♦ ዳግም ምጽአት በቤተክርስቲያን አስተምሮ በዓመት አራት ጊዜ ቀን ተቆጥሮለት ጊዜ ተሰፍሮለት ይታሰባል ከነዚህ ዕለታት መካከል
✔በዓብይ ጾም እኩሌታ በደብረዘይት
✔በወርሃ ጷጉሜ ጓላ ባለ መልኩ ይታሰባል። ጌታችንም በደብረ ዘይት ተራራ ስለ ዳግም ምጽአት " እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።" (የማቴ 24:3፤) ብለው ሐዋርያት በጠየቁ ጊዜ በስፋት አስተምራል ።
♦ የመጀመሪያው ምጽአቱ (በግብር መምጣት)ሥጋ በመልበስ ለሰው መሥዋዕት ሁኖ ሊያድን ለካሳ በፍጹም ትህትና የእኛን ውርደት ተቀብሎ ወደዚች ዓለም ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መለኮቱን ከእኛ ሥጋዊ ጋር አዋሕዶ በበረት በመወለድ መጣ።
♦ ዳግማዊ ምጽአቱ (በኩነት)በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት በፍጹም ጌትነት በኃጥአን (የመጀመሪያ ምጽአቱን) ባልተቀበሉት ላይ ሊፈርድ ዐይን ሁሉ እየተመለከተው በገሃድ ይመጣል፡፡ ‹‹እግዚአብሔርስ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፣ እግዚአብሔር ግልጥ ሁኖ ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይነዳል (መዝ 49፡3) ለፍርድ የሚመጣው ከሦስቱ አካል አንዱ ወልድ ነው፡፡ በፍቃድ አንድ ስለሆኑ።የሚመጣውም ለፍርድ ስለሆነ እጅግ በጣም በሚስፈራ ግርማ ነው።
♦ ጌታችንም በዚህች ምድር በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ሲመላለስ ሐዋርያት ሁሉን ትተው ተከትለውት ነበርና " ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።"በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤" (ዮሐንስ 14:2፤) ብሉ ተስፋውን ከሐዋርያት ጀምሯል።
♦ ቀዳማዊ ምጽአቱ ከልጅ ከልጅ ተወልጅ አድንሃለሁ ያለውን ቤተ አይሁድ በተስፋ ጠብቀውታል ። ክርስቶስ በመወለዱም የደነገጡ ደስ ያላላቸው እነሔሮድስ የአይሁድ ካህናትም ነበሩ በዳግም ምጽአቱም ደስ የማይላቸው " በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።"የሚደነገጡ ከአስሩ ደናግል መካከል በእኩለ ሌሊት ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።"(ማቴ 25:2)
♦ እነዚህን ሁሉ ምልክቶች ፣ማስጠንቀቂያዎች ፣ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ፣ጽኑ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ በአእምሮ ጽላት ቀርፆ በማስተዋል በሃይማኖት እና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ጸንቶ የኖረ የሕይወትን ቃል ሰምቶ የክብር፣የድልና የጽድቅ አክሊልን ተሸልሞ በዘላለማዊ ደስታ ይኖራል። ተስፋዎች የምናደርጋትን መንግስቱንና የምንጓጓላትን ርስቱን ለመውረስ መደንገጥ መንቀጥቀጥ ሳይሆን ንስሐ ገብተን ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን ተቀብለን ተዘጋጅተን ልንጠብቅ ይገባል።