Jinka University @jinka_universit Channel on Telegram

Jinka University

@jinka_universit


እውቀት ለለውጥ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ

Any Question @JKU_BOT

Jinka University (Amharic)

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከተኛ እስኪንኤል ሉቭጥ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፤Jinka University፤ በህዝብ ውስጥ የሚኖሩ ትምህርት ቤቶችን በመላ አካባቢ ማሰራመን ላይ ቦታ አለ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ሴቶች የተማሪዎች አዘገጃቸውን የተረጋገጡትን ለማድረግ የሚገባውን ታሪኮዎች ላይ የሚያምር እውቅና ለማስተካከል ሳይሆን መረጃና ስልጠናውን በዩኒቨርሲቲ ቻናላችን @jinka_university ላይ እንቀርባለን፡፡ ሌክ ብቻ ብለን ማስጠበቅና ለማስቆም መሰረት ካለፈ በስቴዲየም ስዕሉንና የትምህርት ድምፅዎቹን ልንከፍሉ አዲሱ ለሆነው ኢሜይል መዝገበ ይችላሉ፡፡ የተለወጡና የበለጠ ሴቶችን ልንከፍሉ እናመሰግናለን፡፡ ስለእኛ የምንፈልጋቸው ግምት እና ሊጠብቅ እንችላለን፡፡

ላይ ተጨማሪሽ ይህንን ታሪኮችን በተጨማሪሽ ይተይቡ፡፡ ስለዚህ እኛ ለአሥራ ሁለት ማእከል ፎም እና ለህክምና ለምላሸባችን ለእኛ ያለውን ጉዳይ እና መዝገባውን ማግኘት ማለት እናመሰግናለን፡፡

Jinka University

21 Apr, 07:49


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ-አልፊጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በተለይም ለዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!!

ዒድ-ሙባረክ

ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር)
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

Jinka University

06 Oct, 17:55


የሀዘን መግለጫ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረው ተማሪ ብርሃን ካሴ መስከረም 24/2014 ዓ.ም ከአርባምንጭ ወደ ጂንካ እየመጣ ሳለ በተፈጠረ የመኪና አደጋ ባጋጠመው ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማን ሀዘን መሪር ነው።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ብርሃንን አስክሬን ለቤተሰቦቹ ያደረሰ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አመራሮችን ጨምሮ ሽኝት አድርገውታል።

ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹና ለመምህራኖቹ መፅናናትን እንመኛለን

Jinka University

10 Oct, 15:24


👐የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ መልሶ ቅበላ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ የሚኒስትሩ
ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ
------------------------------------------------------------------------
🗣ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲው የተማሪ መልሶ ቅበላ
ለማድረግ ተገቢዉን ዝግጅት ከማድረግ አኳያ ያለበትን ደረጃ ሊገመግም
የተላከው ግብረ-ሀይል በመጀመሪያ ከዩኒቨርሲሲው ማኔጅሜንት ኮሚቴ ጋር
በተለይ ተመራቂ ተማሪዎች ቅበላ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርጓል፡:፡ከውይይቱ
በመቀጠልም በዝግጀት ምዕራፉ የኮቪድ-19 ስረጭትን ከመከላከል አኳያ
ቅድመ ትኩረት የተሰጣቸዉን የመማሪያ ክፍሎች፣የአይ ሲቲ አጠቃቀም፣
የቤተ-መጽሐፍት ከፍሎች አደረጃጀት፣የመመገቢያ ካፍቴሪያና የተማሪዎች
ዶርም አደረጃጀት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡በዚሁ መሰረት የመማሪያ ክፍሎች
ከ15 እስከ 20 ተማሪ፣ የመመገቢያ አዳራሽም በ1 ጠረጴዛ ርቀቱን በጠበቀ
ሁኔታ 2 ተማሪ ብቻ ለማስተናገድና በ1 የተማሪዎች መኝታም 2 ተማሪ ብቻ
ማስተናገድ በሚችል መልኩ መዘጋጀቱን ግብረሀይሉ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡
ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር አካለት ጋር በመሆን ቀሪ
ዝግጅቶችንም ተዘዋውሮ በመመልከት ምክረ ሃሳብ ያቀረበው ግብረሀይሉ
ከተለያዩ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና መምህራን ጋር በነበረው የጋራ
መድረክ ላይ ከቤቱ የተነሱትን የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን
በማንሸራሸር በጥልቀት ተወያይቷል፡፡በመሆኑም ግብረ-ሀይሉ የዩኒቨርስቲውን
ዝግጅት አስመልክቶ ለሚንሰቴሩ የሚያቀርበዉን ግብረመልስ ተከትሎ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው የዝግጁነት ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት መሰረት ዩኒቨርስቲው በመጀመሪያ ተመራቂ ናቻው ያላቸዉን
874 ተማሪዎቹን በጥቅምት ወር 2013 የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ይጠራል
ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@Jinka_University | Share

Jinka University

04 Apr, 16:35


😷ጂንካ ለኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ማቆያ ተዘጋጀ
++++++++++++++++++++++++++++
🗣አያድርገውና የኮሮና ቫይረስ ደቡብ ኦሞ ዞን ምናልባት ቢከሰት በሚል ስጋት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ መንግስት ባስቀጠው አቅጣጫ መሰረት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ማቆያና ለህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ አዘጋጅቷል። የደቡብ ኦሞ ዞን የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረሃይል አባላት እንዲሁም ከዞን ጤና መምሪያና ከጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተውጣጡ አካላት የተመረጡ ህነፃዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ዩኒቨርሲቲው የራሱ የሆነ የኬሚስትሪ ላቦራቶሪ ባይኖረውም በጂንካ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ላቦራቶሪ ከባለድርሻ አካላት (ከክልል/ዞን እና የጂንካ ሆስፒታል ባለሙያዎች) ጋር በቅንጅት የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ለማምረት የግብአት ማፈላለግ/ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ሳኒታይዘር በዞኑ በግዥ እንኳ የማይገኝ ስለሆነ ለህዝቡ ተደራሽ ለመሆን ጂንካ ላይ ማምረት የግድ ይላል።

🏢 @Jinka_University | SHARE

Jinka University

04 Apr, 16:34


🙏ምስጋና ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ለረዱን
++++++++++++++++++++++++++
🗣ከ3300 በላይ የሚሆኑ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሶስት ቀናት ውስጥ 76 አውቶቪሶችን አፈላልጎ ወደመጡበት መመለሱ ቀላል ስራ አልነበረም። በጅምሩም ሆነ በጉዞው ወቅት በርካታ ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች ገጥመውናል። በዚህ ከባድ ሃላፊነትና ርህራሄ በሚጠይቅ አገራዊ ጉዳይ የሰዎችን የመልካምነት ከፍታ ብቻ ሳይሆን የክፋትና የስግብግነት ጥግ ያየንበት አጋጣሚ ነበር። ያሳዘኑን ጥቂት ግለሰቦች ማንሳትም ሆነ መውቀስ አንፈልግም፤ ህልናቸው ይውቀሳቸው። መልካም የሰሩትን ብዙሃን በሙሉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቁምነገር ያመሰግናል። የዩኒቨርሲቲው አመራርና ሰራተኞች (በተለይ ፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት ክፍሎች) እንዲሁም የተወሰኑ የተማሪዎች ተወካዮች በኮሚቴና በግል ያደረጉት መረባረብ እጅግ የሚደነቅ ነው። ወላይታ ሶዶና ሆሳዕና ተልከው ተማሪዎችን እየተቀበሉ ይሸኙ የነበሩት 3 ሰራተኞቻችን (አበበች ፀጋዬ፣ ዕድገትበር እና አስቻለው ሚልኪያስ) ብዙ ለፍተዋልና ምስጋና ይገባቸዋል። በአስተባባሪነት እስከ ጅማ ያጀበው ሰላሙ አደቆ፣ እስከ ነቀምት ያጀበው ፍጹም ሌራ እና እስከ ባህር ዳር ያጀበው ሰርኩ ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ቀና ወጣቶች ናቸው። አውቶቪሶችን በማስተባበሩ ረገድ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊ ሚና እጅግ የጎላ ነበር። ከመምሪያው የተላኩት አቶ በለጠ ሜካና አቶ ካሳሁን ጋልሺ ግቢ ውስጥ ሶስት ቀን ሙሉ ከዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ጋር እኩል ስሯሯጡና ያለእንቅልፍ ይሰሩ ስለነበር ሊመሰገኑ ይገባል። ፀጥታ በማስከበርና አንዳንዴም እስከተወሰነ ርቀት በመሸኘት የፌዴራል ፖሊስ የጎላ ሚና የተጫወተ ሲሆን የልዩ ሃይል፣ የዞን ፖሊስ፣ የጂንካ ከተማ ፖሊስና መከላከያ እንደወትሮ በተጠንቀቅ አብረውን ስለነበሩ እናመሰግናለን። ተማሪዎች በጉዞ ወቅት ችግር እንዳይገጥማቸው በማሰብ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጎንዮሽ በተደረገ ቅንጅት መሰረት ምግብና መኝታ ወይም መኝታ ብቻ እንዲያገኙ ያመቻቹልን ፕሬዚዳንቶች አሉ። በዚህ ረገድ አቶ መርክነህ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ሃላፊ፣ ዶ/ር ሐብታሙ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ዶ/ር ብርሃነመስቀል የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምግብና መኝታ ያዘጋጁ ሲሆን ፕ/ር ታከለ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ አቶ አያኖ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ ዶ/ር ገናናው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ዶ/ር ፍሬው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መኝታ ፈቅደዋል። ለሁሉም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና ያቀርባል። ከዚህ በተረፈ በጉዞው ወቅት አምስት አውቶቪሶች ላይ የተሳፈሩ ተማሪዎች አዲስ አበባ እኩለቀን ደርሰው በተለያየ ችግር ምክንያት ውለው ኮቴቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አድረዋል። በማግስቱ ጠዋት በክብርት ሚኒስቴሯ በፕ/ር ሂሩት ልዩ ትዕዛዝ፣ በአቶ ደሳለኝ ሳሙኤል አስተባባሪነትና በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሃላፊዎች ተባባሪነት የተሻሉ አውቶቪሶች ተመቻችተው ተማሪዎች በደስታ ተሸኝተዋል። በዚህ አጋጣሚ የሚኒስቴሯን ፈጥኖ ደራሽነት፣ የሌሎችን ትብብር እንዲሁም የተማሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ትዕግስት እናደንቃለን። ትብብር ሳንጠይቃቸው በዜግነት ስሜትና በራሽ ተነሳሽነት ተማሪዎች ችግር እንዳይገጥማቸው የተንከባከቡና የተከላከሉ ሁሉ (እነ ብሩክና ሌሎችም) 'ኢትዮጵያዊነት መልካምነት' መሆኑን በተግባር ስላረጋገጡ ለቀናነታቸው በያሉበት የላቀ ምስጋና ይድረሳቸው። ፕ/ር ገብሬ ይንቲሶ ደኮ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

🏢 @Jinka_University | SHARE

Jinka University

04 Apr, 16:33


🚌የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ
*************************************
🗣ተማሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የተወሰነው በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት የተነሳ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ትራንስፖርት አመቻችቷል። ዛሬ በ17/07/2012 ዓም 1286 ተማሪዎች በ33 አውቶቪሶች የተንቀሳቀሱ ሲሆን የርቀት መንገድ ተጓዦች አዳራቸውን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲና በወላይታ ሶዶ ግብሬና ኮሌጅ አድርገዋል። ሁለቱ ተቋማት ላደረጉት አቀባበል እንዲሁም የምግብና የመኝታ አገልግሎት ምስጋናችን የላቀ ነው። በነገው ዕለትም የቀሩት ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ይመለሳሉ። ተማሪዎቻችን በመንገዳችሁ እና በምትሄዱበት ሁሉ መልካም ነገር እንዲገጥማችሁ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ይመኛል። ኮሮናን በጋራ እንከላከል!!

🏢 @Jinka_University | SHARE

Jinka University

16 Oct, 20:57


🕴ልዩ ዝግጅት በጂንካ ዩኒቨርሲቲ
++++++++++++++++++
🗣ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ደማቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም አዘጋጀ። በዝግጅቱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የመንግስት አመራር አካላት፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ደቡብ ኦሞ (ትንሿ ኢትዮጵያ) የሰላምና የፍቅር መንደር ስለሆነች ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ምንጊዜም ከጎናቸው እንደማይለዩ አረጋግጠዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ባህል ክነት ቡድንና ሐበሻ ኢንተርተይንመንት ቡድን ፕሮግራሙን በአዝናኝ ዝግጅት ያደመቁ ሲሆን ታዳሚዎች የምሳ ግብዣ ከተደረገላቸው በሗላ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
ዕውቀት ለለውጥ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ

🏢 @Jinka_University | SHARE