በአሜሪካ እየተስፋፋ የመጣው በይፋ ሰይጣንን ‘የማምለክ’ እንቅስቃሴ
በአሜሪካ “ሰይጣንን የማምለክ” እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተስፋፋ መምጣቱ ተገለፀ፡፡
አሜሪካ ቦስተን የሚገኝ ማሪዮት ሆቴል ውስጥ ሰይጣን አምላኪዎች ተሰብስበዋል። በእንግሊዝኛው ‘ሳታኒስትስ’ በመባል ነው የሚታወቁት።
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮች በአንድ ቦታ ሲሰበሰቡ ይህ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። የሚጠብቁት መሰናዶ ሊጀመር ጥቂት ቀርቷል። ክፍሉ በሻማ ደምቋል።
የሰይጣን አምልኮ ሥነ ሥርዓት ማከናወኛዎች በቅርብ ርቀት ይታያሉ። ‘ትንሹ ጥቁር መድረክ’ የሚል ጽሑፍ ተሰቅሏል። ዘለግ ያለ ሻማ ማብሪያ በአንድ በኩል ተቀምጧል። ፊት ለፊቱ አምስት ጎን ያለው የኮከብ ቅርጽ መሬት ላይ ይገኛል።
እየተካሄደ ያለው ሥነ ሥርዓት ሰዎች በሕጻንነታቸው የተካሄደ ሃይማኖታዊ ሥርዓትን የሚጻረር ነው። የሚታወቀው ‘unbaptism’ በመባል ነው። ‘ፀረ ጥምቀት’ በሚል ሊተረጎም ይችላል።
ቢቢሲ እዚህ መሰናዶ ላይ እንዲገኝ የፈቀደው ሰይጣን አምላኪ “ስም አንሻም” ሲል ይደመጣል። ማንነታቸውን ይፋ የማይደረግ ከሆነ ነው ዝግጅቱ ላይ ለመታደም የፈቀደው።
እስከ መሬት የሚደርስ ሽፍን ልብስ ይለብሳሉ። ጥቁር የፊት መሸፈኛም ያጠልቃሉ። እጃቸው በገመድ ታስሯል። ከዚያም ነጻነትን በሚወክል ሁኔታ ገመዱ ይፈታላቸዋል።
በክርስትና የተሰጣቸውን ጥምቀት በሚነቅፍ ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾችን ይቀዳሉ። ይህን ማድረግ አንዳች ከፍታ እንደሚሰጣቸው ያስባሉ።
በአሜሪካ ስላለው የሰይጣን አምልኮ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮችም ውይይቶች ይካሄዳሉ። ዕምነቱ የፖለቲካ ንቅናቄን ማዕከል ያደረገ ነው። ሃይማኖት እና አገር አስተዳደር መለያየት አለባቸው ብለው ያምናሉ።
የካቶሊክ ጋዜጣ ይህን እምነት “የሃይማኖት ሥነ ሥርዓቶችን እና ምልክቶችን ከማጠልሸት ያልዘለለ” ሲል ከሌሎች ጋር በእኩል መታየቱን ነቅፏል።
ዘገባው፤ የቢቢሲ ነው፡፡