Addis Ababa City Manager Office @aacitymanager Channel on Telegram

Addis Ababa City Manager Office

@aacitymanager


Addis Ababa City Manager Office (English)

Are you looking for reliable information and updates on all things related to Addis Ababa City? Look no further than the Addis Ababa City Manager Office Telegram channel! This channel, with the username @aacitymanager, is dedicated to providing residents and visitors of Addis Ababa with important news, announcements, and resources from the City Manager's Office. Whether you are interested in upcoming events, city development projects, or community initiatives, this channel has got you covered. Stay informed and connected with the latest updates and initiatives from the heart of Addis Ababa. Join us today to be a part of the conversation and stay up-to-date on everything happening in the vibrant city of Addis Ababa!

Addis Ababa City Manager Office

24 Jan, 13:27


በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Addis Ababa City Manager Office

24 Jan, 06:20


ካዛንቺስ አያት የመኖሪያ መንደር በውስጥ:-
- 13,752 የመኖሪያ ቤቶች
- ደረጃውን የጠበቀ ሞል
- የንግድ ሱቆች
- አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
- የጤና ማዕከል
- አራት መዋለ ሕፃናት
- ሁለት የመጫወቻ ቦታዎች
- የህዝብ ፕላዛ
- አረንጓዴ ቦታዎች
- 12,000 ተሽከርካሪ የሚያቆሙ ቤዝመንት ፓርኪንግ
- ለእግረኛ እና ለብስክሌት ተጠቃሚዎች ምቹ የሆኑ መንገዶች ያካተተ ነው::

Addis Ababa City Manager Office

23 Jan, 06:25


የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለህዝቡ በሚገባ በማስተዋወቅ የአገልግሎት እርካታ ለማሳደግ የሚያግዝ የተግባቦት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አስታወቀ።
ጽ/ ቤቱ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ ለኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎቾ እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት " የተግባቦት ክህሎት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በስልጠናው ላይ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ባስተላለፉት መልእክት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ፣ በቴክኖሎጅ የተደገፈ አለምዓቀፋዊነትን የሚመጥን፣ አሰራሩን በማዘመን ላይ እንዳለ ገልፀው እነነዚህን ተግባራት በውጤታማነት ማከናወን የተቻለው ለህዝቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማድረስ በሂደቱ ተሳታፊ እንዲሆን በመደረጉ ነው ብለዋል።
አቶ ተፈራ ሞላ አክለውም መዲናችን በአሁኑ ወቅት ጽዱ፣ውብ እና ለኑሮ ምቹ እየሆነች ከጊዜ ወደ ጊዜ መምጣቷን ገልፀው የዘረጋቻቸው መሠረተ ልማቶች እንዲጠበቁ እና የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዋ አገልግሎቶችም የተሳለጡ በማድረግ ረገድ ለህብረተሰቡ መረጃን በፍጥነት፣ በጥራት ፣በእውቀትና በእምነት ላይ ተመሰርቶ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

21 Jan, 13:18


የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2016ዓ.ም የተሰጡ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ጤናማነት እንዲሁም የተሰራጩ ሰርተፍኬት እና ካርዶች በአግባቡ ስራ ላይ ስለመዋላቸው ኦዲት ማድረጉን አስታወቀ።
ዛሬ ጥር 13 የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ካቀዳቸው የፈፀማቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ለሚድያ አካላት ማብራርያ ሰጥተዋል።
የሲቪል ምዝገባን በተመለከተ:
***
* በስድስት ወራት ውስጥ በከተማው ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ የታቀደ ሲሆን 41,183 (109%) መመዝገብ ተችሏል። ይህም በከተማው ምዝገባ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። ከ2016ዓ.ም አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 103% ብልጫ አሳይቷል። በዘገየ እና የግዜ ገደቡ ያለፈበት ወይም እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያሉ ህፃናት ለመመዝገብ የታቀደው 201,761 ሲሆን 195,402 (96.85) መመዝገብ ተችሏል። ለዚህ አፈፃፀም መሻሻል በጤና ተቋማት የተዘርጋው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ትልቁን ስፍራ ይይዛል።
* ከተከሰተው ጋብቻ 21,674 ለመመዝገብ ታቅዶ 15,574 (72.65%) ምዝገባ ማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7% የምዝገባ ቅናሽ አሳይቷል።
* ከተከሰተው ፍቺ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 (77.34%) ምዝገባ ማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33.99% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።
* ከተከሰተው ሞት 15,716 ለመመዝገብ ታቅዶ 11,376 (72.38%) ምዝገባ በማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 29.83% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።
የነዋሪነት ምዘገባን በተመለከተ:
***
* ወደ ዲጂታል ምዝገባ ያልተቀላቀሉ 339,876 ነዋሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 340,45 (100%) መመዝገብ የተቻለ ሲሆን ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9.17% ብልጫ አሳይቷል። ከዚህ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያ ለመስጠት የታቀደው 370,908 ሲሆን 268,470 ( 72.38%) ማሳካት ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 26.72% ቅናሽ አሳይቷል። ከተሰጡት የነዋሪነት መታወቂያ 99.84 % የሚሆነው ዲጂታል ሲሆን ቀሪው በቤት ለቤት የተሰጠ የማንዋል አገልግሎት ነው።
* ተቋሙ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶችን ችግር የፈታ ሲሆን 25,581 የክልል መሸኛዎች ትክክለኛነት እንዲጣራ ለክልሎች መላኩን የገለፀ ሲሆን አገልግሎት ለማግኘት ሪፖርት ያደረጉ 9,504 አመልካቾችን መሸኛ መርምሮ የነዋሪነት ምዘገባ አድርገው አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
የፋይዳ ምዝገባን በተመለከተ:
***
* በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የፋይዳ ምዝገባን ከብሄራዊ መያወቂያ ጽ/ቤት ጋራ በጋራ ለመምራት በተደረገው ጥረት ላለፉት ሁለት ወራት 1.8ሚልዮን ነዋሪዎችን መመዝገብ ተችሏል።
* በቀጣይ በሚቀመጥ የግዜ ገደብ ቀሪ ያለተመዘገቡ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባም ከልደት ምዝገባ ባሻገር የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅ እንዲሆን ተወስኗል።
ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የተወሰዱ እርምጃን በተመለከተ:
****
* በስድስት ወራቱ በቀላል 25 እና በከባድ 37 በድምሩ 71 ሰራተኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰራተኞች አገልግሎት በገንዘብ በመሸጥ 1 ሰራተኛ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በጠቅላላ 9 ሰራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው ከስራ ታግደው በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛሉ።
* 28 ባለጉዳዮች በወረዳ እና በዋና መስርያ ቤት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው በመቅረብ ለህግ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በድምሩ 110 ሰራተኞች እና ተገልጋዮች በአስተዳደራዊ እና በወንጀል በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
የኦዲት እርምጃን በተመለከተ:
***
* በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ዋና መስርያ ቤትን ጨምሮ 11 ክ/ከተማ እና 27 የወረዳ ጽ/ቤቶች በ2016ዓ.ም የተሰጡ አገልግሎቶች እና ለአገልግሎት መስጫ ስራ ላይ የዋሉ ህትመቶች ኦዲት ተደርጓል።
* በዚሁ መሰረት በተሰጠው አገልግሎት ላይ የተሰራጩ የካርድ ፣ የሰርተፍኬት እና የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባለ መከተል፣ አሰራርን በመጣስ ፣ ጉድለት በመፍጠር፣ ስራን በአግባቡ ባለመምራት እና ጉድለት በመፍጠር በስድስቱ ክ/ከተሞች ጉድለት የተገኘ ሲሆን በዚህም 33 ሰራተኞች ተጠያቂነት ያረፈባቸው ሲሆን 19 በወንጀል ፣ 24 በአስተዳደራዊ እንዲሁም አንድ አመራር ስራን በአግባቡ ባለማምራት በሃላፊነት እንዲጠየቁ መወሰኑን ዋና ዳይሬክተሩ በማብራርያቸው ገልፀዋል።
አቶ ዮናስ በሚሰጡ አገልግሎቶች ውስጥ በቅንነት እና በታማኝነት የሚያገልግሉ ህብረተሰቡም እውቅና የሚሰጣቸውና ጤናማ ያልሆነ ነገር ሲያዩ ለተቋም በመወገን ሌብነትን የሚያጋልጡ ሰራተኞችን እውቅና የሚሰጥበት 2ኛው የሰራተኛ እውቅና መርሃ ግብር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሃላፊው በተቋም ግንባታ ሂደት የመጡ ለውጦችን በማስቀጠል የተሻለ ተቋም ለመፍጠር ስራዎች መቀጠላቸውን የገለፁ ሲሆን የቅሬታ አፈታት እና የስታንዳርድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩና በከፋ ሁኔታ የገጠመውንም የሲስተም ችግር ለመፍታት በቤት ስራነት እንደተያዘ ጠቁመዋል።
ለበለጠ መረጃ፣ በነፃ መስመርጠ7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

21 Jan, 05:42


ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን በሰላም መጠናቀቁን ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ጨምሮ ገልጿል።
በመሆኑንም በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት እና ለበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የፀጥታ ተቋማት አመራርና አባላት የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በመግለጫው ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

17 Jan, 13:11


በመዲናችን የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ መዋቅሮች እና መላ ህብረተሰቡን በስፋት ማሳተፍ ዉጤታማ እንደሚያደርግ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አሰኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ!

Addis Ababa City Manager Office

17 Jan, 13:07


በመዲናችን የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ መዋቅሮች እና መላ ህብረተሰቡን በስፋት ማሳተፍ ዉጤታማ እንደሚያደርግ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አሰኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ!
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመአራር ኮሚሽን የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመደበኛና የሪፎር ም ስራዎች የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ቀርቦ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች በተገኙበት ዉይይት ተካሂዷል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በከተማዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከተማዋን ከማናቸዉም አደጋ ለመጠበቅ በሚደረገዉ ጥረት የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ለሚከፍሉት መስዋዕትነት ክብር እንደሚሰጡም አስታውቀዋል።
አያይዘዉም ከተማዋን ከአደጋ ለመጠበቅ እና የኮሚሽን መ/ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋት የከተማ አስተዳደሩን አቅምና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አበረታች ዉጤት እንደተመዘገበ አስታዉሰዉ በቀጣይ ቀሪ ጊዚያት በስራ አፈጻጸም ዉስንነት በታየባቸዉ የስራ ዘርፎች ላይ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊዎችም የቀረበዉን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በሪፎርም ትግበራ ሂደት ላይ እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ አተኩረዉ ላቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና በኮሚሽኑ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ !

Addis Ababa City Manager Office

17 Jan, 11:47


በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል።

Addis Ababa City Manager Office

07 Jan, 14:55


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!

Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc

Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

07 Jan, 14:54


የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሌት ከቀን በመስራት ላይ የሚገኙ ብርቱ ሰራተኛችን፣ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪዎችን እና የመንግስት ተቋማት አስተባባሪዎችን በማመስገን በጋራ አክብረናል።

በኮሪደር ልማት የስራ እድል አግኝታችሁ በታማኝነት እና በትጋት ሌት ከቀን በመስራት ላይ ለምትገኙ ብርቱ ሰራተኞቻችን ሁሉ ዛሬ እናንተ የጣላችሁት መሠረት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ ታሪክ በመሆኑ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Manager Office

30 Dec, 10:47


ብሔራዊ ቤተመንግሥት የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገለጥበት ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ ለከተማችን ተጨማሪ ዉበት ሆኗታል !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Manager Office

30 Dec, 06:08


የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው የእድሳት ተግባር አሁን አንድነት ፓርክ ከሆነው ከታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጀምሮ ይኽን ትእምርታዊ ስፍራ እንደገና ለታላቅ አገልግሎት እንዲሰናዳ በማድረግ ቀጥሏል። ብሔራዊ ቤተመንግሥት አሁን የሕዝባችንን ጽናት፣ ጥበባዊ አቅምና ርዕይ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበት የሀገራዊ ጉዟችን ዋቢ ሆኖ ይታያል። የቀደመ ግዝፈቱን እና ውበቱን በመመለስ ያለፈ ታሪካችንን እናከብራለን። ለትውልዶችም የኩራትና የተነሳሽነት ዘላቂ ተምሳሌት አኑረናል።
እንሆ የቤተመንግሥት ሙዝየም ለሁሉም ሆኗል።
The restoration of the National Palace is a significant step in preserving our history and cultural legacy. The restoration efforts initiated by Prime Minister Abiy Ahmed, beginning with the Grand National Palace—now Unity Park—have continued with the revitalization of this iconic landmark. The National Palace now stands as a testament to our nation’s journey, embodying the resilience, artistry, and vision of our people. By restoring it to its former glory, we honor our past and create a lasting symbol of pride and inspiration for future generations.
The Palace Museum has now become a site for everyone.
#PMOEthiopia

Addis Ababa City Manager Office

30 Dec, 06:05


የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ጉብኝት
የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ጉብኝት…
See more

Addis Ababa City Manager Office

27 Dec, 05:46


ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት እስካሁን ድጋፍና ፍቅሩን እያሳየን ላለው ህዝባችን 24/7 ሰርተን ልንክሰው እየተረባረብን ነው"!!
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማትን በልደታና ንፋስ ስልክ ከተማ አስተባባሪ የሆኑት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ ደጋፊ ከፍተኛ አመራሮች፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴና የኮሪደር ልማት ተግባሪዎችና፥ አማካሪዎች በተገኙበት ከሳር ቤት እስከ አረቄ ፋብሪካ እንዲሁም ከካርል እስከ አቦ ማዞሪያ ያለው ምልከታ ተካሂዶበታል።
በዚህም የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ እንዳለ ከፍተኛ አመራሮቹ ተዘዋውረው ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያም በመወያየት ኢንጅነር ወንድሙ የቀጣይ አቅጠጫ አስቀምጠዋል።
የሁለተኛው ዙር ሰባተኛ የኮሪደር ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ እንዲሁም ከካርል እስከ አቦ ማዞሪያ ያለውን የኮሪደር ልማትን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ የከተማችንን መልካም ገፅታ ከመለወጥ ባለፈ የህዝባችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ለመፈፀም ሁሉም ባለ ድርሻ አካል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳስበዋል።
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

27 Dec, 05:39


ዛሬ በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል ።
ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ የሚዘልቀውን 21. 5 ኪ.ሜ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የግንፍሌ አካባቢ 19.5 ኪሜ የሚሸፍን ወንዝ ዳርቻ ልማት ፣የካዛንቺስን መልሶ ማልማት ፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና 40.4 ኪ ሜ የሚሸፍን ኮሪደር ልማት እንዲሁም የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር እና የአካበባቢ ልማት ፤ የፒያሳ ልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶች መኖሪያ መንደር ፤ የቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ተርሚናል እና የአቃቂ አዲሱ መንገድ የ37 ኪ.ሜ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ፤ “የብርሃን አዳሪ ት/ቤት" እና የ "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተናል።
በጉብኝታችን ከተማችን መሠረተ ልማት አቅርቦትእና ቅንጅት በፍጥነት እያደገ ያለ መሆኑን፤ የከተማዋን ፅዱና ዉብ በማድረግ ገፅታዋን እየቀየረ ያለ ልማት ፣ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በፍትሀዊነትን እያረጋገጡ ያሉ ሰዉ ተኮር ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን እነዚህ ሥራዎች ብልፅግና ከባለፈው ጉባኤ ወዲህ በቃሉ መሰረት አዲስ አበባን ዉብ አበባ ለማድረግ የተገበራቸው ሥራዎች አካል ናቸዉ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ጉብኝት በምስል : _
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Manager Office

24 Dec, 07:28


በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ የተዘጋጀውና በሪፎርሙ ስኬታማ የሆኑ ተቋማትን ልምድ ለመቅሰምና ለማስፋት የሚያስችል የከተማው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የመስክ ጉብኝት ተጀምሯል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ ሌሎች የፓርቲ አመራሮች እና የቢሮ ሀላፊዎች የተሳተፉበት የመስክ ምልከታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲንም የሚጎበኙ ይሆናል።
#aa_prosperity

Addis Ababa City Manager Office

24 Dec, 05:58


ከሳርቤት - መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት ስራ የደረሰበት ደረጃ ዛሬ አመሻሹን ተገምግሟል::
በግምገማ መድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅና የኮሪደሩ አስተባባሪ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የልደታና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ጨምሮ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የስራ አስተባባሪ አመራሮች ታድመዋል::
በመድረኩ ስራው የደረሰበትን ደረጃና በሂደቱ የታዩ መልካም ተሞክሮዎችና የጋራ ርብርብ የሚያስፈልጋቸው ችግሮች በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርገውባቸዋል::
ኢንጂነር ወንድሙ በግምገማው እንዳሉት የእስከ አሁኑ የስራው ሂደትና ፍጥነት መልካም መሆኑንና በተያዘው ግለት እንዲቀጥል የ24/7 የስራ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል::
ይህ እንዲሆን ደግሞ ግልፅ በሆነ የስራ ክፍፍል እና ቀልጣፋ የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም ድጋፍና ክትትሉም ጠንካራና ወጥ መሆን ይገባል ብለዋል
በቀጣይ በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገባቸው ጉዳዮችም ላይ በኢንጂነር ወንድሙ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል::
የሳርቤት- መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ ኮሪደር (የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው "7ኛ ኮሪደር" ) በንፋስ ስልክና ልደታ ክ/ከተሞች አስተዳደር ውስጥ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከ16 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው ፕሮጀክት ነው::
ታህሳስ 14/ 2017
Lafto Communication- ላፍቶ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇?Addis Ababa City Manager's OfficeGER1
Telgram:-
??👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

06 Dec, 12:04


የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በድንገተኛ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ዋለ::
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በተሰራው ድንገተኛ ኦፕሬሽን የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ::
በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማን ጨምሮ በመላው አዲስ አበባ የትምህርት ቤት አካባቢ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል::
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ ለቡ በተሰራው ኦፕሬሽን የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ እኩይ አላማ የሚያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል::
ቤቱ ሲፈተሽ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ግለሰቡ የፅንፈኛው ቡድን አባልና በትጥቅ ትግል ጭምር ተሳታፊ እንደነበር ታውቋል።
ከፎርጂድ ሰነዱ በተጨማሪ የተለያዩ የጦር ድምፅ አልባ መሳሪያዎችም በግለሰቡ ቤት ተገኝቷል::
በዛሬው እለት በክ/ከተማው በተሰራው ኦፕሬሽን ሺሻና ጫት ቤት፣ግሮሰሪና ፔንሲዮን፣ማሳጅ ቤትን ጨምሮ የትምህርት ቤቶች ዙሪያ በሚገኙ አዋኪ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች ላይ ከ97 በላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

06 Dec, 11:59


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ የመንግስት ተቋማት ሁሉም አገልግሎቶች ላይ የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር አስገዳጅ አሰራር ተቀመጠ
የሃገር አቀፉ የፋይዳ ምዝገባ ስርዓት ለሃገር የሚኖረውን አስተዋፅዖ ከግምት በማስገባት የስርዓቱን ተፈፃሚነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስተባበር የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በጋራ መግባባት በመፍጠር እየተመራ ያለ ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎት ጋር በተያያዘም አስገዳጅ አሰራር ተዘርግቷል።
ይህንኑ መነሻ በማድረግ በአገልግሎት ባህሪያቸው የተለዩ የከተማው ተቋማት በዋናነትም የንግድ ቢሮ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ፣ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የትራፊክ ማናጀመንት ኤጀንሲ ፣ የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ፈቃድ ባለስልጣን፣ የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር ዝርዝር የዝግጁነት እና አፈፃፀም ውይይት ተደርጓል።
አጠቃላይ አሁናዊ የምዝገባ ሁኔታ እና የአስገዳጅ ስርዓቱ አፈፃፀም ገለፃ በብሄራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዲሁም የተቋማቱ የስራ ሃላፊዎች ባሉበት ቀርቧል።
ክቡር አቶ አለማየሁ የፋይዳ ምዝገባ ከከተማ ነባራዊ የእድገት ሁኔታ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ከአካታችነት፣ ከቀልጣፋ አገልግሎት ፣ ከፍትሃዊ የሃብት አጠቃቀም፣ የሃብት አስተዳደር እንዲሁም ከሰላም እና ፀጥታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ከተማዋን ስማርት የሚያደርግ የዲጂታል ምሶሶ በመሆኑ ስራው በቁልፍ ተግባር የሚመራ መሆኑን ገልፀዋል።
የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን በከተማው ያሉ የመንግስት ሰራተኞችም በዚሁ ስርዓት አስገዳጅነት እንዲካተቱ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ስራ መገባቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ
በመድረኩ ያነሱ ሲሆን ከተማዋ የፋይዳ ምዝገባ ተደራሽነትን ሙሉ ለሙሉ ባጠረ ግዜ ተደራሽ ለማድረግ ከብሄራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት ጋር ከኤጀንሲው መዋቅር የመመዝገቢያ አማራጮች በተጨማሪ አዲስ ተደራሽ ተንቀሳቃሽ መዝጋቢዎችን ለማሰማራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ተቋማቱ የፋይዳ ምዝገባ ለአገልግሎት አስገዳጅ ያደረጉ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ አፈፃፀሙ እየተገመገመ የሚሄድ መሆኑ ተነግሯል።
ለበለጠ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

02 Dec, 10:59


የመዲናችን አዲስ አበባን ጽዳት በዘላቂነት ለመጠበቅ እንዲቻል የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በተደራጀ ንቅናቄ ማስወገድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን እና ግብአቶችን ስርዓት ለማስያዝ ከሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብና ፅዱ ለማድረግ እንዲሁም የብልፅግና ተምሳሌትና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የግንባታ ተረፈ ምርቶች ያሉባቸዉ ቦታዎችን በመለየትና ግንዛቤ በመፍጠር የከተማዋን ፅዳት ከማስጠበቅ አንፃር ሁሉም ተቋምና ባለድርሻ አካላት በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
አክለውም የፅዳት ንቅናቄዉ በትናንትናው እለት የተጀመረ ቢሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት የተቋማቸዉን ሀላፊነት በማወቅና ወደ ተግባር በመግባት እንዲሁም የቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በተለይም የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ የተሰማሩ ተቋማት፣አገልግሎት የማይሰጡ መኪናዎች፣ቆሻሻዎችን ለይቶ የመስጠት ፣ስታንዳርድ ያልጠበቁ የማስታወቂያ የመለጠፍ፣የከተማዉን ፅዳት ከማቆሸሽ አንፃር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በሁሉም ተቋማት በኩል መደረግ ስላለበት የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም ፅዳት በሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ባህል እንዲሆን ሰፊ እና ተከታታይነት ያለው ስራ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በዚሁ መድረክ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበርና ቁጥጥር ባለስልጣን አቶ ገዛኸኝ የከተማዋ የፅዳት እንቅስቃሴዎች በይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ተቋማት ሃላፊነት እንደሆነ ጠቅሰው በተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች የሚስተዋሉትን የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ባለቤቶች እንዲያስነሱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ከመስራት ባሻገር ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ግን ህጉን ታሳቢ ያደረገ ቅጣት ተግባራዊ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
ህዳር 23 ቀን 2017 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

02 Dec, 07:07


የሳር ቤት-ላፍቶ-ፉሪ የኮሪደር ልማት
ከሳር ቤት፣ ላፍቶ አደባባይ እስከ ፉሪ አደባባይ የሚካሄደው የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ…
See more

Addis Ababa City Manager Office

02 Dec, 07:03


የ10 ቀናት ከተማ አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ

Addis Ababa City Manager Office

02 Dec, 07:02


በከንቲባዋ የተመራ ልዑክ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጉብኝት

Addis Ababa City Manager Office

02 Dec, 06:58


ከአጥር መልስ - ዘጋቢ ፊልም…

Addis Ababa City Manager Office

13 Nov, 11:59


ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል።
ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።
አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Addis Ababa City Manager Office

13 Nov, 09:54


የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማችንን ድክመት እና ጥንካሬዎቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው በመለየት ገምግመናል።
የስራ ባህላችን ወጪ ቆጣቢ ፣ጥራትና ባጠረ ጊዜ ውስጥ የሰራናቸው ስራዎች ከተማችንን ለነዋሪው ምቹ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ እና የሀገራችንን ገፅታ ለመገንባት የሰራናቸው የኮሪደር ልማትና ከተማዋን መልሶ የማደስ ስራዎቻችን ዉጤታማ ሆነዉ ከተማችን በሩብ አመቱ ብቻ 20 የተለያዩ አህጉርና አለምአቀፍ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ ችላለች።
በዚህ ሩብ ዓመት በየተቋማቱ አቅደን ከፈፀምነዉ አንፃር 86 እጅ ዉጤታማ አፈፃፀም የታየበት ሲሆን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን የሰራንበት፣ የአመራር ቅንጅት፣ የስራ ባህላችን መለወጥ እና ከተማችንን የሚመጥን የስማርት ከተማ ግንባታ ስራዎቻችን ስኬት ያገኘንባቸው ናቸው::
በኮሪደር ልማት ምክንያት ለኑሮ ከማይመች ጎስቋላ አካባቢ ያነሳናቸው ነዋሪዎቻችንን ለኑሮ ምቹ የሆነ ንጹህ የመኖሪያ ቤት እና አካባቢ እንዲያገኙ ማድረግ የቻልን ሲሆን ከተማ ብቻ ሳይሆን የሰው ህይወት አብሮ የታደሰበት አፈፃፀም መሆኑንም ገምግመናል::
ፈተናዎችን እየተሻገርን ባሳካናቸው ስኬቶች ሳንረካ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ከህዝባችን ፍላጎትና ካስቀምጥነው ስታዳርድ አኳያ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ያልተሻገርናቸው መሆናቸውን
አምነን ለመከላከል የዘረጋነዉ አሰራር እንዲሁም ነዋሪው የሰጠንን ጥቆማና አስተያየትን መሰረት በማድረግ የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት የጀመሩ ሲሆን አሁንም አፅእኖት ሰጥተን ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በዘላቂነት ለማረም የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመፍጠር፣ ግልፅነትን እየጨመርን እና ነዋሪውን እያሳተፍን መስራት የሚያስችል አቅጣጫም አስቀምጠናል::
በተጨማሪም በተቋም ግንባታ፣ የሰው ተኮር ስራዎችን ማጠናከር፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ፣ ገቢ አሰባሰብ ማሻሻል፣ የንግድ ስርአቱን ማጠናከር፣ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ከተማ መገንባት እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በመጨረስ ወደ አገልግሎት ማስገባት እና የ2ተኛ ዙር ኮሪደር ስራን በጥራት እና በፍጥነት ማጠናቀቅ በቀጣይ በልዩ በትኩረት የምንሰራቸው ስራዎች ናቸው::
አገልግሎት አሰጣጣችንን ይበልጥ ቀልጣፋና ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ በማድረግ በትጋትና በታማኝነት በማሳተፍ መስራታችንን አሁንም አጠናክረን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Manager Office

12 Nov, 09:24


ዛሬው 4ተኛ አመት 3ተኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባች ሁለተኛ ኮሪደር ስራ ያለበትን በጥልቀት ገምግሟል ።
በግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረግነው የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን ፤የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ ተገምግሟል።
በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ ፣ ንፁህ ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።
ሌሎች ሳይት ላይ አስፈልጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ፤የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እድር ፤ ማህበር እና አብሮነታቸው የመሰረቱት ማህበራዊ መስተጋብር እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ን አቃቂ ፤ገላን ጉራ ፤ፉሪ ሃና ፤አራብሳ አምስት እና ስድስት አያት ሶስት፤ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት ፤አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም የተስተናገዳቸውን እና አፈፃፀሙም ጥሩ መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።
የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ።
በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6ቢሊየን በላይ መከፈሉን የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እና ቀሪ ተነሺዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ። በሌላ በኩል የኰሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል። መረጃን የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዝንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ በመወሰድ እንዳለበት በአፅንኦት ኣንስተዋል ::
በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2879 ሄክታር ስፋት ፤ 135ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን ፤ 240ኪሎ ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች ፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ 114የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ፣ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መረዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር ፣ 50 የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ::
ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የ አንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ተኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው አሳስቧል።

Addis Ababa City Manager Office

12 Nov, 09:22


ኮምፖስት ለማምረት በሚደረገው ሂደት ላይ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እንዲሁም ቴክኖ ሰርቭ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በኮምፖስት ማምረት ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት በስራቸው ላይ በሚያጋጥሙ ዋና ዋና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቻው ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሂዷል::
የውይይቱ ዓላማም በኮምፖስት ዝግጅትና የገበያ ትስስር ዙሪያ ለሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተመላክቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት ከደረቅ ቆሻሻ ኮምፖስ የማምረት ግንዛቤ አነዳልነበር ገልፀው አሁን ላይ ግን በዘርፉ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረበት ዘርፍ ሆኗል ብለዋል።
አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ በመዲናዋ ከሚመነጨው ሊበሰብስ የሚችል ደረቅ ቆሻሻ መጠን አንፃር በዘርፉ የተሰማሩ ማህበራት ገቢያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ከቆሻሻ የሚጠበቀውን ገቢ ግን እየተገኝ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ጨምር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተሞክሮ ለመቅሰም እየመጡ እንደሆነ አክለው ገልፀዋል።
የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 90 ሺህ 175 ቶን ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማገኝት መቻላቸውን ተናግረዋል።
የኮምፖስት ፍላጎት አለ እያልን በተቃራኒው ደግሞ የገበያ ትስስር ችግር አለ ማለታችን ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል። ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የቅንጅት ስራዎቻችን ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል።
የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ዋና አማካሪ አቶ ነጋሽ አረጋ በበኩላቸው ከአረንጓዴ ልማቱ ጋር ተያይዞ ሰፊ የኮምፖስት ፍላጎት እንዳለና በዘርፉ ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አብራርተዋል።
የመወያያ መነሻ የሚሆን ሰነዶችን የኤጀንሲው የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማዕከላት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ባዩሽ ታደሰ የቀረበ ሲሆን በኮምፖስት ማምረት ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ጥንካሬዎችንንና ተግዳሮቶችን በዝርዝር አቅርበዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ስርዓቱ ቢኖርም ክፍተቶች መኖራቸው : የገበያ ትስስር በቂ አለመሆን : የሚመረተው የኮምፖስት ጥራት : ኮምፖስት የሚመረትበት ምቹ የስራ ቦታና ሼድ : በዘርፉ ለተደራጁ ማህበራት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል አናሳ መሆን: ኮምፖስትን ለማምረት የሚፈጀው የጊዜ ርዝመት : ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን እና የመሳሰሉት ኮምፖስትን ለማምረት በሚደረገው ጥረት እንደ ተግዳሮት ተነስቷል::
ከደረቅ ቆሻሻ ኮምፖስት በማምረት ሂደት ላይ የሚስተዋሉትን ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎቹ ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በውይይቱ ላይም የኤጀንሲው አመራሮችን ጨምሮ የክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ፣ በኮምፖስት ማምረት እና በውበትና አረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት ተወካዮች ፣ የመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ቡድን መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
ህዳር 2 ቀን 2017 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

11 Nov, 06:32


መዲናችን ወደ አለም መዲናነት እያደገች ነው!

Addis Ababa City Manager Office

06 Nov, 10:40


በአራት ቀናት የማሌዢያ ቆይታችን ኳላ ላምፑር፣ ሳይበርጂያ እና ፑትራጂያ የተባሉ ከተሞቻቸውን ጎብኝተናል።
በቆይታችን ነባር ከተሞቻቸውን ከማደስ በተጨማሪ አዳዲስ ከተሞችንም እየገነቡ መሆኑን ተመልክተናል። ነባሮቹም ሆኑ አዲስ የሚገነቡ ከተሞቻቸውን ልዩ የሚያደርጋቸው ነዋሪዎች እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸውና ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚገለገሉባቸው ሰፋፊ የህዝብ መዝናኛዎችን፣ የኮንቬንሽንና የገበያ ማዕከላትን፣ መናፈሻዎችን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባታቸው፤ ሰው ሰራሽ ወንዝ እና ሃይቆች በመፍጠር ንጹህ ምቹ እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ አካባቢን መገንባታቸው እንዲሁም ከአጠቃላይ የከተማው ስፋት 38 % የሚሆነውን ለአረንጓዴ ልማት በማዋል ትልቅ ስራ መስራታቸው ነው። የሚገርመው ይህም በቂ አይደለም በማለት፣ ስራው እንደ ቅንጦት ሳይሆን ከመታመም በፊት መከላከል አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ እና የጤና አጠባበቅ ወሳኝ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ዘግይተንም ቢሆን የጀመርነው ስራ እየፈጠነ ነው። እኛ ከእነሱ አንፃር በተሻለ ሁኔታ ክረምትና በጋ ማሞቂያ እና ማቀዝቀዣ የማያስፈልገው፣ ወጥነት ያለው ተስማሚ የአየር ንብረት እና ውሃ፣ ትልቅ የሰው ሀይል እንዲሁም ሰፊ መሬት ያለን ሲሆን ይህን እምቅ አቅማችንን በመጠቀም ከተማችንን ለመለወጥ በመስራት ላይ እንገኛለን።
በተለይ በአዲስ አበባ የአረንጓዴ ሽፋናችን በአምስት ዓመት ውስጥ ከነበረበት 2.8 % ወደ 20 % ማድረስ ችለናል።
ህዝባችንን በማስተባበር በጀመርነው የ24/7 የስራ መርሃግብር የከተማችንን ነዋሪዎች ጤና ለመጠበቅ ወሳኝ የሆነውን ንጹህ እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ አካባቢ መፍጠርን፣ ነዋሪዎች እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው ክፍት ቦታዎችን ማዘጋጀትን፣ ለእግረኛ መንገዶች ትኩረት በመስጠት ምቹና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች መገንባትን፣ ፓርኮችን እና መናፈሻዎችን ማስፋፋትን፣ የአረንጏዴ ልማት ሽፋናችንን አሁን ካደረስነው በላይ ማሳደግን፣ የህፃናትና ታዳጊዎች የመጫወቻ ስፍራዎችን ማስፋፋትን እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን በብዛት መገንባትን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።
ብንዘገይም ገብቶን ጀምረናል፤ አካሄዳችን ትክክለኛ መሆኑንም ከኛ ቀድመው ከተገበሩት ጭምር ተመልክተናል። በቁጭት የጀመርነዉን የዓለም ከተሞች ከደረሱበት የመድረስ ግስጋሴያችን እንፈጥናለን እንጂ ፈፅሞ አንቆምም፤ አንዘገይምም።
እንበርታ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Manager Office

06 Nov, 10:37


የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ።
Ministira Muummee Rippabiliika Giinii, Amaaduu Owurii Baah baga nagaan gara Itoophiyaa dhuftanin jedha.
I welcome to Ethiopia Prime Minister Amadou Oury Bah of the Republic of Guinea

Addis Ababa City Manager Office

28 Oct, 06:35


በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
********************
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ ሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራን፣ የእድር ምክር ቤት አመራሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን አስመልክቶ ምክክር አካሂዷል፡፡
መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዘይነባ ጣሃ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ለዲጂታል ኢኮኖሚው እድገት ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው አገልግሎት በመሆኑ መላው ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ መመዝገብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ በጥሩ ጅማሮ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ነዋሪዎች በሚያቀርባቸው ቦታዎች በመሄድ እንዲመዘገቡ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.etበአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
********************
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ ሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራን፣ የእድር ምክር ቤት አመራሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን አስመልክቶ ምክክር አካሂዷል፡፡
መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዘይነባ ጣሃ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ለዲጂታል ኢኮኖሚው እድገት ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው አገልግሎት በመሆኑ መላው ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ መመዝገብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ በጥሩ ጅማሮ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ነዋሪዎች በሚያቀርባቸው ቦታዎች በመሄድ እንዲመዘገቡ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

28 Oct, 06:27


በጋራ መኖሪያ ሳይቶች ያልተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማጠናቀቅ ለነዋሪ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችል ጉብኝት ዛሬ በከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተካሄደ
ጉብኝቱ የተካሄደው ለነዋሪ በእጣ በተላለፉ በቦሌ አያት 2 ፣ በየካ ጣፎ እና በአራብሳ ሳይቶቸ ሲሆን በቦሌ አያት ሳይት 2 የውሀ ፣ የፍሳሽ ፣ የመብራት እና የመንገድ ስራ አለመሟላቱ ፤ የየካ ጣፎ የመንገድ እና የአራባሳ የወሰን ማስከበር ችግሮች በዋናነት ታይተዋል።
በሁሉም ሳይቶች ዋነኛ ችግር ተብሎ የተነሳው የመንገድ አለመኖር ሲሆን የመንገድ ችግር ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ዝርጋታም እንቅፋት መሆኑን መመልከት ተችሏል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ በጉብኝቱ እንዳሉት ከሁሉም የመሰረተ ልማት ተቋማት የተውጣጡ ቴክኒክ ኮሚቴዎች በየሳይቱ እና በየብሎኩ ያሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው እና ማለቅ የሚችሉትን ችግሮች ለይተው በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።
እንዲሁም በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል ያሉ እና ያልተጠናቀቁ ቀሪ ስራዎችን ስራ ተቋራጮች ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በመስራት እንዲያጠናቀቁ እንዲደረግ እና በየሳይቶቹ ያሉ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በማንሳት አካባቢውን ለነዋሪው ለመኖሪያ ምቹ የማድረግ ስራው በጋራ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
በጉብኝቱ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብረሀም ታደሰ ፤ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት እንዲሁም የመንገድ ፣ የውሀና ፍሳሽ ፣ የመብራት ፣ የግንባታ ፍቃድ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
A.A Housing Development & Administration
Bureau
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et

Addis Ababa City Manager Office

28 Oct, 06:14


የአዝርዕት እርሻ፣ የአበባ ልማት እና የከብት ማደለብ ሥራ የተቀናጀበት የጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ የቅይጥ ግብርና ስፍራ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

1,627

subscribers

13,173

photos

218

videos