታክስ ማስታወቅ፣ የሽያጭ ታክስ፣ ጽጾችና ማስታወቂያዎች፣ ኢ-ታክስ፣ ኢ-ፋይሊንግ፣ ኢ-ክፍያ፣ ኢ-ክሊራንስ ምንነት ላይ ወ/ሪት እታለማሁ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

11 Feb, 11:44


31ኛ ዙር የክፍል ሦስት ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (04/06/2017ዓ.ም)፡- 31ኛው ዙር የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ያዘጋጀው 31ኛ ዙር የክፍል ሦስት ስልጠና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች እየተሰጠ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ታክስ ስሌት ተመላሽና ሌሎች ክፍያዎች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ስለታክስ ስሌት ማስታወቅ፣ በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት፣ የስጋት የታክስ ስሌት፣ የተሻሻለ የታክስ ስሌት እንዲሁም በታክስ ህጉ መሰረት የሚደረጉ ሌሎች ማናቸውም ስሌቶች ላይ አቶ በእውቀቱ በገለጻቸው አንስተዋል፡፡
ከመቀጠር፣ ቤት ኪራይ፣ ንግድ ትርፍ ግብር፣ ኤክሳይዝ ታክስ ማምረቻ ወጪ፣ ስጋት ታክስ ስሌትና በሌሎች በግምት ግብር የሚወሰንባቸው ነጥቦች ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

10 Feb, 12:28


31ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ (03/06/2017ዓ.ም)፡- 31ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተጀመረ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 31ኛ ዙር የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ደረሰኝ እና ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የደረሰኝ አይነቶች፣ የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ፈቃድ፣ ማንዋል ደረሰኝ የሚጠቀም ታክስ ከፋይ ኃላፊነት፣ የማተሚያ ቤት ኃላፊነት፣ አዲሱ ባለ ልዩ መለያ ኮድ የታክስ ደረሰኝ ምንነት፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ምንነትና ጠቀሜታ፣ ደረሰኝን የተመለከቱ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን አቶ ሽፈራው በስልጠናቸው ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሰጣጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

10 Feb, 12:01


ማስታወቂያ ለግብር ከፋዮች በሙሉ!!
ከዚህ ቀደም ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ የካቲት 2 ቀን 2017ዓ.ም ብቻ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ ቀነ-ገደብ አዲሱን QR-Code ያለው የታክስ ደረሰኝ ቀድማችሁ የህትመት ጥያቄ በማቅረብ አሳትማችሁ በመጠቀም ላይ ያላችሁ ታክስ ከፋዮች እያመሰገንን QR-Code ያለው ታክስ ደረሰኝ ታትሞ የደረሳችሁ እና በቀጣይ የሚደርሳችሁ ታክስ ከፋዮች ደረሰኙን ከወሰዳችሁበት ቀን ጀምራችሁ አዲሱን QR-Code ያለው ደረሰኝ በመጠቀም ነባሩ ደረሰኝ እንዲወገድ ታክስ ለምትከፍሉበት ቅ/ጽ/ቤት ወይም ታክስ ማዕከል የደረሰኝ ፎርም በመሙላት ማመልከትና ማስወገድ ያለባችሁ መሆኑን እያሳሰብን፤ በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ ታክስ ከፋዮች መኖራቸውን ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ-ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑና እናሳውቃለን፡፡ ከዚህ ቀነ-ገደብ በኋላ የሚመጣን ታክስ ከፋይ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር

MOR Large Taxpayers Office

08 Feb, 05:20


ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ

ጥር 30/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ በተገለጸው መሰረት ቁጥራቸው 45,226 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸውና ይህን ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡

እንደ ሀገር በገቢው ዘርፍ የሚሰተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በውይይቱ የገለጹ ሲሆን በተለይም የማንዋል ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ስርዓትን በማሻሻል የሚፈለገውን የገቢ ዕድገት ማስመዝገብ ያሰፈልጋል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫ፡- https://shorturl.at/ZLOQR

MOR Large Taxpayers Office

31 Jan, 12:39


ማስታወቂያ
ለክፍል ሁለት ሰልጣኞች በሙሉ
የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ክፍል ሁለት ከጥር 26 እስከ 30 ቀን 2017ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰልጣኖች ሰኞ ጥር 26 ቀን 2017ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ እንድትገኙ ስንል እንገልጻለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር
የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

MOR Large Taxpayers Office

31 Jan, 10:52


44ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (23/05/2017ዓ.ም)፡- 44ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
የዛሬው ስልጠና ህግ ተገዥነት ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው 44ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በስልጠናው የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ ህግ ተገዥነት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ህግ ተገዥነት ከምን እስከ ምን ላይ ባነሱት ስልጠና ዜጎች በፈቃደኝነት ሀቀኛ ሆነው ከሚያገኙት ማንኛውም ገቢ ግብር መክፈል እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡
ግብር ከፋዮች ለህግ ተገዥ መሆን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ የታክስ ህጎችን በማክበር እንደ ሀገር የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ገለጻ አድርገዋል፡፡
የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብትና ግዴታዎች፣ የታክስ ባህሪያቶችና አይነቶች፣ ግብር ከፋዮች ለህግ ተገዥ በመሆን የታክስ ህጎችን አክብረው በሚንቀሳቀሱባቸው ነጥቦች፣ በታክስ ስርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ ህግ ተገዥነትና አስፈላጊነቱ፣ የህግ ተገዥነት ደረጃዎች ላይ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

30 Jan, 11:48


ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (22/05/2017ዓ.ም)፡- 44ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም የተሰጠ ሲሆን፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናቸው፤ ኤክሳይዝ ታክስ ሀብት ከማደላደል፣ ከህብረተሰቡ ጤና፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ያለውን ትስስርና አስፈላጊነት አንስተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ጥሬ እቃዎች፣ የሚከፈልበት ጊዜ፣ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች፣ ፈቃድ አሰጣጥና መሰረዝ፣ ቁጥጥርና ተመላሽ ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የሚመለከታቸው አስመጭዎች እና አምራቾች በሚያስመጧቸው እና በሚያመርቷቸው ዕቃዎች ላይ በሕግ በተቀመጠው አሠራር መሠረት ታክሱን የማሳወቅ እና የመክፈል ግዳታቸውን የሚወጡባቸው ነጥቦች በስልጠናው ተነስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

30 Jan, 11:40


የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ ለሚገኝ ጥቅም የሚያዝ የታክስ ሂሳብ መዝገብ
የታክስ ሂሳብ መዝገብ ማለት ሁሉንም የፋይናንስ ግብይቶችና በንዑስ ምድቦች ውስጥ የተከፋፈሉ ሁሉንም የገንዘብ ልውውጦች የሚይዝ ሆኖ ታክስ ከፋዩ የንግድ ሥራ ሀብትና ዕዳ እንዲሁም የዕለት ተዕለት ገቢውን እና ወጪውን የሚመዘግብበት መዝገብ (journal and ledger) ነው፡፡
1/ የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ ከሚገኝ ጥቅም ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት ማንኛውም ግብር ከፋይ
ሀ) የተላለፈው የካፒታል ሀብት የተገኘበትን ዋጋና ቀን፣
ለ) በሚተላለፈው የማዕድን ወይም የነዳጅ ሃብት ላይ ያለን መብት ወይም የማዕድን ወይም የነዳጅ መረጃን የሚያሳይ ሙሉ መረጃ፣
ሐ) ሃብቱን ለማሻሻል የወጣን ጨምሮ ሌላ ማንኛውም ለሃብቱ የወጣ ወጪ እና
መ) ሃብቱ በሚተላለፍበት ጊዜ ለግብር ከፋዩ የተከፈለ የማስተላለፊያ ዋጋ፣ አጠቃሎ የሚይዝ የታክስ ሂሳብ መዝገብ መያዝ አለበት፡፡
2) የካፒታል ሀብት በስጦታ፣ በእርዳታ፣ በዓይን መዋጮ ወይም በድርሻ መልክ ሲተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ ግብር የመክፈል ግዴታ የተቀባዩ ስለሆነ ይህው ስለመከናወኑ መዝገብ መያዝ አለበት፡፡
3) ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የካፒታል ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም›› ማለት በፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ አንቀጽ 59 መሰረት የካፒታል ሃብትን በሽያጭ፣ በስጦታ፣ በዓይነት መዋጮ ወይም በድርሻ መልክ ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
4) ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም የካፒታል ሃብት በዓይነት መዋጮነት ለተጠቃሚ ሲተላለፍ፣
ሀ) የተላለፈው የካፒታል ሃብት ማስተላለፊያ ዋጋ ወይም
ለ) የማስተላለፊያ ዋጋው ባልታወቀ ጊዜ ሀብቱ በተላለፈበት ወቅት የነበረው የገበያ ዋጋ የካፒታል ድርሻው ዋጋ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

29 Jan, 12:28


44ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (21/05/2017ዓ.ም)፡- 44ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 44ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅና ስረዛ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
አቶ ሽፈራው በስልጠናቸው፤ ቫት ዊዝሆልዲንግ፣ ቲኦቲና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩነትና ተመሳሳይነት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ጠቀሜታ፣ ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የቴምብር ቀረጥ በሰነዶች ላይ የሚጣል የመንግስት ገቢ ምንጪ መሆኑንና ከታክስ ፍትሃዊነት፣ የሀብት ክፍፍል ማመጣጠን ላይ ያለውን ጠቀሜታ፣ ቀረጡ በሚጣልባቸው ሰነዶች፣ ስሌቱ ምን እንደሚመስል፣ ቀረጡን አለመክፈል የሚያስከትላቸው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች እንዲሁም ሱር ታክስ ምንነትና ምጣኔ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

29 Jan, 05:24


ማስታወቂያ
ለግብር ከፋዮች በሙሉ!!
በኢ-ታክስ ግብር የማሳወቂያ ሊንክ የተቀየረ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ወደ ኢ-ታክስ ሲስተም ለመግባት የነበረው የመግቢያ ሊንክ ተቀይሮ በምትኩ etax.mor.gov.et መሆኑን እየገለጽን፤ etax.mor.gov.et/login/login 1st password- click sign in- click- ETAX service 2nd password በመጠቀም ታክሳችሁን ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም ኢ-ታክስን በተመለከተ ለሚያጋጥሙ ችግሮች በስልክ ቁጥር 0114709159 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር
የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

MOR Large Taxpayers Office

28 Jan, 12:31


44ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (20/05/2017ዓ.ም)፡- 44ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 44ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስና ተመላሽ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ተቀናሽ የሚደረጉ ታክሱ የሚጣልባቸው ግብይቶች የተከናወኑበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ፣ በጉምሩክ ዲክላራሲዮን መመዝገባቸው ተረጋግጦ ተመላሽ የሚደረጉበት አግባብ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ተቀባይነት የሌለው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ፣ የተከፈለ ታክስ ተቀናሽ የማይደረግባቸው ነጥቦች፣ የተመላሽ ስርዓቱና ተመላሽ የሚፈቀድባቸው ግብይቶችና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ለራስ የሚደረግ አቅርቦት፣ ያገለገሉ ዕቃዎች አቅርቦት፣ ውርስ የተደረገ ተቀማጭ ገንዘብ፣ የመብት፣ የምርጫና የቮውቸር አቅርቦት፣ የሠራተኛ ጥቅማ ጥቅምና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

27 Jan, 12:42


44ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ (19/05/2017ዓ.ም)፡- 44ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተጀመረ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 44ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ የተጀመረ ሲሆን፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የምዝገባ ስርዓት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምንነት እና ከታክሱ ነጻ የሆኑ አቅርቦቶች፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔዎች፣ ዜሮ ምጣኔ እና ከታክሱ ነጻ የሆኑ አቅርቦቶች፣ ታክሱ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች ስለሚከናወኑበት ቦታ፣ ጊዜና ዋጋ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Jan, 11:05


ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ ስብዕና ግንባታ ላይ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ (17/05/2017ዓ.ም)፡- ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ ስብዕና ግንባታ ላይ በገቢዎች ሚኒስቴር ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ስልጠና ተሰጧል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ድጋፍ እና ክትትል ቡድን ከተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራር የሥነ-ምግባር ቡድን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ወጣቶችን ማዕከል ባደረገው የሥብዕና ግንባታ ስልጠና፤ ዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
ዶክተር ወዳጄነህ፤ ሠራተኞች ስብዕናቸውን በመገንባት ከባቢያዊና የሥራ ደህንነት እንዲሁም ጤንነትን በመጠበቅ ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ በሚረዱ ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ጭንቀት ከአካላዊ፣ አዕምሯዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና የስሜት ጤንነት ጋር ያለው ተዛማጅነት በስልጠናው በዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ ከተዳሰሱ ነጥቦች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ፤ ለሠራተኛው በተለያዩ ጊዜያት የስብዕና ግንባታና የሥነ-ምግባር ስልጠናዎች የሚዘጋጁት ሠራተኛው ከተጣለበት ሀገራዊ ትልቅ ኃላፊነት አንጻር ስራውን በጥሩ ሥነ-ምግባር እንዲፈጽምና የመንግስትን ገቢ ለመሰብሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የገቢ ሰብሰባቢ ተቋሙ የሀገሪቱን ከፍተኛ ገቢ የሚሰበሰብ ስለሆነ ስራን በብቃት መስራትና የሥነ-ምግባር ችግሮችን መቅረፍ፣ መልካም ሥነ-ምግባር መላበስ ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ የምስጋና ሰርተፍኬት ለዶክተር ወዳጀነህ መሀረነ ተበርክቷል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Jan, 07:32


https://youtu.be/3nBoGQr5_NI

MOR Large Taxpayers Office

24 Jan, 12:32


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (16/05/2017ዓ.ም)፡- 92ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት የምዘና ፈተና ተሰጧል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

24 Jan, 12:26


93ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (16/05/2017ዓ.ም)፡- 93ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው በዛሬው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ቅድመ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ቅድመ ግብር በአንድ ግዥ ወይም ዕቃ አቅርቦት(አገልግሎት) ላይ ለሚፈጸም ክፍያ አቅራቢው ከሚከፍለው ክፍያ ቀንሶ ለገቢ ባለስልጣኑ ግብር የሚከፍልበት አግባብ ላይ አቶ በእውቀቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በአንድ ግዥ ወይም የእቃ አቅርቦት ከ10 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ክፍያ ወይም በአንድ የአገልግሎት ውል ከ3‚000 ብር በላይ ለሚፈፀም ክፍያ ለሻጩ/አቅራቢው ከሚከፈለው ክፍያ ላይ 2% ቀንሰው በመያዝ ለባለስልጣኑ ግብር የመክፈል ግደታ በሚኖርበት የቅድመ ግብር ጽንሰ ሃሳብ ላይ አቶ በእውቀቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በስልጠናው ቅደመ ግብር (ዊዝሆልዲንግ) ምንነት፣ የሚመለከታቸው ሰዎች፣ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ተዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

24 Jan, 08:19


ማስታወቂያ
ለክፍል ሁለት ሰልጣኞች በሙሉ!!
የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ከጥር 19 እስከ 23 ቀን 2017ዓ. ም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰልጣኞች ሰኞ ጥር 19 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጀመር ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት

MOR Large Taxpayers Office

23 Jan, 13:21


ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል
አዲስ አበባ (15/05/2017ዓ.ም)፡- 93ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና የንግድ ስራ ገቢ ግብር ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት በተዘጋጀው 93ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ (ሰንጠረዥ ሐ) የንግድ ስራ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የንግድ ስራ ገቢ የሚባለው ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግሎቶችን በመስጠት (መቀጠርን ሳይጨምር) የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን መሆኑንና የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርጎ የተወሰዱ ሌሎች ገቢዎች እንዲሁም ካፒታል ሀብት ጋር ያለውን ዝምድና አንስተዋል፡፡
ንግድ ስራ ገቢ ግብር ምንነት፣ ንግድ ሥራ ገቢ ማስከፈያ ምጣኔዎች ምን እንደሚመስሉ፣ በንግድ ሥራ ገቢ ግብር ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች፣ የወለድ ወጪዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

22 Jan, 12:36


93ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (14/05/2017ዓ.ም)፡- 93ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ያዘጋጀው 93ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና ያለገደብና በገደብ ከገቢ ግብረ ነፃ የተደረጉ ገቢዎች (ሰንጠረዥ ‹‹ሠ››)፣ ወጪ መጋራት፣ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር (ስልጠና ሰንጠረዥ ‹‹ለ››) ላይ ማዕከል አድርጎ ውሏል፡፡
በስልጠናው የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ በገደብ እና ያለገደብ ከገቢ ግብር ነጻ በተደረጉ ገቢዎች ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ውሎ አበል፣ ትራንስፖርት አበል፣ የሥራ ቦታና የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት አበል ከገቢ ግብር በገደብነፃ የተደረጉበትን አግባብ አንስተዋል፡፡
የህክምና ወጭ፣ የጡረታ ገቢ፣ በአለም አቀፍ ስምምነት ነፃ የተደረጉ እና ሌሎች ያለገደብ ነፃ በተደረጉት ገቢዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዑመር እንድሪስ፤ ወጪ መጋራት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ የወጪ መጋራት ውልና አፈጻጸም፣ ወለድ አከፋፈልና ምጣኔ፣ ስሌትና የአሰሪዎች ግዴታን በስልጠናቸው ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሮ ሰዊት ገዳ፤ የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ ቤት በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚጨምራቸው ገቢዎች፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዳታ የሌለበትና ያለበት ግብር ከፋይ፣ የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

18 Jan, 05:56


ማስታወቂያ
ለክፍል አንድ ሰልጣኞች በሙሉ!!
የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ከጥር 13 እስከ 16 ቀን 2017ዓ. ም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰልጣኞች ማክሰኞ ጥር 13 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጀመር ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት

MOR Large Taxpayers Office

17 Jan, 12:51


43ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (09/05/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 43ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ዛሬ በተጠናቀቀው ስልጠና፤ የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሔል ደሳለኝ፤ ህግ ተገዥነት ክፍል ሁለት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናቸው፤ ዜጎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ ግብር ለመክፈል ሙሉ ፈቃደኛ የማይሆኑባቸው ምክንያቶች ከምን የመነጩ ናቸው የሚሉ ጉዳዮችን ያነሱት ወ/ሪት ራሄል፤ ከገቢ አንጻር ትክክለኛ ግብር መክፈል የሚኖረው ሀገራዊና ግለሰባዊ ፋይዳ፣ ግብር ስወራ፣ ግብር ማጭበርበር የሚያስከትላቸው ተጠያቂነቶች፣ ግብር ሊሰወርና ሊጭበረበርባቸው የሚችሉ አጋጣሚዎችን በገለጻቸው ዳስሰዋል፡፡
ወ/ሪት ራሔል፤ ግብር ከፋዮች ከሀሰተኛ ደረሰኝ ጋር መጭበርበርን መከላከል የሚችሉባቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስና ቴምብር ቀረጥ ላይ በሰጡት ስልጠና ስለታክሶች ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ ምጣኔ፣ አስተዳደራዊ ቅጣት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

17 Jan, 11:38


92ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (09/05/2017ዓ.ም)፡- 92ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዛሬው ስልጠና ቅድመ ግብር (ዊዝሆልዲንግ) ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ቅድመ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ቅድመ ግብር በአንድ ግዥ ወይም ዕቃ አቅርቦት(አገልግሎት) ላይ ለሚፈጸም ክፍያ አቅራቢው ከሚከፍለው ክፍያ ቀንሶ ለገቢ ባለስልጣኑ ግብር የሚከፍልበትን ሂደት አቶ በእውቀቱ በገለጻቸው አንስተዋል፡፡
አንድ ግብር ከፋይ ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ሲያስገባ የዕቃዎቹን የጉምሩክ ዋጋ፣ የመድን አርቦንና የማጓጓዣያ ወጪ 3% /ሦስት በመቶ/ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር በቅድሚያ ለባለሥልጣኑ እንደሚከፍል ገለጻ ያደረጉት አቶ በእውቀቱ፤ ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል መሆኑን አንስተዋል፡፡
በአንድ ግዥ ወይም የእቃ አቅርቦት ከ10 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ክፍያ ወይም በአንድ የአገልግሎት ውል ከ3‚000 ብር በላይ ለሚፈፀም ክፍያ ለሻጩ/አቅራቢው ከሚከፈለው ክፍያ ላይ 2% ቀንሰው በመያዝ ለባለስልጣኑ ግብር የመክፈል ግደታ በሚኖርበት የቅድመ ግብር ጽንሰ ሃሳብ ላይ አቶ በእውቀቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በስልጠናው ቅደመ ግብር (ዊዝሆልዲንግ) ምንነት፣ የሚመለከታቸው ሰዎች፣ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ተዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

17 Jan, 06:08


ገቢውን ለማሳደግ በሚረዱ ነጥቦች ላይ አመራሩ ውይይት አደረገ
አዲስ አበባ (09/05/2017ዓ.ም)፡- የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ገቢ ለማሳደግ በሚረዱ ነጥቦች ላይ በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች  ውይይት አድርገዋል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ አመራርና የሥራ ሂደቶች  ባደረጉት  ውይይት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት አመት ግማሽ አመት ዕቅድ ክንውን አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን፤ የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ ለማድረግ በሚረዱ ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሙያዊ ሥነ-ምግባርና ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ባደረገው ውይይት ሥራን ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ በመስራት ኃላፊነትን መወጣትና ገቢውን ማሳካት የሁሉም ስራ ሂደቶች ኃላፊነት መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ አመላክተዋል፡፡
በቀሪ 6 ወራት እቅድ ክንውን አፈጻጸም ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ስራ ሂደቶች  አፈጻጸማቸውን ማሳደግ እንዲችሉ በተለዬ ነጥቦች ላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
በተያየዘ ዜና  ከቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር  በ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት ዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ላይ በተደረገ ውይይት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በበጀት አመቱ የያዘውን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም ሰራተኛ በቀሪ ጊዜያት ከተሰጠው ዕቅድ በላይ  መስራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት አመት ግማሽ አመት 183 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ለመሰብሰብ አቅዶ 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 94% ያሳካ ሲሆን፤  የግማሽ አመቱ  ክንውን አፈጻጸም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውና 41% በመቶኛ እድገት ማሳየቱን መዘገባችን ይታወሳል።

MOR Large Taxpayers Office

16 Jan, 13:15


እርጅና ቅናሽ ላይ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (08/05/2017ዓ.ም)፡- እየተሰጠ በሚገኘው 92ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና የቀጠለ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት እርጅና ቅናሽ እንዲሁም ከተከፋየ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማሳወቅ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ እርጅና ቅናሽ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የእርጅና ቅናሽ ስሌት ዘዴዎች ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ እና ዋጋው እየቀነሰ የሚሄዴ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ፣ የእርጅና ቅናሽ ምጣኔዎች፣ ግዙፋዊ ሀልዎት የሌላቸው የንግድ ሥራ ሀብቶች ላይ አቶ እንዳለልኝ አንስተዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተባ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሼ፤ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ቀንሶ ማሳወቅ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

16 Jan, 12:37


ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (08/05/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 43ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም የተሰጠ ሲሆን፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናቸው ኤክሳይዝ ታክስ ከቅንጦት እቃዎችና ሀብት ማደላደል፣ ጉዳት ከሚያስከትሉና ከማህበረሰቡ ጤና፣ ከገበያ ተፈላጊነታቸው ከማይቀንሱ ምርቶች እንዲሁም ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ያለው ትስስር ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የሚመለከታቸው አስመጭዎች እና አምራቾች በሚያስመጧቸው እና በሚያመርቷቸው ዕቃዎች ላይ በሕግ በተቀመጠው አሠራር መሠረት ታክሱን የማሳወቅ እና የመክፈል ግዳታቸውን የሚወጡባቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
ታክሱ የሚከፈልባቸው ጥሬ እቃዎች፣ የሚከፈልበት ጊዜ፣ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች፣ ፈቃድ አሰጣጥና መሰረዝ፣ ቁጥጥርና ተመላሽ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

16 Jan, 10:28


ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር የሚከፈልበት ስርዓት
ያልተከፋፈለ ትርፍ ማለት የድርጅቱ የሂሳብ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ባለው የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ለባለአክሲዮኖች ያልተከፋፈለ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ባቋቋመው በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የንግድ ሥራ ለሚያካሄድ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ድርጅት ያልተላከ ትርፍ ወይም የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ ያልዋለ የተጣራ ትርፍ ነው፡፡
1. ያልተከፋፈለ ትርፍ በአዋጁ አንቀጽ 61 መሰረት አስር በመቶ (10%) ግብር ይከፈልበታል፡፡
2. አንድ ድርጅት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር እንዲከፍል የማይጠየቀው ድርጅቱ በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላቱን የአክሲዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው የተጣራ ትርፍ መጠን ካሳደገ ነው፡፡ ሆኖም የተጣራው ትርፍ ያልተከፋፈለው የትርፍ ድርሻ ከፊል ከሆነ የዚህ ንዑስ አንቀጽ ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው ባልተከፋፈለው የትርፍ መጠን ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
3. ያልተከፋፈለ ትርፍ ያለው ድርጅት በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠቀሰው የ12 ወራት ጊዜ ካበቃ በኋላ ባለው 2 (ሁለት) ወር ጊዜ ውስጥ ግብሩን አስታውቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡
ማስረጃዎችን ስለማቅረብ
1. አንድ ድርጅት ያልተከፋፈለ ትርፍ የሌለው መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል ቀጥሎ የተመለከቱትን ማስረጃዎች ለባለስልጣኑ ማቅረብ አለበት፡፡
ሀ. በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ የተገኘው የተጣራ ትርፍ ለባለአክሲዮኖች የተከፋፈለ ወይም የባለአክሲዮኖችን የአክሲዮን ድርሻ መጠን ለማሳደግ የዋለ መሆኑን የሚያረጋግጡ እንደቅደም ተከተላቸው በተከፋፈለው የትርፍ ድርሻ መጠን ልክ ግብር ስለመክፈሉ ወይም የድርጅቱ ካፒታል ስለማደጉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
ለ. የአባላት የአክሲዮን ድርሻ እና የድርጅቱ ካፒታል ስለማደጉ የሚቀርቡ ማስረጃዎች እንደ አግባብነቱ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ወይም አግባብነት ባለው የክልል/ከተማ አስተዳደር ቢሮ የፀደቀ የድርጅቱ ቃለጉባኤ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ባለው አካል/ንግድ ቢሮ የድርጅቱ ካፒታል ስለማደጉ የሚገልጽ ሰነዶ፣
2. ድርጅቱ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ያገኘውን የተጣራ ትርፍ ለባለአክሲዮኖች ሳያከፋፍል የአክሲዮን ድርሻቸውን መጠን ለማሳደግ ያዋለው ከሆነ ይኸንኑ የሂሳብ ጊዜው ካበቃ በኋላ ያለው የ12 ወራት ከተጠናቀቀ በኋላ ባለው 2 (ሁለት) ወር ወይም ቀደም ብሎ ባለው ጊዜ ውስጥ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ላይ የተጠቀሱ ማስረጃዎችን በማያያዝ ለባለስልጣኑ ማስታወቅ አለበት፡፡
ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ስለተጣለው ግብር አፈጻጸም
የወጣ መመሪያ ቁጥር 7/2011

MOR Large Taxpayers Office

15 Jan, 13:51


‹‹ሁሉም ሰራተኛ ከዕቅድ በላይ መስራት ይጠበቅበታል››
አቶ ታሬሳ እንሴሱ
አዲስ አበባ (07/05/2017ዓ.ም)፡- ሁሉም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኛ ከተሰጠው ዕቅድ በላይ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሱሴ ገለጹ።
የቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት ዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ላይ ተወያይተዋል።
የቅርጫፍ ጽ/ቤቱን የ2017ዓ.ም በጀት አመት የግማሽ አመት አፈጻጸም ያቀረቡት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሱሴ፤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በግማሽ አመት የዕቅዱን 94% በመቶ ማሳካቱን ገልጸው፤ ጉድለቱን በመሙላት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በበጀት አመቱ የያዘውን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም ሰራተኛ በቀሪ ጊዜያት ከዕቅድ በላይ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በግማሽ አመቱ 183 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ለመሰብሰብ አቅዶ እንደነበርና 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር መሰብሰቡን አመልክተዋል፡፡
የግማሽ አመቱ ክንውን አፈጻጸም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውና 41% በመቶኛ እድገት ማሳየቱን ገልጸው፤ ሰራተኛው መልካም ስነ-ምግባር በመላበስ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚጠበቅበትም አቶ ታሬሳ አሳስበዋል።
የ2017 በጀት አመት ዕቅድ ለማሳካት እያንዳንዱ የስራ ክፍል ሰራተኛ የበኩሉን ኃላፈነት መወጣት እንደሚገባው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

MOR Large Taxpayers Office

10 Jan, 15:28


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (02/05/2017ዓ.ም):- 41ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ  ለሌክሰስ አዲስ ሆቴል ሰራተኞች በዛሬው ዕለት የምዘና ፈተና ተሰጧል።

MOR Large Taxpayers Office

10 Jan, 12:00


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (02/05/2017ዓ.ም)- 91ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት የምዘና ፈተና ወስደዋል

MOR Large Taxpayers Office

10 Jan, 05:28


ማስታወቂያ
ለክፍል አንድ ሰልጣኞች በሙሉ!!
የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ከጥር 05 እስከ 09 ቀን 2017ዓ. ም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰልጣኞች ሰኞ ጥር 05 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጀመር ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት

MOR Large Taxpayers Office

09 Jan, 13:36


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በግማሽ አመቱ 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ሰበሰበ
• ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል
አዲስ አበባ (01/05/2017ዓ.ም)፡- በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት ግማሽ አመት 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ አመራሮች በዛሬው ዕለት በ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት ገቢ አፈጻጸም ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት አመት ግማሽ አመት 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር መሰብሰቡን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ አመላክተዋል፡፡
በግማሽ አመቱ 183 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበርና 173 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 94% መሳካት መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
የ2017 በጀት አመት ግማሽ አመት ክንውን ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውና 41% በመቶኛ እድገት ማሳየቱም ተመላክቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን ደስ አላችሁ የኬክ ቆረሳ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

09 Jan, 07:52


የንግድ ሥራ ከተቋረጠ በኋላ በሚገኝ ገቢ ላይ የግብር ውሳኔ
የንግድ ሥራ ማቋረጥ ማለት በታክስ ከፋይነት ተመዝግቦ የንግድ ሥራ ሲሰራ የነበረና የንግድ ሥራውን ማቆሙን በጹሁፍ ለታክስ ባለስልጣኑ በማስታወቅ ከታክስ ከፋይነት የተሰረዘ ሰው ነው፡፡
ማንኛውም ታክስ ከፋይ የንግድ ሥራ ካቋረጠ በኋላ ገቢ ሊያገኝ የሚችልባቸው ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ታክስ ከፋዩ የንግድ ስራውን ካቋረጠ በኋላ የካፒታል ዕቃዎችን ጨምሮ በእጁ የሚገኙትን ያልተሸጡ ዕቃዎች በመሸጥ የሚያገኘው ገቢ፣
2. በንግድ እንቅስቃሴ ወቅት ሊሰበሰብ የማይችል ገቢ ነው ተብሎ የተሰረዘ ገቢ የንግድ ስራው ከተቋረጠ በኋላ ሲሰበሰብ
የንግድ ሥራ ከተቋረጠ በኋላ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ስለመወሰን
ሀ. ታክስ ከፋዩ የንግድ ሥራ ካቋረጠ በኋላ የሚሸጣቸው ዕቃዎች የተሸጡበትን ዋጋ ማረጋገጥ የማይቻል ከሆነ ዕቃው የተገዛበት ዋጋ ወደ ሽያጭ ዋጋ ተቀይሮ ግብሩ ይወሰናል፡፡
ለ. ታክስ ከፋዩ ዕቃውን የሸጠው የሂሳብ መዝገብ ለሚይዝ ታክስ ከፋይ ከሆነ ዕቃው የተሸጠበት ዋጋ ገዢው በሚያዘጋጀው የግዥ ማረጋገጫ ሰነድ መሰረት ይወሰናል፡፡
ሐ. የንግድ ሥራ ካቋረጠ በኋላ የንግድ ዕቃ የሚሸጥ ታክስ ከፋይ የተርን ኦቨር ታክስ ሰብስቦ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
መ. ታክስ ከፋዩ ድርጅቱን ሲዘጋ በእጁ ያሉትን ዕቃዎች ቆጥሮ ለታክስ ባለስልጣኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
ሠ. ታክስ ከፋዩ ድርጅቱን ከዘጋ በኋላ በሸጣቸው ካፒታል ዕቃዎች ላይ የሚከፈለው ግብር የካፒታል ዕቃዎቹ የመዝገብ ዋጋ (Book value) ከተሸጡበት ዋጋ ላይ ተቀንሶ በሚገኘው ልዩነት ላይ የሚሰላ ይሆናል፡፡
በተራ ቁጥር 2 መሰረት ገቢ ያገኘ ሰው የንግድ ትርፍ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
ለሚከፈለው የንግድ ሥራ ገቢ ተፈጻሚ የሚደረገው የትርፍ ህዳግ ግብር ለደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ጥቅም ላይ የሚውለው የትርፍ ህዳግ ይሆናል፡፡
የንግድ ሥራ ከተቋረጠ በኋላ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር ስለሚከፈልበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 146/2011

MOR Large Taxpayers Office

08 Jan, 05:26


የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረጉበት ሁናቴ
በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ ከተደረጉ ገቢዎች ውስጥ የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ይገኙበታል፡፡ የትራንስፖርት አበል ማለት በቀጣሪው እና በተቀጣሪው መካከል በተደረገ ውል ውስጥ በግልጽ የተመለከተ እና ተቀጣሪው ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ሥራ እንዲሁም ከስራ ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመጓጓዝ እንዲሁም ተቀጣሪው ስራውን ለማከናወን መበደኛ የስራ ቦታው በሚገኝበት ከተማ ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር የሚያስፈልገው የትራንስፖርት ወጪ ለመሸፈን በቀጣሪው የሚከፈል አበል ነው፡፡
እንዴት ነፃ ይደረጋል?
1. በስራ ባህሪው ምክንያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ (1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን፤ ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡
2. አንድ ተቀጣሪ በሥራ ባህሪው ምክንያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ (1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን፤ ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡
3. አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም ባይቀርብም ለዚህ አይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ነው፡፡
4. አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራ ቦታው እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ ለነዳጅ ወጪ በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
5. አንድ ተቀጣሪ ስራውን ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ሲንቀሳቀስ ለመጓጓዣ ወጪ የሚሰጠው ክፍያ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በስራ ላይ ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ወይም በሚያቀርበው ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከከፈለው የአየር፣ የውና እና የየብስ ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡
6. አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ስራን ለማከናወን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ እና የውል ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል መገልገያ ዕቃዎቹ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪ.ግ ሊበልጥ አይችልም፡፡
7. አንድ ግብር ከፋይ ከመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ርቀው ስራቸውን የሚያከናውኑ ሰራተኞች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ የሚያደርጉትን ጉዞ ወጪ የሚሸፍን በሚሆንበት ጊዜ የዚህ ዓይነቱ ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው የቅጥር ውል ውስጥ ቀጣሪው ይህ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሆኖም ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ የሚከፈለው ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረገው በአንድ የግብር አመት ከሁለት የደርሶ መልስ ጉዞ ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
ከግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011

MOR Large Taxpayers Office

06 Jan, 09:20


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (28/04/2017ዓ.ም):- 90ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ  ለኢትዮ-ሱዳን ጠቢብ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች በዛሬው ዕለት የምዘና ፈተና ተሰጧል።

MOR Large Taxpayers Office

03 Jan, 11:53


42ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (25/04/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 42ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ለተከታታይ አምስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ህግ ተገዥነት ፣ ሱር ታክስና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ተሰጧል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሔል ደሳለኝ፤ ህግ ተገዥነት ክፍል ሁለት ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ዜጎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ ግብር ለመክፈል ሙሉ ፈቃደኛ የማይሆኑባቸው ምክንያቶች ከምን የመነጩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ከገቢ አንጻር ትክክለኛ ግብር መክፈል የሚኖረው ሀገራዊና ግለሰባዊ ፋይዳ፣ ግብር ስወራ፣ ግብር ማጭበርበር የሚያስከትላቸው ተጠያቂነቶች፣ ግብር ሊሰወርና ሊጭበረበርባቸው የሚችሉ አጋጣሚዎችን በገለጻቸው ያነሱት ወ/ሪት ራሔል፤ ግብር ከፋዮች መጭበርበርን በምን አግባብ መከላከል እንደሚጠበቅባቸው ከሀሰተኛ ደረሰኝ ጋር የተገናኙ ነጥቦችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ጽንሰ ሃሳብ፣ የሚከፈልባቸውና ነፃ የተደረጉ የገቢ ዕቃዎች እንዲሁም ሰነዶች፣ የታክስ ስሌታቸው ገለጻ ተደርጎባቸዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

03 Jan, 11:38


ቅድመ ግብር ላይ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ (25/04/2017ዓ.ም)፡- 91ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ቅድመ ግብር (ዊዝሆልዲንግ) ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ቅድመ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በገለጻቸው ቅድመ ግብር በአንድ ግዥ ወይም ዕቃ አቅርቦት(አገልግሎት) ላይ ለሚፈጸም ክፍያ አቅራቢው ከሚከፍለው ክፍያ ቀንሶ ለገቢ ባለስልጣኑ ግብር የሚከፍልበትን ሂደት አንስተዋል፡፡
አንድ ግብር ከፋይ ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ሲያስገባ የዕቃዎቹን የጉምሩክ ዋጋ፣ የመድን አርቦንና የማጓጓዣያ ወጪ 3% /ሦስት በመቶ/ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር በቅድሚያ ለባለሥልጣኑ እንደሚከፍል ገለጻ አድርገዋል፡፡
ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል መሆኑንና በአንድ ግዥ ወይም የእቃ አቅርቦት ከ10 ሽህ ብር በላይ ለሆነ ክፍያ ወይም በአንድ የአገልግሎት ውል ከ3‚000 ብር በላይ ለሚፈፀም ክፍያ ለሻጩ/አቅራቢው ከሚከፈለው ክፍያ ላይ 2% ቀንሰው በመያዝ ለባለስልጣኑ ግብር የመክፈል ግደታ በሚኖርበት የቅድመ ግብር ጽንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በስልጠናው ቅደመ ግብር (ዊዝሆልዲንግ) ምንነት፣ የሚመለከታቸው ሰዎች፣ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ገለጻ ተደርጎባቸዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

02 Jan, 15:30


91ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (24/04/2017ዓ.ም)፡- 91ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተሰጧል።
በዛሬው ስልጠና ሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማሳወቅ ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ የታክስ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ ስለሚገኝ ጥቅም አንስተዋል፡፡
በገለጻቸው፤ የደረጃ ለውጥ ሲኖር የሚያዝ የታክስ ሂሳብ መዝገብ፣ የንግድ ዕቃ ቆጠራ፣ የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ፣ የዕዳና የተከፋይ ሂሳብ መዝገብ፣ የታክስ ሂሳብ መግለጫና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ቴክኒካል ሰርቪስ፣ ከዕድል ሙከር ከሚገኝ ገቢ፣ ከሮያሊቲ፣ ከአክሲዮን ማስተላለፍ፣ አልፎ አልፎ ሀብትን በማስተለለፍ፣ በማከራየት ከሚገኝ ገቢ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

02 Jan, 15:28


ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (24/04/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 42ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
የዛሬው ስልጠና ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማዕከል ያደረገ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በሚያስከትሉ ዋጋቸው በመጨመሩ ምክንያት ፍጆታቸው በማይቀንሱ እቃዎች ላይ የሚጣል መሆኑን አቶ በእውቀቱ በገለጻቸው አንስተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ ገቢ ከመሰብሰብ፣ የማህበረሰቡን ጤና ከመጠበቅ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ያለውን ቁርኝነትና ጠቀሜታ በገለጻቸው ያነሱት አቶ በእውቀቱ፤ የታክሱ ምጣኔ ከ5%- 100% በተሽከርካሪዎች ላይ ከ100%- 500% የሚጣልበትን ሁናቴ አስረድተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ጊዜ፣ ነፃ የተደረጉ፣ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ተመላሽ፣ ቁጥጥር በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

01 Jan, 12:36


ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (23/04/2017ዓ.ም)፡- 91ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት እየተሰጠ የሚገኘው 91ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ የንግድ ስራ ገቢ ግብር (ሰንጠረዥ ሐ) ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የንግድ ስራ ገቢ ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግልቶችን በመስጠት (መቀጠርን ሳይጨምር) የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣ የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን እና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች ላይ አቶ እንዳለልኝ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የንግድ ሥራ ገቢ የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ ከሚገኝ ጥቅም ጋር ያለውን ትስስር፣ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ምጣኔ፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች፣ የወለድ ወጪና በተቀናሽነት የሚያዘው፣ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ የእርጅና ቅናሽ አሰራርና የስሌት ዘዴዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

01 Jan, 12:17


42ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (23/04/2017ዓ.ም)፡- 42ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሲሰጥ ውሏል፡፡
የዛሬው ስልጠና ተጨማሪ እሴት ታክስ ምንነትና ትርጓሜ፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች ላይ ማዕከል ያደረገ ነው፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅና ስረዛ፣ ቫት ዊዝሆልዲንግ፣ ቲኦቲና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩነትና ተመሳሳይነት እንዲሁም ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶችን በስልጠናቸው ዳስሰዋል፡፡
በስልጠናው የታክስ ትምህርት ከፋተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምንነትና ትርጓሜ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ በፍጆታ እቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣልና የ15 እንዲሁም 0 በመቶ ምጣኔ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ታክሱ ተመላሽ የሚስተናገድበት፣ ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ፣ ታክስ ስወራና ማጭበርበርን ለመግታት የሚረዳ መሆኑን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

26 Dec, 12:47


89ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (17/04/2017ዓ.ም)፡- 89ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ያዘጋጀው 89ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ስለማስቀረት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ማንኛውም ቀጠሪ ከመቀጠር የሚገኝ ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለተቀጣሪው በሚከፍልበት ጊዜ ከ10% እስከ 35% ባለው ምጣኔ ቀንሶ በማስቀረት ለታክስ ባለሥልጣኑ ማሳወቅ እንደሚኖርበት ያነሱት ወ/ሮ ፅጌ፤ ከዕድል ሙከራ፣ ሀብትን አልፎ አልፎ በማከራየት ከሚገኝ ገቢ፣ የካፒታል ሀብቶች በማስተላለፍ ከሚገኝ ጥቅም ላይ ግብር ስለመጣል፣ ቴክኒካል ሰርቪስ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ ለሚገኝ ጥቅም፣ የደረጃ ለውጥ ሲኖር የሚያዝ የታክስ ሂሳብ መዝገብ፣ የንግድ ዕቃ ቆጠራ፣ የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ፣ የዕዳና የተከፋይ ሂሳብ መዝገብ፣ የታክስ ሂሳብ መግለጫና ሌሎች ነጥቦችን አቶ ሽፈራው በስልጠናቸው አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

26 Dec, 12:33


90ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (17/04/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮ-ሱዳን ጠቢብ ሆስፒታል ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 90ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ያዘጋጀው 90ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ለኢትዮ-ሱዳን ጠቢብ ሆስፒታል ሠራተኞች የተሰጠ ሲሆን፤ ከመቀጠር የሚገኙ የአይነት ጥቅሞች፣ ወጪ መጋራትና የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ከመቀጠር የሚገኝ የአይነት ጥቅም ገቢና ግብር የሚከፈልበትን አግባብ አንስተዋል፡፡
ከመቀጠር ጋር በተገናኘ የሚገኙ በአይነት የሚገኙ ጥቅሞች ምንነትና የታክስ ስሌታቸው እንዲሁም በመቀጠር የሚገኙና እንደ አይነት ጥቅም ተቆጥረው ታክስ የማይሰላባቸው ላይ አቶ እንዳለልኝ ሰፊ አድርገዋል፡፡
የታክስ የክፍያ ስርዓት ምንነት፣ የስሌት መሰረታቸው፣ የቅናሽ ወለድ ብድር፣ የግል ወጪዎች፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ገለጻ ከተደረገባቸው ነጥቦች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ወጪ መጋራት እና የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ቤት በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚጨምራቸው ገቢዎች፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዳታ የሌለበትና ያለበት ግብር ከፋይ፣ የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

26 Dec, 12:14


41ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (17/04/2017ዓ.ም)፡- ለሌክሰስ አዲስ ሆቴል ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 41ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም የተሰጠ ሲሆን፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ ኤክሳይዝ ታክስ የሚመለከታቸው አስመጭዎች እና አምራቾች በሚያስመጧቸው እና በሚያመርቷቸው ዕቃዎች ላይ በሕግ በተቀመጠው አሠራር መሠረት ታክሱን የማሳወቅ እና የመክፈል ግዳታቸውን የሚወጡባቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ ሀብት ከማደላደል፣ ከህብረተሰቡ ጤና፣ ከአካባቢ ጥበቃ አንጻር ያለውን ጠቀሜታ አቶ በእውቀቱ አንስተዋል፡፡ ታክሱ የሚከፈልባቸው ጥሬ እቃዎች፣ የሚከፈልበት ጊዜ፣ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች፣ ፈቃድ አሰጣጥና መሰረዝ፣ ቁጥጥርና ተመላሽ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Dec, 13:23


89ኛ ዙር ስልጠና ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል
አዲስ አበባ (16/04/2017ዓ.ም)፡- 89ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፤ ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 89ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ የንግድ ስራ ገቢ ግብር (ሰንጠረዥ ሐ) ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የንግድ ስራ ገቢ ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግልቶችን በመስጠት (መቀጠርን ሳይጨምር) የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣ የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን ላይ አቶ እንዳለልኝ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በስልጠናው የንግድ ሥራ ገቢ የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ጋር ያለውን ትስስር፣ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ምጣኔ፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች፣ የወለድ ወጪና በተቀናሽነት የሚያዘው፣ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ የእርጅና ቅናሽ አሰራርና የስሌት ዘዴዎች ተነስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Dec, 13:17


41ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (16/04/2017ዓ.ም)፡- 41ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ለሌክሰስ አዲስ ሆቴል ሠራተኞች ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 41ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅና ስረዛ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናቸው ቫት ዊዝሆልዲንግ፣ ቲኦቲና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩነትና ተመሳሳይነት፣ ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የቴምብር ቀረጥ በሰነዶች ላይ የሚጣል የመንግስት ገቢ ምንጪ መሆኑንና ከታክስ ፍትሃዊነት፣ የሀብት ክፍፍል ማመጣጠን ላይ ያለውን ጠቀሜታ፣ ቀረጡ በሚጣልባቸው ሰነዶች፣ ስሌቱ ምን እንደሚመስል፣ ቀረጡን አለመክፈል የሚያስከትላቸው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች እንዲሁም ሱር ታክስ ምንነትና ምጣኔ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

26 Nov, 11:21


39ኛ ዙር ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (17/03/2017ዓ.ም)፡- 39ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 39ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን፤ የዛሬው ስልጠና በተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስ እና ተመላሽ ላይ ተሰጧል፡፡
በስልጠናው የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስና ተመላሽ ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ተቀናሽ እንዲሆን ስለተፈቀደ የግብዓት ታክስ፣ ተቀባይነት የሌለው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ፣ በብልጫ የተከፈለን የግብዓት ታክስ ወደፊት ስለማስተላለፍ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የተከፈለ ታክስ ተቀናሽ የማይደረግባቸው ነጥቦች ያነሱ ሲሆን፤ የተመላሽ ስርዓቱና ተመላሽ የሚፈቀድባቸው ግብይቶች ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎችና አገልግሎቶች፣ በአለም አቀፍ በረራ እና ተያያዥ አገልግሎቶች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Nov, 13:34


39ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ (16/03/2017ዓ.ም)፡- 39ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተጀመረ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 39ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ዛሬ የተጀመረ ሲሆን፤ በስልጠናው የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ትርጓሜና ተጨማሪ እሴት ታክስ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ቀጥታ ያልሆነ ታክስ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ፅጌ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከአስመጪዎች ጀምሮ እስከ ጥሬ ዕቃ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች የሚሰበስቡበት አግባብ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ጠቀሜታ፣ ምጣኔ፣ ነፃ የተደረጉና ታክሱ የሚጣልባቸው አቅርቦቶች፣ ነፃ ተደርገው ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎችን በገለጻቸው አንስተዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ፣ የመመዝገብ ግዴታ፣ በፈቃደኝነት መመዝገብ፣ የምዝገባ አፈጻጸም፣ የተመዘገበ ሰው ግዴታዎች፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከጊዜ፣ ቦታ እና እሴት ጋር ያለው ትስስር ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
  

MOR Large Taxpayers Office

22 Nov, 13:12


38ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (13/03/2017ዓ.ም)፡- 38ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው 38ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና በኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማዕከል አድርጎ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በሚያስከትሉ ዋጋቸው በመጨመሩ ምክንያት ፍጆታቸው በማይቀንሱ እቃዎች ላይ የሚጣል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ ገቢ ለመሰብሰብ፣ የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ፣ ለአካባቢ ጥበቃ አስፈላጊ መሆኑን ያመለከቱት አቶ በእውቀቱ፤ የታክሱ ምጣኔ ከ5%- 100% በተሽከርካሪዎች ላይ ከ100%- 500% የሚጣልበትን ሁናቴ አንስተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ጊዜ፣ ነፃ የተደረጉ፣ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ቁጥጥር ላይ ሌሎች ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

20 Nov, 12:05


38ኛ ዙር ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (11/03/2017ዓ.ም)፡- 38ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 38ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅና ስረዛ፣ ቫት ዊዝሆልዲንግ፣ ቲኦቲና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩነትና ተመሳሳይነት፣ ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የቴምብር ቀረጥ በሰነዶች ላይ የሚጣል የመንግስት ገቢ ምንጪ መሆኑንና ከታክስ ፍትሃዊነት፣ የሀብት ክፍፍል ማመጣጠን ላይ ያለውን ጠቀሜታ፣ ቀረጡ በሚጣልባቸው ሰነዶች፣ ስሌቱ ምን እንደሚመስል፣ ቀረጡን አለመክፈል የሚያስከትላቸው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች እንዲሁም ሱር ታክስ ገለፃ የተደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

MOR Large Taxpayers Office

19 Nov, 12:22


38ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (10/03/2017ዓ.ም)፡- 38ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 38ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፤ የዛሬው ስልጠና በተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስ እና ተመላሽ ላይ ማዕከል አድርጎ ውሏል፡፡
በስልጠናው የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስና ተመላሽ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በሰጡት ገለጻ፤ ተቀናሽ የሚደረጉ ታክሱ የሚጣልባቸው ግብይቶች የተከናወኑበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ፣ በጉምሩክ ዲክላራሲዮን መመዝገባቸው ተረጋግጦ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን በስፋት ዳስሰዋል፡፡
የተከፈለ ታክስ ተቀናሽ የማይደረግባቸው ነጥቦች በስፋት ያነሱ ሲሆን፤ የተመላሽ ስርዓቱና ተመላሽ የሚፈቀድባቸው ግብይቶች ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎችና አገልግሎቶች፣ በአለም አቀፍ በረራ እና ተያያዥ አገልግሎቶች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

18 Nov, 17:46


ለግብር ከፋዮች የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተሰጠ
አዲስ አበባ (09/03/2017ዓ.ም)፡- በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት በዛሬው ዕለት ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት ዛሬ በተካሄደው የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት አሰጣጥ መርሃ ግብር ለ11 የመንግስት ለ16 የግል በድምር ለ27 የድርጅት የሥራ ኃላፊዎች የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተሰጧል፡፡
የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሸዴ፤ ለመንግስት ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፤ ለግል ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች የምስጋና ሰርተፍኬት አበርክተዋል፡፡
የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት የተሰጠው ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ ከታክስ ከፋዩ ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ፣ በታማኝነት የታክስ ግዴታቸውን በመወጣት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናና እውቅና ለመስጠት፣ በቀጣይ በታክስ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች በጋራ ተወያይቶ ለመፍታት፣ በታክስ አስተዳደሩ በተደጋጋሚ በታክስ ከፋዩ የሚነሱ ጥያቄዎች እንደ ግብዓት በመውሰድ መፍትሄ ለማፈላለግ፣ በ2017 በጀት አመት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታቀደውን ብር 342 ቢሊዮን ለመሰብሰብና የሚኒስቴሩን ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሰረት ለመጣል መሆኑ በመድረኩ ተገልዿል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

18 Nov, 12:39


38ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ (09/03/2017ዓ.ም)፡- 38ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 38ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በዛሬ ስልጠና የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ቀጥታ ያልሆነ ታክስ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ፅጌ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከአስመጪዎች ጀምሮ እስከ ጥሬ ዕቃ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች የሚሰበስቡበት አግባብ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ጠቀሜታ፣ ምጣኔ፣ ነፃ የተደረጉና ታክሱ የሚጣልባቸው አቅርቦቶች ላይ ወ/ሮ ፅጌ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ ከጊዜ፣ ቦታ እና እሴት ጋር ያለውን ትስስር አንስተዋል፡፡
ታክሱ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች የሚከናወኑበት ቦታ፣ ጊዜ እና እሴት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

18 Nov, 08:46


በመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (09/03/2017)፡- በመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማዕከል ያደረገ ስልጠና ለፌዴራል ገቢዎች እና ጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና እና ሠራተኞች በዙም እየተሰጠ የሚገኘውን ስልጠና እየተከታተሉ ነው፡፡
ስልጠናውን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ደበሌ ቀበታ አስጀምረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ-ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ስልጠናውን በዙም እየሰጡ ይገኛል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

18 Nov, 08:08


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (09/03/2017)፡- 86ኛ ዙር የክፍል አንድ የሞጁላር የታክስ ትምህርት ስልጠና ላጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የምዘና ፈተና ተሰጠ፡፡

MOR Large Taxpayers Office

15 Nov, 11:51


37ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (06/03/2017ዓ.ም)፡- ለቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 37 ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አዘጋጅነት ለቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና ህግ-ተገዥነት ክፍል ሁለት ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ ህግ- ተገዥነት ላይ በሰጡት ስልጠና ሰዎች ወደ ስራ ሲሰማሩ ታክስ/ግብር/ የማይከፍሉባቸውን ነጥቦች ያነሱ ሲሆን፤ ታክስ አለመክፈል የሚያስከትላቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ዳስሰዋል፡፡
ወ/ሪት ራሄል፤ ግብር መክፈልና የማህበረሰቡ ግንዛቤ አንድምታ፣ ግብርና የመንግስት አስተዳደር አገልግሎት ተያያዥነት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ህዝባዊ ተቆርቋሪነት እንዲሁም ልማት ከግብር ጋር ያለው ትስስር በስልጠናቸው አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

15 Nov, 11:12


29ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (06/03/2017ዓ.ም)፡- 29ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው 29ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዛሬው ስልጠና የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ በታክስ አስተዳደርና የወንጀል ቅጣቶች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የወንጀል ጥፋት በሕግ የተከለከሉ ድርጊቶች መፈጸም ወይም አድርግ የተባለውን አለማድረግ መሆኑን በገለጻቸው ያነሱት አቶ እንዳለልኝ፤ በታክስ ውሳኔ አለመግባባት ሲፈጠር በየደረጃው አቤቱታ የሚቀርብበት ሂደት ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዩን መብት እና ግዴታ፣ አስተዳደራዊ ቅጣት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሚነሳባቸውን እና የማይነሳባቸውን ነጥቦች በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

14 Nov, 13:49


በጥቅምት ወር 70 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ተሰበሰበ
አዲስ አበባ (05/03/2017ዓ.ም)፡- በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት ጥቅምት ወር ብቻ 70 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር መሰብሰቡን ገለጸ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዛሬው ዕለት የ2017 በጀት አመት ጥቅምት ወር ዕቅድ ክንውን አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ ለአመራሮችና ለሠራተኞች በቀረበው የ2017 በጀት አመት ጥቅምት ወር አፈጻጸም በጥቅምት ወር ብቻ 70 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር መሰብሰቡን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
በጥቅምት ወር 78 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው፤ 70 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 90% ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የ2017 በጀት አመት ጥቅምት ወር ክንውን ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ 17 ነጥብ 44 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውና በመቶኛ 33% በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት አመት ለመሰብሰብ ያቀደውን ለማሳካት ሁሉም ሠራተኛ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅበት አቶ ታሬሳ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የምስጋና የኬክ ቆረሳ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

14 Nov, 13:37


37ኛ ዙር ክፍል ሁለት ስልጠና ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (05/03/2016ዓ.ም)፡- ለቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 37ኛ ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት በሆኑና ማህበራዊ ጉዳት በሚያስከትሉ እንዲሁም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ የሚጣል ታክስ መሆኑን አቶ በእውቀቱ አንስተዋል፡፡
አቶ በእውቀቱ በገለጻቸው፤ ኤክሳይዝ ታክስ ገቢ ከመሰብሰብ፣ ሀብት ከማደላደል፣ ከአካባቢ ጥበቃና ከህብረተሰቡ ጤና ጋር ያለው ቁርኝት ያነሱ ሲሆን፤ የኤክሳይዝ ታክስ የዋጋ መሰረት፣ ምዝገባና ፈቃድ፣ ቁጥጥር፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

14 Nov, 13:37


29ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (05/03/2017ዓ.ም)፡- 29ኛው ዙር የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ማስታወቅና ቅጾች ላይ ስልጠና ተሰጧል፡፡
የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ የታክስ ማስታወቅና ቅጾች ላይ በሰጡት ስልጠና የታክስ ማስታወቅ አቀራረብ፣ የመክፈያ ጊዜ፣ በኤሌክትሮኒክስ የታክስ ስርዓት መጠቀም ያለው ፋይዳ፣ በወቅቱ አለማሳወቅ የሚያስከትለው ተጠያቂነትን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

13 Nov, 13:04


37ኛ ዙር የክፍል ሁለት ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (04/03/2017ዓ.ም)፡- 37ኛው ዙር የክፍል ሁለት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ለቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ሠራተኞች ሲሰጥ ውሏል፡፡
በዛሬው ስልጠና ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቴምብር ቀረጥና ሱር ታክስ ላይ ማዕከል አድርጎ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅና ስረዛ፣ ቫት ዊዝሆልዲንግ፣ ቲኦቲና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልዩነትና ተመሳሳይነት እንዲሁም ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ሱር ታክስ እና ቴምብር ቀረጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የቴምብር ቀረጥ በሰነዶች ላይ የሚጣል የመንግስት ገቢ ምንጪ መሆኑንና ከታክስ ፍትሃዊነት፣ የሀብት ክፍፍል ማመጣጠን ላይ ያለውን ጠቀሜታ፣ ቀረጡ በሚጣልባቸው ሰነዶች፣ ስሌቱ ምን እንደሚመስል፣ ቀረጡን አለመክፈል የሚያስከትላቸው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች እንዲሁም ሱር ታክስ ገለፃ የተደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

MOR Large Taxpayers Office

13 Nov, 13:02


29ኛ ዙር የክፍል ሶስት ስልጠና ታክስ ስሌት፣ ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ ሲሰጥ ውሏል
አዲስ አበባ (04/03/2017ዓ.ም)፡- 29ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና ታክስ ስሌት፣ ሌሎች ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ በታክስ ስሌት፣ ሌሎች ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ በሰጡት ስልጠና ትክክለኛ ገቢን በታክስ ስሌት መሠረት አስልቶ ታክስ መክፈል አስፈላጊነት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አቶ በእውቀቱ ትክክለኛ ገቢን በታክስ ስሌት መሠረት ለማስላት ስለታክስ ስሌት፤ ስለታክስ ስሌት ማስታወቂያ፣ በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት፣ የስጋት የታክስ ስሌት፣ የተሻሻለ የታክስ ስሌት፣ አስተዳደራዊ የታክስ ቅጣት ወይም ወለድ ስሌት ወይም በታክስ ሕግ መሠረት የሚደረግ ሌላ ማንኛውም ስሌት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ማሻሻል፣ የሠንጠረዥ “ሀ”፣ “ለ”፣ እና “መ” ገቢ እንዲሁም ከመቀጠር የሚገኝ መደበኛ ገቢን በግምት ስለመወሰን እንዲሁም፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ግብዓት ማቀናነስ፣ ለኤክሳይዝ ታክስ መሠረት የሚሆነውን የማምረቻ ወጪ መወሰን፣ በአማካይ የቀን ገቢ ግምት የግብር ከፋዮች ግዴታና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

07 Nov, 12:15


ቅድመ ግብር ላይ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (28/02/2017ዓ.ም)፡- ለፀደይ ባንክ ሠራተኞች እየተሰጠ በሚገኘው 87ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ቅድመ ግብር እና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ቅድመ ግብር/ዊዝሆልዲንግ/ ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ ቅድመ ግብር ለመንግስት ሜጋ ፕሮጀክቶች የሚኖረውን የጎላ ፋይዳን አንስተዋል፡፡
አቶ በእውቀቱ የቅድመ ግብር አስፈላጊነት፣ ከቅድመ ግብር ነፃ የተደረጉ ግዣዎችን ያነሱት አቶ በእውቀቱ፤ ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ወደ ሀገር ሲገቡ የዕቃዎቹን የጉምሩክ ዋጋ፣ የመድን አርቦንና የማጓጓዣያ ወጪ ክፍያን እንዲሁም የሚከካሱበት አግባብ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በስልጠናው ቅድመ ግብር ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከዲፕሎማቲክና አለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ያለው ትስስር፣ ግብሩን ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ማንነት፣ የቅድመ ግብር ምጣኔ፣ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች ተዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ግብር ቀንሶ ማስቀረት፣ ከራስ ገቢ፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆኑ ሰዎች ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብርን ቀንሶ ማስቀረት፣ ሮያሊቲ፣ ቴክኒካል ሰርቪስ፣ እድል ሙከራ፣ ወለድና ተያያዥ ነጥቦች በስልጠናው ተነስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

07 Nov, 12:09


86ኛ ዙር የክፍል አንድ ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (28/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች 86ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 86ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም ተሰጧል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ በዛሬው ስልጠና ህግ ተገዥነት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ወ/ሪት ራሄል፤ ግብር ከፋዮች ለታክስ ህግ ተገዥ በመሆን የታክስ ህጎችን አክብረው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውና ታክስ መክፈል በሚገባቸው ነጥቦች ዙሪያ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡
ህግ ተገዥነት ማለት ከታክስ ህግ እንዲሁም ከታክስ ከፋይነት አንጻር ያለው ትርጓሜ ላይ ገለጻ ገለጻ ያደረጉት ወ/ሪት ራሄል፤ ግብርና ጥንታዊት ኢትዮጵያ፣ የታክስ አይነቶች፣ የታክስ ባህሪያቶች፣ የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብትና ግዴታዎች፣ የህግ ተገዥነት ምንነትና አስፈላጊነት፣ የህግ ተገዥነት ደረጃዎችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ለሁሉም የግብር ሠንጠረዦችና የግብር ዓይነቶች ተፈጻሚነት ስለሚኖራቸው የወል ድንጋጌዎች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ሃብስ ስለማግኘት፣ ሃብትን ስለማስተላለፍ፣ ሀብትን በማስተላለፍ ስለሚገኝ ገቢ፣ ለሀብት የሚደረግ ወጪ፣ ጥቅምን ወይም ኪሳራን ማስተላለፍ፣ ከግብር ለመሸሽ ስለሚደረግ ጥረትና ዕቅዶች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

07 Nov, 11:53


28ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (28/02/2017ዓ.ም)፡- 28ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተጠናቋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው 28ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዛሬው ስልጠና የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ታክስ ማስታወቅና ቅጾች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በከፋዩ ተቀንሶ የሚያዝን ታክስ በሚመለከት የሚቀርብ የታክስ ማስታወቂያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ፣ የኤክሳይዝ ታክስ፣ የሽያጭ ታክስ ማስታወቂያ እንዲሁም ቅጾች ላይ ወ/ሪት እታለማሁ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ በታክስ አስተዳደርና የወንጀል ቅጣቶች ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ አስተዳደራዊ ጥፋቶችን አንስተዋል፡፡
የወንጀል ጥፋት በሕግ የተከለከሉ ድርጊቶች መፈጸም ወይም አድርግ የተባለውን አለማድረግ መሆኑን በገለጻቸው ያነሱት አቶ እንዳለልኝ፤ በታክስ ውሳኔ አለመግባባት ሲፈጠር በየደረጃው አቤቱታ የሚቀርብበት ሂደት ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዩን መብት እና ግዴታ፣ አስተዳደራዊ ቅጣት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሚነሳባቸውን እና የማይነሳባቸውን ነጥቦች በስልጠናው ተነስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

05 Nov, 13:36


87ኛ ዙር ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (26/02/2017ዓ.ም)፡- ለፀደይ ባንክ ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 87ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ከገቢ ግብር ነፃ በተደረጉ ገቢዎች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
አቶ ሽፈራው ሠንጠረዥ (ሠ) ከገቢ ግብር ነፃ ባደረጋቸው ገቢዎች ላይ በሰጡት ስልጠና ያለገደብ በታክስ ህጉ ነፃ የተደረጉ ገቢዎች የሠራተኛ የህክምና ወጭ፣ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች፣ በተመረጡ ሴክተሮች የሠራተኛ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት፣ የመንግስታት ስምምነቶች ሌሎችን አንስተዋል፡፡
በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች ትራንስፖርት አበል፣ ውሎ አበል፣ የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት አበል፣ የሥራ ቦታ አስቸጋሪነት አበልና ሌሎች በገደብ ነፃ የተደረጉት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ወጪ መጋራት ላይ እና ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የወጪ መጋራት ክፍያ ምንነት፣ ማስከፈያ ምጣኔ፣ ተፈጻሚነትና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች እንዲሁም ሠንጠረዥ ‹‹ለ›› የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

05 Nov, 13:36


86ኛ ዙር ስልጠና ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል
አዲስ አበባ (28/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 86ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሥራ ገቢ የሚወሰነው በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሰረት በሚዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም የገቢ መግለጫ መሆኑን አቶ እንዳለልኝ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ድርጅቶች 30 በመቶ ግለሰብ ግብር ከፋዮች በተቀመጡ የግብር ምጣኔዎች መሰረት ግብር የሚከፍሉበት አግባብን በገለጻቸው አንስተዋል፡፡
ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጭዎች፣ በታክስ ህጉ የተፈቀደ ተቀናሽ ወጭዎች፣ የወለድ ወጪ፣ ለበጎ አድራጎት አላማ የተደረገ ስጦታ፣ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ የእርጅና ቅናሾችና የስሌት ዘዴዎች እንዲሁም ምጣኔዎችን በስልጠናው ተዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

05 Nov, 11:32


28ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (26/02/2017ዓ.ም)፡- 28ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛና ክሊራንስ ላይ ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው 28ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ስለታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስለታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ማሳወቅና ስረዛ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ለታክስ ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች፣ ለታክስ ከፋይነት ለመመዝገብ መሟለት ያለበት ቅድመ ሁኔታ፣ ምዝገባን መሰረዝ፣ ታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥና አጠቃቀም፣ ለውጦችን ማሳወቅና ክሊራንስ በስልጠናቸው የተዳሰሱ ነጥቦች ናቸው፡፡

MOR Large Taxpayers Office

01 Nov, 13:33


ለክፍል ሦስት ሰልጣኞች!!
የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017ዓ.ም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ግብር ከፋዮች ሰኞ ማለትም ጥቅምት 25 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጀመር ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት

MOR Large Taxpayers Office

01 Nov, 13:01


85ኛ ዙር የክፍል አንድ ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (22/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 85ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው 85ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ በሰጡት ስልጠና ከሮያሊቲ ከሚገኙ ገቢዎች ታክስ ማስከፈል፣ ትርፍ ክፍፍል ላይ ታክስ ማስከፈል፣ ከወለድ፣ ከዕድል ሙከራ ከሚገኝ ገቢ ታክስ ማስከፈል፣ ከቴክኒካል ሰርቪስ፣ ቤትና መሬት በማከራየት ታክስ ቀንሶ ማስቀረት ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ምጣኔያቸውን አንስተዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ለሁሉም የግብር ሠንጠረዦችና የግብር ዓይነቶች ላይ ተፈጻሚነት ስለሚኖራቸው የወል ድንጋጌዎች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ሃብስ ስለማግኘት፣ ሃብትን ስለማስተላለፍ፣ ሀብትን በማስተላለፍ ስለሚገኝ ገቢ፣ ለሀብት የሚደረግ ወጪ፣ ጥቅምን ወይም ኪሳራን ማስተላለፍ፣ ከግብር ለመሸሽ ስለሚደረግ ጥረትና ዕቅዶች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

31 Oct, 14:30


27ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (21/02/2017ዓ.ም)፡- 27ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት 27ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ታክስ ማስታወቅና ታክስ መክፈያ ጊዜ፣ ታክስን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ማስታወቅ፣ በታክስ ህግ መሰረት በወቅቱ አለማሳወቅ የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ታክስ አስተዳደርና የወንጀል ቅጣቶች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

31 Oct, 14:11


85ኛ ዙር ክፍል አንድ ስልጠና ተሰጧል
አዲስ አበባ (21/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 85ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና ቅድመ ግብር እና ህግ ተገዥነት ላይ ተሰጧል፡፡
የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ ቅድመ ግብር በንግድ ልውውጥ ወቅት ንግድ ፈቃድ ላቀረቡ አቅራቢዎች ብር 10 ሺህ ጀምሮ ለዕቃዎች ከብር 3 ሺህ ጀምሮ አገልግሎቶች ላይ የሚሰበሰብ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መንግስት ቅድመ ግብር በቅድሚያ መሰብሰብ የሚፈልግባቸውን ነጥቦችን ያነሱት አቶ በእውቀቱ የቅድመ ግብር አስፈላጊነት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አቶ በእውቀቱ ቅድመ ግብር ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች፣ ግብሩን ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተጣለባቸውን ሰዎች ማንነት፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች በስልጠናው ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ ህግ ተገዥነት ላይ በሰጡት ስልጠና፤ የዜጎች ታክስ የመክፈል ባህል አነስተኛ መሆን የሚያስከትላቸው ችግሮችን፣ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህል ማደግ ከሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ጋር ያለውን ጠቀሜታ አንስተዋል፡፡
ግብር ከፋዮች ለታክስ ህግ ተገዥ በመሆን የታክስ ህጎችን አክብረው በመንቀሳቀስ ታክስ መክፈል እንደሚኖርባቸውና ያነሱት ወ/ሪት ራሄል፤ ግብርና ጥንታዊት ኢትዮጵያ፣ የታክስ ባህሪያቶች፣ የታክስ አይነቶች፣ የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብትና ግዴታዎች፣ የህግ ተገዥነት ምንነትና አስፈላጊነት፣ የህግ ተገዥነት ደረጃዎችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

30 Oct, 12:45


85ኛ ዙር ስልጠና ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ላይ ተሰጧል
አዲስ አበባ (20/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 85ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬም ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ ሐ) ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሥራ ገቢ የሚወሰነው በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሰረት በሚዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም የገቢ መግለጫ መሆኑን ያነሱት አቶ እንዳለልኝ፤ ድርጅቶች 30 በመቶ ግለሰብ ግብር ከፋዮች በተቀመጡ የግብር ምጣኔዎች መሰረት ግብር የሚከፍሉበትን አግባብ አንስተዋል፡፡
አቶ እንዳለልኝ በስልጠናቸው፤ ንግድ ሥራ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ፣ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጭዎች፣ በታክስ ህጉ የተፈቀደ ተቀናሽ ወጭዎች፣ የወለድ ወጪ፣ ለበጎ አድራጎት አላማ የተደረገ ስጦታ፣ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ የእርጅና ቅናሾችና የስሌት ዘዴዎች እንዲሁም ምጣኔዎችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

30 Oct, 12:42


በታክስ ስሌት፣ ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ (20/02/2017ዓ.ም)፡- እየተሰጠ የሚገኘው 27ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ በዛሬው ስልጠና ታክስ ስሌት፣ ሌሎች ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባዘጋጀው ስልጠና የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ በእውቀቱ ዳኛቸው፤ በታክስ ስሌት፣ ሌሎች ክፍያዎች እና ተመላሽ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
አቶ በእውቀቱ በስልጠናቸው፤ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ማሻሻል፣ በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት፣ የስጋት የታክስ ስሌት፣ የሠንጠረዥ “ሀ”፣ “ለ”፣ እና “መ” ገቢ እንዲሁም ከመቀጠር የሚገኝ መደበኛ ገቢን በግምት ስለመወሰን የገለጹ ሲሆን፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ግብዓት ማቀናነስ፣ ለኤክሳይዝ ታክስ መሠረት የሚሆነውን የማምረቻ ወጪ መወሰን፣ በአማካይ የቀን ገቢ ግምት የግብር ከፋዮች ግዴታና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን ዳስሰዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Oct, 14:38


ክፍል አንድ ህግ ተገዥነት

MOR Large Taxpayers Office

25 Oct, 11:58


የምዘና ፈተና ተሰጠ
አዲስ አበባ (15/02/2017ዓ.ም)፡- 81ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት የምዘና ፈተና ተሰጧል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

25 Oct, 11:39


ማስታወቂያ
ለክፍል ሦስት ሰልጣኞች!!
የክፍል ሦስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ከጥቅምት 18 እስከ 22 ቀን 2017ዓ.ም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ግብር ከፋዮች ሰኞ ማለትም ጥቅምት 18 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጀመር ሙለጌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት

MOR Large Taxpayers Office

25 Oct, 11:29


84ኛ ዙር የክፍል አንድ ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ (15/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 84ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው 84ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ወ/ሪት ራሄል ደሳለኝ፤ ህግ ተገዥነት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ወ/ሪት ራሄል፤ ግብር ከፋዮች ለታክስ ህግ ተገዥ በመሆን የታክስ ህጎችን አክብረው በመንቀሳቀስ ታክስ መክፈል በሚገባቸው ነጥቦች ዙሪያ ያነሱ ሲሆን፤ ህግ ተገዥነት ማለት ከታክስ ህግ እንዲሁም ከታክስ ከፋይነት አንጻር ያለው ትርጓሜ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በገለጻቸው፤ ግብርና ጥንታዊት ኢትዮጵያ፣ የታክስ አይነቶች፣ የታክስ ባህሪያቶች፣ የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብትና ግዴታዎች፣ የህግ ተገዥነት ምንነትና አስፈላጊነት፣ የህግ ተገዥነት ደረጃዎችን ዳስሰዋል፡፡
የታክስ ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ እንዳለልኝ አሥራት፤ ለሁሉም የግብር ሠንጠረዦችና የግብር ዓይነቶች ተፈጻሚነት ስለሚኖራቸው የወል ድንጋጌዎች ላይ በሰጡት ስልጠና፤ ሃብስ ስለማግኘት፣ ሃብትን ስለማስተላለፍ፣ ሀብትን በማስተላለፍ ስለሚገኝ ገቢ፣ ለሀብት የሚደረግ ወጪ፣ ጥቅምን ወይም ኪሳራን ማስተላለፍ፣ ከግብር ለመሸሽ ስለሚደረግ ጥረትና ዕቅዶች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

24 Oct, 08:20


ለግብር ከፋዮች የሻይ ቡና መስተንግዶ እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ (14/02/2017ዓ.ም)፡- በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች ከጥቅምት 01 ቀን 2017ዓ.ም የጀመረ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017ዓ.ም የሚቆይ የሻይ ቡና መስተንግዶ እየተደረገ ነው፡፡
የ2016 በጀት አመት ሂሳብ መዝጊያቸው ሰኔ 30 የሆነ ግብር ከፋዮች አመታዊ የንግድ ትርፍ ግብር እያሳወቁ ሲሆን፤ የማሳወቂያ ጊዜው ጥቅምት 30 ቀን 2017ዓ.ም ስለሚጠናቀቅ ውድ ግብር ከፋዮች በቀሩት አጭር ጊዜያት ግብራችሁን በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

22 Oct, 13:18


84ኛ ዙር የክፍል አንድ ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (12/02/2017ዓ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እየተሰጠ የሚገኘው 84ኛ ዙር የክፍል አንድ የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ተሰጧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና፤ የታክስ ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ሽፈራው ማሞ፤ ከገቢ ግብር ነፃ በተደረጉ ገቢዎች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ሠንጠረዥ (ሠ) ከገቢ ግብር ነፃ በተደረጉ ገቢዎች ላይ በተሰጠው ስልጠና፤ ያለገደብ በታክስ ህጉ ነፃ የተደረጉ ገቢዎች እንደ የህክምና ወጭ፣ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች፣ የመንግስታት ስምምነቶች እና ሌሎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች ትራንስፖርት አበል፣ ውሎ አበል፣ የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት አበል፣ የሥራ ቦታ አስቸጋሪነት አበልና ሌሎችን አንስተዋል፡፡
የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት መሪ ባለሙያ ወ/ሪት እታለማሁ ተስፋዬ፤ ወጪ መጋራት ላይ በሰጡት ስልጠና የወጪ መጋራት ምንነት፣ ማስከፈያ ምጣኔ፣ ተፈጻሚነት ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም ሠንጠረዥ ‹‹ለ›› የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

MOR Large Taxpayers Office

22 Oct, 12:31


26ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ (12/02/2017ዓ.ም)፡- 26ኛ ዙር የክፍል ሶስት የታክስ ትምህርት የሞጁላር ስልጠና ሲሰጥ ውሏል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ያዘጋጀው 26ኛ ዙር ክፍል ሦስት ስልጠና የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛና ክሊራንስ ላይ ተሰጧል፡፡
የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ፅጌ ደምሴ፤ ለታክስ ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች፣ ለታክስ ከፋይነት ለመመዝገብ መሟለት ያለበት ቅድመ ሁኔታ፣ ምዝገባን መሰረዝ፣ ታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥና አጠቃቀም፣ ለውጦችን ማሳወቅና ክሊራንስ ላይ በስልጠናቸው ገለጻ አድርገዋል፡፡