፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ @amstkilogg Channel on Telegram

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

@amstkilogg


በኢ/ኦ/ተ/ቤ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማዕከል
መርሐ ግብራት ፥
#የቅዱሳን_ታሪክ
#መጽሐፍ_ትረካ
#መጽሐፍ_ጥቆማ
#ብሒላተ_አበው

https://t.me/amstkilogbigubae

በዩትዩብ ቤተሰብ እንሁን ☟☟☟https://www.youtube.com/@5kilogbigubae

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ (Amharic)

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ የሰነዘር ቤተሰብ በመርሐ ግብራት ፣ ፅዋት እና መዝገበ ታሪኮችን በማዕከል የተመለከተ የትምህርት እና መጽሐፍ መረከቦችን እንዲሁም ሌሎች ተከታይ የባሕል ምለሶችን እና አስተያየቶችን በቀላሉ ለመስራት ይችላሉ። የሚባለው የቤተሰብ በአበው መገልገያ እና መጽሐፍ ትረካቶችን ለመግባት፣ የብሒላተን አበውን የመጽሐፍ ጥቆማዎችን ወደ ዩትዩብ ቤተሰብ ያስገቡ። እሱም በቀላሉ ምንም ባል፣ በአቦታ እና አስተያየቶችን ለመስራት ይችላሉ። ማለትም እንደተከተለው በተመለከተ መረጃ ተጠቃሚነትንና አብማጥርነትን እንደሚያሳይ አስተዋዕል ነው።

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 09:03


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🙏🏻🙏🏻🙏🏻

ልዩ የአንድነት ጉባኤ ፦ በእንተ መዝሙር

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ዛሬ ሐሙስ (ህዳር 12) የአንድነት ጉባኤ የሚኖረን ይሆናል።

ቦታ ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ 3ተኛ ፎቅ
ሰዓት ፦ ከ11፡20 ጀምሮ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን 🙏🏻
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

19 Nov, 19:22


በብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ሽኖዳ ፓትርያርክ  ዘግብጽ👇👇👇
           

     ✍️  የንስሐ ሕይወት ✍️
ክፍል 4

((  የንስሐ ሂደት እና አፈጻጸም ))

✍️ ➤ ንስሐ ሦስት የአፈጻጸም ደረጃዎች አሉት ።
                እነርሱም ፦
👉✍️ሀ ✓የንስሐ መጀመሪያ ደረጃ ፣
የንስሐ የመጀመሪያ ደረጃው ኃጢአትን መተው ብቻ ሳይሆን ንስሐ ለመግባት መፈለግ ወይም ማሰብ ነው ።
ይሄ ኃጢአትን ከመተው የሚቀድም ነው ። ሰዎች ንስሐ ለመግባት ባልፈለጉ እና ባላሰቡ መጠን በኃጢአት  እየተደሰቱ ኃጢአትን እየሠሩ ይኖራሉ ። በእነርሱ አመለካከት የያዙት የኃጢአት ኑሯቸው መልካም ስለሚመስላቸው አይለወጡም ። ስለዚህ ንስሐ ለመግባት ማሰብና መፈለግ የንስሐ መጀመሪያው ደረጃ ነው  ።

        👉✍️   ለ  ፦    ሁለተኛው ደረጃ ፦
በንስሐ ሂደት ውስጥ ሁለተኛው ደረጃ ኃጢአትን መተው ነው ።
ኃጢአትን መተው ሲባል ኃጢአትን ከሕሊናና ከልቡና በፍጹም ማጥፋት ነው ። ይህም ኃጢአትን ከማሰብ መለየት ማለት ነው ።
ምክንያቱም ሰው በተግባር ኃጢአትን ባይሰራም በልቡናው የኃጢአት ፍቅር ቢኖረው ኃጢአትም በልቡናው የሚመላለስ ከሆነ ይህ ሰው ንስሐ ገብቷል ማለት አይቻልም ። የዚህ አይነቱ ሰው ኃጢአትን የተወው ወይም ኃጢአት ከመሥራት የተቆጠበው የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ ብሎ  ነው  እንጂ ኃጢአትን ጠልቶ አይደለምና በልቡናው የኃጢአት ፍቅር ቅሪት እያለ ኃጢአትን ትቷልና ንስሐ ገብቷል ማለት አይቻልም ።
ስለዚህ ፀፀቱ ወይም ንስሐው ልቡናው ከኃጢአት እስኪነጻ ድረስ መሆን አለበት ከዚህ አንጻር ኃጢአትን መተው የንስሐ ሁለተኛ ደረጃ ነው ።

       👉✍️ ሐ ሦስተኛ ደረጃ

👉 የንስሐ የመጨረሻው ደረጃ ኃጢአት መተው ነው ።ይሄም ኃጢአትን በፍጹም ልብ መጥላት እና አለማሰብ ባሕርይን ለኃጢአት አለማስገዛት ነው ።ይሄም ደግሞ የፍጹምነት ደረጃ ነው ። ሰው ኃጢአትን ከልቡ ካስወገደና ፍጹም ካላሰባት ከፍጹምነት ደረጃ ደርሷልና ንጹሕ ነው ይባላል ።

ይቀጥላል...

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 04:54


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScs-7PCUfJn-vCBhBkvJ7DwA0snrmkeUWDtWgZoJfomQb5WsA/viewform?usp=sf_link

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️

" እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለኹ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችኹ ነው።" ሮሜ 12÷1

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች !!

ይህ ቅጽ በ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል ITና design ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን ፤አላማውም በግ/ጉባኤው ዉስጥ ያሉ የGraphics Design እና Video editing ሙያ ያላቻውና ባላቸው ሙያ የግ/ጉባኤውን አገልግሎት ለማገዝ ፈቃደኛ የሆኑ አባላትን ዝርዝር ማወቅና በሙያቸው ጉባኤውን የሚያግዙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው ።

ስለዚህ በዘርፉ ጥቂትም ቢሆን ችሎታና የማገልገል ፍላጎት ያላችሁ ልጆች ቅጹን በመሙላት የአገልግሎት በረከት ትካፈሉ ዘንድ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን ።


ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን 🙏🏻
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 10:59


#ደረሰ #ንዑ_ነሐውር #ኑ_እንሄዳለን #ህዳር_8 #አይቀርም

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 05:54


በብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ሽኖዳ ፓትርያርክ  ዘግብጽ👇👇👇
           

     ✍️  የንስሐ ሕይወት ✍️
                ክፍል 3

✍️ ሠ/ ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹሕ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው። ለዚህም ነው ( ጥሩ ውሃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ ትነጻላችሁ ) ከርኲሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስን በውስጣችሁ አኖራለሁ።

የድንጋዩንም ልብ ከውስጣችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዛቴም አስኬዳችኋለሁ።  ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ በማለት የተናገረው ነው።  ሕዝ 30፥25

✍️   ረ / ንስሐ ከኃጢአት እና ከባርነት ነጻ መውጣት ነው። እግዚአብሔር ካልፈቀደለት እና ኃይሉን ካልሰጠው በቀር ተነሳሒ ልቡና ለሰው ልጅ በተለይም ኃጢአት ለሠለጠነበት ዲያብሎስ ለነገሠበት ሰው ከባድ ነው።
ይህንንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ( እውነት እውነት እላችኋለሁ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።

ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም እንግዲህ ልዱ ወልደ እግዚአብሔር አርነት ቢያወጣችሁ አርነት ትወጣላችሁ። ዮሐ   8፥34-36    በማለት ከዚህ የኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣት የሚቻለው ከእግዚአብሔር በተሰጠው እና በምትሰጥ ንስሐ መሆኑን አስተምሮናል ። በእውነት ነስሐ የገባ በፍጹም ልቦናው ወስኖ ኃጢአትን የተወ ሰው በእርግጥ አርነት እንደሚወጣ (እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ  እውነትን ታውቃላችሁ  እውነትም አርነት ያወጣችኋል በማለት አረጋግጧል ))። ዮሐንስ.8፥32

✍️ሰ /  ንስሐ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር እና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው።

👉ሰው በብዙ ምክንያት ኃጢአትን ሊተው ይችላል ለምሳሌ ሰውን ፈርቶ የሚፈልገውን ያክል ኃጢአት ለመስራት በሰዎች ዘንድ አቅም ሳይኖረው ቀርቶ የሚፈልገዎን ኃጢአት ለመፈጸም አቅም ሳይፈቅድለት ቀርቶ ለሚፈልገው ኃጢአት ጊዜ ሳይመቻችለት ቀርቶ። ወዘተ   ፣ ይሄ ንስሐ ሊባል አይችልም።
በመጀመሪያ ኃጢአትን ለመሥራት ማሰብን ፈጽሞ ከልቡና ማጥፋት ይገባል።

የኃጢአት ፍቅር ከልቡ ሳይወጣ ኃጢአትን ትቷል ሊባል አይችልም።
ንስሐ የሚባለው ኃጢአትን ከልቦናው ከመስራት እና ከመተግበር ፈጽሞ መከልከል እና መተው  ነው። ኃጢአትን የሚሰውር አይለማም የማይሰራት እና የሚናዘዝ እና የሚተዋት ግን ሕይወትን ያገኛል። ሲል ጠቢቡ ሰሎሞን ተናግሯል። ምሳ.28፥13

                                        ይቀጥላል...

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 18:56


የሃዘናችን ምንጩ ምን ይሆን?
ረሃብ ነውን? ለረሃቡማ  ሰማይና ምድርን የፈጠረ ሥጋውን ቆርሶ የሰጠ አምላክን የታቀፈች ድንግል ማርያምስ ተርባ የለምን? ውሃ ጥም ነውን? ለጥሙስ ቢሆን ደሙን አፍስሶ ከኃጢአት ያነጻንን ፈጣሪ ይዛ እመ አምላክስ ተጠምታ የለምን? ወይ ልብን የሚሰብር የሰዎች ንግግር ነውን? ለዚያማ የአምላክ እናት ስትሆን የትዕማንን ክፉኛ ንግግር ታግሳ የለምን?ሰዎች  የሚገባንን ክብር አልሰጡንም ብለን ይሆን ሃዘናችን? ለዚያማ እመቤታችንን እንደ አምላክ እናትነቷ ማን አከበራት? እነዚያን ያማሩ እግሮቿን የግብጽ በረሃ ተቀበላቸው እንጂ። ...
ይህ ሁሉ ቢሆን ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው።

እኛንም አምላካችን ከክብር በላይ ባለ ክብር ሊያከብረን ሽቶ ስለሃዘንና መከራችን ለጊዜው ዝም አለን እንጂ እግዚአብሔርን አምኖ ይዞ በተሰደዱበት መቅረት የለምና ፈጽመንአንዘን።

ይልቁንም በስደቷ ከስደታችን ትመልሰን ዘንድ እንለምናት። ከስደቷ  ዛሬ ስለማረፏ እየተደሰትን እጹብ ትኅትናዋን  እንዲህ እናመስግን...

ሚ ዕጹብ በዝኃ ትሕትናኪ ማርያም እግዝእትየ
ምስለ ወልድኪ ባዕል ዘገብረ ሰማየ
ውስተ ደብረ ቁስቋም ኃደርኪ ተመሲለኪ ነዳየ
ኢረከብኪ ሰብአ በህየ ዘይሁበኪ ሲሳየ
ወእመ አኮ ለጽምኪ ማየ።

እመቤቴ ማርያም ሆይ የትሕትናሽ ብዛት ምን ያህል ነው? ሰማይን  ከፈጠረ ከባለ ጸጋው ልጅሽ ጋር ነዳይ መስለሽ በደብረ ቁስቋም አድረሻልና። በዚያም ለረኀብሽ ኅብስት ወይም ለጥምሽ ውኃ የሚሰጥሽ አልነበረምና።
(ሰቆቃወ ድንግል)

ከቁስቋም ማርያም ረድኤት በረከት ለሁላችን ያድለን!

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ፣ ትምህርት ክፍል፣ ትምህርታዊ ስነ-ጽሑፍ ንዑስ ክፍል።

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 10:35


#ንዑ_ነሐውር #ኑ_እንሄዳለን #ህዳር_8 #አይቀርም

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 08:39


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🙏🏻🙏🏻🙏🏻

ልዩ የአንድነት ጉባኤ ፦ የንስሐ ጉባኤ

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ዛሬ ሐሙስ (ህዳር 5) የአንድነት ጉባኤ የሚኖረን ይሆናል።

ቦታ ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ 3ተኛ ፎቅ
ሰዓት ፦ ከ11፡20 ጀምሮ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን 🙏🏻
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 08:38


፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ pinned Deleted message

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 08:08


#ንዑ_ነሐውር #ኑ_እንሄዳለን #ህዳር_8 #አይቀርም

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 17:57


በብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ሽኖዳ ፓትርያርክ  ዘግብጽ👇👇👇
           

     ✍️  የንስሐ ሕይወት ✍️
ክፍል 2

✍️ ለ /,,  ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው ።

👉 ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነውና ። ስለዚህ ነገር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ( እንግዲህ እግዚአብሔር ስለእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን ) ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናችኋለን ። 2ኛ ቆሮ 5፥20 በማለት ተናግሯል።

ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር በሰዎች ልቡና ውስጥ ማደርም ነው ። ሰው ኃጢአቱን ከእርሱ ካላስወገደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሊሆን ስለማይችል ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ማለት ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን መዘጋጀት ነው ። 2ኛ ቆሮ 6፥14

✍️ሐ /  ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው።
  👉 ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወት ማንቀላፋት ነው።  ኃጢአተኛ ሰው ያለበትን ሥፍራ ፣  የወደቀበትን ጉድጓድ ፈጽሞ አያቅም እና በንስሐ መቀስቀስ ያስፈልገዋል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ከኃጢአት እንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደደረሰ ዘመኑን ዕወቁ በማለት ለሮም ሰዎች የጻፈው ከኃጢአት እንቅልፍ ነቅተው ለንስሐ እንዲበቁ ለመቀስቀስ ነው። ሮሜ 13፥11

በዚህ አገላለጽ ንስሐ የሰው ወደ ቀደመው ማንነቱ  መመለስ ነው ። ከኃጢአት የተነሣ ማንነቱን አጥቷልና ። የጠፋው ልጅም ወደ ልቡ ተመለሰ እንዳለ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ላይ።

✍️ መ  /  ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው ።
      👉 ኃጢአት የነፍስ ሞት ነውና። ቅዱስ ጳውሎስም በኃጢአታችን ሞተን ሳለን በክርስቶስ ( ሥጋችንን ተዋሕዶ ሕያዋን አደረገን ) አዳነን።      👉ብሏል ኤፌ 2፥5   ዳግመኛም ( አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሥ ክርስቶስ ያበራልሃል እና።) ሲል ተናግሯል።    ኤፌ   5፥14
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊውም ( እኛ ከሞት ወደ ሕይወት ) እንደተሻገርን እናውቃለን።
ምስክርነቱን ገልጧል።   1ኛ ዮሐ  3፥14 
ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ ( ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት የሚመልሰው ነብሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
ኃጢአት የነብስ ሞት ንስሐ ደግሞ ሕይወት መሆኑን አስተምሯል።  ያዕ 5፥20

ስለዚህ ንስሐ የሕይወት ትንሣኤ ነው  ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወት መሞት ነውና።

ይቀጥላል...

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 05:18


#ንዑ_ነሐውር #ኑ_እንሄዳለን #ህዳር_8 #አይቀርም

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

12 Nov, 05:02


#ንዑ_ነሐውር #ኑ_እንሄዳለን #ህዳር_8 #አይቀርም

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 08:08


በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ፓትርያርክ ዘግብጽ👇👇👇


✍️ የንስሐ ሕይወት ✍️

✍️ክፍል ፩
ስለ ንስሐ በጠቅላላው !
ንስሐ ምንድን ነው ?
ንስሐ ማለት ( ነስሐ ) ከሚለው የግእዝ ግስ ከሚል የመጣ ቃል ነው ። የቃሉ ትርጉም

✍️ሐዘን ፣ ✍️ ቀኖና
✍️ፀፀት ፣ ✍️ የኃጢአት ካሣ
✍️ቁጭት : ( ማለት ነው ( የአለቃ ኪዳነ
✍️ምላሽ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት)
✍️ቅጣት

አንድ ሰው ንስሐ ገባ ሲባል በሰራው ሥራ ተጸጸተ ፣ ክፉ አመሉን ተወ ፣ ባደረገው ስሕተት ፤ በተገበረው ክፋት ተጸጸተ።
ባደረገው ጥፋት ሁሉ መቆርቆሩ መፀፀቱ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚያደርገው ውሳኔ ነው ።

በአጠቃላይ መልኩ ንስሐ ከፍ ብሎ ትርጉም ሲኖረው በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ የሚከተሉትን ፍችዎች እናገኘዋለን ።

✍️ሀ/ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው ።
ከእግዚአብሔር መለየት ኃጢአት ነውና ንስሐ የሚገባው ሰው ከሚሠራው ኃጢአት በሙሉ ልቡ ይመለሳል ።

የበደለውን ፈጣሪውን ስለበደሉ ይቅርታ ይጠይቃል። እግዚአብሔር አምላክም በነቢያት አድሮ ሕዝቡ ከኃጢአት ንስሐ እንዲገቡ እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ ተናግሯል ።
{ ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል }።

እርሷንም አልጠበቃችሁም ፣ ወደ እኔ ተመለሱ ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ። ሚል 3፥7 በማለት ጥሪውን አስተላልፏል ።

በመጽሐፈ ምሳሌ
"ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም ፣
የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረት ያገኛል ።" በማለት ተጽፏል፤ምሳ. 27፥13

በሉቃስ ወንጌል የምናገኘው አባካኙ ልጅ ኃጢአቱ በመረረው እና በተፀፀተ ጊዜ ወደልቡ በመመለስ ወደ አባቱ ለመመለስ ወሰነ ።። አባቱም በሐሴት ተቀበለው ።
ሉቃ 15 ፥18-20
እውነተኛ ንስሐም ሰዎች በበደል እና በኃጢአት ወደ አጡት ሥፍራ ለመመለስ የሚኖራቸው ናፍቆት እና የሚወስኑት ውሳኔ ነው።
ይቀጥላል...

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 08:08


"የንስሐ ሕይወት"

📆 ኅዳር - የንስሐ ወር