ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB] @fkerofficial Channel on Telegram

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

@fkerofficial


የ ኤልሳ[FB] ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል እነሆ

በዚህ ቻናል የ ኤልሳ[FB]ን የስነ- ፅሁፍ ስራዎች በብቸኝነት እንዲሁም ሌሎች ውብ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ
AMAZING QUOTES
MIND QUESTIONS AND OTHERS!
ግጥም
ድርሰት
አጫጭር አባባሎች ፍልስፍናዎች እና ሌሎችም!
@fkerofficial
ELSA[FB] OFFICIAL CHANNEL !

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB] (Amharic)

ኤልሳ[FB] ትክክለኛ ቴሌግራም ቻናል ነው። ይህ ቻናል ከ ኤልሳ[FB] የሚሆነው ጥያቄዎችን እና ሌሎች ድምፅዎችን መስራት ይችላል። ማንኛውም ድምጽ፣ ጥቂት አግኝቶች እና ሌሎች የስሜት ጥቂት ነገሮችን ለመስማት ብቻ ነው። የቴሌግራምን ማንኛውም መረጃ የሚያከብር ስልክ ቻናል ይሆናል። እንደዚሁም ቻናሎችን ከሌሎች ውብ ፐርግራሞች ጋር በማከብር እንዲሁም በአጫጭራት ያገኛሉ። የዚህ ቻናል በተመለከትነት እንዲህ ይሆናል - AMAZING QUOTES, MIND QUESTIONS AND OTHERS፣ ግጥም፣ ድርሰት፣ አጫጭር አባባል፣ ፍልስፍናዎች፣ እና ሌሎችም። እናመሰግናለን @fkerofficial በመጠቆም፣ ኤልሳ[FB] ቀላል ቻናል ነበር።

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

13 Nov, 13:07


የ 2023
2022
2021
2020
2019
2018
2017 ግሩፖች እንገዛለን
በውስጥ መስመር ያናግሩን
👉 @meroda123

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

11 Nov, 15:17


2022 እና ከዛ በፊት የተከፈተ ግሩፕ ያላችሁ እንገዛለን
inbox አውሩን 👉 @meroda123

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

25 Sep, 10:44


መቼ እንለያይ?

መቼ እንለያይ? መቼ እንተያይ?
ትቼህ መጥቻለሁ..
አይንህን ካየሁት ወራቶች አለፉ
በትንፋሽህ ርቀት ዘመናት ከነፉ
ተውኩህ ብዬ ነበር አንተም አልተመለስክ
ከመጣህ ባይህም በጊዜ አልደረስክ
እጠላህ እንደሆን
ጠየኩት አንጀቴን ምስክር እንዲሆን
አንተም አትጨክን
ወይ መጥተህ አትመጣ ወይ መክነህ አትመክን

ኤልሳ[FB]

@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

08 Sep, 17:11


" ምንድነው ማነው የሞተው? "
" ሲፈን ናታ ሳትሰማ ነው እንዴ የመጣኸው? አለኝ አለባበሴን አየሁት ጥቁር ሸሚዝ በ ቀይ ከረባት ከ ጥቁር ጨርቅ ሱሪ ጋር ነው የለበስኩት እውነትም የሰማሁ ነው የምመስለው አውቄ ሲፈን የምትወድልኝን ልብስ የለበስኩ ግን ምንም አላሰብኩበትም ነበር... ቆይ ቆይ ምን? ሲፈን ነው ያለው?
" ሲፈን ነው ያልከኝ? " አልኩት
" አዎዋ ትላንት ጠዋት ሆቴል ውስጥ ነው ራሷን አጥፍታ የተገኘችው አሉ " አለኝ ሳላስበው በጉልበቴ ወደኩ ፊዮሪ እየጮኸች ወደውስጥ ገባች እኔ በተምበረከኩበት ቀረሁ ፎቶዋ ፊትለፊት ተሰቅሏል ፎቶዋን ላለማየት ፊቴን አዞርኩ ማልቀስ አቃተኝ ደነዘዝኩ ደግፈው አስቀመጡኝ ከትላንት ወዲያ ማታ አስታወስኩ ያ ሁሉ ነገር ስንብት ነበር? እንደዛ ያየችኝ ድጋሚ ስለማታየኝ ነበር?... ያለቀሰችው...... መጮህ አቃተኝ እንደ ፊዮሪ እየጮህኩ ባለቅስ ብዬ ተመኘሁ አቃተኝ.. አጋጣሚ ነው? ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኛት የለበስኩትን ልብስ ደግሜ የለበስኩት? ስለምን ማሰብ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ እምባዬ ሲወርድ ጉንጬን ፈጀኝ ረጅም ሰአት ደንዝዤ ተቀመጥኩ እጄ ተንቀጠቀጠ በእምባዬ መሀል ውብ ፈገግታዋ ተጫዋችነቷ ስቀው እንጂ አንብተው የማያውቁ አይኖቿ ቅብጠቷ ሁሉ ነገሯ አይኔ ላይ መጣ ዮኒ ሁልጊዜ የሚለኝ አባባል ትዝ አለኝ " ቻው ብሎህ ለሚሄድ ሰው አትጨነቅ መመለሱ ስለማይቀር... ቻው ሳይልህ እየሄደ ላለ ሰው ስጋ እሱ መቼም ተመልሶ አይመጣም!"... ለሰአታት እያለቀስኩ ቆየሁ ፊዮሪ ስትጮህ ስታለቅስ አይዞሽ ያላት ሰው አልነበረም.. ሄጄ ደግፌ አስነሳኋት ይዣት ወጣሁ... አባቷ በአፈር እየተጨዋቱ ተነሱ ሲሏቸው እንደ ህፃን ልጅ ትከሻቸውን በእምቢታ ከፍ ዝቅ ያደርጋሉ... ፊዮሪን ይዣት ወደመኪናው ተመለስኩ...
"ኤው ስማ እየጠበቁሽ ነው በላት ምንስ ሙሽራ ብትሆን ነውር አደለም እንዴ እንግዳ አስቀምጦ ማርፈድ?" አሉኝ ቆጣ ብለው በተቀመጡበት... የገባሁላቸው ቃል ትዝ አለኝ .... የማነው ጥፋት? የኔ ? የሲፈን? የጊዜ? የአጋጣሚ? ወይስ የፍቅር?...ግን በቃ እንደዚህ ሆነ ማንም የማይጠየቅበት ጥፋት.. ቅኔው ግን.. እኔ ፊዮሪን 5 ደቂቃ ባለማዳመጤ እና ለሷ ስለ ፊዮሪ ባለመንገር ያረፈድኩትን እና ዘላለሜን ስከፍለው ልኖር የነበረውን ዋጋ ሲፈን በ አንድ ቀን በአንድ ነፍሷ ከፈለችልኝ.... ሲፈን! ለኔ ዘላለም መስዋዕት የሆነች ንፁህ ነፍስ... ህይወት ላይ የምንሰራቸው ስህተቶች ሁለት ናቸው ከሁለቱ የተሻለውን ስህተት መምረጥ ግድ ነው የቱስ ይሻላል? ማርፈድ ወይስ መቅረት? የትኛውም ቢመረጥ እንደ ጥፋቱ ክብደትና ቅለት የሚያስከፍለን አንድ ነገር አለ..... " ዋጋ! "






.......................ተፈፀመ..........................



ደራሲ - ኤልሳቤጥ በፍቃዱ ( ኤልሳ[FB] )
......................ጷግሜ 3..........................
........................2016............................




@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

08 Sep, 17:11


ዋጋ







በኤልሳ[FB]






ክፍል 99 [የመጨረሻ ክፍል]







.......... ያማል ግን እውነታ ነው! ድንገት የውጭው በር ገመዱ ተስቦ ተከፈተ
" ሲፈን ናት በሩን ዘግታ ስትመጣ ዮኒ ከውስጥ ወጣ
" እንዴ? ሙሽሪት? ምን ልትሆኚ መጣሽ በዚህ ሰአት? " አላት የእጅ ሰአቴን አየሁት እውነትም 4 ሰአት ሆኗል
" ሞዛዛ " ብላ አቅፋ ሰላም አለችው
" የምሬን እኮነው ሰላም ነው? " አላት
" ባሌ ናፈቀኛ " አለችው
" ወግ ነው አሉ " አለና ስቆ አሳቃት
" የተከበሩ ዮኒ ከባልየው ጋ ትንሽ ደቂቃ ቢሰጠን " አለችው
" ኧረ ካሁኑ ፕራይቬት ምናምን ተጀመረ? ኧረ እገባለሁ ናም ብትሉኝ አልመጣም " ብሏት ገባ ፈገግ አለች
" ሙሽራው...እኔ በዘፈን የተቀወጠ ቤት ስጠብቅ አንተ በረንዳ በረንዳውን ትቆዝምልኛለህ? " አለችኝ ከኋላዬ ካቀፈችኝ ቦሀላ በረንዳው ላይ ከጎኔ ቁጭ እያለች
" ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ልትዪ ነው? " አልኳት
" ቀላል እላለሁ? " አለች
" ከኔኮ ያንቺ ነው የሚገርመው እኔ የወንድ ቤት ነው ለባብሼ መምጣት ነው ቢበዛ ዮኒን ማስወጣት " አልኳት
" ሀሀሀ ቢሆንስ ደሞ ለምንድነው የሚወጣው " አለች
" ግን የምሬን ነውኮ እንዴት መጣሽ? " አልኳት
" ናፍቀኸኝ... ልቤ ሂጂ ሂጂ ሲለኝ መጣሁ " አለች
" ከነገ ጀምሮኮ ? አብረን ልንኖር ነው " አልኳት
" ቢሆንስ ናፈከኛ " አለች ፈገግ አልኩ
" ናኦዴ? " አለች
" ወዬ " አልኳት
" አፈቅርሀለሁ እሺ? " አለችኝ
" እምቢ " አልኳት እምቢ የሁል ጊዜ ቀልዳችን ነው.. ፈገግ አለች
አንገቴን ይዛ ፊቴን ወደሷ ካዞረች ቦሀላ አይን አይኔን አየችኝ ረጅም ደቂቃ ተያየን እይታዋ ውስጤን ሰረሰረው ከተዋወቅንበት ቀን ጀምሮ እንደዚህ አይታኝ አታውቅም አይኖቼን ሰበርኩ
ደግሜ ሳያት አይኖቿ እምባ አቅርረዋል
" ምነው? "
" አባቴ ነገ እኮ ላገባ ነው አባን ላስደስተው ነው " ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች አቀፍኳት... ረጅም ሰአት ዝም ማለት አቃታት አቅፊያት ቆየን ያደረኩት ነገር ልክ እንደሆነ እየተሰማኝ መጣ
የሆነ ሰአት ከእቅፌ ውስጥ ወጣች
" አፈቅርሀለሁ " ብላ ጉንጬን ጥብቅ አድርጋ ስማኝ ተነሳች
" አልመሸም? " አልኳት
"እና እዚህ ልደር? የነገ ሙሽራ እኮነኝ ብዙ ዝግጅት ይጠብቀኛል አንተም ተዘጋጅ ፈዘሀል ሙሽራው " አለችኝ
" እሺ ልሸኝሽ ወይ ዮኒ ይሸኝሽ " አልኳት
" ኖ አያስፈልግም መኪና ይዣለሁ " አለችኝ
ካጠገቤ ተነስታ ውጪው በር ጋር እስክትደርስ ድረስ በፈገግታ አይኗን ከአይኔ ላይ ሳትነቅል ወደኋላዋ እየተራመደች ወጣች ቤት ስገባ ዮኒ እያዘጋጀ ነው ምንም ሳልለው ገብቼ ተኛሁ...
ነጋ ከጠዋት ጀምሮ ሚዜዎቼ እና የስራ ባልደረቦቼ ቤቱን በጭፈራ ሲያቀልጡት አረፈዱ የሆነ ሰአት ላይ ዮኒ
" ሚዜዎቹ ደውለው ነበር ጨርሰዋል ከአባቷ ሳይሆን ከራሷ ቤት ነው የምንወስዳት " አለኝ
" ተስማሙ? " አልኩት
" ምኑን?" አለ
" ቤቱን ነዋ ከአባቷ ቤት ይሁን ብለው ነበር ለቀረፃ አይሆንም እያልኳት አልተስማማንም ነበር ተስማምተው ነው ማለት ነው " አልኩት
" ይሆናል... የቀረ ነገር ከሌለ እንውጣ " አለኝ ወጣን ሰርጉ ላይ ያልተጠራ የባለስልጣንና የባለሀብት ዘር የለም
ሲፈን (የቀድሞ ፊዮሪ) ቤት ገባን ሲፈን ቬሎዋን ለብሳ ተቀምጣለች አባቷ የሉም የተቀመጠ ዘመድ አዝማድም የለም አይኔ ፊዮሪን ከሚዜዎቹ መሀል ፍለጋ ተንከራተተ የለችም ተጠግቼ አይነ እርግቧን ገለጥኩት የሚየውን ማመን አቃተኝ ሙሽራዋ ሲፈን ሳትሆን ፊዮሪ ናት.. አይኔ ሲፈንን ፍለጋ ተንከራተተ የለችም ከፊዮሪ ቤት ወጥተን የመጣንበት ሊሞዚን ውስጥ ገባን ዳግምም አብሮን ገባ
" ሲፈንስ? " አልኳት ከቬሎ ጓንቷ ውስጥ የተጣጠፈ ወረቀት አውጥታ ሰጠችኝ
" ፊዩ ሁሉንም አውቃለሁ ስላንቺ ስለናኦድ ስለ ዳጊ.. ሁሉንም ሆስፒታል ሰምቻቸኋለሁ ስላልነገርሽኝ አልተቀየምኩሽም የ ናኦድ ሙሽራ አንቺ ነሽ ካልፈለግሽ አላስገድድሽም ግን አባን የማይበት አይን የለኝም በዚህ ሰአት እኔ ወደውጪ በርሪያለሁ ስለዚህ ናኦድ በዛ ሁሉ ሰው መሀል ያለ ሙሽራ እንዲቀር ካልፈለግሽ ሙሽራ ሁኚው ይሄንን ብቻ አድርጊልኝ እወዳችኋለሁ መልካም ጋብቻ
ሲፈን " ይላል ደግሜ አነበብኩት እምባዬ መጣ ግራ ገባኝ እንዴት? በምን ፍጥነት አመቻችታ ውጪ ወጣች? አባቷስ?በርግጠኛነት አባቷ ለዚህ ሁሉ መልስ ይኖራቸዋል አባቷን ያሳመነ ምክንያት እኔን ለማሳመን አያንስም ስለዚህ አንድ መፍትሄ አለ ነገ አባቷን ማናገር ! ራሴን ለማረጋጋት እንደ መፍትሄ አስቀምጬው ለመረጋጋት ሞከርኩ ሆቴል ገባን.. የሆቴሉ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ የልጅ አባት መሆኔ ብዙዎችን አስገርሟል
" ድምፅህን አጥፍተህ.... " ያሉም አሉ
ከሆቴል ወደቤት ሄድን ቤትም እስከ ምሽቱ 5:00 ሲጨፈር ቆየን አምስት ሰአት ላይ ሁሉም ተበተነ እኔ ፊዮሪ ዳግም እና ዮኒ ቀረን ዳግም
" ፓፓ " አለ በቀበጥ አጠራር
" ወዬ " አልኩት
" መቼ ነው በስልክ እገዛልሀለሁ ያልከኝን ቻክሌት የምትገዛለኝ? " አለ
"ነገ" አልኩት ሶፋው ላይ ወጥቶ ከቆመ ቦሀላ አቀፈኝ
" ተከዳሁ ማለት ነው? " አለ ዮኒ
" ኧረ በፍፁም " አልኩት ዳግምን በትግል እግሬ ላይ እያስቀመጥኩት
" ና " አለው ዮኒ ፍንጥር ብሎ ተነስቶ ሄደ
" አሁን ማሚ እና ዳዲ ይግቡ እኔና አንተ ደሞ ለብቻችን አብረን እንተኛለን " አለው
" እምቢ እኔ ከ ማሚና ከ ዳዲ ጋር ነው የምተኛው " አለው ሁላችንም ሳቅን ሙሉ ያልሆነ የጎደለ ደስተኛ ለመምሰል የሚሳቅ ሳቅ
ከፊዮሪ እና ከዳግም ጋር ገብተን ተኛን ዳግም መሀላችን ፊቱን ወደኔ አዙሮ አቅፎኝ ተኝቶ እንቅልፍ ወሰደው
ልጄንና ለአመታት የተራብኩትን አይን እያየሁ እንቅልፍ ወሰደኝ.....
በጠዋት ተነስቼ ፊዮሪንም ቀሰቅሼ ትላንት ያሰብኩትን ነገርኳት እሷም ተስማምታ ዳግምን ለዮኒ ትተነው ሲፈን አባት ቤት ሄድን ሰፈር ስንደርስ ግርግር አለ በሲፈን አባት ቤት መደዳ ስንደርስ ብዙ ሰው ወደዛ ቤት እየገባ ይወጣል አልፎ አልፎም የለቅሶ ድምፅ ይሰማል ሰውነቴን ነዘረኝ ከፊዮሪ ጋር ተያየን ምራቄን ዋጥ አድርጌ መኪናዬን አቁሜ ከመኪናዬ ወረድኩ ፊዩም ወረደች ሰውነቴን የሆነ ነገር ወረረኝ ወደቤቱ መግቢያ በተጠጋሁ ቁጥር ጆሮዬ ላይ የሆነ ነገር ልቤ ይነግረኛል " አባቷ አርፈዋል " ማመን አልፈለኩም
"ታዲያ እሺ ከሳቸው ሌላ ማን ይኖራል እዛ ግቢ ውስጥ?" ከህሊናዬ ተሟግቼ ሳልጨርስ አየኋቸው ቶሎ ቶሎ እየተራመዱ ወጡ ነጭ በነጭ ሱፍ ከቆዳ ጫማ ጋር አድርገዋል ወጥተው ደጁ ላይ ተቀመጡ የሰፈር ሰው ግማሹ " ኧረ ግቡ " ይላል
" እንዴ ሙሽራዬ መች መጣች? ሙሽራ ሳይመጣ ይገባል እንዴ? " እያሉ ድንገት አይን ለአይን ተገጣጠምን
" ይሄው እኮ... ንገራቸው እሲ ሲፈኔ ትመጣ የለ? የት ደረሰች ? ለምን ጥለሀት መጣህ ለመሆኑ? " አሉኝና መልሴን ሳይሰሙ ውጪ አቧራ ላይ ተቀምጠው በአቧራ መጫወት ጀመሩ ደንዝዤ ቆምኩ አስተሳሰቤ ቆመ ሰው ከእግር እስከላያችን እየገላመጠ ያየናል... አንዱን ለቅሶ ደራሽ ጠጋ ብዬ ጠየኩት

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

06 Sep, 09:01


@fkerofficial
@fkerofficial
@fkerofficial
#SHARE

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

06 Sep, 08:51


ዋጋ




በኤልሳ[FB]





ክፍል 98





........... በሚመጡት ቀናት ሁሌም አየዋለሁ እሰማዋለሁ ከህይወቴ አይወጣም እናም ማን ያውቃል ምናልባት አንድ ቀን አባቱ እንደሆንኩ ያውቅ ይሆናል... ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባና ዘጋው... "ምንድነው?" አለ
" ልጄ ነው... ዳግም ልጄ ነው " አልኩት እያለቀስኩ በድንጋጤ ካየኝ ቦሀላ መጥቶ አቀፈኝ
" እንዴት አረጋገጥክ ቆይ " አለኝ የተባባልነውን ምንም ሳላስቀር ነገርኩት
" እና አባቱ ነህ እያልከኝ ነው? " አለ
" ከዚህ ቦሀላ አዎ " አልኩት
" ዳጊን የመሰለ ልጅ አባት መሆን መታደል ነው ግን ፊዮሪን ምን አስበህ ነው? " አለኝ
" ማለት? " አልኩት
" እኔ ሳውቅ ፊዮሪን አደለም አሳልፎ መስጠት ተሳስቶ አይኑን የጣለባትን አፈር ስትደባልቅ ነው የማውቅህ... " አለኝ
" እሷ ስለአንተና ስለ ዳግም እንጂ ስለ አንተና ስለሷ አላወራችኝም ከሆነም ግን ምንም ብትል የምትፈልገው ነው መሆን ያለበት እኔስ ሌላ አግብቼ የለ? " አልኩት
" እኔ ፊዮሪን ለሌላ ነገር አስቤያት አላውቅም እኮ " አለኝ
" ከወደደችህ ስትለምዳት ትወዳታለህ ሱስ ነው የምትሆንብህ " አልኩት
" ራስህን ተመልከተው እሲ አላመንክበትም እኮ እጅህ እየተንቀጠቀጠ እየጨበጥከው ነው ደምስርህ ተገታትሯል " አለኝ
" እና አማራጭ አለኝ?... እሷን ካስደሰታትና አንተን ካላስከፋህ በቃ ምንም አድርግላት " አልኩት በመሀል ዳግም አፍንጫው እና አፉ ላይ በተደረገለት ኦክስጅን ላይ
"ፓፓ.." አለ አለቀስኩ ...
ሁሉም ገቡ ሲፈን መጥታ አቀፈችኝ ፊዮሪ አቀርቅራለች
" አባቴ? " አለችኝ
" ወዬ " አልኳት የግዴን ፈገግ እያልኩ
" አንተ ከዮኒ ጋር ሂድና እረፍት አድርግ በቃ እኛ እንቆያለን " አለችኝ
" ኖ ሳይወጣማ አንሄድም " አልኳት ዝም አለች
ሌሊቱን በሙሉ እዛው ቆየን ጠዋት መውጣት ይችላል ተባለ ፊዮሪ አቀፈችው ዮኒ
" እኔ ጋ ና ተዋት እሷን " ሲለው ዮኒ ካላቀፈኝ አለ ዮኒ አቀፈውና ትንሽ ቆይቶ
" ጫማዬን ልሰር ናኦድ ያዝልኝ " አለኝ...አቀፍኩት ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት አይኑ ውስጥ አይኔ ይታየኛል አየኝና ፈገግ አለ ዮኒ ጫማውን አስሮ ቀና ሲል መልሶ እቀፈኝ አለው
" እንደውም እንደዚህ እየተያየን እናውራ አይደል ? " አለው አንገቱን በእሺታ ነቀነቀ ፊዮሪ አቅፌው ዞራ አይታን ፈገግ አለች ሳላስበው ፈገግ አልኩ እሷን እያየኋት ሳላስበው አደናቀፈኝ ወደፊት የምወድቀውን ከመቅፅበት ፊቴን አዙሬ በጀርባዬ ወደኩ ዳግም ምንም አልሆነም እንደውም ሳቀ ጀርባዬን እያመመኝ ሳላስበው አብሬው ሳኩ ሌሎቹ ግን ደነገጡ ፊዮሪ ከላዬ ላይ አነሳችው ከተነሳሁ ቦሀላ ተቀበልኳት ሳታንገራግር ሰጠችኝ ድምፄን አንሾካሹኬ
" ሁለተኛ እንደዚህ እንዳታዪኝ እሺ " አልኳት ቀና ብላ አይታኝ ፈገግ አለች
" አወዳደቅ ላይ ጎበዝ እንደሆንክ ነግረኸኝ አታውቅም ነበር " አለች ሲፈን ሳቅን... ትንሽ እንደሄድን ዮኒ ወደ ጆሮዬ ቀረብ ብሎ
" ውሽምነቱን ካሁኑ መጀመርህ ነው? " አለኝና ሳቀ
" ያምሀል እንዴ? " አልኩት ሳቄ እየመጣ
" ምንድነው ያልከው? ለኔም ንገረኝ " አለው ዳግም
" ልንገርህ? " አለውና አንገቱን በአውንታ ሲነቀንቅለት በጆሮው የሆነ ነገር አለው
" ናኦድ " አለው ዳግም ደነገጥኩ ዮኒን አየሁት
" የሱም ስም ናኦድ ነው " አለው
" አንተ የአባቴን ስም ነው ያለህ? " አለና አቀፈኝ እምባ ተናነቀኝ
ከግቢው ወጥተን በመጣንበት መኪና ወደሆቴሉ ተመልሰን ቀን ላይ ተመልሰን ወደ አዲስአበባ መጣን ዮኒ
" በሉ እንግዲህ የነገ ሙሽሮች ለ24 ሰአት ብትለያዩ ከቻላችሁ አንቺም ሂጂ ተዘገጃጁ እኔም እሱን ሽክ ላርገው " አለ ስቀን ተለያየን
ቤት አመሸን መጠጤን ይዤ ውጪ በረንዳ ላይ ተቀመጥኩ ዮኒ
" ኧረ የነገ ሙሽራ መሆንህን እየረሳኸው ነው ጭፈራው ቢቀር ለሌላው ተዘጋጅ እንጂ በዚህ አይነት ነገ ምን ልትሆን ነው " አለኝ ዝም አልኩት
ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወት የመሸነፍ ስሜት ተሰማኝ ስንት ሰው ይሆን ህይወት ዋጋ አስከፍላ ያሸነፈችው? ስንት ሰው ይሆን ማዳመጥ ባቃተው 5 ደቂቃ ምክንያት ሙሉ ህይወቱን ያጣው? ስንት ሰው ይሆን መናገር የሚችለውን ነገር ሳይናገር በመቅረቱ ቅፅበታት የቀደሙት ስንት ሰው ይሆን የረፈደበት?...የቱስ ይሻላል? ማርፈድ ወይስ መቅረት?
ለ ሲፈን መጀመሪያም ስለ ፊዮሪ ብነግራት የዛሬው ሁሉ ቀርቶ በተቃራኒው ፊዮሪን ባገኘኋት ነበር አሁን ግን በጣም ረፍዷል አርፍጄም መድረስ እችል ነበር ግን ከአንድ አንድ አረፋፈድ መቅረት ይሻላል በቃ መቅረት ከህይወትም ላይ መቅረት ከሆነ ሰው ህይወት ውስጥ እያሉ መቅረት መረሳት መሆን የሚፈልጉትን ሳይሆን መሆን ያለበትን መሆን... ያማል ግን እውነታ ነው..............







ይ....ቀ.....ጥ.....ላ.....ል.......







@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

05 Sep, 06:12


" መዋሸትሽ ልክ አላደረግሽም ለአሁኑ ደናነው ለወደፊቱ ግን ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይቻልም በተደጋጋሚ ስለዚህ ጉዳይ ካሰበና ስሜቱ ከተጎዳ ነገሩን አስጊ ያደርገዋል " አላትና
" አሁን መጀመሪያ ካርድ አውጪለት " አላት ተነስተን ወጣንና ድጋፌን አስለቅቃኝ ብቻዋን ሄደች
ካርድ አውጥታ ስትመለስ ካርዱን ተቀብሏት
" አሁን ገብተሽ ማየት ትችያለሽ " አላት እየተጣደፈች ገባች
" ይሄን መዳኒት ግዛለት " ብሎ ከካርዱ ጋር አብሮ የመዳኒት መግዣውን ወረቀት ሰጠኝ ቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ ፋርማሲ ስሄድ 6 ወረፋ አለ
" ካርዱን ከስር አስቀምጠው " አሉኝ አንድ አዛውንት ግራ መጋባቴን አይተው
ካርዱን ከ 6ቱም ካርድ ስር አደረኩትና በካርዱ መሰረት ስም እየጠራች የመዳኒቱን ወረቀት እያነበበች መስጠት ጀመረች ከኔ ቦሀላም 2 ሰዎች መተው ካርዳቸውን ከኔ ስር አስገቡ... የሆነ ሰአት
" ዳግማዊ ናኦድ " አለች ልቤ 2 ቦታ ትርትር አለ በስህተት ከሆነ ብዬ ጠበኩ የተነሳ የለም ተነሳሁና የመዳኒት ማዘዣ ወረቀቱን ሰጠኋት መዳኒቱን ከካርዱ ጋር መለሰችልኝ ካርዱ እጄ እንደገባ ተሽቀዳድሜ አነበብኩት ዳግማዊ ናኦድ ይላል እምባዬ መጣ ደርቄ ቀረሁ...
መዳኒቱን ለዶክተሩ ሰጠሁትና ግሉኮዙ ላይ ጨምሮለት
"ረፍት ስለሚያስፈልገው አሁን ውጡ " አለን ሁላችንም ወጣን ትንሽ ቆይቼ ጠርቼ ይዣት ሄድኩና ካርዱን አሳየኋት
" ምንድነው ይሄ? " አልኳት
"ምኑ " አለችኝ
" ዳግማዊ ናኦድ  ይላል " አልኳት  ዝም ብላ ቆየች
" እሺ ለምን? " አልኳት
" እና አባትህ ሙሽራ ነው ለሱ ሰርግ ሚዜ ልሆን ነው ልበለው?" አለችኝ.. አለቀስኩ
" ዳግም በትክክል የኔ ልጅ ነው? " አልኳት
" እሺ ምን ላድርግ ? ካናዳ በሄድኩ በ3ኛው ቀን ነበር ለህክምና ጣሊያን የሄድኩት እዛ 3 አመት ቆይቻለሁ እዛ በተደረገልኝ ህክምና ነው መፀነስ እና መውለድ የቻልኩት የተኛሁት ደግሞ ካንተ ጋር ብቻ ነው... የመጣሁት ከሚዜነቴ ባሻገር አባቱን አንተን ላሳየው ነበር ግን ማፈላለግም ሳይጠበቅብኝ ገና በመጀመሪያ ቀኔ ሙሽራ ሆነህ አገኘሁህ... " ብላ አለቀሰች እኔም አለቀስኩ
" አሁንም አፈቅርሻለሁ እኮ " አልኳት
" እኔም አፈቅርሀለሁ ለአመታት ከሀሳቤ ወተህ አታውቅም ግን ምንም ማድረግ አንችልም " አለችኝ
" እንችላለን ልጄ ከዚህ በላይ መጎዳት የለበትም " አልኳት
" እኔም ጓደኛዬ ለ3ኛ ጊዜ ሰርጓ ተበላሽቶ ስትሰበር ማየት አልችልም የዳግምን ነገር እኔ እወጣዋለሁ ፍቃደኛ ከሆነ ዮኒ አባቱ እንደሆነ እንዲነግረው አደርጋለሁ በዚህ ምክንያት ሰርጉ አይበላሽም ዮኒም እሺ ይለኛል " አለች
" ፊዩ እኔኮ አፈቅርሻለሁ" አልኳት
" እኔም አፈቅርሀለሁ ግን መሆን ያለበት ይሄ ነው ጓደኛዬን ለሚስትነት ትቼልሀለሁ ጓደኛህን ለአባትነት ተውልኝ " አለችኝ እያለቀሰች
" ለምን? እኔኮ አባቱ ነኝ አለሁ " አልኳት
" ሰብአዊነት ይሰማህ እንጂ ሲፈንስ አባቷስ? " አለችኝ አባቷስ ስትለኝ በእናቴ የማልኩላቸው ትዝ አለኝ
" መሆን ያለበት እንደዚህ ነው እኔም ረሳሀለሁ አንተም እርሳኝ " አለችኝ ለመጨረሻ ጊዜ ሳምኳት አልተቃወመችኝም በተቃራኒው አቀፈችኝ...
" ናኦዴ በዚህ ምክንያት ሰርጉ ላይበላሽ ቃል ግባልኝ " አለችኝ
" እሺ " አልኳት
" አስቴርን በለኝ " አለችኝ
"እሺ አልኩሽ እኮ " አልኳት
" አስቴርን በል ስሞት " አለችኝ
" አስቴርን! " አልኳት
"እሺ!... " ብላ እያለቀሰች እጄን ስማኝ ረጅም ሰአት ቆይታ ተመለስን ስንመለስ ዮኒ ከዶክተሩ ጋር ቆሟል  ዶክተሩ
" ካርዱን ስጠኝ " አለኝ ሰጠሁት በሩን ከፍቼው ገብቼ አጠገቡ ተቀመጥኩ  ዳግምን ረጅም ሰአት አየሁት ልጄ ነው... ያ በአባት እጦት ሲከፋ ያየሁት ልጅ ልጄ ነው ያ የኔ በሆነ ብዬ የተመኘሁት ልጅ ልጄ ነው ያ ቆንጆ ልጅ ልጄ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርፖርት ሳቅፈው " አባቴ እሱ ነው? " ያለው ትዝ አለኝ አለቀስኩ.... ግን በቃ ህይወት እንደዚህ ናት ዮኒ ጥሩ አባት እንደሚሆነው ምንም አልጠራጠርም ከዮኒ ጋር እስካለ ድረስ ከአይኔ ስር አይሰወርም በሚመጡት ቀናት  ሁሌም አየዋለሁ እሰማዋለሁ.............





ይ...ቀ....ጥ.....ላ.......ል............






@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

05 Sep, 06:12


ዋጋ






በኤልሳ[FB]






ክፍል - 97







.......................እገዛልሃለሁ ብሎኛል " አለኝ  የዳዲ ፎቶ አለህ? አለው ዮኒ
" ኖ የለኝም ማሚ ስልክ ላይ ነው ያለው " አለኝ
ከዮኒ ጋር መላፋት ጀመሩ ዳግም የኔ ልጅ አደለም ብዙም ሳይቆይ ዮኒ እቅፍ ላይ እንቅልፍ ወሰደው መሀላችን አስተኛው
" እና " አለኝ
" እናማ በስተመጨረሻም ፊዮሪም ክዳኛለች" አልኩት
" ቢያንስ  ልጅህ እንዳልሆነ አውቀሀል ይሄ ውሳኔህን ቀለል የሚያደርግልህ ይመስለኛል " አለኝ
" በትክክል !..... የራሷን ህይወት ጀምራለች " አልኩት
" እውነት ነው " አለ
"ግን በቃ አጠገቧ ስሆን ራሴን መቆጣጠር ያቅተኛል ለምን እንደሆነ አላውቅም " አልኩት
"ቢሆንም ራስክን ተቆጣጠር " አለኝ
" እሞክራለሁ " አልኩት
የተደበላለቀ ስሜት ሙሽራነቴን እየረሳሁት መሰለኝ የመጣችው ፊዮሪ ናት እንደጣዖት የማያት ሴት እድሜ ዘመኔን የማውቃት ለአመታት ስጠብቃት የኖርኳት ብዙ ዋጋ የከፈልኩባትና ካንዴም ሁለቴ ያስቀየምኳት የመጀመሪያዬ ሴት.... መጣች አዎ መጥታለች እያየኋት እየነካኋት ነው መጀመሪያ ይሄን ልቀበል ከዛስ? ከዛማ የመጣችው ሰርጌ ላይ ለጓደኛዋ ሚዜ ለመሆን ነው... ከሌላ ሰው የወለደችውን ልጅ ይዛ... የጠፋችውም ስራዋ አሳፍሯት ይሆናል አንድ አመት ሙሉ በየመፅሄቱ እና በየ መንገዱ ዳር አፋልጉኝ ሳስለጥፍም አይታው አውቃ ይሆናል ዝም ያለችው... ስራዋ አሳፍሯት... እሺ ለምን አልጠላትም?  ለምንድነው ስለሷ መጥፎ ማሰብ ያቃተኝ መጥፎው ይቅር ጥሩ ማሰብ ማቆም ያልቻልኩት ለምንድነው? እንጃ... ልቤ ላይ የነበረው የተዳፈነ ፍም አይኗን ካየሁበት ቅፅበት ጀምሮ እንደእሳት እየተንቀለቀለ ያቃጥለኛል ራሴን መቆጣጠር እንዳልችል ያደርገኛል... ረስቼው... ለካ ሁሉንም ርሳው ትላንት ነው የምንተዋወቀው ተብያለሁ... እርሳው! አፏ ላይ እንዴት ቀለላት ስኖርለት የኖርኩትን ነገር እርሳው የከፈልኩትን ዋጋ እርሳው የተሰማኝን ፍቅር እርሳው... ያሳለፍነውን ሌሊት እርሳው... ያረኳትን ነገር እርሳው... ራሴን መቆጣጠር የማልችልበትን ጉዳይ እርሳው... እንዴት ቻለችበት መርሳቱን? ፊት መንሳቱ እንዴት ሆነላት? ነገሩ ቀድሞኑ  ረስታው አይደል ይሄን የመሰለ ቆንጆ የወለደችው... ቅናት እርር አረገኝ  የኔ ልጅ ቢሆን ተመኘሁ... 
ጠዋት በጠዋት ተነስተን ቁርስ እንኳን ሳንበላ ወደ ደብረዘይት ጉዞ ጀመርን እኔ ሙሽሪት ዳግም እና ሚዜዎች ሳሚ ከፊዮሪ ጎን ነው አስሬ ያስቃታል ወደዚያ ደርሰን ከመኪናው በወረድን አልኩ በውስጤ... ደርሰን ቁርስ በላን ሙሉ ቀኑን የከነገ ወዲያ ሙሽሮች እየተባልን በመዝናናት አሳለፍን ፊዮሪን ብቻዋን የማገኝበትን ቅፅበት ፈለኩ ግን አልቻልኩም በተለይ ይሄ ሳሚ የተባለ ሰውዬ ምንም ትንፋሽ ሊሰጣት አልቻለም መሸ!
ካንፋየር አዘጋጅተን ከበን ተቀመጥን የፊዮሪ አይኖች የኔን አይኖች ሽሽት ወዲያ ወዲህ ይሽከረከራሉ እኔ አይኔን መንቀል እንዳልቻልኩት ሁሉ... ውስጤ ሲረበሽ ተነስቼ  ውሀው ዳር ተቀመጥኩ በምሽት ደስ የሚል ድባብ አለው ፀጥ ዕረጭ ያለ ውሀ ህመሙን እንደኔ ዋጥ ያረገ ምስኪን መስሎ ይሰማኛል የግዱን የቻለው ከውስጡ ብዙ ፍጥረታት የሚተራመሱ ከላይ ሲታይ ግን እርግት ያለ ውሀ በፀጥታው ውስጥ ስለ ፊዮሪ ይበልጥ ማሰብ ማቆም አቃተኝ ሳላስበው እምባዬ መጣ ታፍኖ የዋለ እምባ...
" ናኦድ " አለኝ ዮኒ ከኋላ
" ወዬ " አልኩት እምባዬን ጠርጌ
"እያለቀስክ ነው?...   ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? " አለኝ
" እኔንጃ " አልኩት እምባዬን መቆጣጠር እያቃተኝ ሲጠይቀኝ ይባስ ባሰብኝ
" እሺ እኔ ምን ላድርግልህ ምንድነው የምትፈልገው? " አለኝ
" ላወራት እፈልጋለሁ " አልኩት
" አውራታ " አለኝ
" ብቻዋን አላገኛትማ " አልኩት
" ለሱ አያሳስብም አንተ የምታወራትን ነገር በደምብ አስብበት እኔ አመጣታለሁ " አለኝና ተነስቶ ሄደ
መጠባበቅ ጀመርኩ ትንሽ ቆይቶ ዳግም እጇን ይዞ እየጎተተ ይዟት መጣ ወዲያው የዮኒ እቅድ እንደሆነ ገባኝ ልክ እኔ ጋር ሲደርስ
" ማሚ ሸወድኩሽ ዮኒ አደለም እሱ ነው የተራሽ" አላትና እየሳቀ ሄደ... ቆማ ዝም ብላ አየችኝ
" አረፍ እንበል? " አልኳት
" ቆመን ማውራት እንችላለን ብቻችንን መታየቱ ጥሩ አደለም ለምንድነው ያስጠራኸኝ ? " አለችኝ
" ላወራሽ ፈልጋለሁ" አልኳት
" እየሰማሁህ ነው " አለችኝ
" ፊዩ ምንድነው የቀየረሽ? ቆይ አንድ አመት ሙሉ ድፍን ካናዳ አፋልጉኝ ሳይቀር አስለጥፌ ስምሽን በየ ሚዲያው እያስጠራሁ  ስፈልግሽ የት ነበርሽ? " አልኳት
" ካናዳ በገባሁ በ3ኛ ቀኔ ነው ለህክምና ወደ ጣሊያን የበረርኩት ዝርዝሩን ደግሞ ማወቅ አይጠበቅብህም " አለችኝ
" እሺ የዳግም አባት ማነው? " አልኳት
" ማንም ሆነ ማን አይመለከትህም ... ሙሽራ እንደሆንክ ትረሳዋለህ ልበል?" አለችኝ
" ቆይ ምንድነው ፍላጎትህ? " አለችኝ
" ፍላጎቴ ምንም ሆነ ምን አንቺን መረዳት አልቻልኩም " አልኳት
" አይጠበቅብህምም ከዚህ ቦሀላ አዲስ ፊዮሪናና ናኦድ ነን ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ የተዋወቅነው ለጓደኛዬ ሚዜ ለመሆን ስመጣ ኤርፖርት ነው ይሄንን ሁሌም ከጭንቅላትህ ውስጥ አስቀምጠው " ብላኝ ሄደች ድጋሚ የነበርኩበት ጋር ተመልሼ ተቀመጥኩ ውስጤ ምስቅልቅሉ ሲወጣ ይታወቀኛል ጩህ ጩህ አለኝ ድንገት
" ናኦዴ? " አለችኝ ሲፈን
" ምን ሆንክብኝ አባቴ? " አለች በድጋሚ
" ምንም ትንሽ መረጋጋት ፈልጌ ነው " አልኳት ከኔ እኩል ወርዳ ቁጭ አለች
"ፊትህ እኮ ልክ አይደለም የኔ ጌታ? " አለችኝ ጉንጬን በ2 እጇ ይዛ ወደሷ እያዞረች... አየኋት ምንም የማታውቅ የዋህ ንፁህ ነፍስ ትታየኛለች ጉንጬን ስማኝ ተነስታ እጇን ዘረጋችልኝና እጇን ይዤ ተነሳሁ ተቀላቅለን ትንሽ ጊዜ ካሳለፍን ቦሀላ ወደየመኝታችን ተበተንን

መኝታ ክፍሌ ከገባሁ 2 ሰአት ሆነኝ ግን እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ስለፊዮሪ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም የሆነ ሰአት ላይ ጩኸት ሰማሁ ከተኛሁበት ሮጬ ስወጣ ጩኸቱ ከፊዮሪ ክፍል ነው ደንግጬ በሩን ከፍቼ ስገባ ዳግም ነስር በነስር ሆኖ ዮኒ ታቅፎ ይዞት እየመጣ ነው ፊዮሪም ቦርሳዋን ይዛ ተከትላው ስትወጣ ሲፈንም አብራ ፊዮሪን እያረጋጋቻት መጣች ተከራይተን የመጣንበትን ዳማስ እያበረርኩ ሆስፒታል አደረስኩት ፊዮሪ አሁንም አልተረጋጋችም ከድንገተኛ ክፍል ሲያስወጡን አሎጣም ስትል ጥብቅ አድርጌ ያዝኳት ካስወጣኋት ቦሀላ አቀፍኳት
ትንሽ ቆይቶ ዶክተሩ ወጣ
" ቤተሰብ ማነው? " አለ
" አቤት ዶክተር ደናነው? " አለችው ማልቀሷን ሳታቆም
" ተከተዪኝ " አላት  ደግፊያት አብሬ ገባሁ
" አካሉ ላይ የደረሰ ቋሚ በሽታም ሆነ ጉዳት የለም ያ ማለት የተጎዳው አዕምሮው ነው ማለት ነው አዕምሮውን የሚጎዳ የተፈጠረ ነገር አለ? " አላት
" አዎ " አለች ማልቀሷን ሳታቆም
" ምንድነው? " አላት
" አባቱን እንደማገናኘው ነግሬው ነበር የመጣነው እና ውጪ እያለን የሆነ ሰው አባትህ ነኝ  ብሎ እንዲያወራው አደርግ ነበር ስሜቱ እንዳይጎዳ እናም እዚህ ስመጣ ሰውየውን ማግኘት አልቻልኩም አባቱ ደግሞ ሞቷል እና ትክክለኛውን ነገር እና አባቱን እንደማናገኝ ስነግረው ነው እንደዚህ የሆነብኝ " አለችው እያለቀሰች

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

21 Aug, 09:27


ዋጋ







በኤልሳ[FB]





ክፍል - 96






................. እያየችን ነው ተነስቼ ከሲፈን ጋር መደነስ ጀመርን የኔ ፊት ወደ ፊዮሪ ነበር አይኔን መንቀል አልቻልኩም እሷም እንደዛው በትክክል ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላውቅም ስጋዬ የሲፈን መንፈሴ የፊዮሪ እየሆነ መሰለኝ ለሰርጌ ሳይሆን ለቀብሬ ፕሮግራም እየተዘጋጀሁ መሰለኝ ለነገሩ እሷም እኮ ከሌላ ወልዳለች አንድ እኩል ነን እንደውም የሷ ባይብስ... የለም ዮኒ ተነሳና ለፊዮሪ እጁን ዘረጋላት እጁን ይዛ ተነስታ መደነስ ጀመሩ ሲፈን ወደዛው ዮኒ
" ሲፉ ያቺን ዳንስ ለምን አንሞክራትም? " አላት
" ሀሀሀ ና እሺ " አለችው ከፊዮሪ ጋር መደነሱን አቁሞ እጇን እጄ ላይ ከሰጠኝ ቦሀላ ከሲፈን ጋር እንደ ታዋቂ ዳንሰኛ መደነስ ጀመሩ ትንሽ ቆመን ካየናቸው ቦሀላ እጇን ከፍ አድርጌ ወደራሴ አስጠግቻት መደነስ ጀመርን የሆነ ስሜት ሰውነቴን ሲወረኝ ይሰማኛል ስጨብጣት የተሰማኝ ስሜት... ቀስ ብዬ ወደጆሮዋ ተጠግቼ ማውራት ጀመርኩ
" እስከመቼ ነው? " አልኳት
" ምኑ?" አለች
" በዚህ የምንቀጥለው" አልኳት
" እስከመጨረሻው... ሲፍ ማወቅ የለባትም.. ምንም ነገር ሁሉንም እርሳው እኔና አንተ የምንተዋወቀው ትላንት ነው " አለች ትንሽ በዝምታ ቆየን
" አምሮብሻል " አልኳት
" ከሙሽራህ ባልበልጥም " አለች
" እኔ ህይወት ውስጥ አደለም አንቺን የምታክል ካንቺ ጋር ሚዛን ላይ የምትቀመጥ ሴት የለችም... ወልደሽም ቢሆን " አልኳት ምን እያልኩ ነው? ያመኛል? ወዲያው ዳግም ጌም እየተጫወተ ከሶፋው ላይ ወደቀ እጄን ወገቧን አስለቅቃኝ ሮጣ ካነሳችው ቦሀላ አቅፋ የወደቀበት ጭንቅላቱን አሻሸችለት እኔም ለብቻዬ ተቀመጥኩ እሷ እያየችኝ አይደለም ቀልቧ ያለው ልጇ ጋር ነው...
ብዙም ሳይቆዩ እነዮኒ ጨርሰው ተቀመጡ ሲፈን መጥታ እግሬ ላይ ተቀመጠች
" ምን ሆንክ አባቴ? " አለችኝ ዮኒ በመሳቀቅ ፊት ያየናል
" ምነው? " አልኳት
" ፊትህ ልክ አይደለም " አለች
" ደናነኝ " አልኳት ፈገግ እያልኩ
" እሺ " ብላ ግንባሬን ስማኝ ተቀመጠች
" ነገ ከሁሉም ሚዜዎች ጋር ደብረዘይት ለማሳለፍ አስበናል ተዘጋጁ " አለች
" የፊዩም ሀሳብ ነው? ወይስ.." ሳላስበው አቆላመጥኳት እኔም ዮኒም ራሷ ፊዮሪም ደነገጥን
" ኧረ የኔ ነው ግን በቃ መሆን አለበት ፕሮግራም ያዙ " አለች ሲፈን በቀበጥ አነጋገር ማቆላመጤ ትዝም አላላትም ለዚህ ነው በጣም የምታሳዝነኝ መጥፎ ነገሮችን ለማሰብና ለማስተዋል አእምሮዋ ሩቅ ነው!
" እሺ " አልኩ
" በቃ እንሂድ የሆቴሉንም ጉዳይ በዛዉ እንጨራርስ " አልኳት
"አትቆዩም እንዴ? " አለች
" እንቆያለን ዝም በይው... ማታ ይደርስ የለ እንዴ እሱ? " አለ
" ማታ ይሻላል? " አልኩት
" አዎዋ እዚህ እንውላለን ብለን አይደል እንዴ የመጣነው " አለኝ
" እሺ " አልኩት ምን አስቦ ነው እኔ ለራሴ እስኪያስታውቅብኝ ጨንቆኛል
" እና ናኦዴ ጓደኛዬን እንዴት አየህልኝ? "
አለችኝ
" ተለውጣለች...." አልኳት
" ታውቃታለህ እንዴ? " አለችኝ ክው አልኩ
" ያው ስለሷ ብዙም ባታወሪኝም አስመራዊት እንደመሆኗ ቆንጆ ትሆናለች ብዬ ጠብቄ ነበር " አልኳት
" እና ፊዮሪ ምን ይወጣላታል? " አለ ዮኒ በመሀል
" እኮ? "
" ቆንጆ አደለችማ " አልኩት ሲፈን በመሳቀቅ አንዴ እኔን አንዴ ፊዮሪን አየችን
"እና ምንድናት?" አለ
" በጣም ቆንጆ " አልኩት
ሲፈን "ሂድወደዛ..." ብላ ትከሻዬን ገፋችኝ
ፊዮሪ ምንም አላለችም ፈገግ ብላ ዝም አለች
" እኔማ ሀሳቤንም እንዳልቀይር እየፈራሁ ነው " አልኳት
" የምን ሀሳብ? " አለች
" የሚስት ሀሳብ ነዋ ፊዮሪ ሲፈን " እያልኩ ነው አልኩ
" አንተ? " ብላ ሳቀች ሲፈን... ፊዮሪ ቀና ብላ ተኮሳትራ አየችኝ
" ኧረ ቀስ! መቀለድ አይቻልም እንዴ? " ብዬ የቆሰለ ሳቄን ሳኩ
" ጓደኛሽ ግን ቁንጅናዋ እንዳለ ሆኖ ትንሽ ጨዋታ አዋቂነት ይጎላታል " አልኳት
"ሀሀሀ ማ ፊዮሪ? እስክትግባባት ነው ሱስ ነው የምትሆንብህ " አለችኝ ሱስ ነው ልክፍት? አልኩ በሆዴ
" ኧረ ከልጅቷ አናት ላይ ውረዱ " አለ ዮኒ ፊዮሪን እንደማቀፍ እያለ
"ለሁለት እንጫወት? " አለው ዮኒ ዳግምን ፓዱን ተቀብሎ
" እሺ..." አለው ዳግም
ምን አስቦ ነው? ከሲፈን ጋር ስለ ሰርጉ እያወራን ቆይተን ስዞር ፓዱን አስቀምጠው መላፋት ጀምረዋል ፊዮሪ በፈገግታ ታያቸዋለች ቀናሁበት መንፈሳዊ ቅናት እኔ ከልጁ ጋር በሱ ቦታ ብጫወት እና እሷ እንደዚህ ፈገግ ብትልልኝ ብዬ ተመኘሁ ችግሩ በሱ ፋንታ እኔ ብሆን እንኳን እንደዚህ ፈገግ አትልልኝም ፈገግታዋ እንደናፈቀኝ ምንም አልናፈቀኝም
" ደስ ይላሉ አይደል? " አለች ሲፈን መፍዘዜን አስተውላ
" በጣም ልጅ እኮ ደሲላል" አልኳት
" አታስብ ልጅ በልጅ ነው የማደርግህ " ስንት ይሻልሀል?" አለች
" አስራ ሁለት " አልኳት
" ደርዘን? " አለች ሳቅን
"ዮኒ ልጁን እየኮረኮረ ተሸክሞ ይዞት ወጣ"
እኔና ሲፈን ወደ ወሬያችን ተመለስን ፊዮሪም ስልኳን መነካካት ጀመረች ሳናስበው ቀኑ መሸ እራትም እዛው በላን የዳግምና የዮኒ ፍቅር በጣም ፀንቷል ዳግም ከዮኒ ጋር አልለይም አለ
" ለምን እዚህ አታድሩም? " አለች ሲፈን
" አይ ሆቴሉንም አይተን " ሳልጨርስ ዮኒ አቋረጠኝ
" አሁንማ መሸ ነገ ጠዋትም ቢሆን እኔዳለን በዛላይ ዛሬ ከዳጊ ጋር ነው እኔ የማድረው " እያለ መኮርኮር ጀመረ ተኮሳተርኩበት
" አዎ በቃ እዚህ ነው ዛሬ አዳር " አለች ሲፈን ዮኒ ላይ አፈጠጥኩበት
" አዎ ባይሆን ወንዶች ለብቻ ሴቶች ለብቻ እንተኛለን " አለ
" ተስማምቻለሁ" አለች ሲፈን
ብዙም ሳንቆይ እኔ ልተኛ አልኩ የእንግዳ ክፍላችንን አሳየችን ዮኒም ዳግምን ይዞ ተከትሎኝ ገባ ከውስጥ ዘጋን
" አብሮን ነው እንዴ የሚተኛው? " አልኩት
" አዎዋ " አለ ልጁ ታብሌቱን ይዞ ጌም እየተጫወተ ሌላ አለም ውስጥ ገብቷል
" እንዴት ልናወራ ነው? " አልኩት
" ዛሬ የምናወራው እኛ ሳንሆን እሱ ነው ህፃን ልጅ አይዋሽም የፈለከውን መጠየቅ ትችላለህ " አለ ብልጠቱ ገረመኝ ፈገግ አልኩ
" አምጣው አምጣው " አልኩት ታብሌቱን ነጥቆ እየተላፋ አምጥቶ መሀላችን አስተኛው
" እኔንስ አታጫውተኝም? " አልኩት
" አቻውትሀለው " አለኝ
" አባትህስ? " አልኩት
" ዳዲን አላከውም " አለኝ እንደትልቅ ሰው ፊቱ እያዘነ
" ማሚ አገናኝታህ አታውቅም? " አልኩት
" በስልክ ነዋ አይቼው አላክም " አለ ከዮኒ ጋር ተያየን ዮኒ ደነገጠ
" ማለት ዳዲን በስልክ አውርተኸው ታውቃለህ? " አልኩት
" አዎ ሁሌ ነው የሚያወራኝ ግን አይመታም ማሚ ኢቲዮፕያ ነው ያለው ብላኛለች እ..እዚ የመታነው ልናግኘው ነው ሳገኝህ ቻኮሌት ገዛልሀለሁ ብሎኛል " አለኝ.................








ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል........







@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

19 Aug, 13:55


ዋጋ








በኤልሳ[FB]









ክፍል - 95








......................አነሳው
"ሄሎ ናኦዴ " አለች
" ናኦድ ተኝቷል ሲፉ ዮኒ ነኝ " አላት
" ራሱን ተሻለው? " አለች
" ተኝቶበታል " አላት
" እሺ ነገ አብረን የምንውለው ሚዜዎቹን ይዛችሁ ኑ እና ልብስ እንለካለን ንገረው " አለች
" እሺ እነግረዋለሁ " አላት
" እሺ ደናደር " አለችው
" ደናደሪ " አላት
ስልኩን ዘግቶት ዝም ብለን ቆየን
" ራስህን አረጋጋና አስብ " አለኝ
" እሺ " አልኩት ሁለታችንም ወደመኝታ ክፍላችን ሄድን ብተኛም እስከ 8 ሰአት እንቅልፍ እንዳልወሰደኝ አስታውሳለሁ ጠዋት ተነሳን ቁርስ በልተን ሳሚና ልዑልን (የስራ ባልደረቦቻችን) ጠርተናቸው ሲፈን ወደጠራችን ልብስ ቤት ሄድን እነ ፊዮሪ ቀድመው ገብተዋል የወንዶች ልብስ ቤት ነው ሁሉም በተቀመጡበት ገባን የኔ አይን እንደገባን ያረፈው ፊዮሪ ላይ ነው የሷም እኔ ላይ ነበር በየተራ ሰላም መባባል ጀመርን እኔ ሌሎቹን ሰላም እያልኩም እሷን ነበር የማየው በእጅ ሰላም እየተባባልን እሷ ጋር ስደርስ እጇን ዘረጋችልኝ እጇን ጨብጬ ወደኔ ስቤ አቅፌ ሰላም አልኳት ጥብቅ ያለ... የ7 አመታት ናፍቆት እቅፍ... ለምንድነው እንደዛ ያረኩት? ከቤት ስወጣ ከራሴ ጋር ያወራነው እንደዚህ ነበር? አልነበረም! እና? ምን እያረኩ ነው? እንጃ! የሆነ የተቆጣጠረኝ ሀይል ነው እንደዚህ እንዳረግ ያደረገኝ መጨረሻ ላይ ከ ሲፈን ጋር ሰላም ተባባልን ጉንጬን ስማ
" ተሻለህ የኔ ፍቅር " አለችኝ ፊዮሪን አየኋት
ለምንድነው ፊዮሪን የማያት ያመኛል እንዴ?
" ደ.. ደናነኝ " አልኳት
" ደሞ ለምን ጥቁር አረከው ለመለካት እኮ አይመችም " አለች የጥቁር ሸሚዜን ኮሌታ እያስተካከለች
" ትወጂው የለ እንዴ? " አልኳት
" ለቢሮ ነዋ " አለች
" ነው እንዴ? " አልኳት
" ታዲያስ እሺ አሁን ግባና ቀይር ምረጡና ቀይሩ " አለች መጀመሪያ የኔን እያመላለሱ ካስቀየሩኝ ቦሀላ በ4ኛው በነጩ ሱፌ ተስማምተው የሚዜዎቹንም መረጥን ሳሚ በየመሀሉ ከፊዮሪ ስር አልጠፋም እሷም የቀልድ ትስቅለታለች እሷን አይገባትም እኔን ግን ሳየው ገብቶኛል ቀልቡን ጥሎባታል በዛላይ በተፈጥሮው ጥርስ የማያስከድን ቀልደኛ ልጅ ነው ልቤ በቅናት እርር አለ ምን እየሆንኩ ነው? እኔኮ ሙሽራ ነኝ ያውም ባል!...
የኛ ተራ አልቆ እዛው ሞል ውስጥ ቤት ቀይረን የሴቶቹን ማየት ጀመርን ሰባት የልብስ መቀየሪያ ክፍሎች አሉት ሲፈን ከዮኒ ጋር ሲፈን ጋር ገባን ቬሎ ለብሳለች ዮኒ
" አይ አይ ሌላ ሌላ " የሌሎቹን አይተን እስክንመጣ ቀይሪ አላት
" እሺ " አለች ከሷ ጋር ወጥተን ሳሚን አንደኛው በር ላይ ቆሞ እየቀለደ አየነውና ተያየን ሁለታችንም እሱ ወደቆመበት ክፍል ሄድን ከውስጥ ፊዮሪ ትከሻዋ ጋር የቀሚሷን ማንጠልጠያ ታስተካክላለች ዮኒ ሳሚን ሲጠራው እኔ በሩ ጋር የቆመበት ቦታ ላይ ቆምኩ ፊዮሪ ጀርባዋን ሰጥታ የቀሚሷን የጀርባ ገመዶች ለመሳብ ወደኋላ እየታገለች
" ተጫወታ ምነው ዝም አልክ ? ነው ጨዋታ አለቀብህ? " አለች የስሜ ንቅሳት አሁንም ጀርባዋ ላይ እንዳለ ነው ወደውስጥ ገብቼ በሩን ዘጋሁት እስካሁን አልዞረችም ሳትዞር ከኋላዋ ፀጉሯን ከኋላ ወደፊት ካደረኩት ቦሀላ የልብሷን የጀርባ ገመድ ከታች እስከላይ ቀስ በቀስ ስቤ ካሰርኩላት ቦሀላ ፀጉሯን ወደኋላ መለስኩት
" ሳሚ ግን...." አውርታው ሳትጨርስ ዞራ ስታየኝ ደነገጠች የአይን ማርገብገብ የሌለው እይታችን ተደገመ ቃል የሌለው ውስጡ ጩኸት የሆነ ዝምታ እጄን ባዶ ትከሻዋ ላይ አሳረፍኩት ትከሻዋን ሽምቅቅ አደረገችው
" ቆንጆ ሆነሻል " አልኳት
" ምን እያረክ ነው? " አለችኝ ምን እያረኩ ነው?
"ኧ... ይቅርታ... ቀሚሱ ሄዶብሻል ለማለት ነው " አልኳት
"እና መረጥከው? " አለችኝ
" እኔ ወድጄዋለሁ የሚዜዎቹን አላውቅም " አልኳት
" ወጥተን እንያ " ብላ በቆምኩበት ጥላኝ ልቴድ ስትል እጇን ያዝኳት
" ፊዩ እናውራ " አልኳት
" ስለምንድነው የምናወራው? " አለችኝ
" ስለሁሉም " አልኳት
" ናኦድ አሁን ለሁሉም በጣም ረፍዷል ደግሞ የቅዳሜ ሙሽራ እንደሆንክ አትዘንጋ " ብላኝ እጇን አስለቅቃኝ በሩን ከፍታ ወጣች
ልክ በሩን ከፍታ ስትወጣ ሳሚና ሲፈን ሊገቡ በር ላይ ተገጣጠሙ አስገብታቸው ቀሚሷን አዩት
" ሞናሊዛ ራሷ እንዳንቺ አታንፀባርቅም ኧረ ውበት!" አለ
" ከሙሽሪት ግን አትበልጥም አይደል እንዴ አባወራው? " አለች ሲፈን አዎ ማለት አልቻልኩም...
" ይሄኛውን ቬሎ ወደሽው ነው?" አልኳት
" አዎዋ አያምርም? " አለች
" ጥሩ ነው ግን የተሻለ የለም? እዪ እስኪ " አልኳት
" እሺ ራስህ መተህ ምረጥ " አለችና እጄን ይዛኝ እየወጣች ሳሚም ፊዮሪን አቅፏት ዞሬ ሳያት ዞራ ስታየኝ ተገጣጠምን አሁንም ፀጥ ያለ መፋጠጥ
በበሩ ወጥቼ ከአይኗ ስክጠፋ ከአይኔ እስክትጠፋ ተያየን የሲፈንን ልብስ መርጠን ወጣን ሁሉም ከተበተነ ቦሀላ እኔና ዮኒ ልብሳችንን ቤት አስቀምጠን በሲፈን ፕሮግራም መሰረት ሲፈን (የዱሮው ፊዮሪ) ቤት ለምሳ ሄድን ስንገባ ፊዮሪ ሲፈን ዳግም(የፊዮሪ ልጅ) አሉ ምሳ ከበላን ቦሀላ ትንሽ ቆይታ ሲፈን ለስለስ ያለ ሙዚቃ በጂፓስ ከፈተች...
" አሁን ደግሞ ወደ ዳንስ ፕሮግራማችን እንገባለን " ብላ እጇን ለዳንስ ዘረጋችልኝ ፊዮሪን አየኋት እያየችን ነው......









ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል.....









@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

15 Aug, 16:19


ዋጋ





በኤልሳ[FB]





ክፍል - 94







................. ሙሉ ሰውነቴን ነዘረኝ የገዛ ምራቄ ጎመዘዘኝ ዋጥ አደረኩት እጇን ለቀኳት ህልም ውስጥ ያለሁ መሰለኝ ስንላቀቅ ጠብቆ ዮኒ አቅፎ ሰላም አላት ሲፈን ልጁን እንዳቀፈችው ዞራ
"እንዴ ባሌንም እቀፊው እንጂ"... አለቻት ፈገግ ብላ ካየቻት ቦሀላ እኔን ኮስተር ብላ አቀፈችኝ አቀፍኳት ከ ሰባት አመታት ቦሀላ ነካኋት አቀፍኳት ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት የሷ ግን በመንካትና ባለመንካት መካከል ያለ መተቃቀፍ ነበር እጄ አሁንም ይንቀጠቀጣል ለ7 አመታት አሽትቼው የማላውቀው ጠረን ያውም የኔ ጣኦት የፊዮሪና ምን እየሆንኩ ነው? ከቀናት ቦሀላ የማገባ ሰው እኮነኝ... ለቀኳት እሷም ለቀቀችኝ አሁንስ ምን እያረኩ ነው ፊዮሪን እኮነው የለቀኳት ታዲያ ምን ማረግ ነበረብኝ? ሳላስበው አቀርቅሬ ነበር ለካ ሲፈን አገጬን ቀና አድርጋ
" ፍቅር ደናነህ? " ስትለኝ ነው የታወቀኝ
" ደናነኝ ትንሽ ራሴን ነው " አልኳት
" ቤት ገብተህ ታርፍበታለህ... እየው የፊዩ ልጅ እኮነው አያምርም? " አለችኝ አሁን ገና ልብ ብዬ አየሁት ቀይ ጉንጫም የደስደስ ያለው ልጅ ነው አየኝና ፈገግ አለ ወልዳለች? ጥሩ ነው... ግን እንዴት? መውለድ እንደማትችል ነው የማውቀው ወይስ ማደጎ ያሳደገችው ነው? ልጁም ላይ ፈዝዤ ቀረሁ የሲፈን ስልክ ሲጠራ ልጁን አሳቀፈችኝና ስልኳን አነሳች
ፈገግ እያለ አይን አይኔን አየኝ
" ማነው ስምህ? " አልኩት
" ዳግም " አለኝ
ወደዛው ፊዮሪ ተቀበለችኝ
" ማሚ አባቢ እሱ ነው? " አላት
" አደለም ነገ አስተዋውቅሀለሁ አባቢን " አለችው
" እሺ ? " ስትለው
" እሺ " አለ አውራ ጣቱን አፉ ውስጥ አርጎ.... አባቱ አይታወቅም... ቢያንስ አሜሪካ ካለ ሰው አደለም የወለደችው... ሮጬ ጣቶቿን አየሁ ቀለበት አላደረገችም... ኢትዮጵያ ካለ ሰው የ 6 ወይም 7 አመት ልጅ እንዴት ትወልዳለች? ቢንያም! አዎ ቢንያም ነው የሚሆነው የዛን ቀን ማታ ምንም አልተፈጠረም ያለችኝ ውሸቷን ነው ማለት ነው ምክንያቱም ልጁ ከኔ ካልሆነ ከሱ ነው የሚሆነው ደሞ መልኩም እሷን ይመስላል ትክክለኛ ልጇ ነው ወይ ደሞ ልክ እንደሄደች ውጪ ያገኘችው ሰው ነበር እናም ለቫኬሽን ኢትዮጵያ መጥቶ ሊሆን ይችላል.. እንደዚ እንዳይሆን ደሞ ልጁ ያውቀው ነበር እዛ ቢኖር.... ስለዚህ ቢንያም!
ሁላችንም ወደመኪናዬ ሄድን ቁልፍ ሳወጣ ዮኒ ቁልፉን ተቀብሎኝ የመሪውን ቦታ ያዘ
" ናኦዴስ? " አለች ሲፈን
" ራሱን ትንሽ አሞታል " አላት
እኔም በተቃራኒው በር ከፍቼ ገባሁ ሲፈን ፊዮሪ እና ልጇ ከኋላ ገቡ
እነሱን ፊዮሪ ቤት ካደረስናቸው ቦሀላ ወደቤት ሄድን ገብቼ ቁጭ አልኩ ዮኒ
" መጠጥ ላምጣ " አለ አይን አይኔን እያየኝ በእጄ የበቃኝ ምልክት አሳየሁት ስሜቴ ድብልቅልቅ አለብኝ እምባዬ መጣ ደምስሬ ግንባሬ ላይ ሲገታተር ይታወቀኛል ከመኝታ ክፍሌ የመጨረሻ ደብዳቤውን ይዤው መጣሁ ስመለስ ዮኒ መጠጥ ቀድቷል
" ሳይበዛማ ጠጣ " አለኝ በአንድ እጄ ወረቀቱን በአንድ እጄ ጠርሙሱን ይዤ ሳልጠጣ ደግሜ ማንበብ ጀመርኩ አንብቤ ስጨርስ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ወረቀቱን ላለመጉዳት የያዝኩትን ብርጭቆ አጥብቄ ስጨመድደው እጄ ላይ ተሰብሮ ቆረጠኝ ያም አልተሰማኝም እንባዬ መንታ መንታ መፍሰስ ጀመረ ዮኒ
" እረፍ ናኦድ ተረጋጋ በአስቴር " ብሎ አቀፈኝ የእናቴን ስም ጠርቶ ሲያቅፈኝ ባሰብኝ ሳግ ተናነቀኝ አልኮል ይዞ መጥቶ እጄ ላይ አፈሰሰው ቀድሞ መጠጡ ስለፈሰሰበት ይሁን ስሜቱ ከዛ በላይ ስለተሰማኝ አላውቅም ምንም አልተሰማኝም እጄን ጠርጎ ጠመጠመልኝ
"አሁን ተረጋጋና እናውራ " አለኝ
" ምንድነው የምናወራው? " አልኩት
" ማድረግ ያለብንን ነዋ " አለ
" እሺ አውራ ልስማህ " አልኩት
" ልጁ የማን ይመስልሀል? " አለኝ
" የቢንያም " አልኩት
" ከቢንያም ጋር ምን አገናኘው ከሱ ጋር ምን ተፈጠረ? " አለ
" ተፈጥሮ ነበር ማለት ነዋ " አልኩት
" እኔ ግን ያንተ ነው የመሰለኝ " አለ
" ግን የኔ እንዳልሆነ ለኔም ለልጁም አረጋግጣልናለች አባቴ ነወይ ሲላት አደለም አለችው ያ ማለት አባቱን አያውቅም እናም አባትህን አስተዋውቅሀለሁ ተብሏል ስለዚህ የ6 ወይም የ7 አመት ልጅ የኔ ካልሆነ የማን ይመስልሀል? "
" እንደዛ ከሆነ የቢንያም ነው " አለኝ
" ያንን ነው ያልኩህ " አልኩት
" እሺ ምን አሰብክ? " አለኝ
" አላውቅም ከሌላ መውለዷ ለውጥ አያመጣም ሳያት ሳቅፋት የተሰማኝ ስሜት ያው ነው " አልኩት
" ያው ማለት? መቼም ሙሽራ መሆንህን አልረሳኸውም አይደል? " አለኝ
" አልረሳሁም.... ፊዮሪንም ልረሳ አልችልም " አልኩት
" እና ምንድነው ያሰብከው " አለኝ
" እንጃ! ቢሳካልኝ ጨርቄን መጣል " አልኩት
" አሁኑኑ መወሰን አለብህ " አለኝ
" ምንድነው የምወስነው ? እየሆነ ያለው ይገባሀል? እድሜ ልኬን ለሚስትነት ስመኛት የኖርኳት ሴት ሚዜ ሆና እኮነው የመጣችው " አልኩት
" እሷም እኮ ወልዳለች " አለኝ
" ቢያንስ አላገባችም ባትታመን ኖሮ የልጇን አባት ማግባት ትችል ነበር " አልኩት
" መቼም ሲፈንን ስለመተው እያሰብክ አይደለም አይደል? " አለኝ
" እንዴት እተዋታለሁ ወደራሴ እንድመለስ ያደረገችኝ እኮ እሷ ነች እሷን ማሳዘን በራሱ ሌላ ሀጢያት ነው ግን ደሞ እሷን ለማፍቀሬ ፊዮሪን መምሰሏም ምክንያት ነበር " አልኩት
" እና ወስና " አለኝ
" አላውቅም ፊዮሪም ሚዜዬ ስትሆን ማየት አልችልም ሲፈንም በድጋሚ በኔ ያለሙሽራ ስትቀር ማየት አልችልም " አልኩት
" እና ወስና " አለኝ ድጋሚ
" በቃ መወሰን ላንተ ቀላል ነው አይደል? " አልኩት
" ከነገ ጀምሮኮ አብረናቸው ነው የምንውለው የሆነ አቋም መያዝ አለብህ ቢያንስ" አለኝ
" ሲፈንን አገባታለሁ እሱ አይቀርም " አልኩት
"ፊዮሪስ " አለኝ
" ሁኔታዋን አቋሟን ማወቅ አለብኝ " አልኩት
" እሱ ጥሩ ሀሳብ ነው ማን ያውቃል እሷም የልጇን አባት ልታገባ ይሆናል የመጣችው " አለ
" አዎ አንተ ልክ እኮነህ ቢሆንስ? " አልኩት
" አዎ ተረጋጋ መጀመሪያ ፕሮግራሟ ውስጥ እኮ አልነበርክም ከሆነም ፕሮግራሟ ለጓደኛዋ ሚዜ ሆና የልጇን አባት አግኝታ ወይ አግብታ መውጣት ነበር... እየጠበካትም ቢሆን ሳታይህ ነበር መጥታ የምትሄደው " አለኝ
" እውነትህን እኮነው ቢሆንስ? " አልኩት
" ነው እንጂ... ሲፈንን ሳታስከፋ ክብርህን ጠብቀህ ነው መንቀሳቀስ ያለብህ ነፃነት ስጣት " አለኝ
" ልክ ነህ......" አውርቼው ሳልጨርሰው ስልኬ ጠራ ሲፈን ነች ሰአቴን አየሁት 5:30 ይላል በዚህ ሰአት እንዴት ትደውላለች?... በእርግጠኝነት ስለኔ አውርተዋል... እጄ ተንቀጠቀጠ ዮኒ ተቀብሎኝ አነሳው.............







ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል.....





@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

12 Aug, 16:38


ይ......ቀ......ጥ........ላ.........ል......






@fkerofficial

ኤልሳ[FB] _____________________Elsa[FB]

12 Aug, 16:38


ዋጋ





በኤልሳ[FB]






ክፍል 93


.................." ናኦዴ"
" ወዬ "
" የኔ ፍቅር... " አለች አይን አይኔን እያየችኝ ልቤ ትርክክ አለ የሚሉት አማርኛ ዛሬ ነው የተሰማኝ ደረቴ አካባቢ የሆነ ነገር ከውስጥ ወደውጪ ይዘላል
" ምንድነው እሱ " አልኳት ፈገግ ብዬ
" ልንጋባ 6 ቀናት ብቻ እንደቀሩን ታምናለህ? አባማ ካሁኑ እያቀለጠው ነው ብታይ ቤት በገባሁ ቁጥር ሲጨፍር ነው ማገኘው የሰፈሩን ሰው ሁሉ ገና ካሁኑ የጥሪ ካርድ ሰጥቶ ይሄው ሰፈር በገባሁ በወጣሁ ቁጥር አይናቸው አላራምድ ብሎኛል..." ብላኝ ሳቀች
ፈገግ ብዬ እጇን ያዝኳት
" አባ እኮ ካገባሽ ቦሀላ ከዛ ቤት እወጣለሁ አለኝ " አለችኝ ፈገግ ብላ እምባዋ ዱብዱብ እያለ
" የምር? " አልኳት
" አዎ የገዛሽልኝ ቤት ውስጥ እኖራለሁ አለኝ " አለች
ተነስቼ አጠገቧ ከተቀመጥኩ ቦሀላ እምባዋን ጠርጌ አቀፍኳት
ለምን አለቀሰች? ደስታው ነው? እንጂ መቼስ ለዚህ ድራማዋ አይሆን... እንዴት እንደምትነግረኝ ፈርታ ይሆን? ለነገሩ እንዴት አትፈራ በሷ አስተሳሰብ እኮ እኔ ፊዮሪን ረስቻታለሁ ትክክለኛ ማንነቷን ረስቼዋለሁ እናም ሌላ ሴት ለምጄ ላገባ ነው እንዴት አታለቅስ? መቼስ ትነግረኝ ይሆን? እንጃ ወይ አንድ ቀን የጀርባዋን ንቅሳት ሳየው ያውቀኛል ይጠይቀኛል ብላ ይሆናል... ለምን ያንን ቀን ዛሬ አላደርገውም.. አዎ እንደውም ጥሩ ምክንያት አለ ዋና!
" እሺ ተነሺ እንደውም ከዚህ ሙድ ለመውጣት ትንኝ እንዋኝበት " አልኳት
ፈገግ ብላ ካየችኝ ቦሀላ በአውንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀች
" የያዝሽውን ጨርሺና እንነሳ " አልኳት ወዲያው ደነገጠች
" ምነው? " አልኳት
" አይ ናኦዴ ዛሬ አይሆንም ሌላ ቀን ቢዚ ነኝ በዛላይ አንደኛዋ ሚዜዬ ዛሬ ማታ ነው ከውጪ ምትገባው ማታ ቢዚ ስለሆንኩ ቀን ነው ሌላውን መጨራረስ ያለብኝ " አለች
" ከውጪ የምትመጣ ጓደኛ አለችሽ እንዴ? " አልኳት ዱሮ ውጪ ሲባል መጀመሪያ ጭንቅላቴ ውስጥ የምትመጣው ፊዮሪ ነበረች ቀጥሎ ደሞ ክርስቲ ምን አስደነገጠኝ መቼም ፊዮሪ ካላበደች በቀር ክርስቲን ሚዜ አታደርግም ብታረግስ ምን ይፈጠራል? ምንም!
" እና አሁን ቆንጆ ጊዜ አሳልፈን አብረን እንሰራዋለና ማታም አብረን እንቀበላታለን ብቻሽን ከምትሄጂ " አልኳት
" እሺ ግን አሁንም ጊዜ የለኝም ሌላ ጊዜ እሺ የኔ ፍቅር " ብላ ጉንጬን ሳመችኝ
" እሺ " አልኩ በደመነፍስ
" ጎበዝ እኮነህ " አለችኝ ምንድነው ያልኩት እሺ? እሺ ማለት? ለምን እሺ አልኳት? ራሴን ጠየኩ " አትገረም ባክህ በከንፈሯ ጉንጭህ ላይ የወጋችህ ማደንዘዣ ያስቀባጠረህ ተራ ቃል ነው ሌላም ስላልቀባጠርክ አመስግን " አለኝ ከውስጤ የሆነ አካል
" ታውቃለህ ግን ሁሉም ለበጎ ነው እንኳንም ከዚህ በፊት ላገባቸው የነበሩት ወንዶች ቀሩ " አለች ድራማው ተጀመረ አልኩ በሆዴ
" ማን ይበልጣል? " አልኳት
" ተደምረው ራሱ ያንተን ሩብ አያክሉም " አለች
" ታዲያስ! ያኔ በኩራት ሰበብ እየወደድሽኝ ብትተይኝ ኖሮ ይሄን የመሰለ ሰው ነበር ልታጪ የነበረው " አልኳት ኮሌታዬን የፌዝ እያስተካከልኩ
" ፀፅቶኛል የኔ ፍቅር " አለችኝ ከፂሜ ላይ የሆነ ነገር እየጠረገች
" ታዲያስ " አልኳት
" ለነገሩ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አብረን መሆናችን አይቀርም ነበር " አለች
" በምን አስማት " አልኳት
" እኔ ፈርቼ አፍሬ ብተው እንኳን አንተ ስላፈቀርከኝ አትተወኝም ነበራ " አለችኝ በፈገግታ ጭንቅላቷን ወደጎን እያዘነበለች አይን አይኔን እያየች
" ሀሀ በምን አወቅሽ? " አልኳት
" ያስታውቅብሀል እኮ..." አለችኝ ከበፊቱ በበለጠ ፈገግታ አይን አይኔን እያየችኝ
" አንቺም ውሸት ላይ ጎበዝ ነሽ "አልኳት ፊቷ ቅይርይር አለ
" ምነው? " አልኳት
" የምን ውሸት? " አለች እንደቅድሙ አይኔን ማየት እያቃታት አሳዘነችኝ
" እየወደድሽኝ እንዳልወደድሽኝ ማስመሰሉ ላይ ነዋ " አልኳት
"ኧ.... ያው.... " ተርበተበተች
" ያው ምን ?" አልኳት አይን አይኗን እያየሁ እየቀረብኳት
አይኔን ማየት አቃታት ከንፈሯ እንደ ህፃን ልጅ መርበትበት ጀመረ
" ም... ምን....." በአውራ ጣቴ የሚንቀጠቀጠውን ከንፈሯን ካቆምኩት ቦሀላ ግንባሯን ስሚያት
" ማታ ደውዪልኝ የግል ስራሽን ስትጨርሺ " ብያት ተነስቼ ወጣሁ ወዴት ነውም አላለችኝም ለመረጋጋት የራሷ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት ገብቶኛል ከዚህ ቦሀላ አንስቼ ላላስደነግጣት ለራሴ ቃል ገባሁ
አመሻሽ ላይ ከዮኒ ጋር የተለመደ ቤታችን እየጠጣን ሲፉ መጣች
"ፊዮሪ መጣች " አለኝ ዮኒ
ተያይተን ፈገግ አልን እየተጣደፈች ነበር
" ናኦዴ ተነስ ሸኘኝ መኪና አልያዝኩም ሰአቱ በጣም ሄዷል " አለችኝ
" እሺ " ብዬ ስነሳ
" እኔስ? " አለ ዮኒ
" ና አንተም " አለችው
" ይሄን ሰሞን ግን ጣል ጣል አርገሽኛል " ብሎ አቅፎ ሲጨምቃት
"ዮ... ዮኒ... ብላ አየር እንዳጠረው ሰው ሳቀች "
" ሚስቴን ለቀቅ " አልኩት
" በቃ እረፍ ዮኒዬ ባልየው እየቀና ነው " አለች እየሳቀች
" ማ እኔ?... ነይ አሁን ግቢ " አልኳት የጋቢናውን በር ከፍቼ... ከገባች ቦሀላ በሩን ስዘጋው ወይኔ ማዕረጌን ተቀማሁ እሲ ወንድ ከሆንክ እኔን እንደሷ አስገባኝ " አለ የውሸት ኩርፊያ እያኮረፈ
የኋላ በሩን ከፍቼ እባክዎ ይግቡ ፊታውራሪ አልኩት
" አንተ አመረርክ እንዴ? " ብሎ ገብቶ ዘጋው ብዙም ሳንቆይ ኤርፖርት ደረስን መኪናዬን አቁሜ መቀበያው ጋር ቆመን ብዙ ቆየን
" ኡፍ ውሀ ጠማኝ ቆየች እኮ " አለች
" አዎ በጣም " አለ ዮኒ
" ውሀ ገዝቼልሽ ልምጣ " ብያት ስሄድ
" መጣሁ " ብሏት ዮኒም ተከትሎኝ መጣ የታሸገ አንድ ሊትር ውሀ ገዝተን ስንመለስ ስልኬ ላይ ቴክስት ገባ ከኪሴ አውጥቼ ቴክስቱን እያነበብኩ ዮኒ
" ናኦድ " ብሎኝ ቆመ ቀና ብዬ አየሁት ፊትለፊት ከሩቅ የሆነ ነገር ላይ አፍጥጧል አይኑን ተከትዬ ሳይ አይኔን ማርገብገብ አቃተኝ ፊዮሪ.... አዎ ፊዮሪ የኔ.... ትላልቅ ሁለት የኤርፖርት ሻንጣዎች እየሳበች መጣች አይኔን ማመን አቃተኝ ወደ ዮኒ ስዞር ዮኒ ከጄ ላይ የወደቁትን ስልኬንና ውሀውን ሰብስቦ ቀና አለ ተያየን ተመልሼ ወደ ፊዮሪ ስዞር ከሲፈን ጋር ተቃቀፉ ዮኒን እጁን ያዝኩት እሱም ከኔ በላይ አጥብቆ ያዘኝ ከስራቸው እስከ 6 አመት የሚገመት ልጅ አለ ሲፈን ልጁን አንስታ አቅፋ ሳመችው ሲፈን በአይኗ እኛን ስትፈልግ ከሩቅ አይን ለአይን ተገጣጠምን
" እንሂድ " አለኝ ዮኒ መራመድ ጀመርን እግሬን እየደነዘዘኝ ይመስለኛል በትክክል ምን እንደሆንኩ አላውቅም አጠገባቸው ደረስን ፊዮሪ አየችኝ እምባዬ መጣ ዋጥ አደረኩት ፊቷ ላይ ግራ የመጋባትና የመረበሽ ስሜት ይታያል አይናችን ከያየበት ቅፅበት ጀምሮ አይናችንን ማርገብገብ እንኳን አልቻልንም ዮኒ ከጎን ጎንተል አረገኝ አይኔን መንቀል አልቻቸልኩም ሲፈን ከህፃኑ ጋር ስታወራ ቆይታ ወደኛ ዞረች ፊዮሪ አየቻት አይኗ ሲነሳ እኔም አይኔን ነቀልኩ ሲፈንን አየኋት
"ተዋወቁ ምትክ የሌላት አብሯደግ ጓደኛና ሚዜዬ ፊዮሪና ውዱ ባሌ ናኦድ " አለች በየተራ እየጠቆመች ፊዮሪ ቀልቡን እንደተመታ ሰው ደነገጠች ወዲያው
" ፊዮሪና " ብላ እጇን ዘረጋችልኝ
" ናኦድ " ብዬ ጨበጥኳት ሲፈን ከልጁ ጋር ጨዋታዋን ቀጠለች
እጃችን መላቀቅ አቃተው የሁለታችንም እጅ ይንቀጠቀጣል አይናችን መላቀቅ አልቻለም ጥብቅ አድርጌ ጨበጥኳት ሙሉ ሰውነቴን ነዘረኝ... ....