ንፅፅር @hidayaislam Channel on Telegram

ንፅፅር

@hidayaislam


በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስር በመሆን አስፈላጊና አስተማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶችን፦

- ቪድዬዎችን
- ኦድዬዎችን
- አጫጭር መጣጥፎችን

እያዘጋጀ በሀገርኛ ቋንቋ ያቀርባል፡፡

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል (Amharic)

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የሚሆነው የቴሌግራም ማዕከል ነው። ይህ ማዕከል በአስፈላጊና አስተማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶች ላይ የተገለጸ ነው። በዚህ ስልኮ በሚከበርዋት ቴሌግራም የሚደምም ቪድዬዎችን እና ኦድዬዎችን ይጠቀሙ። ይህን ለመጠቀም መጠጣት ይችላሉ። በሒገርኛ ቋንቋ በመጫን ይተረጋግጡ።

ንፅፅር

22 Dec, 14:44


ጳውሎስ ማነው" "ዛሬ በጣም ገራሚ ትምህርት ነው የተላለፈልን"◍ ኡስታዝ ወሒድ◍ ወንድም ዒምራን◍ ወንድም ሳለህ ◍...
https://youtube.com/watch?v=Hr6XIZ7sMGg&si=T6hH7WeSecSPgS2P

ንፅፅር

16 Dec, 23:10


ሁሴንዝሃራ ለወገናችን እውነት ሲገለጥ መልስ
https://youtube.com/watch?v=7aWdLqYzSbg&si=1Sx9xkAC772qWHjc

ንፅፅር

15 Dec, 14:08


◆ትምህርት◆"እውን ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው? ዘፍጥረት 1፥26    ክፍል 3🎙🎧◍ ኡስታዝ  ወሒድ◍ ወንድም አብ...
https://youtube.com/watch?v=HmzRJ_De--E&si=1SMsBfc0Q_RP9oXG

ንፅፅር

15 Dec, 13:39


አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ዛሬ ማታ ለሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ሁላችሁም እንድትመጡ በታላቅ አክብሮት እና ትህትና እንጠይቃለን።

☪️ለጠቅላላ መረጃ

➡️ኢትዮዽያ⬅️
ዐብዱ ራህማን አሕመድ
👉🏼 251-920-781016

➡️አሜሪካ⬅️
ዚነት ሙሐመድ
👉🏼  240-476-5129

➡️ስውዲን⬅️
ጀሚላህ ሳልህ
👉🏼 +46 70 845 84 91

➡️ጣሊያን እና ለተቀረው አውሮፓ⬅️
በያን ኽሊል
👉🏼 +39 340 261 4829

በተረፈ ኒያዎን ለመላክ ከተመቻቸለዎ ከታች ያለውን አካውንት ይጠቀው፦

➡️ከሁሉም ቦታ⬅️
TAWHID ISLAMIC CALL
SOCIETY
   አካውንት ቁጥር
1000614244597
በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ

➡️አሜሪካ⬅️ 
THMWGO Zelle(USA Only)
240-887-4910

ይህንን የዙም ሊንክ በማስፈንጠር በሰዓቱ ይግቡ፦  https://us02web.zoom.us/j/85067436916?pwd=Lzd6bkRRMWdUcjk1YUNmVkw0elJyUT09   Meeting ID: 850 6743 6916  Passcode: 688219     💞 💞❤️💖💕💕💕

ለኸይር ሥራ እንሽቀዳደም! ሼር ሼር ሼር አድርጉት! 
ባረከላሁ ፊኩም

ንፅፅር

15 Dec, 13:39


ይህንን የዙም ሊንክ በማስፈንጠር በሰዓቱ ይግቡ፦  https://us02web.zoom.us/j/85067436916?pwd=Lzd6bkRRMWdUcjk1YUNmVkw0elJyUT09   Meeting ID: 850 6743 6916  Passcode: 688219     💞 💞❤️💖💕💕💕

ለኸይር ሥራ እንሽቀዳደም! ሼር ሼር ሼር አድርጉት! 
ባረከላሁ ፊኩም

ንፅፅር

13 Dec, 23:19


ቁርአን በማዳምጥ ላይ አትሰላቹ!!
🌸

ንፅፅር

13 Dec, 23:17


◆▮ውይይት▮◆

" የባይብል ግጭቶች"

◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ወንድም አብዱል ከሪም
◍ ወንድም ሳለህ
       🆅🆂
◍ ከወገኖች ጋር

ንፅፅር

10 Dec, 21:07


ኢየሱስን ለምን እናመልከዋለን?አብዱል ከሪምሳለህሁሴን
https://youtube.com/watch?v=onKXO5h9M1k&si=mB36CrhAw4pHCl0x

ንፅፅር

09 Dec, 06:07


ኢየሱስ ፍጡር ነው ወንድም ሳለህ አብዱል ከሪም VS ወገኖች
https://youtube.com/watch?v=Gu-TXRy4Az4&si=bk1NPMt-dkbKQiKa

ንፅፅር

03 Dec, 09:26


◆አምልኮተ ማርያም◆የማእድ ምዕራፍ المائدة 5:116 ላይ እስከመጨረሻው ስሙት◍ በእኅት ዝሃራ ሙስጠፍ
https://youtube.com/watch?v=Wsr4o173_pA&si=v9ILy1ZCpGTM8rwv

ንፅፅር

02 Dec, 14:27


ውይይት ካሌብ እና ብሩክ &አብዱልከሪም ኢየሱስ እራሱን አንድኖ አይሁዶችን እንዳምኑ ማድረግ አልቻለም በቻሌንጁ ተሸ...
https://youtube.com/watch?v=8uZYj_27Vrg&si=tgPMKlJxj3CKIcyn

ንፅፅር

29 Nov, 22:40


🎙🌸 سورة سورة فصلت،..القارئ الشيخ عبد الرحمن العوسي
#القراءة برواية حفص عن عاصم💎

ንፅፅር

29 Nov, 22:35


◆▮ውይይት▮◆

"ነገረ ክርስቶስ?"
"ኢየሱስ አምላክ ነኝ ብሏልን?"
➽ "የኢየሱስ ዘላለማዊ ህልውና"


◍ኡስታዝ ወሒድ
◍ ወንድም ዒምራን
        🆅🆂
◍ወገናችን መዋል
◍ወገናችን ፍቅር
◍ወገናችን ኢካብ

ንፅፅር

28 Nov, 22:48


◆▮ውይይት▮◆

"መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?"
"ጽሐፊው ይታወቃል አታወቅም?"
➽ "የባልብል ግጭቶች"


#Part_❸

◍ ወንድም ጀማል
◍ ወንድም ኢብራሂም
        🆅🆂
◍ ከወገኖች ጋር

ንፅፅር

28 Nov, 22:48


An-Naba' النبأ
: Islam Sobhi إسلام صبحي

ንፅፅር

28 Nov, 19:18


ቁርአን በክርስቲያኖች ተጻፈ ብሎ ለዋሸው መልስ
https://youtube.com/watch?v=qKb3_-jaIlU&si=ggO6oDFEHJGD4GhV

ንፅፅር

27 Nov, 14:12


◆ውይይት◆ኢፍትሃዊ የሆነው ማነው?"እስልምና ላይ ጥያቄ።◍ ወንድም ስሚዝ◍ ወንድም ሳለህ◍ ወንድም ሳለህ   🆅🆂◍ ...
https://youtube.com/watch?v=ARXuI6t11s0&si=EXToA5vbR61-03qQ

ንፅፅር

27 Nov, 11:34


በኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተጻፈው "ክርስቶስ ማነው ?" የተሰኘው መፅሐፍ ወንድማችን 'ጀማል ኸዲር' ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሟል። መፅሐፍ በተለያዩ መክተባዎች የሚገኝ ሲሆን መግዛት የሚፈልግ ሰው ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ወንድም አብዱ: +251920781016
ወንድም ጀማል: +251913463746

ንፅፅር

27 Nov, 11:34


ላችሁም ይህን ፕሮፍይል አድርጋችሁ አስተዋውቁት።

ንፅፅር

25 Nov, 23:21


◆ትምህርት◆"በነብያት የተሰበከው ተውሒድ ወይስ ሥላሴ? " ሥላሴ የተወሰደው ከታወታዊያን ነው ያሳዝናል"◍ ወንድም ...
https://youtube.com/watch?v=Q3Von9Oovk0&si=D1IFMDG3ldpNqdc4

ንፅፅር

23 Nov, 22:06


https://youtu.be/IFnzZFAdkIM?si=FZkN-vRPQvv2jFUd

ንፅፅር

23 Nov, 22:01


ሱረቱል ነጅም 📖🎧

ወንድም ሁሴን አሕመድ🎙

ንፅፅር

23 Nov, 22:01


◆▮ውይይት▮◆

"ሰለ ነብያችን ትንቢትﷺ?"
"ኢስላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች


◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ወንድም ዒምራን
        🆅🆂
◍ ወገናችን ወገኖች
  

ንፅፅር

20 Nov, 23:52


◆▮ውይይት▮◆

"ባይብል እንደት ነብያትን አዋረደ"
"ኢየሱስ እራቁቱን ተሰቀለ ኑህ ሰክሮ እራቁቱን ሆነ " ሉጥ ከልጆቹ ወለደ ሌላው ነብይ በኢትዮጵያ እራቁቱን ይሄድ ነበር የሚሉ እና "ሌሎችም የተዳሰሱበት"።

ክፍል2
◍ ወንድም ዒምራን
◍ወንድም ኢብራሂም
◍ሌሎችም
         🅥🅢
◍ ከብዙ ወገኖች ጋር

ንፅፅር

20 Nov, 23:52


ቁርአን የጨለመን ህይወት በብርሃን የሚሞላ፣
የተሳሳተን የሚገስፅና የሚያመላክት...
ውበቱ ማራኪ ተደምጦ የማይጠገብ
የማያቋርጥ የልብ ብርሃን ነው።


ወንድም አቡ በክር

ንፅፅር

20 Nov, 15:52


ርእስ ነገረ ድህነት በኢስላም እና በክርስትና     እስሚዝ 🎙 አቡ ሳለህ🎙 ...
https://youtube.com/watch?v=2RkSD5E-LZ8&si=jJfulxXjVJH7Ykr8

ንፅፅር

20 Nov, 09:27


https://youtu.be/fSyrEk96OXA?si=B4EXCLz-zOcTq5A5

ንፅፅር

19 Nov, 09:53


ክርስቲያኖች ግን እንዴት ተቀበላችሁት ይህን መጽሐፍ?!
https://youtube.com/watch?v=9fChjuICVaQ&si=1CIApMm0wuGJd3KC

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

16 Nov, 22:17


ኢስላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች መልሶቻችንነብያችንን ጅኒ ደፈሯቸው እያሉ ለሚዋሹት ውሸት መልስ*"የዓንሻ ጋብቻ"ሌሎች...
https://youtube.com/watch?v=YkfLDRgrCDE&si=kXRBD4OhA_F5yGao

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

16 Nov, 16:54


ርእስ ምድርን የተሸከመው ዓሣ            ኢምራን አቡ ሩመይሳ 
https://youtube.com/watch?v=FpAvKFvyNSI&si=kxlwcIgPtZAE3DlM

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

15 Nov, 14:39


ከታዳሚያን ጋር ውይይት ጥያቄ  የካፊሮች ጥያቄ እና መልሶቻቸው ክፍል (3)   ደስ ይላል   ኢምራን     ዝሃራ ...
https://youtube.com/watch?v=5yFFotqPjRo&si=INXFHJjSdq21Nuf8

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

13 Nov, 13:42


አዲስ ቪድዮ You Tube ላይ ተለቋል። ግቡና ተመልከቱ።

የካፊሮች ጥያቄ እና መልሶቻቸው የጅን እና የሸያጢን ልዩነት እና አንድነትመልስ 2    ደስ ይላል   ኢምራን    ...
https://youtube.com/watch?v=YLYvdvXI8SY&si=Pa8QnW2V7EV1s_KR

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

12 Nov, 09:46


ኢየሱስ ፍጡር ነው ውይይት ክርስቲያን ወገኖች ጋር አብዱል ከሪም&eljas
https://youtube.com/watch?v=0LCoXhg7ghk&si=NBmwwGmmDTUdTX_3

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

11 Nov, 23:48


የካፊሮች ጥያቄ እና መልሶቻቸው ክፍል (1)ቂሰቱል ገራኒቅ መልስ 1            ደስ ይላል          ...
https://youtube.com/watch?v=60lIblbybas&si=B31stFB68NmLntLk

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


▯▩ ወይይት ▩▯

"ስቅለት በኢስላም"

◍ ወንድም ኢምራን
          🆅🆂
◍ ወገናችን ሳሚ
◍ ወገናችን ሳለህ
◍ ሌሎችም

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


አልገደሉትም

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

ነጥብ አንድ
"ታሪካዊ ዳራ"
ኢየሱስ ከፈጣሪ የሚናገረውን ትምህርት ተሰቶት ነበር፤ ይህ ትምህርት የፈጣሪ ቃል ነው፤ ከእርሱ የሚሰማው ትምህርት የፈጣሪ ወንጌል ነው፦
ዮሐንስ 17:8 *የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና*፤ እነርሱም ተቀበሉት፥
ዮሐንስ 17:14 እኔ *ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ*፤
ዮሐንስ 14:24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ *የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም*።
ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤
ዮሐንስ 12:49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*።
ሉቃስ 5፥1 ሕዝቡም *የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ* ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤
ማርቆስ 1፥14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ *የእግዚአብሔርን ወንጌል* እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፡ *በወንጌልም እመኑ* እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

"በወንጌልም እመኑ" ሲል ከመለኮት የተሰጠውን ወንጌል ብቻና ብቻ ነው፤ ይህንን ወንጌል ለሃዋርያቱ አስተላልፏል፤ "የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ኦሪገን የተሰጠው ወንጌል የአስራ ሁለቱ ወንጌል ሲሆን ጠፍቷል ይለናል። ጄሮም ደግሞ የአስራ ሁለቱ ወንጌል የሃዋርያት ወንጌል እንሆሃነ ተናግሯል፤ ሐዋርያቱ ለደቀመዛሙርቶታቸው ሲያስተላልፉ ቀደ መዛሙርቶቻቸው ይህንን ወንጌል ከሚሰሙት ታሪክ ጋር ቀላቅለው ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ሞክረዋል፦
ሉቃስ 1:1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።”

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


@slmatawahi

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


አምስተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ሰርቲዩስ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የሰርቲዩስ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል።

ስድስተኛ በ 36 AD ጀምረው ይኖሩ የነበሩት ናዝራውያን ወንጌል አዘጋጅተዋል፤ ይህ የናዝራውያን ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ናዝራውያን የሙሴን ሕግ ይቀበላሉ፤ የኢየሱስን በድንግና መወለድ ይቀበላሉ፣ የሌሎችን ወንጌላት አይቀበሉም።

በግሪክ ኮይኔ የተዘጋጁት ወንጌሎች የትዬለሌ ናቸው፤ እነርሱም፦ የቶማስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የባስሊዲስ ወንጌል፣ የበርናባስ ወንጌል፣ የማርኮናይት ወንጌል፣ የኤቦናይት ወንጌል፣ የሰርቲዩስ ወንጌል፣ የናዝራውያን ወንጌል፣ የጴጥሮስ ወንጌል፣ የያዕቆብ ወንጌል፣ የፊሊጶስ ወንጌል፣ የበርተሎሜዎስ ወንጌል፣ የመቅደላዊት ማርያም ወንጌል፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል፣ የሉቃስ ወንጌል፣ የዮሐንስ ወንጌል የመሳሰሉት ናቸው፣ በቁጥር ወደ 47 ይደርሳሉ፣ ዛሬ የቀኖና ወንጌሎች የተባሉት ኦርጅናል አራቱ ወንጌሎች የለም፣ አራቱ ወንጌላት ተጻፉ የሚባሉት ከ 60-100 AD ሲሆን የእነርሱ የቅጂ ቅጂ ብጥስጣሽ"fragments" እና ደንገሎቹ"papiruses" የሚያሳዩት ግን ከ 200-250 AD ነው፦ የማቴዎስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የማርቆስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የሉቃስ ወንጌል ደንገል 75 የሚባለው በ 250 AD፣ የዮሐንስ ወንጌል ደንገል 46 የሚባለው በ 200 AD ነው፣ ዛሬ ያሉት 5800 ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት ኢየሱስ ካስተማረ ከሶስት መቶ አመት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው፤ ዋና ዋናዎቹ ሳይናቲከስ ጥራዝ በ 330 AD፣ ቫቲካነስ ጥራዝ 350 AD፣ አሌክሳንድሪየስ ጥራዝ 400 AD፣ ኤፍሬማይ ጥራዝ 450 AD ላይ የተዘጋጁ ናቸው።

ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ በ 397 AD የካርቴጅ ጉባኤ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የቅጂዎች ቅጂዎች የሆኑትን አራቱን ወንጌሎች ብቻ ቀኖና"canon" አድርጋ ሌሎችን ወንጌሎች "አፓክራፋ" አድርጋለች፤ "አፓክራፋ" የሚለው ቃል "አፓክራፈስ" ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ድብቅ" ማለት ነው፤ ለዛ ነው አምላካችን አላህ፦ "የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?" ብሎ የተናገረው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

“ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን እንዳለ ይህ አንቀጽ ይጠቁማል፤ በወንጌሎች ታሪካዊ ዳራና ፍሰት ዋቢ መጽሐፍት ያደረኩት የአዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑትን የፕሮፌሰር ባርት ሄርማን መጽሐፍት ነው፦
1. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman
2. The Orthodox Corruption of Scripture: The Effect of Early Christological Controversies on the Text of the New Testament. Oxford University Press, USA. 2011
3. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003

ኢንሻላህ በክፍል ሥስት እንቀጥላለን....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


አልገደሉትም

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

“ታሪክ”history” ያለፈውን ክስተት የሚተርክ የምርምር ጥናት”study” እና አሰሳ”investigation” ነው፤ በታሪክ ጥናት ውስጥ ለታሪክ ምንጭ የሚሆኑ ሁለት መረጃዎች አሉ፣ አንደኛው ትውፊት”tradition” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሥነ-ቅርስ ጥናት”archology” ነው፤ “ትውፊት” ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል የሚተላለፍ ቅብብል ሲሆን “ሥነ-ቅርስ ጥናት” ደግሞ በተለያየ ቁስ ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች አስሶና ቆፍሮ የሚያቀርብ የታሪክ ምንጭ ነው፤ ትውፊት ሆነ ሥነ-ቅርስ በባህል”culture” ላይ እና በስልጣኔ”civilization” ላይ መሰረት ያደረጉ ግምት”speculation” ናቸው፤ ስለ ኢየሱስ ማንነት በዓለማችን ላይ አንድ አይነት አቋም ያለው የታሪክ ፍሰት የለም፤ አንዱ ሃሳዌ መሲህ ሲለው ሌላው አምላክ ሲለው፣ አንዱ የፈጣሪ እረዳት ሲለው ሌላው ብቸኛ የፈጣሪ ልጅ ይለዋል፤ አንዳንዶች እንደውም በታሪክ ላይ አልነበረም የሚሉም አልታጡም፤ ስለ እርሱ አራቱ ወንጌል ላይ የምናየውም ትረካም ቢሆን እርስ በእርሱ የተዛባ እና በቅብብል የተገኘ እንጂ ግህደተ-መለኮት አይደለም፤ ታዲያ ይህ ዓለማችንን ያነጋገረ የፈጣሪ ነብይ ትክክለኛ ማንነቱን መናገር ያለበት እራሱ ላኪው ፈጣሪ ነው፤ ኢየሱስን የላከው አላህ ስለ ዒሳ ሲናገር፦
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ *ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

“የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለትም “የሚከራከሩበት” የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት፤ ይህ “መከራከር” የሚለው ቃል “ሚርያህ” مِرْيَة ሲሆን “ጭቅጭቅ” “ንትርክ” ክርክር” ማለት ነው፤ በዒሳ ጉዳይ ሰዎች በመወዛገብ መጨቃጨቃቸውን፣ መነታረካቸውን እና መከራከራቸውን ያሳያል፤ ዒሳ ካረገበ በኃላ ቁርኣን እስከሚወርድበት ጊዜ አራጥቃና በጥራቃ እየተባባሉ መቅኖ ሲያሳጣቸው እንደነበር ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ አስፍሮታል።
“ያ“ በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው” የሚል ነው፤ “እርሱ” በሚለው ቃል ላይ “በ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያመለክተው ስለ ዒሳ አላህ የነገረን ንግግር ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው ማለት ነው፤ “በ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፊ” فِي  ሲሆን “ስለ”about” ማለት ነው፦ That is Jesus, son of Mary. ˹And this is˺ a word of truth, “about” which they dispute.

“ቀሰስ” قَصَص የሚለው ቃል “ቀሰሰ” قصص “ተረከ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ትረካ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና ሁሉን የሚያውቅ ስለሆነ ያለፈውን ክስተት “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት በነብያችን”ﷺ” ላይ ይተርካል፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ስለዚህ ከመልክተኞች ታሪክ አንዱ የዒሳ ታሪክ ስለሆነ ይህ ታሪክ ሲከሰት ነብያችን”ﷺ” በህልውና ደረጃ ስላልነበሩ ሁሉን ዐዋቂው አምላክ ለነብያችን”ﷺ” ይህንን ታሪክ ያወርዳል፤ ይህ ስለ ዒሳ ትረካ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፦
3፥62 *”ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው”*፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

ሰዎች በዒሳ ጉዳይ ከሚወዛገቡበት፣ ከሚጨቃጨቁበት፣ ከሚነታረኩበት፣ ከሚከራከሩበት ነጥብ አንዱ ዒሳ ተሰቅሏል ወይስ አልተሰቀለም ነው፤ አምላካችን አላህ፦ ዒሳን አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን የገደሉትና የሰቀሉት መስሏቸዋል፦
4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

"እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም" ይህንን መለያየት አስመልክቶ ስለ ወንጌላት ታሪካዊ ዳራና ፍሰት፤ በቁርኣን እና በሐዲስ ያለውን እሳቤ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እንቀጥላለን......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


ለምሳሌ፦
አንደኛ በ 50-138 AD የማቴዎስ ተማሪ የነበረው ባስሊዲስ በ 117 AD ላይ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የቀሬናን ስምዖንን እንደሰቀሉት ይናገራል፤ ይህንን ወንጌል በኃላ ላይ የመጡት አበው በ 130-200 AD ይኖር የነበረ ኢራኒየስ፣ በ 150-215 AD ይኖር የነበረ የአሌክሳንድሪያው ክሌመንት ተቃወሙት፤ ብዙ ጊዜ ከባስሊዲስ ወንጌል ላይ 260-340 AD ይኖር የነበረው የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይጠቅስ ነበረ።

ሁለተኛ በ 60-135 AD ይኖር የነበረው በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል፤ በሳይናቲከስ ኮዴክስ ላይ ፓሊካርፕ ለፊሊጵስዩስ በጻፈው ፓሊላርፕ 1፥1 ቀጥሎ የበርናባስ መልእክት 5፥7 ይቀጥልል። እዚህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሰቀሉት ይናገራል።

ሦስተኛ በ 85-160 AD ይኖር የነበረው የሲኖፕ ማርኮይን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የማርኮናይት ወንጌል በ 1740 AD ከተገኙት የሙራቶሪያን ብጥስጣሽ"Muratorian fragment" አንዱ ነው፤ የካርቴጅ ጉባኤ ከማርኮናይት ግሩፕ ውስጥ የዮሐንስን አፓልካሊፕስ"ራእይ" ተቀብላ በእነርሱ የነበረውን የጳውሎስን አፓልካሊፕስ፣ የጴጥሮስን አፓልካሊፕስ፣ የቶማስን አፓልካሊፕስ፣ የእስጢፋኖስን አፓልካሊፕስ፣ የያዕቆብን አፓልካሊፕስ ደብቃቸዋለች።
በማርኮናይት ወንጌል ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የሮማ ወታደር እንደሰቀሉት ይናገራል።

አራተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ኤቦን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የኤቦናይት ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። በ 347-420 AD ይኖር የነበረው ጄሮም ኤቦን በዮሐንስ ዘመን ይኖር እንደነበረ መስክሯል። ነገር ግን ኤቦንን በ 36-115 AD ይኖር የነበረው የቆሮጵሮሱ ኤጵፋኒየስ አውግዞቷል።

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

04 May, 21:37


"እንኳን አደረሳችሁ?"

◍ እኅት ዘሀራ

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

03 May, 09:46


سورة الكهف كاملة تلاوة هادئة وراحة نفسية في يوم الجمعة تريح الأعصاب محمد
ديبيروف Surah al kahf
አዳምጡ

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


ሥነ-ጋብቻ ጥናትMatrimony" እንደሚያትተው አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ለመድረስ ከሚታዩ ምልክቶች አንዱ ሐይድ ማየት ነው። "ሐይድ" حَيْض ማለት "የወር አበባ" ማለት ነው፥ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ደግሞ "ሓኢድ" حَائِض ትባላለች። አንዲት እንስት የወር አበባ ልታይበት የምትችለው አማካኝ ዕድሜ ከ 12-13 ሲሆን እንደየ እንስቷ ሁኔታ ከ 12 በታች እስከ 9 ቶሎ ሊመጣ አሊያም ከ 13 በላይ እስከ 16 ሊዘገይ ይችላል። በኢሥላማዊ መዛግብትም አጥ-ጦበሪን ጨምሮ እንደተዘገበው የአንዲት እንስት የወር አበባ የምታየበት ትንሹ እድሜ ዘጠኝ መሆኑ እንዲህ ተዘግቧል፦
አልካፊ ፊ ፊቅህ ኢብነ ሀንበል፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 74፣ ሸርህ አል– ዑምዳ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 480
*"ትንሹ የሴት ልጅ የወር አበባ የምታይበት እድሜ ዘጠኝ ዓመት ነው"*።

የጋብቻ ጊዜ በጥንታዊ ጊዜ፣ በዘመናዊ ጊዜ፣ በድኅረ-ዘመናዊ ጊዜ ከትውልድ ወደ ትውልድ፥ ከባህል ወደ ባህል ይለያያል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦
*“ለጋብቻ ትንሹ የዕድሜ ገደብ በፊት 12 ዓመት አልያም ከዚያም ያነሰ የነበረው ሲሻሻል እና ከፍ ሲል ቆይቶ በአብዛኛው አገሮች አሁን በ15 እና በ21 ዕድሜ መካከል ሆኗል"*፡፡ Encyclopedia Britannica 2006 page 171.
የጋብቻ ጥናት ምሁር ብራውን ዮናታን፦ *"አብዛኛው የጋብቻ ምሁራን ዓኢሻህ በዘጠኝ ዓመቷ ለዐቅመ-ሔዋን ደርሳለች ብለዋል"*።
Brown, Jonathan (2014). Misquoting Muhammad: The Challenge and Choices of Interpreting the Prophet's Legacy. Oneworld Publications. pp. 143–4.

ጋብቻ ማለት በሁለት ተቃራኒ መካከል ያለ ስምምነት ነው፥ አንድ ተባእት አንዲትን እንስት አስገድዶ ማግባት ሐላል አይደለም። ነቢያችንም”ﷺ” ዓኢሻን ሊደርሱባት ሲሉ ፈቃደኝነቷን ጠይቀዋታል፦
4፥19 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! *”ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ ለእናንተ አይፈቀድም”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا
አል-ሙሥተድረክ አል-ሐኪም ጥራዝ 4 ገጽ 11
ሰዒድ ኢብን ከሲር ከአባቱ አባቱ ከዓኢሻህ "ረ. ዐ." እንዳስተላለፈው፦ *የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ለአዒሻ እንዲህ አሏት፦ *“በዱንያህ ሆነ በአኺራ የእኔ ባለቤት መሆንን አትፈልጊምን? እርሷም፦ “ወሏሂ እፈልጋለሁ እንጂ” አለች፡፡ እርሳቸውም፦ "አንቺ በዱንያህ ሆነ በአኺራም የእኔ ባለቤቴ ነሽ" አሏት"*፡፡ عن سَعِيدُ بْنُ كَثِيرٍ عَنْ أَبِيهِ ، قَالَ حَدَّثَتْنَا عَائِشَةُ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قال لعائشة -رضي الله عنها-: «أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ تَكُونِي زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ؟» قُلْتُ: بَلَى وَاللَّهِ، قَالَ: «فَأَنْتِ زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ».

ሚሽነሪዎች ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" መዳሯ የሚያንገበግባቸው፣ ልወቅልሽ እና ልቆርቆርልሽ የሚሏት አስብቶ አራጅ እና ቅቤ አንጓች ሆነው እንጂ ለእርሷ አስበው አይደለም። እርሷ ጋብቻውን ወዳ እና ፈቅዳ የገባችበት ጉዳይ ነው፥ ለነቢያችን"ﷺ" ልዩ ፍቅር የነበራት ሴት ነበረች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 43
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በማንም ሴት እንደ ኸዲጃህ ቅናት ተሰምቶኝ ዐያውቅም፥ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ብዙ ጊዜ ያነሷት ነበር። እኔን ያገቡኝ እርሷ በሞተች በሦስት ዓመቷ ነው፥ ከጌታቸው ዐዘ ወጀል ወይንም ከጂብሪል"ዐ.ሠ." እርሷ በጀነት ጨፌ ሥርፋ እንዳላት ይበሰሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ مَا غِرْتُ عَلَى امْرَأَةٍ مَا غِرْتُ عَلَى خَدِيجَةَ، مِنْ كَثْرَةِ ذِكْرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِيَّاهَا‏.‏ قَالَتْ وَتَزَوَّجَنِي بَعْدَهَا بِثَلاَثِ سِنِينَ، وَأَمَرَهُ رَبُّهُ عَزَّ وَجَلَّ أَوْ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ أَنْ يُبَشِّرَهَا بِبَيْتٍ فِي الْجَنَّةِ مِنْ قَصَبٍ‏.‏

በሞተችው ሚስታቸው በኸዲጃህ የምትቀናው ፍቅር ካልሆነ ምንድን ነው? ዓኢሻህ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የነበራትን መስተጋብር ለምእመናን ጋብቻ አርአያ እንዲሆነ ብዙ ጊዜ ታነሳለች። ለምሳሌ አንዲት እንስት ከባሏ ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ውስጥ መታጠብ እንደሚችሉ ለማስተማር እርሷ ከባለቤቷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ትታጠብ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 3
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" አል-ፈረቅ በሚባል አንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ قَدَحٍ يُقَالُ لَهُ الْفَرَقُ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" ከጀናባህ በኃላ በአንድ ገንዳ እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ جَنَابَةٍ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 14
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" በአንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር፥ እጆቻችንን በገንዳ ውስጥ ይተካኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ تَخْتَلِفُ أَيْدِينَا فِيهِ‏.‏

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


• من سورة ق .. 🌸 ..° } ..•

@slmatawahi

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መነካካት፣ መብላት እና መጠጣት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ትነካካ፣ ትበላ እና ትጠጣ ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 4
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” እኔ የወር አበባ ላይ እያለሁኝ ጭኔ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር"*። أَنَّ عَائِشَةَ حَدَّثَتْهَا أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَّكِئُ فِي حَجْرِي وَأَنَا حَائِضٌ، ثُمَّ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 10
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አጥብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْسِلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 279
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አበጥር ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 686
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ በወር አበባ ጊዜ አጥንት እግጥ ነበር፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስጋውን ከእኔ ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸው በማሳረፍ ይግጡ ነበር። እንደዚሁም የወር አበባ ላይ እያለሁ በእቃ ስጠጣ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እቃውን ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸውን በማሳረፍ ይጠጡ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَتَعَرَّقُ الْعَظْمَ وَأَنَا حَائِضٌ، فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَشْرَبُ مِنَ الإِنَاءِ فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَنَا حَائِضٌ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 675
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኔ፦ *"ከመሥጂድ ሰሌኑን አምጪልኝ" አሉኝ፥ እርሷም፦ "በወር አበባ ላይ ነኝ" አልኩኝ" አለች። እርሳቸውም፦ "የወር አበባሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ አይደለም" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ نَاوِلِينِي الْخُمْرَةَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏"‏ ‏.‏ فَقُلْتُ إِنِّي حَائِضٌ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ لَيْسَتْ حَيْضَتُكِ فِي يَدِكِ ‏

አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በፆም ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር መነካካት፣ መሳሳም እና አብሮ መተኛት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በፆም ጊዜ ትነካካ፣ ትሳሳም ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 89
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በፆም ወር ውስጥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ይስሟት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ فِي شَهْرِ الصَّوْمِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 79
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ከሚስታቸውን አንዷን(ዓኢሻህን) ይስሙ ነበር፥ ከዚያም ደስ ይላት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ إِحْدَى نِسَائِهِ وَهُوَ صَائِمٌ ‏.‏ ثُمَّ تَضْحَكُ ‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 83
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ሚስታቸውን ይስሙ ነበር፥ ከእናንተ ይልቅ እሳቸው ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُقَبِّلُ وَهُوَ صَائِمٌ وَكَانَ أَمْلَكَكُمْ لإِرْبِهِ

"ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር" የሚለው ኃይለ-ቃል በፆም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ክልክል መሆኑን ለማሳየት ነው። አንዲት እንስት ከባሏ ጋር የጨዋታ ጊዜ ሊኖራት እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የጨዋታ ጊዜ እንደነበራት ትናገራለች፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 102
አቢ ሠለማህ ከዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደዘገበው፦ "ዓኢሻህ ከነቢዩ"ﷺ" ጋር በጉዞ ላይ ሳለች እንዲህም አለች፦ *"ከነቢዩ"ﷺ" ጋር ሩጫ ተወዳደሩኝ እኔም አሸነፍኳቸው፥ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር፡፡ ከወፈርኩ በኃላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ "ብድር መለስኩኝ"*። وَعَنْ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي فَقَالَ ‏ "‏ هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ ‏"‏ ‏.‏

እውነት ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ዓኢሻህ በነቢያችን"ﷺ" የሥነ-ልቦና እና የተክለ-ሰውነት ጥቃት ደርሶባት ቢሆን ከላይ ያለውን የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት ጊዜ ለአማንያን ይጠቅማል ብላ ትተርክ ነበርን? ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የነበሩ የኢሥላም ጠላት ነቢያችንን"ﷺ"፦ "ጠንቋይ፣ ደጋሚ፣ መተተኛ፣ ዕብድ" ወዘተ ሲሉ በዓኢሻህ እና በእሳቸው መካከል የነበረውን ጋብቻ ለምን አልተቹም? እርሷ ስለ ጋብቻዋ በአሉታዊ መልኩ አንድም ቀን አምርራና አማራ የማታውቀውን ሚሽነሪዎች ዙሪያ ገቡን ሳያዩ ኢሥላምን ለማጠልሸት እና ሙሥሊሙን ለማብሸቅ "አስገድዶ መድፈር" የሚሉት የአእምሮ ስንኩላን ስለሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ነገር ግን አላህም ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


ሳኡድዎች ይህን መጽሐፍ
የምትፈልጉ በቴሌ ግራም አናግሩኝ

https://t.me/Zhara_mustefa

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


▯▩ ወይይት ▩▯

"መጀመሪያ ቃል ነበረ"

◍ ወንድም እስሚዝ
🆅🆂
◍ ወገናችን ሳዳም
◍ ወገናችን ሣምሪ

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

01 May, 22:35


የዓኢሻህ"ረ.ዐ." ትዳር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

አንዲት እንስት ወጣት ናት፥ በሙሥሊሞች ዘንድ በአውንታዊ መልኩ በኢሥላም ታሪክ ላይ አሻራዋን ካስተቀመጡ እና ጉልህ ሚና ከተጫወቱት ሰዎች አንዷ ናት። ይህቺ ወጣት ከነቢያችን"ﷺ" ሰምታ ስለ ነቢያችን"ﷺ" ሕይወትና አኗኗር፣ ስለ ውርስ፣ ስለ ጋብቻ፣ ስለ መጨረሻው ዘመን ትምህርት ወዘተ 2,210 የሚደርሱ ሐዲሳትን ተርካለች፥ ቁርኣን የምእመናት እናቶች ከሚላቸው አንዷ ናት፦
33፥6 *"ነቢዩ በምእምናን ከራሳቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፥ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው"*፡፡ النَّبِيُّ أَوْلَىٰ بِالْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَأَزْوَاجُهُ أُمَّهَاتُهُمْ

ይህችም ወጣት ሴት "ኡመል ሙእሚኒን" أُمِّ الْمُؤْمِنِين ማለትም "የምእመናን እናት" በሚል ማዕረግ የምትጠራ ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ናት፥ በአንድ ወቅት ዝሙት ሠርታለች ተብላ የሐሰት ክስ ቀርቦባት አምላካችን አሏህ ሡረቱ አን-ኑር 24፥11-20 ያለውን አንቀጽ ስለ ንጽህናዋ አውርዷል፦
24፥15 *"በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር*፡፡ إِذْ تَلَقَّوْنَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُم مَّا لَيْسَ لَكُم بِهِ عِلْمٌ وَتَحْسَبُونَهُ هَيِّنًا وَهُوَ عِندَ اللَّهِ عَظِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 447
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ዓኢሻህ ሆይ አብሽሪ! አሏህ ስለ ንጽህናሽ ወሕይ አውርዷል፥ ከዚያም ለእርሷ የቁርኣኑን አንቀጽ ቀሩላት። ወላጆቿም፦ "የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" ግንባር ሳሚ!" አሏት፥ እርሷም፦ "ለእናንተ ሳይሆን ለአሏህ ምስጋና ይሁን!" አለች"*። أَنَّ عَائِشَةَ، رضى الله عنها قَالَتْ ثُمَّ قَالَ تَعْنِي النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَبْشِرِي يَا عَائِشَةُ فَإِنَّ اللَّهَ قَدْ أَنْزَلَ عُذْرَكِ ‏"‏ ‏.‏ وَقَرَأَ عَلَيْهَا الْقُرْآنَ فَقَالَ أَبَوَاىَ قُومِي فَقَبِّلِي رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏.‏ فَقَالَتْ أَحْمَدُ اللَّهَ لاَ إِيَّاكُمَا ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 188
አቢ ኢብኑ መለይካህ እንደተረከው፦ *"ዓኢሻህ፦ "በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ" የሚለውን አንቀጽ ትቀራ ነበር፥ "አል-ወልቅ" ቅጥፈት ነው" ትል ነበር። አቢ ኢብኑ መለይካህም፦ "ይህን አንቀጽ ስለ እርሷ እንደሚናገር ከማንም ይልቅ ታውቅ ነበር" አለ"*። حَدَّثَنِي يَحْيَى، حَدَّثَنَا وَكِيعٌ، عَنْ نَافِعِ بْنِ عُمَرَ، عَنِ ابْنِ أَبِي مُلَيْكَةَ، عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقْرَأُ ‏{‏إِذْ تَلِقُونَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ‏}‏ وَتَقُولُ الْوَلْقُ الْكَذِبُ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي مُلَيْكَةَ وَكَانَتْ أَعْلَمَ مِنْ غَيْرِهَا بِذَلِكَ لأَنَّهُ نَزَلَ فِيهَا‏.‏

ዓኢሻህ"ረ.ዐ." አባቷ አቡበከር አስ-ሲዲቅ እናቷ ኡሙ ሩማን ሲሆኑ የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ናቸው፥ ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንድትሆን ለቤተሰቦቿ አሳቡን ያመጣችው የነቢያችን"ﷺ" ሴት ባልደረባ የነበረችው ኸውላህ ቢንት ሐኪም"ረ.ዐ." ናት። ቅሉ ግን ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንደምትሆን ነቢያችን"ﷺ" በሕልማቸው ሁለት ጊዜ አይተዋታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሕልሜ ሁለት ጊዜ አይቼሻለው፥ አንድ ሰው(ጂብሪል) በሐር ጨርቅ ተሸክሞሽ፦ "ይህቺ የአንተ ሚስት ናት" አለኝ። ስገልጥ እነሆ አንቺ ነበርሽ። እኔም ዓኢሻህ ለራሴ፦ "ይህ ሕልም ከአሏህ ከሆነ ይፈጸማል" አልኩኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أُرِيتُكِ فِي الْمَنَامِ مَرَّتَيْنِ، إِذَا رَجُلٌ يَحْمِلُكِ فِي سَرَقَةِ حَرِيرٍ فَيَقُولُ هَذِهِ امْرَأَتُكَ، فَأَكْشِفُهَا فَإِذَا هِيَ أَنْتِ، فَأَقُولُ إِنْ يَكُنْ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ يُمْضِهِ

ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ-ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

30 Apr, 23:06


♡ ቲላዋ ♡ ……………🍃

@slmatawahi

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

30 Apr, 23:06


ሁሉን ቻይ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥284 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አንድ አምላክነት ያለው ማንነት በራሱ ሁሉን ነገር ማድረግ ይችላል። ለምሳሌ አምላካችን አሏህ ሁሉን ነገር በማድረግ ቻይ ነው፦
2፥284 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በባይብልም ቢሆን የኢየሱስ ፈጣሪ እና አምላክ፦ "በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?" በማለት ይጠይቃል፥ መልሱ ለፈጣሪ የሚሳነው ምንም ነገር የለም፦
ኤርሚያስ 32፥28 በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?
ሉቃስ 1፥37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
ኢዮብ 42፥2 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።

ቅሉ ግን ኢየሱስ አብ ሲያደርግ እያየ የሚያደርግ እንጂ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፦
ዮሐንስ 5፥19-20 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፥ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።

"ያ" የሚለውን የሩቅ አመልካችን ተውላጠ ስም አብ ለኢየሱስ ለማሳየት የሚያደርገውን ሥራ ያመላክታል፥ "ይህን" የሚለው የቅርብ አመልካችን ተውላጠ ስም "ያ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ሲሆን አብ ለወልድ እንዲያደርግ የሚያሳየውን ሥራ ያመላክታል። አንድ አምላክነት ያለው ማንነት ምን መሥራት እንዳለበት ሌላ ማንነት እንዴት ያሳየዋል? ኢየሱስ የሚያደርገውን ሁሉ አብ እያሳየው ብቻ ነው፥ "ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል" ሲል የሚሠራውን ሥራ ፈጣሪ እያሳየው ያደርጋል ማለት ነው። ወልድ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አብ ያሳየዋል ማለት ወልድ ሙታንን እንዲያስነሳ፣ ለምጻም እንዲያነጻ፣ ሽባ እንዲተረትር መመሪያ፣ ሥልጣን እና ኃይል ይሰጠዋል ማለት ነው፥ ለምሳሌ ፈሪሳውያን በሰይጧን ዘንድ ያዩት ያደርጋሉ ማለት ሰይጧን መመሪያ እየሰጣቸው ያደርጋሉ ማለት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም በአብ ዘንድ ያየውን ያደርጋል ማለት አብ መመሪያ እየሰጠው ያደርጋል ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።

ኢየሱስ ተአምር እንዲሠራ የጌታ ኃይል ሆኖሎት እንጂ ከራሱ አንዳች ሊያደርግ አይቻለውም። ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ ካልቻለ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም፦
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ዮሐንስ 5፥30 እኔ "ከ"-"ራሴ" አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።

"እኔ" የሚለው ባለቤት "እኔነትን" እንጂ ስጋን አያሳይም፥ ስጋ ብቻውን ማንነት ስላልሆነ "እኔ" አይልም። ነገር ግን ኢየሱስ ከምንነቱ ምንም ማድረግ ስለማይችል "ራሴ" የሚል ድርብ ተውላጠ ስም ይጠቀማል። ጭራሽ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ በፈጣሪ ስም ሲሆን እርሱ ነቢይ ስለመሆኑ የሚመሰክር ነው፦
ዮሐንስ 10፥25 እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል።
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህ የማደርገው ሥራ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።

ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ ሁሉ መልእክተኛ ስለመሆኑ ምስክር እንዲሆን በስጦታ ያገኘው ስለሆነ "አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ" በማለት እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤

"የሰጠኸኝን ሥራ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረውን ሥራ ሙት ማስነሳት፣ ሽባ መተርተር፣ ዕውር ማብራት ወዘተ በእርሱ የሚያምን ሰው ሊያደርገው ይችላል፥ እረ ኢየሱስ ካደረገው በላይ የሚበልጥ ያደርጋል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፥ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።

እውነት ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ቢሆን ኖሮ ሁሉን የሚችል አምላክ ሊያደርግ የሚችለውን ሰው ሊያደርግ ይችላልን? ከሁሉን የሚችል አምላክ በላይ የሚበልጥ ሥራ ሊሠራ ይችላልን? ስለዚህ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ የአምላክነት ሥራ ሳይሆን በጸጋ እና በስጦታ እንዲሥራ የታዘዘው ሥራ ነው፥ ከፈጣሪ እያየ የሚሠራ ማንነት እራሱ ፈጣሪ ከሆነ አንዱ የሚያሳይ ሁለተኛው እያየ የሚኮርጅ ሁለት ፈጣሪ ይሆን ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ፍጡር ብቻ ነው።

ክርስቲያኖች ሆይ! የኢየሱስን ፈጣሪ እና አምላክ አንዱን አምላክ እንድታመልኩ ወደ ኢሥላም እንጠራችኃለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

30 Apr, 23:06


●▯ውይይት ▯●

- "የዮሐንስ ራዕይ"
- "ኢየሱስ ፍጡር ነው"
- "ባይብል ተበርዟል"


◍ ወንድም እስሚዝ
🆅🆂
◍ ወገናችን ሐና

ሌሎችም የተሳተፉበት

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

29 Apr, 20:24


- "ቁርዓን ከአላህ ለመውረዱ ማስረጃ"
- "ሰይጣን በክርስትና አስተምህሮ"
- "የገድላት ቅሌት"


◍ ወንድም ሳላህ
◍ ወንድም አቡ ሳላህ
◍ እኅት ዛህራ

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

29 Apr, 20:24


እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

«እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም #ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ #የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ፡፡

@slmatawahi

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

29 Apr, 20:24


ይገደል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ በሥነ-ኃጢአት ጥናት”hamartiology” ውስጥ “ኃጢአት” ማለት “አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ” ማለት ነው። ኃጢአት “ከባኢሩ አዝ-ዘንብ” كَبَائِر الْذَنب እና “ሶጋኢሩ አዝ-ዘንብ” صَغَائِر الْذَنب ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፥ “ከባኢር” كَبَائِر ማለት “ዐብይ” “ታላቅ” ማለት ሲሆን “ሶጋኢር” صَغَائِر ማለት ደግሞ “ንዑስ” “ትንሽ” ማለት ነው። ከዐበይት ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነፍስን ያለ ሕግ መግደል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

“ቀትሉ አን-ነፍሥ” قَتْلُ النَّفْس የሚለው ቃል ይሰመርበት! አምላካችን አሏህ ነፍስን መግደል ሐራም አርጓል፦
17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ ልብ አድርግ! “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው። "ሕግ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሐቅ" حَقِّ ሲሆን በሐቅ፣ በእውነት፣ በፍትሕ ነፍስ ሊገደል ይችላል። ለምሳሌ በባይብል የአምላክን ስም የሰደበ እንዲገደል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
ዘሌዋውያን 24፥16 የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"።

"ይገደል" ብሎ ትእዛዝ የሰጠው ሙሴ ሳይሆን የሙሴ አምላክ እንደሆነ ዐውደ ንባቡ ላይ፦ "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው" የሚል ቃል አለ፦
ዘሌዋውያን 24፥1 "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው"።

አንድ ሰው ከአንዱ አምላክ ውጪ ሌላ ማንነትን "እናምልክ" ብሎ ቢያስተምርህ ፈጽመህ "ግደለው" የሚል መመሪያ አለ፦
ዘዳግም 13፥6-9 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት "እናምልክ" ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ "ግደለው"፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።

አስመላኪው ብቻ ሳይሆን ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትን የሚሠዋ ይገደላል፥ እንዲሁ የእስራኤልንም አምላክ የማይፈልግ ይገደል ዘንድ መሐላ አለ፦
ዘጸአት 22፥20 ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ "ይጥፋ"።
ዘዳግም 17፥3 ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥
ዘዳግም 17፥5 ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።
2 ዜና 15፥13 የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ።

የጥንቆላ አምልኮ ከአንድ አምላክ ውጪ ስለሆነ "ጠንቋዮች ፈጽመው ይገደሉ" የሚል ትእዛዝ አለ፦
ዘሌዋውያን 20፥27 ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

በተጨማሪም አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ "ይገደል" ተብሏል፦
ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"።

ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ "ይገደል" ተብሏል፦
ዘሌዋውያን 20፥15 ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ "ይገደል"፥ እንስሳይቱንም ግደሉአት።

ግብረ ሰዶም የሚያደርጉ "ይገደሉ" ተብሏል፦
ዘሌዋውያን 20፥13 ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

ከላይ "ይገደል" ወይም "ይገደሉ" የሚለው ፈጣሪ እንደሆነ ልብ አድርግ! በአዲስ ኪዳንም ቢሆን እነዚህ ሕግጋት አልተሻሩም፦
ማቴዎስ 5፥17-18 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት አትሻርም። የፈጣሪን ሕግ የማይረባ እና ደካማ ብሎ በመንቀፍ "ተሽራለች" ያለው ጳውሎስ ነው፦
ዕብራውያን 7፥18 ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ "ተሽራለች"።

የጳውሎስ ትክክለኛ ስሙ "ሳውል" ሲሆን በኃላ ላይ ለራሱ ያወጣው ስም "ጳውሎስ" ነው፥ "ጳውሎስ" ማለት ትርጉሙ "ታናሽ" ማለት ነው። እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም ተሽሯል ብሎ የሚያስተምር ሳውል በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ነው፦
ማቴዎስ 5፥19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ይባላል።

ስለዚህ የተቆላበት እያለ የተጋፈበትን መጠየቅ አግባብ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

4,801

subscribers

206

photos

96

videos