ማስያስ/@Masiyas @masiyas Channel on Telegram

ማስያስ/@Masiyas

@masiyas


በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ቻናል ነው። ማቴዎስ ፲፩፥፳፰-፴ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"
ዲ/ን ግዕዝ ብንያም። +251918031244 ይደውሉ ይጠይቁ።
@Geez44

ማስያስ/@Masiyas (Amharic)

የማስያስ ቻናልnበዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ቻናል ማስያስ ነው። ማቴዎስ ፲፩፥፳፰-፴ አባይ ነው - "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" እናንተ ካፒቲክ። ግዕዝን ብንያምመን ለቅሼ ይደውሉ ይጠይቁ። @Geez44 በድምጽ እና በመንገድ ድርጊቱን ይመልከቱ። ለማስወገድ እማራ ቴሲያን በማቅረብ መፍቼያ እንስሳ ፓይት በማፍጠር እንዲመጣ፣ እና ለበጎ የቆዳ እንዲሆን፣ ለንፁሃን ትኩስ ለፌደራል ለመረዳም ዛሬ አስቻልሌን። ለቀጠሊ ስካል ባባቶ የምንሰብን፣ ለማለፍ አሰሏ። ስንል ቻናል፡ ማስያስ በቅርቤ ካገኘንት እትም ብሎአል።

ማስያስ/@Masiyas

14 Jan, 16:28


አባቶቻችን እንዲህ አሉ!

ክንፍ የሌላት ወፍ ትጥቅ የሌለው ወታደርና የማይጸልይ ሃይማኖተኛ አንድ ናቸው።
................
(ዜና አበው)

ሰው ለጸሎት ሲቆም ሰይጣን ይቀመጣል። ሰው ጸሎት ሲያቋርጥ ሰይጣን ሥራ ይጀምራል።
................
(ዜና አበው)

ጌታ ሆይ
ታላቅ ሲሆን
ታናሽ የሆነ
ንቁ ሲሆን የተኛ
ንጹሕ ሲሆን የተጠመቀ
ሕያው ሲሆን የሞተ
ንጉሥ ሲሆን ራሱን ያዋረደ
እንደ አንተ ያለ ማን አለ?
......................
(ቅዱስ ኤፍሬም)
......................

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

14 Jan, 08:22


እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

ባዶነት ሲሰማን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ማመን ይገባል ። ትልቁ ባዶነት ያለሰው ሳይሆን ያለ እግዚአብሔር መሆን ነው። የቀጠልነውን ኃጢአት ማቆም ፣ ያቆምነውን ጽድቅ መጀመር የባዶነት መድኃኒት ነው። ማኅበራዊነት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። የምንሰጠውም የምንቀበለውም አለ።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

11 Jan, 07:27


ሰው ማለት እንዳንተ ነው

ክፍል ፪

"ሰው ማለት ልክ እንዳንተ ነው። ራስህን ፊት ለፊትህ ማየት ስላቃተህ እንጂ ያ ሰው ማለት አንተ ነህ። አንተ ማለትም ያ ሰው ነህ። ስልክህ ተጠልፎ ሲያስተጋባ የገዛ ድምፅህን መስማት እንደሚያስደነግጥህ ሁሉ ፣ የሰውዬውን ድምፅ ስትሰማ የደነገጥኸው ራስህን ስለሰማኸው ነው። ሰውዬው ያደረገው አንተ የምታደርገውን ነው። ዛሬ ባታደርገው ነገ የምታደርገውን ነው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ እነዚያ የወደቁትን ትወድቀዋለህ ፣ እነዚያ የወጡትን ትወጣዋለህ። ምናልባት በዚያ ሰውዬና ባንተ መካከል ያለው ልዩነት እርሱ በመናገሩ አንተ ዝም በማለትህ ነው። የሁለታችሁም ኅሊና ግን ያው አረም ያለበት ማሳ ነው ። ጠዋት ስትነሣ ያለው ማንነትህ ቀን ላይ እንደ ገጠመህ የቆሸሸ ሰውዬ ነው። ሰውዬው ዋለበት አንተ አረፈድክበት እንጂ ሰው ማለት እንዳንተ ነው ። የአንድ ቀን ውኃ ሲያጣ ራሱን መቀበል የሚያቅተው ማንነት የተሸከምህ ነህ። በውስጥህ የሚበቅሉት ነገሮች ከደጅ የመጡ አይደሉም። ጊዜ የገለጣቸው አዳማዊነትህ ነው። ሰው ማለት እንዳንተ ነው ራራ። ሰው ማለት እንዳንተ ነውና አትደንብር።"

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

10 Jan, 19:08


ሰው እንዳንተ ነው
ክፍል ፩

ዛሬ ላይ ቁሞ ትላንትን በትዝታ ፣ ነገን በስጋት የሚኖር ሰው ማለት እንዳንተ ነው። ዛሬን ለመኖር የማይደፍር ፣ በሰንጣቃ ዓለት እንዳለ በትላንትናና በነገ መካከል የሚተክዝ ነው። ሰው ማለት እንደ አንተ ነው። እውነቴን ነው ፣ የቅዱሳን አምላክ ምስክሬ ነው ፤ የተሰማህን ያ ሰው ተሰምቶታል ፣ ያመመህ ሕመም እዚያ ሰውዬ ጋ እየጀመረ ነው። ሰው ማለት እንደ አንተ ነውና ኅሊናው ሳይወቀስ አይቀርም። ክፋት ሲያበዛ ፣ በበደል ላይ በደል ሲጨምር ፣ ዝምታህን ሰብሮ ክፉ ሊያናግርህ ሲሻ ውስጡ እየተሰቃየ ነው ፣ ባንተ ስህተት ውስጥ ለመደበቅና እፎይታ ለማግኘት እየፈለገ ነው። አንተም ብትሆን እየበደልካቸው ዝም ሲሉህ ያምሃልና ዠ። በጣም ክፉ ስትሆን የሚተፋህ ፣ በጣም ደግ ስትሆን ሰስቶ የሚርቅህ ሰው ማለት እንዳንተ ነው። እንደ አንተም ስለሆነ መሸነፍን የማይፈልግ ይቅርታ ማለትን እንደ ተራራ የሚያይ ነው።

ሰው ማለት እንደ አንተ ነው።

ሲያጠፋ ትክክል የነበረ ትንሽ ቆይቶ ግን ኅሊናው የሚቆስልበት ነው። ሰው እኮ እንደ አንተ ነው ፣ እየራበው በልቻለሁ የሚልህ ፣ ተበድሮ ድግስ የሚደግስልህ ባለ ይሉኝታ ነው። ሰው ማለት እንደ አንተ ነው። መልካሙን ቀን የትላንትን ጥሩ ጊዜ መመለስ ቢያቅተው እውቅና እንኳ ለመስጠት ረጋ ያላለ ነው። አዎ ሰው ማለት እንዳንተ ነው። ቀስት ሁሉ ወደ እርሱ የተነጣጠረ የሚመስለው ፣ አማርኛ የሚቆረጥመው ፣ ፀጉር የሚሰነጥቀው፣ “እንዲህ ያለው ምን ለማለት ፈልጎ ነው ?” የሚለው

ሰው እንዳንተ ነው።

አንተ እርሱን ትፈራዋለህ ፣ እርሱ አንተን ይፈራሃል ፤ በግልጽ ያላወራችሁ መንጋ ፈሪዎች ናችሁ። ምክንያቱም ሰው ማለት እንዳንተ ነውና። በጠጅ ጀምሮ በቅራሪ የሚጨርስ ፣ በጉዳትህ በአንድ ዓይኑ እያለቀሰ በአንድ ዓይኑ የሚስቅ ሰው ማለት እንዳንተ ነው። ሬሳ አስቀምጦ የሚስቅ ፣ ሲደነግጥ “ጥርስ ባዳ ነው” የሚል ሰው ማለት እንዳንተ ነው። ትላንት ስንዴ ዘርቶ ስንዴ ያጭድ ነበር ፣ ዛሬ ገብስ ቀጥሎም እንክርዳድ በማጨዱ ግራ የተጋባ ፣ ሰው ማለት እንዳንተ ነው። ፊትህን እያየ ጀርባህን የሚያጠና ፣ ሳሎን አስቀምጠኸው ጓዳ የሚገባ ፣ ለነገ አስበኸው ማምሻ የማይገኝ ፣ ለዓመት ሰፍረኸው ለዕለት የሚያልቅ ሰው ማለት እንዳንተ ነው። በከመርከው ቊጥር የሚወርድ “የተልባ ስፍር” ሰው ማለት እንዳንተ ነው ፣ መንሸራተት የማይደክመው። አዎ አምላከ አበው ምስክሬ ነው ፣ ሰው ማለት ልክ እንዳንተ ነው።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

10 Jan, 19:05


ተመስገን

በራሳችን ባንረካም ፣ ባንተ ደስ ይለናል። አንተ ነጻ አውጥተኸን ራሳችንን አስረን፣ አንተ ሥራችንን ሠርተህልን እኛ ራሳችንን አስጨንቀን የምንኖር ብንሆንም ፤ አሁንም ባንተ ደስ ይለናል። እኛ እኛ ባንሆንም ፣ አንተ አንተ ነህ ። እንደ እኛ የጠፋን እንዳንተ የተገኘን ነን። ብዙ ሳለን አንድ አንተን መውደድ አቃተን ፣ አንዱ አንተ ግን እኛን ሁሉ ወደድኸን። ሰው ሳይቸግረው ይቸገራል፣ መከራ ሲርቅለት ወደ መከራ ይሄዳል። ከእኛ ጎዶሎ ፣ ካንተ ሙሉ ነው ተመስገን።

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

09 Jan, 17:21


መልኳም የአምላክን መልክ ይመስላል!

"በዓለም የተወለደ ሕጻን ሁሉ እናቱን ወይም አባቱን ይመስላል ይባላል። አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ እናት የወለደችውን መሰለች።"

ማስያስ/@Masiyas

09 Jan, 16:58


ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል።

ትን.ዕን፦ 2፥4: "ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።"

ይህ ክፍል የጻድቅ አኗኗር እንዴት እንደሆነ ይናገራል። ሰዎች በሥጋ አቅማቸው በአእምሮ ብስለታቸው ሌሎችንም ባበረቱበት የብርታት አዋጃቸው መቆምና መኖር የሚሳናቸው ጊዜ ብርቱ ነው። የሰው ልጆች ሁልጊዜ ሙሉ በሆነ ልብ ሊጓዙ አይችሉም። አንዳንድ ጊዜ ያመነታሉ። የሰው ልጆች የማያውቋትን ሕይወት ምንነቷን ማይታወቀውን ዛሬን የሚያጠራጥረውን ነገን እንደተጋፈጡ ይሰማቸዋል እንዴት ነው ምኖረው እንዴትስ ነው የሚኖረው ብለው ለራሳቸውም ለልጆቻቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ለሕዝባቸውም ይጠይቃሉ። አንዳንድ ጊዜ እነርሱ ብቻ ተናጋሪ ስለሆኑ እግዚአብሔር ሲናገር መስማት ይሳናቸዋል። የገዛ ድምጻቸውን እንደ ገደል ማሚቶ መልሰው እየሰሙ የሚጨነቁ ብዙዎች ናቸው። ይህ ዘመን ብዙ ሰዎች በጥያቄ የሚመላለሱበት ዘመን ነው። ይሄ ዘመን ሰዎች እኔ ማነኝ ብለው ራሳቸውን የሚጠይቁበት ሰዎች ማናቸው ብለው ስለሰዎች የሚጠይቁበት ሀገር ምንድን ነው ብለው ስለ ሀገር ፍች የሚፈልጉበት ዘመን ነው። አዎ ሰዎች በሥጋ መኖር ደክሟቸዋል። በፍልስፍና መኖር ደክሟቸዋል። አይዞችሁ የሚለው ቃል ቢያረፍድ እንጂ አያውላቸውም። ሰዎች እየደነዘዙ መኖርም በሱስም ተደብቆ መኖርም ደክሟቸዋል። ታዲያ የሚያኖረን ምንድን ነው?

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል!

አዎ እግዚአብሔር መኖርን ሰጥቶ መኖሪያ ኃይሉን አይነሳም።

"መድኃኔዓለም እከክ ሰጥቶ
ማከኪያ አይነሣም።" ይባላል።


ዕለት ዕለት ከእግዚአብሔር ኃልን ካልተሞላን ሥጋችን ሊጸና መንፈሳችን ሊበረታ መንፈሳችን ሊለመልም አይቻለውም። የሰው ልጅ ትልቅ ውድቀቱ የሚጀምረው ከእግዚአብሔር ጥገኝነት ወጥቶ በራሴ እቆማለሁ ብሎ ማሰብ ሲጀምር ነው። እኛ የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ጥገኞች ነን። እኛ የእግዚአብሔር ዕዳው ነን። የሰይጣን ኃይሉ ሰው ነው። የሰው ኃይሉ እግዚአብሔር ነው። ሰይጣን ከእኛ ጥገኛ የሆነው ለራሱ ጥቅም ነው። ተባይ ከራሳችሁ ፀጉር እናንተ ባለመንከባከባችሁ ምክንያት ይፈጠራል። ከእናንተ አውጥታችሁ ስትጥሉት እናንተን ፍለጋ ይኳትናል። ከእናንተው ክፋት የተነሣ ይነሣል። ሁልጊዜም የሚቦጠቡጠው የእናንተን ኃይል ነው። ሕይወት የገዛ ራሷ ስትቆሽሽ ለገዛ ራሷ የሚያስደነግጥ መጥፎ መንፈስ ትፈጥራለች።
አዎ ለእግዚአብሔር እናስፈልገዋለን። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ከምናስፈልገው በላይ እግዚአብሔር ለእኛ ያስፈልገናል። የሰው ልጆች በዘመናት ሁሉ በደረሰባቸው አሰቃቂ ነገር ሊነገር ሊተረጎም በማይቻል መከራ ውስጥ እያለፉ እግዚአብሔርን ሞግተዋል። ዓይንን የፈጠረ እግዚአብሔር ይህንን አይቶ ማለፍ እንዴት አስቻለው? ጆሮን የፈጠረ እግዚአብሔር ይሄንን ሰምቶ ምነው ዘገየ? ይላሉ። እግዚአብሔርም እንደሌለ ዝም ይላል። እግዚአብሔርም እንደማይሰጥ ይዘገያል። እግዚአብሔርም ግድ እንደሌለው በሕይወት ሲንጎማለሉ ለጊዜው ይዘገያል። ታዲያ በዚህ ሁሉ ውስጥ ከእግዚአብሔር ከራሳችን ከቀልባችን ከሰላማችን ጋር ለመኖር ሞተሩ ምንድን ነው?  ካልን እምነት ነው። እምነት የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ማየት ነው። እምነት የአሁኑን ሳይሆን የሚመጣውን መጠበቅ ነው።  አዎ የአሁኑ ያዝላል አዎ የአሁኑ ለወሬም አይመችም ከአቅማችን በላይ ብንጠራራ የተራራውን ጫፍ አንደርስበትም። አዎ የአሁኑ ምንም ብንለፋ የማይሞላ ሸለቆ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ጥያቄ መልስ አይሰጠንም ራሱ እግዚአብሔር መልስ ነው። ብዙዎቻችን እግዚአብሔር መልስ እንዲሰጠን እየጠበቅን ነው። አንዳንዶቻችን በጸሎት እንጠብቃለን። ሌሎቻችን በፍልስፍና እግዚአብሔርን እንጠብቃለን። እንሞግታለን። እግዚአብሔርን ያገኘን መስሎን አገልጋዮቹን ለማፋጠጥ ወረቀታችንን መገላለጥ እንጀምራለን። እግዚአብሔር ግን መልስ አይሰጠንም። ራሱ እግዚአብሔር በሕልውናው መልስ ነው።

በደርግ ዘመን ረኃብ ተነሣ ለዘለቄታ መፍትሔ ብለው ያሰቡት ነዋሪውን አፈናቅሎ በሌላ ቦታ ማስፈር ነበረ። ነዋሪው ግን "ረሃብ ያልፋል ለሚያልፍ ቀን የተወለድንበትን የወለድንበትን ያደግንበትን የኖርንበትን ቀየ ማኅበራዊ ኑሯችንን ማጣት የለብንም" ብሎ አዘነ። ነገር ግን ኀዘኑ መልስ አላገኘም። ያ ሕዝብ በሠፈራ ስም ተፈናቀለ። ባል ከሚስት ተለያየ አብሮ የኖረ ማኅበራዊነቱ ፈረሰ አላማጁ ለማጅ ሆነ የኖረው መኖሩ ተሰረዘበት ትዝታው ጠፋበት። በዛ ዘመን የነበረው ያ ኀዘንተኛ ሕዝብ እንዲህ ብሎ እግዚአብሔር ወቀሰ።

"አሻቅቤ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ
አንተንም ሠፈራ ወሰዱህ መሰለኝ።"

ብሎ እግዚአብሔርን ሞገተ ገድሎ የማዳን ግጥም ነው። ምነው ጌታ ሆይ ለምን እንዲህ ሆነ እያለ ያ ሕዝብ ስላጣው የማይዳሰስ ሀብቱ አለቀሰ። ሁላችንም በዘመናችን ኑሯችን ውስጥ እግዚአብሔርን የምንሞግትበት ጊዜ ብዙ ነው። እርሱ ግን ሕጻን ልጅ አባቱን እንደሚጠይቀው አባትም የልጁን ጥያቄ ምንም እንኳ ሚዛን የማይደፋ ውኃ የማይቋጥር ቢሆንም እንደ ትልቅ ምርምር እንደ ትልቅ የእውቀት ቃል እንደሚያደምጠው እግዚአብሔር ያዳምጠናል። አዎ እግዚአብሔር ጥያቄያችንን የሚፈራ የሚጠላ አምላክ አይደለም እኛ እግዚአብሔር እያየ ለምን ዝም አለ። እየሰማ ለምን ዘገየ እንላለን። እግዚአብሔር ግን የሚሰራው በእኛ አነሣሽነት አይደለም። እግዚአብሔር የሚሰራው ከእኛ ምክር እየተቀበለ አይደለም። በዘመናት ሁሉ ሰዎች በደረሰባቸው ነገር እግዚአብሔርን ሞግተዋል።
ራስ አዳል የጎጃሙን ንጉሥ ሁላችንም እናውቃለን። በኋላ ተክለ ሃይማኖት የተባሉ ልጆቻቸው በጣም ገጣሚዎች የተባሉ ነበሩ። ታዲያ በድንገት ታመሙ በልጃቸው ተመረዙ ተብሎ የበኸር ልጃቸው በለው አዳል እስር ቤት ተጣለ። ይህ ሰው በጣም ልቡ ተነካ አዘነ በሐሰት ስወነጀል ምነው ጌታዬ ዝም አልክ አለ። በአባቴ ላይ ክፉ እውላለሁ? ይሄ ቀን እንዲህ ብሎ ሰየመኝ ስም አወጣልኝ ብሎ አለቀሰ። ሁላችንም የምናውቀውን ግጥም ገጠመ :-

"የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
አለህም እንዳልል እንዲህ እንዲደረጋል
ልጅ እንዴት ባባቱ መድኃኒት ይምሳል"
ብሎ አለቀሰ ይባላል።

አዎ እግዚአብሔርን የሕልውናውን መገለጫ የሆነውን መምሸቱን መንጋቱን ባየሁ ጊዜ እንዳለ በልቤ አምናለሁ የሚደረገውን ሳይደግሙ ዓለሙን ለእኛ ትተህ የሄድክ ይመስላል። ምነው ጌታ ሆይ ድረስልኝ እያለ በለው አዳል እግዚአብሔርን በለቅሶ ተማጸነ አዎ በዘመናት ሁሉ የሰው ልጆች በደረሰባቸው ነገር እግዚአብሔርን ሞግተዋል። እግዚአብሔርም ለሙግታቸው መልስ ሰጥቷል። ጥያቄያችን ከአንጀት ይሁን እንጂ እግዚአብሔር መልስ አለው። አዎ ለጊዜው እውነት ይዳፈን ይሆናል። ግን ለዘላለም ይጠራል። ለጊዜው ሐሰት አደባባዩን ሞልቶት ሊሆን ይችላል። ግን ለዘለዓለም ላይነሣ ይወድቃል። እውነት ትወድቅ ትነሣለች ሐሰት የወደቀች ቀን ግን ትንሣኤ የላትም። እውነት አትወድቅም አልተባለም ነገር ግን አትጠፋም ትንሣኤ አላት። አማኝ አይሞትም አልተባለም ይሞታል ነገር ግን ይነሣል። የራስ አዳል ሁለተኛ ልጃቸው ራስ ኃይሉ አዳል ይባላሉ። የጎጃምን ሕዝብ ዘርፈሃል በአስተዳደር በድለሃል ብለው ጊዜ ራስ ተፈሪ ይዘው አሰሯቸው ግዛታቸውንም ቀሟቸው። በዚህ ጊዜ ራስ ኃይሉ ኀዘናቸውን ለእግዚአብሔር ገለጡ። ኀዘናቸውን በወቅቱ ፈራጅ ለነበረው ገለጡ።

"ሰው በድዬ ነበር እኔም እንደዋዛ
ቁናው ቁናዬ ነው ትንሽ ዙሩ በዛ"

ይቀጥላል...

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

08 Jan, 09:54


የአበው ተስፋ ተወለደ

አበው መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አደረጉ። በጽድቃቸው እንኳን ሌላውን ራሳቸውንም ማዳን ባልቻሉ ጊዜ የክርስቶስን መወለድ ናፈቁ። አዳም ገነትን አጥቶ ተስፋን ይዞ ወጣ። ከነበረችው ገነት ይልቅ ፣ የገነት ጌታ የእርሱ ልጅ እንደሚሆን በሰማ ጊዜ ልቡ በደስታ ዘለለ። ውድቀቱ ያመጣው መዳን ቢሆን ኖሮ እንኳን ወደቅሁ ባለ ነበር ፣ ለወደቀ ሰው የሚሆን ፍቅር ያለው አምላክ ግን አዳምን ከበደሉ በላይ ካሣ ሰጠው። ተስፋ የሚነገረው/የሚሰጠው በእግዚአብሔር ደግነት ፣ የሚፈጸመውም በእግዚአብሔር ታማኝነት ነው። አበውም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚቀባበሉት ዕንቈ ነበራቸው ፤ እርሱም ክርስቶስ ይወለዳል የሚል ነው። የከፋውና ሁሉ የተነባበረበት ሕፃን “ቆይ አባቴ ይምጣ” እያለ እያለቀሰ ይስቃል። አባቱ እንባውን ያብስለታል ፣ ጠላቶቹን ያሸንፍለታል ። አበውም የክርስቶስን መወለድ ባሰቡ ጊዜ እያለቀሱ ሳቁ።

ጨርሶ እንዳይጨልም ለማታው ክፍለ ጊዜ ጨረቃና ከዋክብትን ያስቀመጠ እግዚአብሔር ፣ የሰው ልጅም በኃጢአት ፣ በመቃብርና በሲኦል ተጨንቆ እንዳይኖር ልደተ ክርስቶስን ተስፋ አድርጎ ሰጠ። አንድ ወንድ ልጅ ይወለዳል እየተባለ ለዘመናት ተስፋ ተደረገ። ያ ልጅ ከተወለደ በኋላም ዳግም ይመጣል እየተባለ ይሰበካል። ከገነት እስከ ምጽአት ፣ ከውድቀት እስከ ፍርድ ቀን የክርስቶስ መምጣት የሰው ልጆች ተስፋ ነው። ይህች ዓለም ያለ ክርስቶስ አድራ አታውቅም። የመጣውና የሚመጣ ጌታ አለን። በመጀመሪያ ምጽአቱ አዳነን ፣ በዳግም ምጽአቱ ይፈርድልናል። በመጀመሪያ ምጽአቱ ከሲኦል ወደ ገነት አፈለሰን ፣ በዳግም ምጽአቱ ከገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያፈልሰናል። ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን። በመጀመሪያው ምጽአቱ አጋንንት አፈሩ ፣ በዳግም ምጽአቱ የናቀን ዓለም ያፍራል። በመጀመሪያው ምጽአቱ ሞት ተገደበ ፣ በዳግም ምጽአቱ መከራ ይገደባል።

አብርሃም አገሩና ተስፋው ሩቅ ነበረ። ክርስቶስ ወደሚወለድበት ምድር ተጠራ። ዕድሜው እየመሸ ቢሆንም ሠርኩን ማለዳ የሚያደርገው ፣ በሞት ላይ ልደት የሚያውጀው እግዚአብሔር በመልካም አሰበው። ለሞት ሲሰናዳ ለሕይወት ተጠራ ። ሌጣውን ሊሞት መሆኑን አምኖ ከተስፋ ጋር ሊቀበር ሲል እግዚአብሔር የብዙዎች አባት አደረገው። የብዙዎች አባት መሆኑን እርሱ አላየም። አብርሃም ጥቂት ልጆችን ብቻ በዓይኑ አየ። እግዚአብሔር ባየለት ነገ ተደሰተ። ተስፋ ማለት እግዚአብሔር ባየልን “ነገ” መደሰት ማለት ነው። አብርሃም የተዘዋወረበትና ድንኳኑን የተከለበት ምድር በኋለኛው ዘመን ክርስቶስ የሚወለድበትና የማዳን ግብሩን የሚፈጽምበት ነው። አብርሃም ወደ ቤተልሔም በሄደ ጊዜ “እኔ በድንኳን ኖርሁ ፣ አንተ በበረት ተወለድህ ፣ ቤት አልባ ሆንህ” ብሎ ክርስቶስን በሩቅ ተሳለመው። ወደ ሞሪያ ተራራ ፣ ወደ ቀራንዮ መጥቶ ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ ባለ ጊዜ ፣ በይስሐቅ ሞት የሚድን ዓለም የለምና የክርስቶስን ቤዛነት ናፈቀ። ከመልከ ጼዴቅ ኅብስትና ጽዋውን ሲቀበል ፣ ዛሬ በሳሌም የተቀበልሁት ኅብስትና ወይን ፣ ነገ በኢየሩሳሌም በታላቁ ካህን በክርስቶስ የሚሰጠው ሥጋና ደሙ ነው ብሎ ተደነቀ። አብርሃም ያመነውና የኖረው የዛሬው አማኝ የሚያምነውና የሚኖረውን እውነት ነው። እምነት በዘመናት መካከል አንድ መልክ ለአማኞች በመስጠት የሚታወቅ ነው።

ይስሐቅን ከሞት ያዳነው ፣ በዱር የተገኘው፣ ያለ ቦታው የታየው ፣ ኃይል እያለው እንደሌለው የሆነው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አብርሃም የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለ ፣ ዮሐንስ መጥምቅም “የእግዚአብሔር በግ እነሆ!” አለ። ያዕቆብ በኤፍራታ ራሔልን ቀበረ። ራሔል በመውለድ ሞተች ፣ ሕያው ልጅን ሰጥታ እርስዋ አንቀላፋች። ራሔል በያዕቆብ መወደድዋ ከሞት አላዳናትም። ወድዶ ከሞት የሚያድን ክርስቶስ ብቻ ነው። መዝሙረኛው “ወዶኛልና አዳነኝ” ያለው ለዚህ ነው። የቤተ ልሔም የቀድሞ ስምዋ ኤፍራታ ነው። ተስፋ ባደረጉት አባቶች ርስት ክርስቶስ ተወለደ። የይሁዳ አንበሳ የይሁዳ ግዛት በሆነችው ቤተ ልሔም ተወለደ። የዳዊት ቤትን አልከዳም ብሎ የቀረው ፣ እናቱ በቤተ ልሔም የሞተችበት ፣ የራሔል ልጅ ብንያም ነው። በታማኙ በብንያም ርስት ክርስቶስ ተወለደ። ዛሬም እርሱ በሚጠብቁት ርስት በፍቅር ፣ በሰላም ይወለዳል። ታማኞችን መለኮት አድራሻ ያደርጋቸዋል። ብዙዎች የከዱትን እኔ አልከዳውም የሚሉ ፣ የቀድሞ ወዳጅነትን የሚያስቡ ዛሬም የክርስቶስ ቤተ ልሔም ናቸው። እርሱ የሚጸየፈው በረትን ሳይሆን ክዳትን ነው።

አብርሃም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ክርስቶስ ከእኔ ወገን ይወለዳል እያሉ ቤታቸውን ንጹሕ አደረጉ። መጻተኝነታቸውን ረሱት። ወደውም ለክርስቶስ ድሀ ሆኑ። በዓለም መጠላታቸውን ናቁት። ነገሥታት አብርሃምን ተጋጠሙት። አንድም ቀን በቤተ መንግሥት አልተጋበዘም። ሁለት ጊዜ ግን ሚስቱን ነጥቀው ፈርዖንና አቤሜሌክ አስደነገጡት። አማኒ በቤተ መንግሥት ለግብዣ ሳይሆን ያመነውን እንዲጥል ይጠራል። እግዚአብሔር ቃሉን አክባሪ ነውና ደግሞም በአብርሃም ላይ የተጠራውን ስሙን አክብሯልና ፣ አሁንም እርሱ የሚወጣበትን ዘር ይከላከላልና ሣራን ከነገሥታት እጅ ፈልቅቆ አወጣት። ክርስቶስ ከነገሥታት ሳይሆን ከመጻተኞች ቤት መወለድን መረጠ። በአብርሃም ድንኳን ሥላሴ አደሩ። ወደ ድንግል ማርያም ሥላሴ መጡ ። አብ አጸናት ፣ ወልድ ልጅ ሆናት። መንፈስ ቅዱስ አከበራት።

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

07 Jan, 09:56


#ዛሬ_እያከበርከው_ያለኸው_በዓል_እንዲህ_ይልሃል፦

#አትጨነቅ
እኔ አምላክህ ላንተ እጨነቃለሁና!

#ደስ_ይበልህ
እኔ ካንተ ጋር ነኝና!

#ተስፋ_አድርግ
ተስፋ እውን እንደሚሆን አይተሃልና!

#ጸልይ
በጸሎት ውስጥ ሁሌ ተአምር አሳይሃለሁና!

#አመስግን
በረከት ሁሉ ተፈቅዶልሃልና።

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

07 Jan, 03:35


የአዳም ተስፋ

የበደለ አዳም ቀና ብሎ ይሄድ ዘንድ ዳግማዊ አዳም ሁኖ መጣ ፣ የስህተት በር የሆነችዋን ሔዋንን ያጽናና ዘንድ ክርስቶስ በተዘጋ ማኅፀን ከሴት ዘር ተወለደ። ገነትን ላጣው አዳም ራሱ ክርስቶስ ገነት ሆኖለት መጣ። ስጦታውን ቢያጣ ሰጪው ዘመዱ ሆነ። ስጦታው የተፈጠረ ነው ፣ ሰጪው ግን ያልተፈጠረ ነው። አዳም ሰማይና ምድር የእርሱ ቢሆኑ ያለ ጌታ ኀዘን እንጂ ደስታ አይሆኑትም ነበር። አዳም የሰማይና የምድር ጌታ ለመሆን አስቦ ከሰይጣን ጋር መከረ ፣ እንኳን ሰማይን ሊያተርፍ ግዛቱ የሆነችውን ምድር አጣ። ክርስቶስ ግን በመወለዱ የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን ዓለመ መንፈስ ፣ ሰይጣንንና ደዌያትን ይገዛ ዘንድ ባለሥልጣን ሆነ። ተጠቃን የሚሉ ወንድ ልጅ  ሲወልዱ ስሙን ደምመላሽ ይሉታል። ክርስቶስም ርስትን ይመልስልን ዘንድ ፣ ጠላትንም ይበቀል ዘንድ ወንድ ልጅ ሆኖ ተወለደ። ክርስቶስ በወንድ አምሳል ስለ መጣ ወንድ ልጅ ክቡር ነው። ክርስቶስ ከሴት ዘር በመወለዱ ከድንግል ማርያም የተነሣ ሴት ሁሉ ክብርት ናት። የሄደችውን ገነት አዳም በዕንባ ፣ አበው በምግባር ፣ ካህናት በመሥዋዕት ፣ ነቢያት በናፍቆት ሊያስመልሷት አልቻሉም። ክርስቶስ ግን በመወለዱ የሰማይ በር ተከፈተ። አዳም በወደቀ ቀን አጋንንት ዘፍነዋል ፣ ክርስቶስ በተወለደ ቀን መላእክት ዘመሩ። ዛሬም በክርስቶስ ልደት የሚዘፍኑ ፣ የሚሰክሩ በአዳም የውድቀት ቀን ከተደሰቱ አጋንንት ጋር ይተባበራሉ። አዳም ሳይወልድ በመበደሉ አንድ ራሴን ነኝ ብሎ ተመክቶ ነበር። ነገር ግን የአባት ዕዳ ለልጅ ይተርፋልና ልጆቹ በደለኛ ሆኑ ። በአንዱ አዳም የተኰነኑ ፣ በአንዱ ክርስቶስ ጻድቃን እንዲሆኑ ፣ ሚዛንም እንዲተካከል ይህ ሆነ።

አዳም በገደል ላይ በመጫወቱ ከጥልቁ ወደቀ። ነገሥታትና ጠቢባን ከገደል ሊያወጡት አልተቻላቸውም። ምድራዊ ሥልጣን ማዕሠረ ኃጢአትን ሊበጥስ ፣ ምድራዊ ጥበብም መቃብርን ሊበዘብዝ አልቻለም። ክርስቶስ ግን ጠቢብ ድሀ ሆኖ መጣ። ጌትነትን ተመኝቶ የሞተው አዳምን፣ ክርስቶስ ክብርን ንቆ ሊታደገው መጣ። የከፍታው ምሥጢር ዝቅታ መሆኑን ሊያስተምረው ክርስቶስ በበረት ተወለደ። ሔዋን ደመኛው ሆና ብትታየው ፣ በእርስዋ ላይ ቢነሣሣባት የመዳኛውን ዘር ያጣው ነበረ። አዳም ይቅርታ በማድረጉ ክርስቶስን አገኘ። ከክርስቶስ የለዩን አንድ ዘመን ላይ ወደ ክርስቶስ ያቀርቡናል። እግዚአብሔር ታሪክን ሲለውጥ ከበደሉን በላይ ይክሱናል። ከቆሸሸው በላይ የሚያጸዳ ባለሙያ አለ። ትልቁ ባለሙያ እግዚአብሔር ምድራዊት ገነትን ላጣው አዳም ሰማያዊ ርስትን ሰጠ። በልጅነት ላይ ክህነትን ደረበለት። መበቀል የፍጡር ጠባይ ነው። እግዚአብሔር ግን ኃይሉን በይቅርታ ገለጠ። ይቅር የሚሉ የሁልጊዜ ብርቱዎች ናቸው። መግደል ብዙዎች ችለዋል ፣ ይቅር ማለት ግን አልቻሉም። ይቅርታ የልዕልና መገለጫ ነው። አባቶችን ከተቀየምን መጀመሪያ የምንቀየመው አዳምን ነው። አዳም የወደቀባትን ቦታ ሳይሆን የተነሣባትን ጎልጎታ እናስታውሳለን።

አዳም ገነትን በራሱ አጣ ፣ በክርስቶስ እንደሚያገኛት ተስፋ አደረገ። ሰው ተስፋ ሰጥቶ ይጸጸታል። እግዚአብሐር ግን ተስፋን እንደ ክብሩ እንጂ እንደ ዕዳ አያየውም። አዳም መውደቅ በቻለበት አቅም መነሣት አልቻለም። ያለ መካሪ የበደሉ ሰዎች በመካሪ ኃይል ሊነሡ ይቸገራሉ። ሰውን ከኃጢአት የሚያላቅቀው ነጻ ፈቃዱ ከኃይለ መንፈስ ቅዱስ ጋር ሲዛመድ ነው። አዳም በሰማይና በምድር ብቸኛ ሆነ። ጥቂት ዘመን በደስታ ኖሮ 5500 ዘመን በስቃይ አሳለፈ። አዳም አባት እናት አልነበረውም ፣ አባትና እናቱ እግዚአብሔር ነበረ። አዳም ሙሉ ስሙ ሲጠራ “አዳም ወልደ እግዚአብሔር በጸጋ” ይባል ነበረ። አባትና እናትህን አክብር የሚለውን ትእዛዝ አዳም ሻረ። አዳም በገነት ውስጥ አነጋጋሪው ፣ የብቸኝነቱ መድኃኒት እግዚአብሔር ነበረ። አሁን ግን ወዳጁን አጣ። እግዚአብሔርም በወዳጁ ቤት ቆሰለ። ክርስቶስ ሰው የሆነው ለአዳም ያለውን ፍቅር ለመግለጥ ፣ የወጣ እንደ ወጣ ይቅር የማይል አምላክ መሆኑን ለማስታወቅ ነው።

አዳም የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሁኖ ተፈጠረ። ክርስቶስ ግን ሊያድነው የዕለት ሕፃን ሆኖ በበረት ተጣለ። አዳም በገነት ብቻውን ነበረ እንጂ ብቸኛ አልነበረም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያለው ብቸኛ አይባልምና። አሁን ሔዋን አጠገቡ ሳለች ብቸኝነት ተሰማው። ብቸኝነት ያለ ሰው ሳይሆን ያለ እግዚአብሔር መሆን ነው። አዳም ተስፋው የክርስቶስ መወለድ ነበረ። ይኸው ተወለደ። እርሱ አሻግሮ መወለዱን አየ ፣ እኛ መለስ ብለን መወለዱን አስተዋልን። ዕለት ዕለት ክርስቶስ መወለዱን የሚያምኑ ጥሙቃን /ተጠማቂዎች በቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ። የእኛ አምላክ አብ የሚወልድ ፣ የእኛ ጌታ ክርስቶስ የሚወለድ ነው። ሰው በመሆኑ አምላክነቱን አልከሰረም። ጌታቸው ባለበት መላእክቱ ተገኝተው ምስጋናውን አቀረቡለት። የዘላለም አባት ፣ በሕፃን መልክ ሲገኝ በመደመም ዝም አሉ። ቅዱስ ገብርኤል ምን ቢያበስር ይህን የልደት ምሥጢር መልመድ አልቻለም። እኔ ደሃው ከመላእክት አእምሮ በላይ ለሆነው ልደትህ ክርስቶስ ሆይ ሰላም እላለሁ!

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

07 Jan, 03:09


ባለጠጋው ደሃ ሆኖ ተወለደ!

በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ! እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ የንጉሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ። ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻን አለቀሰ። በግልጽ እየተመላለሰ እንደ ሰውም ታየ። በጥቂቱ አደገ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ።

ቅዳሴ ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቁጥር :- 15 - 18

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

06 Jan, 19:22


ክርስቶስ ተወለደ #2

ቤተልሔም ክርስቶስ የተራቆተበት ክርስቶስ በሰው የተገፋበት ክርስቶስ ከአድግና ከላህም ሙቀት የለመነበት የተመጸወተበት ነው። እኛ ድሆች ብንሆንም እስከዚህ ደሃ አልሆንም። እኛ ደሃ ብንሆን ግዳች ወድቆብን ነው። እርሱ ደሃ ቢሆን ፈቅዶ ነው። የእኛ ፈቃድማ ዓለሙን ብንገዛው በንነዳው ነው። እርሱ ግን ዓለምን መናቅ ሊያስተምረን እንደምስኪን ሕጻን ሆኖ በደሃ ቤት ደሃ ሆኖ ተገለጠ። የአዳምን እርቃን ይሸፍን ዘንድ እናቱ በመጠቅለያ ጠቀለለችው። በኃጢአተኞች በናዝሬት አድጎ የናዝሬቱ ኢየሱስ ተባለ። የተናቀ የሚመስለውን የአናጢነት ግብር ሙያው አደረገ። ማርያም ሆይ ኢየሱስ የለም? በር ተበላሽቶብኝ ጣራ ተገንጥሎብኝ ግድግዳ ፈርሶብኝ ብለው የሚጠሩት እናት ሆነች። ሥራ በሥራነቱ ክቡር መሆኑን ሊያስተምረን። የሥራ ደረጃ ለሚያወጡ ሰዎች ክርስቶስ በምድር ላይ አናጢ ሆነ። ሚደንቅ ነው። ስለ አናጢው ኢየሱስ ክርስቶስ እያወራን ማነው ዛሬ አናጢን ሚያከብረው። በአህያ ላይ ስለተቀመጠው ጌታ እያወራን አህያን የስድብ ያላደረገ ማነው?

ልደቱ የጌታችን ልደት ትሕትና የተገለጠበት ነው።

ብዙዎቻችን ትሑታን ነን እስኪነኩን ድረስ ተግዳሮቶች እስኪገጥሙን ድረስ የታወቀ ኮ ነው። እኔ ለወደዱኝ ማር ለጠሉኝ ሬት ነኝ ነው ምንለው። ትሕትና ማለት ቀኑ በግድ ሲያስጎነብሰን ማለት አይደለም ወዶ ማጎንበስ ነው። በሚያከብሩን ዝቅ ማለት አይደለም በሚንቁን ፊት በእግዚአብሔር ፍቅር መጽናት ነው። ትሕትና ማለት ዓለምን ጨብጠነው ዕድሉ እያለን ከንቱ ነው ማለት ነው። ትሕትና ማለት በወንድም በእኅታችን ባላቸው ጸጋ መደሰት ነው። በዚህ ዓለም ያሉ ትሕትናዎች ተውኔት ይበዛባቸዋል። ቀራጩ ጋዜጠኛው ዞር እስኪል ድረስ። እኛ ኮ ያለነው እናንተ ስላላችሁ ነው ይላሉ። መለስ ሲሉ እኛ ባንኖር ታልቁ ነበር ይላሉ። የዚህ ዓለም ትሕትና ማስመሰል አለው። ሰይጣን ትሕትና አለው። ሰይጣናዊ ትሕትና ሚባል አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ግን የእውነት ትሑት ነው።  ጌታችን ያለውን አምላክነት በሥጋ ሸሸጎ በደሃ ማንነት ተገለጠ። አዳም የሌለውን ሻተ። ገና ኮ የተፈጠረበትን ምድር መግዛት ማስተዳደር አልጀመረም። ከገነት ወጥቶ እንኳን አላያትም። ገና ኮ አንድ ልጅ እንኳ አልወለደም። ምድሩ አልበቃኝም ብሎ ሰማይም ይገባ'ኛል አለ። በእፀ በለስ ለማግኘት ፈለገ። የዚህ ስድቡ ምንድን ነው ካላችሁ በእፀ በለስ የሚገኝ ከሆነ እግዚአብሔርም አምላክነትን ያገኘው በእፀ በለስ ነው ብሎ ማመን። የባሕርይ አምላክ አይደለኽም ማለት ነው። አዳም የሌለው አምላክነት ፈለገ። ክርስቶስ የሌለውን ሥጋ ከገንዘብ አደረገ። እርሱ ክርስቶስ የሁሉ ወዳጅ ነው። ቤተልሔም የሚናገረው ይህን
ነው። ትሕትና ማለት የሁሉ ወዳጅ መሆን ነው። በቤቴልም ነገገሥታት ነበሩ። በቤተልሔም እረኝች ነበሩ ተገኝተዋል።ከፍተኞችን ዝቅተኞችን በቤተልሔም አገናኘ። ወንጌል ለሁሉም ይገባል ሲል። የዓለም ሁከት መሠረቱ ትዕቢት ነው። ጦርነት ሁሉ መነሻው ትዕቢት ነው። እኔ እበልጥ እኔ አበልጥ ትዕቢት ነው። ጉልቀበታችንን እስኪ እንፈታተሽ የሚል ነው። የጦርነት መሠረቱ ትዕቢት ነው።  የአብዛኛው ቤት መናወጥ መሠረቱ ትዕቢት ነው። የአብዛኛው ትዳር ችግር መሠረቱ ትዕቢት ነው። የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ የሆነ ሰው አለ። አንድ እርምጃ ሲጠየቅ ሺ ይሄዳል። ከቤቱ ሲመጣ እልህ ይጋባል። እሞትላታለው ያላትን እቤቱ ሲመጣ የወደቀ ዕቃ ካላቃና ምንድነው ትርጉም። እሞትልሃለሁ ያለችውን የተዝረከረከ ሸሚዙን ካላነሣችለት ምንድነው ትርጉም። ለዓለም መፍትሔ የሆነውን ትሕትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተግባር ሰበከ። እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝ። በቃል ትሑታን ብዙ አሉ አ!  በእውነት ኃጢአተኛ ሰው ነኝ በእናንተ ፊት መናገር አይገባኝም ይላሉ ሰው ተነሥቶ አንተ አላውቅህም አንተ ኃጢአተኛ ነህ ሲባሉ እንዴት እባላለሁ ብለው ጦር ይመዛሉ። እኛ በልባችን ትሑታን አይደለንም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛውን ትሕትና ገለጠ። እውነተኛውን ትሕትና በቤተልሔም አሳየ አስተማረ። ቤተልሔም የትሕትና መገኛ ምንጭ ናት። ዓለም ትሕትና ጎድሏታል። ቤተልሔም የትሕትና ትምህርት ቤት ነች። እርቅ ማንወደው ትሕትና ስለሌለን ነው። ይቅርታ ከምንጠይቅም ብንሞት እንመርጣለን። ይቅርታ አራት ቃል ከመናገር አራት ሚሊየን ሰው ቢያልቅ እንመርጣለን። ይቅርታ ትሕትና ነው። ትሕትና ደግሞ ክብር ነው። የክርስቶስ ልደት ትሕትና ነው የሚያስብለን የተወለደው ለመሞት ስለሆነ የሚሞተው ደግሞ በኃጢአቱ አይደለም በአዳም ኃጢአት ነው። እንደ ኃጢአቱ መሞት የነበረበት ተቀምጦ በደል የሌለበት በግ መታረዱ በአዳም ተገብቶ በመሰቀል መሞቱ ይህ ትሕትና ድንቅ ትሕትና ነው። ክርሶቶስን ማየት ምንፈልግ ከሆነ ዝቅ በማለት ነው። የዋሻ ጠባዩ ዝቅ ያስብላልና ዝቅ እንበል ልደቱ ዝቅታን ይነግረናል። ግንበስ እንበል ፍሬ የያዘ የገበስ እሸት ሚታወቀው ማጎንበሱ ነውና።

ትሕትናን እንኖረው ዘንድ እርዳን!

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

06 Jan, 19:17


ክርስቶስ ተወለደ #1

እግዚአብሔር ያለስፍራው የዋለ ያለስፍራችን ሊያውለን ነው። የሰው ልጅ ውድቀት ከፍ ያለ መሆኑን ምንረዳው የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ማድረጉ ነው። ባለ አርያሙ ባለ በረት ነው። በመላእክት የተከበበው በእንስሳት ሥር ያደረበት ነው። ጌታችን በቀዳማዊ ልደት ከአብ የተወለደ አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው ነው። በሚቆጠር ልደት ሱታፌን ነሣ። የጌታችን የኢየሱስ ልደት እስከዚህም የሚወደን አለ ብለን የምንደነቅበት ለሞተው ልባችን የፍቅር ትንሣኤ ነው። ሰዎች ቢወዱን ልብሳችን ይለብሱታል ወይ ይወስዱታል። ሰዎች ቢወዱን ልጃቸውን ይድሩልናል ወይ ክርስትና ስጡን ብለው ይጠይቁናል። እግዚአብሔር ቢወደን ሰማይ ምድር ሆነ። ከዚህ ቀደም ሰማይን ለመመልከት ቀና ማለት ይገባን ነበረ። ዛሬ ግን ሰማይንና የሰማዩን ጌታ በከብቶች በረት ወድቋልና ሰማይን ለማየት ወደ ከብቶች በረት ዝቅ ማለት ግድ ሆነ። ሰማይ ያለ ዝቅታ እንደማይታይ ቤተልሔም ይነግረናል። ታላቅ ፍቅር የተገለጠበት ነው። ዲያቢሎስ ያፈረበት ነው። አዳም ወደ ቀደመ መልኩ ክብሩ የተመለሰበት ነው። ስደተኛዋን ሔዋን ለርስት መንግስተ ሰማያት ያበቃ ነው። እኛ ብንበድል እርሱ እንደካሠ ይነግረናል። እኛን ወደ ሰማይ ከፍ ለማድረግ እርሱ ወደ ቤተልሔም ዝቅ አለ። ዝቅታው ከፍታችን ድህነታችን ብልጥግናችን ሆነ። እነ እገሌ መርከብ ላይ ተወለዱ ቢባል በስማቸው መርከብ ቢሰየም ነው። አውሮፕላን የተወለዱ ሰዎች ብዙ ሊወራ ይችላል። በበረት የተወለደ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። በደሃ አርአያ ነው። የተገለጠው ለምን? ለድሆች ተስፋ ለመሆን። እርሱ እናቱን አስፈቅዶ በእናቱ ማኅጸን አደረ ነፍስና ሥጋ ነሣ። ሰማያዊ አምላክ በዘባ ኪሩቤል የነገሠው በድንግል ማርያም ማኅጸን ተወሰነ። ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በጠባብ ማኅጸን ተወሰነ። 9 ወር ከ5 ቀን ፈቅዶ ሕግን አከበረ ራሱ የደነገገውን ሕግም አከበረ። እግዚአብሔር በመገለጥ በመታየት ያምናል። በነቢያት ትንቢት በአበው ሱባዔ ሲሰላ ነበረ። በቅዱሳን አባቶች በርእሳነ አበው ሲመሰጠር ነበረ። በቤተልሔም ራሱን የገለጠበት አገላለጥ ግን እጅግ ድንቅ ነው። ሰይጣና በእባብ ገላ ተሰውሮ አዳምና ሔዋንን ጥሎ ነበረ። በሰው ሥጋ ተሰውሮ አዳምና ሔዋንን ከወደቁበት ያነሣቸው ዘንድ በቤተልሔም ተወለደ። ቤተልሔም ታላቅ ፍቅር የተብራራበት ነው። ፍቅር ማይታይ ነው ፍቅር ማይዳሰስ ነው ተብሎ ነበረ። ፍቅር ግን በቤተልሔም የሚስሙት ሕጻን ልጅ ሆነ። ያን ጊዜም የሚያምኑ ዛሬም የሚያምኑ አንዴ ልጅሽን ስጭኝ ብለው ከእናቱ እቅፍ ለምነው መሳም ይችላሉ። ከናዝሬት ሕጻናት መካከል አፈር ሲበትን ውኃ ሲረጭ ከዛ መካከል ስበው ሊስሙት ይችላሉ። ታቅፎ ሚሳም ሆኖ እግዚአብሔር ወልድ ተገለጠ። አዎ ፍቅር አካል አለው። ፍቅር ዝሩዕ ስሜት ፍቅር ማይጨበጥ አይደለም። ፍቅር ሚታይ ነው ተግባር ነው። ፍቅር የአፍ አይደለም። ለሌላው መስዋዕት መሆን ነው። ፍቅር ከስሜት ይልቅ ለተግባር ያደላ ነው። የነገሥታት የመሳፍንት የመኳንንት ዘመድ መሆን ያስደስት ይሆናል። እኛ ግን አዝማደ ሥላሴ ሆነናል። የሥላሴ ዘመድ ሆነናል ደስ ሊለን ይገባል። ቤተ ዘመድ ሆነናል። ቀድሞ በመልኩ የፈጠረን አምላክ ዛሬ በመልካችን ተወለደ። እኛ እግዚአብሔርን እንመስላለን ብለን ብዙ ዘመን ስንናገር ነበር። እግዚአብሔር እኛን ይመስላል እንል ዘንድ ቤተልሔም አስገደደችን። አዎ በቤተልሔም እኛን መሰለ። ንጉሥ ከደሃ ቤት ቢገባና ቢመገብ ደሃዋ እንዴት ብለው ያለቅሳሉ። ሊቁ እንዴት ከደሃ ቤት አደረ አለ። ባለጠጋ ነው። እንዴት ከከብቶች በረት ተወለደ ባለ አርያም ነው። እንዴት?  አዎ ቤተልሔም ብቸኝነት ለሚያስጨንቃቸው መልስ ነው።  እልፍ አእላፋት ወትልፊት አእላፋት ያሉት እንዴት በደሃ ቤት እንዴት በበረት አደረ? አዎ ለመውለድ የደረሰች እናት ድርስ እርጉዝ ትባላለች። እመቤታችንም እንደዛ ነበር ምትታየው። እመቤታችን ስትወልደው ምጥ አልነበረባትም። ለምን ስንል አስቀድሞ ሔዋን ልጆቿን ያለ ምጥ ትወልድ ዘንድ ታስቧልና። እርሱ ክርስቶስ አዲሱን አዳምን እንደሚመስል የለበሰው ሥጋ አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረውን ሥጋ እንደሆነ ሁሉ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሕናዋም ያለፈችበት መንገድም ሔዋን ከመበደሏ በፊት የነበረው ነው። አዲሲቱ ሔዋን ናት። እመቤታችን የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ ነበር። ነፍሰ ጡር ሴቶች በየሄዱበት ጉዳይ ቅድሚያ ይሰጣሉ። የክርስቶስ ስትሆኑ ግን በሰበአዊነት ሚደደረገው ነገር እንኳ ይነፈጋችኋል። በእንግዶች ማረፊያ ስፍራ ስላልገኘላት በበጎች ማደሪያ ልጇን ልትወልድ ግድ ሆነ። ዓለም ለክርስቲያኖች ቦታ ስፍራ የላትም ለምን አትበሉ ተቀበሉት ለምን? ተነግሮናልና። ጌታችን ዓለም ላይ ሁለት ነጻ ቦታ አግኝቷል አንደኛው በረት ሁለተኛው መስቀል ነው።  አማንያን ስንሆን የመብት ጥያቄ ብናቀርብም መልስ አናገኝም። ምክንያቱም ሀገራችን በሰማይ ነው። ነጻነትን የሚያውጁ የክርስቲያን ነጻነትን ማወጅ አይፈልጉም። እኛ ጌታን አምነን ምነው ተጎዳሁ እንላለን ጌታን አምና የተጎዳች እያለች። አስታውሱ ስለእርሱ መሰደዷን ከሀገር ወደ ሀገር መንከራተቷን ማላዘን አያስፈልግም። አስታውሱ ሊከተለኝ ሚወድ ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሽክሞ ይከተለኝ። ሚለውን። ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በዚህ ዓለም ላይ ለወለደችው ሕጻን እናት ሆና አንድ ቀን አልደላትም። የባለ መስቀሉ እናት ባለመስቀል ነበረች። በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ተባለ። ቅዱስ ስምዖን ምን ነካው? በቤተልሔም ለወለደች ያውም በበረት ለወለደች ከቤተልሔም ናዝሬት ለመጣች የአራስ ጥሪ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ለምን አለ? ልጇን በወለደች ጊዜ የአራስ ጥሪ ሰይፍ ነበር። ያ ጥሪ ደግሞ የሥጋ ከሆነ ከእርሷ የቀደሙ ሰማዕታት  ስለ እርሷ የተናገሩ እነ ኢሳይያስ እንኳ መጋዝ አልፎባቸዋል ቀላል ነው። በነፍስ የሚያልፍ ሰይፍ ግን ከባድ ነው። ለዛ ነው የሰማዕታት እናታቸው የምትባለው በነፍሷ ሰይፍ ስላለፈ ነው። ሰማዕትነት የምንቀበልበት መንገድና ሁናቴ ይለያያል እንጂ አማኝ ሁሉ ሰማዕት ነው። ወይ ነፍሱ ወይ ሥጋው ትሰየፋለች። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደቱ በእውነት ልደቱ የሰማዕታት ማውጫም ነው። በስሙ አምኖ መቀመጥ የለም ክርስቶስ ተወልዶ ቁጭ አላለም። ስደቱ ተከትሎ መጣበት እንጂ። በዓለም ላይ የንጉሥ ልጅ ቢወለድ አይደለም የአንድ ተራ ሰው ውልደት አታሞ ነጋሪት ያስደልቃል። ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ይገደል ዘንድ ትእዛዝ ወጣ ስደትም መጣ። ዓለም ክርስቶስን የተቀበለችው በበረትና በሰይፍ ነው። በበረት ላይ ስደት ከባድ ነው። ያውም ወደ ግብጽ ወደ ሲና በረሃ። ይደንቃል አባቶቹ ከግብጽ ወጥተው የሄዱበትን የተንከራተቱበትን ያን በረሃ ሙሴን በበረሃ የመራው የሙሴ መሪ በእናቱ ጀርባ ላይ ሆኖ እስራኤላውያን ያዩትን መከራ እርሱም በሥጋ ቀመሰው ያዩትን ልይላቸው የቀመሱትን ልቀምስላቸው ብሎ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ለመከራ ጨካኝ እንድንሆን ያደርገናል። አንድ ሰው ሲወለድ ሁለት ነገርን ይዞ ይወለዳል ደስታና መከራን። የፍቅር ታላቅነት በቀራንዮ ተገልጧል። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ቀራንዮ አልጀመረም። ይህ ሁኔታ መግደል የሚችለው በመስቀል ላይ ፍቅሩን ገልጧል። የቀራንዮ መነሻ ግን በረት ነው። የፍቅር መነሻ ግን በረት ነው። ነቢዩ እንባቆም በሁለት እንስሶች መካከል አየውህ ያለው የተገለጠው የበረት ፍቅር የጀመረው የቤተልሔም የበረት ፍቅር።

ማስያስ/@Masiyas

02 Jan, 19:57


አጉል ልማዶችን ተዉ

አጉል ልማዶችን ከሥር ጀምሮ ወላጆች ያስጥሉናል። ቀጥሎ መምህራን ያስተዉናል። መጻሕፍትም እንደ ሸለፈት የሆነውን ፣ ውበትና ጤንነትን የሚጎዳውን ክፉ ልማድ እንድንተው ያግዙናል። የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ለማወቅና ለንስሐ ጊዜው አይረፍድበትም። አጉል ልማድ ባለማወቅ ምክንያት ፣ ሥነ ሥርዓትን ባለመማር ፣ ልቅ በሆነ ባሕል ውስጥ በማደግ ፣ ሥልጣኔ በሚመስል ዘላንነት በመያዝ ሊመጣ ይችላል። አጉል ልማዶች እጅግ ብዙ ሲሆኑ ሁሉንም መንቀስ አይቻለንም። አጉል ልማዶች ትንሽ የሚመስሉ ትልቅ ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። አጉል ልማድ ውስጥ ካለን ከሰዎች ጋር እንጋጫለን። ሰዎች ባይጋጩንም ለእኛ ያላቸው ክብር ይቀንሳል። አንዳንድ ሰዎች ሊነግሩን ይችላሉ። የሚበዙት ግን እየታዘቡ ዝም ይሉናል። በአፍ መፍረድ ፣ በልብ መታዘብ ሁለቱም አንድ ዓይነት ኃጢአት ቢሆንም ሰዎች ታዝበው ዝም ይሉናል። መመከርን መቋቋም የማንችል ፣ ግን ብዙ ግድፈት ያለብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። በዚህ ምክንያት የበለጠ እኛን ላለማጣት ዝም የሚሉን ይበዛሉ።

መኝታ አታብዛ። ገንዘብ እየፈለግህ መኝታ እያበዛህ አይሆንም። አንተ እንድትተኛ የተጉልህ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን እነርሱ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ በረከቶችህ አይደሉምና እልፍ ይላሉ። ያን ቀን በራስህ መቆም ያቅትሃል። የራስህ ሕይወት ስለሌለህ የእነርሱ ህልውና ሲያበቃ ያንተም ያበቃል። ወረተኛ አትሁን። ሸሚዝ እንጂ ሰው አይቀያየርም። ቶሎ ስልቹ ሆነህ መልሰህ እገሌን አታሳዩኝ ፣ አታሰሙኝ አትበል ። ሰው ብዙ ነው ፣ ሰው ጥቂት ነው። ካከበርከው ሰው ብዙ ነው። ከናቅኸው ግን ሰው ጥቂት ነውና አንድ ሰውም ታጣለህ። ወሬ አታጣጥም። “ፐ ፣ ይገርማል ፣ እስኪ ንገረኝ” እያልህ የወሬ ሱስህን አትወጣ። አንዳንዱን ነገር ባትሰማው የተሻለ ነው። ፊት ለፊት ልትነግረው የፈራኸውን ሰው ከኋላው አትማው። ስታወራ ከንፈርህን እየመጠጥህ ፣ ግንባርህን እያሸህ አታውራ። ስትሰብክ አትወራጭ ፣ ከቦታ ቦታ አትፍለስ። እጅህን አታወናጭፍ። ሰዎች በግልህ የነገሩህን ራሳቸው ያውሩ እንጂ ስማቸውን ጠርተህ በአደባባይ አታውራ።

ምግብ ስትመገብ በመጠኑ ጥቅልል እንጂ ሰሐኑን እንደሚወስዱበት ሰው ከልክ በላይ አትጠቅልል። ጥቂት በጥቂት መጉረስ ክብር ነው። ስትበላም አፍህን ገጥመህ ብላ እንጂ ስታላምጥ አጠገብህ ያለ ሰው መስማት የለበትም። በትልቅ ማዕረግ ላይ ያለህ ከሆንህ በአደባባይ ምግብ አትብላ። ጳጳሳት በአደባባይ ባይመገቡ ይመከራል። ወደ ድግስ ስትጠራ በልተህ ሂድ። በምንም መንገድ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ። ጠላት ያለበት ሰው በሴት ፣ በሆዱና በአልኮል መጠጥ ያጠምዱታልና ተጠንቀቅ። ሰዎችን ስታወራና ስታናገር ፊት ለፊት እያየሃቸው ተነጋገር። አፍረህ አንገትህን መቅበር ፣ እንደ ተንኮለኛም ግንባርህን አቀርቅረህ በዓይንህ ግልባጭ ሰውን ማየት በጣም ነውር ነው። ሰው አፍ ውስጥ የምትገባ እስክትመስልም አፍጥጠህ አታነጋግር። ሰዎቹን ራሳቸውን ተመልከት እንጂ የለበሱት ልብስ ፣ ያደረጉት ጫማ ላይ ዓይንህን አትላከው። እንደ ውሻም እግር እግር አትመልከት። ዜማ ስታዜም ፣ መዝሙር ስትዘምር የላይኛውንም የሥረኛውንም ጥርስህን አታሳይ። ጥርሱን የሚያሳይ የሞተና የረገፈ አጽም ብቻ ነው። እቤትህ ሳትጨርስ ደጅ ላይ ወጥተህ ቀበቶህን መፍታትና መዝጋት ነውር ነው። በሰው ላይ ማዛጋት ፣ ሰው ፊት መሐረብ ሳይሸፍኑ ማሳልና ማስነጠስ ተገቢ አይደለም።  ቀጠሮ አክብር። ሁለት ጊዜ ደውለህ ስልክ ያላነሣልህ ሰው ጋ መደወል አቁም።

ሰዎችን ሰላም ብለህ ከሸኘህ በኋላ ዞር ብለህ አትመልከታቸው። ጀርባን የሚያይ ጠላት ነውና ። ከሰዎች ጋር ሆነህ ስልክህን አትጎርጉር። ከተከበረ ሰው ፊት እግርህን አጣምረህ አትቀመጥ። ታላቅህ ሲመጣ ከመቀመጫህ ተነሥተህ ተቀበለው። ሲደወልልህ ስልክህን አንሣ። ማንሣት የማትፈልግ ከሆነ ጉዳዩን ገልጸህ እንዳይደውሉ አድርግ። ሰዎችን በገዛ ስህተታቸው ይቅርታ አትጠይቅ። ይህ እውነትን የሚቀብር ፣ መለማመጥን የሚያሰፍን ነው። ደግሞም ስህተታቸውን እንዳያዩ አስተዋጽኦ ታደርጋለህ። ካልተገራ ሰው ጋር ቀልድ አትቀልድ። ባለጌ ሥራውን አይረሳምና ለመደ ብለህ በርህን አትክፈትለት። ለሰዎች ቀጠሮ ስትሰጥ ጉዳዩንም አብረህ ንገራቸው። “እፈልግሃለሁ ብርቱ ጉዳይ አለ ፣ አሁን አልነግርህም” እያልህ የሰውን ሰላም አትንሣ። የማትጨርሰውን ወሬ አትጀምር። “ይህ ለምን ሆነ ?” አትበል ፤ እንዲህ እንዲሆን እኔ ምን አጥፍቻለሁ ? ብለህ ታረም ። የማምሸት ልማድህን ተው። በጊዜ መተኛትን ልመድ። ሰዎች ሲናገሩ አታቋርጣቸው። እኔ ብቻ ልናገር አትበል። ሁሉን እንደምታውቅ ከተሰማህ ታመሃልና እርዳታ ያስፈልግሃል። ምንም ብትቀራረብ ባለሥልጣንን በአደባባይ አንተ ብለህ አትጥራ። የጎሣና የቋንቋ ትችት ያለበት ወሬ አትጀምር። ያየኸውን የሰው ገመና ለሌላው አትናገር። ይህ የጸሎት እንጂ የወሬ ርእስ አይደለምና። መጓዝ ያለብህ ሰዎች እስከፈቀዱልህ ድረስ ብቻ ነው። ያልተፈቀደልህን መስመር ስታልፍ የተፈቀደውንም ታጣለህ።

http://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

19 Dec, 06:21


#ከስህተት_ትምህርቶች_ተጠንቀቁ

የስህተት ትምህርት መነሻ

1:- ያለ መሪ መጽሐፍ ቅዱስን ከማጥናት ሊከስት ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስን አለ ማንበብ የስህተት ምንጭ ሲሆን ያለ ዓላማው ፣ ያለ ዐውዱ ፣ ያለ መምህር ማጥናትም ለስህተት ይደርጋል።

=) የነገረ መለኮት እውቀት ፣
=) የዓለም አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ጉባዔያት ድንጋጌ ፣
=) የታሪክና የዘመን ስፍር መጽሐፉን ለመረዳት በጣም ያግዘናል።

=) ብሉይ በሐዲስ ፣ ሐዲስ በሊቃውንት ፣ ሊቃውንት በመነኮሳት ሕይወትና ምክር ተተርጉሟል።

=) ብሉይ የጸነነበት ሰው ሐዲስን ይመልከት። ሐዲስ የከበደው ሊቃውንት ያብራሩትን። የሊቃውንትን ትርጉም ያልተረዳው አባቶች ይህን ቃል “እንዴት ኖሩት” በማለት የሕይወት ትርጉም ይፈልግለት። ለብዙ ዶክትሪን መመሥረት ምክንያቱ መሪ የሌለበት የእርስ በርስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነው። በጓዳ ያጠኑትን ወደ አደባባይ ይዘው ሲወጡ ብዙ የስህተት ትምህርቶች ይስተዋላሉ።

የስህተት ትምህርት አንዱ መነሻ ያለ አስተማሪ መንቀሳቀስ እንደሆነ ሁሉ፣

2:- ሁሉም አስተማሪ ሲሆንም ስህተት ይወለዳል። ሁሉም አስተማሪ ሊሆን አይችልም ። አስተማሪነት ጸጋ ፣ ለማስተማር መማር ፣ የአስተማሪነት ሥነ-ሥርዓት ፣ ራስን ለዓላማ መስጠት ይጠይቃል ። መናገር መቻል ፣ ማስተጋባት መቻል ማስተማር አይደለም። ምስክርነትም አስተማሪነት ማለት አይደለም። አስተማሪዎች በምእመን ምስክርነት ፣ በሰባኪው እንግዳ ተቀባይነት ፣ ምእመኑን በቤተ ክርስቲያን ይተክላሉ። ምእመን በጓደኝነት ነፍሶችን ያመጣል። ሰባኪ ደግሞ የዕለት ምግብ ሰጥቶ ያስተናግዳል። አስተማሪው ደግሞ ዘላቂ ሕይወትን በማካፈል ምእመኑን ለክብር ያበቃዋል። ሁሉ አስተማሪ ሲሆን ስህተቶች ይወለዳሉ። መለኪያም እየጠፋ ይመጣል። ትልቅ የሆነው ፣ ሰማይና ምድር የማይችሉት የሃይማኖት ርእስ ወርዶ የነጠላ ቁጨት ውስጥ ይገባል።

3:- ሌላው የስህተት ትምህርት መነሻ ቃሉን ከፍልስፍና አንጻር መተርጎም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት የራሱ ዓላማ አለው። መጽሐፉ የሊቃውንት ሳይሆን የአማንያን መጽሐፍ ነው። ግን የሚመራ ሰው ይፈልጋል (የሐዋ. 8፡31)። ባይተረጎም እንኳ መነበብ ያለበት ፣ በመነበብም ብፅዕና የሚያስገኝ መጽሐፍ ነው (ራእ. 1፡3)። ቃሉ በምን ዓላማ ፣ ለእነማን ፣ መቼ ፣ በማን ተጻፈ ? የመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች እንዴት ሰሙት ? የሚለውን ማሰላሰል ይገባል ። ቍጥሩ አልገባ ሲል ፣ አንቀጹን ፣ አንቀጹ አልገባ ሲል ምዕራፉን ፣ ምዕራፉ አልገባ ሲል ሙሉ ክፍሉን ፣ ክፍሉ አልገባ ሲል የመላውን መጽሐፍ ቅዱስና የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ አሳብ በማስተዋል መተርጎም ይገባናል። ፍልስፍና የራሱ መንገድ ያለው ሲሆን ቃሉን ለመረዳት ግን እምነትና ጸሎት ይፈልጋል። በሥጋዊ አሰሳ ትርጓሜውን መፈለግ ለስህተትና ለመንፈሳዊ ድርቀት ይዳርጋል ።

ይቀጥላል...

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

18 Dec, 19:47


ዓለቴ ክርስቶስ!

እግዚአብሔር ሆይ ማዕበሉ ንብረቴን እንጂ እምነቴን እንዳይነጥቀኝ እርዳኝ!

ጌታ ሆይ የሚያስፈራው ማዕበሉ ሳይሆን አለማመኔ ነው። ማዕበሉ በእምነት ይሸነፋል። አለማመኔን ገስጸውና አለማመኔን እርዳው።

ሰዎች ሄደው አንተ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቀርተሃልና አመሰግናለሁ።

አንዳንድ ሰዎች ፈተና ሲበዛ የሆነ ነገር ላገኝ ነው ብለው እንደ ምልክት ይወስዱታል። እኔ ግን መሞቴ ነው። አለቀልኝ እያልኩህ በፍርሃት መቅኒዬ በአጥንቴ እየረጋ አስቸገረኝ። ፈተና የበረከት ዋዜማ ነውና። ከፈተና በኋላ ያለውን በረከቴን እንዳየው የልቦናዬን ዓይን አብራልኝ።

በፈተና የሚጸና የተባረከ ነውና!

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

17 Dec, 08:12


#ከስህተት _ትምህርቶች_ተጠበቁ!

ሃይማኖት የለሽት እየተስፋፋ ነው። የስህተት ትምህርቶች መጨረሻቸው ሃይማኖት የለሽነት ነው። የስህተት ትምህርት እውነትን ማጣመም ፣ የከበረውን ማዋረድ ነው። ለእግዚአብሔርም ሌላ መልክ መስጠት አንዱ መገለጫው ነው። እግዚአብሔር በመለኮት አንድ ሲሆን በአካል በስም በግብር ሦስት ነው የሚለውን ትምህርት ሦስት አካላትን በመጨፍለቅ አንድ ማድረግ፣ አንድ አምላክነትን በመበተን ብዙ አማልክት መፍጠር አንዱ የስህተት ትምህርት መገለጫ ነው። የስህተት ትምህርት ምንጩ ሰይጣንና ፍልስፍና ነው።

ስለዚህም ምሥጢራትን ማቃለል ጥምቀትን ውኃ ነውቅዱስ ቍርባንን ተራ ማዕድ ነው ማለት ጠባዩ ነው

ሰይጣን በአንድ ጊዜ በማስጣል ውጤታማ አይሆንም። ቀስ በቀስ እያቃለለ፣ የከበረውን ነገር እያሳነሰ ሰዎችን ቅለት ያለማምዳቸዋል። ለዚህም ትክክለኛነት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ዋናው ኢየሱስን ማወቅ ነው ይላቸውና ኢየሱስ አርአያ የሆነበትን ደግሞም ያዘዘውን ጥምቀት እንዲንቁ ያደርጋቸዋል። አጥሩን በማፍረስ በመጨረሻ ከሀዲ ይፈጥራል። የስህተት ትምህርት እግዚአብሔር የለም ብሎ አይጀምርም፣ መጨረሻው ግን እግዚአብሔር የለሽነት ነው። እግዚአብሔር ያከበራቸውን በሰማይም በምድርም ያሉትን መናቅ የስህተት ትምህርት ጠባይ ነው። ራስን ከከበሩት ጋር በማወዳደር ለቅዱሳን ጥላቻን መያዝ ፣ በምድር ካሉት አገልጋዮች ጋር ቁመት መለካካት ሰይጣን ለሰዎች የሚያለማምደው የስህተት ትምህርት ውጤት ነው። እነዚህ ሰዎች በያዙት አቋም ባይረኩ እንኳ የሚሄዱት ወደ ክህደት እንጂ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት አይደለም። ወደ እውነተኛው ሃይማኖት እንዳያቀኑ አስቀድሞ የተትረፈረፈ ጥላችን ተሞልተዋል።

ይቀጥላል....

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

15 Dec, 18:17


ወዳጄ ሆይ!

"ተራ ድብቅ (ልታይ የማትል) ዝምተኛና ታናሽ ሰው ሁን። ወደ ራስህ ትኩረትን ፈጽሞ አትሳብ። ሰዎች ሲያናግሩህ አዳምጣቸው። ነገሮችን በንቃት ተከታተል። ከሚያስፈልጉህ ነገሮች ውጭ አታስብ አትናገር። ስታወራ በቀላሉ በግልጽ በቀጥታ በአጽንዖትና በቀጥታ አውራ። ነገሮችን ከማለም ከማንሰላሰል ከምኞት ራቅ። ሥጋዊና ፍትወታዊ ነገሮችን ከጅምሩ ራቃቸው።

@Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

13 Dec, 18:37


መንግስትህ ትምጣ!

  ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱ ለኃጢአት ድርቀትን በረሃማነትን ከፈለው። የክርስቶስ ምጽአት የሌሊቱ ማለፍ ነው። እርሱ የሚመጣው የንጋት ኮከብ ሆኖ ነው። የንጋት ኮከብ ምንድን ነው? የንጋት ኮከብ ሌሊቱ  አልፎ ጨለማና ብርሃን ሲለያዩ የሚታይ ነው። መከራው ራሱ አልቆ አይቆምም የመከራው ድንበሩ የክርስቶስ መምጣት ነው። የመጀመሪያ የአዳም መከራ የቆመው በክርስቶስ መምጣት ነው። ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱና ሞቱ ለሞት ሞትን ከፈለው። ሞት ለዘመናት ቆንጆ እየነጠቀ ንጉሥን ከዙፋኑ እያንከባለለ ወሰደ ለዘመናት ያለበርና መስኮት ሲንጎማለል ኖረ። ከትልልቅ አባቶች ፈላስፎች አንድስ እንኳ ሞትን ያሸነፈ የለም። የዚህ ዓለም ክቡራን በሁለት ፊደል ሕይወታቸው ተጠናቋል ሞተ በሚል። በሽታ መድኃኒትን ሞቴ ጥፋቴ መከራዬ ማለቂያዬ ብሎ ይጠራዋል። የክርስቶስ መምጣት ለዚህ ዓለም እንዲሁ ነው። እኛ ደግሞ የክርስቶስን መምጣት መድኃኒቴ ሕይወቴ እንለዋለው። ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱ ሞትን ገደበ። በሁለተኛው ምጽአቱ መከራን ይገድበዋል። ክርስቶስ ካልመጣ አንዱ መከራ አልቆ መሬት ሳያስነካ ለቀጣዩ መከራ ያስረክበናል። እቺ ዓለም ቢሻላት እንጂ አትድንም። የክርስቶስ መምጣት የዓለም የእርጅናዋ ዘመን ነው። እርጅና አልጋ ላይ ይጥላል። ዓለም አርጅታ አልጋ ላይ ወድቃለች። ሰው ሲያረጅ በሽታ አልጋ ላይ ይጥለዋል።  ዓለም ታማለች በበሽታ ወድቃ አልጋ ላይ ነች። ዓለም አትታመንም የራሷን ሰው እንኳ ማስደሰት አትችልም።

ኧረ አንቺ ዓለም ኧረ አንቺ ዓለም
የጀመረሽ እንጂ የጨረሰሽ የለም

ተብሏል!

ዓለም  ያለ ክርስቶስ መንገዷ እሾክ ነው። ብትከተሏትም ሞት ነው ባልከተሏትም ክርስቶስን በመከተላችን የሞት ገበታ ያላት ብቸኛ አስቆ ገዳይ አስብታ አራጅ ነች። የክርስቶስ መምጣት የጥያቄው መልስ ነው። ክርስቶስ ሲመጣ ላለብን ጥያቄ መልስ ሊሰጥ አይደለም። ራሱ መልስ ነው። የዓለም መልሷ ጥያቄ ነው። ስልጣኑ ጭስ የማይታይበት ቃጠሎ ነው። አዎ ጌታ ይመጣል። ራሱ ባለቤቱ ነግሯናል ክርስቶስ ብናምነውም ባናምነው ይመጣል። የሚመጣው እመጣለሁ ስላለለ ነው። ይህ ቃል የንጉሥ እውነተኛ ቃል ነው። ያልነገረንን የሚነግሩን ነቢያት አይመጡም። የነገረንን  ግን ይመጣል። በመጨረሻም በልጁ ተናግሮናልና። እኛ በክርስቶስ ታውቀናል። የዘመን መልክ በክርስቶስ ተነግሮናል። የሚጠነቁል አያስፈልግም። በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን እረኛ ነው። ስታስቀድስ ስትቆርብ አላይህም የሚል አባት የሚገስጽ አባት በፍቅር የሚፈልገን አባት ያስፈልገናል። ዛሬ ሃይማኖታዊ  ተውኔት አያስፈልገንም። ከዓለም ክርስቲያን ተለይቶ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብቻ ጋኔን አለብኝ ብሎ ያምናል። የሚጮህበት መድረክ ስላገኘ ይጮሃል። የክርስቶስ ማደሪያ የሆነ ምዕመንና ካህን እንዳይተማመን ራሱ ካህኑ ጋኔን አለብኝ ብሎ እንዲያምን እየተደረገ ነው ያለው። ገንዘባችንን ለእነዚህ እየሰጠን ለወንጌል ግን ዱሽ ነን።  ለወንጌል ፈዘናል ለዘራፊ ተመቻችተናል። እኛ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ነን። ስለመጨረሻ ቀን ሚተረጉም እንጂ እኔ አውቅልሃለሁ የሚል ትምህርት አያስፈልግም። ከወረቀቱ ልንገርህ ወይስ በቀጥታ ከሰማይ ልንገርህ የሚል ቀልድ በጌታ ቃል እየተቀለደ ነው። በእውነት አርዮስም እንዲህ አላዋረደውም። በእውነት ዲያቢሎስም እንዲህ አላዋረደው። ዛሬ የእግዚአብሔርን ልጅ ላይ በስሙ እያፌዙ ነው። እግዚአብሔር የሚያናግረው በቃሉ ነው። ዛሬ ቃሉ ያነሰባችሁ ይቅር ይበላችሁ። ቃሉ ዘላለም የሚያኖር ቃል ነው። አይ አይበቃኝም ብለን ሌላ ቦታ ምንሄድ አለን ይቅር ይበለን።

ጸሎት
ጌታ ሆይ! በሰፈር ልጆች የተጠቃ ሕጻን አባትህ ይመጣል። ያጠቁህን የመቱህን ልክ ያስገባቸዋል ሲባል ምፈራ ከሆነ ምኑን ልጅ ሆንኩት? የክርስቶስ መምጣት ክርሰቲያንን ሊይስደነግጥ አያስፈልግም። አቤቱ በቃልህ አበርታኝ ማራናታ ጌታ ሆይ ተሎ ና። መንግስትህ ትምጣ ብዬ ሊመጣ ነው ስንባል ምንፈራ ከሆነ ክርስቲያን አይደለሁምና ጽድቄን ይቅር በለው!

በረከተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌነ! አሜ!

ታኅሣሥ 04 2017 ዓ.ም

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

12 Dec, 16:32


ማንም

እግዚአብሔር በጊዜ ውስጥ የማይሽረው ቍስል የለም። ከዛሬ ነገ የተሻለ ነው። ከባዱ ይቀላል ፣ መራራው ይጣፍጣል ፣ ዓመፀኛው ይበርዳል። ለሞት የሚፈልጉህ ንዴታቸው ይበርዳል። ያሳደዱህ “ግን ምን ሁነን ነው ?” ብለው ንስሐ ይገባሉ። ያደሙብህ ተጣልተው ይበታተናሉ። ጠላቶችህ እየኮሰሱ ያንተ ቤት ግን እየበረታ ይሄዳል። እውነት እልሃለሁ ከዛሬ ነገ ይሻላል። ብቻ ቅን ሁን። እግዚአብሔርንም ተስፋ አድርግ። ሕይወት የእግዚአብሔር ሂሳብ ናትና ማንም አይዘጋትም።

ታኅሣሥ 3 2016

ማስያስ/@Masiyas

12 Dec, 09:51


ድንግል ሆይ !

ገና በለጋ ዕድሜሽ የዘላለም ምሪትን እንዴት አገኘሽ ? ከሁሉ በላይ የሆነውን ስትቀበዪ አሁንም በትሕትና እንዴት ጸናሽ ? ሰው አምላኩን በሕልሙ አይቶ ይታበያል ፣ አምላክን ወልደሽ አሁንም ትሑት መሆንሽ ይገርማል ። ድንግል ሆይ ! ተከታዮችሽን ደናግል አበዛሽ። ደናግል መሐን አይደሉም፣ ታላላቆችን እንደሚወልዱ ባንቺ ተምረዋል። ድንግልም እንደምትወልድ ያንቺ ሕይወት ያስተምራል። ልጅሽም በገዳመ ቆሮንቶስ ቆይቶ የደናግል መኖሪያን ባረከ ፣ በቃና ዘገሊላም ሰርገኞችን ቀደሰ። ድንግል ሆይ ! አምላክን ማገልገል የከበረ ዋጋ አለው ፣ አምላክን መውለድ ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ነው። ጽኑ ፍላጎትሽ ታናናሾችሽን ማገልገል ነው ፣ ታላቁን አምላክ በማኅፀንሽ ማስተናገድ ፣ በክንዶችሽ መታቀፍ ግን ላንቺ ሁኗል። ማንም ቢመኝ የማያገኘውን፣ በመመረጥ ብቻ አንቺ አግኝተሽዋል። በዚህም ከሴቶች ሁሉ ይልቅ ቡርክት ነሽ። አይሁድ ለሕጋቸው ቀንተው እንዳይጎዱሽ ጥበቃ ሆነልሽ ፣ ሕግን የሰጠው ግን በማኅፀንሽ ነበረ። ሄሮድስ እስከ ግብጽ አሳደደሽ። ልጅሽ የሚጠላ ሁሉ አንቺንም ይጠላሻል።

ድንግል ሆይ ! የልጅሽ ስደት ያንቺ ስደት ነው። የምእመናን ስደትም የልጅሽ ስደት ነው። ከአነስተኛዋ ከተማ ከናዝሬት የአርያሙን ንጉሥ ስተቀበዪ ፣ ገዳዮች ባሉባት መንደር ጠባቂውን መልአክ ገብርኤልን ስታዪ ፣ በረከሱት አገር የተቀደሰውን ልጅሽን ስታስተናግጂ ከቶ ምን አልሽ  ይሆን ? አብርሃም በድንኳኑ ሥላሴን አስተናገደ ፤ አንቺ ግን በማኅፀንሽ አስተናገድሽ ! አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው። የዘላለም አባት ሳለ አንቺን እናቴ ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ወልድ ቡሩክ ነው። የተዋሕዶው አጋፋሪ የሆነው አንቺን ያከበረ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱም ቡሩክ ነው። ጭልጥ ብለው የጠፉ ፣ ደረስን እያሉ ይበልጥ ከመፍትሔው የሚርቁ  የዚህ ዘመን ሰዎች አንቺን ሊማሩሽ ይገባቸዋል። ትሑት በመሆን ታላቅ መሆንን ካንቺ እንማራለን።

ድንግል ሆይ ! ጉልበት የለሽ ማንንም አትጎጂም ፣ በዘመንሽ ግን ብዙ ጠላትነትን አተረፍሽ። ሁሉ በሩን ዘግቶብሽ ልጅሽን በበረት ወለድሽ። ጌታን ወልጄ እንዴት እሰደዳለሁ ባለማለትሽ ዓለሙ ሁሉ እናቴ አለሽ። በነፍስሽ ሰይፍ በማለፉ የሰማዕታት እናት ሆንሽ ፣ የሕማም ሰው ክርስቶስን በመውለድሽ አዛኝቷ ተባልሽ። በእውነት ላንቺ ሰላምታ ይገባል። ቅጥሩ የፈረሰበት ፣ እውቀት እብደት የሆነበት ፣ ሃይማኖት የሕይወት ለውጥ መሆኑን የዘነጋው ፣ መንፈሰ እግዚአብሔርን ትቶ መንፈሰ ትውዝፍትን/የምንዝር ጌጥ ወዳድነትን/ የተከተለ ፣ ቃለ እግዚአብሔርን አግኝቶ ሳለ መልሶ የጣለው ፣ ሁሉን በሚያሳድረው በልጅሽ ብርሃን ምነው በተሰወረ !!!

ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን !


ታኅሣሥ 03 ቀን 2016 ዓ.ም.

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

09 Dec, 17:30


ይህ የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ የጌታን ሥጋና ደም ለመቀበል በሚደረግ ልዩ የሆነ ፍጹም የሆነ የቅዳሴ ጸሎት የሚደረግበት ሥርዓተ ቅዳሴ ዘቅዱሳን አበዊነ 14ቱ ቅዳሴ ነው። እባክዎ አውርደው ለነፍስ ለሥጋ ሕይወት የሆነውን ቃል ይጠቀሙበት ለወዳጅዎም ያጋሩ እናመሰግናለን!

በክርስቶስ ሰላም ሰላም ይሁንላችሁ!
አሜን!

ማስያስ/@Masiyas

25 Nov, 20:40


https://youtu.be/HqyhPq_Jf-g?si=sYMQXyqN-hBrfbhG

ማስያስ/@Masiyas

14 Nov, 13:24


#በስድብ_ፈንታ_አመስግኑ

ብዙ ጊዜ ስንሳደብ እና መጥፎ ቋንቋ ስንጠቀም “እኔ ይህን አለማድረግ አልችልም ልማዴ ነው" እንላለን፡፡ እናም ሲጎዱን አንድ ነገር መናገር ካለብንም፣ በስድብ ፈንታ ምስጋና መናገርን እራሳችንን እናስተምር።

ነገር ግን፣ ሰው እያሰቃየኝ ዝም ማለት አልችልም ትላለህ፡፡ ከመናገርም አልከለክልህም፡፡ ሆኖም ከመሳደብ ይልቅ ምስጋናን ተናገር፡፡ ከመበሳጨት ይልቅ ምስጋናህን ግለጽ፡፡

ለጌታህ መናዘዝ ትችላለህ፡፡ በጸሎትህ ውስጥ ጩኽ፤ እንዲሁ መከራህን ያቀልልሃል፣ ፈታኙም ሰይጣን በምስጋናህ ውስጥ ይሸሻል፣ የእግዚአብሔርም እርዳታ ወዳንተ ይቀርባል። ከተሳደብክ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታ ትከለክላለህ፤ እናም ፈታኙ በአንተ ላይ እንዲበረታ ታደርጋለህ፤ በዚያም እራስህን የበለጠ በህመም ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ብታመስግን ግን የክፉ መንፈስን ጥቃት ትቃወማለህ፡፡

ነገር ግን ምላስ ብዙውን ጊዜ በልማድ ኃይል አንዳንድ መጥፎ ቃላትን ከመናገር ወደኋላ ማለት አይችልም። ከዚያም በምትወድቅበት ጊዜ ኹሉ ቃሉ ከመናገርህ በፊት ጥርሶችህን ጠብቀው ይዘጉ፡፡ ምላስህ የደም ጠብታ ብታፈስስ ይሻላታል፤ ከስድብም በኋላ የማያቋርጥ ቅጣት ከምትቀበል በጊዜው ሥቃይን ብትታገሥ ይሻልሃልና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

11 Nov, 15:30


ወዳጄ ሆይ!

ራስህን ካድ እንጂ ራስህን አትጣል። አገርህ ያልተጠቀመችበት እውቀትህ ርግማን ነው፡፡ ለኪስህ እንጂ ለኅሊናህ መኖር ካልጀመርህ ገና አልተወለድክም። ብዙ መኖር ሳይሆን ብዙ መሥራትን ተመኝ። ሁልጊዜም የሚያስፈልግህ ትዕግሥት ነው። ማፍቀርህም ትዕግሥት ይኑረው። ጨው ያለፈውን ሕመም የሚጠግን ፣ የዛሬውም ምግብ የሚያጣፍጥ ፣ ለነገ እንዳይበላሽ የሚከላከል ነው፡፡ ፍቅርም ያለፈውን ስብራት ይጠግናል ፣ የዛሬውን በረከት እንድታመሰግንበት ያደርጋል፡፡ የነገውን መንገድ ብርሃን ያደርጋል፡፡ አሜን ካለ ማለት በረከት ይቀራል ይባላል፡፡ አሜን ያሰኝልን፡፡ 

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

08 Nov, 17:50


ፍትሐ ነገሥት

አንቀጽ ፳፫/23

1:- ስለ ልብስ፣
2:- ስለ ምግብ፣
3:- ስለ ቤት፣
4:- ስለ ተግባረ እድ ይናገራል።

√ ጥሬ ሥጋ እና ደም መብላት አይገባም። እስመ ነፍስ ተኀድር በደም ስለሚል

√ ሞቶ ያደረ፣ (በሰውነቱ ደሙ ስላለ):: የአውሬ ትራፊ የተለከፈ ከእባብም የተረፈ ሊሆን ስለሚችል ለጣዖት የተሠዋ አይበላም።

1ኛ ቆሮንቶስ ፲፥፳፩፦ "የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።"

√ እየተጠራጠሩ መብላት ኃጢኣት ነው። (ኃጢአት የሚሆነው እግዚአብሔር የቀደሰውን ፍጥረት በአምላክ ሥራ ገብተን ርኩስ ነው? አይደለም? እያልን በመጠራጠር በመብላታችን ነው።


የሐዋ.ሥራ ፲፥፲፭፦ "ደግሞም ሁለተኛ፦ “እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው፥”
የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።"

√ አእምሮን የሚያጠፉ፣ ሰውነትን የሚጎዱ ነገሮችን መብላት አይገባም። አደንዛዥ እፅ (ጫት:አፄ ፋሪስ :ጋንጃ ተያያዥ የሚያሳብዱ ነገሮች) እነዚህ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሆነው በሰው የተቀመሙትይ ይጨምራል። እግዚአብሔር የፈጠረው እርኩስ ሆኖ ሳይሆን በውስጣቸው መርዛማነት ለሰው አካል አደገኛ በመሆኑ ነው።

√ መርዝ ያላቸው ፍጥረታትን፣ (እባብ ጊንጥ ወዘተ) መርዛማና በሌሎች ሕይወት መሞት የሚኖሩ መርዝ የሚበሉ አራዊትን መብላት አይገባም።

√ ለታመመ ሰው ግን ደዌውን የሚያድንለት ከሆነ ማናቸውንም ነገር እንዲበላ ይፈቀድለታል።

√ የሚበላ የማይበላን፣ የማይበላ የሚበላን አይንቀፍ።

√ ከማያምኑት ሰዎች ምግብ አቅርበው ብሉ ቢሏችሁ ባርካችሁ ብሉት። ነገር ግን ለይተው ለጣዖት የታረደ ነዉ ካሏችሁ አትብሉ።

√ ከጥጋብና ከስካር ተጠበቁ።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

08 Nov, 13:54


አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ"

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
(የአህያን ስም በአሳማ በአይጥ በውሻ ወዘተ እየቀየሩ ዐረፍተ ነገር ይሥሩ:: ሃሳቡ ያው ነው) ግዝረትም የማይበሉ ምግቦችም ከ613 የአይሁድ ሕግጋት (The 613 Mitzvot) ውስጥ ናቸው::

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ቄራ (የበሬ)

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" ኤፌሶን 4:29

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

05 Nov, 18:37


#የዘመናት_ናፍቆቴ

"አንተ ረዳኤ ምንዱባን የችግረኞች አጋዥ ፣ አንተ ተስፋ ቅቡፃን የጨለመባቸው መብራት ፣ አንተ አሰጣጥ የምታውቅበት ፣ የመስጠት ችሎታ ያለህ ፣ ከሞት በኋላም የምትጋብዝ ትልቅ ወዳጅ በባሕርይህ ድካም ፣ በአካላትህ ባዕድ የሌለብህ አድሮ ሁሉን ሳጣው አድሮ የማገኝህ ትሰጠኛለህ ብዬ ሳይሆን ሰጥተህ ያኖርከኝ ፣ ከእኔ ምንም ባይገኝም እንደሚያገኝ ሁነህ የፈለግኸኝ ፣ ቤተ ክርስቲያንን የበረሃ ምንጭ አድርገህ የሰጠኸኝ ፣ ጨለማዬ ላይ ይብራ ብለህ ያወጅኽልኝ ፣ የጸናው ማንነትህ ያልጸናውን እኔነቴን ያልናቀኝ ፣ እራመዳለሁ ስል ብወድቅም ተነሥ ብለህ ያበረታኸኝ ፣ እየሠራሁ ሳበላሽ በገርነት ጎበዝ ያልከኝ ፣ በቤትህ ጠፍቼ ሳለሁ በደጅ በጠፉት ስፈርድ የመከርኸኝ በሚያረክሰው ዓለም ያገኘሁህ ጸዓዳ ልብስ አንተ እግዚአብሔር ነህና ተመስገን። የእኔ ሠራተኛ ፣ ጓዳዬን የምትሞላ ፣ በቤትህ ባድርም አንተ ግን በእኔ ውስጥ ያደርህ ፣ ለመማረክ ወጥቼ አንተ ግን የማረከኝ ፣ ቀኑን ሙሉ ስባዝን ቀኑን ሙሉ የፈለግኸኝ ፣ በምቾቴ ስክድህ በመንሣት ሳይሆን አሁንም በመስጠት ያስተማርከኝ ፣ አጢኜ የማልፈጽምህ እግዚአብሔር ተመስገን። የሰዎችና የሁኔታ ጥገኛ ብሆንም ፣ የቀኑ ወሬ ይዞኝ ብጠፋም ፣ ምድራዊ ጠባቂን እየፈራሁ ጠባቂ መልአኬን ባላከብር ፣ ፍርድ ቤትን እየሰጋሁ ትንሣኤ ዘጉባዔን ብረሳም ፣ በዋጋ ገዝተኸኝ በነጻ ብጠፋም ፣ ሥራዎቼን አተልቄ ውለታህን ባሳንስም ፣ የሚያገለግለኝን አገልጋይ ትቼ የሚገዛኝን ባፈቅርም ፣ ባልቀደምሁበት ሂዱ ብዬ ባውጅም ፣ የማትሞት አባት አንተ በይቅርታ ዓይንህ ታየኛለህ። የዘመናት ናፍቆቴ ባንተ እንደሚፈጸም አምናለሁ። አሜን።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

30 Oct, 19:25


ሰውነትህ እንደ ማርያም መግደላዊት በፍርሀት፣ በረዓድ ሁና ከመቃብሩ አጠገብ ትቁም፡፡ መላእክት ምን ያስለቅስሻል ብለው ይጠይቋት ዘንድ፣ ጌታን ባየችው ጊዜ የት ወሰድከው ብላ ተክል ጠባቂውን እንደ ጠየቀችው ትጠይቀው ዘንድ ያን ጊዜ እንድታውቀው ሆኖ ይናገራታል፡፡ በዝግ ደጅ ወደ ጽርሐ ጽዮን በገባ ጊዜ ተነሥተህ ተቀበለው፡፡ በጥብርያዶስ ቁሞ ልጆቼ የሚበላ አላችሁን? ብሎ በጠየቀ ጊዜ ጴጥሮስን ምሰለው፡፡ መላእክት ያዘጋጁትን ማዕድ ከሱ ጋር ብላ፡፡ ባረገም ጊዜ በአንብሮተ እድ ይባርክህ፣ ይሾምህ ዘንድ ራስህን ዘንበል አድርግ ወዳየር ተመልከት፡፡ ጌታ ባረገ ጊዜ በመላእክት ብርሃን ያበራልና፡፡ ጥቂት ቀን በጽርሐ ጽዮን ኑር፡ ቋንቋ የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ ያድርብህ ዘንድ ወንድሜ በፍጹም ትጋት ሁነህ በልቡናህ ይህን አስብ፡፡

                 (አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 34 ገጽ 189-194) 

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

30 Oct, 19:23


አረጋዊ መንፈሳዊ
 
/ከመጽሐፈ መነኮሳት አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 34 ላይ ተወሰደ/                
 
ድንቅ ነገር እነግርህ ዘንድ እወዳለሁና፤ ወንድሜ ጸጥ ብለህ ስማኝ ኅሊናህን ከዝንጋዔ ወስነህ ስማኝ፡፡ ልብህን ከሥጋዊ ሁከት ለይ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ በትሩፋት የተነገረውን ጸጋ ታገኛለህ በትሩፋት መዓዛ ጸጋን ታሸታለህ፡፡
 
ሕፃናትን የፈጠረ ጌታ ትሕትናን የዕለት ጽንስ በመሆን እንደ ዠመረ ዕወቅ፡፡ ትሕትናን ከሱ ተማር፤ ስላንተ የሠራውን ሥራ ሁሉ ታውቅ ዘንድ በትሕትና ኑር፡፡ እርሱን አስመስሎ ይወልድህ ዘንድ አንተን መስሎ ተወለደ፤ ዓለምን የፈጠረ፣ የሁሉ ማረፊያ ጌታ ቤት እንደሌለው በጎል ተወለደ፤ በጨርቅ ተጠቀለለ፣ በተናቀ ቦታ በጎል አደረ፡፡ የሥጋ ሀብት የነፍስ ሀብት መገኛ ሲሆን ለዘለዓለሙ ነግሦ የሚኖር ንጉሠ ነገሥት ጌታ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡ የስደተኞች ማረፊያ፣ መጠጊያ የሚሆን እሱን እሽኮኮ ብለው አሸሹት፡፡ የሁሉ ደስታ የሚሆን ጌታን ሄሮድስ ይገድለዋል ብለው እየፈሩ አሳደጉት፣ መንግሥትን ሁሉ የሚያሳልፍ መከራን የሚያሳልፍ እሱን ጸብ ክርክርን የሚያጠፋ እሱን ይሙት በቃ እንደተፈረደበት ሰው ካገር አስወጥተው ሰደዱት፣ ሞትን የሚያጠፋ እሱ ሲሆን እንገለዋለን ከሚሉ ሸሽቶ አመለጠ፡፡
 ከተለዩ የተለየ፣ ከከበሩ የከበረ ሲሆን አንተን ያከብርህ ዘንድ በውኃ ተጠመቀ፡፡ ልዕልናውንም አብ በዮርዳኖስ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ብሎ ሲመሰክር ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲያርፍበት ታየ፡፡ ካባቱ ጋር ያዋህድህ ዘንድ አንተን ለመሻት የመጣ ወልድ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ከርሱ ጋር ለመኖር በበጎ ሥራ ብትመስለው ወደ አባቱ ያቀርብህ ዘንድ በትሩፋት መጋደልን፣ ድል መንሣትን ያስተምርህ ዘንድ አርባ ቀን ጦመ፡፡ አንተ ቡሩክ ተብለህ ትመሰገን ዘንድ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህስ…” ብለው አይሁድ ዘበቱበት። በአጋንንት እጅ በኃጢአት በትር የተመታ ርእሰ ልቡናህን ያከብር ዘንድ ራሱን መቱት። የሰይጣንን ምክር ሰምታ የሚያሳዝን ኃጢአት የሠራች ሰውነትህን ጣዕም እንዲገኝባት ያደርጋት ዘንድ መራራ ከርቤ ጠጣ፡፡
 
በዕፀ በለስ ምክንያት ከመጣ ሞት ያድንህ ዘንድ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ። ከመቃብር ያስነሣህ ዘንድ ወደ መቃብር ወረደ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣህ ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ይህን ሁሉ ስላደረገልህ ፈንታ አንተ የምትሰጠው ዋጋ ምንድን ነው? እስኪ ንገረኝ፤ ከዚህ ማዕረግ ደርሰህ እርሱን በማየት ደስ ይልህ ዘንድ ከወደድክ የእርሱን ነገር በመናገር የምታደንቅ ብቻ አይሁን እንደ ዮሐንስና እንደ ጴጥሮስ በዓይነ ሕሊናህ ተመልከተው እንጂ። እኔ እንደነገርኩህ እሱን በማሰብ ፀንተህ ኑር። እንዲህ የሆነ እንደሆነ በእውነት ይገለጽልሃል፣ የተወደደ መልኩን ዓይቶ ለማድነቅ እንድትበቃ ያደርግኻል፡፡ በበጎ ፍቅሩ ሰውነትህን እንደ እሳት ያቃጥላታል፡፡ በሱ ዘንድ ባለሟልነትን ሰጥቶ ደስ ያሰኝኻል፡፡ 
 
እንደ እመቤታችን በክንድህ እቀፈው፣ ሰውነትህም እንደ እመቤታችን ለሱ ሞግዚት ትሁን። ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን ይዘው ወደሱ በመጡ ጊዜ እጅ መንሻህን ይዘህ ከርሳቸው ጋር እጅ መንሻውን አቅርብለት፡፡ ከእረኞችም ጋር መወለዱን ተናገር፡፡ ምስጋናውን ከመላእክት ጋር ተናገር፣ ወደ ቤተ መቅደስም ባገቡት ጊዜ እንደ ስምዖን በክንድህ ታቀፈው፤ ወደ ግብጽ በወረደ ጊዜ አሽኮኮ ብለኸው ውረድ። አቅፈኸው ከዮሴፍ ጋር ሂድ፡፡ እንደ ምድረ ግብጽ ያለች ሰውነትህን እንደ ኢየሩሳሌም ያደርጋት ዘንድ ከሕፃናት ጋር ሲድህ ሰርቀህ ሳመው፡፡ በመዓዛው ደስ ይላት እንደነበረች እንደ እመቤታችን የመላእክት፣ የጻድቃን መገኛ የሚሆን የጌታ መዓዛውን አሽት፡፡ እንደ እመቤታችን ያቅፈው የነበረ፣ በመዓዛውም ደስ ይለው የነበረ አንዱን ሰው እንደማውቀው በእውነት እናገራለሁ፤  ሕፃናትን ምሰል፤ በሕፃንነቱ ሳለ ከሄደበት ሁሉ ተከተለው፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ፍቅሩ ባንተ ታድራለች፡፡ 
 
ከሱ ጋር አንድ በመሆንህ ይዳሰስ በነበረ በማኅየዊ ሥጋው ያለ መዓዛን ከሟች ሥጋህ ታሸታለህ፡፡ መምህራን በጠየቁት ጊዜ እሱም በመለሰላቸው ጊዜ አጠያየቁን አመላለሱን አድንቅ፡፡ ለማጥመቅ ከዮሐንስ ጋር ባንድነት ኑር፣ በዮርዳኖስ የሚደረገውን ሁሉ ስማ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ሲቀመጥበት እይ፡፡ በሚጾምበትም ጊዜ ከሱ ጋር ጹም፤ ውኃውን ለውጦ ወይን ባረገ ጊዜ ጋኖችን ውኃ እየመላህ ኑር፤ ከውኃ አጠገብ ከሳምራዊት ጋር በተነጋገረ ጊዜ ያስተማረውን ትምህርት ስማ፤ አብ የሚወደውን በመንፈስ የሚደረገውን ስግደት፣ የሚሰግዱ ሁሉ በመንፈስ ለአብ ይሰግዳሉ ብሎ ሲያስተምር ስማ፤ ሙታንንም ባስነሣ ጊዜ ትንሣኤ እሱ እንደሆነ እወቅ፣ ኅብስቱንም ባበረከተ ጊዜ እንቅቡን ይዘህ ለተሰበሰቡት አድል፣ ወደ ገዳምም በሄደ ጊዜ ሄደህ ሸኘው፡፡ 
 
በመርከብም በተኛ ጊዜ፣ ጌታ ሆይ አድነን ልንጠፋ ነው ብለህ አስነሣው፣ በጉባኤም ከሱ ጋር ኑር፣ በጎዳናም ከሱ ጋር ሂድ፣ ወደ ገዳም ከሱ ጋር ሂድ፣ በመርከብም ከሱ ጋር ኑር፣ ወደ ደብረ ዘይትም ከሱ ጋር አብረኸው ውጣ፣ በምኩራብም፣ ብፁዓን እያለ ሲያስተምር ትምህርቱን ስማ፣ ያስነሣህ ዘንድ ከአልዓዛር ጋር በመቃብር ኑር፣ በኃጢአት ከመጣ ፍዳ ትድን ዘንድ እንደ ማርያም በዕንባህ እግሩን እጠበው፤ በራስህም ጠጉር አድፈው፡፡ የኃጢአትህን ሥርየት ኃጢአትህ ተሰረየልህ ሲል ትሰማ ዘንድ፤ በማዕድም ጊዜ እንደ ዮሐንስ ባጠገቡ ተቀመጥ። ኅብስቱን በባረክ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ከጁ ተቀበል፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜ ከኃጢአት ያነጻህ ዘንድ ቀርበህ እጠበኝ በለው፡፡ ማኅደረ እግዚአብሔር ሰውነትህን ንጽሕት አድርጋት፡፡ እሱን ለማመስገን ብቃ፣ በምግባር፣ በሃይማኖት ተከናወን፡፡ ነገረ ጰራቅሊጦስን ለመማር የበቃህ ትሆን ዘንድ፣ ካምስት ገበያ ሰዎች ጋር ከፊቱ ቁም፣ ከሱ ጋር መከራ ተቀበል፡፡ ይህ አሳች፣ መባልን፣ ሳምራዊ መባልን፣ መዘበቻ መሆንን ተቀበል፡፡
 
ወሪቀ ምራቅን ተቀበል፤ በቀኖት መቸንከርን ተቀበል፣ ከሱ ጋር እንደ እሱ በመስቀል ተሰቀል፡፡ በተነሣ ጊዜ (በመዋሐድ ጊዜ) ደስ ይልህ ዘንድ ከሱ ጋር መፃፃውን ፣ ከርቤውን ጠጣ፡፡ ራሱን ዘለፍ እንዳደረገ አንተም ዘለፍ አድርግ፣ እርሱ እንደ ተነሣ ትነሣ ዘንድ እንደሱ፣ ከሱ ጋር ሙት እኩያን አይሁድ በሱ ያደረጉትን ሁሉ ተቀበል፡፡ የማትመረመር ቸርነቱን ፈጽመህ አድንቅ፣ ምን አደረገ ትለኝ እንደ ሆነ፣ መላእክትን አታጥፉ ብሎ ከለከላቸው፣ ዓለምን፣ በዓለም የሚኖሩትን ሁሉ ያጠፏቸው ዘንድ አላሰናበታቸውም፡፡ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፣ ሙታንም ተነሡ ልቡናችን ግን ከጽናቱ አልተለየም፣ ማለት አላመነም፡፡ ሕዋሳተ ነፍስም ትንሣኤ ኅሊና አልተነሡም። 
 

ማስያስ/@Masiyas

30 Oct, 09:45


መንፈስ ቅዱስ ሆይ !

አብረኸኝ ከሠራህ ፣ ሥራዬን ከሠራህልኝ ፣ እባክህ ልሥራደ ለነበሩት ፣ ላሉትና ለሚመጡት ሕይወታቸው የሆንከው ፣ የብርሃን ጮራ እየፈነጠቅህ ትውልድን የምታነቃው መንፈስ ቅዱስ ሆይ መድረሻዬን እንዳውቅ አንተ ከእኔ ጋር ሁን። መንገዱን ያላገኙ ፣ ከምንጩ አጠገብ ቆመው የተጠሙ ፣ ያላቸውን ከጎደላቸው መለየት ያልቻሉ ፣ በሰዋዊ ቃላት ለመሰበር ቅርብ የሆኑ ፣ ክርስትናና ዓለም የተቀላቀለባቸው መልክ የለሽ የሆኑ ብዙ ጎስቋሎች ይጠብቁሃልና አንተ የልቦች ዕረፍት መንፈስ ቅዱስ ሆይ እባክህ ና።

በቤት በውጭ መራቆት የሰለቻቸው ፣ በአደባባይ የሚቀጡ ፣ በጊንጥ የሚገረፉ ፣ በጸጸት የሚንገላቱ ፣ አንተን ለመውደድ ፍላጎት እንጂ አቅም ያጡ ፣ ትዕግሥት በማጣት ራሳቸውንና ቤታቸውን ያፈረሱ ምስኪኖች አሉና አንተ የአብና የወልድ ሕይወታቸው እባክህ ድረስላቸው ! ጥያቄው ያስጨነቃቸው ፣ የተቺዎች መልስ ሌላ እንቆቅልሽ የፈጠረባቸው ፣ ዝንጉ አእምሮ የሚታገላቸው ፣ ከቤተሰብ ክበብ አፈንግጠው ብቸኝነት የሚያዋራቸው ፣ ለመድረስ እየፎከሩ ጉዞ ያልጀመሩ ፣ በአሳብ ሲነኩ የሚውሉ ፣ ሕልማቸው ፍቺ ያላገኘላቸው የምኞት ፍልመኞችን ታሻቸዋለህና ጸሎትን የምትቀድስ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እባክህ አግኛቸው !

በነፋስ አቅጣጫ የሚጓዙ ፣ በአየር ንብረት አገሩን ፣ በአየር ጠባዩ ቀኑን እየለኩ የሚኖሩ ፣ ሲሞቱ ሊያበቁ የሚጣደፉ ፣ ሰው የማይመጣባቸው ዝጎች ፣ ወደ ሰው የማይሄዱ ሽባዎች ፣ ከነማንነታቸው የሚቀበላቸው ይሻሉና የድሆች አምባ ፣ መሳይ የሌለህ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እባክህ መርምርህ ፈውሳቸው። በጅምር የቀሩ ፣ ዓለም ሊወርሳቸው እግድ ያወጣባቸው ብዙ ትውልዶች አሉና መንፈስ ቅዱስ ሆይ በማይደፈረው አክናፍህ ሰውራቸው። ጰራቅሊጦስ ሆይ፣ ልክ የሌለው ምስጋና ላንተ ይሁን!

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

24 Oct, 05:30


  ዝም ብለህ ተማር

    "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር ! ኹልጊዜ ተማር ! ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር! ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ። ካልተማርህ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት አቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስህ ትሠራለህ፡፡ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች።"

https://t.me/Masiyas

"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"

ማስያስ/@Masiyas

23 Oct, 18:51


#በእርግጥም_የምንሰማው

"በእርግጥም የምንሰማው አሽሙር ከሆነ የሚራመደው እግራችን ይወላከፋል። በእርግጥም የምንሰማው አሉባልታ ከሆነ የተነቃቃው ራእያችን ይከስማል። በእርግጥም የምንሰማው ሰዎች የሚሰጡንን መደብ ከሆነ ጽንፈኝነት ያጠቃናል። በእርግጥም የምንሰማው ራሳችንን ከሆነ ግምታችን ያደናግረናል። በእርግጥም የምንሰማው ጀማውን ከሆነ ሁሉም ነገር ያለቀ ይመስለናል። በእርግጥም የምንሰማው ጠብ ዘሪዎችን ከሆነ እሳቱ እንዳይጠፋ እንጨት አቀባይ ያደርጉናል። በእርግጥም የምንሰማው ትሞታላችሁ የሚሉንን ከሆነ ሕይወት የእግዚአብሔር ቀመር መሆኑን ያስረሱናል። በእርግጥም የምንሰማው የክፉውን ፉከራ ከሆነ የያዝነውን ያስጥሉናል። በእርግጥም የምንሰማው ትላንትን ከሆነ ጸጸት በእሳት ጅራፍ ይገርፈናል። በእርግጥም የምንሰማው ዛሬን ከሆነ ዜናው ያውከናል። በእርግጥም የምንሰማው ነገን ከሆነ ተስፋ ያጥርብናል። በእርግጥም የምንሰማው ኢኮኖሚውን ከሆነ እየበላን ይርበናል። በእርግጥም የምንሰማው  ነፋሱን ከሆነ የረገጥነው መሬት ይከዳናል። በእርግጥም የምንሰማው ሰይጣንን ከሆነ የእግዚአብሔርን ፍቅር ያጠራጥረናል።

ነፍስን የምታሻገር የጻድቃን መሪ የቅዱሳን መመኪያ ፤ አቤቱ የእውቀት ዓይኖችን ስጠን ዘወትር አንተን ያዩ ዘንድ ፥ ጆሮዎቻችንም የአንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ ፥ ሰውነታችን ከጸጋህ ከጠገበች ዘንድ ንጹሕ ልቦናን ፍጠርልን ቸር ሰው ወዳጅ የምትሆን አቤቱ ገናንነትህን ዘወትር እናውቅ ዘንድ!"

ቅዳሴ እግዚእ!

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

18 Oct, 16:07


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!

በቴሌግራም Live stream መንፈሳዊ ጥያቄዎች የሕይወት ፈተናዎችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ፕሮግራም ላዘጋጅላችሁ?

አሳውቁኝ!

ማስያስ/@Masiyas

18 Oct, 16:07


ጸሎተ ምሕላ

በቤትህ የተከልከን ታላቅ ገበሬ ሆይ ይቅር በለን።

ለሰማይ ክብር የጠራኸን ክቡር ሙሽራ ሆይ ማረን።

ሥራህን ካንተ በቀር የሚያደንቀው የሌለ ባለሙያ ሆይ አድነን።

ሀብትህ ጉድለት የማያሳይ ወደር የለሽ ባለጠጋ ሆይ ይቅር በለን።

ሰማይ መንበርህ ፣ ምድር መከዳህ የሆነች ሙሉ ሆይ ማረን።
የአማኞችን መሥዋዕት የምትቀበል ተለማኝ ጌታ ሆይ አድነን።

በረድኤት የወረድከው በሥጋም የተገልጥከው ታላቅ መልስ ሆይ ይቅር በለን።የደካሞችን ሸክም ያቀለልህ ለተከሳሾች የተከሰስህ ቤዛ ሆይ ማረን
ምስጋናን የምትወድ የመላእክት ፈጣሪ ሆይ አድነን።

ርቀው የማይርቁህ ፣ የሙከራ ሁሉ መደምደሚያው ጉልላት እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን
የፊትህ መልክ የማይጠገብ ታላቅ ውበት ሆይ ማረን።
የዘረጋኸው ክንድህ የማይታጠፍ አሻጋሪ አምላክ ሆይ አድነን።

ቀኑን ሌት ፣ ሌቱንም ቀን ስታደርግ የማይቸግርህ መጋቢ ሆይ ይቅር በለን።የሚችለው ያጣውን አመለኛ የምትችል የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ አትጣለን።
እውቀትህ የማይፈተን የማትመረመር ብርሃን ሆይ አድነን።

ወደ ኋላ ለመመለስ ያፈረውን ፣ ወደፊት ለመጓዝ የፈራውን የምታበረታ መጽናናት ሆይ ይቅር በለን።
የማትፈርሰው የድሆች አዳራሽ ሆይ በመልካም አስበን
ዓለማት ያልቻሉህ በድንግል ማኅፀን ራስህን የወሰንህ ሆይ አድነን

እኛን ከራሳችን ጋር ያስማማኸን ጠብ ገዳዩ ኃያል ሆይ ይቅር በለን
ለኃጢአት የተጉትን ለጽድቅ የምታነቃ የሕይወት አለቃ ሆይ ማረን።
የተወረወረን ጦር አጥፈህ የምትጥል የአብርሃም ጋሻ ሆይ አድነን።

ያላወቁህንና የማይወዱህን የምትታገሥ ታላቅ ፍቅር ሆይ ይቅር በለን።
የድሆች ጩኸት ፣ የባልቴቶች መፈናቀል የሚገድህ ሆይ እባክህ ተነሥ።
ራሱን በራሱ በጦር የወጋውን የምትፈውስ መድኅን ሆይ ዛሬ ድረስ።

ማዕበልና ነፋሳት የሚታዘዙህ የፀጥታው ወደብ አቤቱ ይቅር በለን።

ችለው የማይርቁህ ፣ ደፍረው የማይቀርቡህ እሳት ሆይ አቤቱ ማረን።
የሞት ነጋሪትን በእልልታ የምትለውጥ የእነ አስቴር የነ መርዶክዮስ አምላክ አድነን ።

የልባችንን ድንዳኔ ይቅር በለን።
ያልተገራውን ሥጋችንን ይቅር በለን።
የማያባራውን ምላሳችንን ይቅር በለን።
ገፍተን ስለጣልነው ወንድም ይቅር በለን።
ገድለን ስለቀበርነው አቤል ይቅር በለን።
ያለ በደሉ ስለፈረድንበት ምስኪን ይቅር በለን።

ከክፉ ቀን ጥፋቶች አድነን።
ከተመዘዘ ሰይፍ አድነን።
ከታላቅ ዝንጋዔ አድነን።
ከልብ ኩራት አድነን።
ከዝሙት ፆር አድነን።
በምትመጣው መንግሥትህ አስበን።

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

18 Oct, 14:58


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!

በቴሌግራም Live stream መንፈሳዊ ጥያቄዎች የሕይወት ፈተናዎችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ፕሮግራም ላዘጋጅላችሁ?

አሳውቁኝ!

ማስያስ/@Masiyas

14 Oct, 20:58


ወዳጄ ሆይ

ስትጸልይ:-

"ጌታ ሆይ በዚህ ነገር ውስጥ አለህበትን? በሌለህበት ነገር ውስጥ ከመትጋት አድነኝ። ያላንተ መሰብሰብ መበተን ሆኖብኛል።"
እያልክ መጠየቅ አንዱ የጸሎት ክፍል ነው።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

12 Oct, 17:38


ወዳጄ ሆይ!

ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ። ከአገሬ በቀር አገር የለም ፣ ከእናቴ በቀር እናት የለም ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም ፣ ከእገሌ በቀር አገልጋይ የለም አትበል። ጨርሶ መናገር ለዚህ ዓለም ነዋሪ ትዝብት ያተርፍለታል። በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሰቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም። ሌላው ሲያለቅስ የሳቁ በኀዘናቸው አጋር አያገኙም። ካልገዛ በቀር ስጦታውን የሚያቃልል የእግዚአብሔርና የሰው ወዳጅ መሆን አይችልም። ፍላጎት መልካም ነው ፣ ከልክ ያለፈ መሻት ግን በቀን ሰላም ፣ በሌሊት እንቅልፍ የሚነሣ ነው።

ወዳጄ ሆይ !

ሲሰበክ እየተኛህ ፣ ሲወራ የምትነቃ ከሆነ አእምሮህን ጠላት እያደባበት ነውና በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተዋጋ። የዛፍ የመጀመሪያ አካሉ ለስላሳ ነው። የመጀመሪያ ግንኙነትህም ዕድገት እንዲኖረው በመልካም ፍቅርና ትሕትና ወጥነው። ሀብታቸውን ሊያሳዩህ ለሚሹ እዘንላቸው። ከእነርሱ ይልቅ የሠሩት ቤት ዕድሜ አለውና። አንተም ተመክተህ ያለህን ለማሳየት በተነሣህ ቀን መጀመሪያ መቃብርህን ቆፍረህ ሂድ።

ወዳጄ ሆይ !

የታረሰ መሬት የዘር ሞትና ትንሣኤ ነው። የተከፈቱ ልቦችም የቃሉን ዘር ሲያገኙ እኔነትን ቀብረው ፣ አዲስ ሕይወትን ያወጣሉ። የግል ንግግርን አደባባይ ላይ አታውለው ። ስሜትህን ለማያውቁህ አታስነብበው። ጥረትህ ኪሣራ ቢያመጣም በዚህ ዓለም እስካለህ ጣር። የጉባዔ ታላቅነት የሚለካው በሰው ብዛት ሳይሆን በእግዚአብሔር መገኘት ፣ በታላላቆች መታደም ሳይሆን በእውነተኛ አምልኮ ነው። የሚወጥኑ ፣ የሚገነቡ ብቻ ሳይሆን የሚተቹም ያስፈልጉሃል። ተቺዎች በነጻ የሚያገለግሉህ የጥራትና ደረጃ ባለሙያዎች ናቸው። ችላ ተብለህ አድገህ ከሆነ ችላ የተባሉትን አስባቸው። የእምነት ሰዎች ሲወድቁ ብታይ በጣም አትፍረድ ፣ የመነሻውን ምሥጢርም ያውቁታልና። ያሉ የመሰሉ ነገር ግን የሌሉ ፣ የሌሉ የመሰሉ ነገር ግን ያሉ ብዙ ሰዎች ናቸው።

ወዳጄ ሆይ !

ሙሴን ሰው እንዳልቀበረው አስታውሰህ፣ ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደገነዙት አስበህ ሞትህ ሰርግ እንዲመስል አትጓጓ። ክፉ ሰዎችን እየተመለከትህ ታዝናለህና ለሚመለከቱህ ኀዘን ላለመሆን ፈሪሀ እግዚአብሔር ይኑርህ። እግዚአብሔር ለሁሉም ጾታና ወገን ክብር እንዳለው አስብ። በወንዱም በሴቱም ላይ ይሠራልና ምሉዕ እግዚአብሔርን አታጥብበው። ሕይወቴ እግዚአብሔር ነው ማለት ቀርቶ ሕይወቴ ሌላ ነው የሚል ሰው ፣ ለመግደል የማይመለስ ጨካኝ ነው። አንተ የምታስፈልገው ለጠወለጉ ሰዎች ፣ ለተጎሳቆሉ ነፍሶች ነው። ቃላትህ የድምፅህ አቅም ከሞት የሚመልስ እንጂ ወደ ሞት የሚሰድድ አይሁን።

ወዳጄ ሆይ !

የጠነከሩ ልቦችን እንደ ወርቅ የሚያቀልጥ የፍቅር እሳት ነው። ልትደርስበት ያቃተህን ነገር ባዶ ነው ብለህ አትናቀው። ሲኖርህ ድሀን ካላሰብህ ሳይኖርህ ልታስብ አትችልም። ስለማንም ሰው ክፉም ደግም በእርግጠኝነት መናገር አትችልም። የመናገር ብቻ ሳይሆን የመኖር ድፍረትህ እግዚአብሔር ነው። አንድ የካደ ሰውን ስታሳምን የክርስቶስን መስቀል አገዝከው ማለት ነው። ንግግር ማብዛት በራስ ላይ ወጥመድ መታታት ነው።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

06 Sep, 12:46


የዘመኑ መዝሙር 22

ስሜቴ እረኛዬ ነው፣ የሚያስገኝልኝ ነገር የለም። በደረቅ ስፍራ ያሳድረኛል፣ ወደሚያውክ ማዕበል ይመራኛል። ነፍሴን አጠፋት፣ ስለ ግለቱ በጥፋት መንገድ መራኝ። በሰላም መንገድ ብሄድ እንኳ ስሜቴ ከእኔ ጋር ነውና ሁሉን እፈራለሁ። ግብታዊነቱና አለመረጋጋቱ ያነዋውጸኛል። በፊቴ እንቅፋትን አዘጋጀብኝ፣ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በአመድ ቀባው። ጽዋዬ የማይሞላ ነው። ጉድለቱና ንፍገቱ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል ፣ ከዚህ ካልወጣሁ በጥፋት ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

02 Sep, 19:45


ወዳጄ ሆይ!

ጨለማቸውን ልታበሩ ስትፈልጉ ብርሃናችሁን ትተው ጨለማችሁን ያያሉ። ከዚያ የበለጠ ጨለማ ስትሆኑባቸው ክፉ ይሉና ይሸሿችኋል። ታዲያ ብርሃን ቀርቶ ጨለማ የማያነቃውን ሰው ምን ትሉታላችሁ? የሰውን ልጅ ሙሉ ለሙሉ ብርሃን ሙሉ ለሙሉም ጨለማ አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው።

ወዳጄ ሆይ!

ጨለማን ከገፋህ በተቃራኒው ትስበዋለህ። ጨለማን ከተገነዘብክ ብርሃን ታደርገዋለህ። ጨለማን አትግፋ ይልቁን ጨለማን አብራ። የገፋኸው ነገር ሁሉ ይወርስሃል። ጨለማን ብርሃን ካደረክ ግን በጨለማ Fream of reference ስታይ ብርሃኑ አንተ ትሆናለህ። የምታበራው ጨለማ ከሌለህ ግን ጨለማው ያው አንተ ትሆናለህ።

ወዳጄ ሆይ!

ሃይማኖተኛ ነኝ እውነት ከእኔ ጋር ነች። ካለ በኋላ ለአንዲት ነፍስ ከማይሳሳ ጨካኝ ሰው በላይ አስመሳይ ከየት ይገኛል?

ለምን እንደሚኖር የማያውቅ ሰው ፍቅርና ርኅራሄ አይኖረውም።

ሁሌም ጥበብን ፈልግ እውቀት አንተን ለመግደል የተደገሰ ድግስ ነው።

ስለ ራስህ ለሰው ከማስረዳት በላይ ሞኝነት የለም። ሰዎች የሚሰሙ ሲፈልጉ ብቻ ነው።
የእውቀት ጠላት እርግጠኛነት ነው። እገሌን አውቀዋለሁ ብለህ እርግጠኛ በሆንክበት ቅጽበት በዛው ትቀራለህ። እርሱን ግን ከቦታው ፈቀቅ ብሏል።

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

19 Aug, 05:23


"ደብረ ታቦር" (ክፍል ፪)

፫፦ ዓለምን ስለመናቅ ለማስተማር

➣ ዓለምን ምንንቀው በጌታ ብርሃን ነው
➣ በጨለማ ውስጥ አለማየት ብቻ አይደለም። በልኩም አንገምትም ትንሹ ነገር ትልቅ ሊመስለን ይችላል የእርሱ ብርሃን ሲበራ ግን ትልቅ የተባለው ነገር ትንሽ ይሆንብናል። ቁጠኞች የነበሩ ዮሐንስንና ያዕቆብን በዚህ የተነሣ የነጓድጓድ ልጆች ተብለው ተጠርተዋል።
ጌታን ይከተሉት የነበረ ለምድራዊ ዝና ነበር። የሰው ልጅ የምግብ ጥያቄው ሲመለስ የክብር ጥያቄው ደግሞ መቀስቀስ ይጀምራል። ምናልባት እርሱ ክብሩን ሲሰውር እነርሱ የሌላቸውን ክብር ሲፈልጉ ራሳቸውን ታዝበውት ይሆናል።

➣ ደብረ ታቦር የዘመናት ጥያቄ የተመለሰበት ነው።

➣ ሙሴ ፭፻፸ /570 ከአምላኩ ጋር ተነጋግሯል።
ለምን ያኔ አልተገለጠለትም መልከ ጥፉ ስለሆነ አይደለም።  በተስፋ ዘመን ለባላጋራዎች የተነገረው ትንቢት ሙሴ የእግዚአብሔርን መልክ አየ። የዘመናት ርዝማኔ ለእግዚአብሔር ጸሎታችንን አያስረሳውም። አዳምን ሙሴን ኤልያስን መጻጉን ማስታወስ በቂ ነው። አንድን ሕፃን ራቱን ሳይበላ ቢተኛ ቀስቅሰው እንደሚያበሉት መለኮታዊ ግርማውን ሳያዩ የተኙትን እነ ሙሴ ኤልያስን አልዓዛርን ያሉትን ቀስቀሶ አበላቸው።  ዘመኑ አለፈ የሙሴ የጸሎት ዘመኑ ግን አላለፈም። ሞት ለእኛ መጨረሻ ይሆናል ለእርሱ ግን የሥራ መጀመሪያ ነው።

➣ ዋና ክፍል ወን ዘማቴ ፲፯፥፩

➣ ከስድስት ቀን በኋላ የቱ ስድስት ቀን ነው? ጴጥሮስ ከመሰከረ ነሐሴ ፮ (ስንክሳር ተመልከት) በስድስት ከመሰከረ በኋላ ያመኑትን ሊያሳያቸው ጴጥርስን ዮሐንስን ያዕቆብን ይዟቸው ሄደ።

➣ ለምንድን ነው እነዚህን የመረጠው?

ጴጥሮስ :- ሁሉ አሁን ይሁን ሚል ነውና የመለኮቱ ብርሃን ያስፈልገዋል።

ዮሐንስና ያዕቆብ:- እነዚህ ቁጠኞች ለማሰብ ጊዜ ያልነበራቸው ሰዎች ተናግረው ሳይጨርሱ ሚቸኩሉ ነበሩ።

ችኮላቸውን ተመልከቱ።

“ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት።” ሉቃስ 9፥54

የመለኮቱ ብርሃን ካልበራልን ያለው ይሁን አልንም ያልኩት ይሁን ነው የምንለው።  ቁጣ የዘላለማዊ ትክክልኛነት ስሜት ነው አርማለሁ እንጂ እታረማለሁ አይልም። የክብር ችግር ያለበት ሰው ቁጠኛ ነው። ጎርነን ብሎ ንግግሩን በኃይል የሚጀምረው ክብሬን እንዳትነኩ ነው። ይህን አስተሳሰብ መጣል ሚቻለው በወንጌል ትምህርት ብቻ አይደለም የመለኮት ብርሃን ሲበራልን ጭምር ነው።

እንደምናውቀው ከቤታቸው ሲወጡ ወላጆቻችን "ገራሙን ለጎረቤት ሰጥተው ኃይለኛውን ልጅ ራሳቸው ይይዛሉ ጌታ እነዚህን ሰዎች አይነጥላቸውም ነበረ። ምናልባት ሁልጊዜም እግዚአብሔር ከያዛችሁ ኃይለኛ ስለሆናችሁ ሌላ ስለማይቻላችሁ ነው።"

ሴትዮዋን "ቤተክርስቲያን መሄድሽን ባለቤትሽ ይወደዋልን አልኳት "እንዴ ምን ነካህ እኔን አቀዝቅዞለት።" አለችኝ።

ማንም ማይችለን የነበረውን ጌታ ችሎን ቤተሰብ ጓደኛ ጎረቤት ሰላም ሆኗል። ከእርሱ በቀር ማንም አይችለንም። ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው ደብረ ታቦር ተብሎ አልተገለጠም በዚህ እንደገለጠ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉም ያምናሉ። ብቻቸውን በተራራው በመለኮቱ ብርሃን ጴጥሮስ ያን ባየ ጊዜ ምስክርነቴ ለካ ልክ ነው አለ። ይሄው አየሁት እንዲል።
ሁለቱ ደግሞ :- እኛ የሌለንን ክብር ናፍቀን እርሱ ይህን ያለውን ክብር ይዞ ለካ ሰውሯል እንዲሉ ነው።

ቅዱስ ሙሴ:- ደግሞ ያን ሲያይ ወይ ጉድ ጌታ የሽ ዓመት ጸሎትን አትረሳም ከሞት ቀስቅሰህ "ጸሎትን ታበላለህ" ይላል። አንዱ ብርሃን ብዙ መልስ ነው።
ብቻቸውን:- አሁን በዚህ ቤት ብቻችሁን (ለየብቻ) ተቀምጠናል ግን ለእያንዳንዳችን ብቻ ነው የሚመልሰው ለሕዝብ ሲናገር ለግላችን እየተናገረ ነው። ስም ጠቅሶ የመናገር ያህል እርሱ እኛን ይናገረናል።

ያ ልዩ ብርሃን ሲበራ :- የጴጥሮስ ጥያቄ ልዩ ነው ተመለሰለት

የወንድማማቾች ጥያቄም ተመለሰ
የሙሴም የኤልያስም ጥያቄ ተመለሰ።

ዲ/ን ብንያም ጋሻው

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

19 Aug, 05:23


"ደብረ ታቦር"

“ሰሜንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል።”
መዝሙር ፹፱፥፲፪

በስተ ምዕራብ ደቡብ 10 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ተራራ ነው። 572 ኪ.ሜ ከባሕር ጠለል (ወለል) ከፍታ ላይ የሚገኝ ነው።
ደብረ ታቦር በተፈጥሮ ሽቱ የታወደ ተራራ ነው። በደቡብ ስንመለከት እስከ እስራኤል ድረስ እናያለን የካቶሊክ የግሪክ አብያተ ክርስቲያናት አላቸው። በስተ ምሥራቅ ግርጌ ሰፊ ሜዳ አለ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ የሚዘልቅ አርማጌዶን የሚባለው ጦርነት በዚህ ስፍራ ሲሆን ቀጠሮ ያለው ቦታ ነው። ከፍታው 1129 ጫማ እንደሚያህል አጥኝዎች ይናገራሉ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግስቱን ክብር የመለኮቱ ብርሃን ገለጠ ለምን?

1:- አምላክነቱን ለማወጅ ነው።

“እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።” ማቴዎስ ፲፮፥፲፭

በፊሊጶስ ቂሣሪያ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እርሱ ግን ሰዎች እንደሚሉት የሆነ አይደለም።

➊ ኤልያስ
❷ ሙሴ አሉት
❸ እርሱ ግን የነቢያት አምላክ ነው።
❹ በሥጋ መጋረጃ የተጋረደው መለኮት በደብረ ታቦር ተገለጠ።

➣ እግዚአብሔር ራሱን የገለጠባቸው ታላላቅ ተራራዎች አሉ።

፩፦ የሲና ተራራ

፪፦ የኮሬብ ተራራ
ኤልያስ በዝምታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ የሰማበት

፫፦ ደብረ ታቦር  (ክፍል ፩)

➣ በሐዲስ ኪዳን ታላላቅ እውነትን ለዓለም የገለጠባቸው ደግሞ

፩፦ የአንቀጸ ብፁዓን ትምህርትን ተራራ ላይ ገልጧል (የተራራው ስብከት )

➣  በዚህ ተራራ የተለወጠ ሕይወት የከፍታ አኗኗርን ገለጠ።

፪፦ መለኮታዊ ብርሃኑን ለቅጽበት የገለጠበት የታቦር ተራራ ነው።

፫፦ለዓለም መዳንን የገለጠበት የቀራንዮ ተራራ ነው።

ከትንሣኤው በኋላ ያለውን ክብሩን በደብረ ታቦር ገልጧል። ክብሩን የገለጠው ለሚገዳደሩት እርሱ እንደዚህ ነው ለሚሉት ለሚተቹት አይደለም።

ለደቀመዛሙርቱ

➣ ለጴጥሮስ
➣ ለያዕቆብ
➣ ለዮሐንስ ለስምንቱ ደቀመዛሙርት እንጂ።

እኛ በወዳጆቻችን ፊት እንደምንም ለብሰን ነው የምንወጣው። በጠላቶቻችን ፊት ግን ሽክ ብለን ነው ምንወጣው። እርሱ ግን ክብሩን የገለጠው በወዳጆቹ ፊት ነው። እርሱ በጠላቶቹ ፊት ማንነቱን ለማስረዳት አይሰጋምና።

"እግዚአብሔር አይሰጋም
የሚሽረው የለምና።" የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ጸሐፊ የሆኑት አለቃ ዘነብ።

፪፦ የጴጥሮስን ምስክርነት ለማጽናት

ወን.ዘማቴ ፲፮፥፲፮
“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።”

➣ ጴጥሮስ ቸኮለ ለመልካም ቸኮለ "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።" በተፈጥሮ መረዳት አይደለም በሰውነቱ ቅርብ ነው በአምላክነቱ ታዳጊያችን ነው። ጴጥሮስ ያመነውን ተናገረ ጌታ ደግም በደብረ ታቦር ያመነውን ሊያሳየው ፈለገ። ያመነውን ስንናገር ያመነውን እናያለን። ስናይ ያመነውን አይተን እናረጋግጠዋለን። እርሱ ያመነውን እንድናየው ያደርገናል። እምነት ማለት ምን ማለት ነው? ስንል ምንም የሚታይ ነገር በሌለበት ስፍራ ላይ እንዳየን አድርገን ርግጠኛ መሆን ነው። ያለ ምንም መያዣ የእውቀት ዋጋ አይደለም የእምነት ዋጋ በእግዚአብሔር መንግስት ዋጋ አላት።

==) ዲ/ን ብንያም ጋሻው

https://t.me/Masiyas

ማስያስ/@Masiyas

07 Aug, 09:51


ቅድስት ሆይ !

ባንቺ ላይ የተከናወነው የሰው እጅ የለበትም። ድንግል መሬት ታብቅል ብሎ ዕለተ ሠሉስን የባረከ፣ በትረ አሮን  በተአምራት እንድታፈራ አድርጎ ሊቀ ካህኑን ያከበረ ፣ አንቺም እንበለ ዘርዐ ብእሲ ትወልጂ ዘንድ ፈቀደ። ባንቺ ላይ በተከናወነው የሰው እጅ የለበትም።

ቅድስት ሆይ !

ጃንደረቦች ደረቅ ዛፍ ነኝ እንዳይሉ፣ አንቺ በባሕርያዊ መብት ልጄ የምትይውን እነርሱ በጸጋ ልጄ እንዲሉት ድንግል ሳለሽ ወለድሽ። ባሕረ ኤርትራ ከመከፈሉ ፣ መና ከመዝነቡ በላይ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይገሰስ አምላክን መውለድሽ ፣ ኅብስተ ሕይወት ክርስቶስ ካንቺ ቤተ ልሔምነት መውጣቱ ትልቅ ተአምር ነው።

ቅድስት ሆይ !

የአምላክ እናት በመሆንሽ ጠላት በዛብሽ እንጂ አልቀረልሽም። ስትፀንሺ አመክንዮ ፈላጊ ረበናትን ትሳቀቂ ነበር። ስትወልጂ ሄሮድስ ልጅሽን እንዳይገድለው ትሸሺ ነበር። ልጅሽ በሮማውያንና በአይሁዳውያን ሲጠላ ታዝኚ ነበር። ኀዘንሽ የእናትነት ብቻ ሳይሆን የአማኝነትም ነበር። ፍጡር በፈጣሪው ላይ ባደረሰው በደል ትሰቀቂ ነበር። ሁሉ እያለው ሁሉ እንደሌለው በሆነው ልጅሽ የሰዎችን የግፍ ጦር ባሰብሽ ጊዜ ፣ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፍ ነበር። የልጅሽ ጠላቶች ያንቺም ጠላቶች ነበሩ። ስደቱ ስደትሽ ነው። ሰማዕት ዘእንበለ ደም ሁነሽ እሞሙ ለሰማዕታት ተብለሻል ። ደናግል ተስፋ እንዳይቆርጡ ፣ ደረቅ ዛፍ ነኝ እንዳይሉ በድንግልና ወልደሽ ምክሐ ደናግል ሁነሻል።

ቅድስት ሆይ!

ሴቶች ሁሉ ከወለዱ በኋላ ድንግል አይባሉም። ድንግል ሁነው ያለ ዓላማ ቢቀሩ ተፈላጊነት ያጡ ተብለው ይዋረዳሉ። ወልደሽ ድንግል የተባልሽ ፣ ዘላለማዊት ድንግል ተብሎ መጠራት ክብርሽ የሆነ አንቺ ብቻ ነሽ። እንዴት ምንጩ ሳይከፈት ውኃው ይፈስሳል ! ማየ ሕይወት ክርስቶስ ከኅቱም ድንግል ፈልቋል። ብዙ ልጆች እንዳሉሽ ትላንት አይሁድ ፣ ዛሬ ስሑታን አንቺን ለማሳነስ ይናገሩታል። አዎ ያንቺ ልጆች አይቆጠሩም፤ በልጅሽ ያመኑ ሁሉ ልጆችሽ ናቸው።

ቅድስት ሆይ !

በሔዋን ያዘኑ ባንቺ ካልተደሰቱ ይገርማል። በሥጋ ድንግል በመሆንሽ በዚህ ብቻ አልተደነቅንም። በኅሊናም ድንግል ነሽ ። ድንግል በክልኤ/በሁለት ወገን ድንግል ነሽና ለቅዱሱ ቅድስቲቱ አስፈልገሽዋል። ሊቀ ካህናቱ ብቻ በዓመት አንድ ጊዜ የሚገባባት ያቺ ኅቱም መቅደስ ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች። ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ብቻ ያደረበት ያንቺ ማኅፀን ከዚያች መቅደስ ይበልጣል። ከሊቀ ካህኑ ሌላ በዚያች መቅደስ የሚገባ ሰው በሞት ይቀጣል። እሳተ መለኮት በተቀመጠበት ባንቺ ማኅፀንም ፍጡር ይቀመጥ ዘንድ አይቻለውም። መጠን የሌለው ክብር ሳለሽ መጠን የሌለው መከራ ተቀበልሽ። ክብሩ ባየለ ቍጥር መከራውም ብዙ ይሆናል። ሁሉ ያንቺ ይሆን ሁሉን አጣሽ ። ልጅሽ ብቻ ሀብት እንዲሆንሽ “እፎ ቤተ ነዳይ ኀደረ ከመ ምስኪን” ተባለልሽ።

ቅድስት ሆይ !

የቀረበው የሰው ልጅ በአዳም በደል ራቀ ፣ ቀርቦ ወደ እርሱ ቢያቀርበው ሰው አሁንም ጌትነቱን ካደ። የልጅሽን ጌትነት የማያምኑ ፣ በመስቀሉ ሥራ የማይታመኑ ሁሉ ያንቺ ወዳጆች አይደሉም። አንቺን ለመምረጥ በተነሣ ጊዜ ማንንም አላማከረም። በምክረ ሥላሴ ወላዲተ አምላክ ሁነሻል። የልጅሽን አምላክነት የሚያምኑ አንቺን ወላዲተ አምላክ ለማለት አይሰቀቁም። ባለ ሁለት ልደት የሆነው ልጅሽ ፣ ድንግልም እናትም በሆንሽው ባንቺ ገነነ። የሴት ዓለም ክብር ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆች ክብረት መገለጫ ነሽ።

ቅድስት ሆይ !

ሰፊው ዓለም የጠበባቸው ፣ ነግቶ ምሽት የሚመስላቸው ፣ በነፍስ ማዕበል የሚንገላቱ በልጅሽ ሰላም ይረፉ። ቅድስት ሆይ ለምኚልን !

አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው !
ካንቺ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ወልድ ቡሩክ ነው !
ያጸናሽ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው። ለዘላለሙ አሜን።

https://t.me/Masiyas

1,775

subscribers

662

photos

7

videos