Biruh @dailybiruh Channel on Telegram

Biruh

@dailybiruh


“የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።”
— መዝሙር 19፥8
📬📬📬 ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ 📬📬📬
@Biruhfeedback_bot

Biruh (Amharic)

በቅና ተማሪዎች እና በመላእክት ላይ ቅጣት እና ስለ መንግሥት ችግር እስማማለው Biruh ተይዞ ከማበረታታቶች እና መንስኤት መሰመር ማህበረሰብም ከሞት የሞት የመንአኤል አገርና ድርጅት አመታት ያገኘን ስለሆነን። የሴቶችና ወንድምሽን በቅና እሳት አክሱምንና መስተዋድር ላይ አይገቡም። ብሏል እያለ አመታትም የሚገኙ ስፖርቶች ከተቋማቸውን ለመስክ ወደ በጣም ትክክለኛው ታከለ እና ስለ ተጽባበት መከላከያም በአፍሪካ ምእራፍ ለመስክ አቅምጣቸው። ስለህገወሩም ለሆስላም በህልው ምግብ አዊ።

Biruh

21 Nov, 08:33


https://youtu.be/eg9oDFiUZ2M?si=qSReni5ufbNyYNG6

አድሜ ተባረክ አሁንም ጸጋው ይብዛልህ 🙏

እንዲህ አይነት ፀጋ ያላቸውን አገልጋዮቻችንን በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ማበረታታት አለብን ይህ ዘማሪ በአንድ Single Track ብቻ መቅረት የለበትም 20 ሰዎች 5ሺህ ብር እያንዳንዳችን ቢናዋጣ 100,000 ብር ሆኖ ኮራ ብሎ አንድ ሙሉ አልበም እንዲያወጣ ያደርጋል ስለዚህ ይህንን ሥራ እንስራ እኔም አንዱ ነኝ ብቻ በጹሑፍ ማበረታታት አይደለም በሀሳቡ የምትስማሙ በውስጥ መስማር አናግሩኝ🙏 ይህም ከወንጌል ሥራዎች አንዱ ነውና!

Biruh

20 Nov, 19:18


👋ሰላም ውድ የ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ወጣቶች

👉በአድቬንቲስት የመጀመሪያው የወጣቶች የውይይት እና የትምህርት መድረክ በ ኤ ዋይ የደቀመዝሙርነት ትምህርት ቤት!!!


🌼ከህዳር 12 ጀምሮ በ https://t.me/AYBCLUB ቴሌግራም ግሩፕ በቀጥታ ስርጭት በ ተመረጡ ርዕሶች የትምህርት እና የጥያቄ እና የውይይት ፕሮግራም ይኖረናል።

👉ግሩፑን በመቀላቀል በብዙ ይጠቀሙ።

📚ህዳር 12 እና 16 በመጽሐፍ ቅዱስ እና በትንቢት መንፈስ ዙርያ ጥልቅ ጥናት እና ውይይት ይኖረናል።

📅ህዳር 12
🕐ከምሽቱ 3:00-4:00
በቀጥታ ስርጭት( Live stream)

🔖  ያላችሁን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ሁሉ ጻፉልን!! 👉@Kidist_Desalegn

👉ቀጠሯችሁ ከእኛ ጋር ይሁን

https://t.me/AYBCLUB

ተባረኩ!!!
ለአድቬንቲስት ወጣቶች ብቻ!!

Biruh

20 Nov, 15:13


ጭንቀታችን ለምን ይሁን?

ለየትኛው ዓለም ነው ሁልጊዜ የምንጨነቀው? መጽሐፍ ቅዱስ ("ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ"። ፊል 4:4) እያለን የኛ ጭንቀት ለምንድነው? ተጨንቀን በቁመታችን ላይ ስንዝር እንጨምር ይሁንን? ቃሉ እንደምለው... (ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ማቴ. 6:27 እና ሉቃ. 12:25) እናም ጌታ አምላካችን የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእኔ ላይ ጣሉ እያለን የእኛ የጭንቀትን መዓት ተሸክመን የምንገዳገደው ለምን ይሁን? (እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ጴጥ. 5:7) እንዲሁም (ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል እርሱ ይደግፍሃል ለጻድቁም ለዘላለም ሁከትን አይሰጠውም። መዝ. 55:22)

ሌላው ደግሞ በምድር ላይ ምን ያክል እንደምንኖር እኛ አናውቅም ግን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ("የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው"... መዝ. 90:10) ።

ስለዚህ ለየትኛው ዓለም ነው ጭንቀታችን????

መልዕክቴ እግዚአብሔር በሰጠን በዚህች በጥቂት ጊዜ ደስተኞች ሆነን እንኑር! ከዚያም መልካም መልካሙን እንስራ! የጌታን ዱካ እንከተል! የሚያስፈልገንን ሁሉ እርሱ ያውቃልና በእርሱ እንታመን!

እርሱን አስከብረን ማለፍ እንድንችል ጌታ አምላክ በጸጋው ይርዳን!

ወንድማችሁ @MesayD

Biruh

17 Nov, 12:04


በአባታችን መተማመን

አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ እነርሱም አልጎዱኝም"
(ዳንኤል 6፡22)

በጣም ከሚደንቁኝ የሃይማኖት አባቶች ታሪክ አንዱ የዳንኤል ወደ አንበሳ አስኪጣል ድረስ የነበረው እምነት ነው። ዳንኤል በባቢሎን ከዚያም በሜዶንና ፋርስ መግንስት ጊዜ ትልቅ ስልጣ ነበረው። ስልጣን ቢኖረውም በእግዚአብሐር ላይ ሙሉ በሙሉ በመታመን እስከሞት ድረስ ታማኝ ሆነ። እንዲህ አይነት የእምነት ታሪኮች ሊያበታቱንና እኛም በምናልፈው ችግርና መከራ ሁሉ ድል እንድናገኝ፣ በእግዚአብሔርም ላይ ሙሉ በሙሉ የምንታመን እንድንህን ያደፋፍሩናል። ያኔ ከነ ዳንኤል ጋር የነበረው አምላክ አሁንም ከእኛ ጋር ነው። እግዚአብሔር ሳያውቅ በሕይወታችን የሚሆን ነገር እንደሌለ እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል። ዳንኤልን በሰማይ አባቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታመን ያደረገው አምላኩን በሚገባ ለለሚያውቀው ነበር። ዳንኤል በቀን ሶስት ጊዜ በመንበርከክ ራሱን ዝቅ በማድረግ ከልብ የሆነውን ጸሎቱን ወደ ሰማይ አባቱ ያቀርብ ነበር። ዳንኤል የሰማይ አባቱን ሳያነጋግር ቀኑን አይጀምርም ነበር።

አንድ ፓስተር ወደ እሩቅ አገር በአይሮፕላን ሲጓዝ ሳለ ፓይለቱ አስደንጋጭ የሆን መልዕክት አስተላለፈ። በዚያን ጊዜ በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት በሙሉ በድንጋጤ ሲርበደበዱ፤ እንድ ትንሽ ልጅ ግን በተረጋጋ መንፈስ ተኝታ ነበር። ይህ ፓስተር በጣም በመገረም ወደዚህች ልጅ ጠጋ ብሎ እየሆነ ያለውን ነገር ሲነግራት የመለሰችለት መልስ በጣም የሚያስደንቅ ነበር:- ፓይለቱ አባቴ ነው ፤ ዛሬ እቤታችን እንደሚወስደኝ ነግሮኛል ብላ ለዚህ ፓስተር መለሰችለት ፤ ከዚያም ወደ መኝታዋ ተመለሰች። እኛስ ዛሬ ምድርን በቃሉ የፈጠረና ለእኛ እስትንፋስን ካለማቋረጥ ለሚሰጠን ለታላቁ እግዚአብሔር ያለን አምነት እንዴት ነው? በነገሮች ሁሉ ልባችን በተስፋው ቃል ላይ ያርፋል? ልክ እንደትንሽዋ ልጅ አይሮፕላኑ በችግር ላይ ቢሆንም ፓይለቱ አባትዋ ስለነበረ ተረጋግታ እንደነበረ እኛም ሁሉን ቻይ በሆነው አምላካችን ላይ ተስፋችንን እንድናደርግና በአርሱ ብቻ እንድንታመን እንደ ዳንኤል በጸሎት መትጋት አለብን።

እግዚአብሔር የቃሉን እውነታነትና የተስፋውን እርግጠኝነት ራሳችን ሞክረን እንድንለማመደው አንዲህ በማለት ያድመናል:- “ እግዚአብሔር ቸር አንደሆነ ቅመሱ እዩም (መዝ. 34:8)። " ጠይቁ ይሰጣችኋል " በማለትም ያደፋፍረናል (ዮሐንስ 16:24)። የተስፋው ቃሎች ይፈጸማሉ። ሳይፈጸሙ የቀሩበት ጊዜ የለም፣ ለወደፊትም አይኖርም። ወደ ኢየሱስ ስንቀርብና በፍቅሩ ሙላት ስንደሰት ጥርጣሬያችንና ጨለማችን ሁሉ በመገኘቱ ብርሃን ይገፈፋሉ። (ወደ ከርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ገጽ 108)

ልክ ህጻን ልጅ በአባቱ እንደሚተማመን፣ እኛም በሰማይ አባታችን በሁሉ ነገር ልንተማመንበት ይገባናል



የዕለት እንጀራ (ገጽ 186)
@MesayD

Biruh

15 Nov, 08:14


https://www.youtube.com/live/JECG0ExsL9A?si=g8OM9_0KOim-xSNw

Biruh

14 Nov, 14:06


https://youtu.be/2IpgWhAFqjU?si=arMjImFvU6mz7OzT

Biruh

13 Nov, 19:56


እግዚአብሔር እውነቱን ከሰዎች ደብቆ አያውቅም ። ሰዎች ግን በራሳቸው ድርጊት ቃሉ ግልጽ እንዳይሆንላቸው ያደርጋሉ። ክርስቶስ መሲሕ ስለመሆኑ ለአይሁድ በቂ ማስረጃ ተሰጥቷቸው ነበር፤ ሆኖም ትምህርቱ ወሳኝ የሕይወት ለውጥ የሚጠይቅ ነበር። በመሆኑም ክርስቶስን ከተቀበሉ ለዘመናት ሲደሰቱበት የነበረውን ወግ፣ ሥርዓት ራስ ወዳድና አምላካዊ ያልሆኑ ልምምዶችን በሙሉ መተው እንዳለባቸው ተረዱ። የማይለወጠውን ዘላለማዊ እውነት ለመቀበል መስዋዕትነት ይጠይቃል። በመሆኑም በክርስቶስ እምነት ለመመሥረት እግዚአብሔር በማያዳግም መልኩ የሰጠውን ማስረጃ ለመቀበል አልወደዱም። በብሉይ ኪዳን የተጻፈውን እንደሚያምኑ ሲናገሩ የነበረ ቢሆንም በዚያ ውስጥ ግን ስለ ክርስቶስ ሕይወትና ባህሪይ የተነገረውን ምስክርነት ተቃወሙ። ከተለወጡ አስቀድመው ያከማቹትን አመለካከትና ሃሰብ ለመተው ስለሚገደዱ ለመለወጥ ፈሩ። መንገድ፣ እውነትና ሕይወት የሆነውን የወንጌል ሃብት ከእነርሱ ጋር የነበረ ቢሆንም ከሰማይ ሊሰጥ የሚችለውን ታላቁን ስጦታ እምቢ አሉ” (ኤለን ጂ ዋይት፣ የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 55)።

Biruh

12 Nov, 20:25


ሀይማኖቱን ብሎ በ 22 አመቱ ጫማውን የሰቀለው ተጨዋች

ስዊዘርላንዳዊው እግርኳስ ተጨዋች ሲልቫን ዋልነር ሃይማኖቴ ቅዳሜ እንድጫወት አይፈቅድም በሚል ገና በ22 አመቱ ጫማውን መስቀሉን አስታውቋል::

ተጨዋቹ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በሚከተለው እምነት ቅዳሜ ሰዎች ምንም ስራ እንዲሰሩ አይፈቀድም ብሏል::

''እኔ የእየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ነኝ ሀይማኖታዊ የበዓል ቀናት ለእኔ ከምንም በላይ ነው ስለዚህ ቅዳሜ አልጫወትም እግርኳስ ለማቆም ወስኛለሁ '' ብሏል ተጨዋቹ::

ሲልቫን ዋልነር የስዊዘርላንድ ከ 21 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጨዋችም ነበር::

Biruh

10 Nov, 12:43


https://www.youtube.com/live/zv2847kJvnc?si=oVpl65LmMfqsz_ce

Biruh

10 Nov, 09:22


ከፀሐይ በታች

“... ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው”
(መክብብ 1:14)

ጠቢቡ ሰለሞን “ስኬት ናቸው” ተብለው የሚታሰቡትን ብዙ ነገሮች በመክብብ ምዕራፍ 2 ውስጥ ከዘረዘረ በኋላ ሁሉንም አንድ ላይ ሰብስቦ “ ከንቱ ናቸው ” በማለት ይደመድማል። ምንድነው ከንቱ ያደረጋቸው? የሚለውን ሲገልጽ “ ከፀሐይ በታች " መሆናቸው ነው ይለናል። ይህንንም በመክብብ መጽሐፍ ብቻ 29 ጊዜ ጠቅሶታል። እውነትም ከፀሐይ ማዶ ያለውን ነገር ታሳቢ ያላደረገ ማንኛውም ነገር ከንቱ ነው። ከሰማያዊ ነገር የተለየ ሁሉ ከንቱ ነው። ከዘለዓለማዊነት የተለየ ጉዳይ ከንቱ ነው። ከእግዚአብሔር የተለየ ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።

ብዙ ፈላስፋዎች እና ሳይንቲስቶች “ እግዚአብሔርን ገድለናል” በማለት ተናግረዋል፤ በመጽሐፍም ጽፈውታል። ይህንን መስማትም ሆነ ማንበብ በእጅጉ ያስደነግጣል። እነዚህ ሰዎች የተሳካላቸው እና ደስተኞች ይመስላሉ። ነገር ግን ሕይወታቸው ትርጉም የለውም። ምክንያቱም ከፀሐይ በታች ናቸው። በእርግጥ እግዚአብሔር ሟች ባይሆንም፣ እነርሱ ግን ከጥበባቸው ውስጥ ገድለውታል፤ ከስኬታቸው ውስጥ ገድለውታል፤ ከሕይወታቸው ውስጥም እንዲሁ።

ውድ አንባቢ ፡- ነገሮችህ “ ከፀሐይ በታች " ከሆኑብህ የእግዚአብሔር ነገር ከውስጥህ እየሞተ ይሄዳል። ከፀሐይ ማዶ ያለው ከውስጥህ እየሞተ ይሄዳል። ያ ደግሞ ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ። “ ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ” ይለናል በማርቆስ 8፡36 ላይ። አብዛኛውን ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን የምናባክነው ከንቱ በሆነው የዚህ ምድር ኑሮ ላይ ነው። ዛሬ ግን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል። የምናደርጋቸው ማናቸውም ነገሮች ከፀሐይ ማዶ ያለውን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

ከከንቱ ነገር ተላቀን የዘለዓለም ሕይወትን ያማከለ ኑሮ መኖር እንድንችል ፈጣሪ ራሱ ይርዳን

የዕለት እንጀራ (ገጽ 239)

@MesayD

Biruh

08 Nov, 13:28


https://www.youtube.com/live/coUeZvKhkRA?si=bDY2_2zHiwxdMj69

Biruh

08 Nov, 08:56


https://www.youtube.com/live/_c4dGo01o00?si=2oLUA_IIncCEj9l1

Biruh

07 Nov, 12:05


https://www.youtube.com/live/lt6Fx2Zsl5E?si=mQqID2maR7Z-jIuP

Biruh

07 Nov, 07:10


የምላስ ጉልበት

አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ ''
(መዝሙር 141:3)

በዚህ ምድር ሰውን ከሚያሰናክሉ በርካታ ነገሮች አንዱ ምላስ ነው ። ጌታ ኢየሱስ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል ብሎአል (ማቴ. 12:36–37)። ጠቢቡ ሰለሞንም ስለ ምላስ ጉልበት እንዲህ ብሎአል: “ የለዘበች ምላስ ቁጣን ትመልሳለች፣ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታነሳለች ' (ምሳሌ 15:1)። " ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ ጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል ” (ምሳሌ 15:4)።

ምላስ መጠኑ ትንሽ ይሁን እንጂ መገንባት ይሁን ማፍረስ የሚችል ጉልበት አለው። ያዕቆብ ከፈረሶች ልጓም፣ ከመርከቦች መቅዘፊያ፣ እንዲሁም ከእሳት ጋር ያነፃፅረዋል። ምላስ መጠኑ ትንሽ ቢሆንም በሰው ሕይወት ውስጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው መቅዘፊያ በግዙፉ መርከብ፣ ልጓም በትልቁ ፈረስ፣ እንዲሁም ትንሽ እሳት በትልቁ ጫካ ላይ የሚጫወቱትን አይነት ሚና ይጫወታል። በምላስ ምክንያት በሁለት አገሮች መካከል ግጭት ሊፈጠር በሺህዎች የሚቆጠሩ ሊሞቱ ይችላሉ። በምላስ ምክንያት ወህኒ ቤቶች ሙሉ ናቸው። በምላስ ምክንያት ትዳራቸው የፈረሰ ብዙ ናቸው። ያዕቆብ “ምላስ መጥፎ ጉዳት ስለሚያስከትል ዝም በሉ' እያለን አይደለም፤ ነገር ግን ትክክለኝውን ነገር በትክክለኛ ጊዜ ተናገሩ” እያለን ነው

ምላስ የሚያስከትለው ጉዳት በጫካ ውስጥ ከሚነሳው እሳት ጋር ተመሳሳይ ነው። የእሳትን አጥፊነት ማንም ሰው ያውቀዋል። እሳትና ምላስን ከሚያመሳስሏቸው ነገሮች አንዱ ፍጥነታቸው ነው። ምላስ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን ተጉዞ ሊጎዳ ይችላል። አንድ በአገሪቱ በምስራቅ አቅጣጫ ከብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተለቀቀ የቃል ሚሳኤል በአጭር ጊዜ በሌላኛው ጥግ በሚኖሩ ላይ ትልቅ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ምላስ እጅ የለውም፣ ነገር ግን እጅ እንደሚገል ምላስም ይገድላል። እጅ በቅርብ ያለውን ሲገድል ምላስ ግን በሩቅ የሚኖረውንም ሊገድል ይችላል። ዳዊት ስለ ምላስ ከተናገረው አንዱን ልጥቀስላችሁ:- አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፣ አንዳበታቸው በምድር ውስጥ ተመላለሰ ” (መዝ. 73:9)።

ምላስ በምድር ሁሉ የመመላለስ ኃይል አለው። ከዚያም አልፎ ወደ ሰማይም ይደርሳል። በአጠገቡ ያለውን ብቻ ሳይሆን የማያውቀውን እንግዳ ጭምር ሊያጠቃ ይችላል። ያዕቆብ ምላስን hመፀኛ አለም' ብሎ ይጠራዋል (ያዕቆብ 3:6)። አመፀኛ አለም ማለት ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ አለም' ማለት ነው። ያልተቆጣጠሩት ምላስ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳማይታዘዝ አለም ነው። አንድ የማይታዘዝ አመፀኛ አለም በውስጣችን አለ ማለት ነው። ምላስን ለመቆጣጠር ከሰው ውጪ የሆነ ኃይል ያስፈልጋል: " አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ ” (መዝሙር 141:3)

የዕለት እንጀራ (ገጽ 137)
@MesayD

Biruh

06 Nov, 13:00


https://www.youtube.com/live/LiC5pEW1jG8?si=hw9fAU5nio_r7UmH

Biruh

05 Nov, 14:59


https://www.youtube.com/live/cH0II8XN8Zo?si=Y9dRr3apSHTkn9ky

እስራኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ክፍል 1

Biruh

04 Nov, 17:02


https://youtu.be/2eeiA81GXt4?si=lwwU43GI7mWhNz0g

Biruh

03 Nov, 08:08


የፈተና ደስታ

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
(ያዕቆብ 1፡2)

ብዙዎቻችን በፈተና ወይም በመከራ ምክንያት የሚገኝ ደስታን ለማጣጣም አልታደልንም። የዚህ ምክንያቱ ብዙ ነው። ከብዙ በጥቂቱ:-

1 . የሚደርሱብን ፈተናዎች ያዕቆብ እንዳለው በእምነታችን ምክንያት ሳይሆን በሥጋዊ ምኞታችን ምክንያት የሚመጡ ስለሆኑ ነው። *አመጋገብ ላይ ባለመጠንቀቅ በሽታዎች፣ ኑሮ ላይ ባለመጠንቀቅ እዳዎችና ሌሎች ብዙ ችግሮች ይመጣሉ* ።

2 . ብዙ ጊዜ ችግርና መከራ ሲመጣ ክፉ ሰዎች፣ ኃጢአተኞች ስለሆንን የመጣብን ስለሚመስለን በጥፋተኛነት እየተቸገርን የመከራውን መንፈሳዊ በረከት ማጣጣም አንችልም።

3 . የሚደርስብን ችግር ለመንፈሳዊ እድገታችን የሚበጅ ሳይሆን “ *ሰይጣን እኛን ለመጉዳት ያመጣብን ነው* ” ብለን በማሰብ በአምላካችን ላይ ያለው እምነታችን ይሸረሸራል። የመከራ እሳቱ እኛን ለማጥፋት ሳይሆን ለማጽዳት የመጣ መሆኑን ማመን ይከብደናል። በዚህ ምክንያት የፈተናን ደስታ አናውቀውም።

4 . ለፈተና የሚበቃም እምነት ስለማይኖረን በትንሹ ኮሽታ በመደንገጥ ጸሎትን እግዚአብሔርን ለመምሰል ሳይሆን ከፈተናና ከችግር ማምለጫ መንገድ እናደርገዋለን።

በእምነታችን ምክንያት ግን በሥራ፣ በትምህርት፣ በትዳር እና በተለያዩ የኑሮአችን ክፍሎች እንፈተናለን!! ይህን አይነት ፈተና የተፈተነ ሰው በትእግስት የሚበልጥ በረከትን መቀበሉ አይቀርም። አንዳንዶቻችን በትምህርት ቤት በሰንበት ምክንያት እሳት ውስጥ ገብተን እናውቃለን። በእምነታችን በቤተሰብ ውስጥ ችግር ውስጥ ገብተን እናውቅ ይሆናል። ከወዳጅ ዘመድ መሳደድ ይመጣብን ይሆናል። ይህ መከራ መጨረሻው በረከት ነው። ጌታን የሰቀሉት እኛን ቢደበድቡን ስለስሙ ስለሆነ ደስ ይበለን!!

የመከራ በረከቶች ብዙ ናቸው። ከሁሉ በላይ ግን ጠንካራ የሆነ ሕይወት፣ የእግዚአብሔርን እጅ ያየ እምነት ይኖረናል!!

የዕለት እንጀራ (ገጽ 134)
@MesayD

Biruh

02 Nov, 17:27


https://www.youtube.com/live/mFqPxlZj4F4?si=Es_MW3uKRH6mLnot

ተጽፏል የቀጥታ ስርጭት

Biruh

02 Nov, 06:01


በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ፣ በማንኛውም ስቃይና መከራ፣ ነገሮች ሁሉ ሲጨላልሙና የወደፊቱ ሁኔታም በጭንቀት ሲሞላን፣ ከዚህም የተነሳ ረዳተ ቢስና ብቸኛች እንደሆንን ሲሰማን፣ በእምነት ወደ እርሱ ለምንጸልየው ጸሎት ምላሽ ይሆን ዘንድ አጽናኙ ይላክልናል፡፡

መልካም ሰንበት

Happy Sabbath


@DailyBiruh