DBU info Center @dbuinfocenter12 Channel on Telegram

DBU info Center

@dbuinfocenter12


ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋመ

DBU info Center (Amharic)

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋመ እና አስተያየታቸውን ጸሐይ ታሪኩን በማስመለስ የእኛው ቦታን በተጎዳን ስለቀሩን የሚያዘጋጅ የኳሎን እንዴት ለማስተማር በማሰብ እና በማሳያ ደንበኞች ሰንሰለት ላይ እንደሚጠብቁ ታደሳለች። ይህ እትናት ከ Telegram በመግባት ያግኙን የማህበረሰብ ቦታ ነው። ይህ ባለማህበረሰብ ከኳሎን ሰንሰለት ላይ እንዷለን ሲሉ አዝናኝ አውሮፕ የሚሰራበትን የኒኤሜላንኩቱቪታርስ ድምፅ በመሆኑ እንዳደረረ እንጠቀሙን እንደሚታዩ ዜና፣ መረጃ፣ መፈንቅሄ በየዘመን ታጋቁን ተብሎ የተመረጠም የስነልቡርኩት፣ በሳይክል ዩቁቩረር ወዘተኩሽኳልኢና ከኛ ጋር በማሳያ እና በመግባት እና በመላቀቅ ባህርኮታዊ መግባት እንደሚናገር እንከፍታለን።

DBU info Center

21 Nov, 05:41


#urgent


ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ብሄር ተኮር ፀብ እንደተነሳ እና በ አማራ ተማሪዎች ላይ ወከባ እና ድብድብ እያደረሰ እንደሆነ መረጃ እየደረሰን ነው ።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

21 Nov, 05:07


#ጥያቄ


የመግቢያ ሰአት እንዲራዘም ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን እያቀረብን እንደሆነ ይታወቃል ነገር ግን ተማሪ ህብረትም ይሁን የግቢው አመራር አንድ ቀንም መልስ ሲሰጥ አላየንም አሁንም የመግቢያ ሰአት እንዲስተካከል በአንክሮ እንጠይቃለን ።

ማታ ማታ የሚንገላቱ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መቷል ።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

19 Nov, 12:07


የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ለመፈተን እየተዘጋጀሁ ነው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ

ትምህርት ሚኒስቴር ባሻሻለው ስርዓተ ትምህርት መሠረት የመውጫ ፈተና በሚል ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።

በዚህ መመዘኛም የማለፊያ ውጤት ሳያመጡ የሚቀሩ #ተመራቂ_ተማሪዎች ቁጥርም ጥቂት የሚባል አይደለም።

ይህንን ተከትሎም ብዙዎች መጀመሪያ መመዘን ያለበት መምህሩ ነው፤ ተፈትኖ ብቃቱ በታወቀ #መምህር የተማረን ተማሪ ነው መፈተን የሚገባው ሲሉ ይደመጣሉ።

ሸገር ራዲዮ ይህንን ጥያቄ ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘንም ፈተና ሊፈትናቸዉ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሰምቷል።

ይህንን የነገሩን በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ናቸው።

‘’የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም’’ ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለ #ከፍተኛ_የትምህርት_ተቋማት_መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

እስካሁን ባለው ስርአት የዩኒቨርስቲ መምህራን ማስተማር ከመጀመራቸው በፊት ያለው አንድ ዓመት፤ እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት እንዲያገኙ ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል። 
ነገር ግን ይህ በቂ ስላልሆነ ማሻሻያ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።
#ሸገርኤፍም #MoE



ትግላችን ፍሬ እያፈራ ነው ከሁለት አመት በፊት 2015 ላይ መጀመሪያ መምህራን መፈተሽ አለባቸው የሚል አቋም እያራመድን ነበር ።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

19 Nov, 09:43


#inbox


በተስፋ ገ/ሥላሴ ቤተ መጽሐፍት ተማሪዎች ማንበብና ማጥናት ተቸግረናል።
በቤተመጻሕፍቱ ሰራተኞች ቅጡን ያጣ የወሬ እና ማህበራዊ ሚዲያ ድምጽ ጩኸት ምክንያት ተማሪዎች እየተረበሹ ነው።
ተማሪዎች በተደጋጋሚ እያመለከቱ ቢጠይቁም ምላሽ የለም።
በተጨማሪም መብራት ያለ አግባብ ይጠፋል።


አስቸኳይ መፍትሔ እንፈልጋለን !


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

18 Nov, 19:25


#እንዴት_ነው



library ???



https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

16 Nov, 08:11


የጥሪ ማስታወቂያ
===========
በ ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ መግቢያ ቀን ህዳር 18 እና 19 መሆኑን ዩኒቨርስቲው አሳውቋል


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

05 Nov, 09:45


#እንዴት_ነው?


የመግቢያ ሰአት እስከ 1:00 ሰአት ድረስ ብቻ መሆኑ እየተመቸን ባለመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንፈልጋለን !

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

27 Oct, 16:31


#እንዴት_ነው


የዩኒቨርስቲው ምግብ ፣ የመግቢያ ሰአት እንዴት ነው ?.
እስኪ የገባችሁ ተማሪዎች ሀሳብ ስጡበት ።

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

24 Oct, 12:47


#welcome

ዛሬ
ወደ ዩኒቨርስቲ የሄዳችሁ ልጆች በሰላም እንደገባችሁ ተስፋ እናደርጋለን እንኳን ደህና ገባችሁ። በመንገድ ላይ ያላችሁ ልጆች መልካም ጉዞ ይሁንላችሁ ።



https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

23 Oct, 04:50


የዩኒቨርስቲያችን አመራሮች አሁናዊ ገፅታ 😅


ለማንኛውም ይህችን ስእል ምን የሚል መፀሀፍ ላይ cover page እንደሆነች የሚነግረኝ ጎበዝ አንባቢ ተማሪ ካለ ሽልማት ይኖረናል ።

መልካም ቀን

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

20 Oct, 19:34


#Share


DBU info center በአዲስ መልክ በተለያዩ ወጥ በሆኑ ፕሮግራሞች ለመከሰት ዝግጅት እያደረች ትገኛለች ። ስለሆነም ተቋማችን የዩኒቨርስቲውን ተማሪዎች በእኩል አይን በመመልከት ፍትህ እንዲሰፍን ጋዜጣዊ ፅሁፍ በማዘጋጀት እንዲሁም መረጃወችን ቀድሞ በማውጣት ስራ ስትሰራ ቆይታለች ። ይህንኑ ስራዋን ይበልጥ ለማሳለጥ እና ተደራሽነቷንም ለማስፋት ሲባል በቅርቡ አዳዲስ የቻናል አስተዳዳሪዎችን (Admin) ለመሾም ዝግጅት ላይ እንገኛለን ዝርዝር መስፈርቱን በዚሁ የምንገልፅ ሲሆን ምዘናውን በውስጥ የምናደርግ ይሆናል ። በመሆኑም ለራሳችሁ እና ለተማሪዎች ድምፅ መሆን የምትፈልጉ ውግንናችሁ ለፍትህ የሆነ እራሳችሁን ለ ውድድር አዘጋጁ ።

እንዲሁም ቻናላችን የተለያዩ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች በየሳምንቱ ወይ በየ 15 ቀኑ የ telegram ድምፅ ስርጭት ለማስተላለፍ ስለፈለገች sound edition የምትችሉ ልጆች በውስጥ ለማገዝ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን ።



DBU info Center እውነተኛ የተማሪዎች ድምፅ



https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

20 Oct, 04:37


#መግቢያ_confirmed

ከ 2013 ባች ውጭ ያላችሁ የትኛውም department የትኛውም bach ተማሪ እስከ ጥቅምት 20 ባለው መምጣት ትችላላችሁ ትምህርት የሚጀምረው ጥቅምት 25 ጀምሮ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል ። ያልሰሙ ተማሪዎች እንዲሰሙ መረጃውን በተቻለ መጠን ለጓደኞቻችሁ አጋሩ ።



#መልካም_ጉዞ


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

19 Oct, 06:13


የግዕዝ መምህሩ በሲያትል‼️
በጆርጅ ዋሽንግተን ዩንቨርስቲ የምስራቅ አፍሪካና የአረብኛ ቋንቋዎች መምህር የሆነው አሜሪካዊው ሀምዛ ዛፈር በሲያትል ከተማ ላለፉት ሁለት ዓመታት በግሉ ከ200 በላይ ተማሪዎችን የግእዝ ቋንቋ ማስተማሩን ገለፀ።

መምህሩ ቋንቋውን ማስተማር በግሉ የዛሬ ሁለት ዓመት  ሲጀምር ትምህርቱን የሚፈልግ ሰው አይኖርብ ብሎ ቢያስብም በቀናት ውስጥ ከ30 ያላነሱ ተማሪዎች ተመዝግበው ክፍሉን ሞልተውት መመልከቱ ቋንቋውን በግል  ማስተማሩን እንዲገፋበት እንዳበረታታው ይገልፃል፡፡

የግእዝ ቋንቋን ከተቋም ውጭ አንድ የውጭ ተወላጅ በግሉ ትምህርት ቤት ከፍቶ ሲያስተምር  ሀምዛን የመጀመሪያው ያደርገዋል።

በግዕዝ ቋንቋ በርካታ ጥንታዊ የሥነ፡ፅሁፍ፣ የፍልስፍና፤ የሥነ ክዋክብት እንዲሁም የሕክምና  ፅሁፎች በመኖራቸዉ  ቋንቋዉን ማጥናት የመካከለኛዉ ዘመንን የአፍሪካ ስልጣኔና ታሪክ ላይ ለሚደረገዉ ምርምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው  ሀምዛ  ቋንቋዉን እንዳጠና ይናገራል።

ከሴሜቲክ ቋንቋ የሚመደበዉ የግዕዝ ቋንቋ በአክሱም ዘመነ መንግስት ይነገር እንደነበር መዛግብት ይጠቁማሉ ።

በግዕዝ የተፃፉ አበዛኛወቹ መፃህፍት ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸዉ ቢሆኑም የመካከለኛዉ ዘመን ስልጣኔን የሚሳያሳዩ የተለያዩ የስነፅሁፍ፣ የፍልስፍና፤ የህክምናና የስነ ከዋክብት መፃህፍትም በዚሁ ቋንቋ እንደሚገኙ የዘርፉ ተመራማሪወች ይገልፃሉ።

በጀርመን ሃገር የሚገኘው የሃምቡርግ ዩኒቨርስቲ፣ የቻይናው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ እና የካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ  ከኢትዮጵያ ዉጭ የግዕዝ ቋንቋን የሚያስተምሩ  ብቸኛ ተቋማት ናቸው።
©አዩዘሀበሻ


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

18 Oct, 16:09


#notice

ዩኒቨርስቲው በወቅታዊ ሁኔታ ሙሉ የተማሪዎችን በጀት ማሟላት አልችልም በሚል ምክንያት የ2013 ባች ተማሪዎች ብቻ በቅድሚያ እንዲገቡ ለ ኮሌጅ ዲኖች መመሪያ የተላለፈ ሲሆን ዛሬ አንዳንድ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች ለ 2013 ባች ተማሪዎች በክላስ ተወካዮች በኩል እስከ ጥቅምት 15 እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል ። በመሆኑም ሁሉም የ 2013 ባች ተማሪዎች ወደ ግቢ ለመምጣት ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ስንል እናሳስባለን ።


DBU info Center

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

16 Oct, 19:33


#fun

''''' ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ''''


ዮሐንስ 20÷29



''''''''የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ብፁዓን ናቸው '''''''

DBU info center 1÷11


😂😂😂



Just for fun 😘

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

16 Oct, 16:49


#Fake_news

ይህ ከላይ የተገለጸው ምስል official የዩኒቨርስቲው መግለጫ አይደለም ። ነገር ግን እንደሰማነው ከሆነ በ20ዎቹ ውስጥ ተማሪዎች እንደሚገቡ ተረድተናል ።


ዩኒቨርስቲው ባስቸኳይ የመግቢያ ቀንን እንዲያሳውቅ አሁንም እናሳስባለን ።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

14 Oct, 18:09


#መግቢያ ቀን


ዩኒቨርስቲው የመግቢያ ቀን ባለማሳወቁ ተማሪዎች በከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ መውደቃቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ። የመግቢያ ቀን ተራዘመ ከተባለ ወዲህ በዚህ ቀን ትገባላችሁ ባለመባላቸው ስራ እንዳይሰሩ ጭምር እንደሆኑ ነው የተገለጸው ። በተለይ 2013 batch ተማሪዎች የምርቃት ጉዳይ እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀው አስቸኳይ እልባት የማይሰጥ ከሆነ ያዋጣል ብለን ያሰብነውን ትግል ሁሉ ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ብለዋል ።

ዩኒቨርስቲው ይሄንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ 2 ቀን ውስጥ የመግቢያ ቀን የማያሳውቅ ከሆነ DBU info Center እንደ አንድ የሚዲያ ተቋም ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የዩኒቨርስቲው የማናጅመንት አባላት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ የምትጀመር መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን ።


አለምነው
የሺአረግ
ጌትነት
አዝመራው



https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

14 Oct, 04:28


#


አዲስ መልካም ነገር የምንሰማበት ቀን ይሁንልን !።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

10 Oct, 10:50


#why

ተማሪዎች መግባታቸውን እያበረታታን ነገር ግን የሸዋ አካባቢ ተማሪዎች አይገቡም የተባለበትን ምክንያት ፍፁም የማንቀበለው ጉዳይ ነው !

ሸዋ :- መንዝ ግሼራቤል እንድ የሸዋ ጫፍ የወሎ ወሰን ፣ ሸዋ መረሀቤቴ አንድ የሸዋ ጫፍ የ ጎጃም ወሰን ፣ ሸዋ ሚዳ ሬማ ደራ ጎንዶመስቀል እንድ የሸዋ ጫፍ ኦሮሚያ ወሰን ፣ ሸዋ ቡልጋ ቀጠና በረኸት አንድ የሸዋ ጫፍ አፋር ወሰን መሆኑ እየታወቀ እና ለከተማውም በጣም እሩቅ መሆኑ እየታወቀ ዩኒቨርስቲው በግርድፉ የሸዋ ተማሪዎችን አልቀበልም ማለቱ ፍፁም አሳዛኝ ነው ። አሁን በስም ከተቀስናቸው ከላይ ካሉት አካባቢዎች ሰላም የሌለ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ተማሪዎች ቀድመው ወደ ከተማዋ ገብተው ይገኛሉ ። እነዚህን ተማሪዎች አትገቡም ብሎ መከልከል ምን የሚሉት ነው ?


ምክንያታችሁስ ምንድን ነው ?


አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ እንጠይቃለን ?


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

10 Oct, 06:50


#ሰበር


ከሩቅ አካባቢ መጥታችሁ ዩኒቨርስቲው አካባቢ ያላችሁ ልጆች አሁኑኑ ወደ ዩኒቨርስቲ ኑ ዩኒቨርስቲው እንድትገቡ ፈቃድ ሰቷል ።


መረጃውን ለሁሉም ሼር አድርጉ ።

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

08 Oct, 15:08


#መረጃ


ዩኒቨርስቲው በጥቂት ቀን ውስጥ መግቢያ ቀን አሳውቆ ተማሪዎችን እስከ ጥቅምት ግማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ሊያስገባ እንደሆነ አንድ ለመረጃው ቅርብ የሆነ ሰው ሹክ ብሎናል ።

ለዚህ አጭር ጊዜ ቢያንስ እዚህ የደረሱ ልጆችን የዶርም አገልግሎት እንኳን እንዲያገኙ መደረግ አለበት ። የተማሪዎች ህብረት በዚህ ጉዳይ ምንም አለማለቱ እጅግ አሳዛኝ ነው 😭!


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

07 Oct, 13:51


#update

ከሀገሪቱ የተለያየ ጫፍ የመጡ ተማሪዎች ዝናብ ሊዘንብ በመሆኑ ወደ እምነት ተቋማት እየሄዱ ይገኛሉ ። ይህ 👆 ከላይ የምትመለከቱት ተንቀሳቃሽ ምስል ተማሪዎች ወደ ጠባሴ ገብርኤል ሲሄዱ የሚያመለክት ነው ።


ፍትህ ከሩቅ አካባቢ መጥተው ለሚሰቃዩ ተማሪዎች ።

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

07 Oct, 13:12


#ሰበር

ከተለያዩ ሩቅ አካባቢዎች የመጡ በርካታ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ቦርሳ እና ስንቅ ይዝው መተው ዩኒቨርስቲ በር ላይ ቆመው ፍትህ ቢጠይቁም መልስ የሚሰጣቸው አልተገኘም ። በተወካዮች አማካኝነት የዩኒቨርስቲውን አመራር ያናገሩ ቢሆንም የሚመለከተው አካል የለም የሚል ውሀ የማያነሳ መልስ ሰጥቷቸዋል። ይህ ጉዳይ ትልቅ ውሳኔ እና ፊርማ የሚያስፈልገው እንኳን አይደለም በአንድ የስልክ ልውውጥ የሚያልቅ ጉዳይ ነው ። ተማሪዎቹ ከረፋዱ 4 :00 ጀምረው ይህ ዜና እስከሚሰራበት ድረስ በዩኒቨርስቲው በር ላይ ተቀምጠውበት ይገናኛሉ ። ዩኒቨርስቲው የአካባቢውን የሰላም ሁኔታ እና የተማሪዎቹን የ economy ደረጃ አገናዝቦ አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል ። ተማሪዎች በከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ውስጥ ይገኛሉ ።

#ፍትህ_ለተማሪዎች


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

04 Oct, 18:34


for concerned !

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ መስከረም ወር ላይ ተማሪዎችን ሊያስገባ እንደማይችል ዘግበን ነበር ይሄንን ስንል ያለምንም በቂ መረጃ አለነበረም ! ያም ሆነ ይህ ግን የዩኒቨርስቲው አመራሮች በጀት ከኪሳቸው እያዋጡ ተማሪዎች የሚመግቡ ይመስል በጀት የለም የለም ይላሉ ። ይህ ጉዳይ መቼ እንደሚስተካከል ለታሪክ እና ለጊዜ እንተወውና currently ለተፈጠረው ቀውስ የጋራ መፍትሔ ወደ መፈለጉ እንግባ ። ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በ 29 እና በ 30 ኑ ብሎ ከጠራ ቡሀላ 5 ቀን ሲቀረው ላልተወሰነ ግዜ አራዝሜዋለሁ ሲል ትንሽ እንኳን ቅር አላለውም በጣም ያሳዝናል ። በርካታ ተማሪዎች የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ስላልሆነ ተማሪዎች ካሉበት የገጠር ቀበሌ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ደብረ ብርሀን ከተማ ተጠግተው ይገኛሉ እነዚህ ተማሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ ሲራዘም ላልተፈለገ ወጪ ተጋላጭ ይሆናሉ ። እንዲሁም በርካታ ተማሪዎች የplane ticket ቆርጠው በመጠባበቅ ላይ እያሉ መራዘሙን ሰሙ እነዚህ ልጆችም ኪሳራ ውስጥ ናቸው ። ይህ እንግዲህ economically እንዲሁም morally demo የሚያደርግ ተግባር ነው ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነገሮችን ቀድሞ forcast አድርጎ መፍትሔ የሚያበጅ ነበር ዳሩ ያ ባይሆን እንኳን እንዴት ችግሩ እየተነገረው እንኳን መፍታት ያቅተዋል ?🤔


#task1

ሁሉም መደበኛ ተማሪ የዩኒቨርስቲ የ facebook ገፅ ላይ በመግባት comment section ላይ ሀሳቡን ይግለፅ

#task2

በአካባቢው ያላችሁ ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካበቢ መጥታችሁ በቅርቡ ያላችሁ ተማሪዎች በቀጥታ ዩኒቨርስቲ በመግባት ትምህርት ባይጀመር እንኳን ዶርም እና ምግብ ይፈቀድልን ጥያቄ አቅርቡ ። b.c የአንተ የ አንቺ cost share እየቆጠረ መሆኑን አትዘንጉ !

#task3

2013 batch ተማሪዎች የተለየ movement የሚያስፈልጋችሁ ይመስለኛል b.c ጥር ላይ የመመረቃችሁ ነገር 78% በላይ አሳሳቢ ነው ። ስለዚህ ባስቸኳይ የራሳችሁን ኮሚቴ በማዋቀር እራሳችሁን ለትግል ዝግጁ ማድረግ አለባችሁ ።



#🛑justicefordbustudents


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

29 Sep, 14:09


#መረጃ

የመውጫ ፈተና ለወደቁ ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ እና በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች የተማሩትን የሚገልፅ ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ተገለፀ።

የመውጫ ፈተና የወደቀ ተማሪ እንዴት ዓይነት ቴምፖራሪ እንደሚሰጠው እና ሥራ እየሠራ እንደገና መፈተን እንዲችል ሁኔታዎች ይመቻቻል ተብሎአል።


https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

19 Sep, 13:36


#ሰበር_መረጃ

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ መስከረም ወር ላይ ሊጠራ እንደማይችል ያገኘነው መረጃ ያመልክታል ። ለዚህም ዩኒቨርስቲው እንደ ዋና ምክንያት የያዘው በወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ምክንያት በአካባቢው ያሉ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይወስዳሉ መባሉ ነው ። አሁን ባለው ሁኔታ የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና መስከረም መጨረሻ አካባቢ እንደሚሰጥ ታውቋል።

የተማሪዎች ጥሪ ምናልባትም ጥቅምት መጀመሪያ አካባቢ ሊሆን ይችላል የሚል መልስ ሰተውናል ።




https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

18 Sep, 08:58


ዩኒቨርስቲው ላይ ዘመቻ ለመክፈት ተዘጋጅተናል ‼️

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እስከ መስከረም 12 ከስር የተዘረዘሩትን ነገሮች የማያደርግ ከሆነ ዩኒቨርስቲው ላይ ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ለመክፈት ዝግጁ ነን ።

1. የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን እስከ መስከረም 12 ድረስ የማያሳውቅ ከሆነ
2. የ2017 የትምህርት ዘመንን ሙሉ ዕቅዶች የሚያሳይ ካላንደር አዘጋጅቶ ይፋ የማያደርግ ከሆነ ፣ በተለይም ካላንደሩ የ2013 ባቾችን ጥያቄ የሚመልስ መሆን ይኖርበታል ማለትም መቼ መውጫ ፈተና ተፈትነው መቼ እንደሚመረቁ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆን አለበት !

ኃላ አልሰማንም እንዳይሉ ሼር ይደረግላቸው !


©j

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

17 Sep, 03:38


#መረጃ

አንዳንድ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን እያሳወቁ ቢሆንም ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ officially ምንም ያለው ነገር የለም ። ተይዞ የነበረው እቅድም ሊራዘም እንደሚችል ያገኘነው የውስጥ መረጃ ይጠቁማል እንደ ምክንያት የሚያቀርቡትም ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ (ጉዞ ) እንዲሁም በጀትን ነው ። የዚህ አመት መግቢያ መራዘም ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትል አውቆ በፍጥነት እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን ። በተለይ የ2013 ባች ተማሪዎች ጠር ወር ላይ መመረቅ ስላለባቸው የመግቢያ ቀን እጅግ መፍጠን ይኖርበታል ።

ማሳሰቢያ

ዩኒቨርስቲው በዚህ ሳምንት ምንም አይነት መግለጫ የማይሰጥ ከሆነ የተለየ ዘመቻ የምንጀምር መሆኑን ከወዲሁ እንድታውቁት !


© DBU info Center

https://t.me/dbuinfocenter12

DBU info Center

04 Sep, 07:15


#መረጃ

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት

ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

መረጃውን ለተፈታኝ ጓደኞቻችሁ Forward አድርጉላቸው!




https://t.me/dbuinfocenter12
https://t.me/dbuinfocenter12