ሐዲስ በአማርኛ @hadithamharic Channel on Telegram

ሐዲስ በአማርኛ

@hadithamharic


📚ይህ እለታዊ ሶሒሕ የሆኑ ሐዲሶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

አስተያየት ወይም መልእክት ካለዎት በ @HadithAmharic_bot ይላኩ።

ሐዲስ በአማርኛ (Amharic)

ሐዲሶች ስለሆኑ ሎዝ ሸምን ስትከተል የሚችሉበት ቻናል እንዴት ነው? ይህ ቻናል ለሁሉም ሐዋሳት ስነ ስርአት መብት መልእክት መለየትና ስለዚህ የምችል ህይወት ያለው። ሎዝ ሸምን መልእክት ከትእዛዝና ከሚገኙበት አገልግሎትን እንዴት እንደሚፈልግ እና ስለሎዝ ሸምን መጻፍት እንደሚቻለው እንደምንላቸው የሚሆን ስለዚህ ይህ ቻናል በ @HadithAmharic_bot ለመርዳት ለሚጋለጡበት ለሁሉም አማራጭ አገልግሎቶች እንዴት ጥቅም እንደሚሆን ነው።

ሐዲስ በአማርኛ

23 Aug, 07:56


عن عبدالله بن عمر وأبي هريرة رضي الله عنهم أنهما سمِعا رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول على أعوادِ مِنبَره:

[ لَيَنْتَهِيَنَّ أَقْوَامٌ عَنْ وَدْعِهِمُ الجمُعَاتِ أَوْ لَيَخْتِمَنَّ الله على قُلُوبِهمْ ،ثُمَّ ليَكُونُنَّ مِنَ الغَافِلينَ]

📚رواه مسلم

🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዑመር እና አቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚንበራቸው እንጨት ላይ ቆመው እንዲህ ሲሉ ሰምተናል አሉ:-

[ሕዝቦች የጁመዐ ሶላቶችን ከመተው ይከልከሉ። አለዚያ አላህ ልቦቻቸው ላይ ያትምባቸዋል። ከዛም (አላህን ባለማውሳት) ከዘንጊዎች ይሆናሉ።]

📚ሙስሊም ዘግበውታል።

🔖ሐዲስ በአማርኛ:-

Telegram: https://t.me/HadithAmharic
Instagram:https://instagram.com/HadithAmharic
FB: fb.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

08 Aug, 20:22


قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ

[ إِذَا صَلَّى أَحَدُكُمُ الْجُمُعَةَ فَلْيُصَلِّ بَعْدَهَا أَرْبَعًا ]

📚رواه مسلم.

🌸«::::::::::::» «:::::::::::»🌸


የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

(አንዳችሁ የጁሙዐ ሶላትን በሰገደ ጊዜ ከሱ ቡኃላ (ሱና) አራት ረከዐ ይስገድ።)

📚ሙስሊም ዘግበውታል።



https://T.me/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

18 Jul, 19:29


🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ

🔖ሐዲስ በአማርኛ:

ሐዲስ በአማርኛ

13 Jul, 15:29


عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم:

[ صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ ]
            
                   📚رواهُ مسلم 

             🌸«::::::::::::::::::»
«:::::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ቀታዳ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)  እንዲህ  አሉ:-

[ የዐሹራን ቀን መጾም ከርሱ በፊት (ያለፈውን) አመት   ወንጀል ያስሰርዛል  ብዬ  ከአሏህ  እከጅላለሁ። ]

         📚ሙስሊም ዘግበውታል።

●የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን እለተ ዐሹራእ በመባል ይታወቃል።

የዘንድሮ (የ1446 ዓ.ሂ) ዐሹራእ የሚሆነው የፊታችን ማክሰኞ  ሐምሌ 9/2016 ነው:: ከፊቱ ወይም ከኋላ መጾም ተገቢ ነው።

🤲አላህ ይወፍቀን

🔖ሐዲስ በአማርኛ:

Telegram: t.me/HadithAmharic
Instagram: instagram.com/HadithAmharic
FB: fb.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

07 Jul, 19:26


عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ :           
  قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

" أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ
وأفضل الصلاة بعد الفريضة صلاة الليل "

                        📚 رواه مسلم

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

“ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም የአላህ ወር ሙሐረም ነው፣ ከግዴታ ሶላት በኋላ በላጩ ሶላት የሌሊት ሶላት ነው።”

                       📚[ሙስሊም ዘግበውታል።]

ሐዲስ በአማርኛ

16 Jun, 03:55


كل عام وأنتم بخير
تقبل الله منا ومنكم
وعيدكم مبارك

ሐዲስ በአማርኛ

14 Jun, 17:49


عن أبي قتادة الأنصاريِّ رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:-

[ صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى الله أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ ]

                  📚 رواه مسلم

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ቀታዳ አል-አንሷሪ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-

[የዐረፋን ቀን መጾም ከርሱ በፊት (ያለፈውን) አመት እና ከርሱ ቡሃላ(የሚቀጥለውን) አመት ወንጀል ያስሰርዛል ብዬ ከአሏህ እከጅላለሁ።]

          📚ሙስሊም ዘግበውታል።


📆 የዐረፋ ቀን(ዙልሒጃ  9ኛው) ነገ ነው።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

06 Jun, 14:34


አስሩን የዙልሒጃ  ቀናት እንዴት እናሳልፍቻው?

1-እውነተኛ  ተውበት ማድረግ

እነዚህንም ሆነ  ሌሎች የዒባዳ ቀናትን ለመቀበል ከሰራናቸው ወንጀሎች በመጸጸት ወደ አላህ መመለስ አለብን። አላህ እንዲ ብሏል:-

{ ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።﴿ [ሱረ አል-ኑር፣31]

2- ቀኖቹን በአግባቡ ለመጠቀም ቁርጠኛ  መሆን

በዙልሒጃ 10 ቀናት  ውስጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን አላህ በደነገጋቸው ኢባዳዎች ለማሳለፍ ከወዲሁ ራስን እና ያግዘናል ያልነውን ነገሮች በሙሉ ማዘጋጀ ተገቢ ነው።

አላህ እንዲ ብሏል:- {እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፤ አላህም በእርግጥ ክበጎ ሠሪዎች ጋር ነው።﴿[ሱረቱ አል-ዐንከቡት፣69]

3- ከወንጀል መራቅ

የአላህን  ተእዛዛት መፈጸም ወደርሱ እንደሚያቃርብ ሁሉ የከለከላቸውን እና እርም ያደረጋቸውን ነገሮች መዳፈር ከርሱ መራቅን እና ከእዝነቱ ለመባረር ምክንያቶች ናቸው።

🕋 አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ያላቸው ደረጃ

1-አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ  በነዚህ  ቀናት ምሏል

አላህ በሆነ  ነገር ሲምል የዛን ነገር ትልቅነት እና  ደረጃ ያመለክታል፤ አላህ በትልቅ ነገር እንጅ አይምልም። አላህ እንዲህ ብሏል:-

﴾በጎህ እምላለሁ።በዐሥር ሌሊቶችም።﴿
[አል-ፈጅር፣1-2]
ኢብን ከሢርን ጨምሮ አብዛኞች ሙፈሲሮች እንዳሉት ‘አስሩ ሌሊቶች’ የዙልሒጃ  የመጀመሪያዎቹ ናቸው።

2-አላህ በርሱ ውስጥ እሱን ማውሳትን የደነገገባት “የታወቁ ቀናት” መሆናቸው።

አላህ እንዲህ ብሏል:-
﴾በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)﴿
[አል-ሐጅ፣28]
ኢብን ዐባስ እንዳሉት የታወቁ ቀኖች የተባሉት የዙሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስሩ ቀኖች ናቸው።

3- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዱንያ ቀኖች በላጭ መሆኗን ተናግረዋል

ከዐብደላህ ቢን ዐባስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ( ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
[ከነዚህ አስርት(ከዙልሒጃ  የመጀመሪያዎቹ) ቀናት ይበልጥ አላህ ዘንድ በውስጣቸው የሚሰሩ መልካም ስራዎች ተወዳጅ የሚሆኑበት ቀን የለም።] ብለው ሲናገሩ ሶሐቦች፡- ”የአላህ መልእክተኛ ሆ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን?“ በማለት ጠየቁ፤ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):- [ (አዎን!)ነፍሱንና ንብረቱን ይዞ የወጣ፣ ከዚያም አንዱንም ይዞ ያልተመለሰ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን(አይበልጥም።)] አሉ። (አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።)



4- በአስሩ ቀናት ውስጥ የዐረፋ ቀን አለ።

ዐረፋ ከዙልሒጃ የዘጠነኛው ቀን ነው። አላህ ﴾ ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ﴿የሚለውን አያህ ያወረደበት፣ወንጀሎች የሚማሩበት፣ የአላህ ባሮች ከእሳት ነጻ የሚባሉበት ቀን ነው።

5- በአስሩ ቀናት ውስጥ የእርድ ቀን (ዒደል-አድሐ) አለ።

የዙሒጃ አስረኛው የውመነሕር(የእርድ ቀን)የዒድ ቀን  ነው። ከቀናቶች ሁሉ ታላቅ ቀን ነው። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-(አላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ ትልቁ የእርዱ(ዒደል-አድሐ) ቀን ነው።(አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።)

6-ዋና ዋና የዒባዳ አይነቶች በነዚህ ቀናት ውስጥ ተሰብስበው ይገኛሉ።

ኢብን ሐጀር(አላህ ይዘንላቸው እና) እንዲህ አሉ:- “የዙልሒጃ  አስሩ ቀናት ልዩ የሆኑበት ምክንያት ዋና ዋና የአምልኮ አይነቶች እነሱም:ሶላት፣ ጾም፣ ሶደቃ እና ሐጅ በውስጧ  ስለተሰበሰቡ ነው። ይህ(ስብስብ) በሌሎቹ ውስጥ አይገኝም።”

🕋በአስሩ የዙልሒጃ  ቀናት ውስጥ ከሚሰሩ ታላላቅ ዒባዳዎች:- ሐጅ እና ዑምራ፣ ጾም፣ ሶላት፣ ዚክር እና ደቃ ማብዛት ይገኙበታል።



🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram: t.me/HadithAmharic
Instagram: instagram.com/HadithAmharic
FB: fb.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

06 Jun, 14:33


ሐዲስ በአማርኛ pinned Deleted message

ሐዲስ በአማርኛ

04 Jun, 15:05


عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:

[ ما مِن أيَّامٍ العملُ الصَّالحُ فيها أحبُّ إلى اللَّهِ من هذِهِ الأيَّام يعني أيَّامَ العشرِ ، قالوا : يا رسولَ اللَّهِ ، ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ ؟ قالَ : ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ ، إلَّا رَجلٌ خرجَ بنفسِهِ ومالِهِ ، فلم يرجِعْ من ذلِكَ بشيءٍ]

                     📚رواه أبو داوود

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዐባስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ( ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-

[ከነዚህ አስርት(ከዙልሒጃ  የመጀመሪያዎቹ) ቀናት ይበልጥ አላህ ዘንድ በውስጣቸው የሚሰሩ መልካም ስራዎች ተወዳጅ የሚሆኑበት ቀን የለም።] ብለው ሲናገሩ ሶሐቦች፡- ”የአላህ መልእክተኛ ሆ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን?“ በማለት ጠየቁ፤ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):- [ (አዎን!)ነፍሱንና ንብረቱን ይዞ የወጣ፣ ከዚያም አንዱንም ይዞ ያልተመለሰ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን(አይበልጥም።)] አሉ።

                📚አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

30 May, 19:01


🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ

🔖ሐዲስ በአማርኛ:

ሐዲስ በአማርኛ

10 Apr, 16:43


عن ثوبان رضي الله عنه أن رسولُ الله صلى الله عليه وسلم قال:

[ من صام رمضان وستا من شوال فقد صام السنة ]

                   📚رواه إبن حبان

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከሠውባን(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ረመዷንን እና ከሸዋል ስድስት ቀን የፆመ ሰው በእርግጥ አመት ፆመ።]

         📚ኢብን ሒባን ዘግበውታል።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

06 Apr, 14:58


🌾 ስለዘካተል-ፊጥር አጭር ማስታወሻ🌾

1⃣ ትርጉም:- ዘካተል-ፊጥር(ሶደቀተል-ፊጥር):- የረመዷንን ወር ፆም በመጨረስ ግዴታ የሚሆን ሶደቃ(ምጽዋት) ነው።

2⃣ የመደንገጉ ሒክማ(ጥበብ)

💡ለፆመኛው ሰው በረመዳን ፆም ላስገኛቸው ያልተገቡ እና ውድቅ ንግግሮች ማጥሪያ

💡ለሚስኪኖች በጎ ለመዋል እና የዒድ ቀን ከልመና እንዲብቃቁ ማድረግ

💡የዒዱን ቀን ደስታ አብሮ ለመጋራት

💡አላህ  የረመዷንን ፆመ ለመጨረስ ስላበቃን ለአላህ ምስጋናን የምንገልፅበት

3⃣ ሑክሙ(ሸሪዐዊ ድንጋጌው)

✔️ዘካተልፊጥር መስጠት ግዴታ ነው።

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አለ:-
"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)።  ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።)

4⃣ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

▫️የዒድ ለሊት እና ቀን ለራሱ እና በርሱ ላይ መቀለብ ግዴታ ከሚሆኑበት ሰዎች ቀለብ በላይ ያለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

5⃣ ማውጣት ግድ የሚሆነው ከማን ነው?

ከራሱ እና በርሱ ስር ላሉ የሚቀልባቸው ሰዎች(እንደ ሚስቶች፣ ልጆች...)

ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ማውጣት የተወደደ ነው።

6⃣ የሚወጣው ምንድን ነው?

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።

የእህሉን ዋጋ በገንዘብ ቀይሮ መስጠት አያብቃቃም።

7⃣ የሚወጣው የእህል መጠን

ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ዘንቶ

ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

8⃣ ለማን ነው የሚሰጠው?

🔖 በሚያወጣው ሰው አገር ላሉ ደሀ እና ሚስኪኖች

9⃣ የሚወጣበት ጊዜ

📍በላጩ ጊዜ የዒድ ቀን ጧት ከዒድ ሶላት በፊት ነው።

📍ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል።

🕌 ከዒድ ሶላት ቡኃላ ማዘግየት አይፈቀድም።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

05 Apr, 10:30


عن ابن عمر رضي الله عنهما قال:

"فرَض رسول الله صلى الله عليه وسلم زكاة الفطر صاعًا من تمرٍ، أو صاعًا من شعيرٍ، على العبد والحر، والذكر والأنثى، والصغير والكبير من المسلمين، وأمر بها أن تؤدى قبل خروج الناس إلى الصلاة"

         📚رواه البخاري ومسلم


            🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አሉ:-

"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)።  ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"

     📚ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።


ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

30 Mar, 07:37


عن عائشةَ رضِيَ اللهُ عنها أنَّ رسولَ الله صلَّى الله عليه وسلَّمَ قال:

[ تَحرُّوا لَيلةَ القَدْرِ في الوَتْر من العَشرِ الأواخِرِ من رمضانَ]

       📚رواه البخاريُّ

           🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከዓኢሻ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ለይለተል-ቀድርን ከረመዳን መጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ጎዶሎ ለሊቶች ውስጥ (መገጠምን) ፈልጉ።]

       📚ቡኻሪ ዘግበውታል።

ሐዲስ በአማርኛ: https://t.me/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

28 Mar, 02:16


عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:

[ مَن  يَقُمْ  ليلةَ  القَدْرِ إيمانًا  واحتسابًا، غُفِرَ له ما تَقدَّمَ من ذَنبِه ]

      📚متفق عليه

           🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ለይለተል-ቀድርን  በአላህ አምኖ፣ ምንዳን ከአላህ ከጅሎ የሚቆም ሰው ከወንጀሉ ያለፈው ይማርለታል።]

        📚ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

ሐዲስ በአማርኛ: https://t.me/HadithAmharic

ሐዲስ በአማርኛ

22 Mar, 16:30


عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال:

[ ذَهَبَ الظَّمَأُ، وَابْتَلَّتِ الْعُرُوقُ، وَثَبَتَ الْأَجْرُ إِنْ شَاءَ الله]

                    📚 رواه أبو داود

             🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (አላህ ከሁለታቸውም ስራቸውን ይውደድላቸው)  እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያፈጥሩ(ፆም ሲፈቱ) እንዲህ ይሉ ነበር:-

"ዘሀበዝ-ዞመኡ ወብተል-ለቲል ዑሩቁ ወሠበተል-አጅሩ ኢንሻ አላህ"

ትርጉሙ:-

[ ጥሙ ተወገደ የደም ሰሮችም ረጠቡ በአላህ ፍቃድ ምንዳውም ፀደቀ።]


           📚አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic