አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ @amumcgg Channel on Telegram

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

@amumcgg


➣ ይህ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።

📞 ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ
+251941628237

አብርሂ አብርሂ
ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ (Amharic)

ይህ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ይህ ግቢ ጉባኤ የሚሆኑትን በተመለከተ መረጃዎች ድጋፍ የሚሰጡትን ስልኩችን ከታላቅ ሳይቲያን ጋር እንዲገኙ አገልግሎት ተፈጥሯል። የግቢ ጉባኤ ሶስት ዓመታት የሚሆኑትን መረጃዎች ለማግኘት ወደ +251941628237 ላሉ። እናመሰግናለን። ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም የሆነውን ድጋፍ በመጠቀም ተመልከቱ።

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Feb, 10:47


📍ቆይ ቆይ...አለማንበብ ክልክል ነው⚠️

♻️ዘወትር ማግሰኞ የሚቀርብላችሁን ጥያቄ በአዲስ አቀራረብ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

⛔️ኬዞችን ሪፖርት ለማድረግ የሚከተለውን Link ተጠቀሙ👇
https://t.me/Liyu_Filagot_07_bot?start=w33147938

💠ቋንቋዎችና ልዩ ፍላጎት ክፍል/ልዩ ፍላጎት ንዑስ ክፍል
© አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Feb, 05:38


◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
          ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ  ፪
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈


፩፤ እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።

፪፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።

፫፤ በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።

፬፤ ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።

፭፤ እኔም፡— ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ፡ አልሁ።

፮፤ ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር።

፯፤ ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።

፰፤ ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።

፱፤ ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።

፲፤ እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

፲፩፤ እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።

💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ  ፫
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧

፩፤ የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ:-

፪፤ ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት፡ አለው።

፫፤ ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች።

፬፤ ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፡— በአርባ ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች፡ አለ።

፭፤ የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።

፮፤ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።

፯፤ አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ፦ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤

፰፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

፱፤ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

፲፤ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።

ምዕራፍ ፬ ይቀጥላል ...

የነነዌን ሰዎች ፆም እና ጸሎት የተቀበል አምላክ የእኛንም ፆም እና ልመናችንን በቸርነትህ ይቀበል...አሜን !!


መልካም ፆም ፡ መልካም የንስሐ ዘመን
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
📡@amumcgg፡    ይከታተሉን🤝
📥
@AmumcggBot፡    ሐሳቦን ያጋሩን
📸
@abrhigallery፡   የፎቶ ማህደራችን

© አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Feb, 04:57


◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
         ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ  ፩

፩   የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ ።

፪   ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።

፫   ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኰበልል ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።

፬   እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።

፭   መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።

፮   የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ አለው።

፯   እርስ በእርሳቸውም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

፰   የዚያን ጊዜም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን፤ ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት።

፱   እርሱም። እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ በሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን እመልካለሁ አላቸው።

፲   እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው አውቀዋልና እጅግ ፈርተው። ይህ ያደረግኸው ምንድር ነው? አሉት።

፲፩   ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና። ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት።

፲፪   እርሱም። ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው።

፲፫   ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉም።

፲፬   ስለዚህም ወደ እግዚአብሔር ጮኸው። አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልና እንለምንሃለን፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን አሉ።

፲፭   ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።

፲፮   ሰዎችም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፥ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕትን አቀረቡ፥ ስእለትንም ተሳሉ።
            ምዕራፍ ፪ ይቀጥላል ........

የነነዌን ሰዎች ፆም እና ጸሎት የተቀበል አምላክ የእኛንም ፆም እና ልመናችንን በቸርነትህ ተቀበል...አሜን !!

መልካም ፆም ፡ መልካም የንስሐ ዘመን

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Feb, 14:30


የነነዌ ፆም ከነገ ሰኞ /03-06-2017 ዓ.ም/ እስከ ረቡዕ /05-06-2017 ዓ.ም/ ድረስ ለ3 ቀናት በተከታታይ የሚቀጥል ይሆናል።
  
ሁላችንም ከሰኞ ጀምሮ የምናነባቸው የመፅሐፍ ምዕራፎች

   ሰኞ = ት.ዮና ምዕራፍ 1
   ማግሰኞ = ት.ዮና ምዕራፍ 2 እና 3
    ረቡዕ = ት.ዮና ምዕራፍ 4
           
በሦስት ቀን ከፋፍለው እየፆሙ ትንቢተ ዮናስን በማንበብ የፆሙን ሙሉ ታሪክ ማወቅ ይችላሉ።

መልካም ፆም ፡ መልካም የንስሐ ዘመን

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Feb, 06:20


ሴተኛ አዳሪ ስለሆንኩ ጧፉን ልነካ አልችልም❗️


ምን ቢመሻሽም ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትን ተሳልሜ ልምጣ ብዬ ወደ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ፣ ወርሃዊ በዓላቸው እንደመሆኑ መጠን መግቢያው በር ላይ ግርግር አለ፣ አንዲት ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጧፍ የምትሸጥ ነጋዴ ጋር አንዲት ነጠላ የተከናነበች ወጣት ጧፍ ለመግዛት ቆማለች፣ እኔም አጠገባቸው ነኝ "ወንድም ይቅርታ አለችኝ" ወጣቷ "አቤት" አልኳት እኔ ስለማልገባ ነው ይህንን ጧፍ ስጥልኝ" አለችኝ እኔም ተሳልሜ ነው የምመለሰው ለሚገባ ሰው ስጪው" አልኳት እሺ ለሚገባ ሰው አንተ ስጥልኝ አለችኝ፣ እኛ ስንነጋገር ተሽከርካሪ ወንበሩ ላይ ያለችው ጧፍ ነጋዴ ጧፉን እንደያዘች እጇን ዘርግታለች፣ እሺ ችግር የለውም እሰጥልሻለሁ ግን ለምን አንቺ አትሰጪም አልኳት፣ እኔ ሴተኛ አዳሪ ነኝ እንዴት በእጄ እነካዋለሁ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ሲቀደስ የሚበራ አይደለም አረክሰዋለሁ ብዬ ነው አለችኝ ደነገጥኩ
አንዳቺ የሆነ ፍርሃት ሰውነቴን ወረረኝ ከዚህ በኋላ መልስ አልሰጠዋትም። እሺ ብቻ ብዬ ጧፉን ከጧፍ ነጋዴዋ ተቀበልኩላት፣ ብሩን ስትከፈላት እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብላ ስትመርቀኝ አስታውሳለሁ፣ አንገቴን አቀረቀርኩኝ
እኔ ግን ንጹሕ ሁኜ ነው ይህንን ጧፍ የያዝኩት እንዴት ያለሁ ደፋር ነኝ ፣ ለምን እኔም ካንቺ የባስኩኝ ኃጢያተኛ ነኝ እኔም አልነካውም አላልኳትም ስል ራሴን ሞገትኩት፣
አንተ ውሸታም ጧፍ አይደለም ከታቦቱ ጋር ስትጋፋ አላውቅህም ሲል ጭንቅላቴ ወቀሰኝ፣ እኔ ዞርም ብዬ አላየዋትም
ምናልባት እሷ ግን እየተመለከተችኝ ከሆነ ብዬ ወትሮ አደርጌው የማላውቀውን ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ስገባ ተንበርክኬ መሬቱን ሳምኩኝ ፣ አረማመዴንም አስተካከልኩኝ ፣ ምናልባት ንጽሕናዬን ካረጋገጠልኝ ብዬ ወይ አምላኬ በስንቱ ታስተምረኛለህ አቤት ይህን ግን ዮሐንስ ሐጺር በኖረ ስል ተመኘሁ፣
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው የሚባለው ትርጉሙ ለካስ ይህ ነው ወንጌል ላይ ያለው ቀራጭ ትዝ አለኝ ጌታ ያመሰገነው፣ ከዛ ቀራጭ ግን ይህቺ ሴት ትበልጣለች ፣ እርሱስ ወደ ምኩራብ ገብቶ ነው፣ ይህች ሴት ግን ደጄ ሰላሙ ጋር እንኳን አልቀረበችም ፣

እንዲህ ያለ ትሕትና እንደምን ያለትሕትና ነው እንደዚህስ ያለ እግዚአብሔርን መፍራት እንደምን ያለ ፍርሃት ነው

አቤቱ የሰራዊት ጌታ ቅዱስ እግዚአብሔር የማደሪያውን መቅደስ እንፈራው እንቀጠቀጥለት  ዘንድ  ማስተዋልን ስጠን❗️❗️

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Feb, 19:09


📣እነሆ በአዲስ አቀራረብ ተመልሰናል🤗

🔰ዘወትር ማግሰኞ የሚቀርብላችሁን ጥያቄ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

➩ኬዝ ሪፖርት ለማድረግ
https://t.me/Liyu_Filagot_07_bot?start=w33147938

💠ቋንቋዎችና ልዩ ፍላጎት ክፍል/ልዩ ፍላጎት ንዑስ ክፍል
© አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Feb, 11:02


#27 መድኃኔዓለም

ዝክረ - መድኃኔዓለም

        ጥር 27-2017 ዓ.ም

     ምሽት 12:00 ሰዓት
      📍ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

1. የእርጋታ መምህር ነው።

ከእርጋታው የተነሣ "የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስን የጧፍ ክርም አያጠፋም" ተብሏል (ማቴ.12፥20)።

2. የትሕትና መምህር ነው

"ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።" (ማቴ.11፥29)

3. የይቅርታ መምህር ነው።

በመስቀል ተሰቅሎ ይቅርታን ለሰው ልጅ ያደለ እርሱ ነው።
"ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።" እንዲል (ሉቃ.23፥34)።

4. የሰላም፣ የፍቅር፣ የትዕግሥት፣ የሰማዕትነት በጠቅላላው የመልካም ሥራዎች ሁሉ መምህር እርሱ ነው።

እርሱን ሁልጊዜ ማሰብ ለነፍስ ዕረፍት ነው። እኛም ዋና አብነታችን እርሱ ስለሆነ መልካም ሥራዎችን ሁሉ አባታችንን እርሱን መስለን እንሥራ።

እንኳን አደረሳችሁ !!

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Feb, 08:00


@abrhigallarybot

በ2017 ዓ.ም የልደት በዓል ላይ ፎቶ የተነሳችሁ የ ግቢ ጉባኤ አባላት ወንድሞች እና እህቶች በዚህ Telegram bot @abrhigallarybot  እየገባችሁ ፎቶ የተነሳችሁበትን የትኬት ቁጥራችሁን ቦቱ ላይ በማሰገባት  ፎቶአችሁን  መውሰድ(ማውረድ) ትችላላችሁ።እስከ አሁን ድረስ ስለዘገየን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ቀሪ ብር ያለብን እያስታወስን
በ1000409676166 (ታየወርቅ ጣሰው)እናስገባ።

ፎቶ-ቤዛ!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Feb, 19:42


በአንድ ወቅት የግብፅ ፓትሪያሪክ የነበሩት ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ለተማሪዎች ከፈተና በፊት እንዲጸልዩት የደረሱት ጸሎት


+++ ጸሎት +++

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ነገ ፈተና ለምትጀምሩ 17 ባች ተማሪዎች እና በፈተና ላይ ላላችሁ 15 ባች ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!


መልካም ፈተና

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Feb, 06:10


ልዩ -የተመራቂ ተማሪዎች የዝክር መርሐ ግብር

<<ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል >> ማቴ 10፥41

    ጥር 25-2017 ዓ.ም   
      
       ምሽት 11:40
      📍ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
📖 ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
      የፍቅርን ህይወት እንድትለብሱ
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

01 Feb, 13:47


✞          🔔 ጉባኤ ኒቆዲሞስ  🔔                  ✞

“ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።”
      ▬ ምሳሌ 8፥10 ▬

የዛሬ መረሐግብራት :-
              ➽ዝማሬ
              ➽ ስብከት
             ➽ ስነ-ፅሁፍ እና ሌሎች
     
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ
         መዝሙር 40፥9


📆 ጥር-24
ምሽት 12:00
⛪️ በደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ 
🙋‍♀️ወንድም እህቶችን እንጋብዝ!


⚠️ ማሳሰቢያ፤ ለዚህ ታላቅ ጉባኤ ወንድም እህቶቻችንን አለመጋበዝ በእውነቱ ንፉግነት ነው !!
▱▰▱▰▱▰✞▱▰▱▰▱▰▱

#share🤝 #join  t.me/amumcgg

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Jan, 08:57


🌕 "ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፡ 🌷
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና።"

👑◈ እንኳን ለክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሰን ። ◈👑

መልካም በዓል 🙏

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

28 Jan, 18:29


ጥምቀትን በዱርቤ

የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን ዱርቤ ወረዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
በዚህ መልኩ አክብረን ነበር።

🎈ቦታው ከ20 ያልበለጡ ክርስቲያኖች ያሉበት በዝማሬ እንኳን የሚያጅበው ሰው የሌለው አሳዛኝ ስፍራ ነውና...

ለቀጣይ እርሶም ለመሔድ እያሰቡበት እንላለን።🙏


ለተጨማሪ ፎቶዎች👇👇👇

@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Jan, 12:02


ዛሬ የሚዘመሩ መዝሙራት ከላይ በ 📔 pdf ተያይዘዋል።

መልካም በዓል ይሁንልን!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Jan, 08:24


#ጥምቀት #ከተራ #ዝማሬ

ውድ የ ግቢ ጉባኤያችን ልጆች እንኳን አደረሳችሁ።  ዛሬ በ ጥምቀት ዋዜማ ታቦተ-ሕጉ ከደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን (ግቢ ጉባኤ ) ወጥቶ ወደ ጥምቀተ ባህር ስለሚሄድ እኛም በ አንድ ላይ ሆነን በሰልፍ በዝማሬ አጅበን እንጓዛለን።

👉 ቀድመን መዘጋጀት ስላለብን ሁላችንም ከ 7፡30 ጀምሮ ግቢ ጉባኤ እንሰባሰብ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Jan, 19:22


ለዱርቤ ተጓዦች ማስታወሻ

• ማታ ስለሚበርድ የሚሞቅ ልብስ መያዝና የሚመች ጫማ ማድረግ፤

• ክርስቲያናዊ አለባበስ (ነጠላ፣ ሥርዓት ያላቸው ልብሶች..)፤

• 2 ቀን ስለሚታደር ሳይበዛ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማዘጋጀት፤

• ቤተክርስቲያኑ እንደምታዩት ችግር ላይ ስለሆነ የአቅማችንን ያህል መባዕ(እጅ መንሻ) መያዝ፤

• የጸሎት መጽሐፍም እንዳይረሳ።

ሰዓት! ሰዓት! ሰዓት! ቀን 6፡00 ሰዓት መኪና የሚነሣበት ነው!

       ምዝገባ አልቋል!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Jan, 11:07


....ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
....በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ

እንኳን አደረሳችሁ !!
ልዩ የጥምቀት ጉዞ ወደ ዱርቤ ቅዱስ ሚካኤል

ኑ! ሰው ወደ ተራበው ዱርቤ ቅዱስ ሚካኤል በመጓዝ በጉጉትና በስስት የሚጠብቁን ወገኖቻችንን አለሁ እንበላቸው...

ከብዙ ክርስቲያኖች ጋር ሆኖ እግዚአብሔርን ማክበር ትልቅነት ሲሆን ከጥቂት ክርስቲያኖች ጋር ሆኖ እግዚአብሔርን ማክበር ደግሞ በጣም ትልቅነት እና መታደል ነው።

መነሻ -ጥር 10 ከቀኑ 06:00 ሰዓት
መመለሻ - ጥር 12 ከቅዱስ ሚካኤል ንግስ በኋላ

ጉዞው 40 ሰዎችን ብቻ የሚያሳትፍ ሲሆን፤ አሁን ላይ 21 ሰዎች ተመዝግበዋል። ስለዚህ የእርስዎን በጣም ማርፈድ ያስቡበት !!
    አሁኑኑ ለመመዝገብ      
0938540103

መስተንግዶን ጨምሮ - 400 ብር ብቻ


<< እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ >> ትን ዳን 10፥13

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Jan, 20:28


የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የረቡዕ የመዝሙር ጥናት ይሄንን ይመስል ነበር። ነገም ምሽት 12 ሰዓት በመቀሳቀስ ተገናኝተን እንድናጠና ይሁን ሰናይ ምሽት።

ለተጨማሪ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች👇👇

@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

13 Jan, 22:47


ልዩ-የጥምቀት ጉዞ

ሰው ወደተራበው ወደ ዱርቤ ቅዱስ ሚካኤል

ይህ ቤተክርስቲያን በአካባቢው ከ30 የማይበልጡ ክርስቲያኖች ያሉበት ስለሆነ አብረናቸው በዓሉን እንድናከብር እነሆ ብለናችኋል።

በዚህ መሠረት ከጥር 10-12 ወደ ቦታው ተጉዘን በዓሉን እናከብራለን...

ስለ ጉዞው እና ስለቤተክርስቲያኑ ሙሉ መረጃ ለማግኘት በዚሁ በግቢ ጉባኤያችን ቻናል በቅርብ ይጠብቁን።

ጥምቀትን በዱርቤ አከብራለሁ...


http://t.me/amumcgg

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

12 Jan, 16:51


#ፈተና

<< ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፤ ዐሳብህም ትጸናለች። >> (ምሳ. 16፥3)
ነገ የሴሚስተር የመጨረሻ ፈተና ( Semester Final Exam) የምትጀምሩ(13,14,16)ባች ተማሪዎች በሙሉ

💒 እናት ግቢ ጉባኤያችን ሰናይ ፈተና ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቷን ትገልጻለች🙏


📖 የአባቶቻችን የአብርሃም ፥ የይስሐቅ ፥ የያዕቆብ አምላክ ማስተዋሉን ፥ ጥበቡን ፥ አእምሮውን ያድለን

📌እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል በረድኤታቸው ከኛ ጋር ይቁሙልን🙏


🔔🔔🔔መርሳት የሌለብን ዐቢይ ጉዳይ🔔🔔🔔

📜 መጸለይ ፧ ፧ ማማተብ【 ለንባብም ፥ ለፈተናም ፤ ስንጀምርም ፥ ስንጨርስም   】እንዲሁም ስንጨርስ ማመስገን🤲


መልካም ፈተና፤ ቅድስት ኪዳነምሕረት ትርዳችሁ



📜እናት ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Jan, 14:20


ተዘጋጅታችኃል? : የጥያቄዎቻችሁ መልስ

ዛሬ ምሽት በ ጉባኤ ኒቆዲሞስ :-

1. በዚህ ዘመን ንስሐ መግባት ለወጣቶች ለምን ከባድ ሆነ?

2. እንዴት የተቃራኒን ፆታ ፈተና ተቋቁሞ ለክብር መብቃት ይችላል?

3. ከማይመስሉን ሰወች ጋር ህብረትን  መፍጠር በክርስትና ህይወታችን ምን ችግር ያመጣል?

👉 በተጨማሪም ስለ ጥምቀት [ በ 40 እና 80 ቀን መጠመቅ ]ትውፊትክርስቲያናዊ አለባበስ እና ሌሎችም በመምህራን በሰፊው መልስ ይሰጥባቸዋል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!

⚠️ 12:00 ሰዓት ላይ ግቢ ጉባኤ እንገናኝ።

© አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 13:26


⚠️ይነበብ❗️

👉 https://t.me/Liyu_Filagot_07_bot?start=w33147938

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Jan, 20:04


የ2017 ዓ.ም የልደት በዓል ከፎቶ ማህደር በጥቂቱ

ለተጨማሪ ፎቶዎች 👇👇

t.me/abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Jan, 03:52


“ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም  መልሶ ይከፍለዋል።”
— ምሳሌ 19፥17


🎁💖እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓልን ከእናቶች ጋር በጋራ እንድናሳልፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በዕለቱም :-

የማይጠገበውን የእናቶች ጨዋታ እና ምርቃት በዓል በዓል ከሚሸቱ መንፈሳዊ መርሃግብሮች ጋር አጋፔን ጨምሮ አዘጋጅተን🏠 በእናታችን (ውሃ ምንጠጣበት) ቤት እንጠብቃችኋለን።

🕓 8 : 00 ሰዓት
📍ቦታ : መጨረሻ ላይ ውሃ የምንጠጣበት ቤት

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!


ለበለጠ መረጃ 0996909809/0924111488

#story #share

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

07 Jan, 15:20


➣ የ ቀድሞ የግቢ ጉባኤያችን አባላት( ምሩቃን ) በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችሁን በ @Maincampus_gibigubae አድርሱን እናደርሳለን።

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

07 Jan, 04:52


ለዋዜማ ዝግጅት ከአገልግሎት ጅማሬ እስከ ፍጻሜ በሀሳብም፣ በተግባርም፣ በመታደምም ያልተለያችሁ ሁላችሁም እህት ወንድሞች እግዚአብሔር ክብረትን ያድልልን።

መልካም የገና በዓል

#2 ልማት ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Jan, 15:53


ዝማሬው ተጀምሯል !👏

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Jan, 08:56


ሃሌ ሉያ "ዮም ፍስሃ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ " ሎቱ ሰገዱ ሰብአ ሰገል አመፅኡ ዕጣን ከመ አምላክ ውዕቱ፤ወርቀ እስመ ንጉስ ውዕቱ፤ ወከርቤ ዘይተወሀበ ለሞቱ..ለመፍቀሬ ሰብእ


የበዓል ዋዜማ መርሐ ግብራት

1/ ምሽት ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12:00 ሰዓት
   የግቢ በር (የተማሪዎች) ጋር
  ➾ ውዳሴ ማርያም ጸሎት
  ➾ ምስባክ
  ➾ የጋራ ዝማሬዎች

2/  ከ12:00 ሰዓት እስከ 2:00 ሰዓት
    ➾ የእግር ጉዞ በዝማሬ ወደ ሁለቱ አድባራት
      ወደ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን
      ወደ ደብረ ሳህል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

አደራ ለሰልፍ አስተባባሪዎችም ሆነ ለመንገድ ደህነት ሰዎች ቅን እና ታዛዦች እንሁን!!

3/ ሁላችንም ቤተ ክርስቲያን ከደረስን በኋላ ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀው የበዓሉ የማህሌት መርሐ ግብር በቤተክርስቲያን ይካሄዳል። ብዙ ጊዜ የማናገኘው ውድ መርሐ ግብር ስለሆነ የበረታን ሰዎች ከማህሌቱ መርሐግብር ተሳታፊዎች እንሁን!!

4/ ማህሌቱ እንዳለቀ ደግሞ እንደተለመደው የቤተክርስቲያናችን ታላቁ ጸሎት "ጸሎተ ቅዳሴ" የሚቀጥል ይሆናል። ሁላችንም በንቃት ተግተን ሙሉ ቅዳሴውን እንድናስቀድስ ይሁን!!

5/ የቅዳሴው መርሐ ግብር ካለቀ በኋላ  ሁላችንም በህብረት ሳንቀዳደም፣አስተባባሪዎችን ሳናስቸግር ወደ ግቢያችን ተመልሰን በተሰጠን የካፌ ቁጥር መሰረት ካፌ በመግባት የተዘጋጀልንን የማስፈሰኪያ ምግብ በፍቅር እንድንመገብ ይሁን!!

እግዚአብሔር በዓሉን የደስታ፣የፍቅር፣የመተሳሰብ እና የይቅርታ በዓል ያድርግልን።

የዋና በዓሉን መርሐ ግብር ደግሞ በቀጥታ የምናሳውቃችሁ ይሆናል!!

መልካም ዋይዜማ ፤ መልካም የገና በዓል


© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

31 Dec, 07:12


⚠️ቆይ ቆይ እስቲ 'ረጋ' ብላችሁ ከልብ አስቡት...

🧩 አምላክ ለምን ሰው ሆነ ⁉️🤔

🎉 እነሆ ማግሰኞ ደረሰ🤗

🔰ዘወትር ማግሰኞ የሚቀርብላችሁን ጥያቄ ይዘንላችሁ ቀርበናል።


💠ቋንቋዎችና ልዩ ፍላጎት ክፍል/ልዩ ፍላጎት ንዑስ ክፍል
© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

30 Dec, 04:10


#ፈተና
<< ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፤ ዐሳብህም ትጸናለች። >> (ምሳ. 16፥3)

🔰 ዛሬ ፈተና ( 1st Semester Mid Exam) የምትጀምሩ 17 ባች ተማሪዎች በሙሉ

እናት ግቢ ጉባኤያችን መልካም ፈተና ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቷን ትገልጻለች🙏

⚠️ መርሳት የሌለብን ዐቢይ ጉዳይ

📜 ማማተብመጸለይ ለንባብም ፥ ለፈተናም ፣ስንጀምርም ፣ ስንጨርስም እንዲሁም ስንጨርስ ማመስገን።

መልካም ፈተና፤ ቅድስት ኪዳነምሕረት ትርዳችሁ!


© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

27 Dec, 09:00


ዐይኖቻችን ሁሉ ወደ ዶንቤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ናቸው

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

27 Dec, 05:19


ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ዶንቤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

መነሻ - ዛሬ ምሽት  
         12:00 ሰዓት

መመለሻ- ቅዳሜ 19/04/2017 ዓ.ም
                /ከንግስ በኋላ /

#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ

    📞 +251938540103
    📞 +251910268279

🚌 ትራንስፖርት መስተንግዶን ጨምሮ - 250 ብር ብቻ

‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

                 @guzoo_bot
                 @AmumcggBot

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

27 Dec, 04:30


⚠️ይነበብ❗️

👉 https://t.me/Liyu_Filagot_07_bot?start=w33147938

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

25 Dec, 05:19


ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ዶንቤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

መነሻ-አርብ 18/04/2017 ዓ.ም 
         12:00 ሰዓት

መመለሻ- ቅዳሜ 19/04/2017 ዓ.ም
                /ከንግስ በኋላ /

#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ

    📞 +251938540103
    📞 +251910268279

🚌 ትራንስፖርት መስተንግዶን ጨምሮ - 250 ብር ብቻ

‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

                 @guzoo_bot
                 @AmumcggBot

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

23 Dec, 10:14


#ተልባ_ለቀማ

📌 እነሆ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ሌሊት አክብረን ስንመለስ የምንጠቀመውን ተልባ ለበረከት ይሆነን ዘንድ ኑ በአንድነት እንልቀም!

ናፕ ሰዓት ከ 06:30 ጀምሮ እንዲሁም በማንኛውም ሰዓት ፈቃደኛ ለሆኑ ክፍሎችና ቤተሰቦች ክፍት ነው።

☎️ 0910268279/ 0938540103

     አብርሂ አብርሂ ግቢ ጉባኤ

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

23 Dec, 07:41


ከዐቢይ ጉባኤ - ማስታወሻችን

" ስለ ነፍሱ የማያስብ ሰው እርሱ እንስሳ ነው"
ከአርብ ትምህርት የተወሰደ

"እግዚአብሔር በመከራም በደስታም ያስተምራል"
ከአርብ ትምህርት የተወሰደ

"የልቡናችንን በር ማንኳኳት የእግዚአብሔር ድርሻ ሲሆን ዝግጁ ሆኖ በሩን መክፈት ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው"
ከቅዳሜ ትምህርት የተወሰደ

" እኛ የምናውቀው ነገሩ እንደሆነው ሳይሆን እኛ በተረዳነው ልክ ነው "
ከቅዳሜ ትምህርት የተወሰደ

" እግዚአብሔርን ደስታው ያደረገ ሰው መቼም ቢሆን ደስታው አይጠፋም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይኖርበት ጊዜ የለምና።"
ከቅዳሜው ግለ ተውኔት የተወሰደ

"ወጣት ማለት በጠንካራ ስጋ፣ በጅም የፈረጠመ ጡንቻ ውስጥ በኀጢአት የጠቆረች ነፍስ ፣ እጅግ የደከመች መንፈስ ያለው ማለት አይደለም።"

" ዘመናዊነት ማለት በዘመን ከማያረጀው ከእግዚአብሔር ጋር መኖር እንጅ ዘመን ያመጣቸውን መጤ ስርዓቶች ተቀብሎ ማበድ አይደለም"
  ከእሁድ ትምህርት የተወሰደ

" ማረኝ ማረኝ ማረኝ መመኪያዬ
  አርጅቻለሁ እኔ በኀጢአት ጎስቁዬ"

   ከእሁድ መዝሙር የተወሰደ

" ጥፋትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት ሲሆን ፤ ይቅርታን ተቀብሎ ምህረት ማድረግ ደግሞ እጅግ በጣም ትልቅነት ነው"
ከእሁድ ጭውውት የተወሰደ

ለቀጣይ ዐቢይ ጉባኤ እግዚአብሔር በሰላም ያድርሰን!!

አብርሂ አብርሂ
ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

23 Dec, 07:39


ዐቢይ ጉባኤ

🔰 ሦስተኛ ቀን



ለተጨማሪ ፎቶዎች👇👇
@abrhigallery
@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

22 Dec, 13:18


እኛስ ወጣቶች ስለሆንን በክብር ከተጠራንበት የመጨረሻ ቀን ጉባኤ ለመሳተፍ እንሄዳለን ።

እርስዎስ
?

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

22 Dec, 09:38


--------የአብይ ጉባኤ የመጨረሻ ቀን-----

"ኦርቶዶክሳዊ ወጣት"

➨ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እንዴት ያለ ነው?
➨ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እና የጊዜ አጠቃቀም
➨ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እና ዘመናዊነት


በዛሬው መርሐግብር እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ለወጣት ልጆቿ እናታዊ ምክሯን እና አስተምህሮዋን ትነግረናለች


ከእርስዎ የሚጠበቀው "የወጣትነትን ትምህርት ለወጣቶች" ነውና  ከጓደኝዎ ጋር በመሆን በሰዓቱ በቦታው መገኘት ብቻ

ምሽት 𝟭𝟭:𝟯𝟬

📍ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነምህረት [ ግቢ ጉባኤ ]

Profile and story challenge

   📌ይሄን ሎጎ profile ያድርጉት 


#share #share

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

21 Dec, 21:47


ዐቢይ ጉባኤ

🔰 ሁለተኛ ቀን

፤ ነገም ይቀጥላል...


ለተጨማሪ ፎቶዎች👇👇
@abrhigallery
@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 05:29


⭐️እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ የእረፍት በዓል በደህና አደረሰን።⭐️

🎤🎤🎤 ዝማሬ ...

🔸መልካም በዓል🔸

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 05:29


መጋቢውም የዚያችን በረሀ ስም በሰማ ጊዜ አደነቀ እንዲህም አለው ልብህ ጠፍቷል በማለቴ መልካም የተናገርኩህ አይደለምን የምትናገረውን አታውቅምና የዚያ በረሀ መጠኑ የሃያ ሁለት ቀን ጉዞ የሚያስጉዝ ስለ ሆነ በእርግጥ አንተ ወንበዴ ነህ የቅዱስ ሰማዕት መርቆሬዎስ ኃይል ያለ ገመድ አሥሮሃል፣ እርሱ የዚህን ዓለም ክብር ንቆ የተወ፣ ክብር ይግባውና ስለ #ክርስቶስ ስም ከሀዲዎች ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተው የገደሉት፣ #ክርስቶስም በመንግሥቱ ውስጥ የተቀበለው፣ በቦታዎችም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁለት በውስጣቸውም #እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። እርሱ መርቆሬዎስ ለተማፀነበት ሁሉ ይማልዳልና ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራትንም ያደርጋልና።

ያም ወጣት መጋቢውን መልኩ እንዴት ነው ምን ይመስላል አለው መጋቢውም አካሉ አንተን ይመስላል አለው ይህንንም ብሎ ወደ ሥዕሉ ወስዶ ገልጦ አሳየው ወጣቱም በእገሌ በረሀ የታየኝ በእውነት ይህ ነው። በፈረሱም ላይ አፈናጥጦ ወደዚህ ያደረሰኝ ይህ ነው። እነሆ ታጥቋት በወገቡ ላይ ያየኋት የወርቅ መታጠቂያው ይቺ ናት። ስማኝ ልንገርህ እኔ በዚች አገር የምኖር አባቴም ስሙ ረጋ የሚባል መስፍን የሆነ እስላም የሆንኩ ሰው ነኝ። ክርስቲያንም ለመሆን ይች ምልክት ትበቃኛለች አሁንም በቦታ ውስጥ ሠውረኝ ለማንም ሥራዬን አትግለጥ። የክርስትና ትምህርትን አስተምሮ የ #እግዚአብሔርን መንገድ የሚመራኝን አምጣልኝ አለው። እርሱም ያለውን ሁሉ አደረገለት የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው።

ከዚህም በኋላ ወደ ነቢያቸው መቃብር የሔዱ እሊያ እስላሞች በአንድ ወራቸው ደረሱ። ዘመዶቻቸውም ሊቀበሏቸው ወጡ። ይህን ወጣት የመስፍን ልጅ ግን አላገኙትም። አባቱም አደራ ያስጠበቀውን ወዳጁን በጠየቀው ጊዜ እርሱም በበረሀ ውስጥ ቀርቶ እንደ ጠፋ እያለቀሰ ነገረው አባቱም በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ አለቀሰ እንዲሁም ቤተሰቦቹ ሁሉም አርባ ቀኖች ያህል አለቀሱለት።

ከዚህም በኋላ በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ሲወጣ ይህን ክርስቲያን የሆነውን ወጣት አንድ እስላም አየው። ወደ ወላጆቹም ሒዶ እንዲህ ብሎ ነገራቸው ልጃችሁ በበረሀ ውስጥ የሞተ ከሆነ በመርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ያየሁት እርሱን ባልመሰለኝ ነበር፤ እስቲ ሒዳችሁ አረጋግጡ። በሰሙም ጊዜ በስውር ሒደው ፈለጉት አግኝተውትም ይዘው ወሰዱት። እንዲህም አሉት በወገኖቻችን መካከል ልታሳፍረን ይህ የሠራኸው ምንድን ነው አሉት። እርሱም እኔ በሕያው #እግዚአብሔር ልጅ በ #ጌታዬና_በፈጣሪዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ ብሎ መለሰላቸው።

ይህንንም ሲል ታላቅ ሥቃይን አሠቃይተው ከጨለመ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ሽንታቸውን በላዩ እየደፉ የቤት ጥራጊም እያፈሰሱበት ያለ መብልና ያለ መጠጥ በዚያ ሰባት ቀንና ሌሊት ኖረ። እናቱ ግን ቀንም ሌሊትም በላዩ የምታለቅስ ሆነች ከልቅሶዋም ብዛት የተነሣ ከጉድጓድ አውጥተው እኛ ወደማናይህ ቦታ ሒድ አሉት። ወዲያውኑ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በዚያ እያገለገለና እየተጋደለ ሁለት ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ በላዩ የትንቢት ጸጋ ያደረበት አንድ መነኰስ ወደ ምስር ከተማ ሒደህ ሃይማኖትህን ከምትገልጽ በቀር በዚህ መኖር ለአንተ አይጠቅምህም አለው። ወዲያውኑ ተነሥቶ ወደ ምስር ከተማ ሔደ።

አባቱም በአየው ጊዜ ሐኪም ወደ ሚባል ንጉሥ ወስዶ ይህ ልጃችን ነበር የእስልምና ሃይማኖትን ትቶ ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት ገብቷል አለው። ንጉሡም ስለአንተ የሚናገሩት ዕውነት ነውን አለው። እርሱም በበረሀ ውስጥ ሳለ በሌሊት ቅዱስ መርቆሬዎስ እንደ ተገለጸለትና ከእርሱ ጋር በፈረስ እንዳስቀመጠው፣ በምስር አገር ወዳለች ቤተ ክርስቲያኑ የሃያ ሁለት ቀን መንገድ እንደ ዐይን ጥቅሻ አድርሶ ከውስጥዋ እንዳስገባው፣ ሥዕሉንም አይቶ ያመጣው እርሱ መሆኑን እንደ ተረዳ ለንጉሡ ነገረው።

ንጉሡም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ። ታላቅ ፍርሀትም አደረበት አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ አለው። እርሱም በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ዳግመኛም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን እንድሠራ ታዝልኝ ዘንድ እሻለሁ አለው።

ንጉሡም በአስቸኳይ እንዲታነፁለት አዘዘለት። በውስጣቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። እርሱም አበ ምኔት ሁኖ ወደርሱ ብዙዎች መነኰሳት ተሰበሰቡ። ሁለት ድርሳናትንም ደረሰ። ከሀዲያንንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለዚህም መነኰስ የክርስትና ጥምቀትን በተቀበለ ጊዜ ያወጡለት ስም ዮሐንስ ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_25)

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 05:28


ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስተያናት ታነፁለት። #እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፩

ከተአምራቱም አንዲቱ ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ካደ። በዚያንም ወራት ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ነበረ ተአምራቱ በተጻፉበት መጽሐፍ እንደተጻፈ ምእመናን በጽኑዕ ሥቃይ ዑልያኖስ ባሠቃየ ጊዜ መክሮ አስተምሮ ከስሕተቱ ይመልሰው ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስ ወደርሱ መጣ።

ዑልያኖስም ቅዱስ ባስልዮስን በአየው ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችንን ሰደበ። ቅዱስ ባስልዮስንም አሠረው። በዚያ በእሥር ቤትም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕል አይቶ በፊቱ ቅዱስ ባስልዮስ ጸለየ ሥዕሉም ከቦታው ታጣ። ያን ጊዜ ወደ ዑልያኖስ ሒዷልና በጦርም ወግቶ ገደለውና ወዲያውኑ ወደቦታው ተመለሰ ከጦሩም አንደበት ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን እንደገደለው አውቆ እንዲህ ብሎ ተናገረ የ #ክርስቶስ ምስክር ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ራሱን ዘንበል አደረገ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት #እግዚአብሔርን አመሰገነ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፪

የዚህም የቅዱስ መርቆሬዎስ ሌላው ተአምር ከምስር አገር ከመሳፍንት ወገን የሆነ አንድ የእስላም ወጣት ነበረ የእስላሞችንም ሕጋቸውንና መጻሕፍቶቻቸውን ተምሮአል። በአንዲትም ዕለት ወደ ባሕር ዳርቻ በመንገድ አልፎ ሲሔድ አንድ የተፈረደበትን ሰው አገኘ። አስቀድሞ እስላም የነበረ አሁን የክርስትና ጥምቀትን የተጠመቀ የንጉሥ ጭፍሮችም ይዘውታል። ሊአቃጥሉትም ጉድጓድን ምሰው በውስጡ ታላቅ እሳት አንድደው አዘጋጅተውለታል። ብዙዎች ሰዎችም ሲቃጠል ለማየት ተሰብስበው ነበር።

ያም የመስፍን ልጅ ወጣት እስላም ወደ ተፈረደበት ሰው ቀረብ ብሎ "አንተ ከሀዲ ሰው ወደ ሲኦል ለመግባት ለምን ትሮጣለህ በኋላም በገሀነም እሳት ውስጥ ለመኖር አንተ #እግዚአብሔርን ባለ ልጅ ታደርገዋለህና ሦስት አማልክትንም የምታምን ነህና ክፉ ነገር ነውና ይህን ስድብ ትተህ እኔን ስማኝ" አለው ።

ያ የተፈረደበትም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኛ የክርስቲያን ወገኖች ሦስት አማልክትን የምናመልክ ከሀድያን አይደለንም። አንድ አምላክን እናመልካለን እንጂ ይኸውም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ ነው። #ወልድ ከአባቱ ከ #እግዚአብሔር ልዩ አይደለም። የራሱ ቃሉ ነው እንጂ። #መንፈስ_ቅዱስም ሕይወቱ ነው። የሃይማኖታችን ምሥጢር ከአናንተ የተሠወረ ድንቅ ነው። ዛሬ ለአንተ ልብህ ጨለማ ነው በውስጡ የሃይማኖት ብርሃን አልበራም በኋላ ግን ልብህ በርቶልህ እንደ እኔ ስለ #ክርስቶስ ስም በመጋደል መከራውን ትቀበላለህ።"

ያም ወጣት እስላም በሰማው ጊዜ እጅግ ተቆጣ ጫማውንም ከእግሮቹ አውልቆ አፉን ፊቱንና ራሱን ጸፋው። ይህ የምትለው ከእኔ ዘንድ አይደረግም እያለ አብዝቶ አሠቃየው። የተከበረው ሰማዕትም ይህን ያልኩህን አስበህ የምትጸጸትበት ጊዜ አለህ አለው።

በዚያንም ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ሥጋውን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩ ከዚህም በኋላ እሳቱ ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ታላቅ አጥር ሆነ። የንጉሥም ወታደሮች እየጠበቁት ሦስት ቀን ኖረ። ከዚህም በኋላ ከቶ እሳት ምንም ሳይነካው እንደ ተፈተነ ወርቅ ሆኖ ሥጋውን አገኙት። ይህንንም ለንጉሥ ነገሩት። እርሱም እንዲቀብሩት አዘዘ።

ያ ወጣት እስላም ግን እያዘነ ወደ ቤቱ ገባ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን ስለተናገረው ከኀዘኑ ብዛት የተነሣ የማይበላና የማይጠጣ ሆነ። እናቱና ወንድሞቹም ወደርሱ ተሰብስበው የማትበላ የማትጠጣ በአንተ ላይ የደረሰ ምንድን ነው አሉት። ክብር ይግባውና ለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ምስክር የሆነው የተናገረውን ነገራቸው። እነርሱም ይህ አሳች የተናገረውን ተወው በልብህ አታስበው እያሉ አጽናኑት። እርሱ ግን ከቶ ምንም አልተጽናናም።

በዚያም ወራት ወደሐሰተኛ ነቢያቸው መቃብር ለመሔድ የሚሹ ሰዎችን አይቶ ከእሳቸው ጋር መሔድ እፈልጋለሁ ብሎ ለአባቱ ነገረው። አባቱም እጅግ ደስ ብሎት የሚበቃውን ያህል የወርቅ ዲናር ሰጠው ለወዳጁም አደራ ብሎ ሰጠውና አብሮት ሔደ።

በሌሊትም ሲጓዙ እነሆ ብርሃን የለበሰ አረጋዊ መነኰስ ተገለጸለት በፊቱም ቁሞ ትድን ዘንድ ና ተከተለኝ አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ተገልጦ ተናገረው።

በደረሱም ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው ተመለሱ ሰባት ቀንም ያህል ተጓዙ። እነርሱም በሌሊት ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጅ ያ ወጣት ከገመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ። ባልንጀሮቹም በበረሀ ውስጥ ትተውት ሔዱ ከእሳቸው ጋር የሚጓዝ መስሏቸዋልና በተነሣም ጊዜ ተቅበዘበዘ ወዴት እንደሚሔድ አላወቀምና አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ ደነገጠ።

በዘያንም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕት የቅዱሰ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ እንዲህ አለ። ሰዎች ሁሉ በእርሷ ዘንድ እየተሳሉ ይፈጸምላቸዋል። በዚያንም ጊዜ የ #ክርስቶስ ምስክር መርቆሬዎስ ሆይ በዚህ በረሀ ካሉ አራዊት አፍ በዛሬዋ ሌሊት ካዳንከኝና ያለ ጥፋት ካወጣኸኝ እኔ ክርስቲያን እሆናለሁ ብሎ ተሳለ።

ወዲያውኑ መልኩ የሚያምር ጎልማሳ የከበረ ልብስ የለበሰና የወርቅ መታጠቂያ በወገቡ የታጠቀ በፈረስ ተቀምጦ ወደርሱ መጣና አንተ ከወዴት ነህ እንዴት በዚህ በረሀ ውስጥ ጠፋህ አለው። ወጣቱም ስለ ሥጋ ግዳጅ ከገመል ላይ ወረድኩ ባልነጀሮቼ ትተውኝ ሔዱ አለው ባለ ፈረሱም ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ አለው በዚያንም ጊዜ ወደ አየር በረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች ከውስጧ አስገባው። ከፈረሱም ላይ አውርዶ በዚያ አቆመው ወደ መጋረጃ ውስጥም ገብቶ ከእርሱ ተሠወረ።

የቤተ ክርስቲያኑም መጋቤ በሌሊት በመጣ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍቶ ሲገባ ይህን ወጣት ከመካከል ቁሞ አገኘው። ደንግጦ ሊጮህ ፈለገ ጠቀሰውና ወደኔ ዝም ብለህ ና አለው ወደርሱም ሲቀርብ ይቺ ቦታ የማናት አለው የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢም ይቺ በምስር አገር ያለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አንተን ግን ልቡ እንደ ጠፋ ሰው ስትናገር አይሃለሁ ከዚህ ምን አመጣህ አሁንም ንገረኝ አለው። ወጣቱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ልቤ እንዴት አይጠፋ እኔ በዛሬው ሌሊት በእገሌ በረሀ ሳለሁ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ሰው ተገለጠልኝና ከኋላው በፈረሱ አፈናጠጠኝ ከዚህም አድርሶ ተወኝ አለው።

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 05:27


እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ እረፍት) በደህና አደረሰን።

#ኅዳር_25

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕት (ፒሉፓዴር)

አንድ አምላክ በሆነ በ #አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ አምስት በዚች ቀን የስሙ ትርጓሜ መርቆሬዎስ የሆነ ፒሉፓዴር በሰማዕትነት አረፈ። መርቆሬዎስም ማለት የ #አብ ወዳጅ ማለት ነው በሁለተኛ ትርጓሜ የ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።

ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው። የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት በሉት። ሁለተኛም አባቱን ሊበሉት ፈለጉ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው፤ ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለአለ አትንኩት አላቸው።

ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው። በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መጥተው ሰገዱለት። በዚያንም ጊዜ #እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ። አብረውትም ወደ መንደር ገቡ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት። የውሻ መልክ ያላቸውም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ። የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሉ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት። እናቱንም ታቦት አሏት። ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት።

የውሻ መልክ ያላቸው ግን የ #እግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ። ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ #እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው ንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው።

ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የውሻ አርአያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር። ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ። ንጉሡም ከጦር ሠራዊት ጋር የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርአያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ ያመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ። በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው፤ ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ። ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ።

ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በተመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም። ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ። ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሙና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከሀገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች።

ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ። የውሻ መልኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ። የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነቱ ወጣ በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት። ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም። በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው።

ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ። ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ አንደሆነ አወቀችው። እርሱ ግን አላወቃትም።

በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው። እርሱም አባቱ ነው። በተቀመጠ ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ።

የመርቆሬዎስም እናት መጥታ ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆነች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው እጅግም ደስ ብሏቸው #እግዚአብሔርን አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት #እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ።

ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው። ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልብ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ።

ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን #እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ።

እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት። እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ። እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ። ቅዱስ መርቆሬዎስም #እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ አለው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የ #እግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ #እግዚአብሔርን አስበው።

ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት ለምን የፈጣሪህን የ #እግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ አለው።

ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባበረ አስረዱት።

በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው። በመዘግየቱም አድንቆ ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልመጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው። እኔ ክብር ይግባውና #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Dec, 08:47


በአይነቱ ለየት ያለ ለ15 እና 16 ባች software,IT እና Comp ተማሪዎች የተዘጋጀ የአካዳሚክ መርሃግብር፦
ምን ልማር
➽እንዴት ውጤታማ እሆናለሁ
➽የTechnology አለም ከግቢ ውጪ ምን ይመስላል

ወደ ስራ አለም እንዴት ተማሪ ሆኘ መቀላቀል እችላለሁ ?
እና ሌሎች ለዘርፉ አስፈላጊ የሆኑት ጥያቄዎች የሚመለሱበት ነው ።

እናንተም እንዲመለስላችሁ ምትፈልጉትን ጥያቄ ከዚህ በታች በለው👇👇form ማስገባት ትችላላችሁ።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSetaT1-OzYlMxioImLyM_ez-ztvwmSUMZPeV_XrpTcW0tKJAw/viewform?usp=sf_link

🗓 ህዳር 24
ምሽት 2:00-4:00
⛪️ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን 

   
አዘጋጅ ሙያ እና ተራድኦ ነፃ ሙያ ንዑስ ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

01 Dec, 11:16


የ ህዳር ፅዮንን አመታዊ የ ንግስ በዓል ለማክበር በግቢ ጉባኤያችን ወደ ብርብር ማርያም ገዳም የተዘጋጀው ጉዞ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ባማረ መልኩ ተጠናቋል ።

ለረዳን ሁሉን ላደረገ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን አሜን !!!

ለተጨማሪ ፎቶዎች👇👇
@abrhigallery
@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

30 Nov, 07:31


🔔✝️ ጉባኤ ኒቆዲሞስ ✝️🔔
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
እንኳን ለጽዮን ማርያም አደረሳችሁ
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈

✝️ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። ኢሳ 48፥17✝️

እናት ግቢ ጉባኤ ከእናነተ ከልጆቿ የተሰበሰበውን ጥያቄ ምላሽ በክፍል ሁለት መርሐ ግብር ለመመለስ ሁሉንም ጨርሳ የእናነተን መምጣት በመጠበቅ ላይ ትገኛልች🥹
💛 አይኑም ልቡም ለዘለዓለም በሚኖርበት በመቅደሱ እንሰባሰብ💛

📅 ህዳር 21/2017 ዓ.ም
12:00
📍 ደ/ሎ/ቅ/ ኪ/ ቤ/ክ
⚠️ ማሳሰቢያ፤ወንድምና እህቶች በፍቅር ተጠራርተን እንገኝ።

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Nov, 09:51



ወደ ጉዞ ስንመጣ መርሳት የሌለብን ነገሮች:

👉ነጠላ፣ወፍራም ልብስ(ፎጣ) መያዝ፤ ትንሽ ብርዱ😊
👉የግቢ መታወቂያ መያዝ
👉የጉዞ ትኬት መያዝ
👉የጸሎት መጸሐፋ
👉 11 :30 በተማሪዎች በር ሁላችንም እንገኝ

📌ሁላችንም ክርስትያናዊ አለባበስ ይኑረን!
(ወንድሞች ነጠላ መልበስን አትርሱ)
📌ሰዓታችንን እናክብር!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Nov, 19:58


ሰላም ውድ የእግዚከብሔር ቤተሰቦች

ዘወትር በእለተ ማግሰኞ የምንለቅላቹን የእቅበተ እምነት ጥያቄዎች ከናንተው በመጣ ጥያቄ መሰረት ምን ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን Vote በማድረግ ሀሳባቹን አካፍሉን🙏

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Nov, 15:05


ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ታሪካዊቷ ብርብር ማርያም ገዳም

መነሻ- አርብ 20/03/2017 ዓ.ም 
         12:00 ሰዓት

መመለሻ- ቅዳሜ 21/03/2017 ዓ.ም


#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ
    📞 +251938540103
    📞 +251921749667

🚌 ትራንስፖርት መስተንግዶን ጨምሮ - 420 ብር ብቻ

  " የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። "          
                           ትን ኢሳ 60፥14
                 @guzoo_bot
                 @AmumcggBot

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Nov, 06:53


📜 #ምሴተ_ጥበብ

🖊️ በመርሐግብሩ ላይ ሐሳብና አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ፤ በቀጣይ ለሚኖሩን አገልግሎቶች ስለሚረዳን ይኽን ተጠቀማችሁ አድርሱን።

🔹 Telegram @do1920

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

25 Nov, 06:45


ናፔን ለእናቶች

ኑ ለእግዚአብሔር እናበድረው !!

"ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።
  ምሳሌ 19÷17

በናፕ ሰዓት ምሳችሁን ከካፌ ማውጣትና ለእናቶች ማድረስ የምትፈልጉ  በዚህ👇ስልክ
                 0996909809 ደውሉልን

🗓 ዘወትር ከሰኞ-ቅዳሜ
ከቀኑ 5:00-7:00


ሙያ እና ተራድኦ ቅዱሳን መካናት ንዑስ ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 07:20


እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) አደረሳችሁ!

ጾመ ነቢያት ከ ሰባቱ አዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን ከ ህዳር 15 ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ ልደት በዓል ድረስ የሚጾም ጾም ነው::


@amumcgg፡    ይከታተሉን
@AmumcggBot፡    ሐሳቦን ያጋሩ
@abrhigallery፡   የፎቶ ማህደራችን

© አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ -ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

23 Nov, 08:01


📱 በTelegran ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን ...

(በሩቅ ላላችሁ የእናት ግቢ ጉባኤ ልጆች)

#ምሴተ_ጥበብ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

23 Nov, 05:58


   #አዋጅ

ምሴተ ጥበብ

  በዛሬው ዕለት የGC birthdayን እና የሰሞኑ እንግዳዎቻችንን 17 ባቾችን አስመልክቶ ልዩ የምሴተ ጥበብ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።
የክብር እንግዳዎች፦
          የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች (GC)
    
የ2017  ዓ.ም ገቢ ተማሪዎች (fresh)
  
ዛሬ ምሽት 11:20
    ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት

🔑 ግቢው በር ላይ ዝማሬዎች ስለሚኖሩን በተባለው ሰዓት በቦታው ቀድመን እንገኝ
#Story #Profile #Share #Share

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 16:43


ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ታሪካዊቷ ብርብር ማርያም ገዳም

መነሻ- አርብ 20/03/2017 ዓ.ም 
         12:00 ሰዓት

መመለሻ- ቅዳሜ 21/03/2017 ዓ.ም


#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ
    📞 +251938540103
    📞 +251921749667

🚌 ትራንስፖርት መስተንግዶን ጨምሮ - 420 ብር ብቻ

  " የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። "          
                           ትን ኢሳ 60፥14
                 @guzoo_bot
                 @AmumcggBot

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 07:11


🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈

  🥰 ልዩ-የእንኳን ደህና መጣችሁ  መርሐ ግብር 🥰
                                          
   
🔵⚪️ 🎤እንኳን ደህና መጣችሁ ፣       🔵⚪️
⚪️🔵    ወደ እኔ ወደ እናታችሁ፣           ⚪️🔵
🔵⚪️    እጄን ዘርግቼ ስጠብቃችሁ፣     🔵⚪️
⚪️🔵    እንደ እዚህ እኮ የምላችሁ፣       ⚪️🔵
🔵⚪️    ቤተክርስቲያን ነኝ እናታችሁ🎤  🔵⚪️

ውድ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ  ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ የ17 ባች ተማሪዎች እንኳን ወደ ትምህርት ገበታችሁ በደህና መጣችሁ እያልን፤ ግቢ ጉባኤያችን

📆 ዛሬ ሀሙስ ህዳር 12- 2017 ዓ/ም
ከ 11:30 ጀምሮ

⛪️ ልማት ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን

የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር አሰናድታ ትጠብቃችኋለች።

"ጠሪ አክባሪ ስለሆነ በፍፁም አይቀርም "

🔑ከ 17 ባች ውጭ ያለን ባቾች በቦታው ቀድመን በመገኘት እህት ወንድሞቻችን በፍቅር እንድንቀበል ይሁን !!

      እናት -ግቢ ጉባኤ
🔵⚪️🔵⚪️🔵⚪️🔵⚪️🔵⚪️🔵⚪️
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 10:22


               🔔 #ጉባኤ_ኒቆዲሞስ  🔔          

ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ። መዝሙር 34 ፥11

እያለች እናት😊 ግቢ ጉባኤ ከእናንተ የተጠየቀውን ጥያቄ ለመመለስ ሁሉንም ጨርሳ የእናንተን መምጣት በመጠበቅ ላይ ነች🤗

💛 ልዩ ልዩ መርሐግብራት በአምላክ ደጅ። 💛

👉 ከናንተ የተሰበሰቡ ጥያቄዎች የሚመለሱበት መረሐግብር

📆 ህዳር -07 / 2017 ዓ.ም
12:00
📍 ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት

⚠️ ማሳሰቢያ፤ ወንድምና እህቶች በአንድነት በፍቅር ተጠራርተን የጉባኤው አካል እንሁን

         

🗨️ #Share #Profile #Story እናድርግ

©አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 07:27


🔔ዝክር🕯

እንኳን አደረሳችሁ!

🗓 ዛሬ በ 06/03/2017

ምሽት 11፡ 40 ጀምሮ

📌 አዘካሪ   እኅቶች

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 08:29


የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር የቤተ-መፅሐፍት ቀን አከባበር ከፎቶ ማህደር

ለተጨማሪ ፎቶዎች👇👇

@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 05:27


🔔ዝክር🕯

እንኳን አደረሳችሁ!

🗓 ዛሬ በ 05/03/2017

ምሽት 11 ፡ 40 ጀምሮ

📌 አዘካሪ   ሜካኒካል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 05:09


ሁልጊዜ መጽሐፍት ቢመለከት እንጂ ካልተመለከተ የህሊና እርካታን አያገኝም

ማር ይስሃቅ

Share
Story እናድርግ

✍️ ሙያ እና ተናድኦ ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

12 Nov, 05:35


                      መሐረነ አብ
📖 "የልመናዬን ቃል አድምጥ ንጉሴ እና አምላኬ ሆይ አቤቱ ወደ አንተ እፀልያለሁ"
           መዝሙር 5፥2

መሐረነ አብ ቅምሻ
❶➢ ንስአሎ
እንለምነው
❷➢ ናስተምህሮ
ራራልን እንበለው 
❶➢ ለአምላክነ ጻድቅ እስመ ጽድቅ ቃሉ
እውነተኛ የሆነው አምላካችን ቃሉ እውነት ነውና
❷➢ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ
ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ
❶➢ አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን
የድሆች አምላክ የተቸገሩትን የምትረዳ
❷➢ ነህነ ኀቤከ ተማኅፀነ
እኛ ባንተ ተማጽነናል
❶➢ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ
ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ
❷➢ አምላከ ነዳያን ናዛዜ ኅዙናን
የድሆች አምላክ ያዘኑትን የምታጽናና ሆይ
❶➢ ንህነ ኀቤከ ተማኅፀነ
እኛ በአንተ ተማጽነናል
❷➢ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ
ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ
❶➢ አምላከ ነዳያን ወተስፋ ቅቡፃን
የድሆች እና ተሥፋ ለቆረጡ አምላካቸው
❷➢ ንህነ ኀቤከ ተማኅፀነ
እኛ ባንተ ተማጽነናል
{መጽሐፈ ሰዓታት-መሐረነ አብ}

🗓 ወር በገባ ለተከታታይ ሶስት ቀናት(ሰኞ፣ማክሰኞ ፣ረቡዕ)
ምሸት: 11:30
📍 ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ( ግቢ ጉባኤ)



@amumcgg፡    ይከታተሉን
@AmumcggBot፡    ሐሳቦን ያጋሩ
@abrhigallery፡   የፎቶ ማህደራችን

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 09:14


📜 #ኪነጥበብ_ምሸት

ዛሬም እንደገና ...
ዘወትር ሰኞ ምሽት 12:00


መልካም ቀን ይሁንልን 🙌

🔷🔹ሥነ- ጽሑፍ🔸🔶

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 04:47


በአንድ ወቅት ታላቁ ቅዱስ አባት አባ እንጦንስ ከንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የተላከ ደብዳቤ ደረሠው:: ደቀ መዛሙርቱም አባታቸው የንጉሥ ደብዳቤ ስለደረሠው እጅግ በጣም ተደሠቱ:: እርሱ ግን ምንም የተለየ ግምት ሳይሰጠው ወደጎን አለው:: አሁንም ተማሪዎቹ ከመደነቅ ብዛት ለማንበብ በጣም ጓጉ፡፡ አባ እንጦንስ ግን «ልጆቼ ከሰው ለመጣ ደብዳቤ እንዴት እንደዚህ ደስ ይላችኋል? እነሆ የነገሥታት ንጉሥ እግዚአብሔር የብዙ ብዙ ደብዳቤዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልኮልናል፡፡ ለምን በዚህ መልእክት እንደዚህ አትደሰቱም? ለማንበብስ እንዴት አያጓጓችሁም?...

ከጉዞ ወደ እግዚአብሔር መጽሐፍ የተወሰደ

Share
story እናድርግ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Nov, 12:21


በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2016 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2016 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ቅዳሜና እሁድ ህዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሰኞ እና ማክሰኞ ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀምረው ረቡዕ ኀዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ Q የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣ እንዲሁም የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ R እስከ Z የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እየቀረባችሁ በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡፡
 
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ
https://www.amu.edu.et
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 20:06


🌹 ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ... 🌹

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 06:12


ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን::

ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ”በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯  በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “  …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።

መጋቢት ፳፯  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡  ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።

ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ። ጲላጦስም  በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭


@amumcgg፡    ይከታተሉን
@AmumcggBot፡    ሐሳቦን ያጋሩ
@abrhigallery፡   የፎቶ ማህደራችን


® የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ -ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Nov, 08:35


የዕለት ስንቅ -፮

  💠ንስሐ💠

ንሰሐ ሰው ሕይወቱን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለው መንፈሳዊ ጥንካሬ ወይም ኃይል ነው::

ንስሐ በልቡናችን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፍቅረ እግዚአብሔር እንዲወለድ ያደርጋል::

ምክንያቱም በንስሐ ሕይወት የምንኖረው ከሆነ እግዚአብሔር ስለ እኛ ብሎ የተሸከመልንን ሸክምና ይቅር ያለንን እጅግ የከፋ ኃጢአት እንድናስብ ስለሚያደርግና ለእግዚአብሔርም ያለን ፍቅር እያደገ ስለሚሄድ ነው::

        መልካም ቀን !

           #01 ትምህርት ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Nov, 16:05


የዕለት ስንቅ ፭

              " እምነትን ማሳደግ "

" ሐዋርያትም ጌታን፤ እምነት ጨምርልን አሉት።"   ሉቃ 17፥5

ለእምነትህ መንፈሳዊ ምግብን አቅርብለት ፤ ያን ግዜ ጥርጣሬ በርሃብ ይሞታል።

መንፈሳዊ ምግቦች ፦
                 - ቃለ እግዚአብሔር  እና
                 - ቅዱስ ቁርባን ናቸው ።
                         
" ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ። አምናለሁ ፤ አለማመኔን እርዳው አለ።"
                                  ማር 9፥24

             ሰናይ ምሽት !

                  # 01 ትምህርት ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 19:54


📻 መቅረዘ ሕይወት

📣 #ግጥም
      📜 እንዴት ይሆን የምትምረኝ
  

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 09:38


          🔔 #ጉባኤ_ኒቆዲሞስ  🔔          

#ዛሬም_ይቀጥላል

📆 ጥቅምት-23 / 2017 ዓ.ም
12:00


ማሳሰቢያ፤ ወንድምና እህቶች በአንድነት በፍቅር ተጠራርተን የጉባኤው አካል እንሁን !!!
▱▰▱▰▱▰✞▱▰▱▰▱
▰▱

#share🤝 #join  t.me/amumcgg

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

01 Nov, 07:51


               መሐረነ አብ ጸሎት

ምሸት: 12:00

📍 ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ( ግቢ ጉባኤ)

⚠️ ከ ጸሎቱ በኃላ የመቅረዘ ሕይወት🥰 መረሐግብራችንም እንደተጠበቀ ነው

@amumcgg፡    ይከታተሉን
@AmumcggBot፡    ሐሳቦን ያጋሩ
@abrhigallery፡   የፎቶ ማህደራችን

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

28 Oct, 23:29


🙏 እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ያሰበነውን መንፈሳዊ የአንድነት ጉዞ  ወደ ዳግማዊ ዮርዳኖስ ቦረዳ ገዳም ደስ በሚል ሁኔታ አድርገናል። ይህን ለማድረግ ከጀማሪ እስከ ፍፃሜ ላልተለየን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው።

ተጨማሪ ፎቶዎችን
👇👇👇

@abrhigallery

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 09:06


ጉዞ ወደ ቦረዳ ዳግማዊ ዮርዳኖስ ገዳም

ተዘጋጅታችኃል ?

➲ ዛሬ ምሽት ከ እራት በኃላ 11:30 ግቢ በር ላይ እንገናኝ! ማርፈድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው !


የምንይዛቸው ነገሮች
የለሊት ልብስ ( ትንሽ ቀዝቀዝ ስለሚል ጃኬት ነገር)
የጸሎት መፅሐፍ
የጸበል ጀሪካን( ያላችሁ ያዙ )

ስርዓት
ወንድሞች ሁላችንም ነጠላ መልበስ እንዳንረሳ
እህቶችም ስረዓት ያለው አለባበስ ልበሱ ጥፍር ቀለም ዊግና ወዘተ ባይኖር መልካም ነው::

ማርፈድ አይቻልም በሰዓቱ እንገኝ !!!

መልካም ቀን!

ለበለጠ መረጃ    📞 +251938540103
    📞 +251921749667

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

25 Oct, 06:02


⚡️ልዩ የአንድነት ጉዞ 🚌

🗓 መቼ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16

📍የት  ቦረዳ ዳግማዊ ዮርዳኖስ ገዳም

💰 ዋጋ 400 ብር ብቻ (መስተንግዶን ጨምሮ)


🎫 ለጓደኛህ/ሽ ትኬት በመግዛት ልዩ ስጦታ አበርክትለት/ቺላት። 👬 👭

#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ
    📞 +251938540103
    📞 +251921749667

🗨️ ለሁሉም ተማሪዎች እናጋራ!

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

24 Oct, 11:14


⚡️ልዩ የአንድነት ጉዞ 🚌

ወደ ታሪካዊው ቦረዳ ዳግማዊ ዮርዳኖስ ገዳም

መነሻ- ቅዳሜ 16/02/2017 ዓ.ም  
        ምሽት 12:00 ሰዓት
መመለሻ- እሑድ ከመርሐግብር በኋላ

# እኔ_ቅዳሜ_ከአዳር_ጀምሮ_ቦረዳ_ነኝ

እርስዎስ እቅድዎ እንደ ወፎች መብረር ከሆነ ከአሳዎች ጋር ምን ይሰራሉ ??
እንግዲያውስ
#ትኬትዎን_አሁኑኑ_ይውሰዱ
    📞 +251938540103
    📞 +251921749667

🚌 ትራንስፖርት መስተንግዶን ጨምሮ - 400 ብር ብቻ

  "ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ"
           መዝ 65፥5 
                 @guzoo_bot
                 @AmumcggBot

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

24 Oct, 05:11


"ኃጢአታችንን አምነን ብንናገር ግን ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ  የታመነ ነው ቸርም ነው። ከብደላችን ሁሉ ያነፃናል "1ኛ ዮሐንስ1:9

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfWJ7Ax1vAoZ1Trq87LS7H_uros7yoJGdZQWxIhV5I_bS99Cw/viewform?usp=sf_link

ተወዳጆች ይህንን ፎርም ሙሉ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

22 Oct, 06:07


🔔ዝክር🕯

እንኳን አደረሳችሁ!

🗓 ዛሬ በ 12/02/2017

ምሽት 11 ፡ 40 ጀምሮ

📌 አዘካሪ   15ባች

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 18:25


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»
     (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

" ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 19:17)                
ነገ(09/02/2017)  በእለተ ቀዳሚት ሰንበት የነዳያን ልብስ አጠባ በሙያና በጎ አድራጎት ክፍል  ስለተዘጋጀ በእለቱ በመገኘት ከበረከቱ እንዲሳተፉ : ለእግዚአብሔር እንዲያበድሩ በፍቅረ ነዳያን ስም እንጠራለን።
⛪️ ቦታ ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
ጠዋት : ከ2:00 ጀምሮ
👥 እህት ወንድሞቻችንን እንጋብዝ🥰

©️ ⚪️🔵 ሙያ እና ተራድኦ ክፍል⚪️🔵

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 10:36


🔔ዝክር🕯

እንኳን አደረሳችሁ!

🗓 ዛሬ በ07/02/2017

ምሽት 11 ፡ 40 ጀምሮ

📌 አዘካሪ   ሶፍትዌሮች

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 19:52


"ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው!" ምሳ.9:9

🛎ጉዳዩ:ነገ ኮርስ ስለመኖሩ🛎

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነገ እሁድ የ14፣15፣16 ባች ኮርስ ስላለ ሁላችንም ተቀሳቅሰን 12:00 ሰዓት እንገኝ!!
ኦሮምኛ መስማትና መናገር ለምትችሉት ፦ 10:00 ሰዓት

ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።” ( መዝ 34፥11 )  ትለናለች !! እናት ግቢ ጉባኤ

⛪️ ቦታ: ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ

ማሳሰቢያ: ሁላችንም ማስታወሻ ይዘን እንምጣ!!

share በማድረግ ላልሰሙ እህት እና ወንድሞቻችን እናድርስ !!

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏🏻


   ©️ አምዩ ዋና ግቢ ጉባኤ

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 19:29


📜 #ግጥም
🎤 ቶሎ ና ልበልህ ወይስ አትምጣብኝ

🗓 በጉባኤ ኒቆዲሞስ የቀረበ
ጥቅምት 02 - 2017 ዓ.ም


©በመዝሙርና ኪነጥበባት የስነ-ጽሑፍ ንዑስ ክፍል

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 09:37


🔔 #ጉባኤ_ኒቆዲሞስ  🔔

#ዛሬም_ይቀጥላል

📆 ጥቅምት 02 - 2017 ዓ.ም
11:45


ማሳሰቢያ፤ ወንድምና እህቶች በአንድነት በፍቅር ተጠራርተን የጉባኤው አካል እንሁን !!!
▱▰▱▰▱▰✞▱▰▱▰▱
▰▱

#share🤝 #join t.me/amumcgg   

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

11 Oct, 13:35


✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝️

                    
መሐረነ አብ ጸሎት

"በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ!" ኤፌ.6:18


📢📢📢 በጣፋጭ ዜማ የሚደርሰው የመሐረነ አብ የአንድነት ጸሎት እነሆ ደረሰ📢📢📢


12:00 ሰዓት ይጀመራል፤ በሰዓቱ ተገኝተን ጸሎቱን እንድናደርስ ይሁን ።
       

ቦታ : ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
ምሸት: 12:00  (ሰዓት ይከበር)
👥 እህት ወንድሞቻችንን እንጋብዝ🥰

@amumcgg

አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

05 Oct, 20:00



አመ ፳ወ፮ ለመስከረም ዘቀዳማይ ጽጌ በዓለ ቶማስ ወሀብተማርያም ማህሌት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

ዚቅ፦
ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎም፤ናርዶስ ጸገየ ዉስተ አፍሆሙ፤

መግቢያ ዘማኅሌተ ጽጌ

ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፤ተሠርገወት ምድር  

(🌹#በህብረት_ሁሉም🌹)
በስነ ጽጌያት፤ለመርዓዊሃ ትብሎ መርዓት፤ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት።

ማኅሌተ ጽጌ፦
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ  እምዓጽሙ፤ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ወበእንተዝ ማርያም ሶበ  ሐወዘኒ ጣዕሙ፤ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ።
ወረብ
መዓዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ ሶበ ሶበ ሐወዘኒ/፪/
ወበእንተዝ ማርያም አኅሊ ለተዓምርኪ/፪/

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ ወመንክር ስብሐቲከ፤ለዕረፍት ሰንበት ሠራዕከ፤

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ /፪/
አመ  ቤተ  መቅደስ ሠናይትየ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክት ይትለአኩኪ፣ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት

ማህሌተ ጽጌ
ጽጌኪ ማርያም ኮነኒ ሲሳየ ወአራዘ፤ወጸግወኒ እምትካዝ ተአምረኪ መናዝዘ፤ቶማስ ሎቱ አመ ገቦሁ አኃዘ፤እንዘ ይብል ከርቤ እምእዴየ ውኅዘ፣ረከበ በውስተ ቁስሉ አፈወ ምዑዘ

ወረብ-
አመ ገቦሁ ቶማስ ሎቱ አኃዘ/፪/
እንዘ ይብል ከርቤ እምእዴየ ውኅዘ ረከበ  አፈወ ምዑዘ/፪/

ዚቅ-
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወልድ እኁየ ፈነወ ዕዴሁ እንተ ስቊረት፤ለከፎ ሶቤሃ ርስነ መለኮት

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ  መንግሥቱ/፪/

ዚቅ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ፤ ወትምክህተ ቤቱ ለ፳ኤል።

ሰቆቃወ ድንግል
በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕፀተ ግጻዌ ዘአልቦ፤ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንቦ፤ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ ለኩለሄ ረከቦ፤ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ

ወረብ፦
ከማሀ ኀዘን ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ኀዘን/፪/
ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ ዓይነ ልብ ዘቦ/፪/

ዚቅ፦
እወ አማን እምውሉደ ሰብእ አልቦ፤ምንዳቤ ወግፍዕ ዘከማኪ በዉስተ ኩሉ ዘረከቦ፤

መዝሙር ፦
በ ፬
ትዌድሶ መርዓት ፤ እንዘ ትብል ነዐ ወልድ እኁየ ፤ ንፃእ ኀቅለ ፤ ት ፡ ንርአይ ለእመ ጸገየ ወይን ፤ ወለእመ ፈረየ ሮማን ፤ ት ፡ አሰርገወ ሰማየ በከዋክብት ፤ ወምድረኒ በሥነ ጽጌያት ፤ ት ፡ እስመ ውእቱ ወልድ ዋሕድ ፤ እግዚኣ ለሰንበት ፤ ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ ፤ ወልድ እኁየ ቃልከ አዳም ።

አመላለስ፦
ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ/፪/
ወልድ እኁየ ቃለከ አዳም/፬/