~~~~~~~~~~~~~~~~~~
2; ባቢሎን
3; ግሪክ
4; ሜዶን
5; ግብፅ
6; ሮም
7; ኢየሩሳሌም
በመጨረሻው ዘመን እነዚህ ሰባቱ ሀገሮች በሐሳዊው መሲሕ ወይም በውሸተኛው ክርስቶስ ቁጥጥር ሥር የሚውሉ መላውን ዓለም በክህደት ትምህርትና በታላላቅ ምትሐታዊ ተአምራት የሚያስቱና የሚያናውጡ ናቸው።
_______________\\___________
፠ ሰባት ራሶች፦ የተባሉት በመጨረሻው በሐሳዊ መሲህ ዘመን የሚፈጸሙ ሰባቱ ዋና ዋና ኃጢያቶች ናቸው። እነዚህም 7ቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ወይም 7ቱ የኃጢአት ራሶች ይባላሉ!
እነርሱም፦
1) ኃጢያተ አዳም (ወይም የአዳም ኃጢያት
2) ቅትለተ አቤል (የአቤል መገደል)
3) ጥቅመ ሰናዖር (የሰናዖር ህንፃ)
4) ኃጢያተ ሰዶም (የሰዶምና ጎሞራ ሰዎች ኃጢያት)
5) ኃጢያተ እስራኤል (የእስራኤላዊያን ኃጢያት)
6) ቅትለተ ዘካርያስ ካህን (የዘካርያስ ካህን መገደል)
7) ሞተ ወልደ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት) ናቸው።
---------------------------//----------------
------------
1) ኃጢያተ አዳም፦
~~~~~~~~
በምንም የሚያስታችሁ አይኑር ፤ ክህደት ሳይመጣና የአመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያቺ ቀን አትመጣምና።
ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ
ለሁሉም እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ የሚል በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሚቀመጥ ራሱንም እንደ እግዚአብሔር የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው።" 2ኛ ተሰ 2:3-5
----------------------------//----------------
----------------
2) ቅትለተ አቤል፦
~~~~~~~
ማቴ 10:21-36 "ወንድምም ወንድሙን ፣ አባት ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ ፤ ይገድሉዋቸዋልም።"
-----------------------------//----------------
----------------
3) ጥቅመ ሰናዖር፦
~~~~~~~
ዛሬም በእኛ ዘመን የሚያጣላን የዘረኝነት ጉዳይ ነው። አስተውለን ካየነው የቋንቋችን ብዛትና ልዩነት በኃጢአታችን ብዛት እንዳንደማመጥና እንዳንስማማ የተደበላለቀብን እንጂ የጽድቃችን ምልክት አይደለም።
አሁንም በዚህ ሐሳዊ መሲሑ ዘመን ከዚህ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ቴክኖሎጂው ይራቀቃል ፣ ይሰለጥናል። ሰዎችም እጅግ ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ መሳሪያዎች እግዚአብሔር ያለበትን ቦታ ለማግኘት ከጨረቃ አልፈው ይመጥቃሉ ፣ እግዚአብሔርን ግን አያገኙትም ፤ አያዩትም። መዝ 2:4-5 እንዲህ ይላል፦ በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል። እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል ፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። ፣ ትንቢተ አብድዩ 1:1-4 ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰማሁ ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ ፥'ተነሱ ፤ በላይዋም እንነሳና እንውጋት። እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ። አንተ እጅግ ተንቀሃል። በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ እንደሚኖር ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ፤ በልቡም ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል ፥ በልብህ ትዕቢት እጅግ አኩርቶሃል። እንደንስር መጥቀህ ብትወጣ ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን ፥ ከዚያም አወርድሃለሁ' ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በዚህም ጊዜ ሐሳዊው መሲሕ እግዚአብሔር የት አለ? አምላክ ፣ ፈጣሪ እኔ ነኝ" ይላል። ለዚህም ሙት ያስነሳል። እሳት ከሰማይ ያወርዳል ፣ ታላላቅ ተዓምራትን ያሳያል። በዚህም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እያስነገረ በቤተ መቅደስ ይቀመጣል። በዚህን ጊዜ መላው ዓለም አውሬውን ማን ያህለዋል? ማንስ ይመስለዋል? እያለ ይከተዋል ፤ ይሰግዱለታልም። ማቴ 24:23-27 ፣ 2 ተሰ 2:4 ፣ ራዕ 13:4
------------------------//----------------
----------------
4) ኃጢአተ ሰዶም፦
~~~~~~~~
ይህ ግብረ ሰዶም በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ላይ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። በተለይም በሰለጠነው ዓለም ይህ ግብረ ሰዶም ሕጋዊ እንዲሆን ተደርገዋል። በብዙዎችም ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል። ይህ የሚያስረዳን የጊዜው መቃረብና ከዛሬ ሦስት ሺህ ዓመተ በፊት የነበረው ኃጢአት በዚህ ሐሳዊ መሲህ ዘመን እንደ አዲስ መምጣቱንና የግብረሰዶም ኃጢያት በገሀድ እንዲፈጸም መደረጉን ያሳያል። ማቴ 24:15
--------------------------//-------------------------
5) ኃጢያተ እስራኤል፦
~~~~~~~~~~