መዓዛ ሠናይ @meazasenay Channel on Telegram

መዓዛ ሠናይ

@meazasenay


☞ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ
☞እንረዳ
☞እንማማር

ለበለጠ መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡

መዓዛ ሠናይ (Amharic)

መዓዛ ሠናይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ፣ እንረዳ፣ እንማማ። ምንድንዝበር እንደሚከተለው መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውኝ ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡ ይህ እናቱ ለመሆን በቃሊቲ ከተማ ላይ ተከታይ ለአብርሃም፣ ማርሰኞ፣ ረቡዕ፣ ዓርብ እና ቅዳሜ በአሰቃቂ ቦታዎች እንቀበላለን። የሚቀጥሉት አገልግሎቶች ለመሆኑ ለአንዳች በተመሳሳይ እናት ነፃነታቸውን እናቅርብላለን።

መዓዛ ሠናይ

21 Nov, 10:10


ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መዓዛ ሠናይ

20 Nov, 08:44



....የቀጠለ
ድርሳን በእንተ ማርያም ኃጥእት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን አምስት)

ኃጢአተኛዋ ሴት እያለቀሰችና ደረቷን እየደቃች እንዲህ ብላ አሰበች፡፡ እንዴት እንደምትድንም አታውቅም ነበር፡፡ የጴጥሮስን መራራ ልቅሶን የተመለከተና ንስሓውን የተቀበለ ወደ ክብሩም የመለሰው፣ የቀራጩ ጩኸትም ከእርሱ ያልተሠወረ የልብን የሚያውቅ እግዚአብሔር ዳግመኛም የዚችንም ሴት ዕንባዋን ቸል አላለም፡፡ ያን ጊዜም ያቺ ሴት በንጹሕ ልብና በብሩህ ሕሊና እንደተመለሰች ዐወቀ፡፡

እርሷ ግን በእውኑ ቸሩ መምህር ሌሎችን ሰዎች እንደተቀበላቸው ይቀበለኝ ይሆንን? አናግረው ዘንድ አንድ ሰዓት ያክል ይታገሠኝ ይሆንን? በውኑ ስንፍናዬን ሁሉ እነግረው ዘንድ ወደ እርሱ ያቀርበኝ ይሆንን? የመዋረዴንና የኀፍረቴን ነገር ይሰማ ዘንድ ይቀበለኝ ይሆንን? በውኑ አንዲት ቃልን ይመልስልኝ ይሆንን? ብላ አሰበች፡፡

ዳግመኛም ነፍሴ ሆይ ምሕረት ቀርባለች፡፡ ባለመድኃኒቱም በዚህ አለ፡፡ መድኃኒቱም ሩቅ አይደለም፡፡ በእውኑ የምትደፍሪ መድኃኒትሽንም ተስፋ የምታደርጊ ከሆነ ወደ እርሱ ሂጂ አለች፡፡ ከዚህ በኋላ በሃይማኖት ጸናች፡፡ እንደዚህ ስትልም አሰበች:: ስለ ኃጥአን ሲል ወደ ዓለም የመጣው ይህ አይደለምን? ስለ እነርሱ እንደ እነርሱ ሰው የሆነ በመካከላቸውም የተመላለሰ ይህ አይደለምን? የኃጢአተኛውን መመለሱን እና ሕይወቱን እንጂ ሞትን አልፈቅድም ያለ እርሱ አይደለምን? አለች፡፡

ዳግመኛም መልሳ መቶ በግ ያለው ሰው ቢኖር ከእነሱም አንዱ ቢጠፋ ያልጠፉትን ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን ይፈልግ ዘንድ የሄደ አይደለምን? ባገኘውም ጊዜ በትክሻው የተሸከመው ከአልጠፉትም ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእሱ ፈጽሞ ደስ ይሰኛል ብሎ የተናገረ እርሱ አይደለምን?

አሁንም መልሳም እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ ያለ እርሱ እንዲህስ ከሆነ ለምን እሰንፋለሁ? ለምንስ ንስሓን አልፈልግም? እንደ እኔ ክፉን ሥራ የሠራ ሊሰንፍ አይገባውም፡፡ በእኔ መንገድም የሄደ ወደ ንስሓ ይመለስ ዘንድ ይገባዋል፡፡

እነሆ አሁን ወደ እሱ እሄዳለሁ የሚቀበለኝም ከሆነ ሰውነቴን በፊቱ እጥላታለሁ፡፡ በቸርነቱ ብዛትና በምሕረቱ ይቅር ባይ እንደሆነ እነሆ ዐወቅሁ፡፡ ካልተቀበለኝና ቸል ካለኝም እቈጣ ዘንድ ተገቢ አይደለም አለች፡፡

ይህንንም ተናግራ በሃይማኖት ጸናች፡፡ ፈጥና ተነሥታም ገንዘቧን ሁሉ ወርቋን፣ ብሯን፣ ልበሷንና የገዛችውንም ሁሉ ሰበሰበች። እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና ይህን ገንዘብ ወደ ጌታ ወስጄ ባይቀበለኝ እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? አለች፡፡

እርሱም ያመኑበትንና የተከተሉትን ወርቅ ወይም ብር በመቀነታችሁ አትያዙ ብሎ አዝዟቸዋልና፡፡ ነገር ግን እኔ ወደ ገብያ እሄዳለሁ ለጌታ ላቀርበው የሚገባኝንም እገዛለሁ፡፡.....

ይቀጥላል.....

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 105-151)

መዓዛ ሠናይ

20 Nov, 07:04


#ሺ_ጊዜ

ሺ ጊዜ ኃጢያት ስራ ነገር ግን ንስሃ ከመግባት አትቦዝን። የፈጠረህ እግዚአብሔር ጨርሶ አንተን መማር አይሰለችምና። እልፍ ጊዜ በድል ነገር ግን ከእግዚአብሔር አትኮብልል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የደበሉ ወደ እርሱ የሚሸሸጉበት ዕሩሩህ እንጂ የሚሸሹት ጨካኝ አይደለምና።

በጣም ለቁጥር እንኳን በሚታክት ጥፋት ውስጥ ሁን ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከእግሩ ስር አትጥፋ። እግሩ ስር ስትሆን ክብር አለህና በጥፋትህ ብዛት እኔ እንዴት ወደ እግዚአብሔር እቀርባለሁ ብለህ አትራቅ። እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድትቀርብ ልጁን ለአንተ ሲል በመስቀል ሰውቶታልና።

ጉድ የሚያስብል ጉድ ውስጥም ሁን ነገር ግን ገበናህን ከሚሸሸግልህ ከእግዚአብሔር አትሸፍት። የሁሉ ሰው ተግባር በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ ነው። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገርህን እያወቀ ዝም የሚልህ ስለሚምርህ ነው እንጂ ለኃጢአትህ መዝገብ አዘጋጅቶ አይደለም።

ኃጢአቴ ብዙ ነው ብትልም የኃጢአትህ ክምር በጭራሽ እግዚአብሔርን እንዳይሸሽግህ። ከበደልህ ይልቅ የሞተልህን ተመልከት። እግዚአብሔር የኃጥዓን መፍትሔ ነው። ችግር ውስጥ እንዳለህ በተሰማ ቁጥር ወደ ባለመፍትሔው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እጅግ ማትረፊያ ነው። ኃጢአት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር ነውና።

የራስህን መንገድ ብትከተል ጨርሶ ልትወጣው ወደማትችለው መስመር ልትገባ ትችላለህ ከዚህ ይልቅ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴዎስ 11፥28) የሚለውን መለኮታዊ ቃል አምነህ ከነሸክምህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ። እርሱ እንዳለውም ያሳርፍሃልና።

የራስህን ኃጢአት እና የእግዚአብሔርን ጽድቅ እያመዛዘንክ አትኑር። በምንም መልኩ በእግዚአብሔር ልክ ጻድቅ ልትሆን እና የእርሱን የጽድቅ ጥማትም ልታረክ አትችልም። እንዲህ እስክሆን ወደ እርሱ አልቀርብም፣ ይሄንን ልማዴን እስከተው አልጠጋውም አትበል ያንን ልማድህን የሚያስክድ እና የሚያስተው አቅም እና ጸጋ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ እራስህ ጋር አታገኘውምና።

እና ወዳጄ እሩጫ የሚሻለው ወደ እግዚአብሔር ሲሆን ነው። ጌታ እግዚአብሔር የማያሳፍርህ ተቀባይ፣ የማያሸማቀቅህ አዛኝ፣ ፊት የማይነሳህ አቃፊ ነው። እና ወደ እርሱ መምጣት የሁሉ ነገር መፍትሔ ነው።

መዓዛ ሠናይ

20 Nov, 06:34



....የቀጠለ
ድርሳን በእንተ ማርያም ኃጥእት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን አምስት)

እንዲሁም ለዚያች ሴት የጸጋው ባለጠግነት በእርሷ ላይ ወጣ፡፡ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከክፋትም ወደ በጎነት ነፃ አወጣት፡፡ ስሟንም በዓለም ሁሉ እንዲዘክሩ አደረጋት፡፡ ከዚህም በኋላ ከዕለታት በአንዲት ቀን በቀደመው ግብሯ ሳለች የሐር ልብስን ለብሳ፣ አብዝታ አጊጣና ሽቱን ተቀብታ መልኳን በመስታውት ተመለከተች፡፡ የዐይኗ ውበት፣ የጉንጮቿ ቀይነትና የመልኳም ማማር አስደሰታት፡፡ ውበቷንም ስትመለከት ለአንድ ሰዓት ያክል ቆየች፡፡

ከዚህም በኋላ በጎ ሐሳብ ወደ እርሷ መጣ፡፡ ሞት ሆይ መጥተህ ይህን የምታስወግደው የመልኬን ደምግባትስ የምትለውጠው አይደለምን? አለች ይህስ በጎ መዓዛ ያለው ሽታ ወደ ክርፋቱ የሚለወጥ አይደለምን፡፡ የዚህስ ኃይልና ብርታት ፍጻሜው እርጅና እና ድካም አይደለምን? ዛሬ የሚወዱኝስ ነገ የሚነቁኝ አይደሉምን? ዛሬ ይቀርቡኝ ዘንድ የሚወዱስ ነገ ከእኔ የሚርቁ አይደለምን?

እንዲህስ ከሆነ ከልቅሶና ከፍጹም ኵነኔ በቀር ከዚህ ሁሉ እንግዲህ ምን አገኛለሁ? የዚህን ዓለም ገንዘብ ሁሉ ባተርፍ ከሥጋ ድካም ከእርጅና እና ከዐይን መጥፋት ሊያድነኝ ይችላልን? ከዚህስ ሁሉ ቢያድነኝ በውኑ ከሞት ሊያድነኝ ይችላልን? እነሆ ይህ ነገር አይቻልም፡፡

ነፍሴ ሆይ ቃልን ሁሉ እንዳገኘ የሚናገር ሰው በዚያ በፍርድ ቀን ይፈረድበታል ያለውን የዓለሙን ሁሉ ፈራጅ ምን ትመልሽለታለሽ? አለች፡፡ ነፍሴ ሆይ ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ ትሉ ወደማያንቀላፋበት ቅዝቃዜው ወደማይሞቅበትና እሳቱ ወደማይጠፋበት ይወስዱሽ ዘንድ ከእውነተኛው ፈራጅ ትእዛዝ በወጣ ጊዜ እንዴት ትሆኚ ይሆን?

ነፍሴ ሆይ በዚች ሰዓት የሚረዳሽ ማነው? ነፍሴ ሆይ በውኑ በዚህ ዓለም ያገኘሽው መጽናናት ይልቁንም ወዳጆችሽ ኃጢአት ስለ መሥራትሽ በውኑ ይጠቅሙሻልን አለን? ኅብሩ ልዩ ልዩ በሆነ ከቀጭን የተልባ እግር በተሠራ ልብስ ስትደሰት የኖርህ ሰውነቴ ሆይ በምስጋና ጌታ እና ክፉ ሥራህን ሊሰሙ በሚቆሙ የብዙ ብዙ በሆኑ በመንፈሳውያን መላእክት ፊት ዕርቃንህን ስትቆም እንዴት ትሆን ይሆን?

ነፍሴ ሆይ በእውኑ በዚህ በሚያስፈራ የፍርድ ዐደባባይ የሚረዳሽ አለን? የዚህ ዓለም መብልስ በወዲያኛው ዓለም የትል ሲሳይ በምትሆኚ ጊዜ በእውኑ ይጠቅምሽ ይሆንን? ነፍሴ ሆይ በዚህ ዓለም የተደሰትሽው ምን ይረባሻል? ምንስ ይጠቅምሻል? ዐይኖቼ ሆይ በውኑ የሞት ጥላ በጋረዳችሁ ጊዜ የሚጠቅማችሁ የሚረባችሁ ኵል አለን?

አፌ ሆይ በውኑ መራራ የሞት ጽዋን በምትጠጣ ቀን የሚረባህ የሚጠቅምህ የዚህ ዓለም መብል አለን?

በአንተ ብዙዎችን የሸነገልሁብህ አንደበቴ ሆይ ሞት ዝም ባሰኘህ ጊዜ ምን ትሆን ይሆን? በውኑ ከዓለሙ ፈራጅ ጋር መመላለስ ይቻልህ ይሆንን? በቀለበትና በእንሶስላ ስታጌጡ የኖራችሁ እጆቼ ሆይ የሚያስፈራ ሞት በመጣ ጊዜ ምን ትሆኑ ይሆን? ሁል ጊዜ ወደ ዝሙት ስትሮጡ የነበራችሁ እግሮቼ ሆይ ሞት ባሠራችሁ ጊዜ ምን ትሆኑ ይሆን? ማምለጥንም ትፈልጋላችሁ፡፡ ግን አይቻላችሁም፡፡....

ይቀጥላል.......

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 105-151)

መዓዛ ሠናይ

19 Nov, 18:25


ህዳር 11 የጌታችን አያት የእመቤታችን እናት የሆነችው ቅድስት ሐና ያረፈችበት አመታዊ ክብረ በዓል ነው

ከእመቤታችንና ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያካፍለን።

መዓዛ ሠናይ

19 Nov, 11:05


ትሕትና

ትሕትና የትንሽት ምልክት አይምሰልህ ፡፡ ታላቁ መስፍን ሙሴ ፣ ታላቁ ጌታ ክርስቶስ ትሑታን ነበሩ ፡፡ ባለጠግነት ትሕትናን ሊያሳጣህ ሲሞክር ጻድቁ አብርሃምና ጻድቁ ኢዮብ ትሑታን እንደ ነበሩ አስብ ፡፡ ሥልጣን ልብህን ከፍ ሲያደርግብህ “ለንጉሥ በቀን ላይ ቀን ትጨምራለህ” በማለት የተናገረውን ዳዊትን አስብ ፡፡ ምንም ብትነግሥ ለራስህ አንድ ቀን መስጠት አትችልምና ፡፡ ደግሞም “ሁሉም ከንቱ” ያለውን ሽቅርቅሩን ንጉሥ ሰሎሞንን ፣ ጠቢቡን ንጉሥ ይዲድያ የተባለውን በማሰብ አለባበስንና እውቀትን ናቀው ፡፡ ጉልበትህ ሊያስታብይህ ሲሻ ሶምሶምን አስብ ፡፡ ኃይልህ ከኃያላን ፣ ሥልጣንህ ከሠለጠኑት ፣ እውቀትን ካወቁት ጋር ቢነጻጸር በጣም ትንሽ ነው ፡፡ በምድራዊ ነገር ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጸጋም ልትመካ አይገባህም ፡፡ ትምክሕት እጄ ሀብትን ፣ ጽድቄ ጸጋን አመጣልኝ ማለት በመሆኑ ቁጥሩ ከክህደት ነው ፡፡ በጸጋ ሳይሆን በባለጠጋው መመካት ግን ተፈቅዷል ፡፡ ኃጢአትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል ፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል ፡፡

ትሕትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ፡፡ ታጌጥበታለህ ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል ፣ የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይጸየፍሃል ፡፡ ቁመተ ረጅሞች ሲኮሩ ሰማይን የምታይ ይመስልሃል ፡፡ አጭሮች ሲልመጠመጡ መቃብር የገቡ ይመስላል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው ፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ ፡፡ ትሕትና ራስን የማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍጹም አይችሉም ፡፡ ትሕትና የሌሎችን ክብር ማወቅ ነው ፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትሕትና ታስከብረናለች ፡፡ ትሕትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሁኖ መኖር ነው ፡፡ ትሕትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም ሰው አስተማሪ ይሆናል ፡፡ ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኝ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል ፡፡ ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው ፡፡ እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኝ ማለት ነውና ትዕቢት ነው ፡፡ ትሕትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ፣ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ትሕትና እንዳልኖሩ ሁኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው ፡፡

ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትሕትና አይደለም ፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል ፡፡ ትሕትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ ፡- “መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም፡፡” እውነተኛ ትሕትና ለሚያንሱን መታዘዝ ነው ፡፡ ሰው እንደዚህ ሁኖ እንደማይቀር ብናስብ ስንት ሕጻናትን ስንት ድሆችን ባከበርን ነበር ፡፡ ትሕትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለዝማሬና ለንስሐ ያበቃል ፡፡ አበባ ካልታሸ አይሸትም ፣ ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ፡፡ ሰውም ትሑት ካልሆነ መልኩ አይወጣም ፡፡ ትሕትና ያወቁትን ያለ ትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም ፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ፣ ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት ራስን አለማወቅ ነው ፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው ፡፡ የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው ፡፡ የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትሕትና ነውና ስታውቅ ትሑት ሁን ፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ፡፡ ቀና የሚሉት ዛፎች ግን ፍሬ የሌላቸው ናቸው ፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወቅከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ ፡፡ በአንድ ጥቅስ ጫካ የሚገቡ የአቡጊዳ ሽፍቶች ግን ትዕቢተኞች ናቸው ፡፡ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይባላል ፡፡ ቁንጫም እንደ ልቡ ይዘላል ፣ ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ፡፡ ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው ፡፡ ባዶ ሰው ከቀድሞ የከፉ የሰባት ኣጋንንት ማደሪያ ይሆናልና እባክህ ባዶ አትሁን ፡፡

ትሕትና የልብ ነው ፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው ፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው ፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግሥት ፣ መንግሥተ ሥላሴን እየሰበክህ ትሑት ልትሆን ይገባሃል ፡፡ ትልቁን ትሕትና ነገረ ሥጋዌን እየተናገርህ ትሑት መሆን ያስፈልግሃል ፡፡ ተዋሕዶ ማለት ትሕትና ማለት ነው ፡፡ ባለጠጋው መለኮት ከድሃው ሥጋ ጋር የተዋሐደበት ማለት ነው ፡፡ የሥጋ ድህነት ለመለኮት ፣ የመለኮት ብልጥግና ለሥጋ እንዲነገር የፈቀደው ትልቁ የትሕትና ትምህርት ቤት ምሥጢረ ሥጋዌ ነው ፡፡ ምስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን ፣ ኃጢአተኞችንና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው በተዋሕዶ አታምንም ማለት ነው ፡፡ የተዋሕዶ ምሥጢር ሲገባህ በቀራጮችና በኃጢአተኞች አታፍርም ፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ ፡፡

የስድብ አምሮትህን ለመወጣት “ውሾች” ይላል ቃሉ ፣ የነቀፋ ጥማትህን “ተኩላ” ይላል ወንጌሉ እያልህ ከተወጣኸው ኃጢአትና በቅዱሱ ነገር መበደልህ ነው ፡፡ ውሻ ፣ ተኩላ ያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማበደር አይደለም ፡፡ ትሕትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም ፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም ፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሑት ሁን ፡፡ የበላይ የበታች ሁሉም ልቡ ጎረምሳ ሁኗልና የሚያስተነፍስ መዓት ሳይመጣ ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ ፡፡ ትሕትናን በማጣት ያሳዘንከውን እግዚአብሔር በብዙ ትሩፋት አታስደስተውም ፡፡ ትሕትና የእምነት መጀመሪያ ነውና ፡፡

መዓዛ ሠናይ

19 Nov, 11:05



ድርሳን በእንተ ማርያም ኃጥእት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን አምስት)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ክቡር የሆነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሽቱ ስለ ቀባችው ኃጥእት ሴት የተናገረው ድርሳን ይህ ነው ጸሎቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡፡ ሥራን ሁሉ እንሰማ ዘንድ እንደሚገባም እንቀበለው ዘንድ ተገቢ ነው አለ፡፡ ለንጉሡ እንደ ሥልጣኑ ገናንነት መጠን፣ ለሹሙም እንደ አገዛዙ መጠን፣ ለመስፍኑም ለምስፍናው እንደሚገባው መጠን ጸጋው ለአንዱም ለአንዱ ለየራሱ እንደሚሰጠው ይህ ነገር የታወቀ ነውና፡፡

ይህም ለዚህ ለኃላፊው ዓለም ነው፡፡ ለሚያልፈው ሥጋዊ ዓለም እንደዚህ ከሆነ ይልቁንም የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ ወደ ሆነው አምላክ፡የሚያቀርበንን በጎ ሥራ እንፈልግ ዘንድ የቅዱሳን አባቶቻችንና የሰማዕታትን መታሰቢያ በዓላቸውን እናደርግ ዘንድ የሚገባን አይደለምን? መጨረሻ የሌላትን መንግሥተ ሰማያትንም እንወርስ ዘንድ በፍጹም ደስታ እንቀበለው ዘንድም የሚገባ ነው፡፡

ተዘጋጅተው የጌታቸውን መምጣት እንደሚጠብቁ ባሮችም የተዘጋጀን ልንሆን ይገባል፡፡ ለዚህ ኃላፊ ለሆነው ዓለም ከንጉሥ ወይም ከመኰንኑ ትእዛዝ በወጣ ጊዜ እነሆ መልእክቱን ፈጽመው ከፍ ከፍ ሲያደርጉትና ሲያከብሩት እንመለከታለንና፡፡

ለዚህ ለኃላፊው ዓለም እንዲህ የሚያደጉ ከሆነ ክብር ይግባውና በነገሥታና በባለሥልጣናት ላይ ኃይልና ሥልጣን ያለውን የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዛትን ከዚህ እጥፍ ከፍ ከፍ ልናደርጋቸውና ልናከብራቸው አይገባምን? ቅዱስ ወንጌል ጌታው በመጣ ጊዜ በጎ ሥራ ሲሠራ ያገኘው አገልጋይ ብፁዕ ነው ይላልና፡፡

በበጎ ሥራ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ፣ ሕሊናችንንም ብሩህ እናደርግ ዘንድ በነገር ሁሉ ዐይነ ልቡናችንን ወደ እግዚአብሔር እናነሣ ዘንድ በዚህ በኃላፊው ዓለም ጭንቀትም የማንጨነቅ፡እንሆን ዘንድ ይገባናል፤ የማያልፈውንና የማይጠፋውን ትተን በሚያልፈውና በሚጠፋው የምንደክም ከሆን ግን እነሆ ልብ እንደሌላቸው እንደ ሰነፎች እንሆናለን፡፡....

ይቀጥላል......
(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 105-151)

መዓዛ ሠናይ

19 Nov, 11:05



ድርሳን በእንተ ማርያም ኃጥእት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን አምስት)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ክቡር የሆነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሽቱ ስለ ቀባችው ኃጥእት ሴት የተናገረው ድርሳን ይህ ነው ጸሎቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡፡ ሥራን ሁሉ እንሰማ ዘንድ እንደሚገባም እንቀበለው ዘንድ ተገቢ ነው አለ፡፡ ለንጉሡ እንደ ሥልጣኑ ገናንነት መጠን፣ ለሹሙም እንደ አገዛዙ መጠን፣ ለመስፍኑም ለምስፍናው እንደሚገባው መጠን ጸጋው ለአንዱም ለአንዱ ለየራሱ እንደሚሰጠው ይህ ነገር የታወቀ ነውና፡፡

ይህም ለዚህ ለኃላፊው ዓለም ነው፡፡ ለሚያልፈው ሥጋዊ ዓለም እንደዚህ ከሆነ ይልቁንም የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ ወደ ሆነው አምላክ፡የሚያቀርበንን በጎ ሥራ እንፈልግ ዘንድ የቅዱሳን አባቶቻችንና የሰማዕታትን መታሰቢያ በዓላቸውን እናደርግ ዘንድ የሚገባን አይደለምን? መጨረሻ የሌላትን መንግሥተ ሰማያትንም እንወርስ ዘንድ በፍጹም ደስታ እንቀበለው ዘንድም የሚገባ ነው፡፡

ተዘጋጅተው የጌታቸውን መምጣት እንደሚጠብቁ ባሮችም የተዘጋጀን ልንሆን ይገባል፡፡ ለዚህ ኃላፊ ለሆነው ዓለም ከንጉሥ ወይም ከመኰንኑ ትእዛዝ በወጣ ጊዜ እነሆ መልእክቱን ፈጽመው ከፍ ከፍ ሲያደርጉትና ሲያከብሩት እንመለከታለንና፡፡

ለዚህ ለኃላፊው ዓለም እንዲህ የሚያደጉ ከሆነ ክብር ይግባውና በነገሥታና በባለሥልጣናት ላይ ኃይልና ሥልጣን ያለውን የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዛትን ከዚህ እጥፍ ከፍ ከፍ ልናደርጋቸውና ልናከብራቸው አይገባምን? ቅዱስ ወንጌል ጌታው በመጣ ጊዜ በጎ ሥራ ሲሠራ ያገኘው አገልጋይ ብፁዕ ነው ይላልና፡፡

በበጎ ሥራ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ፣ ሕሊናችንንም ብሩህ እናደርግ ዘንድ በነገር ሁሉ ዐይነ ልቡናችንን ወደ እግዚአብሔር እናነሣ ዘንድ በዚህ በኃላፊው ዓለም ጭንቀትም የማንጨነቅ፡እንሆን ዘንድ ይገባናል፤ የማያልፈውንና የማይጠፋውን ትተን በሚያልፈውና በሚጠፋው የምንደክም ከሆን ግን እነሆ ልብ እንደሌላቸው እንደ ሰነፎች እንሆናለን፡፡....

ይቀጥላል......
(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 105-151)

መዓዛ ሠናይ

18 Nov, 05:56


ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡

ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡

ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡ ዝም እንል ዘንድ የሚቈጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው፡፡
/#ንስሐ - #በቅዱስ_ኤፍሬም #መቅረዝ_ዘተዋህዶ_ብሎግ/

መዓዛ ሠናይ

17 Nov, 05:33


ህዳር8 ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ(ኪሩቤል) በዓላቸው ሲሆን ዳግመኛ የአባ ኪሮስ ቅዳሴ ቤታቸው የተከበረበት አመታዊ ክብረ በዓል ነው
ከእመቤታችን,ከአባ ኪሮስ እና ከቅዱሳን ኪሩቤል ረድኤት በረከት ያካፍለን

መዓዛ ሠናይ

17 Nov, 04:00


🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

የፈለጉትን መርጠው ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖

መዓዛ ሠናይ

16 Nov, 11:13


"ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋና፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

መዓዛ ሠናይ

15 Nov, 05:44


ህዳር6 እመቤታችን ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በተመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቁስቋም የገቡበት ዓመታዊ በዓል

መዓዛ ሠናይ

12 Nov, 08:01


ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ሰው አንድ ታላቅ አባትን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ "አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነበንብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደእነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፤ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ የአፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?"

እርሳቸውም፦ "ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም በአፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው። አጋንንትን ለማባረርም ጥቅም ነውና። ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ትደርሰልሃለች፤ ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡" ሲሉ መለሱለት።

(ምንጭ፦ ፍኖተ አእምሮ)

መዓዛ ሠናይ

08 Nov, 09:00


ከቅምሻ የቀጠለ
(ከኤፌሶን ወንዝ ከዲያቆን ሄኖክ መጽሐፍ)
በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ

ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው። አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም። "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል። ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው::  አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል::

ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ። "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ፩ኛ ቆሮ. ፫፥፲፯ ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን? "አሳያቸዋለሁ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ። እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም። ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም። ፈጥነውም ይረሱሃል። ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን። ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ጸጉር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል። እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም። እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም። አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል።

በምሳሌ ልንገርህ፦ ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ። ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው። አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች። እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ። (፩ኛ ቆሮ. ፫፥፩፮-፳፰)

ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል። ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል። በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍጀ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል። እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም። "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም። ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል። "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. ፲፰፥፴፪

የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም። ራሱን መግደሉ ነው። እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው።

ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው። ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም። በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ። አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም፣ በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"

"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. ፲፮፥፳፯-፳፰ ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው።

ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው? የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ። ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን። ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?" ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ።

ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው። የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ። ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው። እንዲህ በለው "ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ" ሚክ. ፯፥፰

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 9-14)

መዓዛ ሠናይ

07 Nov, 13:13


++++++ጠባቧ_መንገድ++++++

"በተጨባጭ እውነታ ሰፊውንና ልቅ የኾነውን መንገድ ይዘን ሳለ ጠባቡንና የቀጠነውን መንገድ እየተከተልን እንደ ኾነ በማሰብ እንዳንታለል በራሳችን ላይ ቅርብ ትኲረት እናድርግ። ቀጥሎ የሰፈረው ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን እንደ ኾነ ያሳይሃል፦ ሆድን ማጎስቆል (ስስትን መግደል)፣ ትጋሃ ሌሊት (ሌሊቱን ሙሉ መቆም)፣ ጥቂት ውኃ መጠጣት፣ ቍራሽ ዳብ መብላት (ከፊለ ኅብስት)፣ በተዋርዶ ድርቅ መንጻት፣ መናቅ፣ ፌዝን መቀበል፣ መሰደብ፣ የገዛ ፈቃድን ቆርጦ መጣል፣ በሚያስቆጣ ነገር መታገሥ፣ ባለ ማጉረምረም ንቀትን መታገሥ፣ ስድቦችን ቸል ማለት፣ ያልተገባ ጠባይን ጸንቶ መታገሥ፤ ሲታሙ አለመቆጣት፣ ሲዋረዱ አለመቆጣት፣ ሲነቀፉ ትሑት መኾን ነው። የገለጽናቸውን ጎዳናዎች የሚከተሉ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴ 5፡3-13።" እንዲል ዮሐንስ ዘሰዋስው። (ሳሙኤል ፍቃዱ (ተርጓሚ)፣ ምዕራግና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 102)።

በዚህ አባት ጽሑፍ ውስጥ አንደኛ ራሳችንን መመርመር እንዳለብን ተገልጿል። ልቅ በኾነው ሰፊ መንገድ በተባለው የዓለማዊነት መንገድ ላይ መኾን አለመኾናችንን በትኩረት እንድናስተውል ምክረ ሐሳብ ቀርቧል። ኹል ጊዜም ቢኾን ትክክለኛ ወደ ኾነው መንገድ ለመግባት አስቀድሞ የቆምንበትን መንገድ እና በዚያ መንገድ እንድንጓዝ ያደረገንን ውስጣዊ ፍላጎት መረዳት ያስፈልጋል። ምን ያህልስ ጊዜ ልቅ በኾነው የኃጢአት መንገድ ተጉዘን ይኾን? ምን ያህልስ የዚያ መንገድ ጣዕም በውስጣችን ቀርቶ ይኾን? እንዴትስ ከዚያ መንገድ መውጣት እንችላለን። እያልን በእርጋታ ለራሳችን ጥያቄ እያቀረብን ራሳችንን እንመርምር።

ኹለተኛው መሠረታዊ ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ የተገለጸበት ነው። ጥቂት መመገብን ከመለማመድ ጀምሮ ማንኛውንም ክፉ የተባሉ ነገሮችን የሚያደርጉብንን መታገሥ ተገቢ መኾኑን ያስረዳል። መንገዱን ጠባብ ያሰኘውም፥ የተገለጹትን ነገሮች ለመተግበር እጅግ የሚከብዱ ስለ ኾነ ነው። ጽድቁንና መንግሥቱን እያሰብን የምንኖር ከኾነ ግን ከባድ ሊኾኑ አይችሉም። ጠባቡ መንገድ ጣዕመ መንግሥተ እግዚአብሔርን እያሰቡ ኃጢአትን መጥላትን ማዕከል ያደረገ ነውና። የሚንቁንን፣ የሚሰድቡንን፣ የሚያሙንን መታገሥ ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ ነው። በእውነትም የሚጠሉንን ላለመጥላት እየታገልንን ኹሌ ራሳችንን ትዕግሥትን ብናለማምድ እግዚአብሔር ይረዳናል። ትዕግሥት በእኛ ጥረት ብቻ ሳይኾን ከእግዚአብሔርም ጸጋ ኾኖ የሚሰጥም ነገር ነውና። እኛ ከልባችን ክፉን በትዕግሥት ስንቀበል እግዚአብሔር ጽናቱን ይሰጠናል። የጠባቡ መንገድ መድረሻው መንግሥተ እግዚአብሔር መኾኑን በሕሊናችን ውስጥ አስቀምጠን፥ መንግሥቱን እያሰብን እንኑር። አንድ ሯጭ ትኲረቱን በሙሉ የሚያደርገው ቀድመውት ያሉ ተወዳዳሪዎች ላይ እንደ ኾነ ኹሉ እኛም ትኲረታችንን ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር አቅጣጫ ካደረግን በእኛ ላይ የሚደረጉ ክፉ ነገሮችን ኹሉ ሳናያቸው ማለፍ እንችላለን።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
           

መዓዛ ሠናይ

06 Nov, 13:49


የጌታ ስቅለት በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡”
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ››
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ›› 
ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡››
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

መዓዛ ሠናይ

06 Nov, 13:49


አልቆም ያለ ደም

"በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" ሉቃ. ፰፥፵፬

ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም። ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው። በልብሱ ጫፍ ብቻ። ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው። የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው።

በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው? ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው። የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን? ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዓሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት። መድኃኔዓለም እንዲህ ነው። ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል፤ በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል። ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል። እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ።

ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው? ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ? እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው። ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ። ላቆመው ብል አልቆም አለኝ። ያላሰርኩበት ጨርቅ፣ ያልሞከርኩት ቅባት፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም። ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም። እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው። ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል።

ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው። ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን። ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ። የእኔን ደሜን መግታት ላንተ ምንህ ነው? ደምህንስ አፍስሰህልኝ የለ? እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር። እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ። በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ። እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል። እነጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 168-170)

መዓዛ ሠናይ

03 Nov, 07:44


🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

የፈለጉትን መርጠው ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖

መዓዛ ሠናይ

02 Nov, 10:27


📚ይህንን መንካት ያለባቸው ኦርቶዶክስ ብቻ ናቸው

የቱን መፅሀፍ ይፈልጋሉ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📚 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካትመፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ 📖▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📘📚 መፅሐፍ ቅዱስ 📘📚 የዋልድባ ገዳም ታሪክ📘📚 መጽሐፈ አክሲማሮስ 📘📚 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት   📘📚 መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት📘📚 ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን 📘📚 ሐይማኖተ አበው📘📚 ራዕየ ማርያም 📘📚 መልክዓ እግዚአብሔር 📘📚 ታቦተ ፅዮንን ፍለጋ📘📚 ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ📘📚 መርበብተ ሰሎሞን 📘📚 የቶ መስቀል ትርጉም📘📚 ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ 📘📚 የ666 ሳይንሳዊ ምስጢር 📘📚 ህይወተ ቅዱሳን 📘📚 ውዳሴ ማርያም 📘📚 እመጓ📘📚 ዝጎራ 📘📚 መርበብት 📘📚 አንድሮሜዳ 1 & 2 📘📚የሳጥናኤል ጎል 1 - 4እና ሌሎችንም መፅሐፍት የሚያገኙበትመንፈሳዊ የቴሌግራም ቻናል ነው ።አሁኑኑ 𝐉𝐎𝐈𝐍 ብለው ይቀላቀሉን▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

2,889

subscribers

139

photos

6

videos