ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከትን ሲመመሩ የነበሩት የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ" የተባለው ሕገወጡ "ቤተ ክህነት" ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታውቋል።
በትግራይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እና ገዳማትን በሕገወጥ መልኩ ተቆጣጥሮ የሚገኘው ይኸው ቡድን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከባድ "የቀኖና" እርምጃ እወስዳለሁ ሲል መዛቱንም ከተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ታውቋል።
የትግራይን ሕዝብ ለፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ይህ ቡድን አሁንም በጥፋት ሥራዎቹ የቀጠለ ሲሆን በ"ሕገ ቤተ ክርስቲያን" ስም አንድ ሰነድ ማጽደቁ ነው የተገለጸው።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እስከ አሁን የተባለ ነገር ባይኖርም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር።
ዘገባውን ለማሰናዳት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ተጠቅመናል።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5